24
Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans የኢትዮ-አሜሪካውያን ድምጽ ሚያዝያ 2006 ቅጽ VI ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል Tax! ታክስ! Tax! ታክስ! Tax! ታክስ! ከጃንዋሪ 2014 ጀምሮ ታክስዎን የሚሠራልዎ በሙያው አንቱታን ያገኘው አክሎግ ነው ጥርስዎን ለመታጠብ፣ ለመነቀል፣ ለማስተካከልና ለሌሎችም ወደ ዊሎ የጥርስ ህክምና ይምጡ አፕል ጋራዥ Apple Auto Repair - Engine - Brakes - Suspension - Transmission - Electrical - Body - Interior More... የመኪናዎን ዘይት ካለቀጠሮ እንቀይራለን $25 ብቻ የዝናብ መጥረጊያዎን ለማስቀየር እቃው እና ጉልበቱ በ20$ ብቻ። ዮሐንስ ተግባሩ፡- 651-3343029 ቴሌፎኑ ለጊዜው ጥሪ አይቀበልም ስለዓይንዎ እናውራ ገጽ 17 ላይ ገጽ 6 ላይ ገጽ 21 ላይ Universal Realty Group ዶ/ር ሲራክ ኃይሉ ለ5ኛ ጊዜ ለተማሪዎች ስኮላርሺፕ ሰጡ የወንጀል ዘገባ፦ ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ ኤፕሪል 21 ቀን 2014 ዓ.ም በተደረገው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር ዓመታዊ የባህል ዝግጅት ላይ ዶ/ር ሲራክ ኃይሉ ለ5ኛ ጊዜ ለ ተማሪዎች ስኮላር ሺፕ ሰጡ። ኤፕሪል 21 ቀን 2014 ዓ.ም በድምቀት በተከበ ረው የኢትዮጵያ የባህል ምሽት ላይ የተለያዩ የብሔ ር ብሔረሰቦች ሙዚቃዎችና ዳንሶች፣ የፋሽን ሾው፣ የተጋባዥ ክብር እንግዳ ንግግር፣ ዓመታዊ ስኮላርሺ ፕ አሸናፊዎች መታወቂያ ፕሮግራሞችና የራት ምሽ ት ቀርቧል። በሚኒሶታ የመኪና፣ የስፖርትና የሥራ ቦታ አደ ጋዎች ለደረሰባቸው ወገኖች ህክምና በመስጠት የሚ ታወቁት ዶ/ር ሲራክ ኃይሉ ዘንድሮም ለ3 ተማሪዎ ች የስኮላርሺፕ በመስጠት ለአሸናፊዎቹ እንደደረጃ ቸው ገንዘብ ሸልመዋል። ወደ 200 የሚጠጉ የሚኒሶታ ሕፃናትን ትምህር ት ቤት ከመከፈቱ (ዶ/ር ሲራክ... ወደ ገጽ 13 የዞረ) እንደዘበት ያለፉት ነፍሶች (እውነተኛ የወንጀል ታሪክ) እነዚህ ሁለት የወንጀል ታሪኮች የተፈፀሙበት ጊዜ ጥቂት ዓመታት ወደኋላ ይርቃል፡፡ ሁለቱም ወ ንጀሎች የተለያዩና የሚያገናኛቸው ነገር የሌለ ቢሆን ም ማጠቃለያቸው ግን ሞት መሆኑ ያመሳስላቸዋል፡ ፡ በተለይ በተለይ የህይወት ህልፈቱ ሳይታሰብ እንደ ዘበት መፈጠሩ ‹የተቆረጠለት ቀን› የሚባለውን አይነ ት አሟሟት ያስታውሳል፡፡ ሁለት ነፍሶች በተለያየ ዓ መት በተለያየ ሁኔታ በተለያዩ ቀናትና በተለያየ ምክ ንያት እንደዘበት አልፈዋል፡፡ ሳይታቀድና ሳይታሰብ ህይወታቸውን የተቀሙት ሰዎች መቃብር ውሎባቸ ው- ገዳዮቹም አስር ቤት አሽጓቸው ተረሳስተዋል፡፡ (ይህን የወንጀል ታሪክ ለማንበብ ገለጥ ገለጥ አድር ገው ገጽ 10 ላይ ይመልከቱት፤ ያንብቡና ይማሩበት) ሚኒሶታ ንቃ የዘንድሮው ትክክለኛው የኢትዮጵያውያን 31ኛው ዓመት የስፖርት ፌስቲቫል የሚደረገው ሚኒሶታ ሳይሆን ሳንሆዜ ነው ለ31 ዓመታት በሰሜን አሜሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ሲያገናኝ የቆየውን ታሪካዊውን የስፖርት ማህበር ተገንጥለው ከሕዝብ ይልቅ አላሙዲንን መርጠው የሄዱት ወገኖ ች በዋሽንግተን ዲሲ ለ3 ተከታታይ ዓመታት የኢትዮጵያውያንን የስፖርት ፌስቲቫል እናደርጋለን ብለው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር አውጥተው ቢንቀሳቀሱም ላለፉት ሁለት ዓመታት በባዶ ስታዲየምና በከፍተኛ ተቃውሞ (ቦይኮት) ለኪሳራ ሲዳረጉ ለ3 ዓመት የከፈሉበትን ስታዲየም በመልቀቅ የዘንድሮውን ኳስ በሚኒሶታ እናደርጋለን ብለው እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም ትክክለኛው የኢትዮጵያውያን ኳስ ጨዋታ ውድድር የሚደረገው በሳንሆዜ ቤይ ኤሪያ እንደሆነ ታውቋል። (ገጽ 19 ላይ ዞሯል) “አውቆም ተከሰተላቸው” ሐዋ. 12 ፀሎት የምትፈልጉ ወይም ጥያቄ ያላችሁ፦ ከፓስተር ደስታዬ ክራውፎርድ በ612-225-8269 ይደውሉ። የፊታችን እሁድ ኤፕሪል 27 6ፒኤም ልዩ ዝግጅት ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፤ ከበረከቱ ተካፈሉ! ስለ አዲሱ የኢትዮጵያ አሰልጣኝ

ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

  • Upload
    others

  • View
    25

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans የኢትዮ-አሜሪካውያን ድምጽ ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል

Tax! ታክስ! Tax! ታክስ! Tax! ታክስ!ከጃንዋሪ 2014 ጀምሮ ታክስዎን የሚሠራልዎ

በሙያው አንቱታን ያገኘው አክሎግ ነው

ጥርስዎን ለመታጠብ፣ ለመነቀል፣ ለማስተካከልና ለሌሎችም ወደ ዊሎ የጥርስ ህክምና ይምጡ

አፕል ጋራዥ Apple Auto Repair

- Engine- Brakes- Suspension- Transmission

- Electrical- Body- InteriorMore...

የመኪናዎን ዘይት ካለቀጠሮ እንቀይራለን

$25ብቻ

የዝናብ መጥረጊያዎን ለማስቀየር እቃውእና ጉልበቱ በ20$

ብቻ።

ዮሐንስ ተግባሩ፡- 651-3343029

ቴሌፎኑ ለጊዜው ጥሪ አይቀበልም

ስለዓይንዎ እናውራ

ገጽ 17 ላይገጽ 6 ላይ ገጽ 21 ላይ

Universal Realty Group

ዶ/ር ሲራክ ኃይሉለ5ኛ ጊዜ ለተማሪዎች

ስኮላርሺፕ ሰጡ

የወንጀል ዘገባ፦

ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ ኤፕሪል 21 ቀን 2014 ዓ.ም በተደረገው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር ዓመታዊ የባህል ዝግጅት ላይ ዶ/ር ሲራክ ኃይሉ ለ5ኛ ጊዜ ለተማሪዎች ስኮላር ሺፕ ሰጡ።

ኤፕሪል 21 ቀን 2014 ዓ.ም በድምቀት በተከበረው የኢትዮጵያ የባህል ምሽት ላይ የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦች ሙዚቃዎችና ዳንሶች፣ የፋሽን ሾው፣ የተጋባዥ ክብር እንግዳ ንግግር፣ ዓመታዊ ስኮላርሺፕ አሸናፊዎች መታወቂያ ፕሮግራሞችና የራት ምሽት ቀርቧል።

በሚኒሶታ የመኪና፣ የስፖርትና የሥራ ቦታ አደጋዎች ለደረሰባቸው ወገኖች ህክምና በመስጠት የሚታወቁት ዶ/ር ሲራክ ኃይሉ ዘንድሮም ለ3 ተማሪዎች የስኮላርሺፕ በመስጠት ለአሸናፊዎቹ እንደደረጃቸው ገንዘብ ሸልመዋል።

ወደ 200 የሚጠጉ የሚኒሶታ ሕፃናትን ትምህርት ቤት ከመከፈቱ (ዶ/ር ሲራክ... ወደ ገጽ 13 የዞረ)

እንደዘበት ያለፉት ነፍሶች(እውነተኛ የወንጀል ታሪክ)

እነዚህ ሁለት የወንጀል ታሪኮች የተፈፀሙበት ጊዜ ጥቂት ዓመታት ወደኋላ ይርቃል፡፡ ሁለቱም ወንጀሎች የተለያዩና የሚያገናኛቸው ነገር የሌለ ቢሆንም ማጠቃለያቸው ግን ሞት መሆኑ ያመሳስላቸዋል፡፡ በተለይ በተለይ የህይወት ህልፈቱ ሳይታሰብ እንደዘበት መፈጠሩ ‹የተቆረጠለት ቀን› የሚባለውን አይነት አሟሟት ያስታውሳል፡፡ ሁለት ነፍሶች በተለያየ ዓመት በተለያየ ሁኔታ በተለያዩ ቀናትና በተለያየ ምክንያት እንደዘበት አልፈዋል፡፡ ሳይታቀድና ሳይታሰብ ህይወታቸውን የተቀሙት ሰዎች መቃብር ውሎባቸው- ገዳዮቹም አስር ቤት አሽጓቸው ተረሳስተዋል፡፡ (ይህን የወንጀል ታሪክ ለማንበብ ገለጥ ገለጥ አድርገው ገጽ 10 ላይ ይመልከቱት፤ ያንብቡና ይማሩበት)

ሚኒሶታ ንቃየዘንድሮው ትክክለኛው የኢትዮጵያውያን 31ኛው ዓመት

የስፖርት ፌስቲቫል የሚደረገው ሚኒሶታ ሳይሆን ሳንሆዜ ነውለ31 ዓመታት በሰሜን አሜሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ሲያገናኝ የቆየውን ታሪካዊውን የስፖርት ማህበር ተገንጥለው ከሕዝብ ይልቅ አላሙዲንን መርጠው የሄዱት ወገኖች በዋሽንግተን ዲሲ ለ3 ተከታታይ ዓመታት የኢትዮጵያውያንን የስፖርት ፌስቲቫል እናደርጋለን ብለው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር አውጥተው ቢንቀሳቀሱም ላለፉት ሁለት ዓመታት በባዶ ስታዲየምና በከፍተኛ ተቃውሞ (ቦይኮት) ለኪሳራ ሲዳረጉ ለ3 ዓመት የከፈሉበትን ስታዲየም በመልቀቅ የዘንድሮውን ኳስ በሚኒሶታ እናደርጋለን ብለው እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም ትክክለኛው የኢትዮጵያውያን ኳስ ጨዋታ ውድድር የሚደረገው በሳንሆዜ ቤይ ኤሪያ እንደሆነ ታውቋል። (ገጽ 19 ላይ ዞሯል)

“አውቆም ተከሰተላቸው”ሐዋ. 12

ፀሎት የምትፈልጉ ወይም ጥያቄ ያላችሁ፦ ከፓስተር ደስታዬ ክራውፎርድ በ612-225-8269 ይደውሉ።

የፊታችን እሁድ ኤፕሪል 27 6ፒኤም ልዩ ዝግጅት ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፤ ከበረከቱ ተካፈሉ!

ስለ አዲሱ የኢትዮጵያ አሰልጣኝ

Page 2: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 2

Page 3: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 3

Ze-Habesha Newspaper is Legally Registered in state of

Minnesota - USA

Founded in December 2008 Publisher :-

ZeHabesha LLC

ዋና አዘጋጅ:-

ሔኖክ ዓለማየሁ ደገፉ

Editor in Chief:-

Henok A. Degfu e-mail:- [email protected]

[email protected]

አዘጋጆች:- ሊሊ ሞገስ፣

[email protected]ሮቤል ሔኖክ፣

[email protected]ቅድስት አባተ

ዘላለም ገብሬ (ቺካጎ)[email protected]

አማካሪ፡- ዶር ዓብይ ዓይናለም

Ze-Habesha newspaper Address:-

6938 Portland Ave, Richfield MN 55423

) 612-226-8326 www.zehabesha.com

www.facebook.com/zehabeshawww.twitter.com/zehabesha

“Journalism can never be silent: that is its greatest virtue and its greatest fault. It

must speak, and speak immediately, while the echoes of wonder, the claims

of triumph and the signs of horror are still in the air.”

Henry Anatole Grunwald

በሚኔሶታ - አሜሪካ የተቋቋመ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ጋዜጣ ነው። ጋዜጣው ዓላማው የማህበረሰባችን የወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ መገኛ መሆን ነው።

ዘ-ሐበሻ ከማንኛውም ሃይማኖት፣ ፖለቲካ ድርጅት፣ ጎሳ፣ ያልወገነ፣ ነጻ ጋዜጣ ነው፡፡

ዓብይ መልዕክት

ከነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)

በመጀመሪያ የክርስትና እምነት ተከታይ አንባቢዎች እንኳን ለ2006ዓ.ም የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ሕወሓት ወደ ሥልጣን መጥቶ በዓይነቱ የተለዬ የጥቁር አፓርታይድ ሥርዓትን በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ካቆመ ወዲህ እጅግ ብዙና ለመቁጠርም የሚያዳግቱ መመሪያዎችንና ዐዋጆችን ቀርፆአል፡፡ አንዳንዶቹን በዘፈቀደና በነሲብ እየቸከቸከ በፈለገው ሰዓትና ወቅት ራሱ ተግባራዊ በማድረግ፣ አንዳንዶቹንም ለማስመሰል ያህል በእንቅልፋምና ደናቁርት የ“ፓርላማ” አባላቱ አማካይነት በዐይን ጥቅሻ በሚታዘዝ የሆዳም ማይማን ጭብጨባ “አጸድቆ” ሥራ ላይ በማዋል ሀገርንና ሕዝብን ማተራመስ ከያዘ ሁለት ዐሠርት ዓመታትን ጨርሶ የሦስተኛውን ዐሠርት አንድ ሦስተኛ ያህል ጊዜ ለማገባደድ ጥቂት ወራት ብቻ ይቀሩታል፡፡

ከቅርቦች ልጀምር፡፡ ቅድም ቡና ስጠጣ እንዲህ የሚል ወሬ ሰማሁ፡፡ እውነት ይሁን ሀሰት ገና አላረጋገጥሁም - ይሁን እንጂ የወያኔን ባሕርይ ለሚያውቅ ይህን ወሬ ሀሰት ነው ማለት የሚያስችል አዲስ ነገር አይገኝም፡፡ ከዚህ የበላለጡ አስቂኝና አስገራሚ መመሪያና ዐዋጆችን እየታዘብን 23 የመከራና ፍዳ ዓመታትን ስላቀናን ይህኛውን የተለዬ አያደርገውም፡፡ የሰማሁት ምን መሰላችሁ - ልማታዊ የወያኔ ሙዚቀኞችና ዳንኪረኞች በኮፒራይት መቸገራቸውን ስላመለከቱና ለዚህም ችግር መባባስ ትልቁን ሚና እየተጫወቱ የሚገኙት የስልኮች ሚሞሪዎችና ብሉቱዝ በመሆናቸው እነዚህን አገልግሎቶች የሚሰጡ ማናቸውም የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ሀገር እንዳይገቡ መንግሥት ማገጃ አውጥቷል የሚል ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ የእጅ ስልኮችና የመሳሰሉት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ማዕቀብ ሊጣልባቸው እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ ለነገሩ ከኢትዮጵያ የወያኔ ሚዲያዎች በውዴታየ ስለራቅሁ ይህ መመሪያ በገሃድ ወጥቶ ይሁን አይሁን እስካሁን አላወቅሁም፡፡ በበዓሉ ምክንያት ከጎረቤት ውጪ ራቅ ወደሚል ሌላ ውጪ አልወጣሁም፡፡ ግን አይሆንም አይባልም፡፡ ወያኔ ከፈለገ “ከዛሬ ጀምሮ ከትግሬ በስተቀር ነጭ ጤፍ እንጀራ የሚበላና ጮማ የሚቆርጥ ሌላ የማኅበረሰብ ክፍል እንዳይኖር ዐውጃለሁ፤ ቢኖር ግን ህገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ እንደቃጣ ተቆጥሮ በአሸባሪነት የክስ ቻርጅ እስከሞት ሊደርስ በሚችል ከፍተኛ ቅጣት ዋጋውን ያገኛል፡፡” ብሎ ሊያውጅ ይችላል፡፡ ማንን ወንድ ብሎ ነው ወያኔ የፈለገውን ከማድረግ የሚቆጠበው? ወያኔ በምን ይዳኛል? በምንም፡፡ ለነገሩ ቀን የሰጠው ጅብ አንበሣንና ነብርን ሲቆረጣጥም ቢታይ ዘመኑ የትንግርት ነውና አያስገርምም፡፡ በኢትዮጵያም ሆነ በተቀረው ዓለም እየሆነ ያለውም ይሄውና ይሄው ብቻ ነው፡፡ ግን ግን በሀገራችን ለወደፊቱ ጅብ የማያሸንፍበትን ቀዳዳ መዝጋት የሚያስችለንን ታላቅ የሦስተኛው ሚሌንየም ሥልት መንደፍ እንደሚገባን ከወያኔው አዋራጅ የተፈጥሮ ልክስክስ ጠባይ የተማርን ይመስለኛል፤ የመንጌን አማርኛ ልጠቀምና ብታምኑም ባታምኑም የአፄውና የደርጉ ሥርዓቶች መንገዱን ባበጃጁለት ወያኔ ክፉኛ ተዋርደናል፡፡ አሸንፎ የማያውቅ ትንሽ ሰው እንዳያሸንፋችሁና መሣቂያና መሣለቂያ እንዳያደርጋችሁ በርትታችሁ ጸልዩ፡፡ ትንሽ ስል ማሸነፍን እንደህልም ይቆጥር የነበረ የባንዳዎችና የሥነ ልቦና ደዌ የተጣባቸው በበቀልና ጥላቻም የተሞሉ ዜጎች ውላጅ የሆኑ መለስን፣ ስብሃትንና ሣሞራን የመሰሉ የታሪክ አራሙቻዎች ማለቴ ነው፡፡ እንደነዚህ ያሉ ቀላሎች በታሪካዊ መደላድሎች መመቻቸት ምክንያት አንዳች ዕድል ካገኙ እንዴቱን ያህል ወጥ እንደሚረግጡና ነገሮችን በምን ያህል ደረጃ እንደሚያበለሻሹ በሚገባ ተረድተናል፡፡ ለማንኛውም ሚሞሪ ያላቸው ስልኮችና መሰል ጋጄቶች ሊከለከሉ ነው አሉ፡፡ አልጋህ ውስጥ ተደብቀህም በሙዚቃ መቆዘም ሊቀር ነው፡፡ ኧረ ባል በሚስቱና ሚስትም በባሏ ቀረጥ እንዳይከፍሉ ያሰጋል፡፡ “እያንዳንድሽ ማን በሚገዛው ሀገር ውስጥ ተኝተሸ ዓለምሽን ትቀጫለሽ?” ብሎ ምቀኛው ወያኔ ለአንድ ግንኙነት ብር 50 ግብር ቢጥልና በየጉያችን ኤሌክትሮኒክ ሥውር ባልቦላ(ማይክሮቺብስ) እንደኖር ፕላንት ቢተክል ባለትዳሮች ምን ይውጠናል? ያቺው ብቸኛ መዝናኛችን ላይ ወያኔ በመብረቃዊ የማጥቃት እርምጃው ቢዘምትባት ወዴትና ለማንስ አቤት እንላለን? የሰይጣን ጆሮ ይደፈን፡፡ የምንተነፍሰውን አየርና የፀሐዩንማ በኑሮ ውድነቱ ላይ ጨምሮ ባልተወለደ አንጀት እያስገፈገፈን ነው፡፡

ከውጭ ሀገራት በበርሜል ዕቃ ማስገባት ተከልክሏል፡፡ በካርቶንና በከረጪት እንጂ በርሜል አይገባም፡፡ ምክንያቱን መጠየቅ አያስ

ፈልግም፡፡ ሊሆን የሚችለው ብቸኛ ምክንያት አንዱ ወያኔ ትግሬ - አንዱ ዘመነኛ በጥጋብ የተወጠረ ትግሬ ወያኔ - የበርሜል ፋብሪካው ገበያው ቀንሷል ማለት ነው፡፡ ለዚህ መፍትሔው ደግሞ ቀላል ነው፡፡ ማታ ሼራተን ወይ ሂልተን ላይ ለሚጋብዛቸው ወያኔ ተጋዳላዮች ለአንዱ ሹክ ማለት ነው - “ከነገ ጀምሮ ከዐረብም ይሁን ከሌላ ሀገር የበርሜል ዘር በቦሌም ይሁን በባሌ ወደኢትዮጵያ ሕዝቦች መኖሪያ ክልሎች እንዳይገባ ጥብቅ መመሪያ አውጣልኝ፡፡” በቃ፡፡ ይቺ ትዕዛዝ ብቻ በቂ ናት፡፡ ከማግስቱ ጀምሮ በርሜል ይቅርና አንዲትም የላስቲክና የብረት ኩባያ ወደሀገር እንዳትገባ ማድረግ ነው፤ ለወያኔዎች ይህን ማድረግ ቀላል ነው፡፡ ሣተናዎቹ ወያኔዎች የፈለጉት ይሆናል፤ ያልፈለጉት አይሆንም - ዘጠና ሚሊዮን ሕዝብ አንቀጥቅጠው መግዛት የቻሉ የአጋንንት ወኪሎች በመሆናቸው ለጊዜው የሚያቅታቸው ነገር የለም፡፡ ይህንን ደግሞ ዕንወቅ፡- እነዚህ ሽል መንጣሪ ዘረኛ የሣጥናኤል ልጆች ከራሳቸው የሚወጣ አንዳችም ኃይል የላቸውም፤ ኃይላቸው የኛ ክፋት፣ የኛ ብዙ ክፋት ነው፡፡ (ለምሳሌ አሁን አንቺ ለኔ መልካም ታስቢያለሽ? ካሰብሽልኝ እሰዬው - ካልሆነ ግን አሁኑኑ ጀምሪውና ሞክሪው፡፡) አዎ፣ በርግጥም ክፉዎች ነን፡፡ በክፋታችንና በአመፀኝነታችንም ሰበብ እያገኘን ያለነውን እያገኘን ነን - በኢትዮ

ጵያ ውስጥ ብቻም ሣይሆን በመላው ዓለም ዙሪያ፡፡ እንጂ እነዚህ የት እንዳሉ እንኳን የማይታወቁ ‹ረቂቅ› ጠላቶቻችን ይህን ሁሉ ሚሊዮን ሕዝብ እንዲህ ኮድኩደው ባላሰቃዩት ነበር፡፡ ወደኅሊናችን ብንመለስ፣ ብንደማመጥ፣ ቁስላችንን ብንመለከት፣ የተፋፋቅነውንና የተጋጋጥነውን በጋራ ለማከም - ለመተካከም- ብንቆርጥ….. እውነቴን ነው የምለው ችግራችንን ለማስወገድ ጥቂት ወራት ብቻ በበቁን፡፡ ግን ብዙዎቻችን በአሉታዊነት የተጠመቅን፣ የክፋታችን ክርፋት ቀድሞን አካባቢን በመጥፎ ጠረን የሚበክል፣ በአስመሳይነትና በሥልጣን ጥም የታወርን፣ በንቀትና በትዕቢት ተወጥረን በጥላቻ ገመድ አንዳችን አንዳችንን የምንጠልፍ፣ በመታች ደብተራና በአባይ ጠንቋይ ድቤ መቺ አበጋር በሰው ላይ እያስመተትንና እያስተበተብን የተቀየምናቸውን ወይም የተመቀኘናቸውን ሰዎች የምናሳብድና የምናደኸይ፣ ለአገዛዝ እንዲያመቸን ብዙኃኑን ዜጎች በማይምነት ጥቁር መጋረጃ ሰነካክለንና በማይረባ የትምህርት ሥርዓት ወጣት ትውልድን አደንቁረን የምናስቀር፣ በሚዲያና በወረቀት ላይ ያልሠራነውን እንደሠራን እያስመሰልን የውሸት ልቃቂት የምንተረትርና የሀሰት እስታትስቲክስ በየዋሃን ዜጎች ጆሮ ዙሪያ የምናዳውር፣ ከጥረት ይልቅ በሰይ

ጣናዊ መንገድና በሙስና በአቋራጭ እንዲያልፍልን የምንሞክር ግብዞችና አንዳችን ለሌላኛችን የማንተኛ ሸፍጠኞች … በመሆናችን የምናስበውን ከመፈጸማችን በፊት ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላከ ኢትዮጵያ ስንኩል ዕቅዳችንንና በራስ ወዳድነት ላይ የተመሠረተ አጥፊ ሤራችንን አስቀድሞ የእምቧይ ካብ ያደርገዋል - ይህን ነገር ‹ሀሰት ነው› ብለህ የምትሞግተኝ ካለህ ወደ ኢትዮጵያ ምጣና ተጨባጩን ማኅበረሰብኣዊ ተራክቦ ተመልከት፤ ከዚያም “አሃ፣ እውነትም ወያኔም ሲያንሰን ነው ለካንስ” ብለህ ልትፈርድ ትችላለህ - ይህንን እነሱም ያውቁታል፤ እኛም እናውቃለን፤ ፈጣሪም ያውቀዋል፤ ሰይጣንም ሣይቀር በሚገባ ያውቀዋል - የክፋት ሠራዊት አባላት ግና ጊዜያቸውን በደንብ እንደሚጠቀሙበት የታወቀ ነውና ካለሰዓቱ ንቅንቅ አይሉም፤ ጅብ የጎረሰውን እያላመጠ ይሞታታል እንጂ እየሞተም ቢሆን መብላቱንና ግዳይ መጣሉን በተስፋ መቁረጥ ምክንያት አይተውም፡፡ የሚመር አውነት ነው፡፡

በሳይጋገር ተቦካና በላም አለኝ በሰማይ ገና ለገና ሥልጣን ተገኝቶ፣ ገና ለገና ወያኔ ወድቆ፣ ገና ለገና በሀገር ላይ “ዴሞክራሲ” ‹ሰፍኖ›፣ ገና ለገና ከአንበሣ አፍ ሥጋ ወድቆ ለጅብ ተርፎ … ተቃዋሚዎቻችን የሚያሳዩትን የርስ በርስ መጠላለፍና የሚያካሂዱትን ዶንኪሾ

ታዊ ፍልሚያ እንኳን አታይም? ከዚህ አንጻር ውጥንቅጡንና አስጠሊታውን የታሪካችንን ገጽታ ስናይ በመቶዎችና በሺዎች በሚገመቱ የፖለቲካና ማኅበረሰባዊ ኩይሣዎች እየተቧደንን በሁለንተናዊ የሥነ ልቦናና አካላዊ ጦርነት ለዘመናት መፈሳፈሳችን የወያኔን ተልእኮ ስኬታማነት ለማረጋገጥ ከማገዛችን ውጪ የትም ልንደርስ አልቻልንም፤ ያማረ ንግግር፣ ያማረ የፖለቲካ ፕሮግራምና የተዋበ ፍልስፍናም እንዲሁ የዕውቀታችንን ምጥቀትና የመጻፍ ችሎታችንን ከማሳየት ባለፈ የረዳን ነገር የለም - እንጂ ለምሁር ለምሁርማ ስንት ሺህ ዶክተርና ፕሮፌሰር ሞልቶን አልነበረምን? የጥንት አስተሳሰብ በዘመናዊ ቆዳ ተሸፍኖ በጠበጠን እንጂ ንግግር ዐዋቂና ነገር ሰላቂማ ሞልቶናል፡፡ እናሳ፡- ከእኛ ከኢትዮጵያውያን በላይ ጉዶችና ተዓምረኞች ይገኛልን? “እባብ ልቡን አይቶ እግሩን ነሣው” እንደምንል የብዙዎቻችን ፍላጎት ከአነጋገራችንና ከዐይነ ውኃችን ጭምር ይታወቃል፤ በክፉ አሳባችንም ምክንያት ውጥናችን ሳይጀመር ይከሽፋል፡፡ እናም እንደመፍትሔ ሁላችንም እውነተኞች እንሁን፤ ማስመሰልን እንጠየፍ፤ ለወገናችን የዓዞን ሣይሆን ለልጇ ስትል እንደተወጋችው ጎሽ ከአንጀት እናልቅስ፤ ከዘረኝነትና (የወያኔ... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

[ፋሲካ 2006]

የወያኔ አስቂኝ መመሪያዎችና አዋጆች

ኦልትራፎርድ...(ከገጽ 1 የዞረ)እንግሊዛዊው በኮሚዩኒቲ ሺልድ ዋንጫ ጨዋታ ማንቸስተር

ሲቲን ሲገጥሙ ትኩረት ከሳበ በኋላ ብቃቱ ሊሻሻል አልቻለም፡፡ ሌላኛው ቡድኑን መልቀቁ አይቀሬ የሚመስለው ተጨዋች ጫማውን ይሰቅላል ተብሎ የሚጠበቀው ሪያን ጊግስ ነው፡፡ በብሪታኒያ የትውልዱ እጅግ ስኬታማ ኮከብ የሚሰኘው ዌልሳዊ ዘንድሮ እንዳበቃለት የሜዳ ላይ ደካማ ብቃቱ አሳብቆበታል፡፡ ከዚህ በኋላ በተጨዋችነት ሳይሆን ምናልባት ለወደፊቱ በዩናይትድ የአሰልጣኞች መቀመጫ የመታየት ዕድል እንደሚኖረው ግምቶችን አግኝቷል፡፡

የአጥቂ አማካዮች /የክንፍ ተጫዋቾች/ማንችስተር ዩናይትድ በመሀል ሜዳ ያሉት የተጨዋቾች እጥረ

ት በሌሎች ቦታዎች አይንፀባረቅም፡፡ ቡድኑ በተቀሩት ሚናዎች ጥሩ አማራጮች ነበሩት፡፡ ሳይጠበቅ አስደናቂ የውድድር ዘመን ያሳለፈው አድናን ያኑዛይ በምርጥ ብቃቱ ራሱን እና ቡድኑን ብቻ ሳይሆን ጫና ውስጥ የቆዩትን ሞዬስም ጠቅሟል፡፡ እንዲያውም በውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ ወራት ወጣቱ የቡድኑ እውነተኛ አደጋ ፈጣሪ እና ብቸኛ በጎ ነገር መስሎ ነበር፡፡

የሁዋን ማታ ዝውውር ድንቅ ግዢ ነበር፡፡ በውድድር ዘመኑ አጋማሽ ማንቸስተር ዩናይትድ ከተቀናቃኙ ቼልሲ ያመጣው ስፔናዊ በቶሎ ውጤታማ ብቃት ለማሳየት የተቸገረ ቢመስልም ቀስ በቀስ ከቡድኑ ጋር መዋሃዱን በተግባር ማሳየት ጀምሯል፡፡ ዌይን ሩኒም በ10 ቁጥር ሚና ማጫወት የሚችለው ቡድ በዚህ ቦታ ብዙ አማራጮች አሉት፡፡ በኦልድ ትራፎርድ የአቅሙን እንዲጫወት እድሉ ያልተሰጠው እና በማይመቸው ቦታ እንዲጫወት እየተደረገ የቆየው ሺንጂ ካጋዋ ሌላኛው የቦታው ድንቅ አማራጭ ነው፡፡ ዩናይትድ ምናልባት በሁኔታዎች ተገድዶ ባለተሰጥኦውን ጃፓናዊ በክረምቱ ሊለቀው እንደሚችል መገመት ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ከሩኒ እና ሮቢን ቫን ፔርሲ ጉዳት በኋላ እስያዊው ከማታ ጋር ያሳየው ድንቅ መግባባት ምናልባት ለመቆየቱ ሰበብ ሊሆን ይችላል፡፡

የክንፍ ተጨዋቾቹ ጉዳይ ግራ አጋቢ ነው፡፡ በማንቸስተር ዩናይትድ በቁጥር ጥቂት የማይባሉ የመስመር ተጨዋቾች ቢኖሩም ባለፉት ሁለት ዓመታት ውጤታማ መሆን ከብዷቸዋል፡፡ በተፈጥሯዊው የክንፍ ሚና ድንቅ ችሎታ ያላቸው አንቶኒዮ ቫሌንሲያ፣ ሉዊስ ናኒ እና አሽሊ ያንግ የሚችሉትን እንኳን ለመስራት የተቸገሩበት እንዲሁም በተመሳሳይ መልኩ የሶስቱም ብቃት ለረጅም ጊዜ ወርዶ የመቅረቱ ሰበብ ብዙ ግልፅ አይደለም፡፡ በተለይ ያንግ ወደ ክለቡ ከመጣ ጀምሮ ይህን ነው የሚባል ያልዋዠቀ ብቃት ማሳየት አልቻለም፡፡ የዩናይትድ ደጋፊዎች ከልባቸው ስንብታቸውን በጉጉት ከሚጠብቁባቸው ተጨዋቾች ቀዳሚው ያንግ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ካስቆጠራቸው ጎሎች እና ለጎል ካቀበላቸው ኳሶች ይልቅ ስሙ በይበልጥ ሳይነካ አስመስሎ ከመውደቅ ጋር በተደጋጋሚ መነሳቱም ለክለቡ አፍቃሪዎች ጥሩ ስሜት አልፈጠረም፡፡

ናኒ እና ቫሌንሲያ ቀደም (ኦልትራፎርድ... ወደ ገጽ 13 የዞረ)

Page 4: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 4

Page 5: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 5

የፊታችን ቅዳሜ ኤፕሪል 26 የዳግማይ ትንሣኤ ልዩ የሙዚቃ

ምሽት በዲጄ ቢኬ እና በዲጄ ኤቲ ተዘጋጅቷል።

ይምጡና ይዝናኑ።

Page 6: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 6

የወሩ ታላቅ ዜና

ቴሌፎኑ ለጊዜው ጥሪ አይቀበልም “የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።...” የምትለዋ አሰልቺ የቴሌ መልእክት ያላጋጠመው ቢኖር ወደ ኢትዮጵያ ስልክ ደውሎ የማያውቅ ሰ

ው ብቻ መሆን አለበት። ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ወደ ቀድሞ ወዳጆቻቸው መደዋወል ጀመሩና በመሃል ተስፋ ቆረጡ አሉ። አስር ለሚያህሉ አርሶአደሮች እና የሰራዊቱ አባላት ዘንድ ደውለው አልተሳካለቸውም። ለሁሉም ጥሪ ያገኙት ምላሽ “የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።” የሚል ሲሆንባቸው ራሳቸውን ነቀነ

ቁ። ሰው ሁሉ የጨከነባቸው መሰላቸው። እንዲህም አሉ። “የሃገሬ ሰው እንኳን የስልክ ጥሪ፤ የእናት ሃገር ጥሪስ መች ተቀበለ።”

ክንፉ አሰፋ ለአመታት በተከታታይ በሁለት ድጅት እያደገች ያለች ሃገር የስልክ መ

ስመር ችግር ይገጥማታል ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ችግሩን በደንብ ላልተረዳው፣ ሰው የሞባይል ስልክ የሚገዛው እንዲሁ ይዞ ለመታየት ነው ያስብል ይሆናል። ይህ አባባል በከፊል ትክክል ነው። ዘመናዊ ስልክ በመያዝ ለላንቲካነት ብቻ የሚጠቀሙበት ሰዎች አይጠፉም። የቻይናው ቀፎ ከሞዴል አርሶ አደሮች አልፎ ተራው አርሶ-አደር እጅ ላይም ገብቷል። አብዛኞቹ ግን ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን አይጠቀሙበትም። ለዚህም ይመስላል በርካታ ተንቀሳቃሽ ስልክ የሚይዙ ሰዎች እንዲሁ ለእይታ እና ለላንቲካ ብቻ የሚመስላቸው። አገልግሎቱን በተመለከተ ግን 99 በመቶ የሚሆነው ችግር የ

መዋቅር ችግር ነው። ለዓውዳመቱ ወደ ኢትዮጵያ ስልክ የደወላችሁ ካላችሁ፤ ይህ ነገር እንደ

ገጠማችሁ እርግጥ ነው። ዘንድሮ ደግሞ ቴሌ ከፍቷል። የሞባይሉ መስመርማ እንደ አይን እልም ብሎ ነው የጠፋው። ከበርካታ ሙከራ በኋላ መስመር ያገኘ ሰው ካለ በደስታ ይዘልላል። የተቀባዩም ስልክ ካቃጨለ ተዓምር ነው የሚባለው። ከርማ ብቅ እንደምትለው የአዲስ አበባ መብራት... ልክ እንደ ቧንቧ ውሃ፤ ስልኳም “መጣች - መጣች!” ብሎ መጨፈሩ አይቀርም።

“እንኳን አደረሳችሁ!” ለማለት እኔም ወደ ሃገር ቤት ስልክ መታሁ። “የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።” የ

ሚል መልስ ነበር ያገኘሁት። ለሁለተኛ ግዜ ስሞክር ደግሞ “የደወሉት ስልክ ለግዜው ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ነው።” የሚል ምላሽ አገኘሁ። ደቂቃ ባልሞላ ግዜ ውስጥ ጥሪ ያማይቀበለው ስልክ ከአገልግሎት መስጫ ክልል መውጣቱ አስገረመኝ። ተስፋ ሳልቆርጥ ደገግሜ ሞከርኩ። ቢያንስ ከአስር ግዜ ሙከራ በኋላ፤ መስመር አገኘሁና ሎተሪ የወጣልኝ ያህል ተሰማኝ።

ደስታዬ ግን ብዙም አልዘለቀም። በመሃል እንግዳ ነገር ተፈጠረ። ስልኩን የተቀበለኝ የደወልኩለት ሰው አልነበረም። የተፈጠረው ክስተት - ባለንበት የመረጃ ዘመን እንደ 17ኛው ክፍለዘመን “ቴሌ በኦፐሬተር መስራት ጀመረ እንዴ?” ያሰኛል። ነገሩ ግን ሌላ ነው። ስልኩን ያነሳው የተለመደው የስልክ ጠላፊ ስለመሆኑ አንዳች ጥርጥር አልነበረኝም። ሶማሌያውያን መርከብ ሲጠልፉ ጸሃዩ መንግስታችን ደግሞ የስልክ ፓይረት መሆኑን ሂዩማን ራይትስ ዎች በዚያን ሰሞን ነግሮን ነበርና።

ውጭ ሃገር ያለ ኢትዮጵያዊ ዘመድ ለመጠየቅ መደወሉ አይቀርም። ተስፋ የማይቆርጥ፤ ደጋግሞ ይሞክራል። እንደ እድል የስልኩን መስመር ካገኘ ደግሞ ሌላ ችግር ይገጥመዋል። ዘው ብለው የሚገቡ የስልክ ጠላፊዎች መስመሩን ያውኩታል። ሌላው አማራጭ ደግሞ አጭር የጽሁፍ መልእክት ነው። በኢትዮጵያ ቴሌኮም አጭር መልእክት ከመላክ ይልቅ ደብዳ

ቤ ጽፎ በፖስታ መላኩ እየፈጠነ መጥቷል። አጭር መልእክት የሚደርሰው ከቀናት ብኋላ ነው። ከላኪው ዘንድ መልዕክቱ መድረሱ ቢረጋገጥም ተቀባዩ ጋ ጨርሶ ላይደርስም ይችላል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ በሰጡት ጋዤጣዊ መግለጫ “የኢትዮጵያ ቴሌኮም ቴክኖሎጂ ከዴንማርክ፣ ከኖርዌይ እና በከፊል ከእንግሊዝ ቴክኖሎጂ ጋር አንድ ነው” ብለው ነበር። በዚህ መግለጫቸው አቶ ሃይለማርያም የኢትዮጵያን የኢንተርኔት አገልግሎት፣ እንዲሁም የስልክ መስመሩ ጥራት እና አስተማማኝነት በደንብ አድርገው ነበር “ለጋዜጠኞቹ” የገለጹላቸው። ይህን ተናግረው እንዳበቁ ግን የራሳቸውም ስልክ መጠለፉን ሰማን። ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንዲሉ አልሰሙት ይሆናል እንጂ፤ “እኛ ሲም ካርድ፤ አንተ ደግሞ ቀፎ ነህ!” ይሏቸዋል - ከላይ

ና ከታች ያሉ አለቆቻቸው። የኢትዮጵያን ስልክ አገልግሎት ከዴንማርክ፣ ኖ

ርዌይ እና እንግሊዝ ጋር አወዳድረው ማወደሳቸው ግን ራሳቸው ካዴሬዎቹንም ሳይቀር ሳያሰፍራቸው አልቀረም። ሰውየው የኢትዮጵያን ቴሌኮም እያወዳደሩ ያሉት 99.9 በመቶ ሳያቋርጥ አገልግሎት ከሚሰጠው አራተኛው ጀንሬሽን የምእራቡ ቴክኖሎጂ ጋር ነው። መቼም ሁሉም ይዋሻሉ። ነብሳቸውን ይመርና አቶ መለስ ዜናዊም ይዋሹ ነበር። ለዛ ያለው ውሸት አለ። እጅ፣ እግርና አይን የሌለው ውሸትም አለ። እንዲህ አይነት ያፈጠጠ ውሸት ግን እመራዋለሁ የሚሉትንም ሕዝብ እንደመናቅ ይቆጠራል። እኚህ ሰው የሞራል እሴታቸውን ሁሉ አሽቀንጥረው ሊጥሉት ይችሉ ይሆናል። ምሁራዊ ግብአታቸውንም ለተራ ፖለቲካ ጥቅም ሊያስወግዱት ይችላሉ። እምነታቸውስ እንዲህ አይነቱን ቅጥፈት ይፈቅድላቸው ይሆን?

የቴሌ የኢንተርኔት አገልግሎት የመንግስት አልባዋ ሶማልያን አንድ መቶኛም። ኮሜዲያን ክበበው ገዳ እንደቀልድ የነገረኝ ቁም-ነገር የኢትዮጵያን ኢንተርኔት ፍጥነት በደንብ ይገልጸዋል። ክበበው ሰሜን አሜሪካ የስራ ጉብኝቱ ወቅት ፎቶ ተነስቶ ለቤተሰቡ በኢሜይል ይልካል። የላከው ፎቶ መድረሱን ለማረጋገጥ በነጋታው ወደ አዲስ አበባ ደወለ።

“ፎቶ ደረሰ?” “አልደረሰም!”ሌላ ቀን እንደገና ደውሎ የላከው ፎቶ እንዳልደ

ረሰ ተነገረው። ለሶስተኛ ግዜ ደውሎ ኢሜይሉ እንደደረሰ ጠየቀ። አሁንም አልደረሰም ተባለ። እንዲህ እያለ ሳምንት ሞላው።

“በሳምንቱ እኔ ቀድሜ ደረስኩ።” ነበር ያለው ክበበው። የኢሜይል መልእክቱ መድረሱ ከተረጋገጠ በኋላ - ሌላ ችግር ገጠመው። ኢሜ

ይሉ ሲከፈት ግማሽ አካሉን ነበር የሚያሳየው። ፎቶው እስኪያወርድ (ዳውንሎድ እስኪያደርግ) ደግሞ ግማሽ ቀን መፍጀቱ ግድ ነበር።

ይህንን አገልግሎት ነው አቶ ሃይለማርያም ከምእራቡ አለም አገልግሎት ጥራትና ፍጥነት ጋር እያወዳደሩ የሚነገሩን። በአስር ሜትር ርቀት ላይ ሆኖ በስልክ መገኛ

ኘት ህልም በሆነበት ሃገር፤ ስለ ስልክ ጥራት መናገር ቅጥፈት ብቻ ሳይሆን የሰውየውንም የሞራል ውድቀት ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ቴሌኮም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀጥሎ ትልቅና ግዙፍ የሃገሪቱ ተቋም ነው። እድገቱ ግን ያሳዝናል። በአስር አመት ግዜ ውስጥ ብቻ እንኳን እድገቱ በ75 በመቶ ቁልቁል ወርዷል። ለዚህ ዋናው ምክንያት ተቋሙ አገልግሎት መስጠቱን አቁሞ ወደ ስለላ ተቋም መቀየሩ ነው። ባለፈው ወር ይፋ የሆነው ባለ 100 ገጹ የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ ይህንን መንግስታዊ የስልክ እና የኢንተርኔት ጠለፋ አረጋግጧል።

“የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የነበረን አንድ ዜጋ አፍነው ካሰሩት በኋላ ውጭ የተደዋወለበትን የስልክ ቁጥር ዝርዝር አሳዩት።” ይላል ጠቀማጭነቱ ዩናይትድ ስቴትስ የሆነው አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም። ሰውየው የታሰረው ያልተከፈለ የስልክ ሂሳብ ኖሮበት አልነበረም። ባለስልጣናቱንም አ

ላማም፣ ወይንም መንግስትን በሃይል ለመገልበጥ አላሴረም። ወንጀሉ፤ ከውጭ ሃገር ስልክ ስለተደወለለትና ከወዳጅ ዘመዶቹ ስለተወያየ ብቻ ነበር። ይህ ደግሞ ፍጹም እንግዳ ነገር ነው። ከተለምዶ ልማታዊ (ቴሌፎኑ.... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

እንደዘበት ያለፉት ነፍሶች(እውነተኛ የወንጀል ታሪክ)

እነዚህ ሁለት የወንጀል ታሪኮች የተፈፀሙበት ጊዜ ጥቂት ዓመታት ወደኋላ ይርቃል፡፡ ሁለቱም ወንጀሎች የተለያዩና የሚያገናኛቸው ነገር የሌለ ቢሆንም ማጠቃለያቸው ግን ሞት መሆኑ ያመሳስላቸዋል፡፡ በተለይ በተለይ የህይወት ህልፈቱ ሳይታሰብ እንደዘበት መፈጠሩ ‹የተቆረጠለት ቀን› የሚባለውን አይነት አሟሟት ያስታውሳል፡፡ ሁለት ነፍሶች በተለያየ ዓመት በተለያየ ሁኔታ በተለያዩ ቀናትና በተለያየ ምክንያት እንደዘበት አልፈዋል፡፡ ሳይታቀድና ሳይታሰብ ህይወታቸውን የተቀሙት ሰዎች መቃብር ውሎባቸው- ገዳዮቹም አስር ቤት አሽጓቸው ተረሳስተዋል፡፡

አንድ ቀልድ የጠራው ሞትጥር ወር 1996 ዓ.ም

አዲስ አበባየየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 ነዋሪ ‹አንዳች እንከን የማይወጣለት ፍቅር ያላቸው ናቸው› ይላ

ል፡፡ ለዓመታት በመቀራረብና በመተሳሰብ የዘለቁት ጓደኛሞች ፍቅራቸው ለብዙሃን ምሳሌ ሆኖም ኖሯል፡፡ በመካከላቸው ያለው የእምነት ልዩነት፤ የህይወት ፍልስፍና አለመገናኘት፤ የቤተሰብ ሁኔታ አንድ አለመሆንና ሌሎችም የጋራ ያልሆኑ መለያዎቻቸው ቢበዙም ከዚህ ሁሉ በላይ ገዝፎ የወጣ የጓደኝነት ፍቅራቸው ሁሉን አስረስቷቸው አንድ አድርጓቸዋል፡፡ እንደብዙዎቹ እምነት የጓደኝነት ሙሉ ትርጉም ስፍራ ይዞ የሚታየውና ጎልቶ የሚንፀባረቀው በእነዚህ ሰዎች ነው፡፡

ሁለቱ ወዳጆች አብረው የሚበሉ አብረው የሚጠጡ መሆናቸው ብቻ አይደለም ‹ጓደኛ› የሚለውን ስያሜ ያሰጣቸው፡፡ ሁለቱም ከመብላትና ከመጠጣት በላይ የህይወታቸውን ክፍተት የሚሞሉበትን ፍቅር መሰጣጣት የቻሉ ነበሩ፡፡ አንዱ ሲቸግረው ሌላው እየረዳው፤ አንዱ ሲጨንቀው ሌላው እያዋየው፤ አንዱ ደስ ሲለው ከሌላው እየተካፈለው ስሜታቸውን እየተጋሩት ኖረዋል፡፡ መወለድ ቋንቋ ነው እስከሚባል ድረስ ሁለቱ ወዳጆች አምሳልነታቸውን አንድ አድርገው ዘልቀዋል፡፡ ዓመታትን የተሻገሩትና የወዳጅነታቸውን ዘመን ትሩፋት የተቋደሱት በመካከላቸው ባለው ፍቅርና መቻቻል ነው፡፡ ለዚህም ይሆናል አንዱ ሌላውን ሲያስተዋውቅ ‹ጓደኛዬ ነው› የሚለው ቃል ብቻውን የሚወክልለት የማይመስለውም፡፡ ‹እንደወንድሜ የማየው ጓደኛዬ ነው› በሚል ቃል የወዳጅነታቸውን ልክ ሞቅ አድርጎ መግለፅን ነው የሚያዘወትሩት፡፡

ብዙዎች የእነዚህን ወዳጅነትና ፍቅር ይቀኑበት ነበርና የአብሮነታቸው ‹ሳይንስ› ለማወቅ ይጥሩ ነበር፡፡ ከሁለቱም ጋር የቅርብ እውቂያ የነበረው ወጣት እንደገለፀው ጓደኛሞቹን አንድ ያደረጋቸው ነገር ሁለቱም ቀልድና ጨዋታ መውደዳቸው ነው፡፡ ‹‹መጫወትና መቀለድ ይወዳሉ፡፡ እንደ ህፃን ልጅ ይላፋሉ፡፡ ይደባደባሉ፡፡ ሰዎች እስከሚገርማቸው ድረስ አይለያዩም፡፡ እንደውም አንዱ ሌላውን ካጣው ‹ሳላይህ ስውል ትናፍቀኛለህ› የሚባባሉ ወጣቶች ናቸው፡፡ ይህ ቅርርባቸው አንዱ ሌላውን እንደራሱ አድርጎ እስኪያውቀው ድረስ ልብ ለልብ ያጣመራቸውን ሁኔታ ፈጥሮም ነበር፡፡

አልፎ አልፎ ቢጋጩም ፀባያቸው ብዙም አይከርርም ነው የሚሉት የሚያውቋቸው፡፡ አንድ ሰው ‹‹ሁለቱም ለሳቅና ለጨዋታ ቅርብ የመሆናቸውን ያህል ለኩርፊያም ያንኑ ያህል ናቸው፡፡ ነገር ግን ኩርፊያቸው ራሱ የቀልድ ስለሆነ የሚያመር የለም፡፡ ለምን አኮረፍከኝ ብሎ መጠያየቅም የለም፡፡ ራሳቸው ማንም ሳይመጣ ይቀራረቡና መኮራረፋቸውን እንኳን ይረሱታል፡፡ ኩርፊያ ሲባል ታዲያ ከሰዓታት ያልዘለለው ዓይነት እንጂ ቀናት የሚፈጀው አይደለም›› ብለዋል፡፡

ጥር 23 ቀን 1996 ዓ.ምቀን ላይ ሁለቱም ከየዋሉበት መጥተው ተገናኙ፡፡ የዋሉበትም እዚያው ቀበሌ 15 ክልል ‹‹ኬር

ኢትዮጵያ እርዳታ ድርጅት›› አካባቢ ነው፡፡ በተለመደው ፍቅርና ሰው ባወቀው የወዳጅነት ውሏቸው ነው ዛሬም የቀጠሉት፡፡ የሚያወቋቸው ሰዎች በሁለቱም ላይ ያነበቡት የተለየ ገፅታ የለም፡፡ የተለመደው ሳቅ- የተለመደው ጨዋታ- የተለመደው ልፊያ- የተለመደው መጎነታተል ዛሬም አለ፡፡ ያያቸው ማንነታቸውን እንኳ ከማወቁ በፊት የአብሮነታቸውን ፍቅር ከፊታቸው የሚቀዳባቸው ሁለቱ ጓደኛሞች ዛሬን እስከ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ያሳለፉት ከዚህ ባልተለየ ሁኔታ ነው፡፡ በመጨረሻ ላይ ግን አንድ ቃል ከሁለቱ ፍቅር መሀል ጥለቅ አለች፡፡ ‹‹ሸፋፋ›› የምትል ቃል፡፡

ተናጋሪው የዘወትሩ ንግግሩን ውጤት የጠበቀ ከፈገግታና ከሳቅ ጋር የሚመላለስ ምላሽ ውስጥ ነው፡፡ አንደኛው እግሩ በመጠኑ ዘወር ያለ መሆኑን አይቶ ነው ሌላውን ሸፋፋ ብሎ የሰደበው፡፡ በእርግጥ ከዚህ ቀደም ይህንን ቃል ተጠቅሞበት አያውቅም ነበር፡፡ ተሰዳቢው ‹ሸፋፋ› የሚለውን የቀልድ ስድብ ሲያደምጥ ውስጡ አንዳች ቁጣ የተተራመሰ መሰለው፡፡ ዘወትር እንደሚያደርጉት ያለ መተራረብ ነውና ተናጋሪው ከአፉ ለወጣው ቃል ቀልብ የሰጠው አልመሰለም፡፡ ከዚህ ቃል በኋላ የዕለቱ የፍቅር ውሏቸው ተቋጨና ተለያዩ፡፡ ተናጋሪው በውስጡ ነገን እየናፈቀና አብረው የሚውሉበትን ሰዓት እያሰበ ወደ ቤቱ ሲገባ ‹ሸፋፋ› የተባለው ደግሞ ከራሱ ጋር እያወራና ብስጭቱ ያመጣበትን ግልፍተኝነት ለማረጋጋት እየሞከረ ሄደ፡፡ ጥቂት ሰዓታት አለፉ፡፡

ተናጋሪው ሰውዬ ከቤቱ ወጣ፡፡ ሚስቱና ልጁን ሰላም ብሎ ወደ ጎረቤት ነበር አወጣጡ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቴሌቪዥን ለማየት ነው፡፡ ቤቱ ቴሌቪዥን የሌለ በመሆኑ ጎረቤት ወዳለው ጓደኛው ነበር የሄደው፡፡ እዚያ እየተጫወተና በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ሙዚቃ እየኮመኮመ ቆየ፡፡ ቀኑ ማመሻሸት ጀምሮ ነበርና ልቡ ወደ ቤቱ በመሄድና እዚያው በመቆየት መካከል ሲወላውል ስሙ ሲጠራ የሰማ መሰለው፡፡ የልጁ ድምፅ ነው፡፡ ‹አባዬ ና ትፈለጋለህ› ሲል ሰማው፡፡

ይህን የ10 ዓመት ህፃን የላከው የአባቱ ጓደኛ የሆነው ያ ‹ሸፋፋ› ተብሎ የተተረበ ሰው ነው፡፡ በልቡ ያሰበውን እኩይ ተግባር አንግቦ ወደዚህ ወዳጁ ቤት ሲመጣ በዚያ እሳት የለበሰ ስሜቱ ውስጥ እንዳለ ሆኖ የፈለገውን ማግኘት አልቻለም፡፡ የሰውየው ሚስት ‹ባልሽ የት ሄደ?› ተብላ ስትጠየቅ ነገሩ ስላላማራት ቤት አለመኖሩን ትናገራለች፡፡ ምንም የማያውቀው የ10 ዓመት ህፃን ደግሞ ብቅ ብሎ ‹አለ- ጎረቤት ቴሌቪዥን ሊያይ ሄዶ ነው› በማለቱ ነው ጥራው ተብሎ የጠራው፡፡

የሚፈልገው ሰው ማን እንደሆነ ለማወቅ ብቅ ያለው ወጣት ጓደኛው መሆኑን ሲያውቅ ፈገግ ብሎ ተናገረው፡፡ ‹‹ምነው በሰላም ነው? አብረን (እንደዘበት.... ወደ ገጽ 14 የዞረ)

SUB-SAHARAN AFRICAN YOUTH and FAMILY SERVICES (SAYFSM)

Lakkoofsa bilbilaa፡ (651)644-3983, (651)644-1470, (612)554-5676የስልክ ቁጥር፤ (651)644-3983, (651)644-1470, (612)554-5676

SAYFSM Dhaaba Hawaasummaa namoota dhalootan Afrikaanota ta’aniifi tajaajila garaagaraa kan laatudha.-Daddarbaa Vayirasii HIV/AIDS to’achuudhaafi dhaabni kun (SAYFSM) barnoota fayyummaa barsiisa, Kondomii raabsa, akkasumas qorannaa dhiigaa tola hojjeata-Qorannaan dhiigaa kun namoota leenjii ga’aa fi ragaa ogummaa qa-baniin raawwatama-Namnni fedha qoratamuu qabu waajjira SAYFSM keessatti yookiin bakka abbaan dhiimmaa itti amanetti qoratamuu danda’a-Namni nubiratti (SAYFSM) qoratamu icitiin odeeffannoosaa sadarkaa cimaatti eegama.**************************************************************************** SAYFSM Dhaabbata MNsure wajjin walii galuudhan namoota In-shuuraansii fayyaa hinqabneefi gargaarsa iyyannoo barreessuu laataHanga ammaatti jiraattota Minnesota tiifi gargaarsa heddu kennee jiraOdeeffannoon abbaan dhimmaa himatu hundi icitiidhaan eegamaMNsure tti iyyannoo galfachuu yoo barbaaddan beellama otuu hin qa-batin yeroo gabaabaa keessatti dhimma keessan xumurattu

* SAYFSM በትዉልድ አፍሪካዊያን ለሆኑ ግለሰቦች የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሰብአዊ ድርጅት ነዉ፤* የ HIV/AIDSን ስርጭት ለመግታት ድርጅቱ (SAYFSM) ኮንዶም ያድላል፣ የጤና ትምህርትና የምክር አገልግሎት ይሰጣል፣ ነጻ የደም ምርመራ ያከናዉናል፤* የደም ምርመራዉ በቂ ስልጥና ባላቸዉና ችሎታቸዉ በተመሰከረላቸዉ ባለሙያዎች ይከናወናል፤* HIV ለመመርመር ፍላጎት ያለዉ ማንኛዉም ግለሰብ በድርጅቱ በጽህፈት ቤት ወይንም ባለጉዳዪ ባመነበት ቦታ ምርመራዉ ሊከናወን ይችላል* በ SAYFSM ምርመራ የሚደረግለት ግለሰብ ሚስጥራዊ መረጃዉ በከፍተኛ ደረጃ ይጠበቃል። ***************************************************** SAYFSM ከMNsure ጋር በመተባበር የህክምና እንሹራንስ ለሌላቸዉ ግለሰቦች የማመልከቻ ቅጽ በመሙላት ሁኔታዉ በፈቀደ መሰረት እንሹራንስ እንዲያገኙ እርዳታ ያደርጋል* እስከ አሁን ድረስ ለብዙሃኑ የሚኒሶታ ነዋሪዎች በርካታ አገልግሎት ሰጥቷል* ባለጉዳይ የሚሰጠን መረጃ በሚስጥር ይጠበቃል* በ MNsure ድረግጽ (web site)የማመልከቻ ቅጽ ለመሙላት ከፈለጉ ያለቀጠሮ ጉዳይዎን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ይፈጽማሉ

1885 University Ave. W #297 St. Paul, MN 55104 Phone: 651-644-3983

Page 7: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

ፖለቲካ ኢኮኖሚ አሜሪካ ማኅበረሰብ

ከጸጋዬ ገብረመድህን አረአያ(የቀድሞው ጦቢያ መጽሔት አምደኛ)

“ መኳንንቶቼ፣ ልጆቼና ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ስለ እናቴ ኢትዮጵያ ሕይወቴን ልሰዋላት ሙሉ ፈቃድ አለኝ። በእኔ ልብ ያለው አሳብ በትክክል በእናንተም ልብ በመታሰቡ በጣም ደስ ብሎኛል።

“ እንግዲህ አሳባችን አንድ ከሆነ ጠንክሩ እንጂ አትፍሩ። ለዘመቻውም አዋጅ አናግራለሁና አይዞአችሁ አትፍሩ!

“ አገሬ ሆይ ስሚ! መኳንንቶቼ፣ ወታደሮቼ፣ ሕዝቦቼ ስሙ…..ወደፊት ገስግሱ እንጂ ወደኋላ አትቅሩ!

“ የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ! ልብ አድርገህ ተመልከት ኢትዮጵያ የተባለችው አንደኛ እናትህ ናት! ሁለተኛ ዘውድህ ናት! ሦስተኛ ሚስትህ ናት! አራተኛ ልጅህ ናት! አምስተኛ መቃብርህ ናት! እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀኸው ተነሳ!”

አንበሳው አጼ ዮሐንስ- ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያለእናታቸው፣ ለሚስታቸው፣ ለልጃቸው፣ ለዘውዳቸውና ለ

መቃብራቸው የተሰውትና በሕይወት ዘመናቸው “አንበሳው አጤ ዮሐንስ” እየተባሉ ይጠሩ የነበሩት ሰማዕት ከሞቱ 125 ዓመት ሆናቸው። አንድ አሜሪካዊ ታጋይ በ1775 በአንድ የፊላደልፊያ ፍርድ ቤት ቀርቦ የታላቁን የእንግሊዝ መንግሥት አመራር በመቃወም በፈፀመው ወንጀል እንዲሰቀል ሲፈረድበት የተናገረው ተጠቃሽ ቃል ነበር። “አዝናለሁ እግዚአብሔር አንድ ነፍስ ብቻ ስለሰጠኝ” ነበር ያለው። አጤ ዮሐንስን በዚያ ታሪካዊ ብጽአት የምለካቸው፣ በዚያው ራሳቸው በመደቡት የወርቅ ሚዛን የምመዝናቸውና ለኢትዮጵያ ተከታታይ ትውልዶች ሁሉ ዘላለማዊ ብሔራዊ ቃል ኪዳን ቀርጸው ያለፉ ታላቅ መሪ ስለሆኑ ነው። በዚህ መስፈርት የኖሩም ናቸው። ደርቡሽ ጀግናውን መሪ ገድያለሁ፣ አንገቱንም ቆርጨ ወስጄ ተጫውቸበታለሁ ሊል ይችላል። ዮሐንስ ተገድሎ የኢትዮጵያ መሬት በደርቡሽ ተወስዶ ቢሆን ቁጭቱ ባነደደን ነበር። እስከማዕዜኑ። ቢያንስ 125 ዓመት የዚያ አካባቢ ኢትዮጵያዊ መሬትነት ተጠብቆ ቆይቶአል። ደርቡሽ የደፈረንስ አሁን ነው። አገር ሲያረጅ እሾህና አሜከላ ያበቅላልና!

አጤ ዮሐንስ - ራሳቸው ባሰፈሩት መዳልው መሠረት ለእናታቸው፣ ለሚስታቸው፣ ለልጃቸው፣ ለዘውዳቸውና ለመቃብራቸው ሕይወታቸውን “ለመሰዋት ሙሉ ፈቃድ አለኝ” እንዳሉት ጽዋውን ተጐንጭተው አለፉ። ልቅሶ መቀመጥ የሚገባቸው “እናታቸው፣ ልጃቸው፣ ሚስታቸው፣ ዘውዳቸውና መቃብራቸው” ደግሞ እንደ ዘመኑ ባህል ቅቤ መቀባት የነበረባቸው ይመስለኛል። በደስታ የሚሞትላቸው መሪ መታደል እንደ ቀላል ነገር የሚታይ አይደለማ። እኔስ በእኔው ደረጃና አጋጣሚውን አውቀዋለሁ። ከጉራና ከአጉል መንጠራራት ጋር ካላያችሁብኝ።

አንድ ጊዜ በጦቢያ ላይ በወጣ ጽሑፍ ምክንያት ከከፍተኛው ፍርድ ቤት እመላለስ ነበር። እንዳጋጣሚ ታላቅ እህቴ ማን እንደነገራት ሳላውቅ በመጨረሻው የፍርድ ዕለት ችሎቱ ሲከፈት ከሕዝቡ መሐል ጉብ ብላለች። እህቴን ሳያት “አርፈህ ብትቀመጥስ? አንተ ታማሚ ነህና ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርገህ ተቀመጥ- እኛንም በስጋት ጨረስኸን” ብላ ትጨቀጭቀኛለች ብዬ ጥርሶቼን ሳፉዋጭ ቆየሁ። ወዲያው ተጠራሁና ፍርደ ገምድሉን የእነ ሽመልስ ከማል ውሳኔ ተቀብዬ የተጣለብኝን አሥር ሺህ ብር መቀጮ ጓደኞቼ ከፍለው ወጣሁ። ከመኪናችን ውስጥ ሁለቱ የጦቢያ አርበኞች ደርበውና ጐሹ ነበሩ። እህቴ ዘርትሁን ከእኛው ጋር ትዳበላለች። አሁን ካሁን ጭቅጭቅዋን ትጀምራለች ስል “በሉ ከሰዓት በኋላ ሁለት ላሞች ሸጨ አሥሩን ሺ ብር እሰጣችኋለሁ። በእኔ በኩል ዛሬ የፌስታዬ ቀን ነው። የጀግና እህት ሆኛለሁ። እግዚአብሔር እኔን ጀግና አድርጐ አልፈጠረኝም። ወንድሜ ከወያኔ ጋር ተቋቁሞ…እንዲህ ሲያስከብረኝ ምነዋ አልደሰት! ሁላችንም በዕድሜና በበሽታ ተቀፍድደን ነው እንጂ ኑሮአችን በዱር በሆነ ነ

በር። አዎን እንደ ደሀ ጨርቅ በመርፌ እየተጠቀጠቅን.. ሽባ ሆነን ጠበቅናቸው” ስትል ሆደ ቡቡ ነኝና እንባዬን ስለቅቀው ሁለቱ ጓደኞቼ ለብዙ ጊዜ የእህቴን ንግግር የመጽናናት መልእክትና የሕዝባችንን ባሮሜትር መለኪያ ያደረጉት ይመስለኛል።( ዛሬ እህቴ ከዘመናት ክስለት በኋላ አርፋለች)

ጌቶቼና እመቤቶቼ፣ ወንድሞቼና እህቶቼ- ልጆቼም! አንድ ውለታ ዋሉልኝ። የአጤ ዮሐንስን አዋጅና ኢትዮጵያን በምን እንደመሰሉአት መላልሳችሁ አንብቡልኝ። መለስ ዜናዊና እሱን ለመሆን የሚፈልጉ ፍጡራን ለመሆኑ ይህን መሆን ሳይሆን ለማንበብ እንኳ እንደሚደነግጡ አይሰማችሁም? ኢትዮጵያ እናት፣ ልጅ፣ ሚስት፣ ዘውድ፣ መቃብር..ሁሉንም ናት። አጤ ዮሐንስን ሠራዊታቸው- የጦር አበጋዞቻቸውና ጭፍራው በሙሉ ያደነቃቸው ፊት ለፊት ፈረሳቸውን እየጋለቡና እንደ አንበሳ እየተጐማለሉ የሚመሩ ጀግና በመሆናቸው ነው። በአዋጁ ላይ እንደተመለከተው ሠራዊታቸውን በማሳሳት መልክ እንኳ ከኋላ አልተከተሉም። በመሐል ሆነው አልተደበቁም። ምሽግ አሠርተው፣ እርድ አስቆፍረው ከዚያ መምራትን አልፈለጉም። እንደ ንጉሥ ዳዊትና እንደ ትልቁ እስክንድር - እንደ አቲላና እንደ ጄንጂስካን ሠራዊታቸውን ከፊት ለፊት የመሩ ልዩ ፍጥረት ነበሩ። The Leadership Secrets of the Rogue Warrior የሚለውን ሪቻርድ ማርኪንጐን አሥርቱ ትእዛዛት ሳነብብ ነበር፤ የመጀመርያውን ትእዛዝ- በእንግሊዝኛው ላስቀምጠው - I am the war lord and the wrathful God of combat and I will always lead you from the front, not the rear በአማርኛው እኔ የጦር መሪና የትግል አምላክ መቅሰፍት ነኝ። ከፊት ለፊት እንጂ ከኋላ ሆኜ አልመራችሁም። እንደማለት ሲሆን በሦስተኛው ትእዛዙ ደግሞ “ እኔ አስቀድሜ የማላደርገውን እንድታደርጉ አልሻም። በዚህም መሠረት እንደኔ ያላችሁ የጦር መኰንኖች ሆናችሁ ትቀረጻላችሁ” ይላል። (የሪቻርድ ማርኪንኮን ሌሎች ትእዛዞችና ለአገር ገድሎ የመሞትን ብፅአት ዛሬ ዘርግፌ ለማለፍ አልሻም። ብቻ ዕድሜውን ይስጠን)

በዚህ ጽሑፍ የመጀመርያው አንቀጽ ላይ የአጤ ዮሐንስ አዋጅና የአገር ምንነት ትርጉም ውብ ሆኖ ቀርቦአል ባይ ነኝ። የንጉሠ ነገሥቱ ቆራጥ ውሳኔ፣ በመሪዎቹና በሕዝቡ መካከል ሊኖር የሚገባው ቁርኝት በግልጽ ታይቶአል። በእኔ እምነት አጤ ዮሐንስ በዚያ ሰዓት የተናገሩት “ቃል ኪዳን” ከኢትዮጵያ ጋር ኢትዮጵያውያን ያካሄዱት ቃለ መሐላ ነበር። ትውልዶች እስከ ምጽአት ድረስ የሚቀባበሉትም መሐላ ነው። በእኔ እምነት ዜግነታቸውን ወደ እንግሊዛዊነት፣ ወደ ጀርመንነት፣ ወደ አሜሪካዊነት የለወጡ እንኳ ሳይቀሩ ኢትዮጵያን በተመለከተ በዚህ ቃል ኪዳን ታስረዋል። እንዲያውም በሚቀጥሉት ወራት ይህንን ቃለ ብፅአት (የአጤ ዮሐንስ የአገር ትርጉም) ቢቻል በየቤታችን በመስተዋት ሰቅለን እንደውዳሴ ማርያም የምናነበንበው መሆን አለበት። የምንኮራበት ቃል- ከአገራችን ጋር ያለንን ኪዳን የምናሳውቅበት ሊሆን ይገባዋል።

የታሪክ ጸሐፊዎች በ19ኛውና በሃያኛው ክፍለ ዘመን የነበሩትን ነገሥታት የሚገመግሙባቸው ሁኔታዎች ሞልተዋል። ወደ ታሪክ ፈጠራና ድርሳነ ደናቁርት የሚያዘነብሉ ደግሞ አየር ዘግነው የሚያወሩት አላቸው፤ የሆነው ሁሉ ሆኖአል። ማናቸውም መሪዎች የኢትዮጵያ መሪዎች ነበሩ። ወደ ውድቀት የወሰዱን ካሉ ታሪክና የአገሪቱ አምላክ ፍትሕ ይሰጣቸዋል። ወደ አኩሪ ድል የመሩንና ያኰሩንን ደግሞ ዛሬ የተፈጠረው ጫጫታና የደንባሮች ሁካታ ሳይሆን ታሪክ ነፃ ያወጣቸዋል። እውነት አርነት ያወጣልና! (የኩባው አብዮታዊ መሪ መፈክርና የትዝታ መጽሐፉ ርእስ History Absolves Me- ታሪክ ይፈርድልኛል የሚል ነው።) በዛሬ ሚዛን- በዛሬው ነፃ ያልወጣና ገና ነፃ መውጣት ባለበት ፍርድ ቤት ሳይሆን በፍትሕ አማልእክት ፍርድ ቤት።

እንደ ማናቸውም የ18ኛና 19ኛ ምዕት ዓመት ነገሥታችን አጤ ዮሐንስ በሩቅ ብዕሲነት (በሰውነታቸው) የሚወቀሱበትና የ

ሚከሰሱበት ውሳኔና አቋም አላቸው። ጄኔራል ናፒየር በአጤ ቴዎድሮስ ላይ ዘመቻ ሲከፍት ከወራሪው ጋር በመቆም፣ የኢትዮጵያን ሙስሊሞች በግድ ክርስትና እንዲነሡ፣ አለዚያ እንዲደመሰሱ አቋም በመውሰድ፣ ከንጉሥ ተክለ ሐይማኖት ጋር በመጋጨታቸው ብቻ ጐጃምን “በማቃጠል”ና የብዙሃኑን ሕዝብ ዓይን በጋለ ብረት በማቃጠል፣ ከአድሚራል ሒወት ጋር በተደረገው ውል ፀረ ኢምፔሪያሊስት አቋም ይዘው ይታገሉ የነበሩትን ደርቡሾች በማስቀየምና በማነሣሣት…..ይወቀሳሉ። አላውቅም የእኔንም አንዱን ቅም አያት ገድለው ይሆናል። ይህን ሁሉ ለአጤ ዮሐንስ ወንጀለኛነት አላነሣም። ላምንም አልፈልግም። ዮሐንስ ለኢትዮጵያ ትርጉም የሰጠ “የኢትዮጵያ ልጅ-- የኢትዮጵያ ባል…የኢትዮጵያ ዘውድ ነበር!”

“አጤ ቴዎድሮስ ብዙ ገደለ፣ ጐንደር ተኝታ ያደረችው ቴዎድሮስ የሞተ ዕለት ነው። ወይም እንደ አንዱ እንግሊዛዊ አላን ሙርሔድ አገላለጥ “ A mad dog let loose in Abyssinia” ነበር። “ይኸ ሁሉ ጥራዝ ነጠቆች አዋቂ ለመባል የሚያራግፉት ተራና ተርታ ኦለቲካ ነው። እንዲያውም ጠላቶቻችንና ጥራዝ ነጠቅ ሒሰኞች ቴዎድሮስን ከዚህ በከፋ ሁኔታ ገልጠውታል። እንደ ገና ምኒልክን ጡት ቆራጭ፣ አምስት ሚሊዮን ኦሮሞ የጨፈጨፈ ግፈኛ ተስፋፊ የሚያደርጉ አሉ። በአየሩ ውስጥ ያለው ቁጥር አለማለቁ! በዚህ ደግሞ ወያኔ ከቁጥር በሽታ አለመዳኑ…! ( አንድ ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የጻፍኋት መጠነኛ ሽሙጥ ነበረች። ተሳካልኝና። ነገሩ እንዲህ ነበር። የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነች አንዲት የቀይ መስቀል ሠራተኛ በደርግ ጊዜ ወያኔ ገደልሁ ያለውን ሠራዊት ቁጥር ደመረችና ከኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ጋር እኩል ይሆንባታል። ከዚህ በመነሳት ነበር እኔ “ከሚመጡት ትውልዶች በመዋስ ነው የገደሉት” ያልሁት። አሁን ሳስበው ደግሞ በሽፍትነት ጊዜያቸው ያልቻሉትን አሁን ተሳክቶላቸዋል። እየገደሉ ናቸው። “ኦሮሞዎች ነን” የሚሉትና መለስ እንደሚለው ግን ፋቅ ፋቅ ሲያደርጉአቸው ወይም ጭንብላቸው ሲወልቅ ወያኔዎች የሆኑ ወገኖች ምኒልክ በዚህ መልክ ከትውልዶች ተበድሮ መግደሉን ይነግሩናል። ጌታ በወንጌሉ እነዚህን ቅዱሳንን ለመግደል፣ ለመስቀልና ለመውገር የተነሡ ኅይሎችን “የሚያደርጉትን አያውቁምና..ማራቸው” ይላል። ከምሕረቱ ተጠቃሚዎች ሊሆኑ ከቻሉ! አለዚያ ግን እነዚህ ነገሥታት ሁሉም እንደ ዘመናቸውና እንደ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች- ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግና ጠላቶችዋን በመመከት ረገድ ከአገሪቱና ከሕዝቡ ጋር ቃል ኪዳን የነበራቸው መሪዎች ናቸው። ጣባቦቹ የአድዋ መኳንንት አጤ ዮሐንስ የተወለዱት በተምቤን በመሆኑ ምን እያደረጉ እንደሆነ እየታዘብን ነው።

ባለፉት ሃያ ሦስት ዓመታት ከዚህ ልክፍትና በሽታ ያልተላቀቁት የሽብር ሪፐብሊክ ካድሬዎች የአድዋን ጦርነት ድል ያለ ምኒልክና ያለ ጣይቱ ለማክበር ሲሩዋሩዋጡ ነበር። ስሙን ለመጥቀስ ያልፈቀደልኝ አንድ የታሪክ ምሁር ይህንን “Hamlet Minus the prince” ብሎኛል። ከመተማ ጦርነት ዮሐንስን ማስቀረት ማለት ነው። ነገሥታቱ የሚገባቸውን ክብር መነፈግ፣ ለአገር ያበረከቱትን መስዋዕትነት መቀማት እንደሌለባቸው ጠንካራ እምነት የነበራቸው ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ ነበሩ። በፖለቲካል ኢኮኖሚ መጽሐፋቸውና በአስተዳደር እውቀታቸው ተደናቂ የነበሩት ገብረሕይወት ባይከዳኝ በአንድ ወቅት በፕሮፌሰር አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ “አጤ ምኒልክ” መጽሐፍ ክፉኛ ተከፍተው የጻፉትን አሳብ ማንሳት ደግና አስፈላጊ ይመስለኛል። አጭር ናት። “ምኒልክን ለማሞገስ ዮሐንስን ማንኳሰስ ያስፈልጋል?” ነበር ያሉት። እውነታቸውን ነው። ነጋድራስ አፈወርቅ በእቴጌ ጣይቱ ውሳኔ ከአዲስ አበባ ርቀው ከቶውንም በኤርትራ መኖር ይዘው ነበርና ያንን መጽሐፍ የጻፉት (ብዙ ቁም ነገርና ታሪክ ቢኖርበትም) እቴጌይቱን መታረቂያ አድርገው ነው እየተባለ ይነገር ነበር። ለእኛ ዘመን ትምህርት ሊሆነን የሚገባው- በዘመነ ግሉባላይዜሽንና- ስለ ግሥጋሴና ነገ ከዛሬ መሻል አለበት - ብርሃንም ከሩቁ አድማስ ባሻገር መ

ታየት አለበት- ለሚለው ትውልድ ፋይዳ ሊኖረው የሚገባው ነገር አለ። እነዚያ የወቅቱን ፈተና በወቅቱ ስልትና ብልሃት ተወጥተውታል። የዚያን ዘመን ፈተና ለመረዳት ደግሞ ሕሊናን ከወቅቱ ጋር ማዛመድን ይጠይቃል። ይህን ካልሁ በኋላ ከአንባቢው ጋር እንዲቀርልኝ የምሻው አንድ ጉዳይ አለ። አጤ ዮሐንስ በደሙ፣ በአጥንቱና በነፍሱ ኢትዮጵያን የቀደሰ መሪ ነው። አጤ ምኒልክ በአንድ አጭር የታሪክ ዘመን ግዙፉን ተግባሮችን የፈጸመ፣ የአገሩን አንድነት የመሠረተ፣ ዓለምን ያስደነቀ- የጥቁርን ሕዝብ መንፈስ ከፍ ከፍ ያደረገ - በሺህ ዓመት ጊዜ ውስጥ ምትክ የማይገኝለት መሪ ነበር። ኢትዮጵያን ባረከ- ኢትዮጵያውያንን አኮራ- ጥቁር ሕዝቦችን ሰው አሰኘ። በዚህ መልክ ነበር በኢትዮጵያ ሰማያት ላይ የታየው ኮከብ ያለፈው። አጤ ዮሐንስ ደግሞ ኢትዮጵያን ለመውረርና የዓባይን ምንጭ ለመቆጣጠር ተደፋፍረው የመጡትን ግብፆች በጉንደት፣ በጉዳጉዲ፣ በጉራዕ ድባቅ የመታ ታላቅ መሪ ነበር።

ዮሐንስ በወደቀበት ሥፍራ ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ኖረውበታል። ይኖሩበታል። በጉበኝነት መልክ እየሄዱ ሳያውቁት ተሳልመውታል። አንድ ሰሞን (በቀዳማዊ ኅይለ ሥላሴ ዘመን) የሱዳን መንግሥት የባለቤትነት ጥያቄ አቀረበ ሲባል ከተወሰኑ የፓርላማ አባላት ጋር ወደዚያ አምርቼ ነበር። በሑመራም፣ በመተማም ወዘተ ከወልቃይት ጠገዴ..እስከ ጸለምት..ድረስ በመኪና ሄደናል። እግር እስከ ወሰደ ድረስ ኳትነናል። የሰው ውበት፣ የመሬት ውበት፣ የተራራ ውበት…ሊገለጥ አይችልም። የንጉሠ ነገሥቱ መኰንኖች፣ ሚኒስትሮች ወዘተ የተቀራመቱትን ጋሻ መሬት መግለጫ ሁሉ ሰምተናል።

ጓንዴና ሰነኔ፣ ከዚያም ወዲህ የሰው ነፍስ የመሰለ ጠመንጃ ከጐናቸው የለጠፉ፣ በአንዱ ጐናቸው ደግሞ ስንቃቸውን የጣፉ የአሥርና የአሥራ አንድ ዓመት ጉብሎች ታገኛላችሁ። እነዚህ ገና ጡጦ ጥለው ወደ አገር ጠባቂነት የተላለፉ ልጆች ስለ መሣሪያ አጠቃቀም ሳይቀር ሲተነትኑላችሁ ይቺ አገር በየትውልዱ የጠላትን ጉሮሮ እያነቀ የሚጥል ጀግና ረሃብ እንደሌላት ትረዳላችሁ። አንዱን ልጅ “ሱዳን ጦር ይዛ ብትመጣብህ ልትወጋት ትችላለህ?” ብዬ ሰነፍ ጥያቄ አቀረብሁለት። “ይህን መሣሪያ ለለበጣ የያዝን ይመስላችኋል? ጌታው ይስሙኝ! እዚህ ከብት የምናቆም ልጆች እንበቃለታለን። ብቻ የመንግሥት ጦር አይምጣብን። ነገር ይበላሽብናል። ሱዳንን እናውቃታለን። ታውቀናለችም” አለኝ። በውቅቱ ..የኢትዮጵያ ድምጽ ጋዜጠኛ የነበረው ወንድም-አከል ጓደኛዬ መርስዔ ኅዘን አበበ ይህን አሳብ ለብዙ ጊዜ ለብዙ ሰው አጫውቶአል።

በትውልድ ከተመካህ በዚያ ዓይነቱ አገር የትውልዶች ሃላፊነት ምን እንደ ሆነ እየተረዱ ያደጉ..በትውልድ መመካት ምን ማለት እንደሆነ ይህ መሬት ከእኛ በፊት የሚያስከብሩት ሰዎች እንደነበሩና ጥለው የወደቁትም ምንኛ እንደቀደሱት የሚረዳ ትውልድ ዝግጅት ስትረዳ ነው። ወጣቶቹ ገና ከሕፃንነታቸው ጀምረው በዚያ አካባቢ ሲገጥመን የኖረውን ችግር ከአባቶቻቸው እግር ሥር ተቀምጠው ሰምተውታል። ለምሳሌ አጤ ዮሐንስ የገጠማቸውን ችግር ሁሉ… የጦርነቱን ሁኔታ ..ወዘተ ለተክለ ጻድቅ መኩሪያ፣ የዮሐንስ ዘመን የታሪክ ምሁር ለነበረው ለዓለሜ እሸቴ፣ የዮሐንስን ዘመን ታሪክ ባይጽፉትም ሲያጫውቱአችሁ ለሚያፈዝዙአችሁ ለጄኔራል አሳይያስ ገብረሥላሴ…የሚያስተምሩ ናቸው። ከእንግዲህ ወዲያ የዚህ ዓይነት ታጋይ ትውልድ ልናፈራ እንችላለን? እጆቻችንን ወደ ሰማይ እንርጭ!

ከዚህ ወግ ለመውጣት እፈልጋለሁ። ከመርስዔ ኀዘን (ነፍሱን ይባርካትና) ጋር ስንነጋገር እንደጋጣሚ ሁለታችንም መሬቱ ልዩ ስሜት ቀሰቀሰብንና “ይህ አካባቢ ታጥሮ የዮሐንስንና አብረውት የቆሙትን- የተሰየፉትንና ሰማዕትነታቸው የተረጋገጠው ያልታወቁ ጀግኖች- መዘከር እንዲሆን አሳቦች ብናቀርብስ?” ተባባልን። ሌላው አሳብ ደግሞ በትላላቅ ሆሄያት “ይኽ ሥፍራ የተቀደሰና የተከበረ ሥፍራ ነው። (የሚታደስ... ወደ ገጽ 9 የዞረ)

የሚታደስ ቃልኪዳን

ዲጄ ይፈልጋሉ?ሰርግዎን፣ የግል ፓርቲዎን፣ ማን

ኛውንም ዝግጅት ለማድረግ ሙዚቃ የሚያውቅ ዲጄ ከፈለጉ ወደ ዲጄ ቢኬ ጋር ይደውሉ።’

651-9556091

Page 8: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 8

እንመካከር

የዶ/ር ዓብይ ምላሽ፦ ምንም እንኳን ከሰጡን መረጃ በመነሳት የጠያቂያችን የጤና እክል ይህ ነው ብሎ እቅጩን ማወቅና መናገር ባይቻልም ባለው መረጃ ላይ ተመስርተን በቀዳሚነት ሊሆን ይችላል በምንለው የጤና ችግር ላይ እንደተለመደው ጠቅለል ያለ ማብራሪያ ለመስጠት እንሞክራለን፡፡ ከሁኔታው እንደተረዳነው ችግሩ በእንግሊዝኛው አጠራር ‹‹Peripheral Neuropathy›› በመባል የሚታወቀው በሽታ ነው፡፡ ይህም ማለት በተለያዩ የጤና እክሎች እጆቻችንና እግሮቻችን ላይ የሚገኙት ነርቮች ሲጎዱ የሚከሰት በሽታ ነው፡፡ የጠያቂያችን እጅ እግሮች ላይ የተከሰቱት የህመም ስሜቶችም ከዚሁ በሽታ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ መገለጫ ምልክቶቹ ናቸው፡፡ በተለይም እጅ እግር ላይ ከሚሰሙ ስሜቶች ያለመሰማት፣ በተቃራኒው ተጋኖ ወይም ተዛብቶ መሰማት ጋር ተያይዞ የሚከሰተው ‹‹Sensory Neuropathy›› የተሰኘው የዚሁ በሽታ አንዱ አይነት የሆነው ችግር እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ ስለሆነም ስለ ‹‹Peripheral Neuropathy›› ምንነት፣ መንስኤዎች፣ ዋነኛ መገለጫ ምልክቶቹ፣ ምርመራዎቹ እና ህክምናዎቹን በተመለከተ ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡ በቅድሚያ ስለ ችግሩ ምንነት በማብራራት እንጀምር፡፡

ውጫዊው የነርቭ ስርዓት Peripheral Neuropathy ማለት ለእጅ እግር ከሚያገለግሉ የነርቭ አይነቶች አንዱ ወይም ከዚያ በላይ በአንዳችን የጤና እክል አማካይነት ሲጎዳ የሚያስከትላቸው የህመም ስሜቶችን ይወክላል፡፡ የህመም ስሜቶቹ መገለጫዎች እንደየነርቭ አይነቶቹ እና ተግባራቸው ይለያያል፡፡

ሴንሰሪይ ኒውሮፓዚይ (Sensory Neuropathy)፡- ይሄኛው አይነት የነርቭ ችግር ዋነኛ መገለጫዎቹ በተለምዶ መሰማት የሚገባቸው ስሜቶች ሳይሰሙን ሲቀሩ አልያም ስሜቶቹ ከተለመደው የተለየ ወይም የተጋነኑ ስሜቶች ሲሆኑና ይህም ያለመመቸትና የህመም ስሜቶችን ሲያስከትሉብን ነው፡፡ ማለትም ሙቀት ቅዝቃዜንና ሌሎች የህመም ስሜቶችን... የመሳሰሉትን መለየት አ

ለመቻል ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም እነዚህ ስሜቶች ተዛብተውና ተጋነው ሲሰሙን ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ የመደንዘዝ፣ የማቃጠል፣ የመጠዝጠዝ፣ የመለብለብና የመሳሰሉት ስሜቶች ሊሰሙን ይችላሉ፡፡ አንዳንዴም ልክ እንደ መርፌ ጠቅ-ጠቅ የማድረግ ስሜት ሊሰማን፣ አሊያም ልክ ነፍሳት ከቆዳ ስር የሚሄዱ የሚመስል አይነት ስሜት የሚያጋጥማቸው ታማሚዎችም አሉ፡፡ የጠያቂያችንም አብዛኞቹ ምልክቶች ከእነዚህ ጋር ስለሚመሳሰሉ ችግራቸው ይሄኛው አይነት የነርቭ ችግር ሊሆንም ይችላል፡፡

- ሞተር ኒውሮፓዚ (Motor Neuropathy)፡- ይኼኛ የነርቭ ችግር ደግሞ የሚያጠቃው ለእንቅስቃሴ የሚረዱ በተለይም የእጅና የእግር ጡንቻዎችን በመሆኑ እነርሱን ማንቀሳቀስ አለመቻል ዋነኛ መገለጫው ነው፡፡ ስለሆነም ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች እንደፈለጉ መንቀሳቀስ አለመቻል፣ በእጅ ጣቶች የሚከወኑ ተግባራትን (ለምሳሌ መጨበጥ፣ ዕቃ ማንሳት፣ መዳፍ... የመሳሰሉትን) መከወን አለመቻል እና የመሳሰሉትን ከእንቅስቃሴ ጋር የተገናኙ ተግባራትን ማከናወን አለመቻልና የእጅ እግር መዛል ዋነኛ ምልክቶቹ ናቸው፡፡

እነዚህ እንግዲህ የ ‹Peripheral Neuropathy› ዋነኛዎቹ አይነቶችና መገለጫዎቻቸው ሲሆኑ በተናጠል ወይም በጋራ ምናልባትም ከሌሎች ማለትም ከማዕከላዊ የነርቭ ስርዓት ችግሮች ጋር አብረው ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ የሚከሰቱበት ሁኔታም ከአጣዳፊ የጤና ችግር ጋር በተያያዘ በአጣዳፊነት (Acute) ወይም ስር ከሰደዱ የጤና እክሎች ጋር በተያያዘ በዘላቂነት (Chronic) ሊሆን ይችላል፡፡ በተመሳሳይም አንድ ነርቭ ብቻ የተጎዳ ከሆነ ሞኖኒውሮፓዚይ (Mononeuropathy) ሲባል ከአንድ በላይ ወይም ብዙ ነርቮች በአንድ ጊዜ የተጎዱ ከሆነ ደግሞ ፖሊኒውሮፓዚ (Polyneuropathy) በመባል ይታወቃሉ፡፡

የውጫዊው የነርቭ ስርዓት መጎዳት (Peripheral Neurop-athy) መንስኤዎች ምን ምንድናቸው?

የተለያዩ ነርቮችን በማጥቃት ለተለያዩ የነርቭ ችግሮች የሚዳረጉ በርከታ የጤና እክሎች አሉ፡፡ በጥቅሉ ከዕጢ ጋር፣ ከልዩ ልዩ ኢንፌክሽኖች ጋር፣ ከመርዛማ ነገሮች ጋር፣ ከመድሃኒቶች ጋር እና ከሌሎችም ስር ሰዳጅ በሽታዎች ጋር የተያያዙ መንስኤዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ዋነኞቹ መንስኤዎችም እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

- የስኳር በሽታ፡- መንስኤ ከሆኑት ስር ሰዳጅ በሽታዎች ቀዳሚው ነው፡፡ በተለይም ሁለተኛው አይነት የስኳር በሽታ የተለያዩ የነርቭ ችግሮችን የሚያስከትል ሲሆን በዋነኝነት ሴንሰሪ ኒውሮፓዚ (Sensory Neuropathy) የተሰኘውን አይነት በተለይም በእጅና በእግር ላይ በማስከተል ከላይ በተጠቀሱት ምልክቶች ይገለጣል፡፡

- አልማዝ ባለጭራ፡- በተለምዶ አልማዝ ባለጭራ እያልን በተለምዶ የምንጠራውና በህክምናው እርፐስ ዞስተር የምንለው ህመም ይህ ሌላው የተለመደ የችግሩ መንስኤ ሲሆን በመጀመሪያ የሚያወጣው ቁስለት ከዳነ በኋላ የሚከሰተው የነርቭ ህመም (post herpetic neuralgia/shingles) በመባል ይታወቃል፡፡ ህመሙ ሁሌም የአልማዝ ባለጭራን ተከትሎ የሚከሰት ባይሆንም ከተከሰተ ግን ከፍተኛ ስለሆነ ማስታገሻ ያስፈልገዋል፡፡

- የአልኮል መጠጥ፡- በአልኮል መጠጥ ውስጥ የሚገኘው ኬሚካል ከነርቮች ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር የተጠቀሰውን ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡ ይህ የሚሆነው ግን ብዙ አልኮል ለብዙ ጊዜ በጠጡ ሰዎች ላይ ነው፡፡

- የቫይታሚን እጥረት፡- ከተለያዩ ምግቦች የሚገኙ ቫይታሚኖች በተለይም ቫይታሚን ቢ12 የተሰኘውና ፎሌት የተሰኘው በሚያስፈልጉን መጠን ካልተወሰዱ የተጠቀሰውን የነርቭ ችግር ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡

- ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ፡- በሽታው የተባለውን የነርቭ ችግርና ሌሎችንም የነርቭ ችገሮች ከሚያስከትሉ የተለመዱ መንስኤዎች አንዱ ነው፡፡ በራሱ በበሽታው ሂደት ብቻም ሳይሆን በሚያስከት

ላቸው ሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች፣ ለህመሙ በሚወሰዱት መድሃኒቶች ሳቢያ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች ሊሆን ይችላል፡፡

- ሌሎች ኢንፌክሽኖች፡- ከኤች.አይ.ቪ ኤድስ ባለፈም ሌሎች ልዩ ልዩ ኢንፌክሽኖች የተባለውን ችግር በማስከተል ይታወቃሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ቂጥኝ፣ የስጋ ደዌ በሽታ፣ የተለያዩ ቫይረሶች እና ሌሎች ባክቴሪያዎች ይጠቀሳሉ፡፡

- ካንሰርና ህክምናው፡- ከዕጢዎችና ካንሰር መገለጫዎች አንዱ ይኸው የነርቭ ችግር ነው፡፡ ከበሽታውም ባለፈ ለፈውስ ተብለው የሚሰጡ መድሃኒቶቹም ችግሩን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡

- ሌሎች ስር የሰደዱ በሽታዎች፡- እነዚህም የነርቭ ችግር በማስከተል ከሚታወቁት መንስኤዎች ይመደባሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የኩላሊትና የጉበት ድክመት፣ ከሆርሞኖች ጋር የተያያዙ በሽታዎች (ለምሳሌ ሃይፓታይሮዲዝም የተሰኘው በእንቅርት ሆርሞን ማነስ ምክንያት የሚከሰተው በሽታ) እና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡

- መድሃኒቶችና መርዛማ ንጥረ ነገሮችን፡- እንደ የተባይ ማጥፊያ፣ (ለምሳሌ ዲዲቲ) ሜርኩሪ፣ እና የመሳሰሉት ማዕድናትና መርዛማነት ያላቸው የፋብሪካ ውጤቶች ወደ ተረፈ ምርቶች፣ እንዲሁም ከላይ የተጠሱትና ሌሎች አንዳንድ መድሃኒቶች የተጠቀሰውን የቫይታሚን እጥረት በማስከተል ለነርቭ ችግር ይዳርጋል፡፡ ይህም ከመድሃኒቶች የበዛ የጎንዮሽ ጉዳት የተነሳ የሚመጣ ነው፡፡

- አካላዊ አደጋ (Physical trauma)፡- ይህም በነርቮች ላይ ወይም በደም አቅርቦታቸው ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር ለተባለው ህመም ሊዳርጉ ከሚችሉት መንስኤዎች አንዱ ነው፡፡ በተመሳሳይም ነርቮቹ በሚያልፉባቸው የእጅና የእግር አጥንት ቀዳዳዎችና ክፍልፋይ መሿለኪያዎች በአደጋ ወይም በበሽታ አብጠው ወይም ጠበው ነርቩን የሚጫኑበት ሁኔታ ከተፈጠረ የተባለውን ተመሳሳይ የነርቭ ችግር (የሚደነዝዘኝ... ከገጽ 22 ይዞራል)

መነሻውን ሳላውቀው እጅ እግሬን የሚደነዝዘኝና የሚያቃጥለኝ ምንድነው?የማክበር ሰላምታዬን እያቀረብኩ ጥያቄዬን አስከትላለሁ፡፡ ከቅርብ ወራት ወዲህ ሁለቱም እጆቼንና ሁለቱንም እግሮቼን እንደመደንዘዝ ያደርገኛል፣ ያቃጥለኛል፣ ይለበልበኛል፣ ልክ በመርፌ እንደሚወጋ ነገር ጠቅ- ጠቅ ያደርገኛል፣ አንዳንዴም ውስጥ ውስጡን የሆነ ነ

ፍሳት የሚሄድብኝ/የሚርመሰመስብኝ ይመስለኛል፡፡ ሲነሳብኝ ማስታገሻ ወስጄበትም አይተወኝም፡፡ ዕድሜዬ በአርባዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገኝና የልጆች አባት ነኝ፡፡ ከዚህ በፊት በግልፅ የታወቀና በሐኪም የተነገረ በሽታም የለብኝም፡፡ ይሁንና ይህ ችግር በተለይም እየደጋገመ ሲመጣብኝ በጣም አሳስቦኛል፡፡ እባክዎትን እንደተለመደው የህመሜ መንስኤ ምን ሊሆን እንደሚችል ከነመፍትሄው ቢያብራሩልኝ!? በ.ተ

ከሰገራዬ በመቀላቀል የሚወጣው ደም መንስኤው የአንጀት ካንሰር ወይስ ኪንታሮት?

በእርግዝና ወቅት የሚፈጠርብኝን

የሰውነት መለጠጥቋሚ ምልክት እንዳያመጣብኝ

ምን ላድርግ?በእርግዝና ወቅት የሚፈጠርብኝ የሰውነት መለጠጥ ቋሚ ምልክ

ት እንዳያመጣብኝ ምን ላድርግ?ጥያቄ፡- የማቀርበው ጥያቄ የ28 ዓመት ወጣት ነኝ፡፡ የዛሬ ዓመ

ት የምወደውን ሰው አግብቼ አብሬ መኖር ጀምሬያለሁ፡፡ አሁን ደግሞ ልጅ የመውለድ ፕሮግራሜን እውን ለማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ እናት መሆን በጣም የሚያስደስት ልምድ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ በማረግዝበት ጊዜ ግን በእርግዝና ወር የሚፈጠረው የሰውነት መለጠጥ ቋሚ ምልክት እንዳያመጣ መከላከል እፈልጋለሁ፡፡ ምን ባደርግ ይሻለኛል?

ራሄል ወሰኑውድ ራሄል፡- መልካሙ ዜና በእርግዝና አልያም በከፍተኛ የክ

ብደት መቀነስ ምክንያት የሚከሰተው ሸንተረር ማጥፋት አስቸጋሪ በመሆኑ ሳይጀመር በፊት መከላከል መፈለግሽ ነው፡፡ ቆዳ ላይ የሚታየው ቀላ ያለ ትንሽ ቆይቶ አንፀባራቂ ወይንም ብራማ ቀለም ያለው ምልክት ወንድ ሴት ሳይል ማንኛውም የሰውነት ክፍል ላይ ሊወጣ ይችላል፡፡ ለምሳሌ በሆድ፣ በችን፣ በጡት፣ በታፋ ወይም በታችኛው ወገን ላይ ሊታይ ይችላል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ምክንያቶች በተጨማሪ ለተለያዩ ምክንያቶች በምንወስዳቸው መድሃኒቶች ምክንያት ጭምር ሊመጣ ይችላል፡፡

ሸንተረርን ለመከላከል የሚቻልባቸው ጥቂት መንገዶች መካከል የሚከተሉትን ልጠቁምሽ እወዳለሁ፡፡

1. ዘይት፣ ቅቤ፣ ሎሽን፣ ክሬም ወይም ለሸንተረር ተብለው የተሰሩ ልዩ ቅባቶችን ለቆዳችን የሚስማማውን በመምረጥ ሁሌም ያለመሰልቸት መቀባት፡፡ እርጉዝ ሴት ምንም አይነት ነገር ከመጠቀሟ በፊት ሐኪሟን ልታማክር የሚገባት ሲሆን ለጤናዋ የማይጎዳ መሆኑን ካረጋገጠች በኋላ በተፈገለው መጠን ያለማቋረጥ መቀባት ይኖርባታል፡፡

2. ‹‹ውሃ ጠጪ›› የሚባለው ተደጋጋሚ ምክር ለቆዳችን ጤናና ውበት በተራ ቁጥር አንድ ላይ ከሰፈረ ከርሟል፡፡ በመሆኑም ሸንተረር ከመከላከያ ዘዴዎች አንዱ ብዙ ውሃ መጠጣት መሆኑ ታምኖበታል፡፡ በቂ ውሃ ቆዳን በማለስለስ ሸንተረር በቆዳችን ላይ የመታየቱን እድል ዝቅ እንደሚያደርግ ጥናቶች የሚጠቁሙ ሲሆን፤ በብዛት የቡናና ሻሂ ተጠቃሚ የሆኑ ሰዎች የጠጡትን ያህል ወይም ከዛ በላይ ውሃ በላዩ ላይ ቢወስዱበት ሸንተረርን ለመቀነስ እንደሚችሉ ታውቋል፡፡

3. አትክልትና ፍራፍሬዎች በብዛት መመገብበሰለጠነው ዓለም ሰዎች ሸንተረርን ለማጥፋት ቀዶ ጥገና የሚያ

ከናውኑ ሲሆን ውጤቱ በግለሰቡ ዕድሜ፣ የቆዳ አይነት እና የምግብ አወሳሰድ ይለያያል፡፡ በሀገራችን ይህንን መንገድ ተጠቅሞ ማስወገድ ስላልተለመደ ከላይ በተጠቀሱት ሁለት መንገዶች ተጠቅሞ መከላከል ይመረጣል፡፡ መልካሙን ሁሉ በእናትነትሽና በእርግዝናሽ መልካሙን ሁሉ እመኝልሻለሁ፡፡

‹‹ከሠገራዬ ጋር ተቀላቅሎ የሚወጣው ደም መንስኤው የአንጀት ካንሰር ወይስ ኪንታሮት? ምንስ ባደረግ ይሻለኛል?››

መላኩ እባላለሁ፡፡ ዕድሜዬ 22 ሲሆን ኪንታሮት እየተባለ የሐበሻ መድሃኒት ያልጠጣሁት ስራ ስር ያልሄድኩበት ህክምና የለም፡፡ አንድ ዶክተር ምን አለ መሰላችሁ? አሜባ (ኪንታሮት ነው) ተብዬ የሀገር መድሃኒት ተሸክሜ ጧትና ማታ በሙቅ ውሃ ፊንጢጣህን ዘፍዝፈው ነበር ያለኝ፡፡ እኔም የዘወትር ስራዬ እሱ ሆነ፣ ለ10 ቀናት ግን ምንም መፍትሄ አላየሁበትም፡፡ ይባስ ብሎ ደም ያለማቋረጥ ሁል ጊዜ ከሰገራዬ ጋር በመቀላቀል ይወጣል፡፡ እንግዲህ አስቡት ለ7 ዓመት ደም ያለማቋረጥ መፍሰስ ማለት አስቡት እንዴት እንደሚከብድ፡፡ የሚገርመው ነገር ደም ከሰውነቴ እየፈሰሰ እኔ የሚሰማኝ ነገር የለም፡፡ ሰውነቴ ከመቀነስና ጧት ከእንቅልፍ ስነሳ ራሴን ከማዞር ውጭ፡፡

ደም ማነስ፣ ውሃ መሰልና ከደም ጋር የተቀላቀለ ተቅማጥ፣ እረፍት የለሽ የህሊና መረበሽ፣ የህሊና ጭንቀት/ቴንሽን/፣ ሰውነቴ በየቀኑ መቀነስና ማስማጥ በየቀኑ የማያቸው ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህን ተስፋ አስቆራጭ በሽታ ለመገላገልና ከስቃይ ለመውጣት የምችለው እንዴት ነው? እባካችሁ ያላችሁን ምክርና መፍትሄ ለግሱኝ፡፡

መላኩ ነኝየዶ/ር ዓብይ ዓይናለም ምላሽ፡- ውድ መላኩ ከሁሉ አስቀድ

መን ለገለፅክልን ምስጋናና አድናቆት የእኛም አፀፋዊ ምስጋና ይድረስህ፡፡ እንደዚህ ከአንባቢዎቻችን የሚሰጠን ማበረታቻ ለበለጠ ጥሩ ስራ ያተጋናል፡፡ ለሰባት ዓመታት መፍትሄ ያጣህለትን ጉዳይ ወደ እኛ በማምጣትህም ሳናመሰግንህ አናልፍም፡፡ ሆኖም ግን ምስጋና ብቻ ሳይሆን ወቀሳም ልንሰነዝርብህ ወደድን በሁለት ጉዳዮች፤ አንደኛ ለሰባት ዓመታት ሁሉ እንደገለፅከው ደም እየፈሰሰህ ችላ ብለህ መቆየትህ ያስወቅስሃል፡፡ በተለይ ችግሩ አንተ እንደገለፅከው ከሆነና ካላጋነንከው ለተሻለ ህክምና መጣር ነበረብህ፡፡ አ

ያድርገውና አንተ እንዳሰብከው ካንሰር ቢሆን ኖሮ በቀላሉ እንዲሰራጭ እድል ሰጠኸው ማለትም አልነበር? እርግጥ ነው የሐበሻ መድሃኒት መሞከርህንና አንድ ሐኪም ጋር ሄደህ የተሰጠህ ህክምና እንዳልጠቀመህ ብትጠቅስም፣ ወይ ተመልሰህ ሐኪሙን ማማከር ነበረብህ፡፡ አልያም ሌላ ሐኪም ጋር መሄድ ነበረብህ፡፡

ሁለተኛው ወቀሳችን ‹‹ያልጠጣሁት የሐበሻ መድሃኒት የለም›› ባልኸው ላይ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ልምድ ለከፋ ጉዳት በተለይም ለጉበት መመረዝ ይዳርጋልና እንዳይለመድህ፡፡ አሁን ከወቀሳው ወደ መፍትሄው እናምራ፡፡

ከገለፃህ እንደተረዳነው ሰገራ ስትወጣ ማስማጥና ደም እየቀላቀለ መውጣቱ ነው፡፡ በተያያዥነት ህመም ይኑረው አይኑረው፣ በወቅቱ ፊንጢጣህ ወደ ውጭ የመውጣትና የመመለስ/አለመመለስ ባህሪይ ይኑረው አይኑረው... ብትገልፅልን ኖሮ ችግሩን ለይቶ ለማወቅ ይበልጥ ይረዳን ነበር፡፡ ያም ሆኖ ይህ በጥቅሉ ችግርህ ከታችኛው የአንጀት ክፍሎች መድማት ጋር የተያያዘ በመሆኑ በዚያ ዙሪያ እንወያያለን፡፡

የችግሩ ምንነትና መንስኤዎችየታችኛው የምግብ መውረጃ/የአንጀት ክፍሎች መድማት

(Lower Gastrointestinal Bleeding) በተለያዩ በሽታዎች ሳቢያ የሚከሰት ሲሆን መገለጫዎቹና የሚያስከትለው ጉዳትም እንደ መንስኤውና እንደ በሽታው ደረጃ ይለያያል፡፡ መነሻው የትንሹ አንጀት የታችኛው ክፍልና ከትልቁ አንጀት እስከ ሠገራ መውጫ ፊንጢጣ ድረስ ባሉት ቦታዎች ካንዱ ሊሆን ይችላል፡፡ መንስኤዎቹም የተለያዩ ናቸው፡፡ በጣም የተለመዱት ግን ኪንታሮት፣ የተለያዩ ዕጢዎች (Polyps and Tumors)፣ በአንጀት ላይ ከረጢት መሰል ክፍተት ሲፈጠር (Diverticula)፣ የአንጀት ግድግዳ መቁሰልን የሚያስከትሉ በሽታዎች (Inflammatory Bowl Diseases=IBD)፣ የፊንጢጣ መሰንጠቅ፣ እና የደም ስሮች መዛባት (Vascular Ectasia) ወዘተ ናቸው፡፡

እነዚህም መንስኤዎች እንደየታማሚው ዕድሜና ሁኔታ የመከሰት ዕድላቸውም ይለያያል፡፡ ለምሳሌ የአንጀት ካንሰርና የደም ስሮች መዛባት ይበልጥ በዕድሜ ጠና ያሉ ሰዎችን ሲያጠቁ በልጆች በወጣቶች ላይ ‹‹IBD›› እና ቀለል ያሉ ዕጢዎች (Juvenile polyps) ይበልጥ ይከሰታሉ፡፡ ኪንታሮት በየትኛውም ዕድሜ ሊከሰት ቢችልም ዕድሜ እየጨመረ ሲሄድ ይበልጥ ይከሰታል፡፡

ውድ መላኩ አንተ የ22 ዓመት ወጣት ስትሆን ችግሩ የጀመረህ ከ7 ዓመት በፊት ማለትም በ15 ዓመትህ ከመሆኑ አንፃር የአንጀት ካንሰር ይሆን? የሚለው ስጋትህ ብዙም አግባብ አይደለም፡፡ የአንጀት ካንሰር በብዛት የሚከሰተው ከ40 ዓመት ዕድሜ በላይ ነው፡፡ ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑ ሰዎች ዘንድ ግን (ለምሳሌ የቅርብ ዘመድ አንጀት ካንሰር የነበረበት ሰው) ከዚያም በፊት ሊከሰት ይችላል፡፡

እናም ያንተ ችግር እንዳልከው ኪንታሮት አሊያም ሌሎቹ በወጣትነት የሚከሰቱት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለማንኛውም ግን ‹‹ታሞ ከመማቀቅ...›› ነውና ተረቱ ወደ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስቶች በመሄድ የከፋ ችግር አለመሆኑን የአንጀትን የውስጥ ክፍል በሚያሳዩ ምርመራዎች (Endoscope) መታየቱ ሊጠቅምህ ይችላል፡፡ በተረፈ የፊንጢጣ ኪንታሮት ካንተም ባለፈ የተለመደ ችግር በመሆኑ ስለሱ ጥቂት ማለትን ወደድን፡፡

የፊንጢጣ ኪንታሮትና መገለጫዎቹየሰገራ መውጫ የመጨረሻው የትልቁ አንጀት ክፍል (anul-

canal) እና ፊንጢጣ በዛ ያሉ የደም ስሮችና የደም ፍሰት ካላቸው የሰውነታችን ክፍሎች አንዱ ነው፡፡ ምክንያቱም በውል ባልታወቀ ሁኔታ እነዚህ የደም ስሮች የመለጠጥ፣ የመላላትና ከዋናው የጡንቻ ግድግዳ ተላቆ ወደ ሰገራ መውጫ ፊንጢጣ የመውረድ ሁኔታ ይከሰትባቸዋል፡፡ ይህም የፊንጢጣ ኪንታሮት በመባል ይታወቃል፡፡ ዋነኛ መገለጫዎቹ የምቾት ማጣት፣ ሰገራን መውጣት መቸገር፣ መድማት፣ የደም ስሮቹና የፊንጢጣ ክፍል ወደ ውጭ

መውጣት፣ እና ባስ ካለም ከፍተኛ የህመም ስሜት ናቸው፡፡ ኪንታሮት የተለያዩ ሂደቶችና ደረጃዎች ሲኖሩት እነዚህም ም

ልክቶች እንደየደረጃው ይለያያሉ፡፡ መፍትሄውም እንዲሁ፡፡ አራት ደረጃዎች ያሉት ሲሆን የመጀመሪያው ከሰገራ ጋር ደም የመቀላቀል አሊያም በመፀዳጃ ወረቀት ላይ ደም የሚታይበት ሁኔታ ነው፡፡ ሁለተኛው ደረጃ ደግሞ ሰገራ ለመውጣት በምናምጥበት ጊዜ የተወሰነው የፊንጢጣ ክፍል/ደም ስሮቹ ወደ ውጪ የሚወጡበት ሁኔታ ነው፡፡ ሆኖም ግን መፀዳዳቱ ሲጠናቀቅ ወደ ቦታው ይመለሳል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በእጅ/በጣት ገፍቶ መመለስን ግድ የሚል ከሆነ ሶስተኛ ደረጃ ደረሰ ማለት ነው፡፡ አራተኛውና የመጨረሻው ደረጃ በጣትም ገፍቶ ለመመለስ የፊንጢጣ ክፍልም መቁሰል ሲጀምር ሲሆን በዚህ ወቅት ከፍተኛ የህመም ስሜት ይከሰታል፡፡ የደም መፍሰሱ ሁኔታም ከደረጃው ጋር እየጨመረ ይሄዳል፡፡

ለኪንታሮት የሚያጋልጡ ሁኔታዎች የተለያዩ ሲሆኑ በአጠቃላይ ወደ ሰገራ መውጫ የአንጀት ክፍል ላይ ሊጫኑና ግፊት ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮች በሙሉ ሁኔታውን ሊያባብሱ ይችላሉ፡፡ ከእነዚህም ተጠቃሾቹ የሆድ ድርቀት (ሰገራ ሲወጣ ብዙ ማማጥን ስለሚጠይቅ) ሆድን ሊያሳድጉና ወደ ታች የሚያሳድረውን ጫና ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮች ማለትም እርግዝና፣ የሆድ ውስጥ ዕጢ፣ ቦርጭ፣ በሆድ ውስጥ የሚከማች ፈሳሽ (ascitus) ወዘተ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

መፍትሄውስ? እንደተለመደው ቀዳሚው መፍትሄ ቀድሞ መከላከል ነው፡

፡ ከተከሰተም እንዳይባባስ ማድረግ ብልህነት ነው፡፡ ለኪንታሮት የሚደረጉት ህክምናዎች እንደየደረጃቸው ይለያያሉ፡፡ በጥቅሉ በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነርሱም ያለ ቀዶ ህክምና የሚሰጡ መፍትሄዎችና ቀዶ ህክምና ናቸው፡፡

የመጀመሪያው (ኪንታሮት... ወደ ገጽ 13 የዞረ)

አንድ ብርጭቆ ውሃ እንኳን

መጨረስ አይሆንልኝም

የተለያዩ ቦታዎች ውሃ መጠጣት ለጤና መልካም መሆኑን እሰማለሁ፡፡ አምንበታለሁም፡፡ እኔ ደግሞ አንድ ብርጭቆ ውሃ እንኳን መጨረስ አይሆንልኝም፡፡ በጣም ብዙ ጊዜ ብሞክርም ምንም ደስ ሳይለኝና ጭንቀት እየሆነብኝ ብዙም አልጠጣም፡፡ በግድ ከምጠጣ በውሃ ፋንታ ሌሎች ፈሳሾች ብወስድ ምን ይመስልሻል?

አመለ ጌታነህይህ የብዙ ሰዎች ችግር ነው፡፡ ውሃ መጠጣት በልጅነታችን

መልመድ ዋናው ጥቅሙ ይኸው በመሆኑ ህፃናትን ከወዲሁ የውሃ መጠጣት ልምድ እንዲያዳብሩ ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ ፈሳሽ ነገር በብዛት መውሰድ የሚያበረታታ ቢሆንም የውሃን ቦታ ግን ሊወስድ አይችልም፡፡ የማዕድን ውሃ እየተጎነጩ እንደ ሎሚ፣ የብርቱካን ጭማቂ በትንሹ ጨምሮ መጠጣትና መለማመድ፡፡ ቀስ እያሉ መጠኑን እያሳነሱ መሄድና ባዶውን መጠጣት ይቻላል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከውሃ ጋር ሊያለማምዶት ይችላል፡፡ አንዴ ውሃን ከለመዱ መመለሻ የለውምና ወደሚፈልጉት ማስዋቢያ ሳሎን ገቡ ማለት ነው፡፡

BISRAT ALEMAYEHU & ASSOCIATES

Meet your Friendly and Experienced professionals@

The Center for Multi-ServicesTax, Insurance, Real Estate, Notary, Application

Forms,Translation and More

ታክስ፣ ኢንሹራንስ፣ ሪል እስቴት፣ ኖታሪ፣ ውክልና፣ትርጉምና በርካታ ተዛማጅ አገልግሎቶች

WISER INSURANCE AGENCY, St. PaulMore Insurance Companies, More Price Choices!

[Auto. Home. Life. Health. Business]

Address: 1821 University Ave. W. Suite S-301 Saint Paul, MN 55104Tel: 651 649 0644 / 651 209 6077 Fax: 651 649 0620

የቀድሞውን ጠ/ሚ/ር ፍቅረሥላሴ ወግደረስ መጽሐፍ ይፈልጋሉ?

እዚህ ሚኒሶታ መጥቶ እየተቸበቸበ ነው። በሰላም

ካፌ እና በሸጋ ሱቅ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ በ612-226-8326 ይደውሉ

Page 9: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 9

አንድ ጊዜ አንዲት እናት ይህንን ታሪክ ነግረውኝ ነበር፡፡እኔና ባለቤቴ የተጋባነው ልጆች ሆነን ነው፡፡ ያኔ እንዳሁኑ ተያይ

ቶ፣ ተጠናንቶ፣ ሰንብቶ፣ ቆያይቶ የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ እንዲያውም የኛ ጊዜ ዘመናይ ነው ተብሎ የተወሰነ ጊዜ ትተያይና ወላጆቹ ለወላጆቿ ሽማግሌ ይልኩና፣ በስንት መመላለስ፣ አጥንትህ ጉልጥምትህ ተጠንቶ፣ ሀብት ንብረትህ ታይቶ ነበር የሚፈቀድልህ፡፡ ዛሬማ መንገድ ላይ ተንበርክኮ አንዲት የሃምሳ ብር አበባ ይዞ መለመን ነው አሉ፡፡ በኛ ዘመን በሬ ጎትተህ፣ መኪና አንጋግተህ፣ ጥሎሽ አግተልትለህም ከተሳካልህ ነው፡፡

ታድያ መጋባት አይቀርም ተጋባን፡፡ የእርሱ ወላጆች የሚያከራዩት ቤት ነበራቸው፡፡ አንዱን ቤት ሰጡንና ኑሮ ጀመርን፡፡ መቼም ፍቅርና ትዳር ለየቅል ነው፡፡ ታድያ እኛ ትዳር እንደጀመርን ባለቤቴ የልጅነት ነገር ሆነበትና ከጓደኞቹ እየተማረ ውኃ ቀጠነ ማለት ጀመረ፡፡ ባልነት ማለት መኮሳተር፣ መጎማለል፣ አንቺ እያሉ መጣራት፣ አምሽቶ መምጣት መሰለው፡፡ ይህን ጠባይ እርሱ እንዳላመጣው ዐውቅ ነበር፡፡ ጓደኞቹ ናቸው ያስተማሩት፡፡ በጊዜ ገብቶ አብረን ነበር ስንስቅና ስንጫወት የምናመሸው፡፡ እንዲያውም የኔ ባልኮ ዘመናይ ነው እያልኩ ነበር ለሰው የምናገረው፡፡ ወጥ ስሠራ እንኳን የሚያቀራርብልኝ እርሱ ነበር፡፡ በኋላ ጓደኞቹ ጠምደው ያዙት፡፡ ‹ለምን ቀሚስ አትለብስም› እያሉ መሳቂያ መሳለቂያ አደረጉት፡፡

የእነርሱን ወሬ መቋቋም ሲያቅተው እንደ እነርሱ ሆነ፡፡ ያገባሁትን ባል ወሰዱብኝና ሌላ ባል አጋቡኝ፡፡ አየህ ብዙ ሚስቶችኮ ባሎቻችንን ተነጥቀናል፡፡ እኛ ስናገባ ያገኘናቸውን ባሎች ወይ ጓደኞቻቸው ወይ ወላጆቻቸው ወይም ደግሞ የሥራ ባልደረቦቻቸው ነጥቀውናል፡፡ ያላገባናቸውን ሌሎች ባሎችም አጋብተውናል፡፡ አንዳንዶቻችንኮ ከተፈራረምናቸው ባሎቻችን ውጭ ነው የምንኖረው፡፡ የኔም እንደዚያ ሆነልህ፡፡

ይህንን ሲተርኩልኝ ባልየው እያሳቁ ያዩናል፡፡ አማትዬው ደግሞ ‹‹መቼም አትረሽም አንቺ›› ይላሉ እርጅና እንኳን ብልቀነሰው ጆሯቸው እየሰሙን፡፡ እርሳቸውም ‹‹ሰው የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩት ያህል ይስቃል›› ብለው በባላቸው ተረቱና ቀጠሉ፡፡

ነጋ ጠባ ጭቅጭቅ ሆነ፡፡ አምሽቶ መምጣት፣ ጠጥቶ መምጣት፣ የት እንደሄደ ሳይናገር ሶደሬና ላንጋኖ ጠፍቶ መክረም፤ የት ገባሽ የት ወጣሽ ማለት አመጣ፡፤ በእርሱ ቤት መቀናቱ ነው፡፡ ጓደኞቹ ሲያወሩ የሰማውን ሁሉ እውነት አደረገው፡፡ እኔም እየመረረኝም እየሰለቸኝም መጣ፡፡

የእርሱ እናት እንዴት ጥሩ ሰው መሰሉህ፡፡ ምናለ እንደርሳቸው ያለውን አማት እንደ ካሴት አባዝቶ በየቤቱ ቢያድሉት፡፡ በዚያ ዘመን እንደ አጤ ቴዎድሮስ ቀድመው የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ከቤታችን አይጠፉም፡፡ ምን ጎደለ? ምን ጠፋ? ነው ሐሳባቸው ሁሉ፡፡ በዚያ ዘመን አማት ልጅ ቤት የሚመጣው እንድም ሊያንጓጥጥ አንድም ሊያመናጭቅ ነው፡፡ አማት ሲባሉ ደርሰው መጥተው ሞያህን፣ ቤትህን ይገመግሙና ይዘረጥጡሃል፡፡ እርሳቸው እቴ፡፡ አንድ ቀን ክፉ ቃል ወጥቷቸው አያውቁም፡፡ ኧረ እንዲያውም ክፉ ቃል የሚባለውን ራሱን የሚያውቁት አይመስለኝም፡፡ የሚጨነቁት ለእኔ ነበር፡፡ ቁጭ ብለው ይመክሩኛል፣ ሞያ ያስተምሩኛል፣ ታሪክ ይተርኩልኛል፡፡ አቤት ቀልዳቸው፡፡ የባሌን ችግር የምረሳው በእርሳቸው ቀልድ ነበር፡፡ ከነገሩኝ በኋላ እንኳን ብዙ ጊዜ ብቻዬን እስቅ ነበር፡፡ ታድያ የቤቱን ችግር ነግሬያቸው አላወቅም፡፡ ለምን ይጨነቁ ብዬ፡፡

በኋላ ግን ባሰብኝ፡፡ ‹‹ቡችላው ሲጮህብሽ ዝም ካልሽው ውሻው ይነክስሻል›› ይባላል፡፡ ጭቅጭቁን ስታገሠው ጊዜ ዱላ ጀመረ፡፡ እርሱን ግን መቋቋም አቃተኝ፡፡ ሲብስብኝ ለእማማ ነገርኳቸው፡፡ አረሩ፣ ደበኑ፡፡ ምን አድርገሽው ነው እንኳን አላሉኝም፡፡ እስኪመጣ ድረስ አብረውኝ ቁጭ አሉ፡፡ አጅሬው አገር ሰላም ነው ብሎ ማታ ነበር የመጣው፡፡ እናቱን ይወዳቸዋልም ያከብራቸዋልም፡፡ ለእናት ለአባቱ አንድ ልጅ ነው፡፡ ከአባቱ ይልቅ እናቱን ነበር የሚፈራው፡፡ እርሳቸውን እንኳን ልጃቸው የሠፈር ሰው እንደ ንጉሥ ነው የሚያከብራቸው፡፡

ሲመጣ እሳት ጎርሰው እሳት ልሰው ጠበቁት፡፡ ‹‹አንተ ይህችን ትመስል ልጅ ያጋባንህኮ ተንከባክበህ፣ አክብረህ እንድትይዛት ነው፡፡ እንድ

የሚከራዩ አማት (አማትና ምራት አንድ ላይ የሚያነቡት)

ከዳንኤል ክብረትDanielkibert.com

ትጫወትባት አይደለም፡፡ በእርሷ ላይ ነው ዱላ የምታነሳው፣ በእርሷ ላይ ነው አምሽተህ የምትመጣው፡፡ አየሁህኮ፣ በዓይኔ በብረቱ አየሁህ፡፡ ይህችን ትመስል ልጅ እንድታበላሽ አልፈቅድልህም፡፡ እኔ ጥሩ ሰው መስለህኝ ነበር የዳርኩልህ፡፡ ለካ እንደዚህ ሆነሃል፡፡ በይ ተነሽ፤ እኔ ምን የመሰለ ባል ፈልጌ እድርሻለሁ፡፡ ያዥ ልብስሽን›› አሉና ያን ጊዜ ሞባይል የለም በቤት ስልክ ለባላቸው ደወሉ፡፡ ባላቸው ፔጆ መኪናቸውን ይዘው መጡና ተነሥቼ ወደ አማቴ ቤት፡፡

እዚያ ስደርስ የእንግዳ ክፍል ተከፈተልኝ፤ ልብሴ ተጣጥፎ ተቀመጠልኝ፡፡ ‹‹አይዞሽ የኔ ልጅ፤ እርሱ የእኔ ልጅ አይደለም፡፡ ልጄ አንቺ ነሽ፡፡ እንኳን መምታት ዘወር ብሎ ሊያይሽ አይችልም›› ተባልኩ፡፡ መቼም የእርሳቸውን ነገር አውርቼ አልጠግበውምኮ፡፡ የእኔ እናት እንጂ የእርሱ እናት አይመስሉኝም፡፡ የእኔ እናትና አባትማ ናዝሬት ስለነበሩ እንዲህ በቶሎ መምጣት አይችሉም፡፡ እናቴም ‹‹ምን ከእኔ የበለጠ እናት አግኝተሻል፤ እኔ ምን አደርግልሻለሁ›› ነበር የምትለኝ፡፡

ባለቤቴ ጨነቀው፡፡ ምን ያድርግ፡፡ መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ ነው የወረደበት፡፡ እናቱን ያውቃቸዋል፡፡ አይወስኑ እንጂ ከወሰኑ ማንም አይመልሳቸውም፡፡ እንደፎከሩት ለሌላ ቢድሯትስ ብሎ ፈራ፡፡ማን ተከራክሮ ይመልሳቸዋል፡፡ እንደ ዘንድሮ ባልና ሚስት ፍርድ ቤት መሄድ ያኔ አይታወቅ፡፡ ምን ያድርግ? ወስከንቢያው ነው የተደፋበት፡፡ ከአንድ ሳምንት በኋላ የእርሱ ሽማግሌዎች የነበሩት ታላላቅ ሰዎች መጡ፡፡ እማማ እሽ ሊሉ ነው፡፡ ‹‹ልጄን እንዲያበላሽ አሳልፌ አልሰጠውም፡፡ ጓደኞቹ ካዋጡት ይዳሩት፡፡ እኔ የሚሳደብና የሚደባደብ ልጅ አልወለድኩም፤ አላሳደግኩም፡፡ ይቺን ትመስል ልጅ ብንድርለት በእርሱ ብሶ ሊማታ፡፡ የለም የለም፤ ልጄን እኔ ምን የመሰለ ጠባይ ከመልክ የተሰጠው ፈልጌ እድራታለሁ እንጂ እርሱማ አይጫወትባትም›› ብለው አሻፈረኝ አሉ፡፡ የእኔ እናት እንጂ የእርሱ እናት አይመስሉም ነበር፡፡ ሽማግሌዎቹም ተጠራጠሩ፡፡ እኛ ቤት የመጡ ነበር የመሰላቸው፡፡ እማማኮ ስለ ምራታቸው የሚያወሩ አይመስሉም፡፡

በሁለተኛው ሳምንት አጅሬ ለካ እናቴ ጋር ደውሏል፡፡ ስትሰማ ደነ

ገጠች፡፡ ለአባቴ ነግራው ሲበሩ መጡ፡፡ ከቤት መውጣቴን ሰሙ፡፡ ደግሞ ወጥቼ የገባሁት አማቶቼ ጋ፡፡ ጉድ ተባለ፡፡ አቤት እማማ የሠሩት ሥራ፡፡ የእርሱ እናት እኔን አልሰጥም ብለው የእኔ እናትና አባት ለእርሱ አማላጅ ሆነው መጡ፡፡ ተገላበጠ፡፡ እማማ እንደ ባሕሉ አስተናገዱና ምን ልታዘዝ? አሉ፡፡ ‹‹ልጃችሁ ሽምግልና ልኮን ነው›› አሉ፡፡ እማማ አልሰጥም ብለው እምቢ አሉ፡፡

‹‹ምንም ብትወልዷት አልፈቅድላችሁም›› አሏቸው፡፡ ቀኑን ሙሉ ሲለምኑ ዋሉ፡፡ አባቴ ብልሃተኛ ነው፡፡ ‹‹እንጥራውና እዚሁ ዋስ ጠርቶ ቃል ይግባ›› አለ፡፡ እማማ ተስማሙ፡፡ ተጠርቶ መጣ፡፡ እየተንቀጠቀጠ ነበር የገባው፡፡ ወዳደገበት ቤት የሚገባ አይመስልም ነበር፡፡ ‹‹ሁለተኛ አንዳች ነገር አልናገራትም፣ እጄን አላነሣም፣ አላመሽም፣ አልጠጣም፣ ከቃሏ አልወጣም ብለህ ቃል ግባ›› አሉት እማማ፡፡ ቃል ገባ፡፡ ዋስ ጥራ ተባለ፡፡ ዋስ ማንን ቢጠራ ጥሩ ነው፤ የእኔን አባት፡፡ እዋሰዋለሁ አለ አባቴ፡፡ ‹‹በል ሁላችንምም ጉልበት ሳም›› አሉት እማማ፡፡ ሳመ፡፡ ‹‹አንድ ነገር ቢልሽ ደውይልኝ፤ ልጄን እወስዳታለሁ፡፡›› አሉ እማማ በማሠሪያው፡፡

እኔም ቤቴ ተመለስኩ፡፡ ኩሽ የለ፤ ዱሽ የለ፡፡ ሰላም፡፡ ጠባዩ ለወጥ ሲል ‹‹ለእማማ እደውላለሁ›› ነበር የምለው፡፡ እንዲህ ‹‹ለእማማ እደውላለሁ›› እያልኩ ይኼው ዐርባ ዓመት ኖርን፡፡ ስናስበው እንስቃለን፤ ለእኛ በሰላም መኖር ምክንያቱ እማማ ናቸው፡፡ ብዙ አማቶች ለልጃቸው አግዘው ከምራታቸው ጋር ነው የሚጣሉት፡፡ እንዲህ እንደርሳቸው ከዝምድና በላይ የሚያስብ አይገኝም፡፡ እናቴ ለእኔ በትረዳ ምን ይገርማል፡፡ አማቴ እናት ሲሆኑ ግን እንዲህ ትዳርን ያዘልቃል፡፡ እርሱማ ልጃቸው ነው፡፡ የት ይሄድባቸዋል፡፡ አሁን አሁን ነገሩ ሲነሣ ‹‹እማማ ግን እውነት ለሌላ ሊድሩኝ ነበር›› እላቸዋለሁ፡፡ ‹‹ባክሽ ላስፈራራው ብዬ ነው፡፡ ስቆርጥ ያውቀኝ የለ፡፡ ጉድ ትሠራኛለች ብሎ ነውኮ የፈራው፡፡ እናቱ ሚስቱን ወሰዱበት ቢባል እነዚህ ጓደኞቹ የሚለቁት ይመስልሻል? ጳውሎስ ኞኞ ነበር በጋዜጣ የሚያወጣው›› ይላሉ እየሳቁ፡፡

መከራየት እኒህን አማት ነበር፡፡

የደናግላን ቁጥር ለምን ቀነሰ?ከገጽ 10 የዞረባወጣው ጥናታዊ መግለጫው የተለያዩ ባህሎች

ውስጥ የሚደረጉ ጋብቻዎችን በ3 ጎራ ፈርጀውታል፡፡ በመጀመሪያ ምድብ ውስጥ የተካተተው ለአቅመ ሄዋን የደረሰችን ልጃገረድና የጎልማሶች ጋብቻ በወላጆች ወይም በቤተሰብ የሚዘጋጅበትን ሲሆን በእነዚህ ማህበረሰቦች ውስጥ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች በዕድሜ ከገፉ በኋላ ከወሲብ ጋር እንዲተዋወቁ ይደረጋል፡፡ እንዲሁም ወሲብ የሚፈፀመው በተቃራኒ ፆታዎች መሃል ብቻ ነው፡፡ በዚህ ምድብ ውስጥ ከተካተቱት ውስጥ ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሀገሮች ማሊ፣ ሴኔጋልና ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ የህንድ ንፍቀ ክበባት (Indian Subcontinent) በዚህ ምድብ ውስጥ ተካትተዋል፡፡

በሁለተኛው ምድብ የተካተቱት ባህሎች (ሀገሮች) ደግሞ ቤተሰቦች ሴት ልጆቻቸውን ጋብቻን እንዲያዘገዩ ወይንም እንዲያቆዩ፣ ግን ጋብቻን እስኪፈፅሙ ድረስ ከወሲባዊ ተራክቦ እንዲታቀቡ የሚያደፋፍሩ (Families encouraged daughters to delay marriage, but to abstain from sexual activity prior to it) ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ወንዶች ልጆቻቸው ከጋብቻ በፊት ከትልልቅ ሴቶች ወይም ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር ወሲብን እንዲፈፅሙና ተሞክሮአቸውን እንዲያዳብሩ ያደርጓቸዋል፡፡ የዚህ ምድብ አባላትም ከደቡባዊ አውሮፓ ፖርቹጋል፣ ግሪክና፣ ሩማንያ እንዲሁም ከላቲን ሀገሮች ውስጥ ብራዚል፣ ቺሊና ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ይገኙበታል፡፡

በሶስተኛው ምድብ የተቀመጠ ባህሎች ውስጥ የሚገኙት ህዝቦች ደግሞ ወንዶችና ሴቶች ወሲባዊ ግንኙነትን ለመፈፀም በተቻለ መጠን ዕድሜያቸው ተቀራራቢ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ከእነዚህ ሌላ ንዑስ ምድቦች ሲኖሩ የወሲብ መፈፀሚያ ዕድሜዎችም ከፍ ዝቅ ይላሉ፡፡ ለምሳሌ በሰሜንና ምስራቅ አውሮፓ ቬርቤን፣ ቼክሪፐብሊክና ሲውዘርላንድ ውስጥ ወንዶችና ሴቶች ወሲባዊ ትውውቅን የሚያደርጉበት ዕድሜ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡

በታላቋ ብሪታኒያ በተደረገ የፆታ ትምህርት ዳሰሳ እንዳሳየው ከሆነ ዕድሜያቸው ከ14-17 ዓመት መሃል ከሚገኙ ወጣቶች ውሳኔ 6 በመቶ ብቻ ከጋብቻ በፊት ወሲብን ያለመፈፀም (መታቀብ) ዝንባሌ እንዳላቸው ታውቋል፡፡

የሴት ድንግልና (Family virginity) በብዙ ባህሎች ውስጥ ከግለሰባዊና ቤተሰባዊ ክብር ጋር የተገናኘም ነው፡፡ እነዚህ ‹‹የሀፍረት ማህበረሰቦች›› (Shame Societies) ተብለው በሚታወቁ ህዝቦች ውስጥ አንዲት ሴት ከጋብቻ በፊት ድንግሏን ብታጣ ለቤተሰቡ ከፍተኛ ሀፍረትና ውርደት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ለምሳሌ በደቡብ አፍሪካው የጋንቱ ማህበረሰብ ውስጥ ድንግል መፈተሽ እና ብልትን መስፋት በስፋት የተለመደ ተግባር ሲሆን፣ የሱዳን ኬንዙ ልጃገረዶችም ለአቅመ ሄዋን ከመድረሳቸው በፊት በአዋቂ ወንዶች የድንግላቸው መኖር ከተፈተሸ በኋላ ያገቧቸዋል፡፡ በዚሁ የኬንዙ ማህበረሰብ ውስጥ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ልጃገረዶችን መግረዝና ንፁህ ሆነው እንዲቆዩ ብልታቸውን መስፋትም ባህላዊ ተግባር ነው፡፡

አንዳንድ ሀገሮች ውስጥ ደግሞ አንድ ወንድ አንዲት ልጃገረድን አስገድዶ ቢደፍር ወይንም ክበረ ንፅህናዋን ቢገስ እንዲያገባት ወይንም ለወላጅ አባቷ ካሳ እንዲከፍል የሚያስገድዱ ህጎችና ደንቦች ተደንግገዋል፡፡ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ድረስ በአንዳንድ ሀገሮች ውስጥ አንደ ወንድ አስገድዶ በመድፈር ድንግሏን ከወሰደና ሊያገባት ፍቃደኛ ካልሆነ ተጠቂዋ የገንዘብ ካሳ ለመጠየቅ የመክሰስ መብት ተሰጥቷታል፡፡ የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ደግሞ በዚህ የአስገድዶ መድፈርና የክብረ ንፅህና መገሰስ/ያለ ፈቃድ ላይ ፈጣንና ዳጎስ ያለ ቅጣት ያስቀምጣል፡፡

ድንግልናቸውን ለሽያጭ ያቀረቡ ልጃገረዶች

ድንግልና የላቀ ክብር ብቻ ሳይሆን የላቀ ዋጋ ያለው ጥሬ ዕቃ ይመስላል፡፡ ‹‹ድንግል ሴት ንፁህ ናት ተብሎ ስለሚታመን ከንፅህናዋ አክሊል በላይ ንፁህ ሰብዕናዋ በዜጎች ዘንድ የላቀ ዋጋ ያሰጠዋል›› ይላሉ- የስነ ልቦና ባለሙያው፡፡ ‹‹ይሄ እንደ ብርቅ የሚታየው የጨዋነት ሚዛን በሀገራችን በተለየ ሁኔታ በተለይ በአሁን ወቅት ደናግላን በልዩ መነፅር (የደናግላን... ወደ ገጽ 23 የዞረ)

Nuru Dedefo, ESQ.Attorney at Law & Counselor

- Car Accidents- Work place Injuries- Immigrations- Family Law- Criminal Law

If you have legal issues, you need a lawyer who fights

for your rights. Nuru Dedefo fights for your rights.

If you have questions, Contact Nuro Dedefo Law Firm at:3989 central Ave, NE, Columbia Heights, MN 55421

(763)-781-5254 (office), (612-559-0489) Cell(763)-781-5279 Fax

የሚታደስ... ከገጽ 7 የዞረየምትረግጡት መሬት ወደ አፈርነት የተሸጋገሩ ንጉሣችንና ሠራዊታችን ነው።” የሚል አሳብም ተለዋወጥን። ብቻዬን ቀረሁ እንዴ? በኤርት

ራና በኦጋዴን ያገኘኋቸው ዛሬም በሕይወት የሚገኙ መኰንኖችና ስማቸውን ያልያዝሁላቸው ኢትዮጵያውያን አሉ። አሉ፣ አሉ። ሃሌ ሉያ! ምን ያደርጋል የትዝታን ጓዝ ተሸክሞ መኖር?

አንዲት ነጥብ ላክልበት መሰለኝ። የሱዳኖቹ የመሬት ጥያቄ የመጣው በ1963 አካባቢ ይመስለኛል። ያን ጊዜም የፓርላማ አባላት ( በተለይ የጐንደር ክፍለ ሀገር ተወካዮች) ሱዳኖች ንጉሠ ነገሥቱን ሊያሳስቱ ነው ተብሎ ሲወራ በግልጽ ተፋለሙአቸው ተብሎ ተወራ። በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ የሱዳን መንግሥት የኤርትራን ወንበዴዎች (ዛሬም ያው ናቸው) መርዳቱ ጣልቃ ገብነትና የጉርብትናን መንፈስ የሚያደፈርስ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትንና የአፍሪካ አንድነትን ቻርተሮች የሚጻረር ነው የሚል አቋም ነበር። በጉርብትና የሚኖሩ አገሮች በየድንበሩ ላይ ካሉ ብሔረሰቦች ጋር የፖለቲካ ጨዋታ ቢጫወቱ- ወይም ለወደፊት ችግር ማስተንፈሻ ቢያደርጉ ክፉ አይደለም። የሞራል ጣጣም የለበትም። ታዲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራችን - ቀልጣፋውና ወሳኙ ከተማ ይፍሩ “በመስተዋት ቤት የሚኖሩ ወደ ሌሎች ደንጊያ በመወርወር የመጀመርያዎቹ መሆን የለባቸውም” የሚል መግለጫ ሰጡ። Those who live in glass houses should not be the first to throw stones to others ነበር የተባለው።

አዎን ወዲያው በዮሴፍ ላጐ የሚመራ የደቡብ ሱዳን ንቅናቄ (አናንያ ሁለት) ሲመሠረት ( በኢትዮጵያ የፖለቲካ ድጋፍ) በወቅቱ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው ሰዲቅ ማኅዲ (ከላይ የጠቀስነው ማኀዲ የልጅ ልጅ) ሮጦ መጥቶ ከጃንሆይ እግር ሥር ወደቀ የሚባል ወሬ ተወራ። “እርስዎ የአፍሪካ አባትና ሱዳንም አገርዎ አይደለችም ወይ?” በማለት ሲማጸናቸው የአናንያ ሁለት መሪ ጆሴፍ ላጐንና ሱዳንን አስታራቂ ሆኑ። በነገራችን ላይ ብዙም ሳይቆይ ነበር ጄኔራል ጃፋር ኒመሪ በመፈንቅለ መንግስት አማካይነት ሥልጣን የያዙት።

ሱዳን ከዚያ በኋላ የመሬት ጥያቄ ያቀረበችበትን ጊዜ ሁኔታ አላስታውስም። ታሪክ በዕዳና በቅጣት መልክ ከጣለብን ከእነ ኅይለማርያም- አንደበት የምንሰማው ካልሆነ በቀር! በዚያ ሰሞን የቀድሞ መሪያችን ኮሎኦኔል መንግሥቱ በኢሳት ቴሌቪዥንና ራዲዮ ተጠይቀው መልስ ሰጥተውበታል። ምን ሲደረግ? በሌላ ሌላ (በአብዛኛው በፈጣን ውሳኔያቸው) መንግሥቱን ከሌሎች ሰዎች ጋር ላማቸው እችላለሁ። የኢትዮጵያን መሬት የሚጠይቅ አሳብን በማስተናገድ ረገድ መጽሐፉ አይጠቅሳቸውም። በነገራችን ላይ በ17ቱ ዓመት የደርግ አመራር እኔም እንዳቅሜ ኢትዮጵያ ከጐረቤት አገሮች ጋር ያላትን ፖለቲካ፣ የድንበር ጥያቄና ሌሎች አለኝታዎች በሚመለከተው ኮሚሽን በአባልነት ሠርቻለሁ። ከሱዳን ጋር በርከት ላሉ ዓመታት በፖለቲካ ባላንጣነት መቆየታችን ይታወሳል። ያንን መጋረጃ ለመቅደድ በተደረገው ሙከራ ካርቱም ላይ ይኸው ኮሚሽን ከሱዳን አቻው ጋር በፍቅር ተመርቶ ባስገኘው ውጤት መሠረት ሁለቱ መሪዎቻችንን ለማቀራረብ ተችሎአል። እንዲያውም የኮሚሽኑ አባላት በዶክተር ፈለቀ ገድለ ጊዮርጊስ- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በሱዳን አቻቸው አማካይነት ከፕሬዚዳንት ኑሜሪ ጋር ስንገናኝ ስለ ግንኙነቱ መታደስ ከእኛ የበለጠ ሱዳኖቹ መደሰታቸውን ተረድተነዋል። ኑሜሪ እንደ ቀልድ አድርገው “ምሥጢር ልንገራችሁ። ከእናንተ ጋር ሆነን ሻዕቢያዎችን እንደምወጋቸው ቃል እገባለሁ” ማለታቸውን አስታውሳለሁ። (በፕሬዝዳንት ኑመሪ ላይ ከ16 የሚበልጡ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች ተደርገው ነበር። ከ12 በማያንሱት የሻዕቢያ ተሳትፎ ነበረበት)

ፕሬዚዳንት ኑሜሪ በፈንታቸው ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ (አሁንም የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አባል ሆኘ) ከመሪያችን ጋር በሰፊው ተነጋግረዋል። እንዲያውም የሁለቱ አገሮች ልዑካን በተገኙበት ጓድ መንግሥቱ “ወንድሜ ፕሬዚዳንት ኑሜሪ ምንም እንኳ ሕመም የሚሰማቸው ቢሆንም ያለ ማቋረጥ አሥራ ሰባት ሰዓት ብቻችንን ተነጋግረናል” ማለታቸውን አልዘነጋውም። ከሱዳን ጋር የመሬት ጥያቄ ቢኖር ባለቤት የሌለው አገር ባገኙበትና ሱዳንን ተገን አድርገው ሲወጉን ለነበረው ውለታው መሬት ከሆነ ያ ሌላ ጉዳይ ነው። የመሬት ጥያቄ ከተነሣ ኢትዮጵያ የተወሰደባትን ( በእንግሊዞች፣ በግብፆች፣ በራስ ደበብና በደጃች ገብረሥላሴ ተዋናይነት) ከሰላን፣ ገዳሪፍንና ከኤርትራም የተሰነይን ባለቤትነት ልታነሣ ትችላለች። የሚያሳዝነው ኢትዮጵያ ልጅ አላወጣችም- በመንግሥት ሰፈር።

ለእኛ ለዛሬዋ የኢትዮጵያ ትውልድ እንደ ሐውልት የጐላ ቅርስ የሚሆነን የንጉሠ ነገሥቱ ከአገሩ ድንበር ላይ ከአያሌ መኳንንቱ ጋር መውደቁ ነው። ለእኛ ለዛሬ የኢትዮጵያ ልጆች ውርሳችንና ቅርሳችን ሆኖ አላስተኛ ሊለን የሚገባው ያንን ዳርድንበር በማስከበር ሒደት ሺህ በሺህ ወገኖቻችን የጠላትን ጉርንቦ እየያዙ፣ እየጣሉ መውደቅ ነው። ጃንሆይ አጤ ዮሐንስ በጠላት ጥይት ከወደቁ በኋላ እንኳ “አስከሬናቸውን” አናስነካም በማለት የተሰውት (ከመኳንንቱ) ትልቁ ራስ አርአያ፣ ቢተወደድ ገብረ መስቀል፣ ደጃች ተድላ፣ ብላታ ገብረማርያም፣ መምህር ወልደ አረጋዊ፣ መምህር ክንፈ ኪሩብ፣ ቄስ ገበዝ ሰላማ…ይገኙበታል። ሌሎች ደግሞ- አትጠራጠሩ- መለከት ያልተነፋላቸው፣ ምንም ያልተዘመረላቸው የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ናቸው። The Unknown Ethiopian Soldiers የሚባሉቱ

አዎን የትናንቱ ለዛሬ፣ የዛሬው ለነገ የሚያወርሰው ይህን መሳዩ የታሪክ ሰንሰለት በምንም ምክንያትና አጋጣሚ መቋረጥ የለበትም። ይህ የታሪክ ሰንሰለት የተበጠሰ ዕለት ሕልውና ዋስትና ያጣል። ይህ ሒደት ለብዙ ምዕት ዓመታት በኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ባሕርይ ላይ ሲታይና ሲያንፀባርቅ ኖሮአል። እንዲህ ያለ ብሔራዊ ፋይዳ ደግሞ ተመልካችን ሳይቀር “የማን ልጅ ነህ? የየትኛው (የሚታደስ... ወደ ገጽ 12 የዞረ)

Page 10: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 10

የደናግላን ቁጥር ለምን ቀነሰ?ከሮቤል ሔኖክድንግልና ወይም ክብረ ንፅህና (Virginity) የሴትነት ወሲባዊ ተአቅቦታና የጨዋነት ሚዛን እንደሆነ በሀገራችንም በሌሎች ሀገራት

ም ይታመንበታል፡፡ ይሄን ተከትሎ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሀገራችን ደናግላን ለመድረክ ወብቅ እያሉና እየተሰባሰቡ የዘመን ጥንካሬያቸውን እያሳዩ ነው፡፡ ዛሬ ፅሑፋችን የደናግላኑን ሰብዕናና በተቀሩት ሀገሮች ላይ የተደረጉ ጥናቶችን ዋቢ አድርጎ የድንግልናን (Virgin-ity) ምስጢር እና ድንግልና በወንዶች ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ ይተነትናል፡፡

‹‹ኬላው ተሰበረኬላው ተሰበረበእናት ባባቱ ቤትተከብሮ የኖረ...ኬላው ተሰበረ››የሚለውን ህዝባዊ መዝሙር (ዘፈን) የሚያስታውስ ይኖር ይሆን? ያውም ከነዜማው የሚያስታውስ ይኖራል ብሎ ማሰብ ይከብዳ

ል፡፡ የወንድ ሚዜዎች የሙሽራውን የአባወራነትና የወንድነት ጥንካሬ ለመግለፅ፡-‹‹እንክትከት አደረጋትስብርብር አደረጋትአሆሆ...የኛ ወጣት...›› እያሉ የጫጉላውን ምሽት ሲያደምቁ... የሴት ቤተሰብ ደግሞ የልጅቱን ጨዋ አስተዳደግ ከጋብቻ በፊት ወሲብ አለመ

ፈፀሟን ለመግለፅ ‹‹ኬላው ተሰበረ...›› ይላሉ፡፡ ‹‹እንክትክት አደረጋት›› የሚሉት ሚዜና የሠርጉ አድማቂዎች ክብረ ንፅህናን በመገርሰስ ሂደቱ አልጋ በአልጋ እንዳልሆነ አድካሚ እንደሆነ ማስረዳታቸው ይመስላል፡፡ ‹‹ኬላው ተሰበረ›› ሲሉም በቀላሉ የማይደፈር የማንነት ድንበር መሆኑንና ክብሩን ከፍ ከፍ ለማድረግ የሚገልፁት ነው ማለት ይቻላል፡፡

ይህ የልጃገረዶች እስከ ጋብቻ ክብርን ጠብቆ የመቆየት የውዳሴ አጀባ በሀገራችን ድምፁ እየሰለለ... ሞገሱ እየኮሰሰ የሄደ ይመስላል፡፡ ጨርሶ ባይጠፋም፡፡ የውዳሴ ዜማው ሆታ በጭብጨባና በጫጉላ ምሽት ከበርቻቻ... ባይገለጥም ወጉ በጥንዶች የፍቅር ሹክሹክታ ውስጥ የራስን ክብር (ድንግልና) አሳልፎ መስጠት አሁንም ያለ ተግባር ነው፡፡ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ይሄ ድንግልናን እስከ ጋብቻ አቆይቶ በጋብቻ ወቅት የክብረንፅህናን ሙሉነት በመሃረብ በተቀባ የክብር ደም ማሳየቱ አሁንም የሚታይበት ሁኔታ እንዳለ ይታሰባል፡፡ አብዛኛው አስተያየት ሰጪ ግን የወቅቱ የጋብቻ ሁኔታ በዘመናዊ ዘፈን ተሸርቦ ‹‹ክብረ ንፅህና ድሮ ቀረ›› የሚለውን በድምፃዊው ማይክ ባይሆንም ‹‹በግልፅ ዝምታ›› ያንፀባርቃሉ ብለው ያስባሉ፡፡ ክብረ ንፅህናን እሰከ ጋብቻ ያለማቆየት ልማድ እየተስፋፋ በመጣበት ሁኔታ ውስጥ ግን ያውም ከመዲናችን አዲስ አበባ ደናግላን መድረክ ላይ ወጥተዋል፡፡ ራሳቸውን ለመድረክ ያላበቁ እህቶቻችንም እንደሚኖሩ ይገመታል፡፡ ‹‹የእኚህ ደናግላን ወደ መድረክ መውጣት አቻዎቻቸውን የመቀላቀል ኃይል ይፈጥራል›› ይላሉ የስነ ልቦና ባለሙያው አቶ ዳንኤል ተሻለ፡፡ ‹‹እስከ ጋብቻ ተጠብቆ የመቆየት ወኔንም ያላብሳል›› ብለዋል፡፡

ድንግልና ምንድን ነው?ወሲባዊ ተሞክሮ በፍፁም የሌላት ‹‹ድንግ

ል›› ተብላ እንደምትጠራ ጥናቶች ይገልፃሉ፡፡ ድንግላዊነት ማለት ድንግል ሆኖ መገኘት ማለት ነው፡፡ የቃሉ መሰረት ቪርጎ (Virgo) ከሚለው የላቲን ቃል የመነጨ ሲሆን ትርጓሜውም ‹‹ወሲባዊ ተሞክሮ የሌላት ሴት›› ማለት ነው፡፡

ልክ እንደ ላቲኑ ሁሉ የእንግሊዝኛውም ቃል ዕድሜን ፆታንና ወሲባዊነትን ሰፋ አድርጎ የሚገልፅ ቃል ነው፡፡ በዚህም መሰረት የጎለመሱ ሴቶችም ድንግሎች ወይም ደናግላት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ወንዶች እና የተለያዩ እምነቶችና መስህቦች ውስጥ በአዲስ አባልነት የሚመለመሉ ሰዎችም ድንግል ሊባሉ ይችላሉ፡፡ አንስታይ የእንስሳ ቤተሰቦችም ወሲባዊ ተራክቦን እስካልፈፀሙ ድረስ ድንግል ናቸው ይባላል፡፡ እስካሁን የታወቀው የእንግሊዝኛው ቃል የመጀመሪያው አጠቃቀም የዋለው ካምበሪጅ ዩኒቨርሲቲ ትሪንቲ ኮሌጅ የሚገኘው የአንግሎ ሳክስን የብራና ፅሑፍ ውስጥ ነው፡፡

በኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ውስጥ የሰፈሩት 18 አይነት የድንግል መገለጫዎች በአብዛኛው ተመሳሳይ ቢሆኑም በ1923 ፍራንክ ሃሪስ ግን በአንድ ሌክቸሩ ላይ ድንግል የሚለውን ቃ ቀልደኛ በሆነ ማብራሪያ ሲተረጉመው ‹‹ቪር Vir›› ሁሉም ሰው እንደሚያውቀው በላቲን ‹‹ሰው›› ማለት ሲሆን ‹‹ጂን-Gin›› ደግሞ በቆየ እንግሊዝኛ ‹‹ወጥመድ›› ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹ድንግል-Virgin›› ማለት ታዳሚዎችን አስቋል፡፡

‹‹Vir- Gin››መምህሩ ፍራንክ ሃሪስ ‹‹Vir- Gin›› በሚል ክፍልፋይ ትርጓሜዎች ቀልዱን መወርወሩ በሀገራችን እንደ ቀልድ የሚታይ አይመስል

ም፡፡ በእርግጥም ድንግልና የወንድ ወጥመድ ይመስላል፡፡ ድንግል የሆኑ ሴቶችን መርጦ ለጋብቻ ማጨት... ድንግልን የሆነችን ሴት ለማቅበጥ አጮልቆ ማየት በተለይ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የደፈጣ ውጊያ ያህል ይታያል፡፡ አንዲት ሴት ድንግል መሆኗን ያወቀ ወንድ ወይም ማህበረሰብ ለሴቲቱ ከሚሰጠው ክብር ባሻገር ለመውደድ መንሰፍሰፍም የሚታይ ሁኔታ ነው፡፡

በ2001 ‹‹የሚስ ቨርጂን›› አሸናፊ የነበረችው ኤልሳቤት ይሄንን ታረጋግጥልናለች፡፡ ‹‹ድንግልናዬን ሰዎች አይተውኝ የሚያውቁበት መንገድ የለም፡፡ በቅርብ የሆኑ ጓደኞቼ ግን ያውቃሉ፡፡ እነሱ ዘንድ ከፍተኛ አክብሮት እንዳለኝ አረጋግጫለሁ›› የምትለን ኤልሳ፤ ነገር ግን የወንዶች ወጥመድ እንደሆነም ታምናለች፡፡

ክብረ ንፅህናዋን /ድንግልናዋን/ በህክምና አረጋግጣና ከደናግላን አቻዎቿ (ከ17 ልጃገረዶች) ጋር ተወዳድራ በውስጣዊ መመዘኛዎች ጭምር በአንደኝነት ተሸናፊ የሆነችው ኤልሳ ወንዶች ለድንግልና የሚሰጡት ክብርና ትኩረት ቢገለጥላትም ‹‹ድንግል ወንድ›› ያጋጥመኛል? ብላ ስታስብ ሳቋ ይቀድማል፡፡ ሆኖም ‹‹ጥሩ ስብዕና ያለው አላማዬንና ጥንካሬዬን የሚከተል ጥሩ ባል በጊዜው አገኛለሁ›› ትላለች- አሁን አላማዋን የማሳካት ሂደት ላይ ናት፡፡

‹‹... እጃችን ገባች ሳይውልም ሳይነጋ!...››...የፈረንሳይ ብሔራዊ ስነ ህዝብ ተቋም ተመራማሪ ሚካኤል ቦዘን በ2003 ዓ.ም (የደናግላን... ወደ ገጽ 9 የዞረ)

ትዝብት ከአሜሪካ

ፒያሣ ገበያ ሲመጡ ምንም እንደማያጡ ይተማመኑ

ያያ... ከገጽ 23 የዞረመልስ፡- ድንቅ አሰልጣን አለን፡፡ መልካም እግርኳስ በመጫ

ወት ላይም እንገኛለን፡፡ ተጨዋቾችም የሚጫወቱት ደስተኛ ሆነው ነው፡፡ ማሻሻል የሚገባን ጥቂት ነገር ነው፡፡ በተገናኘን ቁጥር በርካታ ችግሮችን የሚፈጥሩብን አስቸጋሪ ክለቦች መኖራቸው ግን አይካድም፡፡ ከባርሴሎና ጋር ያደረግነው ጨዋታ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ ከውድድሩ የተሰናበትነው በመጀመሪያው ጨዋታ በሜዳችን በሰራነው ስህተት ነው፡፡ ከሚገባው በላይ ክብር ሰጥተናቸው ነበር፡፡ በመልሱ ጨዋታ ተሽለን የነበረ ቢሆንም ውጤቱን ለመቀልበስ ግን ረፍዶ ነበር፡፡ ለቀጣዩ ዓመት ጥሩ ትምህርት ነው፡፡

ጥያቄ፡- መጪው ጊዜ ብሩህ ይመስላል፡፡ ግን ዘንድሮስ? በ2012 ከሮቤርቶ ማንቺኒ ጋር በመሆን ዋንጫውን አሸንፋችኋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ቡድኑን የሚያሰለጥኑት ደግሞ ማኑኤል ፔሌግሪኒ ናቸው፡፡ በሁለቱ አሰልጣኞች መካከል የጎላ ልዩነት አለ?

መልስ፡- አሰልጣኞቹን ለመመዘን አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ሁለቱም ጠንካራ ሠራተኞች ናቸው፡፡ ማንቺኒ የተለየ ስታይል አለው፡፡ የበለጠ ትኩረት የሚሰጠው በመከላከሉ ላይ ነው፡፡ በፔሌግሪኒ ስር ግን ሲቲ ይበልጥ የሚያጠቃ ቡድን ሆኗል፡፡ ሁሉም ተጨዋቾች በዚህ ደስተኞች ናቸው፡፡ መሻሻሎችንም እያሳዩን ነው፡፡ ሳሚር ናስሪ እና ዴቪድ ሲልቫ ድንቅ ብቃታቸውን እያሳዩ ነው፡፡ ሰርጂዮ አጉዌሮ ደግሞ እንከል አልባ ሆኗል፡፡ በከፍተኛ ሁኔታ እያገዙን ያሉ አዲስ ፈራሚዎችም አሉ፡፡ ሂሰስ ናቫስ እና አልቫሮ ኔግሬዶ በዚህ የውድድር ዘመን ድንቅ ነበሩ፡፡ ከዚህ ሁሉ አድካሚ እና እልህ አስጨራሽ ጉዞ በኋላ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ላይ ዋንጫውን እናነሳለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ጥያቄ፡- እንደ ፈርናንዲንሆ በአጭር ጊዜ ፕሪምየር ሊጉን የለመዱ ብዙ ተጨዋቾችን አላውቅም፡፡ አንተ ምትሃተኛ የሆነ ስራ መስራት እንድትችል ወደ ኋላ በመቅረት ለተከላካይ ክፍሉ ሽፋን ይሰጣል፡፡ አብረኸው ለመጫወት የሚቀል ተጨዋች ነው?

መልስ፡- በጣም ብልህ ነው፡፡ ብራዚላዊውያን ውብ እግርኳስን ይጫወታሉ፡፡ እርሱ ደግሞ ብልሃትን ጨምሮበታል፡፡ አደጋን ማሽተት እና ፕሬስ አድርጎ መጫወት ይችላል፡፡ ያለኳስ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ኳስ በእግሩ ስር ስትሆንም በአግባቡ ይጠቀምባታል፡፡ በሻክታር እያለ የሚጫወተው እኔ በምጫወትበት ስፍራ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ እርሱ ለማጥቃት ወደ ፊት ሲሳብ የተከላካይ ክፍሉን ለማገዝ ወደ ኋላ እመለሳለሁ፡፡ ነገር ግን አንድ ላይ ጥሩ እየተጫወትን ነው፡፡ ብዙ እገዛም አድርጎልኛል፡፡ አሰልጣኙ ከእኛ ብዙ ይጠብቃል፡፡ ኳሷን በይበልጥ እንድንቆጣጠር እና እንድናጠቃ ይሻል፡፡ አንድ ጎል አስቆጥረን በራችንን እንደንዘጋ አይፈልግም፡፡

ጥያቄ፡- ውብ የሆኑ የቅጣት ምት ጎሎችን ጨምሮ በዚህ የውድድር ዘመን 22 ጎሎችን አስቆጥረሃል፡፡ በባርሴሎና በነበርክበት ወቅት በጭራሽ ቅጣት ምቶችን አትመታም ነበር፡፡ አሁን ግን ኳሷ በጎሉ ማዕዘን ላይ እንድታርፍ አድርገህ እየመጠንክ በመላክ ላይ ነ

ህ፡፡ ለውጡ ከየት መጣ? አዘውትረህ ትለማመዳለህ?መልስ፡- በትክክል፡፡ በማንቺኒ ስር ባሳለፍኩት የመጀመሪያ

ው ዓመት ቅጣት ምቶችን እለማመድ ነበር፡፡ በጫወታ ላይ ግን አስቸጋሪ ነበር፡፡ ምክንያቱም ቅጣት ምት በሚገኝባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ኃላፊነቱን ወስዶ ኳሷን የሚመታው ካርሎስ ቴቬዝ ነበር፡፡

ጥያቄ፡- ገብጋባ ነገር ነበር?መልስ፡- አዎን! ማሪዮ ባሎቴሊም እንደዚያው ነው፡፡ ከዚ

ያ በኋላ ግን ነገሮች ቀለል አሉልኝ፡፡ ምክንያቱም ልምድ ያለን ተጨዋች ከመሆኔም በተጨማሪ ከሌሎቹ ይልቅ ረጋ ያልኩኝ ነኝ፡፡ መምታት ስፈልግም ብዙ አልንደረደርም፡፡ የተወሰኑ እርምጃዎችን ብቻ ከኳስ ርቄ አቆማለሁ፡፡ ለእኔ ቅጣት ምቶችን መምታት የጉልበት ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡ ዋናው ነገር ቴክኒክ ነው፡፡ ኳሷን ስትመታ ምጣኔ ሊኖረው ይገባል፡፡ በእንግሊዝ ቅጣት ምቱን ለመከላከል በሚሰራው ግርግዳ ውስጥ በርካታ ረጃጅም ተጨዋቾች ስለሚኖሩ ኳሷ በፍጥነት ወደ ላይ ከፍ እና ዝቅ እንድትል ማድረግ አስቸጋሪ ነው፡፡

ጥያቄ፡- የፍፁም ቅጣት ምት አጠቃቀምን በተመለከተስ የምትለው አለ? ከሜሲ እና ከድሮግባ ጋር በመጫወትህ የቀሰምካቸው ቴክኒኮች አሉ?

መልስ፡- ፍፁም ቅጣት ምት አጠቃቀም ከእርጋታ ጋር በቀጥታ ይይዛል፡፡ ጆ ሃርት ፍፁም ቅጣት ምቶችን በማዳን በኩል በጣም ጥሩ የሆነ ግብ ጠባቂ ነው፡፡ እንቅስቃሴዎቹ ቀልጣፋ ናቸው፡፡ በፍጥነት የሚወረወር ሲሆን እስከ መጨረሻዋ ደቂቃም በትዕግስት ይጠብቃል፡፡ ይህ በልምምድ ወቅት ነገሮችን ከባድ ያደርግብናል፡፡ እኔ ግን ወድጄዋለሁ፡፡ ምክንያቱም በጨዋታ ላይ የምትመታውን ኳስ ሊያድንብህ ከሚችል ምርጥ በረኛ ጋር ልትፋጠት ትችላለህ፡፡ እንዲህ አይነቱን ልምምድ መስራትህ የሚጠቅምህ ያን ጊዜ ነው፡፡

ጥያቄ፡- በ2012 ዋንጫውን ስታሸንፉ ሰርጂዮ አጉዌሮ የማሸነፊያዋን ጎል ያስቆጠረው በመጨረሻዋ እስትንፋሳችሁ ላይ ነበር፡፡ እንደዚያ አይነት ክስተት ዘንድሮም ይደገማል ብለህ ታስባለህ?

መልስ፡- እንደዚያ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በ2012 እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ፈታኝ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ አጉዌሮ ወደ ድንቅ ብቃቱ እንደሚመለስ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ምክንያቱም በዚህ ወቅት በጣም ያስፈልገናል፡፡ ኤዲን ዜኮ እና ኔግሬዶ በዚህ የውድድር ዘመን ድንቅ ናቸው፡፡ አጉዌሮ ደግሞ የተለየ ነው፡፡ ልዩነት መፍጠር ይችላል፡፡

ጥያቄ፡- በሊቨርፑል በተለየ መልኩ የምትመለከተው ግለሰብ አለ?

መልስ፡- በዚህ የውድድር ዘመን የሚጨወቱት እንደ ቡድን ነው፡፡ ብሬንዳን ሮጀርስ ታላቅ አሰልጣኝ ነው፡፡ ሁሉም ሰው በእርሱ ደስተኛ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ብዙም የመጫወቻ ጊዜ ያልተሰጠው ወንድሜ ኮሎ እንኳን በአሰልጣኝ ደስተኛ ነው፡፡ ሁልጊዜም ቡድኑ ለጨዋታ ብቁ እንዲሆን እና ትኩረቱን እንዳያጣ ተግቶ ይሰራል፡፡ በዚህም ምክንያት ለአሰልጣኙ ክብር አለኝ፡፡

Minnesota:- DISTRACTED DRIVING LAWS

በሚኒሶታ ሕግ መሠረት መኪና እየነዱ ቴክስት ማድረግ ወይም ኢንተርኔት መጠቀም ሕገወጥ ነው። ሕጉ እንደሚለው መብራት ላይ ወይም ስቶፕ ሳይን ላይ ቆሞ ራሱ ቴክስት ማድረግም ሆነ ኢንተርኔት መጠቀም አይችልም። ይህን ሲያደርጉ ከተገኙ ፖሊስ ትኬት ይሰጥዎታል። ይጠንቀቁ።

Texting and Web AccessIt is illegal for drivers of all ages to compose, read, or send electronic messages or access the Internet on a wireless device when the vehicle is in motion or part of traffic. This includes being stopped in traffic or at a light.The law does not apply to devices that are permanently affixed to the vehicle or global positioning or navigation systems. Texting and web access statute — M.S. 169.475 Cell Phone Use and TextingIt is illegal for drivers under age 18 to use a cell phone, whether hand-held or hands-free — except to call 911 in an emergency. Permit and Provisional License statues--MS 171.05 and MS 171.055 Subd. 2(a)Cell phone use is totally banned for school bus drivers. School bus driver statute --MS 169.443 Subd. 9(b)

Reckless or Careless DrivingDistracted drivers can be ticketed for reckless or careless driving when their actions demonstrate a disregard for the safety or rights of others. Reckless and Careless Driving Statute - M.S. 169.13 - Source: Minnesota Department of Public Safety

Page 11: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 11

Page 12: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 12

የሚታደስ... ከገጽ 9 የዞረ አገር ልጅ ነህ?” የሚያሰኝ መሆኑን ከአሜሪካ ሕገ መንግሥ

ት አርቃቂ ምሁራን ዋነኛው ቤንጃሚን ፍራንክሊን ያብራራል- በአጭሩ። ከተወሰኑ ሰዎች ጋር ሆኖ በፓሪስ ከተማ ሲወያይ አገርን፣ ብሔራዊ ግዴታን፣ ትግልንና የትውልድ ኅላፊነትን በተመለከተ መግለጫ ሲሰጥ አንዱ፥ “እናት አገርህ ማናት?” ሲለው ፍራንክሊን “እናቴ አሜሪካ ናት” ይለዋል። ሰውዬው ሲመልስ “ለአዲሲቱ አገርህ የሺህ ዓመታት ዕድሜ ሰጥተሃታል” እንዳለው አንብቤአለሁ። ጥንታዊት ኢትዮጵያ አዲስ አገር መሆን እንዳለባት አምናለሁ። የሺህ ዓመታት ታሪክዋ እንዳይዘነጋ የምናደርገው - በቃልም በተግባርም ነው።

አገር ተደፈረ፣ አንድነታችን ተፈታ- በቁም ተሸጥን እያልን…በጫማ ተይዞ የሚሄድ አፈር ሥስት እንዳልነበረን ሁሉ… በእጅ አዙር ቅኝ ገዥነት የተከሰቱትን የወደፊት የኢትዮጵያ ገዢዎች ይኸው ክመሐላችን እያየናቸው ነው። እያቀበጥንና እያፋፋናቸውም ነው። የመሬት ቅርምቱን ጉዳይ በአኅዝ አስደግፈው፣ ከፖለቲካል ኢኮኖሚ ጋር አያይዘው- በሰፊው ሲያብራሩልን የቆዩትን እነ ዶክተር ዓለማየሁ ገብረማርያምን፣ ዶክተር ጌታቸው በጋሻውን፣ ፈቃደ ሸዋቀናን እንደገና እንድታነብቡአቸው ወደነሱ እመራችኋለሁ። በእኔ በኩል ግን እንዲያው የአገሬ ገበሬ፣ ነጋዴ፣ ኢንቬስተር ከውድድር ውጭ የመሆኑን ምሥጢር ደኅና አድርጐ የሚያጫው

ተን ምሁር እየፈለግሁ ነው። የማያልቅ ቂል ጥያቄ ሞልቶኛል። ኢትዮጵያን ቆራርጠን …አንዱን በአዋሽ፣ ሌላውን በአፋር ክ

ልል ሦስተኛውን በጋምቤላ…የምሸጥላቸው ነጋዴዎች- ፈረንጁ- አረቡ- ሕንዱ- ፓኪስታኑ…ከመቶ ዓመት በኋላ “ኢትዮጵያን መጀመሪያ የገዛኋት እኔ ነኝ..እኔ ነኝ” በመባባል ርስበርሳቸው ጦርነት እንዳያበቅሉ የሻጩ (ወያኔ) ሚና ምን ሊሆን ይችል ይሆን? አይ ቴዎድሮስ አንድ ፈረንጅ በመጫሚያው ላይ ይዞት ለሚሄደው አፈር እንዲያ መጨነቅ። አይ ዮሐንስ ሱዳን እንዲህ አንዲት ቀለህ ሳይተኩስ ለሚወርሰው መሬት “ቅዱስ ደምህን” ማፍሰስህ! (ከዚህ ላይ ባቋርጥ የሚከበኝ ባለቅኔ አለ? )

ከ1972 እ.አ.አ ጀምሮ እስከ ደራሲ መንግሥቱ ኀይለማርያም ስደት ድረስ በዓመት አንዴም ሁለቴም በመመላለስና ወራትም በመጨማመር ሕንድን አውቃታለሁ። 1972 ሃያ አምስተኛው የነፃነት በዓላቸው መታሰቢያ ነበር። በዚያ በር ገባሁና የ Insti-tute of Mass Communications የማያቋርጥ ጐብኝ ሆንሁ። Hindustan Times እና All India Radio, Times of India ባልደረባ መሰልሁ። በየዓመቱ ወይም በየስድስት ወሩ የሚጠራው Financial Writers አባልም እየተባልሁ እጋበዝ ነበር። ለነገሩ ስለ ፋይናንስ ስለመጻፍ ችሎታውም ዝንባሌውም አልነበረኝም። ብቻ ሕንድን ከዳር እስከዳር ለማወቅ ቻልሁ።

በመጀመሪያ ሕንድን ስጐበኝ የነበረው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥዕሉ አስደንጋጭ ነበር። ከትልልቆቹ እንደ ሒንዱስታን አ

ቶሚክ ሪሰርች ጣቢያ በር ላይ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ቤት አልባ ደሆች ታያላችሁ። በአግራ በሚገኘው ዝነኛው ታጅ መሐል ግቢ ሌሎች ሺህ በሺህ ደሆች ተረፍርፈው ታያላችሁ። ወደ ካልካታ ስትሄዱ ጐህ ሲቀድድ ጀምሮ ለዓይን ድንብዝብዝ እስኪል ድረስ በፈረስ ምትክ ጋሪ የሚጐትት ሰው ነው። (ሪክሾ ይባላል) በእግራችሁ ስትሄዱ ያም ሩዝ መግዣ ይለምናችኋል። ይኸም አንዲት ቂጣ (ፑሪ) መግዣ አንድ ሩፒ ጣል አድርጉልኝ ይላል። ሕንድ ይህን ሁሉ ችግር ተቋቁማና ድል አድርጋ ትናንት ተራ ሸርፓ (ኩሊ) የነበሩ ሰዎች ቢሊየነሮች መሆናቸው ያስደስታል። ምሳሌነታቸውም ግሩም ነው። ሌላ የሚደንቅ ነገር ደግሞ አለ። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ነፃነትዋ ከ67 ዓመት የማይበልጠው ሕንድ ከኢትዮጵያ የኅብረት ቅኝ ገዥዎች መሐል አንድዋ መሆንዋ ነው። አንድ ጓደኛችን እንደሚለው የአሰብ ወደብ የኢጣልያ ቅኝ ግዛት የሆነው በዚሁ አዝጋሚ ርምጃ ነው። ጁሴፔ ሳፒቶ ትንሽ መሬት ከራሒቶ ባላባቶች ይገዛል። ሩባቲኖ ለተባለ የመርከብ ኩባንያ ያዛውረዋል። ያ በፈንታው ለኢጣልያ መንግሥት ባለቤትነት ያስተላልፈዋል። ባለቤትዋ ኢትዮጵያ እያለች ለኤርትራ ይሰጣል። አባ መስጠት ወያኔ!

ዝነኛው የኢትዮጵያ ማዕድናት ባለቤትና የአዲስ አበባን “ዓይን የሆኑ ቦታዎች” ከልሎ የያዘው የሳዑዲ ነጋዴስ? ሌላው ግለሰብ (ለጊዜው) የኢትዮጵያ ቅኝ ገዥና- እንደ ጁሴፔ ሳፔቶ ቀስ ብሎ ለሳዑዲዎች የሚያስረክባት ነው። የታሪክ መቅድም አድርጋች

ሁ እዩልኝ። አንዳንድ የአሜሪካ ጋዜጦችና ከመስከረም አንዱ የአሜሪካ ትዊን ታወርስ አደጋ በኋላ በታተሙ መጻሕፍት ጭምር ስሙ የተነሳው ግለሰብ (በአሸባሪዎች ገንዘብ አቀባባይነት) ከእኛው ባንኮች እየተበደረ በመግዛት ያጠራቸው ብዙ ብጥስጣሽ መሬቶች አሉ። በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በእስራኤልና በሳዑዲ፣ በግብፅና በኢትዮጵያ ፖለቲካ የበሰለ ትንተና የሚሰጥና መልካም እይታ አለው የሚባለው ምሁር ሐጋይ ኤርሊሽ ነው። ይህ የታሪክና የፖለቲካ ሊቅ የተመለከተውና የደመደመው ጉዳይ አለ። Islam, Chrstianity and Politics entwined በሚለው መጽሐፉ አንደኛው ምዕራፍ ላይ ከአንድ ግለሰብ ጋር ይወያያል። ስለ ሸራተን ሆቴል ፋይዳ፣ ግለሰቡ ምንም ላይሰራባቸው አጥሮ ስለያዛቸው ቦታዎች ይጠይቀዋል። ፕሮፌሰር ሐጋይ እንደሚነግረን እነዚህ ሥፍራዎች የተያዙትና የሚጠብቁት ሦስተኛውን ሒጂራ ነው፤ የመጀመርያው ሒጂራ ሰማንያ አራት የነቢዩ መሐመድ ተከታዮች ወደ አክሱም የተሰደዱበት ነው። ሁለተኛው ሒጂራ እንዲሁ የነቢዩ ተከታዮች የሜካ ስደት (ሒጂራ) ነው። ሦስተኛው ሒጂራ ደግሞ የዋሐቢ መሪዎች የሆኑት የሳዑዲ መሳፍንትና መኳንንት አንዳች አደጋ ሲያንዣብብባቸው የሚጠጉበት ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያ ለሦስተኛው ሒጂራ ዝግጁ ነች። ( የነቢዩ ተከታዮች በአሁኑ ዘመን ስደት ይጠብቃቸዋል ማለት ሳይሆን፣ የነገሥታቱና የመሳፍንቱ የግንባር ሰው የሆነውና በሞራል ድቀት፣ በኢትዮጵያ ዘረፋ- የወያኔ መሳፍንት የንቅዘት (የሚታደስ... ወደ ገጽ 13 የዞረ)

Rebeccca’s Bakery & Cafeteria

2111 East Franklin Ave, Suite 2Minneapolis, MN 55404

Tel: 612 455 0236

ለምረቃ፣ ለልደት፣ ለሰርግ፣ ለዓመት በዓል ወይም መታሰቢያ እና ለተለያዩ ዝግጅቶች ወደ ካፍቴሪያችን ጎራ ይበሉ ወይም በስልክ ይዘዙን! በመስተንግዶአችን ይረኩበታል!

የጾም ኬክ በትዕዛዝ እናዘጋጃለን ናፖሊዮን ባቅላባ ካፑቺኖ የይርጋ ጨፌ ቡና ሻይ በያይነቱ ቬጂ ፒዛ ፎካቻ አልመንድ ቢስካቲ የተለያዩ ኩኪስ ቲራሚሶ የኢጣሊያን ዳቦ እና ሌሎችንም እናዘጋጃለን

በተጨማሪ ወብ ሳይታችንን ይጎብኙ

www.rebeccasbakery.com

(Shega Bakery & Grocery አጠገብ)

Page 13: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 13

የሚታደስ... ከገጽ12የዞረመምህር በመሆን ስሙ የሚጠቀሰው ግለሰብ ነው። ይህን

ተልእኮ በተመለከተ የሐጋይ መጽሐፍ ጥሩ ብርሃን ይፈነጥቃል። በቅርብ ጊዜ በሰፊው በተግባር በሚረጋገጠው የወያኔ ፕሮጄክት መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሦስትና አራት ፎቅ ቤት ለመሥራት የማይችሉ ሁሉ ከከተማው እንዲወጡ ይደረጋል። ድህነታቸው እንደ ሙሴ ለምፃሞች ከከተማ ያባርራቸዋል። ከተማይቱ ለአላሙዲ እንግዶች አትበቃምኮ! በቁማችሁ የረገጣችሁት መሬት ሲሸጥ ተመልካች ስትሆኑ፣ ልጆቻችሁ የሚማሩበትና የሚያድጉበት ሥፍራ አጥተው ሲንቀዋለሉ፣ ለእናንተ የሚሆን ከተማ የለንም ተብላችሁ አውጥተው ሲጥሉአችሁ- ሠርታችሁ ለመብላትና ሞትንም በወጉ ለመጠበቅ በማትችሉበት አዙሪት ውስጥ ስትወድቁ..

በወረቀትና በስክሪፕቶ አማካይነት ብዙ ሮሮ አውጥታችሁ በመጻፍ ትንሽ መገላገል ትችሉ ይሆናል። ለሰው ያካፈሉት አሳብ በአየር ላይ እንዳልቀረ በመገመት ግማሽ ጭንቀታችሁን በመገላገል ብቻ ልትደሰቱ ትችሉ ይሆናል። በቁም መሸጠን የመሰለ ውርደት ግን የማይሽር ጠባሳ፣ አንድዶና አክስሎ የሚጨርስ ካንሰር ነው። በእኔማ በኩል ባናነሳው ይሻላል። ምክንያቱም- ጥቂቶች ብዙሃንን አስተኝተው የሚገርፉበት፣ ንዑሳን እልፍ አእላፍ የሆኑ ዜጐችን ለባርነት የሚዳርጉበት፣ አንድ ግለሰብ ሃያና ሠላሳ ሚሊዮን ሕዝብ የሚነዳበት ተአምር አልታይህ ይለኛል። በባሕላችን አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸው እያለቀሱ ወደ ቤት ሲመለሱ ራሳቸው የተደፈሩ እየመሰላቸው የሚወስዱትን ርምጃ ሁሉ አሰላስላለሁ። እናንተም ምን ይሁን? በሚል ጥያቄ እንደምታጣድፉኝ እገምታለሁ። የድሮ መሪያችን “ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር!” በማለት የ

ጀመሩት ዘመቻ ያን ጊዜ አልሠራም። በምንም ስም ይጠራ የኢትዮጵያ ሕዝብ በገዥዎቹ አማካይነት የታወጀበትን ጦርነት መጀመሪያ መገንዘብ አለበት። ሁለተኛ ለጦርነት በጦርነት መዘጋጀት ያስፈልገዋል። ሦስተኛ ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር የሚለው ቋንቋ ነጃሳ ከሆነ ሌላ እናምጣ። በቁምህ ተሸጠሃል። በቁምህ ትነዳለህ፣ በቁምህ ትሰየፋለህና ነፍስህንና የእናት አገርህን ሕይወት ለመታደግ ዮሐንስን ተከተል። የባለሙያው ሙያ ለትግሉ ይዋል። የብዕረኛው ቃላት ይህን አገር መገለባበጥ ካልቻሉ ከነፍሱ የተቆረጡ አይደሉም። ሠዓሊው ይህን ትግል በሸራው ላይ ሲስል ይቺ መሬት ካልተናወጠች ሥዕሉን ይተወው። የኪነቱ ሰው የትግሉን ዐውድ እንደ እሳተ ጐመራ ካላደበላለቀው በአፍንጫዬ ይውጣ! ከማይክራፎን ጀርባ የሚቀመጠው፣ ለማታ ዜና የሚሯሯጠው ጋዜጠኛ የኢትዮጵያን ሰማያትና ምድር ካልገለባበጠ ሙያነቱ ይቅርብን! በአንድ ማብራሪያ እንሰነባበት።

ጄኔራል መርዕድ ንጉሤ የጦር ኀይሎች ኤታማጆር ሹም በነበሩበት ጊዜ በተደጋጋሚ አሥመራ ላይ እንገናኝ ነበር። ከዚህ ቀደም አንሥቼው ከሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ለማያስታውሱት ይጠቅም እንደሆነ ነው የምደግመው። በቃኘው ሰፈር ግቢ ቆመን ስንጨዋወት “ጸጋዬ ለመሆኑ ይኸን ጦርነት ለማሸነፍ ስንት ጊዜ የሚፈጅ ይመስልሃል?” ይሉኛል። የቪየትናምን፣ የደቡብ አፍሪካን፣ የቻይናን..ጦርነቶች በማንሳት መልስ ለመስጠት ተንደረደርሁ። “እሱን ተወው! ይኸ ማርክሳዊ ምናምን አንተንም ያበላሸህ ይመስለኛል። በእኔ እምነት እዚህ የተመደበው እያንዳንዱ ወታደር ለአንድ ቀን - ለሃያ አራት ሰዓት- ቆሞ ቢዋጋ አንድ ጠላት አይኖርም” አሉኝ። በወያኔ ተቃጠልሁ፣ ከሰልሁ- በገንሁ የሚል አሥር ሺህ ሰው ቆሞ ቢዋጋ ኢትዮጵያ የማትድንበት ምክንያት የለም! ዳግመኛ በጦርነት አልምጣባችሁ? ደኅና ሁኑ!

ኪንታሮት... ከገጽ 8 የዞረየሚያካትተው የሆድ ድርቀትን የሚያስወግዱና ሰገራን በማ

ለስለስ ብዙ ማማጥን የሚከላከሉ መፍትሄዎች ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ እንደ አትክልት ያሉ ለስለስ ያሉ ምግቦችን መመገብ፣ ብዙ ውሃ መጠጣት፣ ሰገራን ይዞ አለመቆየት፣ ይህም ካልሆነ በመድሃኒት መልክ የሚዘጋጁ ብዙ ‹‹ፋይበር ያላቸውን›› ውጤቶች /Fiber Supplements/ እና በፊንጢጣ በኩል የሚገቡ ቅባቶችና ክኒኖችን (Suppositories) መጠቀምን ይጨምራል፡፡ ጠያቂያችንም የተሰጡህ ከእነዚህ ውስጥ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህ ቀለል ላሉት ለመጀመሪያና ለሁለተኛው ደረጃ ኪንታሮቶች የሚሰጥ ህክምና ነው፡፡

ጠና ላሉት ለሶስተኛና ለአራተኛ ደረጃ ኪንታሮት ግን ከዚህ በተጨማሪ የቀዶ ህክምና አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም የተለያዩ አይነት ዘዴዎች አሉ፡፡ አንዳንዴም ቁስለቱና ህመሙ ከበረታ ‹‹ፖታሺየም ፐርማንጋኔት›› በተባለው ኬሚካል መዘፍዘፍም ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

ውድ መላኩ አንተም ወደ ተገቢው ሐኪም በመቅረብ ለችግርህ እልባት እንድታበጅለት በማሳሰብ እንሰናበትህ፡፡ በተለይም ከኪንታሮት ባለፈ ሌላ አሳሳቢ ችግር ላለመሆኑ (ለምሳሌ ዕጢ፣ IBD) እርግጠኛ መሆን ይጠበቅብሃል፡፡ በተረፈ መጨረሻ ላይ የጠቃቀስካቸው የህመም ምልክቶች ማለትም እንደ መክሳት፣ መረበሽ፣ ድካምና ሌሎች የደም ማነስ ምልክቶች ለብዙ ጊዜ ደም በማጣትህ ሳቢያ የተከሰቱና ከዋናው በሽታህ ጋር የተያያዙ ነገሮች ናቸው፡፡ ስለሆነም ዋናው ችግርህ መፍትሄ ሲያገኝ እነዚህም መፍትሄ ያገኛሉ ማለት ነው፡፡ ጤና ይስጥልኝ!

ዶ/ር ሲራክ... ከገጽ 1 የዞረበፊት ሽርሽር በመውሰድ በመልካም ምግባራቸው የሚታወ

ቁት ዶ/ር ሲራክ ለ5 ተከታታይ ዓመታት ለተለያዩ ተማሪዎች ሽልማት በመስጠታቸው በስፍራው በነበረው ተመልካች ዘንድ አድናቆትን ተችረዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ ዶ/ር ሲራክ ጋር ደውለን “ይህን የተማሪዎችን ስኮላርሺፕ ስፖንሰር በማድረጌ የሚሰማኝ ደስታ ልዩ ነው።” ሲሉ ገልጸው በመጪው ኦገስት መጨረሻ ላይም የሚኒሶታ ተማሪዎችን ትምህርት ቤት ከመከፈቱ በፊት ሽርሽር ለመውሰድ ዝግጅቱን ስፖንሰር እንደሚያደርጉ በዚህ አጋጣሚ ገልጸዋል።

ኦልትራፎርድ...(ከገጽ 3 የዞረ)ባሉት ዓመታት ከያንግ በተሻለ ቡድናቸውን ቢጠቅሙም የ

ሚገባቸውን አገልግሎት ሰጥተዋል የሚባሉ አይደሉም፡፡ የፖርቹጋላዊው የኦልድ ትራፎርድ ህይወት ብዙ ተስፋ ተደርጎበት ኖሮ አሁን ወደ ተስፋ አስቆራጭነቱ ቀርቧል፡፡ በክረምቱ ናኒ ከተሰናባቾቹ መካከል ቢገኝ የሚያስደንቅ አይሆንም፡፡ እንደ ናኒ ሁሉ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ሊተካ ይችላል ተብሎ መጠነኛ ግምት አግኝቶ በሰር አሌክስ ፈርጉሰን ብዙ ዕድል የተሰጠው ኢኳዶራዊው ከተፈጥሯዊ የክንፍ ሚናው ይልቅ ፉልባክ ሆኖ መጫወት ወይም ይበልጥ አፈግፍጎ የመስመር ተከላካይን የሚያግዝ አይነት ተጨዋች ሆኗል፡፡

አጥቂዎች፡ የተሰናበቱት ሞዬስ የተጫዋች እጥረት ሳይኖርባቸው ብዙ የተቸገሩበት የቡድኑ ክፍል ነው፡፡ ሩኒ እና ቫን ፔርሲ በግላቸው (ኦልትራፎርድ ወደ ገጽ 14 የዞረ)

Page 14: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 14

ተኩስ በ$25 ብቻ

በቅርቡ ከሃገር ቤት መጥታ በሳሎናችን ሥራ የጀመረችው ስታይሊስት በከተማው በአዳዲስ የሹሩባዋ ዲዛይኗ

ብዙ እየተወራላት ነው፤ መጥተው ይጎብኟት

እንደዘበት.... ከገጽ 6 የዞረ

ውለን ትፈልገኛለህ?› ብሎ ነበር የጠየቀውና ወደ ቆመበት የተጠጋው፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሚስትና ህፃን ልጅ ቆመው ይመለከታሉ፡፡ ወደ ጠሪው ሲቃረብ ያ ‹ጥሩልኝ› ያለ ወጣት በጥፊ ተቀበለው፡፡ ራሱን ለመከላከል ሙከራ በሚያደርግበት ወቅት ደግሞ ያላሰበውን ጩቤውን ከጎኑ አውጥቶ አንገቱ ላይ ሽጦበት ሮጦ ሄደ፡፡ ልጁና ሚስት በሁኔው ተደናግጠው ሲጮሁ የተወጋው ሰው ጥቂት ለመንገታገት ሞክሮ ባለመቻሉ በቁሙ ተዘረረ፡፡ ጎረቤቶች ጩኸት ሰምተው ሲወጡ ከተጎጂው አንገት ስር የሚወርደው ደም አካባቢውን አበላሽቶት ነበር፡፡ ወደ ሕክምና ሊወስዱት ሲያነሱት ግን ህይወቱ አልፋለች፡፡

ማንም ባላሰበውና ባልገመተው ሁኔታ ገዳይ ‹ሸፋፋ አለኝ› በሚል ምክንያት ቤቱ ገብቶ ጩቤ ታጥቆ ለግድያ መውጣቱ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ ቀናቸውን በመተራረብና በመሳሳቅ የሚያሳልፉ ሁለት ጓደኛሞች በግድያ የቆየ የወዳጅነት ፋይላቸውን ሲዘጉ መስተዋሉም ለብዙዎች እንቆቅልሽ ነበር፡፡

ተጠርጣሪው ከሸሸበት በህዝቡ ትብብር ተይዞ ሲጠየቅ ‹በፈለገው ነገር ቢቀልድ ምንም አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን በተፈጥሮዬ እንዴት ይቀልዳል?› ነበር ያለው፡፡ ሁሌም የለመዱት መተራረብና መሰዳደብ ላልታሰበ ግምት ሊያደርሳቸው እንደሚችል የጠረጠረ የለም፡፡ ሟችም ሀገር አማን ብሎ የተቀመጠ- እንኳን በጓደኛ በሌላ ሰው እጠቃለሁ ብሎ የማያስብ እንዲሁም እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ለገዳዩ የነበረው ፍቅር ያልቀነሰ ምስኪን ነው፡፡ በአንዲት ቃል ህይወት ጠፋ፡፡ የጓደኛው ሞት ያሳዘነው የሚመስለው ገዳይ ‹‹ሳላስበው ሰይጣን አሳስቶኝ ያደረኩት ነገር ነው›› አለ፡፡ የሁለቱ ፍቅር በመቃብርና በእስር መደምደሙ ግን ግድ ሆነ፡፡ እናትና ልጅም እያዩት አባወራቸውን ቀበሩ፡፡

ሁለት

የ‹ዱብ ዕዳ› ምሽትነሐሴ ወር 1998 ዓ.ምመሽቷል፡፡ አፋር ኬክ ቤት አካባቢ ከፒያሳ ወደ ሰይጣን ቤት

በሚስደው ቁልቁለት መንገድ ላይ የክረምቱ ዝናብ መውጫ መግቢያ አሳጥቶት የዋለው አዲስ አበቤ በየካፌዎቹና በየሬስቶራንቱ ተጠልሎ ጋብ ሲልለት ነው ወደ አስፓልቶቹ ወጣ ያለው፡፡ በአንፃሩ ሌሎች በየቤታቸው ተቀምጠው የነበሩ ወደ ካፍቴሪያዎች ‹ሞቅ ላለ ሻይ› ጎራ ብለዋል፡፡ ጭር ያለው የክረምት ቀን ምሽቱ አካባቢ ደመቅ ያለ ይመስላል፡፡

ስዩም የ27 ዓመት ወጣት ነው፡፡ የዚያን ዕለት ከእናቱ ጋር ነው የዋለው፡፡ ወደ አመሻሹ ላይ ሲወጣ እቁብ ክፈል ተብሎ የተሰጠውን አንድ ሺ ብር ይዞ ነበር፡፡ ብቻውን ወደ አፋር ኬክ ቤት ጎራ ያለው ሻይ ለመጠጣት ብሎ ነበር፡፡

የስዩም ሰፈር እዚያው አካባቢ ነው፡፡ ቴዎድሮስ አደባባይ አስከሬን አበባ የሚሸጥበት በተለምዶ አበባ ሰፈር ተብሎ የሚጠራው አካባቢ በአካባቢው ልጆች ጋር የሚቀራረብ ቢሆንም ብዙዎች ግን የግሩፕ ፀብ የሚወዱ በመሆናቸው ብዙም ሊጠጋቸው አይፈልግም፡፡ የዚህ ወጣት ስራ መማር መስራት ህይወቱን በአግባቡ መምራት ብቻ ነው፡፡

ሻዩን ጠጥቶ ሲወጣ ከ3 የሚበልጡ ወጣቶች ቆመዋል፡፡ አያውቃቸውም፡፡ እነርሱ ግን የሚያውቁት መሰለው፡፡ አስተያየታቸው አላማረውም፡፡ ከምሽቱ 2 ሰዓት ሆኗል፡፡ አንደኛው ‹ና ወደዚህ› አለው፡፡ ስዩም አካባቢውን ቃኘት አደረገ፡፡ ብዙ ሰው የለም፡፡ ፈራ፡፡ የጠሩት በሰላም እንዳልሆነ ገብቶታል፡፡ ነገር ግን አማራጭ አልነበረውምና ተጠጋቸው፡፡ አጠገባቸው ከደረሰበት ደቂቃ ጀምሮ መጨረሻ እስከሆነው ነገር ድረስ ያዩ ሰዎች ነገሩን ለፖሊስ ተርከውታል፡፡

‹‹ተጠጋቸው፡፡ በዚህ መሀል ወዲያው በላይ የተባለው አንደኛው ጠጋ አለና በያዘው ጫፉ ላይ ብረት ያለው ዱላ አናቱን መ

ታው፡፡ ስዩም ወደቀ፡፡ በወደቀበት ቦታ ጥለውት ይሄዳሉ ሲባል ከየት እንደመጡ ያልታወቁ 11 ወጣቶች ድንገት ደረሱና በወደቀበት ቀጠቀጡት፡፡ ጌቱ የተባለ አንድ ወጣት የስዩም መቀጥቀጥ አልበቃ ብሎት ድንጋይ አምጥቶ ጭንቅላቱን መታው፡፡ ስዩም ጣር ላይ ነበር፡፡ ድንገት ብድግ ብሎ ከዚያ ውርጅብኝ ለማምለጥ ሮጠ፡፡ ብዙ ርቀት ግን አልተጓዘም፡፡ ተደናቀፈና ቦይ ውስጥ ወደቀ፡፡ በዚው ቀረ፡፡ ይህን ያዩና ሲሮጥ የተከታተሉት ደብዳቢዎቹ አልተዉትም፡፡ እዚያው የየድርሻቸውን ደብድበውት ጥለውት ሄዱ፡፡ በዚያን ጊዜ የአካባቢው ሰዎች ለማገላገል ያደረጉት ሙከራ የለም፡፡ የቡድን ፀብ በጣም ይፈራ ስለነበር ነገሩን በዝምታ ከመከታተል ውጪ ምርጫ ያለው አልነበረም፡፡ በቅፅበት ውስጥ የተከናወነው ድብደባ ደግሞ ፖሊስ ለመጥራት አመቺ አልነበረም፡፡ ያም ሆነ ይህ ትቦ ውስጥ የወደቀውን ተደብዳቢ ለማንሳት ወደ ስፍራው የሄዱት የአካባቢው ሰዎች ወጣቱ በዘግናኝ ሁኔታ መሞቱን አወቁ፡፡ በጨለማ ድብደባው ወቅት ሌዘር ጃኬቱን፣ ያጠለቀውን የወርቅ ሀብልና ኪሱ ውስጥ የተገኘውን 1 ሺ ብር የወሰዱት ደብዳቢዎች ተሰውረዋል፡፡

ጥቂት ቀናት ከፈጀ ምርመራና ክትትል በኋላ የተያዙት 11 ተጠርጣሪዎች ግድያውን አንዱ በአንዱ ላይ ሲያላክኩ ቆዩ፡፡ በተለይም የገደልኩት እኔ አይደለሁም ለማለት ከፍተኛውን የድብደባ ደረጃ ወደ ሌላ ለማዞር ጥረት ተደርጎም ነበር፡፡

የግድያው መነሻ የተባለው ነገር ነው ለሁሉም አስገራሚ የነበረው፡፡ ሁሉም ተጠርጣሪዎች ስዩምን አያውቁትም፡፡ ከሁሉም ውስጥ አንዱ ‹ና› ብሎ የጠራው ብቻ ስዩም ‹የአበባ ሰፈር› ልጅ እንደሆነ ያውቃል፡፡ ስዩም ተማሪ ይሁን አስተማሪ ሰራተኛ ይሁን ስራ አጥ የሚያውቅ የለም፡፡ ነገር ግን አንድ እውነት አለ፡፡ ስዩም የአበባ ሰፈር ልጅ ነው፡፡ በአበባ ሰፈር ነዋሪዎችና በእነዚህ ወጣቶች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ፀብ አምርቶ አሁን ሁለቱም ሰፈሮች ለጥቃት ተዘጋጅተው የተቀመጡ ናቸው፡፡ ይህን

ደግሞ አንድም ወጣት ቢሆን ‹ሰፈሩን ላለማስደፈር› እንዲነሳ አድርጎታል፡፡ ይህም የቡድን ፀብን አስፋፍቷል፡፡

ስዩም አንዳች በማያውቀውና በማይጠረጥረው መንገድ ህይወቱ ሲጠፋ ለሰሚ ግራ የሚያጋባ ነበር፡፡ የቡድን ፀብ ተሳታፊ ሳይሆን አበባ ሰፈር የሚኖር ሰው በመሆኑ ብቻ የፀበኞች ጥማት ማስታገሻ መሆኑ ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡

ለዚህ እንደዘበት ያለፈ ህይወት ብዙዎች ‹ቀኑ ከዚህ አትለፍ ቢለው ነው› በማለት ሃሳባቸውን ሊሰጡ ቢሞክሩም ይህን መሰል ክስተቶች ማመዛዘንና ማሰብ በተሳናቸው ሰዎች ወደሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶች እንደሚመራ ፖሊስ ተናግሯል፡፡

የቡድን ፀብ የአዲስ አበባ ከተማ ዋነኛ ችግር በነበረበት በዚያን ዓመት በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የሚፈፀሙ ወንጀሎች ተበራክተው- ብዙዎችም ከህይወት ህልፈት እስከ ንብረት ውድመት ደርሶባቸው መኖራቸው ፖሊስ ችግሩን ለመከላከል ጠንካራ አሰሳ እንዲያደርግ አድርጎታል፡፡ የዚያም ውጤት ነው እነዚን ከ11 ያላነሱ የቡድን ፀብ ተዋንያን ለዚህ አንድ ነፍስ መጥፋት ዋና እና ተባባሪ ወንጀለኛ አድርጎ እንዲከስሳቸውና ወደ ዘብጥያ እንዲያወርዳቸው ምክንያት የሆነው፡፡

ኦልትራፎርድ...(ከገጽ 13 የዞረ)

ድንቅ አጥቂዎች ቢሆኑም እርስ በርስ ሲጣመሩ ግን ውጤታማነት ሳይጎላቸው ለቡድኑ የመጨረሻ አቅማቸውን እንዳይጠቀሙ የሚያግዳቸው እንከን አላጡም፡፡ የሁለቱ በጋራ መጫወት በከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ የተገዛውን ማታ ወደ ክንፍ ይገፋል፡፡ ብሎም ቡድኑ ከስፔናዊው ሊያገኝ የሚችለውን ጥቅም እያጣ ነው፡፡ ምናልባት ዩናይትድ እጅግ ፈታኙን እና ከባዱን ውሳኔ የሚያስተላልፍ ከሆነ እርምጃው (ኦልትራፎርድ... ወደ ገጽ 8 የዞረ)

Page 15: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

ጥያቄ፡- እኔ የማውቀው ሪቼ መወለድህን ነው፤ አንተ ግን ሰዎች ሲጠይቁህ የጨርቆስ ልጅ ነኝ ነው የምትለው፡፡ በትክክል የተወለድከው የት ነው?

መኮንን፡- የሪቼ አጥቢያው ጨርቆስ አይደል...? ሰፈሩ ጨርቆስ ነው፤ ልዩ ስሙ ሪቼ ቢባልም ያው ጨርቆስ ነው፡፡ እኔ በጨርቆስ ሲጠራ ነው ደስ የሚለኝ፡፡

ጥያቄ፡- ሰፈሬ፣ የተወለድኩበት ጨርቆስ ነው ብለህ የምትናገርበትና ይህን በመናገርህ የምትደሰትበት የተለየ ምክንያት አለህ?

መኮንን፡- የወለድኩበት፣ ክርስትና የተነሳሁበት፣ አሁንም የምኖርበት ነው፡፡ አካባቢውን ውስጣ ውስጡን ሁሉ የቤቴን ያህል አውቀዋለሁ፡፡ ጨርቆስ ውስጥ ብዙ አብሮ አደግ ወንድሞችና እህቶች አሉኝ፡፡ ስለዚህ እኔ የጨርቆስ ልጅ ነኝ፡፡ እዚያ ያለው ህይወቱ፣ አኗኗራችን፣ ጨዋታው፣ ደስታው በሙሉ ከውስጤ ጋር ተዋህዷል፡፡ ይህ ደግሞ ሁሌም የጨርቆስ ልጅ መሆኔን በኩራት እንድናገር ያደርገኛል፡፡

ጥያቄ፡- ጨርቆስን በሚመለከት ብዙ ቀልዶች ይነገራሉ፤ አንዳንዶችም ጨርቆስ አካባቢ ከሌላው የከተማችን አካባቢ የተለየ አድርገው ሲያወሱት እንሰማለን፣ አንተንስ እንዲህ አይነት ነገሮች ገጥመውህ አያውቁም?

መኮንን፡- ጨርቆስን በሚመለከት ብዙ ነገሮች ሲባሉ እሰማለሁ፡፡ እንዳልከው ቀልዶችም ይቀለዳሉ፡፡ ነገር ግን የህይወት ትክክለኛው ገፅታ ያለው እኛ ጋር ነው፡፡ በነገራችን ላይ ጨርቆስ ከድህነት ጋር ተያይዞ ሲወሳ ልንሰማ እንችላለን፡፡ እውነታው ግን ሌላ ነው፡፡ በከተማችን ከጨርቆስ በበለጠ ድህነት የተንሰራፋባቸው አካባቢዎች ብዙ ናቸው፡፡ ...በጨርቆስ ዙሪያ የሚነገሩ ቀልዶች እዚያው ጨርቆስ ውስጥ የሚፈጠሩ ናቸው፡፡ በኋላ ነው እየሰፋ የሚሄደው፡፡ ጨርቆስ ብዙ ቀልደኞችን፣ ብዙ ፀሐፊዎችን ያፈራ የህይወትን አስኳል በኑሮህ የምትረዳበት ምርጥ አካባቢ ነው፡፡

ጥያቄ፡- ጨርቆስ ተወልደው ለትልልቅ ቁም ነገሮች የበቁና መልካም ስም ያገኙ ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን፡፡ አንተ እነማንን መጥቀስ ትችላለህ?

መኮንን፡- እነ ተመስገን መላኩ፣ ድርብወርቅ ሰይፉ፣ ዘነበ ወላ፣ ኢሳያስ ግዛው (ኢሳግ ስቱዲዮ)... ብዙ ናቸው፡፡ በተለያየ ሙያ ውስጥ የተሰማሩ ከአውሮፕላን አብራሪነት ጀምሮ የጨርቆስ ልጆች ያልገቡበት የሙያ መስክ የለም፡፡ ዶክተሩ፣ መምህሩ፣ መካኒኩ፣ ኢንጂነሩ... በጥቅሉ የጨርቆስ ልጅ የሌለው ‹‹የለም›› የሚለው ቃል ውስጥ ብቻ ነው፡፡

ጥያቄ፡- እንግዲህ የተወለድከው አዲስ አበባ ያውም ጨርቆስ ነው፡፡ ነገር ግን አሁንም ድረስ የንግግር ዘዬህ ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ይወሰዳል፤ ይህ ከምን የመጣ ነው?

መኮንን፡- እኛ ሰዎች ብዙ ጊዜ በምንወዳቸው ነገሮች ተፅዕኖ ስር መውደቃችን የተለመደ ነው፡፡ እኔ እጅግ አድርጌ ባላገር እወዳለሁ፡፡ እኛም ቤት ሆነ ጎረቤት ሰዎች ለጥየቃ ከባላገር ከመጡ አብሬያቸው ማውራት ደስ ይለኛል፡፡ ከሽማግሌዎችም ጋር መወያየት ደስታን ይሰጠኛል፡፡ ሄድ መጣ ከሚልባቸው ሰዎችም ጋር መጫወት ደስ ይለኛል፡፡ በዚህ ጊዜ ለአነጋገራቸው ልዩ ትኩረቱ እሰጣለሁ፡፡ የባላገሩ እና የሽማግሌዎቹ አነጋገር በእነዚያ ጊዜያት ውስጤ ገብቶ የቀረ ይመስለኛል፡፡ አሁንም ድረስ ባላገርና ሽማግሌ ሳገኝ ከእነርሱ ጋር ማውራት ያስደስተኛል፡፡ በተለይም እኛ በተለምዶ ‹‹ቢጩ›› ከምንላቸው ጋር መጫወት ደስ ይለኛል፡፡

ጥያቄ፡- በብዙ የኮሜዲ እና ሌሎች ገፀ ባህሪያቶችህ ሽማግሌ መስለህ ነው የምትሰራው፣ እኔ እንደውም ከሽማግሌ ውጪ የሰራኸውን ገፀባህርይ አላስታውስም፡፡ ይህ ነገር አስበኸው የሆነ ነው ወይስ በአጋጣሚ?

መኮንን፡- ቀደም ሲል እንደገለፅኩት ከሽማግሌዎችና ከባላገር ሰዎች ጋር የማደርጋቸው ውይይቶች በእኔ አነጋገር ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ በመደበኛው ህይወት ይንፀባረቃል፡፡ ከጓደኞቼ ጋር በምጫወትበት ወቅት አነጋገሩ ሳላስበው ይወጣል፣ ልማድ ሆኖብኛል፡፡ ምናልባት ይሄ ነገር በድራማ፣ ቴአትር እና ፊልም አዘጋጆች ዘንድ መኮንን የሽማግሌን ገፀ ባህሪ ጥሩ አድርጎ ይ

ጫወትልኛል የሚል እሳቤ እንዲኖር አድርጎ ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ ግን ሌሎችን ገፀ ባህሪያትም ጥሩ አድርጌ እጫወታለሁ የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡

ጥያቄ፡- እንደ ወጣት ወይም እንደ ጎልማሳ ደረቱን ነፋ ያደረገ ቆፍጣና ሰው ገፀ ባህሪን ተጫውተህ ታውቃለህ?

መኮንን፡- ከሽምግልና ውጪ እንደ ወጣት ሆኜ የሰራሁት ነበር፣ ነገር ግን ብዙም አልታይም፡፡ ከቴዲ ስቱዲዮ ጋር ነበር የሰራሁት፡፡ እሱ ቢታይ ኖሮ መኮንን ሁሉንም ሆኖ መስራት እንደሚችል ይታወቅልኝ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን የሚያሰራኝ ካገኘሁ እሰራለሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ በሽማግሌ ገፀ ባህሪ ብቻ ተወስኜ እንድቀር ያደረገኝ የዳይሬክተሮች ምደባ ነው፡፡ እነርሱ ይህን ገፀ ባህሪ እርሱ አሳምሮ ይጫወተዋል ብለው ካመኑ መስራት ነው ያለብኝ፡፡ ለዚህ ነው ሌላውን መስራት የማልችል እስኪመስል ድረስ በሽማግሌው ወጣ ያለ ገፀ ባህሪ እንድሞክር ዕድል የሰጠኝ የለም፡፡ ሌላውንም ገፀ ባህሪ መስራት እንደምችል ገብቷቸው ዕድል የሰጡኝ ሳምሶን ወርቁ እና ዳንኤል ኃ/ማርያም ብቻ ናቸው፡፡

ጥያቄ፡- በቲቪም፣ በመድረክም፣ በፊልምም ጋቢ እና ካፖርት ለብሰህ የምትታይ ከመሆኑ አንፃር ሰዎች በመንገድ ሲያገኙህ ምን ይሉሃል?

መኮንን፡- ብዙ ሰዎች ጋቢ ለብሼ ወይም ካፖርት ደርቤ የሚያገኙኝ ስለሚመስላቸው ሸንቀጥ ብዬ ሲያገኙኝ ይደነግጣሉ፡፡ ለካ ሽማግሌ አይደለህም ብለው የሚገረሙ አሉ፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ‹‹እርስዎ›› እያሉ የሚያወሩኝ ሞልተዋል፡፡ በዕድሜ ከእኔ በላይ የሆኑት እንደውም ወልደው ሊያደርሱኝ የሚችሉት ሳይቀሩ ‹‹እርስዎ›› እያሉ ያወሩኛል፡፡

ጥያቄ፡- የእውነት ግን... አንተ እንዲህ ሲሆን ምን ይሰማሃል?

መኮንን፡- ስለ እውነት ለመናገር ደስታ ነው የሚሰማኝ፡፡ ምን ያክል ውስጣቸው እንደገባሁ የማረጋገጥበት አጋጣሚ ስለሆነ ሁሌም ደስተኛ ነው የምሆነው፡፡

ጥያቄ፡- ለአንድ አርቲስት የችሎታው መለኪያ ሆኖ የሚቀርበው የተለያዩ ገፀ ባህሪያትን ወክሎ መጫወት መቻሉ ነው፡፡ ከ

ዚህ አንፃር ከሽማግሌው ወጣ ብሎ ሌሎችንም የመሞካከር ዕቅዶች የሉህም?

መኮንን፡- በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህ አሁን በህዝቡ ዘንድ የምታውቅበት የሽማግሌ ምስል ይቀየራል ብዬ አስባለሁ፡፡ ብዙ ሰዎች በተመሳሳይ የሽማግሌ ገፀ ባህሪ ደጋግመው ስላዩኝ እንደ አርቲስት ሳይሆን የሆነ ቦታ እንደሚያውቋቸው ሽማግሌ ነው የሚያስቡኝ፡፡ ለዚህም ነው ሽማግሌዎቹ ሳይቀሩ ‹‹አንቱ›› እያሉ የሚያወሩኝ፡፡ ስለዚህ ይህን ነገር ለመቀየር አንዳንድ ስራዎች እየሰራሁ ነው፡፡ በቅርቡ ለእይታ የሚበቁ ቀየር ያሉ ገፀ ባህሪያትን እየሰራሁ ነው፡፡

ጥያቄ፡- ከዚያ በኋላ የሽማግሌው ይቀራል ማለት ነው?መኮንን፡- አይቀርም፣ እንደውም በሌላ መልኩ ተጠናክሮ ነ

ው የሚቀጥለው፡፡ በተለይ ከስር ያሉ ህፃናትን በጥሩ ስነ ምግባር የመቅረፅ ሚና ያላቸው ሽማግሌ ሆነው ይመጣሉ፡፡ በዚህ ላይ የራሴን ፕሮጀክት ቀርጬ እየተንቀሳቀስኩ ነው፡፡ ልጆች ሀገራቸውንና ባህላቸውን እዲወዱ፣ ራሳቸውን ከመኪና አደጋ እንዲጠብቁ፣ ጥሩ ስነ ምግባር እንዲኖራቸውና በትምህርታቸው እንዲተጉ የሚያበረቱ ገፀ ባህሪ ሆነው ይመጣሉ፡፡

ጥያቄ፡- የኪነ ጥበብ ህይወትህ መነሻው ከየት ነው?መኮንን፡- እኔ ሁሉ በፈጣሪ ሆነ ነው የምለው፡፡ ባይሆንማ የ

እኔ ሀሳብ ሌላ ነበር፡፡ ትንሽ በቀለሙም፣ ትንሽ በኳሱም ገፋ ብዬ ነበር፡፡ ህይወትን የማሸንፈው፣ እንጀራ የምቆርሰው ከሁለቱ በአ

ንዱ ይመስለኝ ነበር፡፡ ግን የፈጣሪ ፈቃድ ሆነና ወደዚህ መጣሁ፡፡ በትምህርቴ ትንሽ ደህና ነበርኩ፣ ኮሌጅም ገብቼ ኤሌክትሪሲቲ ተምሬያለሁ፡፡ በእግርኳሱም እስከ ምድር ጦር ቢ ቡድን ድረስ ደርሼ ነበር፣ አባቴ ነው ያስተወኝ፡፡ መብራት ኃይል ገብቼ ኤሌክትሪክ ስሰራ ቆየሁና ምኑንም ሳላውቀው በቀጥታ ወደ ኪነ ጥበቡ ዘው ብዬ ገባሁ፡፡ ኤሌክትሪሲቲ ተምሬ ተዋናይ ሆኛለሁ፡፡ ለነገሩ በተፈጥሮዬ አንድ ነገር ላይ ብቻ መቆየት ደስ አይለኝም፡፡ ኤሌክትሪኩ ሰልቸት ብሎኝ ስለነበር ኪነ ጥበብ ጥሩ የለውጥ ቤት ሆኖኛል፡፡ እዚያውም ማርኮ አስቀርቶኛል፡፡ አሁን ሲሸንጠኝ የቤቴን የመብራት ገመድ በጥሼ ከመቀጠል ውጪ ኤሌክትሪኩን እርግፍ አድርጌ ትቼዋለሁ፡፡ ኳሱም ተረት ተረት ሆኗል፡፡

ጥያቄ፡- የኪነት ህይወትህ መነሻ ጊዜ መቼ ነው?መኮንን፡- ጊዜው 1989 ነው፡፡ የሰፈሬ ልጅ አብሮ አደጌ ተ

መስገን መላኩ ከእኔ ቀድሞ ጀምሮ ስለነበር በየተገናኘንበት አጋጣሚ ሁሉ ‹‹አንተ እኮ አርቲስት ብትሆን ያዋጣሀል›› እያለ ይወተውተኝ ነበር፡፡ እኔ ደግሞ ተውኔት የመፃፍ ዝንባሌው ነበረኝ፣ እተውናለሁ ብዬ ግን አስቤ አላውቅም፡፡ በወቅቱ የቴአትር አፃፃፍ ዘዴን ማወቅ እፈልግ ስለነበር መምህራን ማህበር አዳራሽ የፀጋዬ ገ/መድህን ‹‹ሀሁ በስድስት ወር›› ሲሰራ እዚያ ወሰደኝ፡፡ እዚያው ኤሌክትሪክ መስራት ስለምችል አንዳንድ የመድረክ መብራቶችን መስራት ጀመርኩ፡፡ አርቲስት ሳምሶን ወርቁ እዚያ ሲያገኘኝ ‹‹አንተ መስራት ትችላለህ›› አለና በማዘጋጃ ቤት በሚታየው ‹‹የሲኦል ነፍሳት›› ቴአትር እንድሳተፍ አደረገኝ፡፡ በዚሁ ተጀመረ ማለት ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው በእግዚአብሔር ነው፡፡

ጥያቄ፡- ትራጄዲ ገፀ ባህሪያት ይመቹሃል?መኮንን፡- ደስ ይለኛል፡፡ ሰውን ከማሳቅና ከማስለቀስ የቱ ይ

ሻላል ብለህ እንዳትጠይቀኝ እንጂ ትራጄዲም ሌላውም ለእኔ አንድ ነው፡፡

ጥያቄ፡- አትጠይቀኝ ብትለኝም እጠይቅሃለሁ... ከኮሜዲ እና ከትራጄዲ የቱን ነው ይበልጥ የምትወደው?

መኮንን፡- እንደ ሰው ከጠየቅከኝ ምናልባት ኮሜዲው ሊበልጥብኝ ይችላል፡፡ እንደ አርቲስት ከጠየቅከኝ ግን ሁለቱም ለእኔ ልዩነት የላቸውም፡፡ ስሰራ ሁለቱንም በፍቅር ነው የምሰራው፡፡ እንደውም ትራጄዲ የበለጠ ጥንቃቄ እና ተመስጥኦን ስለሚፈልግና ትንሽ ከበድ ስለሚል ደስ ይለኛል፡፡ ሰዎች ከባድ ነገርን መወጣት ይበልጥ ደስታን ይሰጠን የለ? በነገራችን ላይ በጣም ብዙ ሰዎች ያለቀሱበት ‹‹አያትየው›› የሚል ፊልም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት በየመንገዱ በስክሪን ይታይ የነበረ ነው፡፡ እዚያ ላይ እኔ የምጫወታቸው ሽማግሌ ገፀ ባህሪ ብዙ ሰዎችን ያስለቅሱ ነበር፡፡ እናቴ ራሷ እስክትረሳኝና በኋላም ‹‹አፈር አባቱ ይብላ ይሄ ሟርተኛ›› እስክትል ድረስ የተጫወትኩት ነው፡፡ በአብላጫው የተጫወትኩት ኮሜዲን ስለሆነ ሰዎች በኮሜዲያንነት ነው የሚያውቁኝ፡፡

ጥያቄ፡- ኮሜዲያን ነኝ ብለህ ታስባለህ?መኮንን፡- በጭራሽ አላስብም፡፡ ጥያቄ፡- ለምን?መኮንን፡- ኮሜዲ ገፀ ባህሪያትን እጫወታለሁ እንጂ ኮሜዲ

ያን ነኝ ብዬ አላስብም፡፡ጥያቄ፡- የኮሜዲያን ማህበር አባል አይደለህም?መኮንን፡- ነኝ፡፡ጥያቄ፡- ታዲያ ኮሜዲያን የተሰባሰቡበት ማህበር ውስጥ ም

ን ዶለህ?መኮንን፡- ኧረ ነገር አብርድ... ኮሜዲያን ነህ ብለው ጠሩኝ፣

ይሳቃል ኢንተርቴይመንት የተባለ ድርጅት የኮሜዲ ትርዒት ለማሳየት ጋብዞን ሂልተንና ሸራተን ሰርተናል፡፡ የድርጅቱ ባለቤት ‹‹በማህበር ብትደራጁ መልካም ነው›› የሚል ሀሳብ ሲያመጣ ጓደኞቼ የማህበሩ መስራች ስብሰባ ላይ ጠሩኝ፡፡ ማህበር ለማንኛውም ነገር ጥሩ ነው፡፡ ከዕቁቡም ከዕድርም ጀምሮ ያለው የጋራ ነገር ጥሩ ስለሆነ ኮሜዲያን ነኝ ብዬ ባላስብም አባል መሆኔ ክፋት የለውም በሚል ነው አባል የሆንኩት፡፡

ጥያቄ፡- ብዙ ጓደኞችህ ‹‹መኮንን ላዕከ›› በሚለው ስም አይጠሩህም፡፡ ብዙዎቹ ‹‹አባዬ›› (መኮንን... ወደ ገጽ 19 የዞረ)

ኪነጥበብ ጤና ሕይወት ስፖርት

“በጨርቆስ ዙሪያ የሚነገሩ ቀልዶች እዚያው ጨርቆስ የሚፈጠሩ ናቸው”አርቲስት መኮንን ላዕከ

ክፍት የሥራ ቦታHelp Wanted

P-T Office Clerk: Vadnais Heights law firm is looking for a part- time office clerk with good organizational skills who is preferably

fluent in both English and Amharic. Job Duties: This position will include general office duties includ-ing open and closing files, light phone communications with Am-haric speaking clients, calendaring, filing, ensuring files are well

organized and the ability to assist with overflow work when needed. Salary Information: $10.00 per hour, 20 hours per week.

Please email your resume to [email protected].

Page 16: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 16

የካንሰር ሕሙማን ማድረግ ያለባቸው 8 ጥንቃቄ 8 Caregiving Ideas to Help Cancer Patients

ለራስ ምታት ፍቱን የሆኑ የመጠጥና የምግብ ዓይነቶችከኢሳያስ ከበደ

የውጪ ሀገራትን ያህል ባይሆንም በርካቶች ለትንሹም ለትልቁም ህመም ክኒን ወደ አፋቸው ወርወር ማድረግን ከለ

መዱ ቆይተዋል፡፡ መድሃኒቶች በአግባቡ ሲወሰዱ የመርዳት አቅማቸው ከፍተኛ የመሆኑን ያህል ከበሽታ አምጪዎች ጋር ሲላመዱ ደግሞ ጣጣቸው ብዙ ነው፡፡ የጎንዮሽ ጉዳቶችንም ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ለህመሞቻችን ሁሉ ሁልጊዜ ክኒኖችን እንድንወስድም አይመከርም፡፡ ቀለል ያሉትን በአካባቢያዊ፣ አመጋገብ እና አጠቃላይ ጤናማ አኗኗር ብቻ ማስታገስ እና ማዳን እንደምንችል ባለሞያዎቹ ይጠቁማሉ፡፡ ለዛሬ ትኩረት ያደረግነው አንዴ ወይም ሌላ ጊዜ አብዛኞቻችን ገጥሞን በሚያውቀው ራስ ምታት ላይ ነው፡፡ መደበኛው ቀላል ራስ ምታት ወይም ጠንካራው ማይግሬይን ሊሆን ይችላል፡፡ ለዚህ ቀላል መፍትሄ አድርገው ሰዎች የሚወስዱት የራስ ምታት ክኒን ውጠው እንዲሻላቸው መጠበቅ ነው፡፡ ነገር ግን ከክኒኖች በተሻለ ያለጎንዮሽ ጉዳት በምግብና መጠጦች ራስምታቱን በፍጥነት ማስታገስና ማስቀረት እንደሚቻል በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ባለሞያዎች እየገለፁ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ለመደበኛው ራስምታትና ማይግሬይን ፍቱን የተባሉት ምግቦችና መጠጦች የትኞቹ ይሆኑ?

ራስ ምታት የሚደጋግማት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዋ ማህሌት ግርማ ራስ ምታት ሲጀምራት ሰው ማት ራሱ ያስጠላታል፡፡ የለመደችውን ክኒን ካልዋጠች ፍፁም እረፍት አታገኝም፡፡ ክኒኑ ግን ሁልጊዜ በቅርብ ላይገኝ፣ የተፈገለውን ፈጣን ፈውስም ላይሰጣት ይችላል፡፡ ‹‹አንዳንዴ እናቴ ቡና ታፈላልኝና አንድ ስኒ ስወስድበት

ቀለል ይላል፡፡ ምናልባትም ከክኒኑ ቡናው ፍቱን ሳይሆን አይቀርም›› ትላለች ማህሌት፡፡ የማህሌትን ሀሳብ አሁን አሁን የሚደረጉ ጥናቶችም ሳይንሳዊ ድጋፍ እየሰጡት ይገኛሉ፡፡ ቡና ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ተፈጥሯዊ ምግብና መጠጦች ከራስ ምታት ክኒኖች በተሻለ ለቀላሉ ራስ ምታትም ሆነ ከበድ ላለው ማይግሬይን ጥሩ የጎንዮሽ ጉዳት የሌላቸው መፍትሄዎች መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ምስጋና የመጣላቸው ቡና እና የተለያዩ ፍራፍሬዎች በውስጣቸው የያዟቸው ንጥረ ነገሮች ለዚህ አብቅተዋቸዋል፡፡

ቡናቡና በሳይንሱ ከፍተኛ ጥናትና ምርምር ከሚካሄድባቸው አነ

ቃቂ መጠጦች አንዱ ነው፡፡ ለአንዳንዶች ቡና ፍቱን የራስ ምታት መድሃኒት ሲሆን ማይግሬይን ላለባቸው አንዳንድ ሰዎች ላይ በብዛት ሲወሰድ ማይግሬይኑን የሚቀሰቅስበት አጋጣሚ አለ፡፡ ሳይንሱ ሁሉንም የቡና ምስጢር ፈትቶ ባይጨርስም እስካሁን ባሉት ትናቶች መሰረት ግን ቡናን ፍቱን የራስ ምታት መድሃኒት አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡ መጠኑን በልክ ማድረግ አብሮ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ለከባዱ የራስ ምታት ማይግሬይን የሚታዘ

ዙ ክኒኖች ውስጥ የቡና ዋና ንጥረ ነገር ካፌይን ይገኛል፡፡ ስለሆነም ቡና ለራስ ምታት በመፍትሄነት መቅረቡ አስደናቂ ነገር አይሆንም፡፡ ይሁንና መጠኑ በበዛ ቁጥር ራስ ምታትን ከማስታገስ ይልቅ ጭራሽ ሊቀሰቅሰው ይችላል፡፡ ማህሌት ‹‹ብዙ ጊዜ ይህን ሞክሬ ተሳክቶልኛል፡፡ ቡና መድሃኒቴ ነው›› ትላለች፡፡ ሳይንሱም ለዚህ ድጋፉን እየሰጠ ይገኛል፡፡ እጅግም ወፍራም ያልሆነ አንድ

ወይም ሁለት ስኒ ቡና ከሁለት ክኒን የተሻለ ተፈጥሯዊ መድሃኒት ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ሃብሃብሃብሃብ ወይም በእንግሊዝኛው ወተርሜለን በውስጡ እጅግ

ብዙ ፈሳሽ እና ማዕድናትን የያዘ ከፍራፍሬዎችም በትልቅነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በተለይ ከአዲስ አበባ ወደ ናዝሬትና ሐዋሳ መስመር ሲሄዱ በመንገድ ዳር ተሸክመው ሲሸጡት እንመለከታለን፡፡ ሞክረውት እንደሆነ ባላውቅም በጉዞው ወቅት ለሚኖረው ሙቀት እና የውሃ ጥም ሁነኛ መፍትሄ ሆኖ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጥቅሙም ባሻገር ለራስ ምታት ፍቱን መድሃኒት መሆኑ በባለሙያዎች ተጠንቶ ተቀምጧል፡፡ የሪደርስ ዳይጀስት መጽሔት በቅርቡ ባሰፈረው ጽሑፍ ሃብሃብ ለራስምታት ፍቱን ያስባለው ከፍተኛ የውሃ እና ማዕድናት በተለይም ከፍተኛ የማግኒዚየም ማዕድን መጠኑ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ለራስምታት ከሚያጋልጡ ምክንያቶች አንዱ ድርቀት ወይም በሰውነት ውስጥ በቂ ፈሳሽ ያለመኖሩ ነው፡፡ ይህ ፍራፍሬ ደግሞ ይህን ችግር በደንብ ይፈታል፡፡ ከራስ ምታት ክኒን ይልቅ በቅርብ ሃብሃብ ከተገኘ በደቂቃዎች ውስጥ ከራስምታቱ እረፍትን ይሰጣል ብለው ባለሞያዎቹ ይናገራሉ፡፡

ዝንጅብልዝንጅብል ላይ የሚደረጉ ምርምሮች ገና በቅርቡ የተጀመሩ

ቢሆንም በውስጡ የደም ቧንቧዎችን መቆጣት እና ህመም የሚቀንሱ መድሃኒቶች ውስጥ ካሉ ኬሚካሎች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ተመራማሪዎች ማግኘት ችለዋል፡፡ በተለይ በከባድ

የራስ ምታት ወቅት የደም ቧንቧዎችን መቆጣት በማስከተል ራስምታቱ እንዲቀሰቀስ የማድረግ ተግባር ያላቸውን ፕሮስታግላንዲን የሚሰኙ ንጥረ ቅመሞች መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ራስ መታቱን እንደሚያስታግስ የሪደርስ ዳይጀስት መጽሔት ይገልጣል፡፡ ራስ ምታቱን ሙሉ በሙሉ ባያቆመው እንኳ ከራስ ምታት ጋር የሚመጡ ደስ የማይሉ እንደ ማቅለሽለሽ አይነት ስሜቶችን በቶሎ ይቀንሳል፡፡ ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ኢትዮጵያውያን ያለጥናቶቹ ውጤትም ቀድመው ለሆድ ህመም እና ማቅለሽለሽ ዝንጅብል አኝክበት ሲሉ የኖሩት!

ስፒናችትኩስ ስፒናች ጎመን ቅጠል በውስጡ የያዛ

ቸው ቅመሞች ራስ ምታትን በማስታገስ ብቻ ሳይሆን የደም ግፊት መጠንን በመቀነስም በቀደመው ጊዜ ጥቅም እንደነበራቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ አትክልትና ፍራፍሬ በርካሽ ለሚገኝባቸው እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት ይህ ጥሩ ዜና ይመስላል፡፡ በውጪው ዓለም ስፒናችን አብስሎ ወይም በትኩሱ ከቲማቲም ጋር ከትፎ በመብላት ብቻ ሳይሆን ጨምቆ ከመጠጣትም ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ደግሞ ይህ ፍቱን አትክልት ለራስ ምታትም ፈጣን መፍትሄ ይሰጣል ብለዋል፡፡ ቢፈልጉ ጨምቀው ከሻይ ጋ

ር አለዚም ባዶውን ወይም ትኩሱን ቅጠል ሰላጣ እንደሚያዘጋጁት አዘጋጅተው ቢመገቡት ከራስ መታቱ ፋታ እንዲያገኙ እንደሚረዳዎት የተደረጉ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናቶች አመልክተዋል፡፡

ነገር ግን...ለራስ ምታት ፍቱን ተብለው በጥናት ስር ያሉ በርካታ ተፈጥ

ሯዊ ምግቦችና ፈሳሾች (ለራስ ምታት... ወደ ገጽ 22 የዞረ)

በቋንቋ የተነሳ መንጃ ፈቃድማውጣት ተቸግረዋል?

Global Translation & Interpreterበቋንቋ የተነሳ የኮምፒውተር ፈተናውን ማለፍ ተስኖዎታል?

በዚህ የተነሳ መኪና መንዳት አልቻሉም? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር አለ፤

አስተምረን ወስደን እናስፈትንዎታለን።

Tajajila AfaanOromoos Nikennina !

ልብ ይበሉ የእርስዎን ቋንቋ እንናገራለን2400 Minnehaha Avenue Suite - 204

Minneapolis, MN 55404

(612) 275-0970በተጨማሪም የትርጉም ድርጅታችን የፍርድ ቤት ጉዳይ ሲኖርብዎ ወይም በማንኛውም ሰዓት

የትርጉም ሥራ ሲያስፈልግዎ ክፍት ነው።

ከቅድስት አባተብዙዎች በካንሰር ህመም እንደተጠቁ ሲነገራቸው ከመጠን

ያለፈ ፍርሃት ይሰማቸዋል፡፡ በአካላቸው ላይ ትንሽ ለውጥ ሲያዩ ከካንሰሩ ምክንያት የተፈጠረባቸው ይመስላቸዋል፡፡ እንዲህ ያለው ስሜት በመጀመሪያ በሁሉም የካንሰር ህሙማን ላይ የሚፈጠር የተለመደ ክስተት ነው፡፡

በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻችን ጉዳት የሚያስከትሉ የካንሰር አይነቶች አሉ፡፡ በየጊዜው ካንሰር ለመከላከልና ለመለየት የሚረዱ አዳዲስ ስልቶች ይፈለሰፋሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ካንሰርን ለመከላከል የሚያስችሉ ህክምናዎች በመስፋፋታቸው በካንሰር ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ጤንነታቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅ ትልቅ ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በበሽታው ተጠቅቶ እንዴት መኖር እንደሚቻል መጣራት ተጀምሯል፡፡

በካንሰር በሽታ የተጠቁ ሰዎች ጤናማ ሆነው ለመቆየት የሚያስችሏቸውን የተለያዩ ስልቶችን መጠቀም እና ስጋታቸውንና ፍርሃታቸውን ማስወገድ አለባቸው፡፡ ለካንሰር ህሙማን ጠቃሚ ከሆኑ ስልቶች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

1 ስለ በሽታዎ በሚገባ ይወቁ፡- በሽታውን ለማወቅ ስለ በሽታዎ ምንነት የሚገልፁ ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ይሞክሩ፡፡ ዶክተሮች ጋር ቀጠሮ ሲኖሮት ጓደኞችዎን ወይም ከቤተሰቦ አንድ ሰው አብሮዎት እንዲሄዱ ያድር

ጉ፡፡ ወደ ህክምና ማዕከል ከመሄድዎ በፊት ስለ በሽታዎ የሚያሳስቦትንና የሚያስጨንቆትን ጥያቄ ፅፈው ያዘጋጁ፡፡ ይህ ሀሳቦን ለመሰብሰብ፣ ስለ በሽታዎ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት፣ ስለ ህመም ሁኔታ በሚገባ ለመረዳትና በሽታዎን ለማከም ከሚችሉባቸው የተለያዩ ስልቶች ውስጥ አንዱን ለመወሰን እንዲችሉ ይረዳዎታል፡፡ የካንሰር ህሙማን በብዛት ከሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

- የያዘኝ የካንሰር በሽታ ይድናል?- ለመታከም የምችልባቸው አማራጮች ምን ምን ናቸው?- ህመሜን ለማስታገስ በምወስደው መድሃኒት ምን ሊገጥ

መኝ ይችላል? የህመም ስሜት ወይም በአካሌ ላይ አዲስ ለውጥ ይፈጠራል?

- ዶክተሬን ማናገር ያለብኝ ምን አይነት ነገር ሲገጥመኝ ነው?

- የካንሰር ህመሜን ከታከምኩ በኋላ በድጋሚ የመመለስ ዕድሉ ምን ያህል ነው? እንዳይመለስ ምን ማድረግ አለብኝ?

- እኔ በተጠቃሁበት የካንሰር በሽታ ሌሎች ቤተሰቦቼ የመጠቃት ዕድላቸው ምን ያህል ነው?

ብዙ ጊዜ ለእነኚህ ጥያቄዎች የሚያገኙት ምላሽ ባለሙያዎች

የሰጡትን የራሳቸውን ግምት ወይም ስታስቲክስን ተመርኩዘው የቀረቡ መላምቶችን ስለሆነ የተለያዩ ዶክተሮች የተለያዩ መልሶችን ሊሰጥዎት ይችላሉ፡፡

2. ህመሙን ለማስታገስ የሚችሉበትን ስልት ይንደፉ፡- ሁሉም ሰው በተፈጥሮው እንደሚለያይ ሁሉ ህመሙን ለመከላከል የሚጠቀምበት መንገድ አንድ አይነት ሊሆን አይችልም፡፡

የሚከተሉት ሀሳቦች ካንሰር የያዛቸው ሰዎች በሽታቸውን ለማስታገስ እንዲችሉ ያግባቸዋል፡፡

- ራስዎን ዘና ማድረግን ይማሩ- በሽታዎ የፈጠረቦትን ስሜት ለጓደኛዎ፣ ለቤተሰቦና ለህክም

ና ባለሙያዎች ያካፍሉ- ስለ በሽታዎ ያሎትን ዕውቀት ለማስፋት ስለ እርስዎ ህመም

በተለያዩ መንገዶች በጋዜጣ፣ በሬዲዮ፣ በመፅሔትና በሌሎች ሚዲያዎች የሚቀርቡ መረጃዎችን በአግባቡ ይከታተሉ፡፡

- ህመሞን ለመታከም መምረጥ ያለቦትን መንገድ ለመወሰን ሲቸገሩ እያንዳንዱ ውሳኔዎ የሚያስከትልቦትን መንስኤና ውጤት ይለዩ፡፡ አመለካከትዎን የሚያጠናክርሎትን መረጃ ይፈልጉ፡፡

- ብቻዎን ሆነው የሚያስቡበትን ሰዓት ያመቻቹ- ስራዎትንም ሆነ ከዚህ ቀደም ያከናወኗቸው የነበሩ ሌሎች

ተግባሮችን አያቁሙ

3. ከሰዎች ጋር በግልጽ ይወያዩ፡- ስለ በሽታዎ ከቤተሰቦ፣ ከጓደኛዎ እና ከዶክተርዎ ጋር በግልፅ ይነጋገሩ፡፡ በዙሪያዎት ያሉ ሰዎች ስለ ካንሰር መጥፎ መረጃዎች

ን ከእርሶ በመደበቅ ሊንከባከቦት ሲሞክሩ የተገለሉ ሊመስሎት ይችላል፡፡ የሚሰማዎትን ስሜት በግልፅ ከተናገሩ ግን ሌሎችም ለእ

ርሶ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን በግልፅ ስለሚነግሮት መንፈሰ ጠንካራ ይሆናሉ፡፡

4. ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ይከተሉ፡- ጤናማ የሆነ የአኗኗር ዘይቤ በቂ ጉልበት እንዲኖርዎትና የሰውነትዎ ሴሎች ጤናማ ዕድገት እንዲኖራቸው ያግዞታል፡፡ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን በቂ ዕረፍት በማድረግ፣ ተመጣጣኝ ምግቦችን በመመገብ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመስራትና ዘና የሚያደርጉ ነገሮችን ማከናወን ያካትታል፡፡

5. አንዳንድ ነገሮችን ቤተሰቦና ጓደኛዎ እንዲያግዞ ፍቃደኛ ይሁኑ፡፡ ሲታመሙ የሌሎችን እርዳታ ለመቀበል ፍቃደኛ ይሁኑ፡፡ የሌሎችን እገዛ በበጎ ፍቃደኝነት ሲ

ቀበሉ እገዛ የሚያደርጉሎት ሰዎች ጠቃሚ እንደሆኑ እንዲሰማቸውና እርስዎን ለማገዝ ፅኑ ፍላጎት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡

6. የህይወት ግቦንና ጥቅም የሚሰጦትን ነገር ይለዩ፡- የካንሰር በሽታ ጭንቀትና ፍርሃት እንዲፈጠርቦ ያደርጋል፡፡ ይህን ስሜቶን ለሌሎች በማገራት ግን የተፈጠ

ረቦትን ውጥረት ለመቀነስ ይችላሉ፡፡ በህይወትዎ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለይተው በማውጣት አላሰፈላጊ ተግባራትን ትተው አስፈላጊዎቹን ብቻ ያከናውኑ፡፡

7. ቀና አመለካከቶችን ያጎልብቱ፡- እያንዳንዱ ቀን በደስታ ለማሳለፍ ይሞክሩ፡፡ ዛሬ መጥፎ ነገር ቢገጥሞት ወይም ቢያሞት ነገም ህመሜ ይነሳብኛል ብለው

አይስጉ፡፡

8. የሰዎችን የተሳሳተ አመለካከት ለመዋጋት ይዘጋጁ፡- ብዙ ሰዎች ስለ ካንሰር ያላቸው ዕውቀትና አመለካከት የተሳሳተ ነው፡፡ ጓደኞችዎ የካንሰር ህመሞ የሚ

ተላለፍባቸው ሊመስላቸው ይችላል፡፡ የስራ ባልደረባዎ ጤነኛ እንዳልሆኑና ስራዎን በብቃት መስራት የማይችሉ አድርገው ሊገምቶት ይችላሉ፡፡ እንዲህ አይነት አመለካከት ያላቸውን ሰዎች አመለካከታቸውን ሊያሻሽሉ የሚችሉት እርሶ ኖት፡፡ ለእነኚህ ሰዎች የካንሰር ህሙማን ከሌሎች ሰዎች እኩል ስራቸውን በብቃት ለመስራት እንደሚችሉ ጥናቶች ማረጋገጣቸውን ይንገሯቸው፡፡ እርስዎም ስራዎን በርትተው በአግባቡ በመስራት በተግባር ያስተምሯቸው፡፡ ለጓደኞችዎም ካንሰር አደገኛ በሽታ ቢሆን እንኳን እርስዎን እንጂ እነሱን እንደማያሰጋቸው ይንገሯቸው፡፡

ብዙ ሰዎች ለካንሰር ተስማሚና የማይስማሙ ምግቦች እንዳሉ ሲናገሩ ይደመጣል፡፡ እስካሁን ድረስ ግን የካንሰር ታማሚዎች መብላት የሌለባቸው ወይም አብዝተው ሊመገቧቸው የሚገቡ ተስማሚ የሆኑ የተለያዩ ምግቦች ስለመኖራቸው በጥናት የታወቀ ነገር የለም፡፡ ሆኖም ግን (ካንሰር...ወደ ገጽ 19 የዞረ)

Page 17: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 17

የጤና ሞግዚት አዘጋጅ፦ ዶ/ር ዓብይ ዓይናለም

ስለዓይናችን ጤና እንጨዋወትEye Health OverviewRegular eye exams reveal vision problems like nearsightedness, farsightedness, presbyopia, and astigmatism. Your doctor may prescribe glasses or contact lenses. Eye conditions include pinkeye, blepharitis, glaucoma, cataracts, and

macular degeneration.

ማሳሰቢያበዘ-ሐበሻ የጤና አምዶች ላይ የሚወጡ ጽሁፎች በሙሉ ለማስተማሪያነት እና ግንዛቤ ለመስጠት እንጂ እንድትታከሙበት አይደለም። ሁልጊዜም ቢሆን አንድ ህመም ሲሰማ ወደ ዶ/ር ጋር በመሄድ

በዶ/ር ትዕዛዝ እንድትታከሙ አደራ እንላለን።

የግጥም ጉባዔ

አይኔ አያትና…አይኔ ጉድ አደረገኝ፤

አይኗ ጎላ ጎላ... የሚሉ ብዙ ዘፈኖች ከተዘፈነለትና ከተሞገሰው አይናችን የበለጠ

የተሞገሰ የሰውነታችን አካል ያለም አይመስለኝም፡፡መቼም ዓይናችን የዓለምን ገፅታ በማየት ደስታና እርካታ በውስ

ጣችን እንዲፈጠር የሚረዳን የሰውነታችን ክፍል ነው፡፡ ሰው ሰራሽ ካሜራ ምስሎችን ለመቅረፅ ካለው ችሎታ በብዙ ሚሊዮን እጥፍ ይበልጥ አይናችን ምስሎችን የመቅረፅ ብቃት አለው፡፡ አይናችንና አዕምሯችን ባላቸው አስደናቂ ግንኙነት በዓለም ላይ ለሚታዩ ብዙ ነገሮች ትርጉም መስጠት እንችላለን፡፡ የአንድን ነገር ርቀት ለመመዘን፣ ቁሶችን በቀላሉ ለማወዳደር፣ ፅሑፎችንና ምስሎችን ለመተርጎም በማስቻል ረገድ ሌላም የአይናችን ሚና ቀላል አይደለም፡፡ እኛም፣ ብዙ ሰዎች ስለ አይናችን በተደጋጋሚ የሚያነሷቸውን ጥያቄዎችና ለግንዛቤ ይረዳሉ ብለን ያመንባቸውን ሃሳቦች ከዚህ በታች አቅርበናል፡፡

ሰዎች የተለያየ የዓይን ቀለም ለምን ኖራቸው?

ሁለት ቡናማ ዓይን ያላቸው ወላጆች ብዙ ጊዜ የሚወልዱት ልጅ ቡናማ የሆነ የዓይን ቀለም ይኖረዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ሁለት ሰማያዊ የዓይን ቀለም ያላቸው ወላጆች የሚወልዱት ልጅ ሁሌም ለማለት ይቻላል፣ የዓይኑ ቀለም ሰማያዊ ነው፡፡ ነገር ግን የአንዳቸው የዓይን ቀለም ቡናማ ሆኖ የሌላኛው ሰማያዊ ቢሆን፣ የልጃቸው ዓይን በብዛት ቡናማ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ቡናማ የዓይን ቀለም በዘር የመተላለፍ ብቃቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ለዚህም ነው በዓለም ላይ ቡናማ ዓይን ያላቸው ሰዎች ቁጥራቸው ሰማያዊ ዓይን ካላቸው በጣም በዝተው የተገኙት፡፡

ለዓይናችን ቀለም የሚሰጠው አይሪስ የተባለው የዓይናችን ቀለማማ ክፍል ነው፡፡ የዓይናችንን የቀለም አይነት የሚለየውና የአይሪስ ቀለም የሚሰጠው ደግሞ ለመላው የአካላችን ቀለም በመስጠት የሚታወቀው ሜላኒን የተባለው ኬሚካል ነው፡፡ ከፍተኛ የሜላኒን መጠን ቡናማና ጠቆር ያለ የዓይን ቀለም እንዲኖረን ሲያደርግ፣ ዝቅተኛ የሜላኒን መጠን ደግሞ ሰማያዊ ወይም ፈዛዛ አረንጓዴማ የዓይን ቀለም እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ቀላ ያለ(ፒንክ) የዓይን ቀለም ያላቸው ሰዎች ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የሜላሊን እጥረት ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡

ከሁለቱ ዓይኖችዎ ይበልጥ የቱን ይጠቀማሉ?

ከቀኝና ከግራ እጃችን አንዱን ይበልጥ እንደምንጠቀም ሁሉ፣ አይናችንንም እንዲሁ ከቀኙና ከግራው አንዱን አብልጠን እንጠቀማለን፡፡ ከግራና ከቀኝ ዓይን የበለጠ የሚጠቀሙት በካሜራ በኩል ለማየት ወይም በመርፌ ውስጥ ክር ለመክተት የሚጠቀሙበትን ዓይንዎን ነው፡፡

የትኛውን ይበልጥ እንደሚጠቀሙበት ለማወቅ ከፈለጉ፣ ይህንን ሙከራ ይሞክሩ፡፡ የአንደኛውን እጅዎትን አውራ ጣትና ሌባ ጣት አገናኝተው ክብ ይስሩ፣ በክቡ በኩል በቤት ውስጥ አነስተኛ መጠን ያለውን ነገር፣ ለምሳሌ የበሩን እጀታ ይመልከቱ፡፡ በመጀመሪያ አንዱን ዓይን ጨፍነው በሌላኛው በክቡ በኩል ይመልከቱ፡፡ ቀጥለው ደግሞ ሌላኛውን ጨፍነው በክቡ በኩል ያለውን የበሩን እጀታ ይመልከቱ፡፡ ይበልጥ የሚጠቀሙት የበሩን እጀታ በደንብ ማነጣጠርና ማየት በቻለ ዓይንዎት ነው፡፡

ብዙ ማንበብ የማየት ችሎታን ይቀንሳል?እስካሁን ድረስ ብዙ ማንበብ በዓይን ላይ የሚያስከትለው ጉዳ

ት መኖሩ አይታወቅም፡፡ ነገር ግን ለረጅም ሰዓት ቴሌቪዝን መመልከት ወይም በቂ ብርሃን በሌለበት ቦታ መስራት ዓይናችንን እንዲደክም ያደርገዋል፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ብዙ ስራ ስንሰራ ሰውነታችን እንደሚደክም ሁሉ ለረጅም ሰዓት አንድ ነገር ላይ ስናተኩር የዓይናችን ጡንቻዎች ስለሚደክሙ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ዓይናችንን የመድከም ስሜት ከተሰማን በድካም ምክንያት ሳይሆን መነፅር የሚያሳዝዝ የዓይናችን የውስጥ ክፍል ችግር ሊሆን ይችላል፡፡ የዓይናችን መድከም የዓይን በከፍተኛ ሁኔታ የመጎዳት ምልክት ሊሆን ስለሚችል ወደ ህክምና ማዕከል ጎራ ብሎ ሁኔታውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

ጥሩ ብርሃን ያለበት ቦታ ዓይን እንዳይደክም ይረዳል፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ለማንበብ ወይም ለመስራት የሚቀመጥበት ቦታ ብርሃንን ከጎኑ በአንድ በኩል ብቻ በሚያገኝበት ቦታ ማድረግ ይገባል፡፡ በሚሰራው ወይም በሚያነበው ነገር ላይ ጥላ መፍጠር የለበትም፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ እናቶች ልጆቻቸው ልከኛ የሚባል ብርሃን በማይገኝበት ቦታ ሲያነቡ እንደሚጨነቁት፣ ብርሃን በጣም በቂ ከሚባለው ባነሰ ቦታ ላይ መስራት ያን ያህል በዓይን ላይ አደገኛ ጉዳት አያስከትልም፡፡

ዓይን ለምን ደም ይለብሳል?አቧራ፣ ጭስ እና ሌሎች ጥቃቅን ነገሮች በ

ዓይናችን ውስጥ ሲገቡ ዓይናችንን ደም እንዲለብስ ወይም እንዲቀላ ያደርጉታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ከፍተኛ ቅዝቃዜ፣ ትኩሳት፣ ከተለያዩ የውስጥ ህመሞች የተነሳ ድካምና ከመጠን በላይ የአልኮል መጠጥ መጠጣት አይናችንን እንዲቀላ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡

ብዙ ጊዜ የዓይን መቅላት የተወሰነ የህመም ስሜት ቢፈጥርብንም አስጊ የሆነ ጉዳት ግን አያስከትልብንም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ዓይናችን የሚቀላበት ምክንያቱ በጀርም ወይም በሌሎች ተህዋሲያን ተጠቅቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ኮንጃክቲቪቲስ የተባለው የዓይንን ቆብ የሴል ሽፋንን የሚያጠቃ በሽታ ዓይናችንን ያቀላዋል፡፡ ስለዚህ ዓይናችን በተደጋጋሚ የሚቀላ ከሆነ የኮንጃክቲቪቲስ በሽታ ምልክት ሊሆን ስለሚችል የዓይን ህክምና ወደምናገኝበት ማዕከል ጎራ በማለት ምርመራ ማድረግ ይገባናል፡፡

ሜካፕ መጠቀም ዓይንን ይጎዳል?

በኮስሞቲክስ ውስጥ የሚገኙት ቅመሞች ለአንዳንድ ሰዎች አለርጂክ ይሆንባቸዋል፡፡ በእርግጥ በቆዳቸው ላይ አለርጂክ ለሚፈጠርባቸው ሰዎች ታስበው የተዘጋጁ የተለዩ ኮስሞቲክሶች አሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ኮስሞቲክስ አለርጂክ የሚሆንባቸውና ፈፅሞ ለሜካፕ የማይመቹ አንዳንድ ሰዎች አሉ፡፡

ብዙዎቹ የዓይን ኮስሞቲክሶች በቀላሉ እንዳይበላሹ የሚያግዝ ንጥረ ነገር ተጨምሮባቸው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ሆኖም ከጊዜ በኋላ ኮሞ

ቲክሶቹ በቆዳችን ላይ ከሚገኙት ባክቴሪያዎች ጋር ንክኪ ፈጥረው በመዋቢያ መሳሪያው ላይ ሊያርፉ ይችላሉ፡፡ የመዋቢያ መሳሪያው በሌላ ቀን በሜካፑ ብልቃጥ ላይ ሲያርፍ ባክቴሪያዎቹ በብልቃጡ ውስጥ ገብተው ቀስ በቀስ መባዛት ይጀምራሉ፡፡ ስለዚህ የዓይን ሜካፕ የሚጠቀሙ ሰዎች የሚጠቀሙትን ሜካፕም ቶሎ ቶሎ በመቀየር ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

የዓይንን ሜካፕ ሆነ መዋቢያ መሳሪያውን ፈፅሞ ለሌላ ሰው ማዋስ አይገባም፡፡ በኮስሞቲክስ መሸጫ ሱቆች ውስጥ የሜካፖችን አይነት ለማሳየት ለናሙናነት የተቀመጡ ኮስሞቲክሶችን ከመሞከርም መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡

አንድን ሜካፕ ሲጠቀሙ ዓይንዎት ላይ የማበጥ ወይም የማሳከክ ስሜት ከተፈጠረብዎት ወዲውኑ ሜካፑን መጠቀም ያቁሙ፡፡ ማቆም ብቻ ሳይሆን ሲጠቀሙበት የነበረውን ሜካፕና መቀቢያ መሳሪያውን የቆሻሻ ገንዳ ውስጥ መጣል ይገባዎታል፡፡ ፎጣና መታጠቢያ ጨርቆች በባክቴሪያ ሊበከሉ ስለሚችሉ የቤተሰብዎ አባላት በእጃቸው እንዳይነኩት ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ በአጠቃላይ የሜ

ካፕ አጠቃቀምን ከዓይንዎን ጤንነትና ከውበት ምርጫዎ በማነፃፀር ሊጠቀሙ ይገባል፡፡

ዓይንን ሆን ብሎ ማጠናገር ጉዳት ያስከትላል?ብዙ ወላጆች ልጆቻቸው አይናቸውን ሲያጠናግሩ በዚያው ተጠ

ናግተው ይቀራሉ ብለው ይሰጋሉ፡፡ ነገር ግን የአንድ ሰው የዓይኑ ጡንቻዎች ዓይኑን በሚገባ ግጥም አድርገው ለመያዝ ብቁ የሚሆኑበት በሶስት ዓመቱ ነው፡፡ ስለዚህ ልጆች ለጨዋታ ወይም የወላጆቻቸውን አትኩሮ ለማግኘት ብለው የፈለጉትን ያህል በተደጋጋሚ ዓይናቸውን ቢያጠናግሩም ዓይናቸው ተጠናግሮ አይቀርም፡፡

ዓይንዎ የፍቅር መግቢያ ሲሆን‹‹ፍቅር እንደ እንባ ነው፤ ከዓይን ይመነጭና ልብ ላይ ያርፋል›› ነ

በር ያለው ሶቢያን ሶሪስ የተባለ አንድ ምሁር፡፡ እውነትም የፍቅር መቀመጫው ልብ ላይ ነው ቢባልም መግቢያው ዓይን ነው፡፡

ለነገሩ ብዙ ነገሮቻችን በመግቢና በመውጪያ አካላቶቻችን ይገለፁ እንጂ የነገሮቻችን ሁሉ መገለጫ ምንጭ አንጎላችን ነው፡፡ ከዚህም በመነሳት በፍቅር ለመማረክ አንድ ሰው የማረከውን ወይም የማረካ

ትን ወደ ራሳቸው ለማምጣት የሚያነሳሳቸው ነገር መጀመሪያ የሚያዩት በዓይናቸው እስከሆነ ድረስ ለመመሰጣቸው መነሻ የሆናቸው ዓይናቸው ይሆናል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ለየትኛውም እይታችን መልስ የሚሰጠንና ለእይታችን (ለመማረካችንም ሆነ ለመመሰጣችን) ምላሽ የሚሰጠን አንጎላችን ነው ማለት ነው፡፡ ያው ዓይናችን ግን ትልቁን ሚና የሚጫወትልን ይሆናል ማለት ነው፡፡ መቼም ‹‹ዓይኔ አያትና አይኔ ወደዳት... ለምን አይን አየ ተብሎ ዓይን አይከሰስም›› እንዳለው ዘፋኙ ዓይናችንን ከማየት መከልከል አንችልምና እናያለን፤ እንመሰጣለን፤ እንማረካለን፤ ከተሳካ እንፈቃቀራለን፡፡ ታዲያ አይናችንን የፍቅር መግቢያ ብንለው ትክክል አያሰኘንም ትላላችሁ፡፡

የዓይን ሽፋንና የዓይን ውበትበተለያየ ወቅት ሰዎች ከሰውነታቸው ክፍል እንደሌሎቹ አካላቸ

ው ዓይንንም ለይተው በማውጣት የዓይንን ውበት ሲያደንቁ ይሰማሉ፡፡ ብዙ ጊዜ ዓይን ጎላ ጎላ ሲል የተለየ የዓይን ውበት እንዳላቸው አድርገው ይቆጠራል፡፡ ዓይን ሰፋ ያለውን አካባቢ እንደመያዙ ጎላ ጎ

ላ ብሎ ሲታይ ለፊትም ሆነ ፊት ላይ ላሉ ሌሎች የፊት አካላትም ውበትን ያላብሳል፡፡

ሌላው በዓይን ሽፋን በተለይም የታችኛው ቆዳ ላይ ሜላኒን ከሚባለው ኬሚካል በቦታው በዝቶ ከመገኘት የተነሳ ጠርዙ ተለይቶ ጥቁር የሚሆንባቸው ሰዎች አሉ፡፡ ይህ መጥቆር የህመም ምልክትም ሊሆን ስለሚችል መለየት ይገባል፡፡ ጤናማ በሆነ መልኩ ከተገኘ ግን ለዓይን የበለጠ ውበትን የማጎናፀፍ ኃይል ይኖራቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ብዙ ጊዜ በተለይ ሴቶች የታችኛውን የዓይናቸውን የሽፋን ቆዳ በኩል ወይም በሻዶ ሲያጠቁሩ የምናየው፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ ታዲያ ዓይንም መጥፎ ጥላቻን ለመግለፅ እንጠቀምበታለን፡፡

ለምሳሌ ዓይንህን ላፈር...፣ አይኔ እንዳያይህ/እንዳያይሽ እያልን እንገልፃለን፡፡ ይህ ታዲያ የዓይንን ብዙ ቋንቋ የሚናገር አይመስላችሁም? መቼም ውበትም ቋንቋም እንደተመልካቹና እንደተናጋሪው ሰው ነው ቢባልም የዓይን ውበትና መገለጫ ቋንቋዎቹ ግን የጋራ የሆነና አብዛኛውን ሰው የሚያስማሙ ናቸው፡፡

zehabesha.com

በሞቴ ተፈወሽ...!!!ህያውነትሽን ቢያውጅሞትሽን ቢሽረው ሞቴልቤ ስላንቺ ቢመታአጥንትሽ ቢሆን አጥንቴ።ፍንትው ብትል ትንታግሽየኔ ማንነት ጨርቁሶበመውደቄ ክብርሽን ባተርፍመኖሬ ከልን ተላብሶ።

ብዬ እንጂ…….አለመኖሩን ማን ሽቶሞቴን እናፍቃለሁ

ልሙትልሽ ተማፅኖዬ እምባዎቼን እዘራለሁ?!

ዳሩ…..ባልፈፀምሽው ክፉ ወንጀልባላዘመርሽው አዝመራባልቆለልሽው የተንኮል ካብባልወጣሽበት ተራራ።ከሳሽና ዳኛ ሆነውራሳቸው ለራሳቸውፈረዱበሽ እንድትወርጂእንድታርፊ ከጫማቸው።አያውቁም አልል ያውቃሉማንነትሽን አይስቱትምያውቃሉም አልል አያውቁምለክብርሽ ክብር አልቸሩም።

እኔማ…….የቀኝ ኪሴን ስሰፋእያፈሰሰ የግራዬ

የሸሚዜን ቁልፍ ስጠቅምእየወለቀ ጫማዬ።

የውስጥ እንከኔ ሰንጥሮሲቸግረኝ መቃናቱ

አላራምድ ሲሞግተኝአይሎ ጉልድፍነቱ።

አንድ’ታሽ እንዲመሰከርእኔ ስላንች ስዳክር።

ሳያንሰኝ ያይኖቼ ጉድፍሊደቀንብኝ ጋሬጣ

እውነትን እያየ እማያይነጭ ሊደፍርሽ መጣ።ማንነትሽ ተድበስብሶአንችነትሽ ተዘንግቶ

እኔ እያለሁ ሊደፍር አንችንነጭ በትሩን አንስቶ።

እኮ እንዴት…..በምን ቀመር በምን ስሌት????አውቃለሁና አፈርሽ አያበቅልም አሜከላያጎረሰውን የሚነክስበሁለት ስለት የሚበላ።በልጆችሽ ፍቅር ወኔበአንበሶቹ ኮርቼብሽበአምላክሽ ኃይል ጉልበትተማምኜ በጠባቂሽ።ሴባስቶፖልን አንግቤሰላምሽን ልሰብክ ወጥቼከምን ላይ ናቸው ባዋየውአንዱን አጋሬን ጠርቼ።‘እዚህ ደርሰዋል ከቅርቡተጠግተዋል ከሰርጡፈረንጅ አስቧል አሉብሎ ሊያዝዎት እጅ ይስጡ።’በማለት ወዳጄ አረዳኝለካስ የኔም ሰው አያውቀኝ።

እኮ እኔ….የታጠቅ ጌታ ካሳ

ለጠላት እጄን የምሰጥላንዲት ህይወቴ ‘ምሳሳ።እግዜር ክንዱን ባያነሳ

ሰዓቱ አልነጋምና ሴባስቶፖል ግዳይ ባይጥል

የድል ግዜው ሆኖ ገና።ለሃገሬ ክብር ግርማ ለመመለኳ ቋንቋ

አሥሬስ ሞቼ ብነሳበሰላም ለመጠበቋ?!

እናም….እስኪ ሂድና ቃኛቸው ከወዴት እንደደረሱወዳጄም ሸኘሁትናቢረበሽብኝ መንፈሱ።ቃሌን ብትሰማ ቢገባትየእልህ ሲቃዬ ትርጉምጮክ ብዬ ተናገርኳት ከመቅደላ አፋፍ በመቆም።እናቴ ብዬ ክብሬየምንነቴ ፍቺአንቺ በኔ እንድትኮሪእንድከበር እኔ ባንቺ።ነበርሽና ላደርግሽ አንድብጀምረው ብይዝ መንገድሰሜን ገብቼ ስሰምንእየተናደ ደቡቡስመለስ ምስራቅን ክቤ እየፈረሰ ምዕራቡ።ከጫፍ ሳይደርስ ውጥን ህልሜዛሬ ሳይቋጭ ያ ክውኔ።ፈረንጅ ከቦኛል በዙሪያከጆቼ ሊያስር ካቴና።

እናም……ህያውነትሽን ቢያውጅሞትሽን ቢሽረው ሞቴልቤ ስላንቺ ቢመታ

አጥንትሽ ቢሆን አጥንቴ።ራሴን ልሰጥሽ ዛሬይኸው ተዘጋጀሁኝእኔ ልሙትና እናቴ

አንች ተከብረሽ ኑሪልኝ።በሚፈሰው ትኩሰ ደሜበኔ መሰዋት ህልፈት

ብዙ ቴዎድሮሶች አፍሪየሚቆሙ ላንቺ አንድነትቃል ግቢልኝ እናት ሃገር

በመጨረሻው ሰዓትያንድንትሽ ወሬ ዜናበአለሙ ሁሉ ይናኝ

ተከብረሽ ታፍረሽ ኑሪየምሸከመው አፈር ይቅለለኝ።

ይኸው ሰጠሁሽ ሳልሰስትያለችኝን አንዲት ህይወትመለየትሽ ገሀድ ይውጣተከበሪ በኔ ህልፈት።

ተጻፈ፡ በቅዱስ ዳዊትጥቅምት 14/98

Page 18: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 18

Page 19: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 19

ከገጽ 1 የቀጠለበአላሙዲ ስፖንሰር የሚደረጉትና ኢትዮጵያውያንን ለመከ

ፋፈል በኢትዮጵያ ስም ለመነገድ ወደሚኒሶታ መጥተዋል የተባሉት እነዚሁ ወገኖች በሚኒሶታም ከፍተኛ ኪሳራ እንደሚደርስባቸው ከወዲሁ ዝግጅቱን ለመቃወም እየተሰበሰበ ያለው ግብረኃይል ገልጿል።

“በዋሽንግተን ዲሲ ያልተሳካው ኳስ በሚኒሶታ ይሳካል ብለው ማሰባቸው ሞኝነት ነው” የሚሉት እነዚሁ አላሙዲንን ኳስ ለመቃወም የተዘጋጁ ወገኖች ሚኒሶታ በደም ገንዘብ አትገዛም ሲሉ ተናግረዋል።

በተለይም ከድምጻችን ይሰማ ሚኒሶታ፣ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር፣ ከተለያዩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የተውጣጣ አንድ ቡድን “በምንኖርበት ከተማ በወያኔ ተላላኪዎች አንደፈርም” በሚል የተለያዩ የተቃውሞ ዝግጅቶን ለማቅረብ ከወዲሁ ሥራ የጀመረ ሲሆን “የኢትዮጵያውያን ኳስ የሚደረገው በሚኒሶታ ነው” በሚለው የማሳሳቻ ወሬ ሕዝቡ እንዳይደናገር ትክክለኛው ኳስ የሚደረገው በሳንሆዜ ካሊፎርኒያ መሆኑን የሚገልጹ ፍላየሮች እና ፖስተሮች በከተማው እንደሚበተኑ ይኸው ግብረሃይል ለዘ-ሐበሻ አስታውቋል።

የአላሙዲ ኳስ በዋንሽንግተን ዲሲ ቦይኮት እንደተደረገው በሚኒሶታም እንዲሁ “የደም ገንዘብ አንፈልግም” በሚል ቦይኮት እንዲደረግ፤ ወደሳንሆዜ በመሄድም የዕረፍት ጊዜውን ከወገኖቹ ጋር እንዲያሳልፍ ይኸው ግብረሃይል ጠይቋል።

የአላሙዲ ኳስ በሚኒሶታ እንደሚደረግ ሲገለጽ ዘ-ሐበሻ በድረገጿ የሚከተለውን ዜና ትንታኔ አስተናግዳ ነበር።

በአላሙዲ የሚደገፈው ፌዴሬሽን ዲሲን ጥሎ በሚኒሶታ የዘንድሮውን ዝግጅት ሊያደርግ ነው

“ዲሲን ለቀው መሄዳቸው ለእኛ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ድል ነው”

- በዲሲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

(በዲሲ አላሙዲንን ለመቃወም በከተማው ሲዘዋወር የነበረው መኪና ይህን ይመስል ነበር)

(ዜና ትንታኔ) ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የተሰባሰቡበትን ፌዴሬሽን ለሁለት ለመክፈል ተንቀሳቅሷል የሚባለው የወያኔ/ኢሕአዴግ ሥርዓት በአላሙዲ ስፖንሰርነት የሰሜን አሜሪካውን አመታዊ የስፖርት ፌስቲቫል ለመክፈል ቢጥርም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ነባሩን ፌዴሬሽን በማመከተል አሸናፊ መሆናቸው ባ

ለፉት ሁለት ዓመታት በዳላስ እና በዋሽንግተን ዲሲ ታይቷል።

በሼህ መሃመድ አላሙዲ የሚደገፈውና የወያኔ ፌዴሬሽን እየተባለ የሚጠቀሰው aesaone ራሱን ተለጣፊ አድርጎ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ዓመታዊ ዝግጅታቸውን በሚያደርጉበት ሳምንት ላለፉት 2 ዓመታት ሲያደርግ ባዶ ስታዲየም ከመታቀፍ ውጭ የሕዝብን ቀልብ ሊያገኝ እንዳልቻለ በግልጽ የታየ ጉዳይ ነው። እንደ ዋሽንግተን ፖስት ያሉ ሚዲያዎች ሳይቀሩ 2 ሚሊዮን ዶላር የወጣበት ዝግጅት የተገኘው ሰው ቁጥር ያስገርማል እስከማለት ዘግበው ነበ

ር። ኢትዮጵያውያኑ ይህንን የአላሙዲ እግር ኳስ ቦይኮት በማድረጋቸው በስታዲየሙ ከሚገኘው ሰው ይልቅ ከውጭ ሆኖ የሚቃወመው ሰው ይበልጥ እንደነበር በተደጋጋሚ በሚዲያዎች መዘገቡም አይዘነጋም።

በሼህ አላሙዲ የሚደገፈው ፌዴሬሽን ለ3 ተከታታይ ዓመታት በዋሽንግተን ዲሲ የኳስ ውድድሩን እንደሚያደርግ ቀድሞ የ

ገለጸ ቢሆንም፤ በተለይ አምና በዲሲ በተደረገው ዝግጅት ኢትዮጵያዊያኑ የአላሙዲ አፍ በደም ተጨማልቆ የሚያሳይ ፎቶ በትልቅ መኪና ተሰቅሎ በከተማዋ ሲንቀሳቀስ፤ አላሙዲ ባረፉበት ሆቴል አጠገብ ቆሞ ሲውል፤ ሆቴላቸው ውስጥ ሳይቀር ሕዝቡ አላሙዲንን እየተቃወመ የኳስ ውድድራቸውን “በደማችን ጨዋታ ይብቃ” በሚል ስያሜ በመስጠት ከተቃወማቸው በኋላ አላሙዲ ያልጠበቁት ጉዳይ ስለሆነ ወዲያውኑ ውድድሩን አቋርጠው ወደ መጡበት አፍረው እንደተመለሱ በወቅቱ በተለያዩ ሚዲያዎች ተዘግቧል።

አሜሪካ ያለን ኢትዮጵያውያን በገንዘብ አንገዛም፤ እኛ የደም ገንዘብ አንበላም፤ ከደም ገንዘብ ጋርም አንተባበርም በሚል ይህን የስፖርት ፌስቲቫል ቦይኮት ካደረጉ በኋላ የአላሙዲው ፌዴሬሽን ኳሱን ለ3 ዓመት ከከፈለበት የዋሽንግተን ዲሲው RFK ስታዲየም በመቀየር ወደ ሚኒሶታ እንደተዟዟረ የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች አስታውቀዋል።

ከውስጥ አዋቂዎች መረጃ እንደተረዳነው አላሙዲ እንዲህ ያለ ተቃውሞ ይደርስብኛል ብለው ሳያስቡ በዋሽንግተን ዲሲ አፍረው ተመልሰዋል፤ ይህን ተከትሎም ዋናውን የኢትዮጵያውያን ፌዴሬሽኑ ገንጥለው የወጡትን አመራሮች ይኸው የአላሙዲ ፌዴሬሽን ያባረረ ሲሆን በዲሲ ላለፉት 2 ዓመት የታየውን ባዶ ስታዲየምና ተቃውሞ በሚኒሶታ አያጋጥመንም በሚል ኳሱ ዘንድሮ በሚኒሶታ ይደረጋል። በዚህም መሠረት ከጁን 29 እስከ ጁላይ 5 በሚኒሶታ ይህ ቶርናመንት እንደሚካሄድ ለማረጋገጥ ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዲሲ የአላሙዲንን ኳስ ቦይኮት በማድረግ “ላለፉት 2 ዓመታት ያስተባበሩ ወገኖች ይህ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ድል ነው፤ የኛን ቦይኮት ፈርተው መፈርጠጣቸው ያስደስታል፤ በሚኒሶታም ተመሳሳይ ቦይኮት እንደሚገጥማቸው እንተማመናለን” በሚል በሶሻል ሚዲያዎች እየገለጹ ነው። እንደነዚህ አስተያየት ሰጪዎች “ለ3 ዓመት ኮንትራት ፈርመው በ2 ዓመታቸው ለቀው መውጣታቸው የኢትዮጵያውያን የትግል ውጤት ነው።” (ሚኒሶታዎችም እንግዲህ ንቁ ይላሉ ሃገር ወዳዶች)

የዘንድሮው ትክክለኛው የኢትዮጵያውያን 31ኛው ዓመት የስፖርት ፌስቲቫል የሚደረገው ሚኒሶታ ሳይሆን ሳንሆዜ ነው

ሚኒሶታ

መኮንን ላዕከ... ከገጽ 15 የዞረነው የሚሉህ፡፡ ይህ ነገር ከክበበው ገዳ ጋር የ‹‹ሸምሱን›› ቪሲ

ዲ ከሰራችሁ በኋላ የተፈጠረ ነው?መኮንን፡- በየቦታው የተለያየ ስም ነው ያለኝ፡፡ እንዳልከው እ

ሱ ሸምሱን ሆኖ እኔ ሽማግሌውን ሆኜ በሰራነው ቪሲዲ ‹‹አባዬ›› እያለ ነው የሚጠራኝ፡፡ አጠራሩ ቀለል ያለ እና አዝናኝ ስለሆነ አፍ ላይ ቶሎ ይቀራል፡፡ ጓደኞቼ አጠራሩ ስለተመቻቸው ያው ‹‹አባዬ›› ይሉኛል፡፡ እኔን ብዙ ሰው በመኮንን የሚያውቀኝ አይመስለኝም፡፡ ድፍን የፒያሳ ሰው ‹‹አባዬ›› ነው የሚለኝ፡፡ ወደ ተረት ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር ስትወርድ ‹‹አከቤ›› ሲሉኝ ትሰማለህ፡፡ በጉራጊኛ አጎቴ ማለት ነው፡፡

ጥያቄ፡- ቡድን የመምራት ብቃትህን ብዙ ጓደኞችህ ያነሱታል፡፡ ያለህበትን ቡድን አንድ መንፈስ፣ አንድ ልብ የማድረግ ችሎታህ ከየት የመጣ ነው?

መኮንን፡- የአንድ ሰው መገለጫው እና የሰብዕናው መጠንሰሻ ቤተሰብ ነው፡፡ ያደግኩበት አካባቢ ማህበረሰብ ለዚህ ነገር ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡ እኔ ተወልጄ ያደግኩበት ጊቢ አስራ አራት ቤተሰብ ያለበት ነው፡፡ ለአስራ አራቱ ቤት አንድ ኩሽና (ማዕድ ቤት)፣ አንድ ሽንት ቤት፣ አንድ ቧንቧ ነው ያለው፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን ጠብ የለበትም፡፡ ሁሉም በስምምነትና በመደማመጥ ነው ተከባብሮ የሚኖረው፡፡ በፍቅር የሆነ ነገር ሁሉ ያምራል፣ ምንም አያስቸግርም፡፡ የእኛ ሰው ደግሞ የሚያነሳሳውና የሚመ

ራው ይፈልጋል እንጂ ሁሌም ለመተባበር ዝግጁ ነው፡፡ በል እንዲህ አድርግ የሚለው አስተባባሪ ብቻ ነው የሚፈልገው፡፡ ስለዚህ ንፁህ ልብ ይዞ የሚገኝ ሰው ምንም ነገር ማድረግ አይከብደውም፡፡ ይህን ከተወለድኩበት አካባቢ ተምሬዋለሁ፡፡ የሁሉ ነገር ቁልፍ ንፁህ ልብ ነው፡፡ ንፁህ ሆነህ ስትቀርበው ንፁህ ሆኖ የማይቀበልህ ማንም የለም፡፡ ቁልፉ ነገር ይሄ ነው፡፡ እንደውም አንድ ምሳሌ ልንገርህ አንዴ አንበሳ፣ ነብርና ዝሆን ከሰው ጋር ሆነው ሰርከስ እየሰሩ በቴሌቪዥን አየሁ፡፡ እንዴት ነው ሊግባቡና ሊዋደዱ የቻሉት ብዬ ሌሊቱን ቁጭ ብዬ አደርኩ፡፡ መልሱን ያገኘሁት ሊነጋጋ ሲል ነው፡፡

ጥያቄ፡- መልሱ ምንድነው?መኮንን፡- ሰውዬው ነው መጀመሪያ ጫካ የሄደው፡፡ በቃ ራ

ሱን ሰጣቸው፣ ንፁህ ልቡን ይዞ በደመነፍሱ ነው የሄደው፡፡ ልቡ አብጦበት አልሄደም፣ የሚበላውን ሰጣቸውና በሉ፡፡ ከዚያ ደጋግሞ እንደዚያ አደረገ፡፡ ንፁህ ልብ እንዳለው ስላወቁ ወደዱት፡፡ ሲቀር ናፈቁት፡፡ ቆይቶ ሲሄድ ገና ከሩቅ አይተውት ወደ እርሱ መጡ፣ ከዚያ ‹‹ኑ ወደ ከተማ እንሂድና ሰርተን እንብላ›› አላቸው፡፡ በደመ ነፍስ ተግባብተው ያን ትርዒት አሳዩን፡፡ ንፁህ ስትሆን እንኳን ሰው አውሬም ይቀርብሃል፤ ይወድሃል፡፡

ጥያቄ፡- ሰዎችን በስራዎችህ ታስደስታለህ፣ አንተንስ ምን ያስደስትሃል?

መኮንን፡- ከጓደኞቼ ጋር ቁጭ ብለን ውይይት ስናደርግ የተለየ ደስታ አለኝ፡፡ ከዚህ ውጭ ማንበብ በጣም እወዳለሁ፡፡ ካላነበ

ብኩ እንቅልፍ አይመጣልኝም፡፡ ጊዜው ያለፈበት ጋዜጣም ቢሆን የማንበብ ልማድ አለኝ፡፡

ጥያቄ፡- ቦሌ አካባቢ ታይተህ አታውቅም፤ ለምንድነው?መኮንን፡- እኔንጃ... ምክንያቱን ባላውቀውም አይመቸኝም፡፡

ፒያሳ ደስ ይለኛል፣ ጨርቆስ በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ቦሌ ግን ለምን እንደሆነ እንጃ... አይመቸኝም፡፡ ወደዚያ የምሄድበት ጉዳይ እንዲኖረኝም አልፈልግም፡፡ ምናልባት ንፅፅሩን ማሰብ ስለማልፈልግ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን የፈሩት ይደርሳል እንዲሉ ቦሌ አሁን ጨርቆስ ሆኗል፡፡ መሀል ቦሌ ጨርቆስ ክፍለ ከተማ እየተባለ መጠራት ጀምሯል፡፡ የጠሉት ይወርሳል የፈሩት ይደርሳል ማለት እንግዲህ ይሄ ነው፡፡

ጥያቄ፡- በርገር ትወዳለህ? ይመችሃል?መኮንን፡- በልቼው አውቃለሁ፡፡ እንደ በርገር ነው፤ እንደ ቤ

ታችን በር በጣም ገር ነው፡፡ ሸጋ፣ ገራገር ነው፡፡ ጥያቄ፡- ከእከሌ ጋር በሰራሁ ብለህ ተመኝተህ አታውቅም?መኮንን፡- ይሄን ጥያቄ ትናንት ማታም የሆነ ሰው ጠይቆኝ ነ

በር፡፡ እኔ ከእከሌ ጋር በሰራሁ ብዬ ተምኝቼም አስቤውም አላውቅም፡፡ ይልቅ እስከዛሬ አብረሃቸው ከሰራኸው ማን ተመችቶሃል ካልከኝ ፋንቱ ማንዶዬ ነው፡፡ ልጅ ሆኜ በጩጬነቴ እንዴት ተሻምተን እናየው እንደነበር አሁንም ይታወሰኛል፡፡ ‹‹የት ሄደሽ ነበር›› ሲል ሰው ሁሉ እንዴት ደስ እንደሚለው አስታውሳለሁ፡፡ ከፋንቱ ጋር መስራቴ ልዩ ደስታን ፈጥሮብኛል፡፡ ከመስራቴም ባሻገር ያሳየኝ ባህሪ ቀለል አድርጌ በጥሩ ሁኔታ እንድሰራ አድርጎኛል፡

፡ ተተኪን እንዴት ማፍራት እንዳለብን በተግባር አስተምሮኛል፡፡ በነገራችን ላይ ጀማሪን ማስጠጋት ዝናቸውን የሚቀንስባቸው የሚመስላቸው አሉ፡፡ ሌሎች ያላሳዩንን ፊት ፋንቱ አሳይቶኛል፡፡ ያቺ አጋጣሚ ለእኔ ልዩ ትርጉም አላት፡፡ አሁን ባለኝ ህይወትም የፋንቱን አርአያነት ተከትዬ ነው እየተገበርኩ ያለሁት፡፡

ጥያቄ፡- በመጨረሻ ምን የምትለው ነገር አለህ?መኮንን፡- የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፡

፡ ስለዚህ የምናደርገው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር የሚወደድ እንዲሆን በቅን ልቦና እና በንፁህ ልብ ይሁን እላለሁ፡፡ እግዚአብሔር የወደደው ነገር ከሆነ ሁሉም አልጋ በአልጋ ነው፡፡

ስለዚህ ሰዎች ሁሉ ቅን እንሁን እላለሁ፡፡ ሁለተኛ ጥበብና ጠቢባንን ያላከበረ ህዝብና መንግስት አይከበርም አይከብርም ለማለት እወዳለሁ፡፡ ባለሙያው ለሙያው ሲታገል መንግስትም ሙያውን ለማስከበር ቢጥር ለሀገር የሚጠቅም ውጤት ይገኛል፡፡

ከዚህ በተረፈ ለእኔ እዚህ መድረስ እገዛ ላደረጉትና ልረሳቸው ለማይቻለኝ ለአቶ አበበ አያሌው፣ ለመስፈን ከበደ፣ ለሳምሶን ወርቁ፣ ለክበበው ገዳ፣ ለእንዳልክ እሱባለው፣ ለያሬድ አስራት፣ ለሰላማዊት አለማየሁ፣ ለእሸቱ ታዬ፣ ለእህቴ አማከለች ላዕከ፣ ለጌታቸው ላዕከ፣ ለአለማየሁ ላዕከ እኛን እዚህ ለማድረስ ብዙ መስዋዕትነት ለከፈሉት እናትና አባቴ እንዲሁም እስከዛሬ አብረውኝ ለሰሩት እና ለጨርቆስ ነዋሪዎች በሙሉ የከበረ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ እናንተም ታሪክ አለህና ‹‹መድረኩን እንካ ተናገር›› ስላላችሁኝ ከልብ አመሰግናችኋለሁ፡፡

የካንሰር... ከገጽ 16 የዞረእንደማንኛውም ህመምተኛ ተመጣጣኝ ምግቦችን መመገ

ብ በካንሰር ለተጠቁ ሰዎች ጠቃሚ ነው፡፡ የካንሰር ህሙማን የሚወስዱት መድሃኒት የምግብ ፍላጎታቸውን ሊቀንሰውና የሚበሉትን ምግብ ጣዕም ሊቀይረው ይችላል፡፡ ጥናቶች እንዳመለከቱት ተመጣጣኝ ምግቦች ለካንሰር ህሙማን የሚከተሉትን ጥቅሞች ይሰጣቸዋል፡፡

- የጤንነት ስሜት እንዲሰማዎት ያደርጋል- ሌሎችን በማዳበር በሽታ የመቋቋም አቅሞን ያጎለብትሎ

ታል፡፡ - ጉዳት የደረሰበትን ህብረ ሴል (ቲሹ) ለመጠገን የሚረዱ ካ

ሎሪና ፕሮቲንን የማግኘት እድሎን ያሰፋዋል፡፡ - ጥሩ ስሜት ስለሚፈጥርሎት በሽታዎን ለመከላከል የሚረ

ዳዎን መድሃኒት በአግባቡ ለመጠቀም አቅም ይኖሮታል፡፡- በቀን ውስጥ በተደጋጋሚ የሚወሰደው በፈሳሸና በእንክብ

ል መልክ ተዘጋጅቶ የቀረበው መድሃኒት የሰውነትዎን ክብደት ለመጠበቅ ወይም ለመጨመር ያስችሎታል፡፡ የካንሰር ህሙማን ተመጣጣኝ የሆኑ ምግቦችን ለማግኘት ምን ማድረግ አለባቸው?

- የስጋ ጣዕም የማይስማማዎ ከሆነ ጣዕማቸው ቀለል ያሉ እንደ አይብ፣ እርጎ እና ሌሎች የወተት ውጤቶችን በመመገብ ከስጋ የሚያገኙትን ፕሮቲን መተካት ይችላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም

አተር፣ ሽንበራ፣ ባቄላ እና ሌሎች በፕሮቲን የበለፀጉ ጥራጥሬዎችን በመመገብ አካሎት በቂ ፕሮቲን እንዲያገኝ ያድርጉ፡፡

እነኚህን ጥራጥሬዎች ከሩዝና ከዳቦ ጋር ለመቀላቀል የፕሮቲን መጠናቸው የበለጠ መጨመር ይችላሉ፡፡

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ የሚገኘው የአፍ ካንሰር ማህበር ለሀገሪቱ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር አስተዳደር የቀረበው ለወጣት ወንዶች የሚሆን የኤችአይቪ ቫይረስ መከላከያ ክትባት በአፋጣኝ ፀድቆ ተግባራዊ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ ይህን የክትባት ፕሮግራም ለመስጠት ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ የሚጠይቅ በመሆኑ እስካሁን ውሳኔ ባይሰጥበትም የሀገሪቱ ባለስልጣናት ከፍተኛ ውይይት እያደረጉበት መሆኑን አስታውቋል፡፡

በመጨረሻም አሁን ያለውን የቫይረሱን ስርጭት ሊያስረዳ በአሜሪካ ውስጥ ከመቶ ሺ ጎልማሶች ሁለቱ የሚያዙ ሲሆን በዓለማችን ውስጥ ደግሞ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ሲያዙ በአሁኑ ወቅት ለዚህ ቫይረስ ክትባት የተዘጋጀለት ሲሆን ክትባቱም ለሴቶች የማህፀን በር ካንሰርን ለመከላከል በመስጠት ላይ እንደሚገኝ በመግለፅ ነበር ሪፖርቱን ያጠናቀቀው፡፡

በአጠቃላይ የካንሰር ህመምን ከጅማሬው በመመርመር እንደውም ህመሙ ኖረም አልኖረም ለቅድሚያ ጥንቃቄና አስቀድሞ ለማወቅም ምርመራ ማድረጉ ጠቃ ነው፡፡ ችግሩ በአሁኑ ሰዓት ያ

ደጉትን ሀገራት አልፎ ያላደጉ ሀገራት ችግርም እየሆነ ነውና ግንዛቤያችንን ሰልፍ በመውጣት ቀኑን ከማሰብ ዘላለም በህይወታችን ለእኛው ህይወት ቀጣይነት የተግባር ሰዎች ልንሆን ይገባል፡፡ ያኔ የካንሰር ህመምን መቆጣጠር እንችላለን፡፡

ፖርቱጋላዊው... ከገጽ 21 የዞረ እዚያም እንዲሰለጥኑ እንደሚያደርጉ፣ ኢትዮጵያዊያን አሰ

ልጣኞችንም እንዲሁ በአውሮፓ የአሰልጣኞች ስልጠና ካምፖች ውስጥ ገብተው እንዲቆዩና በኋላም በብሔራዊ ቡድኑ ኃላፊነት የእርሳቸውን ቦታ የሚተኩትን አሰልጣኞች እንደሚያፈሩ ሲናገሩ በጥራጣሬ ሰምተናቸዋል፡፡ እውን እነዚህ ቃል ኪዳኖች በቀላሉ የሚፈጸሙ ናቸው? ወይስ በቀዳሚ እጩነት ተይዘው አዲሱን ኮንትራት ለመፈረም የሚያስችሏቸው ባዶ ቃላት ናቸው? ሁሉንም ጊዜ ይፈታዋል፡፡

በዘጠኝ ወራት 33 ጨዋታዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከወጣቶችና ከአዋቂዎቹ ብ

ሔራዊ ቡድን ጋር አብሮ የሚሰራና በተለይ የወደፊቶቹን ወጣቶች ለማፍራት የሚያስችልን አሰልጣኝ ለማግኘት ጥረት ማድረጉንና ማሪያኖ ባሬቶን ማግኘቱን አውጁዋል፡፡ የፌዴሬሽኑን ሃሳብ የሚደግፍ የውጤታማነት ታሪክ ፕሮፌሰሩ ካላቸው እንዲናገሩ ሲጠየቁ በጋና ብሔራዊ ቡድንና ኦሊምፒክ ቡድን 33 የወዳጅነትና የነጥብ ጨዋታዎችን ማከናወናቸውና አብዛኛዎቹን ማሸነፋቸው

ን ገለጹ፡፡ ባሬቶ በአክራ የቆዩት ለዘጠኝ ወራት ነው፡፡ በዘጠኝ ወራት 33 የብሔራዊ ቡድን ጨዋታ አንዴት? በአንድ ወር በአማካይ 3.7 ጨዋታ የሚያደርግ የክለብ እንጂ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሊሆን አይችልም፡፡ 33 ጨዋታ መሆኑን በግልጽ እንግሊዝኛ ሁለት ጊዜ ደጋግመው መናገራቸው በመቅረጸ ድምጽም ተቀርጿል፡፡ ተከታይ ጥያቄዎቼን ላቀርብ እጄን ባነሳ መድረኩ የአንድ ሰው እንዳይሆን ተባለና ድጋሚ እድል እንደማይሰጠኝ ተነገረኝ፡፡ በ2004ቱን ኦሊምፒክ ባሬቶ ጋናን ይዘው ወደ ግሪክ ተጉዘዋል፡፡ ሆኖም በማጣሪያው ሙሉ ቡድኑ በእኔ አሰልጣኝነት ተመርቷል ቢሉ ማን ያምናቸዋል? በኦሊምፒኩ አንደኛ ዙር ከውድድር የወጡበትን ምክንያት ከመግለጽ ይልቅ የተጋጣሚዎቹን ጠንካራነት የሚያጎሉ ምክንያቶች ላይ ማተኮር መረጡ፡፡

ብቸኛው ጠንካራ ጎንትውልደ ህንዳዊው ባሬቶ እስከ 2004 ድረስ በተለያዩ የአው

ሮፓ ክለቦች በሙሉ የአካል ብቃት አሰልጣኝነት መስራታቸውን የሚያረጋግጡ ኦፊሴላዊ ማስረጃዎች ብዙ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዘመናት የአካል ብቃት አሰልጣኝ አልነበረውም፡፡ የሰውነት ቢሻው ቡድን ጉድለት የአካል ብቃት አሰልጣኝነት እንደነበር ብዙ ተብሏል፡፡ አሁን ግን ቡድኑ ሁነኛ የአካል ብቃት አሰልጣኝ አግኝቷል፡፡ የዋና አሰልጣኝነቱ ስራ በውጤታማነት ይታገዝ እንደሆነ የሚያሳምኑ ምልክቶችን ግን ከማሪያኖ ባሬቶ ላገኝ አልቻልኩም፡፡ መልካም እድል ፕሮፌሰር!

Page 20: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 20

የወያኔ... (ከገጽ 3 የዞረ)

ጎጠኝነት አረንቋ ባፋጣኝ እንውጣ፤ ያለንበትን ዘመን እንረዳ፡፡ ወገናችንን እንውደድ - እናፍቅርም፤ ሀገራችንንና ሕዝባችን የምንለውን ወገናችንን ለሥልጣን መወጣጫነት ሣይሆን በሀቅ ወደን እስከሕይወት መስዋዕትነት ትልቅ ዋጋ በመክፈል ከገቡበት አዘቅት እናውጣቸው፡፡ ያኔ ነው ፈጣሪ የሚባርከንና ዕቅዳችንን ቀድሶ በተገቢው መንገድ እውን የሚያደርግልን፡፡ አለበለዚያ ወያኔ አሁን እንደሌለ ሁሉ በሌለበት ሁኔታ አገዛዙን በእጅ አዙር ቀጥሎ የመለስና የመሪ ድርጅቱ የወያኔ አፅም ጉድጓድ ውስጥ ሆነው በሹምባሾቻቸው አማካይነት እስከወዲያኛው እያንቀጠቀጡ ይገዙናል - ልብ አድርጉ የሚገዛን ግን የወያኔ ጥንካሬ ሣይሆን የኛ ልፍስፍስነትና የኛ መጥፎ ሃሳብ ካርማዊ ዕድፍ የሚያጠላብን የመርገምት ውጤት ነው፡፡ አሁንና እስካሁን አንድ ያላደረገን የተለያየው ፍላጎታችን እንጂ የሚደርስብን ግፍና በደል ተለያይቶ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ እስከዚህን ደረጃ ያለያየን ለምንም ዓይነት ሕዝባዊ ስቃይ ሊንበረከክ ያልቻለው ግላዊ የሥልጣንና የሀብት ፍላጎታችን እንጂ በርግጥም በእውነት ተለያይተን እንዳልሆነ ኅሊናችን ያውቀዋል፡፡ (በሰላም ቀን የሀገራችን ልዩ መመኪያ ሊሆናት ይችል የነበረውና በሥልጣንና ሀብት አራራው ምክንያት ግን የወያኔ ሥውር ወኪል (mole/double agent) ሆኖ ሀገሩን በክፉ ቀን ከድቶ ከጠላቶቿ ጋር ያበረው ልደቱ አያሌው እንዲያ በመንታ እያነባ ለኢትዮጵያና ሕዝቧ “ሕይወቱን” እስከመሰዋት በሚደርስ “ጽናት” ዝዋይና ሸዋሮቢት የተንከራተተው ለማንና ለምን እንደሆነ በተለይ አሁን ላይ ቁልጭ ብሎ ይታየናልና ከዚህ ዓይነቱ ቁጭ በሉ አስተሳሰብና ዕኩይ ድርጊት በቶሎ እንውጣ፡፡ እውነቴን ነው - በተለይ ከእንግዲህ ማንም ማንንም ሊያታልል አይችልም፡፡ ሁሉም ነቅቷል ፤ ቀኒቷን ግን በጉጉት ይጠብቃል - የነፃነቷን የማትቀር ቀን፡፡) በበኩሌ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ለዚህ ዓይነቱ ፖለቲካዊ ድራማ የማትመች እንደምትሆን ተስፋ አለኝ፡፡ አማራ - ትግሬ፣ ኦሮሞ - ሶማሌ …. መባባሉ የታይታና ዘመን ያለፈበት የትግል ስትራቴጂ እንጂ ውስጠ ምሥጢሩ ሌላ መሆኑን እናውቃለን፡፡ ሌላው ልብ ማለት የሚገባ ነገር ደግሞ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ዘጠና ሚሊዮን ወንበር የለውም፤ አንድ ነው፡፡ ያንንም በዘር ሣይሆን በ‹ሜሪት›ና በሕዝብ እውነተኛ ምርጫ ማስያዝ ይጠበቅብናል - ጊዜው ሲደርስ፡፡… እውነትን ተናግሮ እመሸበት ማደር እንዲህ ይመስለኛል፡፡ ወዳልተነሳሁበት ርዕስ ጥልቅ እያልኩ ማስቸገሬን ይቅርታ አድርጉልኝ፤ ወድጄን እንዳይመስላችሁ፡፡

በዚህ ዘመን ወያኔዎችን “ይህ እኮ ህገ መንግሥታዊ መፍቴ ነው!” ብትል “እሱን ቀቅለህ ከቤተሰቦችህ ጋር ሆነህ ብላው!” ሊሉ ይችላሉ ብቻ ሣይሆን ዘወትር የሚደግሙልህ ውዳሤ ማርያማቸውና መዝሙረ ዳዊታቸው ነው፡፡ ህገ መንግሥቱ - ምን አለፋህ ወንድሜ - የዐዋጁን በጆሮ እንዳትለኝ እንጂ ለአሰለጥ ትግሬዎችና ለፌዴራል የትግሬ ሠራዊት በፍጹም አይሠራም - ሀገርን በቅኝ ግዛት ለወረረ የአንበጣ መንጋ ምክንያታዊነትና ሰብኣዊነት የሚገመዝዘው ቀልድ በመሆኑ ከጠበንጃ ውጪ የሚታየው የችግሮች ማስወገጃ ሌላ ብልሃት ብሎ ነገር የለም፤ ጤናማና ለኅሊናው ተገዢ የሆነ ትግሬ እንደኛው መሰቃየቱን በታሳቢነት ያዝልኝ ታዲያ - ጥቂትም ቢሆኑ አሉ፤ የምን ጥቂት - ብዙ ናቸው ኧረ! እርግጥ ነው ነገሩ ዕንቆቅልሽና ግራ የሚያጋባ ሊመስል ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚባለውን የሥልጣን ቦታዎችን፣ የንግድ ተቋማትን፣ የአነስተኛና ጥቃቅን ንግዶችን፣ የሕንፃዎችንና የፋብሪካዎችን ባለቤቶች፣ የመንግሥት ቤቶችን በነፃ ተከራዮችን፣ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን፣ የወታደርና የፖሊስ ተቋማትን፣ የደኅንነት መዋቅሩን፣ የባንኩንና የአክሲዮን ሸያጩን፣ ውድ ውድ የሚከፈልባቸው ትምህርት ቤቶችንና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን፣ መዝናኛ ሥፍራዎችን፣ … በጠቅላላው በሀብቱ ማማ ላይ ፊጥ ያለውንና በትንሹም በትልቁም ሲቆጣ የቀድሞ ወንድምና እህቶቹ የአሁን አሽከሮቹና አጫዋች አኗኗሪዎቹ ላይ፣ የሀብቱም አድናቂዎች የሆኑ ሌሎች ምሥኪን “ወገኖቹ” ላይ በዕብሪት “እቧይ” ሲል የምትሰማውን ትግሬ ስታይ ኢትዮጵያ በአንዳች ትግሬያዊ ምትሃትና ሰሜናዊ ዋግ የተመታች ሊመስልህ ቢችል ዘመኑና አበቅቴው ነውና ቻል ማድረግ ሊኖርብህ ነው፡፡ ኧረ እንዲያውም በተጋቦት ትግሬ የሆነ ሌላ ዜጋም ሲያስመስል “እቧይ!” ሲልና የስልክ መጥሪያውን ካለውዴታው ለማስመሰልና ለመወደድ ሲል ብቻ የትግርኛ አድርጎም ልትታዘብ ትችላለህ፤ አቤት ይህ ጊዜ ሲገርም - ራስን ሲያሳጣና ባዶ ሲያስቀር፡፡ ዘመቻው እኮ ሁለገብ ነው - ኢኮኖሚያዊም፣ ወታደራዊም፣ ሥነ ልቦናዊና ባህላዊም፣ ሃይማታዊም፣ ምናምናዊም ሁሉ ነው፡፡ ታዲያን እንዲህ ያለ ነገር በታሪክ አልፎ አልፎ ሊያጋጥም እንደሚችል “ሚዉቴሽናል ክስተት” በመቁጠር መታገስ ይኖርብናል - ቂሎችን ተከትሎ ቂል መሆንና ለቂም በቀል መነሳሳት አይገባም ብቻ ሣይሆን ቂም በቀል የሚወልደው ሌላ ቂም በቀልንና የዐመፃ ተግባርን በመሆኑ ከዚህ ዓይነት ሃሳብ መታቀብ አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው - ከእግዚአብሔር መንገድ የወጡ ሰዎች ከዚሁ የፈጣሪ መንገድ ሊያስወጡን አይገባም - ምንም እንኳን የነሱ ፍላጎት ይሄው ቢሆንም እኛ ግን እነሱ በመጡበት መንገድ በጅልነት ልንማገድበት አይገባንም - ጎጂ ነው፤ ለጊዜው ካልሆነ በዘለቄታዊነት አያዋጣምም፡፡ የአነስታይንን ምክር መቀበል አለብን - “አንድ ችግር በተፈጠረበት የአስተሳሰብ ደረጃ ተጉዞ ችግሩን ማስወገድ አይቻልም፡፡” ክርስቶስም ቀድሞ አለ “ጠላትህን ውደድ፤ አንድ እርምጃ ከእርሱ ጋ

ር እንድትራመድ ቢጠይቅህ ሁለት ድገምለት፤ እጀ ጠባብህን ቢጠይቅህ መጎናጸፊያህንም ድገምለት፤ ግራ ጉንጭህን ቢጠፋህ ቀኝህንም ድገምለት …” ይህ ምክሬ የተለያዩ የትግል አማራጮችን ለሚከተሉ ወገኖች እንደማይጠቅማቸው አውቃለሁና ከነርሱ አንስቻለሁ፡፡ ምርጫን ደግሞ አከብራለሁ - እንደምርጫ፡፡ ይህ አስተያየቴ ተቀባይነት እንዲኖረው የምሻው በተለይ በሃይማኖቱ ማኅበረሰብና በሰላማዊው ሕዝብ መካከል ነው፡፡

አንድ ነገር እንገንዘብ፤ ይህ ጊዜ ዘንጦ ያልፋል፤ ዘንጦ ያላለፈ የክፋት ዘመን በታሪክ እንዳልነበረ ሁሉ ዛሬም አይኖርምና፡፡ በተረፈ ግን እንደውነቱ ከሆነ ይሄ ዘመን ትግሬዎችን አልጠቀመም የሚሉት የጅሎች ፈሊጥ ከፍ ሲል ከገለጽኩት አስቀያሚ ሀገራዊ ገጽታ አኳያ አይገባኝም፡፡ በዚህ ዘመን የማይጠቀም ትግሬ ካለ አእምሮው ጤናማ የሆነና ዛሬ በነገው ቀን ላይ የሚጥለውን ታሪካዊ ዳፋ ከወዲሁ በማጤን አስተሳሰቡን ከአብዛኛው ጭቁን ወገን ጋር ያጣመረ ደግ ትግሬ ብቻ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ትግሬ እንኳንስ በሌባውና በአጭበርባሪው ወያኔ-ትግሬ በእኛ በኢ-ትግሬያውያኑም ጭምር ሞኝ የሆነ ያህል ይቆጠራል፡፡ ለምን ቢባል ጤናማ አእምሮ በጠፋበትና ይሉኝታቢስነት በነገሠበት የዘረኞች አገዛዝ ውስጥ እንኳንስ ትግሬ የሆነ ሰው ይቅርና የትግሬዎች አንጋችና እግር አጣቢ የሆነ ዜጋ ራሱ ትርፍራፊ መቅቡጥ አያጣምና ነው - ስንቱ የመንደር ካድሬ እንዴት እየተዝመነመነ እንደሚኖር አውቃለሁ፡፡ ኅሊና የሌለው ሰው በአንድ አዳር ከብሮ ሊያድር የሚችልባቸው በሮች በርካታ ናቸው - ወያኔ ደግሞ ለፖለቲካው ሥጋት አትፍጠርበት - ትዛዙንም በጭፍን ተቀብለህ ተግብርለት እንጂ ለጊዜውና እስክትሰባለት ድረስ አያርድህም፡፡ Literally speaking, to my understanding, non-Tigrians are slaves of Tigrians in all denotative and connotative mean-ings of slavery. Though we cannot differentiate a Tigrian from non-Tigrian especially with respect to color, unlike the case in the apartheidal South Africa or the segrega-tional US, during which the blacks and whites were eas-ily pinpointed, unless maybe by the so called “number 11”, which, again, some non-Tigrians might have it on their temples in their face as well, the difference in life style and possession of wealth between Tigrians and non-Tigrians is absolutely unfathomable. A Tigrian, unless they fear their conscience, can, for example, kill an Amhara in a broad day light and live out of bars. Don’t get surprised, dear sister or brother! There are more severe punishments inflicted upon the Amharas by the TPLF junta, with the blessing of “some” foreign forces, of course. The ‘world’ has been silent, even at times has also been cooperative, and hence, complicit, while Ethiopia and Ethiopians have been suffering for so long, and be sure, everyone will be paid accordingly. Now in Ethiopia, except Tigrians, no one has the right to demand any right that humanity and/or Ethiopian-ness used to give, relatively in abundance, just some decades ago. I think this is the result of animalism from the side of the Tigrians who are ruling, rather, mis-ruling the nation; to my conviction, I do believe that they are missing certain component(s) in their evolution and I can surely say that Ethiopia is currently ruled by a crew of people who have not yet finished their human develop-ment in terms of evolution. Could they be homosapiens or australopitecus? I don’t know. But, in reality, the situation is regrettable and pitiful, not necessarily from the vantage point of Stockholm syndrome.

አሁን እንጃ እንጂ አንድም ሹፌር ከጂቡቲ አንዲትም ቡትሌ የምግብ ዘይት ይዞ እንዳይመጣ ተከልክሎ ነበር፡፡ እንደሰማሁት የዛሬን አያድርገውና ከወያኔ ጋር ድብን ያለ ፍቅር ውስጥ የነበረው የጌትአስ ኢንተርናሽናል ካምፓኒ ባለቤት - እልም ያለ ማይም ባለሀብት - ነበር አሉ ያስከለከለው፡፡ ልብ አድርጉ! አንድ የከባድ መኪና ሹፌር በመቀመጫ ወንበሩ ግርጌ ወይ ራስጌ ወትፎ የሚያመጣት አንዲት የ20 ሊትር ጀሪካን ዘይት፣ የዘይት አስመጪውን ሁለገብ ባለሀብት ገበያ ሲሻማበት ይታያችሁ፡፡ ያሳዝናል፡፡ ለዚህ ነው እኛ ኢትዮጵያውያን ምቀኝነትን ከሰውነታችን መንጥሮ የሚያወጣ ፍሪ አንቲቫይረስ ማስጫን እንደሚያስፈልገን ዘወትር ለጓደኞቼ የምናገረው - ማካፌ ወይ አቫስትና ካስፐርስኪ ከተገኙ፡፡ ሀብታሞች ገብጋቦች ናቸው፡፡ ሀብታሞች - በተለይ ኢትዮጵያውያን - የሰው ደም መጣጮች ናቸው - በቀሰምና በስሪንጋ አይደለም - ግን ከዚህ በማይተናነስ የገብጋባነትና ስስታምነት ጭካኔ፡፡ ሀብታሞች ሃይማኖት የሌላቸው - አለን ቢሉም ለይስሙላ ካልሆነ ከልብ የሚያመልኩት አምላክ የሌላቸውና ገንዘብን በርሱም ውስጥ ሰይጣንን የሚያመልኩ- የአጋንንት ማደሪያ ናቸው፤ የጨከንኩባቸው አይመስለኝም፡፡ በምናገረው ጥርጥር የለኝም - ክርስቶስስ ለዚህ ሳይሆን ይቀራል ያቺን የግመልና የመርፌ ቀዳዳ ምሳሌ የተናገረባቸው? በነገራችን ላይ የዚያ ማይም ነጋዴ የአሁኑ ዕጣ በስደት መኖር ነው አሉ - ሰይጣኖች ፍቅራቸውም ጠባቸውም አንድ ነው፤ ሁሉም ነገራቸው ወረትና በህገ ወረትም የሚገዛ ነው፡፡ ሲፋቀሩና ሲጣሉ ጊዜ አይወስድባቸውም - በተለይ በዘር ሐረ

ግ የማይገናኙ ከሆነ፡፡ እንደዚህ ዓይነቱን ቀፎ ሀብታም በልዩ የርቀት መቆጣጠሪያ ነው የሚከታተሉት፡፡ ስለሆነም በሀብት እየበለጣቸው ሲመጣ ተተናኮሉት ማለት ነው - በፖለቲካውስ የሚያገኙት አይመስለኝም፡፡ የርሱ ፖለቲካ እንደከብት በልቶና ጠግቦ ከማደር አያልፍምና፡፡ ይቅርታና ብዙው የወያኔ ጥገኛ ሀብታም በምግብና መጠጥ ከርሱን ከመቀብተትና ከማግሳት እንዲሁም በአጠንካሪ መድሓኒቶች የታገዘ እንትኑን ባገኘው እንትን ሁሉ ከማሾለክ ባለፈ ለሀገር የሚቆረቆረውና የሚጨነቀው ባለሀብት ዜጋ ከቁጥር የሚገባ አይመስለኝም፡፡ የዛሬ ሀብታም እንማንትስ ወርቃለማሁን ጨምሮ በብልግናው ጎዳና መትመምና ባህልንና ወግን ማጨቅየት ከወያም ጋር ካባ እየደረቡ በፍቅር መጫወት እንጂ ለሀገር ማሰቡን ትተውታል፤ ለዚህ ወጣቶቹ ተሸለው ተገኝተዋል፡፡ እነአንዱኣለምንና ርዕዮትን ያስቧል፡፡ ሌላውስ ተከድኖ ይብሰል - ሆዳቸውና እንትናቸው ብቻ አይጉደልባቸው እንጂ የሚሸጥን ሀገራዊ ነገር ሁሉ ይቸበችባሉ፡፡

ሁላችሁም እንደምታወቁት ስዬ አብርሃ፣ በኢትዮጵያ የቀድሞ የዲያብሎስ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር መለስ ዜናዊ ሊያውም በጫት ምርቃና አነሳሽነት በደቂቃዎች ውስጥ በተነደፈ የፀረ-ሙስና መሥሪያ ቤት ማቋቋሚያ ዐዋጅ ምክንያት ፍርድ ቤት እንኳን ቢለቀው ለበርካታ ዓመታት እንዲታሰር ተደርጓል፡፡ እንዲህ ናት ኢትዮጵያ! እንዲህ ናቸው ወያኔ ትግሬዎች! የጭንቅላት ችግር ከዚህ በላይ ሊኖር አይችልም፤ ጤናማ የሰውነት ዕድገት ዕጦት ችግር ከዚህ በላይ የለም፡፡ ወያኔ ጋ ፍርድ ቤት የለ፤ ፖሊስ የለ፤ መከላከያ የለ፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የለ፤ የውጭ ገበያ የለ፤ የሀገር ውስጥ ገበያ የለ … ሁሏንም ለግላቸውና በግላቸው ተቆጣጥረው መምነሽነሽ ነው፡፡ ይሉኝታ? ከየት ያውቁና! ሀፍረት? የት ያውቁትና! ትዝብት? የት “ገብቷቸው!”፡፡ ግን እንዳይመስላችሁ፡፡ ሁሉንም ያውቁታል፡፡ የመጨረሻ ዕጣ ፋንታቸውን ሳይቀር በሚገባ ያውቁታል፡፡ ክፋትንና መጥፎነትን የመጨረሻ አማራጫቸው ያደረጉት ሌላ አማራጭ በማጣታቸው ይመስላል - ከመነሻው አበላሽተውታልና፡፡ አንዴ ጨክነው ገብተውበታልናም ከአሁን ወዲያ ሌላ በጎ አማራጭ ያላቸው አይመስለኝም፡፡ ለማንኛውም ማሸነፍንና መሸነፍን የማያውቅ አጉል ሰው አያሸንፍህ፡፡ ቀን አይጣልህ ወንድማለም፡፡ ቀን የጣለውን ቀን እስኪያነሳው ያለውን ውጣ ውረድ ለመረዳት ኢትዮጵያዊ ሆኖ መፈጠር ከበቂ በላይ ነው፡፡ ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን እኛ ኢትዮጵያውንም በወያኔ-ትግሬ ክፉኛ ተፈተንን፤ አንዳንዶቻችን በፈተናው ወደቅን፤ ጥቂቶቻችን ቢያንስ እስካሁኒቷ ደቂቃ ያሸነፍን መስለን አለን፡፡ ጊዜ በእግዚአብሔር ዘንድ ብዙ ነገር ማለት ነውና የጊዜን የማይዘባበቱበት ፍርድ እንጠብቅ፡፡ ቀኑ ቀርቧል!

የወያኔን ዐዋጆችና መመሪያዎች በሚመለከት ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ በእውነቱ እጅጉን ጉደኞች ናቸው፡፡ ሀገር ለመሸጥና ገንዘብ ለማግኘት፣ መኪና ለማስገባት፣ የተወደደ ዕቃ ለማስገባትና ለመሸጥ፣ የሚጠሏቸውን ወገኖች ከገበያ ለማውጣት፣ መሬት ለባዕዳን ለመቸብቸብ፣ ቤትና መሬት ከዜጎች ለመቀማት፣ አንድን ግለሰብ ሳይቀር ለማክበር ወይም ለማደኽየትና ከፈለጉም ዘብጥያ ለማውረድ፣ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ተቀናቃኝን ቀንዱን ለመምታት፣ ኑሮን ሰማይ በመስቀል የሕዝብን ቅስም ለመስበርና በዚያውም ሕዝብን የማጀቱ ጣጣ ውስጥ በመወተፍ ሌላ ቁም ነገር እንዳያስብ በማድረግ የበቀል ጥማታቸውን ለማርካት… ወያኔዎች የማንም እገዛና የዓለም አቀፍ ህግ ከለላ ሳያስፈልጋቸው ያሻቸውን ዐዋጅና መመሪያ አውጥተው - እነሱንና ተላላኪ ጭፍራዎቻቸውን ግን ሲያልፍም የማይነካ መሆኑ መታወቅ አለበት - በደቂቃዎች ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ፡፡ በህግ ስም የፈለጉትን እያደረጉ ሀገርንና ሕዝብን እንደገደሉ ቢያንስ እስካሁን ካለተቀናቃኝ ቀጥለዋል፡፡ ነገስ? ነገ ሌላ ቀን ይሆናል፡፡ ሒሳብ ማወራረዳቸውን መጠራጠር አይገባም፡፡

በሰሞኑ የፋሲካ ገበያ አንዳንድ የአሃዝ ስህተቶችን ከኢሳት ታዝቤያለሁ፡፡ ይህ ስህተት የመረጃ አቀባይ ስህተት ይመስለኛል፡፡ የዕቃዎችና የዓመት በዓሉ ገበያ የዋጋ ዝርዝር አንዳንዱ ትክክል ሆኖ አንዳንዱ ስህተት ነበር፡፡ ስህተት ያልኩት ዋጋው ከእውነቱ የቀነሰ በመሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ የበግ፣የፍሪዳ፣የዶሮ፣ የቅቤ፣ የቀይ ሽንኩርትና የመሳሰሉት ዋጋዎች በኢሳት የተነገረው ከእውነቱ በጣም ቀንሶ ነው፡፡

ሰሞኑን ሁለት ተራራ እሚያህሉ የደለቡ በሬዎች በ90 ሺህ ብር እንደተሸጡ እዚያው የነበረ ሰው አጫውቶኛል፡፡ ዛሬ የበሬ ዋጋ እንዲህ ጥንቡን ጥሎ ለአንድ በጣም የደለበ በሬ ብር 45 ሺህ ተከፈለ እንጂ የዛሬ ዓመት በነበረው የፋሲካ በዓል አንድ በሬ 60 ሺህ ብር መሸጡን ከሁነኛ ሰው በጊዜው ሰምቻለሁ፡፡ 30 ሺህና 20 ሺህማ በብዙ ቦታዎች ተሸጧል፡፡ የምላችሁ እውነቴን ነው፡፡ እያንዳንዳቸው 45 ሺህ ብር የተሸጡት ከብቶች ታዲያ ከውፍረታቸው የተነሣ ወደሚጫኑበት መኪና ለመድረስ የተዘረጋውን የአራት ኪሎ ሜትር ርቀት በእግራቸው ለመጓዝ አንድ ሙሉ ቀን ፈጅተዋል - እያለከለኩና ሊፈርጡ ደርሰው፡፡ 90 ሺህ ብር ሲያነሳቸው ነው አይደል?

የልጄ ልጅ አቡጡ ጢል አድርጎ የሚያነሳው ኮሳሳ በግ ከ1500 ብር ብዙም አይቀንስም - በጣም የደለበውማ ከአራትና ከአምስት ሺህ ድምቡሎ እንዲቀንስልህ ከፈለግህ ከፋሲካና ከዳግማይ ትንሣኤ ማለፍ አለብህ፡፡ ገበያው እሳት ሆኗል፡፡ ያ በኢሳት የሰማሁት ዘፋኝ “ማገዶ ለቃሚ ምን አደከመሽ፤ ኑሮው እሳት ሆኖ ገብቶ ከቤትሽ” ማለቱ በሥነ ጽሑፍ ቋንቋ እንዴት ያለ ምስል ከሳች መሰላችሁ! በነገራችን ላይ ‹ኢሳት ቲቪ› የማልለው በኢሳት ውስጥ ቲቪ ስ

ላለ ነው፡፡ ኢሳት ሲተረተር ‹የኢትዮጵያ ሣተላይት ቴሌቪዥን› አይደል? በእግረ መንገድ “ድህረ ገፅ” የሚሉ ወገኖቼ “ድረ ገፅ” እንዲሉና ትክክለኛው ይህኛው እንደሆነ ብጠቁም ያስነውረኝ ይሆን? “ድህረ” ሲባል “በኋላ” እንደማለት ነው፤ “ድረ” ማለት ግን “ድር” ከሚለው የሸረሪት ድር ውስጥ የተመዘዘ ሆኖ “ዌብ” የሚለውን የ(እንግሊዝኛ?) ቃል በአማርኛ ለመተካት የተሞከረ ይመስለኛል፡፡ ከተሳሳትኩ ይቅርታ፡፡ እናም ‹ፕሊዝ› “ድረ-ገጽ” ወይም “ድረ-ገፅ” እንበል፤ እናስብልም፡፡

ለማጠቃለል ያህል የ500 ብር ደሞዝተኛና የአምስት ልጆች አባት የሆነው አቶ አዝብጤ ሸዋንግዛው በዚህ የሰሞኑ ፋሲካ የቀረበለት ገበያ በመጠኑ ሲዳሰስ ይህን ይመስል ነበር፡- (ጥራቱን ግን ለአንድዬ ብቻ ሰጥተን ነው ታዲያ - ለምሳሌ ቅቤው አንዱ ጉራንጉር ውስጥ ብልጦቹ ኅሊናአልባ ነጋዴዎች ባላገሮችን ሰብስበው ከምናምን ያለቡት ሊሆን ይችላል - የጥራት ጉዳይ በተለይ በምግብ ነክ አቅርቦቶች ላይ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል፤ በዘይትና ማር እንዲሁም በሌላ ሌላው ሥሪቱ የማይታወቅ የምግብ ግዢ አለማለቃችን የፈጣሪ ረድኤት ታክሎበት ነው እንጂ እንደነጋዴዎቻችን ቢሆን ኖሮ የፈለጉትን በቀጥታ ከአውሮፓና አሜሪካ ከሚያስመጡት ከራሳቸው ከሀብታሞቹና ከባለሥልጣኖቻችን በስተቀር አንድም ሰው በሕይወት ባልተገኘ - አሁን የምንመራው ሕይወታችን በ“ሕይወት አለን” የሚያስብል ከሆነ፡፡) ለማንኛውም ቅቤ ከ170 – 200፣ ዶሮ ከ100 – 280(እኔ 120 ብር የገዛሁት ዶሮ ድስቱ በላው መሰለኝ - እውነቴን ነው የምላችሁ ከዕንቁላሎቹ በስተቀር ጠላታችሁ እልም ይበል ሥጋው ድራሹ ጠፋ! ፈረሰኛ ነው እግረኛ የሚሉት የአባውራ ብልት(የዶሮው አጥንት ማለቴ ነው) ቆዳ ይሁን አንገት መሆኑ ተለይቶ ሳይታወቅ ሟሙቶ አገኘነውና በ“ቆይ ብቻ!” የዘመን መውቀሻ ዛቻ ተሳስቀን አለፍን፡፡ ምን ይደረጋል?)፣ የፈረንጅ ቀይ ሽንኩርት ከ12-17፣ በግ ከ1200 – 5000(+)፣ ምን አለፋችሁ ሁሉም ገበያ ድሃ አይነካሽ ነበር፡፡ የዓመት በዓሉ ብቻ ሣይሆን የአዘቦቱ ገበያም ያው ነው፡፡ ነጋዴው ከማን ጋር እልህ እንደተጋባ ማወቅ አልቻልኩም፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዴት ይኖራል? ይህንንም በውል አላውቅም፡፡ ብቻ ይመሻል፤ ይነጋልም፡፡ የሚገርመው ደግሞ መምሸት መንጋቱ ለነሱም ለኛም እኩል መሆኑ ነው፤ ወይ እኛ አናልቅ ወይ እነሱ አይጠረቁ፡፡ ከወያኔ ትግሬዎችና ከአንጋቾቻቸው በስተቀር ሌላው ሰው ሁላ ችግሩን በሆዱ ይዞና ተፈራርቶ መኖርን መርጧል፣ እየኖረ እየመሰለው ግን ሳይኖር ይኖራል፡፡ ሞቶ የሚኖር እንደኢትዮጵያ ሕዝብ የለም እላለሁ፡፡ እንወራረድ! ነገስ? ነገማ ያው ሌላ ቀን ነው፡፡ መልካም ዳግማይ ትንሣኤ፡፡

ቴሌፎኑ... (ከገጽ 6 የዞረ)

መንግስት አስተሳሰብም እጅግ የከፋ!የዜጎች ሁሉ ስልክ በቴሌ በኩል ይጠለፋል። እንደ ስካይፕ እ

ና ቫይበር ያሉ የቮይስ ኦቨር ስልኮች ደግሞ ፊን ፊሸር በተባለ የኮምፒዩተር ቫይረስ አማካኝነት ይጠለፋሉ። በዚህ አይነት በዜጎች የግል ህይወት ሳይቀር እየገቡ ቴሌን ሙሉ በሙሉ የስለላ ተቋም አደረጉት።

ሞባይል ስልክ እና ኢንተርኔት በአፍሪካ አህጉር በእጅጉ እየተስፋፋ ይገኛል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ 30 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጠጠቃሚ እየሆነ መጥቷል። በኢትዮጵያ ግን የስልክ እና የኢንተርኔት ተጠቃሚው ከ2.5 በመቶ አልዘለቀም። ጎረቤት የሆነችው የኬንያ ህዝብ 40 በመቶ የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ ነው። መንግስት አልባዋ ሶማልያ እንኳን፣ ስድስት የቴሌፎንና ስልክ አቅራቢ ኩባንያዎች አሏት። የሶማልያ ህዝብ ጥራት ያለው የስልክ መስመር እና ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆነ ሰንበትበት ብሏል። በኡጋንዳም የዚህ አገልግሎት ሰጪ በመንግስት ሞኖፖሊ ስር አይደለም። ከሰባት በላይ የግል ኩባንያዎች እየተፎካከሩ ፈጣን አገልግሎት እየሰጡ ጠተቃሚውን ህዝብ ወደ 50 በመቶ አድርሰውታል።

ያለነው በመረጃ ዘመን ነውና ያለመረጃ እና ያለ መረጃ ቴክኖሎጂ እድገት አመጣለሁ ማለት ዘበት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ሁኔታ ግን ሃገሪቱን ወደ መረጃ ሳይሆን ወደ ጨለማ ዘመን ነው እየመራት ያለው። እንድምናነበው ከሆነ የኢትዮጵያን ቴሌኮም ለማስፋፋት ከሶስት ቢሊየን ዶላር በላይ ወጪ ሆኗል። ይህ ገንዘብ በትክክል ስራ ላይ ቢውል አባይንም ይገድባል። ለዚህ የእድገት ሳይሆን ይልቁንም የጥፋት ጎዳና ተባባሪ የሆነቸው ቻይናም በውጭ ምንዛሪ እየተከፈላት ቴሌን ብቁ የስለላ ተቋም አድርጋዋለች። የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስትሩም ከተለያዩ የኢንዱስትሪ ሃሮች ጋር በመተባበር የቴሌ ጥራት ላይ ሳይሆን የሚሰራው የስለላ ሃርድዌር እና ሶፍትዌር ማስገባቱ ላይ ነው።

የሃገሪቱ ግብር ከፋዮች ገንዘብ መልሶ ራሳቸውን እንዲያፍን መደረጉ እጅግ ያሳዝናል።

የቴሌ መልስ መስጫ ላይ ያለው መልዕክት ግን መሻሻል አለበት። “ለግዜው” የሚለው ቢቀየር ድርጅቱን ከሃሜት ያድነዋል። እናም መልእክቱ እንዲህ ነው መሆን ያለበት፣

“የደወሉላቸው ደምበኛ ‘ለሁልግዜ’ ጥሪ አይቀበሉም። ..” ከዚያ በኋላ ደዋዩም ተስፋ ቆርጦ መደወል ያቆማል።

Page 21: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 21

ስፖርት

(በመንሱር አብዱልቀኒ )የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከእንግዲህ በማሪያኖ ባሬቶ ይሰ

ለጥናል፡፡ ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ በኢሊሊ ሆቴል በጋዜጠኞች ፊት የሁለት ዓመት ኮንትራቱ ውል ተፈርሟል፡፡ በወር 18ሺህ ዶላር ደመወዝ እንደሚከፈላቸው የተገለጸላቸው የ57 ዓመቱ ፕሮፌሰር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምርጫ የሆኑበት ምክንያት ግን ግልጽ አይደለም፡፡ ጥያቄዎቼ ሁሉ አጥጋቢና አሳማኝ መልስ ሳያገኙ ጋዜጣዊው መግለጫው መበተኑ አሳዝኖኛል፡፡ ከተነሱት አበይት ነጥቦች መካከል ያልተዋጡልኝና ብዙ ጥርጣሬዎችን የጫሩብኝ ነገሮች አእምሮዬን ሲበጠብጡት አምሽተዋል፡፡ እስቲ እነዚህን ነጥቦች ላንሳቸው፡፡

የፌዴሬሽኑ አቋም መቀየርኤፕሪል 17 ቀን 2004 የሱፐር ስፖርት ቴሌቪዥን ድረ-ገጽ

ስለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ያወጣውን ዘገባ ተመልከቱ፡፡ ተቋሙ ሰርቢያዊውን ጎራን ስቴፋኖቪችን ለመቅጠር ማሰቡን አስታኮ ፕሬዚዳንቱ አቶ ጁነዲን ባሻ ለድረ ገጹ በሰጡት ቃለምልልስ ላይ ባሬቶ ለከፍተኛው ስራ ተስማሚ ያልሆኑ አሰልጣኝ መሆናቸውን ከጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባገኙት መረጃ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል፡፡ አቶ ጁነዲን ፌዴሬሽኑ የባሬቶን የኋላ ስራ ህይወት በተመለከተ የራሱን ምርመራ ማድረጉን በገለጹበት ቃለምልልስ ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን እንዲመሩ ተቋማቸው ሊሾማቸው እንደማይችል ግልጽ ያደርጋል፡፡ አሁን ደርሶ ባሬቶ በሙገሳ የተሾሙበት ምክንያት ለእኔ ግልጽ አይደለም፡፡ በጋዜጣዊው መግለጫ ላይ ይህንን ጥያቄ ለአቶ ጁነዲን አቅርቤ የተሰጠው ምላሽ ያስተዛዝባል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በምክንያት ሃሳባቸውን ከማስረዳት ይልቅ ቃለምልልሱን በፍጹም እንዳልሰጡ ክደዋል፡፡ ሱፐር ስፖርት እርሳቸው ያልተናገተሩትን መጻፉን ጠቅሰው ሙግቱን አሳጥረዋል፡፡

ስራ ፈላጊው ባሬቶየማሪያኖ ባሬቶ የኋላ ታሪክ በተረጋጉና በውጤታማነት የታ

ጀቡ ቆይታዎች የተሞላ አይደለም፡፡ በጋና ከዘጠኝ ወራት በኋላ ያለስምምነት በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን ጥለው ወደ ሃገራቸው ገብተዋል፡፡ ባሬቶ በማክሰኞው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይህንን አልካዱም፡፡ የጋና ፌዴሬሽን አብረውት ሊሰሩ የማይመች መሆኑን

በመግለጽ ከርዕሰ ጉዳዩ ሊሸሹ ሞክረዋል፡፡ በወቅቱ ተከሰው ፊፋ ጥፋተኛ መሆናቸውን አረጋግጦ 83ሺ ዶላር ቀጥቷቸዋል፡፡ ቅጣቱን ከኪሳቸው መክፈላቸውን በይፋ አምነዋል፡፡ ከዚያ በኋላ በገቡባቸው ክለቦች ይህ ነው የሚባል የውጤታማነት ታሪክ የላቸውም፡፡ በማሪቲሞ ከአራት ወራት በላይ መስራት አልቻሉም፡፡ በአንጎላ ሊግ ለወራት ሰርተው በስምምነት ውላቸውን አፍርሰዋል፡፡ በሳኡዲ ዓረቢያ አልቃዲሲያ የስድስት ወር ደመወዝ አልተከፈለኝም በሚል ለቀዋል፡፡ በባህሬይን ሊግ በሃገሪቱ በተቀሰቀሰው ፖለቲካዊ ተቃውሞ ምክንያት እንዲሁ ከወራት በላይ መስ

ራት አልቻሉም፡፡ (የባህሬይኑ የእርሳቸው ጥፋት ላይሆን ይችላል) ወዘተ፡፡ ባሬቶ በ2013 ለጋና እንዲሁም ለደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች አሰልጣኝነት አመልክተው ተቀባይነት አላገኙም፡፡ በእነዚህ ነጥቦች መነሻ የኢትዮጵያን ማመልከቻ ሲያስገቡ ብዙ የስራ አማራጭ ኖሯቸው እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ ብዙ አማራጭ የሌለው አሰልጣኝ በአዲሱ ቀጣሪው የሚቀርቡለትን የስራ ቅጥር ቅድመ ሁኔታዎች ለመቀበል ያንገራግራል ብዬ አላስብም፡፡ በማመልከቻውና በድርድሩ ወቅት ባሬቶ ወኪል አልነበራቸውም፡፡ ራሳቸው አመልክተው፣ ራሳቸው በስካይፕ ተደራድረው፣ ራሳ

ቸው በመጨረሻዎቹ ድርድር ከፌዴሬሽኑ ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረው፣ ራሳቸው ውሉን ተፈራርመዋል፡፡ ባሬቶ እንደ አውሮፓዊያን አሰልጣኞች የፊርማ ክፍያ ቢጠይቁም ‹‹አይሆንም›› ስለተባሉ ያለፊርማ ክፍያ ለመቀጠር መስማማታቸው አቶ ጁነዲን ለሚድያው አባላት ነግረዋል፡፡ ለምሳሌ ቀደም ያሉት ዕጩ ጎራን ስቴፋኖቪች በ2006 በጋና ሲፈርሙ 200ሺህ ዩሮ ተከፍሏቸዋል፡፡ አዚህ ባሬቶ 10ሺህ ዶላር እንኳን አልተከፈላቸውም፡፡ በመሰል ዝውውሮች ላይ እንዲህ አይነቱ ውሳኔ የተለመደ አይደለም፡፡ ደረጃቸው ዝቅ ያሉ አሰልጣኞች እንኳን ቢያንስ ኮንትራቱ እንደተፈረመ የአንድ ወር ደመወዛቸው በፊርማ ክፍያ (Signing on Fee) ይከፈላቸዋል፡፡

የባሬቶ ቃልኪዳንበጋዜጣዊው መግለጫ ላይ ማሪያኖ ባሬቶ የመጡት ከዓለም

ምርጡ የእግር ኳስ አካዳሚ መሆኑን ነገሩን፡፡ የስፖርቲንግ ሊዝበን አካዳሚ ክሪስቲያኖ ሮናልዶን፣ ሉዊስ ናኒንና ሲማኦ ሳምብሮሳን የመሳሰሉ ተጫዋቾችን ማፍራቱን ገለጹ፡፡ የዓለም ምርጡ አካዳሚ በማንቸስተር፣ አርሰናል፣ ማድሪድ ሳይሆን በሊዝበን እንደሚገኝ ተናገሩ፡፡ ይህን ጊዜ ጣልቃ ገባሁና የስፖርቲንግ አካዳሚ ከላማሲያ፣ አያክስ፣ ናንት ያነሰ እንጂ የበለጠ የስኬት ታሪክ እንደሌላለው ጠቀስኩላቸው፡፡ በሙግት መንፈስ ሊቀበሉኝ አልቻሉም፡፡ አያክስ በ1995 እንዲሁም ባርሴሎና ከ2009-11 የአውሮፓ እግር ኳስን ሲቆጣጠሩ በአካዳሚዎቻቸው ምሩቃን የጀርባ አጥንትነት በገነቡት ቡድን መሆኑን ማን ያጣዋል? የስፖርቲንግ አካዳሚ ታላላቅ ተጫዋቾችን ቢያፈራም የእነዚህን አካዳሚዎች ያህል ስኬታማ ሆኖ ‹ከዓለም አንደኛ› የሚያስብል አይደለም፡፡ ባሬቶ በኃይለቃል ይህን ሲናገሩ ጋዜጠኞች በአውሮፓ እግር ኳስ ላይ ምንም ግንዛቤ የሌለን አድርገው የሚያስቡ አስመስሏቸዋል፡፡ ሙግታችን የትኛው አካዳሚ ‹ከዓለም አንደኛ› ነው የሚለው መሆኑ ሌላውን ጥያቄም ሊያስረሳን አይገባም፡፡ እውን ማሪያኖ ባሬቶ በስፖርቲንግ አካዳሚ ሰርተዋል? መስራታቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ይህንን ተከትሎም ጆዜ ሞውሪንሆን ለምክር ወደ አዲስ አበባ እንደሚያመጡ፣ ለዕድሜ ብሔራዊ ቡድኖች የሚመለመሉትን ተጫዋቾች በአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ካምፕ ውስጥ ለማስገባትና (ፖርቱጋላዊው... ወደ ገጽ 19 የዞረ)

የፖርቱጋላዊው የኢትዮጵያ አሰልጣኝ ሹመትና ያልተመለሱ ጥያቄዎች

ማንችስተር ዩናይትድ በአውሮፓም እጅ ሰጥቷል፡፡ በባየርን ሙኒክ ሲሰናበት ግን ሽንፈቱ የክብር እንጂ የውርደት አልነበረም፡፡ የዘንድሮውን የቡ

ድናቸው ሁኔታ ጠንቅቀው የሚያውቁት የክለቡ ደጋፊዎችም አስቀድመው ከዚህ የላቀ ነገር አልተመኙም፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት እንግሊዝን ሊግ በአሳማኝ ብርታት ያሸነፈው ቡድን ዘንድሮ ብዙ ድክመቶችን እያሳየ ቆይቶ የውድድር ዘመኑን ሊያጠናቅቅ ተቃርቧል፡፡

ዘንድሮ የሚፎካከርበት ምንም ዋንጫ ያልቀረለት ዩናይትድ አሁን ለከርሞው ለመዘጋጀት በቂ ዕድል ተፈጥሮለታል፡፡ የዝግጅቱ አንድ ስራ በክለቡ ሰፊ ለውጥ ማድረግ ነው፡፡ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በርካታ አዳዲስ ተጨዋቾች በቀዩ ማሊያ ሊታዩ እንደሚችሉ ሁሉ ከክለቡ ጋር በርካታ ስኬቶች ያገኙ ነባር ከዋክብትም ይሰናበታሉ፡፡ በ2014/15 የውድድር ዘመን በኦልድ ትራፎርድ አይታዩም ተብለው የሚታሰቡትን ተጨዋቾች እንደሚከተለው መቃኘት ይቻላል፡፡

የጀግኖቹ ስንብትየሪዮ ፈርዲናንድ፣ ኒማኒያ ቪዲች እና ፓትሪስ-ኤቭራ የ

ኋላ ክፍል ጥምረት ማንችስተር ዩናይትድን በእንግሊዝ ብቻ ሳይሆን በአውሮፓ ለተከታታይ ዓመታት ውጤታማ አድርጓል፡፡ ቪዲች ክረምቱ ሲመጣ ኦልድ ትራፎርድን እንደሚለቅቅ አረጋግጧል፡፡ ኤቭራም የመሰናበቱ ነገር አይቀሬ ይመስላል፡፡ ፈርዲናንድ አካሉ እንደሚገባ አልታዘዝ ካለው ቆይቷል፡፡ ቀድሞ ከአውሮፓ ድንቅ ተከላካዮች አንዱ የነበረው ኮከብ አሁን ፈጽሞ ራሱን አይመስልም፡፡

እነዚህን ሶስት ተጨዋቾች መተካት ቀላል አይሆንም፡፡ ተከላካዮቹ እርስ በርስ ከነበራቸው ድንቅ ውህደት እና አስገራሚ የመከላከል ችሎታ በተጨማሪ በሜዳ እና ከሜዳ ው

ጪ ቡድናቸውን የመምራት አቅም ነበራቸው፡፡ በቀደሙት ዓመታት ዩናይትድ የኤድዊን ቫን ደር ሳርን አገልግሎት ከማጣቱ በፊት በጋራ የፈጠሩት እጅግ ጠንካራ የኋላ ክፍል አሁን በዕድሜ ተፅዕኖ ቦታውን የመልቀቂያ ጊዜ መጥቷል፡፡ ሞዬስ የእነዚህን ተጨዋቾች ችሎታ የያዙ ፈራሚዎችን ብቻ ሳይሆን እነ ቪዲች ከቡድኑ የተከላካይ መስመር የሚያጎድሉትን የካበተ ልምድ የመተካት ከባድ ስራ ይጠብቃቸዋል፡፡

የመሀል አማካይ ክፍልበማንችስተር ዩናይትድ ለዓመታት ተገቢውን ትኩረት

ያላገኘው ክፍል ብለው የሚጠቅሱት አሉ፡፡በተለይ ከጃንዋሪ የሁዋን ማታ ከፍተኛ ዝውውር በፊት በክረምቱ ማርዋን ፌላይኒ ተገዝቶም የዩናይትድ የመሀከል ክፍል ደካማ ነበር፡፡ በእርግጥ የቤልጅየማዊው መምጣት የቡድኑን አማራጭ ጨመረ እንጂ የቡድኑን ጥራት ከፍ አላደረገውም፡፡ ማይክል ካሪክ የአምናውን ድንቅ ብቃቱን መልሶ ማግኘት አልቻለም፡፡ ሆኖም እንግሊዛዊው አሁንም ለቡድኑ በሚያበረክተው የሜዳ ላይ አስተዋፅኦ ከሌሎቹ አጣማሪዎቹ በእጅጉ የተሻለ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ካሪክ ለከርሞ ከቡድኑ ጋር አብረው እንደሚቆዩ ከሚታመንባቸው ተፈላጊ ተጨዋቾች አንዱ ነው፡፡

የዳረን ፍሌቸር እና ቶም ክሌቨርሊ ቆይታ አጠራጣሪ ቢሆንም ስኮትላንዳዊው ሙሉ ጤንነቱን መመለስ ከቻለ ማንቸስተር ዩናይትድን ለመርዳት በቂ ችሎታ እና ጠንካራ ልምድ አለው፡፡ በአንፃሩ ክሌቨርሊ ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት የበዛ ትችት ያስተናገደ እና በደጋፊዎች ዘንድም ተቀባይነቱን ያጣ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከእርሱ ድክመት የበለጠ ወጣቱ ዘንድሮ ለቡድኑ ውጤት ማጣት እንደ ሰበብ መነሳቱ እንደተጋነነ የሚያምኑ ትቂት አይደሉም፡፡

(ከኦልትራፎርድ... ወደ ገጽ 3 የዞረ)

ይህን አምድ ሊሊ ሞገስ ከአፕል ቫሊ ና እና ዳኒ ከሚኒያፖሊስ ያዘጋጁታል

ጥያቄ፡- በ2012 ዋንጫውን ስታሸንፉ ብቸኛ ተፎካካሪ የነበረው ማንቸስተር ዩናይትድ ነው፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን ግን ቼልሲ እና ሊቨርፑል ሁነኛ ተፎካካሪዎች ሆነው ቀርበዋል፡፡ የሊቨርፑል እዚህ ደረጃ መድረስ አስገርሞሃል?

መልስ፡- አስደናቂዎች ነበሩ፡፡ በሳምንት አንድ ጨዋታ ብቻ ማከናወናቸው የረዳቸው ይመስለኛል፡፡ ሁሌም ዝግጁ እና ፍሬሽ ነው፡፡ በሊቨርፑል ደረጃ ላሉ ተጨዋቾች አንድን ጨዋታ ለማከናወን ሳምንት ሙሉ ልምምድ ማድረግ ከፍተኛ ጥቅም አለው፡፡ እስከ መጨረሻዋ ቀን ፉክክሩ ጠንክሮ እንደሚቀጥልም አምናለሁ፡፡

ጥያቄ፡- ከሊቨርፑል ተጨዋቾች በተለየ መልኩ ቀልብህን የገዛው ማን ነው?

መልስ፡- በመከላከሉ ረገድ ጥሩዎች ቢሆኑም የአማካይ ክፍሉ የበለጠ ጠንካራ ነው፡፡ ስቲቭን ዤራርድ አስደናቂ የሆነና የካበተ ልምድ ያለው ተጨዋች ነው፡፡ ልዊስ ሱአሬዝ እና ዳንኤል ስተሪጅ ደግሞ ለማመን የሚያስቸግር ብቃት በማበርከት ላይ ናቸው፡፡ ጎሎችን የሚያስቆጥሩት እንደ ማሽን ነው፡፡

ጥያቄ፡- በቻምፒዮንስ ሊግ ለበርካታ ዓመታት ተመልክቼሃለሁ፡፡ ምርጥ የተከላካይ አማካይ ነበርክ፡፡ አሁን ደግሞ በርካታ ጎሎችን የሚያስቆጥር አማካይ ሆነሃል፡፡ የተቀየረው ምንድ ነው?

መልስ፡- ነገሩ የተጀመረው ቤልጅየም ሳለሁ ነው፡፡ በወቅቱ የተወሰኑ ስልጠናዎችን ለመውሰድ ወደ አርሰናል አምርቼ ነበር፡፡ ከአርሰን ቬንገር ጋር ያደረግኩትን የመጀመሪያ ውይይት አስታውሳለሁ፡፡ ያያ መጫወት የምትፈልገው በየትኛው ስፍራ ነው? ሲል ጠየቀኝ፡፡ አማካይ መሆን እንደምፈልግ ነገርኩትት፡ ‹ለምን? በልምምድ ላይ ስመለከትህ እኮ ከ

አማካይ ይልቅ የምትመስለው አጥቂ ነው› አለኝ፡፡ አሃ! በላይኛው የሜዳው ክፍል የምታጫውተኝ ለዚህ ነው፡፡ ወደ ኋላ መልሰኝ፡፡ መጫወት የምፈልገው እንደ ፓትሪክ ቪዬራ በአማካይ ስፍራ ነው፡፡ ከፓትሪክ የተሻልኩም እሆናለሁ አልኩት፡፡ ‹በፍፁም፡፡ ያ ሊሆን አይችልም፡፡ ማንም ከፓትሪክ አይበልጥም› አለን፡፡

ጥያቄ፡- አሁን ታዲያ ከእርሱ (ቪዬራ) የተሻልክ እንደሆንክ ታስባለህ?

መልስ፡- (ሳቅ) አይ፡፡ ቪዬራ ድንቅ ተጨዋች ነው፡፡ ያሸነፋቸው ሽልማቶች እና ዋንጫዎችም የሚመሰክሩት ያንን ነው፡፡ አርሰን በፊት መ

ስመር እንድጫወት የፈለገው በልምምድ ላይ ወደ ጎሉ ቀርቤ ስጫወት ወደ ጎል ከማደርጋቸው አምስት ሙከራዎች አራቱን አስቆጥር ስለነበር ነው፡፡ በእርግጥ መጥፎ የሚባል አልነበረም፡፡ እኔ ግን መጫወት የምፈልገው በአማካይ ስፍራ ነበር፡፡ ወደ ቤልጅየም ስመለስም አሰልጣኙ በፊት መስመር አሰለፈኝ፡፡ ጥሩ እና አስደሳች ነበር፡፡ ነገር ግን ከዚያ በኋላ ወደ አማካይ ስፍራ ተመለስኩ፡፡

ጥያቄ፡- ወደ ተጫዋችነት ዘመንህ ጅማሬ ልመልስህ፡፡ በታዳጊነትህ ወደ አውሮፓ ስትመጣ የእግርኳስ መጫወቻ ጫማ (ታኬታ) እንኳን አልነበረህም የሚባለው እውነት ነው?

መልስ፡- (ሳቅ…) አዎ፡፡ የ16 ዓመት ልጅ ሳለሁ የምጫወተው የአቢጃን ከተማ ክለብ ለሆነው ኤ.ኤስ.ኢ.ሲ ሚሞላስ (ASEC MIMOSAS) ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት በዚያ መገኘት

እና ራሴን ከእነርሱ ጋር ማነፃፀር አላማዬ ሆነ፡፡ አላማዬን ከግብ ለማድረስ ስልም ወደ ቤልጅየም አመራሁ፡፡ ለቤቬረን ዋናው ቡድንም ተሰልፌ መጫወት ጀመርኩ፡፡

ጥያቄ፡- ከዚያም ወደ ዩክሬን ተዘዋውረህ ተጫወትክ፡፡ ካደግክበት አፍሪካ ፍፁም የተለየ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም፡፡ ትክክል ነኝ?

መልስ፡- አዎን! ለሜታሉርህ ዶኔትስኪ ተጫውቻለሁ፡፡ አስገራሚ ተሞክሮም አግኝቼበታለሁ፡፡ ከአፍሪካ እንደ መምጣቴ እንዴት በአግባቡ መመገብ እንዳለብኝ፣ እንዴት ማረፍ እንዳለብኝ እና እንዴት ሀሳቤን መሰብሰብ እንደምችል መማር ጀመርኩ፡፡ እግርኳስን በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዴት መጫወት እንዳለብኝም ግንዛቤ ጨበጥኩ፡፡ በጥንቃቄ መዝናናት እንዳለብኝ አወቅኩ፡፡ እንደዚሁም እንደ ተጨዋች ብዙ እረፍት ማድረግ እንዳለብኝ እና ትኩረቴን ማጣት እንደሌለብኝ ተገነዘብኩ፡፡

ጥያቄ፡- ባልሳሳት ቀጥሎ ያመራኸው ወደ ግሪም ነው፡፡መልስ፡- አንድ የውድድር ዘመን በኦሊምፒያኮስ አሳልፌለሁ፡፡ ሁለ

ት ዋንጫዎችንም አሸንፌያለሁ፡፡ (ያያ... ወደ ገጽ 23 የዞረ)

እያደግን ነው! ሁለተኛ አስተማሪ እና ሁለተኛ ተሽከርካሪ በመንገድ

ላይ ነው! በቅርብ ቀን ለስራ ዝግጁ ይሆናል!ዲፓርትመንት ኦፍ ፓፕሊክ ሴፍቲ፣ መኪና መንዳት ከመጀመርዎ በፊት አስተማሪዎ ፍቃድ ያለው/ላት መሆኑን ማረጋገጥ እንዳለብዎት ያሳስባል።

“ካሽ እንጂ ቼክ አልቀበልም” “ፖሊስ ከጠየቀህ/ሽ ካዝኔ/ዘመዴ/ጓደኛዬ ነው በል/ዪ” ብሎ ካስጠነቀቀዎት፣ ህገ ወጥ አስተማሪ ነው/ች ማለት ነው።

ፍቃድ ሳይኖራቸው የሚያስተምሩ፣ግብር ሳይከፍሉ ገንዘብ የሚሰበስቡ ሰዎች ናቸው። ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ቢዝነስ ከሚሰራ ሰው ጋር

መተባበር በህግ ሊያስጠይቅ ይችላል። •የሚማሩበት መኪና ፍሬን፣ “የ ስቱደንት ድራይቨር”ማስታወቂያ፣

ከሌለው፣ ህገ-ወጥ አስተማሪ ነው ማለት ነው።

ከሁሉም በላይ፣ ፍቃድ (ላይሰንስ) ከማግኘት በላይ፣ ለህይወትዎ ቅድሚያ ይስጡ!

ማለዳ የመኪና መንዳት ት/ቤትአራት ጊዜ ወድቀው፣ 6 ሰአት ተምረው ሰርቲፊኬት

እንዲያቀርቡ ተጠይቀው ከሆነ ወደኛ ይምጡ። አስተምረን ማስረጃ እንሰጥዎታለን።

በፈለጉትን ቀን እና ሰዓት በ20 ደቂቃ ውስጥ ራሳችን ቀጠሮ አስይዘን እናስፈትናለን

የምናስተምረው ለፈተና ከማዘጋጀት በላይ ነው። ዋጋችን በከተማው ውስጥ ካሉ ት፤ቢትች

ሁሉ እጅግ በጣም ተመጣጣኝ ነው።

ስልክ ቁጥር፦ 612-203-3027

ከኦልትራፎርድ የሚባረሩ ተጫዋቾች ግምታዊ ትንታኔ

“መጫወት የምፈልገው እንደ ቪየራ ነው”

ያያ ቱሬ ይናገራል

Page 22: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 22

በሊሊ ሞገስ

የተስተካከለ የሰውነት አቋም ለመያዝ እና ሸንቀጥ ባለ ቁመና ለመታየት ከአመጋገብ በተጨማሪ የሰውነት እንቅስቃሴን ማድረግ ጠቃሚ እንደሆነ አሌ የሚባል ሀቅ አይደለም፡፡ ይህንን ስንል ለየትኛው ሰውነት ክፍል ምን አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለብን ልናውቅ ይገባል ማለት ነው፡፡

በተለይ ለሴቶች ሸንቀጥ ብሎ እና አምሮ መታየት ከዘመኑ ጋር እንደመራመድም ይቆጠራል፡፡ ለምሳሌ ያህል ቦርጭን ለማጥፋት መሰራት ያለባቸው የሰውነት እንቅስቃሴዎች በተለያየ መንገድ ከፋፍለን ልናያቸው እንችላለን፡፡

ለሆድ ከሚሰሩ የስፖርት አይነቶች ውስጥ አንዱ ወለል ላይ በጀርባ በመተኛት እግርን በቀስታ ወደ ላይ በማንሳት እንዲሁም በቀስታ ወደ ነበረበት በመመለስ የሚሰራ የስፖርት አይነት ሲሆን ይህም ለታችኛው የሆዳችን ክፍል የሚሰራ ነው፡፡ ይህ የስፖርት አይነት የሆዳችን ጡንቻ ለረዥም ጊዜ ተሰብስቦ እንዲቆይ ይረዳናል፡፡

ሌላኛው የሆድ ስፖርት አይነት ‹ሳይክል› የምንለው ሲሆን ይህንንም ለመስራት በጀርባችን በወለል ላይ በመተኛት ከዚያም አንደኛውን እግራችንን ወደ ላይ በማንሳት ሌላኛውን እግራችን በማጠፍ እና ወደ ደረታችን በማስጠጋት እየቀያየርን የምንሰራው የስፖርት አይነት ነው፡፡ ይህንን ስፖርት ቢያንስ ለአስር ጊዜ ያህል ደጋግመን መስራት ይኖርብናል፡፡

ከላይ ከገለፅናቸው የስፖርት አይነቶች በተጨማሪ በእንግሊዝኛው (Set up) የሚባለው የስፖርት አይነት ሌላው የሆድ ስፖርት ሲሆን ይህንንም ለመስራት በመጀመሪያ በጀርባችን መሬት ላይ እንተኛለን፡፡ በመቀጠልም ከወገባችን በላይ ያለውን የሰውነታችንን ክፍል ቀና በማድረግ እና እግራችንን እንደዚሁ ቀና በማድረግ የምንሰራው ስፖርት ነው፡፡ ይህም በቀጥታ ለሆድ የሚሰራ ስፖርት በመሆኑ ለውጡን በአጭር ጊዜ ማወቅ እንችላለን፡፡

ከእነዚህ የስፖርት አይነቶች በተጨማሪ ለሆድ እንዲሁም ለእግር የሚሰሩትን የስፖርት አይነቶች እንጨምርላችሁ፡፡

ለዚህ ከሚረዱ የስፖርት አይነቶች ውስጥ አንዱ በጎን በመተኛት እና እግርን በማንሳት የሚሰራ ሲሆን ይህን ስፖርት ለመስራት በመጀመሪያ በጎናችን በመተኛት እንዲሁም ግራ እጃችንን አጥፈን በመንተራስ እና የቀኝ እጃችንን ደግሞ በመሬት ላይ በማሳረፍ የሚሰራ ነው፡፡ እግራችንን እኩል ማነባበር ይኖርብናል፡፡

በመቀጠልም ሌላውን ሰውነታችንን ክፍል ሳናንቀሳቅስ በቀስታ የቀኝ እግራችንን እስከምንችለው ከፍታ ድረስ በማንሳት ለተወሰኑ ደቂቃዎች ባለበት አቆይተን በቀስታ መመለስ ነው፡፡

በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው እና ለሆድ እንዲሁም ለእግር

የሚሰራው የስፖርት አይነት በእንግሊዝኛው ክላምሼል የምንለው ሲሆን ይህ የስፖርት አይነት የሚሰራው እንደ መጀመሪያው የስፖርት አይነት በጎናችን በመተኛት ቀጥሎም ጉልበታችንን 45 ዲግሪ በማጠፍ ሲሆን የቀኝ እግራችንን የግራ እግራችን ላይ በማነባበር የሚሰራ ነው፡፡ በመቀጠልም የግራ እግራችንን ባለበት ሆኖ የቀኝ እግራችንን በቀስታ እስመክንችለው ከፍታ ድረስ ከፍ በማድረግ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ማቆየትና ወደ ቦታው በቀስታ በመመለስ የሚሰራ የስፖርት አይነት ነው፡፡ ይህንን በድጋሚ በቀኝ ጎናችን በመተኛት መድገም እንችላለን፡፡

ሶስተኛው የስፖርት አይነት ደግሞ ሂፕ ሬስ ወይም በዳሌ አካባቢ የሚሰራ ስፖርት ሲሆን ይህንንም ለመስራት በመጀመሪያ በወለል ላይ በጀርባችን በመተኛት በመቀጠልም ጉልበታችንን እኩል በማጠፍና በመዘርጋት የሚሰራ ስፖርት ነው፡፡

በመቀጠልም ከትከሻችን እስከ ጉልበታችን ድረስ ያለውን አካላችንን በቀስታ ከፍ በማድረግ ቀጥ ያለ መስመር በመስራት ለተወሰኑ ደቂቃዎች መቆየትና ቀስ ብለን ወደ ቦታችን በመመለስ ይህንኑ በተደጋጋሚ መስራት፡፡ በአራተኛ ደረጃ የተቀመጠው የሆድ ስፖርት አይነት ክሮስ ቦዲ ማውንቴን ክላይምበር (Cross body moun-tain climber) ሲሆን ይህንን ስፖርት ለመስራት በመጀመሪያ ሁለቱ እጆቻችንን መሬት ላይ በማሳረፍ ቀጥሎም እግራችንን ወደኋላ በመዘርጋት ቀጥ አድርገን ፑሽ አፕ በምንለው የስፖርት አይነት ሰውነታችንን በማዘጋጀት እጃችን ካለበት ሳይንቀሳቀስ የቀኝ ጉልበታችንን በማጠፍ ወደ ግራ ትከሻችን በማስጠጋት እንዲሁም የቀኝ እግራችንን ወደ ቦታው በመመለስ የግራ ጉልበታችንን በማጠፍ ወ

ደ ቀኝ ትከሻችን ማስጠጋት ይኖርብናል፡፡ ይህንንም በተደጋጋሚ መስራት ይኖርብናል፡፡

ከላይ የዘረዘርናቸው የስፖርት አይነቶች በተደጋጋሚ እና በአንድ ጊዜ እየቀያየርን መስራት የምንችላቸው ስፖርት አይነቶች ሲሆኑ በአጭር ጊዜ ለውጥ ልናገኝባቸው እንችላለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቀለል ያሉ እና በየትኛውም ቦታ ልንሰራቸው የምንችላቸው ስፖርቶች ስለሆኑ በተከታታይ ሳናቋርጥ መከወን ይኖርብናል ሲል ውመንስ ሄልዝ የተባለው መፅሔት ያሳስባል፡፡

የሴቶች ጤና/Womens Health

ሸንቀጥ ማለት ትፈልጊያለሽ?

ሁሉ ነገር በአንድ ላይ የሚገኝበት የኢትዮጵያውያን የገበያ ማዕክል ከጥሩ ፈገግታ ጋር እንቀበልዎታለን

የሚደነዝዘኝ... ከገጽ 8 የዞረሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ - ሌሎችም ብዙም ያልተለመዱ ልዩ ልዩ በሽታዎች ችግሩን

ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡- ይሁንና አንዳንዴ በተለያዩ ምርመራዎች እነዚህም ሆኑ ሌሎች መንስኤዎች ስለመኖራቸው ላይረጋገጥና ትክክለኛው መንስኤ ላይደርስበት ይችላል፡፡ እንዲህ አይነቱ መንስኤ በህክምናው አጠራር ኢዲዮፓቲክ ተብሎ ይታወቃል፡፡ መንስኤው ያልታወቀ እንደማለት ነው፡፡

ምርመራዎቹስ ምን ምን ናቸው?ምርመራዎቹ እንደየመንስኤው ሊለያዩ ይችላሉ፡፡ ይሁንና በ

ሽታው ከተከሰተ ‹‹Peripheral Neuropathy›› መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የሚረዱ ምርመራዎች አሉ፡፡ እነርሱም፡-

ኤሌክትሮማዮግራም፡- የጡንቻዎቻችን የመኮማተርና የእንቅስቃሴ ፍጥነትና ምጣኔን የሚያሳይ ምርመራ እና የሚሰሩ ነርቮችን መለየት፡- እነዚህን ጡንቻዎች ለማንቀሳቀስ የሚረዱት ነርቮች በትክክል መስራት አለመስራታቸውን ለማወቅ የሚያስችል ምርመራ ናቸው፡፡

ህክምናውስ ምንድነው?ፐሪፐራል ኒውሮፓዚ (Pheripheral Neuropathy) ሙሉ

ለሙሉ ለመፈወስ አደጋች ከሆኑ የጤና ችገሮች አንዱ ነው፡፡ ይሁንና ምንም አይነት መፍት ወይም ህክምና የለውም ማለት አይደለም፡፡ ህክምናውም ሆነ የህክምናው ውጤት በዋነኝነት በመንስኤው ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ዋና ዋናዎቹ መፍትሄዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡ - አስቀድሞ መከላከል፡- የመጀመሪያውና አዋጪው መፍትሄ ችግሩ ከመከሰቱ በፊት አጋላጭ ሁኔታዎችን ለይቶ በማወቅ መከላከል ነው፡፡ ለምሳሌ አልኮልን፣ የምግብ እጥረትን፣ አንዳንድ ከላይ የተጠቀሱት ኢንፌክሽኖችን፣ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን የመሳሰሉትን ቀድሞ ማስወገድና መከላከል ይቻላ

ል፡፡ የስኳር በሽታንም ቢሆን ተገቢውን ህክምናና ክትትል በማድረግ የሚያስከትላቸውን ችግሮች ቢያንስ ማዘግየት ይቻላል፡፡

- መንስኤውን ማከም፡- መከላከሉ ካልተቻለና መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ በሽታዎች ከተከሰቱና ችግሩን ካስከተሉ ደግሞ መሰረታዊውን መንስኤ ማከም እጅግ ጠቃሚ ህክምና ነው፡፡

- የህመም ማስታገሻዎችን መውሰድ፡- ህመሙን ለማስታገስ የተለያዩ ማስታገሻ መድሃኒቶች ይሰጣሉ፡፡ የማስታገስ ኃይላቸውም እደየመድሃኒቶቹና በሽታው ይለያያል፡፡ በተለምዶ ለማንኛውም ቀለል ያለ ህመም ከሚሰጡት ማስታገሻ መድሃኒቶች ጀምሮ ጠንከር እስካሉ የነርቭ መድሃኒቶች ድረስ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ በተለይም ልክ ስኳርን ተከትሎ እንደሚከሰተው አይነት የነርቭ ህመም ጠንከር ያለ ከሆነ ትራይሳይክሊክ አንቲዲፕረሳንትስ የተባሉ መድሃኒቶችን ለሚጥል በሽታ የሚሰጡት መድሃኒቶች ሊወሰዱ ይገባል፡፡ - ‹‹ፊዚዮቴራፒ›› እና ቀዶ ህክምና፡- ከዚህ ባለፈም ነርቩን ተጭኖ ከላይ የተጠቀሰውን አይነት ችግር ከተከሰተ በቀላል ቀዶ ህክምና ሊድን ይችላል፡፡ አንዳንዴ በመርፌ በሚሰጡ መድሃኒቶች ማከምም ይቻላል፡፡ ከነርቩ መጎዳት ጋር በተያያዘ የእጅግ እግር መዛል ከተከሰተም በማሸት የማቃቃት ‹‹ፊዚዮቴራፒ›› መስጠትም አንዱ የህክምና ዘዴ ነው፡፡

እንግዲህ ውድ ጠያቂያችን እርስዎም ይህንን ካነበቡ በኋላ የችግርዎን መሰረታዊ መንስኤና መፍትሄውን ለማወቅ ወደ ተገቢው ባለሙያ በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራራ ክትትልና ህክምና እንደሚያደርጉ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ በተለይም የስኳር በሽታ እንዲህ አይነቱን ችግር በማስከተል ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛልና ተመርምሮ ራስን ማወቁ አይከፋም!

ለራስ... ከገጽ 16 የዞረየሚገኙ ሲሆን በአንፃራዊነት ጥሩ ውጤት ካስገኙት መካከ

ል ጥቂቶቹን አነሳሳን እንጂ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡ በዋነኛነት ባለሞ

ያዎች የሚመክሩት ራስ ምታቱን ከማስታገስ ባለፈ ዋናውን የራስ ምታት ምንጭ ፈልጎ መፍትሄ መስጠቱ ላይ ነው፡፡ እንደ ድርቀት፣ ውጥረት፣ ከፍተኛ ድካም መሰል ከስራ እና ማህበራዊ ምክንያቶች መነሻነት የሚመጣውን ራስ ምታት ከክኒን ይልቅ በተፈጥሮ መፍትሄዎች ማስታገስ ቢመከርም ከሰውነት የውስጥ በሽታዎች ምክንያት የሚነሳን ራስ ምታት ግን ምንጩን ካልታከሙት ማስታገስ ይከብዳል፡፡ አልፎ አልፎ ለሚከሰት ራስ ምታት ያነሳሳናቸው አይነት የቤት ውስጥ ቀላል መፍትሄዎች ጥሩ ናቸው፡፡ ተደጋጋሚ ራስ ምታት ግን የባለሞያ እርዳታን ይሻልና ቸል አይበሉት ይላሉ ባለሞያዎቹ፡፡ ራስ ምታት ይደጋግመኛል ስትል ሃሳቧን በመግቢያችን ያጫወተችኝ ማህሌት ከዚህ ምክር ሳትመደብ ትቀራለች ሰላም!

ኦልትራፎርድ...(ከገጽ 14 የዞረ) የሚጀምረው በዚህ ቦታ እንደሚሆን መናገር ይቻላል፡፡ ኮ

ንትራቱን በቅርቡ ካራዘመው እና በቀጣይ ክለቡን ለዓመታት የማገልገል አቅም ከያዘው ሩኒ ይልቅ ቫን ፔርሲ በክረምቱ ድንገት ሊሰናበት ይችላል፡፡

ዳኒ ዌልቤክ እና ሀቪዬር ሄርናንዴዝ የቋሚ ተሰላፊነትን ዕድል ለማግኘት ብዙ ቢመኝም እስካሁን ብዙ ጨዋታዎችን እያደረጉ ያሉት ከተጠባባቂ ወንበር በመነሳት ነው፡፡ ዌልቤክ እንደ አስፈላጊነቱ ከክንፍ እየተነሳ ማጥቃት ቢችልም ቺቻሪቶ እንደ ጎል ጨራሽነቱ ከፊት መስመር ሌላ ሚና መውሰድ አይችልም፡፡ ማክሲኳዊው በኦልድ ትራፎድ በዋና ቡድኑ ድንቅ ብቃት ማሳየት የጀመረው የዛሬ ሶስት ዓመታት ቢሆንም እስካሁን ቋሚ ተሰላፊ አይደለም፡፡ እንዲያውም በሞዬስ ስር የሚሳተፍባቸው ጨዋታዎች ብዛት ቀንሶበት ነበር፡፡

ፊቴ ላይ የመጨማደድ

ምልክትበማየቴ ጨንቆኛል

የአርባ አምስት ዓመት ሴት ነኝ፡፡ ፊቴ ላይ የመጨማደድ ምልክት እያየሁ ሲሆን ያለ ጊዜው የመጣ ስለመሰለኝ ያስጨንቀኛል፡፡ ባለቤቴና ልጆቼ እያጋነንሽ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ የእርጅና ምልክት በመሆኑ ምንም ላደርገው እንደማልችልና እንደሌለብኝ ይነግሩኛል፡፡ እኔ ግን ከፍተኛ የሆነ ሀሳብ ገብቶኛል፡፡ ምን ይሻለኛል?

/ሙ.አ/የተከበርሽ ሙአ-42 ዓመት ሴት መሆን ይዞልን የሚመጣው

የአዕምሮ ብስለትና ፀጋ እንዲህ ነው ብዬ ልጨርስ አልችልም፡፡ የዕድሜ መጨመር በባህና በእውቀት ባሻገር የሰውነት ለውጦች ያሳያል፡፡ እነኚህ ለውጦች መሃል በተለይም የፊት ቆዳ መስመር ማውጣት ሲሆን እኔ በግሌ የህይወት ጉዞ ውበቶች እላቸዋለሁ፡፡

የዕድሜ መጨመር የፊት መስመር ምልክቶች እርግጥም መጀመሩን ለማረጋገጥ በፊታችን የሚታዩትን ለውጦች ማጤን ሊረዳ ይችላል ለምሳሌ፡-

- ቆዳ ሻካራ የመሆን ባህሪ ማሳየት- ቆዳ ላይ እንደትንንሽ እብጠቶች በብዛት መከሰት- ቆዳ የላስቲክነት ባህሪ የሚሰጠውን ‹‹ኢላስቲክ ቲሺውን›› ስ

ለሚያጣ መላላትን ማሳየት፡፡ - ቆዳ ቶሎ የመቆጣት ባህሪ ያመጣለ፡፡ እነዚህ ምልክቶች ሊያ

ስጨንቁሽ ሆነ ችላ ልትዪው ይገባል ብዬ አላምንም፤፤ አዲስ ህፃን ልጅን ቆዳው እንዳይበላሽ ሆነ በቀላሉ እንዳይጎዳ

እንደምንንከባከበው ሁሉ በወጣትነትም ሆነ በማደግ ላይ ቢሆንም ለቆዳችን የምንሰጠው ትኩረት መቀነስ የለበትም፡፡ የአርባ ሁለት ዓመት ቆዳ መስመር ማውጣቱ የሚያስበረግግ ባይሆንም ተቀብሎ ቁጭ ማለትም የሚያዝናና ነገር አይደለም፡፡ በመሆኑም እነዚህን መሰረታዊ ነገሮች ብትከተይ፡፡

- አመጋገብሽን ማስተካከል (የተመጣጠነ ምግብ መመገብ)- የዘር ሁኔታን ማጥናት (በዘር ቶሎ የማርጀትና የቆዳ ለውጥ

የሚይ ከሆነ ቶሎ ልዩ ጥንቃቄ መውሰድ)- ማጨስ ለቆዳ መጨማደድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስለሚያደር

ግ የምታጨሺ ከሆነ ለማቆም መወሰን- ለፀሐይ በብዛት አለመጋለጥ- ጭንቀትን ለማስወገድ ሞክሪ- የፊት ቆዳ ወደታች የመሳብ ባህሪ ስለሚኖረው ወደ ላይ ለስ

ለስ ባለ መልኩ በክሬም ማሸት- የፊት እንቅስቃሴን በመስራት የፊት ጡንቻን ማጠናከር- ክብደት መቆጣጠር- እንቅልፍ በበቂ ማግኘትና በእንቅልፍ ሰዓት ላይ ፊትን ትራ

ስ ላይ እያሻሹ አለማንገላታት (ትክክለኛ ያልሆነ አስተኛኘት ለቆዳ ቶሎ መጨማደድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል)

- በሙቅ ውሃ መታጠብ፣ ሳሙና በብዛት መጠቀም ድርቀት ስለሚጨምርና የቆዳ መድረቅ ለመስመር ቶሎ መታየት ምክንያት ስለሚሆን ከእነዚህ ነገሮች ጋር ያለንን ግንኙነት መቀነስ ይመከራል፡፡

Page 23: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 23

የደናግላን... ከገጽ 9 የዞረእንዲታዩ አድርጓቸዋል›› ብለዋል- ሳይኮሎጂስቱ፡፡ ድንግልናቸውን ለሽያጭ ያቀረቡ ልጃገረዶችን ማንሳት ይቻ

ላል፡፡ በ2004 ዓ.ም የብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ (እንግሊዝ) ተማሪ የሆነች ግብረሰዶማዊት (Lesbian) ልጃገረድ በኢንተርኔት አማካኝነት ድንግሏን በ8,400 ፓውንድ መሸጧ ተነግሯል፡፡ የለንደን ከተማ ነዋሪና የ18 ዓመት ወጣቷ ሮዚ ሬይድ የ44 ዓመት ጎልማሳ ለሆነ ኢንጂነር ሂውስተን ሆቴል የመኝታ ክፍል ውስጥ ድንግሏን ሸጣለት እንደተኛችው ታውቋል፡፡ በ2008 ዓ.ም ኢጣሊያዊቷ የ28 ዓመት ሞዴሊስት ራፋኤል ፈቶ ድንግልናዋን በ1 ሚሊዮን ዩሮ ለጨረታ አቅርባለች፡፡ በዚሁ ዓመት የታሊ ዋይሊን በሚል ተለዋጭ ስም ራሷን የጠራች አሜሪካዊት ኒቫን ግዛት (State) በሚገኝ አንድ የዝሙት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት (Brothel) አማካኝነት ድንግሏን ለጨረታ አብቅታለች፡፡

ለድንግልና ከፍተኛ ዋጋ (ክብር) የሚሰጡ ማህበረሰቦች ከጋብቻ በፊት ግብረ ስጋ ግንኙነትን ያላካተተ በርካታ ወሲባዊ ተግባራትን እንደሚፈፅሙ አረጋግጠዋል፡፡ ለምሳሌ በአፍ ንክኪ (መጥባት፣ መላስ) እና ወንድና ሴት በጋራ ሆነው የማሸት (ሴጋ) ወሲብን ይፈጽማሉ፡፡ ይህ አይነቱ ወሲባዊ እንቅስቃሴ የሴትን ብልት የማይጠልቅ በመሆኑ ‹‹ቴክኒካዊ ድንግልና›› (technical virgin-ity) ተብሎ ይጠራል፡፡ በ1999 ዓ.ም በ29 የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ በ599 የኮሌጅ ተማሪዎች ላይ ወሲባዊ ጥናት ያደረገው የአሜሪካ ሜዲካል አሶሴሽን (ማህበር) ባወጣው ዘገባ መሰረት ዕድሜያቸው በአስራዎቹ ውስጥ በሚገኙ ወጣቶች ዘንድ ‹‹ቴክኒካዊ ድንግልና›› እጅግ ተወዳጅ እየሆነ መምጣቱን አሳውቋል፡፡

በተለይም የሴቷን ብልት በወንዱ ብልት በመንካት የሚደረግ ወሲባዊ ግንኙነት ‹‹የደረጃ ለውጥ›› ወይንም የማይመለስ የድንግልና ማጣት ተደርጎ የሚወሰድበት አንትሮፖሎጂካዊ ምክንያቶች እንዳሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡

የስነ ልቦና ባለሙያው አቶ ዳንኤል ‹‹ቴክኒካዊ ድንግልና››ን ከነፃነት ማጣት ሰቀቀን ጋር አያይዘው ይመለከቱታል፡፡ ወሲባዊ ነፃነትና ግልፅነት ጨርሶ በጠፋበት ሁኔታ ልጃገረዶች በወላጆች ነፃነትና አስተምህሮ ውስጥ ክፉ ደጉን እንዲለዩ ማድረግ እንጂ ድብብቆሽ አካሄድ የተዘዋዋሪ ቀዳዳ ሊከፍት ይችላል ብለው ያስባሉ፡፡ ከላይ የጠቀስኩት ጥናት የሚያሳየውም ይሄንኑ ነው፡፡ ወጣት ልጃገረዶች ድንግልናቸውን በራሳቸው ጨዋነትና ጥንካሬ እንዲያቆዩት ከማድረግና ከማስተማር ይልቅ ድፍን ባለ ግለሰባዊ ወይም ቡድናዊ አመለካከት ተጠፍሮ እንዲቆይ ማስጨነቁ ወጣቶቹን ቤተሰብ አክባሪ ያደረጋቸው ቢሆን እንኳ ስነ ልቦናዊ ጫናው (Physiological impact) ወደ ቴክኒካዊ ድንግልና አሻግሯቸዋል፡፡

የ2001 የሚስርጂን አዲስ አበባ አሸናፊ የሆነችው ኤልሳቤጥ ያሬድ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ትሆናለች፡፡ ኤልሳቤጥ ያሬድ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ትሆናለች፡፡ ኤልሳቤጥ እንደነገረችን በቤተሰብ ውስጥ ፍፁም ነፃነት አላት፡፡ ቤተሰቦቿ ለዚህ ለመብቃቷ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳበረከቱላት አልሸሸገችም፡፡ ‹‹በቤተሰብ ውስጥ ያለው ግልፅነትና ውይይት ነሮችን እንዳውቅና ራሴን በደስተኝነት እንድጠብቅ አድርጎኛል›› ትላለች- ኤልሳ፡፡

ኤልሳ በትምህርት ቤት ውስጥ ጓደኞቿ ራሷን እንደሚመስሉም ትናገራለች፡፡ ሰው ማንን ይመስላል ሰብዕና ያላቸው ጓደኞች ብቻ ሳይሆን የወንድ ጓደኛ ያላቸው ሴቶችንም ትጎዳኛለች፡፡ ‹‹መወስወስና መሳብ ግን የለም›› ትላለች- ለራሷ የሰጠችውን የላቀ ግምት በንግግሯ እየገለፀች፡፡

ድንግልናን ማጣትድንግልናን ማጣት በብዙ ባህሎች ውስጥ ወሳኝ የሆነ የህይ

ወት ሽግግር ተደርጎ የሚወሰድ የመጀመሪያው ወሲባዊ ተሞክሮ ነው፡፡ በአብዛኛው የአንዲት ልጃገረድ ድንግል በወንድ ብልት የሚወሰድ (የሚቀደድ) መሆኑ ቢታወቅም የህክምና ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ግን አንዲት ልጃገረድ ብስክሌት በመንዳት፣

በፈረስ ግልቢያና በጅምናስቲክ እንቅስቃሴም ድንግልናዋን ልታጣ ትችላለች፡፡

በአንዳንድ ሴቶች ላይም ከተለመደው ውጭ የሆነ የብልት ሽፋን (ድንግል) ይከሰታል፡፡ ይህም በተፈጥሮ በጣም ጠንካራ በቀላሉ የማይቀደድ ከመሆኑም ሌላ የወር አበባን መውጫ በመዝጋት ህመም ስለሚያስከትል ይህንን ችግር ለማስወገድ ቀላል የቀዶ ጥገና ህክምና ያስፈልጋል፡፡

የድንግልና ነገር ባህላዊ ስነ ልቦናዊና አንትሮፖሎጂካዊ ግንኙነት እንዳሉት ይታወቃል፡፡ የባህል ተመራማሪዎች እንዳረጋገጡት የተለያዩ ማህብረተሰቦች ውስጥ በፍቅር፣ በወሲብና በድንግል ላይ የተመሰረቱ ‹‹ቅናቶች›› ዓለም አቀፉ የሰው ልጅ መገለጫዎች ናቸው፡፡

ከስነ ልቦና አኳያ በ1985 ዓ.ም በአሜሪካ የተደረገ ጥናት እንዳሳየው ከጋብቻ በፊት ወሲብ የፈፀሙ ሴቶች ብዙዎቹ የትዳር መፍረስ አደጋ እንዳደረሰባቸው ታውቋል፡፡ ድንግልናን እስከ ጋብቻ ድረስ መጠበቅ የጥሩ አስተዳደግና የጨዋነት ምልክት ተደርጎ በሚወሰድበት ማህበረሰብ ውስጥም ከጋብቻ በፊት ወሲባዊ ተራክቦን የፈፀሙ ሴቶች ከድንግሎች የበለጠ ለትዳር መፍረስ የተጋለጡ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

የፊት መስመሩን ዳግም ክሎዘ ይመራዋል፡፡ አጋጣሚውም ከገርድ ሙለር ጋር በጋራ የያዙትን የምንጊዜውም የጀርመን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ሪከርድ ለማሻሻል ጥሩ ዕድል ይፈጥርለታል፡፡ ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች በተለይ ደግሞ በባየርን ለሚጫወቱት የውድድር ዘመኑ ረጅም ነው፡፡ በመጪው ክረምት ደግሞ አጓጊው ፈተና ይጠብቃቸዋል፡፡ የዓለም ዋንጫው በጉጉት እየተጠበቀ ነው፡፡ ተጫዋቾችም ዋንጫውን እያለሙ በሙሉ ጤንነት እና ብቃት ሊቆዩ ይገባል፡፡

ያያ... ከገጽ 21 የዞረጥሩ ዓመት ነበር፡፡ አጋጣሚው ከሪቫልዶ ጋር የምጫወትበ

ት ዕድል ፈጥሮልኛል፡፡ ብራዚላዊው በርካታ ነገሮችን አስተምሮኛል፡፡ ወደ ባርሴሎና ባመራሁበት ወቅትም ልበ ሙሉ እንድሆን እና በራስ መተማመኔ ብርቱ እንዲሆን አድርጓል፡፡ ያን ዓመት የግሪክን ሊግ እና ጥሎ ማለፉን አሸነፍን፡፡

ጥያቄ፡- ከግሪክ ስኬትህ በኋላ አንድ የውድደር ዘመን በሞናኮ አሳለፍክ፡፡ በመቀጠልም ትልቁን ዝውውር በማድረግ ወደ ባርሴሎና አመራህ፡፡ ከዚያም ከሊዮኔል ሜሲ፣ ዣቪ ሄርናንዴዝ እና አንድሬ ኢንዬሽታ ጋር መጫወት ጀመርክ፡፡ ከእንደእነዚህ አይነት ተጨዋቾች ጋር መስራት ምን አይነት ስሜት ይፈጥራል?

መልስ፡- የማይታመን ነበር፡፡ በክለቡ ባሳለፍኩት ሁለተኛ ዓመት ላይ ስድስት ዋንጫዎችን አሸነፍኩ፡፡ ከሞናኮ ለመጣ አፍሪካዊ ተጨዋች አስደናቂ ስኬት ነበር፡፡ በወቅቱ ከትንሽ ክለብ የመጣ ብቸኛው ተጨዋች እኔ ነበርኩ፡፡ ነገር ግን ለጨዋታ እንዴት መዘጋጀት እንዳለብኝ እና ፕሮፌሽናል ተጨዋች መሆን ምን ማለት እንደሆነ ተማር፡፡ ከዚያን ጊዜ በኋላ ወደ ልምምድ የማመራው አንድ ወይም ሁለት ሰዓት ቀደም ብዬ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ለእኔ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

ጥያቄ፡- ከጥቂት ሳምንታት በፊት ዳግመኛ ሊያስፈርመው የሚፈልገው ተጨዋች አንተ መሆንህን ባርሴሎና መናገሩን አንብቤያለሁ፡፡ በዚህ ላይ ምን አስተያየት አለህ?

መልስ፡- (ሳቅ) ይወድዱኝ እንደነበር አውቃለሁ፡፡ ባርሴሎናን ለመልቀቅም ተቸግሬ ነበር፡፡ ፔፕ ጋርዲዮላም እንደሚፈልገኝ ነግሮኝ ነበርር፡ ነገር ግን ክለቡን ለመልቀቅ ትክክለኛው ጊዜ ላይ እንደምገኝ አውቀው ነበር፡፡ በወቅቱ 27 ዓመቴ ነበርር፡ ወደ ሌላ ቦታ አምርቼ ለመጫወት መሞከር ነበረብኝ፡፡ ወደ እንግሊዝ መጥቼ ከትልልቅ ቡድኖች ጋር ዋንጫዎችን ማንሳት እፈልግ ነበር፡፡

ጥያቄ፡- ባለፈው ወር በቻምፒዮንስ ሊጉ በባርሴሎና ተሸነፋችሁ፡፡ ሲቲ የአውሮፓ ሻምፒዮን ለመሆን የሚያስችለውን እርምጃ የሚወስደው እንዴት ነው? (ያያ... ወደ ገጽ 10 የዞረ)

Page 24: ሚያዝያ 2006 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 62 ዕውነት ያሸንፋል ሚኒሶታ ንቃ · Ze-Habesha Newspaper April 2014 No. 62 612-226-8326 Voice of Ethio-Americans

April 2014 I volume VI I No. 62 ሚያዝያ 2006 I ቅጽ VI I ቁጥር. 62 Page ገጽ 24

በሥራ ቦታዎ አደጋ፣ የመኪና አደጋና የስፖርት ጉዳት ከደረሰብዎት እና ካጋጠመዎ እውቅ ካይሮፕራክተር

ከፈለጉ ወደ ካይሮፕራክቲክ ክሊኒካችን ይምጡ

እርሶ የሺ እንጀራን ካልቀመሱ ደንበኞቻችንን ለምን እንደሚመገቡት ይጠይቋቸው፤

የኛ የጥራት ምስክሮቻችን ደንበኞቻችን ናቸው