34
ባሕረ፡ሐሳብ። (2005)

የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

Embed Size (px)

DESCRIPTION

This is a brief presentation on the Ethiopian Orthodox Tewahedo Calender . It explores why there was a need for the calender and, deals with how the days in which the varies fasting and festivals lie are found for the year 2005.

Citation preview

Page 1: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

ባሕረ፡ሐሳብ።(2005)

Page 2: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

ባሕረ፡ሐሳብ።•ይህ፡ርእስ፡ሰፋ፡ያለ፡ትርጕም፡ያለውና፡በውስጡም፡ብዙ፡የሐሳበ፡ዘመን፡ትንታኔዎች፡የሚታወቁበት፡ዐቢይ፡አንቀጽ፡ነው።

•‘ባሕረ፡ሐሳብ’፡መባሉም፡ባሕር፡ጥልቅና፡ሰፊ፥የሰው፡ልጅ፡ባካሉ፡ዋኝቶ፡ሊሻገረው፡የማይችል፡ታላቅ፡የውሃ፡ክምችት፡እንደ፡ኾነ፡የዘመን፡

ክፍልፋዮችም፡በዕላታት፡በሳምንታት፡በአውራኅና፡በዓመታት፡የየዕለታቱ፡

ድቁቅ፡ጊዜያት፡ሳይቀሩ፥ታትተውና፡ተሰፍረው፥በየቀመራቸው፡ተመድበው፡የሚገለጹበት፡ሰፊና፡ጥልቅ፥ሰው፡በሐሳብ፡መልሕቅ፡የሚገሠግሥበት፡የአእምሮ፡መዋኛ፡ስለ፡ኾነ፥ባሕረ፡ሐሳብ፡ተብሏል።

•ባሕረ፡ሐሳብ፡በዝርዝር፡ለማተት፡መነሣት፡ዐባይን፡በጭልፋ፡ይሆናል። ነገር፡ግን፡ባጪሩ፡ቀንጨብ፡አድርጌ፡ለማቅረብ፡ያኽል፡ነው።

Page 3: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

በባሕረ፡ሐሳብ፡ውስጥ፡የሐሳበ፡ዘመን፡ትንታኔዎች፡ለምን፡ እንደተሠሩ፤

• ጌታችን፡የሚወለድበትን፡ዘመን፡ለመረዳት፡

• በዓላትንና፡አጽዋማትን፡ለክቶ፡ለማወቅ፡ነው።

የሐሳበ፡ዘመን፡ዕውቀት፡በዘመነ፡ኦሪት፡ይሠራበት፡እንደ፡ነበር፡ይታወቃል።

ዋናው፡ዓላማ፤

• የአይሁድን፡አጽዋማትና፡በዓላት፡ለማወቅ፤

• የኢየሱስ፡ክርስቶስን፡ዘመነ፡ሥጋዌ፡ለመረዳት፡ነው።

Page 4: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

•በዓሎቻቸው፤ሀ. በዓለ፡መጸለት፤የቂጣ፡በዓል፡ማለት፡ነው። ይኽውም፡ያልቦካ፡እንጀራ፡የሚበሉበት፡ነው።ለ. በዓለ፡መጥቅዕ፤የዘመን፡መለወጫ፡በዓል፡ነው።ሐ. በዓለ፡ፍሥሕ፤ከግብጽ፡ባርነት፡ነጻ፡የወጡበት፡በዓል፡ነው።መ. ልበ፡ምድር፤ባሕረ፡ኤርትራን፡በደረቅ፡የተሻገሩበት፡በዓል፡ነው።ሠ. በዓለ፡ሠዊት፤የአዝመራው፡ሰብል፡የሚታይበት፡በዓል፡ነው።

•ጾሞቻቸው፤ሀ. ጾመ፡አይሁድ፤ለ. ጾመ፡አስቴር፤ሐ. ጾመ፡ዮዲት፤መ. ጾመ፡ነነዌ፡ናቸው።

Page 5: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

ዓመተ፡ዓለም፤ዓለም፡ከተፈጠረ፡ጊዜ፡ዠምሮ፥በፀሓይ፡ላይ፡በተመሠረተው፡ዑደት፡

ሲቈጠር፥እንደ፡ኢትዮጵያ፡የዘመን፡አቈጣጠር፥በዘንድሮው፡መስከረም፥ጠቅላላው፡ዘመን፡7505፡ዓመተ፡ዓለም፡ይኾናል።ይህ፥እንዴት፡እንደ፡ሆነ፡ጠቅለል፡ባለ፡መንግድ፡ሲመደብ፥

• ከአዳም፡እስከ፡ኖኅ፡ 2256፡ዘመን፤• ከኖኅ፡እስከ፡ሙሴ፡ 1588፡ዘመን፤• ከሙሴ፡እስከ፡ሰሎሞን፡ 593፡ዘመን፤• ከሰሎሞን፡እስከ፡ክርስቶስ፡ 1063፡ዘመን፡ይኾናል።

ጠቅላላ፡ድምር፡5500፡ዘመን፡ይኾናል።

Page 6: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

•ዓመተ፡ፍዳ(ዓመተ፡ኵነኔ): ከጌታ፡ልደት፡በፊት፡የተፈጸመ።

•ዓመተ፡ምሕረት፡ ከጌታ፡ልደት፡ወዲህ።

•ዓመተ፡ዓለም፡ ዓለም፡ከተፈጠረ፡ዠምሮ፡

እስካኹን፡ያለው፡ዘመን።

ዓመተ፡ፍዳ(ዓመተ፡ኵነኔ) + ዓመተ፡ምሕረት = ዓመተ፡ዓለም5500 + 2005 = 7505

5500 ዓመት

2005 ዓመት

7505 ዓመት

Page 7: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

መስከረም፤•ጥንት፥ከሥጋዌ፡በፊት፥ባይሁድና፡በዓለም፡ኹሉ፥አኹንም፡በኢትዮጵያና፡በግብጽ፡የወርና፡የዓመት፡መዠመሪያ፡መስከረም፡ነው።

•በምሥራቅ፡ኦርቶዶክስ፡አብያተ፡ክርስቲያናት፥መስከረም፡1፡ቀን፡የቤተ፡ክርስቲያን፡ዐዲስ፡ዓመት፡እየተባለ፡እስካኹን፡ይከበራል።

•በዚህም፡ወር፡በዓመተ፡ዓለም፡ውስጥ፡የሚገኙት፡ጥንታትና፡አቅማራት፥አዕዋዳትና፡ሠግር፥አበቅቴና፡መጥቅዕ፥ስፍረ፡ሰዓትና፡መዛብዓ፡ፀሐይ፥

ሕፀፅና፡የጨረቃ፡ልደት፣ሌሎችም፡ኹኔታዎች፡በየስፍራቸው፡

የሚመደቡበት፡ወቅት፡ነው።

Page 8: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

አበቅቴና፡መጥቅዕ፤• አበቅቴ(epact)፡ ፀሐይ፡የዓመቱን፡ዙር፡በ365፡ከሩብ፡ቀናት፡ስትጨርስ፡ጨረቃ፡ግን፡354፡ቀናት፡ብቻ፡ይፈጅባታል።ከ365፡ሲቀነስ፡354፡የሚገኘው፡ቁጥር፡11፡ስለሆነ፡አበቅቴ፡ከዚህ፡የመጣ፡ነው፡ይላሉ።

•መጥቅዕ፡ አበቅቴ፡ተወልዶ፡የመጅመሪያው፡ወር፡

የሚሞላበት፡ቀን፡ደግሞ፡ መጥቅዕ፡ይባላል።

አበቅቴ = የፀሐይ፡ዓመት፡ዙር - የጨረቃ፡ዓመት፡ዙር11 ቀን = 365 ቀን - 354 ቀን

Page 9: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

በቀላሉ፡ስለ፡ሐሳበ፡ዘመን፡የድሜጥሮስ፡ድርሻ፤

ድሜጥሮስ፡አቤቅቴን፡እና፡ምጥቅዕን፡በተገቢው፡ቦታ፡እንዲውሉ፡ያደረገ፡

ነው።

• አመዳደቡም፡ሱባኤ፡ሲገባ፡በማዕልት(በቀን)፡7x7፡የቀን፡ሱባኤ፡ያዘ፥ተባዝቶ፡የሚገኘው፡ቁጥር፡49፡ነው። በ30፡ሲገደፍ፡19፡ይቀራል፥ይህን፡መጥቅዕ፡ብሎታል።

• እንደገና፡ከሌሊቱ፡7x23፡የሌሊት፡ሱባኤ፡ያዘ፡ውጤቱ፡161፡ይሆናል፡በ30፡ሲገደፍ፡11፡ይቀራል፥ይህን፡አበቅቴ፡ብሎ፡ሰየመው።

አብቅቴ፡እና፡መጥቅዕ፡የተለየ፡አመጣጥ፡እንዳላቸው፡ብዙ፡ሊቃውንት፡

ይናገራሉ

Page 10: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

• ዓዋጅ 1፡ “አበቅቴ፡ወመጥቅዕ፡ክልኤሆሙ፡ኅቡረ፡ኢይበዝኁ፡እም፴፡ወኢይውኅዱ፡እም፴፡ወትረ፡የከውኑ፡፴።”(አበቅቴና፡መጥቅዕ፡ሁለቱ፡በኅብረታቸው፡ከ30፡አይበዙም፥ከ30፡አይጎድሉም፤ዘውትር፡30፡ይሆናሉ።)

• ዓዋጅ 2፡ “አበቅቴ፡ከነሐሴ፡8፡አያንስም፤ከጳጕሜን፡5፡አይበልጥም።”

• ዓዋጅ 3፡ “መጥቅዕ፡ከመስከርም፡15፡አይወርድም፤ከጥቅምት፡13፡በላይ፡አይወጣም።”

አበቅቴ + መጥቅዕ = 30

Page 11: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

አጽዋማትና፡በዓላትን፡ምድብ፡ለማወቅና፡ዓመተዓለምንም፡ለመተንተን፡

ይሚረዱን፡7፡አዕዋዳት፡ወይም፡መስፈሪያዎች፡ አሉ፡እነርሱም፤

ሀ. ዐውደ፡ዕለት፤ከእሑድ፡እስከ፡ቅዳሜ፡ያሉት፡7፡ዕለታት፡ናቸው።

ለ. ዐውደ፡ወርሕ፤ በወርሕ፡ውስጥ፡የሚገኙ፡30፡ቀኖች። በጨረቃ፡ግን፡ባንደኛው፡ወርሕ፡30፡በሁላተኛው፡29፡እየሆኑ፡የሚገኙ፡ዕለታት፡ናቸው።

ሐ. ዐውደ፡ዓመት፤በፀሐይ፡ዑደት፡አቆጣጠር፡በዓመት፡የሚመላለሱ፡365፡ከሩብ፡ዕለታት፡ናቸው። በጨረቃ፡ግን፡354፡ዕለታት፡ናቸው።

• ከዚህ፡በታች፡ያሉት፡በዓመት፡የሚቆጠሩ፡ናቸው።

መ. ዐውደ፡ፀሐይ፤ይህም፡28፡ዓመት፡ይሆናል።በዚህም፡ዕለት፡እና፡ወንጌላዊ፡ይገናኙበታል(4x7=28)።

Page 12: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

ሠ. ዐውደ፡አብቅቴ፤ 19 ዘመን፡ነው።በዚህም፡ፀሐይና፡ጨረቃ፡የተመደበላቸውን፡መንገድ፡እየፈጸሙ፡በተጠሩበት፡ምስኮት(ኆኅት)፡ይገናኙበታል።

ረ.ዐውደ፡መኅተም፤76(19x4=76)ዘመን፡ነው፡በዚህም፡አብቅቴና(19)፡ወንጌላዊ(4)፡ይገናኙበታል። ማኅተም፡መባሉም፡አበቅቴው፡ለአበቅቴ፥ወንጌላዊው፡ለወንጌላውያን፡ፍጻሜ፡በመሆናቸው፡ነው።

ሰ. ዐቢይ፡ቀመር፤ 532(19x4x7=532)፡ዘመን፡ነው። በዚህም፡አበቅቴ(19)፥ወንጌላዊ(4)፥እና፡ዕለት(7)፡ይገናኙበታል።ዕለቱ፡ሰኞ፥አበቅቴው፡18፥ወንጌላዊው፡ዮሐንስ፡ነው።

Page 13: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

መጥቅዕ፤•የዘንድሮውን፡በዓላትና፡አጽዋማት፡በየስፍራቸው፡ለመመደብ፡መጥቅዕ፡የሚውልበትን፡ማግኘት፡አለብን፤መጥቅዕን፡ለማግኘት፡ወንበሩን፡ማቋቋም፡ይኖርብናል።

ወንበር፡ አበቅቴንና፡መጥቅዕን፡ለማግኘት፡የምንሰፍርበት፡መሥፈሪያ፡ነው።

•ለወንበር፡ማዋቀሪያ፡ደግሞ፡ሦስት፡ቀመሮችን፡እንመድባለን፥ እነርሱም፤ሀ. ዐቢይ፡ቀመር ፡ 532(19x7x4=532)፡ዘመን፡ነው። ዓመተ፡ዓለምን፡በዐቢይ፡ቀመር፡ስናካፍለው፡(7505 ፥ 532 = 14 ቀሪ 57)።

ለ. ማዕከላዊ፡ቀመር ፡ 76(19x4)፡ዘመን፡ነው። ከ57፡በላይ፡ስለ፡ኾነ፡ማካፈል፡አያስፈልግም። ቢያስፈልግ፡ግን፡7505፥76= 98 ደርሶ ቀሪ 57

ሐ. ንዑስ፡ቀመር፡ 19፡ዘመን፡ነው። ከላይ፡ያገኘነው፡ቀሪ፡57፡ሲካፈል፡ ለ19፥ ቀሪ፡0፡ይኾናል። ከ19፡ዘመን፡19ኛው፡ማለት፡ነው።በሌላ፡መንገድ፤ 7505፥19= 395 ደርሶ፡ቀሪ፡0 ይሆናል።

Page 14: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

የንዑስ፡ቀመር፡ዓመቶች አበቅቴ መትቅዕ1ኛ 0 30 መስከረም2ኛ 11 19 መስከረም3ኛ 22 8 ጥቅምት4ኛ 3 27 መስከረም5ኛ 14 16 መስከረም6ኛ 25 5 ጥቅምት7ኛ 6 24 መስከረም8ኛ 17 13 ጥቅምት9ኛ 28 2 ጥቅምት10ኛ 9 21 መስከረም11ኛ 20 10 ጥቅምት12ኛ 1 29 መስከረም13ኛ 12 18 መስከረም

Page 15: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

የንዑስ፡ቀመር፡ዓመቶች አበቅቴ መጥቅዕ14ኛ 23 7 ጥቅምት15ኛ 4 26 መስከረም16ኛ 15 15 መስከረም17ኛ 26 4 ጥቅምት18ኛ 7 23 መስከረም19ኛ 18 12 ጥቅምት

የያዝነውን፡ዓመት፡መዠመሪያውን፡እንጂ፡ፍጻሜውን፡ስላላየነው፣ ማለት፡2005ን፡ገና፡ጀመርን፡እንጂ፡አልጨረስነውም፣ሰለዚህ፡ከቀሪው፡ቍጥር፡ከ19፡1፡ይቀነሳል። 19-1=18።

የተገኘው፡18፡ቍጥር፡‘ወንበር’፡ይባላል።በዚህ፡ወንበር፡አማካይነት፡የዘንድሮውን፡አበቅቴና፡መጥቅዕን፡እንመድባለን።

19ኛ 18 12 ጥቅምት

Page 16: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

• አበቅቴ፥ ወንበር፡18፤ የአበቅቴ፡መደብ(11)፡በ18፡ሲባዛ፡198፡ይሆናል፡11x18=198 198፥30= 6፡ጊዜ፡18፡ቀሪ።አበቅቴ፡ 18፡ኾነ፡ማለት፡ነው።

• መጥቅዕ ፥ መጥቅዕ፡መደቡ፡19፡ነው፡ብለናል።19x18=342 342፥30= 11 ፡ጊዜ፡ 12፡ቀሪ።መጥቅዕ፡ 12፡ኾነ፡ማለት፡ነው።

ዓዋጅ 1፥ አበቅቴ (18) + መጥቅዕ(12) = 30

Page 17: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

• በዓዋጅ 3፡መሰረት፤መጥቅዕ፡ሲአንስ፡(ከ13፡በታች፡ሲሆን፡)የመጥቅዕ፡ማረፊያ፡ጥቅምት፡ይሆናል፣ከዚያ፡በላይ፡ከሆነ፡በመስከረም፡ላይ፡ያርፋል።

መጥቅዕ < 13 የመጥቅዕ፡ማረፊያ፡ጥቅምት፡ይሆናል።መጥቅዕ > 13 የመጥቅዕ፡ማርፊያ፡መስከረም፡ይሆናል።

የዘንድሮ፡መጥቅዕ፡12፡ስለሆነ፥የመጥቅዕ፡ማረፊያ፡ጥቅምት፡12፡ይሆናል።

Page 18: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

1.መጥቅዕ፡መች፡ይውላል?(መስከረም፡ወይም፡ጥቅምት)

5.በዓላትና፡አጽዋማት፡የሚውሉበት፡ዕለት፤

2.መስከረም፡1፡መን፡ዕልት፡ይውላል?

3.መጥቅዕ፡የሚውልበት፡ዕለት፤

4.ነነዌ፡የሚውልበት፡ዕለት፤

የበዓላትና፡የአጽዋማትን፡ዕለት፡ለማውጣት፡የምንከተላቸው፡ደረጃዎች

Page 19: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

2. መስከረም፡1፡ቀንን፡ለማወቅ(ዕለተ፡ቀመርን፡ለማወቅ)፤• በባሕረ፡ሓሳብ፡የቁጥር፡ስሌት፡መሠረት፣የመጀመሪያ፡ቀን፡(ጥንተ፡ቀመር)ማክሰኞ፡ነው።

• የዘንድሮ፡ዓዲስ፡ዓመት፡የሚውልበትን፡ዕለት፡ለማወቅ፤

1 ቢተርፍ ማክሰኞ 5 ቢተርፍ ቅዳሜ

2 ቢተርፍ ረቡዕ 6 ቢተርፍ እሑድ

3 ቢተርፍ ሐሙስ 0 ቢተርፍ ሰኞ

4 ቢተርፍ ዓርብ

(ዓመተ፡ዓለም + መጠነ፡ራብዒት) ፥ 7 መጠነ፡ራብዒት = 7505፥4 = 1876 ቀሪ 1

Page 20: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

ዓመተ፡ዓለም = ዓመተ፡ፍዳ(ዓመተ፡ኵነኔ) + ዓመተ፡ምሕረት7505 = 5500 + 2005

መጠነ፡ራብዒት = 7505፥4 = 1876 ቀሪ 1

(7505 +1876) ፥ 7 = 1340 ትርፍ 1

(ዓመተ፡ዓለም +መጠነ፡ራብዒት) ፥ 7

1 ቢተርፍ ማክሰኞ

Page 21: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

3. መጥቅዕ፡የሚውልበትን፡ዕለት፡ለማወቅ፤• መስከረም፡ማክሰኞ፡ይብታል፣ስለዚህ፡የጥቅምት፡12ኛው፡ዕለት፡(መጥቅዕ፡የሚውልበት)፡ለማወቅ፤

መስከረም፡1 ማክሰኞመስከረም፡2 ረቡዕመስከረም፡3 ሐሙስመስከረም፡4 ዓርብ

...ጥቅምት፡1 ሐሙስጥቅምት፡2 ዓርብ

..ጥቅምት፡12 ሰኞጥቅምት፡13 ማክሰኞ• ስለዚህ፡መጥቅዕ፡ጥቅምት፡12፣ሰኞ፡ዕለት፡ይውላል።

Page 22: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

1.መጥቅዕ፡መች፡ይውላል?(መስከረም፡ወይም፡ጥቅምት)

5.በዓላትና፡አጽዋማት፡የሚውሉበት፡ዕለት፤

2.መስከረም፡1፡መን፡ዕልት፡ይውላል?

3.መጥቅዕ፡የሚውልበት፡ዕለት፤

4.ነነዌ፡የሚውልበት፡ዕለት፤

የበዓላትና፡የአጽዋማትን፡ዕለት፡ለማውጣት፡የምንከተላቸው፡ደረጃዎች

Page 23: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

4. ነነዌ፡የሚውልበት፡ዕለት፡ለማወቅ፤• መጥቅዕ፡ይሚውልበት፡ዕለት፡ታይቶ፡ከመጥቅዕ፡እስከ፡ነነዌ፡ስንት፡ቀን፡እንዳለ፡በሕግ፡የተወሰነ፡ነው።የመጥቅዕ፡ዕለት ከመጥቅዕ፡እስከ፡ነነዌ ተውሳክቅዳሜ 128፡ቀን = 4ወር፡8ቀን 8እሑድ 127፡ቀን = 4ወር፡7ቀን 7ሰኞ 126፡ቀን = 4ወር፡6ቀን 6ማክሰኞ 125፡ቀን = 4ወር፡5ቀን 5ረቡዕ 124፡ቀን = 4ወር፡4ቀን 4ኀሙስ 123፡ቀን = 4ወር፡3ቀን 3ዓርብ 122፡ቀን = 4ወር፡2ቀን 2

ሰኞ 126፡ቀን = 4ወር፡6ቀን 6

Page 24: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

• ዓዋጅ ፤ የነነዌ፡ጾም፡የሚጀምረው፡በጥር፡(ወደ፡መጨረሻው)፡ወይም፡በየካቲት፡(ወደ፡መጀመሪያው)፡ነው። ነነዌ፡የግድ፡ሰኞ፡መዋል፡አለባት።

• ወይንም፡ዓዋጁን፡ተጠቅሞ፡በቀላል፡መንገድ፡ለማግኘት፤

የካቲት፡ዓርብ፡ይብታል፡የየካቲት፡18ኛው፡ቀን፡ሰኞ፡ስለሆነ፡በዚኽ፡ቀን፡ነነዌ፡ትውላለች።

መጥቅዕ (ጥቅምት 12)+ 126ቀን = የካቲት 18

የሰኞ፡ተውሳክ + መጥቅዕ = መባጃ፡ሐመር6 + 12 = 18

Page 25: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

1.መጥቅዕ፡መች፡ይውላል?(መስከረም፡ወይም፡ጥቅምት)

5.በዓላትና፡አጽዋማት፡የሚውሉበት፡ዕለት፤

2.መስከረም፡1፡መን፡ዕልት፡ይውላል?

3.መጥቅዕ፡የሚውልበት፡ዕለት፤

4.ነነዌ፡የሚውልበት፡ዕለት፤

የበዓላትና፡የአጽዋማትን፡ዕለት፡ለማውጣት፡የምንከተላቸው፡ደረጃዎች

Page 26: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

•ለአጽዋማቱም፥ነነዌን፡መሠረት፡አድርገው፥ለየራሳቸው፡ተውሳክ፡አላቸው።

አጽዋማትና፡በዓላት ከነነዌ፡እስከ፤ ተውሳካቸውነነዌ (መባጃው፡ሐመር)ዐቢይ፡ጾም 14፡ቀን = 0፡ወር፡14ቀን 14ደብረ፡ዘይት 41፡ቀን = 1፡ወር፡11፡ቀን 11ሆሳዕና 62፡ቀን = 2፡ወር፡ 2፡ቀን 2ስቅለት 67፡ቀን = 2፡ወር፡ 7፡ቀን 7 ትንሣኤ 69፡ቀን = 2፡ወር፡9፡ቀን 9ርክበ፡ካህናት 93፡ቀን = 3፡ወር፡3፡ቀን 3ዕርገት 108፡ቀን = 3፡ወር፡18፡ቀን 18ጰራቅሊጦስ 118፡ቀን = 3፡ወር፡28፡ቀን 28ጾመ፡ሐዋርያት 119፡ቀን = 3፡ወር፡29፡ቀን 29ጾመ፡ድኅነት 121፡ቀን = 4፡ወር፡1፡ቀን 1

Page 27: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

• ዐቢይ፡ጾም ፤ከነነዌ፡እስከ፡ ዐቢይ፡ጾም፡14፡ቀን፡ብለን፡ነበር፡ስለዚህ፤

መጋቢት፡ 2፡ቀን፡ዐቢይ፡ጾም፡ይገባል።• ደብረ፡ዘይት ፤ከነነዌ፡እስከ፡ደብረ፡ዘይት፡41፡ቀን፡ብለን፡ነበር፡ስለዚህ፤

መጋቢት፡ 29፡ቀን፡ደብረ፡ዘይት፡ይውላል።፡• ሆሳዕና ፤ከነነዌ፡እስከ፡ሆሳዕና፡62፡ቀን፡ብለን፡ነበር፡ስለዚህ፤

ሚያዝያ፡ 20፡ቀን፡ሆሳዕና፡ይውላል።

የአጽዋማት፡ ወይም፡ + መባጃ፡ሐመር = አጽዋማቱ፡ወይም፡በዓላቱ:የበዓላት፡ተውሳክ የሚውሉበት፡ቀን፡ይሆናል

የካቲት 18 (ነነዌ) + 41ቀን = መጋቢት 29

የካቲት 18 (ነነዌ) + 14ቀን = መጋቢት 2

የካቲት 18 (ነነዌ) + 62ቀን = ሚያዝያ 20

Page 28: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

• ስቅለት ፤ ከነነዌ፡እስከ፡ስቅለት፡67፡ቀን፡ብለን፡ነበር፡ስለዚህ፤

ሚያዝያ፡ 25፡ቀን፡ስቅለት፡ይውላል።• ትንሣኤ፤ ከነነዌ፡እስከ፡ትንሣኤ፡69፡ቀን፡ብለን፡ነበር፡ስለዚህ፤

ሚያዝያ፡27፡ቀን፡ትንሣኤ፡ይውላል።• ርክበ፡ካህናት ፤ ከነነዌ፡እስከ፡ርክበ፡ካህናት፡93፡ቀን፡ብለን፡ነበር፤

ግንቦት፡21፡ቀን፡ርክበ፡ካህናት፡ይውላል።

የካቲት 18 (ነነዌ) + 67ቀን =ሚያዝያ 25

የካቲት 18 (ነነዌ) + 69ቀን = ሚያዝያ 27

የካቲት 18 (ነነዌ) + 93ቀን = ግንቦት 21

Page 29: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

• ዕርገት ፤ ከነነዌ፡እስከ፡ዕርገት፡108፡ቀን፡ብለን፡ ነበር፡ስለዚህ፤

ሰኔ፡6፡ቀን፡ስቅለት፡ይውላል።• ጰራቅሊጦስ ፤ከነነዌ፡እስከ፡ጰራቅሊጦስ፡118፡ቀን፡ብለን፡ነበር፤

ሰኔ፡16፡ቀን፡ትንሣኤ፡ይውላል።• ጾመ፡ሐዋርያት ፤ከነነዌ፡እስከ፡ጾመ፡ሐዋርያት፡119፡ቀን፡ብለን፡ነበር፤

ሰኔ፡17ቀን፡ርክበ፡ካህናት፡ይውላል።

•ጾመ፡ድኅነት ፤ከነነዌ፡እስከ፡ጾመ፡ሐዋርያት፡ 121፡ቀን፡ብለን፡ነበር፤

የካቲት 18 (ነነዌ) + 108ቀን = ሰኔ 6

የካቲት 18 (ነነዌ) + 118ቀን = ሰኔ 16

የካቲት 18 (ነነዌ) + 119ቀን = ሰኔ 17

የካቲት 18 (ነነዌ) + 121ቀን = ሰኔ 19

Page 30: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

1.መጥቅዕ፡መች፡ይውላል?(መስከረም፡ወይም፡ጥቅምት)

5.በዓላትና፡አጽዋማት፡የሚውሉበት፡ዕለት፤

2.መስከረም፡1፡መን፡ዕልት፡ይውላል?

3.መጥቅዕ፡የሚውልበት፡ዕለት፤

4.ነነዌ፡የሚውልበት፡ዕለት፤

የበዓላትና፡የአጽዋማትን፡ዕለት፡ለማውጣት፡የምንከተላቸው፡ደረጃዎች

Page 31: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

ሕፀፅ፡ደግሞ፡መስከረምና፡ጥቅምት፡1፤ኅዳርና፡ታሕሣሥ፡2፤ጥርና፡የካቲት፡3፤መጋቢትና፡ሚያዝያ፡4፤ግንቦትና፡ሰኔ፡5፤ሐምሌና፡ነሐሴ፡6።

1. ተሡዑ፡ሠርቀ፡ሌሊት፡(7+1+1)=92. አሚሩ፡ሠርቀ፡መዓልት(1)3. ዐሥሩ፡ወሠሉስ፡ሠርቀ፡ወርሕ(13)=9+44. ሠኑየ፡(2)፡ሠርቀ፡ዕለት።

Page 32: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

ወንጌላዊውን፡ለማወቅ።ወንጌላዊውን፡ለማወቅ፡ዓመተ፡ዓለሙን፡ማለት፡7505፡ለ4፡ማካፈል፡ይኖርብናል።

1፡ቢተረፍ፡ይሆናል፡ማቴዎስ። 3፡ቢተርፍ፡ይሆናል፡ሉቃስ።2፡ቢተረፍ፡ይሆናል፡ማርቆስ ። 0፡ቢተረፍ፡ይሆናል፡ዮሐንስ።

ዘመነ፡ዮሐንስ፡ኾኖ፥በ7505፡ዓመተ፡ዓለም።በ2005፡ዓመተ፡ምሕረት፥ባጪሩ፡የቀረበው፡የባሕር፡ሐሳብ፡ትንታኔ፡ይኸው፡ነው።

7505፥4= 1876 ደርሶ፡ቀሪ፡1።ስለዚኽ፡ማቴዎስ፡ወንጌላዊ፡ዘንድሮ፡ይውላል።

Page 33: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

በስመ፡አብ፡በዘንዜከር፡ሐሳባተ፡ሕጉ፡ወትእዛዛቲሁ፡ለእግዚእነ፡ወአምላክነ፡ወመድኃኒነ፡ኢየሱስ፡ክርስቶስ፣ሐሳበ፡ነቢያት፡ወሐዋርያት፣ሐሳበ፡ጻድቃን፡ወሰማዕት፣ሐሳበ፡ኄራን፡መላእክት፣እንዘ፡ሀሎነ፡በዘመነ፡ማቴዎስ፡ወንጌላዊ፡ቡሩክ፡ያብጽሐነ፡እስከ፡ዘመነ፡ማርቆስ፡ዜናዊ።(በዘመነ፡ማቴዎስ፡ወንጌላዊው፡እንዳለን፤እንዲሁ፡እስከ፡ዘመነ፡ማርቆስ፡ዜናዊ፡በሰላም፡ያድርሰን።)

በ ወበ ፡ኮነ፡ዓመተ፡ፍዳ፣በ ወ ፭ ፡ኮነ፡ዓመተ፡ምሕረት፣በ ወበ ወ፭፡ኮነ፡ዓመተ፡ዓለም። ሠረቀ፡ለነ፡ወርሐ፡መስከረም፡ቡሩክ፡ያብጽሐነ፡እስከ፡ወርሐ፡ጥቅምት፡አሜን።(ዓመተ፡ፍዳ፡5500፡ሆነ፤ ዓመተ፡ምሕረት፡2005፡ሆነ፤ ዓመተ፡ዓለም፡7505፡ሆነ። የመስከረም፡ወር፡ገባልን፤እስከ፡ጥቅምት፡ወርም፡በሰላም፡ያድርሰን፡አሜን።)

Page 34: የ2005 ባሕረ፡ሓሳብ (Bahere Hasab an EOTC calender system)

ወስብሐት፡ለእግዚአብሔር፤አነሣሥቶ፡ላስጀመረን፥አስጀምሮ፡ላስፈጸመን፥ለዑል፡እግዚአብሔር፡

ክብርና፡ምስጋና፡ይድረሰው።

አሜን።