7
መለከት #4 0 www.tlcfan.org 4

መለከት - T.L.C.F.A.N INTERNATIONAL MINISTRY || …Š¥ርሱ ስለ እኛ ሃጢያት መሆኑን የሚያሳይ መልካም የጽድቅ ስራ የሃጢያት መወገድ

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: መለከት - T.L.C.F.A.N INTERNATIONAL MINISTRY || …Š¥ርሱ ስለ እኛ ሃጢያት መሆኑን የሚያሳይ መልካም የጽድቅ ስራ የሃጢያት መወገድ

መለከት #4

0 www.tlcfan.org

4

Page 2: መለከት - T.L.C.F.A.N INTERNATIONAL MINISTRY || …Š¥ርሱ ስለ እኛ ሃጢያት መሆኑን የሚያሳይ መልካም የጽድቅ ስራ የሃጢያት መወገድ

መለከት #4

1 www.tlcfan.org

ቀናተኛ አምላክ ነኝ

“5. በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት

በልጆች ላይ የማመጣ 6. ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ

ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።”

ዘጸ.20፥1-3, ዘዳ.5፥9

እግዚአብሔር በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት

በልጆች ላይ የማመጣ ሲል ለማስፈራት ወይም ማለት ስላለበት የተናገረው ቃል አይደለም። እግዚአብሔር

ቀናተኛ አምልክ ስለሆነና እንዳለውም በትውልድ ላይ ይህንን ትዕዛዙ በማያደርጉ ትውልዶች ላይ ፍርዱን

እንደተናገረው ስለሚያመጣ ነው። “እኔን የሚጠላ አባቴን ደግሞ ይጠላል።” ዮሐ.15፥23-25 ኢየሱስ

ይህን ያለው መዝሙረ ዳዊት ላይ በከንቱ ይጠሉኛል የተባለው ይፈጸምባቸው ዘንድ ነው።

“በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጕር በዙ፤ በዓመፅ ያሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ በረቱ፤

በዚያን ጊዜ ያልቀማሁትን መለስሁ።” መዝ.69፥4

የእግዚአብሔርን ዘመን የምናጠና ሰዎች ይህን በቀላሉ ማየት እንችላለን። እግዚአብሔር

እንደተናገው በፊቱ አምጸው ጣኦትን ላመለኩና እርሱን ላልተከትሉት እስከ ሶስተኛና አራተኛ ትውልድ

በሃጢያታቸውና ባለመታዘዛቸው ምክንያት ይፈርድባቸው ነበር። ይህን ብሉይ ኪዳንን ታሪክ ጠለቅ

ብለን ካጠናን በቀላሉ እግዚአብሔር ያለውን እንደሚያደርግ በቃሉ እናረጋግጣለን። ኢየሱስ ይህን ሕግ

በዚያን ዘመን በዚያ ትውልድ ላይ እንደሚፈጽምበት አስታውቋል። እንዳለውም እግዚአብሔር እስከ

አራተኛ ትውልድ ድረስ ጠብቆ ፍርዱን የሮምን ወታደር አምጥቶ መቅደሱን በማፍረስና አመጸኞችን

በመቅጣት ፍርዱን ፈጽሟል። ይህም እግዚአብሔርን የቤቱ ቅንዓት ስለሚበላው ነው። አምላካችን

ቀናተኛ አምላክም ስለሆነ ነው። ስለዚህም ከዚህ ቀደም ብሎ ኢየሱስ በምዕራፍ 15 ላይ ያለውን

ከመናገሩ በፊት እርሱ እወደዋለሁ የምንል ከሆነ በምን እንደምንታወቅ ያስተምረናል።

“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር

እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤. . . ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም

የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ

ራሴንም እገልጥለታለሁ።” ዮሐ.14፥15,21

በእነዚህ ቃሎች እርሱን መውደድ እንዴት እንደሆነ ብቻ ሳይሆን። ትእዛዛቱ የእርሱ

እንደሆኑና ልንታዘዛቸውም እንደሚገባ በግልጽ ለሚከተሉት የገለጠበትና ያስተማረበት ስፍራ ነው።

ጌታን እንወደዋለን የምንል እርሱ የጠየቀንን ደግሞ እናደርጋለን። ደግሞም አድርጉ የተባልነውን ባናደርግ

እርሱ ቀናተኛ አምላክና ቃሉ የሚያከብር ስለሆነ ስለ አመጸኝነታችንና ስላለመታዘዛችን ይቀጣናል

ይፈርድብናል። እርሱ እንደ ሕጉ ሃጢያት ላይ ሳይፈርድ ምሕረትን አይገልጥም ወይም ይቅር አይልም።

እንደፈለግን ብንኖር ከቅጣትና ከፍርድ አናመልጥም።

“ኢያሱም ሕዝቡን፦ እርሱ ቅዱስ አምላክ ነውና፥ እርሱም ቀናተኛ አምላክ ነውና

እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም፤ መተላለፋችሁንና ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም።”

ኢያሱ.24፥19

እንግዲህ ይህን እውነት በደንብ በቃሉ መሰረት ከተመለከትን ሕይወታችንን በቃሉ መሰረት

መርምረን ከእርሱ ጋር መንገዳችንን እናስተካክላለን። ይህን የምናደርግ ከሆንን ደግሞ እግዚአብሔርን

ደስ እያሰኘነው እንዳለንና እንደምንወደው እንድናውቅ እወዳለሁ። በአንጻሩ ደግሞ ይህን እርሱ

የማይወደውን እያደረግን ከሆነ እርሱን በከንቱ እየጠላነው ነው። ይህ ከሆነ በቶሎ ንስሃ እንግባ።

Page 3: መለከት - T.L.C.F.A.N INTERNATIONAL MINISTRY || …Š¥ርሱ ስለ እኛ ሃጢያት መሆኑን የሚያሳይ መልካም የጽድቅ ስራ የሃጢያት መወገድ

መለከት #4

2 www.tlcfan.org

ዛሬ እግዚአብሔር በመታዘዝ ለእርሱ ያለንን ፍቅራችንን እንድንገልጥለት ሁላችሁን

እጋብዛለችኋለሁ። በአንደበት ሳይሆነ በመታዘዝና በተግባር ፍቅራችንን እንግለጥ እናሳይ።

የጌታ፣ የመስቀል፣ የመላዕክትና የጻድቃም ምስልና ቅርጽ

“ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ። በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥

ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ

አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ “ ዘጸ 20

1) በሰማይ ካለው ( ቅዱሳን፣ ማርያም፣ ጻድቃን ሰማዕታት፣ ጸሃይ፣ ጨረቃ. . .ወዘተ

2) በታች በምድር ካለው (ንጉስ፣ መሪ፣ ጻድቃን፣ ሙዚቀኛ፣ አክተሮች. . .ወዘተ)

3) በውሃ ካለው ( አሳ፣ እባብ፣ ማንኛውም ፍጥረት. . .ወዘተ)

4) ማናቸውንም ምሳሌ (ፎቶ፣ ስዕል፣ ቅርጻቅርጽ. . .ወዘተ)

5) የተቀረጸው ምስል (ሃውልት፣ ቤተ መቅደስ፣ ግንብ ወይም የመቅደስ ድንጋይ)

በቃሉ ውስጥ ሙሴ በምድረበዳ የነሃስ እባብ ምስል ቀርጾ በሕዝቡ ፊት በእግዚአብሔር

ትዕዛዝ መሰረት አቁሟል። ሰለሞን በመቅደስ ውስጥ የኪሩቤሎችን ምስል እና የእንስሳቶችን፣ እጽዋዕትና

አውሬ ምስሎችን ቀርጾ አስቀምጧል። ይህ ሕጉን የሚጻረር ነውን? በፍጹም አይደለም!! ነገር ግን እነዚህ

ምስሎችን ሰው ማምለክ ሲጀምር ብቻ እግዚአብሔር እንደ ሃጢያት እንደሚቆጥረውን በቃሉ መሰረት

እንረዳለን። ዛሬም ይህ እውነት ላለንበት ዘመን የሚሰራ ነው። ማንኛውንም ምስል ወይም ምሳሌ

ለአምልኮ ወይም የአምልኮ መልክ ስናስይዘውና ራሳችንን ከእግዚአብሔር ዞር እንዲያደርገን ስንፈቅድ

ሃጢያት ይሆናል። ከላይ ከ1-5 የዘረዘርኳቸውን ከማንኛውም አይነት አምልኮ ጋር ወይም እምነት ጋር

ማያያዝ እግዚአብሔርን ያሳዝናል። ይህ አይነት ኑሮና ተግባር የእግዚአብሔርን ቅንዓት ያስነሳል

ፍጻሜውም ፍርድና ቅጣት ይሆናል። ለመልካም የተሰራ በኋላ ተቀይሮ ጣኦት ሲሆንና ሰዎች አውቀውም

ሆነ ሳያውቁ ሲሰግዱለትና ሲያመልኩት የማይገባውንም ክብር ሲሰጡት የእግዚአብሔር ቁጣና ቅናት

ይህን በሚያደርጉት ሰዎችና ትውልዶች ላይ ይመጣል።

አንዳንድ ሰዎች የተለያዮ ምስሎችን ለአምልኮና ከእምነት ጋር አያይዘው በቤታቸው

ሰቅለዋል። በስሎቹም ዙሪያ ሻማ ያበራሉ ሌላም ሌላም ነገር እንዲሁ። አንዳዶቹም ወደ ምስሎቹ ዞረው

ይሰግዳሉ። ከሁሉ የሚያሳዝነው ግን ፊደል የቆጠሩ ቃሉን አንብበው እውነቱን መመርመር የሚችሉ

ሰዎች ይህንን ሲያደርጉ ማየት ነው። እግዚአብሔር በማንም አይመሰልም!!! ማንም እግዚአብሔርን

አላየውም እንዲሁም ደግሞ ጻድቃንን ወይም መለአክትን ማንም አላያቸውም። ስለዚህ በምንም አይነት

ምስል መስለን ልናስቀምጣቸው አይገባም። ይህ እግዚአብሔር ከማሳዘን ሌላ የመላዕክቱን ሆነ

የጻድቃንን ክብር የሚያሳንስ ነው። መቼም እንደ ባለ አዕምሮ ሰው የሚያስብ ሁሉ የእርሱ ምስል በሌላ

እርሱን በማይመስል ሲቀየር የሚያደስተው ሰው ይኖራል ብዬ አላምንም። ስለዚህ እግዚአብሔርን

የሌለውን ምስል፣ ጻድቃንም ሆነ መለአክት የሌላቸውን ምስል መስጠት እግዚአብሔርን መበደል ነው።

እግዚአብሔር ሙሴ የሰራውንና የነሃሱን እባብ ከተሰጠበት አላማ ውጭ በመዋሉ በባሪያው

በኩል እንደሰበረው የሰለሞን መቅደስንም በተመሳሳይ ምክንያት አፍርሶታል። ይህም ትውልድ

ከእግዚአብሔር ይልቅ በሚታየውና እራሱ በሚስለው በተቀረጸው ምስል አምልኮ ውስጥ ወድቋል። ዛሬ

በተለያየ ታላላቅ የክርስትና እምነት አቢያተ ክርስቲያናት የምናያቸው ምስሎችና ሃውልቶች ይህን

የሚመሰክሩ ናቸው። እነዚህ ፈጽሞ እግዚአብሔርን እንጸማያከብሩ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ሆነ

እኛ በሰማዮ በእግዚአብሔር ነገር ላይ ሃሳባችንን እድናደርግ እንደማያደርጉና እንደማያግዙን ልታውቁ

ይገባል። ይልቁኑ ከእግዚአብሔር ጋር ያጣሉናል። ይህ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቅጣት በግልሰብ እንዲሁም

በሃገር ደረጃ ያመጣብናል።

Page 4: መለከት - T.L.C.F.A.N INTERNATIONAL MINISTRY || …Š¥ርሱ ስለ እኛ ሃጢያት መሆኑን የሚያሳይ መልካም የጽድቅ ስራ የሃጢያት መወገድ

መለከት #4

3 www.tlcfan.org

ስሎችንና የተቀረጹ ሃውልቶችን ማምለክ ወይም በተዘዋዋሪ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ

እንደሚረዱ ማመን የእርሱን ቅጣት እንድንቀበል ያደርጉናል እንጂ በረከትን ፈጽሞ አያመጡልንም።

እግዚአብሔር በቤታችን በርና መቃን ላይ እንድንሰቅል ወይም እንድንጽፍ ያዘዘው ቃሉን ብቻ ነው። ዛሬ

በማንኛውም እምነት ውስጥ ብትሆኑ ከአምልኮ ጋር የተያያዙ የተለያዩ ምስሎች በቤታችሁ ካሉ

ከእግዚአብሔር ጋር ለመስማማት እና ለእርሱ ያላችሁን ፍቅር መግለጥ ከፈለጋችሁ ፈጽማችሁ

አስወግዱት። እግዚአብሔር በቤታችሁ በረከትን ሲያመጣ በላያችሁ ላይ ያለውን ቀንበር ሲሰብር ራሳችሁ

ምስክር ትሆናላችሁ። እግዚአብሔር ለሚታዘዙት ሁሉ የገባው በረከት አለ። ዘዳ.28 አንብቡ። እንኳን

እኛ በሰማይና በምድርም ያሉ ደግሞ ለእርሱ ብቻ እንዲንበረኩና እንዲታዘዙ እግዚአብሔር ይፈልጋል።

“ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥” ፊሊ.2፥10

ሙሴ በእንጨት ላይ በምድረበዳ የናሱን እባብ ሰቅሏል። ዘሁ.21፥8-9 ይህ ደግሞ ሕዝቡን

በጊዜው እግዚአብሔር ስላዘዘ አድኗል ደግሞም ለኢየሱስ መስቀል ሞት ትንቢታዊ ሕግና ጥላ ነበር።

እርሱ ስለ እኛ ሃጢያት መሆኑን የሚያሳይ መልካም የጽድቅ ስራ የሃጢያት መወገድ ምሳሌም ነበር።

ዮሐ.3፥14 ዛሬ ብዙዎች ኢየሱስ ስንል በአእምሯቸው የሚስሉት በእንጨት ላይ የተሰቀለ፣ የማያድግ

በአንድ ሴት የታቀፈ ሕጻን ምስል ወይም በስዕል በተለያየ መልክ ተስሎ ያዮትን መልክ ነው። እስቲ

እራሳችሁን ጠይቁ እውነት ቅድስት ድንግል ማሪያምንና ኢየሱስን ማን አይቶ ሳላቸው? ማነው መልክ

የሰጣቸውስ? ጥቁር ይሁኑ ነጭ ወይም ቀይ ዳማ ማን ያውቃል? ስለዚህ የተሳለው ምስልና የተቀረጸው

ምስል ፈጽሞ ለገንዘብ ማግኛና ሰዎችን ከእግዚአብሔር መንገድ ለማራቅ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

እግዚአብሔር ማንም ያየው የለም። እርሱ እራሱ በምንም እና በማንም እንዳንመስለው ያሳስበናል።

የተሳለው መልካቸውስ ትክክለኛ መልክ ነውን? ይህን ታሪክ ያጠና ሰው የሚመልሰው ቀላል

ጥያቄ ነው። ያለየነው እግዚአብሔር በምስል ስለን ስንመስለው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ እየተላለፍንና

በከንቱ እርሱን እየተጠላነው በትዕዛዙ ላይም እያመጽን ነው። ይህንን ሕሊናችሁ ወይም በውስጣችሁ

የተተከለው የእግዚአብሔር ሕግ ይፍረድ። ሮሜ.2 ጳውሎስ ኢየሱስ በስጋ ለሚያውቁት፣ በአይናቸው

ላዮት፣ በእጃቸው ለዳሰሱት እንዲሁም ቁጭ ብለው በጆሮዋቸው ለሰሙት ሰዎች እርሱ ወደ አባቱ ካረገና

ለጳውሎስም በደማስቆ በክብር ከተገለጠለት በኋላ እንዲህ ብሎ ያስተምራል።

“ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ

እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።”

2.ቆሮ.5፥16

እግዚአብሔርን በምንም መመስል አይቻልም። ጌታ ለሚወደኝ እራሴን እገልጣለሁ ብሏል።

ማድረግ ያለብን ጌታ ራሱን እንዲገልጥልን እርሱን መውደድ ነው። ከእርሱ የተሰጠን ቁልፍ ይህ ነው።

እርሱን ለመውደድ ደግሞ ያዘዘንን ትዕዛዙን መጠበቅ ብቸኛው መንገድ ነው። ቃሎቹ ምንም ውስብስብ

የሆኑ አይደሉም። ኢየሱስ በክብር አርጎ በአባቱ ቀኝ ተቀምጧል። አብሮት በምድር የነበረው ደቀመዝሙር

ጌታ የሚወደው ባሪያው የሆነው የሚታዘዘው ዮሐንስ ጌታን በራእይ ላይ ሲያየው በፊት በሚያቀው

ክብሩ እንኳን አላየውም። ቃሉ ከገለጠው ውጪ እርሱን ልንመስለውና ልንገልጠው አንችልም። ይህም

መልክ ምስል ሰርተን እድናመልክ ሳይሆን እርሱን በሕይወቱና በባሕሪው እንድንመስለው ዮሐንስ

በራእይ ላይ ተቀምጦልናል። ለበለጠ እውቀት የልጁ መልክ የሚለውን መጽሐፌን አንብቡት። ታዲያ

ዛሬም የመስቀሉ አላማ እንደ አባቶች ዘመን ሙሴ እንደሰራው የነሃስ እባብ መልኩን ቀይሮ የሳመውና

የተሳለመው ስይጣን እንደሚርቀው ወይም እግዚአብሔር እንደሚያከብር የሚታመንበት ዘመን ላይ

አለን። እውነት እንጨትና ነሃስ ከመሳለም ወጥተን እግዚአብሔር ለማምለክና ትዕዛዙን ብቻ ለማክበር

እርሱን ሰባብረን ነሑሽታን ብለን መጥራት ይሆንልን ይሆንን? ይህ ጸሎቴ ነው።

Page 5: መለከት - T.L.C.F.A.N INTERNATIONAL MINISTRY || …Š¥ርሱ ስለ እኛ ሃጢያት መሆኑን የሚያሳይ መልካም የጽድቅ ስራ የሃጢያት መወገድ

መለከት #4

4 www.tlcfan.org

አማኞች ሁሉ ማወቅ ያለብን ሃይላችን የመስቀሉ ቃል እንጂ እንጨቱ ወይም መስቀሉ

አለመሆኑን ነው። እንጨቱ ቃሉ እንደሚነግረን የእርግማን ምሳሌ እንጂ የጽድቅ ወይም የበረከት ምሳሌ

አይደለም። መስቀል አንገታችን ላይና ቤታችን ላይ ስናደርግ ወንበዴም በመስቀል ላይ እንደተሰቀለ

መዘንጋት የለብንም። አለበለዚያም ኢየሱስ የተሰቀለበት መስቀል ምሳሌ ነው ብለን በላዮ እንጻፍበት።

ይህን ላሳፍራችሁ እላለሁ። ግን በእውነት ለምን መስቀል አስፈለገ? ቃሉ መስቀል እንድንሳለም ወይም

አንገታችን ላይ እንድናጠለጥል ያዘናልን? ይህን ባናደርግ የሚጎልብን አለ ወይስ እናተርፏለን? በቃሉ

ከመሞላትና የእግዚአብሔር ቃል ከመታዘዝ በላይ ምን ሌላ ምልክት ያስፈልገናል? ሐዋርያት የታወቁት

መስቀልን በአንገታቸው ስላጠለቁ ነውን? ሐዋርያትና ነብያት እግዚአብሔር ስለሚታዘዙት እግዚአብሔር

ከእነርሱ ጋር እንዳለ በሚሰሩት ስራ ማንና የማን እንደሆኑ ይታወቁ ነበር። ለእኛም የእግዚአብሔር

አብሮነት መታወቂያችን ሊሆነን ይገባዋል። በቃሉ የማይገኝ ማንኛውም ወግ፣ ስርዓትና ሃይማኖት

ያመጣብንን ነገር ፈጽሞን ከሕይወታችን ከቤታችንና ከቤተሰባችን እንደ አባቶቻችን እናስወግደው።

ይህን ስል በአንድ ወቅት እንደ እናንተው እኔም የዚህ ወግና ስርዓት እስረኛ ነበርኩ። አሁን ግን በቃሉ ብቻ

ለመኖርና እግዚአብሔር ብቻ ለመታዘዝ ስወስን ወግና ስርዓትን ለእግዚአብሔር ስል ሁሉን ትቻለሁ።

ይህን ማድረጌ ደግሞ በሕይወቴ በረከትን ስላምንና የጣፈጠ እረፍትን እንዳመጣልኝ እመሰክራለሁ።

“ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም

ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ (በመስቀል) ይሰቀል ይገባዋል።’’

ዮሐ.3፥14-15

“በኮረብታም ያሉትን መስገጃዎች አስወገደ፥ ሐውልቶችንም ቀለጣጠመ፥ የማምለኪያ

ዐፀዶቹንም ቈረጠ፤ የእስራኤልም ልጆች እስከዚህ ዘመን ድረስ ያጥኑለት ነበርና ሙሴ

የሠራውን የናሱን እባብ ሰባበረ (የመስቀሉ ጥላ) ፤ ስሙንም ነሑሽታን ብሎ ጠራው።”

2 ነገ.18፥4

“በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ

ከሕግ እርግማን ዋጀን፤” ገላ.3፥13

“የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።’’

1.ቆሮ.1፥18

አንባቢዎቼ የመስቀሉ ቃል እንጂ የእኛ ሃይል መስቀሉ አይደለም። ይህም ቃል ኢየሱስ

በመስቀል ላይ ሆኖ የተናገራቸው ሰባቱ ታላላቅ ቃሎች ናቸው። እነዚህ በራሳቸው በጥልቀት መጠናት

ያለባቸውና የአማኞች ሁሉ ሃይል ናቸው። እነዚህን የመስቀሉ ቃሎች በጥልቀት ስናጠና ምን ያህል ሃይል

እንደሚሰጡን በቀላሉ መመልከት እንችላለን። የመስቀሉ ቃሎች ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው።

1. የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው። (ሉቃ.23፥33-34)

2. ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ። (ሉቃ.23፥40-43)

3. እነሆ እናትህ እነሆ ልጅሽ። (ዮሐ.19፥25-26)

4. “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ" አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ። (ማር.15፥34)

5. ተጠማሁ። (ዮሐ.19፥28)

6. ተፈጸመ። (ዮሐ.19፥30)

7. መንፈሴን በእጅህ ላይ አኖራለሁ። (ሉቃ.23፥46)

የጌታ ቃል ፍጹም የሆነ የሰው ልጆች ሃይል ነው። ዛሬ ግን ቃሉን ጥለን እንጨቱንና ነሃሱን

እንደ እስራኤል ልጆች እያመለክን እንገኛለን። እነርሱ ጌታ ረድቷቸው ሰባብረው ከእግዚአብሔር ጋር

ተጣበቁ እርሱን ብቻ ታዘዙት እኛስ? መስቀል ሃይላችን ነው ተብለን የተማርንና ያመንን ካለን እንግዲህ

በዚህ ቃል መሰረት ራሳችንን እናርም። መስቀል ሳይሆን ሃይላችን የመስቀሉ ቃል ሃይላችን ነው።

Page 6: መለከት - T.L.C.F.A.N INTERNATIONAL MINISTRY || …Š¥ርሱ ስለ እኛ ሃጢያት መሆኑን የሚያሳይ መልካም የጽድቅ ስራ የሃጢያት መወገድ

መለከት #4

5 www.tlcfan.org

ስለዚህ አስተውሉ የገና ልደት በዓል፣ የስቅለት በዓልን ፋሲካን በዓላት እንደ ቃሉ ሳይሆን

እንደ ሃይማኖትና ወግ ስርዓት ልናከብር ስንጥር የእግዚአብሔርን ሕግጋት እንተላለፋለን

እግዚአብሔርንም እናሳዝናለን። እንድናደርግና እንድንጠብቃቸው የተሰጡን የእግዚአብሔር በዓላት

አሉን በእነርሱ ላይ ግን መጨመር ወይም መቀነስ ፈጽሞ አይገባንም።

ዛሬ ባለንበት ዘመን በቃሉ ያልታዘዝነው ማንኛውንም ነገር ምሳሌ በአቢያተ ክርስቲያን ሆነ

በቤታችን አናድርግ። በቃሉ የተመሰሉትንም የተቀመጡትንም ቢሆን እንደተመሰሉበትና እንደተሰጡበት

አላማ ልንማርባቸው መሆኑን ማወቅ አለብን። ስለዚህ ልናመልካቸው፣ በፊታቸው ልንሰግድ፣ ሻማ

ልናበራላቸው፣ ድግስ ልንጥልላቸው፣ እንዲማልዱና እንዲደርሱልን እንድንለምናቸው፣ ፈጽሞ

እግዚአብሔር በቃሉም ሆነ በሕጉ አላዘዘንም። እግዚአብሔርን ወይስ ሃይማኖትን እናስደስት? ሰውን

ወይስ እግዚአብሔር? ምርጫው የእናንተ ነው። ይህ ጳውሎስ የተሻረው ያለው የሃይማኖተኛ ሰዎች

ወግና ልምምድ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ስርዓት እንጂ በእግዚአብሔር ቃልና ሕግ ውስጥ ምንም አይነት

ይህን አድርጉ የሚል ቃል ፈጽሞ ተጽፎ አናገኝም። ስለዚህ ከቃሉ ውጭ የሆነውን ሁሉ ከእለት እለት

ልምምዳችን እናስወግድና ከእግዚአብሔር ጋር እንወግን እርሱን ብቻ ደስ እናሰኝ። ሮሜ.8፥7-8

ከአሮጌው ኪዳን ጋር አብረው ፍጻሜን ያገኙ ሕግጋት አሉ። ነገር ግን ተፈጸሙ ማለት ተሻሩ

ማለት አይደለም። እነርሱንም አሁን ደግመን ልናደርጋቸው ፈጽሞ አያስፈልግም። ምክንያቱም በኢየሱስ

በኩል የተሻለና የከበረ ኪዳንን ትዕዛዝን ስለተቀበልና በኢየሱስ ስራ በኩል የተፈጸሙ ስራዎችና ሕጎች

ስለሆኑ ነው። ለምሳሌ ያህል ለሃጢያት ስርየት በግ አናርድም። በጉ ተቀይሯል ሕጉ ግን አሁንም አለ።

አሁን እጣን አናጥንም ነገር ግን የእጣን ሕግ አሁንም አለ። በአዲሱ ኪዳን እጣን ወደ እግዚአብሔር

በሚደረግ የምስጋናና የምልጃ ጸሎት ተቀይሯል። ይህን ወደፊት ወደ እግዚአብሔር ሕግጋቶች በትምህርት

እየዘለቅን ስንገባ በዝርዝር የምንመለከታቸው ይሆናል። ስለዚህም ነው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ

ተፈጸመ ያለው። መስቀሉ የብዙ ነገሮች ፍጻሜና ጅማሬ ነው።

እንግዲህ በመልከት ቡካቲን ቁጥር 3 እና 4 ትምህርታችን ላይ በጥቂቱ የቃኘነው ከአስርቱ

ትዕዛዛት አንደኛውንና ሁለተኛውን ትዕዛዛት ነው። እነርሱም ፦

1ኛው - ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ የሚለውን ትዕዛዝ እና

2ኛው - የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው፥

አታምልካቸውምም የሚለውን የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው።

እነዚህ ትዕዛዛት ሕዝበ እስራኤል ከግብጽ እንደ ወጣ ከእግዚአብሔር ከእራሱ የተማረው

የመጀምሪያው የእግዚአብሔር ቃሎች ናቸው። በእውነት እነዚህን ትዕዛዛትን ዛሬ እናከብራቸዋለን?

እራሳችንን ካለንበት የሃይማኖትና ድርጅት ወግና ስርዓት ወጥተን ሕጉን ለሰጠን ለእግዚአብሔር ሁላችን

በያለንበት መልስ እንስጥ። እግዚአብሔር ዛሬ በምን አይነት የሃይማኖት ድርጅት ውስጥ እንዳለን

አይገደውም፣ በሃይማኖቱ ስር ሆነን የሰራነው ተዓምር፣ የተናገርነው ትንቢትና ፈውስም አይደንቀውም

ወይም እግዚአብሔርን ወደ መንግስቱ እንዲያስገባን አያደርገውም። ነገር ግን የሚወዱት ትዕዛዛቱን

በቅንነትና እግዚአብሔር በመፍራት የሚታዘዙ እነርሱን ጌታ ያወቃቸዋል ወደ መንግስቱም ያስገባቸዋል።

ትዕዛዙን የሚጠብቁትና እንደ ቃሉና የእግዚአብሔር ፍቃድ የሚኖሩ ስዎችን እግዚአብሔር በመንግስቱ

ይቀበላቸዋል በሩንም ይከፍትላቸዋል። “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥

ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።” ማቴ.7፥21

“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር

እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤. . . ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም

የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”

ዮሐ.14፥15,21

Page 7: መለከት - T.L.C.F.A.N INTERNATIONAL MINISTRY || …Š¥ርሱ ስለ እኛ ሃጢያት መሆኑን የሚያሳይ መልካም የጽድቅ ስራ የሃጢያት መወገድ

መለከት #4

6 www.tlcfan.org