4
uôÅ^M Ö?“ Øun T>’>e‚` ¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö?“ ›=”e+ƒ¿ƒ www.ephi.gov.et ²?“ ኢሕጤኢ ¾ ካቲት 2008 pê 1 lØ` 5 በኢንስቲትዩቱ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በታላቅ ድምቀት ተከበረ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢ ንስቲትዩት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የተቋሙ ከፍተኛ አመራር አ ካላት እና 80 የኢንስቲትዩቱ ሴ . . .ወደ ገጽ 3 ዞሯል በኢሕጤኢ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቢሮ በየወሩ የሚዘጋጅ ት ሰራተኞች በተገኙበት የካቲት 29/2008 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተ ከብሮ ዋለ፡፡ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓለ ም አቀፍ ደረጃ “ Planet 50-50 by 2030,step it up for Gen- የእብድ ውሻ በሽታን መከላከልና መቆጣጠር ላይ የምክክር ስብሰባ ተካሄደ የእብድ ውሻ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በክልል እንዲሁም በሀ ገር አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ጥረቶች ን ከሕብረተሰብ እና ከእንስሳት ጤ ና መስኮች ጋር በማጣመር ተጠናክ ረው እንዲቀጥሉ በማሰብ ከየካቲት 8 - 11/2008 በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ጊቢ ለአራት ተከታታይ ቀናት የምክ ክር ስብሰባ ተካሄደ፡፡ እንደ ስብሰባው አዘጋጆች ገለጻ የም ክክር ስብሰባው ዋና ዋና ዓላማዎ ች የእብድ ውሻ በሽታን ለማጥፋት የStepwise Approach towards Rabies Elimination (SARE) መ ሣሪያን ከኢትዮጵያ አንፃር ያለው ን ሁኔታ መወያየትና የተግባር ል ምምድ መስራት፣ የውሻ ክትባት የRabiesEcon መሣሪያ ናሙናዎ ችን በመጠቀም መለማመድና መ ወያየት፣ Global Health Securi- ties Agenda Zoonotic Disease (GHSA ZD) የሙከራ ፕሮጀክት ላ ይ መወያየት እንዲሁም ዓለም አቀ ፋዊ እና ሀገራዊ የእንስሳት በሽታ የ መከታተያ መርሃ ግብሮች ላይ ልም ዶችን መለዋወጥ ነበሩ፡፡ በምክክር መድረኩ ላይም የRabiesEcon መሣሪያ የማስተዋ ወቂያ ገለፃ የተደረገ ሲሆን GHSA ZD መርሃ ግብር ደግሞ የCDC ተ ወካይ አብራርተዋል፡፡ በስብሰባው ላይ ከተመረጡ የክልል ላቦራቶሪ ፕሮጀክቶችና ከሀገር በቀል ባለድርሻ ተቋማት የተውጣጡ ተሳ ታፊዎች የነበሩ ሲሆን አዘጋጆችም የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የ በሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከ ል(CDC) እና Global Alliance for Rabies Control (GARC) ነበሩ፡፡

uôÅ^M Ö?“ Øun T>’>e‚` ¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö ... No5.pdf · በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ... መደረጉ ሲያብራሩ በተቋሙ ውስ ... ቃና

  • Upload
    lethuy

  • View
    289

  • Download
    12

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: uôÅ^M Ö?“ Øun T>’>e‚` ¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö ... No5.pdf · በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ... መደረጉ ሲያብራሩ በተቋሙ ውስ ... ቃና

uôÅ^M Ö?“ Øun T>’>e‚`¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö?“ ›=”e+ƒ¿ƒ

www.ephi.gov.et

²?“ ኢሕጤኢ¾ካቲት 2008 pê 1 lØ` 5

በኢንስቲትዩቱ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በታላቅ ድምቀት ተከበረ

በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የተቋሙ ከፍተኛ አመራር አካላት እና 80 የኢንስቲትዩቱ ሴ . . .ወደ ገጽ 3 ዞሯል

በኢሕጤኢ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቢሮ በየወሩ የሚዘጋጅ

ት ሰራተኞች በተገኙበት የካቲት 29/2008 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ፡፡ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓለ

ም አቀፍ ደረጃ “ Planet 50-50 by 2030,step it up for Gen-

የእብድ ውሻ በሽታን መከላከልና መቆጣጠር ላይ የምክክር ስብሰባ ተካሄደ

የእብድ ውሻ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በክልል እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ጥረቶችን ከሕብረተሰብ እና ከእንስሳት ጤና መስኮች ጋር በማጣመር ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በማሰብ ከየካቲት 8 - 11/2008 በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ጊቢ ለአራት ተከታታይ ቀናት የምክክር ስብሰባ ተካሄደ፡፡እንደ ስብሰባው አዘጋጆች ገለጻ የምክክር ስብሰባው ዋና ዋና ዓላማዎች የእብድ ውሻ በሽታን ለማጥፋት የStepwise Approach towards Rabies Elimination (SARE) መሣሪያን ከኢትዮጵያ አንፃር ያለውን ሁኔታ መወያየትና የተግባር ልምምድ መስራት፣ የውሻ ክትባት የRabiesEcon መሣሪያ ናሙናዎችን በመጠቀም መለማመድና መወያየት፣ Global Health Securi-ties Agenda Zoonotic Disease (GHSA ZD) የሙከራ ፕሮጀክት ላ

ይ መወያየት እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ እና ሀገራዊ የእንስሳት በሽታ የመከታተያ መርሃ ግብሮች ላይ ልምዶችን መለዋወጥ ነበሩ፡፡በምክክር መድረኩ ላይም የRabiesEcon መሣሪያ የማስተዋወቂያ ገለፃ የተደረገ ሲሆን GHSA ZD መርሃ ግብር ደግሞ የCDC ተወካይ አብራርተዋል፡፡

በስብሰባው ላይ ከተመረጡ የክልል ላቦራቶሪ ፕሮጀክቶችና ከሀገር በቀል ባለድርሻ ተቋማት የተውጣጡ ተሳታፊዎች የነበሩ ሲሆን አዘጋጆችም የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል(CDC) እና Global Alliance for Rabies Control (GARC) ነበሩ፡፡

Page 2: uôÅ^M Ö?“ Øun T>’>e‚` ¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö ... No5.pdf · በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ... መደረጉ ሲያብራሩ በተቋሙ ውስ ... ቃና

¾ካቲት 2008 pê 1 lØ` 5 Ñê 2

በኢንስቲትዩቱ የካይዘን ትግበራ በተጠበቀው ደረጃ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የካይዘን ፍልስፍና አሰራርን ተግባራዊ እንዲደርግ በካይዘን ኢንስቲትዩት በመመረጡ በተቋሙ የካይዘን ፍልስፍና አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡አቶ ሁሴን ፋሪስ የኢንስቲትዩቱ አቅርቦትና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በኢንስቲትዩቱ የካይዘን ፍልስፍና አሰራርን ተግባራዊ ስለመደረጉ ሲያብራሩ በተቋሙ ውስጥ ካይዘንን ተግባራዊ ለማድረግ የግቢ ውበትና ጽዳት ከልቡ፣ የንብረት አስተዳደር ከልቡ፣የሪከርድና ማህደር ከልቡ እና የቢሮ አስተዳደር ከልቡ ተመርጠው ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡

www.ephi.gov.et

ለዚህም ተግባር ይረዳ ዘንድ በአንቦ ዩኒቨርሲቲ እና በስራ አመራር ኢንስቲትዩት ከተቋሙ የተመረጡት ክፍሎች እንዲጎበኙና የልምድ ልውውጥ እንዲያገኙ ተደርጓል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ዳይሬክተሩ አያይዘው እንደገለጹት የንብረት አስተዳደርን በተመለከተ ለረጅም ጊዜ የቆዩ እና የተበላሹ ኬሚካሎችን የማስወገድ ስራን ለመስራት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ጋር ደብዳቤ በመጻጻፍ የዩኒቨርሲቲው ዶክተሮች መጥተው በማየት ስራውን ለመጀመር ቡድን የተቋቋመ ሲሆን የመግባቢያ ስንድ ተፈራርመን በቅርብ ቀን ወደ ስራ ይገባል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በኢንስቲትዩቱ የካይዘን ፍልስፍና አሰራር ተግባራዊ በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ የተለያዩ እንቅፋቶች እየገጠሙ ቢሆንም እንቅፋቶቹን ለማስወገድ የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው ሲሉ ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡ በመጨረሻም ዳይሬክተሩ እንዳስቀመጡት ለካይዘን ትግበራ ዝቅተኛ አመለካከት ያለው ሁሉ አመለካከቱን እንዲቀይር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ቢሰራ እና ሃላፊዎች የካይዘን ትግበራ ዘላቂነት እንዲኖረው እስከ ቡድን መሪዎች ድረስ ያለውን በማየትና ክትትል በማድረግ በትክክል መደራጀታቸው ቢታይ እና መሰራት የሚቻለውን ያህል ቢሰራ መልካም ነው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

Page 3: uôÅ^M Ö?“ Øun T>’>e‚` ¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö ... No5.pdf · በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ... መደረጉ ሲያብራሩ በተቋሙ ውስ ... ቃና

¾ካቲት 2008 pê 1 lØ` 5 Ñê 3

www.ephi.gov.et

ኢንስቲትዩቱ በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከተቋሙ ሠራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ

ኢንስቲትዩቱ የወስጥና የውጪ ተገልጋዮችን አስተያየቶች መሰረት በማድረግ በመልካም አስተዳደርና በተቋ

ከገጽ 1 የዞረ . .ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን der equality “በሚል መሪቃል ለ105ኛ ጊዜ የተከበረ ሲሆን በሃገራችን ደግሞ “ መልካም አስተዳደርን በማስፈን የሴቶች እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት እናረጋግጥ “በሚል መሪቃል ለ40ኛ ጊዜ ተከብሯል፡፡በዚህ መሰረት በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት አማካኝነት ለ5ኛ ጊዜ በታላቁ ሩጫ እና በፓናል ውይይት ተከብ

ሮ ውሏል፡፡ የአንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አመሃ ከበደ በዓሉን አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡ ዶክተር አስቴር ሸዋአማረ ከዘውዲቱ ሆስፒታል እና ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ከሃገር በቀል የልማት ማህበር በመምጣት የልምድ ተሞክሯቸውንና የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን አስመልክቶ ሰፋ ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶች ከመስጠታቸውም በላይ የቀረቡትን ትምህርቶች መሰረት በማድረግ በበዓሉ ላይ የተገኙት ሰራተኞችም የእርስ

በእርስ ውይይትም አካሂደዋል፡፡የአንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አመሃ ከበደ በበአሉ ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት ለሴቶች ከፍተኛ እድገት እና ለውጥ መመሪያዎችና ደንቦች ብቻ የተፈለገውን ያህል ውጤት ማስገኘት ባለመቻላቸው ሴቶች ትምህርት ላይ የበለጠ ትኩረት መስጠት እና መማር ይገባችኋል ይህ ደግሞ ችግሮችን በሚገባ ይፈታል፤ በመሆኑም ኢንስቲትየቱ ለዚህ ተግብር በሚችለው አቅም ሁሉ ከጎናችሁ እንደሚሆንና እንደሚደግፋችሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሙ አገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶች እና አጠናክሮ መቀጠል የሚገባውን ጠንካራ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር የካቲት 25 /2008 ዓ.ም ውይይት አካሄደ፡፡ወይይቱንም የመሩት ዶክተር አመሃ ከበደ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እና ዶክተር ይበልጣል አሰፋ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ናቸው፡፡ ከውይይቱ ቀደም ብሎ የተቋሙ የስድስት ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በአቶ አረጋ ዘሩ የእቅድ፣ ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የቀረበ ሲሆን በመቀጠል

ም ተሰብስቦና ተተንትኖ የተዘጋጀውን የውስጥና የውጪ የተገልጋዮች አስተያየቶች በአቶ አቤል የሻነህ የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ሃላፊ በንባ

ብ ቀርቧል፡፡በቀረቡት ሁለቱ ሪፖርቶች ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ከግብአት አቅርቦት፣ከቆሻሻ ማቃጠያ መሳሪያ ጥገና እና ከተላያዩ የላብራቶሪ ችግሮች ጋር በተያያዘ በርካታ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ የተቋሙ ዳይሬክቶሬት ሃላፊዎችም ያጋጠማቸውን ችግሮችና መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች ከማንሳታቸውም በላይ የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም በማስቀመጥ ለቀረቡት አስተያየቶችና ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ጥረት አድርገዋል፡፡የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክ

ተር አመሃ ከበደ በውይይቱ ወቅት እንዳስቀመጡት በየዳይሬክቶሬቶቹ ስራዎች በትክክል መሰራታቸውን በመገምገም ከታች እስከ ላይ ስራዎች በተቀመጠላቸው መንገድ መስራታቸውን መፈተሸና ከአቅም በላይ የሆኑትን በቀጣይ በምናደርገው ስብሰባ ላይ መቅረብ እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ነገር ግን የምንሰራውን ስራ ዝም ብለ

የምንሰራውን ስራ ዝም ብለን ሪፖርት ማድረግ ብቻ ከውጤት ሊያደርሰን አይችልም፤ መወያየትና ነጥሮ መውጣት ያለበት በትክክል ሊለይ ይገባዋል ስለዚህ ሁሉም የየስራ ድርሻውን ሊወጣ ይገባዋል

ን ሪፖርት ማድረግ ብቻ ከውጤት ሊያደርሰን አይችልም፤ መወያየትና ነጥሮ መውጣት ያለበት በትክክል ሊለይ ይገባዋል ስለዚህ ሁሉም የየስራ ድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡በመጨረሻም የተነሱትን ችግሮች ለመቅረፍና ለማስወገድ በኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በዶክተር ይበልጣል አሰፋ ሃላፊነት የሚመራ ከሚመለከታቸው ዳይሬክቶሬቶችና ሃላፊዎች የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሞ የአጭርና የረጅም ጊዜ መፍትሄ እንደሚሰጥ ስምምነት ላይ ተደርሶ የእለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡

Page 4: uôÅ^M Ö?“ Øun T>’>e‚` ¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö ... No5.pdf · በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ... መደረጉ ሲያብራሩ በተቋሙ ውስ ... ቃና

¾ካቲት 2008 pê 1 lØ` 5 Ñê 4

ኢንስቲትዩቱ የሀገሪቱን የሕክምና ላቦራቶሪዎች የምርመራ አገልግሎት ጥራት ለማሻሻል ከዘረጋቸው መርሃ-ግብሮች አንዱና ዋነኛው በሆነው የውጭ ጥራት ቁጥጥር (EQA) ላይ ከየካቲት 7 - 9/2008 በመቀሌ ከተማ ለ18 ተሳታፊዎች እንዲሁም ከየካቲት 14 – 16/2008 በድሬዳዋ ከተማ ለ23 ተሳታፊዎች በOne World Accuracy EQA ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡

www.ephi.gov.et

ወቅታዊ መረጃኢንፍሉዌንዛ /ጉንፋን መሰል በሽታ/

የኢንፍሉዌንዛ በሽታ የሚመጣው ተላላፊ በሆኑ ረቂቅ ህዋሳት /ቫይረሶች/ ሲሆን ብዙ ሰዎችን በዓመት ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ ለህመም ሊያጋልጥ ይችላል፡፡የኢንፍሉዌንዛ በሽታ የሚተላለፍባቸው መንገዶች ከተለመደው የጉንፋን በሽታ ጋር ተመሳሳይ ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ ለመጥቀስ ያህል የታመሙ ሰዎች በሚያስነጥሱበትና በሚያስሉበት ወቅት ከህመምተኛው የሚወጣው ቫይረስ ያዘለ አየር /ትንፋሽ/ ሌሎች በቅርበት የሚገኙትን ጤነኛ ሰዎች በመበከል እንዲሁም በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር በመጨባበጥና የተበከሉ እቃዎችን በመንካት ሊተላለፍ ይችላል፡፡የኢንፍሉዌንዛ በሽታ ምልክቶች ከጉንፋን ጋር ተመሳሳይ ሲሆኑ የሚከተሉት ናቸው፡-

ትኩሳትየራስ ምታትሳልየጉሮሮ መከርከርየጡንቻና የመገጣጠሚያ

ህመምማስነጠስ ወይም/እና የአፍ

ንጫ ፈሳሽ መብዛትናየመተንፈስ ችግር ናቸው፡

፡ከነዚህም ምልክቶች በተጨማሪ በአንዳንድ ሰዎች እና በህፃናት ላይ የማቅለሽለሽ ወይም የማስመለስ ስሜት እንዲሁም የሆድ ህመምና ተቅማጥ ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች በሆኑ ህፃናት ላይ ከሳልና ከአተነፋፈስ ችግር በተጨማሪ ምግብ መመገብ አለመቻል፣ ጡት አለመጥባት፣ ማንኛውም ነገር ማስመለስ፣ ማንዘፍዘፍ፣ መልፈስፈስና ራስን መሳት ያስከትላል፡፡

ህመሙ ተባብሶ የመተንፈስ ችግር ካጋጠመ፣ ትኩሳት በተከታታይ ከሶስት ቀናት በላይ ከቆየ በአቅራቢያ ወደሚገኘው የጤና ድርጅት በመሄድ ምርመራ ማድረግ እና የህክምና እርዳታ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ በሰውነታችን ስለመኖሩ ብቸኛው ማረጋገጫ መንገድ የላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ ነው፡፡ ምርመራው በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚከናወን ሲሆን በቂ ልምድ ባካበቱ የጤና ባለሞያዎች ከጉሮሮ ላይ በሚወሰድ ናሙና ይሆናል፡፡ የተወሰደው ናሙናም በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተመርምሮ የኢንፍሉዌንዛ መኖር ወይም አለመኖር ይረጋገጣል፡፡የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመተባበር የበሽታውን ሁኔታ በአገር አቀፍ ደረጃ ለመከታተል 8 የጤና ተቋማት /3 ጤና ጣቢያዎችና 5 ሆስፒታሎች/ ተመርጠው በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡ ተቋማቱም በዚህ በሽታ የተጠረጠሩ ህመምተኞችን በመለየት የጤና ምርመራ ያካሂዳሉ፡፡በኢንፍሉዌንዛ በሽታ ከተያዙ የሚከተሉትን ማድረግ ይመከራል፡- በቂ እረፍት ማድረግ፣በተቻለ መጠን ጥሩ መመ

ገብ፣ብዙ ፈሳሽ ነገሮችን መው

ሰድ፣እጆችን በሳሙናና በውሃ በ

የጊዜው መታጠብ እናበሚያስሉበትና በሚያስነጥ

ሱበት ጊዜ አፍና አፍንጫን በሶፍት ወረቀት ወይም በእጅ ክርን መሸፈን ተገቢ ነው፡፡

የክልል ላቦራቶሪዎችን

የአገልግሎት ጥራት

ለማሻሻል ሥልጠና

ተሰጠ

One World Accuracy መርሃ ግብር ውጤቶችን በቀጥታ በኢንተርኔት እንዲያስገቡና በተቋማቸው ሆነው በቀጥታ ግብረ መልስ እንዲያገኙ የበለጠ ለማጠናከርና ስኬታማ እንዲሆኑ

እንደ ኢንስቲትዩቱ የክልል ላቦራቶሪዎች አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ስልጠናው በሀገሪቱ የሚገኙ የህክምና ላቦራቶሪዎችን ዓለም አቀፍ የውጭ ጥራት ቁጥጥር የሆነውን የአንድ ዓለም ጥራት መለኪያ ወይም One World Accuracy መርሃ ግብርን በመጠቀም ውጤቶችን በቀጥታ በኢንተርኔት እንዲያስገቡና በተቋማቸው ሆነው በቀጥታ ግብረ መልስ እንዲያገኙ የበለጠ ለማጠናከርና ስኬታማ እንዲሆኑ ለማድረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም በሀገሪቱ የሚገኙ የህክምና ላቦራቶሪዎችና በOne World Accuracy የሚሳተፉ መረሃ ግብሩን ከተገበሩ በኋላ ውጤቶችን የማስገቢያ ጊዜያቸው ሳያበቃና ግብረ መልሶቹ ወቅታቸውን ጠብቀው እንዲደርሱ በማገዝና የዚህ መረሃ ግብር ተሳታፊ የሆኑ ተቋማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማብቃት የስልጠናው ዋና ግብ እንደነበረ ተጠቁሟል፡፡