Upload
others
View
72
Download
0
Embed Size (px)
Citation preview
1
እ.ኤ.አ ከኦክቶበር 1 እስከ ኖቬምበር 30/2017 የነበረው የአየር ጠባይ ግምገማና በቀሪዎቹ የበጋ ወራት የሚኖረው የአየር ጠባይ አዝማሚያ አጠቃላይ ለዘንድሮው በጋ የአየር ጠባይ ትንበያ በተሰጠበት ወቅት! የትሮፒካል ፓስፊክ
የመካከለኛውና የምሥራቅ ክፍል የባህር ወለል ሙቀት ከመደበኛው በታች እየቀዘቀዘ
የመታየት ሁኔታ በሂደት እየተጠናከረ በመሄድ በበጋው ወቅት የቅዝቃዜ መጠኑ ከ55-60%
በመድረስ በመጠኑ ከመደበኛው በታች መቀዝቀዝ (Weak La Nina) ተጽእኖ ስር የመሆን
እድሉ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ግንዛቤ ተወስዶበታል$ በተጨማሪም የምዕራብ እና
ምሥራቃዊው ህንድ ውቅያኖስ የባህር ወለል ሙቀት ከመደበኛው ጋር በተቀራረበ (Near-
neutral) ሁኔታ በበጋው ወቅትም በተመሳሳይ ሁኔታ ሊቀጥል እንደሚችል መጠበቅ!
ከተጠቀሱት ሁኔታዎች ጋር ተዳምሮ የሚፈጠሩት የከባቢው አየር (Atmospheric
conditions) በአብዛኛው የሀገሪቱ ሥፍራዎች ላይ የበጋው ደረቅ" ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር
ጠባይ እንዲያመዝን እና በመደበኛ ሁኔታ የተሻለ ዝናብ የሚያገኙት የሀሪቱ ክፍሎችም ላይ
ከመደበኛው በታች ዝናብ እንዲኖር ሊያደርግ እንደሚችል መጠቆሙ ይታወሳል። ከዚህም
ሌላ ከደመና ሽፋን መቀነስ ጋር ተያይዞ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ሊጠናከር እንደሚችል
ትንበያ ተሰጥቶ ነበር። በዚህ መሰረት በብዙ ቦታዎች በተለይም በደጋማ የሀገሪቱ ሥፍራዎች
ላይ ከ5 ዲግሪ ሼልስየስ በታች የደረሰ ቅዝቃዜ እንደተመዘገበ መረጃዎች ያሳያሉ። የዘንድሮው
የቅዝቃዜ መጠን ካለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር የቅዝቃዜ መጠኑ የተሻለ
እንደነበር መረዳት ይቻላል። በተጨማሪም ባለፉት ሁለት ወራት የደቡብ አጋማሽ የሀገሪቱ
ክፍሎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ አግኝተዋል።
በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ባለፉት ሁለት የበጋ ወራት የነበረው የአየር ጠባይ ግምገማና
በቀሪዎቹ ወራት ሊኖር የሚችለው የአየር ጠባይ አዝማሚያ እንዲሁም በግብርናው ሴክተር
ላይ አሳድሮ የነበረውና ወደፊትም ሊፈጥር በሚችለው ተፅእኖ ላይ የዳሰሳ ጽሁፍ ይቀርባል።
2
እ.ኤ.አ. ከኦክቶበር 1 እስከ ኖቨምበር 30/2017 የነበረው የአየር ጠባይ ግምገማ
ባለፈው የኦክቶበር ወር በመካከለኛው፣ በሰሜንና በምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ
በአብዛኛው የበጋው ደረቃማው የአየር ሁኔታ አመዝናባቸው የቆየ ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር
ተያይዞም በተለይም በጥቂት ሥፍራዎች ላይ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ እንደጨመረ
ይታያል፡፡ በዚህም መሰረት ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች በተለያዩ ቀናት ከመዘገቡ ጣቢያዎች
መካከል በቡኢ 4.6" 4.5 እና 4.0፤ በደብረ ብርሃን 4.0 እና 3.6፤ በወገል ጤና 2.4 እና
1.7፤ በአምባ ማሪያም 4.5 እና 2.5 እንዲሁም በመሐል ሜዳ 3.0 በዲግሪ ሴልሽየስ
ይገኙበታል፡፡ በሌላ በኩል በወሩ ውስጥ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ
መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ የነበረ ሲሆን፤ በአንዳንድ ሥፍራዎች ላይም ከባድ መጠን
ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ ከባድ ዝናብ ከመዘገቡ ጣቢያዎች መካከል በአቦቦ 49.2፣
በላይበር 38.9፣ በአርጆ 36.4፣ በዲላ 34.7፣ በአይከል 30.1፣ በቦሬ 30.0. በጅንካ 51.3"
በቡለን 51.1 እና 30.6" በሻውራ 32.2" በግምቢ 43.9" በማጂ 50.0 እና 33.6"
በሊሙገነት 38.6" oጨዋቃ 55.4" oኢጃጂ 33.2" በበደሌ 34.8" በጭራ 38.9፣
በቀብሪደሀር 50.0፣ በሐገረ ማርያም 48.7፣ በአይራ 46.2፣ በጋምቤላ 45.6፣ በማይፀምሪ
42.7፣ በጂማ 33.5፣ በዳንግላ 32.4፣ በፓዌ 33.4፣ በሞጣ 33.8፣ በሴሩ 32.5፣ በፉኚዶ 31.5፣
በኮንሶ 30.5፣ እንዲሁም በተርጫ 30.2፣ በሚ.ሜ. ይገኙበታል።
ባለፈው የኖቨምበር ወር በአብዛኛው የሀገሪቱ ቦታዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሓያማና
ነፋሻማ የአየር ጠባይ አመዝኖ የቆየ ሲሆን፤ በተጨማሪም በመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት
ከተጠናከሩ ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በቦታ ሥርጭትም ሆነ በመጠን የተስፋፋ
ዝናብ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ ምሥራቅና በምዕራብ ኢትዮዽያ ላይ የተመዘገበ
ሲሆን፤ በጥቂት ቦታዎችም ላይ ከባድ ዝናብ ተስተውሏል፡፡ ለመጥቀስም ያህል በምዕራብ
አባያ 106.0፣ በሞያሌ 69.7፣ በቦሬ 39.4፣ በአዴት 43.2፣ በአቦቦ 39.5፣ በሀገረማርያም
63.6፣ እና በዶሎመና 47.3 በሚ.ሜ ይገኙበታል፡፡ በሌላ በኩል የሌሊትና የማለዳው ቅዝቃዜ
በመጀመሪያው አስር ቀናት ከነበረው የደመና ሽፋንና ዝናብ ጋር ተያይዞ እምብዛም
ያልተጠናከረ ቢሆንም፤ በሁለተኛውና በሶስተኛው አሥር ቀናት ግን ከደመና ሽፋን መቀነሰ
ጋር ተያይዞ የማለዳውና የሌሊቱ ቅዝቃዜ ተጠናክሮ የቀጠለ በመሆኑ በአብዛኛው የሀገሪቱ
ደጋማ ሥፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ
ተመዝግቧል። በወሩ ውስጥ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ2 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች
3
ከመዘገቡ ጣቢያዎች መካከል ለመጥቀስ ያህል በደብረ ብርሃን -1.6፣ 0.2 እና 1.4፣ በመሀል
ሜዳ -1.2፣ በሀሮማያ 0.0 እና 1.6፣ በወገል ጤና 0.5፣ በአምባ ማርያም 1.0፣ በአርሲ ሮቤ
1.0 ፣ በባቲ 1.6፣ በአዲግራት 2.0፣ በደብረዝት 2.0፣ አዲስ አበባ ቦሌ ኢነጂነሪነግ 2.0፣
በቡኢ 2.0፣ መመዝገቡን ከተሰበሰቡ መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል፡
በአጠቃላይ ባለፉት ሁለት ወራት የነበረው የዝናብ መጠን ሲገመገም ከትግራይ ጥቂት
የደቡብ ትግራይ ኪስ ቦታዎች፣ የምዕራብና የመካከለኛው ትግራይ፤ ከአማራ የሰሜንና የደቡብ
ጎንደር፣ ባህርዳር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን እንዲሁም የኦሮሚያ ልዩ ብሔረሰብ ዞን፤
ቤንሻንጉል-ጉሙዝ፤ ጋምቤላ፤ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ከሀዲያና ከጉራጌ
ዞኖች በስተቀር፤ ከኦሮሚያ ከምዕራብና ምሥራቅ ሸዋ እንዲሁም ከምዕራብ ሀረርጌ ሰሜናዊው
ክፍል በስተቀር እንዲሁም አብዛኛው ሶማሌ ከ25-396 ሚ.ሜ. ዝናብ ከ5-42 ቀናት ያህል
ያገኙ ሲሆን፤ የምዕራብ ትግራይ፤ ከአማራ የወግህምራ፣ ደቡብና ሰሜን ወሎ፣ እንዲሁም ሰሜን
ሸዋ፤ ከአፋር ዞን 1፣ 2 ና 4፤ጅግጅጋ፣ ሀረሪና አዲስ አበባ ደግሞ ከ5 - 25 ሚ.ሜ. የሚደርስ
ዝናብ ከ5 ላነሱ ቀናት ያህል አግኝተዋል (ካርታ 1 እና 2)።
ከኦክቶበር 1 እስከ ኖቬምበር 30/2017 የዘነበው ዝናብ ከመደበኛው ጋር ሲነፃፀር
የመካከለኛውና ምስራቅ ትግራይ፤ ከአማራ የሰሜን ጎንደር፣ ባህርዳር፣ ምዕራብ ጎጃምና የአዊ
ዞኖች እንዲሁም የኦሮሚያ ልዩ ብሔረሰብ ዞን፤ ቤንሻንጉል-ጉሙዝ፤ ጋምቤላ፤ ከደቡብ
ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ከሀዲያና ከጉራጌ ዞኖች በስተቀር፤ ከኦሮሚያ ኢሉአባቦራ፣
ጅማ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ የባሌና የቦረና ዞኖች፤ እንዲሁም በጋ የዝናብ ወቅታቸው
ከሆኑት የሶማሌ ክልል የፊቅ፣ የደገሀቡር፣ የሊበንና የአፍዲር ዞኖች መደበኛና ከመደበኛ በላይ
የሆነ የዝናብ መጠን የነበራቸው ሲሆን፤ በጋ ሁለተኛ ዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሶማሌ ክልል
ደቡብ ምስራቅ አካባቢ አነስተኛ ዝናብ የነበረ በመሆኑ ከመደበኛው በታች የሆነ የዝናብ
መጠን ነበራቸው፡፡ የተቀሩት የሀገሪቱ ክፍሎች በደረቅ የአየር ጠባይ ሰር ሰንብተዋል (ካርታ
3)፡፡
4
ካርታ 1 እ.ኤ.አ ከኦክቶበር 1 እስከ ከኖቬምበር 30/2017 ድረስ የነበረው የዝናብ መጠን በሚ.ሜ
56
410
0
222
46
3092
177
15
178
25266
207
0
142
135
133
68
158 4
16
0
1
148
37
204
144
2
206
128
380
18633
322
68
3
74
82
77
5
3
327
107
120
324
145
10
61
138
0
0
5
178
34
1
224
245
46
93
217
359
3
21
12
255
396
117
222
101
116
219
14
2
296
10419
156
27
16
80
308
0
0
24
9
155
208
40 5
65
24
11
142
205
199
1
118
107
8
282
4
19
149
15
17
56
85
123
8
3
2
7
229
3
26
1
194
0
201
54
319
151
44
168
20
77
1908
136
0
0
12946
0
59
0
114
175
56 5
25
50
100
200
300
400
5
ካርታ 2 እ.ኤ.አ ከኦክቶበር 1 እስከ ከኖቬምበር 30/2017 ድረስ ዝናብ የዘነበባቸው ቀናት ብዛት
13
43
0
15
5
67
21
2
26
220
35
0
22
18
23
11
11 3
12
0
1
22
6
18
23
1
17
25
42
319
34
9
3
10
14
12
4
2
37
16
16
41
23
1
10
16
0
0
3
20
7
1
22
22
7
15
28
29
3
6
3
30
41
14
23
17
19
26
5
2
24
275
20
6
6
12
39
0
0
6
2
21
20
10 2
8
6
4
16
27
30
3
8
21
4
29
2
4
19
5
3
9
23
16
5
2
4
3
31
4
6
1
27
0
15
5
27
20
6
28
5
19
294
16
0
0
299
0
6
0
12
14
13
5
10
20
30
40
50
6
ካርታ 3 እ.ኤ.አ ከኦክቶበር 1 እስከ ከኖቬምበር 30/2017 ድረስ የነበረው የዝናብ መጠን ከመደበኛው ጋር በመቶኛ ሲነፃፀር
ከመደበኛ በታች መደበኛ ከመደበኛ በላይ
7
እ.ኤ.አ ከኦክቶበር 1 እስከ ኖቨምበር 30/2017 የነበረው የአየር ጠባይ
በግብርና የስራ እንቅስቃሴ ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ
በመደበኛ ሁኔታ የበጋ ወቅት አጋማሽ ወራት በአመዛኙ ደረቃማ የእርጥበት ሁኔታ
የሚያመዝንባቸው ቢሆንም፤ አልፎ አልፎ ያልተጠበቀ ዝናብ የሚታይበትም ወቅት ነው፡፡
በተጨማሪም በዚሁ የበጋ የመጀመሪያዎቹ ወራት የአገሪቱ ደቡብና ደቡብ ምስራቅ ቆላማ
ቦታዎች ወቅታዊ የሆነ እርጥበት የሚያገኙበት ወቅት ነው፡፡ ከግብርና እንቅስቃሴ አንፃርም
የመኸር አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች የሰብል ስብሰባና ድኽረ ሰብል ስብሰባ የሚካሄድበት
ሲሆን፤ በደቡብና በደቡብ ምሥራቅ ደግሞ የአርብቶ አደሩና ከፊል አረብቶ አደሩ አከባቢዎች
ለግጦሽ ሳርና ለመጠጥ ውሀ እንዲሁም መጠነኛ የሆነ እርሻ እንቅስቃሴ የሚያከናውኑበት ጊዜ
ነው። በተጨማሪም በነዚሁ አካባቢዎች ለከብቶች ግጦሽ ሳርና ለመጠጥ ውሃ የሚሆን ዝናብ
የሚያገኙበትና ውሃን በተለያየ ዘዴ ለማከማቸት እድል የሚያገኙበት ወቅት ነው። በአንፃሩ
የበጋ ወቅት በአጠቃላይ ሲታይ ለበሽታና ለተባይ መከሰትና መስፋፋት አመቺ ሁኔታ ሊኖር
የሚችልበት ከመሆኑ አንጻር የሰብሎችን ጤናማ ሁኔታ በቅርበት ክትትል ማድረግ
የሚያስፈልግበት ወቅት ነው፡፡ በበጋ ወቅት የሙቀት መጠን ከአዝርዕት ጤናማ እድገት አኳያ
ሊተኮርበት የሚገባ ጉዳይ ሲሆን፤ በአንዳንድ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅና
በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች ላይ ውርጭ መከሰት ሊኖር የሚችል ከመሆኑም ጋር ተያይዞ
በተለይም በአበባና ፍሬ በመያዝ ላይ ለሚገኙም ሆነ ለፍራፍሬ ተክሎች ከፍተኛ ቅድመ
ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚያስፈልግበት ወቅት ነው፡፡
እ.ኤ.አ ኦክቶበር 2017 የበጋው ወቅት የመጀመሪያ ወር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ
በአብዛኛው የሰሜን ምስራቅና የምሰራቅ አካባቢዎች ላይ ከደረቃማ እስከ በጣም ደረቃማ
የእርጥበት ሁኔታ አመዝኖ እንደነበረ የተተነተኑ የአግሮ ሜቲዎሮሎጂ መረጃዎች
ያመለክታሉ፡፡ በመሆኑም ባሳለፍነው የኦክቶበር ወር ደረቃማው የአየር ሁኔታ አመዝኖ
በተስተዋለባቸው አካባቢዎች ላይ ለሚገኙ የደረሱ ሰብሎች ምቹ እንደነበረና ከዚሁ ጋር
ተያይዞ የሰብል ስብሰባ ለመጀመርም ሆነ የድህረ ሰብል ስብሰባ ተግባራትን ለማከናወን አመቺ
እንደነበር መገንዘብ ይቻላል፡፡ በአንፃሩ ሙሉ በሙሉ ባልደረሱና ለእድገታቸው ተጨማሪ
እርጥበትን ይፈልጉ ለነበሩ ሰብሎች የእርጥበት እጥረት ጫና ውስጥ እንዲገቡ ከማድረጉም
በላይ በአጠቃላይ እድገታቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ነበረው፡፡ በሌላ በኩል የእርጥበት ሁኔታው
በተለይም የበጋ ወቅት ዝናብ ተጠቃሚ ወደሆኑት የደቡብና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ
አካባቢዎች ላይ ተስፋፍቶ የታየ ሲሆን፤ ይህም ሁኔታ ጥምር ግብርና ለሚያከናውኑ አርሶ
8
አደሮች የጎላ ጠቀሜታ እንደነበረው ይታመናል፡፡ በተጨማሪም በነዚህ አካባቢዎች ላይ
በስፋት ለሚከናወነው የእንስሳት ልማት አስፈላጊ የሆነውን የአረንጓዴ እፅዋት ልምላሜን
ያሻሻለና የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን ያረጋገጠ ከመሆኑ አንፃር በወሩ ውስጥ የታየው
ከእርጥበታማ እስከ በጣም እርጥበታማ ሁኔታ ለአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር
አካባቢዎች አዎንታዊ ሚና ነበረው (ካርታ 4)፡፡
በተመሳሳይ መልኩ የኖቨምበር ወር የእርጥበት ስርጭቱ ሲገመገም በአብዛኛው
የሰሜን፤ የሰሜን ምዕራብና የሰሜን ምስራቅ እንዲሁም የመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ
ከደረቃማ እስከ በጣም ደረቃማ የእርጥበት ሁኔታ እንዳመዘነባቸው ተስተውሏል፡፡ ምንም
እንኳን ሁኔታው ሙሉ ለሙሉ እድገታቸውን ለጨረሱና በመሰብሰብ ላይ ለሚገኙ ሰብሎች በጎ
ሚና ቢኖረውም እድገታቸውን ላልጨረሱና ተጨማሪ እርጥበት ለሚያስፈልጋቸው ሰብሎችና
ለቋሚ ተክሎች የውኃ ፍላጎታቸውን ለማሟላት አሉታዊ ጎን የነበረው ሲሆን፤ በተጨማሪም
የግጦሽ ሳርና የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን ከማሻሻል አንፃር አነስተኛ ሚና ነበረው፡፡ በሌላ
መልኩ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተሻለ
የእርጥበት ስርጭት የታየ ሲሆን፤ ይህም የተገኘው እርጥበት በተለያየ የእድገት ደረጃ ላይ
ለሚገኙ ሰብሎችና ለቋሚ ተክሎች የውኃ አቅርቦት ምቹ ሁኔታ እንዲኖር አስችሏል፡፡
በተጨማሪም በደቡብና በደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች ለሚኖሩ አርብቶ አደሮችና በከፊል
አርብቶ አደሮች አካባቢ ለግጦሽ ሳርና ለመጠጥ የሚሆን ውኃ በተሻለ መልኩ እንዲያገኙ
ከማስቻሉ አንፃር በእንስሳት ልማት ስራ ላይ እገዛ አበርክቷል፡፡ በአንፃራዊ መልኩ ባሳለፍነው
የኖቨምበር ወር በአንዳንድ ለውርጭ ተጋላጭ በሆኑ ሥፍራዎች ላይ የሌሊቱና የማለዳው
ቅዝቃዜ እየጨመረ በመምጣቱ እድገታቸውን ባልጨረሱና በተለይም በአበባና ፍሬ
በመሙላት የእድገት ደረጃ ላይ በሚገኙ ሰብሎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደቻለ
ይገመታል (ካርታ 5)፡፡
በአጠቃላይ ባለፉት ሁለት የበጋ ወራት በኦክቶበር እና በኖቨምበር የነበራቸው
የእርጥበት ሁኔታ ሲገመገም በተለይም የክረምቱ ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ክስተቶች ቀስ
በቀስ ከመዳከማቸው ጋር ተያይዞ የእርጥበት ሁኔታው ከሰሜንና ከሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ
አካባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በስርጭት እየቀነሰ በአንጻሩ በምዕራብ አጋማሽ እና
በመካከለኛዉ የአገሪቱ ክፍሎች ላይ በተወሰነ ደረጃ የቆየበትና በሂደትም የበጋ ዝናብ
ተጠቃሚ ወደ ሆኑት ወደ ደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተስፋፋ
እንደነበረ ተስተውሏል፡፡ በአጠቃላይ ይህ ሁኔታ በሰሜንና በሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች
9
ለሚገኙ ለደረሱና ተጨማሪ እርጥበት ለማያስፈልጋቸው ሰብሎች በጎ ጎን እንደነበረው
ቢወሰድም በተለያየ ምክንያት ዘግይተው ለተዘሩና እድግታቸውን ላልጨረሱ ሰብሎች
የእርጥበት እጥረት ጫና እንዳሳደረ ግምት መውሰድ ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ
አጋማሽና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ እርጥበቱ የተሻለ ገፅታ የነበረው መሆኑ
በተለያየ የእድገት ደረጃ ላይ ይገኙ ለነበሩ ሰብሎችም ሆነ በአካባቢዎቹ ለሚገኙ ቋሚ ተክሎች
በጎ ሚና እንደነበረው ይታመናል፡፡
10
34 36 38 40 42 44 46 48
4
6
8
10
12
14
ካርታ 4፡ የኦክቶበር ወር 2017 የእርጥበት ሁኔታ
ካርታ 5፡ የኖቬምበር ወር 2017 የእርጥበት ሁኔታ
11
እ.ኤ.አ ከዲሴምበር 1/2017 እስከ ጃንዋሪ 31/ 2018 የሚኖረው የአየር ጠባይ አዝማሚያ
በመደበኛ ሁኔታ የዲሴምበር እና የጃንዋሪ ወራት በአብዛኛው የበጋ ወቅት የአየር ጠባይ
ገፅታዎች የሆኑት ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚያመዝኑበት ከመሆኑም ሌላ
የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ በተለይም ለውርጭ ተጋላጭ በሆኑ ደጋማ ቦታዎች ላይ
የሚያይልበት ጊዜ ነው። በአንፃሩ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብና
በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ እንዲሁም ከበልግ ወቅት መቃረብ ጋር ተያይዞም በጥቂት
የሰሜን ምሥራቅ አማራ ቦታዎች ላይ ዝናብ ይዘንባል። በተጨማሪም ከመደበኛ ሁኔታ ወጣ
ባለ መልኩ በአንዳንድ ዓመታት ወቅታዊ ያልሆነ ዝናብ ይከሰታል።
በመጪዎቹ ሁለት የበጋ ወራት የትሮፒካል ፓስፊክ ውቅያኖስ አብዛኛው ክፍል የባህር
ወለል ሙቀት ቀስ በቀስ ከመደበኛው በታች (La-Nina) ክስተት ተጽእኖ ስር ሆኖ ሊቀጥል
እንደሚችል የሚጠበቅ ሲሆን፤ በአብዛኛው በቀሪዎቹ የበጋ ወራት (ዲሴምበር እና ጀንዋሪ)
የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ስለሚያመዝን የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ
በአንዳንድ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ላይ ይጨምራል።
በዚህም መሰረት በብዙ የሀገሪቱ ቦታዎች ላይ ደረቃማው የአየር ጠባይ ሰፍኖ
እንደሚቆይ የሚጠበቅ ሲሆን! ከዚሁ ጋር ተያይዞም በተለያዩ ሥፍራዎች ላይ የሌሊቱና
የማለዳው ቅዝቃዜ ቀጣይነት ይኖረዋል። በተጨማሪም ከበጋው ወቅት ማብቂያ አካባቢ
የበልግ ወቅት መቃረቢያ ላይ በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ የምዕራብ ወለጋ" የጅማና የኢሉባቦር
ዞኖች! በደቡብ ብሄር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የከፋና የቤንች ማጂ ዞኖች እንዲሁም በምሥራቅ
አማራ የሚገኙ የሰሜን ሸዋና የደቡብ ወሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ
እንደሚያገኙ ይጠበቃል።
እ.ኤ.አ ከዲሴምበር1/ 2017 እስከ ጃንዋሪ 31/ 2018 የሚኖረው
የአየር ጠባይ አዝማሚያ በግብርና የስራ እንቅስቃሴ ላይ ሊያሳድር የሚችለው
ተፅዕኖ
በመጪዎቹ ሁለት የበጋ ወራት ማለትም ከዲሴምበር እስከ ጃንዋሪ 2017/2018
በተሰጠው የአየር ትንበያ መሰረት የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ
እንደሚያመዝን ይጠበቃል፡፡ ከዚሁ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ
12
የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ እንደሚጠናከር ይጠበቃል፡፡ ይህ ደረቃማው የእርጥበት ሁኔታ
ለሰብል ስብሰባና ለድኸረ ሰብል ስብሰባ አዎንታዊ ጎን እንደሚኖረው የሚጠበቅ ሲሆን፤
በአንጻሩ ደግሞ የሚኖረው የእርጥበት እጥረት በአካባቢዎቹ ለሚገኙ ቋሚ ሰብሎች የውኃ
ፍላጎት መሟላትም ሆነ ለአርብቶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ለግጦሸ ሳርና
ለመጠጥ ውኃ አቅርቦት አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ይጠበቃል፡፡ ከሚጠበቀው ቅዝቃዜ
ጋር በተያያዘ በተለይም በቋሚ ተክሎች ላይ በመጠኑም ቢሆን ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፡፡
በተጨማሪም በትንበያው በተጠቀሱት አንዳንድ አካባቢዎች ማለትም በምዕራብ ወለጋ፣
በጅማ፣ በኢሉባቦር፣ በከፋ፣ በቤንች ማጂ፣ በሰሜን ሸዋና በደቡብ ወሎ ዞኖች ከቀላል እስከ
መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል። ይህም ሁኔታ በድህረ ሰብል ስብሰባ
ላይ ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል በተገለጹት አካባቢዎች የሚኖሩ አርሶአደሮችም ይሁኑ
ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በመረባረብ ሰብሎችን ሊሰበስቡ ስለሚገባ በየደረጃው የሚገኙ
የህብረተሰብ ክፍሎች ለዚሁ ጉዳይ ትኩረት ሊያደረጉ ያስፈልጋል፡፡ በአንጻሩ በተጠቀሱት
አካባቢዎች የሚጠበቀው እርጥበት ለበልግ ተጠቃሚዎች ለማሳ ዝግጅት፣ በእድገት ላይ
ለሚገኙና ለቋሚ ሰብሎችም ሆነ ለእንስሳት የግጦሽ ሳርና የመጠጥ ውኃ አቅርቦት የሚኖረው
ሚና ከፍተኛ ሲሆን፤ በተለይም ውኃ አጠር የሆኑ አካባቢዎች የሚገኘውን ውሱን ውኃ
ለማከማቸት ዝግጅት ሊያደርጉ ይገባል፡፡ በሌላ መልኩ የተገኘውን ውሃ ከብክነት መከላከል
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚኖረው አስተዋጽዖ ከፍተኛ ስለሆነ የተሰጠውን የግብርና
ምክረ ሃሳብ በተግባር ላይ ማዋል ያስፈልጋል፡፡