28
ገፅ 8 ገፅ 6 ናፍቆት ዮሴፍ ማህሌት ፋሲል አለማየሁ አንበሴ አለማየሁ አንበሴ ቅፅ 13 ቁጥር 722 ቅዳሜ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ብር 8.00 ህብረተሰብ ገፅ 10 የሰሞኑ አጀንዳ 5 የሰሞኑ አጀንዳ 3 ሰልፍ ወደ ገፅ 2 ዞሯል ሳኡዲ ወደ ገፅ 23 ዞሯል መንግስት ወደ ገፅ 6 ዞሯል ንግድና ኢኮኖሚ ገፅ 18 ገፅ 3 የአቶ መለስ “ራዕይ” የግለሰብ አምልኮን ማጥፋት አልነበረምን!? የኢቴቪ ማሣና ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ “የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ ፈልጓል፤ ግን ለውጡን የሚሸከምለት ፓርቲ ይፈልጋል” ከሳኡዲ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ሰቆቃ ባለ “4 ኮከቡ” ቤል ቪው ሆቴልና ስፓ ዛሬ ይመረቃል ረቡዕ ምሽት በጩቤ የተወጋው የ16 አመቱ ዳዊት መስፍን፤ በመኖሪያ ቤቱ ደጃፍ የሞተ ሲሆን፣ በእግር ኳስ ሰበብ በተከሰተ ፀብ ግድያውን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሶስት ታዳጊዎች በፖሊስ ተይዘዋል፡፡ ዳዊት እና ተጠርጣሪዎች ከአንድ አመት በፊት በእግር ኳስ ክበብ ተጣልተው እንደነበር የሚናገሩት የሟች እናት፣ ብዙ ጊዜ ይዝቱበት ነበር ብለዋል፡፡ በዛቻ ብቻ ሳይመለሱ፣ ታላቅ ወንድሙን በጩቤ ወግተው ለመግደል ሞክረው ነበር የሚሉት እኚሁ እናት፤ የግድያ ሙከራውን ለፖሊስ አመልክተን ለጊዜው ቢታሰሩም ወዲያው ተለቀቁ በማለት ያስታውሳሉ፡፡ ረቡዕ ማታ ከሁለት ሰዓት በኋላ ስልክ ተደውሎለት ከቤት የወጣው ዳዊት፤ ሳይመለስ እንደቀረ እናቱ ገልፀው፣ ወንድሙና ጓደኛው በር ላይ ሞቶ እንዳገኙት ተናግረዋል፡፡ የ10ኛ ክፍል የምስራቅ ጐህ ትምህርት ቤት ተማሪ የነበረው ዳዊት፤ ፀብ የማይወድ ልጅ እንደነበር የሚናገሩት አባቱ አቶ መስፍን አስራት፤ ተጠርጣሪዎቹ ከዚህ በፊት ቤተክርስቲያን አግኝተውት ሊጣሉት ፈልገው ነበር ብለዋል፡፡ ሲተናኮሉት ቆይተው ረቡዕ ምሽት ገደሉት፤ በዚያው ምሽት ተይዘው ጩቤውን ለፖሊስ አሳይተዋል ብለዋል አቶ መስፍን፡፡ ፖሊስ በበኩሉ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን ገልጿል፡፡ የ16 አመቱ ታዳጊ በእግር ኳስ ሰበብ በእኩዮቹ መገደሉን ወላጆች ገለፁ ሠሞኑን በሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ እየደረሠ ያለው ግፍና ስቃይ እንዳሳዘናቸው የገለፁ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፤ የሣውዲ አረቢያ መንግስት እና የኢትዮጵያ መንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ተጠያቂ ናቸው ሲሉ ተናገሩ፡፡ የመድረክ ሊቀመንበር ዶ/ር መራራ ጉዲና፣ ሣውዲ አረቢያ የራሷንም ዜጐች መብት የማታከብር ሃገር መሆኗን ገልፀው፣ በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመው አሠቃቂ ስራ ግን በ21ኛው ክ/ዘመን የማይጠበቅ ግፍ ነው ብለዋል። “ለዜጐቻችን ስቃይ የሳኡዲና የአገራችን መንግስታት ተጠያቂ ናቸው” ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይ በሴቶች ላይ የሚፈፀመው ድርጊት አስነዋሪ ነው በማለት መወገዝ እንዳለበት የተናገሩት ዶ/ር መራራ፤ ዋናው ተጠያቂ የሳውዲ መንግስት ነው ብለዋል፡፡ “በሌላ በኩል ኢህአዴግ ሃገሪቱን የስደት ሃገር አድርጓል” ያሉት ዶ/ር መረራ፤ በሜድትራኒያን፣ በየመንና በደቡብ አፍሪካ መስመሮች የሚሰደዱ ዜጐቻችን የአውሬ ሲሣይ እየሆኑ ነው፤ በሃገር ውስጥም በውጭም የዜጐቹን መብት ማስከበር ያልቻለው የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ መሆን አለበት” ብለዋል፡፡ በሣውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ በትኩረት እየተከታተሉ መሆናቸውን የሚገልፁት የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት በዜጐቻችን ላይ የተፈፀመውን ድርጊት ለመከላከልና ለማስቆም አለመቻሉ መንግስት አልባ መሆናችንን የሚያሣይ ነው ብለዋል፡፡ አቶ አበባው እንደሚሉት፤ የሌላ ሃገር መንግስት ቢሆን ኖሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን እዚያ ሃገር ድረስ ልኮ ሄዶ የዜጐቹን መብት ያስከብር ነበር ብለዋል - አቶ አበባው፡፡ እዚህ ሃገር የውጭ ዜጐች ከቀን ሠራተኛነት ጀምሮ በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ መብታቸው ተከብሮላቸው ይኖራሉ ያሉት አቶ አበባው፤ “የኛ ዜጐች በሳውዲ ከሰውነት በታች ተዋርደው ግፍ የሚደርስባቸው ለዜጐች የሚቆረቆር መንግስት ስለሌለ ነው” ብለዋል፡፡ ለዜጐቻችን ሠቆቃ የመጀመሪያ ደረጃ ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግስት ነው በማለት የሚናገሩት አቶ አበባው፤ ዜጐች በሃገራቸው የስራ እድል የሚያገኙበትን አማራጭ ማስፋት የመንግስት ሃላፊነት ቢሆንም፤ በተቃራኒው በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ከተሞች ብሎኬት የሚሠሩት፣ ሹፌር የሚሆኑት፣ አሣማ በሳኡዲ አረቢያ በኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያና እንግልት ለመቃወም በትላንትናው እለት ሰማያዊ ፓርቲ ጠርቶት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በፀጥታ ሀይሎች የከሸፈ ሲሆን፤ ለሰልፉ የወጡት ሰዎች፣ መንገደኞች፣ በተለያየ ምክንያት ጥቁር የለበሱና ሌሎችም ድብደባ ደርሶባቸዋል፡፡ ጋዜጠኞችን ጨምሮ ከሰባ በላይ ሰዎች በላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ታስረዋል፡፡ በድብደባው ሲቪል የለበሱ የፀጥታ ሃይሎችም እንደተጐዱ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፀጥታ ሀይሎች ከሸፈ በርካታ ሰዎች ተደብድበዋል በላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ከ70 በላይ ሰዎች ታስረዋል የላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ሀላፊ ገልፀዋል፡፡ ሰልፉን የጠራው ፓርቲ አመራሮች ከፅፈት ቤታቸው ሳይወጡ መታሰራቸው የተሰማ ሲሆን የሳኡዲ አረቢያ ኤምባሲ አካባቢ በፌደራል እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ተከቦ ውሏል፡፡ ወደ ኤምባሲው የሚጠጋ፣ ሰብሰብ ብሎ የቆመ፣ ፎቶ ሲያነሳ የተገኘና ሌሎችም በፖሊስ ነጭ ፒክ አፕ መኪና እየተጫኑ ላንቻ አካባቢ በሚገኘው የወረዳ 18 ፖሊስ የተወሰዱ ሲሆን፤ ፖሊስ ጣቢያ ከገቡት ውስጥ የ70 አመት አሮጊት እና የ62 አመት አዛውንት ይገኙበታል፡፡ “ምንም የማውቀው ነገር የለም፤ ከልጄ ጋር መንገድ እየሄድኩ ነው የተያዝኩት” ብለዋል፤ የ70 ዓመቷ አሮጊት፡፡ ከታሰሩት መካከል በድብደባ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ኢዮብ አርጋው የተባለ ወጣት፤ አብረውት በታሰሩት ሰዎች ጉትጐታና ለቅሶ ፖሊስ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ወስዶታል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ረቡዕ ማታ በሰጠው በኢትዮጵያ ያለው የመንግስት ስርአት በርካታ ጋዜጠኞችን እስር ቤት አጉሯል፣ ጠንካራ የግል ጋዜጦችንም ዘግቷል ያለው አንድነት ፓርቲ፤ የሚዲያ ነፃነት እንዲረጋገጥና፣ የታሰሩ ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቀ፡፡ ፓርቲው ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ፤ ሰሞኑን በአዲስ አበባ “መንግስት ጠንካራ ጋዜጦችን ዘግቶ፣ ጋዜጠኞችን እስር ቤት አጉሯል” - ( አንድነት ፓርቲ) በተዘጋጀው ስድስተኛው የአፍሪካ ሚዲያ መሪዎች ፎረም ላይ የተገኙ የሚዲያ ባለቤቶችና አዘጋጆች፤ በሀገሪቱ ስላለው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ችግር፣ ስፋትና ጥልቀት፣ ቃሊቲ ሄደው የታሰሩ ጋዜጠኞችን በማነጋገር ማረጋገጥ ይችላሉ ብሏል፡፡ ጉባኤው በኢትዮጵያ መካሄዱን እንዳልተቃወመ የጠቆመው ፓርቲው፣ በገዢዎች የሚታፈነው የአፍሪካ ሚዲያ ላይ ለውጥ ያመጣል የሚል ተስፋ ግን የለኝም ብሏል፡፡ ሚዲያውን የሚጨቁኑትና የሃሳብ ልዕልና እንዳይኖረው የሚያደርጉት አምባገነን መሪዎች መሆናቸውን በመግለፅ፡፡ “በኢትዮጵያ የግል ጋዜጦችና መፅሄቶች ተልካሻ ሰበብ እየተፈለገ ይዘጋሉ፤ ሥርዓቱን የሚተቹ ጋዜጠኞች አገር ጥለው እንዲሰደዱ ይደረጋሉ፤ ወደ ደራሲያንና የድርሰት ወዳጆች ለሥነ ጽሑፍ እድገት እንዲቆሙ ተጠየቀ “የጋዜጠኞች” ማህበራቱን ኢህአዴግ ራሱ ታዝቧቸዋል!

news paper

Embed Size (px)

DESCRIPTION

1111111111111111111111111111

Citation preview

ገፅ 8

ገፅ 6

ናፍቆት ዮሴፍ

ማህሌት ፋሲል

አለማየሁ አንበሴ

አለማየሁ አንበሴ

ቅፅ 13 ቁጥር 722 ቅዳሜ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ብር 8.00

ህብረተሰብ ገፅ 10

የሰሞኑ አጀንዳ 5

የሰሞኑ አጀንዳ 3

ሰልፍ ወደ ገፅ 2 ዞሯል

ሳኡዲ ወደ ገፅ 23 ዞሯል

መንግስት ወደ ገፅ 6 ዞሯል

ንግድና ኢኮኖሚ ገፅ 18

ገፅ 3

የአቶ መለስ “ራዕይ”

የግለሰብ አምልኮን ማጥፋት

አልነበረምን!?

የኢቴቪ ማሣና ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ

“የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ ፈልጓል፤ ግን ለውጡን የሚሸከምለት ፓርቲ ይፈልጋል”

ከሳኡዲ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን

ሰቆቃ

ባለ “4 ኮከቡ” ቤል ቪው ሆቴልና ስፓ ዛሬ ይመረቃል

ረቡዕ ምሽት በጩቤ የተወጋው የ16 አመቱ ዳዊት መስፍን፤ በመኖሪያ ቤቱ ደጃፍ የሞተ ሲሆን፣ በእግር ኳስ ሰበብ በተከሰተ ፀብ ግድያውን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሶስት ታዳጊዎች በፖሊስ ተይዘዋል፡፡

ዳዊት እና ተጠርጣሪዎች ከአንድ አመት በፊት በእግር ኳስ ክበብ ተጣልተው እንደነበር የሚናገሩት የሟች እናት፣ ብዙ ጊዜ ይዝቱበት ነበር ብለዋል፡፡ በዛቻ ብቻ ሳይመለሱ፣ ታላቅ ወንድሙን በጩቤ ወግተው ለመግደል ሞክረው ነበር የሚሉት እኚሁ እናት፤ የግድያ ሙከራውን ለፖሊስ አመልክተን ለጊዜው ቢታሰሩም ወዲያው ተለቀቁ በማለት ያስታውሳሉ፡፡ ረቡዕ ማታ ከሁለት ሰዓት በኋላ ስልክ ተደውሎለት ከቤት የወጣው ዳዊት፤ ሳይመለስ እንደቀረ እናቱ ገልፀው፣ ወንድሙና ጓደኛው በር ላይ ሞቶ እንዳገኙት ተናግረዋል፡፡

የ10ኛ ክፍል የምስራቅ ጐህ ትምህርት ቤት ተማሪ የነበረው ዳዊት፤ ፀብ የማይወድ ልጅ እንደነበር የሚናገሩት አባቱ አቶ መስፍን አስራት፤ ተጠርጣሪዎቹ ከዚህ በፊት ቤተክርስቲያን አግኝተውት ሊጣሉት ፈልገው ነበር ብለዋል፡፡ ሲተናኮሉት ቆይተው ረቡዕ ምሽት ገደሉት፤ በዚያው ምሽት ተይዘው ጩቤውን ለፖሊስ አሳይተዋል ብለዋል አቶ መስፍን፡፡ ፖሊስ በበኩሉ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን ገልጿል፡፡

የ16 አመቱ ታዳጊ በእግር ኳስ ሰበብ በእኩዮቹ መገደሉን

ወላጆች ገለፁ

ሠሞኑን በሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ እየደረሠ ያለው ግፍና ስቃይ እንዳሳዘናቸው የገለፁ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፤ የሣውዲ አረቢያ መንግስት እና የኢትዮጵያ መንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ተጠያቂ ናቸው ሲሉ ተናገሩ፡፡

የመድረክ ሊቀመንበር ዶ/ር መራራ ጉዲና፣ ሣውዲ አረቢያ የራሷንም ዜጐች መብት የማታከብር ሃገር መሆኗን ገልፀው፣ በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመው አሠቃቂ ስራ ግን በ21ኛው ክ/ዘመን የማይጠበቅ ግፍ ነው ብለዋል።

“ለዜጐቻችን ስቃይ የሳኡዲና የአገራችን መንግስታት ተጠያቂ ናቸው” ተቃዋሚ ፓርቲዎች

በተለይ በሴቶች ላይ የሚፈፀመው ድርጊት አስነዋሪ ነው በማለት መወገዝ እንዳለበት የተናገሩት ዶ/ር መራራ፤ ዋናው ተጠያቂ የሳውዲ መንግስት ነው ብለዋል፡፡ “በሌላ በኩል ኢህአዴግ ሃገሪቱን የስደት ሃገር አድርጓል” ያሉት ዶ/ር መረራ፤ በሜድትራኒያን፣ በየመንና በደቡብ አፍሪካ መስመሮች የሚሰደዱ ዜጐቻችን የአውሬ ሲሣይ እየሆኑ ነው፤ በሃገር ውስጥም በውጭም የዜጐቹን መብት ማስከበር ያልቻለው የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ መሆን አለበት” ብለዋል፡፡

በሣውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን

ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ በትኩረት እየተከታተሉ መሆናቸውን የሚገልፁት የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት በዜጐቻችን ላይ የተፈፀመውን ድርጊት ለመከላከልና ለማስቆም አለመቻሉ መንግስት አልባ መሆናችንን የሚያሣይ ነው ብለዋል፡፡ አቶ አበባው እንደሚሉት፤ የሌላ ሃገር መንግስት ቢሆን ኖሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን እዚያ ሃገር ድረስ ልኮ ሄዶ የዜጐቹን መብት ያስከብር ነበር ብለዋል - አቶ አበባው፡፡

እዚህ ሃገር የውጭ ዜጐች ከቀን ሠራተኛነት ጀምሮ በተለያዩ የስራ

መስኮች ላይ መብታቸው ተከብሮላቸው ይኖራሉ ያሉት አቶ አበባው፤ “የኛ ዜጐች በሳውዲ ከሰውነት በታች ተዋርደው ግፍ የሚደርስባቸው ለዜጐች የሚቆረቆር መንግስት ስለሌለ ነው” ብለዋል፡፡

ለዜጐቻችን ሠቆቃ የመጀመሪያ ደረጃ ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግስት ነው በማለት የሚናገሩት አቶ አበባው፤ ዜጐች በሃገራቸው የስራ እድል የሚያገኙበትን አማራጭ ማስፋት የመንግስት ሃላፊነት ቢሆንም፤ በተቃራኒው በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ከተሞች ብሎኬት የሚሠሩት፣ ሹፌር የሚሆኑት፣ አሣማ

በሳኡዲ አረቢያ በኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያና እንግልት ለመቃወም በትላንትናው እለት ሰማያዊ ፓርቲ ጠርቶት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በፀጥታ ሀይሎች የከሸፈ ሲሆን፤ ለሰልፉ የወጡት ሰዎች፣ መንገደኞች፣ በተለያየ ምክንያት ጥቁር የለበሱና ሌሎችም ድብደባ ደርሶባቸዋል፡፡ ጋዜጠኞችን ጨምሮ ከሰባ በላይ ሰዎች በላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ታስረዋል፡፡ በድብደባው ሲቪል የለበሱ የፀጥታ ሃይሎችም እንደተጐዱ

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፀጥታ ሀይሎች ከሸፈ

በርካታ ሰዎች ተደብድበዋል በላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ከ70 በላይ ሰዎች ታስረዋል

የላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ሀላፊ ገልፀዋል፡፡ ሰልፉን የጠራው ፓርቲ አመራሮች

ከፅፈት ቤታቸው ሳይወጡ መታሰራቸው የተሰማ ሲሆን የሳኡዲ አረቢያ ኤምባሲ አካባቢ በፌደራል እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ተከቦ ውሏል፡፡ ወደ ኤምባሲው የሚጠጋ፣ ሰብሰብ ብሎ የቆመ፣ ፎቶ ሲያነሳ የተገኘና ሌሎችም በፖሊስ ነጭ ፒክ አፕ መኪና እየተጫኑ ላንቻ አካባቢ በሚገኘው የወረዳ 18 ፖሊስ የተወሰዱ ሲሆን፤ ፖሊስ ጣቢያ ከገቡት ውስጥ የ70 አመት አሮጊት እና የ62 አመት አዛውንት

ይገኙበታል፡፡ “ምንም የማውቀው ነገር የለም፤

ከልጄ ጋር መንገድ እየሄድኩ ነው የተያዝኩት” ብለዋል፤ የ70 ዓመቷ አሮጊት፡፡

ከታሰሩት መካከል በድብደባ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ኢዮብ አርጋው የተባለ ወጣት፤ አብረውት በታሰሩት ሰዎች ጉትጐታና ለቅሶ ፖሊስ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ወስዶታል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ረቡዕ ማታ በሰጠው

በኢትዮጵያ ያለው የመንግስት ስርአት በርካታ ጋዜጠኞችን እስር ቤት አጉሯል፣ ጠንካራ የግል ጋዜጦችንም ዘግቷል ያለው አንድነት ፓርቲ፤ የሚዲያ ነፃነት እንዲረጋገጥና፣ የታሰሩ ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቀ፡፡

ፓርቲው ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ፤ ሰሞኑን በአዲስ አበባ

“መንግስት ጠንካራ ጋዜጦችን ዘግቶ፣ ጋዜጠኞችን እስር ቤት አጉሯል” - (አንድነት ፓርቲ)

በተዘጋጀው ስድስተኛው የአፍሪካ ሚዲያ መሪዎች ፎረም ላይ የተገኙ የሚዲያ ባለቤቶችና አዘጋጆች፤ በሀገሪቱ ስላለው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ችግር፣ ስፋትና ጥልቀት፣ ቃሊቲ ሄደው የታሰሩ ጋዜጠኞችን በማነጋገር ማረጋገጥ ይችላሉ ብሏል፡፡

ጉባኤው በኢትዮጵያ መካሄዱን እንዳልተቃወመ የጠቆመው ፓርቲው፣ በገዢዎች የሚታፈነው የአፍሪካ

ሚዲያ ላይ ለውጥ ያመጣል የሚል ተስፋ ግን የለኝም ብሏል፡፡ ሚዲያውን የሚጨቁኑትና የሃሳብ ልዕልና እንዳይኖረው የሚያደርጉት አምባገነን መሪዎች መሆናቸውን በመግለፅ፡፡

“በኢትዮጵያ የግል ጋዜጦችና መፅሄቶች ተልካሻ ሰበብ እየተፈለገ ይዘጋሉ፤ ሥርዓቱን የሚተቹ ጋዜጠኞች አገር ጥለው እንዲሰደዱ ይደረጋሉ፤ ወደ

ደራሲያንና የድርሰት ወዳጆች ለሥነ ጽሑፍ እድገት

እንዲቆሙ ተጠየቀ

“የጋዜጠኞች”

ማህበራቱን

ኢህአዴግ

ራሱ ታዝቧቸዋል!

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 2 ዜና

ማህሌት ፋሲል

ግሩም ሠይፉ

አለማየሁ አንበሴ

ከገቢዎችና ጉምሩክ የሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ በከባድ ሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩት ባለሀብቶች መካከል የምፋሞ ትሬዲንግ ባለቤት የአቶ ምህረተአብ አብርሃና ኩባንያቸውን ጉዳይ የመረመረው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት፤ ጉዳያቸው የሙስና ክስ ባለመሆኑ በሌላ ችሎት እንዲታይ ሲል ከትናንት በስቲያ ብይን ሰጠ፡፡

የፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ፤ በአቶ ምሕረተአብ አብርሃና ኩባንያቸው ምፋሞ ትሬዲንግ ኃላፊ. የተ የግ. ኩባንያ ላይ አምስት ክሶች ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን በጥቅሉ የክሶቹ ይዘት ኩባንያው ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ መክፈል የነበረበትን 3.5 ሚሊዮን ብር የመንግስት ገቢ ግብር አልከፈለም፤ ስራ አስኪያጁ አቶ ምሕረተአብም ጉዳዩን ተከታትለው አላስፈፀሙም የሚል ነበር፡፡

ክሱን ተከትሎ የተከሣሽ ጠበቃ ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት መቃወሚያ፤ ክሶቹ የሙስና አይደሉም፣ የገቢ ግብር አዋጅን የተመለከቱ ናቸው ያሉ ሲሆን አቃቤ ህግ በበኩሉ፤ የሙስና ክስ ባይሆንም ከገቢዎችና ጉምሩክ በተሠጠኝ ውክልና ነው ክሱን ያቀረብኩት ብሏል፡፡

በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት ከትናንት በስቲያ የዋለው ችሎትም፤ በተከሣሽ ጠበቃ በኩል የቀረቡትን ምላሾችና ችሎቱ በጉዳዩ ላይ ያለውን ስልጣን መመርመሩን አስታውቆ፤ 15ኛ ወንጀል ችሎት ከ10 አመት በላይ የሚያስቀጡ የሙስና ወንጀሎችን ብቻ እንዲመለከት ስልጣን የተሠጠው መሆኑን አመልክቷል፡፡ ፍ/ቤቱ በሰጠውም ብይን፤ ጉዳዩ የሙስና አለመሆኑን አቃቤ ህግ ራሱ ያረጋገጠው በመሆኑና 15ኛ ወንጀል ችሎት የሙስና ያልሆኑ ጉዳዮችን የማየት ስልጣን ስለሌለው፣ የአቶ ምህረተአብ አብርሃ ጉዳይ በሌላ ችሎት እንዲታይ አዝዟል፡፡ በተከሣሽ ጠበቃ የቀረቡት ሌሎች የመቃወሚያ ነጥቦችም ጉዳዩን እንዲመለከት ስልጣን በተሰጠው ችሎት በኩል የሚታይ እንደሆነ ፍ/ቤቱ አስታውቋል፡፡

ባለሃብቱ አቶ ምሕረተአብ አብርሃ፤ በሽግግር መንግስቱ ወቅትና ከዚያ በኋላ የሃገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት የአቶ ስዬ አብርሃ ወንድም ሲሆኑ፤ በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም የገቢዎችና ጉምሩክ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፋንታን ጨምሮ የመ/ቤቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ባለሀብቶች በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ሲታሰሩ አብረው የታሠሩ ናቸው፡፡

የባለሀብቱ የአቶ ምህረተአብ ክስ የሙስና ባለመሆኑ በሌላ ችሎት እንዲታይ ተበየነ

ሰልፍ ከገፅ 1 የዞረመግለጫ፤ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ አራት ዋና ዋና ነገሮች እንደሚከናወኑ ገልፆ ነበር፡፡

ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጡ ሁሉ በሳኡዲ የሞቱትን፣ የታሰሩትን እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማሰብና ሀዘናቸውን ለመግለጽ ጥቁር እንዲለብሱና ጥቁር ሪቫን ክንዳቸው ላይ እንዲያስሩ፣ ሙስሊሙ በዕለቱ በጁምአ ሶላት እንዲፀልይ እንዲሁም፣ በሳኡዲ ኤምባሲ በር ላይ ተቃውሞ ከመሰማቱ በፊት ለሞቱት የህሊና ፀሎት ለማድረግና በሳኡዲ አረቢያ እየደረሰ ስላለው አጠቃላይ ጉዳት የሚያትት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ጽሑፍ ቀርቦ ሰልፉ እንደሚበተን ገልፆ ነበር።

ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ ፓርቲው ለከተማው መስተዳድር በደብዳቤ ማሳወቁን እና መስተዳድሩ ምላሽ አለመስጠቱን፤ ይህ ደግሞ ሰልፉ መፈቀዱን የሚያሳይ እንደሆነ ኢ/ር ይልቃል ቀደም ብለው ገልፀው ነበር፡፡

የፓርቲው አባላት እንደገለፁት፤ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃልን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ለሰልፉ ከፓርቲው ጽ/ቤት ሳይወጡ ነው በፖሊስ የተወሰዱት፡፡ በስፍራው ተገኝተን እንደታዘብነው “ልጆቻችን ታረዱ ተገደሉ” እያሉ

የሚያለቅሱ እናቶች የነበሩ ሲሆን “ፖሊስ በህዝቡ ላይ ድብደባና እንግልት ማድረሱ አግባብ አይደለም፤ ይህ ኢትዮጵያ ሳይሆን ሳኡዲ ማለት ነው” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ “ፎቶ አንስታችኋል” በሚል ከሌሎች ሰዎች ጋር በፖሊስ ተይዘው ወረዳ 18 ላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ከስድስት ሰዓት እስከ ስምንት ተኩል ቆይተዋል፡፡

በፖሊስ ጣቢያው ውስጥ ከነበሩት መካከል አብዛኞቹ መንገደኞችና ስለጉዳዩ ምንም እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡

ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ ጋዜጠኞች ብቻ ተጠርተን የጣቢያው ሃላፊ ያነጋገሩን ሲሆን፤ “ሰልፉ አልተፈቀደም፣ ህገወጥ ነው፤ ህዝቡ ኤምባሲውን ሰብሮ ሊገባ ሲል ዝም ብሎ ማየት አይቻልም፣ ነገሩን በክፉ አትዩት ጉዳዩን የኢትዮጵየ መንግስትና የአለም መንግስታት እየተከታተሉት ነው” በማለት ካሜራችንን እና መታወቂያችንን የመለሱልን ሲሆን አንድ ጋዜጠኛ በሞባይሉ ያነሳውን ፎቶ እንዲያጠፋ ተደርጐ ተለቀናል፡፡

ፖሊስ ጣቢያው ውስጥ የነበሩ ከ70 በላይ ሰዎች ማተሚያ ቤት እስክንገባ ድረስ በእስር ላይ እንደነበሩ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በውሃ እጦት ረቡዕ እለት ሰልፍ ከወጡ በኋላ በርካታ ተማሪዎች የታሰሩ ሲሆን፤ ለሦስት ሳምንት ውሃ መቋረጡን በመቃወም የተሰበሰቡ የአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የግቢው ጥበቃ እንደበተናቸው ተገለፀ፡፡

በአቃቂ የሚገኘው የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም በውሀ እጦት መቸገራቸውንና ሰሚ ማጣታቸውን ተናግረዋል። የዩኒቨርሲቲዎቹ አስተዳደሮች በበኩላቸው፤ ውሃ ጨርሶ ጠፍቷል መባሉ የተጋነነ አባባል ነው በማለት፣ የውሃ እጥረት ለማቃለል እየጣሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በውሀ ችግር ሰልፍ አካሄዱ

ዩኒቨርስቲዎች የውሃ እጥረት ለማቃለል እየጣርን ነው ብለዋልበውሃ እጦት የተነሳ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳካሄዱ

የተናገሩ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ረቡዕ ማታ የከተማዋ ፖሊስ የዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ በመግባት በርካታ ተማሪዎችን እንዳሰረ ገልፀዋል፡፡ በማግስቱ የተወሰኑ ተማሪዎች ከእስር መለቀቃቸውንና ግቢው መረጋጋቱም ተነግሯል፡፡

ውሃ ካጣን ሦስት ሳምንት ሆኖናል የሚሉት የአዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በበኩላቸው፤ የዩኒቨርስቲ አስተዳደር መፍትሔ ሊሰጠን አልሞከረም ብለዋል፡፡ ተመራቂ ተማሪዎች ተሰባስበው ሁለት ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሲሞክሩ በግቢው ፖሊሶች እንደተበተኑ ተማሪዎቹ ጠቅሰው፤ አንድ ጄሪካን ውሃ ለመቅዳት ከሶስት ሰዓት በላይ ለወረፋ እንቆማለን ብለዋል፡፡ በሁለት ቀን አንዴ ውሃ ታገኛላችሁ ተብለን በዩኒቨርስቲው

አስተዳደር ፕሮግራም ቢለጠፍም፤ በተባለው ቀን ውሃ አግኝተን አናውቅም ያሉት ተማሪዎቹ፤ ለንጽህና ቀርቶ የመጠጥ ውሃ የምናገኘው በግዢ ነው ብለዋል።

የዩኒቨርስቲው የአለም አቀፍና የህዝብ ግንኙነት ዳሬክተር አቶ ታጉ ዘርጋው፤ የውሃ ችግር የተከሰተው በዩኒቨርስቲው ውስጥ ብቻ ሳይሆን በከተማው ሁሉ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ዩኒቨርስቲው ለሃያ ሺ ተማሪዎች ውሃ የሚያቀርበው የውሃ ጉድጓዶችን በመቆፈር ጭምር ነው ብለዋል፡፡ ሙሉ ለሙሉ ውሃ የለም መባሉ ግነት ነው ያሉት አቶ ታጉ፣ ያለውን ውሃ አብቃቅተን ለማዳረስ ብንሞክርም በተለያዩ ምክንያቶች እጥረት ተከስቷል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የአቃቂ ግቢ ተማሪዎችም የውሀ ችግር እየተባባሰ

መሆኑን ገልፀው፤ በአቃቂ አካባቢ ውሀ እያለ ግቢ ውስጥ ግን በሦስት ቀንም እንደልብ አይገኝም ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡›

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታረቀኝ ታደሰ፣ የውሀ ችግር መኖሩን ጠቅሰው፣ ውሃ ለበርካታ ቀናት ይቋረጣል መባሉ የተሳሳተ መረጃ ነው ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ለሰአታትም ሲሆን ውሀ መቋረጥ እንደሌለበት ዩኒቨርስቲው ያምናል ያሉት ዶ/ር ታረቀኝ፤ ውሀ ሁሌ እንዲኖረን ማድረግ የሚችሉት የውሀና ፍሳሽ ተቋማት ናቸው፤ በበኩላችን ችግሩን ለመቅረፍ አመቺ ቦታ መርጠን፤ ለቦታው ካሳ ከፍለን የውሀ ማከማቻ ታንከር በማስቀመጥ ውሃ እንዳይቋረጥ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የውሃ ጉድጓድ ለመጠቀም ሶስት የውሃ መሳቢያ ሞተሮች አስመጥተናል ብለዋል፡፡

በጅማ ከተማ ጋዜጠኛ ነኝ በማለት አጭበርብሯል የተባለው ቻይናዊ ኢንጂነር ዋንግ ዮንግ ለምርመራ እየተፈለገ ሲሆን፣ የጅማ ፖሊስ ተጠርጣሪውን ከአዲስ አበባ ይዞ ለመውሰድ እያፈላለገ ነው።

ዋንግ ዮንግን በሚመለከት የዜድቲኢ የህዝብ ግንኙነት ተወካይ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፣ ዜድቲኢ ለስራ ወደ ጅማ የላከው ሰራተኛ፤ የለም፤ የተፈላጊውን ማንነት እናጣራለን ብለዋል። ከጅማ ፖሊስ ለቀረበ ጥያቄ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ምላሽ፣ ዋንግ ዮንግ የቴሌኮም ኢንጂነርና የዜድቲኢ ሰራተኛ መሆኑን ገልጿል። የጅማ ፖሊስ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመተባበር ተፈላጊውን ተጠርጣሪ ለመያዝ ሲያፈላልግ እንደቆየና ትናንት የዜድቲኢ ተወካዮችን እንዳነጋገረ ታውቋል።

ፖሊስ ዋንግ ዮንግን ለምርመራ ማፈላለግ የጀመረው፣ ጥቅምት አጋማሽ ላይ ጅማ ውስጥ

ቻይናዊው የቴሌኮምኢንጂነር በጅማ ፖሊስ እየተፈለገ ነውጋዜጠኛ ነኝ በማለት አጭበርብሯል የተባለው ቻይናዊ የዜድቲኢ ሰራተኛ ነው ተብሏል።ZTE፣ ለስራ ወደ ጅማ የሄደ ሰራተኛ የለንም፤ የተፈላጊውን ማንነት አጣራለሁ ብሏል።

“ጋዜጠኛ ነኝ በማለት አጭበርብሯል” የሚል ጥቆማ ከአካባቢው ነዋሪ ከወ/ሮ ታደለች ተመስገን ከደረሰው በኋላ ነው። ጉዳዩም ከካሳ ክፍያ ጋር መያያዙ፣ ከኩባንያዎች ተቀናቃኝነት ጋር የተሳሰረ ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ። ወ/ሮ ታደለች ተመስገን፣ ከሁለት ወራት በፊት ስራ ላይ በአደጋ ህይወቱን ያጣ ሰራተኛ ቤተሰብ ናቸው። የአንድ የአገር ውስጥ ድርጅት ተቀጣሪ የነበረው ሰራተኛ በኢንተርኔት ማስፋፊያ ፕሮጀክት የፋይበር ኦፕቲክስ ዝርጋታ ላይ ነው በአደጋ የሞተው። የሰራተኛው አሟሟት ላይ ጥያቄዎች ተነስተው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ቀጣሪው ድርጅት በበኩሉ፤ ሰራተኛው አስፈላጊ የጥንቃቄ አልባሳትና መሳሪያዎችን ሲጠቀም እንደነበር በፖሊስ ምርመራ መረጋገጡን ገልጿል። ከሟች ቤተሰብ ጋር በመነጋገር ቀጣሪው ድርጅት የመቶ ሺ ብር ካሳ የከፈለ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱን በበላይነት

ፖሊስ ወደ ገፅ 6 ዞሯል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾችን (ዋልያዎቹን) ለመደገፍ ባለፈው ረቡዕ ከባለቤቱ አምለሰት ሙጬ ጋር ወደ ካላባር ናይጄርያ የተጓዘው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን፤ ከጨዋታ መልስ የጀግና አቀባበል ይገባቸዋል አለ፡፡ ከሳምንት በፊት “መሬት ሲመታ” የተሰኘውን ሙዚቃ ቪድዮ ለዋልያዎቹ በመስጠት ለአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው መፅሃፍት ያበረከተው ቴዲ አፍሮ፤ ሙዚቃውን የሰራው አድናቆቱን ለመግለጽና ለማበረታታት እንደሆነ ተናግሯል፡፡ የሙዚቃው ግጥምና ዜማ የቴዲ አፍሮ ፈጠራ ሲሆኑ፣ የሙዚቃ ቪዲዮውን ያዘጋጀችው ባለቤቱ አምለሰት እንደሆነች ይታወቃል፡፡

ቴዲ አፍሮ ከዋሊያዎቹ ጋር ሲገናኝ የሰሞኑ ጉብኝት የመጀመሪያው እንዳልሆነ የገለፁት የድምፃዊው ተወካይ ጌታቸው ማንጉዳይ፤ አምኖ ዋልያዎቹ የቴዲ አፍሮ ተጋባዥ እንግዶች እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡ ብሔራዊው ቡድን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በመጨረሻው ጨዋታ ዋዜማ ቴዲ አፍሮ በጊዮን ሆቴል ባዘጋጀው ኮንሰርት “ብታሸንፉም ባታሸንፉም የክብር እንግዶቼ ናችሁ” ብሎ ዋልያዎቹን ጋብዟቸው ኮንሰርቱን ታድመዋል። በዋሊያዎቹ ስኬት መደነቁንና መመሰጡን ቴዲ አፍሮ ገልፆ፤ ዋልያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተሳተፉበት ወቅት ኮንሰርት እንዳቀረበና ከዛምቢያ ጋር ያደረጉትን የመክፈቻ

ጨዋታ ስታድዬም ገብቶ እንደተመለከተ ይናገራል።ከ5 ወር በፊትም በአውሮፓ የሚኖሩ

ኢትዮጵያውያን ባካሄዱት የባህልና ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ኮንሰርት ሲያቀርብና ከሙዚቃ ከባንዱ ጋር የዋሊያዎችን ማልያ ለብሶ ለስኬታቸው አድናቆቱን አሳይቷል፡፡

የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ በታየበት የስፖርት መድረክ ሁሉ ልዩ ክብርና ኩራት ይሰማኛል ያለው ቴዲ አፍሮ፤ “ዋልያዎቹ በዓለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያንን አንድ በማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል፤ አዲስ ተስፋም ፈጥረዋል። በማንኛውም ውጤት ወደ አገራቸው ሲመለሱ የጀግና አቀባበል ይገባቸዋል ብሏል - ቴዲ አፍሮ

ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ በኮካ ኮላ ኩባንያ ለቀጣዩ የፊፋ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ከሚያሰሩ ይፋዊ ዘፈኖች መካከል የአፍሪካውን ድርሻ እንዲሰራ መመረጡ መመረጡ የሚታወቅ ሲሆን፤ የዘፈኑ ቀረፃ በኬንያ ተከናውኖ ሲሆን በቅርቡ በመላው ዓለም ለአድማጮች እንደሚቀርብ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

በካላባር ከተማ ለሚያደርገው የመልስ ጨዋታ ባለፈው ረቡዕ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻርተር አይሮፕላን ከተጓዙት 215 ኢትዮጵየውያን መካከል፤ 60 ያህሉ የዋልያ ደጋፊዎች ናቸው፡፡ ለአውሮፕላን ትኬት 28ሺ ብር የከፈሉት ደጋፊዎች፣ በናይጄሪያ ቆይታቸው ወደ 40ሺ ብር ገደማ ወጪ እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡

“ዋልያዎቹን ከናይጄሪያ በክብር አንቀበላቸው” - ቴዲ አፍሮ

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 3

ፍፁም ገ/እግዚአብሔር

የሰሞኑ አጀንዳ

ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈተ ሕይወት የተሰማበት አስደንጋጭ ቀን ነበር፡፡ በአድናቂዎቻቸውም በተቺዎቻቸውም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ

ከፍተኛ የሀዘን ድባብ ተፈጥሮ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ አጥብቀው በሚነቅፏቸው ወይም እንደሚጠሏቸው በይፋ በሚናገሩ ዜጐች ዘንድ ሁሉ የተደበላለቀ ስሜት የፈጠረ ክስተት ነበር፡፡

ከሁሉም በላይ የአቶ መለስ የጤና ሁኔታን አስመልክቶ በየጊዜው ትኩስ መረጃ የማግኘት እድል የተነፈገው ህዝብ፣ ድንገት በተነገረው ህልፈታቸው ከመጠን በላይ መረበሹ ወይም በአስደንጋጭ መንፈስ ውስጥ መግባቱ ብዙ ላይገርም ይችል ይሆናል፡፡ ሀገራዊ መልክ ያለው የሚመስለው ቀዝቃዛ የመንፈስ ህብረት ግን ወደለየለት ተስፋ መቁረጥና የእርስበርስ ግጭት ሊያመራ ይችላል እስከሚል አስደንጋጭ ሁኔታ ድረስ፣ ከፍ ያለ ስጋት መፍጠሩን የሚያናፍሱ ዜጐች ነበሩ በማለት፣ ባለፈው ወር ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በዋና ፀሐፊው በኩል በይፋ ሲወቅስም ተሰምቷል፡፡

እንደተባለው አቶ መለስ የዚች ሀገር እጣ ፈንታ ወሣኝ ብቸኛ አሳቢ፣ ተመራማሪ፣ ድህነትን ተረት አድራጊ መሪ፣ የልማታዊ ንድፈ ሃሳብ ቀማሪ፣ በተለይም ለገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የህልውናው

“የአፍሪካ ውድቀት ሁሌም የግለሰቦች አምልኮ ነው”

የአቶ መለስ “ራዕይ” የግለሰብ አምልኮን ማጥፋት አልነበረምን!?

ፈጣሪ ስለመሆናቸው በተለያዩ የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን በየቀኑ እስከ ዶቃ ማሰሪያው ሲሞላ የነበረ ህዝብ፣ የሰውዬውን ህልፈት በድንገት ሲሰማ ባይደነብር፣ ተስፋ ባይቆርጥ ነበረ የሚገርመው፡፡ የህልውናው መሠረት የሆኑት ታላቅ መሪ ለዘላለሙ ሲለዩት፣በአስደንጋጭ የፍርሃት ቆፈን ባይቀፈደድ ነበር የሚደንቀው፡፡ ለሁሉም ሀገራዊ ችግሮቹ ብቸኛ መፍትሔ አፍላቂ የሆኑትን “መተኪያ የሌላቸው” ብልህ ሰው ድንገት ሲያጣቸው፣ መንፈሱ በሀዘን ባይሰበር ነበር የሚያሳዝነው፤ የአብዛኛው ህዝብ የመንፈስ ስብራት እውነተኛ መረጃ ከነበረ፡፡

ሁሉንም ነገር የሆኑትን መሪውን ያጣ አውራ የፖለቲካ ድርጅት ምን ቀርቶት፣ ምን ይዞ ነው ሀገር የሚመራው!? ብለው የሚጠይቁ ጥቂት አስተዋይ ዜጐች እንኳ ሊፈታተነኝ ይችላሉ ብሎ አለመጠርጠሩ ደግሞ፣ ሌላ ግርምት የሚፈጥር የሀገሪቱ መሪር ሀቅ ይመስለኛል፡፡ ቅጥ ያጣ ፕሮፖጋንዳ፣ ቅጥ ያጣ የዘመን መንፈስ ሊፈጥር እንደሚችል አስተውሎቱ ያነሰ ይመስለኛል፡፡ በለብለብ የፕሮፖጋንዳ እውቀት እንዲንሣፈፍ የሚፈለግ ዜጋ፣ በለብለብ ሆይ ሆይታ ሣይታወቅ ዚቅ ሊወርድ ይችላል፤ ያልተፈለገ የመዝቀጥ አደጋ ሊያጋጥመው ይችላል፡፡ የትውልድን ነፃ የማሰብ ፈቃድና አቅም የሚያኮስስ፣ የርዕዮተ ዓለም መሣከር ሁሉ የሚፈጥር ተግባር ነው ማለት ይቻላል፡፡ በትክክለኛ አስተሳሰብ ላይ በጥናት ያልተመሠረተ የፕሮፖጋንዳ ሥራ፣ ውጤቱ ክሽፈት እንደሆነ በብሔር ፖለቲካ ተወጥራ እስከመበተን የደረሰችው የስታሊንን የቀድሞ ሀገር ሶቭየት ህብረትን ብቻ ማስታወስ

ይበቃል፡፡ በሌላ በኩል ኢህአዴግ የአቶ መለስን ሃሳብና

ተግባር ያለመጠን እየለጠጠ፣ሰዋዊ ግብራቸውን ወደ መልአክነት ሲለውጠው፣ “ኢህአዴግ የመላዕክት ስብስብ አይደለም፤ ስህተት አይሰራም ማለት አልችልም” ያሉትን እንኳ ለአፍታ አስታውሶ፣ ከፕሮፓጋንዳው ሊታረም ቀርቶ ሊሽኮረመም አልፈለገም፡፡ ለዚህም ነው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምን ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥትና የኢህአዴግ ወፍራም ባለሥልጣናት ሳይቀሩ፣ በተገኘው አጋጣሚ የአቶ መለስን ራዕይ አስፈፃሚ ስለመሆናቸው በተደጋጋሚ ሲናዘዙና ቃል ሲመዙ የሚታየው፡፡ በርግጥ፣ እንደ አቶ ስብሃት ነጋ ያሉት ነባር የህወሓት ታጋይ፣ “የኢህአዴግ እንጂ፣ የመለስ ራዕይ የሚባል የለም” በማለት የአሠላለፍ ለውጥ የሚያደርጉበት አጋጣሚ እንዳለ መዘንጋት አይቻልም፡፡

አቶ መለስ ለአፍታ ሕይወት ዘርተው እየሆነ ያለውን ቢያዩ ሊበሣጩ ሁሉ እንደሚችሉ የሚመሰክሩላቸው የቅርብ ወዳጆች ያሏቸው መሆኑ ይነገራል፡፡ ባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብም “መለስ የታይታ ነገር አይወድም፤ ለህዝብ ያደረገውን እንዲነገር አይፈልግም፤ ህዝብ እንጂ ግለሰብ ታሪክ አይሰራም የሚል አቋም ያለው…ለህዝብ የተሰዋ ጀግና…” በማለት ግለሰባዊ አምልኮን እንደሚቃወሙ አሥረድተዋል፡፡

የሚገርመው ግን፣ የኢህአዴግም በሉ የመንግሥት ተጠሪዎች ከአቶ መለስ አቋም ጋር እልህ የተጋቡ ይመስል፣ ሁሉንም ድርጅታዊና መንግስታዊ ሥራዎች በአቶ መለስ ስም መጥራት ወይም የእርሳቸው

መታሰቢያ ማድረግ ወይም እርሳቸው አቅድውት እንደነበር መመስከር አልያም የእርሳቸው ራዕይ እንደሆነ ማስነገሩን አሁንም ቀጥለውበታል። እንደተባለው ከአቋማቸው ጋር እልህ ካልተጋቡ በቀር፣ እንዴት በአንደበታቸው እንደተናገሩት፣ በኋላም በመጽሐፍ መልክ እንደታተመ የሚታወቀውን አቋማቸውን ተመልክተው፣ እንደ አቶ ስብሃት ነጋ የፕሮፖጋንዳ ሥልቱን መቀየር ተሣናቸው? ብሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የመንግስትም በሉ የኢህአዴግ ፕሮፖጋንዳን የሚያሠራጩ፣ በአቶ መለስ ስም ምለው የሚያድሩ ካድሬዎች ባይሰሙትም ወይም ባያነቡትም፣ አቶ መለስ ግን፣ “የአፍሪካ ውድቀት ሁሌም የግለሰቦች አምልኮ ነው፡፡ ስሞቻቸውም ሁሌ በመ ፊደል ዘር የሚጀምር ይመስላል፡፡ በዚህ ረገድ ሞቡቱ እና መንግሥቱ ነበሩን፡፡ መለስን ከዚህ ዝርዝር ውስጥ ማስገባት አልፈልግም” ከማለት ያገዳቸው አልነበረም፤ ሊያግዷቸውም አይችሉም፡፡

ለነገሩ አርቆ የሚያስብ የመንግስትም በሉት የድርጅቱ ብልህ ካድሬ ካለ፣ የአፍሪካ ሀገራትን ሁሉ እያጠፋ እንዳለ በማስረጃ አስደግፈው የተቃወሙት “የግለሰብ አምልኮን አሸባሪነት” ለማጥናት ይነቃ ነበረ።

የግለሰቦችን ራዕይ በእውቀትና በእውነት መዝኖ ለሀገር ጥቅም ማዋል የሚሻ የበሰለ የፖለቲካ ተንታኝ ካለ ደግሞ፣ “የአፍሪካ ውድቀት ሁሌም የግለሰቦች አምልኮ ነው” ያሉት ተጠየቂያዊ ሃሳብ፣ “የአቶ መለስ ራዕይ” ብሎ ሊያስተጋባው፣ ሊያስተነትነው ይችል ነበረ፡፡ ለነገሩ አሁንም ጊዜ አለ!

ሳምሶን ጌታቸው ተ.ሥ

አንዳንድ ጊዜ፤ አብረውት ሊኖሩ ግድ የሚል ክፉ ዓመል ያለበትን ተቋም ወይም ግለሰብ ባሕርይውን ተረድቶ መቀበል መቻል ቢያንስ ቢያንስ በየዕለቱ ሲነጫነጩ

ከመኖር ይታደግ ይሆናል፡፡ ነገር ግን፤ የዚያ ክፉ ዓመል ባለቤት ድርጊት ሕይወትን በቀጥታ የሚያጠፋ ሆኖ ሲገኝስ? አመሉ እስኪቃና በትንሹ ተራ እሰጥ-አገባ ውስጥ እየተዘፈቁ መበጣበጥ አይቀሬ ነው፡፡ አብረው አንድ ቤት ውስጥ የታሰሩት ሠው “ክፍሉን አቃጥለዋል” ብሎ ቢነሳ ዝም ማለት አይቻል ነገር!

ባለፈው ማክሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2006 ዓ.ም ከምሽት ሁለት ሠዓት የኢቴቪ ዜና እወጃ ላይ አንድ ለተአማኒነቱና “የሚያውቁ ሠዎችስ ምን ይሉኝ ይሆን?” ብሎ ያልተጨነቀ ዜና ተላልፎ ነበር፡፡

ዜናው በጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ፊት አውራሪነት፣ በአርሲ ዞን ሁለት ወረዳዎች ውስጥ የተፈፀመ የእርሻ ልማት ጀብድን የሚመሰክር ነበር፡፡ ዜናው፤ የአካባቢው ነዋሪዎች መሬትን በማጠንፈፍና በመስመር በመዝራት ከዚህ ቀደም (በሀገራችን ይቅርና በምርታማው የኢቴቪ ማሣ ላይ እንኳ) ከተመዘገቡት ሁሉ እጅግ የላቀና ክብረወሰን የጨበጠ የምርት መጠን እንደሚጠበቅ የሚያትት ነበር፡፡

እንደዘገባውና ጠ/ሚኒስትሩም ደጋግመው ሲናገሩ እንደተደመጠው፤ በዞኗ ሁለት ወረዳዎች ይገኛል ካለ በኋላ፤ የሚጠበቀው የስንዴ ምርት መጠን ግን በሄክታር አንድ መቶ ሃያ ኩንታል ነው የሚል ነበር። ይሄንን የሁለት ሰዓቱን ዜና ብቻዬን ስላዳመጥኩትና ጆሮዬንም ማመን ስላቃተኝ፣ የድጋሚውን ዜና ከምሽቱ አራት ሠዓት ላይ ጠብቄ ከአንድ ሌላ እማኝ የሚሆን ሠው ጋር አብሬ አዳመጥኩት፡፡ ልክ ነው፡፡ በሄክታር አንድ መቶ ሃያ ኩንታል፤ በድጋሚ ስህተቱ ተደገመ፡፡ ወይ የቁጥርን ነገር አለማወቅ!

መቼም ዜናውን፤ የለመድናቸው የኢቴቪ ጋዜጠኞችና አንድን የስንዴ ሰብል ዘለላ የፓፓዬ ዛፍ ለማሳከል የሚጥረው ካሜራቸው ሆነው፤ ዜናውን በምስል ብቻ አግዝፈውት ቢያልፉ ኖሮ እኛም ያው

የኢቴቪ ማሣና ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝእንዳልሰማ ሆነን ማሳለፍ ባልከበደን ነበር፡፡ ችግሩ፤ የሀገሪቱ የመጨረሻው ከፍተኛ ባለሥልጣን በሥፍራው ተገኝተው፤ ይጠበቃል ስለተባለው የምርት መጠን የስህተቱ “አብሳሪ” ሆነው መሣተፋቸው ነው፡፡

ላለፉት አንድና ሁለት ዓመታት ያህል ስንዴ በሄክታር ስልሳ ኩንታል ተገኘ የሚለው ልፈፋ ለሙያው ቅርበት ባላቸው ሠዎች ዘንድ አልዋጥ ማለቱ አስገራሚነቱ ሳያበቃ፤ በሄክታር በአንድ ጊዜ መቶ ሃያ ኩንታል ማምረት ችለናል፤ ወደሚለው መሸጋገሩ ቅዠት ማብዛታችንን ይመሰክርብናል፡፡

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ አማካዩ የስንዴ ምርት መጠን በሄክታር ሰላሳ ኩንታል አካባቢ መሆኑ የሚታወቅ ጉዳይ ነው፡፡ ከፍተኛ የስንዴ አምራች የሚባሉ ሀገራት ምርታቸው በሄክታር ከሃምሳና ስልሳ ኩንታሎች እንደማያልፍ መረጃው በየድረ-ገፁ ቢታሰስ ይገኛል። በተመሣሣይም፤ በኢትዮጵያ እንደ ባሌ ባሉ ለስንዴ ምርት እጅግ ተስማሚ የአየር ንብረትና የቦታ አቀማመጥ ባላቸው ሥፍራዎች እንኳ፤ (ያውም ዘመናዊ የእርሻ መንገዶችን በመጠቀም የሚገኘው) ከፍተኛው አማካይ የምርት መጠን፤ በሄክታር ስልሳ አምስት /35/ ኩንታል አካባቢ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚሁ አካባቢ ያለው የምርት መጠን በገበሬ ማሳ ሲሆን መጠኑ ከጠቀስኩት አነስ ይልና፤ በአማካይ ከሃያ አምስት እስከ ሰላሳ ኩንታል በሄክታር ይሆናል።

ይኼ እውነታ ከጠ/ሚኒስትሩም ሆነ ከአማካሪ ባለሙያዎቻቸው የተሰወረ እንዳልሆነ እሙን ነው። ታዲያ ዋናው ጉዳይ ምንድነው? ጠ/ሚኒስትሩ ማስተላለፍ የፈለጉት ዋና መልዕክትና የዘገባውም ዋና ዓላማ፤ በትንሽ ማሳና በአነስተኛ ገበሬ የእርሻ ምርት ሊያድግ ያዳግተዋል፤ የሚሉ እውቀትን የተንተራሱ ተከራካሪዎችን አፍ ለማስያዝ የታለመ ነበር ዜናው፡፡

ከአንድ ወገን ጋር የተገባውን የ”እንችላለን” “የለም አትችሉም” ክርክር፤ በአፋዊ ሙግት ለመርታት ሲባል ብቻ፤ ፍፁም ከእውነታ ያፈነገጡ ውጤቶችን አስመዝግበናል ማለት… ያውም በሀገር መሪ ደረጃ ከትዝብትም በላይ ያሳዝናል፡፡

ጉዳዩ፤ የሀገሪቱን ሰዎች ከመጉዳቱና ከማሳዘኑ አልፎ፤ ለሌላ ታዛቢም አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ምክንያቱም፤ መቼም አንድ የሀገር መሪ፣ በብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ያውም የመጀመሪያ ዜና ሆኖ ንግግራቸው ሲቀርብ፣ የዓለም ዓቀፍ ሠዎችም ምን ብለው ይሆን ብለው ትርጓሜውን በጉጉት መስማታቸው የማይቀር

ነው፡፡ ታዲያ እንዲህ ያለ ከእውነታና ከሳይንሳዊ መስፈርቶች ያፈነገጠ ንግግር ሲሰሙ… በሌሎች ጉዳዮች ላይ የጠ/ሚኒስትሩ ተአማኒነት መጠራጠራቸው ይቀራል?

ባላንጣን ለማብሸቅ እና ጓዳናችን ሁሉ በስኬት የተሞላ ነው ብሎ ንግግርን ለማሳመር ሲባል ብቻ በሀገራዊ እቅድና ውሳኔዎች ላይ ፍፁም አሉታዊ ተፅዕኖዎችን የሚያመጡ የሀሰት ውጤቶች ተመዘገቡ ማለት ብዙ መዘዝ አለው፡፡ ይኼው በየጊዜው በየወረዳዎች “ከዕቅድ በላይ እየተመረቱ ነው” የሚባለው የምርት መጠን መንግሥት ለሚያከናውናቸው እቅዶችና ውሳኔዎች በታሳቢነት መወሰዳቸው የማይቀር ነው፡፡ ለምሣሌ ትክክለኛው የምርት መጠን ታውቆ ቢሆን ኖሮ፤ ምናልባት፤ ሀገሪቱ ተጨማሪ የስንዴ ምርት በግዢም ሆነ በእርዳታ በወቅቱ ልታስገባ ይቻላት ነበር። ነገር ግን እንደተመረተ የታመነው ወይም እንዲታመን የተወሰነው መጠን ከሀገሪቱ ፍላጎት በላይ ነው የሚል ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ በመቀጠል የስንዴ ምርትን ወደ ውጭ ሀገራት ኤክስፖርት እናደርጋለን ተብሎ ይወሰናል፡፡

ከዚያም፤ በሀገሪቱ ከፍተኛ የምርት እጥረትና የዋጋ ንረት ሲከሰት፤ የተለያዩ ሰበቦች ከመንግሥት ወገን መደመጥ ይጀምራሉ፡፡ ሀብታም ገበሬዎች ምርታቸውን መሸጥ ስላልፈለጉ ወይም ስግብግብ ነጋዴዎች ምርቱን በመጋዘናቸው ስላከማቹ… ወይም ሚሊዬነር ገበሬዎች ስንዴን በተለያየ መልክ መመገብ ስለጀመሩ …. የማያልቅ ንዝንዝ፡፡

ጉዳቱ በዚህ ብቻ አያበቃም፡፡ በሀገራችን በተቋም ደረጃ ብዛትም ጥራትም ያለው የተማረና የሰለጠነ የሠው ሀይል ካላቸው መ/ቤቶች መካከል በግንባር ቀደምትነት ሊጠቀስ በሚችለው ግብርና ምርምር ተቋም ላይም አሉታዊ ተፅዕኖው ሊንፀባረቅ ይችላል። እንዴት? ቢባል፤ በየዓመቱ የአንድና ሁለት ኩንታል ለውጥ /ያውም/ ከተቻለ የምርት ዕድገት ለውጥ ማምጣት እጅግ ትልቅ ስኬት ሆኖ ሳለ፤ በፖለቲካዊ ውሳኔ በብዙ ልፋት የሚደረስበት የምርታማነት መጠን “ከመድረሻው ጣራ በላይ ተደርሷል” መባሉ ተነሳሽነታቸውን ያሽመደምደዋል።

አሁን በገበሬ ማሳ ማግኘት የሚቻለውን ሰላሳ ኩንታል የማይሞላ ምርት፤ (በብዙ ምርምር ጥረት) ሠላሳ አምስት ኩንታል የሚያደርስ ውጤት በአንድ የግብርና ባለሙያ ቢገኝ፣ ምን ብሎ ሪፖርት

ያደርጋል? ምክንያቱም፤ ገበሬው አንድ መቶ ሃያ ኩንታል የሚያመርትበት ደረጃ ቀደም ብሎ (በዜናው አማካኝነት) መድረሱን ሰምቷል፡፡

በዘመናዊ ግብርና ድርጅቶችና በመንግሥት ስር በሚገኙ እንደባሌ ግብርና መሥሪያ ቤቶች እንኳ ተመርቶ የማያውቅ ምርት (ለገበሬ ማሳ ያውም እርሻውም - ውቅያውም በበሬ፣ ምርት ስብሰባው በማጭድ፣ የግብዓት መጠኑ በበቂ ሳይሟላ!) የዓለምን የጊነስ ክብረወሰን የሚወዳደር ምርት አምርተናል ማለት፤ ጉዳዩን ለሚያውቅ ሠው ጥፋ ጥፋ የሚል ስሜት ያጭርበታል፡፡ በአመራረት የተሻለ ደረጃ የደረሱ ሀገራትን ተሞክሮ ወደ ሀገር ቤት አምጥቶ ለማስፋፋት ከመጣጣር ይልቅ የመጨረሻ ኋላ ቀር የአስተራረስ ዘዴን ይዞ መድረሻውን አልፈነዋል ማለት ምን ይሉት ፈሊጥ ይሆን?!

በብዙ ሚሊዮን ብር ከውጭ ሀገራት የእርሻ መሣሪያዎችን እያስመጣ ዘመናዊ የእርሻ ድርጅቶችን የሚመራ ባለሀብት፣ እንዲህ በቀላሉ በበሬ እርሻ ከሶስትና ከአራት እጥፍ በላይ ምርት ተመርቶ ከተበለጠ ልፋቱ ሁሉ ከንቱ ነበር ማለት ነው፡፡

በየዓመቱ ምርትን አሳደግሁኝ በማለት ሥልጣንን ለማዳበርና የበላይ አለቃን ይሁንታ ለማግኘት ከየወረዳዎቹ የሚቀርቡ “የአድገናል - አምርተናል” የቁጥር ጨዋታዎች፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ቁጥር የማያውቁ ሕዝቦች እስክንመስል ድረስ በድፍረት እየተለፈፈ ይገኛል፡፡

የቀድሞ ምክትል ጠ/ሚኒስትርና ግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስትር አቶ አዲሱ ለገሠ፤ ወደሥልጣን ማብቅያቸው ሰሞን… አንድ ያስተላለፉት ትዕዛዝ በዚሁ ጋዜጣ ተፅፎ ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡ ጉዳዩ ምን መሰላችሁ? በወቅቱ ከተለያዩ ወረዳዎች የቀረበላቸውን “ምርት በምርት ሆነናል” የሚል ሪፖርት ካዳመጡ በኋላ፤ በጣም ተቆጥተው አንዳንዶቹ ከፍተኛ መጋነን እንዳለባቸው ስለታወቃቸው ተስተካክለው ይመለሱ ማለታቸውን አንብቤአለሁ፡፡

ባልተለመደ መልኩ የተደመጠው የሚኒስትሩ ተግሳፅ አስገርሞኝም አስደምሞኝም ነበር፡፡ ምን ዋጋ አለው… የገፋበት የለም እንጂ?! ምንአልባት አቶ አዲሱ፤ ድርጅታቸው ከያዘው የ“አጋኖ አምርተናል” አባዜ በማፈንገጣቸው ሂሳቸውን ውጠው ይሆናል። ማን ያውቃል?!

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 4

ታኅሣሥ 29 ቀን 1992 ዓ.ም ተመሰረተዘወትር ቅዳሜ የሚታተም ሳምንታዊ ጋዜጣ

አሣታሚ አድማስ አድቨርታይዚንግ ኃ.የተ.የግ.ማ.

አታሚ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

አራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 17 / የቤት ቁ.984

አድራሻ:- ካዛንችስ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር ገባ ብሎ ከጤና ጣቢያው ጀርባ ቂርቆስ ክ/ከ ቀበሌ 31 የቤት ቁ.376

ስልክ 0115-155-222/ 0115-153-660 ሞባይል 0921-622-040/0911-201-357 ፋክስ 0115-547373 ፖ.ሳ.ቁ 12324

E-mail :- [email protected]/[email protected]/ website www.addisadmassnews.com

ሥራ አስኪያጅ:- ገነት ጎሳዬ (ልደታ ክ/ከ ቀበሌ 04/06 የቤ.ቁ.581) ስልክ 0911-936787

ዋና አዘጋጅ:- ነቢይ መኮንን (ቂ/ክ/ከ ቀበሌ 08/09 የቤት.ቁ.213)ም/ዋና አዘጋጅ:- ኢዮብ ካሣ

ከፍተኛ አዘጋጅ:- ሰለሞን ገ/እግዚአብሔር አዘጋጅ:- ኤልሳቤት ዕቁባይ

ከፍተኛ ሪፖርተሮች:- መንግስቱ አበበ፣ ግሩም ሠይፉ፣ አበባየሁ ገበያው፣ መልካሙ ተክሌ፣ መታሰቢያ ካሳዬ፣ ሰላም ገረመው፣ ናፍቆት ዩሴፍ፣ አለማየሁ አንበሴሌይ አውት ዲዛይነር:- ኮክ አሰፋ፣ ንግሥት ብርሃነ አርቲስት:- ሠርፀድንግል ጣሰው፣ ሽያጭና ስርጭት:- ሰለሞን ካሣ፣ ፎቶግራፈር:- አንተነህ አክሊሉ ዌብፔጅ:- አሰቴር ጎሳዬ፣ ኮምፒውተር ጽሑፍ:- የወብዳር ካሣ

`°e ›”kî ለውጥ ከገፅ 5 የዞረቀበሌ የለም፡፡ እንዲሁም ፓርቲው የእያንዳንዱ ብሔር ጥንቅር ውጤት ነው፡፡

ምናልባት የብሔር ተዋጽኦው ሲነሣ እርስዎ ከሚሉት በተቃራኒ የአማራው ሚና የሚጐላበት እንዲያም ሲል አመራሩ እና ማዕከላዊ ኮሚቴው ለሰሜን ሸዋ አካባቢ ተወላጆች ብቻ የተሰጠ ነው የሚል ወቀሳ ይቀርብበታል…

እዚህ ላይ አሁን የመኢአድን አመራር ጥንቅር ያየህ እንደሆነ ከአማራው፣ ከጐፋው፣ ከወላይታው ያለበት ነው፡፡ ለምሣሌ የፓርቲውን ምክትል ተቀዳሚ ሊቀመንበር ብንወስድ ከጐፋ ነው፣ የመኢአድን የስራ አስፈፃሚ ብትወስድ ኦሮሞች አሉ፤ ለምሣሌ ብሩ ደሲሣ ከአሶሳ አለ፣ ገለቱ ኤጀርሣም አለ፡፡ ስለዚህ ይሄ የጠላት ወሬ ነው። መኢአድን ለማዳከም የሚነዛ አሉባልታ ነው። አማራው ከሌላው ብሔር የበለጠ በዚህ ፓርቲ ውስጥ ተሳትፎ የለውም፡፡ ለምሣሌ የአባላት ጥንቅርን የወሰድን እንደሆን በሰሜን ካለው አባል የበለጠ በደቡብ ነው ያለው፡፡ ከ39 በመቶ በላይ በደቡብ አካባቢ ያሉ ናቸው፡፡ ከሰሜን ሸዋ የመጡ ናቸው የሚባለው የሰሜን ሸዋ ህዝብ ወይም በዚያ የሚገኝ የአማራ ተወላጅ እንዳጋጣሚ ሆኖ አማራው ይገደል በነበረ ጊዜ ፕ/ር አስራት ፓርቲውን ይመሩ ነበር፡፡ ይህ ማለት ግን አመራሩ በጠቅላላ ከሰሜን ሸዋ ነበረ ለማለት አይቻልም። እሣቸው እንደ ፕሬዚዳንት ከሰሜን ሸዋ ይሁኑ እንጂ ከተለያዩ የአማራ ክፍሎች የተውጣጣ የስራ አስፈፃሚ መዋቅር ነበር፡፡ ፕ/ር አስራት፤ የመላው አማራ ህዝብ ድርጅትን ሲያቋቁሙ የአማራው ወይም የአንድ ብሔር ፓርቲ አድርገው ለማቋቋም አልነበረም ፍላጐታቸው፤ ነገር ግን ይገደልና ይሰደድ የነበረውን አማራ ከጥቃቱ ለመከላከል ያህል ያቋቋሙት ነው፡፡ በወቅቱ ለጊዜው አማራው ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እንከላከልና ኋላ ላይ ህብረ ብሔራዊ ሆኖ ሁሉንም ብሔሮች አሣትፎ ይቀጥል የሚል መርህ ነበራቸው፡፡ በዚህ መርህ አሁን ካለበት ደረጃ ደርሷል፡፡ አማራው በዚህ ውስጥ በምንም ሁኔታ የበላይነት የለውም፤ ይሄ የጠላት ወሬ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ከመድረክ ጋር አብረን አንሰራም ብላችሁ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ 10 ፓርቲዎች ያሉበት ቅንጅት በመኢአድ ጉልህ ሚና እየተፈጠረ ነው ያለው፡፡ ከዚህ ፓርቲዎች አብዛኞቹ የጐሳ ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ከመድረክ ጋር አብሮ አያስጉዘንም ያላችሁበት አጀንዳን ወደ ጐን ትታችሁ አሁን እንዴት ከነዚህ ፓርቲዎች ጋር ለመቀናጀት መረጣችሁ?

ትክክል ነው እነዚህ ድርጅቶች የጐሳ ናቸው። ኢህአዴግ ኢትዮጵያን በጐሳ ሲሸነሽን እነዚህ ፓርቲዎች በጐሳቸው… ተደራጅተው ነው፤ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ፓርቲዎቹ የጐሣ ቢሆኑም በኢትዮጵያ ጥላ ስር ሆነን እንታገላለን ያሉ ናቸው። ስለዚህ ፓርቲዎቹ በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር መሆንን የሚሹ ናቸው፡፡ የጐሣ/ብሔር/ ፖለቲካ እንደማያዋጣ አምናለሁ፤ በኢትዮጵያ ጥላ ስር ሆነን ከመኢአድ ጋር እንታገላለን ስላሉ ነው የተቀበልነው፡፡ እንግዲህ የነበሩት 33 ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ከ33ቱ አብዛኞቹ በጐሣችን ብቻ ነው የምንታገለው ስላሉ አማራጫቸውን ይዘው ሄደዋል፡፡ በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ሆነን እንታገላለን ያሉት መኢአድ እንዲያታግላቸው ወደዚህ መጥተዋል፡፡ እዚህ ላይ ግልጽ መሆን ያለበት ከመጡት ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑት የብሔር /ጐሣ/ ድርጅቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ለውጥ ወደ ገፅ 26 ዞሯል

ህብረ ብሔራዊ ናቸው፡፡ ከመድረክ ስብስብ ጋር ያላችሁ መሠረታዊ ቅራኔ

ምንድን ነው? ከስብስቡ ውስጥ በኢትዮጵያዊነት አያምኑም ብላችሁ የምትጠቅሷቸው ፓርቲዎች አሉ እንዴ?

በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ካለማመን ባሻገርም በአንዳንድ ፖሊሲያችንም እኮ እንለያያለን፡፡ ለምሣሌ በመሬት ጉዳይ፤ መኢአድ መሬት የህዝብ ነው፤ መንግስት ሊያዝበት አይችልም ብሎ ነው የሚያምነው፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጥሪት ሊኖረው ይገባል ብሎ ያምናል፡፡ ዜጐች መሬት ተከራይተው ሊኖሩ አይገባም፤ ይሄ የመኢአድ ፖሊሲ ነው፡፡ ነገር ግን የሌሎቹ የመድረክ አባላት ፕሮግራም በዚህ አያምንም፤ የኢህአዴግን ነው ይዘው የሚሄዱት፤ በነገራችን ላይ አንዳንዶቹ ኢህአዴግ ዲሞክራሲያዊ ስላልሆነ ነው እንጂ በፖሊሲ ደረጃ አንለይም ባይ ናቸው፡፡

መድረክ ውስጥ እንደዚያ የሚሉ ድርጅቶች አሉ?

አዎ! በሚገባ የአስሩን ፓርቲዎች ፖሊሲና ፕሮግራም

ካስቀመጡልን ነጥቦች አንፃር በሚገባ መርምራችኋል ማለት ነው?

መቶ በመቶ በሚገባ አጥርተን መርምረናል፣ ፕሮግራማቸውን አንብበን እና ተናበን ነው ይሄን ያደረግነው፡፡

በ1997 ስለተፈጠረው ቅንጅት አመሰራረትና ውድቀት ብዙ ተብሏል፡፡ የአሁኑን ቅንጅት ከፈረሰው ቅንጅት ምንድን ነው የሚለየው?

ቅንጅት ስንል ያው ቅንጅት ነው፡፡ አይለያይም። እያንዳንዱ ፓርቲ የራሱን ህልውና ጠብቆ ነገር ግን የሚመጣው ችግርና አደጋ በአንድ ላይ እንታገላለን ብሎ የሚያምን ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ላይ ተጨፍልቆ አንድ እንደመሆን አይታሰብም፡፡ በ1997ም እያንዳንዱ ፓርቲ በዚህ አይነት ሁኔታ ራሱን የቻለ ነበር፡፡

ግን በአንድ ፕሮግራምና በአንድ የመወዳደሪያ ምልክት ነበር ለምርጫው የቀረበው…

ይሄም ልዩነት አይኖረውም፤ እንደዚያው ነው። ነገር ግን የአሁኑ በየክልሉ ያሉት ፓርቲዎች ቢሮ ካላቸው እንደ ግንኙነት መድረክነት ያገለግላል፤ በየክልሉ በቀላሉ ተደራሽ መሆን ይቻላል፡፡ ከዚያ በተረፈ ከ97 ዓ.ም ቅንጅት ልዩነት የለውም፡፡

ወደ አንድነት ድርድሩ እንመለስና የ97 ቅንጅት ሲፈርስ መኢአድ ህልውናውን ጠብቆ ሲጓዝ “አንድነት” ደግሞ የመኢአድ አባላት የነበሩትን ጨምሮ በቅንጅቱ መፍረስ ቁጭት ባደረባቸው ፖለቲከኞች የተቋቋመ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ያን ጊዜ በአንድነት መጓዝ ያልቻላችሁ አካላት ዛሬ ምን ታይቷችሁ ነው አንድ ካልሆንን እያላችሁ ያለው?

መቼም አንድ ላይ ስትሠራ ትጋጫለህ ትኮራረፋለህ፣ የሃሣብ ልዩነት ይፈጠራል። እያንዳንዱ አመራር ልዩነት ይኖረዋል፡፡ ይሄ እንግዲህ ያለ ነው፡፡ ችግራችን ምንድነው ልዩነት ሲመጣ የግለሰቦች ፀብ ነው ነጥሮ የወጣው፤ ነገር ግን ይሄ መሆን የለበትም፡፡ ግለሰቡን ሣይሆን ከተቃወምንም ሃሳቡን ነው መቃወም ያለብን። ኢትዮጵያውያን የሚጐደለን ይሄ ይመስለኛል። ስለዚህ እንዳልከው አንድነትን የመሠረቱት ብዙዎቹ

በዱሮ ጊዜ በአንድ መንደር አራት ክፉ ክፉ አለቆች ይኖሩ ነበር ይባላል፡፡ እነዚህም፤ አቶ ዓለም፣ አቶ ደመና፣ አቶ ሰማይ ነህ እና አቶ በላይ ይባላሉ፡፡

አቶ ዓለም ለምጣም ሲሆን ሰውን ከሥራ ማባረር የሚወድ ቂመኛና ክፉ ሰው ነው፡፡ በማርፈድ ከሥራ ያስወጣል፡፡ ቆማችሁ ስታወሩ አገኘኋችሁ ብሎ ከሥራ ያስወጣል፡፡ ስጠራችሁ ቶሎ አልመጣችሁም ብሎ ከሥራ ያባርራል፡፡

አቶ ዓለም ደግሞ ከባላገር መጥቶ የሠለጠነ፣ ከሁሉ የምበልጥ ነኝ ባይ፣ ትኩስ ዘናጭ ነው፡፡ ሆኖም ሌላው የለበሰው ማናቸውም ልብስ ያስቀናዋል። በዚህ ምክንያት ደህና የለበሰ ሰው ላይ መጮህ ነው፡፡ ሰበብ እየፈለገ መደንፋት ነው!

አቶ ሰማይ ነህ ደግሞ የሁሉ አለቃ ነኝ ባይ ነው፡፡ ዋና ሥራው መጠራጠር ነው፡፡ ምንም ነገር ይስማ “ይቺማ ነገር አላት” ይላል፡፡ አንድ ሰው ለጨዋታ ብሎ ቀና ነገር ሲነግረውም፤ “ከጀርባው ምን አለው? ምን ቢያስብ ነው?” ይላል፡፡

የመጨረሻው አቶ በላይ ነው፡፡ በላይ እንደስሙ የበላይ ነው፡፡ የመሥሪያ ቤቱ የመጨረሻ ጣሪያ እሱ ነው፡፡ ግን መሀይም ነው! የተማረ ሲያይ ደሙ ይፈላል፡፡ “ወረቀት አደለም! ወረቀት አደለም! ዋናው ሥራ ነው! እዚህ ወረቀት እያንጋጋችሁ አትጐለቱ!” ይላል፤ ጠዋት ገና ሥራ ሲገባ!

እነዚህን ሰዎች በቅጡ የሚያውቅ ባለቅኔ እንዲህ ሲል ገጠመ ይባላል “ዓለም ቡራቡሬ፣ ሁሉን ሰው አታላይ ደመናውን አልፎ፣ አለ ጥቁር ሰማይ የተማረው ከሥር፣ ያልተማረው በላይ”

* * *የሀገራችን ቢሮክራሲ በመልካም ሰዎች ሳይሞላ መልካም አስተዳደር

ማምጣት አዳጋች ነው፡፡ ከመግዛት ባህሪያችን፤ ከአለቅነት ባህሪያችን በፊት ሰው የሚያደርግ ልዩና መልካም ባህሪ ሊኖረን ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ ከቤተሰብ ጀምሮ ከተኮተኮትንበት ግብረገብነት እስከ ትምህርት ወግ -ማዕረግ ድረስ የሠለጠነ አዕምሮና የበሰለ የህይወት ልምድ ውስጣችን መገንባት ይኖርበታል። ከዚያ፤ በሥራ ዓለም የምናገኘው የዕለት ተዕለት ልምድ፣ ከየሰዉ ጋር ያለንን መስተጋብር (Interaction)፣ ትዕግሥትና ሆደ - ሰፊነት፣ ትህትናና ክህሎት፤ ብሎም የአመራር ብቃት እየሠረፀብን ይመጣል፡፡

በዚህ ላይ ነው እንግዲህ ቅጥ ያለው የፖለቲካ አመለካከት ሲጨመርበት፣ በግድ እኔ ያመንኩትን እመን፣ ያን ካላረክ ጠላቴ ነህ፤ የሚል ሰው አንሆንም፤ የምንለው፡፡ ያመንከውን አምነህ፣ ተቻችለን አንድ መሥሪያ ቤት መኖር አያቅተንም ብለን ማሰብ፤ ጤናማና ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ነው። ከማቃቃር ይልቅ ያቀራርበናል፡፡ ከማራራቅ ይልቅ ያስተቃቅፈናል፡፡ ከመጠፋፋት ይልቅ ያስተራርመናል፡፡

በእስተዛሬው የፖለቲካና የማህበራዊ ጉዞአችን ወይ “ብቆጣም እመታሻለሁ፣ ብትቆጪም እመታሻለሁ” ማለት፤ አለበለዚያ ደግሞ “አሸናፊ ነኝ ያለኔ አታውራ”፤ “ተሸናፊ ነህ ስላንተ እንዳይወራ!” እንዳንል ያደርገናል፡፡

መልካም የስፖርት ድጋፍ ባህል መዳበር አለበት፡፡ በስንት ዘመን ዛሬ ያጋጠመንን ዕድል ተመስገን እንበል፡፡ ተጨዋቾቻችን በምንም መመዘኛ ዛሬ የደረሱበት ደረጃ የሚመሰገን ነው፡፡ አንድ ከተመልካቾቻችን የሚጠበቅ ባህል አለ ዘላቂነት የሙሉ ጊዜ ድጋፍ የመስጠት ልምድ! ይሄ በአንድ ቀን ሊሆን የሚችል ባህሪ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ ሆኖም በልቦናችን ይደር ብናሸንፍ ወይም ብንመራ ቴሌቪዢናችንን የበለጠ እንደማንከፍተው ሁሉ፤ ብንሸነፍ ቴሌቪዥናችንን አንዘጋውም፡፡

ከአንድ የጭብጨባና የጩኸት ድጋፍ ድምጽ በአንድ ጊዜ ወደሚደብት የድብርት ድባብ አንግባ፡፡ በየትኛውም ማህበራዊ መስክ፣ ፖለቲካችንን ጨምሮ፤ የሞቅ ሞቅና የለብለብ አካሄድ ደግ አደለም፡፡ ዘላቂ እንሁን በአቋማችን እንግፋ፡፡

አለበለዚየ “ያደሩበት ጭቃ፣ ከጭድ ይሞቃል” ዓይነት ይሆንብናልና በአዎንታዊ ጉዟችን እንግፋ ማናቸውም ውጤት የነገ መንገዳችን መትጊየ ነው፡፡ ፈረንጆች፤ “all that had gone before was a preparation to this; And this is a preparation to this” ይላሉ፡፡ “እስካሁን ያለፍንበት ሁሉ እዚህ ለመድረስ ነበር፡፡ ይሄ ደሞ ለነገ መዘጋጃችን ነው” እንደማለት ነው፡፡

ድል ለዋሊያዎቻችን!

ያደሩበት ጭቃ ከጭድ ይሞቃል

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 5

ፎቶ

አንተ

ነህ አ

ክሊሉ

አቶ አበባው መሃሪ

’í ›e}Á¾ƒ

ለውጥ ወደ ገፅ 4 ዞሯል

ከ“አንድነት” ፓርቲ ጋር ውህደት ለመፈፀም የጀመራችሁት ውይይት ምን ላይ ደረሰ? ውህደቱንስ በዚህን ወቅት መፈፀሙ ለምን አስፈለገ?

ህዝባችንን ካለበት ችግርና የሰብአዊ መብት ጥሰት ነፃ ለማውጣት የጋራ አላማ ያላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአንድ ላይ መስራት ወሣኝነት አለው ብለን እናምናለን፡፡ ተለያይቶ ድምጽ ከመሻማት ይልቅ አንድ ላይ ሆኖ ሃብትንም ሆነ ሌላ ሌላውን አቀናጅቶ መንቀሳቀስ ጠቃሚ ነው፡፡ በህዝቡም ላይ በራስ መተማመንን ፈጥሮ ሃይል ያለው “ሊመራኝ የሚችል ፓርቲ አለኝ” ብሎ እንዲያምን አንድ መሆን ወሳኝ ነው ብለን እናምናለን፡፡ እኔ አሁን ባለው ደረጃ ማለት የምችለው፣ አንድነትና መኢአድ ለመዋሃድ ድርድር እያደረጉ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን መግለጫ ለመስጠት ያስቸግረኛል፡፡ ምክንያቱም ሂደቱ በራሱ ኮሚቴ የሚመራ ነው፡፡ ኮሚቴው ማንም ሰው በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ መስጠት አይችልም የሚል ፕሮቶኮል ፈርሟል፡፡ የየፓርቲዎቹ ባለስልጣናትም ሆኑ ተደራዳሪዎች መግለጫ መስጠት አይችሉም፡፡

ከአንድነት ጋር ውይይት ጀምረናል ብላችኋል፣ አንድነት ደግሞ የመድረክ ግንባር አባል ነው፣ እናንተ ደግሞ መድረክን እንደማትፈልጉት በተደጋጋሚ ገልፃችኋል፡፡ ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል?

መኢአድ በኢትዮጵያ አንድነት ጥላ ስር ለመሄድ ከማይፈልጉ ፓርቲዎች ጋር በጋራ ለመንቀሳቀስ ይቸገራል፡፡ የመኢአድ አወቃቀሩም ሆነ አላማው ሁሉም ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ጥላ ስር መንቀሳቀስ አለባቸው የሚል ነው፡፡ በጐሣም ተደራጅተው በኢትዮጵያ ጥላ ስር ሆነን “አንዲት ሉአላዊት ኢትዮጵያ” በሚለው ስር አብረን እንሄዳለን ካሉ አብሮ ለመስራት ችግር የለውም፡፡

ስለዚህ አንድነት በመድረክ ስር ሆኖ እንዴት ይሆናል የሚለው የራሱ የአንድነት ጉዳይ ነው፤

“የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ ፈልጓል፤ ግን ለውጡን የሚሸከምለት ፓርቲ ይፈልጋል”

• ከ“መድረክ” ጋር ያለው ጥያቄ “አንድነት” ሊፈታው የሚገባው ነው

• ፓርቲያችን ግራ የተጋባ አይደለም

• መኢአድ በሀገሪቱ ካሉ ፓርቲዎች ጠንካራው ነው

• ህዝቡ እውነተኛውንና ውሸታሙን መለየት አለበት

የመኢአድ ጉዳይ አይደለም፡፡ መኢአድ እና አንድነት እየተደራደሩ ነው፤ ሁለቱም ተመሳሳይ ፕሮግራም፣ አላማ፣ ደንብ ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ከመድረክ ጋር ያለውን ጥያቄ አንድነት ሊፈታው የሚገባው ጥያቄ ነው እንጂ የመኢአድ አይደለም፡፡ ይሄ የድርድሩም አካል ነው፡፡

ውህደቱን ስትፈጽሙ አመራሩስ እንዴት ነው የሚደራጀው?

እንግዲህ እንደነገርኩህ በዚህ ላይ መግለጫ ለመስጠት ያስቸግረኛል፡፡ ተደራዳሪዎች ስላሉ ይሄ ነው ብሎ ለማለት ፕሮቶኮሉ ያስረኛል፤ ነገር ግን ውህደት ከተካሄደ ውህደት የሚፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ ይፈፀማሉ ማለት ነው፡፡ ለዚህ ካለአመራሩ ይሄ ይሆናል ማለት አልችልም፡፡

መኢአድ ከሌሎች ፓርቲዎች የሚለየው በምንድነው?

ፓርቲያችን ተመሳሳይ ደንብ እና አላማ ካላቸው ፓርቲዎች የሚለይበት አንደኛ፣ ህብረ ብሔራዊ መሆኑ ነው፡፡ የመኢአድ እምነት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ፣ ጥላ ስር ሆኖ የእያንዳንዱ ዜጋ መብት ሲከበር፣ የሁሉም ዜጋ መብት ይከበራል ብሎ ያምናል እንጂ የአንድ ጐሣ መብት ሲከበር የጐሣው አባላት መብት ይከበራል ብሎ አያምንም። አሁን ለምሣሌ ገዢው ፓርቲ ውስጥ ያለው የብአዴን መብት ሲከበር፣ የእያንዳንዱ አማራ መብት ተከበረ ማለት አይደለም፡፡ የኦህዴድም በተመሳሳይ፤ ሌላው መኢአድ የሚመራው በሊበራል ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ነው፤ ይሄ ከሌላው የሚለየን ይመስለኛል። ሌላው የምንለይበት ፓርቲያችን ግዙፍ የሆነ አደረጃጀት ያለው ነው፡፡ በመላው ሃገሪቱ በሚገኘው እያንዳንዱ ቀበሌ መኢአድ አለ፡፡

በአራቱም ማዕዘናት ቢኬድ መኢአድ የሌለበት

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በቅርቡ ከአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ጋር ውህደት፣ ከሌሎች 10 ፓርቲዎች ጋር ቅንጅት

ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ፓርቲው ከረጅም አመታት በኋላ የፕሬዚዳንት ለውጥም አድርጓል፡፡

ከአዲሱ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ ጋር ፓርቲው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር እየፈጠረ ስላለው ውህደት እና ቅንጅት እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የአዲስ አድማስ

ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፤ በፓርቲው ጽ/ቤት ተገኝቶ አነጋግሯቸዋል፡፡

በማኔጅመንቱና በቦርዱ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ጃካራንዳ አክሲዮን ማህበር

ናፍቆት ዮሴፍ

መጋቢት 20 ቀን 2001 ዓ.ም በ950ሺ ብር ካፒታል ሥራ የጀመረው “ጃካራንዳ ኢንተግሬትድ አግሮ

ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር” የስራ አመራር ቦርድና ማኔጅመንቱ በውዝግብ ላይ ሲሆኑ ከሁለቱም ወገኖች የተለያዩ ቅሬታዎችና አስተያየቶች እየተደመጡ ነው፡፡

በመጀመሪያ የተነሳው ቅሬታ ከማህበሩ መስራችና ስራ አስኪያጅ ከነበሩት አቶ ደመላሽ ወጋየሁና ከሌሎች ሰዎችም ጭምር ሲሆን የስራ አመራር ቦርዱ በአመት ከተፈቀደለት 97ሺህ ብር በላይ በመጠቀምና ወደ 131 ሺህ ብር ከፍ በማድረግ ማህበሩን ለኪሳራ እየዳረጉ ስለመሆኑ፣ የቦርዱ ፀሐፊ አቶ ሙሉ ሸዋ ከስርዓትና ከደንብ ውጭ በየወሩ አምስት መቶ ብር ሊከፈለኝ ይገባል በሚል በፃፉት ደብዳቤ የ19 ወር 9500 ብር ያለ አላግባብ የተከፈላቸው ስለመሆኑ፣ አሁን እየሰራ ያለው ቦርድ መጋቢት 2 ቀን 2004 በተጠራ አስቸኳይ ስብሰባ ጊዜያዊ ቦርድ ሆኖ መመረጡንና ጥቅምት 9 ቀን 2005 ዓ.ም መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ጃካራንዳ ወደ ገፅ 25 ዞሯል

ስልጣኑን ማፀደቅ ሲገባው አለማፅደቁን፣ በየአመቱ ጠቅላላ ጉባኤ መጥራት ሲገባው እስካሁን ስብሰባው አለመጠራቱን፣ ባለአክሲዮኖች የሚያውቁትንና የሚገናኙበትን ሁለት የስልክ መስመሮች ቀይረው በአዲስ ስለተኩት ባለአክሲዮኖች ግንኙነት መፍጠር አለመቻላቸውን፣ ቦርዱ የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ አላዘጋጀም፣ የ2006 አመት በጀትም የለውም፣ ቦርድ ሲመረጥ በንግድ ህግ ቁጥር 349 መሰረት በስራ ዘመኑ ላጠፋቸው ጥፋቶች ዋስትና ማስያዝ ቢኖርበትም በስራ ላይ ያለው ቦርድ ምንም አይነት ዋስትና አለማስያዙን፣ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተው ሳያስታውቁና ንግድ ሚኒስቴር ሳያውቅ ቢሮ መቀየራቸውንና መሰል ችግሮች በቦርዱ እየተከሰተ ስለመሆኑ አንዳንድ ባለአክሲዮኖችና መስራቹ አቶ ደምመላሽ ወጋየሁ ይናገራሉ፡፡

ይህንን በተመለከተም ለፀረ - ሙስና ኮሚሽን፣ ለገቢዎችና ጉምሩክ የህግ ማስከበር ዘርፍ ጽ/ቤት፣ ንግድ ሚኒስቴር የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክቶሬትና ለሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ ማሳወቃቸውን ይናገራሉ፡፡

“ከ2500 በላይ ባለድርሻዎች ያሉትን ጃካራንዳ፤ ማህበርን በማመን አካል ጉዳተኞች፣ አቅመ ደካሞችና ዕድሮች ሳይቀሩ አክሲዮን ገዝተዋል ግን ብሩ በህገ - ወጦች እየተመዘበረ ነው ይህን በማጋለጤና ለምን በማለቴ ከስራና ከደሞዝ አግደውኛል” ይላሉ አቶ ደምመላሽ፡፡

ግለሰቡ አክለውም አክሲዮን ማህበሩ ስራውን በማስፋፋት፣ በምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮ ቲቤ ወረዳ፣ በ300 ሄክታር መሬት ላይ የእርሻ ስራ ልማት የጀመረ “ዩ ኤፍ ቢ ፋርም” የተባለ ድርጅት ለጃካራንዳ በሽያጭ ለማስተላለፍ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት፤ 2.5 ሚሊዮን ብር ያለ ደረሰኝ ከፈፀመ በኋላ ቀሪውን ግማሽ ሚሊዮን ብር ህጋዊ ደረሰኝ ሲያቀርቡ ለመክፈል ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ የድርጅቱ ባለቤቶች ለተከፈላቸው 2.5 ሚሊዮን ብር ህጋዊ ደረሰኝ እንዲያመጡና ቀሪውን ግማሽ ሚሊዮን ብር እንዲወስዱ በቃልም በጽሑፍም ቢጠየቁም “ድርጅታችንን ዘግተናል፤ የምን ደረሰኝ ነው የምትጠይቁን” በሚል ማስቸገራቸውን የገለፁት አቶ ደመላሽ፤ ወደፊት እንዲከፈላቸው የተሰጣቸው ቼክ እንዲታደግ ማድረጋቸውን ጠቁመው አሁን በስራ ላይ ያለው ቦርድ ይህ ጉዳይ በሂደት ላይ መሆኑን እያወቀ እና ሪፖርት ተደርጐለት እያለ ከግለሰቦቹ ጋር በመመሳጠር እንዲሁም የመንግስትን ገቢና የድርጅቱን ጥቅም ለማሳጣት ቀሪ ገንዘባቸው እንዲከፈል ትዕዛዝ ለማኔጅመንቱ መስጠቱንና በዚህም አቶ ደመላሽ በግላቸው ቅራኔ ውስጥ መግባታቸውን ለኢፌድሪ ገቢዎችና ጉምሩክ የህግ ማስከበር ጽ/ቤት ለኢፌድሪ ፀረ ሙስና ኮሚሽን እና ለኢፌድሪ ንግድ ሚኒስቴር የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት በፃፉት ደብዳቤ አሳውቀዋል። “ለተከፈላቸው ክፍያ ህጋዊ ደረሰኝ ሳያቀርቡ ለምን

ቀሪ ክፍያ ይፈፀማል በሚል ቅሬታ በማሰማቴ ቦርዱ በህግ ለመጠየቅ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጽፎልኛል” ያሉት አቶ ደመላሽ ነገር ግን ቦርዱ ለግለሰቦቹ ተባባሪ በመሆን እርሳቸውን ከስራና ከደሞዝ በማገድ ያለምንም ደረሰኝ 50ሺህ ብር የከፈላቸው መሆኑንና ይህም በህዝብ ንብረት ላይ መቀለድ መሆኑን በመግለጽ መቃወማቸውን ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የፃፉት ደብዳቤ ያሳያል። ይህን ጉዳይ የተመለከተው በንግድ ሚኒስቴር የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት ጥቅምት 21 ቀን 2006 ዓ.ም ለጃካራንዳ ኢንተግሬትድ አግሮ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር የስራ አመራር ቦርድ ሊቀመንበር “የአክሲዮን ማህበሩን አጠቃላይ አሰራር ዝርዝር የሚያሳዩ መግለጫዎች እንዲቀርቡ ስለመጠየቅ” በሚል ርዕስ ደብዳቤ የፃፈ ሲሆን፤ ጃካራንዳ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያገኙ ዘንድ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አክሲዮን በመግዛት ያቋቋሙት ማህበር ሲሆን ማህበሩ ለአባላት ጥቅም ከማስገኘት ይልቅ በርካታ አስተዳደራዊ ችግሮች ያሉበት ስለመሆኑ ከመስራች አባላት በጽሑፍና በቃል ቀርበው ለመ/ቤቱ ከሰጡት መረጃ መረዳቱን፣ በተጨማሪም የስራ አመራር ቦርዱ ወቅቱን ጠብቆ አባላትን ለስብሰባ በመጥራት በችግሮች ዙሪያ ማወያየትና መፍትሔ ማፈላለግ ሲገባው እስካሁን ስብሰባ ለመጥራት ፈቃደኛ አለመሆኑን በመግለጽ

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 6 ህብረተሰብ

የሰው ልጅ፤ ፈጣሪ ለክቶ በሰፈረለት የህይወት ዘመኑ ውስጥ እንደየእጣ ክፍሉ ከሚያጋጥሙት እጅግ የከፋ የመከራና የፈተና አጋጣሚዎች መካከል አንዱ ስደት ነው፡፡ ስደት

የሰውን ልጅ ከሰውነት ተራ ያስወጣል፡፡ ስደት የሰውን ልጅ ክቡር ስሙን ይነጥቃል፡፡ ስደት የሰውን ልጅ ከሰው ልጅነት ወደ ቁጥርነት ይለውጣል፡፡

ክቡር በሆነው የሰውነት ስማቸው ሳይሆን “ስደተኛ” በሚለው የወል ስማቸውና በየግል በተሰጣቸው ቁጥር ተለይተው የሚታወቁት ህዝቦች፣ ተወልደው ያደጉበትን፣ እትብታቸው የተቀበረበትን፣ ወግ ማዕረግ ያዩበትን ቀዬ ትተው እግራቸውን ወደተለያዩ አገራት በተለይም ወደ መካከለኛው ምስራቅ የአረብ ሀገራት ለስደት ከነቀሉበት ቀን አንስቶ ስደተኝነታቸው ፍፃሜውን እስከሚያገኝበት ጊዜ ድረስ በቃል እንዲህ ነው ተብሎ የማይነገር እንግልት፣ መከራ፣ ስቃይና ስምና ክብር የሌለውን ሞት ተሸክመውት አብረው ይኖራሉ፡፡

ወደእነዚህ የአረብ ሀገራት በህገጥ መንገድ ከሚሰደዱት ውስጥ ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ስደተኞች፤ ለቤተሰቦቻቸው ከሚልኩት ዶላር በፊት ቀድሞ የሚደርሰው አስከሬናቸው የታሸገበት ሳጥን እንደሆነ በአብዛኞቻችን ዘንድ በግልጽ የታወቀ ነው፡፡

ሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገሯ በህገወጥ መንገድ የገቡ ስደተኞች ህጋዊ የመኖሪያና የስራ ፈቃድ እንዲያወጡ ሰጥታው የነበረው የጊዜ ገደብ ባለፈው ሳምንት ተጠናቋል፡፡ ይህን ተከትሎም የደህንነትና የፖሊስ ሃይሏ ህጋዊ የመኖሪያና የስራ ፈቃድ ባላወጡ ስደተኞች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ትዕዛዝ ሰጥታለች፡፡ የደህንነትና የፖሊስ ሃይሏም በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በስደተኞቹ ላይ ዙሪያ መለስ እርምጃውን መውሰድ ጀምሯል፡፡ እናም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህገወጥ ስደተኞች ለሞት፤ ለእስርና ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገዋል፡፡ ይህ አሳዛኝ ሁኔታ በሳኡዲ አረቢያ በስደት የሚኖሩ ልጆች ያሏቸውን ወላጆች ከወዲያ ወዲህ አራውጧቸዋል፡፡ ከእነዚህ ወላጆች መካከል በስደት ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ የሚኖሩ ሴት ልጆች ያሏቸው ፊሊፒኒያዊትና ኢትዮጵያዊት እናት ከዚህ የሚከተለውን ደብዳቤአቸውን ጽፈው ወደ ሳኡዲ አረቢያ ልከዋል - ባለፈው ሳምንት ፡፡

ደብዳቤ አንድ ለማቲልዳ ባንባንግ ንጉስ አልሳውድ ጐዳና ሪያድ ሳኡዲ አረቢያ የተወደድሽው ልጅ ማቲልዳ፤ ይህን ደብዳቤ

በሰላም እንደምታገኘው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በዚህ ደብዳቤ አማካኝነት አባትሽ ባንባንግ፣ ወንድሞችሽ ፖኩንና ሳሚ፣ ባጠቃላይ መላው ቤተሰቡ የናፍቆት ሰላምታቸውን ያቀርቡልሻል፡፡

ባለፈው ሳምንት ስልክ ደውለሽ በተነጋገርንበት ጊዜ እንደነገርኩሽ ሁሉ እኛ በጣም ደህና ነን፡፡ ሰሞኑን

አልአዛር ኬ

የሁለት ደብዳቤዎች ወግሀገራችንን ከመታው ክፉ ሳይክሎን በክርስቶስና በእናቱ በድንገል ማርያም እርዳታ ተርፈናል፡፡ ሳይክሎኑ ባቅራቢያችን የሚገኙ ከተሞችን ጨርሶ ያልነበሩ ያህል አውድሞ የእኛን ከተማ ግን ሳይነካት ያለፈው በስላሴዎች ተአምር የተነሳ ነው፡፡

ልጄ ማቲልዳ - በሳኡዲ አረቢያ ስደተኞችን በተመለከተ የተነሳውን ግርግርና ፖሊሶች እየወሰዱት ያለውን እርምጃ በቴሌቪዥን እንዳየነው፣ በእውነቱ ስላንቺ ደህንነት ስጋት ገብቶን ነበር፡፡ በተለይ ሁለቱ ወንድሞችሽ ከቴሌቪዥኑ ላይ ተጣብቀው አልላቀቅ ብለው ነበር፡፡ ዜናው በሚቀርብበት በአንዱ ሰአት ላይ የሚያዩሽ ይመስላቸው ነበር፡፡ እነሱንም ሆነ እኔንና አባትሽን ገብቶን ከነበረው ከፍ ያለ ስጋት የገላገለን፣ ሁኔታው በተፈጠረ በማግስቱ የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና የውጭ ሀገር የፊሊፒንስ ሠራተኞች ጉዳይ ማስተባበሪያ ባለስልጣን መስሪያ ቤቶች የሰጡን ደህንነትሽን የሚያረጋግጥ መረጃ ነው፡፡ ወደ ሳኡዲ አረቢያ የላከሽ የውጭ ሀገር ስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲውም ያለሽበትን ሁኔታና ደህንነትሽን የሚገልጽ ደብዳቤ በሶስተኛው ቀን ማለዳ ላይ ለአባትሽ እንዲደርሰው አድርጓል፡፡

መንግስት የፊሊፒንስ የቤት ሰራተኞች ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት በተለይ ደግሞ ወደ ሳኡዲ አረቢያ እንዳይሄዱ ካቻምና ከከለከለ ወዲህ፣ ቀደም ብላችሁ የሄዳችሁትን የእናንተን ወሬ ካለፈው ጊዜ በተሻለ እየተከታተለ መናገር ጀምሯል፡፡ የሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲውም የመንግስትን ቅጣት እየፈራም ቢሆን በሁለት ወር ግፋ ካለም በሶስት ወር አንዴ ስልክ እየደወለ ስለ ደህንነትሽ ያገኘውን ወሬ ያቀብለናል፡፡

ውዷ ማቲልዳ:- ባለፈው ጊዜ በፃፍሽልን ደብዳቤዎችሽም ሆነ በስልክ በተነጋገርን ቁጥር ስራ አግኝተሽ ወደ ሳኡዲ ከመሄድሽ በፊት በማሰልጠኛ ተቋሙ ውስጥ ገብተሽ ተገቢውን የሙያ ስልጠና መውሰድሽ፣ ዘመናዊ የቤት ውስጥ መገልገያ መሳሪያዎችን በሚገባና ያለ አንዳች ችግር መጠቀም እንዳስቻለሽ እንዲሁም የአረቦችን፣ የእስያንና የአውሮፓውያንን ምግቦች እንደ ፈለግሽው ከሽነሸ ማዘጋጀትሽን ስለነገርሽን እኔም ሆነ አባትሽ በጣም ደስተኞች ነን፡፡ ከዚህ በፊት አስረሽ የነበረችው ሴትዮና የባሏ እናት ባንቺ ተደስተው እንዲያ ይወዱሽ የነበረውም በዚህ ትምህርት ባገኘሽው ሙያ የተነሳ ነበር፡፡

ልጄ ማቲልዳ:- ከሙያ ስልጠናው ጐን ለጐን ለአጭር ጊዜ የወሰድሽውን የአረብኛ ቋንቋ ትምህርት በሚገባ በማዳበር ከአሰሪዎችሽ ጋር ሆነ ከተቀረው የአገሬው ዜጋ ጋር ያለችግር መግባባት በመቻልሽ በእውነቱ ልትደነቂ ይገባል፡፡ እሰየው! እንኳንም ወንድሞችሽ እንዳሾፉብሽ አልቀረሽ!

ማቲልዳዬ :- የባለፈውን ስራሽን ለቀሽ በተሻለ ደመወዝ አሁን ካለሽበት ቤት መቀጠርሽ በእውነቱ መልካም ነገር ነው፡፡ በወሰድሽው እርምጃ በተለይ አባትሽ፣ ወንድሞችሽን ልክ እንዳንቺ አስተዋይ መሆን እንዳለባቸው ጧትና ማታ ሲጨቀጭቃቸው ነበር፡፡

የሆኖ ሆኖ ግን መቸም ምስጋና ላንቺ ይሁንና፤ ታናናሽ ወንድሞችሽ ትምህርታቸውን በርትተው በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡ አባትሽም በከተማችን ከሚገኘው የህብረት ስራ ባንክ ትንሽ ገንዘብ ተበድሮ

የተወሰኑ ማሽኖችን በመግዛት፣ የእንጨት ስራ ወርክሾፑን በመጠኑም ቢሆን ማስፋፋት ችሏል። ስራውም ቢሆን ምንም አይልም፡፡ ስላሴዎች ይመስገኑ፡፡

የተወደድሽው ማቲልዳ:- በየወሩ የምትልኪው ገንዘብ፣ ለወንድሞችሽ ትምህርት ቤት ከሚውለው አንድ መቶ ሰባት ዶላር በቀር፣ ቀሪው ስድስት መቶ ዶላር ወደ ሳኡዲ ከመሄድሽ በፊት አባትሽ በስምሽ በከፈተልሽ የባንክ አካውንት ውስጥ እየተቀመጠልሽ ይገኛል፡፡ የአሁኑን የስራ ኮንትራትሽን ከዘጠኝ ወር በኋላ ስትጨርሺ፣ በምንም አይነት ምክንያት ሳታመነቺ ወደ ሀገርሽና ወደ እኔ እናትሽ ቤት ተመለሽ። እኛም እኮ በጣም እጅግ በጣም ናፍቀንሻል፤ የአባትሽ ናፍቆትማ ይቅር አይነሳ! ነጋ ጠባ አንዴ ልጅ በህልሜ ስትታየኝ አደረች ይላል፡፡ አንዴ ደግሞ ልጄ ቀኑን ሙሉ በአይኔ ውል ስትለኝ ዋለች ይላል። የናፍቆቱ ነገር ምኑ ቅጡ፡፡ ብቻ ልጄ ኮንትራትሽን እንደጨረስሽ፣ ሳትውይ ሳታድሪ በቶሎ ተመለሺ፡፡ በሳኡዲ አረቢያ ስራ ይዘሽ ከሄድሽ ጊዜ ጀምሮ እየላክሽ የተጠራቀመልሽ ገንዘብ፣ ከልጅነትሽ ጀምሮ ትመኝው የነበረውን የዲያንግና ባትቾየ (በፊሊፒንስ ተወዳጅ የሆነ የአሳ ምግብና ሾርባ) ሬስቶራንት ለመክፈት በቂ ይመስለኛል፡፡ ምናልባት ገንዘቡ የሚያንስሽ ከሆነም አባትሽ ከቁጠባ ማህበራቸው ሊበደርልሽ እንደሚችል ደጋግሞ ነግሮኛል፡፡

ማቲልዳዬ:- በይ እንግዲህ ደህና ሁኝ፡፡ እስክንገናኝ ድረስ የክርስቶስ እናት አትለይሽ፡፡ አክስትሽ ሚሸሊንና ባላ ጀኦል እንዲሁም አጐትሽ ሮዌ ሰላምታቸውን ያቀርቡልሻል፡፡

ደብዳቤ ሁለት ይድረስ ለሃዋ ሰኢድ ሙሄ ጅዳ - ሳኡዲ አረቢያ ውድ ልጄ ሀዋ:- ከተለያየንበት ቀንና ሰአት አንስቶ

ለጤናሽ እንደምን ትሆኛለሽ? እኔ አልሀምዱላሂ መቸም ከሞት ተርፌአለሁ፡፡ ሰሞኑን አገሩ በሞላ የሳኡዲ መንግስት አበሻውን ሙላ እየገደለ፣ እየደበደበና እያነቀ ዘብጥያ እየከተተ ነው እያለ ሞጥሮ ሲያወራ ስሰማ ጊዜ፣ አንቺን አንቆ እንዳይመልስሽ ብዬ ደንግጬ፣ ትንሽ ከሰሞኑ ሻል ብሎልኝ የነበረው በሽታ ከነጓዙ ጠቅልሎ አገረሸብኝ፡፡ አሁንማ እንጃልኝ እንዲያው እተርፍ ብለሽ ነው?

ውድ ልጄ ሀዋ:- የሳኡዲ መንግስት በዛ ሁላ የእኔ ቢጤ አበሻ ላይ እንዲህ ጨክኖ የተነሳው ምን ሆኖ ነው በይሳ? እንዲያው ምኑ ጂኒ ቢጠጋው ነው አንቺየ! ግን እንዲያው ለመሆኑ ያንቺሳ ነገር እንዴት ነው? ቦሊሶቹ አግኝተው አነቁሽ ወይስ እንዴት ነሽሳ! እኔማ ይህንን የሳኡዲ መንግስት በአበሻው ሁላ ተነሳ መባልን ስሰማ፣ እንዲያው አምርሬ አዝኘ ሳለቅስ ባጀሁ፡፡ ያለቀስኩትም የሚያስለቅሰኝም ሌላ ሳይሆን እድሌ ነው፡፡ ከድፍን ቤት ሙሉ ልጅ አንድ እንኳ ጧሪ ደጋፊ አለማውጣቴ ያስለቅሰኛል፡፡ የቀዬው ሰው ሁላ ቤት ሙሉ ልጅ ከመቀፍቀፍ በቀር ሌላ ሙያ የሌላት እያለ ነጋ ጠባ ያነውረኛል፡፡ የመሀመድ ኑር ይማም ሚስት እኮ ባቅሟ ከባሏ አፋታ ባህሬን የሰደደቻት ትልቋ ልጇ፣ በዚያው ሰሞን የሰደደችላትን ዘመን አመጣሽ ቀሚስ እየበተነች ስትወነንብኝ ትውላለች፡፡

ውድ ልጄ ሀዋ፤ ያን ጊዜ በየመን ከነራህመቶ

ልጆች ጋር እንድትሄጂ ብዬ ለደላላው ያን ሁላ ገንዘብ አባትሽ የከፈለው፣ ጥማድ በሬውን ሽጦ እንደሆነ መቸም አታጭው፡፡ ከሄድሽ ጀምሮ ታዲያ እንደ ሰፈር ጓደኞችሽ እንኳን ዶላሩን ልትልኪ ቀርቶ መጋቢያሽንም እንዲህ ነው ሳትይ ስትቀሪ፣ አባትሽ ቅስሙ ተሰብሮ ወጀጅ ያረገው ጀምሮአል፡፡ እንኳን እንዳንቺ ያለው ልባም ይቅርና ስንቱ ገልቱ አልፎለት፣ ለናት አባቱ ዶላሩን እየላከ፣ አንቀባሮ በሚያሰልፍበት አገር፣ ያንቺ ነገር እንዲህ ሆኖ መቅረቱ ወላሂ በጣም ያሳዝናል፡፡ ለነገሩ ጠላቴ አንቺ ሳትሆኝ እድሌ ነው፡፡

ያንቺ ታላቅ ጓደኞቿን ተከትላ ስንት በረሃና ባህር አቋርጣ፣ ቤሩት ገብታ እየሰራችም ምንም እያለችም የምታገኛትን ለራሷ ሳትል ለእኛ እየላከች አንድ ሁለት አመት ደህና ቀጥ አድርጋ ይዛን ባጅታ ነበር፡፡ አባትሽም አምሮበት ደህና እንዲያው ሰው መስሎ ከርሞ ነበር፡፡ ግናስ የኔው ጠማማ እድል ተከትሏት፣ አሠሪ እመቤቷ በፈላ ውሃ ፊቷን ጠብሳ፣ መለመላዋን ስታባርራት ያገሩ ፖሊስም ለቀም አድርጐ ይዞ ጠርዞ ልኳት፣ የነፈረ አካሏን ይዛ ባዶ እጇን እያጨበጨበች መጣች፣ በኋላም “ሁለት አመት ሙሉ የላኩትን ገንዘብ ውለዱ” ብላ ቁም ስቅላችን ስታሳየን ኖራ፣ ዛሬ እዚህ ነኝ እንኳ ሳትለን የትሜናዋ ሄዳለች፡፡

አንቺዬ:- እንዲያው እኛ ቤት የገባው ሰይጣን ከቶ እንዴት ያለው ይሆን? የዚያች ያክስትሽ የአሻ መቁረጫ ልጇ ዘይነብ ብዙ ሳትከላተም፣ ባሬን ገባች ተብሎ ደስ ሲለነ ገና ሁለት ወር እንኳ ሳይሞላት፣ ያሰማችው ምጣድ በጀ አልል ብሏት፣ እሳቱ መላ አካላቷን ፈጅቷት ተብሎ፣ ሬሳዋ በሰንዱቅ ተጭኖ ለዚያች ከንቱ እናቷ መጣላት፡፡ የአባትሽ የወንድም ልጅ አሚናም እመቤቲቱ ሰይጣን ተጋብቷት፣ ከፎቅ ላይ ወርውራት ተብሎ ተጠርዛ መጥታ፣ እጅ እግሯ አይሰማ፣ ወገቧ አይላወስ፣ በድን ደንጊያ ሆና አለችው።

የሆነ ሆኖ ሃዋ:- እኔም ሆነ አባትሽ ተስፋችንን የጣልነው ባንቺ ላይ ነው፡፡ የሳኡዲው ቦሊስ አንቆ ጠርዞ እንዳይልክሽ፣ ቦሊሱ ባለበት መንደር እንጦለጦላለሁ ብለሽ ወት ወት እንዳትይ አደራ! እኔ እንደምታይኝ በበሽታ ተደይኜ ነው ያለሁ፡፡ አባትሽም ቢሆን እንዲያውም ነፍሱ ስላልወጣች እንጂ በጠና ተይዞ ነው ያለው፡፡

ወንድሞችሽና እህትቶችሽም ቢሆኑ ለትምህርት ቤት የሚከፍልላቸው ጠፍቶ፣ ይሄው የሰፈር አመድ ሲያቦሉ ይውላሉ፡፡ አያትሽ አያ ሙሄም በራብ የተወጋ ጐኑ እንዲያው አንድ ቀን እንኳ ቀና ሳይል፣ በባዶ ቤት እየተቆራመደ ይኖራል። እንዲያው አንደዜ እንኳ እጅሽን ሳትዘረጊለት ድፍት ብሎ ቢቀር ኋላ ይቆጭሻል፡፡

እና አሁንም የሆነ እንደሆነ ተጠርዞ ከሚመጣው አንድ አገር አበሻ የኛ አገር ልጅ፣ ተኛ ወገን የሆነውን ፈልጊና ዶላሩን ላኪልነ፡፡ አደራ በሰማይ አደራ በምድር በምድር! ኋላ እንዲችው ተቆራምደን “አዬ የልጅ ያለህ” እንዳልን፣ እኔም ሆነ አባትሽ ወንድምና እህቶችሽን ባዶ ቤት በትነን ብንሞት ይቆጭሻል፡፡

ያኔ አባቴ አባቴ ብትይ፣ እናቴ እናቴ እያልሽ ወዮ እላለሁ ብትይ ቀየውም፣ አድባሩም አያቆምሽ! እንግዲህ የዶላሩን ነገር አደራ! በሰማይ አደራ በምድር ብዬሻለሁ፡፡

ውድ እናትሽ፤ ሰይዳ ከድር

አዲሱ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፤ መላው የአገሪቱ ደራሲያንና የድርሰት ወዳጆች ከስነ ጽሑፍ እድገት ጐን እንዲቆሙ ጠየቀ፡፡

በቅርቡ የተመረጠው የደራስያን ማህበር አመራር፤ ትላንት በፅ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ፤ ማህበሩ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያካበተውን ልምድና ያከናወናቸውን ተግባራት መሠረት በማድረግ፣ ከዘመን ዘመን ማህበሩን ሲፈታተኑ የቆዩ ማነቆዎችንና ተግዳሮቶችን በማስወገድ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አስታውቋል፡፡ አዳዲስ የአስተሳሰብና የአሠራር አቅጣጫዎችን ቀይሶ፣ አባላቱን ከዳር እስከዳር በማንቀሳቀስ ማህበሩን ወደ ላቀ የእድገት ደረጃ ለማድረስ ቆርጦ መነሣቱንም ገልጿል፡፡

የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ ቀዳሚ የትኩረት እንቅስቃሴ አቅጣጫዎቼ ናቸው በማለት ከዘረዘራቸው መካከል፤ ከ22 ሚ. ብር በላይ ወጪ ይጠይቃል የተባለው “የብዕር አምባ” ግንባታ እንዲጀመር ማድረግ፣ የማህበሩን ገቢ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ማስፋትና የማህበሩን የህትመት ውጤቶች በብዛትም በጥራትም መጨመር የሚሉት ይገኙበታል፡፡ በየክልሎቹ ያሉትን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ቁጥር ለማሳደግ እንደሚሠራና ብዕርተኞች የሚዘከሩባቸውን የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚያካሂድ የገለፀው ማህበሩ፤ የመጽሐፍት ማከፋፈያና መሸጫ መደብሮች፣ በአዲስ አበባ ማዕከላዊ ቦታዎች ላይ ለመክፈት እጥራለሁ ብሏል፡፡ የማህበሩን ጥረት ለማገዝም የድርሰት ወዳጆች ከጐኑ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ደራሲያንና የድርሰት ወዳጆች ለሥነ ጽሑፍ እድገት እንዲቆሙ ተጠየቀ

22ሚ. ብር የሚፈጅ “የብዕር አምባ” ግንባታ ይጀመራል

የሚመመራው ሁዋዌ በበኩሉ 200 ሺ ብር ድጋፍ እሰጣለሁ ብሏል።

ከዚህ በኋላ ነው፣ ዋንግ ዮንግ ወደ ጅማ መጥቶ “ጋዜጠኛ ነኝ በማለት አጭበርብሯል” የተባለው። ቻይናዊው ዋንግ ዮንግ መጥቶ እንዳገኛቸውና ሆቴል ድረስ ጠርቶ እንዳነጋገራቸው የጠቀሱት ወ/ሮ ታደለች፣ “ጋዜጠኛ ነኝ፤ ተጨማሪ ገንዘብ እንድታገኙ አደርጋለሁ፤ አዲስ አበባ እንሂድ” በማለት ሊያግባባቸው እንደሞከረ መናገራቸውን ምንጮች ገልፀዋል። ወ/ሮ ታደለች ለፖሊስ ያመለከትኩት ጥርጣሬ ስላደረብኝ ነው ማለታቸው የተገለፀ ሲሆን ፖሊስ በበኩሉ፤ ዋንግ ዮንግ

ጋዜጠኛ ሳይሆን የቴሌኮም ኢንጂነርና የዜድቲኢ ሰራተኛ መሆኑን ያረጋገጠው ባለፈው ሳምንት ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ባገኘው መረጃ ነው ተብሏል። በእነዚህ መረጃዎች የተነሳ፣ ጉዳዩ በዜድቲኢ እና በሁዋዌ መካከል ካለው ተቀናቃኝነት ጋር የተያያዘ ሳይሆን አይቀርም የሚል ጥርጣሬ መፈጠሩ አልቀረም።

የዜድቲኢ የህዝብ ግንኙነት ተወካይ ስለ ዋንግ ዮንግ ትናንት ተጠይቀው በሰጡን ምላሽ፣ ዜድቲኢ ለማንኛውም ስራ ወደ ጅማ የላከው ሰራተኛ እንደሌለ እርግጠኞች ነን፤ የሰውዬውን ማንነት አጣርተን እናሳውቃለን ብለዋል።

ፖሊስ ከገፅ 2 የዞረ

መንግስት ከገፅ 1 የዞረእስር ቤትም ይወረወራሉ” ያለው ፓርቲው፤ በተለይ የነፃው ፕሬስ በመንግስት የተቀነባበረ ከፍተኛ ጥቃት ይፈፀምበታል ብሏል፡፡

ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ የተካሄደውን የአፍሪካ ሚዲያ መሪዎች ፎረም መጠናቀቅ ተከትሎ “በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ታስረዋል” የሚለውን

የተሳታፊዎች የጋራ አቋም በመቃወም በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ሶስት የጋዜጠኞች ማህበራት በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ “አንድም ጋዜጠኛ በሙያው ምክንያት አልታሰረም፤ የፕሬስ ነፃነት ከማንኛውም የአፍሪካ አገራት በተሻለ ተከብሯል” ማለታቸው ይታወሳል፡፡

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 7 ህብረተሰብ

ኤፍሬም እንዳለ

ጥጋብ ወደ ገፅ 17 ዞሯልማስታወቂያ

የድሬዳዋ የጉዞ ማስታወሻዬ!ነቢይ መኰንን

እንዴት ሰነበታችሁሳ!ስሙኝማ…ይቺ ከተማ ‘ዘመናዊነት’ አፍኖ

ትንፋሽ ሊያሳጥራት ነው፡፡ ቂ…ቂ…ቂ… በፊት ጊዜ “ድንቄም!” የምትል ቃል ነበረች፡፡ እሷ ቃል ‘አቧራዋ ተራግፎ’ እንደገና ጥቅም ላይ ትዋልንማ፡፡ ልክ ነዋ… “ድንቄም!” የምንልባቸው ነገሮች በዙብና! እናማ…የዚች ‘የአፍሪካ መዲና’ ከተማችን የ‘ዘመናዊነት’ ማሳያዎች ድንቄም እያስባሉን ነው፡፡

በቀደም እዚህ የፈረደበት ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ በረፋዱ ሰዓት ቢበዛ አሥራ ሦስትና አሥራ አራት የማይበልጡ ሚጢጢ እሷና እሱ ‘ኪሲንጉን’ ያጦፉት ነበር፡፡ (ስሙኝማ… እዛ ሰፈር እኮ… አለ አይደል… የማይታይ ጉድ የለም፡፡ “ጉድ!” የምንለው የእኔ ቢጤዎቹ እንደሆንን ልብ ይባልንማ!)

ልጅቱ ለጓደኛዋ ምን ትላታለች? “አንድ የማላውቀው ሰውዬ ዛሬ ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ?”

“ምን አለሽ?”“ፍቀጂልኝና ልሳምሽ አለኝ”“እና በጥፊ አጮልሽው?”“አዎ፣ ስሞኝ ሲያበቃ አጮልኩት”ዘንድሮ እኛ ግን…አይደለም ከተሳሙ በኋላ

ማጮል… እንደውም “አትሳመኝና አጠናግርሀለሁ…” ብለው ‘እጅ የሚጠመዝዙ’ እንዳይመጡ ፍሩልኝማ!

ከ‘ኪሶሎጂ’ ሳንወጣ ይቺን ስሙኝማ…እሱዬው እሷን ምን ይላታል… “ጫፍሽን ሳልነካሽ መአት ጊዜ ደጋግሜ ልስምሽ እችላለሁ፡፡ ካልቻልኩ አምስት ብር እቀጣለሁ፡፡” እሷዬው የእልህ ሆነና “እሺ…” ትላለች፡፡ እሱዬው ደጋግሞ ይመጨምጫታል፡፡ “ሳልነካሽ አይደል እንዴ ያልከው! ይኸው ነካኸኝ አይደል!” ስትለው ምን ቢላት ጥሩ ነው… “በቃ፣ አምስት ብርሽ ይኸውልሽ!”

‘ጥጋብ’ እና ‘ዘመናዊነት’…

እናላችሁ… ስልጣኔና ‘ጥጋብ’ እየተደበላለቁ የምንይዘው እያሳጣን ነው፡፡ አባቶቻችን “ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ…” የሚሉት የእውነትም ወደው አልነበረም፡፡

ታዲያማ… ወንበር ላይ ስንወጣ የምንጠግብ፣ የባንክ ደብተራችን ወደ ‘ሲክስ ዲጂት’ ሲያድግ ‘ጥጋብ ሻኛ የሚጨምርልን’፣ መኪና ቢጤ ስንይዝ ‘ጥጋብ ሻኛ የሚጨምርልን’፣ ‘የዘመኑ ሰው’ ወዳጅ ስናደርግ ‘ጥጋብ ሻኛ የሚጨምርልን’፣ ምን አለፋችሁ… በትንሹም በትልቁም ነገር ‘ጥጋብ ዝሆን የሚያሳክለን በዝተናል፡፡

አንድ መጽሐፍ በስማችን ስናወጣ ‘ጥጋብ ሻኛ የሚጨምርልን’፣ በመድረክ ግጥም አዳራሹ ስላጨበጨበልን ‘ጥጋብ ሻኛ የሚጨምርልን’፣ በፊልም ወይም በደራማ “አሪፍ! አሪፍ!” ስንባል ‘ጥጋብ ሻኛ የሚጨምርልን’፣ በኳስ ላይ “እንደ ሩኒ… እንደ ሜሲ ምናምን ስንባል ‘ጥጋብ ሻኛ የሚጨምርልን’፣ …ብቻ፣ ከምንጠግብባቸው የማንጠግብባቸውን ምክንያቶች መዘርዘሩ ይቀላል፡፡

እናላችሁ…ችግሩ ምን መሰላችሁ…ብዙ ጊዜ ‘ዘመናዊነት’ ጋር የሚያያዙት ነገሮች መነሻቸው ጥጋብ ነው፡፡ ሻኛን የጨመረ መስሎ አእምሮን ተከራይ ያጣ ቤት የሚያስመስል ጥጋብ፡፡

እናላችሁ… አናት ላይ የወጣ ‘ጥጋብ’ ከዘመናዊነት እየተቆጠረ “በአማርኛ ዛሬ ቀኑ ስንት ነው?” የምንል እየፈላንላችሁ ነው… ‘ላይኛው ቤት’ አእምሮ ሲታደል ‘ቀሪ’ የነበርን፡፡ ‘ጨ’ እና ‘ቀ’ የተባሉ ፊደላትን ‘ቸ’

እና ‘ከ’ ካላልን ኋላ ቀርነት የሚመስለን ጥጋባችን ዘመናዊነት የሚመስለን እየፈላን ነው፡፡

የቋንቋ ነገር ካነሳን አይቀር ይቺን ስሙኝማ…አንድ የኬጂቢ ሰላይ በመናፈሻ ውስጥ ሲንጎራደድ አንድ ሸምገል ያለ ሰው መጽሐፍ ሲያነብ ያገኛል፡፡ እናላችሁ… “ምን እያነበብክ ነው?” ሲል ይጠይቀዋል፡፡ ሰውየውም “እብራይስጥ ቋንቋ እያጠናሁ ነው…” ይለዋል፡፡

ሰላዩም “እብራይስጥ ማጥናት ምን ያደርግልሀል? እሥራኤል መግቢያ ቪዛ ለማግኘት ዓመታት ይፈጃል፡፡ እስከዛ ደግሞ ልትሞት ትችላላሀ፡፡” ሲል ሞራሉ ላይ ይረማመድበታል፡፡

ሰውየውም “እብራይስጥ የማጠናው ሞቼ መንግሥተ ሰማያት ስሄድ አብረሃምና ሙሴን እንዳናግርበት ነው፡፡ እብራይስጥ መንግሥተ ሰማያት ወስጥ የሚናገሩት ቋንቋ ነው” ይላል፡፡

የኬጂቢው ሰላይም “ስትሞት መንግሥተ ሰማያት ሳይሆን ገሀናም ብትገባስ?” ሲል ይጠይቀዋል፡፡ ሰውየው ምን ብሎ ቢመልስ ጥሩ ነው… “እዛማ ቋንቋው ሩስያኛ ስለሆነ አይቸግረኝም።”

ሀሳብ አለን… እኛ የምንሄድበት ገሀነም (መቼም ከሁሉም ጋር አይቀላቅሉንም!) አፍ መፍቻ ቋንቋው ምን እንደሆነ ይጠናልንማ!

እናላችሁ… ከዚህ በፊት ያወራናት የአሥራ አራት ዓመት ልጇ ሲጋራ ስታጨስ መያዟ ሊነገራት የተጠራች እናት… “እኔ አስተምሩልኝ አልኩ እንጂ ሲጋራ ማጨሷን ተቆጣጠሩልኝ አልኩ!” አይነት

‘ወላጆች’ እየበዙ ሲሄዱ የምር ያሳስባል፡፡ ይቺ እናት ጥጋቧ አናት ላይ ስለወጣ …የአሥራ አራት ዓመት ልጇ ሲጋራ ማጨስ የ‘ዘመናዊነት’… የመሰልጠን ‘ግሪን ካርድ’ ይመስላታል፡፡ ይቺኛዋ መጀመሪያ ላይ አእምሮ ሲታደል ላልነበሩ የተዘጋጀ ‘ማራዘሚያ’ ላይም ያልተገኘች መሆን አለባት፡፡ ቂ…ቂ…ቂ…

በሌላ ቦታ ሚጢጢ ልጇ በጣም አጭር ሚኒስከርት ለብሳ ትምህርት ቤት መምጣቷ ሊነገራት የመጣች እናት፣ ከልጇ የባሰ አጭር ለብሳ ብትመጣ ጊዜ፣የትምህርት ቤቱ ሰዎቹ ሀሳባቸውን ለውጠው ትተውታል፡፡ ለሴትየዋ ገና ሚጢጢ ልጇ ሚኒስከርት መልበሷ የዘመናዊነት ምልክት ነው፡፡

ስሙኝማ…አንድ ጊዜ እንዳወራነው…አለ አይደል… “ልጄ የአሜሪካ ፓስፖርት አገኘ…” “ልጄ የእንግሊዝ ዜግነት አገኘች…” እየተባለ ቅልጥ ያለ ድግስ የሚደገስበት አገር ሆነናል እኮ! ኮሚክ እኮ ነው… ማነነትን አውልቀው ሲጥሉ “ይትባረክ እንደ አብረሀም…” አይነት ውዳሴ… እየሄድን ያለንበት ‘አቅጣጫ መጠቆሚያ የሌለው’ መንገድ ምን ያህል እንዳደነጋገረን የሚያሳይ አይመስላችሁም? (ጥያቄ አለን…ቦሶቻችን መሀል ሌላ ‘የክፉ ቀን ፓስፖርት’ ያላቸው አሉ የሚባለው እውነት ነው እንዴ! አሀ…አንዳንዴ የሚናገሩት ነገር ይሄ ሰውዬ ሌላ አገር አለው እንዴ እያስባለን ነዋ!”)

እናላችሁ… “አማርኛ መናገርና ድንጋይ መወርወር ክልክል ነው...” ብለን በአደባባይ፣ በተከበረው በትምህርት አደባባይ ስንለጥፍ፣ ህሊናችንን ትንሽ እንኳን የማይቆጠቁጠን…አለ አይደል… እንግሊዝኛ መናገር ‘ዘመናዊነት’ የሚመስለን ሰዎች የፈላንበት ዘመን ነው፡፡

(ስሙኝማ…እግረ መንገዴን በእንግሊዝኛ ቋንቋ እየጻፍንም፣ እያነበብንም፣ እየተነጋገርንም መግባባት መሞከር ክፋት የለውም፡፡ እንደውም ከቋንቋው ዓለም አቀፍ ይዘት ልናገኝ የምንችለውን መረጃና፣

የደብረ ብርሃን ጉዞዬን ያጠቃለልኩ የእየሩሣሌም የህፃናትና ማህበረሰብ ድርጅትን የደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፤ ከጋሽ ዓለማየሁ (ከሥ/አስኪያጁ) ጋር ጐብኝቼ ነው፡፡ ከተማው ውስጥ የሚሠራው የግብርናና የልማት ሥራ ሁሉ በሠርቶ ማሳያ ሞዴል መልክ ግቢው ውስጥ ይታያል፡፡ የመኖ ልማት አለ፡፡ የከብት እርባታ ከነወተት ተዋጽኦ ምርት ጥቅሙ፣ በባዮ ጋዝ የሚለማው መኖ፣ አልፋ አልፋ፣ የከብት ድንች፣ ቃሪያ ቲማቲም፣ የክብሪት ዛፍ፣ ጥቁር እንጨት ወዘተ አለ፡፡ “ሰው ባገሩ፣ ሰው በወንዙ

ቢበላ ሣር፣ ቢበላ መቅመቆ ይከበር የለም ወይ ሰውነቱ ታውቆ” የተባለለትን፤

ከዚህ በፊት ያላየሁትን መቅመቆ አየሁ፡፡ “ገጠር ውስጥ ቅቤ ያነጥሩበታል፡፡” ኤሌፋንት ግራስ (ዝሆኔ) አለ፡፡ “የደብረ ብርሃን ተክል አደለም፡፡ የቆላ ወይም የወይና ደጋ ነው፡፡ ሆኖም እዚህ በቅሏል፡፡ አየሩ መለወጡን ያሳያል” አሉኝ፡፡

“ልዩ ልዩ ትምህርትና ሥልጠና እንሰጣለን” አለኝ የከተማ ግብርና ኑሮ ማሻሻያ ሴክሺን ኦፊሰር ቴድሮስ ቡታ፡፡ የተፈጥሮ ማዳበሪያ አየን፡፡ ዘመናዊ የወተት ልማት አለ፡፡ ለህዝቡ ሥልጠና ይሰጥበታል፡፡ ልት የሚባል ለፀጉር መታጠቢያ የሚያገለግል ተክልም አለ፡፡

የሠርቶ ማሳያ ሞዴሉን እርሻ ጐብኝቼ የእየሩሳሌም የህፃናትና ማህበረሰብ ልማት ድርጅትን ድንቅ ጥረት በደብረብርሃን አድንቄ ቀጣዩን የድሬዳዋ ጉዞዬን ላደርግ ፊቴን ወደዚያው አዞርኩ፡፡ እግረ መንገዴን በደብረ ብርሃን እጅግ የሚታወቀውን አዳራሽ የአረቄ መሸጫና መጠጫ እልፍኝ አየሁ፡፡ አንድ ሰው እንዲያስረዱኝ ጠየኩ “የደብረ ብርሃን ሰው የደብረ ብርሃንን ብርድ እንዴት እንደሚቋቋመው ያቃል” አሉኝ፡፡

* * *የድሬዳዋ ጉዞዬ“አደጋ ባህል ከሆነን፣ እስኪ እግዚሃር ይመስገናይኸው ለዓመት ጉድ በቃ!” ፀጋዬ ገ/መድህን “እንኳን ለዓመት ጉድ

አበቃን” ለሚለው ያልታተመ ግጥሙ እንደ አዝማች የተጠቀመበት የግጥም መሥመር ነው፡፡ ግጥሙ ያነጣጠረው፣ አንድ ጊዜ ፍልውሃ አካባቢ በጐርፍ ተጥለቅልቆ ሰውም፣ መኪናም፣ ንብረትም የተወሰደ ጊዜ መዘጋጃ ቤት ቅድመ ዝግጅት እንዴት አያደርግም ለማለት ነበር፡፡ ስለ ድሬዳዋ ጐርፍ ላነሳላችሁ ነው የፀጋዬን ግጥም መጥቀሴ፡፡

አቤ የእየሩሣሌም የህፃናትና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት(ጄክዶ) የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ሲሆን፤ ወዳጄ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ስለድሬዳዋ ጉዞዬ ስፅፍ አንስቼላችሁ ነበር፡፡

ዛሬ ማምሻዬን ከሱ ጋር ነው ቆይታዬ፡፡ አንድ ቡና ቤት ደጃፍ ወንበር አስፋልቱ ድረስ ወጥቶ አግኝተን ተቀምጠን ሻይ ቡና እያልን ነው የምንወያየው፡፡ ነፋሻው የድሬዳዋ አየር በጣም ደስ ይላል፡፡ የቀኑ ቃጠሎ ለማታው ነፋሻ አየር ቦታውን ለቅቆ እሹሩሩ እያለን ነው፡፡

በእኔና በአቤ ጨዋታ ነፋሻው አየርም ተመስጦ “ምነው እነዚህ ሰዎች እስኪነጋ በቆዩልኝ?” ሳይል አልቀረም፡፡

ማታ መኝታዬ ላይ አመሻሻችንን ማስታወሻዬ ላይ እያሳረፍኩ፤ ላስታውሰው ሞከርኩ፡፡

ብዙ ነገር ተጫውተናል፡፡ “የወጌሻ በቅሎ በተኩስ ታልቃለች” የሚለው ተረቱ በተለይ ማርኮኛል፡፡ ወጌሻ በቅሎው በቆሰለች ቁጥር ይተኩሳታል፡፡ እንዲሁ እንደተተኮሰች ትሞታለች፡፡ (አበበ መኰንን) አቤ ጨዋታ ይችላል፡፡ ጨዋታውን ለእኔ በሚጥመኝ ቋንቋ መናገሩ፤ ከሁሉም በላይ ልዩ ያደርገዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው ብዙ አይገኝም፡፡ በጨዋታው ውስጥ ቁም ነገር የሚያኖርና ቁምነገሩን በለዛ የሚያቀርብ በጣም ጥቂት ሰው ነው ያለው፡፡ በዚያ ላይ አቤ በጣም በጣም በጣም ሥራውን ያቀዋል፡፡ ማህበረሰቡን እንደ እጁ መዳፍ መስመሮች ያቀዋል፡፡ የሥራው ብልት የትጋ እንደሆነ ስለሚያቅም ስለሥራው ሲጠየቅ እንደሰላምታ ነው የሚመልሰው፡፡ እንዲህ ያለም ሰው ብዙ አይገኝም፡፡ እንደተፈጥሮው ያህል ተዋህዶታል፡፡ አቤ ድሬዳዋን ራሷን ነው፤ እላለሁ አንዳንዴ በሆዴ መሠረቱ ባሌ አርሲ ነው፡፡ ሥራውን እንዴት እንደሚሠራና፣ ከሥራው ጋር አንድ አካል አንድ

አምሳል የመሆኑን ነገር ሲያጫውተኝ ውስጡ ትልቅ ትምህርት አገኝበታለሁ፡፡

የውይይታችን አንዱ ቁም ነገር፤“ብዙዎቻችን ያተኮርንበትን ነገር ከሚገባው

በላይ ለማሳካት ባለን ውጥን የግል ህይወታችን እየከሳ እየከሳ እየመነመነ፤ ሲነግሩን ሳንሰማ፣ ሲመክሩን እንቢ ስንል፤ እንዲሁ ጊዜያችንን እናባክነዋለን፡፡ አልሠራንም ማለት አይደለም እንሠራለን” ይላል አቤ፡፡ “አዎ ነገሩ የሚገባን፣ ድንገት ብንታመም የምንሠራበት ድርጅት ሁለት ሦስት ወር አብሮን ይቆይ ይሆናል፤ ገንዘብ እያወጣ እያሳከመን እያስታመመ፡፡ እጅግ አሰቃቂው ሰዓት ሲደርስ ግን በሚስትና ልጆች ላይ ትወድቃለህ፡፡ ይሄ ደግሞ “ለምንድን ነው የለፋሁት እስከዛሬ” የሚል ኀይለኛ ፀፀት ይፈጥራል፡፡ ስንሠራ ኖረን ተፀጽተን እንድንሞት መሆን ደግሞ ደግ አደለም፡፡ ስለዚህ ሚዛን የስፈልጋል፡፡ ለድርጅትህ መስጠት ያለብህን ሳትነፍግ፤ ቤተሰብህንም አለመርሳት አለበህ፤” አልኩት፡፡

ጠዋት አቤ ወደሥራ ቦታ ሊወስደኝ መጣ፡፡ “ተነስተሃል?” አለኝ፡፡ “ኧረ አንድ የሚገርም መጽሐፍ እያነበብኩ ነበር፡፡ የMichela Wrong” ን “I Didn’t Do It for you”፡፡ እዚያ ላይ ምን ገረመኝ መሰለህ?

ደራሲዋ ግብጽ ኤርፖርት ያገኘችው አንድ መንገደኛ ፓኪስታናዊ እንዲህ ሲል ይጠይቃታል፡፡

“አንቺስ ምን እየሠራሽ ነው?”“ጋዜጠኛ ነኝ፡፡ ስለ ኤርትራ መጽሐፍ እየፃፍኩ

ነው፡፡ አሁን የምሄደውም ወደዚያ ነው” ትለዋለች፡፡ሽፋሽፍቶቹን ስብስብ አድርጐ፣ በትክክል

አልሰማኋትም በሚል ስሜት፤ “ስለ አልጄሪያ መጽሐፍ እየፃፍሽ?” አላት፡፡ “አይ ስለአልጄሪያ አይደለም፤ ስለ ኤርትራ”“አሃ ስለናይጄሪያ?” አሁን በሃሳብ እየባዘነ ነው፡፡ “አይደለም” አለችው፡፡ አሁን ጭራሹን ገደል የገባ ግምት ገመተ:- “ስለ

አልጀዚራ??”ከአቤ ጋር ተሳሳቅን፡፡ “ወደ አንድ ማህበር ነው የምንሄደው፡፡ አየህ

እያንዳንዷ ትናንሽ ማኅበር ከማህበረሰቡ ትወጣና ሰፍታ ትልቅ አገር ትፈጥራለች፡፡ አንዷ ክር ትመዘዝና ክሯ ተገጣጥማ መረብ ትሆናለች…

ወደ “በድሬዳዋ አስተዳደር ማህበረሰብ መር የአደጋ ሥጋት ቅነሳ የበጐ አድራጐት ማኅበር” ነው የምንሄደው፡፡”

የማኅበሩን ሰብሳቢ አስተዋውቆኝ አቤ ሄደ፡፡ እሳቸውና እኔ ውይይት ቀጠልን፡፡

“እኔ ሻለቃ አየለ ካሤ እባላለሁ፡፡ ማኅበራችን ታሪካዊ አመጣጡ… ድሬዳዋ ብዙ ህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው በጐርፍ የሚጠቁት፡፡ በአራት ሳይቶች ነው አደረጃጀቱ 4 Village ኮሚቴዎች አሉት፡፡ ቦርድ 7 አባላት አሉ፡፡ 4ቱ ከማህበረሰቡ 3ቱ ከውጪ ከሴክተሮች የመጡ፡፡ 1 ዓመት ነው የሠራ ነው፡፡ የጄክዶ አደረጃጀት ከተፈጠረ በኋላ፤ ነው ይሄ ሁሉ፡፡

ከታሪክ እንደምንረዳው ከ1937 ዓ.ም ጀምሮ ነው የጐርፍ ጥቃቱ፡፡ 1973-75 እኛ የምናውቀው ያየነው ነው፡፡ ይህም ፈረቃው በ10 ዓመት፣ በ6 ዓመት፣ በ2 ዓመት እያለ ይከታተል ጀመር፡፡ በየ6 ወሩ እየመጣ ከፍተኛ ጉዳት ያደርስ ነበር፡፡ ህዝቡ ፈጣሪያችን ያመጣብን ነው ብሎ የመቀመጥ ኋላቀር አስተሳሰብ ነበረው፡፡ እሱ ያመጣውን እሱ እስኪመልሰው የሚል ሃሳብ ነበረው፡፡ እየባሰ እየባሰ ሲሄድ ደግሞ “መንግሥት ለምን አይከላከልልንም?” “ለምን ዝም ይለናል ስናልቅ ስንፈናቀል”፤ ይል ጀመር፡፡ 1998 ዓ.ም ላይ እጅግ የከፋ ሆነ! ከደጋው የዘነበው ዝናብ ባጭር ጊዜ ተንደርድሮ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡ ፌዴ/መንግሥቱን ያንቀሳቀሰና ጠ/ሚኒስትሩ ጭምር በቦታው ተገኝተው እንዲያዩት ያስገደደ ነው፡፡ የዓለም አቀፉን ሚዲያም የሳበ ነው! ማህበረሰቡም ራሱን መጠየቅ ጀመረ፡፡ መለወጥ ጀመሩ ገንዳ አዳና ኮካ በደቡብ ወገን ያሉት በጣም ተጠቂ ነበሩ፡፡ በምዕራብ ደሞ አርጌሌ፣ ጂቲ ዜድ፣ መርመረሣ እያለ ቀጠለ፡፡ ድሬዳዋ በድንጋይ የተከበበች ናት፡፡ በ1 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ተምዘግዝጐ ደረሰ - አጥለቀለቀው!! ያ ጉዳት ሐምሌ 29 ቀን ከሌሊቱ 9 ሰዓት ነው! እጅግ አስከፊ ነበር!!

ህብረተሰቡ መፍትሔ አሻ፡፡ “እንዴት እንከላከል?” ማለት መጣ፡፡ የኢየሩሣሌም የህፃናትና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት (የኢህማልድ) እዚህ ጋ ይመጣል፡፡

ቀደም ብሎ በአካባቢው ላይ ይሠራ ነበረ፡፡ በተወካዮች አማካኝነት ለሱ ጥያቄ ቀረበ፡፡ ኢህማልድ (ጄክዶ) ጥያቄውን በአንክሮ ተቀብሎ በአካባቢው ላይ ጥናት ተጀመረ፡፡ ማህበረተሰቡ ውይይት ጀመረ፡፡ ለሣይቶቹ 200 ሰዎች (800) ለነሱ የawareness (የግንዛቤ ማስጨበጥ) ሥራ ተሠራ፡፡ የመንደር ኮሚቴዎች ተፈጠሩ፡፡

ይቀጥላል

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 8

ኤልያስ

ፖለቲካ በፈገግታ

የሚከራዩ የንግድ ቤቶች• ለክትፎ ቤት፣ ለባር፣ ለካፌና ሬስቶራንት

o በቂ የመኪና ማቆሚያ ግቢ ያለው• ለቡቲክ፣ ለሞባይል መሸጫ፣ ለኤሌክትሮኒክስ፣ ለኮስሞቲክስ… የሚሆኑ

o መጠናቸው የተለያዩ 14 ሱቆች ለኪራይ አዘጋጅተናል ቦታ፡- ከደንበል ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ መዞሪያው ላይ እንዲሁም 22 ረዊና ህንፃ ፊት ለፊት ራህማ ካፌ አጠገብ 40 ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሱቆችም አሉን፤ ከሦስት ወር ከኪራይ ነፃ የማለማመጃ ጊዜ ጋርየኪራይ ሰነዱን ደምበል ላይ በሚገኘው ቢሮ ያገኙታል፡፡

0911-659510 / 0911-524338 / 0911-106316

ሲኒመር ትሬዲንግ አክስዮን ማህበር

ማስታወቂያ

ሕፃን ናኦል፡- አስፋው ፆታ ወንድ ዕድሜ 1 ዓመት ከ1 ወር አድራሻ አዳማ ከተማ ቀበሌ 12 የቤት ቁጥር 474.01፣ አባቱ የማይታወቅ ሲሆን እናቱ ወ/ሮ ሲፈን አስፋው ወደ ማሳደጊያ ያስገባችው ሲሆን በጉዲፈቻ ሊሰጥ ስለሆነ ወላጅ ነኝ የሚል ሰው ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ በመቅረብ ወይም ስልክ በመደወል በ10 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲያደርግ እናሳስባለን፡፡

* * *ሕፃን ቃልኪዳን ግርማ ፆታ ሴት፣ ዕድሜ 1 ዓመት ከ7 ወር፣ አድራሻ አዳማ

ከተማ ቀበሌ 12፣ አባቱ የማይታወቅ ሲሆን፤ እናቱ ወ/ሮ መሠረት ግርማ ወደ ማሳደጊያ ያስገባችው ሲሆን፤ በጉዲፈቻ ሊሰጥ ስለሆነ ወላጅ ነኝ የሚል ሰው ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ በመቅረብ፤ ወይም ስልክ በመደወል በ10 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲያደርግ እናሳስባለን፡፡

* * *ሕፃን ሮቤል፡- ፆታ ወንድ፣ ዕድሜ 1 ዓመት ከ8 ወር፣ መጋቢት 3/2004 ዓ.ም.

ሃዋሳ ከተማ ሐይቅ ዳር ክፍለ ከተማ ጉድማሌ ቀበሌ ልዩ ስሙ ውሃ ልማት እድገት በአንድነት ት/ቤት ጀርባ ተጥሎ የተገኘ በመሆኑ፤ ወደ ሕፃናት ማሳደጊያ የገባና በጉዲፈቻ ሊሰጥ ስለሆነ ወላጅ ነኝ ባይ ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ በመቅረብ፤ ወይም ስልክ በመደወል በ10 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲያደርግ እናሳስባለን፡፡

* * *ሕፃን ቶለሳ ፆታ ወንድ፣ ዕድሜ 1 ዓመት ከ7 ወር፣ የካቲት 20/2004 ዓ.ም.

በምዕራብ ወለጋ ዞን ኖሌ ካባ ወረዳ ቡቤ ከተማ ቀበሌ 02 ተጥሎ የተገኘ በመሆኑ ወደ ሕፃናት ማሳደጊያ የገባና በጉዲፈቻ ሊሰጥ ስለሆነ ወላጅ ነኝ ባይ ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ በመቅረብ ወይም ስልክ በመደወል በ10 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲያደርግ እናሳስባለን፡፡

* * *ሕፃን አሜን፡- ፆታ ሴት፣ ዕድሜ 6 ወር እና ሕፃን ማራናታ ፆታ ወንድ፣ ዕድሜ

6 ወር፣ ጥር 27/2005 ዓ.ም. በምዕራብ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ “የተሽከርካሪ መናሃሪያ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተጥለው የተገኙ በመሆኑ ወደ ሕፃናት ማሳደጊያ የገቡና በጉዲፈቻ ሊሰጡ ስለሆነ ወላጅ ነኝ ባይ ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ በመቅረብ ወይም ስልክ በመደወል በ10 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲያደርግ እናሳስባለን፡፡

አድራሻ፣ ችልድረንስ ሀውስ ኢንተርናሽናል ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 06፣ የቤት ቁጥር 088 መገናኛ ዘርፈሽዋል ት/ቤት ጀርባ

ስልክ ቁጥር 0911-412445፣ 0116-676655 ወይም 0116-676649

እንደኔ አላጋጠማችሁ እንደሆነ አላውቅም እንጂ ኢህአዴግ ሌሊት ሌሊት የምርጫ ቅስቀሳ ጀምሯል (ህገ መንግስታዊ መብቱ እኮ ነው!) እኔን የገረመኝ

ግን ቅስቀሳው ሳይሆን ቀኑን ትቶ ሌሊትን መምረጡ ነው፡፡ (ቀንማ “ቢዚ” ነው!)

ባለፈው ሳምንት ነው፡፡ ሰኞ ወይም ማክሰኞ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ሌሊት ላይ እንቅልፍ እምቢ አለኝና ኢቴቪን ከፍቼ ቁጭ አልኩኝ (ብቸኛ “አጫዋቼ” ነው አላልኳችሁም!) ምናልባት ከሌሊቱ 9 ሰዓት ወይም 10 ሰዓት ገደማ ይሆናል፡፡ ኢቴቪ የኢህአዴግ የሴቶች ሊግ አባላትን የልማት እንቅስቃሴ የሚያስቃኝ ፕሮግራም ማቅረብ ጀመረ፡፡ (“የሴቶች ሊግ” የተሰኘ አዲስ ፕሮግራም ሳይሆን አይቀርም!) በኋላ ሲገባኝ ግን የልማት ሳይሆን የምረጡኝ ቅስቀሳ ነገር ነው፡፡ እኔ የምለው … በህዝብ ንብረት ቅስቀሳ ይቻላል እንዴ? (ኢህአዴግም እኮ የህዝብ ንብረት ነው!)

አንድ ጥያቄ ግን አለኝ፡፡ የ2007 ምርጫ ወደ 2006 ተዛወረ እንዴ? ለቀጣዩ ዓመት ምርጫ ዘንድሮ ቅስቀሳ አይጀምርም ብዬ እኮ ነው! እናላችሁ … በኮብልስቶንና በሌሎች “ደሃ-ተኮር” ስራዎች ላይ የተሰማሩ ሴቶች አስተያየት ሲሰጡ፣ እንደሌላው ጊዜ ስማቸው ወይም የሥራቸው ዓይነት አይደለም

“በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ሙሉ በሙሉ ተከብሯል” - የጋዜጠኞች ማህበራት “በኢትዮጵያ ሚዲያ ላይ ለውጥና ማሻሻያ እናደርጋለን” መንግስት ኢህአዴግ ሌሊት ሌሊት የምረጡኝ ቅስቀሳ እያጧጧፈ ነው!

“የጋዜጠኞች” ማህበራቱን ኢህአዴግ ራሱ ታዝቧቸዋል!

ቲቪ ስክሪኑ ላይ የተጠቀሰው፡፡ ለእያንዳንዱ ተናጋሪ “ሊግ አባል” የሚል መግለጫ (Caption) ነው የተሰጠው። (መቼ የተጀመረች ግልፅነት ትሆን?)

አንደኛዋ የሊግ አባል፤ ኢህአዴግ ከጓዳ (ማጀት) አውጥቶ ለአደባባይ እንዳበቃት ገለፀች፡፡ እሷም ብትሆን በጥቃቅን ሳትደራጅ በፊት ነው የሊጉ አባል የሆነችው፡፡ (ባለውለታ ናት ማለት ነው!) ቀጠለች-ሴትየዋ፡፡ “ለሴቷ አማራጭ ያለው ፓርቲ ነው” ስትል አውራ ፓርቲውን በደንብ አሞካሸችው (በእሷ ዓይን “ሲያንሰው” እኮ ነው!) ትንሽ ቅር ያለኝ ግን ምን መሰላችሁ? አባል ለመሆን መዘግየቷ ነው። “በ2001 ዓ.ም ነው አባል የሆንኩት” ብላናለች፡፡ (ያን ሁሉ ዓመት የማን አባል ነበረች?) በነገራችሁ ላይ …ከሴቶች ሊግ አባላት ውስጥ 99 በመቶ ያህሉ በሥራ ላይ የተሰማሩ (employed ወይም self employed) ሲሆኑ በቅርቡ አንድም ሥራ አጥ (zero unemployment) የሊግ አባል እንደማትኖር የሊጉ ሊቀመንበር ተናግረዋል፡፡ (ልብ አድርጉ! “አንድም የሊግ አባል” ነው የተባለው!)

በነገራችሁ ላይ … ሊጉ የሚመራው “ሰጥቶ መቀበል” (ፈረንጆቹ Give and take ይሉታል) በሚለው መርህ ነው፡፡ በአበሽኛ “እከክልኝ ልከክልህ” የሚባለው መሰለኝ፡፡ እናላችሁ … የሊጉ አባላት በ2002 እና በአካባቢና ማሟያ ምርጫዎች ኢህአዴግን በመምረጥ ብቻ ሳይሆን እንዲመረጥ በመቀስቀስም ለፓርቲያቸው ያላቸውን የማይናወጥ “ታማኝነት” አሳይተዋል ብላለች - የሴቶች ሊግ

ሊቀመንበሯ፡፡ (ካላሳዩማ አለቀላቸው!) እኔ የምለው … የሊግ አባል የመሆን ዕድል ላላገኙ

የጦቢያ ሴቶች የሥራ ዕድልና ብድር የሚሰጣቸው ማነው? (ጥያቄ እኮ ነው!) እንደው ለጨዋታ ያህል ነው እንጂ… በኢቴቪ በውድቅት ሌሊት የተላለፈው የሴቶች ሊግ የምርጫ ቅስቀሳ ምንም ክፋት የለውም (አሳቻ ሰዓት ከመቅረቡ በቀር!) የሊጉን ቅስቀሳ ኮምኩሜ ልተኛ ስል ግን አንድ ሃሳብ መጣልኝ። “Drink Responsibly” ወይም “በሃላፊነት ስሜት ተጐንጩ” የሚለውን የቢራ ማስታወቂያ ታውቁታላችሁ አይደል? ኢህአዴግን ጨምሮ ሁሉም የጦቢያ ፓርቲዎች ራሳቸውን ሲያስተዋውቁና ሲቀሰቅሱ “Support Responsibly” ወይም “በሃላፊነት ስሜት ይደግፉ!” የሚል ማስታወቂያ ቢያክሉበት አልኩ-ለራሴ፡፡ (እንዴ … የፖለቲካ የአልኮል መጠን እኮ ከቢራ የአልኮል መጠን በብዙ እጅ ይልቃል፡፡)

እኔ የምለው … ባለፈው ሳምንት በአፍሪካ ህብረት የተካሄደውን የአፍሪካ ሚዲያ መሪዎች ፎረም እንዴት አያችሁት? የአፍሪካ ነገር ሁሌ ችግሯን ሁሉ በፈረንጆቹ ላይ ማላከኳ አናደደኝ እንጂ ጋዜጠኞቹ መወያየታቸውና መወቃቀሳቸው የሚበረታታ ነው። አንድ ቀን ከምዕራባውያን ላይ ወርደው ራሳቸውን መቻላቸው አይቀርማ! የእኔን ትኩረት የበለጠ የሳበው ግን ጉባኤው እንዳይመስላችሁ! በፎረሙ መጠናቀቂያ ላይ ሦስት የጦቢያዋ “የጋዜጠኞች ማህበራት” ያወጡት “ድንቅ” የአቋም መግለጫ ነው። (ሦስቱ ማህበራት ለኢትዮጵያ ብቻ ነው ወይስ ለሶማሊያም?) እናላችሁ … የማህበራቱ መግለጫ የጋዜጠኞች ሳይሆን የ“አብዮታዊ መንግስት” ወይም “ድርጅት” ነበር የሚመስለው፡፡ ከአቋም መግለጫቸው መካከል አንደኛው ደግሞ ከኢህአዴግ ቃል በቃል የተኮረጀ ነው (ኮማ ሳይቀር!) ልዩነቱ ምን መሰላችሁ? ኢህአዴግ በተደጋጋሚ “በኢትዮጵያ ውስጥ ከሙያቸው ጋር በተያያዘ የታሰሩ ጋዜጠኞች የሉም” የሚል ምላሽ ሲሰጥ ደንፍቶ አያውቅም። እነሱ ግን ቀላል ቀወጡት! አገር ይያዝልን እኮ ነው ያሉት፡፡ ቦታው ስላልተመቻቸው ነው እንጂ ሽለላና ቀረርቶ ሁሉ ዳድቷቸው ነበር፡፡ (ኢህአዴግ ራሱ እኮ ሳይታዘባቸው አይቀርም!) እኔማ ምነው በገመገመልኝ ብዬ ነበር፡፡ ለካስ የኢህአዴግ አባል አይደሉም (ናቸው እንዴ?)

የጋዜጠኞች ማህበራቱ ሁለተኛው የአቋም መግለጫ ደግሞ “በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ከየትኛውም የአፍሪካ አገራት የበለጠ ተከብሯል” የሚል ነው፡፡ ይሄኛውም በድንፋታና በጩኸት የታጀበ ነበር፡፡ ይሄን የሰሙ የአፍሪካ ጋዜጠኞችና የሚዲያ መሪዎች አገራቸው እስከሚገቡ እንዴት እንደሚቸኩሉ አልታያችሁም? (ለመሳቅ እኮ ነው!) እንኳን እነሱ ኢህአዴግም ይሄኔ በመግለጫው ፍርስ ብሏል (አይነግረንም እንጂ!) እውነቴን እኮ ነው … መንግስት ራሱ “በአገራችን የፕሬስ ነፃነት ሙሉ በሙሉ ተከብሯል” ብሎ አያውቅም፡፡ (ከየት

አመጡት ታዲያ?) በነገራችሁ ላይ … የአፍሪካ ሚዲያ መሪዎች ፎረም መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ … መንግስታቸው፤ በኢትዮጵያ ሚዲያ ላይ ለውጥና ማሻሻያ እንደሚያደርግ ተናገሩ እንጂ “የፕሬስ ነፃነታችን እንከን የለሽ ነው!” ብለው አልተመፃደቁም፡፡ “ዲሞክራሲውም … ነፃ ፕሬሱም … የሰብአዊ መብት አያያዙም ወደፊት ከልማቱ ጋር እየተሻሻለ ይሄዳል” ነው - የኢህአዴግ አቋም፡፡ (“ከጳጳሱ በላይ አማኝ” አሉ!) የጋዜጠኞች ማህበራቱ ጉዳይ በዚሁ ቢያልቅ “ተመስገን” ነበር፡፡ ባለፈው ሳምንት ምሽት ደግሞ “የነፃ ጋዜጠኞች ማህበር” ፕሬዚዳንትና ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ ይሄንኑ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያብራሩ ተጋብዘው ነበር - በኢቴቪ፡፡

የሚገርመው ታዲያ የምሽቱ አጀንዳ “በኢትዮጵያ የታሰሩ ጋዜጠኞች አሉ የሉም” ወይም “የፕሬስ ነፃነት ተከብሯል አልተከበረም” የሚለው አልነበረም። የአገር ሉዓላዊነት ማስከበር፣ አንድነትና ነፃነትን ማስጠበቅ ወዘተ … ሆነና አረፈው (የአቋም መግለጫ በማውጣት “አርበኝነት” የለም እኮ!)

የኢቴቪ ጋዜጠኛው (ጋባዡ ማለት ነው) ታደሰ ሚዛን፤ ለጋዜጠኞች ማህበሩ ፕሬዚዳንት አስገራሚ ጥያቄ አቀረበ (ሃሳቡን እንጂ ቃል በቃል አይደለም!) “በቀጣይ እንደ CPJ ያሉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ነን ባዮች ‘በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ታስረዋል፣ የፕሬስ ነፃነት ታፍኗል’ እያሉ የሚያወጡትን መግለጫ እንዴት መከላከል ይቻላል?” ፕሬዚዳንቱም አስገራሚ ምላሽ ሰጠ፡፡ “ፅናትና መስዋዕትነት ይጠይቃል” በማለት፡፡ የምን ፅናት ነው? የምንስ መስዋዕትነት? እውነቱን መናገር እኮ በቂ ነው - እንደ ኢህአዴግ፡፡ (እውነት አንፃራዊ መሆኗ እንዳይረሳ!)

ሁለቱን ጋዜጠኞች ወይም የ “ነፃ ጋዜጠኞች” ተወካዮች በኢቴቪ የጋበዘው ጋዜጠኛ፤ አንድ ነገር ግን ሳይሸወድ አልቀረም፡፡ (“አውቆ በድፍረት ሳያውቅ በስህተት” ሊሆን ይችላል!) ምን መሰላችሁ? የጋዜጠኞች ማህበራት ያወጡትን መግለጫ፣ የአገርን አንድነት (ዳር ድንበር) እንደማስከበር ነው የቆጠረው፡፡ (በአቋም መግለጫ “አንድነት” ተከብሮ አያውቅም እኮ!) እናም … ማህበራቱ ወደፊትም ተመሳሳይ መግለጫ በማውጣት የአገሪቱን አንድነት ለማስጠበቅ ይጥሩ እንደሆነ ጠየቀ - ወደ ውይይቱ መጠናቀቂያ ላይ፡፡ (ወይ ፍሬን መበጠስ!) መልሱም “ፍሬን የበጠሰ” ስለሆነ ትቼዋለሁ፡፡

አንድ ጥያቄ አለኝ፡፡ ሦስቱ የጋዜጠኞች ማህበራት ዓላማ ምንድን ነው? (የጋዜጠኞችን መብት ማስከበር እንዳይሉኝ ብቻ!) “ኢህአዴግ ማረኝ” ማለት ይሄኔ ነው፡፡ (“የባሰ አለና አገርህን አትልቀቅ” አሉ!)

እናንተ … እኔም ፖለቲካዊ ወጌን በአቋም መግለጫ ልቋጨው ዳድቶኝ ነበር፡፡ (አንድዬ እኮ ነው ያዳነኝ!) በሉ ሰሞኑን በቴክስት የደረሰኝን “ቧልት” ላካፍላችሁና ልሰናበት፡-

“ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ዕቅድ ጉባኤ ላይ የተሳተፈችና የቡራዩን የስነ ተዋልዶ ጤና ኤክስቴንሽን የጐበኘች አንዲት አሜሪካዊት፣ በተለይ ለኢቴቪ በሰጠችው ቃለ ምልልስ፤ ‘ምነው እኔም ኢትዮጵያ ውስጥ በወለድኩ’ ስትል አድናቆቷን ገለፀች” (ማንም ምንም ቢል የምዕተ ዓመቱ የልማት ግብ እንደሆነ መሳካቱ አይቀርም!!)

ድል ለዋልያዎቹ!!

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 9 ህብረተሰብ

ማስታወቂያ

የዘመን ንቅሳቴን እጮኻለሁ!ከዮሐንስ ገ/መድኀን

ዘመን ወደ ገፅ 21 ዞሯል

ሰውዬው ጢማቸውን ማሳደግና ዘወትር ማለዳ ተነስተው እርጐ መጐንጨት ያዘወትራሉ፡፡ ታዲያ ማለዳ ማለዳ እርጐውን ተጐንጭተውና አጣጥመው

እንደጨረሱ አፋቸውን ሲጉመጠመጡ፣ ከላይኛው የከንፈራቸው ጢም ውስጥ ሰርገው የሚቀሩትን የእርጐ ፍንጣቂዎች ይረሷቸዋል፡፡ ከአፍንጫቸው ሥራ የተረሱት እነዚያ የእርጐ ፍንጣቂዎች መዋል ማደር ሲጀምሩ ጠረናቸው እየተለወጠ የሚፈጥሩት ሽታ ጤና ነሳቸው፡፡ አንድ ቀን ማለዳ ላይ ባለቤታቸውን፡-

“እዚህ ቤት የሞተ ዐይጥ አለ እንዴ?” “ከመቼ ወዲህ አንቱዬ?” “ታዲያ የሚሸተኝ ምንድን ነው? … የለ … የለም

እዚህ ቤት የሞተ ዐይጥ አለ! ያውም የከረመ! … በይ የቤቱን ዕቃ በሙሉ እያወጣሽ ቤቱን አፅጂው!” ቀጭን ትዕዛዝ ያስተላልፋሉ፡፡

“ካሉ ደግ አፀደዋለሁ”“በይ አሁኑኑ ጀምሪ! እስተዚያው እኔም ዘወር

ዘወር ብዬ ልምጣ!” ሰውየው ምላሽ ሳይጠብቁ ከዘራቸውን አንስተው ይወጣሉ፡፡ ነገር ግን ሰውዬው በየሄዱበት ቦታ ሁሉ ያ መጥፎ ጠረን ይከተላቸው ጀመር፡፡ እዚያ ቢሄዱ እዚህ ቢመጡም ያው ሆነባቸው፤ ወደቤታቸው እያዘገሙ ሳለ ሰውዬው እንዲህ አሉ፡- “ዛሬስ የኔ ቤት ብቻ አይደለም፤ አገሩ ሁሉ ገምቷል!”

* * *የአንድ ዘመን ማሕበረሰብ ባህል፣ አስተሳሰብና

የሚከተለው የፖለቲካ ሥርዓት በየግለሰቡ መልካም

ስብዕና ላይ አሉታዊ ጫና ያሳድራል፡፡ በእያንዳንዱ ግለሰብ መልካም ስብዕና ላይ የየዘመኑ ሥርዓት የሚፈጥረው ዕድፍ እየተለመደ፣ ከእያንዳንዱ ማንነት ጋር ሲዋሀድ ያኔ ብክለቱ ይጀምራል፡፡ ይህን በተመለከተ የፖለቲካ ሳይንሱ ምሁር ካርል ማርክስ ሲናገር፡-

“አንድን ሥርዓት ለመጣል ሃያና ሰላሳ ዓመታት መታገል ያስፈልግ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከሥርዓቱ ዕድፍ ለመላቀቅ መቶና ከዚያም በላይ ዓመታት መታገል ያስፈልጋል፡፡”

ትናንት ከትናንት በስቲያና ዛሬ በኛ ማሕበረሰብ ውስጥ የተቀያየሩ የፖለቲካ ሥርዓቶች ያሸከሙን ዕድፍ ጠባሳው ሳይሽር ቁስሉ እያመረቀዘ አላራምድ ብሎናል፡፡ ትናንት ያረፈብን ዱላ ዛሬ ቀና ብለን እንዳንራመድ አስጐንብሶናል፡፡ የኛ ማሕበረሰብ የፖለቲካ ሥርዓቶች ያሸከሙን ዕዳ ምን ይመስላል?

የትናንት በስቲያው በአንድ አጋጣሚ ከአንድ ወጣት ጋር ተገናኝተን

ስናወጋ ያጫወተኝን ላካፍላችሁ ወደድሁ፡፡ የግል ሕይወቱን በተመለከተ እንዲህ ነበር ያወጋኝ፡፡

“አራት ወንድሞቼና ሁለት እህቶቼን ጨምሮ ከእናታችን ጋር ስምንት ሆነን ቀበሌ በሰጠን አንድ ክፍል ቤት ውስጥ እንኖራለን፡፡ አባታችን ወታደር ነበር፡፡ በሰሜኑ ጦር ግንባር ለረዥም ጊዜ ቆይቷል። ኢህአዴግ አዲስ አበባ ከገባ ጊዜ ጀምሮ ብዙዎች ሲመለሱ የኛም አባት ይመለስ ይሆናል እያልን በተስፋ በር በሩን እያየን ስንጠብቅ ከረምን፡፡ እስከ አሁን ድረስ በሕይወት ይኑር ወይ ይሙት የምናውቀው ነገር የለም፡፡ እማዬ እንጀራና አምባሻ እየሸጠች ነው የምታስተዳድረን፡፡ ያገኘነውን ተካፍለን ከጠፋም ቆሎ ቆርጥመን እናድራለን፡፡ እኔና ታናሽ እህቴ 12ኛ ክፍል ጨርሰናል፡፡ ውጤት ግን አልመጣልንም፡፡ የሁሉም ታላቅ እኔ በመሆኔ የእማዬን ድካም እያየሁ በዝምታ መቀመጥ አልቻልኩም፡፡ እንደምንም ተሯሩጬ ታናሽ እህቴን ኬክ ቤት አስቀጠርኳት፡፡”

“አንተስ?” አልኩት ንግግሩን አቋርጬ “ሥራ ለማግኘት ብዙ ጣርኩ፡፡ አልተሳካልኝም

ነበር፡፡ የኋላ ኋላ በአንድ የእንጨት ሥራ ድርጅት ውስጥ ሥራ አገኘሁ፡፡ ተመስገን ብዬ ሥራ ጀመርኩ። ከሶስት ወር በኋላ ግን ድርጅቱ ተዘጋ፡፡”

“ለምን?” “የድርጅቱ ባለቤት ከሰርኩ አለ” “ከዚያስ ሌላ ቦታ አልሞከርክም?” “ለብዙ ጊዜ ሥራዬ ሥራ መፈለግ ብቻ ሆነ።

ነገር ግን አልቻልኩም፡፡ አንድ ቀን ቁጭ ብዬ ሳሰላስል በአካባቢዬ የማያቸው የጉራጌ ብሔረሰብ ተወላጆች ለሥራ ያላቸው ታታሪነት ታሰበኝ፡፡ ሥራ ሳይንቁ ሊስትሮ ሆነው ይጀምሩና ከጥቂት ዓመታት በኋላ ሱቅ ከፍተው ታገኛቸዋለህ፡፡ እኔስ ለምን በሊስትሮነት አልጀምርም? ብዬ አሰብኩኝ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ራሴን ብችል እማዬን አገዝኳት ማለት ነው፡፡ ታናሽ እህቴ ኬክ ቤት ትሠራለች ብዬሃለሁ፡፡”

“እኔ ራሴን ከቻልኩ ለእማዬ ሁለት ሆድ ተቀነሰላት ማለት ነው”

በአነጋገሩ ፈገግ አልኩ፡፡ “የሊስትሮነት ሥራዬን ለመጀመር ግን የሠፈሬን

ሰዎችና የጓደኞቼን ሽሙጥ በመፍራት ብዙ አቅማማሁ፡፡ የኋላ ኋላ ስለ እማዬ ሳስብ ቶሎ ለመጀመር ወሰንኩ”

“ስለ እማዬ ሳስብ ነው ያልከኝ?” “አዎና! እማዬ ድንገት አንድ ነገር ብትሆን፣

ብትታመምብኝ ወይም አያድርገውና ብትሞትብኝ ፀፀቱን አልችለውም ብዬ ጫማ መስፋት ስለምችል፣ ከሊስትሮ ሥራ ጋር ደርቤ እዚያው ከሠፈራችን ጀመርኩ፡፡”

“እንዴት ነው ተሳካልህ?” አልኩት ጥንካሬውን እያደነቅሁ

“ምን ይሳካል ብለህ … በሁለተኛው ቀን ተቋረጠ።”

“ለምን?”

“ሥራውን እንደጀመርኩ በሁለተኛው ቀን እማዬ እየተንደረደረች መጣችና፡-

“አንተ የማትረባ! ብለህ ብለህ ተከብሬ በኖርኩበት ሠፈር ልታዋርደኝ ተነሳህ? … ይኸው ነው የቀረህ! … ምንም ብደኸይ … ምንም ጊዜ ቢጥለኝ … እ … የነማን ዘር መሰልኩህ! አንተ ዘር አሰዳቢ! … የፅጌ ልጅ ሊስትሮ ሆነ ብሎ አገር እንዲስቅብኝ ነው? … ቆሜ ነው ሞቼ!”

“እማዬ እንደዚያን ዕለት በንዴት ስትቃጠል አይቻት አላውቅም፡፡ የሊስትሮ ሳጥኔን ሰባበረቺውና አምባሻ ጋገረችበት እልሃለሁ! … አይ እማዬ በዚያች የሊስትሮ ሳጥን ስባሪ ስንት አምባሻ ጋግራበት ይሆን?” አለኝ ፈገግ ብሎ፡፡ ፈገግታውን አልተጋራሁትም፡፡

የትናንትናውስ? ያኔ … የሰለሞናዊው ዘውድ ሥርዓት ማክተሚያ

ሲቃረብ፣ ዳር እስከዳር የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ አመፅና የተማሪዎች የለውጥ ትግል ተጠቅሞ ወታደራዊው ደርግ በትረ-ሙሴውን ጨበጠ። ጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት እስከሚቋቋም በጊዜያዊነት የሥልጣን መንበር ላይ የወጣው ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት፤ “የነቃ፣ የተደራጀና የታጠቀ የሕዝብ ክፍል የለም” በሚል ሰበብ የጣመውን የሥልጣኝ መንበር ቀስ በቀስ እያመቻቸ መሠረቱን ማጠናከር ያዘ፤ “ኢትዮጵያ ትቅደም” በሚል መፈክር መሪነት፡፡ “ያለምንም ደም እንከኗ ይውደም በቆራጥ ልጆቿ ኢትዮጵያ ትቅደም” በሚል ዜማ፣ የለውጥ ፈላጊውን ስሜት ሊያረግብ ጣረ፡፡ በወቅቱ የነበረው ወጣት ትውልድ፣ በራሱ የሚተማመን ነበርና ይህን ወታደራዊ ብልጠት በዝምታ ሊያልፈው አልፈቀደም፡፡ አመፃቸውን ቀጠሉ፡፡ “ጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት አሁኑኑ!” እያሉ ጮኹ። ወታደራዊው መንግሥት እየጣፈጠው የመጣውን ሥልጣን ላለመነጠቅ ፈራ፡፡

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 10

ከሳኡዲ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

አበሻ ቤት ወደ ገፅ 15 ዞሯልወርቅ ቤት ወደ ገፅ 15 ዞሯል

ህብረተሰብ

አበባየሁ ገበያው

ሰሞኑን በህገወጥ መንገድ ሳኡዲ አረቢያ ከገቡ ብዙ ሺ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች መካከል ዓለም አቀፍ የስደተኞ ተቋም ከ350 በላይ የሚሆኑትን ወደ አገራቸው መልሷቸዋል፡፡ ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው በተቋሙ መጠለያ ጣቢያ ያገኘቻቸውን ሦስት ተመላሾች አነጋግራለች፡፡

ስምህ ማን ነው ?እንድሪስ መሃመድ፡፡እድሜህ ?ሀያ ዓመት ሆኖኛል፡፡ ወደ ሳኡዲ አረቢያ እንዴት ሄድክ ?ገና የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ከጓደኞቼ ጋር መከርን፡

፡ ለምን እንደሌሎች ጓደኞቻችን ሳዑዲ አንሄድም አልን፡፡ ሳኡዲ ሄደው ለወላጆቻቸው ባጃጅ ስለገዙ፣ ቆርቆሮ ቤት ስለሰሩ፣ ንግዱን ስለሚያጧጡፉ --- የአካባቢያችን ልጆች ካወራን በኋላ ለመጓዝ ወሰንኩ፡፡ ለደላላ አራት ሺህ ብር ከፍዬ በእግሬ ዘጠኝ ቀን ተጉዤአለሁ - ባህር ድረስ፡፡ በመጨረሻ ሳኡዲ የገባሁትም በእግሬ ነው፡፡

መንገድ ላይ ችግር አልገጠማችሁም ?.እሱ እንኳን ስቃይ ነበረው፡፡ የመን ድንበር ላይ ተኩሰውብን፣

ግማሾቹ ሲያዙ ግማሾቻችን አመለጥን፡፡ ሳኡዲ ከገባህ በኋላ ሥራ አገኘህ ?አዎ የፕላስቲክ ማምረቻ ውስጥ ነበር የምሰራው፣ ፕላስቲክ ሰሃን፣

ፕላስቲክ ወንበር --- እነሱን ቅርፅ ማስያዝ ነበር የእኔ ሃላፊነት፡፡ ገንዘብ ለቤተሰብ ትልክ ነበር ?አዎ---በወር 2ሺ ሪያድ እልክ ነበር፡፡ እሱስ የድካሜን ያህል

ኮምቦልቻ ቦታም ገዝቻለሁ፡፡ እድሜ ለሳውዲ---.ያጠራቀምኳትን እየበላሁ ወጥሬ እሰራላሁ፡፡

አሁን እንዴት ነው የመጣኸው ?ተይዤ ነው የመጣሁት፡፡ በመገናኛ ብዙኃን ብዙ ኢትዮጵያኖች ስቃይ ላይ እንደሆኑ ተዘግቧል

---ከተማው ሰፊ ስለሆነ እዚህ ለቅሶ እዚያ ጩኸት ነው፡፡ እኔ

አልተመታሁም ግን ሰምቻለሁ---በአይኔም አይቻለሁ፡፡ እስር ቤት ደግሞ መከራውና እንግልቱ ከባድ ነው፡፡ ጃዋዛ (ወታደሮች) እየጠረነፉ እስር ቤት ያስገቡ ነበር፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት እየተሰቃዩ ናቸው፡፡

አንተም ታስረህ ነበር ?.አዎ--- ወር ከሶስት ቀንከአሁን በኋላ ተመልሰህ መሄድ ትፈልጋለህ ?በቃኝ ካላስ፡፡

ስሜ እንድሪስ የሱፍ ይባላል፡፡ ትውልዴ ሃይቅ ነው፡፡ ወደ ሳኡዲ የሄድኩት ትንሽ ለውጥ ፈልጌ ነበር፡፡ በጅቡቲ በኩል ነው የሄድኩት- በባህር፡፡ ጅቡቲን የሚያሳልፈን መሪ ነበረን፡፡ ያውም እኮ የመጨረሻ ልጅ ነኝ፡፡ አባቴም እናቴም እያለቀሱ ነው የሰደዱኝ፡፡ የእነሱ እንባ ነው መሰለኝ አላስቆም አላስቀምጥ ብሎኝ ነበር፡፡

ጉዞው እንዴት ነበር?ምን ትያለሽ? ድካሙንማ ተይው! ወንድም ሴትም በየመንገዳችን

ስንቀብር ነበር፡፡ እየደከማቸው ሲወድቁ እየጣልናቸው ነው የሄድን። ባህር ድረስ ዘጠኝ ቀን ነው የፈጀብን፡፡ ለታመሙት እንኳን ውሃና ምግብ እንዳንሰጥ እልም ያለ በረሃ ነው፡፡ ሁላችንም ደግሞ ስንቃችንን ጨርሰናል፡፡ እኔ በበኩሌ የራሴን ነፍስ ማትረፍና ወርቅ እና ገንዘብ

ይታፈስበታል ከተባለው አገር--- ሳኡዲ መድረስ ነበር የማስበው፡፡ ወርቅና ገንዘብ እንደሚታፈስ ማን ነገረህ?እዛ የሄዱ ጓደኞቼ ሲደውሉሉኝ፣ ገንዘብ ለቤተሰቦቻቸው--

ለወገኖቻቸው ሲልኩ ሳይ እየተጎመጀሁ መጣሁ፡፡ ከዛ የመጣው ይምጣ ብዬ በረሃና ባህር ተሻግሬ ሄድኩ፡፡

ግን በህጋዊ መንገድ መሄዱ አይሻልም ነበር?አይ አንቺ! በህጋዊ መንገድ የሄዱትስ ብትይ የትኛው ክብር

ሲኖራቸው ..በባህር ሄድሽ በአየር ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ እስር ቤት አብረውኝ ሲማቅቁ የነበሩት እንደኛ ያሉት ብቻ መሰለሽ---በፓስፖርት በአየር ሄደውም እኮ ዋጋቸው የኛን ያህል ነው፡፡

ሁለት ሺህ ብር ከፍዬ ጅቡቲ ተሰብስበው ከሚጠብቁ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመርከብ ተሳፍረን ስንሄድ የነበረውን ድካም፣ የዘጠኝ ሰዓት ጉዞ ውስጥ የነበረውን ሰቆቃ---አልነግርሽም፡፡ ማዕበል ተነስቶ --- ጀልባዋ ልትደፋን ደርሳ --- ብታይ ልትጨርሰን፡፡ የመን ወደብ ስንደርስ መሸዋት ከተባለች ስፍራ በመኪና ተጭነን ተጓዝን፡፡ ግን የየመን ፖሊሶች አግኝተውን ቀጠቀጡን፡፡ ‹‹ጅዳ ወይንም ሌላ አገር ደውላችሁ ገንዘብ ሃዋላ አስደርጉ›› ብለው ደበደቡን፡፡ ደሞ ሴቶችን ሶስት አራት ሆነው ነው የሚደፍሩዋቸው፡፡

ከየመን ወደብ ተነስተህ እንዴት ሳኡዲ ወደብ ደረስክ?ገንዘብ ያላቸው ከፍለው ነው በመኪና የሄዱት፡፡ እኔ ግን ገንዘብ

አብዱ እንድሪስ እባላለሁ፣ ከኮምቦልቻ ተነስቼ ከጓደኞቼ ጋር

ነው የሄድኩት---መንገዳችን ጥሩ ነበር፡፡ የመን ከዛም ሳኡዲ ደረስን። ከስምንተኛ ክፍል ነው የሄድኩት..ቤተሰቦቼ ድሆች ነበሩ --- የእነሱን ችግር እያየሁ መቀመጥ አላስቻለኝም፡፡

ስንት ጊዜ ቆየህ ሳኡዲ? አስር ወር ቆይቼ ነው የመጣሁት፡፡ አምስቱን ወር በእስር ቤት፣

አራት ወር ጎዳና ተዳዳሪ ሆኜ ስንከራተት---አንድ ወር ብቻ ነው ተቀጥሬ የሰራሁ፡፡

ምን ነበር የምትሰራው?በግ እጠብቅ ነበር፡፡ ደሞዜ ስምንት መቶ ሪያድ ነበረ፡፡

ደሞዜ እንደነገ ሆኖ እንደዛሬ ፍተሻ ሲያደርጉ አገኙኝና ወሰዱኝ፣ አምልጫቸው ጎዳና ለጎዳና ስንከራተት---መንገድ ለመንገድ ስተኛ-- በመጨረሻ ምግብ እየለመንኩ መኖር ጀመርኩ፡፡ ለማኝ ነበርኩ፡፡

አራት ወር ጎዳና ተዳዳሪ ሆነህ ምግብ የሚሰጥህ ማን ነበር?በህጋዊ መንገድ የመጡ የእኛ ሴቶች አሉ፣ ሥራ የሚሰሩ፡፡

አልፎ አልፎ ምግብ ደብቀው ይሰጡኛል፡፡ ሴቶችም ወንዶችም ብዙ ጎዳና ተዳዳሪዎች አሉ፣ ብዙ እብዶችም አሉ፡፡ ቆም ብለሽ ዞር ስትይ ኢትዮጵያዊ ለማኝ፣ ጎዳና ተዳዳሪ፣ እብድ---አለ በየመንገዱ፡፡ አንዳንዴ ፖሊሶች ከመንገድ አንስተው ያስራሉ፡፡

አንተም ጎዳና ላይ ተገኝተህ ነው የታሰርከው?አምስት ወር ሙሉ በእስር ቤት ነበርኩ፡፡ እስርቤቱ እንዴት ነበር

ብለሽ እንዳትጠይቂኝ--ማስታወስ አልፈልግም፣ ያመኛል፡፡ ዱላውንና ድብደባውን..ማንጓጠጡንና ማንቋሸሹን…አልነግርሽም፡፡ ግን የሰው ዘር ናቸው? እኔ አላውቅም፡፡ ኢትዮጵያኖች እኮ እስር ቤት ሁሉ ይሞታሉ፡፡ ረሃብማ ተይው፡፡ እንኳን ብቻ ለአገራችን አበቃን፡፡

ቤተሰብህ ያለህበትን ሁኔታ ያውቅ ነበር?እንደገባሁ ደውዬ ነበር፡፡ ከዛ ግን አስር ወር ሙሉ የት እንዳለሁ

--- ልሙት ልዳን የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ አሁንም ዝም ብዬ ነው ተሳፍሬ የምሄደው፡፡

በአሁኑ ሰዓት ሳኡዲ ውስጥ ኢትዮጵያኖች እየተንገላቱ ነው ይባላል..

“ሳኡዲ ወርቅ እየዘነበ ነው ቢሉኝ አልሰማም”

“ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት እየተሰቃዩ ናቸው”

“አበሻ ለእነሱ ርካሽ እቃ ማለት ነው”

አብዱ እንድሪስ እንድሪስ መሃመድ እንድሪስ የሱፍ

ፎቶ

አንተ

ነህ አ

ክሊሉ

ፎቶ

አንተ

ነህ አ

ክሊሉ

ፎቶ

አንተ

ነህ አ

ክሊሉ

ፎቶ

አንተ

ነህ አ

ክሊሉ

Website: www.addisadmassnews.com

ገፅ 11 አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

ፊደል ቤት ወደ ገፅ 17 ዞሯል

ህብረተሰብ

ማስታወቂያ

እንደገና ፊደል እንደገና ---- የሞክሼ ፊደላት ጉዳይ!

ሰሎሞን አበበ ቸኮል[email protected]

solomon.abebe.395@facebook

“እንደገና ፊደል እንደገና” የሚያሰኘን እያረፈ የሚነሳው የፊደል ማሻሻል ጥያቄ ጉዳይ ነው። ጥያቄውን የሚያነሱት ምሑራን ምክንያታቸው ምንድነው? በተለይ ጐልቶ የሚነሳው

የሞክሼ ፊደላት ጉዳይ ነው፤ እነዚህንስ መነካካቱ ያስፈለጋቸው ለምንድነው የሚለውን በቅድሚያ መመልከቱ ተገቢ ይመስላል፡፡ ከሞክሼዎቹ የተወሰኑትን የማስወገዱ እርምጃ የሚያስከትለውን ጉዳት/ጉድለት ደግሞ ከዚያ በኋላ እንመለከተዋለን፡፡

አሁን እስኪ ሞክሼ ፊደላቱን ለማጉደል ምን ምን ዓይነት ምክንያቶች እንደሚሰሙ እያነሳን እንመልከት- አንድ ድምጽ፣ አንድ ምልክት

ትክክል፡፡ አንድ ምልክት አንድን ድምጽ ወይም ክፍለ ቃል፣ አንድ ክፍለ ቃልም በአንድ ምልክት መወከል አለበት፡፡ ማንም ሊገምት እንደሚችለው፣ እነዚህ ምልክቶችም እያንዳንዳቸው አንድን ድምጽ ለመወከል የተሠሩ ናቸው፡፡ ብዙዎች አንዱን ድምጽ ሊወክሉ አልተሠሩም፡፡ በእርግጥም አልነበሩም፡፡

እንዲህ የሆነው ከጊዜ በኋላ ነው፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ከአባ ሰላማ ወዲህ ነው ይላሉ፡፡ ግን አይደለም፡፡ ከዚያ ወዲህ፡፡ ቢያንስ በጽሕፈት ላይ ሲቀያየሩ አይታዩም፡፡ ድምፃቸው አንድ ኾነ ተብሎ በጽሕፈትም የአንዱን ለአንዱ ማድረግ ይታይ ነበረ፡፡ ከዚህም ሌላ በአባ ሰላማ ጊዜ ኅርሙኅ ተጨምሯል።

እነዚያ አንድ እየኾኑ ይሕን ይጨምራሉ አይባልም። ደሞም የዚህኛውም ድምጽ አንድ ሆኖ ተገኝቷልና በአባ ሰላማ ጊዜ ሲጨመርም አንድ ድምጽ ይዞ ተጨመረ ማለትን ይመስላል፡፡

በሚገባ የታወቀው ይህ የድምጽ አንድነት የታየው፣ በመጽሐፈ ጥበብ እንደተገለፀው፣ ከልብነ ድንግል ዘመን ወዲህ ነው፡፡ የአምስት መቶ ዘመን ዕድሜ አለው ማለት ነው፡፡ በዚሁ መጽሐፍ የየራሳቸው ድምጽም ተመዝግቧል፡፡ ፍሬ ነገሩ ግን ድምፃቸው በግዴለሽነት ተመሳሰለ ብሎ እንዲወገዱ መጠየቅ አለበት ወይ? የሚለው ይሆናል፡፡ ይህ ምልክቶቹን ድምጽን ለመወከል የተሠሩ በማድረግ፣ ሥነ ልሣናዊ ዕቃዎች ብቻ በማድረግ፣ ስንፍናን እና ጉድለትን በጉድለት መተካትና ማረም፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ምልክቶቹ ያላቸውን ሌሎች አገልግሎቶችና ውክልናዎች እንዳሉ መጣል መሆኑን ካለማየት የሚመጣ ጥያቄ ነው፡፡ በአጭሩ፣ የሰነፍ፣ የደካማና የታካች አቋራጭ መንገድ ነው፡፡ የፊደላት ብዛት

የፊደላት ብዛት ጥያቄ የሚነሣው ይበልጡን በአጠቃላይ ፊደሉን ከመነካካት ጥያቄ ጋር ነው። ከሞክሼ ፊደላት አንጻር አይደለም፡፡ ምናልባት “ፊደሉም ብዙ ምልክቶች ያሉት ነውና ሞክሼዎቹ ሲቀነሱ ያነንም ጥያቄ ይመልስልናል” በሚል ግንዛቤ እንደ አንድ ነጥብ ይነሳ ይሆናል፡፡ ከዚህ ውጭ ፊደሎቹ የበዙት አንዱን ድምጽ የሚወክሉ ከአንድ በላይ የሆኑ ፊደላት ስላሉ ነው የሚል የለም፡፡

እዚህ ላይ ግን ጠቅላላ በፊደል ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችንም ለመመልከት ያህል አንስተነዋል፡፡

የፊደል ብዛት ጥያቄ በአማርኛም ሆነ በግዕዝ የሚጠየቀው ፊደላቱን ካለመለየት የተነሣ ነው።

ፊደላት የገበታ እና የርባታ ተብለው ይለያሉ። የየትኛውም ቋንቋ ፊደል ምን ያህል እንደሆነ ሲጠየቅ የሚነገረውም የገበታው ፊደል ብዛት ነው። የኢትዮጵያው ፊደል በዝቷል ሲባል ግን በቁጥር የሚነገረው የገበታው ከርባታው ሳይለይ ነው፡፡ ለምሣሌ፣ የአማርኛውን ብንወስድ ጠቅላላ ብዛቱ ወደ ሦስት መቶ የሚጠጋ ተደርጐ ይነገራል፡፡ ይህም:-

እያንዳንዱ የገበታ ፊደል በ7 ተባዝቶ - 238ዲቃሎቹ (4x5) = = 20ፍንጽቆቹ = 21ጠቅላላ 279 ይሆናሉ፡፡ እንዲህ በመሆኑ በዝቷል ነው የሚሉት።

በዝተዋል ተብለው መቆጠር የነበረባቸው ግን እንዲህ አልነበረም፡፡ ለየትኛውም ባለ ጽሕፈት ቋንቋ የፊደላት ብዛት ሲጠየቅ ይህን ያህል ነው የሚባለው የገበታው ፊደል ብቻ ነው፡፡ እንግሊዝኛ 26 ፊደል አለው፤ ግሪክ 28 አለው፡፡

ዓረብ 29 አለው፤ የሩስያ 33 ፊደል የሚባለው የገበታ ፊደሉ ብቻ ተቆጥሮ ነው፡፡ የርባታ ፊደሎቻቸውን/ምልክቶቻቸውን/ እንደ አንድ እየቆጠርን እንጠቁም ቢባል፣ እንደ እንግሊዝኛ ያለው ለአማርኛ ከተቆጠረውም በእጥፍና ከዚያ በላይ የሆነ ብዛት ይኖረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የርባታ ሥርዓት በነ ዳንኤልስ “አቡጊዳ” የተባለው ዓይነት ሆኖ፣ በመሠረታዊው ፊደል ላይ የተለያዩ ጭማሪዎች በማድረግ አንድ ምልክት እየተደረገ የሚሠራ በመኾኑ እነዚያንም ደርቦ በመቁጠር ቁጥሩን ማብዛቱ ተገቢ አይደለም። መሠረታዊዎቹ ስንት ናቸው ብሎ ነው መቁጠር፡፡ በዚህ መሠረት ለግዕዝ 26 ፊደላት፣ ለአማርኛ ደግሞ

34 ፊደላት ብቻ ይኖሯቸዋል፡፡እንደዚያም ቢኾን የሞክሼ ፊደላቱ ቢቀነሱ ያን

ያህል ወደ 300 የተጠጉ ናቸው ካሏቸው ውስጥ ምን ያህሉን ነው የሚቀንሱላቸው?... በአጠቃላይ፣ ከሞክሼ ፊደላቱም አኳያም ሆነ ከሌላ፣ የፊደል ብዛት ጥያቄው ተገቢ ጥያቄ አይኾንም፡፡ ፊደላቱም ብዙ አይደሉም፡፡ የቴክኖሎጂ ውጤት ለኾኑ መጻፊያዎች ቸገረ፡-

ይህ ጥያቄ አስቀድሞ “ታይፕ ራይተር” በነበረበት ወቅት፣ በተለይ መጀመሪያ ላይ እንደ አንድ ችግር ተነስቶ ነበር፡፡ በዚህ ፊደሉን የመነካካት፣ እንዲያውም የመለወጥ ጥያቄ እስከ ማንሳት ድረስ ያሳሰቡት፣ በአስፋው ዳምጤ “ጐምቱ አብዮተኞች” ተብለው የተጠሩ እነ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ አንስተውት ነበር፡፡ ይህንን መነሻ አድርጐ የፊደል ነካኪዎችን ታሪክ የጠቃቀሰ የዶ/ር መርሻ አለኸኝ ጥናታዊ ወረቀት፣ ታይፕ ራይተሩ ራሱ ለፊደል እንዲመች ኾነና ፊደሉ ከመቀየር እንደተረፈ ጠቁሟል፡፡ አሁን ደግሞ እንደ አዲስ ለኮምፒውተሩ እንዲመች የሚል ሐሳብ ነው የሚነሳው፡፡ ለኮምፒውተሩ ያልተመቹ ፊደላት ሳይኖሩ ይህን ጥያቄ ለምን እንደሚያነሱት ለማንም አይገባም፡፡ ደግሞም የፊደላቱ ድምፅ አንድ መኾን በቴክኖሎጂው ላይ የሚያመጣው የተለየ ችግር ምን ሊኾን እንደሚችልም አይገባንም። በማንኛውም ቢኾን ስለቴክኖሎጂ ተብሎ ያለው ነገር ይቀነስ ማለት ደግሞ በጭራሽ ተገቢነት አይኖረውም፡፡ ቴክኖሎጂው ለእነዚያ ተብሎ ይሠራል እንጂ፣ እነዚያ ለቴክኖሎጂው አይሠሩም። ለእንግሊዝኛው ወይም ለላቴኑ ፊደላት እንዲኾኑ ተበጁ እንጂ ለቴክኖሎጂው ሲባል እንግሊዝኛው፣

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 12

አድማስ አድቨርታይዚንግ ኃ.የተ.የግል. ማኅበር(የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አሳታሚ)

አንድ ረዳት የሂሳብ ባለሙያ ሰራተኛ ለመቅጠር ይፈልጋል ተፈላጊ ችሎታ በሂሳብ ሙያ (በአካውንቲንግ) ዲፕሎማ እና 4 አመት

መልካም የሥራ ልምድ ወይም ከዚያ በላይ ያለው/ያላትአመልካቾች የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃዎችን በመያዝ ካዛንቺስ

ሰራተኛና ማኅበራዊ አጠገብ ከሚገኘው ቢሮአችን ማቅረብ ትችላላችሁ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0115 15 52 22 / 0115- 15 36 60

ሠራተኛ ይፈለጋል

ህብረተሰብ

ዘንድሮ ብቻ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሄዱ ኢትዮጵያውያን ብዛት ከ160ሺ በላይ ናቸው፡፡ የሳኡዲ አረቢያ መንግስት በአገሪቱ ያሉ ህገወጥ ስደተኞች ህጋዊ

የመኖሪያ ፍቃድ እንዲያወጡ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ የሰባት ወራት እድሜ ነበረው፡፡ ቀነ ገደቡ ባለፈው ሳምንት እሁድ መጠናቀቁን ተከትሎ በኋላ የአገሪቱ ፀጥታ ሃይሎች ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ህገወጥ ያሏቸውን የተለያዩ አገራት ዜጐችን በማሳደድ በማቆያ ካምፕ ውስጥ እየሰበሰቧቸው ይገኛል፡፡

ይሄንን ሰዶ ማሳደድ በመቃወም በሳኡዲ የተለያዩ ከተሞች በተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች እስከ ትናንት በስቲያ ድረስ አራት ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል፡፡ ከዋና ከተማዋ ሪያድ በስተደቡብ በምትገኘውና በርካታ ስደተኞች በሚኖሩባት ማኑፋሃ በተለይ ኢትዮጵያውያን አመፅ የተቀላቀለበት ከፍተኛ ተቃውሞ እንዳደረጉ ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡ ስደተኞች ለተቃውሞ ሰልፍ ገጀራና የተለያዩ መሳሪያዎችን ይዘው የወጡ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሽከርካሪዎችንም አጋይተዋል፡፡ ይሄን ተከትሎም የፀጥታ ኃይሎች

የሳዑዲ የኃይል እርምጃ ያስከተለው ቀውስ

ግሩም ሠይፉ እርምጃ መባባሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተለያዩ ቦታዎች ከተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ጋር በተያያዘ 60 ያህል የሳዑዲ ዜጎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከ100 በላይ ስደተኞች ቆስለዋል ተብሏል፡፡

እስካሁን 23ሺ ያህል ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለአገሪቱ መንግሥት እጃቸውን የሰጡ ሲሆን 10ሺህ የሚደርሱ ህገወጥ ስደተኞች ከፀጥታ ኃይሎች አደን ለመሰወር ሲሉ ስራቸውን አቁመው በተለያዩ ስፍራዎች እንደተሸሸጉ ተነግሯል፡፡

የሳኡዲ ፖሊስ፤ ህገወጥ ስደተኞች ይበዙባቸዋል የተባሉ የሸቀጣሸቀጥ ሱቆች፣ የግንባታ ሳይቶች፣ ምግብ ቤቶች እና የንግድ ማዕከሎችን በመክበብ አሰሳውን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፤ በቅርቡ ደግሞ የቤት ለቤት አሰሳ እንደሚጀምር ታውቋል፡፡ የሳዑዲ ዜጎች በ99 የስልክ ቁጥር በመደወል ህገወጥ ስደተኞችን እንዲጠቁሙም ጥሪ ቀርቧል፡፡

ባለፉት ሰባት ወራት በሳዑዲ የነበሩ ከ1 ሚሊዮን በላይ የተለያዩ አገራት ህገወይ ስደተኞች ወደየአገራቸው የተላኩ ሲሆን ዳግም ወደ ሳዑዲ እንዳይመለሱም እገዳ ተጥሎባቸዋል፡፡ ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ደግሞ የሳዑዲ መንግስት የሚሰጠውን የመኖርያ ፈቃድ በማውጣት፤ ህጋዊ የስራ ፈቃድ እና ውል ይዘው ኑሯቸውን ቀጥለዋል፡፡ የማሳደድ ዘመቻው ለምን?

ሳዑዲ አረቢያ ከ28 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ሲሆን 9 ሚሊዮን የሚሆኑት የተለያዩ አገራት ስደተኞች ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከልም ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ያህሉ ህገወጥ እንደሆኑ ይገመታል፡፡

ህገወጥ ስደተኞችን ከአገር የማባረሩ እርምጃ የተጠነሰሰው የስደተኞች ቁጥር መጨመር የሳኡዲ ዜጐችን ለስራ አጥነት ዳርጓል፣ የሥራ ተነሳሽነትንም አዳክሟል በሚል ቢሆንም ሳዑዲ ከራሷ ዜጐች ውጭ 1 ሚሊዮን ተጨማሪ የሰው ሃይል እንደሚያስፈልጋት መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በህገወጥ ስደተኞች ላይ የሚደረገው ዘመቻ እንዲጠናከር የሚፈልጉት የሳኡዲ ህግ አውጭ አካላት፤ ስደተኞችን ከማሳደድ ባሻገርም በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ የሳዑዲ ዜጎች ላይም ጥብቅ እርምጃ እንዲወሰድ እየመከሩ ነው ተብሏል፡፡

ከሳዑዲ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ አብዛኞቹ ህገወጥ ስደተኞች በዝሙት እና በመጠጥ ንግድ፣ በዝርፊያ እና ሌሎች የወንጀል ተግባራት ላይ የተሰማሩ ሲሆን ይሄም ሳዑዲን ለከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስ እንዲሁም ለባህልና ሃይማኖት ብረዛ ሊዳርጋት ይችላል የሚል ስጋት በንጉሳውያን ቤተሰቡና በመንግሥት ዘንድ እንደተፈጠረ ታውቋል፡፡

ሳዑዲን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ አገራት፣ በስደተኛ ሰራተኞች ላይ የሚደርሰው በደልና ስቃይ ከየትኛውም የዓለም ክፍል የከፋ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ስደተኞች ላይ ፆታዊ ጥቃቶች እና ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ይፈፀሙባቸዋል፡፡ ለስራቸው ተገቢውን ክፍያ እንደማያገኙና በቀን መስራት ከሚገባቸው ሰዓት እጥፍ እንደሚሰሩም ይታወቃል፡፡ በሳምንት ከ108 ሰዓታት በላይ የሚሰሩ ስደተኞች እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከሃይማኖት ጋር በተያያዘም ለከፍተኛ እንግልት የሚዳረጉ ጥቂት አይደሉም ይባላል፡፡

ተቀማጭነቱን በአውስትራሊያ ያደረገው “ዎክ ፍሪ ፋውንዴሽን” የተባለ ተቋም ዘንድሮ ለመጀመርያ ጊዜ “ዘመናዊ ባርነት” በሚል በ162 የዓለም አገራት ላይ ባካሄደው ጥናት፣ ከ38 ቢሊዮን በላይ ህዝቦች ለህገ ወጥ ዝውውር፣ ለአስገዳጅ ስራዎችና፣ ለጉልበት ብዝበዛ መጋለጣቸውን ይፋ አድርጓል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚገመቱት በመካከለኛው ምስራቅ በከፋ ባርነት ውስጥ የሚገኙ ናቸው ብሏል - ተቋሙ፡፡

መሳደዱ ኢትዮጵያውያን ላይ በዝቷል

የሰዶ ማሳደድ ዘመቻው ፈተና ከእስያውያን ይልቅ በአፍሪካውያን ስደተኞች ላይ የበዛ ሆኗል። በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያውያን አበሳቸውን እየበሉ ነው፡፡ የሩቅ ምስራቅ አገራት፡- ፊሊፒንስ፤ ስሪላንካና ኢንዶኔዥያ ዜጎችም መሰቃየታቸው አልቀረም - እንደ ኢትዮጵያውያኑ ባይሆንም፡፡ መሳደዱ በአፍሪካውያን ላይ ያየለው አብዛኞቹ በህገወጥ መንገድ ሳዑዲ የገቡ በመሆናቸው እንደሆነም ታውቋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በ13 የተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ተበትነው የሚገኙ ሲሆን፤ በሳዑዲ፣ ኩዌት፣ ባህሬን፣ ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ፣ ኳታርና የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ይሆናሉ። ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለስራ ከሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ውስጥ 40 በመቶ ያህሉ ህገወጥ ሲሆኑ በየዓመቱ ከ6ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በህገወጥነት ተጠርዘው ወደ አገራቸው እንደሚላኩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ሳዑዲዎችም ተቸግረዋልበአገሪቱ በሚኖሩ ህገወጥ ስደተኞች ላይ

በተከፈተው የማደንና የማሳደድ ዘመቻ፣ የሳዑዲ ዜጐች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችም ተስተጓጉለዋል፡፡ ሱቆችና ምግብ ቤቶች እንዲሁም መዝናኛዎች በሠራተኞች እጦት እንደተቸገሩና የተዘጉም እንዳሉ ታውቋል። ትልልቅ የገበያ ማዕከላት ተዘግተዋል፤ በርካታ የግንባታ ስራዎችም እየተጓተቱ ነው፡፡ “አረቢያን ኒውስ” የተባለ ጋዜጣ እንደዘገበው፤ የሰዶ ማሳደድ ዘመቻው ሳምንት እንኳን ሳይሞላው በየቅጥር ግቢያቸው ያለልክ በተከመረ ቆሻሻ የተማረሩ ብዙ ሺ ትምህርት ቤቶች ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው፡፡

በሳዑዲ ሴቶች መኪና ማሽከርከር አይፈቀድላቸውም፡፡ በሾፌርነት ተቀጥረው ሲሰሩ የቆዩ ስደተኞች ከሳዑዲ መባረራቸውን ተከትሎ፣ በርካታ የቤተሰብ አባላት ወደ ስራ ከመሄድ የተስተጓጐሉ ሲሆን ልጆቻቸውን ወደ ተማሪ ቤት መላክና ገበያ መውጣት እንዳልቻሉም ታውቋል፡፡ በሳኡዲ ከግማሽ ሚ. በላይ የሚሆኑ ስደተኞች በሾፌርነት ተቀጥረው ይሰሩ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 13 ማስታወቂያ

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 14 ዋናው ጤና

መንግሥቱ አበበ

መታሰቢያ ካሣዬ

ጭውውት - ከሴቷ የወባ ትንኝ ጋር1. ሲደክማችሁ በጣም እንወዳለን “በጣፋጩ ደማችሁ” መዓዛ የምንሳብ ሊመስላችሁ ይችላል፡፡ ግን አይደለም፡፡ ከደማችሁ ይልቅ እኛን ወደ እናንተ እንድንሳብ የሚያደርገው፣ የምትተነፍሱት የተቃጠለ አየር (ካርቦንዳይኦክሳይድ) ነው፡፡ በጣም ስትተነፍሱ ብዙ ካርቦንዳይኦክሳይድ (Co2) ታስወጣላችሁ፡፡ ስለዚህ በተለይ ብዙ ሠርታችሁ ወይም የሰውነት እንቅስቃሴ አድርጋችሁ ሲደክማችሁ በጣም ታስጐመዡናላችሁ፡፡2. የቢራ ፍቅርአንዳንዶቻችን ቢራ እንወዳለን፡፡ የሚገርም ይመስላል አይደል? እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፣ የእኛ ፍቅር ከቢራው (ከመጠጡ) አይደለም። እናንተን ስለሚጠቁመን ነው የምንወደው፡፡ እንዴት መሰላችሁ? ቢራ ስትጠጡ የቆዳችሁ ንጥረ ቅመም (ኬሚስትሪ) ይለወጣል፡፡ ያ ነገር ወደ እናንተ ይስበናል፡፡ ለዚህ ነው ቢራ መጠጣታችሁን የምንወደው፡፡ 3. ነፍሰጡር ነሽ? በጣም ታስፈልጊናለሽ እርጉዝ ሆነሽ መውለጃሽ ሲቃረብ ይደክምሻል። ስለዚህ፣ ብዙ ጊዜ እየተነፈስሽ ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ወይም የተቃጠለ አየር ታስወጫለሽ። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ መውለጃሽ ሲደርስ፣ ሆድሽ ከፍተኛ ሙቀት ይፈጥራል። አንዳንዶቻችንን ይህ ሙቀት ወደ አንቺ እንድንሳብና እንድንከብሽ ያደርገናል። እንግዲህ ማሙሽና ሚሚ እናዝናለን! የእኛም ሕይወት አይደል? ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ 4. በወባ ትንኝ መነደፍ አትወዱም አይደል? ሴቷን

ትንሽ ወቀሱ ነገር ግን እኛ ሴት የወባ ትንኞች ይህንን ወቀሳ ስለማንሰማ ተውት፡፡ በእርግጥ አንድ የማይካድ ሐቅ አለ፡፡ ወንድ ወባ ትንኞች፣ የሰው ደም በፍፁም ስለማይመገቡ፣ ስማቸውን በከንቱ አታጥፉ፤ መወቀስ ካለብንም እኛ ሴቶቹ ነን። ወንዶቹ የሚያስፈልጋቸውን የተመጣጠነ ምግብ (ኑትሪሽን)

•ማንን መንደፍ ይፈልጋሉ?•የት መኖር ይመርጣሉ?

•በጣም የሚጠሉት ነገር ምንድነው?

ኢትዮጵያ ወደ ገፅ 24 ዞሯል

ገና በሃያ አምስት ዓመት ዕድሜዋ የስምንት ልጆች እናት መሆኗ ሁሌም ያበሣጫታል፡፡ በላይ በላይ እያከታተለች የምትወልዳቸውን ሕፃናት በአግባቡ ተንከባክቦ

ማሣደግ ህልም ሆኖባታል፡፡ ባለቤቷ ችግሯን ሊጋራትና ሊደግፋት ፈፅሞ አይፈልግም፡፡ ይልቁንም መተዳደሪያቸው የሆነውን የእርሻ ሥራ ለመሥራት ከቤት በሚወጣበት ጊዜ ሁሉ ባለቤቱ እንድትከተለውና አረሙንም፣ ጉልጓሎውንም፣ ሰብል ስብሰባውንም እንድታግዘው ይፈልጋል፡፡

በሆዷና በጀርባዋ ልጆቿን ተሸክማ ማሣው ላይ ደፋ ቀና ስትል ውላ ትመለሳለች፡፡ ከዓመት ዓመት በሽታ እየተጫናትና አቅሟ እየደከመ መምጣቱም ይታወቃታል፡፡ እርግዝናና ወሊድ ተባብረው ጉልበቷን ነጥቀዋታል፡፡ ግን አማራጭ የላትም። ፈጣሪ በቃሽ እስኪላትና ወሊድ የምታቆምበት ተፈጥሯዊ ጊዜዋ እስኪደርስ በየዓመቱ መውለዷ እጣ ፈንታዋ እንደሆነ ታስባለች፡፡ ከዚህ ሥቃይና ችግር ሊገላግላት የሚችል ምንም ነገር እንደሌለ አምና ተቀብላለች፡፡ ሴቶች ሳይፈልጉ ልጅ መውለድ እንዳይችሉ የሚያደርጋቸው መድሃኒት መኖሩን የወሬ ወሬ ብትሰማም፣ ነገሩን አምኖ መቀበሉ

በቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ከምዕተ ዓመቱ የልማት ግብ ግማሹ ላይ መድረስ አልተቻለምኢትዮጵያ ያቀደችው ይሳካላት ይሆን?

አልሆነላትም፡፡ የምትኖርበት ገጠራማው የአፈርደባ ቀበሌ፣ ለትራንስፖርት እጅግ አስቸጋሪ በመሆኑ ነዋሪዎቹ ህክምናም ሆነ በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶችን እንደልባቸው ለማግኘት አልታደሉም፡፡ በሐረሪ ክልል ሶፌ ወረዳ አፈርደባ ቀበሌ ውስጥ ያገኘኋት ይህቺው የስምንት ልጆች እናት፣ ትዳር ከመሰረተችበት የአስራ ስድስት ዓመት ዕድሜዋ ጀምሮ በየአመቱ እርግዝናና ወሊድን

ለማስተናገድ ተገዳለች፡፡ ባለቤቷ አብዱራህማን ሠይድ፣ የልጆቹ ቁጥር ከአመት አመት እየጨመረና ኑሮ እየከበደው መምጣቱ ለአፍታም አሣስቦት አያውቅም፡፡ በሰበብ አስባቡ ከሚከሰተው ሞት ተርፈው ለፍሬ የሚበቁት ጥቂቶቹ ናቸውና የልጆቹን ቁጥር በየዓመቱ ለመጨመር እቅድ አለው፡፡ የባለቤቱ በእርግዝናና በወሊድ መጐዳት ለእሱ ትዝ አይለውም። ለሥራ ጉዳይ ወደ አካባቢው በሄድኩበት

አንድ አጋጣሚ አግኝቼ ያነጋገርኳት ይህችው ሴት፣ ስለ ወሊድ መከላከያ በግልፅ አስረድቶ እንድትጠቀም ያበረታታት አንድም ሰው አለመኖሩን ነግራኛለች፡፡ በአካባቢያቸው ሴቶች በቡድን በቡድን እየተደራጁ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩበትና የሚመክሩበት ሁኔታ እንዳለ ብትሰማም እሷ ወደዚህ ስብሰባና ውይይት እንድትሄድ ባሏ አይፈቅድላትም። እሷ ብቻ ሳትሆን ብዙዎቹ የአካባቢዋ ሴቶች የዚህ ስብሰባና ውይይት ተካፋዮች አይደሉም። እሷንና የእሷ መሰል እድል ያላቸውን ሴቶች ቤት ለቤት በሚደረግ አሠሣ በማግኘት ስለ ቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት፣ ስለ ቅድመ ወሊድና ድህረ ወሊድ፣ ስለ ህፃናት አስተዳደግና መሰል የጤና አገልግሎቶች ለማስተማርና ህብረተሰቡን ለመለወጥ የሚደረግ አንዳችም እንቅስቃሴ አለመኖሩንም ነግራኛለች። በአካባቢው የጤና ኬላና የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ስለመኖራቸው እንኳን አታውቅም። የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞቹም ያለ ፍላጐቷ በየዓመቱ የአዳዲስ ህፃናት እናት ለመሆን የተፈረደባት ሴት መኖሯን አያውቁም፡፡

የዓለም አገራት እ.ኤ.አ በ2015 ዓ.ም ለማሳካት ቃል ከገቡት የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች መካከል አንዱ የሆነው የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት በአገራችንም መሻሻሎችን እያሣየ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2005 ከነበረበት 15 በመቶ በ2011 ዓ.ም 29 በመቶ የደረሰ ሲሆን በተያዘለት የጊዜ ገደብ 66 በመቶ ለማድረስ ዕቅድ መያዙ እየተነገረ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬም ድረስ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ማለት

በሙሉ የሚያገኙት ተክሎች በአበባቸው ውስጥ ከሚያዘጋጁት ጣፋጭ ፈሳሽ (Nectar) ነው፡፡ እኛ ሴቶቹ ግን የሰው ደም ዕንቁላላችንን የሚያሳድግ ፕሮቲን ስላለው እንፈልገዋለን፡፡ የሰው ደም ከተመገብን በኋላ፣ ከ100 እስከ 400 ዕንቁላሎች መጣል እንችላለን፡፡ 5. የሚሸት እግር እንወዳለን እኛ ሴቶች ከሰውነታችሁ ክፍል የምንጠላው የለም፡፡ በእርግጥ ስንቶቻችሁ፣ እግሮቻችሁን ከLimburger cheese 10 እጅ የበለጠ እንደምንወድ አሳይተዋል። ነገር ግን ዛሬ እውነቱን አይደል የምንነጋገረው? ውሸት ምን ያደርጋል? እኛ በፍቅር የምንወደው የሰውነታችሁ ክፍል እጃችሁን ነው፡፡ 6. የዳንስ ቦታ፤ ሠርግና ምላሻችን ነው ፓርቲ (ዳንስ) ቤት በዛ ያሉ ሰዎች እየጠጡ ሲጨፍሩ፣ በጣም በርከት ያለ የተቃጠለ አየር (ካርቦንዳይኦክሳይድ) ያስወጣሉ ወይም ይተነፍሳሉ። ያ ሲሸተን ወደዚያ እንበራለን፡፡ እዚያ ከደረሰን በኋላ መኻል ላይ እጅብ ብለው

ከሚደንሱት ይልቅ ከቡድኑ ውስጥ ነጠል ያሉትን ማጥቃት ይቀለናል፡፡ 7. ገላጣ ቦታ አንወድምለመኖሪያነት፣ በጣም ጥቅጥቅ ያለና በጣም ያደጉ ተክሎች ያለበትን ስፍራ እንመርጣለን። ጨለም ያለና ብዙ እርጥበት ካለው ደግሞ በጣም ይመረጣል። የመዋኛ ገንዳው ውሃ ካልቋጠረ፣ የአካባቢው ቁጥቋጦ ከተመለመለ፣ ሳሩ አጥሮ ከታጨደ ያንን ግቢ ለመኖርያነት ብዙም አንመርጠውም፡፡ የረጋ ውሃ ወይም ኩሬ እንዲፈስ ወይም እንዲጠፋ ከተደረገ፣ መሰደዳችን ነው፡፡ ምክንያቱም ያ ስፍራ’ኮ የዕንቁላላችን መጣያ ነበር! ፀረ-ነፍሳት ያልሆነ ተክል ሲተከል ጮቤ እንረግጣለንDeet እና Picardin የተባሉ ክፍሎች ፀራችን ናቸው። ፀረ-ነፍሳት መርዝ ስላላቸው እነሱ ሲተከሉ፣ ድራሻችን ነው የሚጠፋው፡፡ የማንወዳቸው ሌሎች ተክሎችም አሉ፡፡ እነዚህ ሁለቱ ግን፣ የተለያዩ የደም መምጠጫ አካላችንን ይዘጋሉ፡፡ ሎሚና ባህር ዛፍ ያላቸው መርዝ ደከም ያለ ቢሆንም አንወዳቸውም፡፡

8. Co2 የሚያመነጭ መሳሪያ፤ ለእኛ ደስታችን ነው

ካርቦንዳይኦክሳይድ (Co2) ስለምንወድ እኛን አሳስታችሁ ለማጥመድ ካርቦንዳይኦክሳይድ የሚያመነጭ መሳሪያ ግቢያችሁ በመትከላችሁ፣ “ብልጥ ነን” ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ብልጥ አይደላችሁም፡፡ ምክንያቱም መሳሪያው፣ እኛን ወደ ወጥመዱ ከመክተት ይልቅ፣ በግቢያችሁ፣ የወባ ትንኞችን ቁጥር ሊያበዛው ይችላል። UV (አልትራ ቫዮሌት) በተባለ ጨረር፣ እኛን ለማጥፋት የተሞከረው ዘዴም፣ እርባናው ይህን ያህል አይደለም። ምክንያቱም የማጥመጃው ዘዴ ከሚገድላቸው ነፍሳት መካከል፣ የወባ ትንኞች ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ 9. የዌስት ናይል ቫይረስ (West Nile) ጉዳት የከፋ

ነው- ይህ ቫይረስ በምዕራብ ናይል አካባቢ የሚገኝ ነው። የሚያደርሰውን ጉዳት አስከፊነት ለመረዳት በጣም ቀላል ነው፡፡ በመጀመሪያ ቫይረሱ ያለባቸውን ወፎች እንነክሳለን፡፡ ከዚያም ሰዎችን በመንደፍ ቫይረሱን እናሰራጫለን፡፡ የበጋ ወራት ማብቂያ ደግሞ በቫይረሱ የተጠቁ ወፎችን ለመንደፍ ጥሩ ዕድል ይፈጥርልናል፡፡ ሁነኛ ነጥቦች • የወባ ትንኝ በምትመገብበት ጊዜ የምትመጠው

ከአንድ ጠብታ ደም ያነሰ ነው፡፡ በሰውነታችን 5 ሊትር ደም ይገኛል፡፡

• የወባ ትንኝ በሰዓት ከአንድ እስከ አንድ ተኩል ኪ.ሜ ትጓዛለች፡፡

• በመላው ዓለም ከ3ሺ በላይ የወባ ትንኝ ዝርያ አለ፡፡ 176ቱ የሚገኙት በአሜሪካ ነው፡፡

• ጨዋማ በሆነ ረግረግ ስፍራ የሚኖሩ የወባ ትንኞች ምግብ ፍለጋ ከ64 ኪ.ሜ በላይ ሊሰደዱ ይችላሉ፡፡

• የሰው ልጅ ዝርያ ጂኖች (genes) ከትውልድ ወደ ትውልድ እንደሚሸጋገሩ የሚያጠናው ሳይንስ (genetics) ከመቶ ሰዎች 85ቱ፣ ለወባ ትንኝ ንድፊያ የተጋለጡ ናቸው ይላል፡፡

ምንጭ፡- (Reader’s Digest USA July, 2013)

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 15

ደረጀ ኅብስቱ [email protected]

ጥበብ

ዴካርት ወደ ገፅ 18 ዞሯል

በ17ኛው ክፍለ ዘመን በፈረንሳይ ገኖ የወጣ አፍቃሬ−አመክንዮ ፈላስፋ ነው፤ ዴካርት። በአለም የፍልስፍና ታሪክ ውስጥም የዘመናዊ ፍልስፍና አባት ተደርጎ

ይቆጠራል። የነባሩን የፍልስፍና ባህል እና የዘመኑን የሳይንስ አባዜ አጣምሮ ወጥ ስራ በመስራት ዘመኑን አስደንቋል። የምዕራቡን (የአውሮፓን) ዳግም መነሳሳት ካቀነቀኑት መካከል የሚጠቀሰው የታላቁ ሠዓሊ ሊዮናርዶ ዳቪንቺ እያንዳንዷ የሐሳብ ቅንጣት ከሬኔ ዴካርት ሐሳቦች ጋር ተመሳሳይ እንደሆኑ ይገመታል። በሒሳብ ባለሙያነቱ የሚታወቀው ሬኔ ዴካርት፤ ፍልስፍና በዘመናዊ የሳይንሳዊ ዘዴ እንድትመራ ፈር ቀዳጅ ፈላስፋ ለመሆን በቅቷል። የፍልስፍና ዘዴው በተለየ ሁኔታ የካርቴዚያን ፍልስፍና ተብሎ ተሰይሞለታል። የሒሳብ ቀመሮቹም ካርቴዚያን ማቲማቲክስ እየተባሉ እንደሚጠሩለት ማለት ነው። አናሊቲካል ጂኦሜትሪ እና አናቶሚካል ኤክስፐርመንቶች ላይ ከፍተኛ ስራ እንደሰራ የሚነገርለት ዴካርት፤ የጋሊሊዮ ቀንደኛ አድናቂ ነበር ይነገራል።

ለዴካርት ፍልስፍና ማለት “የጥበብ ጥናት” ማለት ነው፤ “ማንኛውም ሰው ሊያውቀው የሚችል ፍጹም እውቀት የፍልስፍና አገልግሎቶቹ/ጥቅሞቹም ስለ ሕይወት አኗኗር (ሞራል) ስለጤና አጠባበቅ (ህክምና) እና ስለሙያ ፈጠራ (ክህሎት/መካኒክስ) ማወቅ ነው ይላል። ይህንን ሐሳቡን በተምሳሌት

ሬኔ ዴካርት/”እያሰብኩ ስለሆነ ኅልው ነኝ“/

ሲያስረዳም “አንድን ዛፍ ብንወስድ ስር፣ግንድና ቅርንጫፍ አለው። ስሩ ኅላዌን ሲወክል፤ ግንዱ ቁስ/ግዑዝ አካላትን ይወክላል፤ ቅርንጫፎቹ ደግሞ ሞራል፣ህክምና እና ክህሎት ናቸው።” ይለናል። የዛፍ ስሩ ጥልቅ ነው፤ ወደ ውስጥ መሬትን ቆንጥጦ በመያዝ ምግብና ውኃ በማቅረብ ስለሚያገለግለው የዛፉ ኅልውና እንደመሆኑ ሁሉ የፍልስፍና መሰረትም ኅላዌ/ዲበ አካል (metaphysics) ነው። ሌሎች የፍልስፍና ዘርፎችን የዲበ አካል ጥገኞች ያደርጋቸዋል፤ እንደ ዛፉ ግንድና ቅርንጫፍ ማለት ነው።

የሬኔ ዴካርት የዲበ አካል/ኅላዌ ፍልስፍና ከእርሱ ቀደም ብሎ እንደ መጣው ፍራንሲስ ቤከን፤ በስሜት ህዋሳትና በይሆናል ሳይሆን በሒሳብ ስሌት ላይ በመተማመን በእርግጠኝነት ላይ እንዲመሰረትለት ጥሯል። “ከፊት ለፊቴ እሳት ይነዳል፤ የሌሊት ካፖርት ለብሻለሁ፤ ጠረጴዛዬ ላይ ወረቀትና ብዕር ይታየኛል……ነገር ግን እነዚህ ሁሉ እውነት ስለመሆናቸው ምን እርግጠኛ የሚያደርገኝ ነገር አለ? ከዚህ በፊትም ብዙ ነገሮች በእውነት የተከናወኑ መስሎኝ ነገር ግን በህልሜ የሆኑ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። ዛሬስ በህልሜ ላለመሆኑ ምን እርግጠኛ የሚያደርገኝ ነገር አለ? እንዲህ እያለ ነው ዴካርት “ተመስጦውን”/ፍልስፍናውን የሚጀምረው። የ”ጥርጣሬን” መንፈስ በልቦናው ያነግሳታል። ሁሉንም ነገር፤ የ ሚ ያ የ ው ን ፣ የ ሚ ዳ ስ ሰው ን ፣ የ ሚ ያ ሸተ ው ን ፣ የሚቀምሰውን በአጠቃላይ በስሜት ህዋሳቱ አማካኝነት የሚያገኘውን መረጃ በሙሉ ከመቀበል ይልቅ በጥያቄና በጥርጣሬ ያዋክባቸዋል። አውሮፓ ድንበሯ እየተለጠጠ ሳይንስና አዳዲስ ግኝቶች

እየተስፋፉ እንዲሁም አዳዲስ የዓለም ክፍሎችን እየተዋወቁ የመጡበት ዘመን ስለነበር፤ እውቀት ለሰው ልጅ የሚቻል ነገር አይደለም የሚለውን የቀደመ አስተሳሰብ ለመስበር ታትሯል።

እርግጠኛ የሆነ እውቀትን ለማግኘት ዴካርት የተጠቀመበት ዘዴ ደግሞ፤ ከዚህ በፊት እርግጠኛ የሆንባቸውን ነገሮች ሁሉ በመጠራጠር እና ባለመቀበል ነው። እናውቀዋለን የምንለውን ነገር ሁሉ በጥያቄ ማብጠርጠር ማለት ነው።” ዘላቂና የማይናወጥ እውቀትን መመስረት ካለብኝ፣ እስከዛሬ በሕይወት ዘመኔ የሰበሰብኩትን እውቀት ተብዬ ሁሉ ድምጥማጡን ማጥፋት እንዳለብኝ ተገንዝቤአለሁ” ይለናል፤ “ቀዳማዊ ተመስጦ” በተባለው ድርሳኑ በአካባቢያችን ያሉ ነገሮችን ሁሉ እየበረቃቀስን እና እያብጠረጠርን መፈተሽ እንዳለብን ያሳስባል፤ ዴካርት።ይህንንም ተከትሎ ሦስት አፈንጋጭ ሙግቶችን ያቀርባል፤ በዘልማድ የተቀበላቸውን ነገሮች ሁሉ ለማስወገድ እንዲረዱትና እርግጠኛ የሆነ እውቀት ለመመስረት እንዲችል። እያንዳንዱን እምነቱን አንድ በአንድ በመጨፍለቅ ሳይሆን መሰረታዊ የእምነቱን መርሆዎችን ማንገራገጭ እንደ ስልት ይጠቀማል፤ ዴካርት። በመሰረታዊነት የተጠቀመባቸውን ሦስቱን ሙግቶች እንደሚከተለው ማየት ይቻላል።

ሀ) ማንኛውንም ያልተመረመረ ሐሳብ እና በስምምነት የተቀበልነውን ሁሉ በተደራጀና መመሪያዎችን በተከተለ መልኩ በጥርጣሬ መፈተሽ። ወይም ባጭሩ አፈንጋጭነት ልንለው እንችላለን። ይህ በየዋህነት የተቀበልናቸውን አስተሳሰቦች ለማጥቃት የተጠቀመበት ሙግት ነው። “ከጊዜ ወደ ጊዜ የስሜት ህዋሶቼ እያጭበረበሩኝ እንደ ሆነ ደርሸበታለሁ።” የሚለው ዴካርት፤ “ለአንዲት ጊዜ እንኳን ያታለለችኝን የስሜት ህዋሴን አለማመኔ ሁነኛ እርምጃ ነው” ይላል።

ለ) ያልጠራ፣ እራሱን ያልቻለ እና ግጭቶች/መፋለሶች ያሉበትን ሐሳብ አለመቀበል። The Dream Argument (የህልም ሙግት) እየተባለ ይጠራል፤ ሁለተኛው የዴካርት ሙግት።

ማስታወቂያ

ወርቅ ከገፅ 10 የዞረ

አበሻ ከገፅ 10 የዞረ

ድብደባ ቢሉሹ ድብደማ መሰለሽ፡፡ ዝግንን በሚል ሁኔታ ነው የሚደበድቡበት፡፡ ዱላ እኮ መፈንከት ብቻ ሳይሆን የደምስርሽ እንዲቋረጥ ያደርጋል፡፡ ሽባ ነው የሚያደርጉት---.በጣም ይጠሉናል፡፡

ከዚህ በኋላ ተመልሰህ አትሄድም?እንኳንም መጣሁ፡፡ አላህ ለአገሬ ምድር

አበቃኝ፡፡ አሁን አገሬ ስገባ የምሰራውን ስራ እኔ ነኝ የማውቀው፡፡ ለእኔ ብቻ ሳሆን ለጓደኞቼም ትምህርት ነው የምሆነው፡፡ ይጠቅመኛል ያለ ይከተለኛል፣ ያለዚያ የራሱ ጉዳይ፡፡

ምን ልትሰራ አሰብክ?በንግድም ሆነ በሚያዋጣኝ ወጥሬ ነው

የምሰራው፡፡ ሳኡዲ አረቢያ ወርቅ እየዘነበ ነው ቢሉኝ -- ከአሁን በኋላ ስሙን እንኳን መስማት አልፈልግም፡፡ የቅጣታቸው አከፋፍ ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ… አውራ ጣትና አውራ ጣትን በገመድ ያስሩና ርቆ ከተሰቀለ ባላ ላይ ያቆማሉ፡፡ ከስር የተቆመበትን ወንበር ጎትተው ሲጥሉት ..ስቃዩና ሰቆቃው አይጣል ነው፡፡ ስንቱ የጀርባ ህመምተኛ፣ ስንቱ መሽናት አቅቶት እየተንፏቀቀ እንዳለ ብታይ …አየሽው /ክብዱን እያሳኝ ለምጥ/ ይሄ ለብዙ ጊዜ ያሰቃየኝ ቁስል ነው ደብድበውኝ፡፡ የእኔ ጓደኛ ተደብድቦ ተደብድቦ በሽተኛ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ መለሱት---በተመለሰ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሞተ። መቼም ብዙ መከራ አሳለፍን፡፡

ከሌላቸው ወጣቶች ጋር ሆኜ በረሃ ለበረሃ አስር ቀን ተጓዝን፡፡ በመሃል የሚሞት አለ፤ ለመቅበር እንኳን አቅም አልነበረንም፣ ጥለነው ነው የምናልፍ። ባለፍንበት መንገድ ክፉኛ ሽታ ያለበት ያጋጥመን

ነበር፡፡ ምን መሰለሽ? እንደኛ ሳኡዲ ለመግባት ተሽሎክሉከው መንገድ የሚያሳብሩ ሰዎች ሞተው፤ የሚቀብራቸው አጥተው በየስፍራው ተጥለዋል፡፡ ውይ…አጥንታቸው ብቻ ቀርቶ--.ስናይ እናለቅስ ነበር፡፡ አብረውኝ የነበሩ ጓደኞቼም ሞተው አልቀዋል፡፡

/በረዥሙ ተንፍሶ ለአፍታ ቆዘመ/ አንዱ ከሃገሬ

አብሮኝ ተነስቶ ሳኡዲ ድንበር ሲደርስ ሞተ፡፡ አሁን ለቤተሰቦቹ ምን እንደምናገር እንጃ?

እንዴት ወደ ሳኡዲ ገባህ?እንደምንም ተሽሎኩልኬ ሳኡዲ ገጠር ገባሁና

በእረኝነት ስራ ጀመርኩ፡፡ስንት ይከፍሉህ ነበር ?.አራት መቶ ሪያድ ተቀጥሬ ነበር፤ ግን የሰራሁት

ለሁለት ወር ነው፡፡ እሱንም በኪሴ ይዤ ወደ ጓደኞቼ ስሄድ ሌባ ቀማኝ፡፡ ጓደኞቼ ጋ ስሰራም እንዲሁ ያገኘሁትን ገንዘብ ተነጠቅሁ፡፡ እና የሚመስለኝ አበሻ ለእነሱ ርካሽ እቃ ማለት ነው፡፡ ጢባ ጢቤ የሚሉት፡፡ አንድ ማዳም ‹‹ባሌን ልትቀማኝ ነው፣ ይዛብኛለች›› ብላ ያሰበቻትን ኢትዮጵያዊ ፣ እጅዋን እንደቆረጠቻት አውቃለሁ፡፡ አሰርተው ገንዘባቸውን ይከለክሏቸዋል፡፡ ስንቱ ኢትዮጵያዊ ነው መንገድ ለመንገድ እያደረ የሚኖር--

እስር ቤት ነበርክ ?አዎ ሁለት ወር እስር ቤት ነበርኩ፡፡ ጠዋት

አንድ ቂጣ፣ ማታ አንድ ቂጣ ነበር የሚሰጡን፡፡ ብዙ እስር ቤት አላቸው፣ ብዙ አበሻም እስር ቤቱን አጣቦታል፡፡ ስንናገር ‹‹ዝም በሉ ከብቶች›› ተብለን እንደበደባለን፡፡ ባህሬንና ፓኪስታኖች ሲያወሩ ያዳምጧቸዋል..እኛን ግን ንቀታቸው የትየሌሌ ነው።

አሁን ወደ ትውልድ አገርህ ነው የምትመለሰው?ደውዬላቸዋለሁ፡፡ ወደ ቤት ነው የምመለሰው።

ሐ) እራስን በማወቅ፤ ከዓለት በጠነከረ መሰረት ላይ ሐሳባችንን መስርተን፤ በማንኛውም ጥርጣሬ የማይነዋወጥ ከራስ ከውስጥ የመነጨ “እያሰብኩ ስለሆነ እኔ ኅልው ነኝ” የሚል ግለሰባዊነት ላይ

“ የፍጽምና ባህሪ ያለው ፈጣሪ ደግሞ ጎደሎና ሐሰት የሆነ ነገር/ሐሳብ እንድናስብ አይፈቅድም፤ምክንያቱም

ከባህሪው ጋር አይስማሙምና ማለት ነው።

እዚህ ዓለም ላይ ያሉ ቁስ አካላትም (በሰው ውስጥ ያሉትንም ጨምሮ) እውነት

ናቸው ማለት ነው። የተምታታ ሐሳብ እንዲኖረኝ የሚያደርገኝ ሙሉ የክፋት አቅሙን አሟጥጦ

የሚጠቀም ያ “አወናባጅ ዲያብሎስ” ነው እንጂ ፈጣሪ

ሊሆን አይችልም። የአወናባጁን ዲያብሎስ ምክር እየለየን ማሰብ ከቻልን፣ ወደ

እርግጠኛ እውቀት የምናደርገው ጉዞ የተሳካ ይሆንልናል

ማለት ነው።

Position: General Forman Qualification: Technical College Diploma Experience: Minimum 8 years of relevant

experience specially in multi store building construction

Employment Status: Contract Required No. 1 (one)Salary: As per the company’s salary scale and benefits package Place of work: Addis Ababa

Interested and qualified applicants are invited to submit their non-returnable applications with CVs and copies of their testimonies in person to our office located at the Mechare Meda Compound within 7(seven) days of this announcement.

Tel. 011 371 57 00/011 371 56 93 Mechare Meda compound (Sarbet)

HUDA Real Estate PLCVACANCY ANNOUNCEMENT

HUDA Real Estate PLC (Member of the MIDROC Ethiopia Technology Group) is looking for competent and dedicated professionals for the following post.

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 16

Interested Bidders fulfilling the above Minimum requirements must:i. Collect the bid document from November 18, 2013 to November 29, 2013 during office hours by paying a non returnable Birr 50.00.

ii. Deliver the completely and appropriately filled document to PSI/Ethiopia office in a sealed envelope before Friday November 29, 2013 at 5:00 PM.

iii. Tenders received after the closing date and time, received through e-mail, telegraph or telephone WILL be automatically rejected. iv. Suppliers should submit Bid Security Bond Amounting ETB 10,000 in the form of CPO or Bank Guarantee in the Technical Proposal Envelopev. PSI/Ethiopia reserves the right to cancel the whole bid, accept or reject any or all of the bids.

Address: PSI/EthiopiaBole Sub City Kebele 03/05; Bole Medhanialem Church Area; Adjacent to EDNA Mall; Opposite Harmony Hotel; Tel: - +251-11 618 9590 / 618 9553 / 618 7489 Fax: - +251-11 662 7762, Addis Ababa, Ethiopia

Invitation to Bid INDEFINITE QUANTITY CONTRACT

PROVISION OF OFFICE SUPPORT SERVICES (Photocopy/Binding/Certificate Printing)(PSI/003/2014)

PSI/E would like to invite all interested companies to compete for the supply of Office Support Services. NOTE: - The purpose of this Invitation to Bid is to solicit bids from local vendors who specialize in Office Support Services (Photocopying/Binding/Certificate printing …etc) for its needs through 2014 with a possibility of extension for extra one year based on performance.

Minimum requirement to participate in the bidCriteria

1 Does the company willing to invoice PSI on a Monthly Basis?

2Does the supplier Submitted clear copies of Renewed Business License, TIN Certificate and VAT Registration Certificate?

3 Having at least 2 heavy duty Photocopy machine with ADF4 Having at least 1 unit of Comb Binding Machine5 Having at least 1 unit of High Volume Color Printer6 Having at least 1 unit of Laminating Machine Capable of Laminating A4 size paper/Certificate7 Is the Organization willing to Deliver the completed work up to PSI Ethiopia Office/Warehouse?8 Is supplier willing to fix its price through the contract period?

To compete, interested bidders who fulfil the above pre-requisite must:i. Collect the bid document from November 18, 2013 to November 29, 2013 during office hours by paying a non returnable Birr 50.00.

ii. Deliver the completely and appropriately filled document to PSI/Ethiopia office in a sealed envelope before Friday November 29, 2013 at 5:00 PM.

iii. Tenders received after the closing date and time, received through e-mail, telegraph or telephone WILL be automatically rejected. iv. Suppliers should submit Bid Security Bond Amounting ETB 10,000 in the form of CPO or Bank Guarantee in the Technical Proposal Envelopev. Bidders are required to follow all stated instructions and submit all required information and documents, failure to do so will be grounds for

automatic disqualification. vi. PSI/Ethiopia reserves the right to cancel the whole bid, accept or reject any or all of the bids.

Address: PSI/EthiopiaBole Sub City Kebele 03/05; Bole Medhanialem Church Area; Adjacent to EDNA Mall; Opposite Harmony Hotel; Tel: - +251-11 618 9590 / 618 9553 / 618 7489 Fax: - +251-11 662 7762, Addis Ababa, Ethiopia

Invitation to Bid INDEFINITE QUANTITY CONTRACT

PROVISION OF MALE CONDOM DEMONSTRATION MODEL(PSI/002/2014)

PSI/E would like to invite all interested companies to compete for the sign an indefinite quantity contract for the supply of Male Condom Demonstration Model (Penile Model) through 2014 with a possibility of extension for additional one year.Immediate Requirement = 2,000 Pieces

Minimum requirement to participate in the bidSr. No Criteria

1 Does the supplier submit clear copies of Renewed Business License?

2 Does the supplier submit clear copies of TIN Certificate?

3 Does the supplier submit clear copies of VAT Registration Certificate?4 Does the supplier Accept PSI Payment Term?

5 Does Supplier submit Bid Security Bond amounting ETB 10,000 CPO or bank guarantee

6 Does the sample Presented is acceptable to PSI Ethiopia?7 Does the supplier willing to Fix per unit Price for the duration of the contract?

ማስታወቂያ

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 17 ማስታወቂያ

Invitation to Bid INDEFINITE QUANTITY CONTRACT

STATIONARY ITEM SUPPLY(PSI/004/2014)

PSI/E would like to invite all interested companies to compete for the supply of Various Stationary Items. NOTE: - The purpose of this Invitation to Bid is to solicit bids from local vendors who specialize in Supply of Stationary Items needed for various projects through 2014.

Minimum requirement to participate in the bid

To compete, interested bidders who fulfil the above pre-requisite must:i. Collect the bid document from November 18, 2013 to November 29, 2013 during office hours by paying a non returnable Birr 50.00.

ii. Deliver the completely and appropriately filled document to PSI/Ethiopia office in a sealed envelope before Friday November 29, 2013 at 5:00 PM.

iii. Tenders received after the closing date and time, received through e-mail, telegraph or telephone WILL be automatically rejected. iv. Suppliers should submit Bid Security Bond Amounting ETB 10,000 in the form of CPO or Bank Guarantee in the Technical Proposal Envelopev. Bidders are required to follow all stated instructions and submit all required information and documents, failure to do so will be grounds for

automatic disqualification. vi. PSI/Ethiopia reserves the right to cancel the whole bid, accept or reject any or all of the bids.

Address: PSI/EthiopiaBole Sub City Kebele 03/05; Bole Medhanialem Church Area; Adjacent to EDNA Mall; Opposite Harmony Hotel; Tel: - +251-11 618 9590 / 618 9553 / 618 7489 Fax: - +251-11 662 7762, Addis Ababa, Ethiopia

1 Criteria  Does the supplier submit Clear copies of renewed & relevant business license, VAT Certificate and TIN Certificate?

Does Supplier submit Bid Security Bond as per PSI Requirement?Does the supplier willing to accept PSI Payment Terms?

  Does the supplier have a dedicated shop with at least 1 full time staff?  Does the supplier have either Fax or email for future communication with PSI?  Is the supplier willing to fix the price for the contract period?  Does the Product Sample Quality Provided acceptable to PSI Ethiopia?  Is the supplier willing to deliver the items ordered at PSI Warehouse at Gerji area?

• Bidders may obtain bidding documents from PSI Ethiopia Office (See Address Below) during office hours starting from November 18, 2013 until November 29, 2013 by paying a non-refundable fee of Br. 50 (fifty birr).

• Wax sealed and stamped bid documents must be delivered to PSI Ethiopia office on or before Friday November 29, 2013, 4:00 p.m. late bids shall be rejected. Bids must be submitted along with Br. 10,000.00 (Ten Thousand Birr) bid security in the form of Cash Payment Order (CPO) or Bank Guarantee in the Technical proposal envelope.

• PSI Ethiopia reserves the right to reject any or all bids.PSI Ethiopia AddressPSI/Ethiopia, Bole Medhaneyalem Church area, adjacent to Edna mall, opposite to Harmony Hotel Tel: - +251-116-189553/90 Fax: +251-116-627762, Addis Ababa, Ethiopia

Invitation for definite Quantity Contract for the Production, Transportation and Installation of

70 Metal Sign boards Bid No. PSI/001/2014

1. PSI Ethiopia, an International Humanitarian Organization, invites sealed bids from eligible bidders to produce and install 70 sign boards in different parts of the country.

2. Interested bidders are required to fulfill the following prequal-ification criteria

Sr.No. Criteria1 General Prequalification

 

Submitting Clear copies of renewed & relevant business license, VAT registration Certificate , TIN Certificate

 Submit Bid Security Bond amounting birr 10,000.00 in CPO or bank Guarantee

 willing to accept PSI Payment Terms (30 days after delivery)

2 Machine Availability and FunctionalityHaving at least 1 piece of Large Size (3 Meter or Above) Digital Printing Machine capable of printing at 1200 DPI (in good working condition)

እውቀት እንደሚያሰፋልን የታወቀ ነው፡፡ ችግሩ የሚመጣው ግን እንግሊዝኛ የምንጠቀመው፣ ‘አማርኛ ቀሺም’ ስለሆነ አይነት የቀሸመ አስተሳሰብ ሲኖር ነው፡፡ እናማ…ሰዎች የቋንቋ ችሎታቸውን ለማሻሻል የሚያደርጉት ጥረት ሁሉ አሪፍ ነው፡፡ ግን በእንግሊዝኛ ማሰብና በአማርኛ ወይንም በሌላ አገርኛ ቋንቋ ማሰብ ልዩነቱ የሀሳብ ክብደትና ቅለት ሳይሆን የተጠቀምንበት ቋንቋ ነው…አለቀ፡፡)

እናላችሁ… “አማርኛ መናገርና ድንጋይ መወርወር ክልክል ነው...” ከሚለው ‘ማስታወቂያ’ ጀርባ ያሉ ሰዎች የውጪ አገር ሰዎች ከሆኑ የለየላቸው ዘረኞች ናቸው፣ አበሾች ከሆኑ ‘ዘመናዊ እንቁላል ሻጮች’ ናቸው፡፡ ቂ…ቂ…ቂ…

ስሙኝማ… ‘እንደ አሜሪካዊ ለመናገር’ በጉሮሯቸውና በአተነፋፈሳቸው ላይ ‘ሽብር የሚነዙ’ ሞልተውላቸኋል፡፡ አሀ… ስምንት ደብል

ጥጋብ ከገፅ 7 የዞረ

ፊደል ከገፅ 12 የዞረ

ብርሌ በአርባ አምስት ደቂቃ ውስጥ የጠጣ ሰው እንኳን የእነሱ ያህል ፊደሎቹን አይፈረካክስም! እነኚህ አይነቶቹ ዋናው ግባቸው ምን ይመስለኛል መሰላችሁ… ‘የፈረንጅ አፍ’ ለማወቅ ሳይሆን ‘የፈረንጅ አፍ እንደሚያውቁ’ ሌላው እንዲያቅላቸው ነው፡፡ እንግዲህ ጨዋታም አይደል… እንደው ዝም ብሎ “አድንቁኝ!” ምናምን ማለት አሪፍ አይደለም፡፡ ይቺን ስሙኝማ…ሰውየው ለራሱ ያለው አመለካከት ትንሽ የተጋነነ ነው፡፡ ታዲያላችሁ… አድናቆት ፍለጋ አንዱ ጓደኛውን “አንድ ሰው አንድ አህያን ሲደበድብ ባየውና አህያውን ባስጥለው ምን አይነት ፍቅር አሳየሁ ማለት ነው?” ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ጓደኛ ሆዬ ምን ብሎ መለሰለት መሰላችሁ… “ወንድማዊ ፍቅር!”

እናላችሁ… በግድ “አድንቁኝ!” አሪፍ አይደለም!‘ጥጋብ’ እና ‘ዘመናዊነትን’ መለየት

የሚያስችለውን ልቦና ይስጠንማ!ደህና ሰንብቱልኝማ!

ላቲኑ - ሌላውም በጭራሽ አልተነካም፡፡ ቴክኖሎጂ ያለውን በሚመጥንና በሚያካትት መጠን ይሠራል እንጂ ያለው ነገር ለቴክኖሎጂው ሲባል መሠረቱን እንዲለቅ አይደረግም፡፡ ስለዚህ ጥያቄውን የማይረባና ተገቢ ያልኾነ አድርገን እንጥለዋለን፡፡ የሥነ ጽሑፍ ዕድገት ጥያቄ፡-

“የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ” የማለትም ያህል ይሆናል፡፡ ከፊደላቱ የተወሰኑትን አጉድሎ የየትኛውም ቋንቋ ሥነ ጽሑፍ አልተመነደገም። በሞክሼ ፊደላት ሰበብ ይህ የስነ ጽሑፍ ዕድገት ይጠቀስ እንደኾነ አፍን ሞልቶ መናገር ባይቻልም፣ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ፣ ዘንድሮም የነዚህን የሞክሼ ፊደላትን ነገር የሚያነሳሱት ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ፣ በአንድ የመጽሔት ጽሑፋቸው ላይ ፊደላቱ ከገበታው መገኘታቸውን በማማረር፣ “የድሮን ነገር ለመጠበቅ ወግ ሲባል የዛሬው ዘመኑ እንዲጋረድብን /እንዲጨልምብን” መደረግ እንደሌለበት በሚከብድ ኃይለ ቃል የጻፉትን በማሰብ፣ የእነዚህ ፊደላት መኖር እንዲያ ያለ ጽልመት ውስጥ እንደሚጨምረን የታሰበው ምናልባት ከዚህ የሥነ ጽሑፍ ዕድገት ጋር ታስቦ ይኾን እላለሁ፡፡

ይህ የስነ ጽሑፍ ዕድገት ጥያቄ በኢትዮጵያ

ቋንቋዎች ጥናት ተቋም አስቀድሞ እንደ አንድ ነጥብ ሲጠቀስ እናስታውሳለን፡፡ ለሞክሼዎቹ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በፊደላቱ ላይ ለሚወሰድ እርምጃ የተጠቀሰ ነበር፡፡

የስነ ጽሑፍ ዕድገት ጥያቄ ፊደልን በማጉደልና በመለወጥ ረገድ ከሚነሣ ይልቅ እንዳሉ ቢቀመጡ ከሚናገረው ወገን ቢጠቀስ የበለጠ በተመቸ ነበር። ፊደልን በመነካካት (በመቀየር፣ በማጉደል …) ስነ ጽሑፍ እንዴትም ኾኖ እንደማይበለጽግ ሲታሰብ፣ ጥያቄው ጩኸትን የመቀማት ያህል ኾኖ ይታሰባል። ይልቅስ ዛሬ ድምፃቸው አንድ ኾነ ተብሎ እንዳሻ በመጻፍ የሚታየውን ጉድለት ለማስቀረት፣ የነዚያን አገባብ ለይቶ ዐውቆ፣ ማሳወቅና መጠቀም እንጂ፣ የነዚህ መኖርስ ስነ ጽሑፍን ሊበድለው አይችልም።

ለማጠቃለል፣ በሞክሼ ፊደላቱ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ያሉት ሰበቦች እነዚህን የመሰሉ ሲኾኑ፣ አንዳቸውም ግን ሚዛንን ሊያነሱ ቀርቶ እንደ ምክንያት እንኳ ሊቆጠሩ አቅም ያላቸው አይደሉም። ይልቅስ በተቃራኒው፣ “ማሻሻል” በምትል መልካም ቃል የሚታሰበው የመቀየር፣ የማጉደልና ሌላም እርምጃ ቢፈጸም የሚደርሰው ጥፋትና ጉድለት ብሶ እንደሚገኝ ማስተዋል ይገባል፡፡

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 18

ፎቶ

አን

ተነህ

አክ

ሊሉ

ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 200 ሚ.ብር ይፈጃል

ንግድና ኢኮኖሚ

መንግሥቱ አበበ

ለባህሬን የምትሮጠው አትሌት ማርያም የሱፍ ጀማልና ባለቤቷ አቶ ወንድወሰን ዲሶ (ታረቅ) በአዲስ አበባ ከተማ መገናኛ አካባቢ፣ ከዳያስፖራ አደባባይ ፊት ለፊት ዳገቱ ላይ ያሠሩት ዘመናዊ ባለ “4 ኮከቡ” ቤላ ቪው ሆቴልና ስፓ ዛሬ ይመረቃል፡፡

የቬላ ቪው ሆቴልና ስፓ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወንድወሰን ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ፣ ሆቴሉ 35 ክፍሎችና ስፓ ሲኖረው፣ ስፓው በውበትና በትልቅነት በመዲናችን ብቻ ሳይሆን በአገራችንም የመጀመሪያው እንደሆነ ተናግሯል፡፡ በ “ሶፍ ኦማር” የተሰየሙ ስፓ፣ አዋሽ ሳውናና ስቲም፣ ዳሎል ጃኩዚ ትክክለኛው ሞሮኮ ባዝ፣ የእጅ፣ የእግርና የጥፍር መዋቢያ፣ የሴቶችና የወንዶች ፀጉር ቤት፣ ቦብ ማርሌ የፊት ማስዋቢያ እንዲሁም በላሊበላ፣ አክሱም፣ ፋሲለደስና ኮንሶ የተሰየሙ የማሳጅ ክፍሎች እንዳሉት ሥራ አስኪያጁ አብራርቷል፡፡

ሆቴሉ ላይ ሆኖ አዲስ አበባን መመልከት ልብ ይማርካል ያለው ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ከጀርባ ያለው ተራራ ፈረንሳይ ሌጋሲዮንን ከመጋረዱ በስተቀር በሁሉም አቅጣጫ ከተማዋን ፍንትው አድርጐ በማሳየት፣ በከተማዋ ካሉ ሆቴሎች ሁሉ ይልቃል ብሏል፡፡ ቬላ ቪው በፈረንሳይኛ “ጥሩ፣ ውብ፣ ቆንጆ፣ እይታ” ማለት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ባለ ስንት ኮከብ እንደሆነ ተጠይቆ ባለቤቱ ሲመልሱ፣ ከሆቴልና ቱሪዝም ሚ/ር የመጡ ባለሙያዎች ሆቴሉ ያሉትን ፋሲሊቲዎች ካዩ በኋላ፣4 ኮከብ ሊያሟላ እንደሚችል አረጋግጠው፣ “ከፈለጋችሁ 5 ኮከብ ጠይቁ” እንዳሏቸው ተናግሯል፡፡ ሆቴሉ የመዋኛ ገንዳና ከቤት ውጭ ስፖርቶች ማካሄጃ ቢኖረው፣ ባለ 5 ኮከብ ደረጃ ሊያሟላ እንደሚችል ጠቅሶ፣ መጀመሪያውኑ ዕቅዳቸው ባለ 4 ኮከብ ስለሆነ፣ በዚሁ ደረጃ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት እንደሚቀጥሉ ተናግሯል፡፡

ባለ “4 ኮከቡ” ቤል ቪው ሆቴልና ስፓ ዛሬ ይመረቃል

የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ እንዳለ ሆኖ፣ ሆቴሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ የስዊስ፣ የፈረንሳይና የጣሊያን ምግብ እንደሚያዘጋጅ የገለፀው አቶ ወንድወሰን፣ ለዚህም በፓሪስ ሂልተንና በሌሎች ታዋቂ ሆቴሎች የሠራና ብዙ ልምድ ያለውን ፈረንሳዊ የምግብ አዘጋጅ (ሼፍ) መቅጠሩንና በፓሪስ ሂልተን በኃላፊነት ትሠራ የነበረችውን ፈረንሳዊት በኦፕሬሽን ማናጀርነት ማምጣቱን አስታውቋል። እንዲሁም ሠራተኞቹ እንግሊዝኛ፣ ጀርመንኛ፣ ዐረብኛ፣ ፈረንሳይኛና ኪስዋሂሊ አቀላጥፈው የሚናገሩ ስለሆነ፣ ከእንግዶች ጋር የመግባባት ችግር እንደማይኖርና ከፍተኛ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስታውቋል፡፡

የሆቴሉ ግንባታ 95 ከመቶ የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ ጥቂት የሚቀር ሥራ ስላለው ወጪው በትክክል ያለመሰላቱን ባለ ሀብቱ ጠቅሶ፣ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 200 ሚሊዮን ያህል ብር እንደሚፈጅና ለ143 ዜጐች የሥራ ዕድል መፈጠሩን፣ በአጠቃላይ ሥራው ሲጠናቀቅም የሠራተኞቹ ቁጥር 250 እንደሚደርስ ተናግሯል - አቶ ወንድወሰን፡፡

ከሁሉም በላይ የሚያስጨንቃቸው የእንግዶቻቸው ደኅንነት በመሆኑ፣ 67 የደህንነት መቆጣጠሪያ ካሜራዎችና እሳት ቢነሳ ጪስ ጠቋሚ መሳሪያዎች መተከላቸውን፣ በሪሞት መቆጣጠሪያ የሚታዘዙት አምፑሎች 12 ዓይነት ቀለም እንደሚፈነጥቁ፣ … ተገልጿል፡፡ ከጃፓን የተገዙት የመታጠቢያ ክፍል ዕቃዎች ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያላቸው ሲሆን የ30 ዓመት ዋስትና የተረጋገጠላቸው መሆኑም ተነግሯል፡፡

የቤላ ቪው ሆቴል ግንባታ ስድስት ዓመት ያህል እንደፈጀ የጠቀሰው አቶ ወንድወሰን፣ ቦታው ዳገት ላይ በመሆኑ በተፈጠረው አስቸጋሪነት፣ የሚያምርና የሚያኮራ ነገር ለመሥራት በመፈለጋቸውና አንድ አገልግሎት ሰጪ መ/ቤት በፈፀመባቸው በደል፣ ግንባታው ሊዘገይ መቻሉን ገልጿል። የተፈፀመባቸው በደል ምን እንደሆነ ተጠይቆ ሲመልስ፣ “ጥሩ መ/ቤቶች የመኖራቸውን ያህል በደል የፈፀመብንም አለ፡፡ ሙስና ገንዘብ መስጠትና

መቀበል ብቻ ሳይሆን የመልካም አስተዳደር ጉድለትም ሙስና ነው፡፡ ይህን ኢንቨስተሮችን የሚያባርር በደል፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ማወቅ አለበት፡፡ አራት ኪሎ የሚገኘው የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን ጽ/ቤት ከፍተኛ በደል አድርሶብናል፡፡ ያልገባንበት ባለሥልጣንና ኃላፊ ቢሮ የለም፡፡ ሊያነጋግሩን እንኳ ፈቃደኞች

አይደሉም፡፡ ይኼ ሆቴል ሥራው ያለቀው ከአምስት ወር በፊት ነው፡፡ መብራት ስለሌለን፣ የተገጠሙትን ዘመናዊ መሳሪያዎች መሞከር አልቻልንም፡፡ እንቢ ብለውን ቆይተው “እንግዲያውስ አገሪቷን ጥለን እንወጣለን” ስንላቸው በስንት መከራ ባለፈው ሳምንት አስገቡልን፡፡ የዚያኑ ያህል ጥሩ መ/ቤቶችም ስላሉ መመስገን አለባቸው። ቴሌና የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን እራሳቸው አስገብተውና ፈትሸው ነው ያስረከቡን፡፡ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ የመብራት ኃይል በደል በእኛ ላይ ብቻ አይደለም፡፡ ሌሎችንም እያስለቀሰ ነው፡፡ አንተ ዕድለኛ ነህ፤ እኛ ከ8 ወር በላይ ጠብቀን አልሆነልንም’ ያሉኝ አሉ” በማለት ምሬቱን ገልጿል፡፡

ለበርካታ ዓመታት ስዊስ የኖረው አቶ ወንድወሰን አትሌት የነበረ ሲሆን፣በአሁኑ ወቅት የባለቤቱ የማርያምና የባህሬን ብሔራዊ አትሌቲክስ ቡድን አሠልጣኝ ነው፡፡

መድረስ። (“Cogito, ergo sum”)“የስሜት ህዋሳት አንዳንዴ ያጭበረብሩናል።

ባለ ጠርዙን ማማ ከሩቅ ስናየው ድቡልቡል አድርገው ያሳየናል፤ ቀጥ ያለ እንጨት ውኃ ውስጥ ብንከትተው ስብርብር ያለ ሆኖ ይታዩናል፤ ስለዚህ የስሜት ህዋሳት የሚታመን ብያኔ አይሰጡንም ማለት ነው። አንዳንዴ ደግሞ ህልምና እውኑን መለየት ይቸግራል፤ “አልጋው ላይ እንዳልተጋደመ ሰው ሁሉ ጥርት ያሉ ምስሎችን አያለሁ፤ በህልሜ መሆኑን እንኳን የምለይበት ምንም ምልክት አጣለሁ” ዴካርት ይህንን እያምሰለሰለ ይቀጥልና እንዲህ ይለናል። “በስሜት ህዋሳቶቼ የማገኘውን መልእክት ባልቀበልም ይኸው ደግሞ ሌላ እውነት የሚመስል ነገር የሚያሳውቀኝ ሌላ መንገድ አለ።” የህልሙን እና የስሜት ህዋሳቱን መልእክት ይበልጥ እያፍተለተለ ከፍ ወዳለ ሃሳብ ይወሰደዋል። “የሚያታልለኝ ኃይል አለ ማለት ነው።ፈጣሪ ይህንን ሊያደርግብኝ ይችላልን? ይህንን ካደረገብኝማ “ፍጽምና” ባህሪው ሊሆን አይችልም። ስለዚህ እኔን ለማወናበድ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ የሚሰራ ሌላ አወናባጅ ዲያብሎስ አለ ማለት ነው” ይላል ዴካርት።

ስለዚህም የዚህን አወናባጅ ዲያብሎስ ምክር ለማሸነፍ ሐሳቦቸን ግልጽ፣ ልዩ (እራሱን የቻለ) እና እርስ በርሱ የማይፋለስ በማድረግ ወደ ፍጹማዊው የፈጣሪ ባህሪ ማስጠጋት አለብን ማለት ነው። ሐሳባችንን በዚህ ቀመር ማስላት ከቻልን፣ በንጹህ ልቦናችን ፈጣሪ እውነትን ስለሚለግሰን ለምናስበው ነገር እርግጠኛ መሆን ይቻለናል ማለት ነው።

በዚህ የሒሳብ ቀመራዊ አስተሳሰብ እየተመራን የማንጠራጠረው እውቀት ካገኘንና ጥያቄዎቻችንን ሁሉ መመለስ ከቻልን የእራስ ኅልውና አገኘን ማለት ነው። በአካባቢያችን ያሉትን ሁሉንም እየተጠራጠርንና እየጠየቅን በቀላሉ ስለ ህልውናቸው እርግጠኛ መሆን አንችልም፤ ነገር ግን አንድ መካድና መጠራጠር የማልችለው እውነት አለ፤ ይኸውም በአሁኑ ሰዓት እያሰብኩ መሆኑን ልቦናዬ እየነገረኝ ነው።

“እያሰብኩ ስለሆነ ኅልው ነኝ ማለት ነው” ይለናል ዴካርት። ሁሉንም የቀደሙ እውቀቶችን እንዲፈትሻቸው የነገረው አንድ እርግጠኛ የሆነ ሳይንሳዊ እውቀት ፍለጋ ሲሆን፤ አንድ እርግጠኛ እውነት ካገኘ ሙሉ ፍልስፍና አድርጎ ሥጋና ደም እንደሚሰጠው እርግጠኛ ነበረ፤ ዴካርት። ስለሆነም አሁን ልቦናው የሚነግረው እርግጠኛ እውቀት እያሰበ መሆኑን ሆኖ አገኘው። እኔ ግን ምንድን ነኝ? ይላል እንደገና። የሚያስብ ቁስ ነኝ ማለት ነው። አዎን እያሰብኩ መሆኔን መካድ ስለማልችል፤ እኔ የማስብ ነገር ነኝ ማለት ነው። የማስበው በአእምሮዬ ነው፤ አእምሮ ደግሞ ግዙፍ አካል የለውም። ረቂቅ ነገር ነው፤ ስለሆነም አይበሰብስም፣ አይፈረከስም፣ አይሞትም ማለት ነው። ሆኖም አሁንም መልስ ያላገኘንለት ነገር አለ። እኔ ከየት መጣሁ? እናትና አባቶቼ ለእኔ መፈጠር ምክንያቶች እንጂ ፈጣሪዎቼ አይደሉምና።

የእራሳችን አስገኝዎች እኛው እራሳችን ልንሆን ደግሞ በፍጹም አንችልም። ስለሆነም ማሰብ እንድንችል አድርጎ የፈጠረን ፍጹም እና “ገባሬ ኩሉ” የሆነ ፈጣሪ መኖሩን በዚሁ እንረዳለን ማለት

ነው፤ ይለናል ዴካርት። የፍጽምና ባህሪ ያለው ፈጣሪ ደግሞ ጎደሎና ሐሰት የሆነ ነገር/ሐሳብ እንድናስብ አይፈቅድም፤ምክንያቱም ከባህሪው ጋር አይስማሙምና ማለት ነው። እዚህ ዓለም ላይ ያሉ ቁስ አካላትም (በሰው ውስጥ ያሉትንም ጨምሮ) እውነት ናቸው ማለት ነው። የተምታታ ሐሳብ እንዲኖረኝ የሚያደርገኝ ሙሉ የክፋት አቅሙን አሟጥጦ የሚጠቀም ያ “አወናባጅ ዲያብሎስ” ነው እንጂ ፈጣሪ ሊሆን አይችልም። የአወናባጁን ዲያብሎስ ምክር እየለየን ማሰብ ከቻልን፣ ወደ እርግጠኛ እውቀት የምናደርገው ጉዞ የተሳካ ይሆንልናል ማለት ነው።

ልዕለ መልካምነት ባህሪው የሆነ ፈጣሪ መኖሩን ማወቅ አለብን። እዚህ ዓለም ላይ ያለው እውነት ስለመሆኑ እርግጠኛ እንድንሆን የሚያደርገን ፈጣሪ ፍጹም እና የመልካሞች ሁሉ መልካም በመሆኑ፣ ለኛም ግልጽ የሆነና የጠራ ሐሳብን ይለግሰናል፡፡

ዳካርት፤ ግልጽነት፣ ልዩነት እና አለመፋለስን እንደ ሒሳብ ቀመር፣ የአንድን ጉዳይ እውነተኝነት/እርግጠኝነት የምንመዝንባቸው አድርጎ ስለቀመራቸው በቤተሰቡ ስያሜ “”የካርቴዚያን ዲበ አካል” ተብሎ ተሰይሞለታል።

የአውሮፓዊያን የፍልስፍና አስተምህሮ ለመጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳቦች መልስ ለመስጠት መፍጨርጨሩ አልቀረም፡፡ (ፈላስፋው አማኝ ነኝ አሊያም ኢ−አማኒ ነኝ ቢልም)። የቀደመው የአውሮፓ ፍልስፍና የሳይንስን እና የመጽሐፍ ቅዱስን ግጭት፤ የመጽሐፍ ቅዱስን ረቂቅነት ማስገንዘብ፤ ወይም ሳይንስ መጽሐፍ ቅዱስን ሲያፈርሳት የሚከሰተውን ባዶነት መተንተን የሚመሳስሉ ሐሳቦች ያደሉበታል።

ዴካርት ከገፅ 15 የዞረየዴካርት አካሄድም ከዚሁ የተለየ አይመስልም። የስህተቶች ሁሉ ምንጭ አወናባጁ ዲያብሎስ ነው ይለናልና። “I will suppose therefore that ………rather some evil genius of the utmost power and cunning has employed all his energies in order to deceive me.”

በኛ አባቶች ትምህርት ዘንድ ደግሞ አንዳንድ ለየት ያሉ ታሪኮችን እንሰማለን። እኛው እራሳችን በራሳችን ፈቃድ የምናመነጫቸው የክፋት ሐሳቦች አሉን።

ከስሜት ህዋሶቻችን ከቅዠታችንም ባሻገር የሆኑ የክፋት ሐሳቦች። በአንድ ገዳም ውስጥ የተከሰተ እንደሆነ የሚነገር አንድ ታሪክ ለዚህ ማስረጃ የሚሆነን ይመስለኛል። ጉዳዩ እንዲህ ነው፤ የአንድ ገዳም ኃላፊ/አበመኔት/ ገዳማዊያኑን እየጎበኙ ሳለ ወደ አንድ አባት ዋሻ ይዘልቃሉ። እናም አባትን እንቁላል በጧፍ ሲጠብሱ ያገኟቸዋል፤ የጾም ወቅት ነበርና በመጥበሻ ቢጠብሱት እንቁላሉ ሊሸትና ሊታወቅባቸው ስለሆነ በጧፍ ተያይዘውታል። ኃላፊውም ይደነግጡና “ኧረ! ኧረ! አባቴ ምን ነካዎት? በጾሙ እንቁላል?” ይላሉ። ባለዋሻውም ተጸጽተው “ኧረ ይቅር ይበሉኝ ሰይጣን አሳስቶኝ ነው” ማለት። ጋሽ ዲያብሎስ ደግሞ ወዲያው ከተፍ አለና “ኧረ ይቺን እንቁላል አጠባበስ ያለዛሬም አላየኋትም” አለ አሉ።

የኛ አባቶች እንዲህ ናቸው፤ ደረቅ እና ረቂቅ ሐሳቦችን በምሳሌና በተረት እያዋዙ ማቅረቡን ተክነውበታል። እንዲች ያለች መጽሐፍ ቅዱሳዊ አንድምታና ፍልስፍና ለኢትዮጵያዊ ካልሆነ ለአውሮፓዊ የምትቻለው አይመስለኝም።

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 19

አጭር ልብወለድ

እሳቱ ወደ ገፅ 23 ዞሯል

ጥበብኪነጥበባዊ ዜና

መልካሙ ተክሌ

በባህል አብዮቱ ወቅት፤ ቀይ ቃፊሮቹ፤ በየደረሱበት ያገኙትን ማናቸውንም አይነት ምስሎች እየሸረካከቱ፣ እየቦጫጨቁ ይጥሉ ጀመር፡፡ ከሊቀመንበር

ማኦ ምስል በቀር፡፡ የሀገረ ቻይናን ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሳ ቅርሶች ሁሉ እንክትክት አድርገው እየሰባበሩ ዱቄት አደረጉት፡፡ አንድም የመጽሀፍ ዘር የተባለ ሳይቀራቸው፤ ከያለበት ሰብስበው በማውጣት እሳት ለቀቁበት፡፡ ከሊቀመንበር ማኦ መጻሕፍት በቀር፡፡

በተቃዋሚ ጎራ የተፈረጁ ቤተሰቦች ዕጣ ፈንታ እጅግ መራር ነበር፡፡ ቀይ ቃፊሮቹ፤ ድንገት በራቸውን በርግደው ይገቡና ጓዳ ጎድጓዳቸውን ይበረብራሉ፤ የቤት እቃዎቻቸውን፡- ብስክሌት፣ የግርግዳ ሰአት፣ ጥሩ ጥሩ ልብሶችንና የህፃናት መጫወቻዎችንም ሳይቀር፤ ዋጋ ያወጣልናል ብለው የገመቱትን ነገር ሁሉ እየሰበሰቡ ይወስዳሉ። የማይፈልጉትን እንኳን አይተዉትም፤ ወደ ውጪ እየወረወሩ ከስክሰው ያደቅቁታል እንጂ፡፡ በቤተሰቡ አባላትም ላይ ጭካኔ የተሞላበት ድብደባ ይፈጽማሉ፡፡ አንዳንድ ልጃገረዶች፤በቤተሰቦቻቸው ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ያረገቡ መስሏቸው ለአብዮተኞቹና ጭፍሮቻቸው ክቡር ገላቸውን አበርክተዋል፡፡

በመንደሩ ውስጥ የሚኖሩ ድሃ ጭሰኞች፣ የበኩር ልጅ የሆነ አንድ መልከ ጥፉ ጎረምሳ ነበረ። ዕድሜው ከሰላሳዎቹ ቢዘልልም ሰነፍ፣ ዘልዛላና ጅላጅል ቢጤ ስለሆነ ትዳር ያልያዘ ‹‹ቆሞ ቀር›› ነው። “ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” እንዲሉ፤ በሀገሬው የተፈጠረውን ፖለቲካዊ ምስቅልቅል እንደጥሩ አጋጣሚ ቆጥሮ፣ በአንድ እጁ ማስፈራሪያ፣ መሸንቆጫ ጉማሬ አለንጋውን፤ በሌላ እጁ ቡትሌውን ጨብጦ፤ አዛዥ ናዛዥ ሆኖ ቁጭ አለ። ሀይ ባይ አጣ፡፡ በአሳቻ ሰአት ወጣት ልጃገረዶች ባሉበት የተቃዋሚ ቤተሰቦች ቤት እንዳሻው ዘው እያለ፤እምቡጥ ኮረዳዎቹን እያርበደበደ፤ እምቢኝ ብለው ሲተናነቁት እጃቸውን ጠምዝዞ ገፍትሮ በመጣል ጉልበት ከድቷቸው በወደቁበት ጨምድዶ ይዟቸው፤ አይናቸውን እያቁለጨለጩ ሲንፈራገጡ፤ይበልጥ ትንፋሽ አሳጥቶ ጉሮሯቸውን አንቆ በመያዝ፤ ልብሳቸውን እየሸነታተረ፤ አስገድዶ ይደፍራቸዋል፤ በእንባ እየታጠቡ፡፡

አቶ ሻንግ ደግሞ፤ ዕድሜያቸው ከስድሳው

እሳቱድርሰት - ሺ ፓንግ ፋን

ትርጉም - ፈለቀ የማርውሃ አበበ

የገፋ፤ በሰዎች ዘንድ በፀባይና ምግባራቸው የተከበሩ አዛውንት ናቸው፡፡ አብዛኛውን ዘመናቸውንም ያሳለፉት የባለጸጋ ነጋዴዎችንና የባለስልጣን ቤተሰቦች ልጆችን፤ ቱባውን የቻይና ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶችን፣ የኪነ ጥበባት፣ ኃይማኖታዊ ፍልስፍና … ትውፊታዊ አንድምታዎችን እውቀት በማስተማር ነው፡፡

ከሦስት ትውልዳቸው ጀምሮ በቅብብሎሽ የመጣውን ጥንታዊውን ዕምቅ ጥበብ ስለወረሱም፤ በጥልቅ ልቦና የተፀነሱ በርካታ የፈጠራ ስራዎችን አምጠው የወለዱ፤ ሰማየ ሰማያት የመጠቁ ረቂቅ ቅኔዎችን ስንኝ የሰደሩ… እንዲሁም ልዩ ግንዛቤ እሚሻውን የቻይናን የፊደል አፃፃፍና ትርጓሜ (ካሊግራፊ) ክህሎት ያካበቱ ‹‹አራት አይና›› ልሂቅ ናቸው፡፡ ይኸውም አፍ በእጅ የሚያሲዝ አድናቆትን የተናኘ ጉምቱ ስብዕናቸው፤ ከሚኖሩበት መንደር አልፎ በሌሎቹም አጎራባች ከተሞች ሁሉ፤ እንደ ብርቅ የሚታዩ ስመ ጥር ሰው አድርጓቸዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ዝናቸውን ያገነነው ግን ያሏቸው የመጻሕፍት ብዛት ነው፡፡

ከአያት ቅድመ አያቶቻቸው ጀምሮ፤ ቤተሰቦቻቸው ሁሉ ከፍተኛ የንባብ ፍቅር ያደረባቸው ነበሩ፡፡ የርሳቸው የመጽሀፍ ቁርኝት ደግሞ እብድ ሊያሰኛቸው የሚያደርስ ነው። ከሚያገኙት ገቢ አብዛኛውን ለመጻሕፍት መግዣ ያውላሉ፡፡ እንዲያውም፤ አንዳንድ ሰዎች፤ ‹ለመጽሀፍ መግዣ ያወጡትን ገንዘብ… እርሻ ቢያስፋፉበት ኖሮ፤ እንዴት ያሉ የመሬት ከበርቴ መሆን በቻሉ ነበር!› ይሏቸዋል፡፡ በመጻሕፍት ስብስቦቻቸው አይነት፤ በሰሜን ቻይና ውስጥ አቻ አይገኝላቸውም። በቁጥር ከሦስት ሺህ በላይ መጻሕፍት አሏቸው፡፡ አንዳንዶቹ በዋጋ

የማይተመኑና በሚንግ ና ሶንግ ዘመን (ከአምስት እስከ ስምንት መቶ አመታት በፊት) የተደጎሱ ናቸው፡፡ አቶ ሻንግ፤ በደብሊው ከተማ በተካሄደው የፖለቲካ ምክክር መድረክ ላይ፤ በክብር አባልነት ተጋብዘው የተሳተፉበት ጊዜም ነበር፡፡

ከ1949ኙ ለውጥ በኋላ ግን አቶ ሻንግ፤ ወደ ቀድሞው የመምህርነት ሞያ አልተመለሱም፡፡ ወደ ትውልድ መንደራቸው አቅንተው በጭሰኝነት መተዳደር ጀመሩ፡፡ ስለ ግብርና መጠነኛ ዕውቀት ስለነበራቸው፤ የመንደሩ ነዋሪዎች መልካም አቀባበል ነበር ያደረጉላቸው፡፡ አዛውንቱ ፤ አስተዋይ፣ ታማኝና ግብረገብ አዋቂ ከመሆናቸውም ባሻገር፣ የአዲስ አመት ብስራት መግለጫዎችን፣ በመንደሪቱ ውስጥ ለሚደገሱ የሠርግ በዐላት የሚሆኑ መጥሪያዎችን በማዘጋጀት፣ ስዕሎችን በመሳልና ግጥሞችን በመፃፍም ስለሚተባበሩ፤ በነዋሪዎቹ ዘንድ ተወዳጅ ሰው ሆኑ፡፡ እናም፤ እንደ አንድ ምስኪን ጭሰኛ ተረጋግተው በሚመሩት ሰላማዊ የገጠር ህይወት፤ ከፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ጦስ ሉተርፉ ችለዋል፡፡

የግርግሩ ወቅት ግን፤ እገሌ ከእገሌ፣ ትንሽ ትልቅ ሳይል፤ በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላሉት ሆነ በጭሰኝነት ለሚንገታገቱት ድሆች ሳይቀር እረፍት የሚነሳ አስከፊ ጊዜ ሆነ፡፡ ዜጎች፤ በየጣራቸው ስር የሚገኙ መጻሕፍቶቻቸውን አንዲትም ሳያስቀሩ መቀዳደድ ወይም ማቃጠልና ይህንኑም ድርጊታቸውን በየመንደሮቻቸው ታጥቀው ለሚንጎማለሉት የቀይ ቃፊሮቹ ጭፍሮች አሊያም ለአዛዥ ካድሬዎቻቸው ያሉበት ድረስ ሄደው የማሳወቅ ግዴታ ተጥሎባቸው ነበር፡፡ አዬ የቀን ጎዶሎ! እንግዲህ የአቶ ሻንግ መጻሕፍት ዕጣቸው ምን ይሆን? አዛውንቱ

“የቃቄ ወርድዎት” ትያትር ሊቀርብ ነው

ከመቶ ሃምሳ አመታት በፊት፣ በጉራጌ የሴቶች መብት ተሟጋች እንደነበረች በሚነገርላት የቃቄ ወርድዎት ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን በጥናት ላይ የተመሰረተ “የቃቄ ወርድዎት” የተሰኘ ትያትር በቅርቡ ለተመልካች እንደሚያቀርብ ብሔራዊ ትያትር ገለፀ፡፡

ትያትር ቤቱ ይሄን ትያትር ለማቅረብ ባለፈው ማክሰኞ ከጉራጌ ዞን አስተዳደር፣ ከጉራጌ ልማት ማሕበር እና ከቤተ ጉራጌ ባሕል ማዕከል ጋር የ1ሚ.259ሺ ብር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ በፊርማ ሥነ ሥርአቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የብሔራዊ ትያትር ቤት ዳይሬክተር ጀነራል አርቲስት ተስፋዬ ሽመልስ፤ ትያትሩ ከፆታ ጋር የተያያዙ የግንዛቤ ችግሮችን ለማስወግድ እንደሚያግዝ ገልፀዋል፡፡ “ትያትር ቤቱ ትያትሮች ከኢንተርኔት እየታጨዱ የሚቀርብበት አይደለም” ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በጥናት ላይ የተመሠረቱ ሥራዎች ቦታ እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ሽኩር በበኩላቸው፤ የቃቄ ወርድዎት “ለወንዶች ብዙ ሚስት ከተፈቀደ ለሴቶችም ብዙ ባል መፈቀድ አለበት” ማለቷን በመጥቀስ ለሴቶች መብት መከበር ያደረገችውን አስተዋፅኦ አብራርተዋል። “የቃቄ ወርድዎት” የተሰኘውን ትያትር የደረሰው ፀሃፌተውኔት ጫንያለው ወልደጊዮርጊስ ሲሆን “አዳብና” የተባለውን ትያትር ለመድረክ ያበቃው ዳግማዊ ፈይሳ እንደሚያዘጋጀውም ለማወቅ ተችሏል፡፡

“የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ፓርኮች ማውጫ” ታትሞ ወጣ

የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብቶች ዝርዝር የያዘ የተፈጥሮ ፓርኮች ማውጫ ታትሞ መውጣቱን “ሀገሬ ኮሙኒኬሽን” አስታወቀ፡፡ ከትናንት በስቲያ በነፃ መሠራጨት የጀመረው ቅጽ ፩ ማውጫ፣ 118 ገፆች ያሉት ሲሆን 59 ወንዞች፣ 40 ተራራዎች፣ 26 ሐይቆች፣ 24 ፓርኮች፣ 12 ዋሻዎች እና ሌሎችም በርካታ መረጃዎችን አካትቷል፡፡ “ቱባ” የተሰኘውን በየሁለት ወሩ የሚወጣ የቱሪዝምና ባሕል መጽሔት እያሳተመ የሚያሰራጨው “ሀገሬ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን”፤ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የቱሪዝም ማውጫ ሲያዘጋጅ የአሁኑ ሁለተኛው ሲሆን ከሁለት ሳምንት በፊት የሰሜን ሸዋ ዞንን መስሕቦች የሚያስተዋውቅ ማውጫ ማዘጋጀቱ ይታወሳል። ድርጅቱ የጎንደር መስሕቦች የሚተዋወቁበት ማውጫ በቅርቡ ለማስመረቅም በዝግጅት ላይ እንደሆነ ገልጿል። የ“ሐገሬ ሚዲያ ኮሙኒኬሽን” ሥራ አስኪያጅና የተፈጥሮ መስህብ ዳይሬክተሪው ዋና አዘጋጅ አቶ ሄኖክ ስዩም ስለማውጫው ሲናገሩ፤ “የሀገራችን የተፈጥሮ ሀብቶች ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ ልማት እንዲውሉና ሀገራችንን እንድንጎበኝ መነሳሳትን የሚፈጥር ነው” ብለዋል፡፡

የዳንኤል ክብረት “አራቱ ኃያላን” ሳምንት ይመረቃል

በተለያዩ የህትመት ውጤቶች ላይ በሚያቀርባቸው ወጎችና መጣጥፎች የሚታወቀው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ያዘጋጀው “አራቱ ኃያላን” አዲስ መጽሐፍ በመጪው ሳምንት እሁድ 4 ሰዓት ላይ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚመረቅ “አግዮስ ሕትመትና ጠቅላላ ንግድ” አስታወቀ፡፡ በምረቃው ዕለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ፣ ዶ/ር ውዱ ጣፈጠ እና ዶክተር አምሳሉ ተፈራ በመጽሐፉ ላይ አስተያየት እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡

“የኔታ” የሥዕል ኤግዚቢሽን ሐሙስ ተከፈተ

አርባ ሠዓሊዎች ትናንት ሥራዎቻቸውን በሰኔሬድ አቀረቡ

የሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ ሥራዎች የሚቀርቡበት “የኔታ” የተሰኘ የስዕል ኤግዚቢሽን ከትላንት በስቲያ በላፍቶ አርት ጋለሪ ተከፈተ፡፡ በኤግዚቢሽኑ የቀረቡት ሥዕሎች አዳዲስ ሲሆኑ ኤግዚቢሽኑ ለሁለት ሣምንታት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል አርባ ሠዐሊዎች ትናንት ከሰአት በኋላ በሰነሬድ ሬስቶራንት የስዕል ኤግዚቢሽን አቅርበዋል፡፡ ሠዓሊዎቹ የሥዕል ኤግዚቢሽኑን ከማቅረባቸው በፊት ስራዎቻቸውን ለአድናቂዎቻቸው እንዳሳዩ ታውቋል፡፡

“የአቡጄዲ ግርግር” ዛሬ ይመረቃልደራሲና ሀያሲ ፍቃዱ ልመንህ ያዘጋጀውና ስለ

ፊልም ጥበብ የሚያትተው “የአቡጄዲ ግርግር” መጽሐፍ ዛሬ ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ በጣይቱ ሆቴል “ጃዝ አምባ” እንደሚመረቅ ዮዳሔ ሕትመትና ፊልም ሥራ አስታወቀ፡፡ በዕለቱ አንጋፋው የፊልም ባለሙያ ብርሃኑ ሽብሩ በመጽሐፉ ላይ ዳሰሳ የሚያቀርብ ሲሆን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምሕር ጳውሎስ አዕምሮ “የኢትዮጵያ ፊልም የወደፊት ዕጣ ፈንታ” በሚል ርእስ የመወያያ ጽሑፍ ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ “የአቡጄዲ ግርግር” በሃያ አንድ የኢትዮጵያ ፊልሞች ላይ የተሰሩ ሂሶችን አካትቷል፡፡

“ኦቴሎ” በትግርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ለንባብ ቀረበ

በአስረስ አሰፋ ተፅፎ በድንቅስራው ደረጄ እና ያሬድ መንግስቴ የተዘጋጀው “የእኔ እውነት” የተሰኘ ትያትር ከህዳር 14 ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ለተመልካች እንደሚቀርብ ተገለፀ፡፡ ትያትሩ ከአንድ አመት በላይ ተደክሞበታል ያሉት አዘጋጆቹ፤ ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 10 ሰዓት እንደሚታይም አስታውቀዋል፡፡ የትያትሩ ደራሲና ፕሮዱዩሰር አለም ሲኒማን የመረጡትን በመንግስት ትያትር ቤቶች ወረፋው አታካች በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ “ዓለም ሲኒማ ቀና ትብብር አድርገው ወዲያው ነው የፈቀዱልን፤ በቦሌ መንገድ ግንባታ ምክንያት ዘገየ እንጂ አምና ነበር የሚከፈተው” ሲሉም አክለዋል፡፡

በትያትሩ ላይ በ“ሰው ለሰው” የቴሌቪዥን ድራማ የምትሰራውን አርቲስት ምስራቅ ወርቁን ጨምሮ ተዘራ ለማ፣ ዳዊት ፍቅሬ፣ ጥሩዬ ተስፋዬ፣ ቢኒያም ፍቅሩ፣ አስረስ አሰፋ፣ ፍቅሩ ባርኮ እና እምነት ከፈለ ተውነውበታል፡፡

የእንግሊዛዊው ፀሐፌ ተውኔት ዊሊያም ሼክስፒር ድንቅ የተውኔት ስራ የሆነው “ኦቴሎ” በትግርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በመፅሃፍ ወጣ፡፡ ተውኔቱን ወደ ትግርኛ ለመመለስ አንድ ዓመት እንደፈጀበት ያስታወሰው አንጋፋው ደራሲና መምህር ኃይለመለኮት መዋዕል፤ ለዚህ ሥራው ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን የተረጎመውንና በርካታ የተውኔቱን የእንግሊዝኛ ቅጂዎች እንደተጠቀመ ገልጿል፡፡ ተውኔቱ ለመድረክ ይበቃ እንደሆነ የተጠየቀው ተርጓሚው፤ መፅሃፉን ያሳተመው በብድር እንደሆነና ለመድረክ ዝግጅት አቅም እንደሌለው ጠቅሶ፤ ስራውን ያዩ ግለሰቦች ግን ወደ መድረክ ሊለውጡት እንደሆነ ተናግሯል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፎክሎር ዶክትሬት ዲግሪ ተማሪ ገዛኸኝ ፀጋውና ሌሎች ተባባሪዎች ባደረጉት ጥረትም የትግርኛ ቋንቋ በሚሰጥባቸው ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች መፅሃፉ ለማስተማርያነት ሊሰራጭ እንደሆነ አክሎ ገልጿል፡፡

120 ገፆች ያሉት “ኦቴሎ” የተውኔት መፅሃፍ፤ በአይናለም፣ በሜጋ እና በዩንቨርሳል መፃህፍት መደብሮች በ30 ብር ለሽያጭ ቀርቧል፡፡ ኃይለመለኮት ተውኔቱን በ1964 ዓ.ም የተረጎመው ሲሆን በአብዮቱ ጊዜ መሰል መፅሃፍት ተሰብስበው ሲቃጠሉ በወንድሙ አማካኝነት ቆፍሮ በመቅበር፣ ከ42 ዓመታት በኋላ አሻሽሎ ለንባብ እንዳበቃው ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ፤ በዶክተር ዮናስ አድማሱ አርታዒነት አምና ለንባብ ያበቃው “የዮፍታሄ ህይወትና ስራ” ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በብሄራዊ ቤተመጻሕፍት ውይይት

“የእኔ እውነት” ትያትር ለመድረክ ሊበቃ ነው

በዩፍታሄ ንጉሴ ህይወትና ስራዎች ላይ ውይይት ይካሄዳልእንደሚደረግበት ሚዩዚክ ሜይዴይ አስታወቀ።

ውይይቱን የሚመሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትያትር መምህር የሆኑት አቶ አሰፋ ወርቁ ናቸው፡፡

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 20 ጥበብ

ሌሊሳ ግርማ

የግጥም ጥግ

እኔ የተረዳሁትን ማንም ስላላወቀ እንጂ ሀሳቡ ምንም አዲስ ነገር የለውም፡፡ ንግድ ማለት ቅይይር ማለት ነው፡፡ እንደ ልዋጭ። አንዱን እሴት ትቀበልና በእሱ ፋንታ ሌላውን ትሰጠዋለህ፡

፡ ከልውውጡ የምታተርፈውን ነገር (እሴት) መሰብሰብ እና እንደገና በትርፍ ለመለወጥ መሞከር፡፡ ነጋዴ የመሆን ትርጉሙ በአጭሩ ይሄ ነው፡፡

የሚለወጠው ነገር የሚፈለግ መሆን አለበት፡፡ በዚህ በጨፈገገ ትውልድ ላይ እንደ ሳቅ የሚያስፈልግ ነገር የለም፡፡ ሳቅ ውስጡ የሌለው ማንም የለም፡፡ ሳቅን ፍለጋ ግን ገንዘቡን ከፍሎ “ኮሜዲ ሾ” ይገባል። ኮሜዲያን እንደ “አባ ገና” በትልቅ ስልቻ የሳቅ ገፀ በረከት ይዞ የሚዞር ይመስለዋል ታዳሚው፡፡ ግን ትልቅ ስልቻ ይቅርና ኪሱን የሚሞላ ሳቅ እንኳን ይዞ አይመጣም - እንዲያውም በተቃራኒው በኪሱ ያለው ለቅሶ ነው፡፡ እነሱ ታዳሚዎቹ በውስጣቸው ይዘው ያልመጡትን ሳቅ ኮሜዲያኑ ሊሰጣቸው አይችልም።

ኮሜዲያኑ አስማተኛ ነው፡፡ ማስመሰል ነው ስራው፡፡ ከተመልካቹ ሆድ ውስጥ ያወጣውን ሳቅ ከራሱ ሆድ ያፈለቀው አስመስሎ ማቅረብ፡፡ እኔ የገባኝ ሀሳብ ይሄ ነው፡፡ ሀሳቡን ተጠቅሜ የልዋጭ ሰራተኛ ሆንኩ፡፡ ከሰው ውስጥ የተደበቀውን ነገር ግልፅ አድርጌ መልሼ እሸጥለታለሁ፡፡ በሚስጥር፡፡

ሚስጥሩ፡- “If you don’t bring it here, you won’t find it here!” የሚል ቢሆንም፤ ሚስጥሩን ለታዳሚዬ ከገለፅኩለት አስማቴ ይነቃል፡፡ ሲነቃ፤ ጥበብ መሆኑ ይቀራል፡፡ ተራ የወሮበላ ማጭበርበር ይሆናል፡፡ መንገዱን ሳልገልፅ፤ መነሻውን እና መድረሻውን ብቻ ይፋ በማድረግ አስማቴን እሰራለሁ፡፡

አስማተኞቹ እና ሚስጢራቸው

መነሻው ይሄ ነው፡፡ መነሻው እንዲህ ነው። ሁሉም ሰው የሚፈልገው ነገር አለ፡፡ አንዳንዱ መሳቅ ነው የሚፈልገው፤ ሌላው ማዘን፣ ሌላው ማፍቀር፣ ሌላው መክበር ወይንም መከበር … ሁሉም የሚፈልገው እና ሊያሟላው ያልቻለ አንድ ፍላጐት አለው፡፡ ያ ነው መነሻዬ፡፡ ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለው መንገድ የእኔ ሚስጢር ነው። መድረሻው ሁሉንም እንደየፍላጐታቸው መንካት መቻል ነው። መሳቅ የፈለገው ስቆ፣ ማልቀስ የፈለገው አልቅሶ፣ ማፍቀር የፈለገ ፍቅሩን አግኝቶ … ወደ ቤቱ እንዲሄድ ማድረግ፡፡ መነሻው ላይ ቃል እገባለሁ። ፍላጐቶች ሁሉ ስኬታቸውን እንደሚያገኙ፡፡ መድረሻው ላይ ብር እቀበላለሁ፡፡ ፍላጐታቸውን ከእነሱ ጋር ላገናኘሁበት፡፡

ጥበብ እና አስማተኝነት የደላላነትም ስራ ነው። ፈላጊ እና ፍላጐቱ የሚገናኙበት ምስጢር ግን ከእኔ ጋር ተደብቆ ይቆያል፡፡ የእኔ አስማተኝነት ያለው ሚስጢሩን እስከጠበቅሁ ድረስ ብቻ ነው። ከባድ የሚመስሉ ነገሮች ከብደው የሚቆዩት የክብደታቸው ምክንያት ሳይገለፅ እስከቆየበት ጊዜ ድረስ ነው። ሁሉም ሚስጢር ሲጋለጥ አስቀያሚ እና ተራ ይሆናል፡፡ የኔ ሚስጢር ደግሞ በጣም ቀላሉ ነው። መስታወት ፊት ፈላጊውን ማቆም ነው፡፡ ራሱን በመስታወቱ እየተመለከተ… ግን መመልከቱን እንዳያውቅ በእኔ አማካኝነት የራሱ ምስል ነፀብራቅ እንዲታየው አደርጋለሁ፡፡ መሳቅ የፈለገ ደንበኛዬ ራሱን በእኔ ትርጓሜ ውስጥ ያያል፡፡ ከራሱ የማንነት ምስል በላይ የሚያስቅ ነገር ምን አለ?

ማልቀስ ለፈለገውም ተመሳሳይ ነው፤ ከራስ ምስል በላይ የሚያስለቅስ ነገር ምን ይኖራል? … ግን ያጣውን ነገር ራሱ እንዳያገኝ፣ እኔ በእሱ እና የራሱ ምስል ነፀብራቅ መሀከል ቆሜ አስተረጉምለታለሁ። የራሱ ምስል በእኔ አማካኝነት ሲተረጐም ከማናደድ እስከ ማሳቅ፣ ከማሳቀቅ እስከ ማራቀቅ … ከተስፋ መቁረጥ እስከ ተስፋ ማግኘት ሊለዋወጥ ይችላል። አስማቴም ይኸው ነው፡፡ የጥበብ አስማት ሚስጢር።

ባለ ፍላጐቱ በራሱ አይን ነፀብራቁን ቢመለከት

የሚያየው ፍላጐቱን እንጂ መድረሻውን አያይም። ራሱን በራሱ አይን ሲመለከት ጉድለት እንጂ ሙሉነት አይታየውም፡፡ ሁሉም ሰው ለራሱ እይታ ጉድለት ነው፡፡ እንደአጋጣሚ ሙሉ ቢሆን እንኳን ጉድለት ነው ለራሱ አይን የሚታየው፡፡ ስለዚህ አስማተኛ ያስፈልገዋል፡፡ ጉድለቱን ሞልቶ የሚነግረው። ሙሉነቱን ይዤ የምመጣው ከሌላ ቦታ አይደለም፡፡ ከራሱ ኪስ አውጥቼ ነው ወደ ፍላጐቱ የሚያደርሰውን ክፍያ የምሰጠው፡፡ ግን አስማት እንደመሆኑ፣ የሞላሁለትን ፍላጐቱን ይዞ ከትያትር ቤቱ ወጥቶ የወል ቤቱ ሲደርስ፣ ከአስማቱ በፊት ወደነበረው ማንነቱ ይመለስና ጐዶሎ ይሆናል፡፡

ሳንድሬላ በአስማተኛዋ አያቷ (አክስቷ) አማካኝነት ከአመዳም ገረድነት ወደ እፁብ ድንቅ ልዕልትነት ተቀየረች፡፡ አያቷ (አክስቷ) የከወነችው አስማት እኔ ያወራሁላችሁን ነው፡፡ ሳንድሬላን የቀየረቻት… ስለ ራሷ ያላትን አመለካከት በመቀየር ነው፡፡ ገረዲቱ በራሷ ፊት ስትቆም ይታያት የነበረውን ምስል ወደ ልዕልት ምስል ቀየረችው፡፡ ሳንድሬላ ውስጥ ቀድሞውኑ ልዕልት የመሆን ፍላጐት ወይንም ምኞት ባይኖር ኖሮ፣ በአስማተኛዋ አያቷ ሀይል ሆነ በጠንቋይ ድግምት ልትፈጠር፣ ልትለወጥ አትችልም ነበር፡፡ ፍላጐቷን እና መፍትሄዋን ከእራሷ ውስጥ አውጥታ አለበሰቻት፡፡ ከተቀዳደደ ልብሷ ውስጥ በእንቁ የተንቆጠቆጠ ቀሚስ በአስማት አማካኝነት አለበሰቻት፡፡ ከራስ ምስሏ ጋር የተቆራኙትን አይጦች፣ በነጫጭ ፈረሶች ተካችላት፡፡ ዱባውን ደግሞ ወደ ሰረገላ፡፡

በአስማተኛ አያቷ የተለወጡ ማንነቷን ይዛ ልዑላኖቹ ጋር ተቀላቀለች፡፡ ህልሟን በጥበብ አስማት እውን አድርጋ ልዑል አፈቀረች፡፡ ስድስት ሰአት ከሌሊቱ ሲሆን … አስማቱ ወደ ቀድሞው ተፈጥሮው ተቀየረ፡፡ አይጥም አይጥ፣ ዱባውም ዱባ … ሳንድሬላም ተመልሶ ተራ አመዳም ገረድ ሆነች፡፡ አስማት እና ተአምር የሚለያዩት አንዱ ወደነበረበት ይመለሳል፡፡ ሌላኛው አስማት ሆኖ ይቀራል፡፡

ጥበብ የራስን ምስል ከጉድለት ወደ ሙሉነት የምትቀይር መስታወት ናት፡፡ በመስታወቷ የሚታየውን ምስል ወደ ታዳሚው ፍላጐት የሚቀይረው ሰው ጥበበኛ ይባላል፡፡ ራስን በራስ የሚቀይር ልዋጭ እንደማለት ነው፡፡ ራስን በራስ አማካኝነት የሚቀይረው ባለሞያ ጥበበኛ ተብሎ ሲጠራ መስማት የተለመደ ቢሆንም፣ ዋናው ስሙ ግን አስማተኛ ነው፡፡

የጥበብ ታዳሚው ራሱን ይዞ ወደ ትርዒቱ ስፍራ ይመጣል፡፡ በፍላጐት ተሞልቶ፡፡ የትርዒቱ ስፍራ የስዕል ሸራ፣ የመጽሐፍ ገፆች ወይንም የትያትር መድረክ ሊሆን ይችላል፡፡ ከራሱ ውስጥ ስሜቶቹን እንደ ክራር እየቃኘ … ፍላጐቱን፣ ምኞቱን ከጉድለት አውጥቶ ሙሉ ያደርገዋል - ባለ ሞያው ከተራ ቃላቶች ውስጥ ለእያንዳንዱ ታዳሚው የሚሆን መፍትሄ ያገኛል፡፡

ማልቀስ ለሚፈልገው ለቅሶ … መሳቅ ለሚፈልገው ሳቅ፡፡ የሚስቅ እና የሚያለቅሰው ታዳሚው ራሱ ቢሆንም …ሳቁና ለቅሶው ግን በራሱ ላይ ነው፡፡ በራሱ አማካኝነት ነው፡፡ በትክክል የሚገጣጥመው ጥበበኛ ካገኘ… ማንኛውም ሰው በውስጡ ሙሉነት አለ፡፡ ልዕልቷ ሳንድሬላን ትሆናለች፤ በአስማተኛው አማካኝነት፡፡ ሳንድሬላም ልዕልቷን፡፡

ግን አሁን አሁን፤ አስማተኛ የመሆን ሳይሆን አስማተኛን የማጋለጥ ፍላጐት እያደረብኝ ነው፡፡ የቆዩ የአስማት ሚስጢሮች ካልተጋለጡ አዳዲሶቹ አይፈጠሩም፡፡ ጠንከር ያሉ ወይንም ፍቻቸው ቶሎ የማይደረስበት መንገዶችን ለመፍጠር ቀላሎቹ የአስማት ሚስጢሮች “tricks” መጋለጥ አለባቸው። እውነተኛ አስማተኛ የሚለየው … ከፍላጐት ወደ ግኝቱ በሰው ስሜት መሰላል አማካኝነት ሲወጣጣ … የተወጣጣበትን መሰላል በመደበቁ አይደለም። መንገዱን እየገለፀም… ማንም መንገዱን ተከትሎ እሱ የከወነውን አስማት መስራት ሲያቅተው ነው፡፡ ሚስጢርን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን መግለፅም አዳዲስ አስማቶች እንዲፈጠሩ በይበልጥ ያግዛል፡፡

ሚስጢሩ ቢገለፅ እንኳን ማንም ማከናወን የሚችለውን አስማት እየሰሩ እውነተኛ ጥበበኛ መሆን አይቻልም፡፡ የወል የአስማት ትርዒት፣ ይትባህል እንጂ ጥበብ አይሆንም፡፡ ሚስጢሩ ቢገለጥም ማከናወን ከባድ የሆነ አስማት ሳንድሬላን አንዴ ልዕልት ካደረጋት በኋላ፣ ከሌሊቱ ስድስት ሰአት ላይ ወደ አመዳም ገረድነት (ብቃት ባለው አስማተኛ በተሰራ ጥበብ ላይ) አትለወጥም፡፡ ልዕልት እንደሆነች ትቀራለች፡፡

መለወጧ ባይቀር እንኳን፤ በሰአታት ውስጥ ሳይሆን ብዙ ዘመናት ይፈጅባታል፡፡ ለምሳሌ ዶስትዮቪስኪ እንደዛ አይነት አስማተኛ ነው የሚሉ አሉ፡፡ እኔ ደግሞ ኧ. ሄሚንግዌይ አስማቱን የሚሰራበት ሚስጢር ቢገለፅ እንኳን ማንም ሊያከናውነው የማይችል የአስማት አይነት ነው የሚሰራው ባይ ነኝ፡፡

የአስማታቸው ሚስጢር ሲጋለጥ፤ ሁሉም በየቤቱ ደብዳቤ ለመፃፍ የሚጫጭረውን ያህል ጥበብ ፈጥረው

ማስታወቂያ

ግማሽ-መንገድ መሄድ ይቅር እንዝለቅ እስከጐሉ ጫፍ

ድጋፍ የለም በግማሽ-አፍ’ ከልባችን እንደግፍ!የወረት ነው የሚመስል-ካሸናፊ ጋራ እፍ-እፍ

አኪሩ ሲዞር ማቀርቀር-ተሸናፊን ረግጦ ማለፍ!መቼ በኳስ ብቻ ሆነ - ታይቷል በሌላም

ምዕራፍ፡፡ቋሚ እንሁን እንጽና’እንጂ ከእሳት ወደ በረዶ

መወንጨፍ ከጽንፍ ወደ ጽንፍክñ አመል ነው ዥዋዥዌ-ዛሬ ጓዳ@ነገ ደጃፍ”

ስናገባ ብቻ ዘራፍ!ስንሸነፍ ጉልበት ማቀፍ!

ሲሞቅ እንደ እንፋሎት መትነን@ሲበርድ እንደግዑዝ ነገር’ፍፁም ዲዳ በድን

መሆንእሪ ስንል ጐል አግብተን’ያመት-ባል ገበያ

መስለን@በለስ ነስቶን ድል ባይቀናንሬሳ የወጣው ቤት መሆን@ኧረ ጐበዝ! ቋሚ እንሁን !ገብቶ መፋለም ቢያቅተን

መደገፍ እንዴት ይጥፋብን?! ከፊልሙ እንዳልተዋደደ ከግብሩ እንዳልተዋሃደ ከትወናው ጋራ ሠምሮ’ወጥ ሆኖ አብሮ እንዳልሄደከቦክስ ኋላ እንደሚመጣ’የቀሽም ፊልም አጃቢ

ድምጽከድርሰቱ እንደተፋታ’እንዳላማረ ኮሾ አንቀጽሙሉ ጨዋታ መደገፍ’መጮሁ እንዴት ያቅተን?በቴፕ አፍ የተፈጠረ’የዲጄ ነው እንዴ ድምፃችን?

ባገርም ጉዳይ ይሄው ነው፡-ቅጥ-አንጣ በድላችን

ሲበልጡን ቆፈን አይያዘን- መቼም መቼም የትም ቢሆን

ሙሉ ጊዜ ቋሚ እንሁን! እናግዝ ልጆቻችንን!መቼም ኢትዮጵያዊነትን’የውጪ ባዕድ አልሰጠንእኛው ውስጥ የበቀለ እንጂ’ “የዲጄ” አይደለም

ድምፃችንብንሸነፍም እኛው’ብናሸንፍም እኛው ነን!በወረት አንለዋወጥ’እንደግፍ ከልባችን!

እናግዝ አገራችንን!!(ለኢትዮ-ናይጄሪያ የኳስ ፍልሚያና ለኢትዮጵያውያን

ደጋፊዎች) ኀዳር 2 ቀን 2006 ዓ.ም

ግማሽ-መንገድ መሄድ ይቅር- “የዲጄ”አይደለም ድምፃችን

የተገኙም አሉ፡፡ ቀላሉን የአስማት ሚስጢር በማጋለጥ… ከባባዶቹ እንዲፈጠሩ መንገድ ማመቻቸት ነው… ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጀመርኩት ስራ፡፡ እናም እላለሁ፤ አስማተኛ አስማቱን በከረጢት ይዞ አይዞርም፡፡ አስማቱን የሚፈጥረው ከታዳሚዎቹ ፍላጐት እና ነፀብራቅ በመነሳት ነው፡፡ ታዳሚዎቹ ሀዘን፣ ደስታ፣ ተስፋ እና አንዳች ፍላጐት በውስጣቸው ቀብረው ወደ አስማተኛው ባይመጡ አስማተኛው ብቻውን የሚከውነው አንዳች ነገር ባልኖረው ነበር፡፡ If you don’t bring it here you won’t find it here! ይላችኋል፤ ጥበበኛው ባዶ ከረጢቱን እያሳየ፡፡

የአስማተኛው ጥሬ እቃዎች እናንተ ናችሁ፡፡ ጥሬ እቃዎቹን ከተራ ወደ እፁብ ድንቅነት የሚቀይርበት መንገድ ነው ሚስጥሩ፡፡ ጥበበኛ ሚስጢረኛ ነው። ምርጥ ሚስጢረኛ ግን ሚስጢሩን የሚደብቅ ሳይሆን ለመግለፅ የሚሞክር ነው፡፡ ሚስጢረኛ የሆነበትን ሚስጢር ለመፍታት በሚያደርገው ሙከራ እና ሂደት …እናንተን ከፍላጐታችሁ ወደ ግባችሁ ያደርሳችኋል፡፡ ሚስጢሩን ለመፍታት በሚሞክርበት ጊዜ ነው አስማቱ የሚፈጠረው፡፡ ከከባድ ሚስጥሮች ፍቺ የሚገኝ አስማት ነው ልዕለ - ጥበብ፡፡ የልዕለ ጠቢብም አሻራ:- ሚስጥርን መግለፅ እንጂ መደበቅ አይደለም፡፡ በተገለፀ ቁጥር የሚደበቅ ሚስጥርን ለመፍታት ጠንካራ አስማተኞች ያስፈልጉናል፡፡ እውነተኛ አስማተኞች፡፡ ካርታን ደርድሮ “ቀዩዋን ያየ” እያሉ የሚያጭበረብሩት…እውነተኛም፣ ሚስጥረኛም አስተማኛም አይደሉም። ምናልባት “ወሮበላ” ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ግልፁን ሚስጢር የሚያደርግ እና ሚስጢሩን ለመግለፅ በሚሞክር መሀል የሰማይ እና የምድር ያህል ርቀት አለ፡፡ አንደኛው ወሮ በላ ይባላል፡፡ ሌላኛው አስማተኛ ነው፡፡ አስማተኝነትን ከሌላ አስማተኛ በመማር ሚስጢሮችን እና አፈታታቸውን አጥንቶ፣ “የጥበቡ ጥሪ አለኝ” የሚል ሊጀምር ይችላል፡፡

አዲስ አስማት መፍጠር ካልቻለ … ወይንም ካልሞከረ ግን በስተመጨረሻ የሚገባው ወደ ማጭበርበሩ ነው፡፡ ቀላልን ሚስጢር ከባድ አስመስሎ ወደመደበቁ፡፡

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 21

መሠረታዊው ማንነቱና ሥልጣን ያለ መነጠቅ ፍላጐቱ ፍራቻን አስከትሎ ጭካኔን ወለደ፡፡ “ያለ ምንም ደም” የሚለው ዜማ ቀረና ስልሳዎቹን የአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት

“የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች ልጆቿም ያልቃሉ እሷም ትሞታለች፡፡” አስተጋባ፡፡ የያኔዎቹ ወጣቶች ለማስፈራሪያው ዜማ

አልተበገሩም፡፡ ወታደራዊው መንግሥት ከሥልጣን እንዲወርድ በአቋማቸው ፀንተው ጮኹ። ወታደራዊው መንግሥት ያነገበውን መሣሪያ በማውረድ አፈ ሙዙን በወጣቶቹ ላይ ደገነ፡፡ ፍርሃቱ ጭካኔን ወለደ፡፡

ወጣቶቹም ወኔያቸውን አንግበው ከተደገነባቸው አፈ ሙዝ ፊት ለፊት በጽናት ቆሙ፡፡ በእኒያ ወጣቶች ደረት ላይ የተወደረው አፈ ሙዝ በጭካኔ ተሳበ፡፡ ጥይት በወጣቶቹ ላይ በጭካኔ ተርከፈከፈ፡፡ የምድረ ኢትዮጵያ ወጣት ታደነ፡፡ እሥር ቤቶች ተጣበቡ። የየቀበሌ ጽ/ቤቶች ወደ እሥር ቤት ተለወጡ፡፡ ግርፋትና ስቃይ በረከተ፡፡ የብዙ ሺህ ወጣቶች ሬሣ በየአውራ ጐዳናው፣ በአደባባዩና በየጢሻው እንደ ውሻ ሬሣ ተጣለ፡፡

በነዚያ ወጣቶች ላይ ፍርሃት በወለደው ጭካኔ የተዘራው ጥይት ለቀሩት ኢትዮጵያውያን ልጓም ሆነ፡፡ ጥርጣሬና ፍርሃት ነገሰ፡፡ በራስ መተማመን ጠፋ፡፡ ጠቢባን በቡርሻቸውም ሆነ በብዕራቸው ፈሩ፡፡ ፍርሃታቸው ማስመሰላቸውን እንደ ብልጠት ይቆጥሩት ዘንድ አስመረጣቸው፡፡ የመረጡትንም ተካኑበት፡፡

ይህን ጊዜ አዕምሮ ዛገ፡፡ እጆች ዛሉ፡፡ ጣቶችም ዶለዶሙ፡፡ ዐይኖች ወደ ውስጥ ማየታቸውን አቆሙ፡፡ ጆሮ ብቻ ዳባ አልለብስም አለ፡፡ ብዕር ማስመሰሉን አነባ…ጥበብ ወገቧ እስኪለመጥ ድረስ በሀዘን አቀረቀረች፡፡ እውነት ወዴት ነሽ? ውበት የት አለሽ? ከቶም ያለ የለም፡፡ ታዳጊዎች፤ ታላላቆቻቸው በብዕራቸውም በቡርሻቸውም በስብዕናቸውም ሲያስመስሉ አስተዋሉ፡፡ እያስተዋሉም ወደወጣትነት ተሸጋገሩ፡፡ አኢወማ ዘምሩ ሲላቸው ዘመሩ፡፡ መፈክር አሰሙ ሲላቸው በመሽቀዳደም ግራ እጃቸውን እያወጡ ፎከሩ፡፡

“ከመምሕሩ ደቀ መዝሙሩ” እንዲሉ ከታላላቆቻው እጥፍ ፈሪዎች፣ እጥፍ አስመሳዮች ሆኑ፡፡ ብሔራዊ ውትድርና መጣ፡፡ ሽሽት ተከተለ። ቤት ዘግቶ መደበቅ፤ ከአሁን አሁን ተያዝኩ የሚል ሥጋት አየለ፡፡ የእያንዳንዱ ወጣት ልብ ሥጋት እያባነነው፣ የፍርሃት ከበሮውን መደለቅ ተያያዘ። ታላላቆቻቸውን ጉራማይሌ ተነቀሱ፡፡ ከፈሩት ታላላቆቻቸው መቶ እጥፍ እየፈሩ፣ ከኒያ ፀንተው ከወደቁት ታላላቆቻቸው የወረሷት ትንሽዬ በራስ መተማመን ከፍርሃት ትንፋሻቸው ጋር እየተነፈሷት ብን ብላ ትጠፋባቸው ጀመር፡፡

ይህን ጊዜ ከፊሉ በአኢወማ ዙሪያ ማስመሰሉን ተካነበት፡፡ ከፊሉም ስደትን መረጠ፡፡ ጥቂቱም ሕይወቱን በዘዴ ለማክረም ውትድርና ተቀጠረ። በለስ ያልቀናው ብሔራዊ ውትድርና ዘመተ፡፡ ብዙዎቹ የሞት ገፈት ቀማሾች ሆኑ፡፡ የሞተውም ሞተ፡፡ የተረፈውም ሙት ደመ ነብሱ እየመራው፣ ከፍርሃቱና ከማስመሰሉ ጋር መወዛወዙን ቀጠለ፡፡

ሥፍራው ቢለያይም እኔና እናንተ ከእነሱ ጋር አለን፤ አሊያም የእነሱ ልጆች ነን፡፡

ትናንት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች አመራርና አባላት የነበሩ ዛሬ ባሕር ማዶ ሆነው በሚያሳትሟቸው መፃሕፍት የሚያስነብቡን ትረካ፣ የትዝታ ድንኳን ጥለው ትናንትናቸውን እያለቀሱ፣ የኛን ዛሬ ሀዘንተኛ አድርገዋት፣ ነጠላዋን ካዘቀዘቀች’ኮ ከራረመች፡፡

ሁሉም “ትክክል ነበርኩ” እያለ በትዝታ የተወልን ሽንፈት፣ ትሩፋቱ ለቅሶ ብቻ ሆነ፡፡ የሀገራችን የትግል ታሪክ መቋጫው ምባ ብቻ ነው፤ በልቅሶ የተሞሸረ ሽንፈት፡፡ አቤት የዚች ምድር ለቅሶ! አቤት የዚች ምድር እምባ መብዛቱ! ዛሬም ድህነት ቅነሳ፣ ሙስና፣ የአመለካከት ለውጥ፣ ረሃብና ድርቅ በየመድረኩ ላይ አጀንዳ እየቀያየረ በባዶ አንጀታችን እናለቅሳለን። ያላየው ድርቅ ያልጐበኘው እምባችንን ብቻ ነው። ለቅሶ በኛ መንደር፣ ልቅሶ በኛ ቀዬ፣ ለቅሶ በኛ አደባባይ በሽበሽ ነው? የሰቀቀን ለቅሶ የሚያበቃበት ቀን እየናፈቀን በናፍቆት መኖሩ ተስፋ ሆነን እንዴ ጐበዝ? እንባችንን የምናብስበት የተስፋ መሀረብ ከቶ ከየት ይገኝ ይሆን?

አጋጣሚ ከሚያገጣጥመኝ የዘመኔ ዘመነኞች መሃል ጥቂት የማይባሉት “ነፋስ ሲነፍስ ጐንበስ

ብሎ ማሳለፍን ከሣር ተማር!” የሚለውን ምሳሌያዊ አነጋገር አዘውትረው ሲናገሩ ሰማሁና፤

“ለምን?” ስላቸው “መስለህ መኖር ካልቻልክ አከተመልህ ለመኖር

ትንሽ ብልጥ መሆን አለብህ፤ ምስማሩን አሊያም መዶሻውን መሆን ያንተ ምርጫ ነው፤ ሲያዙህ እሺ አሜን እያልክ እንደሰው አምሮብህ ከሰው ሳታንስ መኖር ከቻልክ ሌላ ምን ትፈልጋለህ? ከጊዜው ጋር ተስማምቶ መኖር ብልጠትም ዕውቀትም ነው” አሉኝ፡፡

ምሳሌያዊ አነጋገር ከፍላጐት ጋር ተጣረሰ። አድርባይነት እንደ ብልጠትም ዕውቀትም ተቆጥሮ ብዙዎችን “ዐዋቂ” አሰኘ፡፡ ብዙዎች አድር ባይነታቸውን እንደ ብልጠት እየቆጠሩ፣ ህሊናቸው ላይ ተኝተው በብልጠታቸው ተኮፈሱ፡፡ አስመሳይነታቸው የኩራታቸው ምንጭ ሆነ፡፡

አንድ ወጣት ገጣሚ የቋጠረው ስንኝ ነብሴን ማርኮታል :-

“ሰውማ ሙዝ ሆና ተልጦ ቢበላ” ውስጡ በተጣለ ላዩ በተበላ ሰው እንደ ሙዝ ተልጦ ባይበላም የኔ ዘመን

ዘመነኞች ግን አበላሉን ተክነውበታል! በአስመሳይ ክህሎቱ አንዱ አንደኛውን እንደ ሙዝ ሳይልጠው እርስ በርስ ይበላላ ይዟል፡፡ ያውም የሚጣለውንና የሚበላውን ሳይለይ፣ መብላቱን ወይም መበላቱን አሊያም መጣሉን ሳያውቅ ደመ ነብሱ እየመራው፣ በሆዱ ለሆዱ ስለሆዱ ብቻ መኖር መረጠ፡፡ የመረጠውንም እንደ ብልጠት ቆጠረው፡፡

ሁሉም ለሆዱ በሆዱ ሲጋፋ ህሊናውን ረሳ። የተጣለበትን ኃላፊነት ወደ ጐን በመተው ሰርቆና ዘርፎ አሊያም ዕምነት አጉድሎ ሀብታም ለመሆን መጣደፍ እንደ ጀብድ ተቆጥሮ ያስከብር ጀመር። ህሊናውን ሲረሳ ሰው የመሆኑን ክብር ከእግሮቹ ሥር ጣለና ራሱን በራሱ አቀለለ፤ ሰው ማለት ለሰው እንደገለባ ቀለለ፡፡ የሆዱን ሲያሳድድ አንዱ ላንዱ አልታኘከው እያለ እንደ አንጆ ሥጋ እርስ በርስ መጣጣል ተለመደ፡፡ ህሊና ረከሰ፤ ሥጋ ተወደደ፡፡

አንድ ኪሎ ሥጋ መቶ ስልሳ፤ መቶ ሰማኒያ ይሸጣል፤ ይቸበቸባል!

ሰው ዋጋ አላወጣም፡፡ ሰሞኑን የወጣና ሲኒማ አምፒየር በመታየት ላይ ያለው “ድሮና ዘንድሮ” የሚለው ፊልም “ሎጐ” እንዲህ ይላል:- “ከማትረባ ነብስ ድፍን መቶ ብር ሲጠፋ ያንገበግባል” ለመሆኑ የሰው ዋጋው ስንት ነው?

ልብ በሉ! እኔ በእናንተ ውስጥ አለሁ፡፡ የዘመኔ ዘመነኞች ሆይ፤ ማንነታችንን

የሚያረክስና ስብዕናችንን የሚያዋረድ ዝቃጭ የሥርዓት ዕድፍ ተሸክመን እያለ…በድህነት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቃ፣ ጉስቁልናዋ በዝቶ፣ የሰቆቃ ሲቃዋ ሰቀቀን ሆኖባት፣ ሀዘኗ ልክ አጥቶ የደም ዕምባዋን በምትናጥ ሀገረ ኢትዮጵያ፣ በዚች ምድረ ሀበሻ፣ መልካም ስብዕና ያለው ታታሪ ዜጋ ተፈጥሮ፣ ሀገራችን በዕድገቷ ሽቅብ ተመንጥቃ ለማየት መመኘት ይቻላል፤ ምኞት አይከለከልምና! ነገር ግን ይህ ምኞት “ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” እንዲሉ ከግብራችን ጋር ያልተዋሀደ ከንቱ ምኞት ነው፡፡

እያንዳንዳችን ከተሸከምነው የሥርዓት ዕድፍ ራሳችንን ለማላቀቅ፣ ከራሳችን ጋር ግብግብ እንግጠም፡፡ በመጀመሪያ ከየራሳችን ማንነት ጋር መታገል እንጀምር፡፡ ይህን ስናደርግ እንደ አንድ ማህበረሰብ በኛ ራስ ወዳድነት የተበከለውን የዘመናችንን አየር ለማጽዳት አንድ እርምጃ ተራመድን ማለት ነው፡፡

አጀንዳ ሳንጨርስ፣ በዐውደ ጥናት ሰበብ የሕዝብ ገንዘብ ሳይባክን፣ የአመለካከት ለውጥ እውን የሚሆንበት ጅማሮ የሚታየውም ይህን ጊዜ ነው፡፡ መራሩን መድኃኒት ስንወስድ፣ ከራስ ማንነት ጋር ትግል ስንጀምር! ነገር ግን ዛሬ በአንድ ጊዜ ከየራሳችን ማንነት ጋር ትግል ብንጀምር እያንዳንዳችን የተሸከምነው ዕድፍ ተራግፎልን በራሱ የሚተማመን ትውልድ በኛ ሕብረተሰብ መሃል ዛሬውኑ አይፈጠርልንም፡፡ ይህን የምንጠብቅ ከሆነ ተሳስተናል፡፡ እኛ ችግኝ ተካዮች እንጂ ፍሬውን ተቋዳሽ አለመሆናችንን እንመን፡፡

የዘመኔ ዘመነኞች ሆይ፤ በዘመናችን የተከሰቱ ሥርዓቶች ያሸከሙን ዕድፍ መጥፎ ጠረን የዘመናችንን አየር በክሎታል፡፡ የመልካም ስብዕና፣ በራስ የመተማመን አየር አጥሮን ቁና ቁና እየተነፈስን፣ የአመለካከት ለውጥ እያልን በሚቆራረጥ ድምጽ መቃተት ጀምረናል፡፡ የሚያሸት አፍንጫ ካለን፡፡ ከህመማችን የሚፈውሰን ፍቱን መድኃኒት በእጃችን

ዘመን ከገፅ 9 የዞረ

ዘመን ወደ ገፅ 25 ዞሯል

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 22 ዓለምአቀፍ

ኤልሳቤት ዕቁባይ

ጋምቢያ ከኮመን ዌልዝ አባልነቷ መውጣቷ የመነጋገሪያ ርአስ ሆኗል፡፡ ከአርባ አምስት አመት በኋላ ከአባልነት ለመውጣት ለምን ወሰኑ?

ዜናው አነጋገሪ ሊሆን አይገባም ነበር፡፡ ጋምቢያ ይህን ውሳኔ የወሰነችው ከቅኝ ግዛት ጋር ከተያያዙ ነገሮች ነፃ መሆን ስለምትፈልግ ነው፡፡ በተለይም ምንም አዲስ ነገር በሌለበት ሁኔታ ውሳኔ የሚሰጠው ከአንድ ወገን ብቻ ሲሆን አባል መሆን ለምን ይጠቅማል፡፡ እኛን ሳያዳምጥ “ይህን አድርጉ” እያለ በሚያዝና ብቻውን በሚወስን ተቋም አባል ከመሆን መውጣቱ የተሻለ ነው፡፡ ስለዚህ ነፃነታችንን ካገኘን ከአርባ ስምንት አመት በኋላ ቅኝ ግዛት እና እንግሊዝ በቃን ብለናል፡፡ ወደኋላ መለሱን እንጂ የትም አላደረሱንም፡፡ የዚህ አመት ዋናው መፈክራችን “እንደ ባህላችንና እንደ ሀይማኖታችን እንኑር” የሚል ነው፡፡ ስለዚህ ኮመን ዌልዝ ሀይማኖታችንም ባህላችንም አይደለም፡፡ ከቅኝ ግዛት ጋር ንኪኪ ባላቸው ተቋሟት አባል መሆን አንፈልግም፡፡ በጋምቢያውያንነታችን መቀጠል እንፈልጋለን፡፡

በመንግስታቱ ድርጅት ያደረጉት ንግግር በመገናኛ ብዙኀን በአሉታዊ መንገድ መዘገቡን ተከትሎ አባልነትዎን መሰረዝዎስ?

በጣም የሚገርመኝ ነገር አለ፡፡ ከአንድ ሰውጋር ያለሽን ግንኙነት ለማቋረጥ በመጀመሪያ ከዛ ሰው ጋር ችግር መፈጠር አለበት የሚል አስተሳሰብ አለ። ይህ ለኔ ትክክል አይደለም፡፡ ችግር ካለ ችግሩን መፍታት ነው፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት ኮመን ዌልዝ የቅኝ ግዛት ተቋም ነው፡፡ ስለዚህ ከአሁን በኋላ አባል አይደለንም፡፡ በነገራችን ላይ ከኮመን ዌልዝ ብቻ ሳይሆን ከቅኝ ግዛት ጋር ግንኙነት ካለውና የቅኝ ግዛት ዘመንን ከሚያስቀጥል ማንኛውም ተቋም ጋር ግንኙነት አይኖረንም፡፡ ምክንያቱም ከቅኝ ግዛት ያተረፍነው ድህነት፤ ኋላቀርነት፤ብዝበዛ እና ባርነትን ነው፡፡

በዚህ ዘመን ለባርነት ተጠያቂ ከሆኑ አገሮች ጋር ትስስር ሊኖረን አይገባም፡፡ አይሁዳውያን እና ሌሎች ህዝቦች ለደረሰባቸው በደል ካሳ ተከፍሏቸዋል፡፡ አፍሪካን ግን ማንም ዞር ብሎ አላያትም፡፡ ባርነትንና ቅኝ ግዛትን ያመጣችብን እንግሊዝ ካሳ ልትከፍለን ቀርቶ ይቅርታም አልጠየቀችንም፡፡ ጋምቢያውያን በቅኝ ግዛት ቀንበር ስር በነበሩባቸው አመታት ማንም ሳይንቲስቶች እና ዶክተሮች እንዲሆኑ ስልጠና አልተሰጣቸውም፡፡ ለሌሎችም አፍሪካውያን እድል አልተሰጠም፡፡ እኛ ልክ እንደ ሌላው የሰው ዘር አይደለንም?

ምእራባውያኑ አሁንም አፍሪካ ኋላ እንድትቀር ይፈልጋሉ ብለው ለምን ያምናሉ?

አንቺ አለምን እየዞርሽ የምታይ ጋዜጠኛ ነሽ፡፡ ልክ እንደ ዱባይ ወይም የመካከለኛው ምስራቅ አገራት በቀድሞ ቅኝ ገዢያቸው ያደጉ የአፍሪካ አገሮችን ልትነግሪኝ ትችያለሽ? ሌሎችን የምትከተይ ከሆነ መምራት አትችይም፡፡ እኛ አፍሪካውያን ለዘመናት ስንከተላቸው ኖረናል፡፡ አሁንም እየተከተልናቸው ነው፡፡ በቃ ካላልን ወደፊትም እንከተላቸዋለን፡፡ ኋላ የቀረነውም ለዚህ ነው፡፡ ለአፍሪካ ያለኝ መልእክት መከተሉን አቁመን መሪ እንሁን ነው፡፡ በአፍሪካ እና በምእራባውያኑ ግንኙነት አፍሪካ ተጠቃሚ እየሆነች አይደለም፡፡ ተጎጂ ናት፡፡ እኔ እና ጋምቢያ ማንንም መከተሉን ትተን የራሳችንን ሀይማኖት፣ ባህል እና እምነቶች መከተል ጀምረናል፡፡ አፍሪካ በተፈጥሮ ፀጋ የታደለች አህጉር ሆና ለምን ድሀ ሆነች? አውሮፓውያኑ ምን ስለሆኑ ነው አፍሪካውያን ምን

“የአፍሪካ መሪዎች የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ ላይ ሲጮሁ አፍራለሁ”

የጋምቢያው ፕሬዚዳንት ያያ ጃሜ “ኤች አይቪን አድናለሁ” በማለታቸው ለረጅም ጊዜ ከሚዲያ ዘገባ የማይጠፉ ፕሬዚደንት አድርጓቸው ነበር፡፡

በቅርቡ ደግሞ አገራቸው ከኮመንዌልዝ አባልነቷ መውጣቷን በድንገት ማወጃቸውን ተከትሎ የዓለም መነጋገሪያ ሆነዋል፡፡ ፕሬዚደንቱ ከ“ኒው አፍሪካን” መፅሄት ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ

ለጋዜጣው በሚመች መልኩ ተጠናቅሮ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

መስራት እንዳለባቸው የሚያስተምሩት? ከቅኝ ግዛት አንስቶ እስካሁን ራሳቸውን የአፍሪካ ፈጣሪ አድርገው ያስባሉ፡፡ ጋምቢያ በቃ እያለች ነው፡፡ በሙዚቃቸው መደነስ ስታቆሚ አምባገነን ይሉሻል፡፡

ሌሎች የአፍሪካ አገሮች የእርስዎን ውሳኔ የሚከተሉ ይመስልዎታል?

የሚጠቅመንን መከተል ጥሩ ውሳኔ ነው፡፡ ወደ ኋላ የሚመልስሽን የምትከተይ ከሆነ፣ አላዋቂ ብቻ ሳይሆን የምትሆኚው በህዝብሽ ፍላጎት እየሰራሽ አይደለም ማለት ነው፡፡ ቅኝ አገዛዝና የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ በማንኛውም መልኩ ከአፍሪካ መወገድ አለባቸው፡፡ ምክንያቱም ትርፉ ውርደት እና ስድብ ነው፡፡

የሌሎች ድርጅቶች አባልነትዎን ግን አልተዉም? ውሳኔዬ ወደ ሌላ መተርጎም የለበትም፡፡ እኔ

ያልኩት በጣም ግልፅ ነው፡፡ ከቅኝ ግዛት እና ከእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ጋር ከተያያዘ ማንኛውም ተቋም ጋር ግንኙነት አንፈልግም፡፡ ይህ ማለት ግን ሌሎች የአለም አቀፍ ተቋማትን ያጠቃልላል ማለት አይደለም፡፡ ኮመንዌልዝ የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ተቋም ብቻ ሳይሆን የምርጫ ሂደትም የለውም፡፡ አንድ ግለሰብ የህይወት ዘመን መሪ ነው፡፡ ይሄ ምን አይነት ዲሞክራሲ ነው? ተረዳሽኝ?

እንግሊዞቹ በነሱ ላይ ብቻ የዘመቱ አይመስላቸውም?

እንግሊዞቹ ኮመንዌልዝ የነሱ እንደሆነ ካሰቡ ለመውጣታችን ጥሩ ምክንያት ይሆናል፡፡ ለምንድነው የራሳቸው እንደሆነ የሚያስቡት?

ሌላው ተመሳሳይ ድርጅት ደግሞ አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አንዱ ነው፡፡ ድርጅቱን ከሚመሩት መካከል በእርስዎ መንግስት ያገለገሉት ፋቱ ቤንሶዳ ይገኙበታል፡፡ ድርጅቱ ከአፍሪካ መሪዎች ተቃውሞ እየገጠመው ነው፡፡ በፍርድ ቤቱ ላይ ያለዎት አስተያየት ምንድን ነው?

እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ፍርድ ቤቱ የቅኝ ገዢ ተቋም አይደለም፡፡ በቅርቡ ነው የተቋቋመው፡፡ ነገር ግን በሌሎቹ ተቋሟት ላይ እንደምናደርገው አባል ለመሆን እጅግ በጣም ፈጣኖች ነን፡፡ አባል እንሆንና ካፀደቅነው በኋላ ምን እንደሚል ማንበብ እንጀምራለን፡፡

ከዛ ነገሮችን ወደ ኋላ ለመመለስ አስቸጋሪ ይሆንብናል፡፡ ዘለን ከአንዱ ወደ አንዱ አንሳፈር ብዬ ጓደኞቼን አስጠንቅቄያለሁ፡፡ ሁሉም አውቶብስ ውስጥ መዳረሻውን ሳናውቅ እንሳፈራለን። ሾፌሩ በመሀል ላይ “አፍሪካውያን ውረዱ” ሲል ለምን ተሳፈርን ብለን መጠየቅ እንጀምራለን። ከአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባላት መካከል አፍሪካ ብዙውን ድርሻ ትይዛለች፡፡ ፍርድ ቤቱ በእግሩ እንዲቆም ያደረገችው አፍሪካ ናት፡፡ እኔ መጀመሪያም ተናግሬ ነበር፣ዝም ብለን ከመቀላቀላችን በፊት ምን እንደሚል በጥሞና እንየው፡፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በራሳችን ፈቃድ ተጎጂ የምንሆንበትን ጉዳይ ቀድመን ተስማምተናል። የፕሬዚደንት አልበሽርን ክስ አንዳንድ የአፍሪካ አገሮች ሲቃወሙት፣ አንዳንዶች ደግፈውታል፡፡ ፍርድ ቤቱ የአፍሪካ ህብረትንም ሳያሳውቅ መሪዎችን እንዲከስ ይስማማሉ፡፡ ድርጅቱ የአውሮፓ አገራት መሪዎችን ያለ አውሮፓ ህብረት ፈቃድ መክሰስ ይፈቀድለታል? ይህ ትልቅ ስድብ ነው፡፡ አንድ ክስ የሚቀርበው ወይ በክስ አቅራቢ አገር ወይም በፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ነው፡፡ የአፍሪካ መሪዎች ፍርድ ቤቱ ላይ ሲጮሁ አፍራለሁ፣ምክንያቱም ከአልበሽር ጉዳይ

በስተቀር የሌሎቹ ክስ የቀረበው በራሳቸው በአፍሪካ መንግስታት ነው፡፡ ራሳችን ክስ እናቀርብና መልሰን አይሲሲ ዘረኛ ነው እንላለን፡፡

ስለዚህ አይሲሲ አፍሪካውያንን ያድናል በሚለው አይስማሙም?

አዎ አልስማማም፡፡ አፍሪካ ችግር ካለባት ችግሯን በራሷ መፍታት አለባት፡፡ ችግሩን ወደ አፍሪካ ህብረት ከማምጣት ይልቅ ወደ አይሲሲ መውሰድ አያሳፍርም?

ጋምቢያዊቷ ሚስ ቤንሶውዳ በፍርድ ቤቱ እያከናወኑት ባለው ተግባር ይኮራሉ ማለት ነው?

እሷ አለም አቀፍ ሰራተኛ ናት፡፡ ኩራት የሚሰማኝ ጋምቢያዊት ስለሆነች ሳይሆን የአፍሪካ ሴት ስለሆነች ነው፡፡ ይህ ቦታ ቀደም ሲል በአፍሪካውያን የሚታሰብ አልነበረም፡፡ ዛሬ በአፍሪካዊት ተይዟል፡፡ ስለዚህ ከተቋሙ ጋር መተባበር አለብን፡፡ ለአይሲሲ ስል ሳይሆን ለእውነት ስል፡፡

ስምዎ ብዙ ጊዜ በጥሩ አይነሳም፡፡ እ.ኤ.አ በ1994 ዓ.ም ስልጣን ከያዙ በኋላ ምን ሰራሁ ይላሉ?

ከጥቂት አመታት በፊት ምንም ዩኒቨርሲቲ አልነበረም፡፡ ኮመንዌልዝን የተውንበት አንዱ ምክንያት ይሄ ነው፡፡ እንግሊዞቹ አራት መቶ አመታት ሲገዙን፣ አንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብቻ ነው የሰሩት፡፡

እውነትዎትን ነው? እየነገርኩሽ፡፡ ነፃ ከወጣን በኋላ ለ30 ዓመታት

ያስተዳደረው መንግስት ይባስ ብሎ አንድም ት/ቤት ወይም ሆስፒታል አሊያም ዩኒቨርስቲ አልገነባም፡፡ የብሪቲሽ ቅኝ አገዛዝ ቢያንስ አንድ ት/ቤት ሰርቷል - ለጥቂቶች ቢሆንም፡፡ እንግዲህ ብሪቲሾች በአራት መቶ አመት ውስጥ አንድ ትምህርት ቤት ከሰሩ ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርሲቲ ለመስራት ስንት ተጨማሪ አመታት የሚፈልጉ ይመስልሻል? ወደ አንድ ቢሊዮን አመት፡፡ ከኮመንዌልዝ ለመውጣት ስለመወሰናችን ማንንም እንዳላማከርን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ እነሱ የሚፈልጉት በቅድሚያ ነግረናቸው ፈቃዳቸውን እንድናገኝ ነው፡፡ እኛ የማንም አገልጋይ አይደለንም። እኛ በየአመቱ ከኮመንዌልዝ ከምናገኘው ጥቅም ይልቅ የምንከፍለው ይበልጣል፡፡

በምእራብውያኑ መገናኛ ብዙሀን እና በተቃዋሚ ፖለቲከኞች ዘንድ አምባገነን ተብለው ነው የሚታወቁት፡፡ የግብረሰዶማውያን መብትን ጨምሮ በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ጥሰት ይወቀሳሉ፡፡ እርስዎ ምን ይላሉ?

አዎ የልማት አምባገነን ነኝ፡፡ የለውጥ አምባገነን ነኝ፡፡ በሌሎች ትእዛዝ የማይሰራ አምባገነንም ነኝ፡፡

ጋምቢያ ውስጥ ግን የህዝብ አገልጋይ ነኝ፡፡ ረጅም መንገድ መጥተናል፡፡ ገና ረጅም መንገድ ይቀረናል። የምንመካው በፈጣሪ እና እንደ ሰው በሚቆጥሩን አገሮች ነው፡፡ ግብረሰዶማዊነትን ጋምቢያ ውስጥ በፍፁም አንፈቅድም፡፡ የመንግስት አስተዳደርን በተመለከተ ደግሞ እነሱ አፍሪካን ይገዙ በነበረ ጊዜ አፍሪካውያን በምርጫ ተሳትፈው ያውቃሉ? ሰብአዊ መብት፣ ነፃነትና መልካም አስተዳደር ቅኝ ገዢዎችን የሚመለከት አይመስልም እኮ፡፡

ተቃዋሚዎችንና ጋዜጠኞችን በመግደልም ይወነጀላሉ---

ሰውን ሰቅሎ መግደል አፍሪካ ውስጥ የመጣው በቅኝ ገዢዎች ነው፡፡ ከቅኝ ግዛት በፊት አፍሪካ ውስጥ የነበረው ክፍያ ነው፡፡ ሰው የሚሞተው በጦርነት ላይ ብቻ ነበር፡፡ የጭካኔ አይነት አፍሪካውያን ላይ ሲፈፅሙ ኖረው የሰብአዊ መብት አስተማሪ መሆን ይፈልጋሉ፡፡ አፍሪካውያንን በአንድ መርከብ ላይ እንደ ሰርዲን አሽጎ ወስዶ፣ አሜሪካን ገበያ ላይ በጨረታ ከመሸጥ፣ ከዛም ከውሻ ያነሰ ኑሮ እንዲኖሩ ከማድረግና አህጉሪቱን ከመዝረፍ በላይ ምን የመብት ጥሰት አለ? ለዚህ ኢ-ሰብአዊ ድርጊታቸው ይቅርታ እንኳን ያልጠየቁ፣ አፍሪካን ስለ ዲሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት ሊያስተምሩ ይችላሉ?

ጋምቢያ የነዳጅ ሀብት አላት?አዎ አለን ፡፡ ጥቅም ላይ ያላዋልናቸው ማእድኖች

እና ነዳጅ አለን፡፡ እስከ ዛሬ ነዳጃችንን ያላወጣነውም አምስት በመቶ ብቻ ለእኛ ተሰጥቶ የቀረው ሌሎችን ተጠቃሚ በሚያደርግ ስምምነት መገዛት ስለማልፈልግ ነው፡፡

የተፈጥሮ ሀብትን ለልማት ማዋልንን እና ግሎባላይዜሽንን እንዴት ያዩታል?

ግሎባላይዜሽን ማለት የተፈጥሮ ሀብትን ዝም ብሎ መስጠት አይደለም፡፡ ሁሉም ኩባንያዎች መጥፎ ናቸውም አላልኩም፡፡ ምርጫ ሊሰጠን ይገባል፡፡ ሞራል ካላቸው ሀብቱ የአፍሪካውያን እንደሆነ ከሚያምኑ ጋር እንሰራለን፡፡ ቻይና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለአፍሪካ አምባገነኖች እርዳታ ታደርጋለች የሚል ተደጋጋሚ ስሞታ እንሰማለን፡፡ ግን እነሱ ራሳቸው የቻይናን ካፒታል ኢንቨስትመንት ይቀበላሉ፡፡ የቻይና የአፍሪካ አጋር ሆኖ መምጣት ለአፍሪካ ምርጫ ሰጥቷል፡፡ የቻይናን ስም የሚያጠፉትም ለዚህ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ብሪክስ አገሮች እየመጡ ነው፡፡ ዋናው ነገር ከሚጠቅመን ጋር መስራት ነው፡፡ ሁሉም ምእራባውያን ደም መጣጮች አይደሉም፡፡

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 23

መልሱን በገፅ 24 ይመልከቱ

እስቲ ገምቱ!የሚከተሉትን የእንግሊዝኛ ቃላት ፍቺ

ለማወቅ በመሞከር የቃላት ሞክሩ፡፡1. Blush2. Friended 3. Headstrong4. Linseed5. Leprosy6. Oculist7. Pedicle8. Reins9. Serpent10. Sheath

ያሉዋቸው መጻሕፍት ከሦስት ሺህ በላይ ስለሆኑ፤ እንዲህ በቀላሉ ካንዱ ስርቻ የሚሸጎጡ፣ ወይም አንዱጋ የሚደረጉ አይደሉም - መቸም፡፡ አቶ ሻንግ ደግሞ፤ መጻሕፍታቸው፤ በሌላ ማንም ባዕድ እጅ ንክች እንዲደረግባቸው ከቶም አይሹም፡፡ ምን ሲደረግ! ‹‹መፅሀፍቶቼ ለእኔ ህይወቴ ናቸው!›› ይላሉ፡፡

የዛን እለት ግን አይቀሬው መከራ እውን ሆነ፡፡ የሆነው ሁሉ የሆነው… እሳቸው በሌሉበት ነበር፡፡

ሚስታቸው፤ መቼም ይሁን መች፤ ያው የእነርሱም ተራ ሲደርስ፤ በድንገት መዝጊያቸው በሀይል ተከፍቶ፤ ቤታቸው እንደሚበረበር ታውቅ ነበርና፤ አዛውንቱ፤ አይናቸው ሥር መጻሕፍቶቻቸው ሲቃጠሉ እንዳያዩ ስትል፤ራቅ ያለ ስፍራ የሚኖሩ ዘመዶቻቸውን ጠይቀው እንዲመጡ አግባብታ ሸኘቻቸው፡፡ ወዲያውም፣ ጊዜ ሳታጠፋ፣ በርራ በመንደሩ ወደሚያንዣብቡት ቀይ ቃፊሮች ዘንድ ሄዳ፤ እጅ መንሳት፤ ባለቤቷ አቶ ሻንግ በሌሉበት፤ አሁኑኑ በፍጥነት መጥተው፤ መጻሕፍቶቹን ከቤት በመውሰድ ውለታ እንዲውሉላት ተማፀነቻቸው፡፡

መጻሕፍቱ፤ ተለቃቅመው ተወስደው ዋና ከተማ ሲደርሱ፤ ቀይ ቃፊሮቹ ባስመዘገቡት ታላቅ ስኬት፣ ከአዛዦቻቸው ሙገሳና ውዳሴ ተዥጎደጎደላቸው። ምክንያቱም፤ እስከዛሬ ከዜጎች ታዛ ወጥተው ከታዩት መጻሕፍት ሁሉ በብዛት በመብለጣቸውና ከመጻሕፍቱ ጋርም፤ አዛውንቱ እድሜ ዘመናቸውን ሙሉ ሲጠበቡባቸው የኖሩት ሁለገብ የጥናትና ምርምር ዶሴዎች፤ ውብ የፈጠራ ድርሰቶች፣ በርካታ ያለቁ የስዕል ቅቦች፣ በእንጥልጥል ያሉ ያልተቋጩ ስራዎች፣ አዳዲስ ጅምር ንድፎችና ቁጥራቸው የማይታወቅ ቅኔዎች ጥራዞችም አብረው ተጭነው ነበር፡፡ አብዮተኞቹ አደልበው ለሚመገቧቸው አሳማዎች የሦስት ቀን መኖ በመሆን፤ የተረፈውም ለምግብ ማብሰያ ማገዶነት ውሎ ባለስልጣናቱን ከቀለብ ወጪ አድኗቸዋል፡፡

አቶ ሻንግ፤ ዘመድ ጥየቃ ከሄዱበት ተመልሰው የሆነውን ነገር ሁሉ በሰሙ ጊዜ፤ ራሳቸውን መቆጣጠር ተስኗቸው መሬት ላይ ተዘረሩ፡፡

እሳቱ ከገፅ 19 የዞረልጆቻቸው፤ አፋፍሰው ተሸክመው፤ ወደ ቤት አስገቧቸው፡፡ አልጋ ላይ አስተኟቸውና ሀኪም በቶሎ መጥቶ እንዲያያቸው አደረጉ፡፡

ከሳምንት በኋላ፤ አዛውንቱ ከህመማቸው ቢያገግሙም፣ በዕድሜያቸው ላይ አስር አመታት ያህል የጨመሩ መስለው፤ እርጅት ብለው ታዩ፡፡ ቀኑን ሙሉ፤ ተጠራርገው የተወሰዱት መጻሕፍቶቻቸው ለዘመናት በክብር የኖሩበትን፤ እራቁቱን የቀረ ባዶ መደርደሪያ፤ ትክ! ብለው እያዩ፤ በፅናት ሲሰበስቧቸው የኖሩት የመጻሕፍት አይነት ድቅን ሲሉባቸው፤ ተንሰቅስቀው ያነባሉ፡፡

እነዚያ እፁብ ድንቅ መጻሕፍት የተደራጁት፤ ከቅድመ አያታቸው ዘመን ጀምሮ እስከ ሦስት ተከታታይ ትውልድ የቤተሰቦቻቸው ውርስ ነበሩ። እርሳቸውም በተራቸው እየገዙ፤ ላባቸውን ጠብ አድርገው፣ ደም ተፍተው ሰርተው ከሚያገኟት ገቢ ላይ እየቆጠቡና ላደረባቸው የንባብ ፍቅር ተሸንፈው፤ ጦም እያደሩም ጭምር ነበር ያጠራቀሟቸው፡፡

‹‹እኮ መፅሀፎቼ ምን በደሉ? አምላኬ ሆይ!›› እያሉ ያለቅሳሉ፡፡ ግን ደግሞ፤ በድብቅ እንጂ፤ ፊት ለፊት ሀዘንን መግለፅ በአብዮቱ የተከለከለ ነው! ቤትን ዘግቶ መነፋረቅ ይቻላል!!! ነው ህጉ፡፡ ባለቤታቸው፤ ሀዘናቸውን እንዲረሱ የምትችለውን ሁሉ ብትጥርም ከንቱ ድካም ሆነባት፡፡ አዛውንቱ፤ ለአምሳያ ታሪክ ትዝብታቸው እንዲህ ሲሉ ስንኝ ቋጥሩ...

ሺህ መጻሕፍት ተቃጥለውጢሱ ነክቶ ሰማይ፤ንጉሠ ነገስት ቺንአይን ኖረው እሚያይ፡፡(ንጉሠ ነገስት ቺን፤ በፈላጭ ቆራጭ አገዛዙ

የታወቀ፣ ከሁለት ሺህ ሁለት መቶ አመታት በፊት በነበረው የንግሥና ዘመኑ፤ የትየለሌ መጻሕፍትን በማቃጠሉና አምስት መቶ ያህል ልሂቃን ዜጎችን በመፍጀቱ የሚታወቅ ግፈኛ ንጉሥ ነበር፡፡)

ሊቀመንበር ማኦ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ከእኛ ጋ ሲነፃፀር፤ ንጉሠ ነገስት ቺን ምንም

ነበር፤ እኛ በቁርጠኛው አመራራችን፤ በልሂቃን ነን

ባይ ዜጎቻችን ላይ የወሰድነው የማያዳግም ቆራጥ እርምጃ፤ ከእሱ መቶ እጥፍ የሚያስከነዳ ነዋ!››

እጅግ ብርቅና ውድ የሆኑ ቅርሶች ሁሉ እሳት ተማገዱ፡፡ መጻሕፍት,፣ ረቂቅ የስዕል ጥበብ ውጤቶች፤ቤተሰቦች ከጥንት በውርስ የተላለፈላቸውና ለረዥም ዘመናት በክብር የያዙዋቸው የትውልዳቸው የዘር ሀረግ መጠበቂያ መዛግብት፤ እናም አሮጊቶች ከልጃገረድነት ዕድሜያቸው ጀምሮ ከየቁምሳጥኖቻቸው አናት ላይ በልዩ ሙዳየ ሳጥን ከፍ አድርገው ሰቅለው,፣ እስከዚህ ጊዜ ድረስ በትዝታው እየታደሱ በስስት ያቆዩዋቸው፡ ለማይደገመው የሠርግ ቀናቸው የለበሷቸው ውብና ደማማቅ አልባሳት ሁሉ፡፡

የተቃዋሚ ጎራ አባላቱና ቤተሰቦቻቸው፤ ገና ለአካለ መጠን ያልደረሱ እምቦቃቅላ ልጆቻቸውን ጭምር ይዘው፤ በእሳቱ ዙሪያ እንዲሰባሰቡ፤ ከዚያም ፊት ለፊታቸው የሚንቀለቀለውን ነበልባል ከብበው፣ በደንብ ጥስቅ አድርጎ እንዲቆረቁራቸው ታስቦበት ኮረት በተነሰነሰበት ጉርብጥብጥ መሬት ላይ፤ ልብሳቸውን ወደ ባታቸው እየሰበሰቡ,፣ በሌጣው ጉልበታቸው እንዲንበረከኩ ተገደዱ፡፡

ቀይ ቃፊሮቹ፤ ከኋላቸው ዙሪያቸውን እየተሯሯጡና በቁጣ እያምባረቁባቸው፤ እጃቸው የገባውንም አፈፍ አርገው እያምቸለቸሉ ያሰቃዩዋቸዋል፡፡ ጀርባቸውን ይዠልጧቸዋል። ሴቶቹን በፀጉራቸው መሬት ለመሬት እየጎተቱና ዞማቸውን ቆዳቸው ስር ገብተው እየመደመዱ፤ በአናታቸው አመድና ትቢያ ይነሰንሱባቸዋል፡፡

በድንገት፤ አንዱ ጠብደል ቀይ ቃፊር፤ ‹‹ጩኹ!›› የሚል ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ ከዚያም እየፎከረ,፣ እየፎገራ፤ ‹‹እናንተ ጭራቅና ሰይጣኖች ናችሁ! እኛ አብዮት ነው ያቀጣጠልነው፤ የአብዮታችን ወጋገን ደግሞ፤ ነበልባሏ አራስ ልጅም ልትበላ ትችላለች! እህ ምን ታመጣላችሁ እሺ?! በሉ‚ኮ ለእነርሱ አልቅሱላቸው! ለአብዮታችን ለምንሰዋቸው ጨቅላዎች!እ?! አልቅሱኮ ነው የምለው!! በሉኮ አልቅሱ!!!›› እያለና አስሩን እየዘላበደ፡ እየደነፋ፣ እያቅራራ፤ በያዘው አንጀት የሚያሳርር ብረት አለንጋ ያለ ርህራሄ ይነርታቸው ጀመር። ከመሀከላቸው፤ ስቃዩን መቋቋም ያቃታቸው፤ ራሳቸውን መርዳት የማይችሉ አቅመ ደካሞች፤ ጉልበታቸው እየተብረከረከ ወደሚግለበለበው እሳት ወደቁ፡፡ ከመላ አካላቸው ሁሉ በፊት፤ ፀጉርና የአይን ሽፋሽፍቶቻቸው በነበልባሉ ሲንጨረጨሩ፣ ሽታው አካባቢውን ያቆንሰዋል፡፡

አንዲት ለጋ ቀምበጥ፤ በእድሜ የገፉትን የምስኪን እናትና አባቷን ሰቆቃ ማየት ከአቅሟ በላይ ሆኖባት፣ ድምጿን ከፍ አድርጋ ‹‹እኔን ግደሉኝ! ቤተሰቦቼን ተዉአቸው! እባካችሁ ልለምናችሁ?! በእነሱ ፈንታ ይኸው እኔን ግደሉኝ?!›› አለች፡፡ ግን ማንም ጉዳዬ ያላት አልነበረም፡፡ ወዲያውም ራሷን ወደ እሳቱ ወረወረች፡፡ ሙሉ ለሙሉ የወደቀችበት እሳት በቅፅበት ከፀጉርና ሽፋሽፍቷ ጀምሮ ልብሶቿን እያያያዘና እያቀጣጠለ አገነተራት፡፡ ሁለት ደጋግ ሰዎች፤ ጎትተው ወደ ዳር አወጧት፡፡ ሆኖም ግን እሳቱ መላ አካሏን ፈጅቶ በልቷታል፡፡ አንድም ያልተቃጠለ የሰውነት ክፍል አልነበራትም፡፡ በተለይ ፊቷ ክፉኛ በመጎዳቱ፤ መልኳን አይቶ ለመለየት አስቸጋሪ ነበር። ስምንቱ የእጅ ጣቶቿም ተጎርደው ስለወደቁ፤ በቀድሞ ቦታቸው ላይ ምልክታቸው ብቻ ቀረ፡፡

ይህቺ መከረኛ ውብ ወጣት፤ምንም በማታውቀው ጉዳይ፤ ‹‹ያለፈው ስርአት ርዝራዦች ዲቃላ!›› በሚል ነው በተቃዋሚነት የተኮነነችው፡፡ የሀኪም እርዳታ ማግኘት የሚታሰብ አልነበረምና፤ ለረዥም ጊዜ ሳትገላበጥ በአንድ ጎኗ ብቻ በተኛችበት ደንዝዛ ከረመች፡፡ ቆይቶም ዘመዶቿ፤ በእሳት ነፍሮ የተወለጫጨመ ሰውነቷን አጣጥበው ሲያበቁ፤ ባህላዊ መድኃኒት ነው ያሉትን ቅጠል ጨምቀው አሻሹላት፡፡

ሆኖም ግን፤ የደረሰባት ቃጠሎ፤ በወቅቱ ተገቢውን ህክምና ስላላገኘ፤ ፊቷ የቋጠረው ደምና መግል እያደር እያዠ፣ እያመረቀዘ፤ ፍፁም ሌላ አይነት አስፈሪ ግን ደግሞ አንጀት የሚያላውስ አሳዛኝ አይነት ገፅታ ይፈጥር ጀመር፡፡ በእቶኑ ስለት ተቆርጥመው የተጎነደሹ ውብ ጣቶቿ ተተክለውባቸው የነበሩት፤ በእሳቱ ረመጥ ነፍረው፣ አርረው የከሰሉት የእጅ መዳፎቿም፤ ፈጽሞ መንቀሳቀስ የማይችሉ፤ በድን ሆነው ቀሩ፡፡

ምንጭ - (Australian Short Stories No.58 -1997. THE FIRE Shi Pang Fan.)

ማስታወቂያ

Flintstone homes is a real estate businesslaunched in 2008 by Flintstone Engineering, a prominent construction firm in the country.

Flintstone homes, one of the leading real estate companies in the city, would like to work with professionals architects on its upcoming new project.

• The project site is located at Bole sub city aroundOlympia square which rests on 1800 m2 plot area

• The company is planning to build an eight story mixed use building on the plot

This is, hence, an invitation for individual architects to participate in the architectural design competitionwith their design ideas for the project.

Those interested professionals can contact the company with the following e-mail address and can get further information on the project.

Email:[email protected] HOMES

Expression of interest

ሳኡዲ ከገፅ 1 የዞረየሚያረቡትና የመሣሠሉትን ስራዎች የሚሠሩት የውጭ ሃገር ዜጐች ሆነዋል” ብለዋል አቶ አበባው። የሣውዲ አረቢያ መንግስት “ከሃገሬ ውጡልኝ” ቢል እንኳ፤ የስደተኞችን ሰብአዊ ክብር በጠበቀ መልኩ ማስፈፀም ነበረበት ያሉት አቶ አበባው፤ “ነገር ግን ኢትዮጵያውያኑ በፖሊስ እየተገደሉና እንደ አውሬ እየተሣደዱ ነውና በዚህም የሣውዲ መንግስት ተጠያቂ ይሆናል” ብለዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገፆችና መገናኛ ብዙሃን ላይ የሠላማዊ ሠልፍ ጥሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ መግለጫዎችን ሲሠጥ የነበረው የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው፤ የሣውዲ አረቢያ መንግስት ህገወጥ የሚላቸውን ስደተኞች በህገ ወጥ መንገድ ማሠቃየቱ በምንም መዘዘኛ ተቀባይነት እንደሌለው ገልፀው፤ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ደካማነት የሚያረጋግጥና የኢትዮጵያንም ህዝብ የሚንቅ ድርጊት ነው ብለዋል። የአገራችን ባለስልጣናት ጉዳዩን የተመለከቱበት መንገድ አሣዝኖኛል፤ አሣፍሮኛልም ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ “ጥንታዊ ታሪክና ክብር ካለው ሃገር መሪዎች የሚጠበቅ አይደለም” ብለዋል፡፡ በየአመቱ አንድ ሚሊዮን ስራ አጥ እየተፈጠረ መሆኑን የሚናገሩት ኢ/ር ይልቃል፤ ወጣቱን ለስራ ፈጣሪነት የሚጋብዝ ነገር አለመኖሩ አንድ የስደት መንስኤ ነው ብለዋል፡፡ “የተማረና አቅሙ የፈቀደ በቦሌ ይሄዳል፤ ያልተማረው ደግሞ ውሃ ይብላኝ እያለ በረሃ እያቋረጠ ይሄዳል” የሚሉት ኢ/ር ይልቃል፤ “አገር እያደገች ዜጐች ስደትን ይመርጣሉ የሚለው የባለስልጣናት አባባል ውሸት ነው” ይላሉ፡፡ የሣውዲ አረቢያ መንግስት በዜጐች ላይ የፈፀመው አሠቃቂ ድርጊት ሳያንስ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትና የመንግስት ሚዲያ ለጉዳዩ የሠጡት አናሣ ትኩረት አሳዝኖኛል ብለዋል - የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር፡፡

በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጐቻችን ሲሰቃዩና የሰው ህይወት ሲጠፋ፣ መንግስት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት አልሰጠም የሚሉት ኢ/ር ይልቃል፤ የኢትዮጵያ እና የሣውዲ አረቢያ መንግስት በእኩል ደረጃ ተጠያቂ ናቸው ብለዋል፡፡

የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በበኩላቸው፤ ፓርቲያቸው ጉዳዩን በአፅንኦት እየተከታተለው መሆኑን ገልፀው፤ በሳውዲ የተፈፀመው ተግባር በእጅጉ የሚያሣፍር እና የሚያሣዝን ነው ብለዋል። ማንኛውም ሃገር የራሱን ህግና መመሪያ ሊያወጣ ይችላል ያሉት ዶ/ር ነጋሶ፤ ይሁን እንጂ “ፍቃድ አላሣደሡም” በሚል ሰበብ ዜጐቻችን የሠው ልጅን ክብር በሚያዋርድ ሁኔታ ለስቃይ መዳረጋቸው ብሄራዊ ሃፍረት ነው ብለዋል። ድርጊቱን በፈፀሙት አካላት ላይ ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑን ዶ/ር ነጋሶ ጠቅሰው፤ የሣውዲ አረቢያ መንግስትና የፖሊስ ሃይሉ በህግ ሊጠየቅ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ “አሁን ግን በዜጐቻችን ላይ እየተፈፀመ ባለው ድርጊት የአገራችን ሉአላዊነት ተነክቷል፤ የኢትዮጵያ መንግስትም ይህን የማስጠበቅ ሃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ አይደለም” ብለዋል ዶ/ር ነጋሶ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ጠበቅ ያለ አቋም መውሠድ እንዳለበትና ዜጐች ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ በአስቸኳይ መፍትሔ መስጠት እንዳለበትም አሣስበዋል፡፡

የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ስራ አጥነትና የመሣሠሉት ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች የሃገሪቱን ዜጐች ለስደት እየዳረገ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ነጋሶ፤ መንግስት ድክመቱን እንዲያሻሽል ሁሉም ዜጋ ግፊት ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 24

ኢትዮጵያ ከገፅ 14 የዞረ

ተለየን በድንገት በብዙ ሁካታየብዙዎች አባት የብዙዎች መከታነበር መመኪያችን ምሶሶ ማገርቅጣው ተለይቶን አይ አቤት መደበርናፈቀን ድምፅህ ሳቅ ጨዋታህአብዬ ቆንጆው የትነው መኖርያህትጉነትህ ታታሪ ኮስታራ ለስራተምረናል ካንተ ምን እንደምንሰራአባታችን አሉ የሚያውቁህ በሙሉጮኸው አለቀሱ አዘኑ በሙሉናፍቆት ለካ እንዲህ ነው ናፈከን ሁላችንንታዲያ ምን ያደርጋል ራቅህ ከአይናችንአትሂድ ብልህም እሄዳለሁ አልከኝሂድ እንግዲህ ይቅናህ ለእኔም እግዜር አለኝአብዬ አብዬ አንተ መልከ ቀናእንግዲህ ማን ይቀበለን ቤትህ ፈረሰናአትመለስ በቃ ሸኘንህ በጩኸትወደሰማያዊው የዘላለሙ ቤትአደራ እንላለን አምላክን በለቅሶበቀኝ እንዲያቆምህ ነፍስህን ቀድሶ

አብዬ እንወድሃለንከባለቤቱ፣ ከልጆቹ ከቤተሰቦቹ

የአቶ ቅጣው መሸሻ ዶሪየ1ኛ ዓመት መታሰቢያ

እግዚአብሔር የወደደውን አደረገ መዝ 135፣6የአቶ ቅጣው መሸሻ ዶሪ የ1ኛ ዓመት መታሰቢያ ህዳር 13 ቀን 2006 ዓ.ም በአንስሮ ወረዳ ዳለቴ ማርያም ቤተክርስቲያን

በፀሎት ታስቦ ይውላል፡፡

ደግና የጥሩ አባት ተምሳሌት የነበርከው አባታችን

ሁሌም ከህሊናችን አትጠፋም፡፡

በደብረ ሐሚን ተ/ኃይማኖት ቤተክርስቲያን ህዳር 10/2006

ዓ.ም በፀሎትና ፍትሐት ነዳያንን በመዘከር ታስቦና

ተከብሮ ይውላል፡፡ከባለቤታቸውና ልጆቻቸው

የአቶ ወልደማሪያም ብዛኔየ2ኛ የሙት ዓመት መታሰቢያ

በቅንነትና በደግነት የሄደ ከአልጋው ላይ ያርፋል (ኢሳ.54፣2)

ምን ማለት እንደሆነ ፈፅሞ የማያውቁ ሚሊዮኖች በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ይገኛሉ፡፡ በዘርፉ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ከ34ሺ የሚበልጡ የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ሰልጥነው በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እንዲሰማሩ ቢደረግም የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች የማይደርሱባቸውና ዛሬም ሳይፈልጉ በየዓመቱ የሚወልዱ እናቶች በርካቶች ናቸው፡፡

ባለሙያዎች ህብረተሰቡን ለማዳረስ እንዲሁም አስተማማኝና በጤናቸው ላይ ጉዳት ሊያስከትል የማይችል የወሊድ መቆጣጠሪያ ለመስጠት አሁንም የአቅም ውስንነት ችግር አለባቸው፡፡ የአገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ያለባቸው ምን አይነት ሴቶች እንደሆኑ፣ መጠቀም የሚገባቸው የትኛውን አይነት የእርግዝና መቆጣጠሪያ ዘዴ እንደሆነ ግልፅ ማብራሪያ በማግኘት ረገድ ችግር እንዳለባቸው ተጠቃሚዎቹ ይናገራሉ፡፡

ሰሞኑን በUSAID የሚደገፈውን የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ለማየት ወደ ሻሸመኔ ከተማ ተጉዤ ነበር፡፡ አካባቢው የትራንስፖርት አገልግሎት እንደ ልብ የሚገኝበት እንደመሆኑ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደ ሆስፒታሉና ሌሎች ጤና ተቋማት የሚመጡ ነዋሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ማደጉን የከተማው አስተዳደር ምክትል ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ውድነሽ ብሩ ይናገራሉ። በአካባቢው አንድ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ ለአምስት መቶ ነዋሪዎች ተመድቦ ይሠራል፡፡ ይህ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር እንደሆነና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዋ ህብረተሰቡ ውስጥ በመግባት በአግባቡ ለማስተማርና የግንዛቤ ለውጥ ለማምጣት እንቅፋት እንደሚሆን በሥፍራው ያገኘናቸው የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 ዓ.ም የተደረገው የሥነ ህዝብ ጤና ጥናት እንደሚያመለክተው፣ 29 በመቶ የሚሆኑት በመውለጃ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች፣ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን የቻሉ ሲሆን ይሄም እ.ኤ.አ በ2005 ዓ.ም ከነበረው 15 በመቶ ጋር ሲነፃፀር በእጥፍ መጨመሩን ያሳያል፡፡ በሌላ በኩል 25 በመቶ ያህሉ በመውለድ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች፣ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት መጠቀም ቢፈልጉም በተለያዩ ምክንያቶች ዕድሉን ለማግኘት እንዳልቻሉ ይኸው ጥናት ይጠቁማል፡፡

የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ከሆኑት ሴቶች መካከልም አብዛኛዎቹ የአጭር ጊዜ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሲሆኑ ይህንን ለማሻሻልም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት የተለየ ትኩረት በመስጠት፣ ሴቶች የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሰፊ ቅስቀሣ ያደርጋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 ዓ.ም በክንድ

ሥር የሚቀበር የወሊድ መከላከያ፣ በ2010 ደግሞ ሉፕ የተባለውን የወሊድ መከላከያ አገልግሎት ለህብረተሰቡ በስፋት ለማዳረስ ተንቀሳቅሷል፡፡

በጤናው ዘርፍ የምዕተ ዓመቱ የልማት ግብ ከሆኑት መካከል ያልተሟላ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ፍላጐትን ማሟላት አንዱ ነው፡፡ በዚህ መሠረትም የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ሽፋኑን 66 በመቶ ለማድረስ እቅድ ተይዟል፡፡ ሆኖም በምዕተ ዓመቱ ይደረስበታል ተብሎ በዕቅድ የተያዘው ቁጥር ላይ መድረስ እንደማይቻልና አገሪቱ በዚህ ዘርፍ የተሳካ ዕድገት አለማስመዝገቧ ይነገራል፡፡ መንግስት ለቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ግብአት ለማሟላት የሚያስችል በጀት መድቦ መንቀሳቀስ የጀመረው እ.ኤ.አ በ2007 ዓ.ም ነው፡፡ ከዚያ በፊት አገልግሎቱ ይሰጥ የነበረው በአጋር ድርጅቶች እርዳታና ድጋፍ ነበር፡፡

መንግስት እንቅስቃሴ በጀመረበት ዓመት፣ ከአገር ውስጥ ገቢ 910.000 ዶላር፣ ከጋራ ቋት ደግሞ 12 ሚሊዮን ዶላር መድቦ ወደ ተግባር የገባ ሲሆን ይህም በየዓመቱ እየጨመረ በመሄድ ክልሎችም ለዚሁ አገልግሎት ከራሳቸው በጀት መመደብ ጀምረዋል፡፡

ለዚህ ዕቅድ እውን መሆን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የህዝብ ተወካዮች፣ የጐሣ መሪዎች፣ ማህበራት፣ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ መ/ቤቶች የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች ያልተቋረጠ ድጋፍና ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው ባለፈው ማክሰኞ ተጀምሮ ትናንት በተጠናቀቀው 3ኛው አለም አቀፍ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ጉባኤ ላይ ተገልጿል፡፡ “የተሟላ ምርጫ የተሟላ አቅርቦት” በሚል መሪ ቃል፣ ለአራት ቀናት ሲካሄድ በቆየው ዓለም አቀፋዊ ጉባዔ ላይ ከ3ሺ በላይ ተሳታፊዎች የተካፈሉበት ሲሆን ከ100 በላይ የጥናት ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጐባቸዋል። “አገሪቱ በዘርፉ በምዕተ ዓመቱ ልታሳካው ያቀደችውን ማሳካት ይቻላት ይሆን?” የሚለው ጉዳይ ግን የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል፡፡

መልስ1. የኃፍረት መቅላት2. ወዳጅ ያለው3. አንገተ ደንዳና4. ተልባ5. ለምፅ6. የዓይን ፈዋሽ7. ቅማል8. ቀበቶ9. እባብ፤ዘንዶ10. አፎት

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 25 ጃካራንዳ ከገፅ 5 የዞረ

ጥቅምት 25 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ በስምንት ሰዓት በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ውይይት ለማድረግ በምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት እንዳገኙ ለቦርዱ ሰብሳቢ የፃፉት ደብዳቤ በዝግጅት ክፍላችን ይገኛል፡፡

“ያለ ደረሰኝ ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮኑን ብር ለግለሰቦቹ እንዴት ልትሰጡ ቻላችሁ በሚል ለአቶ ደመላሽ ላነሳነው ጥያቄ “አሁን ካለው ቦርድ በፊት ስራ ላይ የነበረው ቦርድ ባስተላለፈው ትዕዛዝ መሰረት ክፍያ ፈጽመናል” ሲሉ መልሰዋል፡፡

የቦርድ አመራሮች ራሳቸው ቼክ ፈራሚ ራሳቸው ፈቃድና ወሳጅ በአጠቃላይ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው የሚሰሩበት አካሄድ ፈጽሞ ከህግ ውጭ በመሆኑ አሁንም ተቃውሟቸውን እንደሚቀጥሉ የተናገሩት አቶ ደመላሽ በአሁኑ ሰዓት እኔን ተክተው የሚሰሩት አቶ ፍቅረማርያም ሃ/ጊዮርጊስ የቁጥጥር ኮሚቴ ሆነው በሚሰሩበት ጊዜ ከላይ በቦርዱ ላይ ባነሳናቸው ቅሬታዎች ዙሪያ አብረው ይሰሩ እንደነበር ጠቁመው የቁጥጥር ኮሚቴ ሆነው ሳለ ስራ አስኪያጅ ሆነው መሾማቸው ከህግ አሰራር ውጭ ነው በማለት ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል። “እስካሁን ከላይ የገለጽኳቸውን 11 ነጥቦች ለንግድ ሚኒስቴር፣ ለድርጅቱ የውጭ ኦዲተር እና ለሚመለከታቸው አቅርቤያለሁ” ያሉት የቀድሞው የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ እና አደራጅ አሁንም ችግሮች ባለመቀረፋቸው የህዝብ ንብረትና ገንዘብ አደጋ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የእኔነት ስሜት ተሰምቷቸው የሚሰሩ ሰራተኞች በደሞዝ ማነስ ስለመሰናበታቸው በቦርዱ የተባረሩ ሠራተኞች ስለመኖራቸው እና በመሰል ጉዳዮች ስለተነሱት ቅሬታዎች በአስቸኳይ ምላሽ ካልተገኘ የድርጅቱ ህልውና አደጋ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የማህበሩ ባለድርሻና የቀድሞው የማህበሩ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ የነበሩት አቶ ጌታቸው ገብረየስ በበኩላቸው በአዲስ አበባ በሃላፊነት በሚሰሩበት ወቅት 12.5 ሚሊዮን ብር መሰብሰባቸውን ገልፀው “እኛን አምነው ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸው አካል ጉዳተኞች ሳይቀሩ አክሲዮን ገዝተው ጥቅም ሲጠብቁ ኩባንያው አሁን ያለበት ችግር ላይ መገኘቱ አንገት ያስደፋል” ይላሉ፡፡ ለድርጅቱ መቋቋም ደም የመስጠት ያህል መስዋዕትነት እንደከፈሉ የሚናገሩት አቶ ጌታቸው በዚህም ለጤና እክል ተጋልጠው በፈቃዳቸው ስራቸውን መልቀቃቸውን፣ ነገር ግን አሁን ያለው የቦርዱ አሰራርም ሆነ ኩባንያው ያለበት ሁኔታ ስጋት እንደሆነባቸው ይናገራሉ፡፡

“አሁን ሥራ ላይ ካለው ቦርድ በፊት የነበሩት ሁለት ጊዜ የተመረጡ የቦርድ አመራሮች በድርጅቱ ላይ ባደረሱት ጥፋት በጠቅላላ ጉባኤ ተሽረው አሁን ያለው ቢመረጥም ጥፋት እንጂ ልማት አላመጣም” ያሉት አቶ ጌታቸው፣

የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ቦርዶች ላይ መንግስት እርምጃ ቢወስድ ኖሮ ሶስተኛው ለእንዲህ አይነት ስህተት አይነሳሳም ነበር ሲሉ አማረዋል፡፡

“ይህንን በመቃወም እንቅስቃሴ እያደረገ ያለው አቶ ደመላሽ ከመስከረም ስድስት 2006 እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2006 ዓ.ም ድረስ ከስራም ከደሞዝም መታገዱ የቦርዱን ችግር ያሳያል” ብለዋል፡፡

ከላይ የተቀሱትን ቅሬታዎች መነሻ በማድረግ የቦርዱ አባልና ፀሐፊ የሆኑትን አቶ ሙሉ ሸዋ ከበደን ያነጋገርን ሲሆን ቦርዱ በአስቸኳይ ስብሰባ የተመረጠ እንደመሆኑ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ስልጣኑን ለምን አላፀደቀም የሚለውን ጥያቄ አስቀድመናል የቦርዱ ፀሐፊው መጋቢት 2 ቀን 2004 ዓ.ም በተጠራ ጠቅላላ ጉባኤ የቀድሞ የቦርድ አባላት ያጠፉት ጥፋት ተገልፆና የሚባረሩት ተባረው በተደረገ ምርጫ አሁን ስራ ላይ ያለው ቦርድ ሃላፊነት መረከቡን ገልፀው ይሁን እንጂ ይህ ቦርድ ሀላፊነት ሲረከብ ኩባንያው በብዙ ምስቅልቅል ችግሮች ውስጥ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡ በተለይም የድርጅቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ የነበረው አቶ ደመላሽ ወጋየሁ ተናኜ የተባለው ግለሰብ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ በሀላፊነት እየተንቀሳቀሰ እንደነበርና መጋቢት ሁለት በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ መሳተፉን፣ ከዚያም በጉባኤው ምርጫ መሰረት አሁን 18 ወራት በመስራት ያስቆጠረው ቦርድ የመጀመሪያው ስራ ርክክብ ማድረግ እንደነበር ገልፀው የቀድሞው ቦርድ ጋር ርክክብ ከማድረግ ይልቅ ህጋዊ ቦርድ አይደላችሁም በሚል ወደ ፍርድ ቤት ሄደው ከፍተኛ ክርክር እንደነበርና ጉዳዩ በፍትህ አካል ታይቶ “ጉባኤው የመረጠውን አካል ህጋዊ አይደለህም ማለት አይቻልም” ሲባል ተፈርዶባቸው 36ሺህ ብርም እንደተቀጡ የቦርዱ ፀሀፊ ይናገራሉ፡፡

“ከዛን ጊዜ ጀምሮ የኩባንያውን ውስብስብ ችግሮች በመፍታት ረገድ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ከማድረግ አልቦዘንም” የሚሉት ፀሀፊው አቶ ደመላሽም የቦርዱን ችግሮች ለመፍታት አብሮ ከቦርዱ ጋር ሲሰራ እንደነበረም አስታውሰዋል፡፡ ጉባኤው የቀድሞውን የድሬክተሮች ቦርድ ሲያሰናብት አቶ ደመላሽ በስራ አስኪያጅነት እንዲቀጥል ስምምነት ላይ መደረሱን የሚገልፁት አቶ ሙሉ ሸዋ፣ “አቶ ደመላሽ አልፀደቁም ህጋዊ አይደሉም ለሚለው እኛ ለሶስተኛ ጊዜ የተመረጥን እንጂ ለኩባንያው አዲስ አይደለንም” ካሉ በኋላ ግለሰቡ ከስራ የተሰናበተው ለአክሲዮን ማህበሩ አባላትም ሆነ ለሌሎች አካላት ውዥንብር የመንዛት እንቅስቃሴ ላይ በመሆኑ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ አቶ ደመላሽ “በኩርፊያ በገዛ ፈቃዱ ጳጉሜ አንድ ቀን 2005 የኩባንያውን ስራ ለቆ የተለያዩ ለማህበሩ ጐጂ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ እንደሆነ ደርሰንበታል” ይላሉ አቶ ሙሉ ሸዋ፡፡

“የድሬክተሮች ቦርድ በወር አንድ ጊዜ እየተገናኘ ማኔጅመንቱን ይቆጣጠራል እንጂ ዝቅ ብሎ ኦፕሬሽናል ስራአይሰራም” የሚሉት የቦርዱ ፀሀፊ፣ “እኛ ስራውን ስንረከብ ከገጠሙን ፈተናዎች ውስጥ የ2002፣ የ2003 እና የ2004 ዓ.ም ሂሳብ አለመመርመሩ ነው” የሚሉት አቶ ሙሉ ሸዋ ከዚያም ቦርዱ በያዘው አቋም የ2003 እና የ2004 ዓ.ም ሂሳብ በውጭ ኦዲተር መመርመሩን ይናገራሉ። የውጭ ኦዲተሩም የማህበሩ አባላት የሰየሙት በመሆኑ በሂሳብ አያያዙም ላይ በርካታ ችግሮች እንዳሉበት አስተያየት ሰጥቷል ብለዋል፡፡ “ለረጅም ጊዜ ስራ አስኪያጅ ሆኖ እንደመስራቱ የውጭ ኦዲተሩ ችግሮች ብሎ በሰጣቸው አስተያየቶች ላይ ለጠቅላላ ጉባኤ ስራ አስኪያጁ ምላሽ እንዲሰጥ በማለት የስብሰባ ፈቃድ አውጥተን፣ የአዳራሽ ኪራይ ተነጋግረን ጨርሰን እያለ ጉዳዩ ወደ ውጥረት ሲገባ ጳጉሜ 1 ቀን 2005 ዓ.ም ከስራ እንድናሰናብተው ጠየቀን” ሲሉ አብራርተዋል፡፡

“አንድ አክሲዮን ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ሲጠራ ዋናውን እና አባለት መስማት የሚፈልጉት የፋይናንስ ሪፖርት ነው” ያሉት የቦርዱ ፀሀፊ፣ የፋይናንስ ሪፖርት በምናዘጋጅበት ጊዜ እንቅፋቶችን የፈጠረብን ያለው አቶ ደመላሽ ነው” ብለዋል። ፀሀፊው አክለውም ብዙ የአክሲዮኑ ባለ ድርሻዎች አዲሱን ቦርድ የአቶ ደመላሽ አሸርጋጅ አድርገው በመውሰድ “ሰውየው አጭበርባሪ ነው ለምን አትሰሙንም” በሚል ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበር ይላሉ፡፡ ጳጉሜ አንድ ቀን ስራውን ሽባ አድርጐ ሲጠፋ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ የፋይናንስ ሪፖርት ተደርጐ ጉባኤው የሚወሰነውን ሰምተህ መሰናበት አለብህ በሚል ደብዳቤ መፃፋቸውን እና የፃፉትን ደብዳቤ ኮፒ ሰጥተውናል፡፡

የቦርዱን አመታዊ በጀት በተመለከተ ከ97ሺህ ብር እንዴት 131ሺህ ብር አደገ ለሚለው ጥያቄ አቶ ሙሉ ሸዋ ሲመልሱ ቦርዱ እንደማንኛውም የአክሲዮን ማህበር ቦርድነቱ በንግድ ህጉና በአክሲዮን ማህበር መተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ወርሀዊ አበልና የስብሰባ አበል እንዳለው ገልፀው፣ ወርሀዊ እና የስብሰባ አበሉን የሚከፍለውም አቶ ደመላሽ እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡

“ማህበሩ በትክክለኛ በጀት የሚንቀሰቀስ አልነበረም ትክክለኛ በጀት በ2004 ዓ.ም የሰራነው እኛ ነን” የሚሉት አቶ ሙሉ ሸዋ ከመጠን በላይ ተከፈለ የሚባለው ሊሆን አይችልም ምክንያቱም በወር የሚከፈለው እና በስብሰባ የሚከፈለው አባል የታወቀ ነው ብለዋል፡፡ “ምናልባት ከፍ ብሏል ብሎ አቶ ደመላሽ የገለፀው በማህበሩ የተለያዩ ችግሮች ሳቢያ በርካታ ስብሰባዎች ይካሄዱ እንደነበር፣ በድርጅቱ ላይ የተመሰረቱ በርካታ ክሶች እንደነበሩ፣ አቶ ደመላሽን በየሳይቱ ለስራ በላክነው ቁጥር “ሰዎች ሊገድሉኝ እየተከታተሉኝ ነው” ሲል እሱን ለማዳን ወደ አዋሽ እንደሚሄዱ፣ ባኮቲቤ ላይም ሽፍቶች ሊገድሉኝ ነው ሲል ተነስተው እሱን ለማዳን እንደሚሄዱ ገልፀው ይህ ሁሉ ወጪ ሲወጣ ያውቃል ግን በደብቅና ለቦርዱ አባላት ጥቅም ተብሎ የባከነ ሳይሆን እርሱ ለፈጠራቸው ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ነው ይላሉ፡፡ “ከዚህ በተረፈ ላጠፋው ጥፋት ሽፋን ለመፍጠር በቦርዱ ላይ ስም የማጥፋት ዘመቻ ቢከፍትም ማንም ከህግ የሚያመልጥ ስለ ሌለ እኛም ካጠፋን እሱም ካጠፋ በህግ እንጠየቃለን” ብለዋል አቶ ሙሉ ሸዋ፡፡

“ጥቅምት ሰባት ቀን በስድስት ገፅ ደብዳቤ ቦርድ ደንቆሮ ነው በሚል ዘለፋ አካሂዷል” ሲሉም ተናግረዋል የቦርዱ ፀሀፊ፡፡

ቦርዱ እስካሁን ጠቅላላ ጉባኤ ለምን አልጠራም በሚል ላነሳነውም ጥያቄ ስራ ላይ ያለው ቦርድ መጋቢት ወር 2004 መመረጡን ፀሀፊው አስታውሰው፣ በንግድ ህጉ መሰረት የበጀት አመቱ ባለቀ በሶስት ወር ስብሰባ መጥራት ግድ መሆኑንና የበጀት አመቱ ባለቀ በሶስት ወር ስብሰባ ለማካሄድ የ2004 የበጀት ሪፖርት መጠየቃቸውን ሆኖም እንኳን የ2004 የ2002 እና የ2003 ሪፖርት እንደሌለ እንደደረሱበት ይህ ሁሉ ሪፖርት ሳይስተካከል ጠቅላላ ጉባኤ መጠራት እንደማይቻልና ይህን ሲያስተካክሉ ስብሰባውን እንዳልጠሩ ተናግረዋል። ከአቶ ደመላሽ ጋር የጠባቸውም መነሻ ይሄው እንደሆነ ያብራራሉ፡፡

“የ2003 የሂሳብ ሪፖርት አቅርብ ሲባል ሂሳብ ያዧ ዘግታበት ሄዳለች በሚል ማስመርመር አልቻልኩም አለ”

የሚሉት ፀሀፊው ቦርዱ ለቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስና ለፌደራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንተ አመልክቶ ፖሊስና የፍትህ አካላት ባሉበት ሳጥኑ መከፈቱን፣ የ2003 እና የ2004 ዓ.ም በብዙ ውጣ ውረድ እንዲዘጋ ማድረጋቸውን ገልፀዋል። ጉባኤው ለሾመው የውጭ ኦዲተር እንዲመረመርም ተደርጓል ይላሉ፡፡

“ይሁን እንጂ የ2005ን ጠቅላላ ጉባኤ እንዳንጠራም አቶ ደመላሽ እንቅፋት ሆኖብልና” ይላሉ ምክንያቱንም ሲያስረዱ፣ ሂሳቦችን በማሳከርና ውዥንብር በመፍጠር እንዲሁም የ2005ን የፋይናንስ ሪፖርት ሀርድና ሶትፍ ኮፒ ወስዷል ከዚያም ኮምፒዩተሩ ውስጥ ቫይረስ በመክተት ድራሹን አጥፍቶታል ይላሉ። ተጠባባቂ ስራ አስኪያጁ አቶ ፍቅረማሪያም ሃ/ጊዮርጊስ ሲጠይቁትም ለማቅረብ ፈቃደኛ አልሆነም ይላሉ፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ ከ 2500 በላይ አባላትን ጠርቶ ምን ይነገራል” ሱሉ ጠይቀዋል የቦርዱ ፀሀፊ።

“ቦርዱ በትክክል የሰራው 13 ወር ነው ከዚያ በፊት ያሉትን ስምንት ክሶች ስናስተካክል ነበር” ያሉት አቶ ሙሉ ሸዋ ከነዚህ ክሶች ውስጥ አንዱ ገንዘብ ያዧ ሊደፍረኝ ነበር ያለ አግባብ ከስራ ተባርሬያለሁ” የሚል እንደነበር ያብራራሉ፡፡

በንግድ ሚኒስቴር የምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት ለቦርዱ የፃፈውን ደብዳቤ በተመለከተም ቦርዱ ለሚኒስቴሩ ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት ምላሽ የሰጠበትን ደብዳቤ ከቦርዱ ፀሀፊ አግኝተናል፡፡ ደብዳቤው ለምን ስብሰባ እንዳልጠራ አቶ ወጋየሁ ፈፀሙ ያለውን ስህተትና እየተካሄዱ ያሉ ጉዳዮችን ለዳይሬክቶሬቱ ፅፏል፡፡

“አቶ ደመላሽ ወጣትና የሀሳቡ አመንጪ ነው በሚል እምነትና ሀላፊነት ጥለንበት ነበር” የሚሉት ፀሀፊው አሁን ጥሎ ሲሄድ የስድስት ወር የቤት ኪራይ፣ የሶስት ወር የሰራተኞች ደሞዝ፣ የስድስት ወር የቢሮ ስልክ ሂሳብ፣ ቀጥተኛ መስመር ያለው የተንቀሳቃሽ የሶስት ወር ሳይከፍል እጅግ በርካታ ኪሳራዎችን አድርሶ እንደሆነ ይናገራሉ። ገንዘቡን ለመክፈል ባደረግነው ጥረት ከዚህ በፊት ከቦርዱ እውቅና ውጭ በዱቤ 160 ከብቶችን ሸጦ በፍ/ቤት ግለሰቦቹን አሳስረው አክሲዮን ማህበሩን ሂሳብ በመሰብሰብ እየተንቀሳቀሱና እዳዎችን እየከፈሉ እንደሚገኙ ፀሀፊው ተናግረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ቲኬ ህንፃ ላይ የተከራየው ቢሮ ከማህበሩ አቅም በላይ 40ሺህ ብር በወር እንደነበረ፣ ከዚያም ቦርዱ ወደ 20ሺህ ዝቅ የሚል ቢሮ መከራየቱን፣ አሁን ደግሞ የነገው ሰው ት/ቤት ፊት ለፊት ባለ 12ሺህ ብር ቢሮ በመከራየት ኩባንያውን ከወጪ እየታደጉ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

ሰራተኞችን ቦርዱ እያባረረ ነው የሚባለውን በተመለከተ በየሳይቱ ያሉ ፕሮፌሽናል ሰራተኞችን እያባረረ የነበረው አቶ ደመላሽ መሆኑንና የቦርዱ አባላት ግን አግባብተው መመለሳቸውን ከነዚህም ውስጥ አንድ ሳይንቲስት እና አግሮኖሚስት እንደሚገኙበት ፀሀፊው ገልፀዋል፡፡

ሁለት የስልክ መስመሮችን መቀየር አስመልክቶም ፀሀፊው መስመሮቹ መቀየራቸውን አምነው እሱ ደውሎ በርካታ ገንዘብ በመቁጠሩ ቴሌ ሄደው ማዘጋታቸውን ሌላ አዲስ መስመር ቦርዱ ማውጣቱንና ለአባላት ማሳወቁን ገልፀዋል፡፡

ማህበሩ የመተዳደሪያ ደንብ የለውም የተባለውን በተመለከተ እርሱ ከስራ የለቀቀው ከሁለት ወር በፊት ነው ይህን ጥያቄ እስከ ዛሬ ለምን አላነሳም ሲሉ ጠይቀው ማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ያለው መሆኑን እንዲሁም የ2006 በጀት የለውም መባሉንም አስተባብለዋል፡፡

ያነጋገርናቸው አንድ ከፍተኛ አክሲዮን ያላቸውና ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ ግለሰብ በሁለቱ ወገኖች ውዝግብ በህዝብ ንብረትና ገንዘብ ላይ ኪሳራ እንዳይደርስ መንግስት በአፋጣኝ ጣልቃ ገብቶ እልባት እንዲያገኝ አሳስበዋል፡፡

ጉዳዩን ንግድ ሚኒስቴር እየተከታተለው እንደሆነ በደረሰን ጥቆማ መሰረት ንግድ ሚኒስቴር በተደጋጋሚ ከመደወል ባሻገር ሀላፊው በሰጡን ቀጠሮ ቢሯቸው ድረስ ብንሄድም አስቸኳይ ስብሰባ እንደገቡ የነገሩን በመሆኑ ምላሽ ማግኘት አልቻልንም፡፡

ውስጥ እያለ በዘመናችን መንገድ ላይ ማስመሰላችንን ተንተርሰን፣ በራስ ወዳድነት ቃሬዛ ላይ እንደተኛን በለመድነው ማስመስል “የሀኪም ያለህ” እያልን ማቃሰት ይዘናል፡፡ የመድኃኒቱ ፈዋሽነት አሊያም አጠቃቀሙ የጠፋብን አሳዛኝ የዘመን በሽተኞች! ከፊሎቻችን የመድኃኒቱ ፈዋሽነትና አወሳሰዱ ሳይጠፋብን፣ የመድኃኒቱን መራርነት ፈርተን ነው በማስመሰል “የሃኪም ያለህ” እያልን አማራጭ ፍለጋ ዘመናችንን የምናቃስተው፡፡ ዞሮ ዞሮ መድኃኒት የሚያስፈልገን በሽተኞች መሆናችን አያጠያይቅም፡፡

በየዕለቱ የሚወሰድና ለዓመታት የማያቋርጥ መራር መድኃኒት፣ ከማንም በላይ ከምንወደው ከራሳችን ማንነት ጋር መታገል ነው፡፡ ከእሬት የመረረ ቢሆንም ከጽኑ በሽታችን የሚፈውሰን መድኃኒት እሱ ነው፡፡

የዛሬው ቁስላችንን ሳይሆን የትናንት ጠባሳችንን በትዝታ እየታመምን፣ ዛሬን ዛሬን የምናለቅስበት እኛ፤ ከዛሬው ህመማችን ባሻገር የመልካምነታችን ንጋት ተስፋው እየታየን፣ በዘመናችን የምንደሰተው

መቼ ይሆን? የትውልድ ቀጣይነታችን ወንዙ በዘመን ሸለቆ

ውስጥ ስለሌለ ሳይሆን፣ በራስ ወዳድነት ለቅሶ የዕምባ ጅረት እየሰራ ቁልቁል የመፍሰሱ ማክተሚያ መቼ ይሆን? የዘመናችን ውቅያኖስ በራስ ወዳድነታችን ሞገድ ተናውጧልና ባህሩ ፀጥ እንዲል ከዘመናችን መርከብ ላይ የምትወረውረው ዮናስ የት ነህ?

የዘመኔ ዘመነኞች ሆይ፤ ምጤ እናንተ ናችሁና… እናንተን እጮኻለሁ!

በእኔ ውስጥ ስላላችሁ እናንተን እጮኻለሁ! ሰው መሆናችንን እያለምኩ እኛን እጮኻለሁ! ጆሮዎቻችሁ ወደ ድምጼ አቅጣጫ ተቀስረው

ጩኸቴን እስክታዳምጡ ድረስ እጮኻለሁ! ሀዘኔን የሚያስረሳ፣ ሕልሜን ዕውን አድርጐ

ተስፋዬን የሚያለመልም ድምጽ እስክሰማ ድረስ የዘመን ንቅሣቴን እጮኻለሁ!

“ሕይወት ከባድ ነች፤ የበጐች መንጋ የውሾች ግትልትል አይደለችም፡፡

እያንዳንዱ ውሻ ግን እንደየድምፁ ይጮኻል”ማክሲም ጐርኪይ

ዘመን ከገፅ 21 የዞረ

ማስታወቂያ

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 26

ፀሐይ ተፈረደኝ (ከኢሶግ)

ላንቺና ላንተ

ይህንን አምድ አዘጋጅቶ የሚያቀርብላችሁ ESOG-Ethiopian Society of Obstetricians and Gynecologists (የኢትዮዽያ የፅንስና የማህፀን ሀኪሞች ማኅበር) ነው፡፡ (በፖ.ሣ.ቁ 8731 ስልክ 011-5-506068/69 ልታገኙን ትችላላችሁ)

ለውጥ ከገፅ 4 የዞረ

እ.ኤ.አ ኦክቶቨር 17/20013 በኢትዮጵያ ደግሞ ጥቅምት 7/2006 ዓ/ም ጾታን መሰረት ባደረገ ጥቃት ምክንያት ለሚደርሱ የአካል፣ የስነልቡና ፣የህግና የጤና ችግሮች በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ማእከል ተመሳሳይ አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል አንድ ወጥ መመሪያ በማስ ፈለጉ በተዘጋጀው ረቂቅ ላይ ውይይት ተደርጎአል፡፡ በኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስ..ር አስተባ ባሪነት ከህግ፣ ከፖሊስ ከስነልቡና ፣ ከሴቶች ወጣቶች እና ህጻናት ሚኒስ..ር የተውጣጡ ሙያ ተኞች በኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሮጀክት ቢሮ ስብሰባውን ሲያደርጉ የማህበሩ አባላት እና የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች አስፈላጊውን ገለጻ አድርገዋል፡፡ ይህንን ረቂቅ በማዘጋጀት ረገድም በኢትዮጵያ ጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሮጀክቱን ሲመሩ የቆዩ የማህበር አባላት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። ስብሰባውን እንዲከፍቱ የተጋበዙት የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት ነበሩ፡፡ ዶ/ር ይርጉ እንደገለጹት...

“...የስብሰባው አላማ የጾታዊ ጥቃት የደረሰበት ሰው ወደ ሕክምና በሚመጣበት ጊዜ ሊደረግለት የሚገባው አገልግሎት በምን መልክ መሆን አለበት የሚለውን ለመፈተሸ ነው፡፡ የጾታዊ ጥቃትን በሚመለከት ለሚሰጠው ስልጠና ካሪኩለም ተዘጋጅቶ በአገር አቀፍ ደረጃ ስራ ላይ ውሎአል፡፡ ነገር ግን የስራ ሂደቱን በሚመለከት ወጥነት የሚጎድለው አካሄድ ስለአለ አሁን የሚደረገው ጥረት ይህንን ለማስተካከል ነው፡፡ በአብዛኛው ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶች ስለሆኑ አንዲት ሴት ይህ ችግር ሲገጥማት ወደህክምና መስጫ ተቋም ወይንም ወደ ህግ ተቋም እንዲሁም ወደስነልቡና አገልግሎት ልትሄድ ትችላለች፡፡ ይህም አንዲት ጥቃት የደረሰባት ሴት በመጀመሪያ ልታገኛቸው የምትፈልጋቸው ተቋማት እንደሆኑ እርግጥ ነው። ነገር ግን መንገዱን ከጀመሩት በሁዋላ የሚገጥማቸው ችግር ቀላል የማይባል ነው፡፡ ...ለምሳሌ ወደ ጤና ተቋም ብትሄድ በመጀመሪያ ከፖሊስ ወረቀት አምጪ ልትባል ትችላለች። ወደህግ ቦታ ስትቀርብ ደግሞ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ የህክምና ሁኔታዎች ቸል ሊባሉ የሚችሉበት አጋጣሚ ይኖራል። ስለዚህም የስራ ሂደቱ ወጥ ቢሆን እንዲሁም የሚሰሩት ስራዎች የህክምናው ለህግ ፣ የህጉ ለሕክምናው ግልጽ ቢሆኑ እንዲሁም የማህበራዊእና የስነልቡና ስራ የሚሰሩት ባለሙያ ዎች አሰራራቸው ግልጽ ቢሆን የሚሰጠው አገልግሎት የተሳካ ይሆናል፡፡ አገልግሎቱም በሁለት መልክ መፍትሔ የሚሰጥ ይሆናል የሚል እምነት ይኖራል፡፡

1. ጥቃትን መከላከል የሚያስችል ፣2. ጥቃት ከደረሰም አስፈላጊውን እርዳት ሁሉ...

ሕክምና...ሕግ...የማህበራዊና ስነልቡና አገልግሎት ድጋፍ መስጠት የሚቻልበት የስራ ሂደት ይፈጠራል .....ብለዋል፡፡

በረቂቅ ዶክመንቱ ላይ እንደሚነበበው...ጾታን መሰረት

“...በአንድ ማዕከል...ሁሉን አገልግሎት...”

ያደረገ ጥቃት ሲባል ወንድንና ሴትን ሳይለይ በሁለቱም ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የሚመለከት ቢሆንም በተለምዶ የሚታየው ግን በተለይ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በዚህ ዘርፍ ተጎጂ ሲሆኑ ነው፡፡ ለዚህም እንደ አንድ ምክንያት የሚጠቀሰው በወንዶችና ሴቶች መካከል ያለው ኃይል ወይንም አቅም ተመጣጣኝ አለመሆኑ ነው፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አገላለጽ መሰረት በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት ጾታን መሰረት ያደረገ እና በአካል እንዲሁም ስነአእምሮ ላይ ጉዳት ከማድረሱም በተጨማሪ ተያይዞ ለሚመጣ የስነልቡና ጉዳት የሚዳርግ ነው፡፡

በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት አለምአቀፋዊ ሲሆን መሰረቱ እሩቅ የሆነ እንዲሁም ዘዴ የተሞላበት የኃይል አለመጣጣም የሚታይበት ከመሆኑም ባሻገር በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለውን የአካል ተፈጥሮአዊ ልዩነት በግልጽ የሚታይበት ነው። በዚህም ምክንያት ጀንደር በሚለው የማህበራዊ ስርአት አወቃቀር ለሴቶች እና ለወንዶች ሲሰጥ የኖረውን ደረጃ እና የአኑዋኑዋር ዘይቤ ምን ያህል ሴቶች ላይ ጫና ያደርስ እንደነበር መገለጫው ነው፡፡ ለዚህ ምስክሩም ብዙውን ጊዜ ወንዶች በሴቶች ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት በህብረተሰቡ ዘንድ እንደ ጥፋት ሳይቆጠሩ እንዲያውም የሚወሰደው የህግ እርምጃ አነጋጋሪ የሚሆንበት አጋጣሚ በብዙ ሀገሮች የሚስተዋል በመሆኑ ነው፡፡

በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች የት እና እንዴት ወይንም በማን ተብሎ ሊከፋፈል የማይችል በአጠቃላይም የትም ቦታ ፣በማንኛውም ሰው ተብሎ ሊገለጽ እንደሚችል ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡

በሴቶች ላይ የሚፈጸም ወሲባዊ ጥቃት በቤት ውስጥ፣ በመኖሪያ አካባቢ፣በትምህርት ቤት ፣በስራ ቦታ ...ወዘተ ሊደርስ እንደሚችል የተለያዩ ማስረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በሴቶች ላይ የሚደርሱ ወሲባዊ ጥቃቶች በቤተሰብ፣ በጉዋደኛ፣ በስራ ባልደረባ፣ በማያውቁት ሰው ...ወዘተ ሊፈጸሙ የሚችሉ ጉዳቶች ናቸው፡፡

በጾታ ጥቃት ምክንያት ጉዳት መድረስ ማለት የሰብአዊ መብትን እንደመጋፋት የሚቆጠር ነው፡፡ ለዚህም እማኝ የሚሆኑት የተለያዩ አለምአቀፋዊ መድረኮች ናቸው፡፡ ለምሳሌም...

(CEDAW) 1979, World conference on human rights ,Viena,1993, International conference on population and Development (ICPD),Cairo,1994, UN fourth conference of women ,Beijing ,1995,Declatation of the General Assembly of the united nations on the elimination of Violence against Women,,. Beijing platform of Action, Millennium Development goals(MDGs)…. ወዘተ

ከላይ ለምሳሌነት የተጠቀሱት አለምአቀፍ ስብሰባዎችና ሌሎችም መድረኮች በተስማሙበት መሰረትም በጾታ ጥቃት ያደረሰ ሰው አስፈላጊውን የህግ ቅጣት እንዲያገኝ ሐገሮች የተስማሙበት ሲሆን ለተጎጂዎችም የአካል ጤንነት እንዲሁም የህሊና ነጻነት የሚያስገኝ ነው፡፡

በወሲባዊ ጥቃት ምክንያት የሚደርሰው የጤና ችግር የህብረተሰብ የጤና ችግር ተደርጎ የሚወሰድበት መንገድም አለ። አንዲት ሴት በደረሰባት ወሲባዊ ጥቃት ምክንያት ከሚደር ሱት የጤና እውክታዎች መካከል ...የአካል ጉዳት...ከባድ የእራስ ሕመም...በቋሚነት ሊገጥም የሚችል የጀርባ ሕመም... የስነልቡና መቃወስ ...እንደ ድብርት ...ፍርሀት ...እንቅልፍ ማጣት ...መርሳት... በራስ የመተማመን ብቃትን ማጣት የመሳሰሉ ችግሮች ሊገጥሙዋት ይችላሉ፡፡ በዚህም ምክን ያት አብዛኛውን ጊዜ በእራሳቸው ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚሞክሩ ሴቶች በርካታ ናቸው፡፡ የእና ቶችን ሞት ከሚያባብሱ መካከል የሚመደብ ሲሆን ለኤችአይቪ ኤድስ ተጋላጭ የሚሆኑትም ቀላል የሚባሉ ኤደሉም፡፡

ጾታን መሰረት ያደረገ ወሲባዊ ጥቃት የኢኮኖሚም ጉዳይ ነው፡፡ ለዚህ ተጋላጭ የሆኑ ግለሰቦች በሚደርስባቸው የጤና መጉዋደል ምክንያት የእራሳቸው እንዲሁም የቤተሰባቸው ገቢ ከመቃወሱ በተጨማሪ ለአገልግሎቱ የሚውለው ወጪ ብዙ ነው፡፡ አንድ ጥናት እንደሚያ መለክተው በባንግላዴሽ በ2010/ በአጠቃላይ የቤት ውስጥ ጥቃት በገንዘብ ሲሰላ 1.8/ቢሊዮን ዶላር ያህል ነበር፡፡ በ1996 እ.ኤ.አ በቺሌ በተደረገው ጥናት ሴቶች በሚደርስባቸው ወሲባዊ ጥቃት ምክንያት ሊያገኙት የሚገባቸውን ወደ 1.56/ ቢሊዮን ዶላር አጥተዋል፡፡ በዚሁ

መልክ የተለያዩ ሐገሮችን እውነታ ጥናቶች የሚያሳዩ ቢሆንም ወደሀገራችን መለስ ስንል ግን ዝርዝር በሆነ መልክ መረጃውን ማግኘት የሚያስችል ጥናት አልተደረገም፡፡ ቢሆንም ግን ከተለያዩ መረጃዎች መረዳት እንደሚቻለው በገጠርም ይሁን በከተሞች ችግሩ በሰፋ መልኩ የሚስተዋል መሆኑን ነው። በወሲባዊ ጥቃት ብቻም ሳይሆን በአጠቃላይ በቤት ውስጥ ጥቃት ምን ያህል ሴቶች ተጎጂ ሆነዋል የሚለውን ለመለካት ባይቻልም እንኩዋን በ2011 /በአገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው..ሃመ እንደተመለከተው ብዙ ሴቶች መብታቸውን እንደማያውቁና ወንዶችም ሴቶ ችን መጉዳት እንደጥፋት የማይቆጥሩት መሆኑን ነው፡፡ ለምሳሌም በዳሰሳ ጥናቱ ከተካተቱት ተሳታፊ ሴቶች 68 ኀ ወንዶች ቢመቷቸው ምንም ነውር እንደሌለበት የገለጹ ሲሆን 45 ኀ የሚሆኑት ወንዶች ደግሞ ሴቶች በወንድ መመታታቸው አግባብነት ያለው አድርገው እንደሚቀበሉት ተናግረዋል፡፡

በሴቶች ላይ የሚደርስ ጾታዊ ጥቃት ከልማት ጋር የሚያያዝ ጉዳይም ነው፡፡ የምእተ አመቱን የልማት ግብ ለማሳካት የሚያስችሉ ነጥቦችን መከወን በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመቀነስ እንደሚረዳ እሙን ነው፡፡ አገራት በዚህ ዘርፍ በጥንካሬ መስራት እንደሚጠ በቅባቸው የአለም የጤና ድርጅት አስምሮበታል ..ሳሳቈስቋቋሽቃሸ ባሽቄቁስቃሰስ ሮሸሮሽቃቋ.. ብቄቂስቃ ሮቃሳ ሮሰሻሽስባሽቃሸ ..ሻስ ቂሽቁቁስቃቃሽበቂ ሳስባስቁቄቅቂስቃ.. ሀቄሮቁቋ ፡ሠሃሑ 2005...

የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት የጾታን ጥቃት በሚመለከት በማህበሩ ሲሰራ የቆየውን እና ወደፊት ምን ለማድረግ እንደሚገባ ሲገልጹ የሚከተለውን ብለዋል፡፡

.....ቀደም ባለው ጊዜ ይህንን ጥቃት በሚመለከት ደረጃውን ያልጠበቀ ሕክምና እና ደረጃውን ያልጠበቀ የህክምና ማስረጃ የሚሰጥበት ሁኔታ የነበረ ሲሆን እ.ኤ.አ ከ2001 -2002/ ድረስ ባለው ጊዜ የተወሰኑ ሞዴል ክሊኒኮችን በመስራት እና ወሲባዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች በአንድ ተቋም ውስጥ የተሟላ አገልግሎት የሚያገኙበትን እና በተቻለ መጠንም በቂ የሆነ ሕጋዊ ማስረጃ የሚያገኙበትን ሁኔታ ሲያመቻች ቆይቶአል። ከዚያም በሁዋላ ይህንን በአዲስ አበባ ብቻ ሲሰጥ የቆየውን አገልግሎት ወደሌሎች መስተዳድሮችም በ ማስፋፋት በአዳማና በአዋሳ ሞዴል ክሊኒኮቹን በማመቻቸት ስራዎች እየተሰሩ ቆይተ ዋል፡፡ለወደፊቱም ያለው እቅድ አሁን ያሉትን ሞዴል ክሊኒኮች ከሁለት ወደሰባት ከፍ ለማድረግ ነው፡፡ ለዚህም ማእከላቱ የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ናቸው፡፡ የዚህም ምክንያቱ በዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት ከተቻለ ከዚያ የሚወጡ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የቅድመ ምረቃ እና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ወደስራ በሚሰማሩበት ወቅት አገልግሎቱን በተቻለ ፍጥነትና ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ሊያስፋፉ ይችላሉ የሚል እምነት ስለአለ ነው..... ብለዋል ፡፡

ይቀጥላል

ሰዎች ከዚህ አኩርፈው የሄዱ ናቸው። ያኔ በተለያዩ ምክንያቶች ሄደዋል፡፡ አሁን ግን ከስህተቶቻችን ተምረን አብረን ጠንክረንና ተባብረን እንሠራለን። አንድ ጊዜ ተጣልተናልና መልሰን አብረን መስራት አንችልም የሚል እምነት አይኖረንም፡፡ እየተጋጨንም ዞረን ደግሞ ስህተታችንን አምነንና ተማምነን መስራት ምንም ማለት አይደለም፡፡ ለወደፊትም አለመግባባቶች ቢኖሩ በዚህ መልኩ እየተማመኑና እየተወያዩ መሄዱ ይቀጥላል የሚል እምነት ነው ያለኝ እና ከዚህ አንፃር ቢታይ መልካም ነው፡፡

በየጊዜው ፓርቲዎች መድረክ፣ ትብብር፣ ህብረት፣ ቅንጅት እያሉ በጋራ እየተሰባሰቡ ሲወድቁ ሲነሱ የኢትዮጵያ ህዝብ ታዝቧል፡፡ መኢአድም የዚህ ሂደት አንዱ አካል ነው፡፡ ለወደፊትስ ፓርቲያችሁ በዚህ ሁኔታ እስከየት ድረስ ነው ሊጓዝ የሚችለው?

እንግዲህ ባለፉት 22 አመታት የፓርቲዎች ስብስብ አንድ ሲሆን ሲለው ደግሞ ሲፈርስ ኖሯል፡፡ እንደ እኔ አመለካከት ይሄ የሆነው ሁሉም ነገር በግለሰቦች ፍላጐት ላይ የተመሠረተ ስለነበረ ነው፡፡ ይሄ ኢትዮጵያንም ሆነ ዜጐቿን የጐዳ ትልቁ በደል ነው፡፡ አንዳንዱ የፓርቲ አመራር ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ቆሜያለሁ ካለ፣ ራሱን ለዚያ አላማ መሸጥ አለበት፡፡ ግቡ ወይም የሩቅ አላማው ኢትዮጵያውያንን ነፃ ማውጣት ወይም በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ሠፍኖ ማየት መሆን አለበት። ግን በዚህች ሀገር እስካሁን ሲደረግ የቆየው እኔ ሊቀመንበር ካልሆንኩ፣ የኔ ፓርቲ የበላይ ካልሆነ ሲባል ነው፡፡ ከዚህ አንፃር አሁንም ቢሆን መኢአድ ሊያደርግ የሚችለው የጋራ ትግል አስፈላጊነትን ያምናል፤ ስለዚህ እስከቻለው ድረስ ከአላማው ጋር ከሚስማሙት ጋር አብሮ ይሠራል፡፡ ይህ መሆኑ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ አንደኛ ድምጽ አይሻሙም፤ በሁለተኛ ደረጃ በህዝቡ ላይ በራስ የመተማመን ስሜትን መፍጠር ይቻላል። አለኝታ የሚሆን ፓርቲ አለኝ ብሎ እንዲያምን ይገደዳል፡፡ ደካማና የተነጣጠለ ፓርቲ ሆነው ካያቸው ግን ህዝቡ እምነት ሊጥልባቸው ይቸገራል እና መኢአድ አሁንም| ተመሳሳይ ፕሮግራም ካላቸው ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት ቁርጠኛ ነው፤ ግን ይሄ የሚሆነው በቅንነት፣ በእውነተኛነት ኢትዮጵያን እያሰበ ከሚመጣ አካል ጋር ነው፡፡ ሸር ይዞ ከሚመጣ ጋር ግን ለመስራት ይቸገራል፡፡

መኢአድ ራሱ አንዴ ሲቀናጅ፣ ሲዋሃድ፣ ሲተባበር

ሲያሻው ደግሞ ቅንጅቱና ውህደቱን ሲያፈርስ የኖረ ፓርቲ ነው፤ አሁንም በዚህ አዙሪት ውስጥ መሆኑን ያዩ ወገኖች ፓርቲው ግራ የተጋባ ነው ሲሉም ይደመጣል…

ፓርቲያችን ግራ የተጋባ አይደለም፡፡ ግልጽ አላማ ግልጽ የሆነ ፕሮግራምና ደንብ ያለው ፓርቲ ነው። ፓርቲው ህብረ ብሔራዊ፣ ብዙ አባላትና ደጋፊዎች በውጭም በሀገር ውስጥም ያለው በመልካም አመራር የሚመራ ፓርቲ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን አምነው ከሚመጡ ፓርቲዎች ጋር ለመስራት መኢአድ ዝግጁ ነው፤ ነገር ግን የሚመጡትን ፓርቲዎች ለመምራት የሚሞክር ሳይሆን አብሮ የሚሰራ ነው፡፡

በየክልሉ ያሉ ቢሮዎቻችሁ እየተዘጉባችሁ እንደሆነ ስትገልፁ ከርማችኋል፡፡ ከነዚህ ክልላዊ እና ጐሣዊ ፓርቲዎች ጋር ለመቀናጀት የወሰናችሁበት ሚስጥር ምናልባት ዳግም ለመጠናከር አስባችሁ ይሆን?

ይሄም ዝም ብሎ ግምታዊ አስተያየት ነው እንጂ ፓርቲው አሁን በየትም ቦታ ብትሄድ ቢሮ አለው ወይም መዋቅር አለው፡፡ እንደተባለው በተለያዩ ጫናዎች ምክንያት በተለይ የወረዳዎቹ ቢሮዎች ተዘግተው ነበር፡፡ ይሄ ደግሞ መኢአድን ብቻ ሣይሆን ሌሎችንም ጐድቷቸዋል፡፡ ስለዚህ አሁን መኢአድ በሃገሪቱ ካሉ ፓርቲዎች ጠንካራው ነው ብል ስህተት አይደለም። በሀገር ውስጥም በውጭም ያሉ ደጋፊዎቻችን ለፓርቲው መጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው። እዚህ ያለው አመራርም የተዘጉ ቢሮዎችን ለማስከፈት ጥረት እያደረገ ነው። እስከ 2007 ድረስ ሙሉ ለሙሉ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ቢሮ ይኖረናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ይህን ካልኹ፣ አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ፤ “አንድ ላይ ካልተባበራችሁ፣ ካልሠራችሁ ለትግሉ አስቸጋሪ ነው” በሚል ህብረት እንድንፈጥር እየጠየቀ ነው፡፡ ስለዚህ መኢአድ፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወደ አንድ መጥቶ፣ ጠንካራ ፖለቲካ ፓርቲ ተፈጥሮ፣ መወዳደር አለባቸው እንጂ መቶ ደካማ ፓርቲዎች ዝም ብለው መጮህ የለባቸውም የሚል እምነት አለው፡፡ ከዚህ አንፃር ነው እንጂ እኛ ድክመት ኖሮብን በእነሱ ለመሸፈን አይደለም፡፡ እነሱ ብዙም ይዘው የሚመጡት ነገር የለም፡፡

መኢአድ ከሌላው የተሻለ ሰፊ ህዝባዊ መሠረት ካለውና አደረጃጀቱም ጠንካራ ከሆነ በምርጫ ወቅት ለምን ተፎካካሪ ሊሆን አልቻለም?

ፓርቲው እየታገለ ያለው እሱ ብቻ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን

ባለቤት እንዲሆን ነው፡፡ እንደተባለው ፓርቲው ጠንካራ መሠረት ያለው ቢሆንም ከገዢው ፓርቲ የሚደርስበት ጫናም በዚያው ልክ የሰፋ ነው። አባላቱ ንብረታቸውን ይነጠቃሉ፣ ይታሰራሉ፣ ይደበደባሉ፤ ሰዎች የፓርቲው አባል ስለሆኑ ብቻ የተለየ ጥቃት ይደርስባቸዋል፡፡ እንደነዚህ አይነት ተጽእኖዎች ደግሞ ሊያራምዱ አይችሉም፡፡ በሌላ መንገድ ገዥው ፓርቲ የራሱን የደህንነት አባላት እና ካድሬዎች በየፓርቲዎቹ ውስጥ ሰግስጐ ያስገባል፡፡ በዚህም በፓርቲ ውስጥ መናወጥ ይፈጥርና የፓርቲውን አመራር ያዳክማል፡፡ ይሄ በማዕከል ብቻ ሳይሆን በዞንና በወረዳም ጭምር የሚደረግ ነው፡፡ እንደነዚህ አይነት ተጽእኖዎች ናቸው ከፍተኛ ችግር የፈጠሩት፡፡ ህዝቡም መወጣት ያለበትን ሃላፊነት መወጣት አለበት፡፡ እውነተኛውንና ውሸታሙን መለየት መቻል አለበት፤ ዳር ሆኖ መመልከቱ አይጠቅምም፡፡

ተቃዋሚዎች ለመዳከማቸው ገዢውን ፓርቲ ተጠያቂ ያደርጋሉ፤ ገዥው ፓርቲ ደግሞ ጠንካራ ተቃዋሚዎች ባለመኖራቸው ሸክሜ በዝቷል እያለ ነው…

እዚህ ላይ ሁለት ነገር ነው የሚታየኝ፡፡ አንደኛ አቶ መለስም በህይወት በነበሩ ጊዜ የተናገሩት ነው፡፡ ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ ቢመጣ ሩቅ መንገድ ሄደን እንቀበለዋለን ተብሎ ነበር፡፡ ነገር ግን ቅንጅት ተፈጥሮ ጠንካራ ፓርቲ ሲመጣ በጥይት ግንባሩን ነው ያሉት። ይሄ አባባል እንግዲህ ፖለቲከኞቻችን ለይስሙላ የሚጠቀሙት መሆኑን አረጋጋጭ ነው፡፡ “እንዳይበላ ግፋው እንዳያማህ ጥራው” አይነት ነገር ነው፡፡ አሁንም አቶ ኃይለማርያም የተናገሩትን ሰምቸዋለሁ “ሌሎቹ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሃላፊነትን መሸከም ስላልቻሉ የሃገሪቱ ሸክም ሁሉ ኢህአዴግ ላይ ወድቋል። ተበራቱ” የሚል ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ኢህአዴግ ምንም አይነት ሃላፊነት ሊሸከም የሚችል ፓርቲ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ለምን? የኢትዮጵያን ህዝብ ሰብአዊ መብት እየጣሰ ያለ ፓርቲ፣ ሃላፊነት እሸከማለሁ ቢል አይታመንም፡፡

በሁለተኛ ደረጃ የኢትዮጵያን ህዝብ አዎንታ የተቀበለ ፓርቲ አይደለም፡፡ በሃይል፣ በመሳሪያ ስልጣን የያዘ ፓርቲ ነው፡፡ እኔ የማዝነው አቶ ኃይለ ማርያም በጣም ክርስቲያን ናቸው ይባላል፤ ግን በእዚህ አይነት ጉዳይ ላይ የሚናገሩት ነገር ከእምነታቸው ይቃረንብኛል፡፡ እነሱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን

ያቁሙና ከዚያ በኋላ ጠንካራ ተቃዋሚ ካጡ ይሄን ነገር ሊናገሩ ይችላሉ፡፡

መኢአድን ጨምሮ ብዙዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በግለሰብ አውራዎች ላይ የተመሠረቱ ሆነው ይታያሉ። ከፕሮግራምና አላማቸው ይልቅ ፕሬዚዳንቶቻቸው ጐልተው ይወጣሉ፡፡ የሚሆነው ለምን ይመስልዎታል?

በእርግጥ ይሄ ነገር መሆን የሌለበት ነው፡፡ አመራር ብቻ አይደለም፤ አባላትም በሁሉም ነገር ላይ ተሣትፎአቸው መጠየቅ አለበት፡፡ የእነሱ ተሣትፎ ከሌለበት የኔ ነው የሚሉት ነገር ሊኖር አይችልም። በመጀመሪያ ደረጃ አባላቱ የኔ ነው ሊሉ የሚችሉት ፓርቲው አሣታፊ ሲሆን ነው፤ ስለዚህ እንደነዚህ አይነት ነገሮች በቀጣይ ሊታረሙ የሚገቡ ናቸው፡፡ አመራሩና አባላቱ የውስጥ እኩል ተሣትፎ ሊኖራቸው ይገባል። አንድ ሰው አንድ ፓርቲ ሊሆን አይገባም። የእከሌ ፓርቲ ሊባል አይገባም፡፡ መኢአድ ያንን ለማድረግ እየሰራ ነው፡፡ በአደረጃጀቱም ትልቁን ስልጣን የሚሰጠው ከታች ላለው ነው፡፡ የፓርቲ አመራሮች ራሳቸውን ለአባላቱ ተገዢ ካላደረጉ፣ ነገ ለሚመሩት የኢትዮጵያ ህዝብ ተገዢ ሊሆኑ አይችሉም።

የ2007 ምርጫ እየተቃረበ ነው፡፡ መኢአድ ከምርጫው ምንድን ነው የሚጠብቀው?

እኛ ስራችንን እየሰራን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አዎንታውን ከሰጠን ስልጣን ለመያዝ ከመጓዝ የሚያግደን ነገር የለም፣ ነገር ግን የመጫወቻ ሜዳው በትክክለኛው መንገድ ካልሄደ የኢትዮጵያን ህዝብ ልናማው አንችልም፡፡

እኛንም ህዝቡ ሊያማን አይገባም፤ ማማት ያለበት ገዢውን ፓርቲ ነው፡፡ በጥይት በዱላ እየደበደበ አባላቶች እንዳይሳተፉ የሚያደርግ ከሆነ፣ በምርጫ ወቅት ካርድ እየሰረዘ አሽነፍኩ የሚል ከሆነ፣ በምርጫ ወቅት ታዛቢዎቻችንን እየደበደበ፣ በመድሃኒት እያሠከረ እያስተኛ የሚዘርፍ ከሆነ መታማት ያለበት ገዢው ፓርቲ ነው፡፡ መኢአድ በ2007፤ መቶ በመቶ አሸንፋለሁ ብሎ እየተራመደ ነው ያለው፤ ይሄን ደግሞ እርግጠኞች ነን። ለምን ካልን አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ ፈልጓል፤ ግን ለውጡን የሚሸከምለት ፓርቲ ይፈልጋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬ በብዙ መልኩ መብቱ ተጥሷል። የሃገሪቱን የኢኮኖሚ ትሩፋት መጠቀም ተስኖታል፡፡ የቀን ሠራተኛው፣ ብሎኬት ሠራተኛው፣ ዶሮ አርቢው ሣይቀር ከውጭ እየመጣ ነው፡፡ የሀገሪቱ ዜጋ መጠቀም አልቻለም፡፡

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 27

ናይጄርያ 2፡1 ኢትዮጵያ - ክፍል 2

ስፖርት አድማስ

ግሩም ሠይፉ

ብራዚል የምታዘጋጀው 20ኛው የዓለም ዋንጫ የቀረው 7 ወራት አካባቢ ነው፡፡ እስከዛሬ ማለፋቸውን ያረጋገጡት አዘጋጇን ብራዚል ጨምሮ 21 ብሔራዊ ቡድኖች ናቸው፡፡ አፍሪካን በመወከል ወደ ብራዚል የሚጓዙት 5 ብሔራዊ ቡድኖች የሚታወቁት ደግሞ ዛሬ ፤ነገ እና ማክሰኞ በሚደረጉ 5 የመልስ ጨዋታዎች ናቸው፡፡ አፍሪካን የሚወክለው የመጀመርያ ብሄራዊ ቡድን የሚታወቀው ነገ 12 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ላይ ዋልያዎቹ ከናይጀሪያ አቻቸው ጋር በካላባር በሚገናኙበት ወሳኝ ፍልሚያ ነው፡፡ ሌላው የዛሬ ጨዋታ ሴኔጋል በሜዳዋ አይቬሪኮስትን የምታስተናግድበት ይሆናል፡፡ ነገ ካሜሮን ከቱኒዚያ ሲጫወቱ ማክሰኞ እለት ግብፅ ከጋና እንዲሁም አልጄርያ ከቡርኪናፋሶ የመጨረሻዎቹ ሁለት የመልስ ጨዋታዎች ያደርጋሉ፡፡

ረቡዕ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ዋና አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ መግለጫ በሰጡበት ወቅት‹‹ የዓለም ዋንጫ ጉዳይ ከዛሬ በኋላ ያበቃለታል፡፡ በመደጋጋፍ ተጫውተን ናይጄርያን በማሸነፍ ታሪክ ለመስራት ተዘጋጅተናል፡፡ ለወደፊቱ እንደ እርሳስ የሾለ ብሄራዊ ቡድን እንዲኖረን ከስር መሰረቱ መስራት ያስፈልገናል፡፡›› በማለት ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል አዲሱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በሳምንቱ አጋማሽ ላይ አዲስ አበባ ስታዲየም በመገኘት ከናይጀሪያ ጋር ለሚጠበቀው ወሳኝ ጨዋታ በልምምድ ላይ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በማበረታት ያላቸውን አድናቆት ነገረዋቸዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ‹‹ ከናይጄሪያ ጋር ካላባር ላይ የምታደርጉትን የ90 ደቂቃ ወሳኝ ፍልሚያ እመለከታለሁ እንደምታሸንፉ እምነቴ ነው ፤ጎል ስታስቆጥሩ እያጨበጨብኩ ደስታዩን እገልፃለሁ …በድል እንንደምትመለሱ እምነቴ ነው›› ብለዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲን ባሻህ ደግሞ ‹‹ ስትመለሱ የጀግና አቀባበል በማዘጋጀት ባለፉት አንድ አመታት ላደረጋችሁት አስተዋፅኦ ምላሽ የሚሆን ማበረታቻ እንሰጣለን ›› ሲሉ ለእያንዳንዳቸው የመኪና ሽልማት እንደሚሰጥም በአቶ አብነት ገብረመስቀል ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ በቀረቡ የቦነስ ክፍያዎች ለግብፅ ተጨዋቾች በነፍስ ወከፍ 25ሺ ዶላር፤ ለአይቬሪኮስት 18 ሺ ዶላር፤ ለጋና 15ሺ ዶላር፤ ለናይጄርያ ደግሞ 5ሺ ዶላር እንደሚበረከትላቸው ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

ቋሚ አሰላለፉ እና የግብ እድሉየኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 30 ተጫዋቾች ወደ

ካላባር ተጉዘዋል፡፡ ሁሉንም ተጨዋቾች ለመውሰድ የተወሰነው ከመልሱ ጨዋታ ለሴካፋ ውድድር እና ለቻን በቂ ተመክሮ እና ልምድ እንዲያገኙ ተብሎ ነው፡፡ በውጭ አገር የነበሩትን ዩሱፍ ሳላህ እና ሆነ ፉአድ ኢብራሂምን አልጠራሁዋቸዉም ያሉት አሰልጣኝ ሰዉነት ፤ ከቡድኑ ጋር አብረው ልምምድ ለመስራት በጠየቁት መሰረት እድሉን እንደሰጧቸው በማስረዳት እነ ጌታነህና ሳላሀዲንን የሚያስቀምጥ አቋም እንደሌላቸዉም ገልፀዋል፡፡ አሰልጣኝ ሰውነት እንዳረጋገጡት አዲስ አበባ ላይ በተደረገው የመጀመርያ ጨዋታ ላይ በጉዳት ያልተሰለፈው ወሳኙ የአጥቂ መስመር ተጨዋች ጌታነህ ሙሉ ለሙሉ ተሽሎታል፤ ስለዚህም በዛሬው ጨዋታ መሰለፉ የማይቀር ይሆናል፡፡ በአጠቃላይ ዝግጅቱ ብሄራዊ ቡድኑ ከጥቅምት 11 ቀን ጀምሮ ሰርቷል። በሳምንቱ አጋማሽ ላይ በውጪ የሚጫወቱትን ሳላዲን ሰዒድ፤አዲስ ህንፃ፤ጌታነህ ከበደ፤ፉአድ ኢብራሂም ፤የሱፍ ሳላህን ጨምሮ ሁሉም ተጨዋቾች ተሟልተው እስከ ረቡዕ በአዲስ አበባ ልምምዳቸውን ሰርተዋል፡፡ በሞቃታማው ካላባር

ለሚደረግ ጨዋታ በራሳችን አየር ሰርተን አንድ ቀን ሲቀረው ብንሄድ ይሻላል በሚል ተመካክረው ነው፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ ካላባር ከገባ በኋላ ከፍተኛ ባረፈበት የቻናል ቪው ሆቴል ጥበቃ እየተደረገለት ልምምዱን በ5 ደቂቃ ርቀት በሚገኝ ሜዳ ላይ ላለፉት ሁለት ቀናት ሰርቷል፡፡

ለዛሬው ወሳኝ የመልስ ጨዋታ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የሚከተሉትን አጨዋወት በተመለከተ ሲናገሩ አጥቅቶ መጫወትን እንደሚያተኩሩበት ቢያመለክቱም ግብ እንዳይገባብን ከፍተኛ ጥንቃቄ እናደርጋለንም ብለዋል፡፡ ዋና አሰልጣኝ ሰውነት በዋልያዎቹ አሰላለፍ 4-4-2 ወይንም 4-3-3 ፎርሜሽን ሊጠቀሙ ይችላሉ እየተባለ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ የማጣርያ ጉዞ ከዋልያዎቹ አባላት በተለይ አንዳንዶቹ ከፍተኛ ሚና ነበራቸው፡፡ በሁሉም ዘጠኝ ጨዋታዎች በመሰለፍ 799 ደቂቃዎች የተጫወተው አበባው ቡጣቆ በከፍተኛው ግልጋሎቱ የሚጠቀስ ተጨዋች ነው፡፡ አምበሉ ደጉ ደበበ በ7 ጨዋታዎች ለ630 ደቂቃዎች፤ ስዩም ተስፋዬ በ8 ጨዋታዎች ለ655 ደቂቃዎች፤ አይናለም ኃይሉ በ6 ጨዋታዎች 540 ደቂቃዎች እንዲሁም አዳነ ግርማ በ7 ጨዋታዎች 417 ደቂቃዎች በመጫወት አስተዋፅኦ ነበራቸው። በዛሬው ጨዋታም እነዚህ ተጨዋቾች ወሳኝ አገልግሎት መስጠታቸው ይጠበቃል፡፡

የዋልያዎቹ ግምታዊ አሰላለፍግብ ጠባቂ ሲሳይ ባንጫተከላካዮች - አበባው ቡጣቆ፤ ደጉ ደበበ፤ አሉላ ግርማ፤ አይናለም ሃይሉአማካዮች - አስራት መገርሳ፤ ሽመልስ በቀለ፤ ምንያህል ተሾመ፤ አዳነ ግርማአጥቂዎች - ሳላዲን ሰኢድ፤ ጌታነህ ከበደ

ዛሬ በካላባር በሚደረገው ጨዋታ ትልቁ እና አስፈላጊው ሚና ከዋልያዎቹ የአጥቂ መስመር ተሰላፊዎችም ይጠበቃል፡፡ በዓለም ዋንጫው 9 የማጣሪያ ግጥሚያዎች ኢትዮጵያ ያስመዘገበቻቸውን 14 ጐሎችን አምስት ተጨዋቾች አስመዝግበዋል፡፡ በ7 ጨዋታዎች 617 ደቂቃዎችን በመጫወት 4 ጐል ያስቆጠረው ሳላሃዲን ሰኢድ ሲሆን ጌታነህ ከበደም በተሰለፋቸው 5 ጨዋታዎች 317 ደቂቃዎችን በመጫወት እኩል 4 ጐሎች አስመዝግቧል፡፡

በ7 ጨዋታዎች 508 ደቂቃዎችን የተጫወተው ሽመልስ በቀለ ሁለት ጐሎችን አስቆጥሯል፡፡ በ4 ጨዋታዎች 192 ደቂቃ የተሰለፈውና ኡመድ ኡክሪ 581 ደቂቃዎችን የተጫወተው ምን ያህል ተሾመ በ5 ጨዋታ 204 ደቂቃዎች ያገለገለው ቀሪዎቹን ሦስት ጐሎች በነፍስ ወከፍ አስቆጥረዋል፡፡

ውጤቱ ምን ሊሆን ይችላል?የናይጄርያን ብሄራዊ ቡድን በካላባር በሚገኘው

የዩኤስ ኡስዋኔ ስታድዬም በቅርብ ጊዜ ተሸንፎ አያውቅም፡፡ ለማሸነፍ ከጫፍ ደርሶ አንድ እኩል አቻ የወጣው የሃራምቤ ኮከቦች የተባለው የኬንያ ብሄራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫው የምድብ ማጣርያ ነበር። በ1994፤ በ1998፤ በ2002 እና በ2010 እኤአ ላይ አራት ዓለም ዋንጫዎችን የተሳተፈችው ናይጄርያ ዛሬ ኢትዮጵያን ካሸነፈች አምስተኛው ተሳትፎዋን ስታረጋግጥ ኢትዮጵያ ደግሞ የመጀመርያ ታሪካዊ ስኬቷ ይሆናል፡፡

የቀድሞው የግብፅ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሃሰን ሺሃታ ለዓለም ዋንጫ የማለፍ እድል አላቸው ብለው በልበሙሉነት ግምት የሰጡት ለአይቬሪኮስት፤ ለአልጄርያ እና ለናይጄርያ ነው። ናይጄርያ ኢትዮጵያን ጥላ የምታልፈው በሁለቱ ቡድኖች ያለው ልምድ ከፍተኛ ልዩነት ስለሚፈጥር ነው ብለው ሃሰን ሺሃታ ተናግረዋል፡፡ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት ሮይ ሆጅሰን

ኢትዮጵያ እጆቿን ለዓለም ዋንጫ ዘርግታለች

በበኩላቸው 20ኛው የዓለም ዋንጫን የማሸነፍ እድል የሚኖረው ከአውሮፓ አገሮች ይልቅ ለአፍሪካ ተወካዮች ነው ብለው ተናግረዋል፡፡ የብራዚል አየር ንብረት የሚስማማው ለአፍሪካ ብሄራዊ ቡድኖች መሆኑን የጠቀሱት ሆጅሰን የአፍሪካ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች በአውሮፓ የክለብ እግር ኳስ ያላቸው ልምድንም እንደ ከፍተኛ አቅም ተጠቅመው ዓለም ዋንጫን ሊያሸንፉት ይችላሉ ብለዋል፡፡ነገ ዋልያዎቹ ከንስሮቹ ጋር በሚያደርጉት ትንቅንቅ ጨዋታው ስንት ለስንት ይጠናቀቃል? ቀድሞ ማን ጎል ያሰቆጥራል? ለዋልያዎቹ እነማን ያገባሉ? የሚሉት ጥያቄዎች በተለይ ባለፉት ሶስት እና አራት ቀናት በከፍተኛ ደረጃ መላው ኢትዮጵያዊን እያነጋገሩ ነበር፡፡ በዛሬው ጨዋታ ኢትዮጵያ 2ለ0 ወይም 3ለ2 ማሸነፍ ከቻለች በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ለዓለም ዋንጫ ማለፏን ታረጋግጣለች፡፡ በሜዳዋ የምትጫወተው ናይጀሪያ በጨዋታው አቻ ውጤትና በማንኛውም ውጤት ማሸነፍ፤ በ1 ጎል ልዩነት መሸነፍ እንዲሁም 0ለ0 ፣ 1ለ1 እና 3ለ3 አቻ መለያየት ይበቃታል፡፡

ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ ዛሬ ካላባር ላይ በሚያደርጉት የመልስ ጨዋታ ውጤቱ ምን ሊሆን ይችላል ? በሚል ጥያቄ ኢትዮፉትቦል በድረገፁ አንባቢዎቹን አሳትፎ ነበር፡፡ 331 አንባቢዎች ድምፅ በመስጠት ተሳትፈዋል፡፡ ኢትዮጵያታሸንፋለች ያሉት 67.07 በመቶ ሲሆኑ ናይጄሪያ እንደምታሸንፍ የገመቱት 29.31 በመቶ ናቸው። 3.63 በመቶ ደግሞ አቻ ውጤት ተንብየዋል። በሌላ በኩል ታዋቂው ጐል ስፖርት ድረገጽ አንባቢዎችን በማሳተፍ በሠራው የውጤት ትንበያ በቀረቡ 3 የውጤት ግምቶች ሙሉ ለሙሉ አሸናፊነቱ የተሰጠው ለናይጀሪያ ነው፡፡ 12.46 % 2ለ0፣ 10.38 % 3ለ1 እንዲሁም 18.69 % ያህሉ 3ለ0 በሆነ ውጤት ናይጀሪያ በሜዳዋ ኢትዮጵያ እንደምታሸንፍ ገምተዋል፡፡ ሶከርዌይ በሰራው ትንበያ ደግሞ ናይጄርያ 73.4 በመቶ እንዲሁም ኢትዮጵያ 23.8 በመቶ የማሸነፍ እድል ሲኖራቸው አቻ የሚወጡበት ግምት ደግሞ 8 በመቶ ነው፡፡ በሶከርዌይ ድረገፅ ናይጄርያ 0 ኢትዮጵያ 2 ብለው የገመቱ 24.9 በመቶ፤ ናይጄርያ 3 ኢትዮጵያ 0 ብለው የገመቱ 20.97 በመቶ ናይጄርያ 2 ኢትዮጵያ 0 ብለው የገመቱ 12.9 በመቶ ናቸው፡፡

አዲስ ህንፃ ያለውን ምርጥ የኳስ ችሎታ ሱፐር ስፖርት

ያደነቀለት ሌላው የዋልያዎቹ ወሳኝ ተጨዋች አዲስ ህንፃ ነው፡፡

“የአፍሪካ ሻምፒዮን መሆናቸውን ብናከብርም በምንም ሁኔታ ዝቅተኛ ግምት ሊሰጡን አይችሉም” ብሎ ለሱፐር ስፖርት የተናገረው አዲስ ህንፃ፣ “ስለ ዓለም ዋንጫ የምናልመው ሁልጊዜ ነው፡፡

በሜዳችን ባደረግነው የመጀመያ ጨዋታ ህልሞችን መና የቀረ መስሎ ነበር፡፡ ግን ፍጻሜው ገና አልለየለትም” ብሏል።

አስራት መገርሳ የሱፐር ሱፕርት ዘጋቢ አስራት መገርሳን ተወዳጁ

የዋልያ ተጨዋች ብሎታል፡፡ አዲስ አበባ ላይ በተደረገው የመጀመሪያው ጨዋታ ላይ የነበረው ምርጥ ብቃት የናይጀሪያ ምክትል አሰልጣኝ ዳንኤል አሞካቺን አሳስቦት ነበር የሚለው ዘገባው በወቅቱ ንስሮቹ በከፍተኛ ሞገስ የመሃል ሜዳውን በተቆጣጠረው አስራት በኩል መጫወታቸውን ትተው በክንፍ እንዲንቀሳቀሱ ሲጮሆባቸው ነበር ብሏል፡፡ ስቴፈን ኬሺም በናይጀሪያ ቋንቋ “ቾይ” ወይም ዋው ብሎ አስራት መገርሳን አደንቆታል።

አበባው ቡጣቆ የዋልያዎቹ ወሳኝ የግራ መስመር ተመላሽ ተጨዋች

የሆነውና በሁሉም የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ግጥሚያዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበረው አበባው ቡጣቆ በበኩሉ ለሱፐር ስፖርት በሰጠው አስተያየት “እግዚአብሔር ከኛ ጋር ነው” ብሏል፡፡ ፀሎት ያደረግነው በካላባር ለኩራት የሚያበቃን ገድል ለመፈፀም ነው” ያለው አበባው ‹‹ለናይጀሪያውያን የማይቻል የመሰለውን ነገር ችለን እናሳያቸዋለን›› ሲልም ተናግሯል፡፡ እንደ ሱፐር ስፖርት ገለፃ አበባው ቡጣቆ በቅርብ ጊዜ በቱርክ ክለቦች ዓላማ ውስጥ መግባቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ደጉ ደበበ የኢትዮጵያ ተከላካይ መስመር ምሰሶ ተብሎ በሱፐር

ስፖርት የተሞካሸው አምበሉ ደጉ ደበበ ነው፡፡ “በካላባር ግዙፍ ተራራ መውጣት አለብን፡፡ እንደማንኛውም የእግር ኳስ ተጨዋች ውጤቱ በ90 ደቂቃዎች ይወሰናል ብለን ተስፋ አድርገናል፡፡

ናይጀሪያውን ጥንካሬያቸው ፈጣን የመልሶ ማጥቃት አጨዋወታቸው ስለሆነ ይህን በትኩረት እንከላከላለን” በማለት ደጉ ደበበ ለሱፐር ስፖርት በሰጠው አስተያየት ተናግሯል፡፡

ሰውነት ቢሻው

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሕዳር 7 ቀን 2006 ዓ.ም ገፅ 28 ማ

ስታ

ወቂ