40
ኩር ለህብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን! 22ኛ ዓመት ቁጥር 26 ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም ዕትም ዋጋ 2 ብር ገጽ 9 ገጽ 40 - ውለታ ቢስ ትውልድ - ጣና ያፈራቸው ገጽ 23 ገጽ 7 ገጽ 11 - ፀደቀ - ለእናት እና ልጅ ሁሉም እጅ ለእጅ - የማስታወቂያ ባለቤቱ ማን ነው? ገጽ 18 - ትኩረት - ትኩረት ለሚሹት ሱራፌል ስንታየሁ ሙሉ አብይ ስርጭቱን በናይል ሳት ወደ ገጽ 20 ዞሯል ገጽ - 5 በውስጥ ገፆች ደረጀ አምባው ወደ ገጽ 20 ዞሯል ወደ ገጽ 20 ዞሯል ) Frequency- 12341 ) Symbol rate - 27500 ) FEC- 3/4 ) Polarization horizontal መከታተል ይችላሉ:: “የወረቀት ‘ምሁራን’ እየተፈለፈሉ ነው!” ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር የቆየዓለም ደሌ ኢትዮጵያ በአቦካዶ ምርት የአውሮፓን ገበያ መቆጣጠር ትችላለች ነዋሪዎች በመሠረተ ልማት ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ገለፁ ሴቶች “አልችልም” ከሚል አመለካከት መላቀቅ አለባቸው ተባለ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የደሃና ወረዳ ነዋሪዎች በመሠረተ ልማት አቅርቦት ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ገለፁ:: የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ከደሃና ወረዳ አስተዳደር ጋር በመተባበር ህብረተሰቡን የወረዳው አመራሮች ፊት ለፊት አገናኝቶ በመልካም አስተዳደር ዙሪያ አወያይቷል:: ግንቦት 14 ቀን 2008 ዓ.ም አምደ ወርቅ ከተማ በእነለጋ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የደሃና ወረዳ ነዋሪዎች “ወረዳዋ በመሠረተ ልማት ተጠቃሚ ባለመሆኗ ኢትዮጵያ ያላትን ምቹ የአየር ንብረትና የግብርና ኤክስቴንሽን ስልት ተጠቅማ አቦካዶን በስፋት ብታመርት የአውሮፓን ገበያ መቆጣጠር የሚያስችል አቅም እንዳላት ተገለፀ:: ሰሞኑን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የዘርፉ ባለሙያዎች በሜጫ ወረዳ አቦካዶ እያመረቱ ወደ አውሮፓ ገበያ ለማቅረብ እንቅስቃሴ ላይ ያሉ ግለሰቦችና ቀበሌዎችን ተሞክሮ ተዘዋውረው ጐብኝተዋል:: በኢትዮጵያ ስድስት ክልሎች በተመረጡ ወረዳዎች ከ10 ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የአቦካዶ ምርት እንዲስፋፋ እያደረገ ያለው የ’ማሻቩ’ ፕሮጀክት አስተባባሪ እስራኤላዊው ሚስተር ኦፈር ካህን እንዳሉት ኢትዮጵያ ያላት ምቹ የአየር ንብረትና የምትከተለው የግብርና ኤክስቴንሽን ዘዴ አንድን ሴቶች ባለፉት 25 አመታት ያገኙትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማስቀጠል “አልችልም” ከሚለው ኋላ ቀር አመለካከት ራሳቸውን ማላቀቅ እንዳለባቸው ተገለፀ:: ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ሴቶች የግንቦት 20ን የብር ኢዮበልዩ በዓል አክብረዋል:: በዚህ ጊዜ በአማራ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ወጣቶችና ህጻናት ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሉባባ ኢብራሂም እንደተናገሩት ባለፉት 25 ዓመታት ሴቶች ከጓዳ ወጥተው በፖለቲካው፣ በትምህርቱ፣ በጤናው፣ በልማቱ፣… ዘርፍ ተጠቃሚ መሆን ጀምረዋል:: ወ/ሮ ሉባባ አክለውም ባለፉት 25 ዓመታት ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፖሊሲ ተቀርፆ ተግባራዊ በመደረጉ በፖለቲካው ዘርፍ በቀበሌ 42 በመቶ፣ በወረዳ 42 ነጥብ 52 በመቶ እንዲሁም በክልል 47 በመቶ የምክር ቤት አባላት ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል:: በትምህርቱ፣ በልማቱና በጤናው ዘርፍም ሴቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን አብራርተዋል:: እነዚህን እምርታዎች አጠናክሮ በመቀጠል የተሻለ ደረጃ ለመድረስም ሴቶች “አንችልም” ከሚለው ኋላቀር አመለካከት ራሳቸውን አላቀው “እንችላለን!” ሲሉ እንደሆነ ወ/ሮ ሉባባ ተናግረዋል:: በአማራ ክልል ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ በበኩላቸው ባለፉት ጌታቸው ፈንቴ ወደ ገጽ 20 ዞሯል ኢንተርፕራይዞች “የሚገባንን ድጋፍ ተነፍገናል” አሉ “ከመንግስት ማግኘት የሚገባንን ድጋፍ መነፈጋችን የልማታችን እንቅፋት ሆኖብናል” ሲሉ በአማራ ክልል በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ተናገሩ::የአማራ ክልል ምክ/ፕሬዝዳንት አቶ ብናልፍ አንዷለም በበኩላቸው ችግሩን ለመፍታት የሚያስችል አሰራር እንደሚዘረጋ ጠቁመዋል:: የአማራ ክልል ቴከኒክ ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ “የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዞች ልማት ሽግግር ለህዳሴያችን!” በሚል መሪ ቃል ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ ኤግዚቢሽንና የፓናል ውይይት አዘጋጅቷል::ከከሚሴ አካባቢ ከመጡት ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች መካከል አብዱልከሪም ኢብራሂም እንደተናገው ከአንድ ነጥብ አምስት ሞዴል አንቀሳቃሾች እውቅናና የምስክር ወረቀት አግኝተዋል

ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩርለ ህ ብ ረ ተ ሰ ብ ለ ው ጥ እ ን ተ ጋ ለን !

22ኛ ዓመት ቁጥር 26 ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም ዕትም ዋጋ 2 ብር

ገጽ 9

ገጽ 40

- ውለታ ቢስ ትውልድ

- ጣና ያፈራቸውገጽ 23

ገጽ 7

ገጽ 11- ፀደቀ

- ለእናት እና ልጅ ሁሉም እጅ ለእጅ

- የማስታወቂያ ባለቤቱ ማን ነው?

ገጽ 18

- ትኩረት - ትኩረት ለሚሹት

ሱራፌል ስንታየሁ

ሙሉ አብይ

ስርጭቱን በናይል ሳት

ወደ ገጽ 20 ዞሯል

ገጽ - 5

በውስጥ ገፆች

ደረጀ አምባው

ወደ ገጽ 20 ዞሯል

ወደ ገጽ 20 ዞሯል

) Frequency- 12341 ) Symbol rate - 27500 ) FEC- 3/4

) Polarization – horizontal

መከታተል ይችላሉ::

“የወረቀት ‘ምሁራን’ እየተፈለፈሉ

ነው!”

ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር የቆየዓለም ደሌ

ኢትዮጵያ በአቦካዶ ምርት የአውሮፓን ገበያ መቆጣጠር ትችላለች

ነዋሪዎች በመሠረተ ልማት ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ገለፁ

ሴቶች “አልችልም” ከሚል አመለካከት መላቀቅ አለባቸው ተባለ

በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የደሃና ወረዳ ነዋሪዎች በመሠረተ ልማት አቅርቦት ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ገለፁ::

የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ከደሃና ወረዳ አስተዳደር ጋር በመተባበር ህብረተሰቡን የወረዳው አመራሮች ፊት ለፊት አገናኝቶ በመልካም አስተዳደር ዙሪያ አወያይቷል:: ግንቦት 14 ቀን 2008 ዓ.ም አምደ

ወርቅ ከተማ በእነለጋ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የደሃና ወረዳ ነዋሪዎች “ወረዳዋ በመሠረተ ልማት ተጠቃሚ ባለመሆኗ

ኢትዮጵያ ያላትን ምቹ የአየር ንብረትና የግብርና ኤክስቴንሽን ስልት ተጠቅማ አቦካዶን በስፋት ብታመርት የአውሮፓን ገበያ መቆጣጠር የሚያስችል አቅም እንዳላት ተገለፀ::

ሰሞኑን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የዘርፉ ባለሙያዎች በሜጫ ወረዳ አቦካዶ እያመረቱ ወደ አውሮፓ ገበያ ለማቅረብ እንቅስቃሴ ላይ ያሉ ግለሰቦችና ቀበሌዎችን ተሞክሮ ተዘዋውረው ጐብኝተዋል::

በኢትዮጵያ ስድስት ክልሎች በተመረጡ ወረዳዎች ከ10 ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የአቦካዶ ምርት እንዲስፋፋ እያደረገ ያለው የ’ማሻቩ’ ፕሮጀክት አስተባባሪ እስራኤላዊው ሚስተር ኦፈር ካህን እንዳሉት ኢትዮጵያ ያላት ምቹ የአየር ንብረትና የምትከተለው የግብርና ኤክስቴንሽን ዘዴ አንድን

ሴቶች ባለፉት 25 አመታት ያገኙትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማስቀጠል “አልችልም” ከሚለው ኋላ ቀር አመለካከት ራሳቸውን ማላቀቅ እንዳለባቸው ተገለፀ::

ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ሴቶች የግንቦት 20ን የብር ኢዮበልዩ በዓል አክብረዋል:: በዚህ ጊዜ በአማራ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ወጣቶችና ህጻናት ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሉባባ ኢብራሂም እንደተናገሩት ባለፉት 25 ዓመታት ሴቶች ከጓዳ ወጥተው በፖለቲካው፣ በትምህርቱ፣ በጤናው፣ በልማቱ፣… ዘርፍ ተጠቃሚ መሆን ጀምረዋል::

ወ/ሮ ሉባባ አክለውም ባለፉት 25 ዓመታት ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፖሊሲ ተቀርፆ ተግባራዊ በመደረጉ በፖለቲካው ዘርፍ በቀበሌ 42 በመቶ፣ በወረዳ 42 ነጥብ 52 በመቶ እንዲሁም በክልል 47 በመቶ የምክር ቤት አባላት ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል:: በትምህርቱ፣ በልማቱና በጤናው ዘርፍም ሴቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን አብራርተዋል::

እነዚህን እምርታዎች አጠናክሮ በመቀጠል የተሻለ ደረጃ ለመድረስም ሴቶች “አንችልም” ከሚለው ኋላቀር አመለካከት ራሳቸውን አላቀው “እንችላለን!” ሲሉ እንደሆነ ወ/ሮ ሉባባ ተናግረዋል::

በአማራ ክልል ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ በበኩላቸው ባለፉት

ጌታቸው ፈንቴ

ወደ ገጽ 20 ዞሯል

ኢንተርፕራይዞች “የሚገባንን ድጋፍ ተነፍገናል” አሉ

“ከመንግስት ማግኘት የሚገባንን ድጋፍ መነፈጋችን የልማታችን እንቅፋት ሆኖብናል” ሲሉ በአማራ ክልል በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ተናገሩ::የአማራ ክልል ምክ/ፕሬዝዳንት አቶ ብናልፍ አንዷለም በበኩላቸው ችግሩን ለመፍታት የሚያስችል አሰራር እንደሚዘረጋ ጠቁመዋል::

የአማራ ክልል ቴከኒክ ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ “የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዞች ልማት ሽግግር ለህዳሴያችን!” በሚል መሪ ቃል ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ ኤግዚቢሽንና የፓናል ውይይት አዘጋጅቷል::ከከሚሴ አካባቢ ከመጡት ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች መካከል አብዱልከሪም ኢብራሂም እንደተናገው ከአንድ ነጥብ አምስት

ሞዴል አንቀሳቃሾች እውቅናና የምስክር ወረቀት አግኝተዋል

Page 2: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 2

ርዕሰ አንቀፅ

ይድረስ ለበኩር

በኩርዋና አዘጋጅ፡-

ጥላሁን ቸሬ ስልክ፡- 0918 70 60 08 E mail– [email protected]

ምክትል ዋና አዘጋጆች ፡-ትምህርታዊ አምዶች፡- ይህዓለም መለሰ

Email- [email protected]መዝናኛ አምዶች ፡- አብዮት ዓለም Email- [email protected]

በኩር በአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በየሳምንቱ የሚታተም የሰኞ ጋዜጣ

አዘጋጆች፡-

ጌታቸው ፈንቴ አባትሁን ዘገየ Emial [email protected] ጌትነት ድልነሳ [email protected] ሙሉ አብይ [email protected]

ደምሴ ሃሰን አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ዋጋው አድማሱ አድራሻ ፡- አማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዋናው መ/ቤት - ባህር ዳር

ፖ ሳ.ቁ 955 ስ.ቁ /+251/ 058 226 50 18 E-mail [email protected] Web www.amma.gov.et

በጽሁፍ መልዕክት(sms) ab. በማስቀደም 8200

የማስታወቂያ አገልግሎት ፡ ስልክ ቁጥር 05 82 26 49 88 05 82 26 57 32 ፋክስ ቁጥር 05 82 20 47 52

[email protected] [email protected]አታሚ፡- ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

አዲስ አበባ

ታህሳስ 7 1987 ተመሰረተ

አቶ ያየህ ፈጠነ ከሰሜን ሸዋ እና አቶ አረጋው ጋሻው ከደቡብ ወሎ ላጋምቦ አቅስታ ከተማ የላካችሁልን መልክት ደርሶናል:: አቶ ያየህ በጥያቄና መልስ ላይ ከመሳተፍ በተጨማሪ በጋዜጣችን ላይ ስለሰጡን ገንቢ አስተያየት፣ አቶ አርጋው ደግሞ ጋዜጣችንን አንብበው ስላላኩልን ማረሚያ በዝግጅት ክፍሉ ስም በጣም እናመሰግናለን! በተረፈ ያነሳችኋቸውን እርምቶች በአዘጋ ጆችና በአጠቃላይ የዝግጅት ክፍሉ በትኩረት በማየት ለማስተካከል ጥረት እናደርጋለን:: ለወደፊቱም በጋዜጣው ላይ የምታዩዋቸውን መስተካከል የሚገባቸውን ጉዳዮች እንድትልኩልን አደራ እንላለን::

የቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሲቋቋም የራሱ የሆኑ ተልዕኮዎች አሉት:: ዋናውና ቀዳሚው ደግሞ ገበያው የሚጠይቀውን ብቃት ያለው የሰው ኃይል በአመለካከትና በክህሎት ገንብቶ ማውጣት ነው:: ሌላውና ሁለተኛው ደግሞ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በስፋት እንዲቋቋሙ በማድረግ ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር ነው::

የሥራ ዕድል ከመፍጠር በዘለለም ኢንተርፕራይዞች በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማድረግ ከሀገር ውስጥ ገበያ አልፎም የውጭ ገበያ ምርቶች እንዲመረቱ የገበያ ትስስር መፍጠርም የቢሮው ተግባር ሆኖ ተቀምጧል::

የሀገራችንን ምጣኔ ኃብታዊና ማህበራዊ ልማትና ዕድገትን በተሻለ ሁኔታ የሚያሳድጉ ቴክኖሎጂዎችን በመኮረጅ ማስፋፋትም ከቢሮው የሚጠበቅ አንኳር ተግባር ነው:: እነዚህን ተግባራት በመከወን ለሀገራችን ኢንዱስትሪዎች መሰረት ለመጣልም በክልላችን በርካታ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ወደ ስራ ገብተው ተግባራቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ::

በነዚህ ኮሌጆች አማካኝነትም በርካታ ወጣቶች ከድህነት ወጥተው ሚሊየነር ሆነዋል:: ችግር ፈች ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር፣ በመኮረጅና ወደ ህብረተሰቡ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግም ገቢ ከማግኘት ባለፈ የአርሶ አደሩና የሌላው ማህበረሠብ አመራረት እንዲዘምን ለማድረግ ጥረት ተደርጓል::

በሀገራችን የቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ዋና የትኩረት መስክ የሆነው የስራ መፍጠሪያ መስክ በመሆኑ ነው:: ከዚህም በተጨማሪ ኢንተርፕራይዞች የልማታዊ ባለሀብቶች መፍለቂያ መሰረት መሆናቸው ሌላው የትኩረት መስክነታቸው መገለጫ ነው:: በከተሞችም ሆነ በገጠር የሚገኘው አብዛኛው በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የሚሰማራ የህብረተሰብ ክፍል ጉልበቱን ተጠቅሞ ኑሮውን ለማሻሻል እንጂ በጥገኝነት ለመክበር የማይፈልግ መሆኑ ኢንተርፕራይዞች የሀገሪቱን የወደፊት እድል የሚወስኑ ሆነው ተገኝተዋል::

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ክህሎትን ሰርቶ በመማር ማሳደጊያ በመሆናቸው ለአምራች ዘርፉ መስፋፋትና ማደግ መሰረቶች ናቸው::

የአምራች ዘርፉ የሚስፋፋው ደግሞ ከመሰረቱ አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችን ወደ መካከለኛ፣ መካከለኛዎችን ወደ ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች በማሸጋገር መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው:: ይህን በማድረግ በኩል ግን አሁንም በፍጥነት ሊሻሻሉ የሚችሉ ችግሮች መኖራቸው በየመድረኩ እየተገለፀ ነው:: ከአንዱ ደረጃ ወደ ሌላ ተሸጋግረው የመስሪያና የመሸጫ ቦታ ያላገኙ በርካታ ናቸው:: ያገኙትም ቢሆኑ መሰረተ ልማት ያልተሟላላቸው በመሆናቸው ፈጥነው ወደ ስራ ለመግባት አይችሉም::

መንገድ፣ መብራትና ውሀ ያልተሟላላቸው ባዶ ህንፃዎች ተረክበው “አቤት” የሚሉ ኢንተር ፕራይዞች በርካታ ናቸው:: የሚሰሩ ሸዶች ወይም የስራ ቦታዎች ደረጃቸው ለዘርፉ በሚፈለገው ደረጃ አለመሆንም በየአካባቢው ጐልተው የሚታዩ ችግሮች ናቸው:: ኢንተርፕራይዞች ከተሸጋገሩ በኋላ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል አለማድረግም በሚፈለገው ውጤት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም:: ድጋፍና ክትትል ሲደረግም ለውጥ በሚያመጣ መልኩ አለመሆን በጉልህ እንደሚታይ ጥናቶች ያመለክታሉ::

የዚህ ሁሉ ችግር ዋናው ምንጭ ደግሞ የሚመለከታቸው አካላት ተናቦ አለመስራትና የኢንተርፕራይዞችን ሀገራዊ የምጣኔ ኃብት ፋይዳ አለመረዳት ነው ተብሎ ይታሰባል::

ሌላውና ዋናው ምክንያት በሽግግር ወቅት ምልመላና መረጣ ላይ ጥራት ያለው፣ ግንዛቤው የተለወጠና ፈተናዎችን በራሱ ጥረትም ማለፍ የሚችል፤ ከጠባቂነት የወጣ፣ ለመለወጥ የተዘጋጀ ዜጋ አለመምረጥ ለእንቅፋቶች መሰረት ሊሆን ይችላልና መጤን ይገባዋል::

ስለዚህ ቢሮው ያለመውን ግብ ያሳካ ዘንድ ለመረጣና ምልመላ ግልጽ የሆነ መስፈርት ማውጣት ይጠበቅበታል:: ካለውም በየወቅቱ አፈፃፀሙን ተቆራርጦ መገምገምና የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ ግድ ይለዋል::

ከሁሉም በላይ ደግሞ ኢንተርፕራይዞች በሀገራችን የሚታየውን የስራ አጥነት ችግር ከማቃለል፣ የሀገሪቱን ምጣኔ ኃብት ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ከማሸጋገርና የውጭ ምንዛሪ ከማስቀረትና ከማምጣት አኳያ የሚጫወቱት ሚና ላይ አሁንም መግባባት ላይ መድረስ ያስፈልጋል::

በአጠቃላይ ሀገራችን የምታደረገው ምጣኔ ኃብት ሽግግር እውን የሚሆነው በኢንተርፕራይዞች አስተዋፆ መሆኑን በምክንያት ማመን ያስፈልጋል:: ለዚህ ደግሞ የተጠያቂነት ስርዓት በመዘርጋት ዘርፉ የታለመለትን ዓላማ እንዲመታ ማድረግ የሁሉም ባለድረሻ አካላትን ተሳትፎ ይጠይቃል::

ከፍተኛ ሪፖርተሮች፡- ታምራት ሲሳይፀጋዬ የሽዋስ [email protected]አዲሱ አያሌውአብርሃም አዳሙአብርሃም በዕውቀትሙሉጌታ ሙጨ [email protected]ደረጀ አምባውሱራፌል ስንታየሁ

ሪፖርተር፡-ጌትሽ ኃይሌ[email protected]

ፎቶ ሪፖርተር፡- ሰለሞን ሀዲስተባባሪ የካርቱን ባለሙያ፡- ብርሃኑ ክንዱ

የኮምፒዩተር ፅህፈት እና ግራፊክ ዲዛይነር፡- የኔሰው ማሩእመቤት አህመድአለምፀሐይ ሙሉደጊቱ አብዬ

ህትመት ክትትልና ስርጭት፡-

ለታሳታፊነት ብታበቁን ?

ትኩረት ለኢንተርፕራይዞች!

ከዝግጅት ክፍሉ

ለ ህ ብ ረ ተ ሰ ብ ለ ው ጥ እ ን ተ ጋ ለን !

ውድ የበኩር ጋዜጣ አዘጋጆች እንደምን ከርማችኋል! እኔ በጣም ደህና ነኝ:: ደስታ ይትባረክ እባላለሁ:: በወልድያ መምህራን ኮሌጅ የስነ ጥበብ እና ዲዛይን መምህር ነኝ:: ለስነ ጽሁፍ ልዩ ፍቅር አለኝ:: በተለያዩ አጋጣሚዎች የስነ ጽሁፍ መሰረታዊ የስልጠናዎችን ወስጃለሁ:: ይህም በርካታ ጽሁፎችን ለመፃፍ አግዞኛል:: በተለያየ አጋጣሚ የፃፍኳቸውን ልብወለዶች እና እንደ ጉዞ ማስታወሻ ወይም የትዝብት ጽሁፎች ወደ እናንተ ስልክ በድፍረት ሳይሆን ራሴን ለመልካም እንደሚቀና ተማሪ አድርጌ በማሰብ ነው:: በኩር ጋዜጣን ልጅ እያለሁ በከሚሴ ከተማ ትሰራጭ ስለነበር በወቅቱ የማንበብ ዕድልም ነበረኝ:: በአስተያየትም ይሁን በጽሁፍ ዝግጅት የተሳትፎ ጥያቄ ሳቀርብ ይህ የመጀመሪያዬ ነው:: ውድ የበኩር ጋዜጣ አዘጋጆች ስራዎቼን በትዕግስት ተመልክታችሁ በማቃናት እና ወደ እናንተ ጋዜጣ ቅርጽ በመውሰድ ወይም ደግሞ ተገቢውን አስተያየታችሁን በመስጠት ወደ ተሻለ መንገድ እንደምትመሩኝ ተስፋ አደርጋለሁ::

ደስታ ይትባረክወልድያ

ተሣታፊያችን አቶ ደስታ ይትባረክ ላደረሡን ጽሁፍና አስተያየት በጣም እናመሠግንዎታለን:: ጽሁፉዎ አሥፈላጊው አርትኦት ተሠርቶለት የጋዜጣውን ደረጃ የሚያሟላ ከሆነ እንደሚታተም ልንገልጽልዎት እንወዳለን::

ከዝግጅት ክፍሉ

Page 3: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 3በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ኢኮኖሚና ልማትኢኮኖሚና ልማትኢኮኖሚና ልማት

ሱራፌል ስንታየሁ

ወደ ገጽ 40 ዞሯል

አጫጭር ዜናዎች

ወደ ገጽ 28 ዞሯል

ውሃን እንደ "ባንክ" በጉድጓድ

እህል እንዲወልድአርሶ አደር ውቤ አድማሴ በምንጃር ሸንኮራ

ወረዳ ቦሎስላሴ ቀበሌ አቡጭ ሃገር ጎጥ ነዋሪ ናቸው:: ዕድሜያቸው ሃምሳዎቹ አጋማሽ ላይ ደርሷል:: በእርሻ ስራ መተዳደር ከጀመሩ ደግሞ ከሰላሳ ዓመት በላይ ሆኗቸዋል:: የራሳቸው የሆነ ሁለት ሄክታር መሬትም አላቸው:: ለሃያ ዓመት ያክል ይህን መሬታቸውን በዓመት አንድ ጊዜ ጤፍ፣ገብስ፣ሽምብራ… እይዘሩ በደሳሳ ጎጃቸው ቤተሰቦቻቸውንና ራሳቸውን ሲያስተዳድሩ ኑሮዋል::

በየዓመቱ እያረሱ፣ እየዘሩ፣ እያረሙና፣ እያጨዱ… እህል ወደ ጎተራቸው ቢያስገቡም የልፋታቸውን ያክል ግን ተጠቃሚ ለመሆን አልቻሉም:: አርሶ አደሩ እንደሌሎች አካባቢዎች አርሶ አደሮች በዓመት ሁለትና ሦስት ጊዜ ለማምረት እና ለመጠቀም ቢመኙም ተፈጥሮ እንዳደላችባቸው አምነው ተቀመጡ:: ምክንያቱም በአቅራቢያቸው

የሚፈስ ወንዝ ቢኖር ኖር እሱን ጠልፈው ወደ ማሳቸው አስገብተው ከአንድም ሁለት ሦስት ጊዜ

ማምረት ይችሉ ነበር::የገፀ ምድር ውሃ

በአቅራቢያቸው የለም ማለት ግን በመስኖ ለማልማት ብቸኛው አማራጭ እሱ ብቻ ነው ማለት እንዳልሆነ አርሶ አደሩ ዘግይተውም ቢሆን ተረድተዋል:: ሌላ አማራጭ አለኝ ብለው ያሰቡት ደግሞ የከርሰ ምድር ውሃ ነበር:: በማሳቸው አጠገብ መሬት ቆፍረው ውሃ አፍልቀው በመስኖ ማልማት እንደሚችሉም ተረዱ:: አካፋና ዶማቸውን ይዘው ቁፋሮ ጀመሩ:: ሁለት ሜትር፣ ሦስት ሜትር… ወደ ታች እየቆፈሩ አዩት:: ድንጋዩ ተጋድሞ ጠበቃቸው ውሃ የሚባል ነገር ናፈቃቸው:: እስከ አራት እና አምስት ሜትር ድረስ

ድንጋይ በዲጅኖ እየፈለቀቁ፣ ኮረት በአካፋ እየዛቁ ቢያወጡም፤ ከድንጋዩ ላይ ድንጋይ እንጅ ውሃ ማውጣት ተሳናቸው::

አርሶ አደሩ በመስኖ ለማልማት ያላቸውን ፍላጎት ለማሳካት የአቅማቸውን ሁሉ ጥረት አደረጉ:: የቀረው ሌላ አማራጭ መፈለግ ነው:: እንደሌሎች አካባቢዎች በማሳቸው አጠገብ ወንዝ ባይኖርም፣ እንደሌሎች አካባቢ አርሶ አደሮች መሬት ቆፍረው ውሃ በቅርበት አግኝተው መስኖ ማልማት ባይችሉም በዓመት የተወሰኑ ወራት ግን እንደሌሎች አካባቢ አርሶ አደሮች በክረምት ወራት ዝናብ እንደሚያገኙ ያውቁታል::

እናም በክረምት ወራት የሚመጣን ዝናብ ጠብቆ በዓመት አንዴ እያመረቱ ከመቀመጥ ይልቅ ለምን ይህን የክረምት ዝናብ አቁሬ በማስቀመጥ በበጋ ወራት በመስኖ አላለማም ሲሉ አሰቡ:: በ1995 ዓ.ም ይህን መሬታቸውን በአንድ በኩል ለሰብል ዘር እያረሱ በእረፍት ጊዜያቸው ደግሞ የዝናብ ማቆሪያ ጉድጓድ እየቆፈሩ አሳለፉት ሁለት ሜትር ተኩል ጥልቀት ያለው እና ወደ ጎን ሁለት ሜትር በሁለት ሜትር የሚሆን ስፋት ያለው ጉድጓድ በመቆፈር በላዩ ላይ ዙሪያውን ጆኦሜምብሬን አልብሰው አስቀመጡት::

ይህ ጉድጓድም በየጊዜው በሚጥለው ዝናብ ከአፉ እስከ ገደፋ ሞላላቸው:: በክረምት ዝናብ በመታገዝም ጤፍ፣ ገብስ፣ ሽምብራ ዘሩና የ1995 ዓ.ም የምርት ጊዜያቸውን እንደ በፊቱ በዓመት አንድ ጊዜ አምርተው አለፉት:: ይህ ጊዜ በግብርና ሥራቸው በዓመት አንድ ጊዜ የሚያመርቱበት የመጨረሻው ዓመት ነበር::

በ1996 ዓ.ም በክረምት ዝናብ ታግዘው ያመረቱበትን ሰብል ሰብስበው ካስገቡ በኋላ መሬታቸውን ማረስ ጀመሩ:: እንደ በፊቱ በዓመት

በምስራቅ ጐጃም ዞን በአዋበል ወረዳ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎች ላይ የክህሎት ስልጠና መሰጠቱ ምርት እና ምርታማነታችንን እንድናሳድግ ይረዳናል ሲሉ የወረዳው አርሶ አደሮች ገለጹ::

ስልጠናውን ከወሰዱ አርሶ አደሮች መካከል የየካይት ቀበሌ አርሶ አደር ደምሴ ይታየው እና ገበያው ደመቀ እንደገለጹት ስልጠናውን ማግኘታቸው ከባህላዊ አስተራረስ ወደ ዘመናዊ አስተራረስ እንዲሸጋገሩ ይረዳቸዋል::

የአዋበል ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ደሳለኝ ልቅናው እንደገለጹት በሶስት ዙር ለ11 ሺህ 471 አርሶ አደሮች የእርሻ ድግግሞሽ፣ የዘር መጠን፣ የመዝሪያ ጊዜ፣ የግብአት አጠቃቀምና ሌሎች የክህሎት ስልጠናዎችን በተመለከተ ስልጠና ተሰጥቷል::

አርሶ አደሩ ስልጠናውን ምን ያህል እንደተገነዘቡት ለማወቅ የብቃት ምዘና መሰጠቱን የገለጹት ባለሙያው በዚህም ሁለት ሺህ 202 አርሶ አደሮች ምዘና የወሰዱ ሲሆን ከነዚህ ውሰጥም አንድ ሺህ 893 አርሶ አደሮች መብቃታቸውን ማረጋገጡን ገልጸዋል::

ስልጠናውን ከወሰዱት መካከል 717 ሴቶች መሆናቸውን ባለሙያው ተናግረዋል::

መረጃውን ያደረሰን የአዋበል ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው::

በአኘል ምርት ከ500 በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ሆኑ

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በፋግታ ለኮማ ወረዳ በማህበር ተደራጅተው በደጋ ፍራፍሬ ማልማት ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገብ መቻላቸውን ገለፁ::

ከማህበሩ አካላት መካከል አርሶ አደር መለሰ በሪሁን እና አርሶ አደር ባይነሳኝ አበበ እንደተናገሩት በአኘል ምርት ከተሰማሩበት ጊዜ ጀምሮ በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ችለዋል:: የማህበሩ አባላት ከ1500 እስከ 40 ሺህ ብር ድረስ ትርፍ በመከፋፈል መቆጠብ መቻላቸውን ገልፀው በ2008/ለ2009 ዓ.ም ከ100 ሺህ በላይ የአኘል ችግኝ በማፍላት ለገበያ አዘጋጅተዋል::

የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ ፈጠነ በበኩላቸው በአኘል ምርት የተሰማሩ አርሶ አደሮችን ሙያዊ ድጋፍና ክትትል ከማድረግም በላይ የገበያ ትስስር ለመፍጠርና ለማፈላለግ ከክልሉ ግብርና ቢሮ ጋር በመቀናጀት እየተሰራ ነው ብለዋል:: እንደ አቶ አዲሱ ገለጻ በደጋ ፍራፍሬ ምርት ስምንት ቀበሌዎችን በማሳተፍ ከ180,900 በላይ የአኘል ችግኞችን በማልማት ከ500 በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል:: አርሶ አደሮችም ከችግኝ ሽያጭ ወደ አኘል ምርቱ ሊያተኩሩ እንደሚገባ አቶ አዲሱ አሳስበዋል ሲል የወረዳው መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል::

አርሶ አደሮች የግብርና ቴክኖሎጂ

ስልጠና አገኙ

በአንድ በኩል ለሰብል ዘር እያረሱ በእረፍት ጊዜያቸው ደግሞ የዝናብ ማቆሪያ ጉድጓድ እየቆፈሩ አሳለፉት ሁለት ሜትር ተኩል ጥልቀት ያለው እና ወደ ጎን ሁለት ሜትር በሁለት ሜትር የሚሆን ስፋት ያለው ጉድጓድ በመቆፈር በላዩ ላይ ዙሪያውን ጆኦሜምብሬን አልብሰው አስቀመጡት::

Page 4: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 4 ዜና ትንታኔ

ደረጀ አምባው

ወደ ገጽ 24 ዞሯል

በምዕራብ ጐጃም ዞን ሜጫ ወረዳ በወተት አባይ ቀበሌ የሚገኘው ሰፊ ሜዳ ከሁለት ዓመት በፊት ከአህያና በቅሎ መዋያ የዘለለ ሚና አልነበረውም:: አሁን ግን ወረዳውና የአካባቢው ነዋሪዎች በመነጋገርና በመግባባት ‘ልቅ ግጦሽን’ በማቆማቸው ገጽታው ተቀይሯል፤ ነዋሪዎች ከዚህ ሜዳ ሳር እያጨዱ አስረው ለሚቀልቧቸው እንስሳት መኖ በማዋላቸው እንስሳቱ በሦስት ወር ውስጥ ለገበያ እየደረሱ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ አድርገዋል::

ሰሞኑን በሜጫ ወረዳ በሚገኙ የአቦካዶ አምራች ቀበሌዎች ከእስራኤል ሀገር የመጡ ባለሙያዎች፣ ከየዘርፉ የተጋበዙ አስተባባሪዎችና ልዩ ልዩ ባለሙያዎች ጉብኝት አካሂደዋል::

አቶ አስማማው ወርቁና ጓደኞቹ ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በተፈጥሮ ሐብት አስተዳደር፣ በእንስሳት ሳይንስና በሂሣብ አያያዝ የትምህርት መስኮች ተምረዋል:: የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ይዘውም በመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥረው ለመስራት ተዘጋጅተው ነበር:: ይህ አልሆን ሲላቸው ተሰባስበው” አስማማውና ጓደኞቹ” የሚል የህብረት ሥራ ማህበር በማቋቋም ከሰኔ 2007 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ግብርና ገብተዋል::

እነዚህ ወጣቶች በፍራፍሬ ልማት ተሰማርተው ራሳቸውን ለመቀየር መንቀሳቀስ ጀመሩ:: “ማሻቩ” የተባለው እስራኤላዊ ፕሮጀክት ደግሞ ከጎናቸው ቁሞ ‘አይዟችሁ’ አላቸው:: የተሻሻሉ የአቦካዶ ዝርያዎችን አምጥቶ ሰጣቸው:: ወጣቶቹ ፕሮጀክቱ የሰጣቸውን 50 የ’ሃስ’ እና ‘ኢንቲንግር’ የተባሉ

የአቦካዶ ዝርያዎች በመትከል ሥራቸውን ጀመሩ::ከአቦካዶው ልማት ጐን ለጐን የበሬ ማድለብና

እንስሳት እርባታ ሥራም ይሰራሉ::ሥራውን ከጀመሩ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ

ከብቶችን አድልበው በመሸጥ 85 ሺህ ብር ገቢ ማግኘታቸውን የማህበሩ ሊቀመንበር አስማማው ወርቁ ተናግሯል::

“ከብቶች የሚደልቡት በአቦካዶ ተክሉ ዙሪያ ባለው ክፍት ቦታ የሚበቅለውን ሣር እየተመገቡ ነው፤ አቦካዶውንም ከሰው ሰራሽ የማዳበሪያ ይልቅ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ‘ኮምፖስት’ መጠቀማችን አካባቢው ከምንጊዜውም በላይ አረንጓዴ እንዲለብስ አድርጐታል” ብሏል ሊቀመንበሩ::

በዚሁ ቀበሌ የተደራጁ 14 ማህበራት ሲኖሩ ሁሉም ተመሣሣይ ምርት በማምረት ገበያን ለመሳብ

ጥረት እያደረጉ መሆኑን አባላቱ ይናገራሉ::የ10ኛ ክፍል ትምህርቱን ያጠናቀቀው ሙላት

አሌ እንደተናገረው በሜጫ ወረዳ በአትክልት፣ ፍራፍሬና ከብት ማድለብ ከጓደኞቹ ጋር ተደራጅቶ እየሠራ ነው:: ከማሻቩ ፕሮጀክት ያገኙትን ስልጠናና ችግኝ በመጠቀም 80 አቦኮዶዎችን በመትከል ተጠቃሚ ለመሆን ጥረት እያደረጉ ነው::

ከህብረተሰቡ ጋር በመመካከርና በመተማመን በመደራጀታቸው ለልቅ ግጦሽ ሲውል የነበረው ሜዳ የተፈቀደላቸው መሆኑን ያስደሰተው ወጣት ሙላት የወረዳና ቀበሌ አመራሮች ከህዝቡ ጋር ለመግባባትና ለማስፈቀድ ያደረጉት እልህ አስጨራሽ ጥረት እንዳስደነቀው ገልጿል:: የመርዓዊ ከተማ 01 ቀበሌ ነዋሪው አቶ ሞላ በቀለ ከከተማው ሥራ ይልቅ የገጠሩ ሥራ ይበልጥብኛል በማለት ወደ ከተማዋ

ዙሪያ የሚገኙ ቀበሌዎች ወጣ ብለው በባህር ዛፍ ንግድ ላይ ተሠማርተው ነበር:: የባህር ዛፍ ንግዱ ብዙም ውጤት ያልሰጠው አቶ ሞላ የሚጠቀምበትን መሬት የአፈር ለምነት በማስመርመር ከማሻቡ ፕሮጀክት ባገኘው 200 የአቦካዶ ችግኝ ሸፍኖታል:: በአተካከሉም ሆነ በእንክብካቤው ዙሪያ የአካባቢው የግብርና ባለሙያዎች እገዛ ስላልተለየው አቦካዶው በመልካም ቁመና ላይ ሲገኝ ፍሬውንም እየጠበቁ ነው::

“ቀንም ሆነ ሌሊት በእርሻ ቦታ ላይ ነኝ” የሚሉት አቶ ሞላ በፍራፍሬው ስር በበቀለው ሳርም ከብቶችን በመቀለብ የተሻለ የወተት ምርት እያገኙ መሆኑን ገልፀዋል::

አርሶ አደር ሞላ በባለሙያዎች ምክር በመታገዝ ባዘጋጁት ሰው ሰራሽ ማዳበሪያና ሌሎች የሠሯቸው ስራዎች ከወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት የውሀ መሣቢያ ሞተር በሽልማት አግኝተዋል:: ቋሚ ተክሎችን በሣምንት ሦስት ቀን ውሀ በማጠጣት ምርቱ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዲደርስ ጠንክረው እየሰሩ ነው::

የወተት አባይ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ የችግኝና ዘር ማባዣ ኃላፊ አቶ እንዳለ ገላ እንደሚናገሩት በ”ዩኤስ አይ ዲ” ማሻቩ እና ግብርና ሚኒስቴር ትብብር የሚካሄደው ይህ ፕሮጀክት የአርሶ አደሩን ህይወት ለመቀየር አልሞ የተነሣ ነው::

ሥራውን በሦስት ሄክታር የጀመረው ይህ ፕሮጀክት ትልቁ ስራው አርሶ አደሮች ወደ ተሻለ ቴክኖሎጂ እንዲሸጋገሩ ማገዝ ነው::

ባለፉት ሦስት ዓመታት ከአርሶ አደሩ ጀምሮ እስከ ግብርና አስተባባሪዎች ድረስ የተግባር ስልጠና

ለአርሶ አደሩ የተዘጋጁ ምርጥ የአቦካዶ ችግኞች

“የአርሶ አደሮችን ኑሮ ከመሠረቱ ሊቀይር የሚችልበትን ስራ ማቀጣጠል የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ ነው”ሚስተር ኦፈር ካህንየማሻቩ ፕሮጀክት አስተባባሪ

ኢትዮጵያ በአቦካዶ ምርት የአውሮፓን ገበያ መቆጣጠር ትችላለች

Page 5: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 5በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. እንግዳችን

ወደ ገጽ 26 ዞሯል

አብርሃም በዕውቀት

“የወረቀት ‘ምሁራን’ እየተፈለፈሉ ነው!”

ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር የቆየዓለም ደሴ መምህርና ተመራማሪ

ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር የቆየዓለም ደሴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ትምህርትና ባሕርይ ጥናት ኮሌጅ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተባባሪ ዲን፣ መምህርና ተመራማሪ ናቸው:: የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በትምህርትነክ ስነ-ልቦና (Educational Psychology)፣ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በዕድገት ስነ-ልቦና (Developmental Psychology) እና የሦስተኛ ዲግሪያቸውንም በተግባራዊ የወጣቶች ዕድገት ስነ-ልቦና (Applied Developmental Psychology of Youth) ሁሉንም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለዋል::

ረ/ፕሮፌሰር ዶክተር የቆየዓለም በግልና በቡድን በመሆን “የኢትዮጵያ ወጣቶች የዕድገት ሁኔታ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች የዕድገት ተግዳሮቶችና እሴቶች፣ የቅድመ-መደበኛ ትምህርትና ሕጻናት፣ የድሕረ-ምረቃ ትምህርት የአማካሪዎችና ተመካሪዎች ግንኙነት፣ የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የትምህርት ክትትል ሁኔታ እና የድሕረ-ምረቃ ተማሪዎች

የሚሠሯቸው ጥናቶች ጥራት” በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥናቶችን ሠርተዋል:: ዛሬ የበኩር እንግዳችን ሆነው የድሕረ-ምረቃ ተማሪዎች የሚሠሯቸው ጥናቶች ምን ያህል ጥራት አላቸው በሚል የሰሩትን ጥናት ውጤት በተመለከተ ሀሳቦችን ያካፍሉናል፤ መልካም ንባብ!

የድሕረ-ምረቃ ጥናቶች ያሉበትን የጥራት ደረጃ እንዴት አገኙት?

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድሕረ-ምረቃ ትምህርት የጀመረው እ.ኤ.አ በ1978 ነው:: እኔም ከጓደኞቼ ጋር ሆኜ የሠራኋቸው ሁለት ያህል ጥናቶች አሉ:: ከዚያን ጊዜ አንስቶ እስካሁን ያለውን የድሕረ-ምረቃ ተማሪዎች ጥናት ተመልክተናል፤ በውጤቱም በተለይ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ጥናቶች ጥራት በእጅጉ እየወረደ፣ እየቀነሰ መምጣቱን ነው ሪፖርቶቹ የሚያመላክቱት::

በተለይ በቅርብ ጊዜያት በተመራቂዎች እየተዘጋጁ ያሉት ጥናቶች ጥራት ከሚጠበቀው

ደረጃም (standard) እጅግ በጣም የወረደ እየሆነ መጥቷል:: በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ ወደፊት ለሚፈጠሩ ምሁራን ትልቅ አደጋ እየተፈጠረ መሆኑን ጥናቶች አሳይተውናል:: እንዲያውም የድሕረ-ምረቃ ትምህርት ጥናቶች ተማሪዎች አላስፈላጊ ስነ-ምግባርን የሚማሩባቸው እየሆኑ ነው፤ ተመራቂዎች ሠርቀው እየተመረቁ ነው::

ሥርቆት ሲባል አንድ ቦታ ወይም ዩኒቨርሲቲ የተሠራ የሌላ ሰው ጥናትን ወስዶ በማቅረብ ለመመረቅ መሞከርንና መመረቅን ያካትታል:: አንዳንዴ የአጥኝው ስም ብቻ ተቀይሮ እንዳለ ጽሑፉ ይቀርባል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ የአጥኝው ስምና የጥናት ቦታው ተቀይሮ ይመጣል፤ ከድረ ገፅ ሌላ አገር ላይ የተሠራን ጥናት እንዳለ ገልብጦ የማምጣት ሁኔታም አለ:: አንዳንዴ ደግሞ ሁለትና ከዚያ በላይ ጥናቶች አቀላቅሎ የመውሰድና ያለማመስገን ሁኔታ አለ:: በአጠቃላይ በድሕረ-ምረቃ ትምህርት ተማሪዎች እየተሠሩ ያሉ ጥናቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥራታቸው በአስደንጋጭ ሁኔታ እየቀነሰ መጥቷል::

የጥናት ሥራዎችን ከፍሎ የማሠራት ሁኔታ እንዳለም ሲወራ እንሰማለን፤ በጥናታችሁ አረጋግጣችሁታል?

አዎ! በጣም በብዛት አለ፤ በተለይ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ጥናቶች እንደ ሥራ ቆጥረው ገንዘብ እየተቀበሉ የሚሠሩ ሰዎች አሉ፤ የሚያሠሩትም ብዙ ናቸው:: ጥናቶችን ከፍለው የሚያሠሩ፣ የሌሎችን ሰዎች ጥናቶች ገልብጠው የሚያቀርቡ፣ በድረ-ገጽ የተለቀቁ የውጭ አገር ጥናቶችን መልሰው ጽፈው የሚያመጡ ከሆነ የወደፊት ተመራማሪነታቸው በመመረቂያ ጽሑፋቸው ተዘግቷል ማለት ነው::

የቅድመ-ምረቃ (የመጀመሪያ ዲግሪ) ትምህርት ዋና ዓላማው ተማሪዎች ስለሚማሩት የትምህርት ዘርፍ አጠቃላይ የሆኑ ዕውቀቶችን ይዘት እንዲያውቁ፣ ሳይንሳዊ ጽንሰ-ሀሳቦችን እንዲረዱ፣ ለሥራ ዓለም ዝግጁ እንዲሆኑ ማድረግ ነው:: የድሕ-ምረቃ ትምህርት ግን ጥናትና ምርምር አድርጎ አዳዲስ ዕውቀቶችን ማፍለቅን ዓላማ ያደረገ ነው::

የድሕረ-ምረቃ ትምህርት ተከታታዮች ያለውን ዕውቀትና ጽንሰ-ሀሳብ እንዲፈትሹ፣ እንዲመረምሩ፣ እንዲጠይቁ ይጠበቃል:: ይህንን የሚያደርጉት ደግሞ በጥናትና ምርምር ነው:: አሁን ያለው ዕውነታ ግን ይህ አይደለም፤ የድሕረ-ምረቃ ተማሪዎች አቋራጭ መንገድ በመፈለግ በቀላሉ መመረቅ ላይ አተኩረው እየተሯሯጡ ነው:: ለመመረቅ የሚያስችላቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና ብቃት እያዳበሩ አይደሉም:: በዚህ የተነሳ የድሕረ-ምረቃ ጥናት ጥራት በእጅጉ እየወረደ መጥቷል፤ በዚያው ልክ የተመራቂዎቹም ጥራትና ብቃት እያሽቆለቆለ ነው::

ለእነዚህ የጥራት መጓደሎች ምክንያቶቹ ምንድን ናቸው?

ምክንያቶቹ በርከት ያሉ ናቸው:: አንደኛው ምክንያት ለድሕረ-ምረቃ ትምህርት የሚገቡት ተማሪዎች ጥራት በራሱ ዝቅተኛ መሆን ነው:: ለዚህ መርሀ-ግብር የሚገቡ ተማሪዎች በራሱ የሚጠበቅባቸው አቅም፣ ዕውቀትና ክሕሎት አለ:: በቅድመ-ምረቃ ትምህርት ጥሩ የሆነ ግንዛቤ ያላቸው ምሩቃን ናቸው ወደ ድሕረ-ምረቃ መምጣት ያለባቸው፤ አሁን እየሆነ ያለው ግን ይህ አይደለም::

...ወደፊት ለሚፈጠሩ ምሁራን ትልቅ አደጋ እየተፈጠረ መሆኑን

ጥናቶች አሳይተውናል:: እንዲያውም የድሕረ-ምረቃ ትምህርት ጥናቶች

ተማሪዎች አላስፈላጊ ስነ-ምግባርን የሚማሩባቸው እየሆኑ ነው፤

ተመራቂዎች ሠርቀው እየተመረቁ ነው::

Page 6: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 6 መዝናኛ ቅምሻደረጀ አምባው

ጥያቄና መልስየ24ኛ ሳምንት ጥያቄ

መላሾች ወ/ሪት ብዙ ጌጥ ዘውዴ ከሰሜን ሸዋ

መንዝ ላሎ ወረዳና ያየህ ፈጠነ ከሰሜን ሸዋ እያንዳንዳቸው ሦስት፤ በተመሣሣይ ከሰሜን ሸዋ መንዝ ላሎ ወረዳ ካሊድ በድሩ ሁለት መልሰዋል:: በተመሣሣይ ዲያቆን ብሩክ አንለይ ከደብረታቦር ሁለት፣ አባይነህ መስፍን ከቋሪት ደግሞ አንድ በመመለስ ተሳትፈዋል:: ሁላችሁንም በዝግጅት ክፍሉ ስም እናመሰግናለን::

የ26ኛ ሣምንት ጥያቄ

1. ሰሞኑኑን በካናዳ ኦታዋ ማራቶን አሸናፊ የሆነው ኢትዮጵያዊ ማን ይባላል? የጨረሰበትን ሰዓት ይግለፁ?

2. “ኦፔክ” የተባለው የነዳጅ አውጭ ሀገራት ድርጅት መቸ ተመሰረተ?

3. ኢህአዴግ በ1983 ዓ.ም አዲስ አበባን የተቆጣጠረበት ዘመቻ ስም ማን ይባላል?

የ24ኛ ሣምንት ጥያቄ

1. ዶክተር ወለደመስቀል ኮስትሬ የአለም ምርጡ አሰልጣኝ ተብለው የተሸለሙት መቼ ነው?

2. የአውሮፓ ሰንደቅ አላማ በአውሮፓ ኀብረት የፀደቀው መቼ ነው?

3. የስሪላንካ የቀድሞ ስም ማን ይባላል?

የ24ኛ ሳምንት ጥያቄ መልስ

1. 2006 ዓ.ም

2. 1978 ዓ.ም

3. ሲሎን

ህፃኗ ጋዜጠኛ

ወደ ገጽ 20 ዞሯል

• አዕምሯችን እስከ አምስት ዓመት ዕድሜ በፍጥነት ያድጋል

• ቦብ ማርሊ ለልጁ የተናገረው “ገንዘብ ህይወትን ይገዛል” የመጨረሻ ንግግር

• ማስቲካ እያላመጣችሁ ሽንኩርት መክተፍ አይንዎን ከማስቀለስ ነፃ ያደርገዋል

• የሰዎች የታፋ /ጭን/አጥንት ከስሚንቶ ምሶሶ /ኮንክሪት/ የበለጠ ይጠነክራል::

• ግንቦች ግማሸ ኪሎ ማር ለማዘጋጀት ሁለት ሚሊዮን አበቦችን ይቀስማሉ

ምንጭ bootstrike.com

በጋዜጣችን ይዘቶች ላይ አስተያየት፣ ለጥያቄዎች መልስ መላክ ለምትፈልጉ በጽሁፍ መልዕክት(sms)

ab. በማስቀደም 8200 ወይም በስልክ ቁጥር 0918 70 60 08 ጻፉልን::

5. ሕንድህንድ ሰፊ ሀገር ከመሆኗ በተጨማሪ በሕዝብ ብዛቷም በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትቀመጣለች:: ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩ በርካታ ዜጐች ቢኖሯትም ነዳጅ በየቀኑ ለዕለት ተዕለት ኑሯቸው የሚጠቀሙ ዜጐች ባለቤትም ናት:: ህንድ ለየቀኑ እንቅስቃሴዋ 3 ሚሊዮን 182 ሺህ በርሜል ነዳጅ ትጠቀማለች::

4. ሩሲያ

በምጣኔ ኃብታዊ ደረጃዋ ተፎካካሪ የሆነችው ሩሲያ ለተለያዩ አገልግሎቶች ለምትጠቀምባቸው ተሽከርካሪዎች በርካታ ነዳጅ ተጠቃሚ ናት:: ሀገሪቱ በርካታ ፋብሪካዎች ያሏት መሆኑም ለነዳጅ አጠቃቀሟ ከፍተኛነት አንዱ ምክንያት ነው:: ሩሲያ በቀን 3ሚሊዮን 199 ሺህ በርሜል ነዳጅ በየቀኑ ያስፈልጋታል::

3. ጃፓንጃፓን አነስተኛ የመሬት መጠን ቢኖራትም በጣም ብዙ ህዝብ ያላት ሀገር ናት:: በምጣኔ ኃብት ዕድገታቸው ከተረጋጉት ሀገራት ተርታ በግንባር ቀደምትነት የምትጠራው ይህች ሀገር የበርካታ ፋብሪካዎች ባለቤት ናት:: በመጓጓዣ ዘርፍም የዓለምን አብዛኛውን የተሽከርካሪ ፍላጐት የምታሟላ ከመሆኗ ጋር ተዛምዶ አብዛኛው ዜጐቿ የተሽከርካሪ ተጠቃሚ መሆናቸው በርካታ ነዳጅ እንድትጠቀም አድርጓታል:: ጃፓን ለአንድ ቀን ብቻ የሚያስፈልጋት የነዳጅ መጠን 9 ሚሊዮን 400 ሺህ በርሜል ያህል ነው::

ከፍተኛ የነዳጅ ተጠቃሚ ሀገራት

2. ቻይናአስደናቂ የዕድገት ጐዳና ላይ የምትገኘው ቻይና በአለማችን ግዙፍ ፋብሪካዎችን የመሠረተች አገር ናት:: ሀገሪቷ ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ያሏት በጣም ሀብታምና ድሀ ዜጐችን ያቀፈች ሀገር ስትሆን አብዛኛው ህዝብ የተሽከርካሪ ባለቤት ነው:: አብዛኛዎቹ ፋብሪካዎች ተመጣጣኝ የሰው ሀይል ቀጥረው ይሠራሉ:: እነዚህ ፋብሪካዎችም የነዳጅ ዘይት የሚፈልጉበት ጊዜ መኖሩ ሀገሪቱ የምትጠቀመውን የነዳጅ ፍጆታ በቀን አራት ሚሊዮን 452 ሺህ በርሜል አድርሶታል::

1. ዩናይትድ ስቴትስ /አሜሪካ/ልዕለ ኃያሏ አሜሪካ ዜጐቿ ባለፀጐች ከመሆናቸው ጋር ካላቸው ተርታ በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ላይ ትገኛለች:: አብዛኛው ነዋሪ የተሽከርካሪ ባለቤት ከመሆኗም ባሻገር በነዳጅ የሚሰሩ በርካታ ማሽኖች ባለቤት ናት:: ራሷን የነዳጅ ባለቤት ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ብትሠራም አብዛኛውን የነዳጅ ኃብት የምትጠቀመው ግን በመግዛት ነው:: ለአንድ ቀን የሚያስፈልጋት የነዳጅ ፍጆታም 19 ሚሊዮን 150 ሺህ በርሜል መሆኑን አዲስ የወጡ የቶፕቴን መረጃዎች አመልክተዋል::

ሀገራችን ኢትዮጵያ በነዳጅ አጠቃቀሟ 92ኛ ደረጃ ላይ ስትሆን ከ25 ዓመት በፊት 12 በርሚል በቀን የነበረው ነዳጅ ዛሬ 57 ሺህ በርሚል መድረሱን ምንጫችን ኢንዴክስ መንዲ ዶት ኮም በዘገባው አስነብቧል::

ጡረተኛው ፊሊፒንሳዊ የሒሣብ ባለሙያ ሐረናንዶ ጓንሳኦ ነፃ ጊዜውን የሚያሳልፍበት ጥሩ መንገድ ፈጥሯል:: በልጅነት ዘመኑ ይጠቀምባቸው የነበሩትን መጽሕፍት በማሠባሠብ ከቤቱ በረንዳ ላይ በከፈተው የህዝብ ቤተመጽሐፍት በሰፈሩ መማር ያልቻሉ የድሀ ቤተሰብ ህፃናትን በማስነበብ አገልግሎት ተጠምዷል::

አብዛኛው የሰፈሩ ህፃናት የቤተሰባቸውን ገቢ ለማገዝ ትምህርታቸውን በማቋረጥ የቀን ስራ

5ቱ

ይሰራሉ:: የሐርናንዶ ትንሽ ቤተመጽሐፍትን ደግሞ ትምህርታቸውን ላቋረጡት ለነዚህ ህፃናት ማካካሻ ሆኖላቸዋል::

እርሱ ከቤተሰቦቹ የወረሰው መልካም ነገር “የማይጠገብ የማንበብ ፍቅር” እንደሆነ ይናገራል:: “70 ዓመት ከመሙላቴ በፊት ለአካባቢ የነዋሪዎች አንድ ነገር ማድረግ እፈልግ ነበር:: በእጄ ያሉት ሀብቶቼ ደግሞ መጽሐፎቼ በመሆናቸው ይህን ማንበቢያ በማዘጋጀት ከትምህርታቸው የተለያዩ

የማይጠገብ የማንበብ ፍቅርህፃናትን የማንበብ ፍቅር ለማገዝ እጥራለሁ:: መጽሐፍት የሚነግሩኝ ነገር አለ:: የነገሩኝን ነገርም ለሌላ እንድነግር በማድረግ ሐሳባቸው እንዲሰራጭ ይፈልጋሉ:: እንዲነበቡ ይፈልጋሉ” በማለት ከመጽሐፍት ጋር ያለውን ቁርኝት ይገልፃል::

በቤቱ በረንዳ ውስጥ ከ15 ዓመት በፊት የጀመረው የ’ንባብ ጥግ’ ዛሬ በተለያዩ የህፃናት መጽሐፍ ክምር ተጨናንቋል:: በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በጐ ሐሳቡን በመደገፍ መጽሐፍትን በስጦታ ያቀርቡለታል:: በየዕለቱ በመጽሐፍት የተሞሉ ሳጥኖችን የሚሰጡት በርካታ በጐ አድራጊዎች በስራው እንዲበረታ ጽናት ሆነውታል:: በበረንዳ ጥግ የተጀመረው የማስነበብ ሥራ አሁን ወደ ዋናው ቤት ገብቷል:: ቤቱ ከጥግ እስከ ጥግ በተለያዩ የህፃናት መጽሐፍት ተሞልቷል::

“በማኒላ ከተማ 50 የህዝብ ቤተመጽሐፍት ቢኖሩም ሁሉም የሚጠይቁት ነገር አለ” የምትለው የአልጀዚራ ቃል አቀባይ ማርጋ አርቲጋስ “ከጥንቃቄ

ደንቦች ጋር ክፍያ የመጀመሪያው መሟላት ያለበት የአባልነት ግዴታ ነው:: በሐርናንዶ ቤተመጽሐፍት ግን ምንም መስፈርት ባለመኖሩ ሁሉም ታዳጊዎች ገብተው ለመጠቀም ያስችላቸዋል” በማለት ልዩነቱን ተናገራለች::

“መጽሐፍትን በመደርደሪያ ማስመቀመጥ ተገቢ አይደለም” የሚለው ሔርንናዶ “መጽሐፍት ሊነበቡና የሰውን ህይወት ሊለወጡ ሲገባ ‘ቤት ጠባቂ’ ማድረግ ሞኝነት ነው” በማለት መጽሐፍትን ከማስቀመጥ ይልቅ ልንጠቀምበት እንደሚገባ ያሳስባል::

አሁን የ10 ዓመት ልጅ ናት:: ሚታ ጃና ጂሀድ ትባላለች:: ልክ እንደ እድሜ እኩዮቿ በፍልስጤም ምድር እየቦረቀች መጫወት፣ ገመድ በመዝለልና በትምህርት ቤት የሚገኘውን ደስታ በማጣጣም አልዘለቀችም::

የጨዋታ አጋሯ የሆነው የዕድሜ እኩያዋ በተባራሪ ጥይት ተመቶ ከጐኗ ህይወቱ ሲያልፍ መመልከቷ ሁሉንም ነገር ቀይሮታል:: በእስራኤልና ፍልስጤሞች መካከል በየቀኑ በሚደረገው የተኩስ ልውውጥ ታዛቢ የሆነችው ጃና ከጓደኛዋ ሞት በኋላ በምታየው ነገር መጨነቅና መናደድ ጀመረች::

Page 7: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 7በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ትዝብትትዝብት

ሱራፌል ስንታየሁ

ወደ ገጽ 32 ዞሯል

አፈር ብቻ

ተቆልሎበት፣

ዳርና ዳር አራት

እንጨቶች ቁመው

በአንድ ዙር ብቻ

ሽቦ ተጠምጥሞበት

የተረሳ መቃብር

አየሁኝ:: በራስጌው

ላይም በቆራጣ

ቆርቆሮ እጅግ

የተከበሩ የዓለም

ሎሬት ሚትር

አርቲስት አፈወርቅ

ተክሌ የሚል ጽሁፍ

ሰፍሮበታል::

የሰው ልጅ መጨረሻው ሞት ነው:: ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ያረጃል፣ ይሞታል:: ሳያድግና ሳያረጅ የሚሞተውም ብዙ ነው:: ዕድሜ ሰጥቶት ብዙ ዓመታት የመኖር ዕድል ያጋጠመው ሰው ለራሱና ለቤተሰቦቹ ከመኖር ያለፈ ለሃገር የሚጠቅም ጠብታ ነገር ሳያስቀምጥ እስከ ወዲያኛው ያልፋል:: ስለ ሞት ሳስብ የሚገርመኝ ንግግር አለ፤ “ለቅሶው ደምቆ ነበር?” የሚል::

ለቅሶው ደመቀ፣ አልደመቀ ምንአልባት ለቋሚ ካልሆነ በቀር ለሟች ምን ጥቅም ይኖረዋል! ሰው በታመመበት እና በተሰቃየበት ጊዜ አይዞህ፣ በርታ… እያሉ ምግብ፣ መድሃኒት፣ ውሃ… ይዘው ያልጠየቁ ታማሚው በሞተ ጊዜ “ለቅሶው ደሞቆ ነበር” ሲሉ ስሰማቸው ‘እንኳንም ሞተልን’ የሚሉ ይመስለኛል::

ከመነሻዬ ለሃገር የሚጠቅም ጠብ ያለ ነገር ሳያስቀምጡ ያልፋሉ ልበል እንጂ ጥቂት ቢሆንም ለሃገራችን ታላቅ ታሪክ ሰርተው፣ አንቱ የተባሉ ባለውለታዎቻችን መኖራቸውን ሳላነሳ አላልፍም:: ለሃገራቸው ታላቅ ታሪክ ይስሩ እንጂ ሃገራቸው ታላቅነታቸውን እየዘነጋች እንደሆነም ይሰማኛል::

ይህን ጽሁፍ እንድከትብ ያነሳሳኝ አንድ ነገር ነው:: በበኩር ጋዜጣ ግንቦት 15/2008 ዓ.ም

በትዝብት ዓምድ ላይ ‘ጀግኖቿን የማታከብር አገር’ በሚል ርዕስ የተፃፈው ትዝብት ውስጤን ክፉኛ አመሰው:: በዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ሞት ዙሪያ የሚያጠነጥን ሆኖ ሰዎችን ከሞቱ በኋላ ብቻ ባናስታውሳቸው መልካም ነው የሚል ይዘት የያዘ ጽሁፍ ነበር::

በእርግጥም በታመሙና በተቸገሩበት ጊዜ ከጐናቸው ሆነን በቁማቸው አለንላችሁ ብለን ልናበረታታቸው እንደሚገባ እምነቴ ነው:: ሆኖም ግን ከሞቱስ በኋላ ቢሆን ምናልባትም እስከ ሶስተኛው ቀን /ይህም ሲበዛ ነው/ ካልሆነ በቀር መለስ ብለን ሟቾቻችንን መቼ እናስታውሳቸዋለንና:: የለቅሶው ቀን ከንፈር ይመጠጣል፣ ይታዘናል፣ ይለቀሳል… በቃ!:: በለቅሶው ያልተገኙም ‘ለቅሶው ደምቆ ነበር?’ ብለው ጠይቀው ያልፋሉ:: ከዚያ በኋላ ስለ ሟች ማሰብ ‘ውሾን ያነሳ ውሾ’ ዓይነት ተረት ይመስል ማንም አያስባቸውም::

ጀግኖቿን የማታከብር አገር የሚለውን ትዝብታዊ ጽሁፍ ሳነብም ውስጤን ክፉኛ ያመሰው የአንድ ታላቅ ኢትዮጵያዊ አባት ከሞቱ በኋላ መዘንጋታቸውን ባሰብኩ ጊዜ ነበር:: በ2005 ዓ.ም ወደ ሰሜን ሸዋ ዞን ለሥራ ባቀናሁበት ጊዜ አዳሬን አዲስ አበባ አድርጌ ነበር:: በማግስቱ ጠዋትም አራት ኪሎ የሚገኘው ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ጐራ አልኩ::

ቅጥር ግቢውን ዘልቄ ስገባ በስተቀኝ በኩል በርካታ የመቃብር ስፍራዎችን /ሐውልቶችን/ አስተዋልኩ:: የደጅ አዝማች እገሌ፣ ፊት አውራሪ እገሌ፣ ጄኔራል… ይልና ከሐውልቶቻቸው ስር ትልቅ ታሪክ የሰራ፣ የተከበረ፣ የተወደደ… በተወለደ በዚህ ዓመቱ አረፈ:: ስም ከመቃብር በላይ ይውላል… የሚል

አጭር የህይወት ታሪክ በእብነበረድ ተቀርፆላቸው አስተዋልኩ::

የእነዚህ ጀግኖች ሐውልት ሊቆም የቻለው ልጅ በመውለዳቸው፣ ቤተሰብ ስላላቸው ካልሆነ በቀር ሳይወልዱና ሳያገቡ ወደ ጦር ሜዳ ዘምተው ቢሞቱ ወይም ድል አድርገው ተመልሰውም ልጅ፣ ቤተሰብ ካልመሰረቱ ሐውልት ሊቆምላቸው እንደማይችሉ አሰብኩ:: ሃገሬን ከጠላት ወረራ ደምተውና ቆስለው ነፃነቴን በደማቸው በአጥንታቸው አውጀውልኛል ብሎ ሐውልት የሚያቆም አይደለም የሚያስባቸው ትውልድ ይኖራል ብሎ መገመት ከባድ ነው::

… ወደ ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ልመልሳችሁ:: ግራዝማች፣ ቀኝ አዝማች፣ ፊት አውራሪ… እገሌ የሚለውን የመቃብር ስፍራ እያየሁ በቀኝ በኩል የክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰን ሐውልት አስተዋልኩ:: አንዳንድ ወጣቶች ሐውልቱን ተደግፈው ፎቶ ይነሳሉ፤ አድናቂዎቹ ናቸው መሰል:: እዚህኛው አጠገብ የጋዜጠኛ ተርጓሚና ደራሲ ማሞ ውድነህ፣ የደራሲ ክቡር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ሀውልት ቁሟል:: ‘አይዟችሁ አልሞታችሁም አልኩ’ ትተውልን ያለፉትን ስራዎቻቸውን እያሰብኩ::

በዚህ የሙታን መንደር ውስጥ ከአንድ መቃብር በስተቀር ሁሉም ሐውልት የቆመላቸው ናቸው:: በመቃብር ስፍራ ሆኖ ማሰብ ደስ ይለኛል:: ከአንዱ ፊታውራሪ መቃብር ሐውልት ሥር ቁጭ ብየ ማሰብ ጀመርኩ:: ሐውልቶች ሁሉ በአቅራቢያቸው ሐውልት አልባ ስለሆነው መቃብር የከፋቸው መሰለኝ:: ‘ከኛ በምን ያንሳል? ለዚህ ታላቅ ሰው ሐውልት አቁሙለት!’ ብለው ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ፣ በጩኸት የሚናገሩና ሰሚ አጥተው ያልሞትነውን አደራ በይ ትውልድ ብለው የሚወቅሱን መሰለኝ::

ከእነዚህ ሐውልት ከቆመላቸው መቃብር አጠገብ አፈር ብቻ ተቆልሎበት፣ ዳርና ዳር አራት እንጨቶች ቁመው በአንድ ዙር ብቻ ሽቦ ተጠምጥሞበት የተረሳ መቃብር አየሁኝ:: በራስጌው ላይም በቆራጣ ቆርቆሮ እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሚትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የሚል ጽሁፍ ሰፍሮበታል::

በ1924 ዓ.ም ተወልደው በ2004 ዓ.ም በ80 ዓመታቸው ያረፉት እኒህ አንኮበር ያፈራቻቸው ታላቅ ሰው በሀገራችን ከሚገኙ የሎሬት ማዕረግ ካላቸው አራት ሰዎች ውስጥ አንዱ ናቸው:: የኖቬል ሽልማት ሰአሊዎችን አያካትትም እንጂ፤ ቢያካትት ኑሮ ይህንን ሽልማት ሊያገኙ የሚችሉ ኢትዮጵያዊው የስነ ጥበብ ዋርካ፣ እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሚትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ይሆኑ ነበር:: እኒህ ታላቅ ሰው በሃገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚቀርቡ የስዕል አውደርዕዮች እና የስቴዶንድ ግላስ ስራዎቻቸው በክብር አንቱ እንዲባሉ አስችሏቸዋል::

በአያሌ ሺህ ዘመናት የሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ከየሃገሮቻቸው ሰንደቅ ዓላማ ጋር ምርጥ የፈጠራ ስራዎቻቸው ወደ ጨረቃ የተላኩላቸው ሁለት መቶ ሊቃነ ጠበብት እና ሊቃውንት አሉ:: ከእነዚህም ውስጥ አንዱና ብቸኛው ኢትዮጵያዊ፤ ስራዎቻቸው ከሃገራቸው ሰንደቅ ዓላማ ጋር ወደ ጨረቃ የተላኩላቸው ሊቀ ጠቢብ አፈወርቅ ወልደ ነጐድጓድ /እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሚትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ናቸው::

እኒህ የውጪ ሃገር ትምህርታቸውን ጨርሰው ዲግሪያቸውን ይዘው ወደኢትዮጵያ እንደተመለሱ ሚኒስትር መሆን ይችሉ ነበር:: ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ዲግሪ ያለው ኢትዮጵያዊ ከሆነ ይህን ማዕረግ ለማግኘት የሚሳነው አልነበረምና:: እሳቸው ግን በሙያቸው ሃገራቸውን ለማገልገል፣ ስሟን ለማስጠራት እንጂ ለስልጣን ጉጉት አልነበራቸውም::

አዲስ አበባ ውስጥ በተካነ ጠቢብ የተቀረፀ፣ ውብ ቀራፂ ግሩም ስራ ሲነሳ የዳግማዊ አፄ ሚኒልክ ሐውልት ይታወሳል:: ሐረር ከተማ ውስጥ ደግሞ የራስ መኮንን ወልደሚካኤል ሐውልት ድቅን ይልብናል:: ይህንን የሀረር ከተማ ያማረ የጥበብ ጌጥ ያነጿቸው የአፈወርቅ ወልደ ነጐድጓድ ጠቢብ አእምሮና ትጉህ እጆች ናቸው:: ዛሬ ግን አንኮበር የተወለዱት እኒህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ዋርካ በህይወት የሉም:: ሆኖም ግን ጽኑዕ ሥራ መሰረት ያለውን የጥበብ ዘር በኢትዮጵያዊያን ትውልዶች ልብና አእምሮ ላይ ዘርተው አልፈዋል:: ኢትዮጰያዊያን ትውልዶችም ክቡር ቅርሶቻቸውን እና ድንቅ ስራዎቻቸውን በእኛ ውስጥ ከእኛ ጋር ለዘላለም እንዲኖር አድርገዋል::

እኒህ ስራዎቻቸው ጨረቃ ላይ ከነሃገራቸው ሰንደቅ ዓላማ በክብር የተላከላቸው ስማቸውን ጨረቃ ላይ ያፃፉት ብቸኛው ሰአሊ፣ ቀራፂ፣ ክቡር ኢትዮጵያዊ የጥበብ ሰውን የተቆለለባቸውን የመቃብር አፈር አየሁ፤ አፈርኩ:: ስማቸውን ጨረቃ ላይ ያፃፉት ሰው በመቃብራቸው ላይ በደብዛዛ ቀለም፣ በቆራጣ ቆርቆሮ “እንጀራ አለ”፣ “ሹርባ እንስራለን”… እንደሚባል የመንደር ማስታወቂያ እንኳን አልተጨነቁበትም፤ እናም ከመቃብር መንደር ውስጥ ሁኜ አዘንኩ… አሰብኩም::

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሚትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ከመሞታቸው በፊትና በኋላ የነበራቸውን የሃገር ፍቅር፣ ሙያ ክብር፣ እውቀት ባህል… እና ስራዎቻቸውን አሰብኩ:: ሳይሞቱ በዙሪያው ያሸረግዱና፣ ይወድቁ ይነሱላቸው የነበሩትን ሰዎችም አሰብኩ:: ከሞቱ በኋላ ግን አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት ቀን ተለቀሰ፣ ከንፈር ተመጠጠ… በቃ!::

እኒያ! ሐውልት ቀራጭ… እኒያ! ጥበበኛ፣… እኒያ!

ውለታ ቢስ ትውልድ

Page 8: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 8 ዜና ትንታኔ

ወደ ገጽ 32 ዞሯል

ጌታቸው ፈንቴ

ኢንተፕራይዞች የሚገባንን ድጋፍ ተነፍገናል አሉ

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት በሀገራችን የግብርና መር ኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ላይ ተመስርቶ የራሱ ፕሮግራምና ዝርዝር የድጋፍ ፓኬጅ ተዘጋጅቶለት ተግባራዊ መሆን ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል::

በቆይታውም ለስራ አጥ ዜጐችና በተለያዩ የምርትና የአገልገሎት ስራዎች ለተሰማሩ በርካታ ኢንተርፕራይዞች የሚያስፈልጋቸውን የማደራጀት፣ የማሰልጠን፣ የፋይናንስ ድጋፍ፣ የማምረቻና መሸጫ ቦታ አቅርቦት እና የገበያ ትስስር ድጋፎች እንዲያገኙ በማድረግ ሰፊ የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩና ለድህነት ቅነሳ ፕሮግራሙ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ታልሞ እየተሠራ ነው::

የአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችን የደረጃ ሽግግርና ልማት ትኩረት ተሰጥቶት የመደገፋቸው ምክንያትም ዋነኛዎቹ የስራ ዕድል መፍጠሪያ መስኮች፣ የልማታዊ ባለሀብቶች መፍለቂያዎች፣ የልማታዊ መንግስት መሠረቶች እና ቀጣይነት ያለው የቴክኒዮሎጅ ልማት የሚካሄድባቸው መሆናቸው ነው::

“የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዞች ልማት ሽግግር ለህዳሴያችን!” በሚል መሪ ቃል ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ የኢንተርፕራይዞች በዓል ተከብሯል:: ለአምስት ቀናት በቆየው በዚሁ በዓል ላይ ከተከናዎኑ ተግባራት መካከል ወደ መካከለኛ ደረጃ በተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች ፋይዳ፣ ተግዳሮትና መፍትሄ ላይ ለመምከር የተጠራው የፓናል ውይይት አንዱ ነው::

ውይይቱ ከጐንደር ዩኒቨርሲቲና ከአማራ ክልል ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የተውጣጡ ባለሙያዎች ያቀረቡትን መለስተኛ የዳሰሳ ጥናት መሠረት አድርጐ ነው የተካሄደው::

የባለሙያዎቹ ጥናት እንዳመለከተው የመጀመሪያው አምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሚሽን ዕቅድ ዘመን በማኑፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን፣ በከተማ ግብርና፣ በአገልግሎት እና ንግድ ዘርፍ 213 ሺህ 656 ኢንተርፕራይዞች ተቋቁመዋል::

እነዚሁ አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች የሚያስፈልጋቸውን የመስሪያና መሸጫ ቦታ ለማሟላትም መንግስት 4 ሺህ 677 ሸዶች እና 66 ህንፃዎችን ገንብቶ በተመጣጣኝ የኪራይ ዋጋ ከማዘጋጀቱም በላይ ወደ 24 ሚሊዮን ካሬ ሜትር የሚጠጋ የለማ ቦታ ለ154 ሺህ 985 አንቀሳቃሾች ማቅረብ መቻሉን ጥናታዊ ጽሁፉ አትቷል::

የቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ባለፉት አምስት አመታት ጥራት ያለው

ስልጠና በመስጠትና ስራ ፈላጊ ዜጐችን አደራጅቶ የሥራ እድል በመፍጠር ዙሪያ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ከአጋር አካላት ጋር የጋራ ዕቅድ ነድፎ በመንቀሳቀሱም ከመንግስትና የግል ኮሌጆች የተመረቁ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሥራ ፈላጊዎች አጫጭር ስልጠናዎችን እንዲያገኙ አድርጓል::

በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት የኢንተርፕራይዞችን ምርትና ምርታማነትን የሚያሻሽሉ 561 ዓይነት ቴክኒዮሎጂዎች መሸጋገራቸውንና ከ107 ሚሊዮን በላይ ሀብት ማፍራት መቻሉንም የጥናቱ አቅራቢዎች አመልክተዋል::

የኢንተርፕራይዞቹን የፋይናንስ ፍላጐት ከማሟላትና አቅማቸውን ከማጠናከር አንፃር በተለይ የቁጠባ ልምድ እንዲኖራቸው ግንዛቤ በመፍጠር ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ቆጣቢዎች አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር መሰብሰቡንና ወደ 468 ሺህ የሚጠጉ አንቀሳቃሾችን የብድር ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም በአዎንታዊነት አስቀምጦታል- ጥናቱ::

በገበያ ልማትና ግብይት ዘርፍ ባለፉት አምስት አመታት የስድስት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ብር የገበያ ትስስር በመፍጠር ከ741 ሺህ በላይ አንቀሳቃሾችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል:: የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት ለማቅረብ ሀገራችንና ክልላችን ከውጪ ያስገቡት የነበረውን ምርት መተካት መጀመራቸውና የውጪ ምንዛሬን ማስቀረት ማስቻሉም ከኢንተርፕራይዞቹ ስኬቶች አንዱ መሆኑ ተጠቅሷል::

ኢንተርፕራይዞቹ ከውጪ ይገባ የነበረን ምርት በመተካት ሳይወሰኑ ጥራት ያለው ምርት በማዘጋጀት ወደ ውጪ ሀገር በመላክ በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪና ትርፋማ ለመሆን በተደረገ ጥረትም የ16 ኢንተርፕራይዞች ምርት ወደ ውጪ ተልኮ ወደ 166 ሺህ የሚጠጋ የአሜሪካ ዶላር የውጪ ምንዛሬ መገኘቱም ተጨማሪ ስኬት ነው ተብሏል::

ሞዴሎችን በመለየትና ተሞክሮን ቀምሮ በማስፋት በኩል በእቅድ ዘመኑ ከተፈጠሩት 4 ሺህ 800 ያህል ሞዴል ኢንተርፕራይዞች መካከል የ1 ሺህ 623ቱ ተሞክሮ ተቀምሮ ወደ 28 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች ማስፋት መቻሉም ተጠቃሽ ስኬት ነው ብሏል - የጥናቱ ሪፖርት::

እነዚህን ሁሉ ስኬቶች ተከትሎ ሰሞኑን እውቅና አግኝተው የተሸጋገሩትን 97 ኢንተርፕራይዞች ጨምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት ለክልሉ 943 ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እያንዳንዳቸው ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ ካፒታል በማፍራት ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝነት መሸጋገራቸው በእቅድ ተይዞ ከነበረው 650 ቁጥር

አንፃር እጅግ ከፍተኛ ስኬት እንደሆነ ተሠምሮበታል::ባለፉት አምስት አመታት በአማራ ክልል

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢነተርፕራይዞችን በማቋቋምና በመደገፍ ኢንተርፕራይዞቹ ለበርካታ ዜጐች የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙ ጥራት ያላቸውና ተወዳዳሪ ምርቶችን ለገበያ እያቀረቡ፣ አትራፊና ቆጣቢ እንዲሆኑ ተደርጓል::በተደረገው ጥረትም ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል አፍርተው ወደ መካከለኛ ደረጃ ኢንተርፕራይዝነት እንዲሸጋገሩ በማድረግ በኩል ስኬታማ የሚባሉ ተግባራት ተፈጽመዋል:: ይሁን እንጂ ኢንተርፕራይዞቹ ወደ መካከለኛ ደረጃ ከተሸጋገሩ በኋላ ግን ትኩረት ተነፍጓቸው በችግር መሸበባቸውን ጥናቱ ዋቢዎችን እየነቀሰ አመላክቷል::

ከተግዳሮቶቹ መካከልም የመስሪያና የመሸጫ ቦታና የፋይናንስ አቅርቦት መጓደል፣ መሠረተ ልማት አለመሟላት፣ የአጋር አካላት አለመቀናጀትና የክትትልና ድጋፍ እጦት ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ጥናቱ አመላክቷል::

የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾቹ በበኩላቸው በጥናቱ የቀረበው ችግር እውነትና በስራቸው ላይ ከፍተኛ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን አብራርተዋል::

ከከሚሴ አካባቢ ከመጡት ኢንተርፕረይዝ አንቀሳቃሾች መካከል አብዱልከሪም ኢብራሂም እንደተናገረው አሉሙኒየም እያቀለጠ ብረት ድስት በማምረት ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል አፍርቶ ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ደረጃ አሳድጓል::

ምርቱንም ሾንኬ ፕላስቲክ ማምረቻ በተባለው ድርጅቱ አማካኝነት ደቡብ ሱዳን ድረስ ሄዶ ገበያ ትስስር መፍጠር ቢችልም በመካከለኛ ኢንተርፕራይዝነት ሊያገኝ የሚገባውን መንግስታዊ ድጋፍ ማግኘት አለመቻሉ በስራው ላይ ትልቅ እንቅፋት እንደሆነበት ተናግሯል::

“ይኼን ውሃ ምን ያስጮኸዋል? ቢባል ከውስጡ ያለው ደንጋይ ነው እንጂ” በሚል ምሳሌያዊ አባባል ሀሳቡን ያጀበው አብዱልከሪም የመስሪያ ቦታ እጦት፣ ብድር አቅርቦትና ቢሮክራሲያዊ አሰራር ኢንተርፕራይዞችን እያስጮሃቸው እንደሆነ ተናግሯል::

ከደብረብርሃን ከተማ የመጣችው ወ/ሪት ሶፊያ መሀመድ በጨርቃ ጨርቅ ልማት ዘርፍ ተሰማርታ ከጥቃቅንና አነስተኛ ወደ መካከለኛ ደረጀ የተሸጋገረች ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሽ ነች::

ወ/ሪት ሶፊያ እንደምትለው ኢንተርፕራይዞቹ ወደ መካከለኛ ደረጃ ከተሸጋገሩ በኋላ እገዛ እያገኙ አይደለም:: ለአብነትም ለኢንተርፕራይዞቹ ብድር

ከሚያቀርቡት አጋር አካላት አንዱ የሆነው አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ሄዶ የብድር አገልግሎት ለማግኘት ያለው ውጣ ውረድ አሰልቺና ስራ አስፈቺ ነው፤ ውጣ ውረዱን አልፈውም ቢሆን የሚጠየቀው ዋስትና ከፍተኛ፣ የሚፈቀደው የብድር መጠን ደግሞ እጅግ አነስተኛ ነው ብላለች::

አብቁተ የሚጠይቀውን ያህል ዋስትና ማቅረብ ከቻልንማ ከሌሎቹ ባንኮች በአነስተኛ ወለድ መበደር ምን ያቅተናል? ስትልም ጠይቃለች፤ የወለዱ መጠን ከፍተኛ መሆኑ ሌላው ተግዳሮት መሆኑን በመጥቀስ::

ከጐንደር ከተማ በመኪና አካል ሥራ የተሰማራው አንድ የመካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሽ ደግሞ በሁለተኛው ዙር የደረጃ ዝውውር ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝነት ሲያድጉ 500 ካሬ ሜትር የመስሪያ ቦታ እንደሚሰጣቸው ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ቃል አንደተገባላቸው ገልጿል:: የተገባላቸው ቃል በሌሎች አካባቢዎች ተግባራዊ ሲደረግ ጐንደር ላይ “የክልሉ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ‘እንዳትሰጡ’ የሚል ደብዳቤ ጽፎልናል” በሚል የከለከሏቸው መሆኑን ገልጿል::

በውይይቱ ላይ የተገኙት በአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም(አብቁተ) የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክ/ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አጋዠ ጌታሁን የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ለብድር አስተማማኝ ዋስትና መጠየቁ የህዝብን ገንዘብ በአግባቡ ለመጠበቅ ሲባል በመሆኑ ጽሁፍ አቅራቢዎቹም ሆኑ አንቀሳቃሾቹ እንደጥንካሬ እንጂ እንደ ችግር ሊቆጥሩት አይገባም ብለዋል:: ይሁንና የብድር መጠኑን ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾቹ በሚያቀርቡት ዋስትና ልክ ለማቅረብ እንደማይቸገሩ ተናግረዋል::

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የባህርዳር ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበሩ አስማማው ባንኩ ኢንተርፕራይዞች ዘጠኝ በመቶ ወለድ በመክፍል የሚጠቀሙበት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በመንግስት የተመደበለት ስለሆነ ለብድር የሚመጡ ኢንተርፕራይዞችን ለማገልገል የተዘጋጀ መሆኑን ይፋ አድርገዋል::

በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ላይ ለተነሱ ችግሮች ምላሽ የሰጡት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለስልጣን የሰሜን ምእራብ ሪጅን የሪቴል ቢዝነስ ኃላፊ አቶ አስመላሽ በዛብህ ናቸው:: እሳቸው አንዳሉት የችግሩ ዋነኛው መንስኤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያጋጠመው የኃይል አቅርቦት እጥረት መሆኑን በመጥቀስ አንቀሳቃሾቹ ችግሩን ተረድተው ለተወሰነ ጊዜ እንዲታገሱ ጠይቀዋል::

በግለሰቦች የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮችን ግን በክልል ደረጃም ኮሚቴ የተዋቀረ በመሆኑ እየገመገሙ በመገምገም በችግር ፈጣሪዎች ላይ ርምጃ እንደሚወስዱ ገልጸዋል:: አድሎና ፍትሃዊ ያልሆነ አሰራር ሲያጋጥማቸው እንዲጠቁሙም አሳስበዋል::

የጐንደር ከተማ ኢንተርፕራይዞች ቃል የተገባላቸው ቦታ እንዳይሰጥ ደብዳቤ የፃፈው የክልሉ ንግድ ኢንዱስትሪና ገበያ ልማት ቢሮ ደግሞ “እገዳውን የጣለው ኢንተርፕራይዞቹ የደረጃ ሽግግር ያደረጉት ሳያሟሉ በመሆኑ ነው” የሚል ምላሽ ሰጥቷል:: ይሁንና ለኢንተርፕራይዞቹ የደረጃ ሽግግርን ከሚያጸድቁና እውቅና ከሚሰጡ አጋር አካላት አንዱ ራሱ የቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮና ንግድ ኢንዱስትሪና ገበያ ልማት ቢሮ ሆኖ ሳለ “እውቅና የተሰጣቸው ሳያሟሉ ነው” ማለቱ ትክክለኛና ፍትሃዊ እንዳልሆነ መድረኩን የመሩት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም ተናግረዋል::

ለሞዴል ኢንተርፕራይዞች ሽልማት ሲሰጥ

Page 9: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 9በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ማህበራዊአጫጭር ዜናዎች

ወደ ገጽ 28 ዞሯል

ትኩረት - ትኩረት

ለሚሹትሱራፌል ስንታየሁ

የምሳ ለትምህርት ኘሮግራም ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ እንደረዳቸው በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ የኘሮግራሙ ተጠቃሚ ህፃናት ተናገሩ::

በወረዳው አብሰላ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአንዲት በጎ አድራጊ ግለሰብ የህፃናት ምገባ መርህ ግብር ተጀምሯል፣70 ህፃናትም ተጠቃሚ ሆነዋል::

ወይዘሮ አጀቡሽ በዙ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ በተወለዱበት ወረዳ የበጐ አድራጐት ስራውን የጀመሩት ህፃናት በአመጋገብ ስርዓት ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይነጠሉ በማሰብ እንዲሆነ ተናግረዋል::

በቀጣይም የምሳ ኘሮግራሙን ወደ ቁርስ ለማሳደግ ማሰባቸውን የገለፁት ወይዘሮ አጀቡሽ ኘሮግራሙን ውጤታማ ለማድረግና ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር መንግስትና ህብረተሰቡ ከጐናቸው ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል::

ተማሪ አዲሱ ፈጠነና ምሳ አንዷለም በምገባ ኘሮግራሙ ተሳታፊ መሆናቸው ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉና ውጤታማ እንዲሆኑ እንደረዳቸው አስረድተዋል::

የአብስላ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ አየሁ ምህረት በበኩላቸው ከኘሮግራሙ መጀመር በፊት ህፃናት ትምህርታቸውን ለመከታተል ይቸገሩና ያቋርጡ እንደነበር አስታውሰው ከኘሮግራሙ መጀመር በኋላ ግን ህፃናት በትምህርታቸው ውጤታማ እንደሆኑ ጠቁመዋል::

የመፅሃፍ እጥረት ችግርን

መፍታት አልተቻለም

የመፀሐፍ እጥረትና የክፍል ጥበት በትምህርታቸው ላይ እንቅፋት መሆኑን የሰቆጣ ወረዳ የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ገለፁ::

የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነው ብሩክ ኪሮስ በመፅሃፍ እጥረት ምክንያት የቤት ስራ ሳንሰራ እና በክፍል ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ለመሆን ቀድመን ሳናነብ በመግባታችን እየተጎዳን ነው ይላል::

ያም ሆኖ ተማሪዎች ችግሩን ለመፍታት በየ አደረጃጀታቸው የጥናት ክፍለ ጊዜ በማውጣት እየተረዳዱ መሆኑን ተማሪ ብሩክ ተናግሯል:: በክፍል ጥበት ምክንያት በዳስ ውስጥ እየተማሩ መሆኑን ደግሞ ሌላው ተማሪ ቢሰጠኝ ያለው ገልፆል::

አቶ በሪሁን መሃሪ የሰቆጣ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ በብሄረሰብ አስተዳደሩ በሚገኙ ስድስት ወረዳዎች የመማሪያ ክፍሎች እጥረት እና በኸምጠኛ ቋንቋ በሚሰጡ የትምህርት አይነቶች እንዲሁም በአንዳንድ የትምህርት አይነቶች የተማሪ መፅሃፍ ጥምርታው ዝቅተኛ መሆኑን ገልፀዋል::

ይህም በትምህርት ጥራቱ ላይ አሉታዊ ተፅፅኖ እያሳደረ መሆኑን ተናግረዋል:: የመፅሃፍ እጥረት እንዳለ ብናሳውቅም በህትመት እጥረት እስከ አሁን መድረስ አልቻለም ብለዋል::

በቀጣይ ግን እነዚህን ችግሮች ለማቃለል ቅድመ ዝግጅቶች የሚደረጉ መሆኑንና መፅሃፍቱ የማይደርሱ ከሆነ በኮፒ ለማዳረስ ይሞክራል ማለታቸውን ባልደረባችን ግርማ ተጫነ ዘግቧል::

የትምህርት ቤት

ምገባ ተጀመረየአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በመልካም

አስተዳደር ዙሪያ በነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ባካሄደው ህዝባዊ ውይይት “እንደሌሎች ተማሪዎች ለእኛ ትኩረት እየተሰጠን አይደለም:: ቁጥራችን በየትምህርት ቤቱ ከመቶ እጅ አንድ እንኳን አይበልጥም:: ሆኖም ግን በርካታ ቁጥር ላለው ተማሪ የመማሪያ መሣሪያዎች እየተሟላለት ለአነስተኛ ተማሪ የመማሪያ መሣሪያዎች ሊሟሉልን አልቻለም? ነገ ከነገ ወዲያ ሌላ አካባቢና ክልል ከሚኖሩ ተማሪዎች ጋር ነው የምንወዳደረው:: እናም ልፋታችንን ከንቱ ባታስቀሩብን?…” በማለት ጥያቄ ያነሳው ተማሪ ትዝ አለኝ አይነ ስውር ተማሪ ነው::

ጥያቄው ‘ይህ ችግር በነፋስ መውጫ ከተማ ብቻ ነው ወይስ በሌሎች አካባቢዎችም ይስተዋላል’ የሚል ጥያቄ ፈጠረብኝ:: እናም በሚያዝያ ወር ወደ ሰሜን ሽዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ሳቀና ጥያቄውን የሰራየ አካል አደረኩት:: ይህንኑ ለመቃኝትም በአረርቲ ከተማ ወደሚገኘው ፊታውራሪ ታደሰ ጌታ ብቻ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ዘለኩ::

አይነ ስውራን ተማሪዎች የሚገኙበትን መማሪያ ክፍል ጠያይቄ ተነገረኝና ወደ ክፍላቸው ጐራ አልሁ፡፡ ከ 10 የሚበልጡ ተማሪዎች በአንድ ክፍል ቁጭ ብለው አገኘኋቸው ሆኖም ግን እንዳየኋቸው ደነገጥሁ፡፡ ምክንያቱም ዓይነስውር ያልሁኑ ተማሪዎችን በማየቴ ነው፡፡ መምህርቷን ስጠይቃት “መስማት የተሳናቸው ናቸው“ አለችኝ፡፡ እንደገና ተገረምሁ፣ ደነገጥሁ፡፡ ማየት የተሳናቸውንም መስማት የተሳናቸውን እንዴት ባንድ ላይ ማስተማር

ይቻላል እያልሁ ማውጣትና ማውረድ ጀመርሁ፡፡ ይባስ ብሎ ደግሞ የትምህርት ደረጃቸውን

ስጠይቃቸው የተለያየ ነው:: አምስተኛም፣ ስድስተኛም ክፍሎች በአንድ ላይ ትምህርት ይሰጣቸዋል:: የመቀላቀላቸውን ምክንያት ለግሌ እያሰብኩ ተማሪዎችን በመማር ማስተማሩ ላይ ያለውን ሁኔታ እንዲያጫወቱኝ ጋበዝኳቸው:: የአራተኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ይትባረክ ዓለም “የምንማርበት መፅሃፍ የተሟላ አይደለም:: በቃል የሚያስተምሩንን ብቻ በመስማትና በማስተወስ ነው የምንማረው:: በተደጋጋሚ ጠይቀን ‘ይሟላላችኋል’ ይሉናል:: ሆኖም ግን እስከ አሁን ምንም ነገር የለም” አለኝ::

የስምንተኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ደረጀ ተስፋዬም “መፅሃፍ የለም:: እናም መምህራን ለሚያዩ ተማሪዎች በሚያስተምሩበት ልክ ትምህርት ስለሚሰጡ ተቸግረናል” ሲል የይትባረክን ሀሳብ ያጠናክራል:: በተለይም መምህሩ ስለሚፈጥን ለአይነ ስውራን በፍጥነት ሰምቶ ማስታወሻ ለመያዝ እንደሚቸገሩም ተማሪ ደረጃ ተናግሯል:: ለአይነ ስውራን የተዘጋጀ መፅሃፍ ቢኖር እሱን አንብበው መረዳት ይቻለ እንደነበርም ገልፀዋል፣ ሆኖም ግን

በልዩ ፍላጐት መማሪያ መፅሃፍ እጥረት ተቸግረናል የሚሉት የፊታውራሪ ታደሰ ጌታ ብቻ ት/ቤት ተማሪዎች

“የምንማርበት መፅሃፍ የተሟላ አይደለም::

በቃል የሚያስተምሩንን ብቻ በመስማትና

በማስተወስ ነው የምንማረው:: በተደጋጋሚ

ጠይቀን ‘ይሟላላችኋል’ ይሉናል:: ሆኖም

ግን እስከ አሁን ምንም ነገር የለም”

Page 10: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 10

ሳምንቱ በታሪክታሪክ

የሀዋይ ደሴት በሱናሚ መመታት

(ታምራት ሲሳይ)

አዲሱ አያሌው

የሮናልድ ሬገን የካሊፎርኒያ ገዥ

መሆን

የነፃነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ በደቡብ አፍሪካ ከታሰሩበት የሮቢን ደሴት “ትግላችሁን ቀጥሉ” የሚለው መልዕክታቸው በድብቅ ወጥቶ ለጥቁር አፍሪካውያን የተሰማው በዚህ በያዝነው ሳምንት 1980 እንደውሮፓውያን አቆጣጠር ነበር::

በ1952 የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ መሪ የሆኑት ማንዴላ “ሰላማዊ አመጽን፣ የስራ ማቆም አድማን፣ ሰልፎችንና ሌሎች ተቃውሞዎችን በጥቂቶቹ ነጮች ላይ አነሳስተዋል” በሚል ለእድሜ ልክ እስራት ወህኒ ወርደው እንደነበር ይታወሳል::

የኔልሰን ማንዴላ መልዕክት

የቀድሞው ተዋናይ ሮናልድ ሬገን በአገር አሜሪካ የሪፕብሊካን ፓርቲን በመወከል የካሊፎርኒያ ግዛት ገዥ የሆኑት በዚህ በያዝነው ሳምንት 1966 እ.ኤ.አ ነው:: በዚሁ ሂደትም ኋላ ፕሬዝዳንት ሆነው ለመመረጥ ሁኔታዎችን አመቻችተዋል:: ቀደም ብሎ የዴሞክራት ፓርቲ ተከታይ የነበሩት ሬገን እያደር ቅር የተሰኙባቸው ፖሊሲዎች በመኖራቸው ወደ ሪፕብሊካን ፓርቲ ገብተው ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድረው ለማሸነፍ በቅተዋል::

የ6ቀኑ ጦርነት በጋዛ ሰርጥ መቀስቀስእስራኤል በድንበሯ አካባቢ ስጋት በሆኑባት

የአረብ ሀይሎች በተለይም በግብጽና በሶሪያ ላይ ጥቃት በማካሄድ የአፀፋ ምላሽ የሰጠችው በ1967 እ.ኤ.አ በያዝነው ሳምንት ነው::

ከጥቂት ቀናት በኋላ የተባበሩት መንግስታት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ቢወሰንም እስራኤል ቀደም ብሎ ከያዘቻቸው የጋዛ ሰርጥ፣ ምስራቅ እየሩሳሌምና በጆርዳን ሰር ከነበሩት በተጨማሪ በዕጥፍ ግዛቷን በኃይል አስፋፍታ ይዛ ነበር::

በቺሊ ጠረፍ አካባቢ የተፈጠረው የመሬት መንቀጥቀጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ቺሊያውያንን ህይወት አጥፍቶ ያስነሳው ከፍተኛ ማዕበል የፓስፊክ ውቅያኖስን ተሻግሮ የሀዋይ ደሴትን በመምታት ለ61 ሰዎች ህልፈት መንስኤ የሆነው በዚህ በያዝነው ሳምንት 1960 እ.ኤ.አ ነበር::

የሱናሚ ማዕበሉ በምዕራብ ፓስፊክ ውቅያኖስን ተሻግሮ የጃፓን ደሴቶችንም በመምታት ከ180 በላይ ዜጐችዋን ለህልፈት ሲያበቃ ከ50 ሺህ በላይ ዜጐችዋን ቤት አልባ አድርጓል::

አውሮፓዊቷን ሀገር እንግሊዝን እና የደቡብ አሜሪካዊቷ አርጀንቲናን ለጦርነት አሰልፈው አጠዛጥዘዋል፤ የፎክ ላንድ ደሴቶች:: ታዲያ በእነዚህ ደሴቶች የይገባኛል ጥያቄ ጦርነት ውስጥ የገቡት እነዚህ ሁለቱ አገራት አንዳቸው የሌላቸውን ወታደራዊ አሰላለፍ እና የሚገኙ በትን አቅጣጫ አጣርተው ለማወቅ የወታደራዊ ስለላ ማድረግ አስፈላጊያቸው እና ወሳኙ ነገር ነበር:: ስለሆነም እነዚህ ሁለት አገራት ለጦርነት ተሰልፈውባቸው በነበሩ ጊዜያት ወታደራዊ ስለላን በመጠቀም መረጃን ለማግኘት ከሚያዝያ እስከ ሰኔ 1982 ዓ.ም ባሉት ሶስት ወራት የተለያዩ አገራት ያከናወኑት ተግባር ወደር የሌለው እንደነበር ይነገርለታል:: ታዲያ እኛም ለዛሬ ስለዚህ ታሪካዊ ሁኔታ በመጠኑ ልናስነብባችሁ ወደድን::

በወቅቱ በሁሉም አገራት መካከል ማለትም በእንግሊዝና በአርጀንቲና መካከል የተደረገው ጦርነት በፖለቲካ ግፊት የታጠረ እና እጅግ ዘመናዊ በሆኑ መሳሪያዎች የተቀለጣጠፈ ነበር:: ታዲያ ጦርነቱ በእንዲህ ያለ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም በዘመናዊው ሚሳኤል ከሚደርሰው ጉዳት ይልቅ በፖለቲካው

ፈጣኖቹ የመረጃ ልውውጦች

በኩል የሚደርሰው ውጥረት የባሰ ነበር:: በመሆኑም ይህን የፖለቲካ ውጥረት ለመሻገር ከሚሳኤል በላቀ ፍጥነት ትክክለኛ መረጃ የሚያስፈልግበት ጦርነት ሆነ::

በወቅቱ የአርጀንቲናን የራዳር ፍጥነትና የአሰላለፍ መስመር መጠን እንግሊዝ ከፍተኛ የማወቅ ጉጉት ነበራት:: የእንግሊዝ የባህር ሀይል ተወርዋሪ ጦር ብዛት፣ አሰላለፍ መጠንና ጦርነቱን በየትና መቼ እንደሚጀምሩት ለማወቅ ደግሞ አርጀንቲና ከፍተኛ ጥረት ታደርግ ጀመር:: ይህን ለማድረግ የሚጠቀሙባቸው ዘመናዊዎቹ የኤሌክትሮኒክስ የስለላ መሳሪያዎች ያስተላልፏቸው መረጃዎች መደነጋገርና ግራ መጋባቶችን እየፈጠሩባቸው የተቸገሩ ስለሆነም ሁለቱም ወገኖች ከተወሳሰቡ የኤሌክትሮኒክስ ዘመናዊ የስለላ መሳሪያዎች ይልቅ ጥንታዊውን የስለላ ዘዴ መከተሉን መረጡ::

በዚህም መሰረት ማለትም ጥንታዊውን የስለላ ዘዴ በመጠቀም እንግሊዝ የአርጀንቲና ጦር ስታንሊይ የተባለችውን ደሴት ከመያዙ ሁለት ሳምንት አስቀድመው ቦነስ አይረስ ውስጥ የነበሩ የእንግሊዝ የመረጃ ሰራተኞች ጠቅላላውን የአርጀንቲናን የጦር ስልት ለማግኘት ቻሉ:: ይሁን እንጂ የዚህ መረጃ

ሪፖርት የደረሳቸው የእንግሊዝ ባለስልጣኖች እምነትና አስተሳሰብ ጋር ሊዋሀድ ባለመቻሉ ባግባቡ ስላልተጠቀሙበት ብዙም ውጤት ሳያመጣ ቀርቷል:: ይሁን እንጂ የእንግሊዝ የመረጃ ሰራተኞች ግን እዚያው አርጀንቲና ውስጥ ሆነው ያጠራቸውን ከመቀጠል ወደ ኋላ ኣላሉም:: የኋላ ኋላ ጦርነቱ አይቀሬ መሆኑ ሲታወቅ ግን የእንግሊዝ ሰላዮች የመረጃውን ጣጣ ጥንታዊው አሰራር አውጥተው መልሰው ለዘመናዊው ኤሌክትሮኒክስ መረጃ መለዋወጫዎች በመተው ከአርጀንቲና ወጡ::

በወቅቱ የዘመናዊዎቹ የኤሌክትሮኒስ የመረጃ መለዋወጫ ባለቤቶች የነበሩት ደግሞ ሀያላኑ አሜሪካ እና የቀድሞዋ ሶቬት ህብረት ናቸው:: የእነዚህ የሁለቱ አገሮች ሳታላይቶች ከሰማይ ላይ ሆነው መሬትን ቁልቁል እየተመለከቱ የሰበሰቡትን መረጃ ወደየሀገሮቻቸው ያስተላልፋሉ:: በመሆኑም እንግሊዝና አሜሪካ መረጃን ለመለዋወጥ ቀደም ብለው የተፈራረሙት ውል ስለነበራቸው በውሉ መሰረት አስፈላጊውን መረጃ እየሰበሰበች እንድታካፍላት እንግሊዝ አሜሪካንን ጠየቀች:: አሜሪካም በውሉ መሰረት ተስማማች::

እንግሊዞች የራሳቸው መረጃ ከአሜሪካ እንደሚያገኙ እርግጠኛ በመሆናቸው ቢደሰቱም ሌሎች ራስ ምታት ግን ነበረባቸው:: ይሄውም በወቅቱ ሶቬየት ህብረት የምትሰበስባቸውን መረጃዎች ለአርጀነቲና የመስጠቷንና አለመስጠቷን ጉዳይ እርግጠኛ መሆን አለመቻላቸው ነበር እንቆቅልሽ የሆነባቸው ጉዳይ:: እነዚህ ሁለት ነገሮች ናቸው እንግሊዞችን ግራ ያጋቧቸው:: የመጀመሪያው ሶቬት ህብረት ከአርጀንቲና ጋር የንግድ ስምምነት ስለነበራት እህልና ሥጋ ስታስገባ ኖራለች:: በመሆኑም ለንግድ አጋሯ የስለላ መረጃውን ታበረክት ይሆናል የሚል ስጋት አለ:: በሌላ በኩል ደግሞ በወቅቱ በአርጀንቲና እና በሶቬት ህብረት መካከል ሰፊ የፖለቲካ ርዕዬተ ዓለም ልዩነት የነበረ መሆኑ መረጃ

ወደ ገጽ 34 ዞሯል

ማረሚያግንቦት 15/2008 ዓ.ም ዕትም በሳምንቱ

በታሪክ አምድ በወጣው ሩዋንዳን የተመለከተ መጣጥፍ ተበቃዮች ቱስቲዎች ናቸው የሚለው በስህትት ስለሆነ ተበቃዮች የሁቱዎች ጐሳ አባል መሆናቸውን ከይቅርታ ጋር እንጠይቃለን፡፡

Page 11: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 11በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ጥበብ

ወደ ገጽ 36 ዞሯል

ከመፃሕፍት ገፆች

“በዛሬው ዘመን ሳይጋቡ መፋታት በተማሩት ሰዎች ውስጥ ተጋብቶ መፋታት ባልተማሩት፣ ውስጥ ይበዛል:: በኔ አስተያየት ሳይጋቡ መፋታት በተማሩት ሰዎች ውስጥ የሚበዛበት፣ ምክንያት ልቡሰ ጥላቸው ተመሣሣይ ስለማይገኝለትና አስቀድሜ እንዳጫወትሁሽ- በመጀመሪያ በወረቀት ማስፈር የሚገባቸውን የልቡሰ ጥላቸውን መግለጫ ስለሚዘነጉ ነው-- በትሆናለች ፣ በምስቅልቅል ልቡሰ ጥላ እየተመሩ እውነተኛ ልቡሰ ጥላቸው የሠነዘረውን እየተዉ፣ በዓይን ዐዋጅ ስለሚመሩ-- እንዳጫወትሁሽ ማለት ነው…” እያለ፣ ያመጣዋል አደፍርስ ጥላ እንደ በረዶ ካጥር ውጭ ሲዝናና ፂወኔን ባህርማሽላ እሸት ስትቆርጥ፣ ያያትና ጠጋ ብሎ ቆረጣውን እየረዳት ሲያወራ… ፂወኔ፣ ስለነበረ አነጋገሩ ባድናቆትና ባክብሮት ዓይን እየተመለከተች ነበር የምታዳምጠው…

“… ከተጋቡ በኋላ የሚፋቱት ከየቦታው እየመጡ ከተማውን የሚያጣብቡት ወንዶችና ሴቶች ምክንያት ግን ምን ይመስልሻል?... ባባትና እናቶቻቸው ልቡሰ ጥላ ትይዩ ተመሥርቶ የነበረው ልቡሰ ጥላቸው ድንገት እከተማ በመምጣት ስለሚያድግባቸው ነው::

አደፍርስከዳኛቸው ወርቁ

“ሰው ሥራ የሚገባው በ2፡30 ነው:: አንተ ሁል ጊዜ በለሊት እየተነሳህ የምትኸደው ኸት ነው?” አሉት ወይዘሮ አስማሩ እናውጋው፤ የ30 ዓመቱ ልጃቸው ፀደቀ ታየ እንደተለመደው ከንጋቱ በ11፡30 ተነስቶ ከቤት ሊወጣ ልብሱን ሲለባብስ ሁኔታው በእጅጉ እያሳሰባቸው::

ይልቁንስ ጥያቄውን ተይውና የሚቀመስ ነገር ካለ ስጪኝ” አላቸው፤ ከእናቱ አልጋ አጠገብ ካለች ኩርሲ ላይ ቁጭ ብሎ ጫማውን እያሰረ::

“እንዴት ነው ጥያቄውን ተይው ማለት?!...” ንግግራቸውን አላሥጨረሳቸውም:-

“አይ እናትዬ! ጥያቄሽ በጊዜው መልስ ያገኛል፤ ‘ለሁሉም ጊዜ አለው’ ያለውን ንጉሥ ታውቂዋለሽ?” ጥያቄያቸውን በጥያቄ መለሰላቸው::

ወይዘሮ አስማሩ አብራቸው ወደተኛችው የ25 ዓመት ልጃቸው ስመኝ ታየ ዞረው፡-

“ማነው እሱ ልዤ?” ሲሉ ጠየቋት::“አይ እማዬ ይሄ ደግሞ ጠፋሽ?!” አለቃ ገብረ

ሀና ናቸው!” አለቻቸው፤ እናቷንና ወንድሟን እያፈራረቀች እያየች::

ፀደቀ ከጣሪያ በላይ ሳቀ፣ “አይ የእኛ ተማሪ! ይሄን አገር ያወቀው፣ ፀሐይ የሞቀው ድንቅ አባባል የተናገረውን ሰው ሳታውቂ!..”

“እኔ ትምህርት ቤት የምመላለሰው እንዳንተ ተረት ለመቃረም አይደለም፤ እሺ! ሲያናድድ!” አለችና ብርድ ልብሷ አለማወቋን የሚሸፍንላት ይመሥል ተሸፋፍና ተኛች::

“ያንቺ ጓደኞች ይሄኔ በሌሊት ተነስተው ጥናቱን ይለበልቡታል፤ አንቺ ጡት እንደሚጠባ ህፃን ከእናትሽ ጋር ተኝተሻል! ወይ ትምህርትሽን ጠንክረሽ አትማሪ ወይ ቁም ነገር አትሠሪ! ተነሽ!” አለና ጮኸባት:: ስመኝ ግን መልስ በመስጠትም ሆነ በመነሳት ፋንታ ተሸፋፍና መተኛትን መረጠች::

“’ለሁሉም ጊዜ አለው’ ያለው ጠቢቡ ሰለሞን ነው:: እና እንደ እሱ ጠቢብ መሆን ባልችል እንኳን እኔም ካንቺ መተኪያ ከሌለሽ እናቴ ያላነሰ ለምወዳት አገሬ ‘አንድ ቁም ነገር መሥራት አለብኝ’ ብየ ይሄው…” አለና ንግግሩን ገታው::

እናቱ “ምን ቁም ነገር ሊያወጋኝ ነው?” ብለው በጉጉት ሲጠብቁት ዝም በማለቱ ተበሳጭተው፡- “ነገርን ጀምሮ መተው ምን የሚሉት ክፉ አባዜ ነው? እንደ ጀመርህ ጨርሰው! ላገርህ የምትሠራው ቁም ነገር ምንድነው?! ሁለት ዓመት ሙሉ የማይነገር ቁም ነገር! ሁል ጊዜ ‘የምሠራው ሥራ አለኝ’ እያልህ በለሊት ከቤት መውጣት ከጀመርህ ይሄው ሐምሌ አቦ ቢመጣ ድፍን ሁለት ዓመት ሊሞላህ አንድ ወር ብቻ ነው የቀረው! ምንድነው እናት የማታውቀው ቁም ነገር?!” ዓይን ዓይኑን እያዩ ወቀሳ አዘል ጥያቄያቸውን አቀረቡለት::

“አይ እናትዬ! አይዞሽ አትቸኩይ! ብቻ አንቺ ኑሪልኝ! የሁለት ዓመት ድካሜን አንቺም ሆንሽ ይህቺ ሰነፍ እህቴ ዳር ሲደርስና ለፍሬ ሲበቃ አንድ ቀን ታዩታላችሁ:: ያኔ ‘ሁሉም እንዳንተ ቁም ነገር ቢሠራ አገራችን ባጭር ጊዜ ትለወጥ ነበር ’ እንደምትሉ አልጠራጠርም፤ እናትዬ በእውነት ትኮሪብኛለሽ! እኔ ያንቺ ልጅ! ላገሬ ያለኝን ፍቅር በተግባር ነው የምገልፀው…” ሲል በብርድ ልብሷ

አባትሁን ዘገየ

ተሸፋፍና የእናቷንና ወንድሟን ምልልስ ስታዳምጥ የቆየችው ስመኝ “ሰነፍ” የምትለዋን ቃል ስታሰላስል ቆይታ “እንግዲህ በቃ!” ብላ ብርድ ልብሷን ገላልጣ የሌሊት ልብሷን እንደለበሰች ከተኛችበት በቁጭት ተነሳች:: ፀደቀም፣ “አዎ! እህቴ ከእንግዲህ እንቅልፍ፣ መኝታ፣ስንፍና ይበቃል! የተግባር ሰዎች ልንሆን ይገባል!” አለና እናቱን ስሞ ወደ መፀዳጃ ቤት ሄደ::

ወይዘሮ አስማሩ በወንድሟ ወቀሳ ተገፋፍታ ከመኝታዋ በቁጭት ተነስታ ቁም ሳጥኑ ፊት ለፊት ባለው የቁም መስተዋት እየተዟዟረች ራሷን የምታስተውለውን ልጃቸውን፡-

“የእኔ ቆንጆ! ቆንጆ ነሽ! አስሬ ራስሽን እየተዟዟርሽ ብትመለከቺው የለለ ውበት ከየትም አይመጣም:: ይልቁንስ በለሊት ተነስቶ እንደ ልማዱ ልህድ ማለቱ ስለማይቀር በባዶ ሆዱ እንዳይወጣ ብየ ማታ የሠራሁት ሽሮ አለ፤ ምድጃውን ሰኪና ቶሎ አሙቂለት:: እንጀራም በትሪው ከድኘ አስቀምጫላሁ! ፈጠን በይ አቅርቢለት!...” አሉ::

ወዲያው የሰፈሩ፣ የሩቅ የቅርቡ፣ ባዕድ ዘመዱ ስለ ፀደቀ በሌሊት ከቤቱ እየወጣ ጠፍቶ መዋል ምክንያት የሚያወራው ሁሉ በዓይነ ህሊናቸው መጣባቸውና በሀሣብ ጭልጥ ብለው ሄዱ፤

* * *“አንቱ ሴትዮ እሮ ይሂን ልዥዎን አንድ ይበሉት!

ሰፈር፣ አገር አሰደበ! “ ይላል አንዱ:: “እኮ ምን አርጐ ነው አገር ሰፈር ያሰደበ?!”

ወይዘሮ አስማሩ መልሰው ይጠይቃሉ::“ምን የማይወራ ነገር አለ!... ‘ዠሮ ለባለቤቱ

ባዳ ነው’ የሚባለው ለካ እውነት ነው! ስንት ጉድ እየተወራ!...”

“እኮ የሚወራውን ይንገሩኛ!... “ ከንፈራቸውን በብስጭት እየነከሱ አሁንም ይጠይቃሉ::

“እቁባት ይዟል!... ትምህርቱ እምቢ ብሎት በዚያ በኸትሜና በአባጠር፣ በየሸረት ተጠንቋይ ቤት እየኸደ ነው!...” ሲባል እንሰማለን፤ እኛ ምን እናውቃለን” ይላል፤ ወሬ አቀባያቸው:: በዚህ ጊዜ ወይዘሮ አስማሩ፡-

“ታላወቃችሁ ምን ትቀባጥራላችሁ! ሰው እንደሆን ተመሬት አንስቶ የለለ ስም መለጠፍ ልማዱ ነው! ወዲያ ይህዱልኝ! የእኔ ልዥ በእንዲህ ያለው አጓጉል ነገር አይጠረጠርም፤ጎበዞች ተዋሉበት ይውላል እንጂ!” ብለው ወደ ቤታቸው ይገባሉ::

ቆይቶ ሌላ ሰው፣ ሌላ ወሬ ይዞላቸው ይመጣል:: “ምነው አፈሩን በበላሁት! የእኒያ የደጓ ልዥ! ያለ አባት አሳድገው! ምን አጋጠመው?” እያለ አዛኝ መስሎ ድምጹን ከፍ አድርጎ ከበር ሳይደርስ እየቀባጠረ ወንዱም ሴቱም ይመጣል:: ወይዘሮ አስማሩ ቤታቸው በር ላይ ቆመው “ምንድነው ነገሩ?” ብለው ሲጠይቁ፡-

“እናቴ እንዲያው ምን አጋጠመዎ?! ትናንት በሰፈሩ ሰው ሁሉ ‘የአስማሩ ልዥ የሰው ነፍስ ጠፍቶበት ነገሩን በእርቅ ለመጨረስ ገጠር ይመላለሳል!...’ እያለ ሲያወራ” ነበር ይላል::

ወይዘሮ አስማሩም ወሬ አቀባዩን “ኤድያልኝ ኤድያ! እኔ አስማሩ እናውጋው! ሟርተኛ ሁላ! ህዱልኝ ወዲያ!...” ብለው በቆመበት ትተውት ወደ ቤታቸው ይገባሉ::

ሌላውም ሌላ ሌላ ወሬ እያየዘ ይመጣል:: ይሰማሉ! መጠርጠራቸው፣ መስጋታቸው፣ መጨነቃቸው ባይቀርም “ባይኔ በብረቱ ካላየሁ በቁም ነገር፣ በሥነ ምግባር አንጨ ሴቲቱ እንደ ወንድ ሁኜ ያሳደግሁት ቁም ነገረኛ ልዠ ይኸን አያደርግም፤አላምንም!” ብለው ሁሉንም እንዳመጣጡ ይመልሳሉ::

ልጃቸው ከዋለበት ውሎ ማታ ሲመጣ ሲሰሙት የዋሉትን አንድ ባንድ እያነሱ ‘እውነት ነው አሰት?’ ሲሉ ይጠይቁታል:: ሀሠት መሆኑን፣እውነቱን የሚያውቁበት ቀን መቃረቡን አስረግጦ ሲነግራቸው

“ተመስገን! እንኳን ሁሉም ነገር አሰት ሆነ!” ብለው ይተኛሉ:: ይሄን እያሰላሰሉ “እስከመቼ ነው እንዲህ የምሆነው? ልዠ የሆዱን ገላልጦ የማይነግረኝ ለምንድነው? ምን እየሠራ ነው? ወዴት እየኸደ ነው? ...” በሚል የሀሳብ፣ የጥያቄ ጋጋታ አእምሯቸውን ሲያስጨንቁ ፀደቀ “እናትየ ቁርሱ ደረሰ?...” እያለ ገባ:: ከገቡበት የሀሣብ ማጥ ወጡ::

“ቁርሱን በሰላም ይብላልኝ፤ ልዠን ከዚህ

ፀደቀ

አደፍርስ

ፐ… ዛሬ የምርቃት ቀን ነው፤ አብዛኛው

ተማሪ ሰሞኑን ገቢውን ሲሽሞነሞንበት ነበር የሰነበተው:: ሽመልስ ሱፍ አልለበሰም፣ ጂንስ ሱሪ በሸሚዝ እንጂ:: አዲስ ሸሚዝ ገዝታ ያመጣችለት ሰብለ ነበረች፤ ማስታወሻ ይሁንህ ብላ፤ ልትሄድ ስትል:: ከዚያ በተረፈ ሁሉም ነገር የነበረው ነው… ጫማውም፤ ሱሪውም…

ሰውነቱን አንጽቶ ፀጉሩን አበጥሮ::… ከዚህ አዳራሽ እንደወጣ፤ አበባ

የሚያበረክትለት የለም፤ በወላጅ ወዳጅ አይከበብም፤ የካሜራ ብልጭታ አያጅበውም፤ በቪዲዮ አይቀረጽም::

… በዚህ የደስታ ቀን እናቱ እጐኑ የለችም፤ ወንድሙ እጐኑ የለም፤ ከዚህ እንደወጣ ግብዣ የሚያሰናዳለት ሰውም የለም፤ ብቻውን ነው፤ ብቻውን::

… በዚህ የደስታ ቀን፤ የማዕረግ ተመራቂ መሆኑን በሕዝብ መሐል ሲሰማ፤ እሰይ የኔ አንበሳ ብሎ ትከሻውን አቀፎ ያበረታታው የለም::

… አንድም ፎቶ፤ ከማንም ጋር::ተመራቂዎች ባሰናዱት መጽሔት

ላይ፤ የዘንድሮ ተመራቂዎች ፎቷቸው አለ፤ ከፍልቅልቅ ደስታ ጋር፤ ከመፈክሮች፤ ከጥቅሶች፤ ከምክሮችና ከምስጋና ቃላት ጋር:: ለዚህ ያደረሰክኝ እኔ ማን ነኝ የሚሉ… እናቴ፣ አባቴ ለዚህ በቃሁላችሁ የሚሉ… ይኸው ጥቁር ካባ ደረብኩ፤ ቆብ ደፋሁ የሚሉ… ያስተማራችሁን ተማሩ የሚሉ… የሚሉ… ብዙ ብዙ ተማሪዎች::

‘እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አላችሁ…’

የሚለውን ነባር መዝሙር ሲያዳምጥ ግን ዕንባ ተናነቀው፤ ሲቃው መጣ…

ጽላሎትእንዳለጌታ ከበደ

Page 12: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 12 ማስታወቂያ

ባህር ዳር

ከሣሽ ሙሉቀን ሃ/ማርያም በተከሣሽ 1ኛ ወ/ሮ የማርያም ወርቅ ሞሌ 2ኛ አቶ ፈቱ ሽፋ ሲራጅ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክርክር ጉዳይ ተከሣሾች ለሰኔ 10 ቀን 2008 ዓ/ም 3፡ዐዐ እንዲቀርቡ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባ/ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት------------------------------------------

በከሣሽ አብክመ ህንፃ ስራዎች ኮ/ድርጅት በተከሣሽ 1ኛ ራስ አገዝ አገልግሎት ህ/ስ/ማ 2ኛ መለሰ ዋሲሁን 3ኛ ሞላ ሞትባይኖር መካከል ስላለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ ከ1-3 የተጠቀሱት ተከሣሾች ለሰኔ 08 ቀን 2008 ዓ/ም 3፡ዐዐ ቀርበው እንዲከራከሩ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባ/ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት------------------------------------------

አመልካች ወ/ሮ ፈንታነሽ ዘገየ ተጠሪ አቶ አሸናፊ ይደግ መካከል ስላለው የመጥፋት ውሣኔ ይሰጥልኝ አቤቱታ አመልካች ባለቤቴ ወይም ተጠሪ ከሰኔ 05 ቀን 2003 ዓ/ም ለስራ ብሎ ወጥቶ ያልተመለሰ እና አድራሻው ያልታወቀ በመሆኑ የመጥፋት ውሣኔ ይሰጥልኝ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ስለሆነም ተጠሪ ካለ አለበለዚያም ያለበትን የሚያውቅ እና ጥቅም አለኝ የሚል ካለ ለሰኔ 15 ቀን 2008 ዓ/ም እንዲቀርብ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባ/ዳር ከተ/አስ/የከ/ነ/ጉ/የመ/ደ/ፍ/ቤት

------------------------------------------

ምዕራብ ጐጃም

አመልካች ወ/ሮ እምየ እርቂሁን የመጥፋት ውሣኔ ይሰጥልኝ አቤቱታ መሠረት አቶ አለልኝ ጋሹ ገለታ የመጥፍት ውሣኔ ሊሰጥበት ስለሆነ ራሱ ወይም መኖሩን የሚያውቅ ሌላ ሰው እስከ ሰኔ 27/2008 ዓ/ም ፍ/ቤት ቀርቦ እንዲያመለክት ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የቁጭ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት------------------------------------------

አቶ አማረ ባዩ አየለ በመርዓዊ ከተማ ቀበሌ 01 ውስጥ በምስራቅና በሰሜን መንገድ፣ በምዕራብ አዘነ አበበ ፣ በደቡብ ሰሜ ተገኘ አዋስኖ የሚገኘው የመኖሪያ ቦታቸው ካርኒ ቁጥር 861753 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የመርዓዊ ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------

አመልካች አቶ እንዳሌ እንኳሆነ ስላቀረቡት የመጥፍት ውሣኔ ይሰጥልኝ ጥያቄ በበርቀኝ በረበይ ቀበሌ ኗሪ የነበረችው የአመልካች እናት ወ/ሮ እናት ተረፈ ከ2006 ዓ/ም ጀምሮ ከቀበሌዋ የጠፋች ስለሆነ ተፈላጊዋ አለሁ ወይም አለች የሚል አካል ካለ እስከ ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓ/ም ድረስ እንዲቀርብ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የጃቢጠህናን ወረዳ ፍ/ቤት------------------------------------------

አቶ ደረጀ አሰፋ በአዴት ከተማ ቀበሌ 01 በምስራቅ 63 ቁጥር ፣በምዕራብ መንገድ ፣በሰሜንና በደቡብ ክፍት ቦታ የሚያዋስነው መኖሪያ ቤት የምሪት ካርታ ቁጥር 0143/95 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የአዴት ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------አቶ

አለባቸው ካሴ በዱርቤቴ ከተማ ቀበሌ 02 ለድርጅት የተሰጣቸው ቦታ በሰሜን ኡስማን፣በደቡብ

አረጋ አላምነህ፣በምዕራብ መንገድ፣ በምስራቅ ጉዳይ አለባቸው ተዋስኖ የሚገኘው ቦታ ካርኒ ቁጥር 013940 ስለጠፋባቸው በማንኛውም

ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የዱርቤቴ ከተማ መሪ ማ/ቤት------------------------------------------

አቶ ዮናስ ሆድሞኝ በደምበጫ ከተማ ቀበሌ 02 ሰፈር

አዲስ በአዋሣኝ ሰሜን አለባቸው ውቤ ፣በደቡብ አስናቀ ታደለ ፣በምዕራብ መንገድ ፣በምስራቅ ዘላለም ባይሌ የእጣ ቁጥር 3 የሆነውን ቦታቸው ካርታ ቁጥር 528/08 እና ካርኒ ቁጥር 010076 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የደምበጫ ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------

አቶ ታደገ አላዛር በደምበጫ ከተማ ቀበሌ 01 ሰፈር አዲስ በአዋሣኝ በሰሜን ደስታ ስንታየሁ ፣በደቡብ ቄስ ዘበናይ ጌትነት ፣በምዕራብ መንገድ ፣በስምራቅ ክፍት ቦታ የሆነው ቦታ ካርታ ቁጥር 443/08 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የደምበጫ ከተማ አገ/ጽ/ቤት

------------------------------------------

ምስራቅ ጐጃም

እነ ሃዋ ጡሐር 3 ራሣቸው በብቸና ከተማ ቀበሌ 04 በአዋሣኝ በሰሜን እንድሪስ አደም ፣በደቡብ ፋጡ ስሌ ፣በምስራቅ መንገድ ፣በምዕራብ አሊመት ያሲን የሚያዋስነው የመኖሪያ ቦታ ካርታ ቁጥር ብቸ0-411/99 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የብቸና ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------

በይግባኝ ባይ ወ/ሮ ዋጋ ፀጋየ ጠበቃ አቶ አለወንድ ሙሴ በመልስ ሰጭ ወ/ሮ ዓመለ ይሁኔ፣ ወ/ሮ ዝይን ምትኩ፣ አቶ አየነው አለነ፣ አቶ ደሴ ታምሩ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ መልስ ሰጭዎች ክስ የቀረበ መሆኑን አውቀው ለሰኔ 02 ቀን 2008 ዓ/ም እንዲቀርቡ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት------------------------------------------

ወ/ሮ ለወየ ጋሻነህ ባስከፈቱት የመጥፋት ውሣኔ ይሰጥልኝ አቤቱታ አቶ ደረጀ ጌትነት የተባሉት ከደጀን ወረዳ ከየናኛት ተገኔ ቀበሌ መኖሪያ ሃገራቸውን ለቀው ስለሄዱና አሁንም ያሉበት ስለማይታወቅ የመጥፋት ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡ ስለዚህ ተፈላጊው ካሉ ለሰኔ 03 ቀን 2008 ዓ/ም እንዲቀርቡ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የደጀን ወረዳ ፍ/ቤት------------------------------------------

አቶ ይመር ያሲን ሙሐመድ በብቸና ከተማ ቀበሌ 02 በአዋሣኝ በሰሜን ካሣ ይብሬ፣ በደቡብ መንገድ፣ በምስራቅ ይሣ አህመድ፣ በምዕራብ ይበልጣል አለሙ የሚያዋስነው የመኖሪያ ቦታ ሣይት ቁጥር ብቸ0.0174/88 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የብቸና ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------

አቶ እንዳለ የኔፀጋ በደብረ ወርቅ ከተማ በ01 ቀበሌ የሚገኘው የመኖሪያ ቤታቸው በአዋሣኝ በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ ጌታቸው ልመንህ፣ በምስራቅ ታሪኩ ጌትነት፣ በምዕራብ ሽለምን አበበ የሚያዋስኑት ቤት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታቸው ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የደ/ወርቅ ከተማ መሪ ማ/ቤት

------------------------------------------

አዊወ/ሮ በላይነሽ ተሻለ አዛገ በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 02 የሚገኘው የመኖሪያ ቤታቸው ካርታ እና ኘላን ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የእንጅባራ ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------

ካሸች አምላኬ አሊጋዝ በቻግኒ ከተማ ቀበሌ 03 ልዩ ሰፈራ ደበታ የሚገኘውን የመኖሪያ ቤታቸው የምሪት ካርኒ ቁጥር 015290 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውማውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የቻግኒ ከ/አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------

ወ/ሮ ወርቅነሽ ደመላሽ በቅላጅ ከተማ የሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው የምሪት ካርኒ ቁጥር 0120 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የቅላጅ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት------------------------------------------

ኢሣ ሙሐመድ ቃሲም በቻግኒ ከተማ ቀበሌ 03 ልዩ ሰፈራ ሽሮ- ሜዳ የሚገኘውን የመኖሪያ ቤታቸው ውል የዞረበት ካርኒ ቁጥር 009724 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የቻግኒ ከተ/አገ/ጽ/ቤት

------------------------------------------

ደቡብ ጐንደርአቶ ገበያው አድማሱ በመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር በቀበሌ 02 በምስራቅ ክፍት ቦታ፣ በምዕራብ ብርሃን ታገለ፣ በሰሜን የከብት ገበያው እና በደቡብ የገበያ ቦታ የሚያዋስነው 8 ካሬ ሜትር የድርጅት ቦታ ካርታ እና ኘላን ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይገባኛል ወይም ይዠዋለሁ የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ይቅረብ፡፡

የመካ/ኢየሱስ ከተ/አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------

አቶ ግዛቸው ደሴ በካርታ ቁጥር 12/1472/1472 በሆነ ተመዝግቦ የነበረው የድርጅት ቤት ካርታ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የነፋስ መውጫ ከተ/አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------

አቶ ማርዬ ሽፈራው በአርብ ገበያ ከተማ በይዞታ መዝገብ ቁጥር 1 ገጽ 7 ተራ ቁጥር 192 ተመዝግቦ የሚገኝ በሰሜን ሙሉዬ ተፈራ፣ በደቡብ ጊዜወርቅ አድማሱ፣በምስራቅ አምሣሉ ካሣው፣ በምዕራብ መንገድ የሚያዋስነው ስፋቱ 250 ካሬ ሜትር የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የአርብ ገበያ ከተማ መሪ ማ/ቤት------------------------------------------

ዋና ኢንስፔክተር መሠረት ደባልቄ ይማም በደብረ ታቦር ከተማ በስማቸው የሚገኘው በካርታ ቁጥር 8.2/103/276/2003 የተሰጣቸው ኘላን ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የደብረ ታቦር ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------

አቶ አለምነው አባተ በደብረ ታቦር ከተማ በስማቸው ተመዝግቦ የሚገኘው በካርታ ቁጥር 1339/58/74 የተሰጣቸው ካርታ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የደብረ ታቦር ከተማ አገ/ጽ/ቤት

------------------------------------------

ሰሜን ጎንደር አመልካች ወ/ሮ ጡባ ገበየሁ ልጄ ወ/ሮ አዲሴ በላይ

ከ5/1/2000 ጀምሮ የሄደችበትን ሣታሣውቀኝ የጠፋች ስለሆነ የመጥፋት ውሣኔ ይሰጠኝ ብለዋል፡፡ ተቃዋሚ ካለ ለሰኔ 6 ቀን ማክሰኝት ተዘዋዋሪ ችሎት እንዲቀርብ ከፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የጐንደር ዙሪያ ወ/ፍ/ቤት------------------------------------------

አመልካች ወ/ሮ መድሃኒት አማረ አድራሻ ጐንደር ከተማ ቀበሌ 02 ተጠሪ መንገሻ ገብረስ አመልካች ፍ/ቤቱን በተጠሪዋ ላይ የመጥፋት ውሣኔ እንዲሰጠኝ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ተጠሪው ወይም የቀረበውን የመጥፋት ውሣኔ አቤቱታ የሚቃወም ካለ ለሰኔ 10 ቀን 2008 ዓ/ም ከቀኑ 5፡ዐዐ እንዲቀርብ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የጐንደር ከተ/አስ/የከ/ነ/ጉ/የመ/ደ/ፍ/ቤት

------------------------------------------

ደቡብ ወሎአቶ መኮነን ሲሣይ በደሴ ከተማ በመናፈሻ ክፍለ ከተማ በቀበሌ 08 ክልል በካርታ ቁጥር 6023 በቤት ቁጥር 1705 የተመዘገበ ካርታ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የመናፈሻ ክ/ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------

አቶ አባተ ጌታሁን በደሴ ከተማ በመናፈሻ ክ/ከተማ በቀበሌ 08 ክልል በካርታ ቁጥር 20313 የተመዘገበ ካርታ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የመናፈሻ ክ/ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------

ወ/ሮ ደመቁ ማብሬ በደሴ ከተማ በሣላይሽ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 06 ማዕከል 02 ክልል በካርታ ቁጥር A=0190 በቤት ቁጥር 897/ሀ የተመዘገበ ካርታ ስለጠፋባቸው በእዳ ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የሣላይሽ ክፍለ ከተ/አስ/ጽ/ቤት

------------------------------------------

ሰሜን ወሎአቶ ወዳጆ አዳነ ሞላ በሮቢት ከተማ 01 ቀበሌ

ላላቸው ቤት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታና ኘላን

ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ

ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው ከወጣበት

ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ

በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የሮቢት ከተማ መሪ ማ/ቤት

------------------------------------------

አቶ ሞላ ከበደ በቆቦ ከተማ 04 ቀበሌ የሚገኘው

የመኖሪያ ቦታ ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር መ2-

2/670/2002 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት

ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ጋዜጣው

ከወጣበት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ተቃውሞውን

ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የቆቦ ከተማ አገ/ጽ/ቤት

------------------------------------------

ሰሜን ሸዋወ/ሮ በለጡ ብርቄ በደብረ ብርሃን ከተማ

ቀበሌ 02 የሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው

በቁጥር 0946 የተመዘገበ ካርታና ፕላን

ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት

ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ

ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ

20 ቀን ድረስ ካልቀረበ በምትኩ ሌላ

የሰጣቸዋል።የደብረ ብርሃን ከ/አገ/ጽ/ቤት

------------------------------------------

Page 13: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 13በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍትህ/መልካም አስተዳደር

ወደ ገጽ 16 ዞሯል

ሱራፌል ስንታየሁ

ደሃና ወረዳ

ፊት ለ

ሙሉ ዓብይ

መሪዎችን ያተጋ የውይይት መድረክ ንፋስ መውጫ ከተማ

ፊት “ሆስፒታል ቢገነባም የህንፃ ለውጥ እንጂ የሙያተኛና የመሳሪያ ለውጥ አልተደረገም”

የአማራ ብዙሃን መገኛና ድርጅት ከአሁን በፊት በ13 የዞን ከተሞችና ከተማ አስተዳደሮች ላይ በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ህብረተሰቡን ከአመራሩ ጋር ፊት ለፊት በማገናኘት ሲያወያይ መቆየቱ ይታወሳል:: በወረዳ ደረጃ የመጀመሪያው የሆነውን የከተሞች መድረክ ለ14ኛ ጊዜ ግንቦት 14/2008 ዓ.ም በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በደሃና ወረዳ በእነለጋ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል:: ነዋሪዎችም በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ችግር ናቸው ያሏቸውን ጉዳዮችና ከአመራሩ የተሰጡ ምላሾችን ይዘን ቀርበናል::

ማህበራዊ የአምደ ወረቅ ከተማ ነዋሪ የሆኑት መምህር

ውበቱ ደስታ በዳሃና ወረዳ ሆስፒታል መገንባቱ ለነዋሪዎች መልካም ቢሆንም አሁንም ችግሩ አልተፈታም ባይ ናቸው:: ምክንያታቸው ደግሞ በፊት በጤና ጣቢያ የታከሙም ሆነ አሁን በሆስፒታሉ የሚታከሙ ህሙማን የተለየ አገልግሎት እያገኙ አይደለም ይላሉ:: “ሆስፒታሉ በተሟላ መሳሪያ አገልግሎት እየሰጠ አይገኝም:: በጤና ጣቢያው ሲያክሙ የነበሩ ሙያተኞች በሙሉ ወደ ሆስፒታሉ እንዲገቡ ተደርጓል:: የህንፃ ለውጥ እንጂ የሙያተኛ እና የህክምና መሳሪያ ለውጥ ብዙም አልታየበትም::” ሲሉ በህክምና ዘርፍ በወረዳዋ ላይ ችግር መኖሩን ተናግረዋል::

በዳሃና ወረዳ አዚላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ

አዲስ አባተ ደግሞ በገጠር አካባቢ ትምህርት ቤቶች እየተረሱ ነው፣ በትምህርት ጥራት ላይ እየተሰራ አይደለም ብለዋል:: እሳቸው በሚኖሩበት አካባቢ በአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት በ1965 ዓ.ም የተሰራ አንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብቻ መኖሩን ይናገራሉ:: ይህም ሆኖ በትምህርት ቤቱ ያለጊዜው እየቀረ መጋቢት ላይ ቅጥር እየተፈፀመ ተማሪዎች በቂ እውቀት ሳያገኙ ከክፍል ክፍል እንዲዘወወሩ እየተደረገ ነው ብለዋል:: ለዚህም ለአብነት ብለው ያነሱት የአምስተኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው የራሳቸው ልጅ ‘ሀ፣ ሁ፣ ሂ…’ ፊደላትን አስተካክላ መፃፍ እንደማትችል በመታዘባቸው እንደሆነ ተናግረዋል::

መልስየዳሃና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ

ታምሩ ቢሞረው በሆስፒታሉ ግንባታና በጤና ጣቢያ ዙሪያ በመድረኩ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል:: በህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ታማሚን በሚገላምጡ፣ ሰአት በማያከብሩ፣… የስነ ምግባር ችግር ያለባቸውን የህክምና ባለሙያዎች በመገምገም፣ በማስጠንቀቅ፣ በመቅጣትና በማባረር ችግሮች እንዲፈቱ ጥረት ማድረጋቸውን ገልፀው የተሻለ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል:: ይህ ማለት ግን ሙሉ በሙሉ ጥሩ ሰርተናል ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል::

በጤና ጣቢያ ይሰሩ የነበሩ ባለሙያዎችን ወደ

ሆስፒታሉ መወሰዳቸውን አምነው ካጋጠማቸው የባለሙያ እጥረት የተነሳ እንደሆነ ይናገራሉ:: በጤና ባለሙያ እጥረት የተነሳ በአምደ ወርቅ ጤና ጣቢያ አንድ ባለሙያ ብቻ አገልግሎት የተሰጠበት ጊዜ እንዳለ በትውስታም አንስተዋል:: አሁንም ቢሆን የላቦራቶሪና የፋርማሲ ባለሙያ ለመቅጠር ጥረት አድርገው ተወዳዳሪ በማጣታቸው ችግሩ እንዳለ ገልፀው እንደገና ቅጥር ለመፈፀም ግን ጥረት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል:: በቅርቡም ሁለት የህክምና ዶክተሮችን እንደቀጠሩ እና ተጨማሪ ሶስተኛ ዶክተር ለመቅጠር እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል:: የመድሃኒት እጥረት እያጋጠማቸው ታማሚዎች መድሃኒት ከውጪ እንዲገዙ ሲያደርጉ እንደነበር ተናግረው ችግሩን ለመፍታት በ91 ሺህ ብር ከደሴ በቅርቡ መድሃኒት ማስመጣታቸውን ተናግረዋል::

“ለውጥ አደረገ እንጂ ሆስፒታሉ አገልግሎት እየሰጠ አይደለም” ለተባለው ሆስፒታሉ ሙሉ አቅሙን እንዳይጠቀም ካደረጉት ነገሮች የመብራት መቆራረጥ አንዱ ነው ብለዋል:: መብራት ብዙውን ጊዜ ስለሚጠፋ በጄኔሬተር ለመስራት ቢገደዱም

የነዳጅ እጥረት መኖሩ ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ችግር እንደሆነባቸው ተናግረዋል::

በቀን ከአንድ በርሚል በላይ ነዳጅ እንደሚጨርሱ ገልፀው እናት በወሊድ ላይ እያለች ነዳጅ እያለቀ ጄኔሬተር የሚቆምበት አጋጣሚም መኖሩን ተናግረዋል:: እናቶችን ከቀበሌ ወደ ሆስፒታል ለወሊድ በአምቡላንስ አምጥተው ከተገላገለች በኋላም መልሰው ቤቷ ድረስ በመውሰድ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት እያደረጉ እንደሆኑ ተናግረዋል::

የዳሃና ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈታለሽ ምህረቴ በትምህርት ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል:: በወረዳዋ የመምህር እጥረት እንዳለባቸውና ይህንን ችግር ለመቅረፍ ሁለት ነጥብና ከዚያ በላይ ያላቸውን አስረኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎችን በምዘና ካሳለፉ በኋላ በረዳት መምህርነት ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል እንዲያስተምሩ በማድረግ እጥረቱን ለመቀነስ ጥረት ማድረጋቸውን ይናገራሉ::

“...ጥያቄያችን ከውይይት መድረክ በኋላ ፈጣን ምላሽ አግኝቷል::”አቶ በለጠ ዳኛው -የከተማዋ ነዋሪ ወደ ገጽ 16 ዞሯል

ባለፈው ሳምንት ዕትም በነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር የካቲት 20/2008 ዓ.ም በተካሄደ የመልካም አስተዳደር ውይይት ላይ የተነሱ ቅሬታዎች ምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ በቦታው ተገኝተን ነዋሪዎችንና አመራሩን በይዞታ መሬት፣ በመስሪያና መሸጫ ቦታ እና በሌሎች ዙሪያ የደረሱበትን ማስነበባችን

ይታወሳል:: በዚህ ዕትም ደግሞ የመጨረሻውን ክፍል በኢንቨስትመንት፣ በፅዳት፣… ላይ የተነሱ ጥያቄዎች ምን ምላሽ እንዳገኙ ልናስነብባችሁ ቃል ገብተን ነበር፤ እኛም በቃላችን ተገኘተናል፤ መልካም ንባብ::

ኢንቨስትመንትአቶ በለጠ ዳኛው የተባሉ በከተማው የ03 ቀበሌ

ነዋሪው የካቲት 20/08 የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እና የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር በመተግበር ባካሄዱት የመልካም አስተዳደር ውይይት ላይ በአካባቢው ሰፊ የባህር ዛፍ ምርት ስላለ ይህን የሚያስተናግድ የኢንዱስትሪ መንደር እንዲመሰረት ጠይቀው ነበር::

ሌላው የአቶ በለጠ ጥያቄ ባለሀብቶችም ወደ አካባቢው ገብተው የባህር ዛፍ ምርቱን በመጠቀም ችፑድ ፋብሪካ የሚከፍቱበት ሁኔታ ይመቻች? የሚል ነው::

አቶ አድማስ ጌታሁንም “ለወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር ፋብሪካ ይሰራልን?” ሲሉ ጠይቀው ነበር::

እኛም ከኢንዱስትሪ መንደር ምስረታ ጋር ተያይዘው የተነሱት የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከሁለት ወር በኋላ ምን መፍትሄ አገኙ? ስንል ጥያቄ ያነሱ ግለሰቦችንና አመራሮችን ጠይቀን ነበር::

በቅድሚያ ያነጋገርናቸው አቶ በለጠ ዳኛው “የኢንዱስትሪ መንደር ይከለልልን የዘመናት

ጥያቄያችን ከውይይት መድረክ በኋላ ፈጣን ምላሽ አግኝቷል:: ሌሎች ጥያቄዎች ግን ምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ አላውቅም” አሉን::

እኛም የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽንና አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰርኩ ታረቀኝን አነጋግረናቸዋል:: እርሳቸው እንደሚሉት በአካባቢው ለችፑድ ፋብሪካ የሚሆን

በቂ የባህር ዛፍ ምርት በመኖሩ ፋብሪካ እንዲከፈት የህብረተሰቡ የረጅም ጊዜ ጥያቄ ነው:: ይሁን እንጂ፣ አነስተኛ ከተሞች በፕላናቸው ላይ የኢንዱስትሪ መንደር የለውም:: ቢሆንም ግን የችፑድ ፋብሪካ

ለመክፈት ጥያቄ ያቀረበ አንድ ባለሀብትም ስለነበር በተደጋጋሚ ለክልል ባቀረብነው ጥያቄ መሠረት ሁለት ነጥብ አራት ሄክታር መሬት ተፈቅዶ እንደነበር አቶ ሰርኩ አስታውሰዋል::

“ይሁን እንጂ፤ ባለሀብቱ የቀረበለት መሬት ከጠየቀው በታች በመሆኑ ጥያቄውን ሰርዟል:: አሁን ግን ነዋሪዎች በመድረኩ ላይ ያነሱትን ጥያቄ መሰረት አድርገን ለክልሉ ኢንቨስትመንት ያለመሰልቸት በመጠየቃችን 20 ሄክታር የኢንደስትሪ መንደር እንድንከልል ተፈቅዶልናል:: ከመድረኩ በኋላ ጥሩ ሰራን ያልነውም ይህ ነው” ብለዋል::

ካሁን ቀደም ተፈቅዶላቸው ተከልሎ የነበረውን ሁለት ነጥብ አራት ሄክታር መሬትም ከጥቃቅንና አነስተኛ ወደ መካከለኛ ባለሀብትነት ላደጉ ስድስት አንቀሳቃሽ ኢንተር ፕራይዞች መከፋፈሉንም አቶ ሰርኩ አብራርተዋል::

ካሁን በፊት የችፑድ ፋብሪካ ቦታ ጠይቀው ለነበሩትም ሆነ ሌሎች በዱቄት፣ በብሎኬት… ምርት መሳተፍ የሚፈልጉ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ጥያቄ ቢያቀርቡ በቂ ቦታ እንደሚያገኙ አቶ ሰርኩ አረጋግጠዋል::

“ለወጣቶች የስራ እድል አልተመቻቸላቸውም” ለተባለው ቅሬታም አቶ ሰርኩ ሲያብራሩ በአካባቢው ካለው የባህር ዛፍ ምርት ጋር ተያይዞ “ከሌላ አካባቢ የመጡ ባለሀብቶች ዛፉን ቆርጠው ስለሚወስዱት

“...የውይይት መድረክ ለዘመናት የቆየ ችግር የፈታ፤ ሆድና ጀርባ የነበረን አመራርና ህዝብ ለአንድ አላማ ያነሳሳ ነው”አቶ አድማስ ጌታሁን -የከተማዋ ነዋሪ

Page 14: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 14 ማስታወቂያ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያየዚገም ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለዚገም ወረዳ ውሃ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ለ2008 በጀት ዓመት ለንጹህ

መጠጥ ውሃ ተቋማት አገልግሎት የሚውል አፍሬዲቭ የእጅ ፓምኘ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር እንዲችሉ ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፣

3. ተጫራቾች የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 50 ሺህ ብር እና በላይ የሚደርስ ከሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/

ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች

ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የእቃውን ዝርዝር/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 15.00 በመክፈል ከዚገም ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት

ጽ/ቤት ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 01 ዘወትር ተከታታይ ቀናት ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1

በመቶ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፋይናንስ ህጋዊ ደረሰኝ በዚገም ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ

ልማት ጽ/ቤት ማስያዝ አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች ከዚህ ጋር በተያያዘው የዋጋ መሙያ ሰነዱ መሠረት ዋጋ በመሙላት ከመጫረቻ ሰነዳቸው

ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች ኦርጅናል የጨረታ ሃሣቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በዚገም ወረዳ

ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በግዥ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው

የጨረታ ሣጥን ዘወትር በተከታታይ ቀናት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለ ጀምሮ

በሚቆይ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡3ዐ ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡

10. ጨረታው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚገም ወረዳ ገንዘብና

ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በግዥ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 05 በ4፡ዐዐ የጨረታ

ሣጥኑ ታሽጐ በዚሁ እለት 4፡3ዐ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሣቸው ምክንያት ባይገኙ የጨረታ

ፖስታው እንዲከፈት በማድረግ ውድድሩ ይካሄዳል፡፡

11. መስሪያ ቤቱ 20 በመቶ መቀነስ ወይም መጨመር የሚችል ይሆናል፡፡

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ

ነው፡፡

13. በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ካሉ በግዥ መመሪያው መሠረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

14. እቃዎችን እስከ ዚገም ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

15. አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ድምር ይሆናል፡፡

16. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በዚገም ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በአካል በመገኘት

ወይም በስልክ ቁጥር 0920501612 ወይም 0918125634 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የዚገም ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያየባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤት መምሪያ ለመምሪያው አገልግሎት የሚውል የጽህፈት

መሣሪያ የጽዳት እቃዎች እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ

የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/ቲን/ያላቸው፣

4. የግዥ መጠን ከብር 50 ሺህ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ

መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን

ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የሚገዙ የጽህፈት መሣሪያዎችን ፣የጽዳት እቃዎችን እና የደንብ ልብስ ዓይነትና ዝርዝር

መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 20.00 በመክፈል ከግዥ ፋይናንስ ንብረት

አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 ማግኘት ይችላል፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ብር 1 በመቶ

በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና

ወይም በጥሬ ገንዘብ በመምሪያው ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን ይህ ማታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስታወቂያው

አየር ላይ በሚቆይባቸው ተከታታይ ለ10 ቀናት የሚያቀርቡትን ዋጋ ወይም የመወዳደሪያ

ሃሣብ በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ

በታሸገ ፖስታ በመምሪያው የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ

ቁጥር 1 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ድረስ

ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመምሪያው አዳራሽ በ11ኛው

ቀን 4፡ዐዐ ታሽጐ 4፡3ዐ ይከፈታል፡፡

11. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ3 ቀናት በኋላ

በ2 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበት ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል

መፈረም ይኖርበታል፡፡

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ

መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. የጨረታ መክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡

14. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 01 ድረስ

በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582262434 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤት መምሪያ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት ለዕቃ ማከማቻ አገልግሎት የሚሆን መጋዝን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች /አከራዮች/

ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶችና ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡

2. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሣቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፡፡

4. የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በነፃ በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 05 መብራት ሃይል ጀርባ የቤቶች ልማት ህንፃ ላይ ከሚገኘው የባህር

ዳር ገቢዎችና ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር R-304 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በጥንቃቄ በመሙላትና በሚገባ በማሸግ እንዲሁም በዋጋ መሙያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በግልጽ በማስቀመጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት

ይኖርባቸዋል፡፡

7. የጨረታ ሣጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የሐብት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር R-304 ጠዋት 4፡3ዐ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው

ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በ17ኛው ቀን 4፡ዐዐ ተዘግቶ 4፡3ዐ ይከፈታል፡፡

8. የጨረታው አሸናፊ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10 በመቶ /ሲፒኦ/ በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10. ተጫራቾች የመጋዝኑን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ በጨረታ ሰነዱ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡

11. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የንግድ መረጃዎችን ኦርጅናል ለብቻው አቅርበው ማሣየት ይኖርባቸዋል፡፡

12. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0582263346/0582263321/0920573278/0913056614 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት

Page 15: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 15በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ኪንና ባህልየኪን ዜናዎች

በሸጋው ሙሉማር

አማርኛ በአማርኛ

ወደ ገጽ 30 ዞሯል

በምስራቅ ጐጃም ዞን በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ የልጅነት ጋብቻን ለመከላከል በቀበሌና ከወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂደ::

የወረዳው ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ማናየሽ ዳኘ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት በወረዳው እየተፈፀሙ ካሉ ጐጂ ልማዳዊ ድርጊቶች አንዱ የልጅነት ጋብቻ ነው፡ ይህንን ለመከላከልም የሌሎችን አጋር አካላት ድጋፍ የሚጠይቅ በመሆኑ መወያየት አስፈላጊ ነው ብለዋል::

የልጅነት ጋብቻ በህፃናት ላይ የጤናና የስነ ልቦና ችግር ከማስከተሉ በተጨማሪ ኢኮኖማያዊ ቀውስን የሚያስከትል ስለሆነ ከቀበሌ እስከ ወረዳ ያለ አመራር የህዝብና የመንግስት አደረጃጀቶችንና የሐይማኖት አባቶችን በመጠቀም ከመቸውም የበለጠ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ ኃላፊዋ ገልፀዋል::

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ እስከ 2017 የልጅነት ጋብቻን እንደ ሀገርና እንደ ክልል ለማስቀረት ስምምነት የተደረሰ በመሆኑ በወረዳውም እንደ ሌሎች የልማት ዘርፎች የእቅድ አካል በማድረግ ማስወገድ ይገባል ብለዋል::

የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደገለፁት የሴቶች የልማት ቡድኖችን በማጠናከር በየቀበሌው የልጅነት ጋብቻን ለማስቀረት ከውይይቱ ጥሩ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ተናግረዋል ሲል የወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዘግቧል::

የጉና ተራራ ተከለለበጉና ተራራ ዙሪያ እየተፈፀመ ያለውን ህገወጥ

እርሻና ልቅ ግጦሽ በማስቆም እየደረሰ ያለውን የስነ ምህዳር መዛባት ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለፀ::

በደቡብ ጐንደር ዞን የሚገኘውና ከ28 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሸፍነው የጉና ተራራ 12 የሚሆኑ የፋርጣ፣ የላይ ጋይንት እና የእስቴ ወረዳ ቀበሌዎች አረሶ አደሮች በሀገ ወጥ መንገድ ለእርሻ፣ ለልቅ ግጦሽ ለህገወጥ የቤት ግንባታ እየተጠቀሙበት ይገኛል::

አካባቢውን በዘላቂነት ጥብቅ ስፍራ ለማድረግ ከሶስቱም ወረዳዎች ከተውጣጡ የጉና ዙሪያ አርሶ አደሮች ተወካዮች ጋር ውይይት ሲደረግ የደቡብ ጐንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እዘዝ ዋሴ እንደገለፁት የጉና ተራራ ከ44 በላይ ምንጮች መፍለቂያ፣ የጣና ገባር የሆኑት የእርብና የጐማራ ወንዞች መነሻ ቢሆንም በአካባቢው አርሶ አደሮች እየታረሰና በርካታ እንስሳት በልቅ ግጦሽ ተሰማርተው የሚውሉበት በመሆኑ አደጋ እየደረሰበት ይገኛል::

በአርሶ አደሮቹ ተይዞ ህገወጥ እርሻ፣ልቅ ግጦሽና ህገወጥ ግንባታ እየተሰፋፋበት የሚገኘውን የጉና ተራራን ከልሎ በማስከበር የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ከተጠቃሚ አርሶ አደሮችና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በተደረገ ተከታታይ ውይይቶች መግባባት ላይ በመደረሱ ሰሞኑን የክለላ ስራው ተከናውኗል ብለዋል::

የክለላ ስራው ከሁለት አመት በፊት የተጀመረ ቢሆንም በትኩረት ማነስና በአካባቢው አርሶ አደሮች የተሳሳተ አመለካከትና ግላዊ ተጠቃሚነት የተነሳ ውጤታማ ሳይሆን መቆየቱን ተናግረዋል::

በውይይቱ ተሳታፈ የነበሩ የአካባቢው አርሶ አደሮችም በተሳሳተ አመለካከትና ከአጭር ጊዜ የግል ተጠቃሚነት ፍላገት በመነሳት በጉና ተራራ ላይ ህገወጥ እርሻና ልቅ ግጦሽ ሲያከናውነበት መቆየታቸውን ገልፀዋል::

የአርሶ አደሮቹ የአመለካከት ችግር እንዳለ ሆኖ መንግስትም በህገወጥ የተያዘውን መሬት በመከለል፣ በማስጠበቅና ተደጋጋሚ ጥፋት በሚፈፅሙት ላይ ህጋዊ ርምጃ በመውሰድ በኩል መዘግየቱን የአካባቢው ኗሪዎች ገልፀዋል ሲል የደቡብ ጐንደር ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት ዘግቧል

የልጅነት ጋብቻን ለማስቀረት ርብርብ ይጠይቃል

ሞሸለቀ = ገሸለጠ፣ ገፈፈ፣ ላጠ፣ ፈጀ፣ አቃጠለ፣ ላፈረፈረፈ = ጣለ፣ ለሸለሸ፣ አስተኛ፣ አጋደመሰከነ = ወረደ፣ ዘቀጠ፣ ረጋ፣ ጨመተቀረሻሸመ = ኮረሻሸመ፣ ቆረጣጠመ፣ አደቀቀተገተገ = አጠጋግቶ በብዛት ተከለ(ችግኝን) ዘባ = ጐበጥ አለ፣ ተለመጠ፣ ተጣመመ

ክፍል አንድእንደ መንደርደሪያ…ይህ ፅሁፍ በ2005 ዓ.ም በካህሳይ አብርሃ

ተፅፎ ለንባብ የበቃውን፤ “የአሲምባ ፍቅር” የተሰኘውን መፅሃፍ በወፍ በረር የሚዳስሳ ነው:: የመፅሃፉ ደራሲ በአሲምባ በነበረው የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ሰራዊት ወይም ኢህአሰ በተባለው የኢህአፓ ወታደራዊ ክንፍ ውስጥ የነበረ ታጋይ ነው:: ከተራ ታጋይነት እስከ ሃይል መሪነት በቆየባቸው ጥቂት አመታት፤ በአሲምባ ውስጥ ያሳለፈውን ውጣ ውረድ፤ የትግልና የፍቅር ህይዎት የሚዳስስ፤ እውነተኛ ታሪክ ነው::

ታሪኩ ከተከናወነ ከ30 አመታት በኋላ ለንባብ የበቃው “የአሲምባ ፍቅር” ያ ትውልድ የወጣ የወረደበትን፤ ሀገርና ህዝብ ለሚባል እውነት የተከፈለውን መስዋዕትነት፤ የነበረውን የአላማ ፅናት፣ ፍቅርና ትግል በሚገባ ያሳያል:: አዲሱ ትውልድ ስለ ኢህአፓ ምንነትና ማንነት፤ በአጭር ጊዜ ስሙ ገኖ፤ በአጭር ጊዜ ለምን እንደተበተነ፤ ፍንጭ ይሰጣል ብዬ አምናለሁ::

ባለቅኔው ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን “የሰው ልጅ አንድም ከፊደል ሀ ብሎ፤ አንድም ከመከራ መዝገብ ዋ ብሎ ይማራል::” እንዳሉት ያ ትውልድ በርሃብና በእርዛት፤ በመከራና በጦርነት ለዚህ ትውልድ ልዕልና ዋጋ ከፍሏል:: በእኔ እምነት ይህ ትውልድ፤ ከዚያ ዘመን ትውልድ፤ ከሊቅ አፍም ይሁን ከመፅሀፍ ያገኘው እውቀት በቂ ነው ብዬ አላስብም::

ደራሲ፣ ገጣሚና ጋዜጠኛ ነብይ መኮንን በመፅሀፉ ጀርባ በሰጠው አስተያየት “የካህሳይ ኩርባዎች ወላጆቹ፣ ከሱ ጋር ነፍስ የተቀባበለው ይመር ንጉሴ የተባለው ገበሬና አሲምባ የወለደት ድላይ የተባለች ጓድ- ፍቅረኛው ናቸው::” ይላል:: ስለዚህ የካህሳይን ኩርባዎች አንድም ከመፅሀፉና ከደራሲው ጋር ከነበረኝ ቆይታ፤ ሁለትም ከአንዳንድ ታሪካዊ መፃህፍትና ተዛማች ሁነቶች ጋር እያዛመድሁ የወፍ በረር ቅኝቴን አቀርባለሁ::

ታሪካዊ ዳርበኢትዮጵያ ህዝቦች የትግል ታሪክ ውስጥ፤

በየጊዜው ሲቀሰቀስ የነበረው አመፅ በ1930ዎቹ ይበልጥ ተጠናክሮ ወጣ:: በተለይ በጎጃም፣ በወሎ፣ በባሌና በትግራይ… በነበረው የገበሬዎች አመፅ

ኩርባዎች

ተስፍፍቶ፤ በተለያየ ጊዜና ዘመን ህዝቡ በስርዐቱ ላይ ተቃውውን ሲያሰማ ነበር::

ለዘመናት ውስጥ ውስጡን ሲንፈቀፈቅ የነበረው ህዝባዊ አብዮት ነፍስ የዘራው፤ በወርሃ ታህሳስ 1953 ዓ.ም ነበር:: ይሁንና በገርማሜ ንዋይና በመንግስቱ ንዋይ አማካኝነት የተጠነሰሰው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በወጉ የተደራጀና የተቀናጀ ባለመሆኑ ሳይወለድ ሞተ:: አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ሙከራውን “በግብታዊነትና በስሜት የተደረገ ነበር::” ይላሉ:: ያም ሆኖ ግን በዘመኑ የነበረውን አስተሳሰብ በመቀየር ረገድ ትልቅ ፋይዳ ነበረው:: ምክንያቱም “ሰማይ አይታረስ፤ ንጉስ አይከሰስ፤” በሚል ልማዳዊ አስተሳሰብ ተቀይዶ፤ ብሶቱን በሆዱ ይዞ ለኖረው ህዝብ የከሸፈው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ‘ይህም አለ ለካ!’ አንዲል አስችሎታል::

ራሳቸውን ከሰለሞናዊ የዘር ግንድ ጋር ያስተሳሰሩትና “ሥዩመ እግዚያብሔር ነኝ::” በማለት ለ43 አመታት ያህል ሃገሪቱን ያስተዳደሩት አፄ ኃይለ ስላሴ፤ ከየአቅጣጫው የተነሳውን አመፅ መቋቋም አልቻሉም:: ችግሩን ለማርገብ የተለያዩ ማሻሻያዎችን ቢያደርጉም፤ የንግስና ዘመናቸውን ግን ማራዘም አልቻሉም:: በዚህም የሃገሪቱ የመጨረሻው ንጉሰ ነገስት በመሆን ስልጣናቸውን ለቀቁ::

በወቅቱ ከተለያዩ ወታደራዊ ክፍሎች የተውጣጡ ጥቂት መስመራዊ መኮንኖች፤ ለዘመናት ውስጥ ውስጡን ሲንተከተክ የኖረውን ህዝባዊ አመፅ መከታ አድርገው፤ በአቋራጭ መንበረ ስልጣኑን ተቆጣጠሩት::

ስልጣኑን የተቆጣጠሩት መኮንኖች፤ ራሳቸውን ግዚያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ብለው በመሰየም፤ ሀገሪቱን ማስተዳደር ጀመሩ:: ደርግ ከመነሻው “ያለ ምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም!” ብሎ ቢነሳም፤ የህዝቡን የዘመናት ጥያቄ መመለስ ግን አልቻለም:: ምክንያቱም የህዝቡን የለውጥ ፍላጎት መሰረት አድርጎ ወደ ስልጣን ቢመጣም፤ ሀገሪቱን ለማስተዳደር የሚችል ቅድመ ዝግጅት አልነበረውም:: በዚህ ሳቢያም ህዝባዊ አመፁ ማገርሸት ጀመረ::

‘ከድጡ ወደ ማጡ!’ እንዲሉ የህዝቡ ኑሮና ሮሮ እያየለ ሄደ:: በዚህ ሳቢያም የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደ እንጉዳይ መፍላት ጀመሩ:: ከእነዚህ የፖለቲካ ሀይሎች መካከል ስሙና ዝናው የናኘው፤ በርካታ አባላትን በአጭር ጊዜ በማፍራት ጎልቶ የወጣው፤ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ወይም ኢህአፓ ነበር::

ኢህአፓ በገጠር የተራዘመ የትጥቅ ትግል በማካሄድ ወታደራዊውን መንግስት ከስልጣን ለማውረድ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ሰራዊት ወይም ኢህአሰ የተሰኘ ወታደራዊ ክንፍ መሰረተ::

ሰራዊቱንም በትግራይ አሲምባ፣ በጎንደር በለሳና ጠለምት አካባቢ ስልጠና በመስጠት የትጥቅ ትግል ጀመረ:: ይሁንና በውስጡ በተፈጠረው ልዩነት ሳቢያ እየተፈረካከሰ ሄዶ ህልውናው መክሰም ጀመረ::እነሆ አመታት አለፉ… ነገሮች ሁሉ ባልተጠበቀ ፍጥነት ተለዋወጡ:: ስርአቱን ለመገርሰስ በገጠር የተራዘመ የትጥቅ ትግል የጀመሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይና (ህወሃት) እና የኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢህዴን) በ1980 ዓ.ም አጋማሽ ጥምረት ፈጠሩ:: የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ወይም ኢህአዴግ የተባለው ጥምረት ወታደራዊውን ስርአት በወርሃ ግንቦት በ1983 ዓ.ም አስወገደ:: ደርግ ለ17 አመታት የነገሰበትን ዙፋንም ተረከበ::

እነሆ አሁንም አመታት ነጎዱ… ነገር ግን በአንድ ወቅት ከሊቅ እስከ ደቂቅ የተከተሉት ገናናነቱ የተመሰከረለት “ጥቁሩ ቮልሸቪክ” እየተባለ የተሞካሸውን የኢህአፓ ትክክለኛ ታሪክ ለትውልዱ በሚገባ ተላልፏል ለማለት ያዳግታል:: ምክንያቱም በዚያ የታሪክ ሂደት ውስጥ ያለፉት ታጋዮች ኢህአፓ በሃገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ የነበረውን ሚና፣ እድገትና ለውድቀቱ መንስኤ የነበሩ ታሪኮችን ከስሜት በፀዳ መልኩ አላቀረቡትም፤ እርስ በእርሳቸው የሚጣረሱም ናቸው:: በዚህ ሳቢያ የአሁኑ ትውልድ ያለፈውን እውነተኛ የኢህአፓ ታሪክ ያውቃል ከተባለም በዘመኑ እልፍ ወጣቶች ስለማለቃቸውና ለውድቀቱም ተጠያቂው ድርጅቱ ስለመሆኑ ሊነግረን ይችል ይሆናል:: በተረፈ ስለ ሌሎች ምክንያቶችና በድርጅቱ በሀገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የነበረውን ጉልህ ድርሻ በውል ተገንዝቧል የሚል ዕምነት የለኝም::

ስለዚህ የኢህአፓን የውድቀት መንስኤ በሚገባ ለመረዳት በወቅቱ የነበሩ ባለ ታሪኮች ታሪኩን በሚገባ ሊነግሩን ግድ ነው፤ ኢህአፓ በኢትዮጵያ ህዝቦች የትግል ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሚና የተጫወተ፤ በሃገሪቱ ለተፈጠረው የፖለቲካ ለውጥ መሰረት የጣለ መሆኑ አይካድምና!

እንደ አለመታደል ሁኖ ብዙዎቹ የሀገራችን የታሪክ ድርሳናት የተፃፉት በራሳችን ሰዎችና በባለ ታሪኮች አይደለም:: ይህ ባለመሆኑም ያለፈው ትውልድ ለህዝቦች ልዕልና የከፈለው መስዋዕትነት በዘመን ብዛት እየደበዘዘ ነው:: ትውልዱም በራሱ ታሪክ ከመኩራት ይልቅ፤ ታሪክ እያለው ታሪክ አልባ ሆኗል:: ለዚያም ይመስለኛል የራሱን ጀግኖች ዘንግቶ፤ የሆሊውድና የቦሊውድ የፊልም ተዋናዮችን ታሪክ ነጋሪ የሆነው::

ይህ ለምን ሆነ? ካልን ባለ ታሪኮቻችን የኢህአፓን ታሪክ በወጉ ለትውልድ

የካህሳይ

Page 16: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 16

ወደ ገጽ 32 ዞሯል

መሪዎችን ያተጋ... ከገፅ 13 የዞረ

ንፋስ መውጫ ከተማ

በአዚላ ትምህርት ቤት ለመገንባት የዋግ ልማት ማህበር ሊሰራ እቅድ ይዞ ነበር:: ለማህበሩ

ፊት ለፊት... ከገፅ 13 የዞረ

የሚቀረን ነገር አለ:: ሆኖም ግን የትምህርት ጥራቱ የወረደ ነው የሚያስብል ደረጃ ላይ አይደለንም::

የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ከመምህራኑና ከመንግስት ኃላፊዎች በተጨማሪ ወላጆችም ልጆቻቸውን በቤት ውስጥ በትምህርቱ ላይ እገዛ በማድረግ እጃቸውን ሊያስገቡ ይገባል ብለዋል::

ቃል የተገባው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ስላልተሰበሰበ ግንባታው ሊዘገይ ችሏል:: ሆኖም ግን ትምህርት ቤቱ ሳይገነባ አይቀርም፤ አይቋረጥም ብለዋል::

“በትምህርት ጥራት ላይ ሙሉ በሙሉ አስጠብቀን እየሰራን ነው ብለን እናምንም ብዙ

የአካባቢው ወጣቶች ተጠቃሚ አልሆኑም” የሚል ቅሬታ በኗሪው መነሳቱን ጠቁመዋል:: ነገር ግን በከተማ አስተዳደሩ ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ጽ/ቤት በኩል በተለይ ከባህርዛፍ ምርት ጋር ተያይዞ የሰው ኃይል ሲጠየቁ ወጣቶችን መልምለው እንዲሰጡ ታስቦ ነበር:: ሆኖም በባለሀብቶቹ የተጠየቀውን የሰው ሀይል ማቅረብ እንዳልተቻለ አቶ ሰርኩ ጠቁመዋል:: “እነርሱ ደግሞ ቆርጠው የሚያነሱበት የጊዜ ገደብ ስለተቀመጠላቸው የእኛ አካባቢ ወጣቶች ካልሰሩ እጃቸውን አጣምረው መቀመጥ የለባቸውም:: ከአካባቢያቸው የሰው ሃይል አምጥተው እያሰሩ ናቸው-ይህን እኛ አንቃወምም” ብለዋል::

መፍትሄ ሊፈለግለት ይገባል?” ሲሉ የጠየቁት አቶ አወቀ ያለው ነበሩ::

ከመድረኩ በኋላ ግን ቆሻሻን በየቦታው መጣል ቀርቶ በየአቅራቢያ ቆሻሻ የሚጠራቀምበት ጊዜያዊ ቦታ ተዘጋጅቷል:: ቢሆንም ግን ቆሻሻውን ከየአካባቢው አጠራቅሞ ቶሎ ቶሎ ራቅ ወዳለ አካባቢ በመጣል ረገድ እጥረት እንዳለ አቶ አወቀ ተናግረዋል::

አቶ አወቀ ይህን ይበሉ እንጂ፤ እኛ በተዘዋወርንባቸው አካባቢዎች በየቦታው ቆሻሻ ተዝረክርኮ አስተውለናል::

የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽንና አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰርኩ

ደሃና ወረዳ

የጽዳት ችግር መኖሩን በማመን የነዋሪዎችን ሀሳብ ተጋርተዋል:: ይህን ችግር ለመፍታትም ቀደም ባሉት ጊዜያት ከከተማው ራቅ ያለ ዘመናዊ የቆሻሻ ማስወገጃ ለማዘጋጀት በእቅድ ተይዞ እንደነበር አቶ ሰርኩ ጠቁመዋል::

ይሁን እንጂ፣ ከተማው ሰፍቶ የተመረጠው ቦታ መኖሪያ ሰፈሮች መሀል በመሆኑ ለቆሻሻ ማጠራቀሚያው በታሰበው አካባቢ ያሉትን ነዋሪዎች የግድ ግምት ከፍሎ ማስነሳት እንደሚገባ አቶ ሰርኩ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል:: ሆኖም በአቅም ጉዳይ እስካሁን ተግባራዊ ባይደረግም በሂደት ግን የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል::

ከመድረክ ውይይት በኋላም ነዋሪዎችን በማወያየት በየቤታቸው በ20 ሜትር ክልል ያለውን ለማጽዳት ስምምነት ላይ ተደርሶ የከተማው ጽዳት ጅምር መኖሩን አቶ ሰርኩ ጠቁመዋል:: ከየአካባቢው የተሰበሰበ ቆሻሻ የሚወገድበት ጊዜያዊ ቦታ መዘጋጀቱንም ተናግረዋል:: ተፋሰሶችም በተመሳሳይ መጽዳዳት መጀመሩን ጠቁመዋል::

የውይይቱ ውጤት በነዋሪዎች እይታ

አቶ በለጠ ዳኘው የተባሉ የከተማዋ ነዋሪ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ኗሪውንና አመራሩን በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ፊት ለፊት አገናኝቶ ማወያየቱ የከተማው ነዋሪዎች ችግር በህዝቡና በአመራሩ በይፋ እንዲታወቅ አስችሏል ይላሉ:: ከዚህ ባለፈም ለዘመናት ሲነሳ የነበረው “የኢንዱስትሪ መንደር ይገንባልን” ጥያቄ ምላሽ ያገኘው በመድረኩ መሆኑን ተናግረዋል::

አስር አለቃ ደመቀ ቀለሙ በበኩላቸው መድረኩ በህዝብ ዘንድ ትልቅ ንቅናቄ መፍጠሩን ተናግረዋል:: ህዝቡ “እውነትም ዴሞክራሲ አለ!” እስከማለት መድረሱን ጠቁመዋል:: ከዚህ ባለፈ በመድረክ የተነሱ ሀሳቦችም ለመሪዎች ትልቅ ግብአት መሆናቸውን አስር አለቃ ተናግረዋል::

“ይህ በመሆኑም” ይላሉ አቶ ሰርኩ “በቀጣይ ግን ከተማ አስተዳደሩ የኢንዱስትሪ መንደር በመከለሉ ባለሀብቶች ከገቡ እና የታሰበው ፋብሪካ ከተከፈተ ወጣቱ የስራ እድል ይፈጠርላቸዋል::

የባህርዛፍ ምርቱንም ለባለሀብት ከመሸጥ በኢንተርፕራይዝ ደረጃ የተደራጁ የአካባቢው አንቀሳቃሾች እየተወዳደሩ እንዲሰሩ በቀጣይ መታሰቡንና አሁን እየሰሩ ያሉ መኖራቸውንም አቶ ሰርኩ ተናግረዋል::

ጤናበከተማው ነዋሪ በአቶ አድማስ ጌታሁን ተነስቶ

የነበረው ጥያቄ ደግሞ “በነፋስ መውጫ ከተማ ተገንብቶ የተመረቀው ሆስፒታል መሳሪያ አልባ ነው:: የሙያተኛ እጥረትም ስላለ ይሟላላት?” የሚል ነበር::

ከውይይቱ በኋላ ግን ችግሩን ለመፍታት ጥረት በመደረጉ በሆስፒታሉ ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመር እየተዘረጋ እና ሙያተኞችም እየመጡ እንደሆነ አቶ አድማስ አረጋግጠዋል::

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ፋንታሁን ሰለሞን እንዳሉን ደግሞ የሆስፒታሉ ስራ አለመጀመር የእለት ተእለት የህሙማን ጥያቄ ነበር:: ከውይይት መድረኩ በፊት የኤሌክትሪክ መስመር አለመዘርጋት፣ ለራጅ ክፍል ጨረር የማያስወጣ በር አለመገጠም፣ ቀዶ ጥገና ክፍል መሳሪያዎች አለመገጣጠም ችግሮች ነበሩ:: በአሁኑ ወቅት ግን የኤሌክትሪክ መስመሩ ተዘርግቷል:: ለቀዶ ጥገና ክፍል አስፈላጊ የሆኑት የደንብ ልብሶችና ሌሎች ግብዓቶች በተወሰነ ደረጃ ቢቀሩም በቅርቡ ይሟላሉ:: በባለሙያ ቁጥርም የተሟላ ባይሆንም ለውጥ አለ::

ፅዳት“የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ ወይም ማስወገጃ

ቦታ ባለመኖሩ ቆሻሻ የትም ይጣላል:: በዚህም ምክንያት የከተማው ፅዳት ተጓድሏል:: በቀጣይ

“የውሃ መቆፈሪያ ማሽን መጣ ይባላል - ውሃ ሳያወጣ ተመልሶ ይሄዳል”

“በመሰረተ ልማት ዝርጋታ የተዘነጋን ህዝቦች ነን”

“በፊት ውጣ እባል ነበር ዛሬ ግን ስብሰባው ግባ በመባሌ ደስ አለኝ”

“...ከመድረኩ በኋላ ጥሩ ሰራን ያልነውም ይህ ነው” አቶ ሰርኩ ታረቀኝ - የነፋስ መውጫ ከተማ አስ/ከ/ል/ኮን/አገ/ጽ/ቤት ኃላፊ

Page 17: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 17በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ለወጣቶችከዚህም ከዚያም

ወደ ገጽ 29 ዞሯል

አብርሃም አዳሙ

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ብዙዎች ነግሰው አልፈውበታል:: በዘመናዊና በባህላዊ የሙዚቃ ስልቶች ተጽዕኖ የፈጠሩ ስራዎች ዛሬም ድረስ ዘመን ተሻግረው ለጆሮ አይሰለቹም:: ዝነኛው የኢትዮጵያ የዘመናዊ ሙዚቃ ንጉስ ጥላሁን ገሠሠ ህይወቱ እስካለፈበት 2005 ዓ.ም ድረስ ለ40 አመታት በሃገሪቱ የሙዚቃ ታሪክ ትልቅ ተጽዕኖ ፈጥሮ አልፏል:: የእርሱ ስራዎች ትናንት ብቻ ሳይሆን ዛሬም እንደ አዲስ ይደመጣሉ:: ወደፊትም ይህን የዝና ስፍራ የሚያጡት አይመስልም::

ዝነኛዋ አቀንቃኝ አስቴር አወቀም ብትሆን በሙዚቃ ንግስና ውስጥ ካሉ ስመጥር አርቲስቶች አንዷ ናት::

እርሷ 24 የሚደርሱ አልበሞችን ለኢትዮጵያ ሙዚቃ አበርክታለች:: ሆኖም ከጥላሁንና ከአስቴር

ጃኖዎቹባሻገር እነ መሃሙድ አህመድ፣ ሙሉቀን መለሠ፣ ጌታቸው ካሳ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ ብዙነሽ በቀለ፣ ሂሩት በቀለ፣ ታምራት ሞላ፣ ኤፍሬም ታምሩ፣ መልካሙ ተበጀ፣ ሜሪ አርምዴ እና አስናቀች ወርቁን የመሳሰሉ አርቲስቶች የኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ መዝገብ ሲከፈት ስማቸው በጉልህ የሚነበቡ ስመ ጥርና ቀደምት የጥበብ ሰዎች ናቸው:: ከእነዚህ የሙዚቃ ሰዎች አንዳንዶቹ ሙዚቃን ከአፍላው እድሜያቸው እስከ መቃብራቸው ድረስ ህይወታቸውን የሙዚቃ መድረክ ላይ አቁመው ያለፉ ናቸው:: ቀሪዎችም አደራቸውን ለተተኪዎቻቸው ያስተላለፉ፣ አንዳንዶችም ዛሬም ድረስ “ሙዚቃ ህይወቴ” ብለው የሚኖሩ ናቸው::

በሌላኛው የኢትዮጵያ የሙዚቃ መዝገብ ውስጥ ወጣቱን ሙዚቃ ቀማሪ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ

አፍሮን) ሳያመሰግኑ ማለፍ ከባድ ይሆናል:: ከ15 አመታት በፊት ወደ ሙዚቃ ኢንዱስትሪው የተቀላቀለው ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ አድማጩን የልብ ትርታ ያቆመ የሙዚቃ ስራዎችን አበርክቷል:: ብዙዎች ቴዲ አዲሱ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉስ እንደሆነ ይናገራሉ:: የእርሱ ስራዎች ከደቡብ አፍሪካ እስከ አሜሪካ ከመካከለኛው ምስራቅ እስከ አውስትራሊያ በስፋት ተደምጠውለታል:: ምን አልባትም የኢትዮጵያ ሙዚቃ ይበልጥ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እያገኘ የመጣው በዘመነ ቴዲ አፍሮ እንደሆነ ይነገራል:: የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከቅርብ አመታት ወዲህ ሬጌና ሮክን የመሳሰሉ የሙዚቃ ስልቶች ከሃገርኛው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ለዛ ጋር ተዋህደው መቅረባቸው ነው::

ይህንን መንገድ ወደ ላቀ ደረጃ ካሸጋገሩት ሙዚቀኞችና የሙዚቃ ቡድኖች መካከል ሌላኛው በቅርብ ስሙ እየገነነ የመጣው ጃኖ የሙዚቃ ቡድን ግንባር ቀደሙ ነው ይላል ሲኤን ኤን:: ጃኖ ባንድ ከአምስት አመታት በፊት ነው የተመሰረተው:: ታዋቂው የሙዚቃ መድረክ አዘጋጁ አዲስ ገሰሰ ደግሞ የዚህ ባንድ መስራችና ስራ አስኪያጅ(ማናጀር) ሆኖ እስከ ቅርብ ጊዜ ሰርቷል::

ጃኖ ባንድ አሁን በኢትዮጵያ ዘመነኛ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ አዲስ ሃሳብና ስልት ይዞ መምጣት የጀመረ ባንድ ነው:: ኢትዮ - ሮክ የባንዱ መለያ የሙዚቃ ስልት ቢሆንም ከዚህ ውጪ ሬጌን ከድንቅ የሙዚቃ ቅመራ ጋር አዋህደው ይሰራሉ:: ጃኖዎች ምንም እንኳ የሙዚቃ ስልታቸው ከባህር ማዶ የተቀዳ ቢሆንም ቆየት ያሉ ሃገራዊ የሙዚቃ ስራዎችን በማንሳት ዳግም እንዲያንሰራሩ ማድረግ የቻለ ባንድ እንደሆነ ፎርቹንን ጠቅሶ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል::

በምዕራብ ጐጃም ዞን በቡሬ ከተማ አስተዳዳር በከተማ ግብርና ኢንቪስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶች ውጤታማ መሆናቸውን ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ::

የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለባቸው ገነቱ እንደተናገሩት በከተማ ግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶች በተለያዩ የችግኝ ምርቶች ውጤታማ እየሆኑ ነው::

በተለይ ለመኖሪያ ቤትና፣ ለሆቴሎች፣ ለድርጅት፣ ተቋሞችና ለመዝናኛ የሚሆኑ የአበባ ችግኞችን በስፋት እያለሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል::

ከወጣቶች መካከል የጉድ ሆኘ ችግኝ ጣቢያ ባለቤት የሆኑት ወይዘሮ ቦሰና እያሱ እንደተናገሩት “ወደ ዚህ ስራ አንድገባ ያደረገኝ ነገር የተለያዩ ችግኞችን ለማፍላት ለእኔና ለሃገሬ መጥቀም እንዳለብኝ የውስጤ ራዕይ ነበረኝ:: ስለሆነም ከተማ አስተዳደሩ 600 ካ.ሜ ቦታ ከአስረከቡኝ በኋላ በ50 ብር መነሻ በማድረግ ስራየን ከባለቤቴ ጋር ጀምረሁ አሁን 40.ሺህ ብር ለመድረስ ችያለሁ በውስጤም ለሁለት ግለሰቦች የስራ ዕድል ፈጥሬያለሁ” ማለቱን የቡሬ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል::

የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው

ወጣቶች ተጠቃሚ ሆኑ

በምዕራብ ጐጃም ዞን ቋሪት ወረዳ ስራ አጥ ወጣቶችን በተለያዩ የስራ ዘርፎች በማደራጀት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የወረዳው ቴክኒክ፣ ሙያ እና ኢንተርኘራይዝ ል/ጽ/ቤት አስታወቀ::

መንግስት ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ በሚሰራባቸው ማኑፋክቸሪንግ፣ ከተማ ግብርናና ኮንስትራክሽን ዘርፎች ወጣቱን በማደራጀት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል:: መንግስት ወጣቱን በማደራጀትና የስራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ ለማድረግ በወጣው መርሐ ግብር መሰረት እንደ ወረዳ በ2008 በጀት ዓመት ስድስት ሺህ 453 ስራ አጥ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ አቅደን 92 ከመቶ ያህሉን በከተማና በገጠር የስራ ዕድል ፈጥረናል ሲሉ የቋሪት ወረዳ ቴክኒክ፣ ሙያ እና ኢንተርኘራይዝ ል/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መኳንንት ወርቅነህ ገልፀዋል::

በብረታብረት ስራ ተሰማርተው ውጤት ያስመዘገቡት አቶ ስዩም ምህረት መንግስት ባመቻቸልኝ የብድር፣ መስሪያና መሸጫ ቦታ ላይ ሙያየን ተጠቅሜ እየሰራሁ ነው፤ በተጓዳኝም የንብ ማነብ ስራ በመስራት ከኪራይ ቤት ወጥቼ ቤተሰቦቼን በአግባቡ መምራት ችያለሁ ብለዋል::

በአንድ ሺህ 500 ብር መነሻ ካፒታል እንዲሁም ቴ/ሙ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በአደረገልኝ ድጋፍ የተሻለ ለውጥ ለማመጣት ከአነስተኛ ታዳጊ ወደ መካከለኛ ታዳጊ መሸጋገር ችያለሁ፤ ኘሮጀክት በመቅረጽ ለወጣቶች መዝናኛ በማዘጋጀት እኔንም ወጣቱንም ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራሁ ነው ሲል ሌላው አቶ አለበል አለሙ ተናግሯል::

ወጣቶች በከተማ

ግብርና ተሰማሩ

Page 18: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 18 ከተማ ልማትከአብክመ ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ጋር በመተባበር የቀረበ

ወደ ገጽ 29 ዞሯል

ማስታወቂያ ባለቤቱ

ማን ነው?

የአብርሃም በዕውቀት

አዕምሮ ደሳለኝ በዓፄ ሠርፀድንግል አንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት የስምንተኛ ክፍል የልዩ ፍላጎት ተማሪ ነው:: አዕምሮ ዓይነ-ስውር ሲሆን በባሕር ዳር ከተማ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ የብዙዎችን እገዛ ይፈልጋል:: የመኪና መንገድ የሚያቋርጠው አንድም በድምፅ በመታገዝ መኪና በቅርብ ርቀት መኖር አለመኖሩን አድምጦ አለበለዚያም ሌሎች ዓይናማ ሰዎች ሲሻገሩ አብሮ በመሻገር ነው::

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን አስፓልት መንገድ ለማቋረጥ ድምፅን እንደ አንድ አማራጭ መጠቀም ወደ ማቆም ደረጃ ደርሷል፤ ምክንያቱም “ከአንድም ሁለትና ሦስት ጊዜ ከአደጋ ተርፌያለሁ፤ አንድ ቀን ባሕር ዳር ከተማ ከጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ወደ ዳሸን ባንክ ለመሻገር ቆሜ በቅርበት የሚመጣ መኪና መኖር አለመኖሩን አዳመጥኩ:: አጠገቤ ላይ ቆሞ የፊልም ማስታወቂያ ከሚናገር የመኪና ላይ ስፒከርና ጀኔሬተር በቀር የሚሰማኝ አልነበረም:: ከዚያ መንገዱ ነፃ ነው ብዬ ለመሻገር ገባሁ፤ ለካስ ሌላ የሚያልፍ መኪና ኖሮ ድንገት መሀል ላይ ደረሰብኝ:: እኔ የትም መሮጥ አልችልም፤ በሾፌሩ ብርቱ ጥረት ወደ አስፓልቱ አካፋይ ተጋጭቶ አተረፈኝ” በማለት በድምፅ ማስታወቂያዎች አማካኝነት የደረሰበትን የመጀመሪያውን አስደንጋጭ ገጠመኝ አጫወተኝ::

ሁለተኛ ገጠመኙንም ቀጠለ “ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ነው:: በሕር ዳር ከተማ ከፓፒረስ ሆቴል በኩል ተነስቼ ወደ ገበያው አቅጣጫ ለመሻገር መንገዱ ዳር ላይ ቆሜያለሁ:: ከፊት ለፊት ካሉት አትክልት መሸጫ ቤቶች አካባቢ ደግሞ ‘የባሕር ላይ ጉዞ ወደ ጣና ሐይቅ ገዳማት’ እያለ የሚጮኽ መኪና ላይ የተጠመደ ስፒከርና ጀኔሬተር አለ:: ከዚያ መንገድ ዳር ቆሜ አዳመጥኩና ከፓፒረስ በኩል ወደ ሞንታርቦው አቅጣጫ መሻገር ጀመርኩ፤ አንደኛውን አቅጣጫ መንገድ በሰላም ተሻገርኩ:: ከአካፋዩ ላይ ትንሽ ቆም ብዬ ሳዳምጥ ከስፒከሩና ጀኔሬተሩ ውጭ የሚሰማ ድምፅ አልነበረም:: ቶሎ ለመሻገር እየገሰገስኩ ገባሁ አንድ ከአደባባዩ በፍጥነት ሲወጣ የነበረ የቤት መኪና ለትንሽ ሳተኝ፤ ለነገሩ ሳተኝ ማለት አልችልም፤ በመጠኑ በጎኑ መትቶ አስፓልቱ ላይ ጥሎኛል”

አዕምሮ እንደሚናገረው በተደጋጋሚ ከመኪና አደጋ ተርፏል፤ የአደጋውን መንስኤ ግን ከአዕምሮና ሌሎች ዓይነ-ስውራን ውጭ ማንም ያጤነው

መሆኑን እርግጠኛ መሆን ያስቸግራል:: ዓይነ-ስውራን በእግራቸው ሲጓዙ ለተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ እየተጋለጡ ያሉት በመንገድ ላይ በሚነገሩ ገደብ አልባ የድምፅ ማስታወቂያዎች የተነሳ መንገድ ጠቋሚ ድምፆችን መስማት ስለማይችሉ ነው::

አዕምሮ ከማስታወቂያዎች ጋር በተያያዘ በድምፅ አልባዎቹም ላይ ቅሬታ አለው:: “ለምሳሌ ባሕር ዳር ከገበያ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ በቀኝ በኩል ስትመጣ በርካታ ተንቀሳቃሽ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች እየጠለፉ ይጥሉሀል:: አንዳንዶቹ የተተከሉ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ደግሞ እግራቸው ከአትክልቱ ውስጥ ይሆንና ሰሌዳው ግን ከአትክልቱ ወጥቶ ወደ እግረኛ መንገዱ ይገባል:: ይኼኔ በዱላ ስንፈትሻቸው አይገኙም፤ ድንገት ብቻ

ግንባራችንን ይመቱናል፤ ወደ ሱቆቹ ጠጋ ብለን እንዳንሄድ ደግሞ ወደ እግረኛ መንገዱ አስጠግተው የሚያስቀምጧቸው ሸቀጦች ይጠልፉናል:: ብቻ የማስታወቂያ ሰሌዳ አተካከልና ማስነገር እንዲሁም ሳይተክሉ በእግረኛ መንገድ ላይ ማስቀመጥን የሚከለከል ሕግ ቢኖረው ጥሩ ነበር” ይላል አዕምሮ::

ማስታወቂያ በባሕር ዳር ከተማ የውበትና ጽዳት መጓደል፣ የድምፅ ብክለት፣ የእንቅስቃሴ ስጋት ምንጭ ነው ቢባል ማጋነን አይመስልም:: እኔ ተዘዋውሬ ባስተዋልኳቸው የባሕር ዳር ከተማ ሁሉም አካባቢዎች ማስታወቂያ ያልተለጠፈበት አጥር፣ የስልክ እና የመብራት እንጨት ምሶሶዎች እና ባጃጅ ማግኜት ዕድለኛ መሆንን ይጠይቃል:: ምክንያቱን ባላውቅም አዳዲስ በተተከሉት የብረት የመብራት ምሶሶዎች ላይ ብቻ ብዙም ማስታዎቂያ ተለጥፈው አላየሁም::

ወ/ሮ አብሥራ ሙሉዓለም በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጊዮርጊስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘውና በሌሎችም አምስት የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ማስታወቂያ በመለጠፍ አገልግሎት ላይ ተሠማርተው ይገኛሉ:: እርሳቸውም የማስታወቂያ መለጠፊያና ማስነገሪያ ስርዓት አለመበጀት ከተማዋን ዋጋ እያስከፈላት እንደሆነ ይናገራሉ::

“እኔ ማስታወቂያ በየቦታው መለጠፉንና እንደልብ ማስነገሩን የምቃዎመው ገበያ ስለሚቀርብኝ አይደለም፤ በሰሌዳ ላይ ሲለጠፉ ማስታወቂያዎች ሆን ተብሎ ስለማይቀደዱ፣ ዝናብ ስለማያጠፋቸው፣ ቀናቸው ሳያልፍም ሌላ ማስታወቂያ ላያቸው ላይ ስለማይደረብባቸው ነው፡፡ ግን የቤትህ አጥርና ተጨንቀህና ተጠበህ ቀለም ያስቀባኸው ግድግዳ በማትፈልገው ማስታወቂያ ተዝጎርጉሮ ስታገኘው ያበሳጫል:: በመኪና እየዞሩ የሚቀሰቅሱትም ቢሆን በየመንደሩ እየመጡ በጠዋቱ እንደመርዶ ነጋሪ ሲጮኹብህ፣ ማታ ደክሞህ መተኛት በፈለክበት ሰፈርህ መጥተው ሲያምባርቁብህ ያበሳጫል” ብለዋል ወ/ሮ አብሥራ::

ወ/ሮ የአብሠራና ሌሎችም ተደራጅተው የማስታወቂያ መለጠፍ አገልግሎት የሚሰጡት በአምስት የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ሰሌዳዎች ሲሆን በቀን ለሥራ ቅጥር ማስታወቂያ አምስት ብር እና ለጨረታ ማስታወቂያ 10 ብር ያስከፍላሉ:: ማስታወቂያ አስነጋሪዎች አንድ ቦታ ከከፈሉ በቀሪዎቹ ላይ እነወ/ሮ የአብሥራ ተንቀሳቅሰው ይለጥፋሉ፤ የተከፈለበት ቀን ሲያልቅም ያነሳሉ::

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስለማስታወቂያ

“ተግባሩ ተቀንጭቦ ለኮሙኒኬሽን፣ ተቀንጭቦ

ለባሕልና ቱሪዝም፣ የተወሰነው ደግሞ ለደንብ

ማስከበር የተሰጠ በመሆኑ በአግባቡ ለመምራት

አስቸጋሪ አድርጎታል፤ እኛ የፈቃድ አገልግሎቱን ብቻ

ትኩረት ሰጥተን እንሠራለን፤ ነገር ግን ከፈቃድ ውጪ

የሚሠሩትን፣ የሚያሠራጩትንና ከተፈቀደላቸው

ገደብ በላይ የሚያስተዋውቁትን ለመቆጣጠር ስልጣን

የለንም::”አዕምሮ ደሳለኝ ተማሪ

“እኔ የትም መሮጥ አልችልም በሹፌሩ ብርቱ ጥራት ወደ አስፓልቱ አካፋይ ተጋጭቶ አተረፈኝ “

Page 19: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 19በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ከዓለም አካባቢ

አጫጭር ዜናዎች(አብርሃም አዳሙ)

አብርሃም አዳሙ

የእስራኤል ተሟጋቾች የእስራኤል - ፍልስጤም

ፍጥጫ እንዲያቆም ጠየቁ

ወደ ገጽ 39 ዞሯል

ወደ ገጽ 32 ዞሯል

በሶርያ አማጽያንና በመንግስት ወታደሮች የተከበቡ ከተሞች አስቸኳይ እርዳ ያስፈልጋቸዋል ተባለ

ከ19ኛው ክፍለ ዘመን በፊት በአውሮፓና በአሜሪካ የባሪያ ንግድ ትልቅ ቦታ ነበረው:: ከአፍሪካ፣ ከእስያና ከአንዳንድ የላቲን አሜሪካ ሃራት ዜጎች ለባርነት ወደ እነዚህ ሃገራት ተጉዘዋል:: ሆኖም ከ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በኋላ ማለትም የእንግሊዝ የኢንዱስትሪ አብዮት መቀጣጠልን ተከትሎ ባርነት ‹ንግድ› መሆኑ በይፋ እንዲቆም ተደረገ:: የዚህ ምክንያቱ ደግሞ የሰውን ጉልበት የሚተኩ የኢንዱስትሪ ውጤቶች በአብዮቱ መፈጠራቸው ነው:: ነገር ግን የቀደመው ባርነት በዓለም ላይ ይፋዊ ንግድ መሆኑ ቢያከትምም አሁን ሌላኛው የባርነት ንግድ በይፋ ተከፍቷል ይላል ቢቢሲ::

ዛሬ ላይ ዘመናዊ ባርነት ወይም የጉልበት ብዝበዛ በመላው ዓለም እየተጧጧፈ ነው:: መቀመጫውን አውስትራሊያ ያደረገው ‹‹ወክ ፍሪ ፋውንዴሽን››ን ጫምሮ ሌሎች አዳዲስ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በእስያ ብቻ ከ45 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ወደ ዘመናዊ ባርነት እየገቡ ይገኛሉ:: ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት የባርነቱ ሰለባዎችም ልዩ ልዩ ጥቃት ይደርስባቸዋል::

ፋውንዴሽኑ በ2016 ባወጣው ዓለም አቀፍ የባርነት ማውጫ (Global Slavery Index) ላይ ስለ ዘመናዊ ባርነት ወይም የጉልበት ብዝበዛ ትርጉም ‹‹አንድ ሰው ራሱን መከላከል በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ በዛቻ፣ በማስፈራራት፣ በጉልበት ወይም በሃይል፣ በጥቃት፣ በማስገደድ እና በማታለል

የሚደርስበት የስራ ጫና ባርነት ወይም የጉልበት ብዝበዛ ተደርጎ ወሰዳል›› ይላል::

እንደ ጥናቱ ከሆነ ዘመናዊ ባርነት ከተጠቀሰው ጉዳይ ውጭ ያሉ የስራ ሁኔታዎችን ሊያካትት ይችላል:: በዘመናዊ ባርነት ሰለባዎቹ በጥቃትና በሃይል ካለፈቃዳቸው እንዲሰሩ ከማድረግ ባሻገር እዳ ለመክፈል ሲባል የነጻ ጉልበት አገልግሎት እንዲሰጡ ይገደዳሉ:: ይህ አይነቱ ባርነት የዕዳ ባርነት በሚል የሚታወቅ ሲሆን ልጅን ለጉልበት ብዝበዛ አሳልፎ መሸጥ፣ የግዳጅ ጋብቻና የግዳጅ የቤት ሰራተኝነት በዚህ ሊካተቱ ይችላሉ::

ታዲያ አሁን በመላው ዓለም ጎልተው የሚጠቀሱና ከፍተኛ የጉልበት ብዝበዛ የሚካሄድባቸው አምስት ዓይነት የዘመናዊ ባርነት ምሳሌዎች እንዳሉ ይነገራል:: አምስቱንም ባርነቶች በዚህ ጽሁፍ እንመለከታለን::

የባህሩ ኢንዱስትሪየሰብዓዊ መብት ተማጋቾች እንደሚሉት

ከሆነ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በህገወጥ ዝውውር

በግዳጅ በዓሣ ማጥመድ ስራ ላይ ይሰማራሉ:: አብዛኞቹም ማንም ሳያያቸውና እርዳታ ሳያገኙ ለዓመታት በባህር ዳርቻዎች ውስጥ ታፍነው የሚኖሩ ናቸው:: ተጠቂዎቹ እነደሚናገሩት ከሆነ ማንም ከነዚህ ስፍራዎች አለያም ከተሰማራበት የዓሣ ማጥመድ ተግባሩ ለማምለጥ ቢሞክር እጣ ፋንታው ሞት ነው::

በእንዲህ ዓይነቱ ተግባር ደግሞ ታይላንድን የሚስተካከላት የለም:: ሃገሪቱ የባህር ምግቦችን ከሚያቀርቡ የዓለም ሃገራት በሦስተኛነት ትቀመጣለች:: ለዚህ ተግባር ሲባልም ከበርማና ከካምቦድያ በህገወጥ ዝውውር የሚመጡ በሽህ የሚቆጠሩ ዜጎች ይህን ሕይወት ይቀላቀላሉ:: ታዲያ ለዚህ ስራ የሚመጡ ሁሉም ዜጎች በፋብሪካዎች እንደሚቀጠሩ ቃል ተገብቶላቸው ነው:: ሆኖም ታይላንድ ከገቡ በኋላ በግዳጅ በዓሣ ጀልባዎች ላይ የጉልበት ሥራ እንዲሰሩ ይገደዳሉ:: የታይላንድ መንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ዝውውሩን ለማስቆም ጥረት እየተደረገ ነው ይላሉ::

ከጉልበት ብዝበዛው ያመለጠ አንድ በርማዊ ሁኔታውን አስመልክቶ ለቢቢሲ እንደተናገረው በትንሽ ጀልባ ላይ በቀን ከ20 ሰዓት ያላነሰ ዓሣ በማጥመድ ያሳልፋል:: እርሱ ለዚህ ስራው ምንም ዓይነት ክፍያ

ዘመናዊ ባርነትግዙፉ የስደተኞች ጣብያ ሊዘጋ ነው

በኬንያ የሚገኘውና የዓለማችን ትልቁ የስደተኞች ጣቢያ የሆነው ዳዳብ በመጭው ህዳር ወር እንደሚዘጋ ኬንያ አስታወቀች::

የኬንያ የሃገር ውስጥ ሚኒስትሩ ጆሴፍ ኒኬሴሪ እንዳሉት ዳዳብን ለመዝጋት ሃገራቸው ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ ደርሳለች:: ስደተኞችን ለማስወጣትም ኬንያ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ከሶማልያ መንግስት ጋር በቅንጅት እንደምትሰራ አስታውቀዋል::

ዳዳብ የስደተኞች መጠለያ፣ የሶማልያ ግጭትን ተከትሎ በፈረንጆቹ 1991 የተከፈተ ሲሆን በወቅቱ በጦርነቱ የሚፈናቀሉ ሶማሊያውያንን በመታደግ ትልቅ ሚና አበርክቷል:: በአሁኑ ወቅትም ከ300 ሺህ በላይ ሶማሊያውያን በዚህ የስደተኞች መጠለያ ይኖራሉ::

ሆኖም ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ መጠለያ ጣቢያውን መሰረት በማድረግ ከአልሸባብ የሚሰነዘሩ የሽብር ጥቃቶች እንዳሰጓት ኬንያ አስታውቃለች:: ለመጠለያው መዘጋትም ሃገሪቱ እየደረሰባት ያለው ጥቃት ቀዳሚ ምክንያት መሆኑን ቢቢሲ ጠቁሟል:: ኬንያ ጣብያውን ለመዝጋት 10 ሚሊዮን ዶላር መድባለች::

በሌላ በኩል ባለፈው ዓመት በኬንያ 148 ተማሪዎች የተገደሉበትን የጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ የሽብር ጥቃት የመራው ሙሃመድ ኩኖ መገደሉን የሶማልያ ባለስልጣናት አስታውቀዋል:: አልሸባብ መሪው ስለመገደሉ ያመነ ሲሆን የሰውየው መገደል ለሶማልያና ለፀረ አልሸባብ ተዋጊዎች ትልቅ ድል እንደሆነ ተነግሯል::

በሶርያ በዘለቀው የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት በአማጽያንና በመንግስት ወታሮች የተከበቡ ከተሞች አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ያፈልጋቸዋል ሲሉ አሜሪካ፣ እንግሊዝና ፈረንሳይ አሳሰቡ::

ሃገራቱ እንዳሉት የሶርያ መንግስት በሰኔ ወር መጀመሪያ ሊደረግ የነበረውን የሰብዓዊ እርዳታ ስምምነት መጣሱን አስታውቀዋል:: የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የእስራኤል የሰላም ተደራዳሪዎች በእስራኤልና ፍልስጤም በድንበር አካባቢ እንዲሁም በጋዛ ያለው ፍጥጫ እንዲያቆም ጠየቁ:: የቡድኑ መሪ የሆነው ኤሪክ የሊን ለአልጀዚራ እንዳለው በእስራኤልና ፍልስጤም መካከል የአቋም ለውጥ እንዲመጣ ቡድኑ የሰላምና እርቅ ስብሰባ በጋዛ እንደሚያደርግ ተናግሯል::

‹‹እስራኤልና ፍልስጤም ስምምነት ላይ የሚደርሱበት ጊዜ እስኪመጣ ጥረታችንን እንቀጥላለን:: ሁላችንም በጋዛ የሚገኙ ፍልሰጤማውያን እኩል መብት እንዳላቸው እንገነዘባለን:: ከእነርሱም ጋር እየሰራን ነው›› ሲል የሊን ተናግሯል::

የቡድኑ የሰላም ጥሪ በሃማስና በሌሎች የሰላም ተደራሪዎች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቱን አልጀዚራ አስነብቧል::

የተባበሩት መንግስታ የምግብ ድርጅት እርዳታው ሊደርስ የሚችልበትን መንገድ ሊያመቻች ይገባል::

ቃል አቀባይ የሆኑት ጆን ኬርቢ ለቢቢሲ እንዳሉት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሶሪያውያን ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ድጋፍ ይሻሉ:: ጨምረው እንዳሉት

Page 20: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 20

ከገፅ 1 የዞረ

ኢትዮጵያ ...

ከገፅ 1 የዞረ

ሴቶች...

ከገፅ 1 የዞረ

ኢንተርፕራይዞች ...

ከገፅ 1 የዞረ

ነዋሪዎች...ተችግረናል” ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል::

በዚሁ ወረዳ የ01 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ቄስ አዳነ ምህረቴ እንደተናገሩት ከአምደ ወርቅ - ተከዜ ያለውን 48 ኪሎ ሜትር መንገድ ለመስራት ታስቦ ግንባታው ቢጀመርም ከአራት ዓመት በላይ ወስዶም ቢሆን እስካሁን አላለቀም:: በዚህም ከአምደ ወርቅ - ባህር ዳር ለመድረስ 280 ኪሎ ሜትር ብቻ ይወስድብን የነበረውን መንገድ በሠቆጣ ዙረን ከ600 ኪሎ ሜትር በላይ ለመጓዝ ተገደናል ብለዋል::

የአምደ ወርቅ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ እምወደው ባየ በበኩላቸው ከአምደ ወርቅ - ተከዜ እየተሰራ ያለው መንገድ የግራምባጥ እና የሲልዳ ከተሞችን በቅርብ ርቀት እየተዋቸው መሄዱ ከተሞቹ በመሠረተ ልማት ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ማድረጉን በቅሬታቸው ገልፀዋል::

የአምደ ወርቅ - እብናት መንገድ ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ሙሀመድ እንድሪስ ከአምደ ወርቅ - ተከዜ ያለው መንገድ መልከዓ ምድራዊ አቀማመጡ ምቹ ባለመሆኑ መንገዱን በታሰበው ጊዜ ማጠናቀቅ አልቻለም ብለዋል:: የግራምባጥ እና የሲልዳ ከተሞችም መንገድ ሥራው ከተጀመረ በኋላ የተመሠረቱ ስለሆኑ እንጂ ከተሞቹ የመሰረተ ልማቱ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ታስቦ የተሠራ አይደለም ብለዋል:: መንገዱ የመዘግየት ሁኔታ ቢታይበትም

በ2009 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚሠጥም ቃል ገብተዋል::

አቶ ሙሉ ስዩም የተባሉ የከተማዋ ነዋሪ ደግሞ ከተማዋ አብዛኛውን ጊዜ የመብራት ተጠቃሚ አይደለችም:: መብራት ሲመጣም ሀይሉ ይበዛና በቴሌቪዥን እና በሌሎች ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ገልፀዋል::

የአምደ ወርቅ ዲስትሪክት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ አዳነ በሰጡት ምላሽ የመብራት መስመሩ ምሰሶ በእንጨት የተሠራ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ብዙውን ጊዜ ስለሚወድቅ የሀይል መቆራረጥ እንደሚያጋጥም ተናግረዋል:: ይህም የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እንዲቃጠሉ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፤ ችግሩን ለመፍታትም የእንጨት ፖሎችን በኮንክሪት ፖሎች ለመቀየር ጥያቄ ማቅረባቸውን አስረድተዋል::

የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይልማ ወርቁ የመንገድ ስራው በ2007 ዓ.ም ያልቃል ቢባልም በማሽን እጥረትና የአካባቢው መልከዓ ምድራዊ አቀማመጥ ምቹ ባለመሆኑ ምክንያት ግንባታው መዘግየቱን ገልፀዋል:: የግራምባጥ እና የሲልዳ ከተሞች ግን የተመሰረቱት የመንገድ ሥራው ከተጀመረ በኋላ ሳይሆን ቀደም ብለውም የነበሩ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ይልማ ወርቁ፣ አቶ ሙሀመድ እንድሪስ ከተሞቹ የመንገዱ ግንባታ ከተጀመረ በኋላ የተመሰረቱ ናቸው ብለው የሰጡት ምላሽ ትክክል አለመሆኑን ተናግረዋል::

አዲስ ቴክኖሎጂ በቀላሉ ወደ አርሶ አደሮች ለማዳረስ የሚያስችል ነው:: ሀገሪቱ ይህን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም አቦካዶን በዘመናዊ መንገድ ብታመርት የአውሮፓን ገበያ የመቆጣጠር አቅም ይኖራታል ብለዋል::

ፕሮጀክታቸው የአቦካዶን ምርት በስፋት በማምረት ለአውሮፓና አረብ ሀገራት በማቅረብ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት አድርጐ እየሠራ መሆኑን የገለፁት አማካሪው እስካሁን በተላኩ ምርቶች የፈረንሣይ ሸማቾች መደሰታቸውን ገልፀዋል:: እስራኤል ፕሮጀክቱን ለመደገፍ የምርጥ ዘር አቅርቦትና ስልጠና ላይ የምታደርገውን እገዛም አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል::

የሜጫ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ደግአረገ በበኩላቸው የአካባቢው ወጣቶች በአቦካዶ ምርት ተሰማርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የወረዳ አስተዳደሩ የየአካባቢውን አርሶ አደሮች በማነጋገር ልቅ ግጦሽ እንዲቆምና በአቦካዶ ልማት እንዲተካ ማድረጉን ገልፀዋል:: በተደረገው ጥረትም በወረዳው የሚገኙ አራት ሺህ ወጣቶች አቦካዶ እንዲያመርቱ እገዛ እየተደረገላቸው መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል::

ባለፈው የምርት ዘመን 48 ኩንታል የአቦካዶ ምርት ለውጭ ገበያ መቅረቡን የገለፁት የጽ/

ቤት ኃላፊው ምርቱን የተጠቀሙ ኩባንያዎች ተጨማሪ ምርት እንዲላክላቸው እየጠየቁ በመሆኑ በቀጣዩ ዓመት በሁሉም የወረዳዋ ቀበሌዎች የተሻሻሉ የአቦካዶ ዝርያዎችን በማስፋፋት ወደ ውጭ የሚያቀርቡትን ምርት መጠን ለመጨመር ከማሻቡ ፕሮጀክት ጋር በቅንጅት እየሠሩ መሆኑን አብራርተዋል::

የአስማማውና ጓደኞቹ የህብረት ስራ ማህበር ሊቀመንበር አቶ አስማማው ወርቁ እንዳሉት ደግሞ በፍራፍሬ ልማት ተሰማርተው ራሳቸውን ለመቀየር ሥራ ጀምረዋል:: ማሻቩ በተባለው ፕሮጀክት እገዛ የተሻሻሉ የአቦካዶ ዝርያዎችን ተክለው እያለሙ መሆኑን ገልፀዋል:: ሊቀመንበሩ አክለውም ከሌሎች የግብርና ሥራዎች ጋር አቀናጅተው በመስራት እንስሳትን አድልበው አንድ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 85 ሺህ ብር ማግኘታቸውን ገልፀዋል::

በወረዳው ከሚገኙ 40 ቀበሌዎች በ24ቱ አርሶ አደሮቹ ተደራጅተው አቦካዶ በማምረት ላይ የተሠማሩና በወረዳው 39 ቀበሌዎችም የልቅ ግጦሽን በማስቆም የፕሮጀክቱን ዘላቂነት ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል::

ዝርዝር ዘገባውን በገጽ 4 ይመልከቱ

የሚሠማትን ነገር ምሽት ላይ መፃፍ ጭንቀቷን ቀለል ያደረገላት ስለሚመስላት በየእለቱ ትጽፋለች:: ይህን ተከትሎም የአጐቷና አክስቷ መገደል ‘በሀገሪቱ ፍትህ እንቅስቃሴ ጣልቃ መግባት አለብኝ’ የሚል መደምደሚያ ላይ አደረሳት::

ከዌስት ባንክ ከተማ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ናባ ሳልህ መንደር ነዋሪዋ ጃና ይህ ሁሉ ሲሆን የሰባት ዓመት ህፃን ነበረች:: ታዲያ በዚህ እድሜዋ በአካባቢዋ የሚካሄደውን ግጭት በእናቷ ዘመናዊ ስልክ ተደብቃ ትቀርጽ ነበር:: በመንደሯ የሚታዩ ሰላማዊ ሰልፎችን፣ ከእስራኤል ፖሊሶች ጋር የሚደረገውን ግጭት በሙሉ ትቀርፃለች::

በሙያው በሰለጠኑ ጋዜጠኞች ስለጉዳዩ የሚቀርቡት ዘገባዎች ግን ውስጧን ያሳምሟታል:: ሁልጊዜም እውነታውን ያድበሰብሱታል:: እርሷም ይሄን ለማጋለጥ የምትቀርፃቸውን ምስሎች በዩቲዩብ፣ ፌስቡክና ሰናፕቻት በመሳሰሉት ማህበራዊ ድረ

ከገፅ 6 የዞረ

ህፃኗ...ገፆች በመልቀቅ የጀማሪ ጋዜጠኛ ስራዋን ጀመረች::

ከምትለቃቸው ምስሎች ጋርም ‘እኛ አሸባሪ አይደለንም:: የሚደርስብንን ግፍ ተመልከቱ’ የሚሉ አጫጭር ገላጭ ዐረፍተነገሮች ትጨምራለች:: በከፈተችው የፌስቡክ ገጽም 80 ሺህ ተከታዮችን አፍርታለች::

የጃና እናት “ልጃችን በትምህርቷ እንድትገፋ ብንፈልግም ዝም እንድትል አንገፋፋትም ለነፃነቷ መታገል አለባት” በማለት የልጇን ሥራ ይደግፋሉ:: ጃና ከእናቷ ጋር በመሆን በአቅራቢያቸው ወደሚገኙ ትልልቅ ከተሞች በመዘዋወር የሚፈጠሩ ነገሮችን በምስል በመቅረጽ በቀጥታ ማስተላለፍ ስራዋን እስከ አሁን ቀጥላለች::

“ሳድግ በሙያው የሠለጠንኩ ጋዜጠኛ በመሆን ለሲኤን ኤን እና ፎክስ ኒውስ መስራት እፈልጋለሁ እነዚህ ታላላቅ ሚዲያዎች ሁልጊዜም በፍልስጤም ላይ የሚከናወኑ ነገሮችን በግልጽ አያወሩም::” እንዳለች ያስነበበን የአልጀዚራ ዘገባ ለዚህም እርሷ በሚዲያው ገብታ በፍልስጤም የሚፈፀመውን እውነት ማሳየት ዓላማዋ ነው ሲል አትቷል::

25 ዓመታት በአመራር ቦታዎችም ሴቶች በወረዳ 30 በመቶ፣ በክልል 17 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ጠቁመዋል:: ይህ በቀጣይ ሴቶች የአመለካከት ችግሮቻቸውን ፈትተው በብዛታቸው ልክ በሁሉም ዘርፍ ተሳትፏቸው 50 በመቶ ማድረስ እንዳለባቸው ወ/ሮ በላይነሽ አስገንዝበዋል::

የበአሉ ተሳታፊ ኮሎኔል ፀጋ ተወልደ በበኩላቸው “ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታችንን ለማረጋገጥ ያለፉት ታጋይ ሴቶች ያስቀመጡልንን ስንቅ ይዘን ከወንዶች ጐን መስራት አለብን:: ሴት

ስለሆን ብቻ የሚሰጠን ነገር የለም፣ ስለዚህ በሁሉም ዘርፍ የሚቀሩንን ታግለን ማሳካት አለብን” ብለዋል::

በአማራ ክልል የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሰራተኛና የበዓሉ ተሳታፊ ወ/ሮ ፈለግ አድማሱ በበኩላቸው ባለፉት 25 ዓመታት ሴቶች በሁሉም ዘርፎች ተሳታፊና ተጠቃሚ ቢሆኑም የበለጠ ለመስራት የአማራ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ሴቶችን አስተባብሮ ሊመራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል::

የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፈንታዬ ጥበቡም ሴቶች ባለፉት 25 ዓመታት ያገኟቸውን ውጤቶች መሠረት አድርገውና ችግሮችን ለይተው በመስራት ለበለጠ ውጤት እንደሚተጉ ተናግረዋል::

ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል አስመዝግቦ ወደ መካከለኛ ደረጃ ቢሸጋገርም እንደ መካከለኛ ደረጃ ኢንተርፕራይዝ ባለቤትነቱ ሊያገኘው የሚገባውን መንግስታዊ ድጋፍ ማግኘት አለመቻሉ በስራው ላይ እንቅፋት እንደፈጠረበት ተናግሯል::

አብዱልከሪም እንደሚለው የመስሪያ ቦታ፣ የገንዘብ ብድር እና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አለመኖር እንዲሁም ቢሮክራሲያዊ አሠራርና ኪራይ ሰብሳቢነት ሥራቸውን እየተገዳደራቸው መሆኑን ጠቁሟል::

ከደብረ ብርሃን ከተማ የመጣችው ወ/ሪት ሶፊያ መሀመድ ደግሞ ኢንተርፕራይዞቹ ወደ መካከለኛ ደረጃ ኢንተርፕራይዝነት ከተሸጋገረች በኋላ በሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እገዛ እየተደረገላት አይደለም::ለአብነትም

ለኢንተርፕራይዞቹ ብድር የሚያቀርቡ አጋር አካላት ብድር ለማግኘት ያለው ውጣ ውረድ አሰልቺና ስራ አስፈቺ መሆኑን ገልጻለች::ውጣ ውረዱን ቢያልፉትም እንኳ የሚጠየቁት ዋስትና ትልቅ በመሆኑ ወደ ሌሎች አበዳሪ ተቋማት ሄደው በከፍተኛ ወለድ ለመበደር መገደዳቸውን ገልጻለች::

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ብናልፍ አንዱለም ውይይቱን ሲያጠቃልሉ የመካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ችግሮች ለይቶ መፍትሄ በመስጠት በኩል የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ እንደነበር ተናግረዋል::

ምክትል ፕሬዝዳንቱ አክለውም በቀጣይ እያንዳንዱ አጋር አካል የተሰጠውን ኃላፊነት መወጣት አለመወጣቱ ክትትል እንደሚደረግበትና ተጠያቂነትን የሚያስከትል አሰራር እንደሚዘረጋ ተናግረዋል::

የዚህን ዘገባ ሙሉ ሀሣብ በገጽ 8 ይመልከቱ

የኢንተርፕራይዞች በዓል በሞዴሎች ሽልማት ተጠናቋል

Page 21: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 21በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. የሔዋን ገጽየሔዋን ገጽ

አባትሁን ዘገየ

ከዚህም ከዚያም

ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል

እየተሰራ ነው

ወደ ገጽ 24 ዞሯል

በገጠር የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት ተደራሽነት መስፋፋት የሴቶች የጉልበት አንግልትና የስራ ጫናን ማቃለል መቻሉን በምዕራብ ጐጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

በወረዳው የገጠር ቀበሌ የንፁህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ አለም ደለለ በሰጡት አስተያየት ከዚህ በፊት በአካባቢው የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት ባለመኖሩ በበጋ ወራት ውሀ ፍለጋ ረጅም የእግር መንገድ በመጓዝ ለጉልበት ድካምና ለጊዜ ብክነት ተጋልጠው ቆይተዋል፡፡

ዛሬ ግን በመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ የንፁህ መጠጥ ውሀ ተቋም በመገንባቱ በቅርባቸው የመጠጥ ውሀ አገልግሎት ተጠቃሚ ከመሆናቸው በተጨማሪ ያላግባብ ይባክን የነበረው ጉልበትና የስራ ጊዜ መቃለል መቻሉን ወይዘሮ አለም ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ወይዘሮ አንለይ መኮንን የተባሉ የወረዳው ኗሪ እንደገለፁት በዚህ ዓመት በመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ የንፁህ ውሀ ተጠቃሚ በመሆናቸው ጤናቸው ተጠብቋል፡፡

የወረዳው ውሀ ኢነርጅ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለኝ ዳኘ በበኩላቸው በገጠር ቀበሌዎች የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት አሁን ካለበት 51 በመቶው ወደ 58 በመቶ ከፍ ለማድረግ ከሦስት ሚሊዮን 900 ሺህ ብር በላይ ካፒታል ውጭ አንድ መቶ አስራ አነድ የንፁህ መጠጥ ውሀ ተቋማት በመገንባት ላይ ናቸው ማለታቸውንም የወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል፡፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል ትኩረት ሰጥተው በመስራት ላይ እንደሚገኝ የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት አስታወቀ::

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ይበልጣል ሙኔ ለወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት እንደገለፁት በወረዳችን የሚከናወኑ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል በቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ የእቅዳቸው አንድ አካል አድርገው በመያዝ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል:: ግንዛቤው የተፈጠረው በቀበሌና በወረዳ ደረጃ በተገኙ መድረኮች ሲሆን ለሀይማኖት አባቶች፣ ለተማሪዎችና ለአመራሮችም ተሰጥቷል ብለዋል::

ቀጣይም በተለይ በወረዳችን እየተከናወነ የሚገኘውን የልጅነት ጋብቻ ለመከላከል ከፍትህ ጽ/ቤት፣ ለሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤትና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር ትኩረት ሰጥተው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል:: ለህብረተሰቡም ይህንን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ለማስቀረት የግንዛቤ ፈጠራ ስራውን አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉም ተናግረዋል::

የውሀ ግንባታዎች የሴቶችን የስራ ጫና እየቀነሱ

ነው

ጐረቤታም እናቶች ሰብሰብ ብለው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች እያወሩ ነው:: ድንገት ወሬያቸው ወደ ልጅ አስተዳደግ ተቀየረና ተጠናክሮ ቀጠለ:: ከወሬያቸው እንደተረዳሁት አንደኛዋ እናት ሶሰት ልጆች በየሁለት ዓመቱ ልዩነት አካታትለው ወልደዋል:: እኚህ እናት ሶስቱም ልጆቻቸው በየተራ እየታመሙባቸው ቁም ስቅላቸውን እንዳዩ ተናገሩ:: “ልጅ ማሳደግ እንዲህ ከባድ መሆኑን ባውቅ ኖሮ መቼ እሞክረው ነበር” እንዳሉም አስታውሳለሁ::እኚህ እናት እንዳሉት በእርግጥም ልጅ ማሳደግ በጣም ከባድ ነው:: በተለይም አሁን አሁን እናቶች ይህን እውነታ ይበልጥ እየተረዱት የመጡ ይመስላሉ::

በመሆኑም “ልጅ በዕድሉ ያድጋል” በሚለው ያረጀ ያፈጀ አባባል ተተብትበው በላይ በላይ ከሚወልዱት ይልቅ “ልጅ ማሳደግ ከባድ ነው” የሚለውን እውነት በማጤን አቅደው የሚወልዱ እናቶች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል::በቅርቡ ወደ ኮምቦልቻ ከተማ አቅንቼ በነበረበት ወቅት

“ልጅ በእድሉ ያድጋል…”፤ ያለፈበት ብሂል

በ”03 ኮምቦልቻ ጤና ጣቢያ” አግኝቼ ያነጋገርኳቸው እናቶች፣ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች ያረጋገጡልኝም ይህንኑ እውነት ነው:: ወይዘሮ ሙሉቀን ስማቸው የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪ ናቸው:: ወይዘሮዋ “የስድስት ዓመት ልጅ አለኝ:: የወለድሁት ፈልጌ ነው:: አሁን ስላደገ፣ እኔም ጀምሬው የነበረውን ትምህርቴን ስላጠናቀቅሁ ከባለቤቴ ጋር ተመካከረን ተጨማሪ ልጅ ለመውለድ ስለወሰን ክንድ ላይ ያስቀበርሁትን የረዥም ጊዜ የወሊድ መከላከያ ለማስወጣት ነው የመጣሁት” ሲሉ የቤተሰብ ዕቅድ ተጠቃሚነታቸውን ገልፀውልኛል::ወይዘሮ ሙሉቀን እንደነገሩኝ የዛሬ

ስድስት ዓመት አካባቢ የመጀመሪያ ልጃቸውን ከወለዱ በኋላ ከባለቤታቸው ጋር ተነጋግረው የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ለመከታተል ወስነዋል::ትምህርታቸውን እስከሚያጠናቅቁ ድረስ ላለመውለድም ከባለቤታቸው ጋር ተስማምተዋል:: ይህ ስምምነታቸውም ተተግብሯል::

በዚህም ወይዘሮዋ በጣም ተጠቃሚ ሆነዋል፤ “አቅጀ መውለዴ ለእኔም ሆነ ለልጄ ጤንነት ጠቅሞኛል:: በ”ኢኮኖሚ” ረገድም አልተቸገርሁም:: በልጅ ላይ ልጅ ብደራርብ ኖሮ እንኳን ከፍየ ለመማር ልጀንም በአግባቡ ማሳደግ ይሳነኝ ነበር:: አሁን ግን ልጄ የሚፈልገውን እያገኘ ዘና ብሎ አፀደ ህፃናት ትምህርት ቤት ገብቶ ተምሯል” ሲሉ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው ያስገኘላቸውን ፋይዳ አብራርተውልኛል::

“ሶስት ልጆች አሉኝ:: የመጀመሪያ ልጀን የወለድሁት በ16 ዓመቴ ነው:: አቅጀው ወይም አስቤው አልነበረም የወለድሁት:: አሁን ግን የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኛለሁ” ያሉኝ ደግሞ ወይዘሮ ፋጡማ መሀመድ ናቸው:: ወይዘሮዋ እንደገለፁልኝ ጤና ጣቢያው የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎችን እንደ እናቶች ፍላጐት እያቀረበ ነው:: እርሳቸውም ቀደም ሲል መርፌ ነበር ይጠቀሙ የነበሩት:: አሁን ደግሞ በክንድ የሚቀበረውን መቆጣጠሪያ ዘዴ እየተጠቀሙ ነው::

በጤና ጣቢያው የድህረ ወሊድ አገልግሎት እየተሰጣቸው ያገኘኋቸው ሌላዋ እናት ወይዘሮ ሶፊያ ሰይድም፣ አንድ ልጅ ብቻ እንዳላቸውና ይህን ልጃቸውንም የወለዱት አቅደው እንደሆነ አጫውተውኛል:: የሚጠቀሙበት የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴም የረዥም ጊዜ እንደሆነ ገልፀውልኛል:: “የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት መጠቀም የልጆችን ፍላጐት እያሟሉ ሳይጨናነቁ ለማሳደግ ይረዳል:: የመማር ዕድላቸውን ያስፋል:: ለልጆችም ሆነ ለእናቶች ጤንነት ይጠቅማል:: ይሄን የጤና ባለሙያዎች በሚሰጡኝ ትምህርት፣ በተለይም ደግሞ በተግባር አይቸዋለሁ” የሚሉት ወይዘሮ ሶፊያ ሳያቅዱ መውለድ ከማህበረሰቡ፣ ወልዳ መከራ አይታ ካሳደገች እናትም ጋር ሳይቀር እንደሚያራርቅ ጠቁመዋል::

ሲስተር ዘሀራ ሰይድ በ”03 ኮምቦልቻ ጤና ጣቢያ” የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ባለሙያ እንደሚሉት ደግሞ በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ

እናቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ የመጠቀም ልምዳቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መጥቷል:: የባሎች ግንዛቤም ዳብሯል:: በዚህ የተነሳ አገልግሎቱን ለማግኘት ከሚስቶቻቸው ጋር ወደ ጤና ጣቢያው የሚመጡ ባሎች እንዳሉም ሲስተር ዘሀራ ይናገራሉ::ይህ ግንዛቤ ሊመጣ የቻለውም “እናቶች ህፃናት ታሞባቸው ይዘው ሲመጡ፣ ክትባት ለማስከተብ፣ ለተለያዩ የጤና ምርመራዎች ሲመጡ ስለቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ጠቀሜታ ስለምናስተምራቸው ነው” ብለዋል::

“እናቶች የበለጠ የሚጠቅማቸው የረዥም ጊዜ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ ነው” የሚሉት ሲስተር ዘሀራ ስለጠቀሜታው በማስረዳት ብዙዎቹን እናቶች የዚህ ዘዴ ተጠቃሚ እያደረጉ እንደሆነ ጠቁመዋል::

አቅጀ አንድ ልጅ ወልጃለሁወይዘሮ ሶፊያ ሰይድ

ወ/ሮ ሙሉቀን ስማቸው የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ሲሰጣቸው

Page 22: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 22 ለህፃናት ለህፃናት ከዚህም ከዚያምደረጀ አምባው

እንቆቅልሽ

1. ሁለት ወንድማማቾች በመንገዱ ግራና ቀኝ ይኖራሉ ነገር ግን ተያይተው አያውቁም እነማን ናቸው?

2. የአህያ መቃብር እወቁልኝ?

3. ሁሉን የምታለብስ ዛፍ ማን ናት?

የእንቆቅልሽ መልስ

1. አይን

2. የጅብ ሆድ

3. ጥጥ

አንድ ዓይናችን ጠንካራ ሁለተኛው ደካማ እይታ እንዳለው ታውቃላችሁ::

የማይሰራ ሰዓት በቀን ሁለት ጊዜ በትክክል ይቆጥራል::

ማር ምን ጊዜም አይበላሽም::አቮካዶ ለወፎች መርዛማ ነው::ጀሮ እና አፍንጫ ዕድገታቸውን

የማያቋርጡ ሲሆን ዓይን ግን ስንወለድ ያለን እስክንሞት አብሮን ይቆያል::

በዓመት በአማካኝ ሰባት ሺህ ጊዜ እንተነፍሳለን፡፡

ምንጭ፡- livin3.com

ተማሪባለ ህንፃውልጆች እንደምን ሰነበታችሁ?

ሰሞኑ የሚታየው ቀዝቃዛ አየርና ዝናብ የክረምቱን

መምጣት ይጠቁማል… አይደል? ክረምት እየመጣ ነው ማለት ደግሞ የዓመቱ ትምህርት እየተጠናቀቀ ነው ማለት ነው:: የዓመቱ ትምህርት ደግሞ እንዲሁ አይጠናቀቅም ፈተና ይዞ ብቅ ይላል:: ታዲያ ልጆች ከበፊቱ በበለጠ ደብተራችሁን የምታዩበት ጊዜ በመሆኑ ጨዋታን በጣም መቀነስ ይገባችኋል:: ‘እሺ!’ አላችሁ? ጐበዞች!

ሰሞኑን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች አንዱ ወደ ሆነው አዞል አካዳሚ ጐራ ብዬ በጉብዝናው ለየት ያለ ሽልማት ያገኘ ልጅ አነጋግሬያለሁ::

ኤርምያስ ዓለም ይባላል:: እድሜው 10 ዓመት ሲሆን የሶስተኛ ክፍል ተማሪ ነው:: ከሁለተኛ ወደ ሶስተኛ ክፍል ሲዘዋወር 98 ነጥብ ስምንት አማካይ ውጤት በማምጣት አንደኛ ሆኖ ተዘዋውሯል:: በዚህ ዓመት ደግሞ በአንደኛው ወሰነ ትምህርት አሁንም 98 ነጥብ ስምንት በማምጣት አንደኛ በመሆን የአምናውን ውጤት አስጠብቋል::

የቀን ውሎውን እንዲያጫውተኝ ስጠይቀው ሁልጊዜ ከመኝታው የሚነሳው ከንጋቱ 11 ሰዓት ከ30 እንደሆነ ገለፀልኝ:: ከዚያም እስከ 12 ሰዓት አንድ ትምህርት እስከ 12 ከ30 ደግሞ ሁለተኛውን ትምህርት አጥንቶ ለትምህርት ቤት ጉዞ ይዘጋጃል::

ትምህርት ቤት ውስጥ መምህር ሲያስተምር በጥሞና እንደሚያዳምጥ የሚናገረው ኤርምያስ በትምህርት ሰዓት ዋና ዋና ነጥቦችን በማስታወሻ ይይዛል:: ከትምህርት ሰዓት በኋላም የያዘውን

ሁለት ወንድ ልጆች የወለደ አንድ ድሃ ሰው ነበር:: ታሞ በመድከሙ ለሞት በተቃረበ ጊዜ ያለው ሀብት አንድ አህያ ብቻ ስለ ነበር ይህንኑ ልጆቹ እንዲካፈሉት ተናዘዘ:: ወዲያው ከኑዛዜው በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሞተ::

ከሟቹ ልጆች አንደኛው ልጅ በጣም ባለፀጋ ሲሆን ሁለተኛው ግን የእለት ምግብ የሌለው ችግረኛ ነበር:: ከድህነቱም ብዛት ገና አባቱ ከመሞቱ የሚበላው ቸገረው:: ስለዚህም ከበርቴ ወንድሙን “እባክህ ወንድሜ ይህንን አህያችንን

የአንድ ድሃ ሰው ኑዛዜሸጠን እንካፈል” አለና ለመነው:: ባለፀጋው ወንድሙም በሀብቱና በገንዘቡ ብዛት ተመክቶ ለችግረኛው ወንድሙ “እኔ አርጄ ነው እንጂ ሸጨ አልካፈልም” ሲል በመቃወም መለሰለት::

ሁለቱ ወንድም አማቾችም በዚህ ምክንያት ተጣሉ:: በሀገሩ ከሚገኘው ዳኛ ዘንድ ሄዱ:: ወንድማማቾቹም ወደ ፍርድ ቤት የመጡበትን በየተራ ዘርዝረው አመለከቱ:: ዳኛውም በሁለቱም በኩል የቀረበለትን መግለጫ ከሰማ በኋላ “አርዳችሁ ተካፈሉት” ብሎ ፈረደ:: በዚህ ጊዜ ሀብታሙ በጣም ደስ አለው ችግርኛው ግን አዝኖ አምሮ አለቀሰ:: ሆኖም ከዳኛ የተሰጠ ትእዛዝዝ መከበርና መፈፀም ስላለበት አህያው ታረደና ሥጋው ሁለት ቦታ ተመደበ:: ያህያው ስጋ ከተከፈለ

በኋላ ባለፀጋው ድርሻውን ለውሾቹ ሰጣቸው ድሀው ግን እንኳን ውሻ ዶሮ የሌለው ነበርና ፈንታውን ከታረደበት ሜዳ ላይ ጥሎት ሄደ::

ከዚህ በኋላ ደሀው እያዘነና እየተከዘ ተቀምጦ ሳለ በድንገት “ቤቴን በእሳት አቃጥዬ እሄዳለሁ” ብሎ ተነሳ:: የሚኖርበት ጐጆና የባለፀጋውም ትልልቅ አዳራሾች ባንድ አጥር ግቢ ውስጥ ይገኙ ነበር::

በዚህ ጊዜ ባለፀጋው ከብቱና ገንዘቡ አሳዝኖት “ግምቱን ልስጥህ እንጂ ለምን ታቃጥላለህ? ያለዚያ የኔም ቤት አብሮ ሊነድ አይደለምን?” ሲል ጠየቀው:: እሱም “እንቢ እኔ ገንዘብ አያስፈልገኝም ቤቴን አቃጥዬ ነው የምሄደው” ሲል መለሰለት::

“እንግዲያውስ ዳኛ ሳይፈርድ እንዲሁ ተነስተህ አታቃጥልም” በማለት ተጣሉ:: ወደ

ፍርድ ቤትም ለማመልከት ተያይዘው ሄዱ:: ዳኛውም የሚያውቁት ያው ከዚህ በፊት የዳኛቸው ነበር:: እሱም ሁለቱም ባለጋራዎች ያመለከቱትን ከሰማ በኋላ “ቤቱን አቃጥሎ ይሄድ እንጂ ለማን ብሎ የደከመበትን ጥሎ ይሄዳል” ብሎ ፍርድ ሰጠ::

ባለጐጆውም ዳኛው እንደ ፈረደለት ቤቱን በእሳት ለኮሰው:: በዚህ ጊዜ ነፋስ ነበረና የባለፀጋ ወንድሙን አዳራሽ እሳቱ ተምዘግዝጐ አያያዘው ምንም ቢጯጯህና ቢደክምም ለማዳን ስላልቻለ እልፍኙ ማድ ቤቱ ጐተራውም ሳይቀሩ በሙሉ ተቃጠሉበት::

ልጆች በሰው ላይ ተንኮል በማሰብ መጥፎ መስራት በራስ ላይ ችግር ስለሚያመጣ ሁልጊዜም ለሌላ ሰው ቅን ሁኑ!

ማስታወሻ በማንበብ እውቀቱን ያጠናክራል:: በጣም የሚወደው የትምህርት ዓይነት

ሂሳብና እንግሊዝኛ ሲሆኑ በሁለቱም ትምህርቶች ምንም ጥያቄ ላለመሳሳት እንደሚጥር ይናገራል:: በአንደኛው ወሰነ ትምህርት እንግሊዝ 100 ሲያመጣ ሒሳብ 99 አግኝቷል::

ከትምህርት ቤት መልስ ከዘጠኝ ሰዓት እስከ 10 ሰዓት እረፍት ካደረገ በኋላ የቤት ሥራውን በመስራት ጀምሮ እስከ አንድ ሰዓት ተኩል ድረስ ያነባል:: ከራት በኋላ

ስዕሉን በመሣል ተለማመዱ

ፊልሞችን በቴሌቪዥን በመመልከት ያሳልፋል::

ለወደፊቱ መሆን የሚፈልገው የህዋ ተመራማሪ ሲሆን ለዚህም እንደ ምክንያት የሚያነሳው ሃገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የተሻለ ደረጃ ደርሳ ለማየትና ስሟን ለማስጠራት ነው::

ቤተሰቦቹ የሚከብደውን በማስረዳት፣ ቤት ሥራ ከሰራ በኋላ ለእነርሱ በማሳየት ትክክለኛነቱን እንደሚያረጋግጡለት ይናገራል:: ዘወትር የሚያጠናበትን ፕሮግራም ያወጡለት ወላጆቹ በሰዓቱና በትምህርት ዓይነቱ ላይ ከእርሱ ጋር ውይይት በማድረግ ከተስማሙ በኋላ ነው::

ባለፈው ዓመት ባመጣው ከፍተኛ ውጤት በትምህርት ቤቱ ውስጥ ከሚገኙ ህንፃዎች አንዱን ህንፃ በስሙ ለአንድ ዓመት የተሰየመለት ኤርምያስ ከፍተኛ ኩራት እንደሚሰማው ይናገራል:: ይህን ህንፃ በሌላ ጐበዝ ተማሪ ላለመነጠቅ ከበፊቱ በበለጠ በማጥናት እየተጋ መሆን ገልጿል::

“ተማሪዎች ጊዜያቸውን በሰዓት በመከፋፈል ማጥናትና ከደብተራቸው ጋር ያላቸውን ፍቅር መጨመር ከቻሉ ከፍ እያሉ ሲሄዱ በቀላሉ ውጤት ላይ ይደርሳሉ” ያለው ኤርምያስ ውጤትን ለማሻሻል ሁልጊዜም ጥረት የሚያደርግ ተማሪ ያሰበው ላይ እንደሚደርስ መገንዘብ እንዳለበት ይመክራል::

ልጆች! ካነበባችሁት ታሪክ ቁም ነገር አገኛችሁ? መልካም እንግዲህ ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም የተሻለ ውጤት ለማምጣት ሁልጊዜ መጣር በመጨረሻ ካሰቡት ቦታ እንደሚያደርስ ታሪኩ ያስገነዝባልና በምክሩ ተጠቀሙበት::

እስከ ምሽቱ አምስት ሰዓት በየግማሽ ሰዓቱ ትምህርት በመቀያየር ያጠናል::

በየመካከሉ ባሉ ትርፍ ጊዜዎቹ ከሰፈር ልጆች ጋር በመጫወት ወይንም የሕፃናት

Page 23: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 23በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ጤናችንጤናችን

ከአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ ጋር በመተባበር የቀረበ አጫጭር ዜናዎች

ሱራፌል ስንታየሁ

“ማጅራት ገትር ከኢቦላ የከፋ ነው”

ወደ ገጽ 34 ዞሯል

እናቶች የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት

እያገኙ ነው

(አብርሃም በዕውቀት)

አንዲት የስኮትላንድ የሕክምና ባለሙያ ለቢቢሲ እንደተናገረችው ዓለም አምርሮ ከሚፈራው ኢቦላ ይልቅ የማጅራት ገትር በሺታ የከፋ ነው:: ፓውሊን ካፈርኪ የተባለችው የስኮትላንድ የጤና ባለሙያ በአውሮፓውያኑ 2014 ነበር ወደ ሴራሊዮን አቅንታ የፀረ-ኢቦላ ዘመቻ የጀመረችው:: ነገር ግን በዚያው ዓመት ታሕሳስ ወር እሷም በኢቦላ በመጠቃቷ ወደ ሀገሯ ተመልሳለች::

ባለፈው የአውሮፓውያኑ ጥቅምት ወር ደግሞ ከኢቦላ በሚገባ ባለማገገሟ የተነሳ የማጅራት ገትር በሽታ ተጠቂ ሆና ወደ ሆስፒታል በድጋሜ ገብታለች:: አገግማ ከወጣች በኋላ ማጅራት ገትር በሽታዋ አገርሽቶባትም በየካቲት ወር ለሦስተኛ ጊዜ ሆስፒታል ተኝታለች::

የማጅራት ገትር የሕመም ስሜቱ በጣም ከባድ በመሆኑ መቋቋም ተስኗት በማደንዘዣ ታግዛ በሰመመን ውስጥ ሆና ሕክምና መከታተሏን የገለፀችው የጤና ባለሙያዋ “በተለይ በመጀመሪያዎቹ ቀናት የነበረው ሕመም እጅግ ከባድ ነው:: ያም ሐኪሞችን ስላሳሰባቸው በሰመመን ውስጥ ቆይቼ ከሕመሙ እፎይታ አግኝቻለሁ:: ብዙዎች የኢቦላን አደገኛነት ናገራሉ፤ ለእኔ ግን በጣም አደገኛው በሺታ ማጅራት ገትር ነው” ብላለች::

ከ22 ሺህ በላይ እናቶች የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን በምስራቅ ጐጃም ዞን የስናን ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ገለፀ፡፡

በስናን ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት የጤና መረጃ ተጠሪ ባለሙያ አቶ አዲሱ አብርሃም በወረዳ ደረጃ 22 ሺህ 70 እናቶች የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ በስብሰባዎች፣ በትምህርት ቤቶችና በጤና ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እየተሰጠ ነው ብለዋል፡፡ አገልግሎቱን በሶስት መንገድ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን የገለፁት ባለሙያው በክንድ የሚቀበር 4ሺህ 986 እናቶች በማህፀን የሚቀመጥ 161 እና የአጭር ጊዜ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት የሚያገኙ እናቶች ቁጥር 16 ሺህ 923 ናቸው፡፡

የተመጣጠነ የህዝብ እድገት ለኢኮኖሚ መሻሻል ያለው አስተዋጽኦ የጐላ መሆኑን በመገንዘብ የተለያዩ አማራጮችን በማቅረብ የቤተሰብ መሪዎች አባወራው ወይም እማወራዋ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረጉ ነው ብለዋል፡፡

ያልተፈለገ እርግዝናን የሚከላከል እንዲሁም አራርቆ ለመውለድ ያለውን አቅም በመገንዘብና ከሌሎች የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎቶች በተለየ የጐንዮሽ ጉዳት ስለሌለው በረጅም ጊዜ የወሊድ መቆጣጠሪያ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል ሲሉ ባለሙያዋ መናገራቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል፡፡

ወደ ሰሜን ሸዋዋ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ ስሄድ ለመጀመሪያ ጊዜየ ነው:: ሚያዚያ 1 ቀን 2008 ዓ.ም አረርቲ ጤና ጣቢያ ለስራ ጉዳይ ተገኝቻለሁ:: ወ/ሮ ዘይነባ ሁሴንም የመጀመሪያ ልጃቸውን ከቀኑ 6፡00 በዚሁ ጤና ጣቢያ ተገላግለው ነበር:: ከምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ፊናናጆ ቀበሌ የወሊድ ጊዜያቸው በመድረሡ በጤና ባለሙያዎች ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ በአምቡላንስ ወደ አረርቲ ጤና ጣቢያ ከመውለጃ ቀናቸው ሁለት ቀን በፊት እንደመጡ አጫወቱኝ::

በጤና ጣቢያ ቆይታቸውም በነፍሠ ጡሮች ማቆያ ክፍል እሳቸውንና አብረዋቸው የመጡት ቤተሠቦቻቸው ምግብ፣ ሻይ፣ ቡና… ሁሉንም የሚፈልጉትን ነገር እያገኙ መቆየታቸውንና ደስተኛ ሆነው መሠንበታቸውን ነገሩኝ::

ወ/ሮ ዘይነባን ከማዋለጃ ክፍል አናግሬ ስወጣ በስተቀኝ በኩል ከአስር የሚበልጡ ነፍሠጡር እናቶች ከአንድ አዲስ የህንፃ ቤት በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው አስተዋልኩ:: ወደ እነዚህ እናቶች ዘንድ ቀረብ ብዬ አነጋገርኳቸው::

ወ/ሮ ውብየ አይዛ ከአምራቢት ቀበሌ ወደ አረርቲ ጤና ጣቢያ ከመጡ 15 ቀን እንደሆናቸው ነገሩኝ:: የመጡበት ዋናው ምክንያትም ነፍሠጡር በመሆናቸው በጤና ጣቢያ እንዲወልዱ ተብሎ ነው:: በቤታቸው እያሉም በየጊዜው የቀበሌ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ክትትል ያደርጉላቸው እንደነበርና አሁን የመውለጃ ጊዜያቸው በመቃረቡ ከቤታቸው በአምቡላንስ እንዳመጧቸው አጫወቱኝ::

ወይዘሮ ውብየ በአረርቲ ጤና ጣቢያም የጤና ባለሙያዎች በየጊዜው የነፍሡጡሮች ማቆያ ቤት ድረስ እየሄዱ ክትትል እያደረጉላቸው እንደሆነ ገለፁሉኝ:: በጤና ጣቢያው ውስጥ ራሳቸውም ቡና እያፈሉ፣ በሠራተኞችም የሚፈልጉት ነገር እየቀረበላቸው ቤታቸው ያሉ እስኪመስላቸው የወሊድ ቀናቸውን እየጠበቁ እንደሆነ አጫወቱኝ::

በዚህ ጤና ጣቢያ ለነፍሠጡሮች ማቆያ ተብሎ በተዘጋጀው ባለአራት ክፍል አዲስ ቤት ውስጥ ፍራሽ ዙሪያውን ተዘርግቶበታል፣ ወለሉ የፕላስቲክ ምንጣፍ ተነጥፎበታል፣ ጽዱና ማራኪ መሆኑ እናቶች በቆይታው ጊዜ ምቾት አግኝተው እንዲወልዱ እያደረጋቸው ስለመሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም::

ከወ/ሮ ውብየ ጋር ወደ አረርቲ ጤና ጣቢያ አብሯቸው የመጣው አርሶ አደር በላይ ምትኩ ለነፍሡ ጡሮች ብቻ ሳይሆን አብረው ለሚመጡ አስታማሚ ቤተሠቦችም ጤና ጣቢያው ቡና፣ ምግብ፣ ምኝታ፣.. በማዘጋጀት ድጋፍ ያደርጋል ይላል:: ይህ መሆኑ ደግሞ ማንኛዋም እናት ወደ ጤና ጣቢያ ሄዳ እንድትወልድ ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥራልም አሉኝ::

በአረርቲ ጤና ጣቢያ በተገነባው ባለ አራት ክፍል የእናቶች ማቆያ እየተዟዟርኩ ጉብኝት እያደርኩ ቆየሁ:: በሌላኛው ክፍል ውስጥም አምስት

የሚደርሱ እናቶች በተዘረጋላቸው ፈራሽ ላይ ግማሾቹ ተቀምጠው፣ ግማሾቹ ደግሞ ጋደም ብለው ሀሣብ ይለዋወጣሉ፤ በጤና ጣቢያው ያላቸውን ቆይታ በተመለከተም አነጋገርኳቸውና ሁሉም ደስተኞች መሆናቸውን ገለፁልኝ::

ከአጊራ ቀበሌ የመጡት ወ/ሮ ሂሩት አለሙ በጤና ጣቢያው ከገቡ 16ኛ ቀናቸው እንደሆነ ይናገራሉ:: እሳቸውም እንደ ሌሎች እናቶች በቤታቸው በጤና ባለሙያ ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው የመውለጃ ቀናቸው ሥለደረሠ በአምቡላንስ ወደ አረርቲ ጤና ጣቢያ መላካቸውን አጫወቱኝ::

ወ/ሮ ሂሩት ከአሁን በፊት ሁለት ልጆችን በቤታቸው ተገላግለው ነበር:: እሳቸው ምንም እንኳን በቤት ውስጥ ቢወልዱም ሁሉንም በሠላም ነበር የተገላገሉት:: ሆኖም ግን በአካባቢያቸው በቤት ውስጥ የሚወልዱ እናቶችም ሆኑ ልጆቻቸው ሞቱ ሲባል መስማትና ማየት የተለመደ እንደነበር ይናገራሉ::

ለእናት እና ልጅ ሁሉም እጅ ለእጅ

በአረርቲ ጤና ጣቢያ የመውለጃ ጊዜያቸውን የሚጠብቁ ነፍሰ ጡር እናቶች

Page 24: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 24

ከገፅ 4 የዞረ

ኢትዮጵያ...ከገፅ 21 የዞረ

በ”03 ኮምቦልቻ ጤና ጣቢያ” አዋላጅ ነርስ የሆኑት ሲስተር ቃል ኪዳን አሊም እናቶች የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እንደሚመክሩና እንደሚያስተምሩ ገልፀውልኛል:: “በየ15ቀኑ እንዲሁም በየወሩ ከጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር ሆነን በያካባቢው በመዘዋወርም የምክር አገልግሎት እንሰጣቸዋለን:: እናስተምራቸዋለን:: ካስተማርናቸውና ግንዛቤያቸው ከዳበረ በኋላም የሚፈልጉትን የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ ጠይቀን በፍላጐታቸው መሰረት አገልግሎት እንሰጣለን” በማለትም የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን አጠናክሮ ለመቀጠል እየተደረገ ስላለው ጥረት ተናግረዋል::

አቶ ጥላሁን ፈንታየ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት የእናቶችና ወጣቶች ጤና አገልግሎት ባለሙያ ናቸው:: “ትልቁ ሥራችን ያልተፈለገ ወይም ያልታቀደ እርግዝናን መከላከል ነው” የሚሉት ባለሙያው የ2008 እቅዳቸውን ለማሳካት ጥሩ እንቅስቃሴ እንዳደረጉና በዚህም በዘጠኝ ወሩ ውስጥ ከአጠቃላይ እናቶች 75 በመቶ ያህሉን የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ አቅደው 85 በመቶ አፈፃፀም መድረሳቸውን ጠቁመዋል::

አቶ ጥላሁን እንደገለፁት እናቶች የሚፈልጉትን

የወሊድ መቆጣጠሪያ አገልግሎት በፈለጉበት ጊዜ የማግኘት መብት አላቸው:: ባለሙያዎች ለእናቶች የምክር አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ ይሄን ውሰጄ፤ ይሄን አድርጊ ብለው ማስገደድ እንደማይችሉ ገልፀዋል:: የእናቶችን መብት አክብረው፣ ምርጫና ፍላጐታቸውን ጠብቀው እየተመካከሩ መሥራታቸውም ለአፈፃፀማቸው መሻሻል እንደረዳቸው ተናግረዋል::

ሲ ስ ተ ር መቅደስ ሀዲስ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እንዳሉት ደግሞ በኮምቦልቻ ከተማ ዕድሜያቸው ለመውለድ የደረሱ ወደ 26 ሺህ እናቶች ይገኛሉ::

“እነዚህ እናቶች የተሟላ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት እንዲያገኙ እየሠራን ነው” የሚሉት ሲስተር መቅደስ በዘጠኝ ወራት ውስጥ 24 ሺህ እናቶች የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን አውስተዋል:: ሲስተር መቅደስ እንደተናገሩት እናቶች የመረጡትን የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ እንዲጠቀሙ ጥረት ያደርጋሉ:: ሆኖም “የረዥም ጊዜ የወሊድ መከላከያ ዘዴ ካጭር ጊዜው የበለጠ አስተማማኝ በመሆኑ እሱን እንዲጠቀሙ እንመክራለን” ብለዋል:: የረዥም ጊዜ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴን እንዲጠቀሙ ሲያደርጉ ተገቢውን የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ሠርተውና አሳምነው እንደሆነም ገልፀዋል::

“ልጅ በእድሉ ያድጋል…”...መሰጠቱን የገለፁት ኃላፊው ስልጠናው የአርሶ አደሮችን የክህሎት አቅም በማሳደግ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ሥራ እንዲሠሩ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል::

አቶ እንዳለው እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ ከእስራኤል ሀገር በሚመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ዝርያዎች በመታገዝ ለሚሠራው ስራ አንድ የማሰልጠኛ አዳራሽ በወረዳው አስገንብቷል:: አርሶ አደሮች ወደ ማሰልጠኛ ቦታው በመምጣት የንድፈ ሀሣብና የተግባር ልምምድ አድርገው ከተመለሱ በኋላ በየራሳቸው ማሳ እንደሚተገብሩት ተናግረዋል:: በዚህም የአርሶ አደሩን ህይወትና ኑሮ እንዲለውጥ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል::

ወረዳው ለመጀመሪያ ጊዜ አቦካዶን ወደ ውጭ በመላክ ነዋሪውን ተጠቃሚ ማድረጉን የሚናገሩት የጣቢያ ኃላፊው በዚህ ዓመት ሰኔ ወር ላይ ከሚሰበሰበው ምርት እስከ 10 ቶን የአቦካዶ ምርት ወደ ውጭ ሀገራት ለመላክ ዕቅድ መያዙን ጠቁመዋል::

የሜጫ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተመስገን ደግአረገ በወረዳው በተመረጡ 24 አቦካዶ አብቃይ አካባቢዎች ከእስራኤል ሀገር ዝርያቸው መጥቶ የተዳቀሉ 25 ሺህ የአቦካዶ ችግኞች ተሠራጭተዋል:: በቅርቡ በተደረገው ቆጠራ 18 ሺህ ያህሉ በተፈለገው ደረጃ አድገው ፍሬ ይሠጣሉ ተብለው የሚጠብቁ መሆናቸውን ተናግረዋል::

በወረዳው ከሚገኙ 40 ቀበሌዎች መካከል በ24 ቀበሌዎች ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮች ተደራጅተው ‘ይህ ምርት ይጠቅመናል!’ ወደሚል አስተሳሰብ መቀየራቸውን የገለፁት ኃላፊው የፕሮጀክቱን ዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችለው የልቅ ግጦሽን በ39 ቀበሌዎች በተሳካ ሁኔታ ማስቆም መቻሉን ገልፀዋል::

አቶ ተመስገን አክለውም በወረዳው ከስድስት ሺህ በለይ ለሆኑ ወጣቶች በዚህ ዘርፍ የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል:: ከእነዚህ ውስጥ አራት ሺህ ያህሉ አቦካዶ አብቃይ በሚል ተለይተው ልዩ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀዋል::

የአትክልትና ፍራፍሬ ሥራ የረዥም ጊዜ ዕቅድና ትዕግስት የሚያስፈልገው በመሆኑ፣ ቋሚ አትክልቶች ደርሰው ጥቅም እስኪሰጡ ድረስ ወጣቶችን በንብ ማነብ፣ በማድለብና በእርባታ ስራ እንዲሠማሩ መደረጉን አቶ ተመስገን ተናግረዋል::

ባለፈው የምርት ዘመን 48 ኩንታል አቦካዶ ለአውሮፓ ገበያ መቅረቡን የገለፁት ጽ/ቤት ኃላፊው ምርቱ ተቀባይነት በማግኘቱ የተለያዩ ኩባንያዎች ተጨማሪ ምርት እንዲቀርብላቸው ጥያቄ እያቀረቡ ነው ብለዋል:: ስራውን ዘላቂነት ባለው መልኩ ለማካሄድና ዝርያውን በሁሉም ቀበሌዎች ለማዳረስ

አርሶ አደሩ ከዚህ የተሻለ ተጠቃሚ መሆን የሚችልበትን መንገድ ለማሳካት ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውንም ገልፀዋል:: የኩባንያዎችን ፍላጐት ለማርካትና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቀጣዩ ዓመት በ26 ቀበሌዎች ላይ በሁሉም አርሶ አደሮች የተሻለ ምርት በማምረት ወደውጪ የሚያቀርቡትን አቦካዶ ቁጥር ለመጨመር የቅንጅት ሥራ እንደሚሠራ አብራርተዋል::

“የማሻቩ ፕሮጀክት ስልጠናውን በተግባር እያሳየ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ለውጥ እንድናመጣ እየረዳን ስለሆነ ባለውለታችን ነው” በማለት ፕሮጀክቱ በአርሶ አደሩ ዘንድ የተሰጠውን ከፍ ያለ ግምት አቶ ተመስገን ገልፀዋል::

የማሻቡ ፕሮጀክት በሜጫ ወረዳ የአቦካዶ ምርትን ለማስፋፋት እያደረገ ያለውን ጥረት ተዘዋውረው የተመለከቱት የኦሮሚያ ማሻቩ ፕሮጀክት አስተባባሪ ወ/ሮ አማረች ተስፋ አርሶ አደሮችና ወጣቶች በስልጠናው ያገኙትን እውቀት ወደ ስራ በመተርጐማቸው በአጭር ጊዜ ጥሩ ውጤት ሊያመጡበት እንደሚችሉ ያላቸውን እምነት ተናግረዋል::

እስራኤል ሀገር ተገኝተው የተለያዩ አካባቢዎችን መጐብኘታቸውን የተናገሩት ወ/ሮ አማረች እስራኤላዊያን የኢትዮጵያን አይነት መሬት፣ ውሀና የአየር ንብረት የላቸውም:: ነገር ግን ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ የሚሠሩት ሥራ የሚደንቅ ነው ብለዋል::

ሁለት ነጥብ ስምንት ቶን የአቦካዶ ምርት ወደ አውሮፓ ገበያ ወረዳቸው እንዳቀረበ የተናገሩት በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን መሰንቃን ወረዳ አስተባባሪ አቶ አመርጋ መንጅ በጉብኝቱ ያገኙትን እውቀት አቅማቸውን እንዳጐለበተው ተናግረዋል:: ከዚህ በኋላ ምን መስራት እንዳለባቸው በር መክፈቱንና የአካባቢው የመንግስት አመራሮች ትኩረት መስጠት ለውጤቱ ከፍተኛ መሆን ዋና መሠረት እንደሆነ አይተናል ገልፀዋል::

የማሻቩ ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት እስራኤላዊው ሚስተር ኦፈር ካህን የኢትዮጵያ የአየር ሁኔታ ለአቦካዶ ምርት ምቹነትና የኢትዮጵያ የግብርና ቴክኖሎጂ ስርፀት ስልት (ኤክስቴንሽን ፕሮግራም) አሠራርና አደረጃጀት ማራኪነት በጥናት በመረጋገጡ ፕሮጀክቱ ሀገሪቱን እንዲመርጥ ካደረጉት መስፈርቶች መካከል መሆናቸውን ገልፀዋል::

በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ስድስት ክልሎች በተመረጡ ቦታዎች አቦካዶን በስፋት በማምረትና ጥሩ ገበያ በመፍጠር የአርሶ አደሮችን ኑሮ ከመሠረቱ ሊቀይር የሚችልበትን ስራ ማቀጣጠል የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል:: ለዚህም 10 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር ተመድቦ የምርጥ ዘር አቅርቦትና የባለሙያ ስልጠና እየተካሄደ መሆኑን አብራርተዋል::

በተለያዩ ቦታዎች እንደ ችግር የሚቀርበው አርሶ አደሮች ፕሮጀክቱን በሙሉ ልቡ በመቀበል ስራውን

የአቦካዶ ምርት በአውሮፓ ገበያ ከፍተኛ ተቀባይነት እንዳለው የሚናገሩት አማካሪው እስራኤል በዚህ ምርት የአውሮፓን ገበያ ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገች ነው:: ኢትዮጵያም በዘርፉ በደንብ መስራት ከቻለች በተመሳሳይ ገበያውን ዘልቃ የመግባት ዕድሉን ታገኛለች ብለዋል::

ከኢትዮጵያ የተመረቱትን ጥቂት ቶን የአቦካዶ ምርቶች የፈረንሣይ ካምፓኒዎች እየተሻሙት መሆኑን አክለው የገለፁት አማካሪው የአረብ ሀገራትም ፊታቸውን ወደዚች ሀገር የሚያዞሩበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ገልፀዋል::

በኢትዮጵያ የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሚኒስቴር የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር ወርቃፈስ ወ/ፃዲቅ አርሶ አደሮች አቦካዶን በስፋት በማምረት በጠንካራ መሠረት ላይ የተጣለ የውጭ ንግድ እንቅስቃሴ ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ የተሻለ ለውጥ እንዲያመጡ ማድረግ ትልቁ የፕሮጀክቱ ራዕይ መሆኑን ተናግረዋል:: ይህንን ራዕይ ተግባራዊ ለማድረግ በቀጣዮች ሦስት ዓመት ለውጥ የሚያመጡ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል::

“ዕውቀቱን ማሻገር ያለብን እኛ ነን!” ያሉት ዶ/ር ወርቃፈስ ባለሙያዎች መሸከም ያለባቸውን ኃላፊነት በብቃት በመወጣት አርሶ አደሮች መሠረታዊ የኑሮ ለውጥ እንዲያመጡ ሊታገሉ እንደሚገባ አሳስበዋል::

የዚህ ፕሮጀክት ሌላው ዓላማ ከፍተኛ ምርት ማሳደግ ብቻ ሣይሆን ሞዴል የሆኑ አርሶ አደሮችን በማፍራት ወደ ውጭ በመላክ ዘርፉ ጠንካራ መሠረት የሚጥል ዕውቀቶችን ማስተዋወቅ ላይ ትኩረት አድርጐ እንደሚሰራ ተናግረዋል::

ተቆራርጠው አለመያዛቸው መሆኑን አማካሪው ተናግረው፤ ይህ ችግር ከተቀረፈና በደንብ መስራት ከተቻለ በቀጣዩ ዓመት ህብረተሠቡ ምርቱን ወደ ውጭ የማቅረብ ስራውን በተሻለ መልኩ አጠናክሮ እንደሚጀምር ገልፀዋል::

ከሀገሬው ምርት ጋር በመዳቀል የተዘጋጁ የአቦካዶ ችግኞች

Page 25: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 25በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ሳይንስና ቴክኖሎጂ

(አብርሃም በዕውቀት)

ሰሞነኛ ዜናዎችየዓለም የታዳሽ ኃይል ተጠቃሚነትእያደገ ነውአብርሃም በዕውቀት

በኤች አይ ቪ ተጠቁ

ደም ሳቢያ ሺዎች

በሕንድ በተበከለ

በዓለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ታዳጊ ሀገራት ከአደጉ ሀገራት በበለጠ ለታዳሽ ኃይል መዋዕለ-ንዋያቸውን ማፍሰሳቸው አስገራሚ መሆኑን ቢቢሲ በምንጭነት የተጠቀመው ጥናት ይገልጻል:: በዓለማችን በዚህ ወቅት ከስምንት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በታዳሽ ኃይል ዘርፍ ተሠማርተው እንደሚገኙም ተጠቅሷል::

በተለይ ያለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት 2015 ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የታዳሽ ኃይል ተጠቃሚነት የጎለበተበት ሆኖ ተመዝግቧል:: በዓመቱ በታዳሽ ኃይል ላይ የፈሰሰው መዋዕለ-ንዋይ ታዳሽ ያልሆኑ የኃይል ምንጮችን ለመገንባት ከወጣው በእጥፍ የሚበልጥ መሆኑን የተደረጉ ጥናቶች አረጋግጠዋል::

ለዓመታት ለታዳሽ ኃይል የሚመደበው መዋዕለ-ንዋይ እየጨመረ መምጣቱ ቢታወቅም በአውሮፓውያኑ 2015 147 ጊጋ ዋት ታዳሽ ኃይል መመንጨት ተችሏል:: ይህም በአፍሪካ አሁን ላይ በሁሉም የኃይል አማራጮች እየመነጨ ያለውን ኃይል ያክል እንደማለት ነው::

ምንም እንኳ የአውሮፓውያኑ 2015 የዓለም የነዳጅ ዋጋ በእጅጉ ያሽቆለቆለበት ዘመን ቢሆንም ቻይና፣ የተባበሩት አመሪካ፣ ጃፓንና ሕንድ ለታዳሽ ኃይል እጅግ ከፍተኛ መዋዕለ-ንዋያቸውን ያፈሰሱ ሀገራት መሆናቸውም በዘገባው ተጠቅሷል:: አጥኚዎቹ እንዳሉት በ2015 የነዳጅ ዋጋ ብቻ ሳይሆን የታዳሽ ኃይል ዋጋም መቀነሱ ለዘርፉ ትኩረት ማግኜት አስተዋፅዖ አበርክቷል::

ጥናቱን ያካሄዱት የተገበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የኃይል አቅርቦት ባለሙያዎችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የወከሏቸው ባለሙያዎች ናቸው:: የጥናት ቡድኑ ዋና ፀሐፊ ክርስቲን ሊንስ እንዳሉት በ2015/147 ጊጋ ዋት ታዳሽ ኃይል በዋናነት ከነፋስና ፀሐይ ኃይል ማመንጨት መቻሉ የታዳሽ ኃይል ዘርፉን ተወዳዳሪነትና አዋጭነት ያሳያል::

ክርስቲን ሊንስ ″ታዳሽ የኃይል አማራጮች የብዙ ሀገራት ምርጫዎች እየሆኑ ነው፤ በርካታ ሀገራትም በዘርፉ የሚያፈሱት መዋዕለ ንዋይ ጨምሯል:: ይህም ለዘርፉ ማደግ ትልቅ ተስፋ ነው² ብለዋል:: ለዘርፉ በ2015 (እ.ኤ.አ) 286 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጭ መሆኑንም ጥናቱ አሳይቷል:: ከዚህ ውስጥ ቻይና ከሲሶ በላዩን አውጥታለች፤ ይህም ታዳጊ ሀገራት ከበለፀጉት በላይ ለታዳሽ ኃይል ማውጣታቸውን ያመላከተ ሆኗል::

ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርታቸው ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ መዋዕለ-ንዋይ ለታዳሽ ኃይል በዓመቱ ያፈሰሱ ሀገራት ሞሪታኒያ፣ ሁንድራስ፣ ኡራጓይና ጃማይካ ናቸው:: ²ይህም የታዳሽ ኃይል አቅርቦት በዋጋ እየቀነሰ መምጣቱንና ታዳጊ ሀገራት ለታዳሽ ኃይል ትኩረት መስጠታቸውን የሚያመላክት ነው² ብለዋል ዋና ፀሐፊዋ ሊንስ::

ቢቢሲ እንደጻፈው ²የኃይል ፍላጎት በእጅጉ እያደገ ቢሆንም ታዳሽ የኃይል አማራጭን የመጠቀም ዝንባሌም እያደገ ነው:: ታዳሽ ኃይልን በከፍኛ ደረጃ በመጠቀም ሠንጠረዡን የምትመራው ብሪታንያ መሆኗም ለብዙዎቹ መደነቅን ፈጥሯል::

ሀገሪቱ በቀደሙት ዓመታት ጀምሮ ታዳሽ ያልሆነ ኃይል ቅነሳን ስትከተል ቆይታለች፤ ከትራንስፖርት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘም እስካለፈው ታህሳስ ወር ድረስ ብቻ 60% ታዳሽ ያልሆነ ኃይልን ቀንሳለች::

ምንም እንኳ የአውሮፓውያኑ የመዋዕለ-ንዋይ ፍሰት በ2015 ውድቀት የታዬበት በመሆኑ ለታዳሽ ኃይል የተደረገው የመዋዕለ-ንዋይ ፍሰት በ21 በመቶ የቀነሰ ቢሆንም የአህጉሩ አጠቃላይ የኃይል አቅርቦት ግን 44 ከመቶው በታዳሽ ኃይል መሸፈን ችሏል ያለው ዘገባው 173 የዓለም ሀገራት ከፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በኋላ ለታዳሽ ኃይል ልዩ ትኩረት እንደሰጡም ያትታል:: በተባበሩት አሜሪካ ብቻ 154 ኩባንያዎች ሙሉ በሙሉ የታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ለመሆን ወስነዋል::

ቢቢሲ በዘገባው ላይ ባይጠቅሳትም ኢትዮጵያም የታዳሽ ኃይልን በፖሊሲ ደረጃ ቀርጻ በመምራት ዓለም በምሳሌነት የሚወስዳት ሀገር ነች:: ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃልን ከውኃ፣ ከፀሐይ፣ ከነፋስ፣ ከደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻና ከእንፋሎት በማምረት የአረንጓዴ ልማት ኢኮኖሚ ተጠቃሚ ከሆነች ውላ አድራለች::

በሕንድ በአንድ ሆስፒታል በተፈጠረ የሕክምና ስህተት ሁለት ሺህ 234 ሰዎች በኤች አይ ቪ መያዛቸውን ቢቢሲ ዘገበ:: ቢቢሲ የአገሪቱን ባለስልጣናት ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ባለፉት 17 ወራት ብቻ ነው ይህን ያህል ዜጎች በደም ልገሳ አማካኝነት ለኤች አይ ቪ የተጋለጡት::

መረጃው ይፋ የተደረገው በአገሪቱ የኤች አይ ቪ (ኤድስ) መቆጣጠሪያ ድርጅት አማካኝነት ሲሆን የመረጃ ነፃነት አቀንቃኞች የድጋፍ ፊርማ አሰባስበው መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው መግለጫው የተሰጠው:: የመረጃ ነፃነት አቀንቃኙ ቸታን ኮታሪ ለቢቢሲ እንደገለፁት በሕንድ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ኤች አይ ቪ በደማቸው ውስጥ ይገኛል::

በደም ልገሳ አማካኝነት የኤች አይ ቪ ተጋላጭ ሆነዋል የተባሉት ከሁለት ሺ በላይ ሰዎች አብዛኞቹ በአገሪቱ ሰሜናዊ ግዛት ዩታራ ፕራዳሽ ነዋሪ ናቸው ተብሏል:: አብዛኞቹ የሰሜናዊ ግዛት ናቸው ይባላሉ እንጅ ምዕራባዊ ግዛቶቿ ጉጃራትና ማሃራሽትራም በርከት ያሉ ነዋሪዎች በቫይረሱ የተያዙባቸው አካባቢዎች ናቸው:: የአገሪቱ መዲና ደልሂም 264 ዜጎቿ የስተቱ ሰለባ ሆነውባታል::

ሚስተር ኮታሪ ²ይህ አሀዝ በመንግሥት የታመነው ነው፤ እኛ ግን ቁጥሩ ከተጠቀሰው ከሦስት እጥፍ እንደሚበልጥ መረጃ አለን² ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል::

በሕክምና ሕግ መሠረት ሆስፒታሎች በልገሳ የሚያገኟቸውንና ለሰዎች የሚሰጡትን ደም ከኤች አይ ቪ፣ ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ፣ ወባ እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ ግዴታ

አለባቸው:: ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ምርምራዎች እያንዳንዳቸው እስከ 18 የአሜሪካን ዶላር ወጭ ስለሚጠይቁ አብዛኞቹ የሕንድ ሆስፒታሎች የምርመራ መሠረተ ልማቱ የላቸውም::

በታላቋ የሕንድ ከተማ ሞምባይ እንኳ ሦስት የግል ሆስፒታሎች ብቻ ናቸው ኤች አይ ቪን መመርመር የሚችሉት:: ትልልቅ የመንግሥት ሆስፒታሎችም እነዚህን የምርመራ መሠረተ ልማቶችን እንዳላሟሉ ሚስተር ኮታሪ አስረድተዋል::

የዓለማችን ረዥሙና ጥልቁ የባቡር መተላለፊያ ዋሻ ወደ ሁለት አስርት ዓመታት የሚጠጋ ጊዜ ፈጅቶ ተጠናቀቀ::

አጠቃላይ 75 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ባለሁለት መተላለፊያ ዋሻ እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት ያላቸው ባቡሮችን በስዌዘርላንድ አልፕስ ተራሮች ሥር አሾልኮ የሰሜንና ደቡብ አውሮፓ ሀገራትን ያስተሳስራል:: ስዌዘርላንድ “ዋሻው የአውሮፓን የደረቅ ጭነት ማጓጓዝ ሂደት ሥር ነቀል ለውጥ ያመጣ ነው፤ ከዚህ ቀደም በሚሊዮኖች የጭነት መኪናዎች ረዥም ርቀት ይጓጓዙ የነበሩ ጭነቶች ከእንግዲህ በባቡር በቀላሉ ይንቀሳቀሳሉ” ስትል አሞካሽታዋለች::

ዋሻው እስከዛሬ በዓለም አንደኛ የነበረውን የጃፓኑን ሴይካን ዋሻ (53.9 ኪሎ ሜትር ርዝመት) በመብለጥ የዓለማችን ረዥም መሆኑ ተረጋግጧል:: ፈረንሳይና እንግሊዝን የሚያገናኘው የቻነል ዋሻም (50.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት) ወደ ሦስተኛ ደረጃነት ተገፍቷል::

ከ 12 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር የፈጀው ፕሮጀክት ከመጀመሩ በፊት በስዊዝ ዜጎች “ይሠራ? ወይስ አይሠራ?” የሚል ሕዝበ ውሳኔ ድምፅ እ.ኤ.አ በ1992 ተሰጥቶበታል:: በውጤቱም በበርካታ አካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪዎች ዘንድ ከፍተና ድጋፍ አግኝቶ ነበር::

አሁን ግንባታው የተጠናቀቀው ዋሻ እስከ ሁለት ነጥብ ሦስት ኪሎ ሜትር ጥልቀት በተራሮች ሥር እና እስከ 46 ዲግሪ መጠነ ሙቀት በሚደርስ አለት ውስጥ ያልፋል:: መሐንዲሶቹ ወደ 73 የሚደርሱ የተለያዩ ባሕርያት ያላቸው አለቶችን ቆፍረዋል፤ ፈርክሰዋል፤ አንዳንዶቹ ልክ እንደ “ግራናይት” ጠንካሮች እንደነበሩም መስክረዋል:: እንደ ስኳር በቀላሉ የሚፈጩ አለቶችም አጋጥመዋቸዋል:: በቁፋሮው 28 ሚሊዮን ቶን የሚመዝኑ አለቶች የወጡ ሲሆን አብዛኞቹ ለዋሻው ግንባታ አርማታ ሙሊት አገልግለዋል::

አሁን የተጠናቀቀውና ለአገልግሎት ክፍት የሆነው ዋሻ የኔዘርላንዷን ሮተርዳም እና የጣሊያኗን ጀኖዓ ከተሞች ያስተሳስራል:: በቀጣይ የአውሮፓውያኑ ታሕሳስ ዋሻው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ጉዞዎች ሁሉ ወጣ ገባና ጠመዝማዛ መሆናቸው ቀርቶ ቀጥ ያለ ዋሻ ይሆናል:: 260 የደረቅ ጭነት ማመላለሻ እና 65 የመንገደኞች መመላለሻ ባቡሮችም በውስጡ ይወነጨፉበታል:: የዋሻ ውስጥ ጉዞው በመንገደኞች ባቡር ቢበዛ 17 ደቂቃ ብቻ ይወስዳል::

ዋሻው የተገነባው በተጨማሪ እሴት ታክስና በነዳጅ ላይ ከሚጣል ግብር በሚሰበሰብ ክፍያ ታሳቢነት በአስርት ዓመታት ሊመለስ ውል ተገብቶ በተወሰደ ብድር ነው:: ዋሻው ስዌዘርላንድን ሸቀጥንና ሕዝብን ለማጓጓዝ ብቻ ሳይሆን ለቱሪስት መዳረሻነትም ስለሚያስመርጣት ብድሩን መመለስ አይከብዳትም ብሎ ቢቢሲ ዘግቧል::

የዓለማችን ረዥሙ የባቡር ዋሻ ተከፈተ

Page 26: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 26

“የወረቀት ‘ምሁራን’ ”... ከገፅ 5 የዞረ

የመመረቂያ ጽሑፉን ሠርቆ ሠራሁ የሚል ዜጋ ከሙስና ነፃ ሆኖ አገርና ወገን ሊያገለግል አይችልም::

ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር የቆየዓለም ደሴ - መምህርና ተመራማሪ

ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በድሕረ-ምረቃ ትምህርት የሚሰጡት ትምህርቶች ተማሪዎቹን ለምርምር የሚያበቁ አለመሆን ነው:: ለምሳሌ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድሕረ-ምረቃ ትምህርት ሁለት ዓመት ይፈጃል፤ አንደኛው ዓመት ሙሉ በሙሉ የጽንሰ-ሀሳብ ትምህርት ሲሆን ሁለተኛው ዓመት ደግሞ የምርምር ነው:: ነገር ግን በመጀመሪያው ዓመት ተማሪዎቹ የሚወስዷቸው የቀለም ትምህርቶችና በሁለተኛው ዓመት የሚሠሯቸው ጥናቶች መስተጋብር በእጅጉ የላላ ነው:: ተማሪዎቹ ትርጉም ባለው ሁኔታ በቀለም ትምህርቱ ለጥናቱ አይዘጋጁም::

ሦስተኛ ምክንያት ሆኖ ያገኘነው ደግሞ ተማሪዎቹ ራሳቸው ለትምህርታቸው ንቁ ተሳታፊ አይደሉም:: ትምህርቱን እንደ ሌላ አማራጭ እንጅ እንደዋና ነገር አድርገው አይወስዱም፤ በዚህም የተነሳ ሰፊ ጊዜያቸውን ለጥናትና ምርምር አይመድቡም::

አማካሪዎችም (Advisors) ለተማሪዎቹ የጥናት ጥራት መጓደል አስተዋፅዖ እንዳላቸው በጥናታችን አረጋግጠናል:: አማካሪዎች በትክክል ለተማሪዎች ጊዜ ያለመስጠት፣ የጥናት ንድፎችን (proposals) በሚገባ አለማዬት፣ የመረጃ አሰባሰብ ዘዴና ሂደቱን አለመከታተል፣ በበቂ ሁኔታ አለመደገፍና ሰፊ ጊዜ አለመስጠት ለጥራቱ መጓደል አስተዋፅዖ እያደረጉ ነው::

ሌላው ምክንያት ደግሞ አብዛኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ከሁለተኛ ዲግሪ ይልቅ ለሦስተኛ ዲግሪ መርሀ ግብሮች ትኩረት መስጠታቸው ነው:: የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራምን ቀለል አድርጎ የመመልከት ሁኔታ በዩኒቨርሲቲዎቹ ይስተዋላል:: የተማሪዎቹ የጥናትና ምርምር የስነ-ምግባር መርሆዎችን (Research ethics) አለመከተልም ሌላው ለጥራት መጓደል ምክንያት እንደሆነ አስተውለናል::

ለእነዚህ የጥራት መጓደሎች ማሳያ የሆኑ ነገሮች ተገኝተዋል?

አዎ! በርካታ ማሳያዎች አሉ እንጅ! የሌሎችን ሥራዎች መኮረጅና ተገቢውን ዕውቅና አለመስጠት፣ ከድረገፅ የሌላ አገር ጥናትን ገልብጦ መስጠት፣ የሚሉት እኮ ማሳያ ናቸው:: የውሸት ዘገባ (ሪፖርት) መጻፍ፣ መረጃ ሳይሰበስቡ ሰብስበናል ማለት፣ መረጃ የሚሰበስቡበትን ዘዴ መጠይቅ ወይም ቃለ-ምልልስ ትክክለኛነት (validity) ሳይፈትሹ ፈትሸናል ማለት፣ የውሸት መረጃ መፍጠር፣ … ሁሉ የጥናትን ትክክለኛነት የሚያዛቡ ግን በድሕረ-ምረቃ ተማሪዎች ጥናት ወቅት እየተፈፀሙ ያሉ የጥናት ጥራት መጓደል ማሳያዎች ናቸው::

የድሕረ-ምረቃ ትምህርቶች በአብዛኛው

በመንግሥት ተቋማት ድጋፍ የሚደረግላቸው ተማሪዎች የሚከታተሏቸው መሆናቸው ለጥራት መጓደሉ አስተዋፅዖ ያደርግ ይሆን?

እንዳልከው አስተዋፅዖ የማድረግ ዕድሉ ሰፊ ነው:: በእኔ እምነት አንዱ አሉታዊ ተፅዕኖ እያመጣ ያለው ትምህርትን የምንማረው ለማዎቅ ሳይሆን የጥቅም ትርፍ ለማግኜት መሆኑ ነው:: በእርግጥ የተማረ ሰው ባለው ዕውቀትና ክሕሎት ልክ ዕያደገ መሄድ አለበት፤ ነገር ግን የሚማረው ዕድገትን በማሰብና በአቋራጭ ለማደግ በሚል መሆን የለበትም::

ብዙ ጊዜ የመንግሥት ተቋማት ከሠራተኞቻቸው ለተወሰኑት የትምህርት ዕድል ይሰጣሉ፤ ተገቢም ነው:: ነገር ግን “ተማሪዎቹ ዕድሉን ስላገኙ ይማሩ? ወይም ፍላጎቱ ኑሯቸው ዕድሉን ያግኙ?” ማረጋገጫ የለም:: ለትምህርት ትክክለኛ ግምት አለመኖርም አንዱ ምክንያት እንደሚሆን ግን አምናለሁ:: ብዙ ጊዜ ለመጀመሪያ ዲግሪ፣ ለሁለተኛ ዲግሪ፣ ለሦስተኛ ዲግሪ የምንሰጠው ግምት ከዕውቀቱ ይልቅ ለወረቀቱ ያጋደለ ነው:: ስለዚህ የትምህርት

ዕድሎች በመንግሥት በኩል ሲመጡ ወረቀቱን ብቻ በማሰብ ለመማር መሯሯጥና ዕድሉን ካገኙ አይቀር ደግሞ ለመመረቅ የጥናት ሥራዎችን ከመስረቅ እስከ መግዛት ሊኬድ እንደሚችል መገመት ይቻላል::

በእርግጥ መንግሥት ከሚሰጠው ዕድል በተጨማሪ በግላቸው እየከፈሉ የሚማሩ ሰዎችም በዝተዋል:: ነገር ግን በግላቸው የሚማሩትም ቀደም ሲል እንደጠቀስኩት በቅድመ ምረቃ ትምህርታቸው ጥሩ አቅም ኖሯቸው ለበለጠ ዕውቀት ይማሩ ወይም የተሻለ የመቀጠር ዕድላቸውን በወረቀታቸው ለማሳደግ ይማሩ ማረጋገጫ የለም:: ነገር ግን እኛ ባደረግነው ጥናት ያረጋገጥነው ለጥናትና ምርምር ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ መጓደል አስተዋፅዖ እያደረገ ያለው የተማሪዎች ብቃት አናሳ መሆን ነው::

ጥናትና ምርምር መሥራት የሚጠይቀው ዕውቀት ምንድን ነው?

ጥናትና ምርምር ለመሥራት አጠቃላይ የጥናትና ምርምር መሠረታዊ ዕውቀቶች ያስፈልጋሉ:: ቀዳሚው ነገር አጠቃላይ የጥናትና ምርምር ዕውቀትና ክሕሎት ነው:: ጥናትና ምርምር የራሱ የሆነ ዑደት አለው:: ሲጀመር አንስቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ መታለፍ ያለባቸው ቅደም ተከተሎች አሉ፤ እነዚያን ሂደቶች በሚገባ መገንዘብ፣ እንዴት ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ፣ ከየት ወደ የት መሄድ እንዳለበት፣ … ማዎቅ ያስፈልጋል:: ነገር ግን በብዙዎቹ ተማሪዎች ላይ ይህ ነገር የለም::

በሁለተኛ ደረጃ ጊዜን በአግባቡ መጠቀም መቻል፣ ራስንና አካባቢን የመረዳትና የመግለፅ ክሕሎት፣ ራስን በራስ የማስተማር ክሕሎት ሁሉ ያስፈልጋሉ:: ምክንያቱም የድሕረ-ምረቃ ትምህርት በአብዛኛው በመምህር ወይም በአማካሪ የሚመራ ሳይሆን በራስ የሚመራ ነውና:: ስለሆነም እነዚህ ክሕሎቶች ከድሕረ-ምረቃ ተማሪዎች ይጠበቃሉ፤ ግን አብዛኞቹ የሏቸውም::

ከድሕረ-ምረቃ ተማሪዎች የሚጠበቁ ግላዊ

ብቃቶች (personal qualities) አሉ፤ ለአብነት ትጋት፣ ተነሳሽነት፣ ትኩረት መስጠት፣ ራስን ለዓላማ ተገዥ ማድረግ፣…:: እነዚህም የሉም፤ እንዲያውም በአብዛኛው ትምህርት ገበታቸው ላይ አይገኙም:: አንዳንድ ተማሪዎችን የሚፈትነው ደግሞ በሚማሩበት የትምህርት መስክ ዘርፍ ያለውን የጥናትና ምርምር ልምድና ሁኔታ ያለመረዳት ችግር ነው::

የዩኒቨርሲቲዎች የእርስ በእርስ ግንኙነትና የመረጃ ልውውጥ ደካማ መሆን ለጥናት መሠራረቁ በር አልከፈተም?

በሚገባ እንጅ! አንድ ዩኒቨርሲቲ ላይ የተሠራ የጥናትና ምርምር ሥራ እኮ የግለሰቡ ሥም ብቻ ተቀይሮ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ላይ ይቀርባል፤ ብዙ ፈታኞች ይህን ከዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ ተዘዋውረው ሲፈትኑ ያገኙትል:: ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መቀሌ፣ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ባሕር ዳር፣ … ጥናቶች ይንከራተታሉ:: አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ላይ ያማክሩት የነበረ ተማሪ ጥናት ሌላ ዩኒቨርሲቲ ላይ ሌላ ተማሪ ሊፈትኑ ሲሄዱ ሥሙን ብቻ ቀይሮ ሲያቀርበው ያገኛሉ::

በዩኒቨርሲቲዎች መካከል ያለው ግንኙነት መላላት፣ የመረጃ ልውውጥ አለመኖር፣ የሚሠሩት ጥናትና ምርምር ውጤቶች በዩኒቨርሲቲዎቹ ድረገፆች ያለመለቀቅና በቀላሉ ለአማካሪዎች ተደራሽ ያለመሆን ሁሉ ለመመረቂያ ጥናቶች መሠረቅ በር እየከፈቱ ያሉ ጉዳዮች ናቸው::

ጥናቶች ከመመሪቂያ ማሟያነት አልፈው ችግር ፈች አለመሆናቸውም በሚሰረቁበት ጊዜ እንዳይታወቁ እንደሚያደርግ ይገመታል፤ ትክክል ነው?

በሚገባ እንጅ! ብዙ ጊዜ በኛ በድህረ-ምረቃ ትምህርት ተመራቂዎች የሚሠሩ ጥናቶች ለመመረቂያ ማሟያነት ብቻ እንዲውሉ አይመከርም፤ ነገር ግን አብዛኞቹ ተማሪዎች የሚሠሯቸው ጥናቶች ከዚያ

ሲያልፉ አይታዩም:: ወደ ተግባር ቢወርዱ ኖሮ ግኝቶቹ ወደ ሕብረተሰብ ዕውቀትነት ይሸጋገራሉ፤ ከብዙዎች ዘንድም ይደርሳሉ:: ሁሉም ሰው የሚያውቀውን ነገር ደግሞ “የእኔ አዲስ ግኝት ነው” ብሎ ለማቅረብ የሚደፍር አይኖርም:: እንዲያውም ከመፍትሔዎች ሁሉ የተሻለው ዘዴ ይህ ሳይሆን አይቀርም፤ ጥናቶቹን ተግባር ላይ ማዋል::

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጅምሩ አለ:: የምርምር ውጤቶችን በድረገፁ የመልቀቅ፣ አደራጅቶ ለፖሊሲ አውጭዎች እንዲደርሱ የማድረግ ሥራዎች አሉ:: ግን አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ በጣም አስደንጋጭ ነው፤ በዚህ ብቻ መፍታት የሚቻል አይመስልም::

በጥናታችሁ ያስቀመጣችሁት የመፍትሔ ሐሳብ ምንድን ነው?

ጥናቱ ያተኮረው ችግሩን በጥልቀት ማጥናት ላይ ነው፤ የመፍትሔ ሐሳቦቹ ደግሞ ሰፊ ጥናትና የበርካታ ባለድርሻ አካላትን ሁሉ ጥረት የሚጠይቁ ናቸው:: ይህ እንዳለ ሆኖ ግን እንደመፍትሔ ብዙ ነገሮችን ማንሳት ይቻላል:: ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የሚማሯቸው ጽንሰ-ሐሳቦችና ሚሠሯቸው ጥናቶች የተያያዙ መሆን አለባቸው የሚለው አንዱ የመፍትሔ ሐሳብ ነው:: የሚሰጡት የጽንሰ-ሐሳብ ትምህርቶችም በሚገባ ተማሪዎቹን የሚያዘጋጁ መሆን አለባቸው::

የአማካሪዎች ክትትልና እገዛም የተጠናከረ መሆን ይኖርበታል:: አማካሪዎቹ በተዳጋጋሚ ከተማሪዎቹ ጋር የሚገናኙና በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ የሚነጋገሩ ከሆነ ተማሪዎቹ የሌሎችን ጥናት ለመገልበጥ በራስ መተማመን ያንሳቸዋል፤ በተጨማሪም በራሳቸው ለመሥራት ተነሳሽነታቸው ይጨምራል:: የጥናት አሠራር መመሪያ ማውጣት፣ ተማሪዎቹ ጥናት ሲሠሩ መከተል ያለባቸውንና የሌለባቸውን አካሄዶች እንደ አሠራር ዘርግቶ ለተማሪዎች ማሳወቅ፣ መከታተል ያስፈልጋል::

የዩኒቨርሲቲዎችን የእርስ በእርስ ግንኙነት መጨመር፤ የተማሪዎችን የጥናት ውጤቶች ለየዩኒቨርሲቲዎቹ ማሕበረሰቦች የሚደርሱበትንና ዕውቅና የሚፈጠርበትን ሁኔታ ማመቻቸትም ከመፍትሔዎች አንዱ ነው:: በተለይ እኛ እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጀመርነው የኮምፒዩተር ፕሮግራም (sofeware) አለ:: የኮምፒዩተር ፕሮግራሙ የተመሳስሎ አመልካች (similarity index) የሚያሳይ ነው:: በዚህ የኮምፒዩተር ፕሮግራም መሠረት የጥናት ወረቀቱን ስንፈትሸው ከ20 በመቶ በላይ ከሌላ ጥናት ጋር ተመሳሳይነት ካለው ውድቅ ይደረጋል::

ወደ ድሕረ-ምረቃ የሚገቡ ተማሪዎችን ጥራት ማስጠበቅ አንድ መፍትሔ አይሆንም?

በጣም ጥሩ መፍትሔ ይሆናል፤ ግን ሁለንተናዊ የሆነ የመዋቅር ለውጥ ይጠይቃል:: ተማሪዎቹ ለድሕረ-ምረቃ የበቁበትን የትምህርት ሒደት ሁሉ መቃኘት የሚጠይቅ ነው:: ከአንደኛ ደረጃ፣ ሁለተኛ ደረጃ፣ መሠናዶ፣ የቅድመ ምረቃ ምርሀ-ግብሮች አካሄድ ጋር ሁሉ የሚገናኝ ነው:: እነዚህን ሂደቶች ሁሉ በጥራት ካለፉ ነው ወደ ድሕረ-ምረቃ ትምህርት የተሻሉ ተማሪዎች ሊመጡ የሚችሉት::

እንደ አጠቃላይ ግን አሁን ያለው ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ነው:: የመመረቂያ ጽሑፎች በእጅጉ ከደረጃ በታች ናቸው:: ችግሩ የዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ሳይሆን የአገርም ነው፤ የመመረቂያ ጽሑፉን ሠርቆ ሠራሁ የሚል ዜጋ ከሙስና ነፃ ሆኖ አገርና ወገን ሊያገለግል አይችልም:: ተዓማኒና ቅን የሕዝብ አገልጋይ የመሆን ዕድሉ በጣም የጠበበ ነው፤ በፍጥነት ዩኒቨርሲቲዎች የቁጥጥር ሥርዓታቸውን አሻሽለው ቀጣዩን ጊዜ ከድንቁርና ሊታደጉት ይገባል:: ጥናትና ምርምር የማይሠሩ የወረቀት “ምሁራን” እየተፈለፈሉ ነው::

ለነበረን ቆይታ አመሠግናለሁ!

እኔም በዚሁ አጋጣሚ የጥናት ውጤቴን ለሕዝብ እንዳደርስ ስላደረጋችሁኝ አመሠግናለሁ!

Page 27: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 27በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. እጽዋት/እንስሳት

ወደ ገጽ 36 ዞሯል

አባትሁን ዘገየ

ሳይንሳዊ መጠሪያው አርካሴ ይሰኛል:: “የሀሩሩ ገነት!” ሲሉ የሚያንቆለጳጵሱትም አሉ:: በተለይ በበረሀማ አካባቢ ሲገኝ ከሚፈጥረው ልዩ ሀሴት አንጻር ይህ የቁልምጫ ስሙ ቢያንሰው እንጂ እንደማይበዛበት ይነገርለታል::

“የት የት ይገኛል?” ብለን ከጠየቅን ደግሞ ከበረሀ እስከ ዝናብ ጠገብ አካባቢዎች በመላው ዓለማችን በስፋት ከሚታወቁ የእፅዋት ዘሮች አንዱ ነው:: ስለምን ላወጋችሁ እንደፈለግሁ የገመታችሁ ይመስለኛል፤ ከሆነ መልካም ካልሆነም የዛሬው ጽሁፌ በዘንባባ ላይ የሚያጠነጥን መሆኑን ትረዱልኝ ዘንድ ባክብሮት እጠይቃለሁ::

የሀሩሩ ገነት ወይም ዘንባባ ለመጀመሪያ ጊዜ በምድራችን መኖሩ ከተረጋገጠ 80 ሚሊዮን ዓመታት እንዳስቆጠረ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊትም ሜሶፖታሚያን የሀሩሩን ገነት መትከልና ማሳደግ እንደጀመሩ ይታመናል::

በዓለም ላይ ወደ 2 ሺህ 600 የዘንባባ ዝርያዎች እንዳሉም ይገመታል:: የዝርያዎቹን መገኛ ቦታዎች ዘርዘር አድርገን እስኪ እንይ፤

በዓለማችን ከሚገኙት የዘንባባ ዝርያዎች ከሁለት ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት ጥቅጥቅ ባሉ የሀሩር ደኖች ውስጥ ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል:: ጥቂቶቹ ደግሞ ጐርፍ በሚያጠቃቸው የተራቆቱ አካባቢዎች ይገኛሉ:: ከባህር ወለል በላይ እስከ አንድ ሺህ ሜትር ከፍታ ባላቸው ተራሮችም እንደማይታጡ ይነገርላቸዋል:: ሳር እንዲሁም ቁጥቋጦ በሚበዛባቸው ስፍራዎችም የተለያዩ የዘንባባ ዝርያዎችን ማየት አይገድም:: የዘንባባ ተክሎች የአካባቢ ተፅዕኖን መቋቋም የሚችሉ በመሆናቸውም በጣም አሲዳማ በሆነ አፈር ላይ ሳይቀር ይገኛሉ::

መገኛቸውን በአገር ደረጃ የተመለከትን

ሀሩሩ“ገነት”እንደሆነ ደግሞ ማዳጋስካር በርካታ አገር በቀል የዘንባባ ዝርያዎችን በመያዝ የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዛ እናገኛታለን:: ኮሎምቢያ ደግሞ በርካታ የዘንባባ ዝርያዎችን በመያዝ ከዓለማችን አገሮች ተወዳዳሪ እንዳልተገኘላት መረጃዎች ይጠቁማሉ:: የሀሩሩን ገነት በአረብ ባህረ ሰላጤ፣ በመላው አፍሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ፣ ደቡብና ደቡብ ምሥራቅ ኤዥያ፣ሜክሲኮ… እናገኛለን::

የዘንባባ ዝርያዎች እንደሚኖሩበት አካባቢ በመጠንም በጣም የተለያዩ ሆነው እናገኛቸዋለን:: በቁጥቋጦነት ደረጃ የሚታ ወቀው ድንኩ የዘንባባ ዛፍ ቻሜሮፕስ ሂዩሚሊስ በመባል ይታወቃል:: ይህ ዝርያ በደቡባዊ ፈረንሣይ ይገኛል::

ዋክስ ዘንባባ ደግሞ እስከ 70 ሜትር በሚደርሰው ቁመቱ ከሁሉም የዘንባባ ዝርያዎች ተወዳዳሪ እንዳልተገኘለት ተመስክሮለታል::

ኮኮ ደ መር የተባለው ዝርያ ከ የ ት ኛ ው ም የዘንባባ ዛፍ ዝርያ የሚበልጥ ግዙፍ ዘር የታደለ በመሆኑ ይታወቃል:: ኮኮ ከ30 እስከ 50 ሴንቲ ሜትር ዲያሜትር የሚደርስ ስፋትና ከ15 እስከ 30 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ዘሮች አሉት::

ራፊያ የተባለው የዘንባባ አይነት ደግሞ እስከ 25 ሜትር ርዝመትና ሶስት ሜትር ስፋት ባለው ቅጠል ግርማ ሞገስን ተላብሶ ይታያል::

ዘ ን ባ ባ ን በቅጠሎቹ ቅርጽም በሁለት ከፍሎ

ማየት ይቻላል፤የማራገቢያ እና የላባ ቅርጽ ያላቸው በሚል:: የማራገቢያ ቅርጽን ተላብሰው የሚገኙ የዘንባባ ቅጠሎች በግንዱ መጨረሻ ላይ እጅብ ብለው የሚገኙ ሲሆኑ የላባ ቅርጽ ያላቸው ቅጠሎች ደግሞ እንደ ላባ በግንዱ የትኛውም ክፍል በቅለው ይታያሉ::

በርካታዎቹ የዘንባባ ዛፎች ቀላ ያሉ እና ግንዶቻቸው ቅርንጫፍ አልባ ናቸው:: ነገር ግን፣ አልፎ አልፎ ግንዶቻቸው በርካታ ቅርንጫፎች ያሏቸው እንደ ራታን ያሉ የዘንባባ ዝርያዎችም ይገኛሉ:: እነዚህ የዘንባባ ዝርያዎች ዓመቱን ሙሉ በአረንጓዴ ቅጠሎች የተዋቡ ናቸው:: የቅጠላቸው ቅርጽም ላባ መሰል ወይም ግማሽ ክብ ነው:: ቅጠሎቹ ከታች የቱቦ ቅርፅ ይዘው ይስተዋላሉ:: ዕድሜ እየጨመሩ ሲሄዱም እየተዘረጉና እየተበተኑ ቅርጻቸውን ይቀይራሉ::

የ ዘ ን ባ ባ ዛፎች በርከት ያሉ አበባዎች አሏቸው:: የአበባዎቹ መገኛ ቅርንጫፎቻቸውም የተለዩ ናቸው:: አ በ ባ ዎ ቹ ባመዛኙ ጥቃቅን ሲሆኑ የኮከብ ቅርፅ አላቸው:: ብዙውን ጊዜም ቀለማቸው ነጭ ሆኖ እናገኛቸዋለን:: ፍ ሬ ያ ቸ ው ም ባመዛኙ አንድ ዘር ይኖረዋል:: አንዳንድ ዝርያዎች ደግሞ ሁለትና ከዚያ በላይ ዘሮች ሊኖሯቸው ይችላሉ::

ኮሪፋ በሚል ስያሜ የሚታወቀውን የዘንባባ ዝርያ ደግሞ በአበባ ብዛት

የሚወዳደረው የለም:: በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ጥቃቅን አበባዎች የተንቆጠቆጠ ነው:: ይህ ዝርያ እስከ ሰባት ነጥብ አምስት ሜትር የሚረዝሙ አበባዎች እንዳሉትም መረጃዎች ያመለክታሉ::

ዘንባባን በአበቃቀሉ በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፤ ተበታትኖ እንዲሁም እጅብ ብሎ የሚገኝ በሚል:: እጅብ ብሎ ይገኛል ሲባል በአንድ አካባቢ ብቻ እንዳልሆነ፣ ይልቁንም እዚህም እዚያም ሰብሰብ ብሎ እንደሚገኝ ማጤን ያሻል::

ዘንባባ በሚሰጠው ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ በሰው ልጅ የዕድገትና ስልጣኔ ታሪክ ጉልህ ስፍራ ይዞ ይገኛል:: በዚህም መሰረት የሰው ልጅ የዘንባባ ተክሎችን መጠቀም የጀመረበት ጊዜ ከጥንታዊ ስልጣኔ መስፋፋት ሊቀድም እንደሚችል ይገመታል::

የሰው ዘር ከዘንባባ ጋር ባለው ጥብቅ ቁርኝት የተነሳ ለምግብነትም ሆነ ለመጠጥነት የሚጠቀምባቸው በርካታ ምርቶች የዘንባባ ውጤቶች እንደሆኑ ይታመናል:: በዚህም መሰረት ዘንባባ በስፋት ከሚታወቀው የዘንባባ ለውዝ እና ተምር በተጨማሪ የተለያዩ ምግቦችን ለማምረት ይውላል:: የዘንባባ ዘይት፣ የዘንባባ ወይን፣ በተለያዩ የዓለማችን አካባቢዎች ለምግብነትና ለመጠጥነት ይውላሉ:: የዘንባባ ዘይት ከመዋቢያነቱ እስከ ምግብነቱ ድረስ በዕለት ከዕለት ህይወት ያገለግላል::

የዘንባባ ዛፎች ግቢዎችን፣ መናፈሻዎችን፣ መንገዶችን፣ የባህር ዳርቻዎችን… ለማስዋብም ይጠቅማሉ:: በተለይ ቀደም ባሉት ዓመታት የዘንባባ ዛፎች የድል፣ የሰላም… ተምሳሌቶች ተደርገው ይወሰዱ ነበር:: በመካከለኛው ምሥራቅ በመፅሐፍ ቅዱስ ከ30 ጊዜ በለይ እንዲሁም በቁራን 22 ጊዜ ተጠቅሶ ይገኛል፤ ዘንባባ ወይም የሀሩሩ ገነት::

የዘንባባ ስፖንጅማ ግንድ ጦርነት ጊዜ የሚተኮሱ ጥይቶችን መክቶ በማስቀረት ረገድ ጥቅም ላይ እንደዋለ ተመዝግቦ ይገኛል::

ዘንባባዎች አገራችንን ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አገራት ምንጣፍ፣ መጥረጊያ፣ ብሩሽ፣ ዘንቢል፣ ባርኔጣ፣ ፍራሽ፣ ገመድ… ለማምረት ይጠቅማሉ:: በጥቅሉ ሲታይ ከአንድ የዘንባባ ዛፍ ጥቅም ላይ የማይውል ክፍል እንደሌለ ይነገራል::

Page 28: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 28

ከገፅ 3 የዞረ

ከገፅ 9 የዞረ

ትኩረት - ትኩረት...

ውሃን እንደ...

የፊታውራሪ ታደሰ ጌታ ብቻ አይነ ስውራን ተማሪዎች

አንድ ጊዜ ለሚያመርቱት የእህል ሰብል ዝግጅት ግን አለነበረም:: በዘመናቸው ሲመኙትና ሲጓጉለት ለነበረው የመስኖ ልማት ለመጠቀም አስበው ነው:: እናም ከሁለት ሄክታር መሬታቸው ላይ ቀነስው አረሱና መደብ ሰርተው ሽንኩርት ተከሉ::

በ1995 ዓ.ም ቆፍረው በክረምት ዝናብ ያቆሩትን ውሃ በባልዲ እየጠለቁ የተከሉትን ሽንኩርት በማጠጣት መንከባከብ ጀመሩ:: ጎን ለጎንም ሃያ እግር የማንጎ ችግኝ፣ ሃያ አምስት እግር አቦካዶ፣ አምስት እግር ብርቱካን፣ ስምንት እግር ሙዝ፣ ከአስር እግር በላይ የሞሪንጋ(ሽፈራው) ዛፍ አርባ ሶስት እግር ቡና እና ከመቶ ሃምሳ እግር በላይ ጌሾ ተክለውበት ቆዩ::

አራት ወር ባልሞላ ጊዜ ሽንኩርታቸው ደረሰላቸውና ከሰላሳ ኩንታል በላይ ማግኘት ቻሉ:: በዚህም ገና የመጀመሪያቸው የመስኖ ስራቸው ከሆነው የሽንኩርት ሽያጭ ከሦስት ሺህ ብር በላይ ማግኘት ቻሉ:: ቀሪው የ1996 ዓ.ም የሰብል ጊዜ ደግሞ መሬታቸውን አዘጋጁና በክረምት ዝናብ በመጠቀም በዓመት ሁለት ጊዜ ማምረት ቻሉ::

መጀመሪያ የቆፈሩት ጉድጓድ የዝናብ ውሃ አቁሮ ሽንኩርትና ቋሚ ተክሎችን እንዲያለሙ እገዛ ቢያደርግላቸውም በሰፊው ለማልማት ግን አላስቻላቸውም ነበር:: እናም አማራጭ አድርገው የወሰዱት ሌላ ተጨማሪ የውሃ ማቆሪያ ጉድጓድ መቆፈር ነበር:: ወዲያውም ሦስት ሜትር በሶስት ሜትር ስፋት ያለውና ሁለት ሜትር ተኩል ጥልቀት

ያለው ጉድጓድ በመቆፈር ጆዮሜምብሬን አልበሰው የክረመት ዝናብን መጠባበቅ ጀመሩ::

አርሶ አደር ውቤ በ1996 ዓ.ም ሁለት የውሃ

ማቆሪያ ጉድጓዶችን አዘጋጀተው በቀሪ ጊዜያቸው ደግሞ ለሰብል ምርት የሚሆን መሬታቸውን እያረሱ ቆዩ:: በክረምት ወራትም ሁለቱም ጉድጓዶች በዝናብ ውሃ ሞልተው ቁጭ አሉላቸው:: በጤፍ፣ በገብስና በሽምብራ የዘሩትን መሬት አጭደውና ወቅተው

እህላቸውን ካስገቡ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ለመስኖ ስራ ተዘጋጁ::

መሬታቸውን አርሰውና አለስለሰው መደብ በማዘጋጀት ከበፊቱ በተሻለ ሽንኩርት ተከሉበት:: በ1996 ዓ.ም ጀምረውት የነበረውን ቋሚ አትክልትም 20 እግር የነበረውን የማንጎ ችግኝ ወደ 50 አሳደጉት:: 25 እግር የነበረውንም አቦካዶም 50 አደረሱት፣ አምስት የነበረውን የብርቱካን ችግኝ 10 አደረጉት:: ስምንት እግር ሙዝ የነበረውንም 10 ጨምረው ወደ 18 ከፍ አደረጉ:: 60 እግር ቡና

ጨምረው ወደ 103 ከፍ አድርገው ተከሉበት:: የጌሾ ችግኞችንም ከ300 መቶ አደረሱና በሁለት ሰፋፊ ጉድጓዶች ያቆሩትን የዝናብ ውሃ በመጠቀም ቋሚ አትክልቶችንና ሽንኩርታቸውን ማልማት ቀጠሉ::

በ1997 ዓ.ም ከሽንኩርት ብቻ ከ20 ሺህ ብር

በላይ ማግኘት ቻሉ:: አርሶ አደር ውቤ ያቆሩትን ውሃ በጀሪካን እየጠለቁ ቋሚ አትክልቶችንና የሽንኩርት ልማታቸውን በማጠጣት ለሁለት ዓመት ያህል ቢቆዩም በዛው አልገፉበትም:: ጉድጓዶች አጠገብ የእግር ፔዳል በመግዛት በዚያ እየወዘወዙ በማውጣት በኘላስቲክ ቱቦ ማጠጣት ጀመሩ:: አርሶ አደሩ በአሁኑ ወቅት ሦስት ሰፋፊ የውሃ ማቆሪያ ጉድጓዶችን አዘጋጅተው ሽንኩርት በስፋት እያለሙ ይገኛሉ::

በ2007 ዓ.ም ብቻ ከ70,000 ሺህ ብር በላይ ሽንኩርት ሽጠው ማግኘት እንደቻሉ ይናገራሉ:: በዚህ ዓመትም ከ10 ሺህ ብር በላይ ለማግኘት እንደሚችሉ በማሰብ አራት ጥማድ ሽንኩርት ለመትከል በዝግጅት ላይ ናቸው:: ከቋሚ አትክልቶች ደግሞ “በየጊዜው ጌሾ፣ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ሎሚ… በመሸጥ በዓመት እስከ 40,000 ሺህ ብር ድረስ አገኛለሁ” ይላሉ::

የበሌ ስላሴ ቀበሌ የሰብል ልማት ባለሙያ የሆኑት አቶ ተሾመ ቡታ አርሶ አደር ውቤ ታታሪና ትጉህ ሰራተኛ መሆናቸውን ገልጾ ሌሎች አርሶ አደሮችም እሳቸውን በማየት ጉድጓድ በመቆፈርና ውሃ በማቆር በመስኖ ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ ብሎናል:: በቀበሌው በአሁኑ ጊዜ 359 ሄክታር መሬት በመኸር ሽንኩርት እየለማ መሆኑንም ገልፆልናል::

መፅሃፍ በሌለበት፣ በፍጥነት ትምህርት ተቀላቅለው ለመማር መቸገራቸውን ተማሪ ደረጀ ተስፋየ በምሬት ገልፆልናል::

ሌላው የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ኢዮብ ወሰኔ የስድተኛ ክፍል ተማሪ እያለ አንዳንድ እጥረቶች ቢኖሩም የእንግሊዝኛ፣ የሂሳብ፣ የህብረተሰብ፣ የሥነ

ዜጋ መፅሃፍት ተሟልቶላቸው እንደነበር በማስታወስ ትምህርቱን በደንብ መከታተል ችሎ እንደነበር ገለፀልኝ:: ሆኖም ግን አሁን ሰባተኛ ክፍል ሲሆን የመፀሃፍ እጥረት ስላጋጠመው ትምህርቱን በደንብ ለመከታተል አስቸጋሪ እንደሆነበት ይናገራል::

መንገድ ሲሄዱ የሚዳስሱበት ዱላ(ኬንት) ተሟልቶላቸዋል፣ የብሬል ችግርም የለባቸውም

ሆኖም ታች ክፍል ያሉ ማየት የተሳናቸው ተማሪዎች ብሬል፣ ስታይላስ (ፊደል መውጊያ)፣ ስላት(የመፃፊያ ወረቀት) እጥረቶች እንዳሉባቸው ተማሪ እዮብ ይናገራል::

ማየትና መስማት የተሳናቸውን ተማሪዎች በአንድ ላይ አድርጋ ስታስተምር ያገኘኋትን መምህርት ፅጌ ዝናቡን እንዴት አድርጋ ማስተማር እንደምትችል እና የምልክት ቋንቋም ሆነ መስማት የተሳናቸውን ፊደል በመለየት ያላትን ዕውቀትና የተሰጣትን ስልጠና በተመለከተ ጠየቅኳት:: ደብረ ብርሃን ተልካ ለ45 ቀናት መሰልጠኗን ነገረችኝ::

እናም ገብቶሽ ነው የምታሰተምሪው? አልኳት:: “መስማት የተሳናቸውን እቸግራለሁ:: ማየት የተሳናቸውን ግን መፅሃፉን እያነበብኩ ስለማስተማራቸው የእነሱ ይሻለኛል” ስትል መለሰች:: መምህርቷ ማየት የተሳናቸውን ለማስተማር ይቅለላት እንጅ ማየት የተሳናቸው የሚጠቀሙበትን ፊደል ግን በደንብ አታውቀውም:: የምታስተምራቸውም ማየት ለሚችሉ ተማሪዎች የተዘጋጀላቸውን መፅሃፍ ነው፡

እናም የአንድ ተማሪ ውጤት የሚለካው በፈተና ነው እና አይነ ስውራን የሚፅፉትን ማንበብ ካልቻልሽ እንዴት ነው ፈተና የምታወጪው? የምታሪሚላቸውስ? ሌላው ጥያቄየ ነበር:: “የአይነ ስውራን ፅሁፍ ማንበብ ስለማልችል በቃል እፈትናቸዋለሁ::” ስትል በአጭሩ መለሰች::

የፊታውራሪ ታደሰ ጌታ ብቻ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ወይዘሮ ስመኝ ካሳን ዕውቀቱ በደንብ በሌላቸው መምህራን ትምህርት ለምን ይሰጣል? ለተማሪዎች የመማሪያ መሣሪያዎች አለሟሟላት ችግሩ ምንድ ነው? የተለያየ ክፍል ደረጃ ያላቸውን ተማሪዎችስ በአንድ ላይ ማስተማሩ ለምን አስፈለገ? የሚል ጥያቄ አቅረብኩላቸው::

“መምህራኑ አጭር ስልጠና የወሰዱ በመሆናቸው ልክ ነው ገብቷቸው ያስታምራሉ ብሎ ማሰብ ይከብዳል:: ሆኖም ግን ነባርና ዕውቀት ያላት መምህር ታማ በመቅረቷ ተማሪዎች ዝም ብለው ከሚውሉ በሚል በጀማሪ መምህር እንዲሰጥ አድርገናል:: ተማሪዎች ተቀላቅለው የሚማሩትም ከመምህሯ መቅረት ጋር ተያይዞ ነው:: የመማሪያ መፅሃፍት እኛም ለሚመለከተው አካል ጥያቄ አቅረበን አልተፈታልንም:: ሆኖም ግን ከአራት ሺህ አምስት መቶ ብር በላይ በግላችን ወጪ አድርገናል” አሉኝ::

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የመረጃና ዕቅድ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ተስፋየ መንገሻ የተማሪዎችን የመማሪያ መፅሃፍት በተመለከተ በተደጋጋሚ ጥያቄ የቀረበ ቢሆንም ምላሽ ሊያገኙ እንዳልቻሉ ይናገራሉ:: ምክንያቱን ሲጠይቁ ደግሞ የልዩ ፍላጎት መማሪያ መሣሪያ አምራች ድርጅቶች አናሳ በመሆናቸው እንደሆነ መልስ ማግኝታቸውን ገለፁልኝ:: ወደ ፊት ግን ዕቅድ ተይዞ ለሁሉም ተማሪዎች በቁጥራቸው ሁሉንም የትምህርት አይነት ለማሳተም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል::

Page 29: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 29በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.

ከገፅ 18 የዞረ

የማስታወቂያ...

ያወጣው አዋጅ ቁጥር 759/2004 ለማታስወቂያ አስነጋሪዎች፣ ለማስታወቂያ ወኪሎችና ማስታዎቂያ ነጋሪዎች መብትና ግዴታዎችን እንዲሁም አሠራሮችን አስቀምጧል:: ከመገናኛ ብዙኃን ውጪ የሚተላለፉ ማስታወቂያዎችን በሚመለከት “ስለውጪ ማስታወቂያ” ብሎ በአዋጁ አንቀፅ 21 የሚከተለውን አስፍሯል:: “1/ ማንኛውም ሰው አግባብ ካለው የመንግሥት አካል ፈቃድ ሳያገኝና እንደ አግባብነቱ ባለቤቱ ወይም ባለይዞታው ሳይስማማ፡-

ሀ) በማንኛውም ሕንጻ፣ ግድግዳ፣ አጥር፣ የአውቶቡስ ፌርማታ፣ ምሰሶ፣ የቴሌኮም አገልግሎት መስጫ መሣሪያ ወይም ሌሎች መሰል ነገሮች ላይ፤

ለ) በማንኛውም መንገድ፣ አውራጎዳና፣ የባቡር ሀዲድ ወይም የሕዝብ መጓጓዣ ላይ፤ ወይም

ሐ) በማንኛውም የሕዝብ አገልግሎት በሚሰጥ ሥፍራ ላይ፤

የውጪ ማስታወቂያ መለጠፍ፣ መስቀል፣ መትከል ወይም በሌላ መንገድ ማስቀመጥ አይችልም::”

“2/ ማንኛውም የውጪ ማስታወቂያ ከመንገድ ምልክት ወይም አቅጣጫ ጠቋሚ ምልክት ጋር በሚመሳሰል፣ ዕይታን በሚጋርድ፣ የትራፊክ እንቅስቃሴን በሚገታ ወይም ደህንነቱን በሚቀንስ ወይም የአካባቢን ገጽታና ውበት በሚያበላሽ መልኩ መቀመጥ የለበትም::”

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ምክትል መምሪያ ኃላፊ አቶ በሰላም ይመኑ “የውጪ ማስታወቂያዎችን በሚመለከት በፌዴራል ደረጃ የሚያስፈፅመው አካል የብሮድካስት ባለስልጣን መሆኑ በአዋጅ ቢገለፅም ባለስልጣኑ በክልሎችና ከዚያ በታች ባሉት የመንግሥት መዋቅሮች ቅርንጫፍ የሌለው በመሆኑ የአዋጁን ተፈጻሚነት አስቸጋሪ አድርጎታል” ይላሉ::

የውጭ ማስታወቂያ አገልግሎትን ከአካባቢ ብክለት፣ ጽዳትና ውበት፣ እንዲሁም ከአካል ጉዳተኞች ጋር በተያያዘ ጉዳት እንዳያደርስ አድርጎ ለልማት ለማዋል በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በአነስተኛ ከተሞች ጭምር በባለቤትነት የሚሠራ አካል እንደሚያስፈልገው ያስረዱት ምክትል መምሪያ ኃላፊው “አዋጁ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትን በየደረጃው ያለ

በቀድሞው የቡድኑ ኃላፊ (ማናጀር)አዲስ ገሰሰ ተመርጠው ባንዱን የመሰረቱት የቡድኑ አባላት ቁጥር አስር ወጣት ሙዚቀኞች ነበሩ:: ቡድኑ በተለያዩ ጊዜያት ለህዝብ የለቀቃቸው ነጠላ ዜማዎች ይበልጥ ተወዳጅነትን አትርፈውለታል:: በተለይም ‘አይራቅ’ የተሰኘው የቡድኑ ነጠላ ዜማ የብዙ መገናኛ ብዙሃን ተመራጭ የዜማ ግብዣ እስከመሆንም ደርሷል:: የጃኖ የሙዚቃ ቡድን የመጀመሪያ አልበም ‘ኤርታሌ’ ይሰኛል:: በዚህ ስራ አስሩም የቡድኑ አባላት የተሳተፉ ሲሆን የአልበሙ መሰራት ዋና ዓላማ ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነትን ማግኘት ነበር:: ከዚህ አልበም ስራ በኋላ ግን የተወሰኑ አባላት ቡድኑን ለቅቀው ወጥተዋል:: እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የቡድኑ አባላት ስምንት ወጣቶች ናቸው:: ሚካኤል ሃይሉ ሊድጊታሪስትና የሙዚቃ ዳሬክተር ነው:: ይህ ወጣት የሙዚቃ ሰው አዲሱን የቴዲ አፍሮ “ጥቁር ሰው” አልበምና የሚካኤል በላይነህን “ናፍቆትና ፍቅር” አልበምን በማቀናበር ይታወቃል:: ሌላኛው ወጣት ኪሩቤል ተስፋዬ የቡድኑ ኪቦርዲስትና ባንድ ሊደር ነው:: ድራመሩ ዮሃንስ መኮንን፣ ቤዝ ጊታሪስቱ ዳን ኤል ነጋሽ፣ እንዲሁም ድምፃውያኑ ሔዋን ገብረወልድ፣ ዲበኩሉ ታፈሰ፣ ሃሌሉያ ተክለፃድቅና ሃይሉ አመርጋ (ሁሉም ዕድሜያቸው በ20ዎቹ የሚገኙ ናቸው) የጃኖ ባንድ አባላት ናቸው::

ከገፅ 17 የዞረ

ጃኖዎቹጃኖዎች ከመጀመሪያው የአልበም ስራቸው

“ኤርታሌ” በኋላ በአብዛኛው ወጣት የሙዚቃ አድማጭ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን ማትረፍ ችለዋል:: በተለይም የቡድኑ መለያ የሆነው ኢትዮ

ሮክ ስልት ተወዳጅነታቸውን አስመስክሮላቸዋል:: ጃኖዎች ለየት ከሚያደርጋቸው ጉዳይ አንዱ የመድረክ ስራቸውና አያያዛቸው ነው:: በአሁኑ ወቅት በሚሰሩበት ክለብ ኤች ቱ ኦ (H2o)

የሚያሳዩት ድንቅ የመድረክ ብቃት ከፍተኛ አድናቆት እንዲያገኙ አድርጓቸዋል::

ጃኖዎች ከዓመት በፊት “ስለብሬቲንግ ዘ ኘሬይድ ኦፍ ኢትዮጵያን ሙዚክ” በሚል ባህር ዳርን ጨምሮ በመላ ሃገሪቱ ትልልቅ ከተሞች ያቀረቡት የሙዚቃ ድግስ ከብዙ የሃገር ውስጥ አድናቂዎቻቸው ጋር አገናኝቷቸዋል:: ከዚህ

ባለፈም በመላው ዓለም በመዟዟር ባቀረቧቸው ዝግጅቶች ከትልልቅ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ሰዎች ጋር ለመገናኘት መንገድ ከፍቶላቸዋል::

ጃኖዎች በቅርቡ “ይነጋል” ከሚለው

አልበማቸው ነጥረው የወጡት ሁለት ዜማዎች የቡድኑን አቅም አስመስክረዋል:: ከተበታተነ የሙዚቃ አሰራር ወጥተው በአንድ የሙዚቃ ቡድን ስር የተሰባሰቡት እነዚህ ወጣት ሙዚቀኞች አሁን መንገዳቸውን በስኬት ማጀብ የጀመሩ ይመስላል:: ምንም እንኳን ከማናጀሩ አዲስ ገሰሰ መውጣት በኋላ የቡድኑ ህልውና አደጋ ላይ ቢመስልም

በጠንካራ መንፈስ ለሁለተኛ አልበም ስራ በቅተዋል:: ይህ ሁለተኛ አልበማቸው ቆየት ያሉ የሙዚቃ ስራዎችን

ከመዳሰሱ ባሻገር ጠንካራ ማህበራዊ ጉዳዮችን መምዘዝ የቻለ ነው::

በዚህ የሙዚቃ ቡድን ውስጥ እንደ ይለማ ገብረአብ ያሉ ተዋቂ የዜማና የግጥም ደራሲዎችም ተሳትፈውበታል::

ከባህላዊ የኢትዮጵያ ልብስ ጃኖ ስያሜውን የወሰደው ጃኖ ባንድ አሁን በኢትዮጵያ

የዘመናዊ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የራሱን አሻራ ከማሳረፍ ባለፈ የሃገሪቱን ሙዚቃ ወደ ዓለም መድረክ ይዞ የወጣ ባለ ራዕይ ባንድ ለመሆን በቅቷል::

መዋቅር በተወሰነ ደረጃ ኃላፊነት እንዳለበት ስለሚሰጥ ተግባሩን ለመፈፀም ከክልል ጀምሮ የሰው ኃይልና ባለሙያ ሊመደብለት ይገባል” ብለዋል::

አቶ በሰላም እንዳሉት የውጭ ማስታወቂያን መከታተል፣ መቆጣጠርና ስርዓት ማስያዝ የሚጠይቃቸው ክህሎቶችና የሙያ ዝግጅቶች አሉ:: “የድምፅ መጠንን እንቆጣጠር ብንል ‘የሚፈቀደው ምን ያህል መጠን ነው? ማስታወቂያ አስነጋሪዎችስ በተግባር የሚለቁት ድምፅ ምን ያህል ነው?’ የሚሉትን የሚመዝንና ማብራሪያ የሚሰጥ ባለሙያ ያስፈልገዋል:: በጽሑፍ የሚሰራጩ ማስታወቂያዎችንም ይዘት፣ የቋንቋ አጠቃቀምና የመሳሰሉትን የሚቆጣጠር

ባለሙያም መዋቅርም የለም” ብለዋል:: ከቋንቋ አጠቃቀም አኳያም የማስታወቂያ አዋጁ

በአንቀፅ 21 ተራ ቁጥር 3 “የውጭ ማስታወቂያ በአገር ውስጥ ቋንቋ ወይም ፊደል የተጻፈ መሆን ወይም በውጪ ቋንቋ ወይም ፊደል ጭምር የተጻፈ ሲሆን የአገር ውስጥ ቋንቋው ወይም ፊደሉ ከውጪው ቋንቋ ወይም ፊደል አስቀድሞ ወይም ከላይ ሆኖ የተጻፈ መሆን አለበት” ይላል::

ነገር ግን የማስታወቂያ ፈቃድ አገልግሎትን እንዲሰጥ የተሰጠው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሌሎች ከማስታወቂያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን መልክ ለማስያዝ ስልጣን እንደሌለው አቶ በሰላም ያስረዳሉ:: “ተግባሩ ተቀንጭቦ ለኮሙኒኬሽን፣ ተቀንጭቦ ለባሕልና ቱሪዝም፣ የተወሰነው ደግሞ ለደንብ ማስከበር የተሰጠ በመሆኑ በአግባቡ ለመምራት አስቸጋሪ አድርጎታል፤ እኛ የፈቃድ አገልግሎቱን ብቻ ትኩረት ሰጥተን እንሠራለን፤ ነገር ግን ከፈቃድ ውጪ የሚሠሩትን፣ የሚያሠራጩትንና

ከተፈቀደላቸው ገደብ በላይ የሚያስተዋውቁትን ለመቆጣጠር ስልጣን የለንም:: የተሰጠን ኃላፊነቱ እንጅ ኃላፊነቱን የሚመራው የሥራ መደብም አልመጣም” ሲሉም አቶ በሰላም ምላሽ ሰጥተዋል::

ያም ሆኖ ከተሰጣቸው ውስን ኃላፊነት በመነሳት የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደርን የማስታወቂያ ስርዓት ፈር ለማስያዝ ረቂቅ ደንብ ማዘጋጀታቸውንና በቅርቡ በሚመለከተው አካል ሲፀድቅ ሥራ ላይ እንደሚውል አቶ በሰላም ተናግረዋል:: እርሳቸው እንዳሉት የተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ “ማስታወቂያ የሚለጠፍባቸውን ቦታዎች፣ በድምፅ ማስታወቂያ የሚነገርባቸውና የማይነገርባቸው አካባቢዎች፣ በድምፅ ማስታወቂያ ሲነገር የሚኖረው የድምፅ ገደብ፣ የማስታወቂያዎች ስነ-ምግባርና ሕጋዊ መሆን፣ የማስታወቂያዎች ትክክለኛነትና ተዓማኒነት፣… ሁሉ አሠራር ተቀምጦለት የሚቆጣጠርና የሚያስፈጽም አካልም ተመድቦለት ከዘርፉ መንግሥት ገቢ የሚያገኝበት፣ ዜጎችም የሥራ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑበት ይሆናል::”

ረቂቅ ደንቡ ፀድቆ ሥራ ላይ እስኪውል ግን አሁንም ባልተቀናጀ መልኩ የማሥታወቂያ ሥራው መቀጠሉ አይቀርም:: እንደ አዕምሮ ደሳለኝ ያሉ በማስታወቂያዎች እየተጎዱ ያሉ የሕብረተሰብ ክፍሎችም በቶሎ የሚታደጋቸው ይሻሉ:: እንደባሕር ዳር ሁሉ አዲስ አበባም በውጪ ማስታወቂያዎች ስርዓት ማጣት የምትታዎቅ ከተማ ነበረች:: አሁን ላይ በአዲስ አበባ ከፍተኛ መሻሻሎች አሉ:: ከአዲሱ ገበያ በፒያሳ እስከ ለገሀር፣ ከለገሀር በአውቶቡስ ተራ እስከ ስድስት ኪሎ፣ ከስድስት ኪሎ በአራት ኪሎ መገናኛ- አያት ድረስ ተዘዋውሬ ተመልክቻለሁ:: የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ በር (በየካቲት 12 አደባባይ በኩል) ያለው አጥር በበርካታ የፊልም፣ የአስጠኝ ፈላጊዎች፣ የዲሽ ተካዮች፣ የሥራ፣ … ማስታወቂያ ከመጥለቅለቁ በቀር ሌሎች አጥሮች፣ የስልክና የመብራት ምሶሶዎች ሁሉ ከማስታወቂያ ፀድተዋል:: ከተንቀሳቀስኩባቸው ታክሲዎች ውስጥም የድሮዎቹ አጉራ ዘለል ጥቅሶች የሉም::

በባሕር ዳር ከተማ ባየኋቸው ባጃጅና ታክሲዎች ውስጥ ግን ፆታ ተንኳሽ፣ ኃይማኖት ሰባኪ፣ የወንድ የበላይነትን አንፀባራቂ፣ የወጣቶችን ራዕይ አልባነት መካሪ ጥቅሶች ተመልክቻለሁ:: በባጃጆቹ ውስጥና ኋላ ላይም የሆቴሎች፣ ሸቀጦች፣ የጤና ተቋማት፣ የተለያዩ ድርጅቶች ማስታወቂያዎች ተመልክቻለሁ:: ማስታወቂያዎቹ በሚመለከተው አካል የታወቁና ይሁንታ የተሰጣቸው ስለመሆናቸውና ስለሕጋዊነታቸው ግን አንዳች ማስረጃ የላቸውም::የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ምክትል መምሪያ ኃላፊ

አቶ በሰላም ይመኑ

Page 30: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 30

ባለማስተላለፋቸው ነው እላለሁ:: ያ ማለት ግን ስለ ኢህአፓ አነሳስና ውድቀት በባለ ታሪኮች የተፃፉ መፃህፍት የሉም ማለት አይደለም:: ለአብነት ያህል የኢህአፓ አመራር የነበረው ክፍሉ ታደሰ “ያ ትውልድ” በሚል ርዕስ በሶስት የመፃህፍት ቅፆች ስለ ኢህአፖ ፅፏል፤ በኢህአፓ ወታደራዊ ክንፍ ውስጥ የነበረው አስማማው ሃይሉ (አያ ሻረው) የኢህአሰን ታሪክ “ከጐንደር ደንቢያ እስከ ዋሽንገተን ዲሲ” እና የኢህአሰ ታሪክ በሁለት ቅጽ መፃህፍት አሳትሟል፤ በህይዎት ተፈራ የተፃፈው “tower in the sky”፣ የመኮንን ገብረ ዝጊ “ፍቅር በዘመነ ሽብር”ና ሌሎችም… ይጠቀሳሉ::

በ2005 ዓ.ም በደራሲ ካህሳይ አብርሃ የተፃፈው “የአሲምባ ፍቅር” ደግሞ በድርጅቱ ውስጥ የነበረውን እውነት ከራሱ እይታና ገጠመኝ በመነሳት ነው የሚተርከው:: አንድ ታሪክ በባለ ታሪኩ መፃፉ ደግሞ ለታማኝነት ቅርብ ያደርገዋል:: በዚህ ሀሳብ ላይ ደራሲ፣ ገጣሚና ጋዜጠኛ ነብይ መኮንን በመፅሃፉ ጀርባ የሰጠው አስተያየት ይጠቀሳል::

“እስካሁን ካነበብኳቸው በኢህአፓ ላይ ያተኮሩ በተለይ በአማርኛ ከተፃፉት መፃህፍት መካከል የካህሳይን መፅሃፍ ለይቸ ወድጀዋለሁ:: ቀና ነው:: በህፃን የየዋህነት ቀለም የተፃፈ ነው:: ስለ ራሱ ለራሱ ለመንገር ብሎ እንጅ ለሌሎች ለመንገር ብሎ የፃፈው አይመስልም:: ፅሁፉ ያን ዘመን እንደገና ከሌሎች ጋር እንድወያይበት አድርጎኛል::”

የካህሳይ ኩርባ አንድ - ወላጆቹደራሲ ካህሳይ ተወልዶ ያደገው በቀድሞው

ትግራይ ጠቅላይ ግዛት፣ በአጋሜ አውራጃ፣ ዛላ አንበሳ ወረዳ በምትገኘው ጥርቀ በተባለች የገጠር መንደር ነው:: የቤተ ክህነት ትምህርቱ እስከ ቅዳሴ የዘለቀው ካህሳይ የአርሶ አደር ቤተሰቦቹን እንግልት እያየ ነው ያደገው:: ባደገበት ቀዬ አንዱ ያጣ የነጣ ሌላው ደግሞ መሬትና ምርት የተትረፈረፈው የመሆኑ ምስጢር በለጋ አእምሮው ይመላለስ ነበር::

በአንድ ማለዳ ወላጅ አባቱ ወደ አንድ ባላባት ቤት ይዘውት ይሄዳሉ:: በጓሮው በር ተደብቆ የመጣው ባላባት አርሶ አደር አይመስልም:: ረጅምና ወፍራም፣ ወዘናው የሚያብረቀርቅ ነው:: አባቱ ለባላባቱ ሸሽገው ገንዘብ ሲሰጡት ያያል:: በሁኔታው የተገረመው ብላቴና አባቱን ይጠይቃቸዋል:: ቀጥሎ የሆነውን እንዲህ ይተርክልናል፡-

“ዳኛ ስለሆነ፤ እኔ የምፈልገውን እንዲያደርግልኝ ነው::” ግራ በመጋባት አባቴን ዐይን ዐይኑን አየሁት::

“እዚህ ሀገር ለዳኛ ገንዘብ ካልሰጠህ ምንም ነገር ማድረግ አትችልም:: ስለዚህ ሁላችንም ጉቦ እየሰጠን ነው የምንኖረው::” አለኝ አባቴ ጉዳዩ እንዲገባኝ::

“ሁሉም ሰው ጉቦ የሚሰጥ ከሆነ ዳኛው ለየትኛው ያግዛል?” አልኩት::

“የሚፈርደውማ የበለጠ ገንዘብ ለሰጠው ነው::” አለኝና “አየህ? የምሰጠው ወድጀ እንዳይመስልህ፤ ይፈርድብኝና ያለኝን አጣለሁ ብዬ ከመፍራት ነው እንጅ፤ ለእርሱ የምሰጠውን ገንዘብ ለአንተ ልብስ መግዣ ባደርገው በጣም ደስ ይለኝ ነበር:: እንዲህ ካላደረግሁ ግን መሬቴን እነጠቅና የጠላት መጫወቻ እሆናለሁ::” ብሎ አስረዳኝ፤ (የአሲምባ ፍቅር ገፅ 31)

ወቅቱ ባለጉልበቶች የሚኖሩበት፤ የዳርዊን አመክንዮ ሃያሉ የሚያሸንፍበት (survival of the fittest) የሚተገበርበት ነበር:: እናም ካህሳይ ይህ በአንድ ሀገር ልጆች ያለው የህይዎት እንቆቅልሽ ግራ እያጋባው ነበር ያደገው::

በአካባቢው ከስድስተኛ ክፍል በላይ ትምህርት ቤት ባለመኖሩ የጀመረውን ዘመናዊ ትምህርት ለመቀጠል ወደ አዲግራት ከተማ አቀና:: በ1964 ዓ.ም የስምንተኛ ክፍል ተማሪ በነበረበት ወቅት ደግሞ፤ የሃገሪቱ የፖለቲካ ትኩሳት ውስጥ ውስጡን የሚብላላበት፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በየስርቻው ስለፖለቲካ የሚወያዩበት አመት ነበር:: አንድ ቀን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው የንጉሱን ስርዐት በመቃወም አመፅ ወጡ:: ወታደሮች ተኩስ ከፈቱ፤ ከተማዋ በተኩስ እሩምታና በተማሪዎች ጩኸት ተናወጠች::

“እኔና የትምህርት ቤት ጓደኞቸ በተፈጠረው ረብሻ ግራ ተጋብተን በድንጋጤ መሸሽ ጀመርን::

ኢትዮጵያ ሆቴል አጠገብ ጨረቃ ቤት የሚባል ነበረ:: እየሮጥን ገባንና በየአልጋው ስር ተደበቅን:: ወታደሮች በየቤቱና በየቡና ቤቱ እየገቡ ሲፈትሹ፤ እኛንም ከተደበቅንበት እየጎተቱ አወጡን:: ወታደሮቹ ትናንሾቹን ወደ ቤታችን እንድንሄድ ሲለቁን፣ ትላልቆቹን ግን እየደበደቡ፣ እገፈተሩና እየጎተቱ መኪና ላይ ጭነው ወደ እስር ቤት ወሰዷቸው::” (የአሲምባ ፍቅር ገፅ 29)

ይህ በመፅሃፉ የተገለፀው እውነት ወደ ኋላ ላይ ለተቀጣጣለው ህዝባዊ አብዮት እርሾ ነበር:: በህዝቡ ውስጥ የነበረው የለውጥ እርሾ አይሎ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በስፋት መንቀሳቀስ ጀመሩ:: የህዝቡን የዘመናት ብሶትና ጥያቄ ያነገበው ኢህአፓ ደግሞ በወጣቱና በምሁራን ዘንድ ተቀባይነት ነበረው::

በለጋ ዕድሜው፣ በቀዬው የሚኖሩ አርሶ አደሮችንና የቤተሰቦቹን የህይዎትና የኑሮ ልዩነት እያዬ ያደገው ደራሲው፤ የወቅቱን የፖለቲካ ትኩሳት ከነባራዊ ሁኔታው ጋር እንዲያገናዝብ እድል ፈጠረለት:: እናም ለተበደለው ህዝብ ጠበቃ ለመሆን ትምህርቱን አቋረጠ:: የህይዎት ኩርባዎቹ ከቤተሰቦቹና ከትምህርቱ ነጠሉት:: ኢህአፓን ለመቀላቀል ወደ አሲምባ በረሃ አቀና::

“መስከረም 27 ቀን 1968 ዓ.ም እኔና ታደሰ አፅብሃ በድቅድቁ ጨለማ ከዛላ አንበሳ ተነስተን፤ ኢህአፓዎች ይገኙበታል ወደ ተባለው መነኩሲቶ አቅጣጫ መንገድ ጀመርን:: ስንሄድ አድረን ረፋድ ላይ መነኩሲቶ ደረስን::” (የአሲምባ ፍቅር፤ ገፅ 35)

ብዕርና ወረቀት የያዙ ጣቶቹ ወታደራዊውን የደርግ መንግስት በመጣል፤ የህዝቡን የዘመናት ጥያቄ ለመመለስ የጠበንጃ ቃታ ላይ አረፉ:: ሁሉም ከድል በኋላ ይደርሳል::

ካህሳይ አንደ ዘመኑ ወጣቶች ወደ ሰራዊቱ ሲቀላቀል አብሮት የተጓዘው ጓደኛው ታደሰ አፅብሃ ነበር:: ታደሰ ግን ምክንያቱን ሳይነግረው ከትግሉ ጎራ ሳይደርስ ይመለሳል:: ከደራሲው ጋር በነበረኝ ቆይታ ሁኔታውን አጫውቶኝ ነበር::

“የወጣነው ለትግል ነበር:: ግን ታደሰ ተመለሰ:: እኔ አሲምባ ገባሁ:: ትግሉን ከተቀላቀልሁ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ለአንድ ግዳጅ ስንቀሳቀስ አግኝቸው ነበር:: ታደሰ ትግሉን ባለ መቀላቀሉ እንዳዘነና እንደ ተፀፀተ ነገረኝ:: በዚሁ ተለያየን::”

ከአመታት በኋላ ግን ለአንድ ህዝባዊ አላማ ወደ አሲምባ በረሃ አብሮት ሊወጣ የነበረው ታደሰ፤ የአምባገነኑ ወታደራዊ ስርአት ጋሻ ጃግሬ እንደ ነበር መስማቱን ሲነግረኝ እያዘነ ነበር:: ያ ዘመን ዕርስ በዕርስ መተማመን ያልነበረበት፣ አሳዛኝ ክስተቶች የታዩበት፣ ፈታኝ ጊዜ እንደ ነበር ለመረዳት አያስቸግርም ነበር::

የካህሳይ ኩርባ ሁለት - አሲምባየካህሳይ ሁለተኛው የህይዎት ኩርባ

የሚጀምረው አሲምባ በረሃ እንደ ገባ ነበር:: በድርጅቱ መመሪያ መሰረት ቤሰቦቹ ያወጡለትን ስም ቀየረ፤ ካህሳይ መባሉ ቀርቶ አማኑኤል ተባለ:: ምክያቱም በአካባቢው የነበሩት የደርግ የደህንነት ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን እንዳያንገላቷቸውና እንዳይታወቁ ነበር:: (ከዚህ በኋላ አማኑኤል ወይም ደራሲው እያልሁ እቀጥላለሁ::)

አማኑኤል ዛሬም ከአመታት በኋላ ሲያስበው ስሜቱን የሚነሽጠው የድርጅቱ ቃለ መሃላ እንደሆነ ይናገራል::

“እኔ ለሀገሬና ለኢትዮጵያ ህዝብ እስከ መጨረሻው ለመስዋዕትነት ተዘጋጅቸና በኢትዮጵያ አቢዮታዊ ሰራዊት ስር ሁኘ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃ እስኪወጣ እስከ ህይወቴ ፍፃሜ ድረስ በትግል ጎዳና እጓዛለሁ!” የሚል ነበር:: (የአሲምባ ፍቅር፤ ገፅ 44)

“…የሚገርምህ?… አሲምባ እንደ ገባሁ የኢህአሰ ሰራዊት ለመሆን የምንገባው ቃል ኪዳን ነበር:: ለመጀመሪያ ጊዜ ቃል ስገባ የተሰማኝ ስሜት ዛሬም ድረስ አለ:: እስካሁን ድረስ ባለው ዘመኔ እንደዚያ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም::” ይላል::

ያ ትውልድ ላነገበው አላማ በፅናት እንዲቆም የሚያደርግ የኢትጵያን ህዝብ በደልና ሰቆቃ የፍትህና የነፃነት እጦቱን ለመታደግ አንድያ ህይወታቸውን ቤዛ አድርገው የነፃነት ሻማ ለመለኮስ ሲነሱ፤ ዘመናትን ተሻግሮ በእዝነ ህሊናቸው የሚመላለስ ቃለ መሀላ ነበር::

“…ያኔ የህዝብ አደራ ስትቀበል፤ ህዝባዊ አደራ ሲጣልብህ አስበው?...” ሲል መልሶ ጠየቀኝ:: አይን አይኑን ከማየት በቀር መልስ አልነበረኝም:: ከ35 አመታት በኋላ ቃለ መሃላውን አነበነበልኝ:: ስሜቱ ደፈረሰ:: ከአሲምባ ጎንደር፣ ጠለምት፣ ወሎና እብናት ሲጓዝ ያሳለፈውን የህይዎት ውጣ ውረድ፤ ድልና ሽንፈት፤ መማረክና መስዋዕትነት ለአፍታ በእዝነ ልቡናው ሲላወስ፤ እንባው እንዳይወርድ አይኑን አስሬ ያርገበግባል:: ሀዘኑ ቢጋባኝም ያስሜት ፈንቅሎት ሊወጣ ሲታገለው ሳይ ገረመኝ:: ምክያቱም እሱ እድለኛ ሁኖ ያለፈውን ትውልድ የታሪክ አሻራ ለመዘከር በቅቷልና::

ያ ትውልድ በዛሬው ትውልድ አይን ሲታይ ብዙ መልኮች፣ ብዙ ወጎች አሉት:: አንድም በወጉ ተደርዘው የቀረቡ የታሪክ ድርሳናት አለመኖር፤ ሁለትም ደግሞ በተለያየ መልኩ በሀገራችን ታሪክ ውስጥ ጥቁር ትዝታ ያጠላበት መሆኑ፤ በደፈናው አንድ ትውልድ የተቀጠፈበት እየተባለ ስለሚወጋም ይመስለኛል:: ምንም እንኳን የደርጉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት፤ ኮሎኔል ፍስሃ ደስታ በ2008 ዓ.ም ባሳተሙት “አቢዮቱና ትዝታዬ” በተባለው መፅሃፍ ይህን እውነት

“…አንድ ትውልድ የሚለው አይገባኝም:: ስምንት ሽህ አካባቢ እንደሆነ የልዩ አቃቢ ህግ የክስ መዝገብ ያስረዳል:: እኔ የማምነው ይሄን መረጃ ነው:: ምክንያቱም የልዩ አቃቢ ህግ ያረጋገጠው ስለሆነ…” ሲሉ ባይስማሙበትም::

ወቅቱ የህዝቡ የዘመናት ሰቆቃ አንገፍግፏቸው፤ ወደ በረሃ ለትጥቅ ትግል የወጡት ወጣቶች፤ መከራቸው የበዛ እንደ ነበር፤ የያኔው አማኑኤል የአሁኑ ካህሳይ በግልፅ ቋንቋ ማስፈሩን ግን አደንቃለሁ:: እርግጥ ነው በስራ ምክንያት ስንቀሳቀስ ያገኘኋቸውና በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ ተሰልፈው የነበሩ ታጋዮች፤ የዚያ ዘመን ትውስታቸው ከዚህ የተለየ እንዳልሆነ አጫውተውኛል::

ለአብነት የኢህዴን ብአዴን ታጋዮች ይጠቀሳሉ:: የበለሳ አርሶ አደሮች አባ ፈረደ (ጥቁሩ ቮልሸቪክ)፣ አርባ ፀጓሩ አባ ንጋቱ፣ የጉሃላዋ እናት ወይዘሮ አስረበብ፣ የአበርገሌዎቹ ታደሰ ምሩፅና መኮነን ገብርዬ (ጨርግድ)፣ የአርማጭሆወቹ ታጋይ ሻምበል ፀሃይ፣ ታጋይ ይቻላልና የድርጅቱ መስራችና ነባር ታጋዮችም ሆኑ ሌሎች ኢህአፓን ቀድመው የተቀላቀሉ ታጋዮች ለዚህ እውነት ህያው ምስክር ናቸውና::

“የአሲምባ ፍቅር” ደራሲ የያኔው የኢህአሰ አባል ካህሳይ በድርጅቱ ውስጥ የነበሩ እውነተኛ ታሪኮችን በመፅሃፍ መልኩ ማቅረቡና የተለየ የታሪክ አንጓ የያዘ በመሆኑ የተለየ ሁኖብኛል::

የነበረው ስርአት በህዝብ ላይ የሚያደርሰው መከራ አንገሽግሿቸው፤ ነፍጥ አንስተው ለህዝብ ልዕልና በርሃ የወጡት ታጋዮች፤ አንድያ ህይወታቸውን ቤዛ ሊያደርጉ ሲነሱ፤ የሚተኙበት አበባ ምንጣፍ፣ የጣፈጠ ምግብ፣ የሚጠቱትና ንፅህናቸውን የሚጠብቁበት ንፁህ ውሃ ማግኘት የሚያስቡት አልነበረም:: ምክንያቱም የትጥቅ ትግሉ አንድ መራር ገፅታ የምግብ፣ የውሃና የአልባሳት ችግር ነበረና:: ለዚህ ማሳያ የሚሆነው ደግሞ ደራሲው በትግል ጅማሬው ያስተዋለው እውነታ ነበር::

“ከትውውቁ በኋላ ምግብ ቀረበልኝ:: የገበሬ ልጅ በመሆኔ የምግቡ ዓይነትም ሆነ አቀራረቡ የፈጠረብኝ ስሜት አልነበረም:: ለእኔ ያንን ቡድን መቀላቀል የፈጠረብኝ ስሜት ከምንም በላይ ነበር:: ኢትዮጵያን ለመታደግ ከቆመ ድርጅት ጋር መሰለፌ የፈጠረብኝ መንፈሳዊ ኩራት አጥለቅልቆኛል::

“አዘውትረን የምንበላው በጋለ ድንጋይ (በቃፄላ) ላይ የሚጋገር ቂጣ…” ነበር:: (የአሲምባ ፍቅር) ገፅ 40ና ገፅ 59::

ለህዝብ እውነት ሲባዝኑ ላያቸው ላይ የፈላውን ቅማል፣ የወረደባቸውን የበረዶ ዝናብ፣ ያለፉበትን ውርጭና ሃሩር ማስታወስ ግን ለዚህ ትውልድ ትርጉም ይኖረዋል:: ምክንያቱም ያለፈው ትውልድ የመከራ ቀንበራቸውን ሰብረው፤ አሁን ላለው ሰላም የከፈሉት መስዋዕትነት ነበር:: ቢሆንም ግን ያለፉበት የመከራ ዘመን ነገም በትውልዱ ቅብብሎሽ ከዘመን ዘመን ይሸጋገር ዘንድ ያለፈውን እውነት በውል ሊያውቀው ይገባል ብዬ አስባለሁ::

ይህን የምለው በዘመናዊነትና በቴክኖሎጅ እድገትና ተፅዕኖ ሳቢያ አሻግሮ የሚያማትረው

ትውልድ፤ ስለ ሆሊውድና ቦሊውድ ተዋንያኖች፤ ስለ አለማቀፍ እግር ኳስ ተጫዋቾችና ስለ ሌሎች ታዋቂ ሰዎች አፋሽ አጎንባሽ መሆን የለበትም:: እንደ ታጋይ ታሪክ ፈንቴ፤ እንደ ታጋይ ማርታ፤ እንደ ታጋይ ድላይና ሌሎችም ጀግኖቻችን በፊልም ሳይሆን በገሃድ መስዋዕትነት የከፈሉ አያሌ ኢትዮጵያዊ ጀግኖችቻችን ማንነት፤ ከነሻኪራ፣ ከነአንጀሊና ጁሊ፣ ከጀነፈር ሎፔዝና ከሌሎችም በላይ ያደንቋቸው፣ ያከብሯቸው ዘንድ፤ የተሰውለትን አላማ ዘመን ያሻግሩ ዘንድ፤ ገድላቸው እንዲህ በመፅሃፍ ሊዘከር ይገባዋል፤ ቢቻል በፊልምም::

ለዚህ ነው በ“አሲምባ ፍቅር” መፅሃፍ ውስጥ የተሳሉት ባለ ታሪኮች ከራስ ፀጉራቸው እስከ ቁምጣቸው የሰፈረባቸውን ቅማል በተራ ሲቀማመሉ እንደ ነበር ደራሲው እንደ ወረደ የፃፈው:: ለአብነት ታጋይ ጓዶችን በመቅመል የሚደሰተው ፀጋዬ ገብረ መድህን ወይም በትግል ስሙ ፀጋዬ ደብተራው ይጠቀሳል::

“…ፀጋዬ ግለኝነት የማያጠቃው፤ ከራሱ ይልቅ ለሌሎች ጓዶች የሚጨነቅና ቅድሚያ የሚሰጥ ነበር:: ምግብ በምንመገብበት ጊዜ አንድ ሰው ምግቡን ቀድሞ ከጨረሰና ቅር ብሎት ከተመለከተ ፀጋዬ የራሱን ድርሻ ሲሰጥ ማየት የተለመደ ነበር:: በበርሃ ውስጥ ከሚፈትኑን ችግሮች አንዱ የነበረው የልብስና የፀጉር ቅማል ነበር:: መቸም ማከክን ተላምደነው እጃችን ስራ ፈቶ አይቆይም:: ችግሩ ጠንከር ሲልም ለማስታገስ እርስ በርስ መቀማመል የተለመደ ሲሆን፤ ፀጋዬን ግን የሚያህለው አልነበረም:: ጊዜ ኖኑሮት አንድ ሰው ሲያክ ካየ ዝም አይልም፤ ጠጋ ብሎ እናት የልጇን ራስ እንደምትደባብስ ሁሉ እሱም በደስታ ይደባብሰዋል:: በተለይ ሰፋ ያለ ጊዜ ካለው፤ እሱ እንዲቀምለን ተራ የምንገባበት ወቅት እንደ ነበረ ትዝ ይለኛል:: እሱ ግን አይሰለችም:: የእርካታ ስሜት ነበር የሚታይበት::” (የአሲምባ ፍቅር፤ ገፅ 106)

በነገራችን ላይ እነዚህ ተዳፍነው የነበሩ ታሪኮች መውጣታቸው አንድም የዚያ ዘመን ትውልድ ያለፈበትን የህይወት እውነት ለመረዳት፤ ሁለት ለባለ ታሪኮች ቤተሰቦችም ሆነ ለታሪክ እንደ ማስታወሻነትም እንደ ታሪክ ሰነድነትም ያገለግላል:: ለምሳሌ ከዓመታት በኋላ የወንድሙን ታሪክ ከዚህ መፅኃፍ ያነበበው፤ የፀጋዬ ገብረ መድህን ወይም የፀጋዬ ደብተራው ወንድም ገብርኤል ገብረ መድህን፤ በሶስተኛው እትም ላይ የተሰማውን ስሜት እንዲህ ገልፆታል::

“ስለ ፀጋዬ ብዙም የማውቀው ነገር አልነበረም:: በቤተሰባችን ውስጥ ፀጋዬ ታይቶ እንደጠፋ ህልም ነው:: ሳንጨብጠው የቀረብን ቅዠት፤ አሁን ግን የአሲምባ ፍቅር በሚለው መፅሃፍ እሱ ጋር ቅርብ የነበረ ሰው፤ ብዙም ሳላውቀው ስለተለየኝ ወንድሜ ታሪክ ሲተርክ ሳነብ በጣም ነው ስሜቴን የነካው:: በተለይ ቅማሉን ሲቀምሉለትና እሱም ሲቀምልላቸው የነበሩ ጓደኞቹ ከእሱ ጋር ጫካ ለጫካ ሲንከራተቱ የነበሩ የቅርብ ሰዎች ታሪካቸውን ሲፅፉ ሳይ ፀጋዬን ቅርቤ ድረስ ያመጡልኝ ያህል ነው የተደሰትኩት::”

ሌላው አብነት የሚሆነን ኤርትራ እያለ በተማረው መጠነኛ የህክምና ሙያ፤ ታጋይ ጓዶቹን የሚያሰለጥነው ጌራ ነው:: ለአሰልጣኛቸው ክንዳቸውን ዘርግተው መርፌ እየተወጉ የሚሰለጥኑ ታጋዮች እንዳይጎዱ ብዙ ጊዜ ፀጋዬ ደብተራው ነበር መለማመጃ ሆኖ የሚቀርበው::

“…ጌራ የህክምና ሙያ ስልጠና የወሰደው ከአራት ጓዶቹ ጋር ጠፍተው ከኢትዮጵያ ለመውጣት ሲሞክሩ ሶማሊያ ውስጥ ታስረው ከተፈቱ በኋላ ነበር:: ከእስር ሲፈቱ አብረው ከነበሩ የኤርትራ ተወላጅ ተማሪዎች ጋር ወደ ኤርትራ ከገቡ በኋላ በኢፒ ኤል ኤፍ (ሻዕቢያ) ዶክተሮች አማክኝነት ሰለጠኑ:: ጌራ ጎበዝና ታታሪ አሰልጣኝ ከመሆኑም ሌላ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የህክምና ዕርዳታ የሚያደርግልን እሱ ስለ ነበር በቅፅል ስም ዶክተር እያልን እንጠራው ነበር::” (የአሲምባ ፍቅር፤ ገፅ 58::)

እውነተኛ ታሪኮችን የያዘው ይህ መፅሃፍ የእነዚያ ታጋዮች ታሪክና ኑሮ እንዴት እንደ ነበር ማንበብ ቢያምም ያ ትውልድ የከፈለውን መራር የህይወት እውነት ፍንትው አድርጎ ያሳያል ብዬ አምናለሁ::

ይቀጥላል

ከገፅ 15 የዞረ

የካህሳይ...

Page 31: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 31በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ማስታወቂያ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያየምስራቅ ጎጃም ዞን ብአዴን ጽ/ቤት በደ/ማርቆስ ከተማ ለሚያስገነባው G+6 ቢሮ ግንባታ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የግንባታ ማቴሪያሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸው፡፡2. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣3. ተጫራቾች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡5. የጨረታ ሰነዱ የሚሸጠው በምስራቅ ጎጃም ዞን ብአዴን ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ይሆናል፡፡6. እያንዳንዱ ዋጋ የሚሞላው በነፃ ገበያ ላይ ተመስርቶ መሆን ይኖርበታል፡፡7. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ

አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ለምስራቅ ጎጃም ዞን ብአዴን ጽ/ቤት ተብሎ በማሰራት ማቅረብ አለባቸው፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ኦርጅናል አንድ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግና ከላይ በሁለቱም ፖስታዎች በአንድ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግና ከላይ በሁለቱም ፖስታዎች ላይ የተፃፉትን በሙሉ በማጠቃለያ ፖስታው ላይ በማስፈር መመለስ አለባቸው፡፡ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ደ/ማርቆስ ከተማ ምስራቅ ጎጃም ዞን ብአዴን ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርበታል፡፡

9. ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡ዐዐ ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡3ዐ ይከፈታል፡፡10. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የሚከፈት

ይሆናል፡፡11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው የሚታሸገውና የሚከፈተው በሚቀጥለው

የስራ ቀን ከላይ የተገለፀውን ሰዓት ጠብቆ ይሆናል፡፡12. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በተመለከተው መሰረት የእያንዳንዱን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ

መግለጽ አለባቸው፡፡13. ስርዝ ድልዝ ካለ ጨረታው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡14. በማንኛውም ሁኔታ ተጫራቾች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ/ ተመስርቶ/ መጫረት

አይችሉም፡፡15. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ

ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሣቸውን ማግለል አይችሉም፡፡16. ንብረቱ የሚቀርብበት ቦታ ምስራቅ ጎጃም ዞን ብአዴን ጽ/ቤት ደ/ማርቆስ ከተማ መሆኑን

እንገልፃለን፡፡17. የሚቀርቡትን እቃ ናሙና የጨረታ ሰነዱ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ የሚችሉ እና የቤተ ሙከራ

ፍተሻ የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች የሚወጣ ወጭን ተጫራቾች የሚሸፍኑ እና ተፈትሾ የሚያልፍ መሆን አለበት፡፡

18. የእቃውን መጠን እስከ 20 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡19. በጨረታ ማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩ በግዥ መመሪያው መሠረት ተገዥ ይሆናሉ፡፡20. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ

የተጠበቀ ነው፡፡21. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ከምስራቅ ጎጃም ዞን ብአዴን ጽ/ቤት በግንባር ቀርበው ወይም በስልክ

ቁጥር 0587717144 ወይም በሞባይል ቁጥር 0910013595 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን ብአዴን ጽ/ቤት

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ደቡብ ጐንደር ዞን የደ/ታ/ፖ/ቴ/ሙ/ኮሌጅ ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን 1. የመኪና ጎማ 2. የመኪና እቃ 3. የፀጉር ቤት እቃ 4. የግብርና እቃ 5. የኮንስትራክሽን እቃ 6. ፀረ-አረም መድሃኒቶች 7. የተለያዩ የግብርና ዘሮች 8. የፅህፈት መሣሪያ 9. ብረታ ብረት 10. የተለያዩ ኮስሞቲኮች 11. የቤትና የቢሮ እቃዎች 12. የሻሂ ማሽን 13. የደንብ ልብስ 14. ጣውላና የጣውላ ውጤቶች 15. የግንባታ እንጨት 16. የኤሌክትሪክ እቃ 17. ብሎኬት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ድርጅት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸው፣3. የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን

የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የቫቱንም ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የሚገዙ የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 40.00 በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

8. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ታ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ በግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የፖስታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ክፍል በቢሮ ቁጥር 1 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እስከ 3፡ዐዐ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ3፡3ዐ ታሽጎ 4፡ዐዐ ይከፈታል፡፡

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሆኖ ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች ላወጡት ዋጋ ኮሌጁ ተጠያቂ አይሆንም፡፡

11. ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ እና በላይ ከተፈፀመ ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ 2 በመቶ ይቀነሣል፡፡

12. ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት 5,000.00/አምስ ሺህ ብር /በላይ ሽያጭ ከተፈፀመ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተቀንሶ ይቀራል፡፡

13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0584411232 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0584410447 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

14. ርክክቡን በተመለከተ የደ/ታ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ለባለሙያ እያሣየ

ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

የደብረ ታቦር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

INVITATION TO BIDTo: All contractors of category GC-10/Bc-9 & Above with license valid for the year 2008 E.C and can present short term registration certificate for construction work service for the Maintenance of Office and Meeting Hall.ANRS Office of Audit General has invited wax sealed bids comprising of Financial Proposal from eligible Bidders for Providing the necessary labor, material & Equipment for the construction and completion of the Maintenance of office and meeting Hall1. The priced (Financial) bid documents may be obtained by any interested eligible bidders on the submission of a written application to ANRS Office of Audit

General. P.O.Box 479 Tel: 0582201992 or 0582262719 Fax:0582201694 and upon payment of non-refundable birr:100/One Hundred Birr/

To whom all inquires and correspondences should be addressed 2. Each bid must be accompanied by an acceptable bid bond in the sum equal to 2% of the bid amount including VAT in CPO, which shall remain in forces for 90

calendar days from the bid opening date and shall be in separate envelope. The successful bidder will be required to furnish a performance bond in the sum of 10% of the gross bid sum within 15 days from signature.

3. Bidders are warned that they must read and comply in full with the “INSTRUCTION TO BIDDERS” 4. The construction of works shall be completed within a maximum 120 Calendar Day 5. All bids must be submitted based on the free market price and current basic materials price must be attached with the bid document.6. The priced bid documents shall be in separate envelopes & wax-sealed/ one original & one copy/. 7. All Bid will be Evaluated based on financial least bidder.8. Scaled Priced bid documents shall be submitted to ANRS Office of Audit General Room Number 9 on 21 Calendar day from the first date of advertisement

at 2:00 PM hours and shall be Publically opened the same day /21 Calendar day from the first date of advertisement/ and the same place at 3:00 PM Hours in ANRS Office of Audit General when the names of the bidders and the amount of their bids will be declared. Bidders are advised to attend the opening of bids.

9. Bidders may obtain further information from ANRS Office of Audit General 10. Bidders must present certificate of VAT registration.11. The ANRS Office of Audit General reserves the right to reject any or all bids without giving reasons therefore and to waive informalities and irregularities,

which do not constitute a material modification in the bids received.

ANRS Office of Auditor General

Page 32: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 32

ከገጽ 16 የዞረ

ከገጽ 8 የዞረ

ኢንተርፕራይዞች ...

ከገፅ 7 የዞረ

ውለታ ቢስ...“አማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ያካሄደው

የውይይት መድረክ ለዘመናት የቆየ ችግር የፈታ፤ ሆድና ጀርባ የነበረን አመራርና ህዝብ ለአንድ አላማ ያነሳሳ ነው” ያሉት ደግሞ አቶ አድማስ ጌታሁን ናቸው::

መሪዎችን ያተጋ... ንፋስ መውጫ ከተማ

አቶ አድማስ አክለውም “ከተማ አስተዳደሩ ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የውይይት መድረክ በኋላ ከነዋሪው ጋር ድጋሜ በቅርቡ ባካሄደው መድረክ ላይ ሪፖርት ሲያቀርብ የሰራውን፣ በረጅም ጊዜ የሚሰራውን፣ ከአቅሙ በላይ ሆኖ ለዞን ያስተላለፈውን በግልጽ አሳውቆናል:: ይህ ሲሆን ሁሉም ለስራ ዝግጁ ይሆናል” በማለት ከመድረክ በኋላ የመጣውን ለውጥ ከበፊቱ በማነፃፀር ገልፀዋል::

አቶ አወቀ ያለውም “የካቲት 20/2008

ዓ.ም የተካሄደው የመልካም አስተዳደር ውይይት አመራሮች አሰራራቸውን ለማስተካከል አሯሩጧቸዋል:: ካሁን በፊትም ጥያቄያችን ምላሽ ሳያገኝ ለፍልፈን እንቀር ነበር፤ አሁን ግን ይህ እየቀረ ነው” ብለዋል::

ዶ/ር ፋንታሁን ሰለሞን በበኩላቸው የውይይት መድረኩ የረዥም ጊዜ የህዝብ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ እንዳስቻለ ተናግረዋል::

አቶ ፀጋዬ አራጌ፣ ወ/ሮ የሽ አባይ፣ ወ/ሮ ፋንታ ታደሰና አስር አለቃ ደመቀ ቀለሙ በበኩላቸው በመድረኩ ያነሷቸውን ችግሮች ከመፍታት ይልቅ ዘለፋ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል::

የውይይት መድረኩ በአመራሩ እይታ

የከተማው ከንቲባ አቶ ሙላው ጤናው እንደሚሉት በተዘጋጀው መድረክ ህዝቡ ብዙ ነገር አሳይቶናል:: የአገልግሎት አሰጣጣችን የተንቀራፈፈ ነው:: ከስብሰባ በኋላ ግን የስብሰባ ሰዓታችንን ማታ አድርገናል:: የማናውቃቸውን ችግሮች ህዝቡ ነግሮናል:: ከዛ ተነስተን በአገልግሎት አሰጣጥ ችግርና በኪራይ ሰብሳቢነት አዘቅጥ እጃቸውን አስገብተው የነበሩ አራት የቀበሌ አመራሮችን ከኃላፊነታቸው አንስተን ጉዳያቸው በህግ እንዲታይ አድርገናል::

አቶ ሰርኩ ታረቀኝ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽንና አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ በበኩላቸው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ያካሄደው የውይይት መድረክ በወቅቱ ከህዝቡ ጋር እየተገናኘን የመልካም አስተዳደር ችግሮቹን ካልፈታን፤ ነገ፤ ከነገ ወዲያ የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ካልቻልን፤ ይሁንታውን እያጣን እንደምንሄድ ያመላከተን በመሆኑ ጅምሩን አጠናክሮ ቢቀጥል መልካም ነው” ብለዋል::

በአቶ ፀጋዬ አራጌ የተነሳውን ቅሬታ ግን ሁለቱም አመራሮች ያቀረቡት ቅሬታ ትክክል እንዳልሆነና ከመድረክ በኋላም ችግራቸውን ዞን በጠራው ስብሰባ ላይ መናገራቸውን አልሸሸጉም:: ለሌሎችም ቢሆን ተገቢው ምላሽ መስጠቱን ተናግረዋል::

“...የአገልግሎት አሰጣጣችን የተንቀራፈፈ ነው:: ከስብሰባ በኋላ ግን የስብሰባ ሰዓታችንን ማታ አድርገናል::”አቶ ሙላው ጤናው - ከንቲባ

“...የውይይት መድረኩ የረዥም ጊዜ የህዝብ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ አስችሏል::” ዶ/ር ፋንታሁን ሰለሞን - የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር

እኒያ የዓለም ታላቅ ሰው፣ እኒያ ለህዝባቸው እና ለሃገር ኩራት የነበሩና ስማችንን በኩራት ያስጠሩ፣ የስንቶችን መታሰቢያ ሐውልት በድንቅ ጥበባዊ ሙያቸው ያቆሙ ክቡር ሰው፤ ለራሳቸው ግን አልሆኑም:: በሐውልቶች መካከል ሐውልት አልባ መቃብር ተጭኗቸዋል:: እርሳቸው ለሃገራቸው ክብር ሰጡ እንጂ፤ እሳቸው ለህዝቦች ኩራት ሆኑ እንጂ፣…ሃገራቸው ሆነች ህዝባቸው ለእሳቸው ብድራቸውን አልከፈሉም::

እሳቸው ግን ለሙያ ፍቅር፣ ለሃገር ክብር ሲሉ ኖሩ እንጂ ለእሳቸው ሐውልት፣ ለእሳቸው መቃብር እንዳልተጨነቁ ይታወቃል:: እንዴትስ ሊጨነቁ ይችላሉ?:: ‘ኩራት የሆንኩላቸው ህዝቦቼ፣ ሰንደቅ ዓላማዋን በጨረቃ ላይ ያውለበለብኩላት ሃገሬ፣ ወገኔ አሉ’ ብለው አስበው ይሆናል:: ውለታ ቢስ ትውልድ ሆንንባቸው እንጂ::

የጥንት ማንነታችንን፣ የጥበብ፣ እውቀት፣ ስልጣኔ፣.. ፈር ቀዳጅ መሆናችንን በዘመኑ ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ አሳይተዋል:: አሁን ባለ አደራው ህዝብ ነበር፣ ሃገር….::

እኛ ግን በዋና ከተማችን አደባባዮች የእነማንን ሐውልት እንዳቆምን እናውቀዋለን:: የቦብ ማርሌ፣ ፑሽኪን…. ሐውልቶች ካልቆሙ ብለን አቧራ

ስናስነሳ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው:: ለውጭ ሃገር ዜጋ አምላኪ ካልሆንን በቀር ከእጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሚትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የበለጠ ለኢትዮጵያ ህዝብ እኒህ ሰዎች ሰርተዋል ብዬ አላምንም:: ሐውልት በአደባባይ ማቆም ይቅርና በመቃብሩ ላይ ድንጋይ ማስቀመጥ እንኳን ተሳነን:: በመቃብሩ ላይ ሸረሪት አድርቶበት፣ ጉንዳን ሲረማመድበት ማየት ያማል!

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የዚህ ታላቅ ባለውለታ መቃብር ሐውልት አልባ ሆኖ እንደቀጠለ ሰምቻለሁ:: የመቃብር ሐውልት ለማሰራት ኮሚቴ ተቋቋመ ሲባል የሰማሁትም እንደሞት አካባቢ ነበር:: መቃብሩ ግን ሐውልት አልቆመለትም:: ነው ወይስ ኮሚቴዎችም ሞተውብን ይሆን?

ለማንኛውም ሰዎች ከመሞታቸው በፊት ስናሽቃብጥላቸው እንደነበረ ሁሉ ከሞቱ በኋላም ልናሸረግድላቸው ይገባል:: ስለኛም ስም፣ ስለ ሃገራችን ዝና ለኖሩልን አባቶች ክብር ልንሰጣቸው ይገባል… ለውጭ ዜጐች የምንጨነቀውን ያህል ለራሳችን ለወገኖቻችንም ልናስብላቸው ይገባል:: አንድ ቀን ሞትን ድል ነሰተው የመነሳት እድል ቢያጋጥማቸው ‘እናንተ አደራ በይ፣ ውለታ ቢስ ትውልዶች’ የሚሉን ይመስለኛል::

“በአጠቃላይ መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ከመንግስት ሊደረግላቸው የሚገባ ድጋፍ ሁሉ ተዘንግቷል፤ በዚህም ምክንያት ወደ ፊት ይህንኑ ዘርፍ የሚያግዝ ራሱን የቻለ ኤጀንሲ የተቋቋመ ስለሆነ ከዚህ በኋላ ትኩረት ያገኛል” ያሉት ደግሞ የፌደራል አነስተኛና ጥቃቅን ኢንዱስትሪ ልማት ኤጀንሲ ተወካይ ናቸው::

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ብናልፍ አንዱአለም ውይይቱን ሲያጠቃልሉ “የመካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ችግሮች ለይቶ

መፍትሄ በመስጠት በኩል የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ እንደነበር ተረድተናል” ካሉ በኋላ “እያንዳንዱ አጋር አካል የተሰጠውን ኃላፊነት መወጣቱ ክትትል የሚደረግበትናተጠያቂነት የሚያስከትል አሰራር እንዘረጋለን” ብለዋል::

በኢንተርፕራይዞቹ በኩልም ሁሉንም ነገር ከመንግስት ብቻ መጠበቅ የሚያቀጭጭ እንጂ የሚያጠናክር እንዳልሆነ ጠቅሰው ችግሮችን በመቋቋም ለአሸናፊነት እንዲነሳሱ አሳስበዋል::

ከገጽ 19 የዞረዘመናዊ ...

አይታሰብለትም:: ማንም ለማምለጥ ቢሞክር ደግሞ እግሩን አለያም እጁን ተቆርጦ ወደ ባህር እንደሚጣል ያየውን ዋቢ አድርጐ ተናግሯል::

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ፊል ሮበርትሰን በ2014 ወደ ስፍራው አቅንቶ ያየውን ሲጽፍ፣ ‹‹ በዚህ የባህር ኢንዱስትሪ ምንም ህግ የለም:: ስፍራው እጅግ አስፈሪ ነው:: ሰዎቹ መስራት የማይችሉ ከሆነ እንኳ ‹ጠቃሚ አይደሉም› በሚል አዘዋዋሪዎቹ ወደ መጡበት አይመልሷቸውም፤ይልቁንስ ይገሏቸዋል እነጂ::›› ሲል ስለሁኔታው ገልጿል::

የዕፁ ፋብሪካመረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ቁጥራቸው

ከ10 ሺህ እስከ 13 ሺህ የሚደርሱ የዘመናዊ ባርነት ተጠቂዎች በእንግሊዝ ይገኛሉ:: አብዛኞቹም ከአልባንያ፣ ከናይጀሪያ፣ ከቬትናም እና ከሮማንያ የመጡ ናቸው:: ሦስት ሺህ የሚደርሱ የቬትናም ህጻናት ደግሞ ብቻቸውን በእንግሊዝ የካናቢስ እርሻ ላይ በጉልበት ስራ ያሳልፋሉ::

አብዛኞቹ ተጠቂዎች እንደሚናገሩት ከሆነ ለቤተሰቦቻቸው ደህንነት ሲሉ ከእርሻው አምልጠው

ለመሄድ አይፈልጉም:: ከተጠቂዎች አንዱ የሆነው ላም የ16 ዓመት ታዳጊ እያለ ነው ወደ እንግሊዝ የመጣው:: ያኔ እርሱ ወደ እንግሊዝ ሲመጣ ለቤተሰቦቹ የተሻለ ገንዘብ ለመላክ ተስፋ አድርጎ ነው:: ነገር ግን ያሰበው ሳይሆን ራሱን በተንጣለለው የካናቢስ እርሻ ውስጥ እንዳገኘው ለቢቢሲ ተናግሯል:: ‹‹አስታውሳለሁ፤ የሆነ ሰው ወደኔ መጥቶ ከዚህ እርሻ ለማምለጥ ብሞክር እንደሚደበድበኝ እና እንደሚገለኝ ያስጠነቀቀኝን::››

ላም እርሱ ይሰራበት የነበረውን የእርሻ ቦታ ፖሊሶች ከደረሱበት በኋላ በአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ተከሶ ለፍርድ ቀርቦ ነበር:: ነገር ግን በህገወጥ ህፃናት ዝውውር የምክር ማዕከል እርዳታ አሁን በነጻ ተለቋል::

የወሲብ ባርነትዘመናዊ ባርነት ከሚከናወንባቸው ትልቁ

የዓለማችን ህገወጥ ንግድ መካከል ነው ወሲብ:: የዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት መረጃ እንደሚጠቁመው ከሆነ በመላው ዓለም አራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዜጎች በወሲብ ባርነት ውስጥ ይኖራሉ:: ሻንድራ ዎዎሩንቱ በአሜሪካ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን በብርቱ ከሚታገሉ የሰብዓዊ መብት አቀንቃኞች መካከል አንዷ ናት:: እርሷ በፈረንጆቹ 2001 በአሜሪካ የወሲብ ባርነት ሰለባ ነበረች::

ወደ ገጽ 38 ዞሯል

Page 33: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 33በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ሰዎች ምን ይላሉ?

አብርሃም በዕውቀት

የግንቦት 20 በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀውን የባሕርዳር የንግድ ትርኢትና ኤግዚቪሽን አስመልክቶ ተሳታፊዎች ምን አሉ?

ወ/ሪት ሐዋ አያሌው ከደሴ የጌጠኛ ድንጋይ መቁረጫ

ፈጠራ ባለቤት

መርጌታ ታዬ ተስፋሁንከደቅ ደሴት ጎብኝ

አቶ መኳንንት አሰፋ ከባሕር ዳር የፈሳሽ ሳሙና አምራች አቶ ይመስገን ታደለ

ከደብረማርቆስ የፒቢሲ ዋንጫዎች አምራች

አባ ኃይለየሱስ ኪዳነማርያምከካሪማ መድኃኒዓለም ቅድስት ወለተጴጥሮስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም የአልባሳት ምርቶች ሻጭ

በላይ ዘለቀ ክፍለ ከተማ በሳሙና ማምረት ሥራ የተሰማራን ወጣቶች ነን:: ይህ የንግድ ትርኢትና ኤግዚቪሽን ለኛ ትልቅ ዕድል ነው:: ምርታችንን ለተጠቃሚዎች በሚገባ አስተዋውቀንበታል፤ በእርግጥ በባሕርዳር ከተማ በርካታ ደንበኞች ስላሉን የገበያ ችግርም የለብንም:: ቢሆንም ግን ወደፊት ምርታችንን የማሳደግ

ሐሳብ ስላለን እና ከባሕርዳር ውጭም የመጡ ተሳታፊዎች ስላሉ ምርታችንን በደንብ እንድናስተዋውቅ በር ከፍቶልናል::

ከዚህ ቀደም በነበሩ ባዛሮችም ምርታችን ስናስተዋውቅ በርካታ ደንበኞችን ማግኘት ችለናል፤ መኪና አጣቢዎች፣ ሆቴሎችና ሌሎችም ድርጅቶች ደንበኞቻችን ሆነዋል:: የአሁኑም ሰፊ ዕድል ይፈጥርልናል ብለን አስበናል፤ ከብዙዎች ጋርም ተዋውቀናል:: እኛም ምርታችንን ለማስተዋዎቅ ስንል ዋጋ በጣም ቀንሰን እየሸጥን ነው፤ ፈሳሽ ሳሙና በሊትር 13 ብር ነው የምንሸጠው፤ በመደበኛ ገበያ ግን በሊትር ከ25 እስከ 30 ብር እንሸጣለን ወደ ምርት ከገባን ገና ስድስት ወራችን ቢሆንም ጥሩ ተቀባይነት አለን::

እኔና ሦስት ጓደኞቼ ከቀንድ ይመረት የነበረውን ዋንጫ የሚተካ ዋንጫ ከፕላስቲክ እያመረትን ነው:: በደብረማርቆስና አካባቢው ምርታችን በጣም ተፈላጊ ነው:: ይህ የንግድ ትርኢትና ኤግዚቪሽን ደግሞ የበለጠ ምርታችን አስተዋውቆልናል:: በርካታ የባሕርዳር እና አካባቢው ነዋሪዎች መጥተው ምርቶቻችንን ገዝተዋል፤ ለተለያዩ ማኅበራትና ዕድሮች በብዛት እንድናቀርብለቸውም እየጠየቁን ነው::

ከደብረማርቆስ አካባቢ ውጭ ምርቶቻችን በብዛት ማቅረብ የቻልነው ደብረኤልያስ ወረዳ አካባቢ ነበር:: ደብረኤልያስ አካባቢ በወር እስከ 2000 ፍሬ ዋጫዎችን እንሸጥ ነበር፤ አሁን ግን በባሕርዳር አካባቢም ሰፊ ተጠቃሚ እንዳለ በዚሁ አጋጣሚ አይተናል:: እንዲህ ያሉ መድረኮች በተለያዩ ከተሞች ቢዘጋጁ የበለጠ የገበያ ዕድል የሚፈጥሩ እንደሆነ ተረድቻለሁ፤ ዕድሉን በማግኘታችንም በእኛ በኩል ደስተኞች ነን::

የንግድ ትርኢትና ኤግዚቪሽኑ ላይ ለመሳተፍ የመጣሁት ከደሴ ወ/ሮ ስህን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ነው:: እኔ ያቀረብኩት ፈጠራ የጌጠኛ ድንጋይ ጠረባን ከሰው እጅና ጉልበት በተሻለ አስተካክሎ ለመጥረብ የሚያስችል ነው:: የድንጋይ ብክነትንና አላስፈላጊ ድካምን ይቀንሳል፤ በቀን እስከ 400 ጥርብ ጌጠኛ ድንጋዮችን ያመርታል:: የሚንቀሳቀሰውም በኤሌክትሪክ ጉልበት ሲሆን ሁለት የፈረስ ጉልበት ያህል አቅም አለው::

በመምጣቴም በብዙ መልኩ ተጠቃሚ ሆኛለሁ:: ቀዳሚው ነገር የፈጠራ ሥራዬ ላይ የተለያዩ ሰዎችን አስተያዬት መቀበሌና ፈጠራዬም

ይህ የንግድ ትርኢትና ኤግዚቪሽን ለሻጭም ለሸማችም በጣም ጥሩ ዕድል የፈጠረ ነው:: የቀረቡትን ፈጠራዎችና ሸቀጦች ተዘዋውሬ ተመልክቻለሁ:: ብዙዎቹ ፈጠራዎች የሚያጓጉ ናቸው:: በተለያዩ ቅርጾች የተሠሩ አልጋዎች፣ በገዳማት አካባቢ በእጅ የሚሠሩ አልባሳት፣ ዘመናዊ የሆኑ የብሎኬት ማምረቻዎች፣ የተለያዩ የልብስና ገላ ፈሳሽ ሳሙናዎች፣ ለመስኖ አገልግሎት የሚውሉ ዘመናዊ የውኃ መግፊያዎች፣ … ብቻ በርካታ አዳዲስ ነገሮችን አይቸበታለሁ::

በተለይ የውኃ መግፊያው ለእኔ በጣም ጥሩ ፈጠራ ሆኖ ስላገኘሁትና በአካባቢያችንም ውኃ ወደ ደሴቱ ለማውጣት አስፈላጊ ስለሆነ በቀጣይ ለመግዛት አስቤያለሁ:: በዋንጫ ቅርፅ የተሠሩት የፕላስቲክ መጠጫዎችም በጣም ጥሩ ናቸው:: እነሱንም ለመግዛት አስቤያለሁ:: ወደፊትም እንዲህ ዓይነት አዳዲስ ፈጠራዎችን የምናውቅባቸው መድረኮች ቢበዙ ጥሩ ነው::

የግንቦት 20ን 25ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው የንግድ ትርኢትና ኤግዚቪሽን ለእኛ በጣም ጥሩ ነው:: በዚህ ዓይነቱ መድረክ ብዙ የምትሸጥበት ሳይሆን ብዙ ደምበኛ የምታፈራበት ስለሆነ ጥሩ የመተዋወቂያ ዕድል ፈጥሮልናል:: በገዳሙ መነኮሳት የሚመረቱ ምርቶችን ለተጠቃሚዎች በሚገባ አስተዋውቀንበታል፤ በሽያጭ ደረጃም ጥሩ መሸጥ ችለናል:: ፎጣ፣ የአንገት

ፎጣ፣ ሹራብ፣ የአልጋ ልብስና ሌሎችንም በእጅ ሥራና በማሽን እያመረትን ለገበያ እያቀረብን ነው:: አዲስ ወደ

ማምረት የገባን ስለሆነ ከደንበኞች ብዙ ማበረታቻ አግኝተናል:: ከሌሎች አቅራቢዎችም

የአመራረትና የሽያጭ ስልታቸውን ልምድ አግኝተናል፤ በአጠቃላይ ይህ ዕድል መፈጠሩ ለእኛ መልካም አጋጣሚ ነው::

ተቀባይነት ማግኘቱን ይበልጥ ያረጋገጥኩበት መሆኑ ነው:: ይህም በፍጥነት የፈጠራ ሥራዬን ወደ ሥራ እንዳስገባና የገበያ ችግርም እንዳይገጥመኝ በር ይከፍትልኛል ብዬ እገምታለሁ::

ከሌሎች አካባቢዎች ከመጡ የፈጠራ ሥራዎችም ብዙ ትምህርት አግኝቻለሁ:: በየአካባቢያችን ያሉ ችግሮችን ለመፍታት

አካባቢያዊ ፈጠራዎችን ማበረታታት ተገቢ እንደሆነና ትኩረትም እንደተሰጠው የተመለከትኩበት ነው::

በንግድ ትርኢትና ኤግዚቪሽኑ ብዙ ፈጠራዎችን አይቻለሁ:: በዚህ መልኩ ለዕይታ የቀረቡ ፈጠራዎች ደግሞ ወደ ሕብረተሰቡ የመግባትና ገበያ የማግኜት ዕድላቸው ሰፊ ነው::

Page 34: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 34

ፈጣኖቹ...ከገፅ 10 የዞረ

ከገፅ 23 የዞረ

ለእናት እና ልጅ...የመለዋወጥ ደረጃ ላይ ላያደርስ ይችላል የሚለው ጉዳይ አከራካሪ ሆነ::

ሌላውና ከእነዚህ ከሁለቱ ጉዳዮች ውጪ የሆነውና በእንግሊዞች ዘንድ የተገነዘቡት ጉዳይ ደግሞ በወቅቱ ሶቬት ህብረት በሳተላይቶቿ አማካኝነት የምታጠራቅመውን መረጃ ለአርጀንቲና ብታቀብል በአርጀንቲና የጦር ሀይል ውስጥ የሚገኙ ፀረ ኮሚኒስት የጦር መኮንኖች መረጃዎቹን ሁሉ ለአሜሪካ ሊያቀብሉ ይችላሉ:: ይህ መሆኑ ደግሞ የሶቬትን የሳታላይት ምስጢራዊ መረጃዎች ለማጥናት አሜሪካ ስለሚመቻት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል:: ስለሆነም ሶቬት ህብረት እጅግ ከባድ ያልሆኑ መረጃዎችን ብቻ ለአርጀንቲና ልትሰጥ ትችላለች ተብሎ ነው የታመነው::

ከዚህ ሌላ በግልጽ የታወቀው ነገር ግን ሶቬት ህብረት ስለ ሁለቱ አገራት ማለትም ስለ እንግሊዝና አርጀንቲና ውዝግብ ጠቅላላ ሁኔታ ለማወቅ የሚስችላትን ክትትል /የሳተላይት ስለላ/ እያደረገች መሆኗ ነው:: ለዚህም አገልግሎት የመደበቻትን “ፒሪሞሪ” የተባለች የስለላ ማጠናከሪያ መርከቧን በእስኮትላንድና አየርላንድ መካከል አቁማ የእንግሊዝና የአሜሪካ ጠላት የኒዩክሌር ተሸካሚ መርከቦችን እንቅስቃሴ መከታተል ጀመረች:: ይህችን መርከብ ክትትል ስታደርግ “ካንቤራ” የተባለችው የእንግሊዝ ጦር መርከብ ወደ ፎክ ላንድ ለመሄድ ስትነሳ ተመልክታታለች:: ይህችው በመጠኗ

አነስተኛ የሆነችው መርከብ በራዳርና በሬዲዮ ሙያዎች የላቀ ችሎታ የነበራቸው 117 ሰራተኞችም ነበሯት::

ሶቬቶች ከዚህ ሌላ ቲዩ 142 ቢአር የተባለ የባህር ኃይል አሳሽ አውሮፕላንም በዚሁ መስመር ላይ እንዲሰማራ እና መረጃ እንዲሰባሰብ አድርገዋል:: ይሄው መረጃ ሰብሳቢ ሰላይ አውሮፕላን ደግሞ ከሰባት ሺህ ማይል ርቀት ላይ ሆኖ በረቀቁ የኤሌከትሮኒክስ መሳሪያዎች አማካኝነት ማንኛውንም እንቅስቃሴ እንዲከታተል የተመደበ ነበር:: መነሻው አንጐላ ውስጥ ለዋንዳ አጠገብ ከሚገኘው የኩባ አየር ሀይል ጦር ሰፈር ነበር:: አውሮፕላኑ ታዲያ በተገጠሙለት ዘመናዊ መሳሪያዎቹ አማካኝነት የእንግሊዝን የባህር ኃይል መርከቦች ብቻ ሳይሆን በሬዲዮ የሚያደርጉትን ንግግር ሁሉ መጥለፍ የሚቻል ነበር::

ሶቬቶች ምንም እንኳን ይህን ዘመናዊ አውሮፕላንም ሆነ መርከቧን ለስለላ ተግባር ብታሰማራም እንግሊዝ ባወጀችው የጦር ክልል መስመር ውስጥ ማስገባትና ውዝግብ መፍጠር አልፈለጉም:: ስለሆነም በእነዚህ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘመናዊ መሳሪያዎች ምትክ ሳተላይቶቻቸው መረጃውን እንዲሰበሰቡ መረጡ:: ለዚህም የአርጀንቲና ጦር የፎክ ላንድን ደሴት ከመውረሩ ከሁለት ቀናት በፊት ስምንት የሚደርሱ ኮስሞ ሳተላይቶችን ልታስወነጭፍ ችላለች::

ይቀጥላል

አሁን ግን ሁሉም እናቶች ወደ ጤና ጣቢያ ሄደው በሠላም ተገላግለው እናትና ልጅ በሠላም ወደ ቤታቸው እንደሚመለሡ እና ሀዘን በወሊድ ሳቢያ መቅረቱን አወጉኝ:: እሳቸው አረርቲ ጤና ጣቢያ በቆዩበት 16 ቀን ውስጥ ከ20 በላይ እናቶች እየወለዱ በሠላም ወደ ቤታቸው መሄዳቸውንና አንድም እናት ሆነች ጨቅላ ሞተች ሲባል እንዳልሠሙ ይናገራሉ::

እነዚህ እናቶች በጤና ጣቢያው በተዘጋጀላቸው ፍራሽ ቤታቸው ያሉ እስኪመስላቸው የሚተኙበትና የሚያርፉበት፣ ቁርስ፣ ምሳ፣ እራት በየጊዜው እየተዘጋጀ የሚያቀርብላቸው ከሌላ አካል ባገኙት ገንዘብ ሳይሆን ከራሳቸው ወጪ ባደረጉት ገንዘብና

የከተማ ነዋሪው ደግሞ 50 ፣ 50 ብር ተጠይቆ ከህብረተሠቡ በተገኘ ገንዘብ ተሠርቶ ህብረተሠቡን እያገለግለ ያለ የእናቶች ማቆያ ነው ይላሉ::

የተሠራው ቤት ሻወር እና መፀዳጃ ቤት የተዘጋጀለት በመሆኑ ንጽህናቸውን ጠብቀው ለመቆየት አመቺ ቦታ ነው:: ወደፊትም አልጋ ለማሠራት ዕቅድ መያዛቸውን አቶ ዳምኗል አጫውተውናል::

በአረርቲ ጤና ጣቢያ አዋላጅ ነርስ የሆነችው ሲስተር አስናቁ ቶሎ ለእናቶች ማቆያ ማሠሪያ በየገጠሩ እየሄደች “አንድ ብር ለአንድ እናት” በሚል አርሶ አደሩን ገንዘብ እህል እንዲያዋጡ በማድረግ ሠርታለች::

በጤና ጣቢያውም ለነፍሰጡሮች የሚሆን ዱቄት፣ እህል፣… በመጋዘን እንዳለና በየጊዜው እየተዘጋጀ እየቀረበላቸው መሆኑን ገልፃ እናቶች ለመውለድ ምልክት ሲያዩ ወደ ጤና ጣቢያ መጥተው ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው ከተገላገሉ በኋላ 24 ሰአት ያህል ቆይተው ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ ብላለች::

በአረርቲ ጤና ጣቢያ በህብረተሠቡ ወጪ የተገነባው የእናቶች ማቆያ ክፈልና እንክብካቤ በሌሎች አካባቢዎችም በስፋት ተጠናክሮ ቢቀጥል መልካም ነው እንላለን::

እህል ነው:: ለዚህም ማረጋገጫ የሆኑኝ ወ/ሮ ሂሩት አለሙ ናቸው:: “ለነፍሰጡር እናቶች ማቆያ ቤት ሊሠራ ነው ገንዘብ አዋጡ” ተብለው ሲጠየቁ እሳቸውም አራት ብር እና ሁለት ኪሎ ጤፍ ከጐተራቸው አፍሠው ሰጥተዋል::

እናም መልካም ማድረግ ለራስ ነውና ዛሬ ይሄው እሳቸው ላሳዩት መልካም ምግባር መልካም መስተንግዶ እንዲያገኙ ሆነዋል:: በዚህ ለነፍሰጡሮች ማቆያ ክፍል ግንባታና በጤና ጣቢያ ቆይታቸው ለሻይ ቡና ብሎም ለምግብ ወጪ እንዲሆናቸው ሁሉም የወረዳው ነዋሪ ተሣትፎ አድርጓል:: ከወ/ሮ ሂሩት ጋር ወደ አረርቲ ጤና ጣቢያው የመጣው የወ/ሮ ሂሩት ታላቅ ወንድም አቶ ብርሀኑ አለሙ ገንዘብም እህልም ማዋጣቻቸውን ገልፀው በጤና ጣቢያው ለነፍሠጡሮችም ሆነ ለአስተማሚዎች የሚደረገው እንክብካቤ እንዳስደሰታቸው ይናገራሉ::

በጤና ጣቢያው ለነፍሠጡር እናቶች ምግብ፣ ሻይ፣ ቡና፣… በማዘጋጀት እንክብካቤ የምታደርገው ትዕግስት መሸሻ ተቀጥራ መስራት ከጀመረች አመት እንደሆናት ትናገራለች:: ለነፍሠጡሮችም ጠዋት ቁርሳቸውን ዳቦ በመኮረኒ፣ ሩዝ ከሻይ ጋር ታቀርባለች:: ምሳና እራት እንጀራ በሽሮ፣ ከክክ ወይም ከድንች ወጥ ጋር ትሠራላቸዋለች:: መክሠስ ደግሞ ጥራጥሬ በመቁላት ወይም በመቀቀል ታቀርባለች:: ቡና እያፈላች፣ ገንፎ እያገነፋች ሁሉ እንደምታቀርብ አጫወተችን:: ከዚህ ውጪ

የእናቶችን አንሶላ በየጊዜው እያጠበች ንጽህናቸውን በመጠበቅ ድጋፍ ታደርጋለች::

በወረዳው አረርቲ፣ ባልጪ፣ ቦሎስላሴ፣ ድሬ እና ክርስቶስ ሠምራ የተባሉ አምስት ጤና ጣቢያዎች መኖራቸውን የገለፁልኝ ደግሞ የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የእናቶችና የወጣቶች ስነተዋልዶ ባለሙያ አቶ ዳምኗል ተገኘወርቅ ናቸው:: በወረዳው በሚገኙ አምስቱም ጤና ጣቢያዎች ልክ እንደ አረርቲ ጤና ጣቢያ ሁሉ ባለ አራት ክፍል የእናቶች ማቆያ መዘጋጀቱንና እናቶች በቆይታቸው ሁሉንም ነገር ተጠቃሚ ሆነው እንደሚቆዩ ገልፀውልኛል::

እያንዳንዱ አርሶ አደር አራት ብርና ሁለት ኪሎ ጤፍ፣ ባቄላ፣ ስንዴ፣ ሽምብራ፣… ቤት ያፈራውን ተጠይቀው ሁሉም ደስተኛ ሆነው አዋጥተዋል::

ለጋዜጣችን አስተያየት

ካላችሁ በጽሁፍ መልዕክት(sms) ab. በማስቀደም 8200 ላኩልን

በህብረተሠቡ ተሣትፎ የተሠራው የአረርቲ ጤና ጣቢያ የነፍሰ ጡሮች ማቆያ ክፍል

Page 35: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 35በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ማስታወቂያ

የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያበወረታ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማትና ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ

ቁጥር 721/2004 አንቅጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በ2008 በጀት ዓመት 4ኛ ዙር ጨረታ ለንግድ አገልግሎት

የሚውሉ 10 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም

1. መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ጨረታው በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ

ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነዱን

የማይመለስ ብር 300.00 በመክፈል ቢሮ ቁጥር 04 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡

2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ

2፡3ዐ እስከ ምሽቱ 11፡ዐዐ ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 04 ይሆናል፡፡

3. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡ዐዐ ይሆናል፡፡

4. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በ3፡ዐዐ ሁሉም ተጫራቾች

ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበትን ቦታ በተመለከተ በውስጥ

ማስታወቂያ የሚገልፅ ይሆናል፡፡

5. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ ማግኘት ይቻላል፡፡

6. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የወረታ ከተ/አስ/ኢ/ልማት እና ከተ/አገ/ጽ/ቤት

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያየአብክመ አመራር አካዳሚ ለ2009 በጀት ዓመት በግቢው ውስጥ ለሚሰጡ የተለያዩ የአመራር ስልጠናዎች

አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የከብትና የበግ ስጋ፣ ሎት 2 አትክልትና ፍራፍሬ፣ ሎት 3 እንቁላል ፣ሎት 4 ዳቦ፣

ሎት 5 የባልትና ውጤቶች ፣ሎት 6 የታሸገ የማዕድን ውሃ ፣ሎት 7 በርበሬና ቅመማ ቅመም፣ ሎት 8 ሸቀጣ ሸቀጥ

፣ሎት 9 የማገዶ እንጨት፣ ሎት 10 ጤፍ ፣ሎት 11 የምግብ ቤትና የመስተንግዶ እቃዎች ፣ሎት 12 የጽዳት እቃዎች፣

ሎት 13 ቅቤ ፣ ሎት 14 የወፍጮ አገልግሎት እስከ ታህሣስ 30/2009 ዓ/ም ድረስ በሚቆይ ውል በግልጽ ጨረታ

በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር

የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ ቲን/ ያላቸው፣

3. የግዥው መጠን 50 ሺህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ

መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን

ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 20.00 ብር በመክፈል በአመራር አካዳሚው ግቢ ቢሮ

ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡

6. የሚገዙ የእቃዎችን /አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ከጨረታ ሰነዱ

ማግኘት ይቻላል፡፡

7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ግንቦት 29/2008

ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በአመራር አካዳሚው የግዥ እና ፋይናንስ

አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ብር 1 በመቶ በባንክ

በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ

ገንዘብ በአመራር አካዳሚ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በአመራር

አካዳሚው ግዥ እና ፋይናንስ አገልግሎት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ

ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከግንቦት 29/2008 እስከ ሰኔ 14/2008 ዓ/ም 4፡ዐዐ ድረስ ማስገባት

ይኖርባቸዋል፡፡

10. የጨረታ ሣጥኑ ሰኔ 14/2008 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡3ዐ ተጫራቾች /ህጋዊ

ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

11. የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ

ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

12. አመራር አካዳሚው ከሎት 1-13 ድረስ ያሉትን የሚወዳደረው በነጠላ ዋጋ ሲሆን ሎት 14 /የወፍጮ

አገልግሉትን / የሚያወዳድረው በድምር/ በጠቅላላ ዋጋ ነው፡፡

13. አመራር አካዳሚው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14. በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡

15. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል

በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582262360 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ አመራር አካዳሚ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያየአብክመ አመራር አካዳሚ በአካዳሚው ውስጥ ያለውን አስተዳደር ህንፃውን፣ መማሪያና መወያያ

ክፍሎችን መሰብሰቢያ አዳራሾችን፣ መኝታ ቤቶችን፣ ቤተ-መጽሐፍቱን እና በተጨማሪ በግቢ

ውስጥ የተሽከርካሪና የእግር መንገዶችን ኮሪደሮችንና በረንዳዎችን እንዲሁም ሁሉንም በአመራር

አካዳሚው የሚገኙ መፀዳጃ ቤቶችን ለ2009 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት

ለአሸናፊዎች በመስጠት ማፀዳት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉና መስፈርቱን

የሚያሟሉ ተጫራቾች፣ በአመራር አካዳሚው ግቢ በመገኘት የሚፀዱትን ክፍሎችን አጠቃላይ

የግቢውን ሁኔታ በአካል ካዩና ከገመገሙ በኋላ ከግንቦት 29/2008 ዓ/ም እስከ ሰኔ 14/2008 ዓ/ም

ድረስ የጨረታ ሰነድ በመግዛት ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፣

3. የግዥው መጠን 50 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ

መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን

ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 20.00 ብር በመክፈል በአመራር አካዳሚ ግቢ የግዥ

እና ፋይናንስ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡

6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ለያይቶ

በጥንቃቄ በማሸግ በፖስታዎች ላይ ቴክኒካል፣ ፋይናንሻል፣ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘቡን

በአመራር አካዳሚው የገቢ ደረሰኝ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል ፣ ፋይናንሻል ፣ ሲፒኦ

ብሎ በመፃፍና በአንድ ትልቅ ፖስታ በማስገባት በአመራር አካዳሚው ግዥ እና ፋይናንስ

አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከግንቦት

29/2008 ዓ/ም እስከ ሰኔ 14/2008 ዓ/ም 11፡ዐዐ ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 1

በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ

ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በአመራር አካዳሚ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፣

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአመራር አካዳሚው አዳራሽ

ሰኔ 14/2008 ዓ/ም በ11፡3ዐ ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን ሰኔ 15/2008 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡3ዐ

ይከፈታል፡፡

9. የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም

ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

10. ተጫራቾች አላስፈላጊ ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበትን ቅጽ ሞልተውና ፈርመው

ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር መመለስ አለባቸው፡፡

11. አመራር አካዳሚዉ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ

ነው፡፡

12. በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፣

13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ

በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582262360 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ አመራር አካዳሚ

የጨረታ ማስታወቂያየፍርድ ባለመብት ጋሻየ ካሣሁን የፍርድ ባለ እዳ አዲሱ አብየ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ

ክርክር ጉዳይ የባለእዳው ንብረት የሆነ በባለቤቱ ወ/ሮ መልሽው መንጌ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ኮድ

01-04146 አ/ማ የሆነው መኪና የግምቱ መነሻ ዋጋ ብር 43,768.18 /አርባ ሶስት ሺህ ሰባት መቶ

ስልሣ ስምንት ብር ከ18/100 ሣንቲም/ ሆኖ ሰኔ 25 ቀን 2008 ዓ/ም ከጠዋቱ ከ3፡ዐዐ እስከ 6፡ዐዐ

ባለው ጊዜ ውስጥ በባ/ዳር ከተማ አስ/በ2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በግልጽ ጨረታ

ይሸጣል፡፡ ስለዚህ ይህንን መኪና በጨረታ ለመግዛት የምትፈልጉ ሁሉ ከላይ በተገለፀው ቀንና ቦታ

በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የጨረታው አሸናፊው እንደታወቀ ከጨረታው

ገንዘብ ውስጥ ¼ ኛውን በሞ/85 የሚያስይዙ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

የባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍ/ፍ/ቤት

Page 36: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 36

የሀሩሩ ...ከገፅ 27 የዞረ

ከገፅ 11 የዞረ

ፀደቀ...በላይ አላስጨንቀውም፤ እውነቱን ለማወቅ ሌላ መላ ብመታ ይሻለኛል” ብለው

“ደርሷል ልዠዋ! ተቀመጥና ተቋደስ!” አሉት:: “ሰነፍ!” በመባሏ አሁንም ንዴቷ ያልበረደላት እህቱ ስመኝ ኮስተር እንዳለች ቁርሱን አቀራርባለት መጽሀፏን ከማንበቢያ ክፍል አመጣችና እናቷ አጠገብ ቁጭ ብላ ታነብ ጀመር:: ፀደቀ እህቱ ያለወትሮዋ መጽሀፍ ማንበብ በመጀመሯ “ አስደናቂ ነገር፤ ደስ የሚል ለውጥ!” ሲል አሰበ:: ውስጡ በሀሴት ሲጥለቀለቅ ታወቀው:: እንዲህ በደስታ እንደተዋጠ አንዴ እናቱን፣ አንዴ እህቱን እያስተዋለ ቁርሱን በልቶ ጨረሰና ሁለቱንም በየተራ ስሞ “ደህና ዋሉ!” ብሎ፡-

አእዋፍ በሰማይ ሰምተው ሲዘምሩአራዊት በጫካ በየጢሻው ዱሩፍጥረታት ተገንዝበው የተፈጥሮን ምስጢርእያሉ ዘመሩ አረንጓዴ ምድር::…………..ዛፉ ዛፉ እስትንፋሴልጠብቅህ እንደራሴ::ዛፉ ዛፉ አረንጓዴአንተ ባትኖር እኛስ አለን እንዴ?!…

የሚለውን እጅግ አብዝቶ የሚወደውን ዘፈን በተንቀሳቃሽ ስልኩ እያዳመጠ ከቤት ወጣ::

ወይዘሮ አስማሩ ልጃቸው የሚሄድበትን፣ ደግሞም የሚሠራውን ለማወቅ ይረዳኛል በሚል የመቱትን መላ ሲያሰላስሉ ስለነበር የልጃቸው እግር ከቤት እንደወጣ፡-

“ልዠ ሳያይሽ ራቅ ብለሽ እየተከተልሽ የሚኸድበትን፣ የሚገባ የሚወጣበትን እይው! አደራ ልዠ!... ደከመኝ ብለሽ መድረሻውን ሳታይ እንዳትመለሽ!” አሏት ስመኝን::

“ስከተለው ድንገት ዞር ብሎ ቢያየኝስ?...” በሚል ትንሽ ካቅማማች በኋላ እሷም የሚሄድበትን የማወቅ ከፍተኛ ፍላጎት ስለነበራት “እሺ!” ብላ ተከተለችው::

ፀደቀ ባከል ገብርኤል በተለምዶ ታናሽ ቤት ከሚባለው ሰፈር ከሚገኘው ቤቱ ወጥቶ ሙዚቃውን ከፍ አድርጎ እንደከፈተ ስልኩን ከጆሮው አስጠግቶ እያዳመጠ አብሮ እየዘፈነ በቀጥታ ያመራው ወደ ፍኖተ ሰላም ነበር:: ስመኝ ጉዞዋን በእሱ ፍጥነት እየመጠነች ተከተለችው:: ቀጥ ብሎ ወደ ሰሜን ወጥቶ ወደ ወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት አመራ:: በዛፍ ተከልላ ወደ ጽህፈት ቤቱ ሲገባ ተመለከተችው::

* * *ከሰላሳ ደቂቃ ቆይታ በኋላ ካንድ ከምታውቀው

የግብርና ልማት ጽህፈት ቤት ሠራተኛ ጋር ዶማ፣ አካፋ፣ በላስቲክ የተጠቀለለ ነገር ተሸክሞ ተንቀሳቃሽ ስልኩን ከጆሮው አስጠግቶ እንደያዘ ሲወጣ አየችው::

እንዳትታይ በዛፉ ይበልጥ እየተከለለች እያለ ዘበኛው “ጐበዞች! እይዟችሁ! በርቱ! ፀደቀ! እሰይ!... “ ሲሉ ሰማች:: የምን መቆፈሪያና አካፋ ነው? የተሸከሙትስ ምንድን ነው? ዘበኛው ደግሞ የሚያበረታታቸው እሱም በድብቅ በሚከናወነው ሥራ ተጋሪ ሆኖ ነው?...” እያለች አሰላሰለች:: ወንድሟና የግብርና ባለሙያው ከግቢው ወጥተው ወደ ሰሜን አቅጣጫ ጉዞ ሲጀምሩ፡- “ዘበኛውን ለምን አልጠይቀውም? እንዲህ ደጋግሞ ‘በርቱ! አይዟችሁ!’ የሚለው በምስጢር ስለሚከናወነው አንዳች ተግባር የሚያውቀው ነገር ቢኖረው ነው” ስትል አሰበች፤ አንዴ ዘበኛውን ፤ አንዴ ወንድሟንና አብሮት እየተጓዘ ያለውን ባለሙያ በርቀት እየተመለከተች:: ወዲያው “ወንድሜ ያልነገረኝን ምስጢር ይሄ የማያውቀኝ ዘበኛ ሊነግረኝ እንዴት ፈቃደኛ ይሆናል? ከንቱ ሀሣብ ነው” አለችና ወንድሟንና ባለሙያውን መከተል መረጠች::

ወንድሟና ባለሙያው ወደ ሰሜን ለአስር ደቂቃ ያህል ከተጓዙ በኋላ ደቢስ ጊዮርጊስ እንዲሁም አባጠር ማርያም መገንጠያ ላይ ሲደርሱ የደቢሱን መገንጠያ ወደ ግራ ትተው የአባጠርን መንገድ ተያያዙት::

ስመኝ ሁለቱ ምስጢረኞች ግብርና ጽህፈት

ቤቱ አካባቢ ቆማ በነበረችበት ጊዜ ርቀዋት ስለነበር ከዕይታዋ እንዳይሰወሩ ሮጥ ሮጥ ማለት ግድ ሆነባት:: ሆኖም መንገዱ ዳገት ቢጤ ስለነበር ትንፋሽ አጠራት፤ ጉልበቷ ዛለባት:: ድካሟ እንዲህ ሲፀናባት መቀመጥ አሰኛት:: ነገር ግን፤ የእናቷ የአደራ እና የተማፅኖ ቃል ታወሳት፤ “… አደራ ልዠ!.. ደከመኝ ብለሽ መድረሻውን ሳታይ እንዳትመለሽ!...” ሲሉ ያስጠነቀቋት መልሶ መላልሶ አቃጨለባት::

ጥርሷን ነክሳ፣ ያለች የሌለች አቅሟን አጠራቅማ ተከተለቻቸው:: ሆኖም ዳገቱን እንደምንም ጥራ ተጣጥራ ከወጣች በኋላ መቀጠል ተሳናት:: በመሆኑም ከዳገቱ ደረት ላይ ሆኖ አምስት ኪሎ ሜትር ያህል ርቆ እስከሚገኘው ኩንቻት ተራራ ድረስ በርቀት ማየት ስለሚቻል ቁጭ ብላ መድረሻቸውን መከታተሉን መረጠች፤ መቼም ርቀው ቢሄዱ ከኩንቻት ተራራ አያልፉም፤ ብላ በማሰብ::

ወንድሟና ባለሙያው የአባጠር ማርያምን መንገድ ይዘው ቁልቁል ከወረዱ በኋላ ለአስር ደቂቃ ያህል ካይኗ ተሰወሩባት:: ከማርያም ቤተ ክርስቲያን በግራ ባለው መንገድ ከሄዱ ስለማይታዩዋት ስጋት ገብቷት ስትንቆራጠጥ የቀኙን መንገድ ይዘው ኖሮ ከቤተ ክርስቲያኗ አልፈው ወደ ኩንቻት አቅጣጫ ሲሄዱ በርቀት ተመለከተች:: ካይኗ ባለመሰወራቸው እየተደሰተች “ዓይንሽ ለቅጽበት ከእነሱ ከተነቀለ ብር ብለው ይጠፉብሻል” የተባለች ይመስል እንዳፈጠጠችባቸው ረዥሙን ሜዳ ጨርሰው ዙንኪት ሸጥ ደረሱ::

ሸጡ ውስጥ ገብተው ለሁለት ደቂቃ ያህል ጠፍተውባት ከቆዩ በኋላ ከሸጡ ባሻገር ያለውን ዳገት ሲወጡ ተመለከተች:: ወደ ቀኝ የሚወስደውን ተገንጣይ መንገድ ትተው ወደ ኩንቻት የሚያመራውን ዳገታማ መንገድ ይዘው ያዘግሙ ጀመር:: ዳገቱን እያዘገሙ ወጥተው አምባጓሮን ወደ ግራ ትተው የኩንቻትን ተራራ መውጣት ጀመሩ:: ተራራውንም አስተዋለችው፤ አረጓዴ ሸማ ለብሷል:: ዓይኖቿን ሳትነቅል በጥንቃቄ ስታያቸው ተሰወሩባት:: “ድንገት ገላጣ ቦታ ላይ ይታዩኝ ይሆናል” በሚል ተስፋ ዓይኖቿ እስኪቦዙ ድረስ ብታፈጥም ጫካው ውስጥ እንደገቡ ቀሩባት::

ተራራው ከሁለት ዓመት በፊት ከወንድሟ ጋር ቁርቢ ያሉ ዘመዶቿን ልትጠይቅ ስትሄድ በጣም የተራቆተ፣አለቱ ያገጠጠ ነበር:: ያኔ ወንድሟ “ይሄ ተራራ ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ነበር:: አጋሙን፣ ቀጋውን ፣ ዶቅማውን … እየለቀምን የምንበላበት፣ ዘንባባ ቆርጠን ሰሌን የምንሠራበት፣ ግርማ ሞገሱ የሚያስፈራ ቦታ ነበር:: ሆኖም ደኑ ተመንጥሮ እንደምታይው መሬቱ በሚያሳዝን ሁኔታ ተራቁቷል:: የዛሬ ሶስት ዓመት አካባቢ ተማሪ እያለሁ በትምህርት ቤት በያዝነው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በዘመቻ መጥተን ጽድ ተክለንበት ነበር:: ነገር ግን፣ ከተተከለ በኋላም የሚጠብቀውና የሚንከባከበው በማጣቱ ከተተከለው ብዙው ሳይፀደቅ ቀረ:: የፀደቀውም በሰውና በእንስሳት ኮቴ ደረቀ፣ በጣም ያሳዝናል!...” እያለ ስለተራራው መራቆት በቁጭት የነገራት ታሪክ ታወሳት::

“እንዴት ነው ነገሩ? ማን ዓለማው ታዲያ ?... ፀደቀና ባለሙያው ወደ ቦታው ዶማና አካፋ ይዘው የሄዱትስ ለምንድነው? የተሸከሙትስ?... እያለች ታሰላስል ገባች:: ወዲያው “ቦታው ድረስ ሂጅ ሂጅ፣ሄደሽ አረጋግጠሽ ነይ! ” የሚል አንዳች ብርቱ ስሜት አንዳች ታላቅ የማወቅ ጉጉት አደረባት:: ሳታስበው ጉልበቷ ጠነከረ:: ወኔዋ ሞላ፤ ሰነፍ አለመሆኗን ማሳየት እንዳለባት፣ ትክክለኛውን መረጃ ለእናቷ ማቀበል እንደሚገባት ስታስብ ቆየችና ተነስታ ወደ ኩንቻት ገሰገሰች::

* * *ኩንቻት ተራራ እንደደረሰች ያየችውን ፈፅሞ

ማመን ተሳናት:: ተደመመች:: ተራራው በተለያየ እፅዋት ተሸፍኗል:: ጽድ፣ ዋንዛ፣ ባህር ዛፍ፣ አጋም፣ ቀጋ፣ ሳር ምድሩን አልብሶታል:: ጫካው ፍርሀት አሳደረባትና ቆም አለች:: ብዙም ሳትቆይ ሁለት ዶማና አካፋ የያዙ አርሶ አደሮች ከአምባ ጓሮ ወጥተው ወደ ጫካው ሲያመሩ ዓይታ ተከተለቻቸው::

አርሶ አደሮቹ ሞቅ ያለ ወሬ ይዘዋል:: ለራሷም

ባስደነቃት ብርታት ተሞልታ ስትጓዝ ደጋግመው ስለዚህ ተራራ መለወጥ ያወራሉ:: የለውጡ ባለቤት የሆነን አንድ ሰው ደጋግመው ያመሰግናሉ:: በምስጋናቸው መሀል ድንገት የወንድሟን ስም የሰማች መሰላትና ይበልጥ ለማረጋገጥ ሮጥ ሮጥ ብላ ደረሰችባቸው::

“እንዴት ያለ የተባረከ ልዥ ነው! ከእኛ ከትልልቆቹ ልቆ የዛሬ ሁለት ዓመት ‘ይህን ተራራ ተባብረን እናልማው፤ ወደ ቀድሞው ጫካነቱ እንመልሰው’ ሲል አላመንነውም ነበር፤ የከተማ ቀጣፊ ብለንም ልንተናኮለው አስበን ነበር” አሉ፤ አንደኛው አርሶ አደር:: ሁለተኛውም ቀበል አድርገው፡-

“ያን ጊዜማ መች ሠማነው! ‘እናልማው፤ እንጠብቀው፤ እንንከባከበው’ እያለ ደጋግሞ ሲናገር ብዙዎቻችን በጥርጣሬ ዓይን እያየነው ‘የልጅ ነገር’ ብለን እንደቆመ ትተነው ነበር የሄድነው:: እሱ ግን ‘ለውጡን ሲያዩ ዛሬ የሄዱት ሁሉ በሄዱበት መንገድ ተመልሰው ይመጣሉ’ በማለት አስር የማይሞሉ ሰዎችን ይዞ ዙሪያውን አሳጥሮ፣ ይሄን ደን አስተከለ:: ተዚያ ሁላችንም ተባብረን መኮትኮት፣ማረም፣ውኃ ማጠጣት ሥራችን ሆነ:: ችግኙ እንደ ስሙ በሙሉ ፀደቀ:: እና ይኸው እንዲህ አረንጓዴ ሸማ ለበሰ:: የደረቀችው የዙንኪት ምንጭ መልሳ ፈለቀች:: አፈሩ ዳነ:: ቆይቶ ደግሞ ብዙ ጥቅም ይሰጠናል:: የተባረከ ልዥ! ዕድሜውን ያርዝመው! … “ አሉና በረዥሙ ተነፈሱ::

አርሶ አደሩ “ፀደቀ” ሲሉ ስመኝ ጣልቃ ገብታ “ፀደቀ ማን ?” ስትል ጠየቀች:: ሁለቱም ከኋላቸው ስትከተላቸው አላዩዋት ኖሮ ቆም ብለው“ ይቺ ደሞ የማናት ?” በሚል እያስተዋሏት፡-

“ፀደቀ ታየ” ሲሉ መለሱላት::“ወንድሜ ነው! እኔ ስመኝ ታየ እባላለሁ:: ሁለት

ዓመቱ ነው ይኸው በሌሊት ከቤት እየወጣ ጠፍቶ የሚውልብን:: ዛሬ ጠዋትም ከቤት ወጥቶ ዶማና አካፋ ይዞ ወደ ዚህ ሲመጣ ተከትየው!…” የደስታ ሲቃ አላናግራት አለ::

“በይ ነይ! ዓይንሽ ታምር ያያል:: ወንድምሽ አገሬውን አስተባብሮ በሠራው ድንቅ ሥራ የአገሬው ሰው የደን ልማቱን የእሱ የድካም ውጤት ነው ብሎ “ ኩንቻት ፀደቀ የደን ልማት ” ብሎ በስሙ በሰየመለት በዚህ ደን በሚገኝ ገላጣ ቦታ ዛሬም ከህዝቡ ጋር ችግኝ እየተከለ ታገኝዋለሽ፤ ወንድምሽ ሁሌም ከእኛ ጋር ነው” አሉ::

ሁለተኛው አርሶ አደርም ቀበል አድርገው፡-እ! ዋ!... ‘ስምን መልዐክ ያወጣዋል’ የሚባለው

ለካ እውነት ነው:: ፀደቀ እኛን አስተባብሮ ባደረገው ጥረት ይኸን ዛፍ እንዲህ አፀደቀ:: በእኛም ፀደቀብን፤ በእንስሳቱ በአእዋፉ ፀደቀበት” እያሉ ወደ ጫካው ሲጠጉ፡-

“ኩንቻት ፀደቀ የደን ልማት” የሚል በቆርቆሮ ላይ በአረንጓዴ ቀለም ተጽፎ የተተከለ ሰሌዳ ተመለከተች:: ወንድሟ ለሁለት ዓመታት በሌሊት ከቤቱ እየወጣ ሲሠራው የኖረውን ታላቅ የልማት ውጤት ስታይ፣ስሙ ከፍ ብሎ ተፅፎ ስትመለከት ሳታስበው የደስታ እንባ አነባች:: በዚህ ቅጽበት፡-

ዛፉ ዛፉ እስትንፋሴ ልጠብቅህ እንደራሴ

የሚለው ዜማ በጆሮዋ ጥልቅ አለ:: ጫካውን አቆራርጣ ድምጹን ወደ ሰማችበት ሮጠች::

ከተራራው አናት ገላጣ ስፍራ ላይ ወንድሟ አርሶ አደሮችን እያስተባበረ ችግኝ ሲተክል አየች:: ቆም ብላም አስተዋለችው:: ወንድሜ ለካ ለሁለት ዓመታት ታህል እንቅልፍህን አጥተህ እንዲህ ስትሰቃይ የኖርከው ይህን ለውጥ ለማምጣት ነው” እያለች ደኑን እንዳዲስ ታስተውል ጀመር::

በአገራችን እንዲሁም ባለማችን ከተሞች እንደምናስተውለው ባሁኑ ጊዜ ዘንባባ መናፈሻዎችን፣ መንገዶችን፣ መዝናኛ ቦታዎችን… ለማስዋብም አገልግሎት ላይ ሲውል ይስተዋላል::

በሮማዊያን ዘመን የዘንባባ ዝንጣፊ የድልና የአሸናፊነት ምሳሌ ተደርጐ ይወሰድ ነበር:: በመሆኑም ሮማውያን በጨዋታም ሆነ በጦርነት ጊዜ ድል አድርገው ለሚገቡ ወገኖቻቸው የዘንባባ ዝንጣፊ በሽልማት መልክ ያቀርቡላቸው እንደነበረ ታሪክ መዝግቦላቸዋል:: አይሁዳዊያንም በክብረ በዓላት ጊዜ የዘንባባ ዝንጣፊዎችን ይዘው አደባባይ ይወጡ ነበር::

ዘንባባዎች እንደ ሄይቲ፣ ጉዋም፣ ፍሎሪዳ፣ ደቡብ ካሎሪና፣ ሳሞኦ ባሉ በርካታ አገራት ባንዲራዎችና ማህተሞች ላይ ተቀርፀው ይታያሉ::

ዘንባባዎች በጥንታዊውም ሆነ ባሁኑ ዘመን በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ከሀይማኖት ጋር ተያይዞ በርካታ ትርጉሞች ይሰጣቸዋል:: በጥንቱ ዘመን የኢየሩሳሌም ክርስቲያኖች የነፍስ ጠላት የሆነውን ኃይል ድል መሆን ለማመልከት የዘንባባ ዝንጣፊ ይይዙ ነበር:: የጻድቃን ነፍስ ስጋን ስለማሸነፏ ለማመልከትም ክርስቲያኖች የዘንባባ ዝንጣፊዎችን ይይዛሉ:: በጥንታዊያን ግብፆች ዘንድም የዘንባባ ግንዶች መርዘም ረዥም ዕድሜን ይወክሉ እንደነበር ተመዝግቦ ይገኛል::

ዘንባባዎች የሰውን ልጆች ህይወት የተሻለና አስደሳች እንዳደረጉት ይታመናል:: ባንጻሩም ዘንባባዎች ባይኖሩ ኖሮ የሰው ልጅ ወደ ሞቃታማና በረሀማ አካባቢዎች የመንቀሳቀስ፣ የመስፋፋትና

የመኖር ዕድሉ የተገደበ ሊሆን ይችል እንደነበር ምሁራን ያስረዳሉ::

ዘንባባ ይህን ያህል ጠቀሜታ ያለው ተክል ቢሆንም የተለያዩ የዘንባባ ዝርያዎች አሁን አሁን እንደ ሌሎች በርካታ እፅዋት ቁጥራቸው እየተመናመነ በመሄድ ላይ ይገኛል:: የከተሞች መስፋፋት፣ ማዕድን ቆፍሮ የማውጣት እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው እንዲሁም ደኖችን እየመነጠሩ ለእርሻ ቦታ ማዋል በዘንባባ ተክሎች ላይ አደጋን ከጋረጡ ችግሮች ተጠቃሽ ናቸው::

የዘንባባ ዛፎችን ውስጣዊ ክፍል እየቦረቦሩ ለተለያዩ ምርቶች ማዘጋጃነት በግብአትነት መጠቀምም ሌላው አደጋን የጋረጠ ችግር ነው:: ምክንያቱም የዘንባባው ውስጣዊ ክፍል እየተቦረቦረ ሲወጣ ዘንባባው የመድረቅ እጣ ፋንታ ስለሚያጋጥመው ነው::

በተፈጥሮ ጫካ ውስጥ የሚበቅሉ የዘንባባ ዛፎችን ለቤት ውስጥ ቁሳቁስ መሥሪያነት ማዋልም ዝርያቸው እንዲመናመን ብሎም እንዲጠፋ ሊያደርግ የሚችል ሌላ ችግር እንደሆነ ይታመናል:: ከዚህ በተጨማሪም የጫካ ዘንባባ ዘሮችን ዘንባባ ለሚተክሉና ዘሮቻቸውን ለሚሰበስቡ አካላት መሸጥም ለዝርያቸው መመናመን ምክንያት የሚሆን ሌላው የስጋት ምንጭ ነው::

የዘንባባ ዛፎችን ከሰው ልጆች በተጨማሪ የተለያዩ ነፍሳትም ያጠቋቸዋል:: ራሲላ ኢንዲካ፣ ካሪዮብሩቸስ ግለዲሴ ከሚጠቀሱት አጥቂ ነፍሳት ጥቂቶቹ ናቸው::

ከዚህ በላይ በጠቅስናቸው ምክንያቶች የተነሳ ቢያንስ በመቶዎች የሚቆጠሩ የዘንባባ ዝርያዎች በመጥፋት አደጋ ላይ ይገኛሉ:: በመሆኑም የዘንባባ ዝርያዎችን ከመጥፋት ለማዳን የዘንባባ ተንከባካቢ ልዩ ቡድን እ.ኤ.አ በ1984 ተቋቋሟል:: ቡድኑ ዛፎቹ የሚገኙበትን ተጨባጭ ሁኔታ በተመለከተ በመላው ዓለም በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች በርካታ

መረጃዎችን ሰብስቧል:: መረጃዎቹም አደጋውን በጉልህ አሳይተዋል:: በመሆኑም ቡድኑ ከመጥፋት የዳኑትን ዝርያዎች ለመንከባከብና ለመጠበቅ እ.ኤ.አ በ1996 ዕቅድ መንደፉ ተጠቁሟል፤ ያመጣው ለውጥ ባይገለጽም::

ምንጭ- ዘ ፍሪ ኢንሳይክሎፔዲያ፣ሰን ፓልም ትሪስ ዶት ኮም፣ኤም ኤን ኤን ዶት ኮም፣ዴትኩፕ ዶት ኮም፣ኤደን ፕሮጀክት ዶት ኮም

Page 37: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 37በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ማስታወቂያ

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፍ/ሰላም ቅርንጫፍ ተበዳሪዎች ለጋራ መኖሪያ ቤት /ኮንዶምኒየም/ መግዣ የወሰዱትን የብድር ገንዘብ በውሉ መሰረት ባለመክፈላቸው ለብድሩ አመላለስ ዋስትና ይሆን ዘንድ በመያዣነት የሰጡትን የጋራ

መኖሪያ ቤት /ኮንዶሚኒየም/ ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና 216/1992 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

ተ.

የተበዳሪው ስም የሚሸጠው ቤት የይዞታ ማረጋገጫ

/ካርታ/ቁጥር

ቤቱ የሚገኝበት ህንፃ

ቁጥር

የቤት

ቁጥር

የጨረታ መነሻ

ዋጋ

ሐራጅ የሚካሄድበት

አይነት አገልግሎት ከተማ ሣይት ቀን ሰዓት ቦታ

1. ሃዋ አብዲ አህመድ ባለ 2 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/025/138/04 ፍ/ሰላም ፋርን 22 025 148,567.00 28/10/08 3፡ዐዐ-5፡ዐዐ ቤቱ በሚገኝበት

2. ሃብታሙ ጌትነት ይስማው ባለ 1 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/024/30/04 ፍ/ሰላም ፋርን 17 024 129,966.79 28/10/08 6፡3ዐ-8፡3ዐ ቤቱ በሚገኝበት

3. መምስጋናው ታገለ ወርቅነህ ባለ 2 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/021/302/04 ፍ/ሰላም ፋርን 23 021 139,034.38 28/10/08 9፡0ዐ-11፡0ዐ ቤቱ በሚገኝበት

4. ይታይህ ደስታ ካሣ ባለ 3 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/025/251/04 ፍ/ሰላም ባከል 1 025 195,510.68 29/10/08 3፡ዐዐ-5፡ዐዐ ቤቱ በሚገኝበት

5. ባንችአለም አራጌ አየለ ባለ 3 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/012/224/04 ፍ/ሰላም ፋርን 13 012 192,170.06 4/11/2008 3፡ዐዐ-5፡ዐዐ ቤቱ በሚገኝበት

6. ጀግናው ውዱ አለሙ ባለ 1 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/023/04/04 ፍ/ሰላም ፋርን 3 023 124,553.60 4/11/2008 7፡ዐዐ-9፡ዐዐ ቤቱ በሚገኝበት

7. ግርማ መኮነን ተፈራ ባለ 1 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/022/422/05 ፍ/ሰላም ፋርን 5 022 142,061.81 4/11/2008 9፡3ዐ-11፡3ዐ ቤቱ በሚገኝበት

8. መንግስቱ ታከለ ጌታሁን ባለ 2 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/021/179/04 ፍ/ሰላም ፋርን 10 021 177,631.59 5/11/2008 3፡ዐዐ-5፡ዐዐ ቤቱ በሚገኝበት

9. ጌታሰው ዳርቻ ይመር ባለ 2 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/016/313/04 ፍ/ሰላም ባከል 2 016 194,853.00 29/10/08 7፡ዐዐ-9፡ዐዐ ቤቱ በሚገኝበት

10. ተስፋ ወረቀት ውቤ ባለ 1 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/025/32/04 ፍ/ሰላም ፋርን 7 025 165,687.02 5/11/2008 7፡ዐዐ-9፡ዐዐ ቤቱ በሚገኝበት

11. አሸናፊ ቦጋለ ተሰማ ባለ 2 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/026/148/04 ፍ/ሰላም ፋርን 24 026 188,360.72 5/11/2008 9፡3ዐ-11፡3ዐ ቤቱ በሚገኝበት

12. አሰፋ ታደሰ ኪዳኑ ባለ 1 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/002/441/05 ፍ/ሰላም ፋርን 14 002 138,833.40 6/11/2008 3፡ዐዐ-5፡ዐዐ ቤቱ በሚገኝበት

13. ራሄል አፈወርቅ ሽታ ባለ 1 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/625/406/05 ፍ/ሰላም ፋርን 17 025 151,784.71 6/11/2008 7፡ዐዐ-9፡ዐዐ ቤቱ በሚገኝበት

14. ስማቸው ባንቴ ልየው ባለ 3 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/022/220/04 ፍ/ሰላም ፍራን 12 022 199,251.18 6/11/2008 9፡3ዐ-11፡3ዐ ቤቱ በሚገኝበት

15. ሽመልስ አለባቸው ካሣ ባለ 1 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/024/367/04 ፍ/ሰላም ፍራን 23 024 141,836.51 7/11/2008 3፡ዐዐ-5፡ዐዐ ቤቱ በሚገኝበት

16. ታደግ ግርማው ስዩም ባለ 1 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/013/57/04 ፍ/ሰላም ፍራን 11 013 145,986.85 7/11/2008 7፡ዐዐ-9፡ዐዐ ቤቱ በሚገኝበት

17. ተመስገን መኮነን ከበደ ባለ 1 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/004/06/04 ፍ/ሰላም ፍራን 22 004 124,539.59 7/11/2008 9፡3ዐ-11፡3ዐ ቤቱ በሚገኝበት

18. ተስፋዬ ብናየው አበጀ ባለ 1 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/003/269/04 ፍ/ሰላም ፍራን 17 003 129,410.51 8/11/2008 2፡ዐዐ-4፡ዐዐ ቤቱ በሚገኝበት

19. ያረጋል አዳምወርቅ ደጉ ባለ 1 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/023/271/04 ፍ/ሰላም ፍራን 12 023 162,287.91 8/11/2008 4፡3ዐ-6፡3ዐ ቤቱ በሚገኝበት

20. ዮሐንስ ውብነህ አዳነ ባለ 1 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/014/358/04 ፍ/ሰላም ፍራን 21 014 139,919.38 8/11/2008 7፡3ዐ-9፡3ዐ ቤቱ በሚገኝበት

21. ዘመናይ ዘይኑ ጅብሪል ስትድዮ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/004/118/04 ፍ/ሰላም ፍራን 18 004 58,738.24 8/11/2008 9፡45-11፡45 ቤቱ በሚገኝበት

22. ዝይን አለሙ አየለ ባለ 1 ምኝታ ለመኖሪያ የጋ/መ/መ/027/26/04 ፍ/ሰላም ባከል 3 027 150,993.47 29/10/2008 9፡3ዐ-11፡3ዐ ቤቱ በሚገኝበት

ማሣሰቢያ፡-

1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል የሐራጁ መነሻ ¼ በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በማስያዝ ወይም በጥሬ ገንዘብ ይዞ በመቅረብ መጫረት ይችላል፡፡

2. የቤቱን ሁኔታ ቤቱ ከሚገኝበት ቦታ ድረስ በመገኘት ወይም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ዲስትሪክት ብድር ማገገሚያ ክፍል ወይም ፍኖተ ሰላም ቅርንጫፍ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

3. ጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ካልከፈለ ለሐራጁ መነሻ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡

4. በንብረቱ ላይ ከመንግሰት የሚፈለጉ የስም ማዛወሪያና ሌሎች ወጭዎችን የጨረታ አሸናፊ ይከፍላል፡፡

5. ባንኩ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ዲስትሪክት

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበቻግኒ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ስታንዳርዱን የጠበቀ ሆቴል/ ለባለ 3 ኮከብ እና ከዚያ በላይ አገልግሎት የሚውል ቦታ ልዩ ስሙ ጣና በለስ ሆቴል ፊት ለፊት 01 ቀበሌ የቦታ ስፋት 2500 ካሬ ሜትር የቦታ ደረጃ 2ኛ የሆነውን ቦታ

በልዩ ጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1. ማንኛውም ተጫራች ባለ 3 ኮከብ እና ከዚያ በላይ አገልግሎት የሚውል ሆቴል መገንባት የሚችል፣

2. የሚተላለፈውን ቦታ ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ቻ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤቶችና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 35 በመግዛት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የቦታ ግዥ ዋጋ 5 በመቶ ከባንክ ከተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በማሸግ ማስያዝ አለባቸው፡፡

5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከቻግኒ ከተማ አስተዳደር ከ/ል/ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ቁጥር 35 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ

ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ቦታ በአካል መጥተው ማየት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ከ/ል/ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ቁጥር 35 ጨረታው በወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ታሽጎ 4፡3ዐ ይከፈታል፡፡

ይህ ቀን ብሄራዊ በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ታሽጎ በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

9. የገዙትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ በመፈረም እና የድርጅቱን ማህተም እና አድራሻ አድርጎ መመለስ አለበት፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለው የዋጋ አሞላል ተቀባይነት የለውም፡፡

10. ተጫራቾች ለግዥ መመሪያ ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከቻግኒ ከተማ አስተዳደር ከ/ል/ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ቁጥር 35 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582250019/0005/199

በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገ/አ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Page 38: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 38

የአካባቢውን ወጣቶች አሰባስቦ በሚያዝያ በ2003 ዓ.ም ወደ ክለብነት አደገ::

በዚያው አመትም በአካባቢው ለስፖርቱ ፍቅር እና ፍላጐት ያለው አንድ ወጣት ወደ ፌደራል ተልኮ የውሃ ዋና አሰልጣኞች ስልጠናን ወስዶ ተመልሶ ስለነበር በአሰልጣኝነት ክለቡን ተረከበ:: ይሁን አንጂ ክለቡ ከዚህ አመት ጀምሮ በተሳተፈባቸው ውደድሮች ብዙም ውጤታማ ሊሆን አልቻለም:: ክለቡን ውጤታማ ለማድረግ ቀጥታ ወጣቶችን መርጦ ወደ ስልጠና ከማስገባት ይልቅ ታዳጊዎችን ከታች ጀምሮ ማሳደግ እንደሚሻል ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ስምምነት ላይ በመደረሱ ወደዚሁ ሥራ መገባቱን የክልሉ አሰልጣኝ አቶ ደመላሽ ጨቅሌ ነግረውናል::

ክለቡ ታዳጊዎችን አቅፎ ተገቢውን ስልጠና መስጠት ከጀመረ ወዲህ ውጤታማ እየሆነ ሊመጣ ችሏል:: ከወረዳ ባለፈ ለዞኑ እና ለክልሉ በውሃ ዋና ጥሩ እንዲመጣ ማድረግ የቻሉ ታዳጊ ወጣቶች ማፍራት ቻለ:: ከዚህም አልፎ በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚደረገው የፕሮጀክቶች ስለጠና ወጣቶችን ማስመረጥ መቻሉንም አሰልጣኙ ገልጾልናል::

ክለቡ ባለፉት ሁለት አመታት ለወረዳው፣ ለዞኑ ብሎም ለክልሉ በርካታ ሜዳሊያዎችን በማስገኘት በውሃ ዋና ስፖርት ውድድር ቀዳሚ እንዲሆኑ የላቀ ድርሻ አበርክቷል:: በ2006 ዓ.ም በዞን ደረጃ በተካሄደው ሻምፒዮና በዋና 52 ሜዳሊያዎችን ወረዳው እንዲያገኝ ያደረጉት የዚሁ ክለብ ልጆች ነበሩ:: በዚሁ አመት በመላው የሰሜን ጐንደር ውድድርም 20 ወርቅ፣ 23 ብር እና 22 ነሀስ በድምሩ 65 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ወረዳውን ቀዳሚ አድርገዋል:: በዚሁ አመት በተደረገው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎችም አንድ ሴት ለክልሉ አስመርጧል::

ክለቡ በውጤታማነቱ በመቀጠሉም በ2007 ዓ.ም በተካሄደው የክልሉ የተማሪዎች ውድድር ዞኑን በመወከል የተሳተፉት አብዛኛዎች የዚሁ ክለብ ተጫዋቾች 30 ወርቅ፣ 18 ብር እና 17 የነሀስ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ዞኑ የሁለተኛ ደረጃን ይዞ እንዲጨርስ አድርገዋል:: በያዝነው አመት በመላው አማራ ጨዋታዎችም 19 ወርቅ፣ 23 ብር እና 28 ነሀስ ዞኑ መሰብሰብ እንዲችል አስችለዋል:: በዚሁ አመት አራት ሴቶችና አንድ ወንድ ክልሉን ወክለው በመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች እንዲሳተፍ አስመርጧል:: እነዚሁ ልጆችም ክልሉ በውሃ ዋና የበላይ ሆኖ እንዲጨርስ ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር:: 27 ወርቅ፣ ሁለት ብርና አራት የነሀስ ሜዳሊያዎችን ለክልሉ ያስገኙት ከዚሁ ክለብ የተመረጡ ልጆች ናቸው:: አምስት ታዳጊዎችም ከክለቡ ተመርጠው አዲስ አበባ በሚገኘው የስፓርስ አካዳሚ ለስልጠና እንዲገቡ ተደርጓል::

የጣቁሳ ወረዳ የውሃ ዋና ክለብ አባላት ለዚህ ሁሉ የበቁት ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ ሆኖላቸው አይደለም:: ይልቁንም በርካታ መሰረታዊ ነገሮች ባልተሟሉበት ሁኔታ ለስፖርቱ ባላቸው ፍቅር በመበረታታት ነው:: በመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች በነጠላ ሰባት በቡድን ሶስት በድምሩ 10 የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለክልሉ ያሰገኘው ከዚህ የተገኘው ጥላሁን አያሌው ነው:: ጥላሁን እንደገለፀልን በክለቡ የታቀፉት ልጆች የዋና ልምምዳቸውን የሚያደርጉት በጣና ሀይቅ ላይ ነው:: ውሃው ስለሚቆሽሽም ጥሩ ስሜት አይሰማቸውም:: ለውድድር ወደ ሌላ አካባቢ ሲሄዱም ብዙ ጊዜ ለውጤት የማያበቃቸው በመዋኛ ገንዳ ልምምድ ባለማድረጋቸውና ለእነርሱም አዲስ ስለሚሆንባቸው ነው:: ውሃው በጣም ሲጐድል ልምምድ ስለሚያቆሙ እየተቸገሩ ይገኛሉ:: በአካባቢያቸው የመዋኛ ገንዳ ቢኖር ግን የበለጠ ውጤታማ መሆን እንደሚችሉም ጥላሁን ነግሮናል::

በግሏ አምስት በቡድን ደግሞ ሶስት በድምሩ ስምንት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለክልሉ ያስገኘችው ሀናም አስፈላጊው የዋና ትጥቆች እና ተመጣጣኝ የላብ መተኪያ እንደማያገኙ ነግራናለች:: ሀና እንደገለፀችልን ልምምድ የሚሰሩት ንፁህ ባልሆነው የጣና ውሃ ላይ ሲሆን ትጥቅ አብዛኛውን ጊዜ የሚያሟሉት በግላቸው ነው:: በወር የሚያገኙት

ከ400 ብር የማይበልጥ ደመወዝ የድካማቸውንና ጉልበታቸው የሚተካ አይደለም:: ስለሆነም እነዚህ ነገሮች ወደ ፊት ሊታሰብባቸውና ሊሟሉ እንደሚገባም ሀና ተናግራለች::

በመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ክልሉ ካገኛቸው የወርቅ ሜዳሊያዎች አብዛኞቹን ያመጡት የክለቡ ልጆች እንደሆኑ አሰልጣኙ ደመላሽ ጨቅሉ ተናግረዋል:: ይህ ሁሉ የሆነው ግን ገንዳ ሳይኖር በጣና ላይ እየዋኙ በግል ብቃታቸውና ጥረታቸው ነው:: ገንዳ ቢኖር ደግሞ አገር የሚያስጠሩ ወጣቶች ሊፈሩ እንደሚችሉም ተናግረዋል::

አሁን ከመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ከተመለሱ በኋላ የጣና ውሃ በጣም በመጉደሉ ልምምድ እንዳልሰሩ የተናገሩት አሰልጣኙ ገንዳ ቢኖር ኖሮ ግን ይህ ችግር እንደማይፈጠር ተናግረዋል:: ዋናተኞቹ በክለቡ የሚከፈላቸው ደመዎዝ በቂ ባለመሆኑም በወር እስከ አንድ ሺህ 600 ብር ወደ ሚከፍሉ ክለቦች ለመሄድ እየማለሉ ነው:: የትጥቅ ችግርም አለ::

ጣና ያፈራቸው...ከገጽ 40 የዞረ

የወረዳው አስተዳደር በአመት 60 ሺህ ብር እየመደበ ክለቡን ለማጠናከር በሚያደርገው ጥረት ብቻ እስካሁን እንደሚሰሩ የተናገሩት አሰልጣኙ ይህ ግን ለደመወዝ፣ ትጥቅና ለሌሎችም ወጪዎች በቂ እንዳልሆነ ገልፀዋል:: ስለሆነም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት እገዛ ካላደረጉ ክለቡ የወደፊት እጣ ፋንታው አስቸጋሪ እንደሚሆንና በስፖርቱ አቅም ያላቸው የአካባቢው ወጣቶችም ከስመው እንዲቀሩ የሚያደርግ መሆኑንም አሰልጣኙ ነግሮናል::

እኛም በቦታው በተገኘንበት ወቅት ልጆቹ ልምምድ የሚሰሩበት የተሟላ ትጥቅ እንደሌላቸው ተረዳን:: የሚዋኙበት የጣና ሀይቅም እጅግ ቆሻሻ ከመሆኑም በላይ በመጉደሉ ጭቃው እንደሚታይ አስተዋልን:: ስለሆነም ይህ ተስፋ ያለው ክለብ ወደ ኋላ እንዳይመለሰ የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ ቢፈልጉ ጥሩ ነው እንላለን::

የጣቁሳ የውሃ ዋና ክለብ ከተመሰረተ ጥቂማ አመታት ብቻ ቢሆነውም ውጤታ እንደሆነ የገለፁት

ደግሞ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ መላኩ አለምነው ናቸው:: ክለቡ የወረዳ አስተዳዳሩ በሚያደርግለት ጥቂት ድጋፍ ብቻ ታግዞ ለዚህ የበቃው በልጆቹና በአሰልጣኙ ጥረት መሆኑን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መላኩ ተናግረዋል::

በክለቡ የመዋኛ ገንዳም ይሁን ለልጆቹ በቂ ትጥቅና የላብ መተኪያ አያገኙም መባሉ ትክክል መሆኑን የተናገሩት አቶ መላኩ ወደ ፊት እነዚህን ችግሮች ለመፍታት እየሰሩ መሆኑንም ጠቁመዋል::

የደልጊ ከተማና የወረዳው ኗሪዎችን በማንቀሳቀስ በቂ ገንዘብ ለማሰባሰብ መታቀዱን የተናገሩት አቶ መላኩ የመዋኛ ገንዳ ለማሰራት ምን ያህል ብር እንደሚጨርስ ዞኑ እንዲያሰጠናላቸው እየተናጋገሩ መሆኑንም ጠቁመዋል:: ዞኑ የሚፈጀውን ገንዘብ ካሳወቃቸው በኋላ ከክልሉ፣ ከዞኑም ሆነ ከሌሎች አጋር አካላት ድጋፍ ለማሰባሰብና ገንዳውን ለማሰራት ኘሮጀክት ለመንደፍ በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም አስተዳዳሪው ተናግረዋል::

ውድድር ሲካሔድ

ከገጽ 32 የዞረዘመናዊ ...

እርሷ ከሃገሯ ኢንዶኔዥያ ወደ አሜሪካ የመጣችው በሚያማልለው የአሜሪካ የሆቴል ኢንዱስትሪ ውስጥ እንደምጥቀጠር ቃል ተገብቶላት ነው:: ሆኖም የተቀበላት ወኪሏ ገና ከኤርፖርት ሳትወጣ ለወሲብ ነጋዴዎች አሳልፎ እንደሸጣት ትናገራለች:: ታዲያ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሻንድራ የወሲብ ንግድን ሳትፈልግ በግድ ተሸክማው ኖራለች::

‹‹በወቅቱ የወሰደኝ ሰው 30 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንዳለውና በየጊዜው ከምሰራው ስራ 100 ዶላር እዳ እንደከፍለው ያስገድደኝ ነበር::›› ብላለች:: ሻንድራ ከዚህ ሕይወት አምልጣ ከወጣች በኋላ ለኤፍ ቢ አይ ባደረገችው ጥቆማ ሌሎች ተጠቂዎችን ከስቃይ ታድጋለች:: ነገር ግን ይህ ባርነት በበዙ የዓለማችን ክፍል አስከፊ ገጽታው አሁንም ቀጥሏል::

የግዳጅ ልመናበህጻናት መለመን በአውሮፓ፣ በአፍሪካ፣ በእስያ፣

በመካለኛው ምስራቅና በላቲን አሜሪካ አዲስ ነገር አይደለም ይላል ቢቢሲ:: በእነዚህ አህጉራት ህፃናት በአሳዛኝ ሁኔታ መንገድ ዳር ተቀምጠው እንዲለምኑ ይገደዳሉ:: የዚህ ስቃይ ሰለባ የሆነ አንድ ህጻን ለጥናት አድራጊዎች እንደተናገረው ‹‹ምንም እንኳ ለማኝ ብሆንም ለዚህ ስራየ አይከፍለኝም:: በእርግጥ ገንዘብ አገኛለሁ:: ግን የኔ አይደለም:: አሰርዬ እኔ ለምኜ ያመጣሁትን ገንዘብ ለሌሎች ደመወዝ አድርጎ

ይከፍላል:: ጥሩ ምግብና በቂ እንቅልፍ እንኳ በቅጡ አላገኝም::›› ብሏል::

ሌላው ሰለባ ደግሞ ‹‹እኔ ሁልጊዜ በፍርሃት ውስጥ ነው የምኖረው:: ለቀጣሪየ ስጋት እንዳልሆን ምንም ነገር ለማንም መናገር አልችልም:: አለበለዚያ ከፍተኛ ቅጣት ይጠብቀኛል›› ሲል የሚደርስበትን ስቃይ ገልጿል::

ከተዘጉ በሮች በስተጀርባአብዛኛውን ጊዜ ዘመናዊ ባርነት ለብዙሃኑ

በግላጭ የሚታይ አይደለም:: ባርነቱን ለማረጋገጥ የተዘጉ ቤቶችን ማንኳኳትና ርቀው የሚገኙ የእርሻ ቦታዎችን መጎብኘት ይጠይቃል:: ቢቢሲ ለዚህ በማሳያነት ያቀረበው ከሳምንታት በፊት በእንግሊዝ በሚገኝ አንድ ቤተሰብ ውስጥ ለ20 ዓመታት ያለምንም ክፍያ የጉልበት ስራ ሲሰራ የነበረ ግለሰብ

መገኘቱን ነው:: የ46 ዓመቱ ማይክል ሂዩዝ በዚህ ቤተሰብ ውስጥ በግዳጅ የግንባታ ስራና ሌሎች ከባድ ስራዎችን በመስራት ሁለት አስርት አመታትን አሳልፏል::

ማይክል በአሰሪዎቹ የአትክልት ስፍራ ውስጥ በሚገኝ ጠባብ ክፍል ውስጥም ያለ በቂ ውሃና ሙቀት ሁለት አመታትን አሳልፏል:: በሌላ በኩል ከወራት በፊት ባለቤቱን የቤት ሰራተኛ አድርጓት ስለተገኘው እንግሊዛዊ በማስረጃነት ያቀረበው ቢቢሲ ግለሰቡ ሚስቱን ሁሉንም የቤት ስራ እንድትሰራ ከማድረጉም ባለፈ ከቤት ውስጥ እንዳትወጣ በማድረግ ድብደባ ፈጽሞባታል ብሏል:: እናም እንዲህ ያሉ ከተዘጉ በሮች በስተጀርባ የሚፈጸሙ ዘመናዊ ባርነቶች በሃገረ እንግሊዝ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም እንደሚገኙ ዘገባው ጠቁሟል::

Page 39: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

ገጽ 39በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.

ከገጽ 40 የዞረ

ፀባዬ ታርሟል-...

ከገጽ 40 የዞረ

የፔሌ...

ሊደገም ይችላል የሚል ስጋት ቢያድርባቸውም ሞሪኒሆ ግን አይደገምም እያሉ ነው::

ሞሪኒሆ በፖርቹጋል ሊዝቦን ዩኒቨርሲቲ

እንደተናገሩት “እኔ ልምዴም ሆነ አሁን ያለሁበት ሁኔታ ለግጭት የሚዳርገኝ ባለመሆኑ፣ ከጋርዲዮላ ጋር የማደርገው አንዳች ነገር የለም” ብለዋል:: ዋናው

ትኩረታቸውም ዮናይትድን ወደ ቀደመ ዝናውና ክብሩ መመለስ እንጂ ከማንም ጋር መጋጨት እንዳልሆነ ሞሪኒሆ ለስካይ ስፖርት ተናግረዋል::

ሞሪኒሆና ጋርዲዮላ በስፔን ተቀናቃኝ በነበሩበት ወቅት

ከሚያቀርባቸው ሽልማቶች መካከል በታዋቂው ሜክሲኳዊ የእግር ኳስ ቀራጭ የራሱን ምስል የቀረፀበትን የግሉ ዋንጫ ከ400 መቶ ሺህ እስከ 600 ሺህ ፓውንድ ያወጣል ተብሎ ተገምቷል:: ከዚህ በተጨማሪ የአለም የእግር ኳስን ሐገሩ ስታሸንፍ ያገኛቸው መዳሊያዎች ደግሞ ከ100 እስከ 200 ሺህ ዶላር ያወጣል ተብሎ ተገምቷል:: ከዚህ ውጪ

አንድ እሺኛ ግብ ያስቆጠራት ኳስ፣ ሲጫወትበት የነበረው የሐገሩ ክለብ ባለድል ሲሆን የተሸለመው የጣት ቀለበት፣ የእጅ ሰዓት፣ ለብሷቸው የተጫወቱ ማሊያዎችና ጫማዎች፣ ፓስፖርቱ፣ ፊልም

የሰራበት ጫማ፣… የመሳሰሉት ቁሳቁስ ለጨረታ ይቀርባሉ ተብለዋል:: በጨረታውም ከሁለት ነጥብ አምስርት ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባው ጨምሮ ገልጿል::

የሰባ አምስት አመቱ ፔሌ ለጨረታ ያቀረባቸውን ቁሳቁስ ለመግዛት ሐገራትና ባለሐብቶች ጥያቄ እያቀረቡ ነው:: ጥያቄ ካቀረቡ ሐገራት መካከል

ቻይና፣ ጃፓን፣ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ሜክሲኮ፣ የአረብ እና የላቲን አሜሪካ ሐገራት ይገኙበታል:: በርካታ ሐገራት ለመሳተፍ ፍላጐት ማሳየታቸው የጨረታውን ዋጋ ከፍ ሊያደርገው እንደሚችልም ተገምቷል::

ስለጨረታው የተጠየቀው ፔሌ “የተለያዩ ክብሮችን በተቀናጀህ ጊዜ ያገኘሃቸውን ቁሳቁሶች ለሽያጭ ማቅረብ አስቸጋሪ ነው:: ነገር ግን አንዳንዴ የምትገደድባቸው ሁኔታዎች ይኖራሉ::

ይህ በመሆኑም የግሌ የሆኑ ስጦታዎችን ለጨረታ አቅርቢያለሁ:: ንብረቶችን ለጨረታ ማቅረቤም ለእኔ ብቻ የነበሩት ንብረቶች የሁሉም ሰው ንብረት እንዲሆኑ ለማድረግ እድል ስለሚሰጥ ደስተኛ ነኝ” ብሏል::

ለጨረታ ከቀረቡት የፔሌ ሽልማቶች በከፊል

ከገጽ 19 የዞረ

በሶሪያ ... ይህ በእንዲህ እንዳለ የእንግሊዙ

የውጭ ጉዳይ ዋና ፀኃፊ ፍሊፕ ሃሞነድ በበኩላቸው በዓለም አቀፉ የሶርያ ድጋፍ ቡድን በሰኔ ወር መጀመሪያ ሊደረግ የተፈቀደው ውስን እርዳታ ስለመድረሱ ያጠራጥራል ሲሉ ገልጸዋል:: በአሁኑ ወቅት በቀጣናው ያሉ ከተሞች በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ መሆናቸው አሳሳቢ ነው ያሉት ዋና ፀኃፊው እርዳታው በአውሮፕላን ካልደረሰ ጉዳቱ የከፋ እንደሚሆን ተናግረዋል:: “እርዳታውን በአውሮፕላን ማሰራጨት ውስብስብ፣ ውድ እና አደገኛ ቢሆንም በተከበቡ ከተሞች የሚኖሩ ዜጎችን ለመታደግ የመጨረሻ አማራጭ ነው” ሲሉ ገልጸዋል::

የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በበኩሉ በጉዳዩ ላይ ለመምከር ቀጠሮ ይዟል:: አሜሪካና እንግሊዝም እርዳታው እንዲፋጠን ሩስያና ኢራቅ በሶሪያ መንግስት ላይ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ ጥሪ አስተላልፈዋል::

Page 40: ግንቦት 29 ቀን 2008.pdf

በኩር ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 40 በኩር ስፖርትበኩር ስፖርትበኩር ስፖርትበኩር ስፖርት

ወደ ገጽ 38 ዞሯል

ፀባዬ ታርሟል-

ሞሪኒሆ

አዲሱ አያሌው

ወደ ገጽ 39 ዞሯል ወደ ገጽ 39 ዞሯል

ሙሉ ስሙ ኢዲሰን አራንቴስ ዶ ናስሊሜንቶ ፔሌ ይሰኛል:: ወደዚች ምድር የመጣውም እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በጥቅምት 23/1940 ነው:: የትውልድ ሐገሩ ደግም የላቲኗ ብራዚል ነች:: የክፍለ ዘመኑ ምርጥ የእግር ኳስ ሰው በሚል በአለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር ሽልማት የተበረከተለት ፔሌ በጨዋታ ዘመኑ ያገኛቸውን ሁለት ሺህ ሽልማቶችና ስጦታዎችን ለጨረታ ሊያቀርብ መሆኑን ቢቢሲ ስፖርት ከሰሞኑ በድረ ገፁ አስነብቧል::

የክፍለ ዘመኑ ምርጡ የእግር ኳስ ፈርጥ ፔሌ የግሉ የሆኑ ሽልማቶችን ለጨረታ ያቀረበው ለእራሱ ገቢ ማስገኛ ይሆን ከጤናው ጋር በተያዘ ጉዳይ ዘገባው በውል የገለፀው ባይኖርም አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ግን የራሳቸውን መላ ምት እየሰነዘሩ ነው:: ለአብነት ዳን አሊሰን የተባሉ የጨረታ አስተባባሪ ባለሙያ ፔሌ የግሉ የሆኑ ውድ ንብረቶችን ለጨረታ የሚያቀርበው ባለፉት 12 ወራት ጀርባው ላይ ያጋጠመውን ህመም ለመታከም ሳይሆን አይቀርም ብለዋል:: ከዚህ ጐን ለጐንም ፔሌ የጐን እና የፊኛ ቀዶ ህክምና ስለሚያስፈልገው ለዚህ ሊያውለው አስቦ ሊሆን ይችላል ሲሉ አሊሰን ተናግረዋል::

ጌትነት ድልነሳ

ፖርቹጋላዊው ሆዜ ሞሪኒሆ በጣሊያኑ ኢንተርሚላን፣ በስፔኑ ሪያል ማድሪድ፣ በፖርቹጋሉ ፓርቶ እንዲሁም በእንግሊዙ ቸልሲ ያገኙትን ስኬት በእንግሊዝ ሐያል ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድ ለመድገም ውል ተፈራርመዋል:: በሶስት አመት ቆይታቸውም ክለቡን ለክብር ከማብቃት ጐን ለጐን ከሌሎች አሰልጣኞች፣ ዳኞችና ተጫዋቾች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማሻሻል መዘጋጀታቸውንም ለጐል ዶት ኮምና ለስካር ስፖርት ተናግረዋል:: በተለይ የቀድሞው የባርሲሎና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲን ለማሰልጣን ውል መውሰዳቸውን ተከትሎ ግጭቶች ይፈጠራሉ ተብሎ ከአሁኑ ቢፈራም ሞሪኒሆ ግን “እመኑኝ

ጌትነት ድልነሳ

አንዳች ግጭት አንፈጥርም፣ በስፔን የነበረውን ጉዳይም በእንግሊዝ ምድር አናደርገውም ፀጋዬ ታርሟል” ብለዋል::

በተለይ በ2011 እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ጋርዲዮላ ለጋዜጠኞች በሞሪኒሆን ሸንቆጥ የሚያደርግ አስተያየት መስጠታቸውን ተከትሎ የሁለቱ አሰልጣኞች መፋጠጥ ጀመረ:: ብዙም ሳይቆዩ ሞሪኒሆ የጋሪዲዮላን ረዳት አይናቸውን መቧጨራቸውን ተከትሎ ፍጥጫው ይበልጥ እየጦፈ የመገናኛ ብዙሐን ትኩረት ስቦ ነበር:: ይህን አካሄድ የፈሩት አንዳንድ ግለሰቦች ሞሪኒሆና ጋርዲዮላ ሁለት ተቀናቃኝ ቡድኖችን ለማሰልጠን ወደ እንግሊዝ ማቅናታቸውን ተከትሎ በስፔን የነበረው ጭቅጭቅ በዚህ

ፔሌ በጨዋታ ያገኛቸው የወርቅ መዳሊያዎች

አንድ ሺህ 283 ግብ በማስቆጠር ስሙን በአለም የድንቃድንቅ መዝገብ ያሰፈረው ፔሌ በሰኔ ወር በእንግሊዝ በሚከፈተው ጨረታ ላይ

የፔሌሽልማቶች ለጨረታ ሊቀርቡ ነው

በአማራ ክልል ከሚገኙ ውብና ድንቅ የተፈጥሮ መስህቦች መካከል የጣና ሀይቅ አንዱ ነው:: በዚህ ሀይቅ የሰሜን ጫፍ አካባቢ ደግሞ በሰሜን ጐንደር ዞን የጣቁሳ ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችው ደልጊ ትገኛለች:: በጣና ሀይቅ ዳርቻ የሚገኘው የደልጊ ወደብ ደግሞ ለከተማዋም ሆነ ለአካባቢዋ ኗሪዎች ምርታቸውን ወደ ባህር ዳርና ሌሎች አካባቢዎች

ጣና ያፈራቸው

በጀልባ እንዲልኩ እንዲሁም የሚፈልጉትን ሸቀጥና ምርት እንዲያስገቡ ያግዛቸዋል:: ወደቡ ከዚህም ባሻገር የአካባቢው ወጣቶች በጣና ሀይቅ ላይ ለመዋኘት የሚወጡበትና የሚገቡበት ቦታም ነው::

ታዲያ እኔም ለዛሬ ስለ ጣና ሀይቅም ሆነ ስለ ደልጊ ወደብ ማንሳቴ ያለምክንያት አይደለም:: ይልቁንም ወደ አካባቢው አቅንቼ በጣና ሀይቅ

ላይ እንደ አሳ እየዋኙ ያደጉትንና በአሁኑ ወቅት በውሃ ዋና ስፖርት ክልሉን ቀዳሚ ማድረግ የቻሉ ወጣቶችን ያፈራውን የጣቁሳ ውሃ ዋና ክለብን

እንቅስቃሴ ለመቃኘት ነበር:: የጣቁሳ ውሃ ዋና ፕሮጀክት የጀመረው በ2001 ዓ.ም ነው:: ፕሮጀክቱ

የደልጊ ታዳጊዎች በጣና ሐይቅ ላይ ሲለማመዱ

ሞሪኒሆ ጋርዲዮላ