27
1 ydb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ ?ZïC KLላዊ mNGT db#B nU¶T Uz@È DEBUB NEGARIT GAZETA OF THE SOUTHERN NATIONS, NATIONALITIES AND PEOPLES REGIONAL STATE ማውጫ ደንብ ቁጥር 87/2003 በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የይርጋዓለም ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ለማቋቋም የወጣ ደንብ ደንብ ቁጥር 87/2003 በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የይርጋዓለም ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ለማቋቋም የወጣ ደንብ መግቢያ በሀገሪቱም ሆነ በክልሉ ያሉትን የመለስተኛና የመካከለኛ ደረጃ ሐኪሞች የከፍተኛ ደረጃ ስፔሻሊቱ ሕክምናን ስልጠና የሚያገኙበትን ዕድል በማመቻቸት በአጭር ጊዜ ውስጥ የማፈለገውን የከፍተኛ ሕክምና ባለሙያዎችን በብዛትና በጥራት ማምረት ሀገሪቱ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አኳያ አንገብጋቢ እየሆነ በመምጣቱ፤ በዓይነታቸው ከባድና ከፍተኛ በሚባሉ በሽታዎች የተጋለጡ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በሀገሪቱ የጤና ሽፋን ተጠቃሚ ለማድረግ በዘርፉ በልዩ ሁኔታ ምርምር የሚደረግና ሥልጠና የሚሰጥ ተቋም መመስረት አስፈላጊነት ላይ በመታመኑ፤ የክልሉን የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳና በጤናው ዘርፍ የተፈለገውን ለውጥ ለማስመዝገብ የሚያስችል የተለየ የሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ማቋቋም በማስፈለጉ፣ 17¾ ›mT q$_R 7 êú ከጥር 5 ቀን 2003 bdb#B B/@éC½B/@rsïCÂ ?ZïC KLMክር b@T -ÆqEnT ywÈ ደንብ

ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

  • Upload
    others

  • View
    3

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

1

ydb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ ?ZïC KLላዊ mNGሥT

db#B nU¶T Uz@ÈDEBUB NEGARIT GAZETA

OF THE SOUTHERN NATIONS, NATIONALITIES ANDPEOPLES REGIONAL STATE

ማውጫ

ደንብ ቁጥር 87/2003

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የይርጋዓለም ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ

ለማቋቋም የወጣ ደንብ

ደንብ ቁጥር 87/2003

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የይርጋዓለም ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ

ለማቋቋም የወጣ ደንብ

መግቢያ

በሀገሪቱም ሆነ በክልሉ ያሉትን የመለስተኛና የመካከለኛ ደረጃ ሐኪሞች የከፍተኛ ደረጃ

ስፔሻሊቱ ሕክምናን ስልጠና የሚያገኙበትን ዕድል በማመቻቸት በአጭር ጊዜ ውስጥ

የማፈለገውን የከፍተኛ ሕክምና ባለሙያዎችን በብዛትና በጥራት ማምረት ሀገሪቱ ካለችበት

ነባራዊ ሁኔታ አኳያ አንገብጋቢ እየሆነ በመምጣቱ፤

በዓይነታቸው ከባድና ከፍተኛ በሚባሉ በሽታዎች የተጋለጡ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በሀገሪቱ

የጤና ሽፋን ተጠቃሚ ለማድረግ በዘርፉ በልዩ ሁኔታ ምርምር የሚደረግና ሥልጠና የሚሰጥ

ተቋም መመስረት አስፈላጊነት ላይ በመታመኑ፤

የክልሉን የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳና በጤናው ዘርፍ የተፈለገውን ለውጥ

ለማስመዝገብ የሚያስችል የተለየ የሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ማቋቋም በማስፈለጉ፣

17¾ ›mT q$_R 7ሀêú ከጥር 5 ቀን 2003

bdb#B B/@éC½B/@rsïCÂ ?ZïCKLል Mክር b@T -ÆqEnT ywÈ ደንብ

Page 2: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

2

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ክልል መንግሥት የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር

ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 133/2003 አንቀጽ 44/3/ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡

ክፍል አንድ

ጠቅላላ

1. አጭር ርዕስ

ይህ ደንብ “የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰበቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የይርጋዓለም

ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 87 /2003” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2. ትርጓሜ

በዚህ ደንብ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በቀር፡-

1. “ክልል” ማለት የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰበቦችና ሕዝቦች ክልል ነው፡፡

2. “ቢሮና ኃላፊ” ማለት እንደቅደም ተከተላቸው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰበቦችና

ሕዝቦች ክልል ጤና ቢሮ እና የጤና ቢሮ ኃላፊ ነው፡፡

3. “ኮሌጅ” ማለት የይርጋዓለም ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ነው፡፡

4. “ሚኒስቴር” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞከራሲያዊ ሪፖብሊክ ትምህርት

ሚኒስቴር ነው፡፡

5. “የአካዳሚክ ማህበረሰብ” ማለት በኮሌጁ ውስጥ በመደበኛነት ወይም በጊዜያዊነት

በመማር፣ በማስተማር እና በምርምር ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሰዎችን

ያቀፈ ነው፡፡

6. “የአካዳሚክ ሠራተኛ” ማለት በኮሌጁ በማስተማር ወይም የምርምር ጉዳዮችን

የሚመራና ኃላፊነት የተሰጠው አካል ነው፡፡

7. “የአካዳሚክ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኛ” ማለት የአስተዳደር፣ የቢዝነስ አመራር፣

የፋይናንስና የሂሣብ ሥራ፣ የምግብ አገልግሎት ማቅረብ፣ የጥገና፣ የጥበቃና

ደህንነት ወይም የመሳሰሉትን ተግባራት የሚያከናውን የኮሌጁ ሠራተኛ ነው፡፡

8. “ቦርድ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ 14 መሠረት የሚሰየም የኮሌጁ አመራርና ቦርድ

ነው፡፡

Page 3: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

3

9. “አካዳሚክ ኮሚሽን” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ 23 መሠረት የተቋቋመው ኮሚሽን

ነው፡፡

10.“ሰው” ማለት የተፈጥሮ ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፡፡

3. መቋቋም

የይርጋዓለም ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ከዚህ በኋላ “ኮሌጅ” እየተባለ የሚጠራ የከፍተኛ

ሕክምና ስልጠና የሚሰጥ ሆኖ ሕጋዊ ሰውነት ያለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም

በመሆን በዚህ ደንብ ተቋቋሟል፡፡

4. ተጠሪነት

ኮሌጁ አግባብ ባላቸው የሀገሪቱ ሕግ መሠረት ለሚኒስቴሩ ያለው ተጠሪነት እንደተጠበቀ

ሆኖ በክልል ደረጃ ተጠሪነቱ ለቢሮው ነው፡፡

5. የኮሌጁ አቋም

1. ኮሌጁ

ሀ/ የአመራር ቦርድ ፣ አካዳሚክ ኮሚሽን፣ ዲንና ምክትል ዲኖች፣

ለ/ የአካዳሚክ ሠራተኞች

ሐ/ የአስተዳደርና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች እና

2. ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ፋካልቲዎችና ሌሎች የሥራ ክፍሎች ይኖሩታል፡፡

6. ዓላማ

ኮሌጁ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡-

1. የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን የከፍተኛ ሕክምና ባለሙያዎች እጥረት ለመፍታት

በሚያስችል መልኩ በእውቀት፣ ክህሎትና በመልካም ሥነ ምግባር የታነፁ የከፍተኛ

ሕክምና ባለሙያዎች በማሰልጠን በቂ የሰው ኃይል ማፍራት፣

2. ተገቢውን የመማር ማስተማር ሥርዓት በመዘርጋት ትኩረት በሚሹ የጤና ጉዳዮች

ላይ ችግር ፈቺና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ምርምሮችን ማካሄድና ማስረጽ፤

3. በአገሪቱ የጤና ፍላጐት ላይ የተመሠረተና ትኩረቱ በእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር

ላይ የሆነ ምርምርን ማራመድና ማጐልበት፤

4. አገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን የማያስችሏትን፣ ጥራቱን የጠበቀና

ሀገራዊ ፋይዳ ያለውን የጤና አካዳሚክ ማህበረሰብን በመፍጠር በአርአያነት ተጠቃሽ

የሆነ ተግባራትን መፈፀም፤፡

Page 4: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

4

7. ስለኮሌጁ አካዳሚያዊ ነፃነት

1. ኮሌጁ ዓላማውን ለማሳካት በሀገሪቱ ባለው ሕግ መሠረት አካዳሚያዊ ነፃነት

ይኖረዋል፣

2. ኮሌጁ በዚህ ደንብና አግባብነት ባላቸው የአገሪቱ ሕጐች እንዲሁም በዓለም አቀፍ

መልካም ልምድ መሠረት የአካዳሚያዊ ነፃነት አተገባበር በሥርዓት እንዲመራ

ማድረግ ይኖርበታል፣

3. ኮሌጁ በዚህ ደንብና አግባብነት ባላቸው የአገሪቱ ሕጐች እንዲሁም በዓለም አቀፍ

መልካም ልምድ መሠረት የአካዳሚያዊ ነፃነት አተገባበር በሥርዓት እንዲመራ

ማድረግ ይኖርበታል፣

8. የትምህርት መርሃ-ግብር

1. የኮሌጁ የትምህርት መርሃ-ግብር

ሀ/ በመደበኛ

ለ/ በተከታታይ ወይም

2. በብቃት ማሻሻያ አስፈላጊነት በሚኖራቸው መስኮች እውቀትና ክህሎትን

ለማስተላለፍ የአጭር ጊዜ ስልጠናዎችን ሊሰጥ ይችላል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡

9. የሥርዓተ ትምህርት ይዘት

1. ኮሌጁ የሥርዓተ ትምህርት ቀረፃ፣ ትግበራና የምዘና ዓላማ ተማሪው ተገቢው

ሳይንሳዊ እውቀት፣ በነፃ የማሰብን የሚያበረታታ፣ ተግባር ተኮር የሆነ ነባራዊ

ሁኔታን ያገናዘበና መልካም ሙያዊ ስብእናን እንዲጨብጥ በማድረግ ብቁ የጤና

ባለሙያን ማዘጋጀት ይሆናል::

2. ኮሌጁ የትምህርት ክፍሎቹ የሥርዓተ ትምህርት ቀረፃ ሚኒስቴሩ ባስቀመጠው

በተገቢ የምሩቃን ብቃት መመዘኛዎች እንዲመራ ማድረግ አለበት::

10. የአካዳሚክ ዘመንና የበጀት ዓመት

1. ኮሌጁ የሚያሰለጥነው የሙያ መስክ የአካዳሚክ ዘመን በሚኒስቴሩ በተቀመጠው

የአካዳሚክ ዘመን ይሆናል፡፡

2. የኮሌጁ የበጀት ዓመት የመንግሥት በጀት ዓመት ይሆናል፡፡

11. የኮሌጅ ደረጃ

1. የኮሌጁ ደረጃ አግባብ ባለው ሕግ መሠረት በሚኒስቴሩ ይወሰናል፡፡

Page 5: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

5

2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሌጁ ከዲግሪ በላይ

የሆነ ማዕረግ የሚያስመርቅ ነው፡፡

12. የኮሌጁ ተግባርና ኃላፊነት

ኮሌጁ የሚከተሉት ተግባራትና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡

1. ሚኒስቴሩ በሚያወጣው የምልመላ መስፈርትና መመሪያ መሠረት ተማሪዎችን

መቀበል፤

2. የክልሉን የከፍተኛ ሕክምና ባለሙያን ፍላጐት መሠረት በማድረግ ብቃት ያላቸውን

የሰለጠኑ ሐኪሞች በብዛትና በጥራት የማፍራት፤

3. አገር አቀፍ መለኪያዎችን መሠረት ያደረገ የትምህርትና ስልጠና መርሃ ግብር

በመቀየስ ቦርድ ሲያፀድቅለት በሥራ ላይ ማዋል፤

4. እንደአግባብነቱ በትምህርቱ ኘሮግራሞች በመሰልጠንና ተገቢውን የተማሪዎች ምዘና

በማድረግ ተፈላጊውን ውጤት ላስመዘገቡ ሰልጣኞች ተገቢውን የትምህርት ማስረጃ

የዲግሪ፣ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪ ማስረጃ የመስጠት፤

5. እንደአስፈላጊነቱ የተለያዩ የስልጠና፣ ጥናትና ምርምር ክፍሎችን ማቋቋምና

ማጠናከር፤

6. የትምህርትና ስልጠና መረጃ መሣሪያዎችንና መፃሕፍትን በማሰባሰብ የቤተሙከራና

ቤተመፃሕፍትን በማዘጋጀትና በማደራጀት የመማር ማስተማሩን ሂደት ምቹ

የማድረግ፤

7. ከሀገር ውጭ ከሚገኙ መሰል ዩኒቨርሲቲዎችና የሕክምና ተቋማት ጋር ግንኙነት

የመፍጠርና የሕክምና ቴክኖሎጂዎችንና መሣሪያዎችን በግዢም ሆነ በእርዳታ

እንዲገኝ በማድረግ የኮሌጁን አቅም ማሳደግ፤

8. ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት ለሕብረተሰቡ የመስጠት፣

9. ልዩ የትኩረት አቅጣጫ በሚፈልጉ የጤና ዘርፎች ቢሮው ወይም በመንግሥት

ሲፈለግ በልዩ ኘሮግራም የአጭርና የመካከለኛ ደረጃ ስልጠናዎችን በማዘጋጀትና

በመተግበር የሰርተፊኬትና ዲኘሎማ ማስረጃ የመስጠት፣

10.የኮሌጁ ሠራተኞችና ተማሪዎች ስለሚያገኙት የሕክምና አገልግሎት ቦርዱ

በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የመፈፀም፤

11.ጤና ነክ የሆኑ ትምህርታዊ መረጃዎችን በኤሌክትሮኒክስና በሕትመት ሚዲያዎች

ወይንም በዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም የማሰራጨት፣

Page 6: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

6

12.የተማሪዎች ትምህርት ወጪ ክፍያ፣ የአገልግሎት ክፍያና ሌሎች ከተለያዩ

ምንጮች የሚያገኛቸውን ገቢዎች በአግባቡ የመሰብሰብ በቦርድ ሲፈቀድም በሥራ

ላይ የማዋል፡፡

13.ለኮሌጁ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች የአካዳሚክ ማዕረግና ሰርተፊኬቶችን

የመስጠት፣

14.ሌሎች ዓላማውን ለማሳካት የሚያስችሉ ተዛማጅ ተግባራትን የማከናወን ኃላፊነት

ይኖርበታል፡፡

ክፍል ሁለት

ስለኮሌጁ አመራር አካላት ተግባርና ኃላፊት

13. ኮሌጁ የሚከተሉት የአመራረ አካላት ይኖሩታል፡-

1. የአመራር ቦርድ፣

2. ዲንና ምክትል ዲኖች፣

3. የአካዳሚክ ኮሚሽን፡፡

ምዕራፍ አንድ

ስለቦርድ

14. ስለኮሌጁ የአመራር ቦርድና ምልዓተ-ጉባዔ

1. የአመራር ቦርድ ሰብሣቢውን ጨምሮ 7 አባላት ይኖሩታል፡፡ ቦርዱ የሴቶች ተሣትፎ

ያለበት መሆን ይኖርበታል፡፡

2. ከቦርዱ ሰብሣቢ በተጨማሪ ሦስት ድምፅ መስጠት የሚችሉ አባላት በቢሮው እጩ

አቅራቢነት በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ይሰየማሉ፡፡

3. የኮሌጁ ዲን ከአካዳሚክ ኮሚሽኑና ከኮሌጁ የአስተዳደር አካላት ጋር በመመካከር

ሦስት የቦርድ አባል እጩዎችን በማቅረብ በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት

ይሰየማሉ፡፡

4. የኮሌጁ ዲን ድምጽ የማይሰጥ የቦርድ አባልና ፀሐፊ ይሆናል፡፡

5. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /2/ እና /3/ መሠረት የሚሰየሙ የቦርድ አባላት

በኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያሉ ወይም ያገለገሉና በተለይ በማስተማር ወይም

በምርምርና በግል ስብዕናቸው፣ እውቀታቸው፣ ልምዳቸውና አትኩሮታቸው የታወቁ

ግለሰቦች በአጠቃላይ ለኮሌጁ ዓላማና ተልዕኮ መሳካት አስተዋጽኦ ለማበርከት

የሚችሉ መሆን ይገባቸዋል፡፡

Page 7: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

7

6. በርዱ በራሱ ውሣኔ ማንኛውንም ሰው በአስረጂነት በስብሰባዎች ሊያሳትፍ ይችላል፡፡

7. አምስት ድምፅ መስጠት የሚችሉ የቦርዱ አባላት ሲገኙ መልዓተ ጉባዔ ይሆናል፡፡

8. የቦርዱ ሰብሣቢ ጊዜ በተቆረጠለት ስብሰባ የሚመራ ሰብሣቢ ከመሀከላቸው

በመምረጥ የስብሰባውን አጀንዳ ይፈጽማሉ፡፡

9. ቦርዱ የስብሰባው አካሄድ የሚመለከት የአሠራር ሥነ-ሥርዓት ሊያወጣ ይችላል፤

10.ቦርድ በጉዳዮች ላይ ውሣኔ የሚያሳልፈው በአብላጫ ድምፅ ይሆናል፡፡ እኩል ድምፅ

በተሰጠ ጊዜ የቦርዱ ሰብሣቢ የሚደግፈው አቋም በአብላጫ ድምፅነት ይፈረጃል፡፡

15.ስለቦርዱ መደበኛ ስብሰባዎች

1. የቦርዱ መደበኛ ስብሰባዎች በዓመት ከሦስት እስከ አራት ጊዜ ይሆናል፡፡

2. የመደበኛ የስብሰባው ጊዜ ቦርዱ ኃላፊነቱን ለመወጣት በሚያስችለው መልኩ

በተለይም የእቅድና የበጀት ዝግጅቶች እንዲሁም አፈፃፀም ላይ አስተዋጽኦ ለማድረግ

እንዲችል በሚያደርገው ወቅቶች እንዲሆን ያደረጋል፡፡

3. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /2/ እንደተጠበቀ ሆኖ ቦርድ በሰብሣቢው ጥሪ ወይም

ድምፅ የመስጠት መብት ካላቸው አባላቱ አንድ ሦስተኛው (1/3) በሚጠይቁበት ጊዜ

አስቸኳይ ስብሰባ ማድረግ ይችላል፡፡

4. የቦርዱ ሰብሣቢ ሁሉም የቦርድ ስብሰባዎች በቂ ዝግጅት የተደረገባቸው መሆኑን፣

ሠነዶቹ በጥንቃቄ መጠበቃቸውንና መያዛቸውን፣ ቦርድ በሚያዘው መሠረት

ውሣኔዎቹ በትክክል ለሚመለከታቸው መተላለፋቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

16. የቦርዱ አባልነት መቋረጥ

የቦርድ አባልነት በሚከተሉት ምክንያቶች ሊቋረጥ ይችላል፡፡

1. ቢሮው በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የአገልግሎት ዘመን ሲያበቃ፤

2. በፈቃደኝነት ከአባልነት በመልቀቅ፤

3. በሞት፣ በሕመም ወይም በከባድ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘት፣

4. በከባድ ጥፋት፣ ችሎት ማጣት ወይም ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ከባድ የሆነ

ድክመት በማሳየት ወይም ባለመቻል/

5. ቢሮው ቦርዱን ሙሉ ለሙሉ ለመቀየር ወይም በከፊል ለመለወጥ ውሣኔ ላይ

ሲደርስ፡፡

Page 8: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

8

17. ስለቦርዱ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ

1. ቦርዱ የተሻለ አመራር ለመስጠት የሚያስችለውን ግንዛቤ ለማግኘት የራሱን የሥራ

አፈፃፀም ግምገማ ማድረግ ይኖርበታል፣

2. የቦርዱ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ድምጽ የመስጠት መብት ባላቸው አባላትና የኮሌጁ

ዲን በተገኙበት በዝግ ስብሰባ ያካሄዳል፡፡

3. የቦርዱ ሰብሣቢ የግምገማውን ውጤቶች በየወቅቱ ለመስተዳድር ምክር ቤትና

ለቢሮው ሪፖርት ያደርጋል፡፡ የቦርድ ሰብሣቢው ከቢሮው ጋር መደበኛ የጋራ

መድረክም በዓመት ሁለት ጊዜ ይኖራል፡፡

4. ቦርዱ ግምገማውን መቼና እንዴት እንደሚያካሄድ ይወስናል፤ ሆኖም በዓመት

ቢያንስ አንድ የክትትል ግምገማና አንድ የማጠቃለያ ግምገማ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

18. የኮሌጁ የአመራር ቦርድ ኃላፊነት

1. የኮሌጁ ቦርድ የተቋሙ የበላይ አመራር ሆኖ የሚከተለው ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡

ሀ/ ኮሌጁ የዚህን ደንብና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ሕጐች መተግበራቸውንና

በተቋሙ ውስጥ መልካም አስተዳደር መስፈኑን መከታተልና ማረጋገጥ፣

ለ/ የኮሌጁን ዕቅድ፣ በጀት፣ የትኩረት አቅጣጫ፣ አደረጃጀት፣ አስተዳደርና አሠራር

ሥርዓት፣ የውስጥ ደንብና የአካዳሚክ ኘሮግራሞችን በሚመለከት የሚቀርቡለት

ሃሣቦችን መርምሮ ማጽደቅና ተግባራዊነታቸውን መከታተል፣

ሐ/ በኮሌጁ ዲን በሚቀርብ ሃሣብ ላይ በመመርኮዝ ምክትል ዲኖችንና ሌሎች

አካዳሚክ ኃላፊዎች እንዲሁም የአካዳሚክ ኮሚሽን አባላት እንደአግባቡ

የሚታጩበት፣ የሚሰየሙበት ወይም የሚመደቡበትና የሚመረጡበትን

ሥርዓትና የአገልግሎት ዘመናቸውን የሚመለከቱ መመሪያዎችን ማውጣት እና

በትክክል መተግበራቸውን መከታተል፡

መ/የኮሌጁ ዲን እጩን ለሹመት እንደአግባብነቱ ለክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት

ወይም ለቢሮ ማቅረብ እና ዲኑ ምክትል ዲኖችን ማሰየም፤

ሠ/ አግባብነት ያላቸው ሕጐች ተፈፃሚነት እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም ምክትል

ዲን ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ ከፍተኛ የሆነ ድክመት ካሣየ ከኃላፊነት

ማሰናበትን ጨምሮ የዲሲኘሊን እርምጃ መውሰድ፣ ዲኑን የሚመለከት ሲሆን

የቢሮውን ኃላፊ በማማከር እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፣

ረ/ ለኮሌጁን ኤዲተሮች ክፍያቸው መወሰን፣

Page 9: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

9

ሰ/ የኮሌጁን የስትራቴጂክ እቅድ፣ ዓመታዊ እቅድና በጀት ማቅረብና ሲፀድቁም

ተፈፃሚነታቸውን መከታተል፣ የተቋሙን የክንውን ሪፖርትና የፋይናንስ

መግለጫን ማቅረብና ማፀደቅ፤

ሸ/ የኮሌጁ ዋና ዋና እና ጥቃቅን ገቢዎቹን ትክክለኛ የሂሣብ መዝገብ መያዙንና

ወጪዎቹ በበጀት መሠረት መሆናቸውን መከታተልና ማረጋገጥ፣

ቀ/ የኮሌጁ ሌሎች የአመራር አካላት ከባድ የሕግ መጣስ ተግባር በሚፈጽሙበት

ጊዜ ወይም ከባድ የሆነ የገንዘብ ብክነት ስለመከሰቱ ጥርጣሬ ካለ ወይም

በእርግጥ ተከስቶ ከሆነ በራሱ ስልጣን ክልል ተገቢውን የመፍትሔ እርምጃ

መውሰድና ወዲያውኑ ለቢሮው ሪፖርት ማቅረብ፤

በ/ የክልሉ መንግሥት የሠራተኞች አዋጅና ደንቦች መሠረታዊ መርሆች ላይ

በመመስረት የአስተዳደርና የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችን ቅጥር፣ እድገት፣

ዲስፒሊን፣ ደመወዝ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን የሚመለከት ፖሊሲን

እንደአስፈላጊነቱ እንዲዘጋጅ ማድረግና ማጽደቅ፤

ተ/ ኮሌጁን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ መረጃ የመጠየቅና የማግኘት እና ለቢሮው

ወይም ለሚኒስቴሩ ሪፖርት ማድረግ፣

ቸ/ በኮሌጁ ውሣኔዎች ላይ ቅሬታ ሲቀርብ መመርመርና የመጨረሻ ውሣኔ

መስጠት፤

ኃ/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ተራ ፊደል /ቸ/ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሌጁ

ቅሬታዎችን በተፋጠነ መንገድ ተቀብሎ የሚፈታበት የተሟላ ተቋማዊ ሥርዓት

ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፣

ነ/ የኮሌጁን አካዳሚክ ክፍሎች፣ የአስተዳደር አካላቱን የሥራ አፈፃፀም በዲኑ

ሪፖርት መሠረት ከእቅድ አኳያ መገምገም፤

አ/ የአካዳሚክ ኮሚሽን ውሣኔዎችና የሚያወጣቸው የአካዳሚክ ሕጐች

መፈፀማቸውን መከታተል፤

ከ/ ከኮሌጁ ዲን ወይም በአካዳሚክ ኮሚሽኑ የተላለፈ ውሣኔዎች የተቋሙን ተልዕኮ

የሚጐዱ ወይም ይህንን ደንብ ወይም ሌሎች የሀገሪቱን ሕጐች የሚቃረኑ ሆነው

ሲገኙ ውሣኔዎቹን መሻር፣

ኸ/ የራሱን የአሠራር ሥነ ሥርዓትና የውስጥ አስተዳደር ደንብና አባላቱን

የሚመለከት የዲሲኘሊን ደንብን ማውጣት፤

Page 10: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

10

ወ/ የኘሮፌሰርነት የማዕረግ እድገትን በአካዳሚክ ኮሚሽን ሲቀርብለት ማፀደቅ፣

ዐ/ በዲኑ በሚቀርብ ምክር ላይ ተመስርቶ ኮሌጁ ለትምህርት የሚያስከፍላቸውን

የተለያዩ ክፍያዎች ዓይነትና መጠን መወሰን እንዲሁም የክልሉ መስተዳድር

ምክር ቤት በወሰነው መሠረት የተቋሙን ገቢ ግምት ውስጥ በማስገባት

የተለያዩ ተካፋይ አበሎችን፣ የትርፍ ሰዓት ክፍያዎችንና የመሳሰሉትን መወሰን፣

2. የቦርዱ ተጠሪነት ለቢሮው ነው፡፡

3. የኮሌጅ ቦርድ አባላት ጥቅማ ጥቅሞች በቢሮው አቅራቢነት በክልሉ መስተዳድር

ምክር ቤት የሚወሰኑ ሲሆን የሚሸፈኑት በኮሌጁ ነው፡፡ ሆኖም የተቋሙን አቅም

ያገናዘበ መሆን አለበት፡፡

ምዕራፍ አራት

ስለኮሌጁ ዲንና ምክትል ዲኖች

19. ስለኮሌጁ ዲንና ምክትል ዲኖች ሹመትና የሥራ አፈፃፀም ግምገማ

ሀ/ የኮሌጁ ዲን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /መ/ መሠረት ቦርዱ አወዳድሮ

ከሚያቀርባቸው እጩዎች መካከል በክልሉ መስተዳድሩ ምክር ቤት ይሾማል፡፡

ለ/ የዲን የኃላፊነት ቦታ በቦርድ በሚሰየም አካል በይፋ ለተወዳዳሪዎች ይገለፃል፡፡

ሐ/ የኮሌጁ ምክትል ዲኖች ቢሮው አወዳድሮ ከሚያቀርባቸው እጩዎች መካከል

የተሻለ ብቃትና ዝግጁነት ያለው ተመርጦ በመስተዳድር ምክር ቤት ይሰየማል፡፡

ሆኖም ተወዳደሪዎች በይፋ እንዲጋበዙ ከተደረገ በኋላ መሆን ይኖርበታል፡፡

መ/ የውድድርና የምርጫ ሥነ ሥርዓት ዝርዝር መመሪያ በቦርዱ ይወጣል፡፡

ሠ/ የኮሌጁ ዲን የሥራ ዘመን ስድስት ዓመት ሲሆን የምክትል ዲኖች አራት ዓመት

ይሆናል፡፡ ሆኖም በተደጋጋሚ ሊሾሙ ይችላሉ፡፡

ረ/ ቦርዱ፣ የዲኑንና የምክትል ዲኖች የሥራ አፈፃፀም የክትትል ግምገማ በዓመት

ሁለት ጊዜ ያካሂዳል፡፡

ሰ/ መደበኛ የዲንና የምክትል ዲኖች ካልተሰየሙ ተጠባባቅ ዲን ወይም ተጠባባቂ

ምክትል ዲን ሆኖ መቆየት ይቻላል፡፡ ሆኖም የቆይታ ጊዜው ከ180 ቀናት በላይ

መሆን የለበትም፡፡

Page 11: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

11

20. የኮሌጁ ዲን ኃላፊነትና ተግባር

1. የቦርዱ ኃላፊነት እንደጠበቀ ሆኖ የኮሌጁ ዲን ዋና ሥራ አስፈፃሚ በመሆን

የሚከተሉት ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡

ሀ/ የኮሌጁን ዓላማና ተልዕኮ ለማሣካት ይችል ዘንድ ይመራል፣ ያስተዳድራል፤

ለ/ የኮሌጅ አካላትና ማህበረሰብ የከፍተኛ ትምሀርት ዓላማዎችንና የኮሌጁን መሪ

እሴቶች ማክበራቸውን ያረጋግጣል፤

ሐ/ ኮሌጁ ክልሉ በጤናው ዘርፍ በሚፈልገው መጠንና ዓይነት ከፍተኛ ጥራትን

የተከተለ ብቃት ያላቸውን የጤና ምሩቃንን ማፍራቱን ያረጋግጣል፤

መ/መማር፣ ማስተማርንና ምርምርን የሚያበረታታ ምቹ የኮሌጁ ማህበረሰብን

ይፈጠራል፣ በቀጣይነት ይገነባል፤

ሠ/ የኮሌጁ የምርመራና የማማከር ተግባራት ሁሉ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ሀገራዊና

ክልላዊ ጉዳዮች ላይ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፤

ረ/ ኮሌጁ ዓላማውን ለማሳካት ከሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል ባለድርሻ

አካላት፣ አግባብነት ካላቸው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች

ጋር በዘላቂነት ግንኙነት እንዲፈጠር ያደርጋል፤

ሰ/ ኮሌጁ በሰው ኃይሉ፣ በአደረጃጀቱና አሠራሩ ለተቋሙ ተልዕኮ የሚመጥን ብቃት

ያለው የውስጥ አመራርና አስተዳደር ሥርዓት እንዲኖረው ያደርጋል፤

ሸ/ የአካዳሚክ ኃላፊዎችና የአካዳሚክ ኮሚሽን አባላትን የአሰያየም ሥርዓትን

በማዘጋጀትና በቦርድ በማፀደቅ በተግባር ላይ ያውላል፤

ቀ/ በትምህርትና ምርምር አግባብነትና ጥራት፣ በተቋማዊ ነፃነትና ተጠያቂነት፣

በአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነትና በወጪ ቆጣቢነት መርሆች ላይ

በመመስረት የትምህርት ክፍሎች አደረጃጀትን ለአካዳሚክ ኮሚሽኑና ለቦርዱ

አቅርቦ ያስወስናል፤ ሲፈቀድም በተግባር ላይ ያውላል፤

በ/ የቅጥር ኃላፊነት ቦታዎች በውድድር የሚያዙ መሆኑንና ከኃላፊነት መነሳትም

በሥራ አፈፃፀም ግምገማ፣ በዲሲኘሊን ጉዳይ እና በአገልግሎት ዘመን ማብቃት

ብቻ ላይ ተመስርቶ መሆኑን ያረጋግጣል፣

ተ/ ተቋማዊ የደረጃ መለኪያዎችን ያዘጋጃል፣ የኮሌጁ የአካዳሚክና የአስተዳደር

ሥራዎች በወጡት መለኪያዎች መሠረት መፈፀማቸውን ያረጋግጣል፣

Page 12: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

12

ቸ/ የኮሌጁን ገቢና ወጪ አግባብነት ባላቸው የፋይናንስ ሕግ መሠረት

መንቀሳቀሳቸውንና መያዛቸውን ያረጋግጣል፣

ኃ/ የአካዳሚክ ኮሚሽኑና ሌሎች አስተዳደራዊና ውስጣዊ ስብሰባዎች በበቂ ዝግጅትና

ወቅታቸውን ጠብቀው እንዲካሄዱ ያደርጋል፤

ነ/ በኮሌጅ ውስጥ ወይም በኮሌጁና በሦስተኛ ወገኖች መካከል የሚነሱ

አለመግባባቶችን የተቋሙን ተልዕኮና ጥቅሞች ከማሳካት አኳያ በሰላማዊና

ሕጋዊ መንገድ እንዲፈቱ ያደርጋል፤

ኘ/ የኮሌጁ እንቅስቃሴና መሠረታዊ ግንኙነቶች በተገቢው የመረጃ ሥርዓት

መመዝገባቸውን፣ መረጃው በአግባቡ መጠበቁንና አግባብነት ላላቸውም ተደራሽ

መሆኑን ያረጋግጣል፣

አ/ የኮሌጁን እቅድና በጀት ያዘጋጃል፣ ሲፀድቁም ያስፈጽማል፤

ከ/ ስለኮሌጁ እቅድ አፈፃፀም ለቦርዱና ለሚመለከተው ክፍል ወቅቱን የጠበቀ

ሪፖርት እና መረጃ ያቀርባል፤

ኸ/ ኮሌጁ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርገው ማናቸውም ግንኙነት ተቋሙን

ይወክላል፤

ወ/ በኮሌጁ ስም የባንክ ሂሣብ ይከፍታል፣ ያንቀሳቅሳል፡፡

ዐ/ የወጪ ጉዞዎቹን በታቀዱና ለተቋሙ ባላቸው ፋይዳ ላይ የተመሠረቱ

መሆናቸውን ያረጋግጣል፣

2. ዲኑ ሙሉ ጊዜውን ለኮሌጁ ሥራዎች ያውላል፤ ለአገልግሎቱ ተገቢውን ደመወዝና

ጥቅማ ጥቅሞች ያገኛል፣

3. ዲኑ በሁኔታዎች አስገዳጅነት ሥራው ላይ በማይገኝበት ጊዜ ከምክትል ዲኖቹ

አንዱን ሊወክል ይችላል፣

21. ስለምክትል ዲኖች ኃላፊነትና ተግባር

1. የምክትል ዲኖች ቁጥር ቦርዱ ከቢሮው ጋር በመመካከር አስፈላጊ ናቸው ብሎ

የሚወስነውን ያህል ይሆናል፡፡

ሀ/ የኮሌጁን ተግባራት በማቀድ፣ በማደራጀት፣ በመምራትና በማስተባበር ዲኑን

ያግዛሉ፡፡

ለ/ በዲኑ ተለይተው የሚሰጧቸውን ሥራዎች ያከናውናሉ፡፡

Page 13: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

13

ሐ/ ዲኑ በማይኖርባቸው ጊዜ ተለይቶ ውክልና የሰጠው ምክትል ዲን ለዲኑ

የተሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፡

2. ምክትል ዲኖች አብዛኛውን የሥራ ጊዜያቸውን ለኮሌጅ ሥራ ያውላል፤

ለአገልግሎታቸውም ተገቢ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅሞች ያገኛሉ፡፡

22. ስለዲኑና ምክትል ዲኖች አገልግሎት መቋረጥ

1. የኮሌጁ ዲን ወይንም ምክትል ዲኖች ከሚከተሉት ምክንያቶች በአንድ ከኃላፊነቱ

ሊሰናበት ይችላል፡-

ሀ/ በፈቃዱ ሥራ በመልቀቅ፣

ለ/ በችሎታ ማጣት፣ በከባድ ጥፋት፣ በህመም ወይም በሞት ምክንያት የተሰናበተ

ከሆነ፣

ሐ/ በፈቃድ ከ180 ተከታታይ ቀናት በላይ ከሥራ ከተለየ፤

መ/ያለፈቃድ ከ45 ተከታታይ ቀናት በላይ ከሥራ ከተለየ፤ ወይንም

ሠ/ የአገልግሎት ጊዜው ሲያበቃ፡፡

2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ በተደነገገው መሠረት ከቦርድ በሚቀርብለት ሃሣብ

መሠረት ወይም የቦርዱ ሃሣብ ባይቀርብም ተገቢ እርምጃ ነው ብሎ ካመነ

እንደአግባቡ ርዕሰ መስተዳድሩ ዲኑን ከሥራ ማሰናበት ይችላል፡፡

3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ መሠረት ቦርዱ ምክትል ዲኖችን ከኃላፊነት

ሊያሰናብት ይችላል፡፡

4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በሦስት ተከታታይ

የክትትል ወይም በአንድ ጥቅል የሥራ አፈፃፀም ግምገማው የዲኑ ወይም የምክትል

ዲኖች በኃላፊነት መቀጠል ተቋሙን ይጐዳል ተብሎ ቦርድ ካመነ እንደአግባብነቱ

ከኃላፊነቱ እንዲሰናበት እርምጃን ሊያስወስድ ይችላል፡፡

ምዕራፍ ሦስት

ስለአካዳሚክ ኮሚሽን

23. ስለአካዳሚክ ኮሚሽን ኃላፊነት

የቦርዱ ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አካዳሚክ ኮሚሽኑ አካዳሚክ ጉዳዮችን በሚመለከት

መሪ አካል በመሆን የሚከተለው ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡

1. የኮሌጁን የትምህርት ዘመን መወሰን፣

Page 14: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

14

2. የኮሌጁን አካዳሚክ ኘሮግራሞችና ሥርዓተ ትምህርቶቻቸውን መወሰን፣ የትምህርት

ክፍሎች የሚሰጡትን ትምህርት እና የሚያካሄዱበትን ምርምር ጥራትና አግባብነት

ለማረጋገጥ እንዲችሉ መመራትና አቅጣጫ ማስያዝ፣

3. የትምህርትና ምርምር ኘሮግራሞችን በሚመለከት የአካዳሚክ ማህበረሰቡ

የሚተዳደርበትን ደንብ ማውጣትና ስለመከበሩም መከታተል፤

4. የዶክትሬት ዲግሪ የሚሰጥበትን ወይም የሚሰረዝበትን ሁኔታዎች መወሰን፤

5. ኮሌጅ አቀፍ የትምህርት አግባብነትና ጥራት ማጐልበቻና የተማሪዎች ምዘና

ሥርዓትን ማውጣት፤

6. በአካዳሚክ ኃላፊነት ስለሚሾሙት ጥያቄ ሲቀርብለት ለዲኑ ምክር መስጠት፤

7. የኘሮፌሰር ማዕረግ ተገቢ ሆኖ ሲያገኘው ደግፎ ለቦርድ ማቅረብና በተባባሪ ኘሮፌሰር

ዕድገት ላይ የመጨረሻውን ውሣኔ መስጠት፤

8. በትምህርት ክፍሎች በሚቀርብ በኘሮፌሰር ደረጃ የሚፈፀም የአዲስ ቅጥር ጥያቄ

ላይ መወሰን፤

9. በዲኑ በሚቀርበው የውሣኔ ሃሣብ መሠረት በተቋሙ እውቅና ሊሰጣቸ የሚገባ ልዩ

አስተዋጽኦ ላስመዘገቡ ሰዎች የክብር ዲግሪ ወይም ሌሎች ሽልማቶችን መስጠት፤

10.በኮሌጁ ሥር ስለሚኖሩት የትምህርት ክፍሎች መከፈት፣ መዝጋት ወይም መዋሃድ

በኮሌጁ ዲን በሚቀርበው የውሣኔ ሃሣብ መሠረት መርምሮ ማጽደቅ፤

11.የትምህርትና ሥልጠና ነክ ጉዳዮችን በማጠናት የመፍትሔ ሃሣብ ለቦርድ ወይም

ለቢሮው ማቅረብ፤

12.የፈተና አሰጣጥ ዘዴና የተማሪዎችን የማለፍና ያለማለፍ ሁኔታዎችን ይወስናል፤

13. የኮሌጁን የተማሪዎች የትምህርትና ሥልጠና ደረጃ አወሳሰን፣ ምረቃን የሚመለከቱ

መመዘኛ መስፈርቶችን ያወጣል፤ በነዚህ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችና

ቅሬታዎችን መርምሮ ውሣኔ ይሰጣል፤

14.የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ያወጣል፤

15.በሌሎች ሕጐች የሚሰጠውን ኃላፊነት ወይም በኮሌጁ ዲን የሚመራለትን ጉዳይ

ያከናውናል፡፡

24.የአካዳሚክ ኮሚሽን አባላት

1. የኮሌጁ የአካዳሚክ ኮሚሽን አባላት ቁጥር በኮሌጁ የትምህርት ክፍሎች ብዛት አኳያ

በቦርድ የሚወሰን ሆኖ የሚከተሉት የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት ናቸው፡፡

Page 15: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

15

ሀ/ የኮሌጁ ዲን - ሰብሣቢ፣

ለ/ የኮሌጁ ምክትል ዲኖች - አባልና አስረጂ፣

ሐ/ የኮሌጁ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ዲን - አባል

መ/የሬጅስትራር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ - አባል

ሠ/ የተማሪዎች ዲን - አባል

ረ/ የትምህርት ክፍሎች የበላይ ተጠሪዎች - አባል

ሰ/ የመምህራን ተወካይ ሁለት / ከወንድና ሴት/ - አባልና ፀሐፊ

ሸ/ የተማሪዎች ካውንስል ተወካይ ሁለት / ከወንድና ሴት/ - አባል

2. የአባላቱ አብላጫው ቁጥር በኮሌጁ ዲን የሚመረጡ ሆኖው ለኃላፊነት የሚመጥኑና

በተቋሙ ውስጥ በተነፃፃሪ ረጅም አገልግሎት ያላቸው የአካዳሚክ ሠራተኞች

ይሆናሉ፡፡

3. ለአፈፃፀም ውጤታማነት ሲባል በአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባልነትና የአባላት ብዛትን

እንዲሁም የሥራ ዘመን ለውጥ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በኮሌጁ ዲን ምክር

መሠረት ቦርዱ ማሻሻያ ማድረግ ይችላል፡፡

25.ስለአካዳሚክ ኮሚሽኑ ሰብሰባዎች

1. የአካዳሚክ ኮሚሽኑ የአባላቱን ዲሲኘሊን ጨምሮ የራሱን መደበኛና አስቸኳይ

ስብሰባዎች በሚያወጣው ደንብ ውስጥ ይወስናል ፣

2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ድንጋጌ ሲጠይቅ ወይም ከአባላቱ አንድ ሦስተኛው

ሲጠይቁ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሄድ ይችላል፡፡

3. ኮሚሽኑ የኮሌጁ ዲን ወይም ቦርዱ ሲጠይቅ ወይም ከአባላቱ አንድ ሦስተኛው

ሲጠይቁ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሄድ ይችላል፡፡

4. ኮሚሽኑ የኮሌጁ ዲን ስብሰባዎች በበቂ ዝግጅት እንዲካሄዱ፣ በተገቢ መንገድ በቃለ

ጉባዔ መዘገባቸውንና መጠበቃቸውን፣ ውሣኔዎች ለሚመለከታቸው በትክክል

መተላለፋቸውንና መተግበራቸውን ያረጋግጣል፡፡

5. ከኮሚሽኑ አባላት ከግማሽ በላይ በስብሰባው ላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል፣

ውሣኔዎቹም በአብላጫ ድምጽ ይሆናል፤ ለውሣኔ የሚሰጡ ድምፆች እኩል ከሆኑ

የሰብሣቢው ድምጽ ወሣኝ ይሆናል፡፡

Page 16: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

16

6. ኮሚሽኑ በኃላፊነቱ መሠረት የትምህርት ክፍሎችን፣ የኮሚቴዎቹንና እንደ አንድ

አካል የራሱን የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል፣ የግምገማው ውጤት በዲኑ አማካኝነት

ለቦርዱ ይቀርባል፡፡

7. ኮሚሽኑ ለሥራው አስፈላጊና አስረጂ የሆኑ ሰዎችን በስብሰባው ሊያሳትፍ ይችላል፡፡

26. ስለኮሌጁ ሬጅስትራር ተግባርና ኃላፊነት

ሬጅስትራሩ ተጠሪነቱ ለኮሌጁ ዲን ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡

1. ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፈ መዘክር/ሪኮርድ/ እንዲኖር ያደርጋል፣ የመመዝገቢያ

ሌሎች አስፈላጊ ቅፃቅፆችን ያዘጋጃል፣

2. የኮርስ ካታሎጐችን ያዘጋጃል፤ በአካዳሚክ ኮሚሽኑ ሲፈቀድ ሥራ ላይ ያውላል፤

3. የዓመቱን የአካዳሚክ ካላንደር ያዘጋጃል፤ እንደአስፈላጊነቱ በየሴሚስተሩ መጨረሻ

ለቀጣይ ሴሚስተር የሚሆን ኮርስ በአካዳሚክ ኮሚሽን ያስወስናል፣ ያስፈጽማል፤

4. የተማሪዎች ውጤት በአካዳሚክ ካሌንደሩ መሠረት አጠናቅሮ ለኮሚሽኑ ውሣኔ

ያቀርባል፣ ለሰልጣኞች ውጤታቸውን ይሰጣል፣ የወደቁና የሚመረቁ ሰልጣኞችን

በመለየት ለሚመለከታቸው አካላት በወቅቱ ያስተላልፋል፤

5. የተማሪዎችን ስታስቲካዊ መረጃ ለኮሌጁ የሥራ ክፍሎችና ለበላይ አካላት በወቅቱ

ያሰራጫል፤

6. የተመረቁና ተሸላሚ ተማሪዎችን ስም ዝርዝር ለኮሚሽኑ አቅርቦ ያስወስናል፤

7. በተለያዩ ትምህርት ስልጠና መርሃ ግብሮች፣ የሰልጣኞች አመዘጋገብ፣ ሪኮርድ

አያያዝና ግንኙነት አመቺ ሁኔታ ይቀይሳል፤

8. የየኘሮግራሙን ሰልጣኞች ይመዘግባል፣ ያስመርቃል፣ ኮሌጁን ሲለቁ ማንኛውም

በተገቢው ጊዜ ይሰጣል፤

9. ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትና በዲኑ የሚመሩለትን ሥራዎች ያከናውናል፡፡

ክፍል ሦስት

ስለሌሎች የኮሌጁ አካላት መብትና ግዴታ

ምዕራፍ አንድ

ስለኮሌጁ ተማሪዎች

27. የኮሌጁ ተማሪዎች መብት

1. የዚህ ደንብ ሌሎች ድንጋጌዎችና አግባብነት ያላቸው ሌሎች ሕጐች እንደተጠበቁ

ሆነው የኮሌጁ ተማሪዎች የሚከተሉት መብቶች ይኖራቸዋል፡፡

Page 17: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

17

ሀ/ በመመራመር እውነትን የመፈለግና ሃሣብን በነፃነት የመግለጽ፤

ለ/ በመማሪያ ክፍል፣ በተቋም ጊቢና በሕብረተሰቡ ውስጥ ለመማር አመቺ ሁኔታን

የማግኘትና የመጠቀም፤

ሐ/ በኮሌጁ ውስጥ ሰብዓዊ መብታቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ የመኖርና የግል

ንብረታቸውን ደህንነት የማስጠበቅ፤

መ/በኮሌጁ ጉዳዮች ላይ በሕጋዊና ሰላማዊ አግባብ አቋማቸውን በነፃነት የማራመድ፤

ሠ/ ማንኛውም ዓይነት አድልዎና ትንኮሣ እንዳይደርስባቸው ሕጋዊ ከለላን

የማግኘት፤

ረ/ ለማንኛውም የመምህርና ተማሪ ግንኙነት ገጽታዎች የፍትሐዊነት ተጠቃሚ

የመሆንና ለመማር የሚያነሳሳ መልካም ተቋማዊ ድባብን የማግኘት፤

ሰ/ በኮሌጁ ንብረት የመጠቀም፤

ሸ/ ስለአካዳሚያዊ ብቃታቸው በዚህ ደንብ በተደነገጉ መርሆዎችና በኮሌጁ አካዳሚክ

መመዘኛዎች መሠረት የመመዘን፤ ኢፍትሐዊ ምዘና ሲፈፀም ቅሬታን በተቋሙ

ሥርዓት መሠረት በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ የማቅረብና ፍትህ የማግኘት፤

ቀ/ ግልጽነት ባለው ሥርዓት በአካዳሚክ ሠራተኞች የሥራ አፈፃፀምና በአካዳሚክ

ኘሮግራሞች አፈፃፀም ግምገማ ላይ የመሳተፍ፤

በ/ የግል ትምህርት ማህደራቸውና መረጃዎች ሚስጥር ለመጠበቅ የሚያስችል

ሥርዓት ተጠቃሚ የመሆን፤

ተ/ በሕግ አግባብ በተቋቋሙ የተማሪዎች ሕብረት ውስጥ የመሳተፍ እና በኮሌጁ

መገልገያዎች የመጠቀም፤

ቸ/ ኮሌጁ ሥርዓተ ትምህርት ሲያዘጋጅ ወይም ሲከልስ እና ሥራ ላይ ሲያውል

አስተያየት የመስጠት መብት፤

ኃ/ በኮሌጁ ውስጥ የመገናኛ ዘዴዎችን የመጠቀም፤

ነ/ በዚህ ደንብ መሠረት የወጪ መጋራት ሥርዓት ተጠቃሚ የመሆንና የምክር

አገልግሎት የማግኘት፤

28. ስለኮሌጁ ተማሪዎች ግዴታ

1. የዚህ ደንብ ሌሎች ድንጋጌዎችና አግባብነት ያላቸው ሕጐች ተፈፃሚነት እንደጠበቀ

ሆኖ ማንኛውም የኮሌጁ ተማሪ የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩበታል፤

Page 18: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

18

ሀ/ በክፍል የመገኘትና ትምህርቱን በሚገባ የመከታተል፣ የማንኛውም አካዳሚክ

ሠራተኛ የመማር ማስተማር ሂደቱን የመምራትና የመቆጣጠር ሥልጣንን

የማክበር፤

ለ/ በተመዘገበበት ትምህርት የተቀመጡ የብቃት መመዘኛዎችን የማሟላት፤

ሐ/ የኮሌጁን ዓላማዎችንና የተቋሙን መሪ እሴቶች የማወቅና የማራመድ፤

መ/በክፍል ውስጥም ሆነ በተቋሙ ግቢ ውስጥ በሕግ የተጠበቀውን የሌሎች ሰዎችን

መብት የማክበር፤

ሠ/ አግባብነት ያላቸውን ሕጐች እንደዚሁም በዚህ ደንብ ድንጋጌዎች ላይ

የተመሠረቱትን የኮሌጁን መመሪያዎችና ደንቦች የማክበር፤

ረ/ ከማንኛውም ሕገ-ወጥ ድርጊት እና ከማንኛውም ከሥነ ምግባር ውጭ ከሆኑ

ተግባራት የመቆጠብ፤

ሰ/ የግልም ሆነ የጋራ የተማሪ ጥቅሞች አደጋ ላይ የሚወድቁበት ጊዜ በሠላማዊና

በሕጋዊ መንገድ ቅሬታን በማሰማት መፍትሔን የመሻት፤

ሸ/ የኮሌጁን ንብረት በጥንቃቄ የመያዘና የመጠቀም፣ ሆን ተብሎ ወይም

በቸልተኝነት ምክንያት በተቋሙ ንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ተጠያቂ የመሆን፣

ቀ/ በዚህ ደንብ ድንጋጌዎች መሠረት ተቋሙ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች መከፈል

የሚገባውን ክፍያ የመፈፀም፡፡

2. ኮሌጁ የተማሪዎች የሥነ-ምግባር ደንብና የዲስኘሊን እርምጃ ለመውሰድ የማያስችል

ተገቢ ሥርዓት የማውጣት ግዴታ አለበት፡፡

29. የተማሪዎች ቅበላ

1. ኮሌጁ በዶክትሬት ዲግሪ ለሚሰጠው ትምህርት በጤና መስክና በተዛማጅ ዘርፎች

ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸውና በሚኒስቴሩ ደንብ መሠረት አስፈላጊውን

መመዘኛ የሚያሟሉ ይሆናል፡፡

2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ እንደተጠበቀ ሆኖ የመግቢያ ፈተና ሊዘጋጅ

ይችላል፡፡

3. ከዚህ በላይ በንዑስ /1/ እና /2/ ላይ የተደነገገው ቢኖርም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት መስፈርት መሠረት ተማሪዎችን

ተቀብሎ ማሰልጠን ይችላል፡፡

Page 19: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

19

30. ስለኮሌጁ ሠራተኞች

ኮሌጅ፡-

ሀ/ የአካዳሚክ ሠራተኛ፣

ለ/ የአስተዳደርና የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ይኖሩታል፡፡

31. የአካዳሚክ ሠራተኛ መብት

1. ማንኛውም የኮሌጁ አካዳሚክ ሠራተኛ በሌሎች አግባብነት ባላቸው ሕጐችና የዚህ

ደንብ ሌሎች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው የሚከተሉትን መብቶች ይኖሩታል፡፡

ሀ/ በኮሌጁ ተልዕኮ መሠረት የአካዳሚክ ነፃነትን የመጠቀም፣

ለ/ በኮሌጁ የውስጥ ደንብና መመሪያዎች መሠረት ምርምር የማካሄድና ሙያዊ

የምክር አገልግሎት የመስጠት፤ እንዲሁም በኮሌጁ ደንብና መመሪያ መሠረት

የምርምር እረፍቶችን በመውሰድ ለሀገር ጠቃሚ የሆነ ምርምሮችና ጥናቶች

ማካሄድ፤

ሐ/ የውስጥ ደንብና መመሪያ መሠረት ሙያውን የሚያዳብር በሀገር ውስጥና

በውጭ ሀገር ትምህርትና ስልጠና የማግኝት፤

መ/በኮሌጁ የውስጥ ደንብና መመሪያ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ በሚኒስቴሩ

በሚወጣ ሀገራዊ መስፈርት መሠረት የሙያ ዕድገትን የማግኘት፤

ሠ/ በኮሌጁ አቅም ላይ የተመሠረተ ደመወዝና ጥቅማጥቅም የማግኘት፤

ረ/ በኮሌጁ የትኩረት አቅጣጫ፣ ዕቅድ፣ የውስጥ ደንብና መመሪያዎች ዝግጅትና

የሥርዓተ ትምህርት ቀረፃ ላይ እንደአመቺነቱ የመሳተፍና በመማር ማስተማር

ሂደት አግባብነትና ጥረት ላይ አስተያየት የመስጠት.

ሰ/ የግል ማህደሩን፣ ስለሥራ አፈፃፀሙ የተደረገ የግምገማ ውጤትን የማወቅና

ሚስጠሮቹ ከሕግ አግባብ ውጪ እንዳይገለጥበት የማድረግ፤

በ/ በኮሌጁ ዕቅድ፣ ዕድገት፣ የትኩረት አቅጣጫ፣ ሁኔታና የክንውን ውጤቶች

መረጃ የማግኘት፤

Page 20: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

20

ተ/ በዲሲኘሊን ጉዳይ የመሰማት ዕድል የማግኘትና ተገቢ ያልሆነ ውሣኔ

እንዲነሳለት የመጠየቅና ፍትህን የማግኘት፤

2. ኮሌጁ የአካዳሚክ ሠራተኞቹን በሚመለከቱ የመብት ጉዳዮች ላይ በአሳታፊ ሂደት

ላይ የውስጥ ደንብና የአፈፃፀም ሥርዓትን የመቅረጽና ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት

አለበት፤

32. የአካዳሚክ ሠራተኛ ግዴታ

1. የዚህ ደንብና በሌሎች አግባብነት ባላቸው ሕጐች የተደነገጉ ድንጋጌዎች እንደተጠበቀ

ሆኖ የኮሌጁ አካዳሚክ ሠራተኛ የሚከተሉትን ግዴታዎች ይኖሩበታል፡፡

ሀ/ መላ ዕውቀቱንና ክህሎቱን ለሠልጣኞች የማድረስ ወይም የማስተላለፍ፣

ለ/ ልዩ ድጋፍ ለማያስፈልጋቸው ተማሪዎች ልዩ ድጋፍ ማድረግን ጨምሮ

የአካዳሚክ ምክር አገልግሎትና የሕብረተሰብ አገልግሎት የመስጠት፤

ሐ/ በራሱ የሙያ መስክ ችግር ፈቺና ለሀገር ጠቃሚ የሆነ ምርምር የማካሄድ፣

ዕውቀትና ክህሎትን የማሸጋገር፣ የሚያስተምረውን ትምህርት በጥናትና ምርምር

ላይ የተመሠረተ የማድረግና በየጊዜው የማሻሻል፣

መ/በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ተማሪዎች በሚዛናዊነት የማስተናገድ ሙያዊ

ሥነ ምግባርን በተላበሰ ሁኔታ ሙያዊ ብቃትን የማረጋገጥ፣

ሠ/ ኮሌጁ የሚመራባቸውን እሴቶች የማክበር፣ የመተግበርና አካዳሚክ ነፃነቱን

በሙያዊ ሥነ ምግባር እና አግባብ ባላቸው የዚህ ደንብ ድንጋጌዎች የመጠቀም፤

ረ/ ሙሉ የሥራ ጊዜውን ለኮሌጁ የማዋል፤

ሰ/ በመማር ማስተማር ሂደት የራስን የፖለቲካ አመለካከት ወይም ሐይማኖት

በተማሪዎች አመለካከት ላይ ከመጫን የመቆጠብ፤

ሸ/ ኮሌጁ በዚህ ደንብና በአካዳሚክ ኮሚሽኑ ደንብ መሠረት የሚሰጡትን ሌሎች

ተግባራት የማከናወን፤

በ/ ከሌላ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ጋር አስቀድሞ በሚደረግ ስምምነት መሠረት

የአካዳሚክ ሠራተኛን በጋራ ስለመቅጠር በዚህ ደንብ የተደነገገው እንደተጠበቀ

ሆኖ፣ ሙሉ ኃይሉን፣ የሥራ ጊዜውንና ትኩረቱን ለኮሌጁ የማዋል፣

ተ/ የኮሌጁ የጤና ባለሙያ የሆኑ የአካዳሚክ ሠራተኞች በኮሌጅ የማስተማሪያ

ሆስፒታል ውስጥ በሙያቸው ተገቢውን አገልግሎት የመስጠት፤፡

Page 21: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

21

33. አካዳሚ ሠራተኛን በጋራ ስለመቅጠር

1. አካዳሚክ ሠራተኛን በጋራ መቅጠር ተፈፃሚ የሚሆነው የትምህርት አግባብነትንና

ጥረትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የአካዳሚክ ሠራተኛ እጥረት ሲገጥም

እንደመልካም መፍትሔ ሆኖ ሲገኝ ነው የጋራ ቅጥር ተግባራዊ ሲደረግ ከሌሎች

ተቋማት ወይም የምርምር ማዕከሎች ለጋራ ጥቅም የሚያበቃ ሙያዊ አቅም

ያለውን ባለሙያ የሚመለከት ይሆናል፡፡

2. አንድ አካዳሚክ ሠራተኛ ወይም መንግሥት ሠራተኛ አቅሙ ካለው በራሱ ፈቃድ

የሆኑ አካዳሚክ ሠራተኞችን የጋራ ቅጥር የሚመለከቱ አግባብነት ያላቸው ሌሎች

ሕጐች እንደተጠበቁ ሆነው የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የመተባበር ግዴታ

ይኖርባቸዋል፡፡

3. የቅጥሩ ሁኔታ፣ ቅጥሩ የሚቆይበት ጊዜ፣ ደመወዝና ሌላ ጥቅማ ጥቅሞችን

እንዲከውኑ የሚፈለጉ ተግባራትና ጊዜን ማደላደል የመሳሰሉት ለተቀጣሪውና ደንብና

ሥርዓት መሠረት ይወሰናሉ፡፡

4. የጋራ ቅጥር የሚመለከቱ ድንጋጌዎች የግል ተቋማትን አይመለከትም፡፡

34. የአስተዳደርና የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች መብትና ግዴታ

1. የኮሌጁ የአስተዳደርና የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ሕግ

መሠረት ይተዳደራሉ፡፡

2. የኮሌጁ ቦርድ አግባብ ባለው የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መርሆዎች ላይ

በመመስረትና የተቋሙን አቀም በማገናዘብ የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች አሰተዳደር

ዝርዝር መመሪያን ማውጣት ይችላል፡፡

3. ማንኛውም የኮሌጁ የአስተዳደርና የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኛ አግባብነት ላላቸው

ሕጐችና የተቋሙ መመሪያዎች የመገዛትና በተግባርም የከፍተኛ ትምህርት

ዓላማዎችንና የተቋሙን መሪ እሴቶች የማክበር ግዴታ አለባቸው፡፡

ምዕራፍ ሁለት

ስለኮሌጁ ሆስፒታል

35. የኮሌጁ ሆስፒታል

1. ኮሌጁ የይርጋዓለም ሆስፒታልን ለተግባር ልምምድ ያለማንም ከልካይነት

ይጠቀምበታል፡፡

Page 22: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

22

2. አካዳሚክን በተመለከተ የተግባር ልምምድን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ

ዝርዝር መመሪያዎችን ቦርዱ ያወጣል፣

3. የይርጋዓለም ሆስፒታል መደበኛ ሥራዎችና አስተዳደር ቀደም ሲል በነበረው

አኳኋን የሚመራ ይሆናል፡፡

4. የኮሌጁ አካደሚክ ሠራተኞች የጤና አገልግሎት በሆስፒታሉ መስጠት በሚችሉበት

ሁኔታ ላይ ቢሮው መመሪያ ሊያወጣ ይችላል፡፡

5. ኮሌጁ እንደአስፈላጊነቱ ሌሎች ሆስፒታሎችንና የሕክምና ምርምር ማዕከሎችን

የማቋቋምና የማስፋፋት መብት ይኖረዋል፡፡

ክፍል አራት

ምዕራፍ አንድ

ስለአስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር

36.የጤና ቢሮ ስልጣንና ተግባር

1. ቢሮው በዚህ ደንብና በሌሎች ሕጐች ድንጋጌዎች የሰጠው ኃላፊነት እንደተጠበቀ

ሆኖ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡

ሀ/ ኮሌጁ የሀገሪቱን ብሎም የክልሉን የጤናውን ዘርፍ የትኩረት አቅጣጫ ተክተሎ

መጓዝን የማረጋገጥ፤

ለ/ የኮሌጁ ቦርድ ሰብሣቢና ሌሎች የቦርድ አባላትን እንዲየሰሙ በእጩነት

የማቅረብና የማሰወሰን፣

ሐ/ ኮሌጁ የሚያቋቁማቸው የጤና አገልግሎት መስጫና የምርምር ማዕከሎች ሁኔታ

የመገምገም፤

መ/በክልሉ ያለውን የከፍተኛ ሕክምና ባለሙያ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ

ዘዴዎችን በመቀየስ ከኮሌጁ ጋር ተባብሮ የመስራት፤

ሠ/ ኮሌጁ ዓላማውን ለማሳካት የሚያስችል አደረጃጀት እንዲኖራቸውና ሌሎች

አስፈላጊ ተግባራትን የማከናወን ተግባራት ይኖሩታል፡፡

2. የኮሌጁ የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት ካሪኩለም፣ የአካዳሚክ ደረጃ እና የጥራት

መመዘኛዎችን በተመለከተ በትምህርት ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ መመዘኛዎች

መሠረት የሚተገበር ሲሆን በዚህ ረገድ ክትትልና ግምገማውም በሚኒስቴሩ

ይሆናል፡፡

Page 23: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

23

ምዕራፍ ሁለት

ስለኮሌጁ በጀት፣ የገንዘብ አስተዳደርና ኦዲት

37. የኮሌጁ በጀት

1. ኮሌጁ በጀቱ በክልሉ መንግሥት የሚመደብለት ሲሆን በአደረጃጀቱም በስትራቴጂክ

ዕቅድ ስምምነት ላይ በተመሠረተ የጥቅል በጀት ሥርዓት መሠረት ይሆናል፡፡

2. በጀቱ የአምስት ዓመት ጠቋሚ ጥቅል በጀት ሲሆን በየዓመቱ እየተገመገመ

የሚስተካከል ይሆናል፡፡

3. ኮሌጁ የገንዘብ ፍላጐቱን ለማሟላት በዚህ ደንብ መሠረትና በሌሎች ሕጐች

ከተፈቀዱ ሌሎች ምንጮች ገቢዎችን ማሰባሰብ ይችላል፡፡

4. ኮሌጁ የጥቅል በጀት አሠራር ተጠቃሚ ለመሆንና አስተዳደሩን በአግባቡ ለመምራት

ይችል ዘንድ የገንዘብ መረጃዎችን የሚያስተዳድርበትን አቀም መገንባት ይኖርበታል፡፡

5. የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኮሌጁ የዚህን አንቀጽ ድንጋጌዎች ተግባራዊ

ለማድረግ እንዲችል ተገቢውን እገዛ ያደርጋል፡፡

6. ኮሌጁ ከሦስተኛ ወገኖች ስጦታዎችን መቀበል ይችላል፤ ሆኖም የሚያገኘው ስጦታ

ከተቋሙ አቋም ተልዕኮና ዓላማ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የማይኖረው መሆን

ይኖርበታል፤

7. ኮሌጁ ከሦስተኛ ወገን ስለሚያገኘው ገንዘብና ኢንቨስትመንት፣ ስለሚያገኘው ገቢ

ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ፣ ለቢሮውና ለሚመለከተው አካል የማሳወቅ ግዴታ

አለበት፡፡

38.የድጐማ በጀት

1. ኮሌጁ በአገልግሎት ላይ ያልዋለ የቀዳሚው ዓመት ጥቅል በጀት የተቋሙ ድጐማ

በጀት ሆኖ ወደሚቀጥለው የበጀት ዓመት እንዲተላለፍና ለተቋሙ አገልግሎት

እንዲውል ሊደረግ ይችላል፡፡

2. ኮሌጅ የድጐማ በጀትን በካፒታል በጀት መልክ ብቻ ይጠቀምበታል፡፡

3. የድጐማ በጀት ከዓመቱ ጥቅል በጀትና ከተቋሙ ገቢ ከሚገኘው ገንዘብ ጋር

እንደተቋሙ አጠቃላይ ዓመታዊ በጀት በቦርዱ የሚፀድቅ ይሆናል፡፡

Page 24: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

24

39. የገንዘብ አስተዳደር

1. የኮለጁ ዲን የተቋሙን የገንዘብ ጉዳይ በሕግ፣ በቅልጥፍና፣ በውጤታነት፣ በቁጠባና

በግልጽነት መርሆዎች ላይ ተመስርቶ የመምራትና የማስተዳደር ኃላፊነትና

ተጠያቂነት ይኖርበታል፡፡

2. ሕግ በሌላ ሁኔታ ያስቀመጣቸውን በጀትን አስቀድሞ በቦርድ ማጽደቅ አሠራር

እንደተጠበቀ ሆኖ በፀደቀለት የሥራ ዕቅድ መሠረት ገቢውን በነፃነት የመጠቀም

መብት ይኖረዋል፡፡

3. በጀት ባልፀደቀበት ወቅት ቦርድ በጀቱን እስኪያፀድቀው ድረስ የኮሌጁ ዲን የተቋሙ

መደበኛ ሥራ እንዳይስተጓጐል በቀዳሚው የበጀት ዘመን አሠራርና መጠን መሠረት

ወጪ እንዲያደርግ ለቦርድ ስልጣን ሊሰጠው ይችላል፡፡

40.ገቢን ስለማግኘት

ኮሌጁ የሚከተሉት የገቢ ምንጮች ሊኖሩት ይችላል፡፡

ሀ/ ኮሌጅ ከሚሰጠው አገልግሎት ወይም ከሚያከናውነው ሥራ የሚገኝ ገቢ፣

ለ/ የኮሌጁ ሠራተኞች በፈቃደኝነት ከሚያደርጉት መዋጮ፤

ሐ/ ለኮሌጁ ከሚሰጡ ስጦታዎችና እርዳታዎች፤

መ/ ከሌሎች ሕጋዊ የገቢ ምንጮች

41. የገቢ ፈንድ

1. ኮሌጁ በቦርዱ አስወስኖ በቢሮ ሲፀድቅ የገቢ ፈንድ ማቋቋም ይችላል፤

2. የፈንዱ የገቢ ምንጮች የሚከተሉት ይሆናሉ፤

ሀ/ በኮሌጅ የገቢ ማስገኛ ድርጅቶች የሚደረግለት መዋጮ፤

ለ/ በበጀት ዓመቱ ሥራ ላይ ያልዋለ የፈንዱ ገንዘብ፤

ሐ/ ስጦታዎች እና ሌሎች ሕጋዊ የገንዘብ ምንጮች፡፡

3. ፈንዱ ቦርድ በሚያፀድቀው መሠረት ለኮሌጁ ልዩ ልዩ የአቅም ግንባታ ተግባራት፣

ለሽልማትና ለሌሎች ተግባራት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡

4. የፈንዱ አጠቃቀም የበጀት ሥርዓትን የተከተለ ይሆናል፡፡

42. ሪፖርት ስለማቅረብና ቁጥጥር

1. ኮሌጁ

ሀ/ በስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ በመመስረት በአግባቡ ተመዝኖ የፀደቀውን ዓመታዊ

የአፈፃፀም ሪፖርትና በኦዲተር የተመረመረ የሂሣብ ሪፖርት እንደአግባብነቱ

Page 25: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

25

ለቢሮው ወይም ለሚመለከታቸው የክልል አካላት ማቅረብና የበጀት ዓመቱ

ትምህርታዊና ሌሎች መረጃዎችን የማሳተም፣

ለ/ በማናቸውም ጊዜ በሚኒስቴሩ ወይም በሚመለከተው የክልል አካል የሚጠየቀውን

መረጃ መስጠት ይኖርበታል፡፡

2. ኮሌጅ እንደአግባብነቱ በሚኒስቴሩ ወይም በሚመለከተው የክልል አካል ሕግንና

የስትራቴጂክ ዕቅድ ስምምነቱን ማክበሩን ለማረጋገጥ ቁጥጥር ሊደረግበት ይችላል፡፡

3. እንደአግባብነቱ ሚኒስቴሩ ወይም ቢሮው ከሕግ፣ ከመንግሥት ፖሊሲ፣ ከኮሌጁ

ተልዕኮ ወይም ደንቦች ጋር የሚጋጩ የቦርድ፣ የዲን ወይም የአካዳሚክ ኮሚሽን

ውሣኔዎችን ሊሽር ይችላል፡፡

43. የሂሣብ መዛግብት

1. ኮሌጁ በዲኑ ኃላፊነትና አስተዳደር ሥር የሚመራ የተቋሙ ግዴታዎችንም ታሣቢ

ያደረገ የገቢና የወጪ ሂሣብን ጨምሮ አግባብነት ያለው የሂሣብ አያያዝና ሪፖርት

የማቅረቢያ ሥርዓትን መዘርጋት ይኖርበታል፤

2. ኮሌጁ የደብል ኢንትሪ ሂሣብ አያያዝን የመከተል፣ ተቀጽላ የሆኑ ተግባራት ገቢና

ወጪዎችን ከሌሎች ገቢዎችና ወጪዎች ለይቶ የመያዝ እና ለሁሉም የገቢና

ወጪ ጉዳዮች የሂሣብ አያያዝ አጠቃላይ ሥርዓትን የመከተል ግዴታዎች

ይኖረታል፡፡

3. ኮሌጁ የተቋሙን ሃብትንና እዳን ለመለካት ቀለል ያለ የመመዘኛና የኦዲት ሥርዓት

ለመጠቀም የሚያስችሉ የሂሣብ አያያዝና ሪፖርት አቀራረብ መመሪያዎች መሠረት

የሂሣብ መዛግብቱን ያደራጃል፡፡

44. ኦዲት

1. በኮሌጁ ውስጥ ራሱን የቻለና ለዲኑ ተጠሪ የሆነ የውስጥ ኦዲት ያቋቁማል፤

2. የኮሌጁ የውስጥ ኦዲት ክፍል ኃላፊ በዲኑ አቅራቢነት በቦርድ ይሰየማል፤

3. የውስጥ ኦዲት የኮሌጁን የአፈፃፀም፣ የፋይናንስና ንብረት ኦዲት አከናውኖ ለዲኑና

ለቦርድ ያቀርባል፣

4. የክልሉ ዋና ኦዲተር ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የኮሌጁ ሂሣብ በቦርድ በተሰየመ

የውጭ ኦዲተር በየዓመቱ ተመርምሮ ውጤቱ ለዲኑ፣ ለቦርዱና እንደአግባብነቱ

ለሚመለከተው የክልል አካል መቅረብ ይኖርበታል፡፡

Page 26: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

26

ክፍል አምስት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

45. የአገልግሎት ክፍያዎች

ኮሌጁ ለትምህርት አገልግሎቶች ክፍያ መጠየቅ ይችላል፤ የሚጠየቀው ክፍያ ዓይነት፣

መጠንና የክፍያ አፈፃፀም አግባብ በዚህ ደንብ ሌሎች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው

ቦርድ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡

46. ወጪ መጋራት

በኮሌጁ የሚሰጠውን ሥልጠና ተከታትለው የሚጨርሱ ሰልጣኞች በሙሉ የትምህርቱን

ወጪ በአገልግሎት ብቻ እንዲሸፍኑት ይደረጋል፡፡ ለዚህም ማረጋገጫ የውል ግዴታ

መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡

47. አገልግሎት በሌሎች ወገኖች እንዲሰጥ ስለማድረግ

1. ኮሌጁ ተገቢና ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል ሆኖ ሲያገኘው የድጋፍ ሰጪ

አገልግሎቶችን በሌሎች አገልግሎት አቅራቢዎች እንዲሰጥ ሊያደርግ ይችላል፤

2. ኮሌጅ አገልግሎት በሌሎች አቀራቢዎች እንዲሰጥ ሲያደርግ የአገልግሎቱ

ተጠቃሚዎች ለዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ አገልግሎት ለማግኘት መቻላቸውን

ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

48. የመማሪያ ሕንፃዎችና ቁሳቁሶች በተመለከተ

1. የሀዋሣ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ይርጋዓለም ቅርንጫፍ የማስተማሪያ ሕንፃና ንብረት

በዚህ ደንብ ለተቋቋመው የይርጋዓለም ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተላልፏል፡፡

2. የንብረት ርክክቡ አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ይፈፀማል፡፡

49. መመሪያ የማውጣት ሥልጣን

1. ቢሮው /ቦርዱ/ ይህን ደንብ ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ መመሪያዎች ሊያወጣ

ይችላል፡፡

2. የኮሌጁ ቦርዱ ይህን ደንብና በዚህ ደንብ ተለይቶ በተሰጠው ጉዳዮች ላይ ለማስፈፀም

ሚያስፈልጉ የውስጥ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል፡፡

50. የተሻሩ ሕጐች

ከዚህ ደንብ ጋር የሚቃረኑ ማንኛውም ሕጐች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች ወይም የአሠራር

ልምዶች ተፈፃሚነት አይኖራቸውም፡፡

Page 27: ydb#B B/@éC½ B/@rsïC ?ZïC KLላዊ mNGሥT db#B nU¶T Uz@È...1 ydb#b b/@éc½ b/@rsïc ?zïc klላዊmngሥt db#b nu¶t uz@È debub negarit gazeta of the southern nations,

27

51. ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ

ይህ ደንብ በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ከፀደቀበት ከጥር 5 ቀን 2003 ዓ/ም ጀምሮ

የፀና ይሆናል፡፡

ጥር 2 ቀን 2003 ዓ.ም.

ሽፈራው ሽጉጤ

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት

ርዕሰ መስተዳድር