22
I I A A (ኤፍ ኤም 96.3) ድንግልና Aዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዘጋጆች፡- በፍቃዱ ኃይሉ Aስማማው /ጊዮርጊስ ኤዶም ካሣዬ ምንታምር ካሣሁን ሰኔ 2002..

ድንግልና በአዲስ አበባ (Virginity in Addis Ababa)

Embed Size (px)

DESCRIPTION

የአዲስ አበባ ወጣቶች ስለድንግልና ያላቸውን አመለካከት፣ ስንቶቹ ድንግል እንደሆኑ፣ ድንግልናቸውን ማጣታቸው የሚቆጫቸው ምን ያሀሉ እንድሆኑ፣ እና ሌሎችም ከድንግልና ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በጥናቱ ተዳስሰዋል:: (What do Addis Ababians think about virginity? How many of them are virgins? How many regret losing it? Many other related issues are covered by the study)

Citation preview

IIሉሉዥዥንን የየሚሚዲዲያያናና ኮኮሙሙኒኒኬኬሽሽንን ሥሥራራዎዎችች

AAዲዲስስ መመዝዝናናኛኛ ((ኤኤፍፍ ኤኤምም 9966..33))

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ

Aዘጋጆች፡-

በፍቃዱ ኃይሉ

Aስማማው ኃ/ጊዮርጊስ

ኤዶም ካሣዬ

ምንታምር ካሣሁን

ሰኔ 2002ዓ.ም.

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

1

ቅደመ-መግቢያ

Aዲስ መዝናኛ በኤፍ ኤም 96.3 ዘወትር ቅደሜ ከምሽቱ 3፡00 Eስከ Eኩለ ሌሊት የሚዘልቅ የመረጃና

የመዝናኛ የሬዲዮ መርሓ-ግብር ነው፡፡ በAዲስ መዝናኛ የተለያዩ Aገር Aቀፍ Eና ዓለም Aቀፍ የመረጃና

ተግባቦት ቴክኖሎጂ፣ የመዝናኛ Eና Aስተማሪ ዜናዎች Eና ትንታኔዎች ይቀርባሉ፤ ከነዚህም ውስጥ

የICT (Information and Communication Technology) ትኩስ ዜናዎችና ትንታኔዎች፣ ማህበረሰባዊ

ጉዳዮች ዳሰሳ (የኑሮ ነገር፣ የፍቅር ነገር Eና ተምሳሌታዊ ነገር ይጠቀሳሉ፡፡) ከዚህም በተጓዳኝ የመዝናኛ

ዜናዎች Eና ጥUመ ዜማዎችም የመርሓ-ግብሮቹን ጣEም Eንዲስማሙ ሆነው ወደAድማጮች ጆሮ

ይንቆረቆራሉ፡፡

Aዲስ መዝናኛ ለተጠቀሱት ንUሳን መርሓ-ግብሮቹ Aስፈላጊውን ምርምር በዝግጅት ክፍሉ ባለሙያዎች

Aማካኝነት ያካሂዳል፡፡ በዚህ መሠረት ይህንን ‹‹ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ›› የተሰኘ ጥናት

Aዘጋጅቷል፡፡ መሰል Aዝናኝ ብሎም ማሕበራዊ ፋይዳ ያላቸውን ጥናቶች በመቀጠልም ለማዘጋጀት

Eየተጋ ይገኛል፡፡

መግቢያ

ድንግልና በወጣቶች መካከል Aዝናኝም Aሽኮርማሚም ርEሰ ጉዳይ ነው፡፡ ዋናው ቁምነገር ግን ወጣቱ

በድንግልና ላይ ያለውን Aመለካከት Eና ወቅታዊ ሁኔታ በማየት የወደፊቱ ፆታዊ ግንኙነት ምን

ሊመስል Eንደሚችል ምናባዊ ምስል መቅረፅ መቻል ነው፡፡ ለዚህም ነው ‹‹ድንግልና በAዲስ Aበባ

ወጣቶች Eይታ›› የሚለውን ርEስ መርጠን የተነሳነው፡፡ በመሆኑም የጥናቱ መሠረታዊ ትኩረት

በድንግልና Eና ከድንግልና ፅንሰ ሐሳቦች ጋር የተገናኙ ማሕበራዊ፣ ባሕላዊ Aስተሳሰቦችንና ግለሰባዊ

ስነልቦናዎችን መቃኘት Eና Aንድምታውን ላዘጋጀናቸው ጥያቄዎች በተለያዩ ወጣቶች የተሰጡ ድምር

ምላሾች ላይ ተንተርሶ መተንተን ነው፡፡

በዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ ውስጥ ድንግልናን ማጣት ወይም መስጠት የሚሉ ቃላት Eያፈራረቅን

የተጠቀምን ሲሆን Eነዚህ ቃላትን የተጠቀምንባቸው የመጀመሪያ ጊዜ ፆታዊ ተራክቦን ለማመልከት ብቻ

በመሆኑ Eንደቃላቱ ቀጥተኛ ፍቺ ‹ማጣት› Eንደማጉደል ወይም ‹መስጠት› Eንደ ገፀ-በረከት

Eንዲተረጎሙ Aይደለም፡፡ Eንደዚሁም በዚህ ፅሁፍ ውስጥ ድንግል ማለት ፆታዊ ተራክቦ (ወሲብ)

ፈፅሞ የማያውቅ የሚል ትርጉም Aለው፡፡ በመሆኑም ዝንየትን (በEንቅልፍ ልብ /በሕልም/ የሚፈፀም

ወሲብን) ወይም የራስ በራስ ወሲብን (ሴጋ/Masturbation/ን) Aይወክሉም፡፡

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

2

የጥናቱ ዓላማ

የጥናቱ ዋንኛ ዓላማ ልክ Eንደ Aዲስ መዝናኛ ዓላማ ሁሉ Eያዝናኑ ማስተማር ነው፡፡ በAብዛኛዎቹ

የIትዮጵያ ብሔረሰቦች ባሕልና ልማድ ድንግልና (በተለይም የሴት ልጅ) ለጋብቻ Eንደቅደመ ሁኔታዎች

ይቆጠር ነበር፡፡ ይህ Eውነታ Aሁን በAዲስ Aበባችን ተቀይሯል ወይስ የተለወጠ ነገር የለም?

የሚሉትንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በጥናት ላይ ተመርኩዞ መመለስ ሌላው የጥናቱ ዓላማ ነው፡፡

በጥቅሉ ‹‹ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ›› በሚል የተደረገው ይህ ጥናት ዓላማው፡-

ምን ያህል ያላገቡ የAዲስ Aበባ ወጣቶች ድንግል Eንደሆኑ ግምት ማስቀመጥ፣

ድንግልናቸውን ያጡ/የሰጡ ወጣቶች መቼ Eንዳጡ፣ በዚህም ይቆጩ Eንደሆነ ማወቅ፣

ድንግልናን ለተወሰነ Eድሜ ጠብቆ ስለማቆየት ወጣቶች ያላቸውን Aመለካከት ለይቶ ማወቅ፣

የAዲስ Aበባ ወጣቶች ከወላጆቻቸው ጋር ስለድንግልና ምን ያህል Eንደሚወያዩ ማወቅ Eና

ወጣቶች በድንግልና ላይ ያላቸው Aመለካከትና መነጋገር መቻላቸው በፆታዊ ተራክቦ የሚተላለፉ

በሽታዎችን Eና ያልተፈለገ Eርግዝናን ከመቆጣጠር Aንፃር መጫወት የሚችሉትን ሚና

መተንተን ከብዙ በጥቂቱ የጥናቱ Aቢይ ዓላማዎች ናቸው፡፡

የጥናቱ ዘዴ

ጥናቱ የተደረገው ባላገቡ የAዲስ Aበባ 120 ወጣቶች ላይ ነው፡፡ ጥናቱን ለማድረግ 13 ጥያቄዎችን

ያካተተ መጠይቅ (ተያያዥ ሰነድ-2ን በመጨረሻው ገፅ ላይ ይመልከቱ) ለነዚህ ወጣቶች ተሰራጭቷል፡፡

መልሶቹ Aንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የAዲስ Aበባ ወጣቶችን ሁሉንም ሕዝበ-ፅፍ (Demography)

Eንዲወክሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተድርጓል፡፡

የናሙናው ወካይነት

በጥናቱ ከተሣተፉት ውስጥ 51.7% ያክሉ ሴቶች ናቸው፡፡ ይህም በAዲስ Aበባ የሴት ወጣቶች ቁጥር

ያለውን መጠነኛ ብልጫ Eንዲወክል በማሰብ የተደረገ ነው፡፡ በተጨማሪም ከሁሉም የAዲስ Aበባ

ማEዘናት ከሚገኙ ወጣቶች መረጃውን ለመሰብሰብ ጥረት ከመደረጉም ባሻገር የEድሜ ክልሉም

ብዙሃኑን ወጣት ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው፡፡ በዚህም 14% 19 ዓመት Eና ከዚያ በታች፣ 43% ከ20

Eስከ 24 ዓመት Eና 43% 25 Eና ከዚያ በላይ Eድሜ ያላቸው ወጣቶች Eንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡ በዚህ

መሠረት ጥናቱ ያካለለው Aማካይ Eድሜ (mean age) 23.8 ነው፡፡

ምንም Eንኳን የናሙናው ቁጥር በ120 ቢወሰንም ወካይነቱ ግን ከጂOግራፊያዊ መገኛ፣ ከፆታ Eና

Eድሜ Aንፃር ሁሉንም የAዲስ Aበባ ወጣቶች በመጠኑ Eንዲወክል ሆኖ ተዘጋጅቷል፡፡

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

3

የመደምደሚያው Aንድምታ

በዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ ውስጥ የሚሰነዘሩት መደምደሚያዎች በሙሉ የተቀመጡት በፅሁፉ ውስጥ

በሰፈረው የተጓዳኝ ጥናቶች ቅኝት፣ በመጠይቁ ምላሾች Eንዲሁም በAዘጋጆቹ ውይይት ላይ ተመስርቶ

ነው፡፡

የተጓዳኝ ጥናቶች ቅኝት

ድንግልና

ድንግልና ፆታዊ ተራክቦ ፈፅሞ ሳያደርጉ መቆየት ማለት ነው፡፡ ድንግልና ብዙውን ጊዜ ከሴት ልጅ

ፆታዊ ተራክቦ ልምድ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ቢሆንም ፆታዊ ተራክቦ ፈፅሞ የማያውቅ ወንድም ድንግል

ይባላል፡፡

ወንዶችና ሴቶች በስንት Aመታቸው ድንግልናቸውን ያጣሉ በሚል በተለያዩ ሃገራትና ባህሎች ዙሪያ

E.ኤ.A. በ2003ዓ.ም. ጥናት ያደረጉት ማይክል ቦዞን (ከፈረንሳይ ብሔራዊ ደቱደስ ዲሞግራፊክስ)

ምርምሩን በሦስት ምድብ ከፍለው Aስቀምጠውታል፡፡

በመጀመሪያው ምድብ ወላጆች ከሚፈልጉት Eድሜው የገፋ ሰው ጋር ሴት ልጆቻቸውን በለጋ

Eድሜያቸው (Aሥራ ቤትን ያልተሻገሩ) ለጋብቻ የሚሰጡበት ነው፡፡ ይህ ምድብ Aንዳንድ የEስያ

ሃገራትን Eና በተለይም ከሰሃራ በታች ያሉ Aገራት ውስጥ ያሉትን Eንደ ማሊ፣ ሴኔጋል Eና Iትዮጵያ

ያሉትን ሃገራት ያካትታል፡፡

በሁለተኛው ምድብ ልጆቻቸውን ለጋብቻ Eንዳይጣደፉ የሚያደፋፍሩ ወላጆችን ያካትታል፡፡ ሆኖም ልጆቹ

ድንግልናቸውን Eንዲያቆዩ ይጠበቅባቸዋል፡፡ Eንዲያም ሆኖ በዚህንኛው ምድብ ወንዶች ከሴቶች ይልቅ

የቅደመ ጋብቻ ወሲብ ልምድ የማዳበር መብት Aላቸው፡፡ በዚህ ምድብ ውስጥ ላቲን ሃገራት፣ ደቡብ

Aውሮፓ Eና የEስያ ሃገራት ተካትተዋል፡፡

በሦስተኛው ምድብ ውስጥ ደግሞ ሴቶችና ወንዶች ድንግልናቸውን በተቀራራቢ Eድሜ የሚያጡበት

ነው፡፡ በዚህ ምድብ ውስጥ ላቲን ያልሆኑ ካቶሊክ Aገራት፣ ቻይናና ቪየትናም ተካተዋል፡፡ ላቲን ባልሆኑ

ካቶሊክ Aገራት ወንዶችና ሴቶች ድንግልናቸውን የሚያጡት ብዙውን ጊዜ ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

4

ምክንያት Eድሜያቸው በጣም ከፍ ካለ በኋላ ነው፡፡ በቻይና Eና ቪየትናምም በባሕላዊ Eሴቶቻቸው

ድንግልናን ጠብቆ ለማቆየት ከፍተኛ ዋጋ ስለሚሰጡ Eንዲሁ ዘግይተው ድንግልናቸውን ከሚያጡት

ምድቦች ውስጥ ይካተታሉ፡፡

በመጨረሻም ሰሜን Eና ምስራቅ Aውሮፓ ውስጥ ወጣቶች ድንግልናቸውን የሚያጡት በAንፃራዊ

Aነስተኛ Eድሜያቸው ነው፡፡ ይህ ምድብ ሦስት፤ ንUስ ምድብ ሁለት ስዊዘርላንድ፣ ጀርመን Eና ቼክ

ሪፐብሊክን ያካትታል፡፡

የሦስቱም ምድቦች በAማካይ ሲሰላ ብዙ የዓለማችን ወጣቶች ድንግልናቸውን የሚያጡት ከ14 Eስከ 17

ዓመት Eድሜ ሲሆናቸው ነው፡፡

ይሁን Eንጂ በማንኛውም ባሕል ውስጥ ድንግልና የተከበረ ዋጋ Aለው፡፡ ይህ በተለይም ከጋብቻ በፊት

ፆታዊ ተራክቦን በሚከለክሉ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ Eሴቶች ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት Aለው፡፡

ሆኖም Aንትሮፖሎጂስቶች ድንግልናን መጠበቅ ግድ በሆነባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ሳይቀር ሰዎች

ብልቶቻቸውን መንካት ያካተተ፣ የሴቶች ድንግልና መገለጫ የሆነውን ስጋ (hymen) የማይጎዱ የወሲብ

ስሜትን የሚኮረኩሩ ድርጊቶችን ለየብቻቸው ወይም ከተቃራኒ ፆታ ጓደኞቻቸው ጋር Eንደሚፈፅሙ

ይናገራሉ፡፡

ድንግልና በIትዮጵያ

ድንግልና በIትዮጵያ Aብዛኛዎቹ ባሕሎች (በAማራ፣ በOሮሚያና በትግራይ) በተለይም ለሴቶች በጋብቻ

Eንደ ቅደመ ሁኔታ ይቆጠራል፡፡ ሆኖም በAንዳንድ የደቡብ ክልል ብሔረሰቦች ውስጥ ለሁለቱም

ፆታዎች የቅድመ ጋብቻ ወሲብ Aይከለከልም፡፡ በከተማዎች Aካባቢ ይህ ልማድ Eየተቀየረ ሲሆን

በIትዮጵያ ገጠራማ Aካባቢዎች ዛሬም ድረስ ድንግልና የጋብቻ ቅደመ ሁኔታ ውስጥ Eንደሚመደብ

ጥናቶች ይመሰክራሉ፡፡ የገጠር ወንዶች ከከተማ ወንዶች ይልቅ 3 ወይም 4 Eጥፍ በላይ ድንግል ሴት

ማግባት ይፈልጋሉ፡፡

በገጠር የሚኖሩ Iትዮጵያዊያን ከከተማ ነዋሪዎች ይልቅ ከ3 Eጥፍ በላይ ድንግልናን Eስከጋብቻ ጠብቆ

ማቆየት ተገቢ Eንደሆነ ያምናሉ፡፡ ሆኖም 67% የሚሆኑት በጥናቱ የተካተቱ ሰዎች ወንዶች ድንግልናን

Eስከጋብቻ ጠብቆ መቆየት Eንደሚከብዳቸው ተናግረዋል፡፡

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

5

ካላገቡ የገጠር ሴቶች መካከል በ17 ዓመት Aማካይ Eድሜ ክልል ውስጥ 3.4% ብቻ ድንግልናቸውን

Aጥተዋል፡፡ በዚሁ Aማካይ Eድሜ ከጋብቻ በፊት ፆታዊ ተራክቦ የፈፀሙ የገጠር ወንዶች ደግሞ

11.3% ናቸው፡፡

14% ወንዶች Eና 81% ሴቶች ደግሞ ድንግልናቸውን ያጡት በጋብቻ በ16 ዓመት Aማካይ

Eድሜያቸው Eንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በከተሞች በተለይም በAዲስ Aበባ የጋብቻ Eድሜ በጣም ከፍ Eያለ

Eንደሆነ የሚያመለክቱ ጥናቶች Aሉ፡፡ ስለዚህ በAዲስ Aበባ Eንደገጠራማ የIትዮጵያ ክልሎች

ድንግልናን Eስከጋብቻ ማቆየት Aስቸጋሪ ይሆናል፡፡

ድንግልናን ማጣት

ድንግልናን ማጣት የሚለው ቃል በራሱ Aወዛጋቢ ነው፡፡ ከድንግልና ጋር በተያያዘ በAማርኛ መስጠት

የሚለው ቃል ማጣት ከሚለው Eኩል ትርጉም Eንዲሰጥ ሆኖ ሊነገር ይችላል፡፡ ሆኖም ማጣት Eና

መስጠት ትርጉማቸው ለየቅል ነው፡፡ ማጣት ሳይወዱ የሚደረግ ሲሆን መስጠት ግን ፈቃደኝነት

የተመላበት ነው፡፡

ድንግልና በቋንቋው ውስጥ ክብር የሚል ስያሜም Aለው፡፡ ‹‹ክብሯን የጠበቀች›› ማለት ድንግልናዋን

ያላጣች/ያልሰጠች ማለት ነው፡፡ የቋንቋው ትርጉም ድንግልና በባሕል ውስጥ ያለውን Eሴት

ያመለክታል፡፡ ድንግልናዋን የጠበቀች ሴት ‹‹ክብሯን የጠበቀች›› ከሆነች ድንግልናዋን ያልጠበቀች ደግሞ

‹‹ክብሯን ያጣች›› የሚል Aንድምታ ይኖረዋል፡፡

የባሕል Aንትሮፖሊጂስቶች ፍቅርና ቅናት የዓለም ሁሉ ሰው ባሕርይ Eንደሆነ ሲያስቀምጡ ለድንግልና

የተሰጠው ክብርም ከዚሁ የቅናት ስሜት ጋር የተያያዘ Eንደሆነ ይገልፃሉ፡፡ ድንግልናን መጠበቅ

ለሰውልጅ ቅናት Aንድ መፍትሄ Eንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡

የስነልቦና ተመራማሪዎችም ድንግልናን ከጋብቻ በፊት ማጣት ለፍቺ Eንደምክንያት ሊቀመጥ ይችላል

ይላሉ፡፡ በAሜሪካን Aገር በተደረገ ጥናት በድንግልና ካገቡ ሴቶች ይልቅ ከጋብቻ በፊት የፆታዊ ተራክቦ

ልምድ የነበራቸው ሴቶች የመፋታት Eድላቸው የሰፋ ነው፡፡

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

6

ድንግልና Eንደገና ማበጀት

ሃይመናይዜሽን ይባላል፡፡ ድንግልናን Eንደነበር መልሶ የማስቀመጥ የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና ዓይነት

ነው፡፡ ሕክምናውን ለማከናወን ከሰላሳ ደቂቃ የረዘመ ጊዜ Aይወስድም፡፡ ሃይመናይዜሽን ድንግልናን

የመጠበቅ ባሕላዊ Eሴቶች በሚበረቱባቸው በEስያ Aገራት ሕንድና ቻይና ውስጥ በሰፊው Eየተተገበሩ

ነው፡፡

ሆኖም ሶሺዮሎጂስቶች ሃይመናይዜሽን ማሕበራዊ Eሴትን የሚያሳጣ Aደገኛ ሁኔታ ነው በማለት

ይቃወሙታል፡፡ ሃይመናይዜሽን በሰፊው የሚተገበረው በመደፈር ድንግልናቸውን ላጡ ሴቶች ብቻ

መሆን Eንዳለበት ባለሙያዎቹ ይናገራሉ፡፡

የቅድመ ጋብቻ ወሲብ

በገጠራማ የIትዮጵያ Aካባቢዎች ጋብቻ በAንፃራዊ የልጅነት Eድሜ ይፈፀማል፤ Aብዛኛዎቹ ሴቶችም

ከጋብቻ በፊት ምንም Aይነት የፆታዊ ተራክቦ ተሞክሮ የላቸውም፡፡ የገጠር ወንዶች ከገጠር ሴቶች

ይልቅ ድንግል ማግባት ይፈልጋሉ፡፡ የገጠር ወንዶች ድንግልናቸውን ባለመጠበቃቸው የሚደርስባቸው

ችግር የለም ሆኖም የገጠር ሴቶች ድንግልናቸውን ካልጠበቁ ይገለላሉ፣ የትዳር Aጋር የማግኘት

Eድላቸውም የጠበበ ይሆናል፡፡ በAንዳንድ የIትዮጵያ ማሕበረሰቦች ውስጥ ድንግልናቸውን ያልጠበቁ

ሴቶችን የሚያገባቸው ፈት የሆነ ወንድ ብቻ ነው፡፡

በከተማዎች ውስጥ ሁኔታዎች Eየተለወጡ ነው፡፡ የጋብቻ Eድሜ ወደላይ ከፍ Eያለ ሲሆን የቅድመ

ጋብቻ ወሲብም Eየተዘወተረ ነው፡፡ የቅድመ ጋብቻ ወሲብ በከተማ ውስጥ የዛሬ 50 ዓመታት ከነበረው

በጣም ከፍ ያለ ሲሆን የቅደመ ጋብቻ ወሲብ ነፃነት በAንዳንድ ሃገራት የሴተኛ Aዳሪነትን Eንደቀነሰ

ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡

የቅድመ ጋብቻ ወሲብ ላልተፈለገ Eርግዝና Eና ለAባላዘር በሽታዎችም Eንደምክንያት ይጠቀሳል፡፡ ብዙ

የቅደመ ጋብቻ ወሲብ ልምድ ያላቸው ወጣቶች ስለ Aባላዘር በሽታ Eና መከላከያ መንገዶቹ ያላቸው

ግንዛቤ Aናሳ ነው፡፡

ዋቢ ንባቦች፡-

biomedcentral.com - Traditional values of virginity and sexual behaviour in rural Ethiopian youth: results from a cross-sectional study - accessed in June 2010

asociatedcontent.com – accessed in June 2010 wikipedia.org – Virginity – accessed on June 10th 2010 Psychological Self-Help - by Dr. Clayton E. Tucker-Ladd

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

7

የጥናቱ ግኝት በተሳታፊዎች ምላሽ መሠረት የድንግል ሴቶች ቁጥር ከወንዶች Eጅግ የላቀ ነው፡፡ 59% የሚሆኑት

ወጣቶች ድንግል Eንዳልሆኑ ሲናገሩ ይህንን በፆታ ስንመነዝረው ደግሞ የድንግል ወንዶችን ቁጥር ወደ

29% ብቻ ያደርሰዋል፡፡

52% የሚሆኑት በጥናቱ

የተሳተፉ ሴቶች ድንግል

Eንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

ቻርት 1፡- የጥያቄ Aንድ (ድንግል ነህ/ሽ?) መልሶች በፆታ

ከታች በቻርት 2 ላይ Eንደሚታየው ብዙዎቹ ወጣቶች (79% ያክሉ) ድንግልናቸውን የሚያጡት ከ25

ዓመት Eድሜ በላይ ሲሆናቸው ነው፡፡ 47% ያክሉ ወጣቶች ከ20 Eስከ 24 ዓመት ባለው የEድሜ

ክልል ወቅት ድንግልናቸውን Eንዳጡ ሲናገሩ 14% የሚሆኑት ደግሞ ከ19 ዓመት በታች ሆነው

ድንግልናቸውን Eንዳጡ ተናግረዋል፡፡

ቻርት 2፡- የጥያቄ Aንድ (ድንግል ነህ/ሽ?) መልሶች በEድሜ

59% የሚሆኑት ወጣቶች ድንግልናቸውን ከሚወዱት ሰው ጋር፣ በመልካም Aጋጣሚ Eና በገዛ

ፈቃዳቸው Eንዳጡ ሲናገሩ 30% ያክሉ ደግሞ በፈቃዳቸው ነገር ግን በማይፈልጉት Aጋጣሚ

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

8

ድንግልናቸውን Eንደሰጡ ተናግረዋል፡፡ ድንግል ካልሆኑት ወጣቶች መካከል Aብዛኛዎቹ (21%)

ድንግልናቸውን ያጡት ኮሌጅ ውስጥ ነው፡፡

ቻርት 3፡- የጥያቄ Aራት (ድንግልናህ/ሽን ማጣትህ/ሽ ይቆጭሃል/ሻል?) መልሶች በEድሜ

ድንግል Eንዳልሆኑ ከተናገሩት ወጣቶች መካከል 21% የሚሆኑት ድንግልናቸውን ማጣታቸው

Eንደሚቆጫቸው ተናግረዋል፡፡ ይህን በፆታ ስናሰላው 23% ወንዶችና 17% ሴቶች ናቸው፡፡ ከነዚህም

መሃከል 43%ዎቹ ከ20 Eስከ 24 ዓመት ሲሆናቸው፣ 33% ያክሉ ከ19 ዓመት በታች የሆኑ

ወጣቶችም Eንዲሁ ድንግልናቸውን ማጣታቸው Eንደሚቆጫቸው ገልፀዋል፡፡

ድንግልናን መስጠት የሚሰጣቸውን ትርጉም በተመለከተ 39% የሚሆኑት ሴቶች ‹‹Eውነተኛ ፍቅርን

መግለፅ ነው›› ብለው ሲናገሩ በተቃራኒው 38% የሚሆኑት ወንዶች ደግሞ ‹‹ምንም ትርጉም

Aይሰጠኝም›› ብለው መልሰዋል፡፡ ድንግልናን መስጠት ‹‹Eውነተኛ ፍቅርን መግለፅ ነው›› ብለው

የሚያምኑት ወንዶች ከ14% Aይበልጡም፡፡ በሌላ በኩል 60% ሴቶችና 42% ወንዶች ድንግልና በዚህ

ዘመን ወሳኝ ቁም ነገር ነው ብለው ያምናሉ፡፡

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

9

ቻርት 4፡- የጥያቄ Aምስት (ድንግልናን ማጣት ለኔ) መልሶች በፆታ

በተያያዘም 63% ያህል ወጣቶች የድንግልና ፅንሰ ሐሳብ ወይም ድንግልናን ለተወሰነ Eድሜ ጠብቆ

ማቆየት ‹‹ጠቃሚ›› Eንደሆነ ያምናሉ፡፡ ይሁን Eንጂ 62% የሚሆኑት ወጣቶች ድንግልና ለጋብቻ

Eንደቅድመ ሁኔታ መቀመጥ የለበትም ብለው ተናግረዋል፡፡

60% ያክል ወጣቶች ከሁለቱም ወላጆቻቸው ጋር ስለድንግልና Aውርተው Aያውቁም፡፡ 9%ዎቹ

ከEናቶቻቸው ጋር ያወሩ ሲሆን 2%ዎቹ ብቻ ደግሞ ከAባቶቻቸው ጋር Aውርተው ያውቃሉ፡፡

በተመሳሳይ መልኩ 83% የሚሆኑት ወጣቶች ከጓደኞቻቸው ጋር ስለድንግልና ያወራሉ፡፡

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

10

ቻርት 5፡- የጥያቄ ሰባት (ድንግልናን ለተወሰነ Eድሜ ጠብቆ ማቆየት) መልሶች በፆታ

በጥናቱ ከተሳተፉት መካከል Aብዛኛዎቹ (74%) ድንግልና በባህላችን ለሴቶች በጣም Aስፈላጊ ነው ያሉ

ሲሆን፣ 25% ያክሉ ብቻ ድንግልና በባህላችን ለወንዶች በጣም Aስፈላጊ ነው ሲሉ መልሰዋል፡፡

59%ዎቹ ወጣቶች ደግሞ ድንግልና ለወንዶች ‹‹ያን ያህል Aስፈላጊ›› Aይደለም ብለው ያምናሉ፡፡

በመጨረሻም 73% ያክሉ ወጣቶች ድንግልናቸውን ለትዳር Aጋራቸው ቢሰጡ Eንደሚመርጡ

ተናግረዋል፡፡ ሆኖም 11% ያህል ወንድ ወጣቶች በተራ Aጋጣሚ፣ ከማንኛውም ሰው ጋር

ድንግልናቸውን ቢያጡ Eንደማይቆጫቸው ያምናሉ፡፡

Eድሜና ድንግልና

Eድሜ Eየጨመረ ሲመጣ ድንግልናን ጠብቆ የማቆየት Eድሉ Eየቀነሰ ይመጣል፡፡ በዚህም 80% ከ19

ዓመት Eና ከዚያ በታች የሆኑ ወጣቶች ድንግልናቸውን የጠበቁ ሲሆን፣ 53% ከ20 Eስከ 24 Eና 21%

ብቻ ከ25 ዓመት በላይ የሆናቸው ወጣቶች ድንግልናቸውን መጠበቅ Eንደቻሉ በምላሻቸው ተናግረዋል፡፡

ቀጥሎ ያለውን ስንጠረዥ 1 ይመልከቱ፡፡

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

11

በመቶኛ ተ.ቁ. ጥያቄ ምርጫ <19 20 - 24 25> ድምር

Aዎ 80% 53.33% 21.28% 42.99% ድንግል ነህ/ነሽ? Aይ 20% 46.67% 78.72% 57.01% 1

ድምር 14.02% 42.06% 43.9% 100% Aዎ 33.33% 42.86% 5.56% 20% ድንግል ካልሆንክ/ሽ፡-

ድንግልናህን/ሽን ማጣትህ/ሽ ይቆጭሃል? Aይ 66.67% 57.14% 94.44% 80% 4

ድምር 5% 35% 60% 100% ጠቃሚ ነው 66.67% 63.64% 63.83% 64.15% ጎጂ ነው 13.33% 2.27% 2.128% 3.77% ጠቃሚም ጎጂም Aይደለም 20% 20.45% 21.28% 20.75%

የድንግልና ፅንሰ ሐሳብ (ድንግልናን ለተወሰነ Eድሜ ጠብቆ ማቆየት)...

ጠቃሚም ጎጂም ነው 0% 13.64% 12.77% 11.32% 7

ድምር 14.15% 41.51% 44.3% 100% ከባለቤቴ 85.71% 71.43% 69.57% 72.55% ከጋብቻ በፊት ለማገኘው/ኛት ፍቅረኛዬ 7.143% 26.19% 21.74% 21.57%

ድንግልናህን/ሽን ከማን ጋር ብታጣ/ጪ ትመርጣለህ/ጫለሽ (ትመርጥ/ጪ ነበር)? በተራ Aጋጣሚ ባጣው

Aይቆጨኝም 7.14% 2.38% 8.696% 5.882%

13

ድምር 13.73% 41.18% 45.1% 100% ሰንጠረዥ 1፡- የመጠይቅ መልሶች በEድሜ

Aነጋጋሪ ግኝቶች

1ኛ - 30% ወጣቶች ድንግልናቸውን በማይፈልጉት Aጋጣሚ Aጥተዋል

58% የሚሆኑ ወጣቶች ድንግልናዬን በምፈልገው Aጋጣሚ፣ ከምወደው ሰው ጋር ነው ያጣሁት ብለው

ቢመልሱም 30% የሚሆኑት ግን በማይፈልጉት Aጋጣሚ፣ ከማይፈልጉት ሰው ጋር ነገር ግን በገዛ

ፈቃዳቸው ድንግልናቸውን Eንዳጡ ተናግረዋል፡፡ ይህ በጣም Aደገኛ Eና ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ጉዳይ

ነው፡፡ ቻርት 6ን ከቀጣዩ ገፅ ይመልከቱ...

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

12

ቻርት 6፡- የጥያቄ ሁለት (ድንግልናህ/ሽን በምን Aጋጣሚ Aጣህ/ሽ?) መልሶች በፆታ

በማይፈልጉት Aጋጣሚ ድንግልናቸውን ያጡ ወጣቶች ከቁጭቱ በስተጀርባ ለተለያዩ Aደጋዎች

የተጋለጡ ናቸው፡፡ ምናልባትም Eነዚህ ወጣቶች በዚህ ያልተፈለገ Aጋጣሚ ማድረግ የነበረባቸውን

ጥንቃቄ ማድረግ Aይቻላቸው ይሆናል በዚህም ራሳቸውን ላልተፈለገ Eርግዝና ብሎም ለAባላዘር በሽታ

የሚያጋልጡበት Eድል የሰፋ ነው፡፡

2ኛ - 60% ወጣቶች ከሁለቱም ወላጆቻቸው ጋር ስለድንግልና Aንድም ቀን Aውርተው Aያውቁም

በተራ ቁጥር Aንድ የተገለፀው Aነጋጋሪ ውጤት በቤተሰባዊ ውይይት ወጣቶች ቅድመ ጥንቃቄ

Eንዲያደርጉ ግንዛቤ በማስጨበጥ ሊቀነስ የሚችል ችግር ነው፡፡ ሆኖም የቤተሰብ ውይይት በተለይም

በድንግልና ጉዳይ ላይ የተመናመነ ነው፡፡ 14% የሚሆኑት ወጣቶች ብቻ ከEናታቸውም ከAባታቸውም

ጋር ስለድንግልና ያወሩበት Aጋጣሚ Aለ፡፡ ይሁን Eንጂ 60% የሚሆኑት ከሁለቱም ጋር Aውርተው

Aያውቁም፤ 9% የሚሆኑት ከEናታቸው ጋር ብቻ Eና 2%ዎቹ ደግሞ ከAባታቸው ጋር ብቻ Aውርተው

ያውቃሉ፡፡

በተለይም ደግሞ Aባቶች ከወንድ ልጆቻቸው ጋር ስለድንግልና ፈፅሞ Aያወሩም፡፡ 3% ሴቶች ግን ከዚህ

በተሻለ ከAባቶቻቸው ጋር ስለድንግልና Aውርተው ያውቃሉ፡፡

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

13

ቻርት 7፡- የጥያቄ ስምንት (ስለድንግልና ከወላጆችህ/ሽ ጋር Aውርተህ/ሽ ታውቂያለሽ?) መልሶች በፆታ

3ኛ - ድንግልና ለሴቶች ‹በጣም Aስፈላጊ›፣ ለወንዶች ግን ‹ያን ያህል Aስፈላጊ Aይደለም›

ድንግልና በልማድ ለሴቶችም ለወንዶችም Aስፈላጊ Eንደሆነ ይታመናል፤ ይሁን Eንጂ በሴቶቹ ላይ

ይጠነክራል፡፡ በከተማ የሚኖሩ ሰዎች የAኗኗር ዘይቤያቸው የተለየ በመሆኑና Eና የትምህርት Eድሉም

ስላላቸው የድንግልና Aስፈላጊ ቁምነገርነት Eየተመናመነ Eንደመጣ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ይሁን Eንጂ

በጥናታችን ላይ ከተሳተፉት 81% ወንዶችና 68% ሴቶች ድንግልና ለሴቶች ‹‹በጣም Aስፈላጊ››

ቁምነገር ነው ሲሉ፣ 63% ወንዶችና 54% ሴቶች ድንግልና ለወንዶች ‹‹ያን ያህል Aስፈላጊ Aይደለም››

ሲሉ መልሰዋል፡፡ ድንግልና ለወንዶች ‹‹በጣም Aስፈላጊ›› ነው ብለው የተናገሩት 22% ወንዶችና 29%

ሴቶች ናቸው፡፡

ይህ Aሃዝ በተዘዋዋሪ የሚያመለክተው ሴቶች በAዲስ Aበባ Aሁንም ድረስ ድንግልናቸውን ጠብቀው

መቆየት Eንደሚጠበቅባቸው ወጣቶቹ የሚያምኑ መሆኑን ነው፡፡

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

14

ቻርት 8፡- የጥያቄ Aሥራ Aንድ (በባህላችን ድንግልና ለሴቶች ምን ያህል Aስፈላጊ ነው?) መልሶች በፆታ

ከዚሁ ፈቀቅ ሳይል 71% የሚሆኑት ወንዶች ድንግል Aይደሉም፤ ነገር ግን Aሁንም 42%ዎቹ ወንዶች

ድንግልና ለጋብቻ Eንደቅድመ ሁኔታ ሊመደብ ይገባል ባይ ናቸው፡፡ ይህ Eርስ በርሱ የሚጋጭ Eውነታ

የፆታ Eኩልነት ፅንሰ ሃሳብን የሚጋፋ ነው፡፡ ድንግልናቸውን ያልጠበቁ ወንዶች ከሴት ልጅ ድንግልናን

ይጠብቃሉ የሚል መደምደሚያ ማሳለፍ ይቻላል፡፡ ከሴት መልስ ሰጪዎች መካከል 33%ዎቹ ብቻ

ድንግልና ለጋብቻ ቅደመሁኔታ መሆን Aለበት ብለው ያምናሉ፡፡

Eንዲያም ሆኖ ከመላሾቻችን መሃል 4% የሚሆኑት ሴቶች ድንግልናቸውን ተገድደው Aጥተዋል፡፡

4ኛ - 10% የሚሆኑት ወንዶች ድንግልናቸውን በተራ Aጋጣሚ ቢያጡ Aይቆጫቸውም

69% ያህሉ ወጣቶች ድንግልናቸውን ከባለቤታቸው ጋር ቢያጡ ይመርጣሉ፡፡ 26%ዎቹ ደግሞ ከጋብቻ

በፊት ከሚያገኙት ፍቅረኛቸው ጋር ለማጣት ፈቃደኛ ናቸው፡፡ ሆኖም Aንድም ሴት ድንግልናዋን በተራ

Aጋጣሚ ለማጣት Aትፈልግም፡፡ በተቃራኒው ግን 10.7% ወንዶች ድንግልናቸውን በተራ Aጋጣሚ

ቢያጡት Eንደማይቆጫቸው ተናግረዋል፡፡

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

15

ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ድንግልናቸውን ከባላቸው ጋር ቢያጡ ይመርጣሉ፡፡ 78% የሚሆኑት ሴቶች

ድንግልናዬን ከባለቤቴ ጋር (ከማገባው ወንድ ጋር) ባጣ Eመርጣለሁ ብለው ሲመልሱ 59% የሚሆኑት

ወንዶች ብቻ ድንግልናዬን ከሚስቴ ጋር (ከማገባት ሴት ጋር) ባጣ Eመርጣለሁ ብለዋል፡፡

ይሁን Eንጂ ወንዶች ከዚህ መልሳቸው ጋር የሚጋጭ መልስም Aላቸው፡፡ ምንም Eንኳን 11%

የሚሆኑት ወንዶች ድንግልናቸውን በተራ Aጋጣሚ ቢያጡ Eንደማይቆጫቸውና 30% የሚሆኑት ደግሞ

ከጋብቻ በፊት ከሚያገኟት ፍቅረኛቸው ጋር ድንግልናቸውን ማጣት Eንደሚፈልጉ ቢናገሩም 23%

የሚሆኑት ወንዶች ድንግልናቸውን ማጣታቸው Eንደሚቆጫቸው ተናግረዋል፡፡ ድንግልናቸውን

በማጣታቸው የሚቆጩት ሴቶች ቁጥር 17% ብቻ ነው፡፡

ቻርት 9፡- የጥያቄ ሁለት (ድንግልናህን/ሽን ከማን ጋር ብታጣ/ጪ ትመርጣለህ/ጫለሽ/ትመርጥ/ጪ ነበር?)

መልሶች በEድሜ

በጥቅሉ 21% የሚሆኑት ወጣቶች ድንግልናቸውን በማጣታቸው ይቆጫሉ፡፡ ይህም በማይፈልጉት

Aጋጣሚ ድንግልናን ከመስጠት ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡ ወጣቶች በድንግልናና በመጀመሪያ የፆታዊ

ተራክቦ ሙከራቸው የሚፀፅታቸውን ስራ Eንዳይሰሩ ግንዛቤ የማስጨበጡ ስራ Eምብዛም Eንዳልተሰራ

Aመላካች ነው፡፡

5ኛ - የሴትና ወንድ ወጣት መልሶች ልዩነት

በAንዳንድ ምላሾቻቸው ሴቶችና ወንዶች Aስደማሚ ልዩነቶችን Aስመዝግበዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ

ድንግልናን ማጣት የሚሰጣቸው ስሜት Aንዱ ነው፡፡

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

16

38% ያህል ወንዶች ድንግልናን ማጣት/መስጠት ለኔ ‹‹ምንም ትርጉም Aይሰጠኝም›› ሲሉ፣ 14%ዎቹ

ደግሞ ‹‹Eውነተኛ ፍቅርን መግለፅ ነው›› ብለው መልሰዋል፡፡ ‹‹ምንም ትርጉም Aይሰጠኝም›› ብለው

የመለሱት ሴቶች 27% ሲሆኑ ብዙዎቹ (39%ዎቹ) ግን ‹‹Eውነተኛ ፍቅርን መግለፅ ነው›› ብለው

ያምናሉ፡፡

በሌላ በኩል 67% የሚሆኑት ሴቶች ድንግልናቸውን ከሚወዱት ሰው ጋር፣ በመልካም Aጋጣሚ Eና

በገዛ ፈቃዳቸው Eንዳጡ ሲናገሩ 53% ብቻ የሚሆኑት ወንዶች ተመሳሳይ መልስ ሰጥተዋል፡፡ ሆኖም

35% ያክሉ ወንዶች በማይፈልጉት Aጋጣሚ ድንግልናቸውን Eንዳጡ ተናግረዋል፡፡ ድንግልናቸውን

በማይፈልጉት Aጋጣሚ ያጡ ሴቶች Aሃዝ 22% ብቻ ነው፡፡

በመጨረሻም በዚህ ዘመን ድንግልና ወሳኝ ቁም ነገር ነው ብለው ያስቡ Eንደሆነ ሲጠየቁ ‹‹Aዎ›› ብለው

የመለሱት ወንዶች ቁጥር 42% ሲሆን ይህንኑ መልስ የሰጡት ሴቶች ግን 60% ናቸው፡፡

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

17

መደምደሚያ ባሕል Eና ልማድ ፍቺያቸው ለየቅል ነው፡፡ ባሕል ማለት በAንድ ወቅት ብዙሐኑ የማሕበረሰቡ Aካል

የሚስማማበት Eሴት ሲሆን ልማድ ደግሞ ከጥንት ጀምሮ ሲተገበር የነበረ ሲወርድ፣ ሲወራረድ

Eዚህኛው ትውልድ ጋር የደረሰ Eምብዛም የማይለወጥ Eሴት ማለት ነው፡፡ በዚህ ፍቺ መሰረት ባሕል

ይወለዳል፣ ያድጋል Eንዲሁም ይሞታል፡፡ ድንግልናን የተመለከቱ ባህላዊ Eሴቶቻችንም Eንዲሁ

በማህበረሰባችን ውስጥ Eየተወለዱ፣ Eያደጉና Eየሞቱ Eዚህ ደርሰዋል፡፡ የEኛ ጥናትም ያጠነጠነው

በEነዚህ የድንግልና Eሴቶች ዙሪያ ነበር፡፡ የAዲስ Aበባ ወጣቶች ስለድንግልና ያላቸው Eይታ ዛሬ ላይ

ምን ይመስላል?

ድንግልና ከግማሽ ምEተ Aመት በፊት በAብዛኛው የIትዮጵያ ክፍሎች (በገጠርም፣ በከተማም) ክብር

ያለው፣ ለጋብቻ ቅድመ ሁኔታ የሆነ ቁምነገር ነበር፡፡ ዛሬስ?

Eያደገ የመጣው ከተሜነት Aዲስ Aበባያውያንን ለድንግልና ይሰጥ የነበረውን የንግስና ክብር Eንዲቀንስ

Aድርጎታል፡፡ ይሁን Eንጂ Aሁንም ክብሩ Aልሞተም ማለት ይቻላል፡፡ ከ50% በላይ የሚሆኑ ወጣቶች

ድንግልና ወሳኝ ቁምነገር Eንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ከሲሦ በላይ የሚሆኑትም ድንግልና ለጋብቻ Eንደ ቅድመ

ሁኔታ ሊቆጠር ይገባል የሚል ጠንካራ Eምነት Aላቸው፡፡

Eዚሁ Aዲስ Aበባ ውስጥ በድንግልና ጉዳይ ወጣቶች ከወላጆቻቸው ጋር ጮክ ብለው ለመነጋገር ገና

Aልደፈሩም፡፡ ከ60% በላይ ወጣቶች ድንግናን የተመለከቱ ወሬዎች Eናትና Aባታቸው ፊት ትንፍሽ

ብለው Aያውቁም፡፡ ይህ በተለይም ፀረ ኤድስ Eንቅስቃሴዎች በሰፊው Eየተደረጉ ባለበት በዚህ ጊዜ

Aሳሳቢና ሊቀረፍ የሚገባው Eውነታ ነው፡፡ የዝምታው ይሰበር Eንቅስቃሴዎች ዛሬ ከትላንት ምንም

Eንዳልተራመዱ Aመላካችና የማንቂያ ደወል ልንለውም Eንችላለን፡፡

ድኅረ-ጥቆማ

ይህ ጥናት የተከናወነው በውሱን የሰው ሃይል፣ ጊዜና በጀት Eንደመሆኑ የራሱ የሆኑ ተግዳሮቶች

ነበሩበት፣ ጥናቱን በተሻሻለ የሰው ሃይል፣ ጊዜና በጀት በመስራት ግን ከዚህ የተሻሉ ተጨባጭ ሃገራዊ

መረጃዎችን በማሕበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማፍራት ይቻላል፡፡

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

18

ተያያዥ ሰነድ-1፡- የመጠይቅ መልሶች

ምላሽ ምላሽ በመቶኛ ተ.ቁ. ጥያቄ ምርጫ

ወንድ ሴት ድምር ወንድ ሴት ድምር Aዎ 17 32 49 29.31% 51.61% 40.83% ድንግል ነህ/ነሽ? Aይ 41 30 71 70.69% 48.39% 59.17% 1

ድምር 58 62 120 48.33% 51.67% 100% ከምወደው ሰው ጋር፣ በገዛ ፈቃዴና በመልካም Aጋጣሚ 21 18 39 52.5% 66.67% 58.21% በማልፈልገው Aጋማሚ፣ ግን በፈቃዴ 14 6 20 35% 22.22% 29.85% ተገድጄ 2 1 3 5% 3.70% 4.48%

ድንግግ ካልሆንክ/ሽ፡- ድንግልናህ/ሽን በምን Aጋጣሚ Aጣህ/ሽ?

በሌላ ሁኔታ 3 2 5 7.5% 7.41% 7.46%

2

ድምር 40 27 67 59.7% 40.3% 100% ከ10ኛ ክፍል በፊት 11 6 17 22% 11.76% 16.83% ከ12ኛ ክፍል በፊት 11 3 14 22% 5.882% 13.86% ኮሌጅ ውስጥ 11 10 21 22% 19.61% 20.79% ከኮሌጅ ከወጣሁ በኋላ (ከ12ኛ ክፍል በኋላ) 6 8 14 12% 15.69% 13.86% Eስከጋብቻ Eቆያለሁ 7 13 20 14% 25.49% 19.80%

ድንግልናህ/ሽን መቼ Aጣህ/ሽ (ወይም Eሰከመቼ ትጠብቀዋለህ/ቂዋለሽ)?

Eስከመቼ Eንደምቆይ መገመት Aልችልም 4 11 15 8% 21.57% 14.85%

3

ድምር 50 51 101 49.5% 50.5% 100% Aዎ 10 5 15 23.26% 17.24% 20.83% ድንግል ካልሆንክ/ሽ፡-ድንግልናህን/ሽን

ማጣትህ/ሽ ይቆጭሃል? Aይ 33 24 57 76.74% 82.76% 79.17% 4 ድምር 43 29 72 59.72% 40.28% 100%

Aዲስ ነገር ማወቅ ነው 16 10 26 32% 22.73% 27.66% በራሴ ላይ ያለኝን ስልጣን ማወቅ ነው 6 4 10 12% 9.09% 10.64% መዝናናት ነው 2 1 3 4% 2.27% 3.19% Eውነተኛ ፍቅርን መግለፅ ነው 7 17 24 14% 38.64% 25.53%

ድንግልናን ማጣት (መስጠት) ለኔ....

ምንም ትርጉም Aይሰጠኝም 19 12 31 38% 27.27% 32.98%

5

ድምር 50 44 94 53.19% 46.81% 100% Aዎ 24 36 60 42.11% 60% 51.28% በዚህ ዘመን ላንተ/ቺ ድንግልና ወሳኝ ቁምነገር

ነው? Aይ 33 24 57 57.89% 40% 48.72% 6 ድምር 57 60 117 48.72% 51.28% 100%

ጠቃሚ ነው 35 41 76 60.34% 66.13% 63.33% ጎጂ ነው 3 1 4 5.17% 1.61% 3.33%

7 የድንግልና ፅንሰ ሐሳብ (ድንግልናን ለተወሰነ Eድሜ ጠብቆ ማቆየት)...

ጠቃሚም ጎጂም Aይደለም 12 13 25 20.69% 20.97% 20.83%

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

19

ምላሽ ምላሽ በመቶኛ ተ.ቁ. ጥያቄ ምርጫ

ወንድ ሴት ድምር ወንድ ሴት ድምር ጠቃሚም ጎጂም ነው 8 7 15 13.79% 11.29% 12.5%

ድምር 58 62 120 48.33% 51.67% 100% ከEናቴ ጋር Aውርቼ Aውቃለሁ 2 8 10 3.57% 13.56% 8.70% ከAባቴ ጋር Aውርቼ Aውቃለሁ 0 2 2 0% 3.39% 1.74% ከሁለቱም ጋር Aውርቼ Aውቃለሁ 9 7 16 16.07% 11.86% 13.91% ከሁለቱም ጋር Aውርቼ Aላውቅም 36 33 69 64.29% 55.93% 60%

ስለድንግልና ከወላጆችህ/ሽ ጋር Aውርተህ/ሽ ታውቂያለሽ?

Eርግጠኛ Aይደለሁም 9 9 18 16.07% 15.25% 15.65%

8

ድምር 56 59 115 48.7% 51.3% 100% Aዎ 24 19 43 42.11% 33.33% 37.72% ድንግልና ለጋብቻ ከቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ

ሊመደብ ይገባል? Aይ 33 38 71 57.89% 66.67% 62.28% 9 ድምር 57 57 114 50% 50% 100%

በጣም Aስፈላጊ ነው 13 17 30 21.67% 28.81% 25.21% ያን ያህል Aስፈላጊ Aይደለም 38 32 70 63.33% 54.24% 58.82% በባህላችን ድንግልና ለወንዶች ምን ያህል

Aስፈላጊ ነው? ፈፅሞ Aስፈላጊ Aይደለም 9 10 19 15% 16.95% 15.97% 10

ድምር 60 59 119 50.42% 49.58% 100% በጣም Aስፈላጊ ነው 46 42 88 80.7% 67.74% 73.95% ያን ያህል Aስፈላጊ Aይደለም 9 18 27 15.79% 29.03% 22.69% በባህላችን ድንግልና ለሴቶች ምን ያህል

Aስፈላጊ ነው? ፈፅሞ Aስፈላጊ Aይደለም 2 2 4 3.51% 3.23% 3.36% 11

ድምር 57 62 119 47.9% 52.1% 100% Aዎ 45 52 97 80.36% 85.25% 82.91% ስለድንግልና ከጓደኞችህ/ሽ ጋር ታወራላችሁ? Aይ 11 9 20 19.64% 14.75% 17.09% 12

ድምር 56 61 117 47.86% 52.14% 100% ከባለቤቴ 33 46 79 58.93% 77.97% 68.7% ከጋብቻ በፊት ለማገኘው/ኛት ፍቅረኛዬ 17 13 30 30.36% 22.03% 26.09% ድንግልናህን/ሽን ከማን ጋር ብታጣ/ጪ

ትመርጣለህ/ጫለሽ (ትመርጥ/ጪ ነበር)? በተራ Aጋጣሚ ባጣው Aይቆጨኝም 6 0 6 10.71% 0% 5.22% 13

ድምር 56 59 115 48.7% 51.3% 100%

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

20

ተያያዥ ሰነድ-2፡- መጠይቅ

መጠይቅ - ድንግልና በAዲስ Aበባውያን Eይታ

Aዲስ መዝናኛ በኤፍ ኤም 96.3 ዘወትር ቅዳሜ ምሽት ከሦስት Eስከ ስድስት ሰዓት የመዝናኛና መረጃ ሰጪ ፕሮግራሞችን ወደ Aድማጮቹ ያደርሳል፡፡ ከነዚህም መካከል በፍቅር ጉዳዮች ላይ ለሚያቀርባቸው የፍቅር ነገር ለተሰኙ መረጃዎቹ Eና ለሌሎችም Aስፈላጊ ጥናቶችን ያደርጋል፡፡ ይህ መጠይቅም የተሰናዳው ለዚሁ መረጃ ለማሰባሰብ ሲሆን ድምር ውጤቱ ሰኔ 12፤ 2002 ዓ.ም. በተለመደው ሰዓት ይቀርባል፡፡ Eባክሽ Aንቺም መጠይቁን በEውነተኛ መረጃ በመሙላት ተባበሪን፡፡ ለዚህም በቅድሚያ በAዲስ መዝናኛ ስም Eናመሰግናለን!!!

Eድሜ ከ19 በታች ከ20 Eስከ 24 ከ25 በላይ

1. ድንግል ነሽ? (Aዎ___/Aይ___) 2. ድንግል ካልሆንሽ፡- ድንግልናሽን በምን Aጋጣሚ Aጣሽ?

a. ከምወደው ሰው ጋር በገዛ ፍቃዴ Eና በመልካም Aጋጣሚ b. በማልፈልገው Aጋጣሚ ግን በፈቃዴ c. ተገድጄ d. ሌላ (_______________________________________)

3. ድንግልናሽን መቼ Aጣሽ? (ወይም ድንግልናሽን Eስከመቼ ትጠብቂያለሽ?) a. ከ10ኛ ክፍል በፊት b. ከ12ኛ ክፍል በፊት c. ኮሌጅ ውስጥ d. ከኮሌጅ ከወጣሁ በኋላ e. Eስከጋብቻ Eቆያለሁ f. Eስከመቼ Eንደምቆይ መገመት Aልችልም

4. ድንግል ካልሆንሽ፡- ድንግልናሽን ማጣትሽ ይቆጭሻል? (Aዎ___/Aይ___) 5. ድንግልናን ማጣት ለኔ . . .

a. Aዲስ ነገር ማወቅ ነው b. በራሴ ላይ ያለኝን ስልጣን ማወቅ ነው c. መዝናናት ነው d. Eውነተኛ ፍቅርን መግለፅ ነው e. ምንም ትርጉም Aይሰጠኝም

6. በዚህ ዘመን ድንግልና ላንቺ ወሳኝ ቁምነገር ነው? (Aዎ___/Aይ___) 7. የድንግልና ፅንሰ ሐሳብ (ድንግልናን ለተወሰነ Eድሜ ጠብቆ ማቆየት)

a. ጠቃሚ ነው b. ጎጂ ነው c. ጠቃሚም ጎጂም Aይደለም d. ጠቃሚም ጎጂም ነው

8. ስለድንግልና ከወላጆችሽ ጋር Aውርተሽ ታውቂያለሽ? a. ከናቴ ጋር Aውርቼ Aውቃለሁ b. ካባቴ ጋር Aውርቼ Aውቃለሁ c. ከሁለቱም ጋር Aውርቼ Aውቃለሁ d. ከሁለቱም ጋር Aውርቼ Aላውቅም e. Eርግጠኛ Aይደለሁም

9. ድንግልና ለጋብቻ ከቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ ሊመደብ ይገባል?(Aዎ___/Aይ___) 10. በባህላችን ድንግልና ለሴቶች ምን ያህል Aስፈላጊ ነው?

a. በጣም Aስፈላጊ ነው b. ያን ያህል Aስፈላጊ Aይደለም

ድንግልና በAዲስ Aበባ ወጣቶች Eይታ Aዲስ መዝናኛ

21

c. ፈፅሞ Aስፈላጊ Aይደለም 11. በባህላችን ድንግልና ለወንዶች ምን ያህል Aስፈላጊ ነው?

a. በጣም Aስፈላጊ ነው b. ያን ያህል Aስፈላጊ Aይደለም c. ፈፅሞ Aስፈላጊ Aይደለም

12. ስለድንግልና ከጓደኞችሽ ጋር ታወራላችሁ? (Aዎ___/Aይ___) 13. ድንግልናሽን ከማን ጋር ብታጪ ትመርጫለሽ?

a. ባሌ b. ከጋብቻ በፊት ለማገኘው ፍቅረኛዬ c. በተራ Aጋጣሚ ባጣውም Aይቆጨኝም