154
የሐይማኖት አፈና በወያኔ አገዛዝ Surafel Tekleab Fentawn

surafel book final 01.pdf

  • Upload
    trananh

  • View
    311

  • Download
    32

Embed Size (px)

Citation preview

1

የሐይማኖት አፈና በወያኔ

አገዛዝ

Surafel Tekleab Fentawn

2

መግቢያ በሃገራችን ኢትዬጵያ ሃገር ውስጥም ሆነ በስደት በውጭ አለማት ለምትኖሩ

ውድ ኢትዬጵያውያን በዚች መጽሃፍ ውስጥ ለተከበራችው ውድ አንባቢያን

በወያኔ አገዛዝ ዘመነ መንግስት ጊዜ የሚደረገውን የሃይማኖት አፈና እና ረገጣ

እንደ ኢትዬጵያዊነቴ እና እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነቴ ያለኝንና የተሰማኝን

እንዲሁም ያየውትንና የምሰማውን የሃገሬንና የቤተክርስቲያኔን እንዲሁም

የወገኔን ጭቆና እና በደል በምን ላይ እንደኖረና እንዳለ የተሰማኝን ሐዘንና

ስሜት ለወገኔ ለማካፈል ሲሆን የመጽሃፌ ርዕስም “ የሐይማኖት አፈና በወያኔ

አገዛዝ” የሚል ሲሆን ጉዳዩም በስልጣን ላይ ያለዉ የወያኔ መንግስት ስልጣን

ከያዘበት ጀምሮ በተለያዩ የሃይማኖት ተቌማት በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ

ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና በሙስሊም ሃይማኖት ዙሪያ ጣልቃ በመግባት

የራሱን ዘርና ጎሳ በየ ቦታው የበላይ ሃላፊ በመሾም በቤተ ክርስቲያንና በመስጊድ

ውስጥ የሚገኙትን የሃገር ቅርስ እንዲሁም ሃብትና ንብረት በመዝረፍ ላይ

እንደሆነ ና የሾማቼዉ የበላይ ሃላፊወችም ሥልጣናቼዉን መከታ በማድረግ

በማን አለብኝ መብት ቤተክርስቲያኗን በዘር በመከፋፈል እና የድሮ አባቶቻችን

ያቆዩልንን ቅርስና ንብረት በመዝረፍ ትልቅ ስራ እየተሠራ እንደኖረና በአሁኑ

ሰአትም እንደቀጠለ ሲሆን ፖለቲካውም ይሄው እስካሁን ድረስ 23 (ሃያ ሶስት)

አመታትን በግፍና በበደል ምርጫዎችን በማጭበርበር የህዝብን ነፍስ እንደ

እንስሳ ነፍስ በማጥፋት በጀብድነት በእስርቤት ንጹሃን ዜጏችን አፍሶ እስር ቤት

ውስጥ በመክተትና በማሰቃየት ረገድ የሚታወቀውን ዘረኛው የወያኔ መንግስት

ከሚሰራቼው መጥፎ ስራወች ከብዙ በጥቂቱ ለማሳወቅ ይሆናል፡፡

መልካም ንባብ፡

3

Contents መግቢያ ................................................................................... 2

ሲኖዶስ ማለት የሃይማኖት ፓርላማ ማለት ሲሆን እነሱም ፡ ....................... 7

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸሟቸው

ዐበይት ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፦ ................................................ 8

፩ ትክክለኛው ወይም ስደተኛው ሲኖዶስ የሚባለው በሰሜን አሜሪካ

በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ የ ሚገኘው ሲሆን ................................ 16

ሚ ላዕሌነ፤ ምን ገዶን? ............................................................... 19

ዋልድባ ገዳም .......................................................................... 25

ትንሣኤ ዘክርስቶስ - የክርስቶስ ትንሳኤ ............................................. 37

ሱባኤ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ምንይመስላል? ..................................... 49

የኢትዩጵያ ሙስሊሞች አቭዬት ከየት ወደ የት ነዉ? ............................. 58

ኢሃዴግ በሙስሊሙ ሃይማኖት ጣልቃ መግባት .................................. 74

የወያኔ ምርጫ መቃረብ ............................................................... 78

ወዴት ነው ጎተራው ? ............................................................... 91

ወገኔ ተነስ ! ........................................................................... 94

ውድ ታጋይ ወገኖቼ ፤ ................................................................ 97

ውድ ታጋይ ኢትዮጵያዊ፤ ............................................................. 98

አይቀሬው የህውሓት ውድቀትና በፍርሃት ድባብ ውስጥ የምትኖረው መቀሌ

......................................................................................... 103

የወያኔ መንግስት በአማረው ህዝብ ላይ የሚያስከትለው ጭቆና! .............. 114

የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታና የወደፊት የትግል አቅጣጫ ........................ 118

ዲሞክራሲ ............................................................................ 126

4

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ለማኝ መንግስት አመጣጥና አወዳደቅ .............. 129

ልማታዊ መንግስት ከሌባ መንግስት ጋር ሲነጻጸር ............................... 139

ታላቁ ቅጥፈት በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ልማታዊ መንግስት፣ .............. 144

5

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ያበረከትችውን

አስተዋጽዖ መዘርዘር ለቀባሪው እንደማርዳት ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ

ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተለይ ሕግና ሥርዓትን አውጥታ፤ ካህናትና ምዕመናን

በአንድነትና በመከባበር የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓተ እምነት፤ ዶግማና ቀኖና

እንዲጠብቁና እንዲያስጠብቁ፤ በልማትና በማኅበራዊ ጉዳዮች በሕብረተሰቡ

ዘንድ መረዳዳትና መቻቻል እንዲኖር አድርጋለች፣ በማድረግም ላይ ትገኛለች።

ይህም ለሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓል።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ሁሉ ተግባራት ለዘመናት ስታከናውን

የቆየችው በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለውን መንፈሳዊና አስተዳደራዊ

የሥልጣን ተዋረድ በመጠቀምና በማክበር ነው። ይህም አሠራር ለዘመናት

ሳይፋለስ ቆይቷል። ይህንን ከሀገሪቱ ከ50% በላይ የሆነና በሚሊዮን የሚቆጠር

ምዕመን ይዛ በሕግና በሥርዓት ባታስተዳድር ኖሮ የቤተ ክርስቲያንቱ ሰላም

ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱም ሰላም ሊደፈርስ እንደሚችል እሙን ነው። የቤተ

ክርስቲያንን መንፈሳዊና አስተዳደራዊ የሥልጣን ተዋረድ ለማስጠበቅ እና በቤተ

ክርስቲያንቱ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች ተፈፃሚነት የሕግ

ከለላ በመስጠት በየጊዜው የነበሩት ነገሥታትና የመንግሥት አካላት በቂም

ባይሆን የበኩላቸውን አስተዋጽዖ አበርክተዋል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት የቤተ ክርስቲያኒቱን ዶግማና ቀኖና ለማፍረስና

ሀብቷንና ንብረቷን ለመዝረፍ እንዲያመች መንፈሳዊና አስተዳደራዊ የሥልጣን

ተዋረዷን መጣስ እየተለመደ መጥቷል። እነዚህን ሕገ ወጥ ተግባራት

ለመከላከል የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ ጠባቂና ወሳኝ አካል የሆነው ቅዱስ

ሲኖዶስ እና በየደረጃው ያሉ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አመራር አካላት

የሚወስኗቸው ውሳኔዎችና አመራሮች ተግባራዊ እንዳይሆኑ ብዙ እንቅፋቶች

እያጋጠሟቸው ነው። ለዚህም እንደማሳያነት በቦሌ የቆመው የፓትርያርኩ

ሐውልተ ስምዕ መፍረስና በሐዋሳ ሀገረ ስብከት በተፈጠሩ ችግሮች ላይ

የተወሰኑት ውሳኔዎችን ለማስፈፀም ያለውን ፈተና መግለፅ ይቻላል። ከዚህ

አንጻር ስንመለከተው፦

1. የቤተ ክርስቲያንቱን ዶግማ፤ ቀኖና እና ትውፊት ለማስከበር እና የቤተ

ክርስቲያንቱን ሀብት እና ንብረት ከውድመትና ከዝርፊያ ለመታደግ ጥረት

በሚያደርጉ አባቶች ላይ እየተደረገ ያለው ዛቻ፤ ጫና እና ማስፈራሪያ ከጊዜ ወደ

ጊዜ እየተባባሰ የሚገኝ ጉዳይ እንጂ የሚቀንስ ሆኖ አለመገኘቱ፤ ይህም ጉዳይ

“መንግሥት በሀገሪቱ የለም፤ ሕግና ሥርዓት አስከባሪ የለም፣ መንግሥት ለቤተ

6

ክርስቲያኒቱ ደንታ የለውም”’ እስከኪባል ድረስ አድርሶታል።

2. ባለፈው ዓመት በተደረገው በብፁዓን አበው ላይ የደረሰውን ድብደባ፤

አፈናና ዛቻ የፈፀሙት ግለሰቦች ለፍርድ አለመቅረብና ሕጋዊ ቅጣት አለማግኘት

ምዕመኑ በመንግሥት ላይ ያለውን ተስፋ እስከመጨረሻው እንዲሟጠጥ

አድርጎታል።

3. በዚህ ዓመትም በጥቅምት ወር በተደረገው ጉባኤ ላይም ቢሆን ብዙ ብፁዓን

አባቶች የማስፈራሪያ ዛቻዎች በስልክ እና በአካል ተሰንዝረዋል። አሁንም የቤተ

ክርስቲያኒቱ ዶግማና ቀኖና እንዲጠበቅ፤ ሀብቷ እና ንብረቷ እንዳይዘረፍ፤ እና

የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ የሥልጣን ተዋረድ እንዲጠበቅ

በሚታገሉ አባቶች ላይ ከእነዚህ ቡድኖች የሚሰነዘረው ማስፈራሪያ ቢጨመር

እንጂ አልቀነሰም።

4. በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በቅዱስ ሲኖዶሱ የተወሰኑት ውሳኔዎችንም

ለማስፈፀም አለመቻሉ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ሆነው በዝርፊያና የቤተ

ክርስቲያንን ሰላም በማደፍረስ ምዕመኑን ተስፋ በማስቆረጥ ሥራ ላይ

የተሰማሩት ቡድኖች በቤተ ክርስቲያኒቱ ብሎም በሀገሪቱ ሰላም እና ልማት ላይ

ከፍተኛ አደጋ እንደሚጥሉ ለማወቅ ማስረጃና ጥልቅ ምርምር አያሻውም።

5. አሁንም ቢሆን መንግሥት በራሱ የሚያደርገውን አስተዳደራዊ በደል

ምዕመኑ የሚታገሰውን ያህል በእምነቱ ሲመጣበት ሊታገስ እንደማይችልና

የቤተ ክርስቲያኑ ዶግማና ቀኖና እንዲጠበቅ፤ ሀብቷ እና ንብረቷ እንዳይዘረፍ፤

እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ የሥልጣን ተዋረድ

እንዲጠበቅ አስፈላጊውን መስዋዕትነት መክፈል እንደሚችል አውቆ መንግሥት

ሊያስብበት ይገባል።

6. በፖለቲካው ረገድ በቅርቡ በሰሜን አፍሪካ በኢ-ፍትሐዊ አስተዳደሮች ላይ

የተደረገው ዓይነት ሕዝባዊ አመጽ ለመሪዎች መባረር ምክንያት እንደሆነው

ሁሉ ይህ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደረገው በደል ማቆም ካልተቻለ በኢትዮጵያ

ምዕመኑ ወደዚህ ዓይነት ቁጣ ሊራመድ እንደሚችል መንግሥት ሊረዳው

ይገባል።

7. ስለሆነም የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ የሥልጣን ተዋረድ

እንዲጠበቅ እና በቤተ ክርስቲያንቱ የበላይ ጠባቂና ወሳኝ አካል በሆነው በቅዱስ

7

ሲኖዶስ እና በየደረጃው ባሉ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አመራር አካላት

የሚወሰኑት ውሳኔዎችና አመራሮች በእምነቱ ቀኖናዊ አሠራር መሠረት ተፈጻሚ

እንዲሆኑና ከላይ ለተጠቀሱት ለእውነተኛ የቤተ ክርስቲያንቱ አካላት መንግሥት

አስፈላጊውን የሕግ ከለላ ሊሰጥ ይገባል እንላለን።

8. መንግሥት የሀገሪቱን ሰላም ለማስከበር የቤተ ክርስቲያኗን ሰላም ማስከበር

ይጠበቅበታል።

በሀገር ውስጥም ሆነ በመላው አለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ምእመናን ና ሚመናት ሃዋርያዊት ጥንታዊት ታሪካዊት ና ብሄራዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋቤተክርስቲያንህዶ በረጅሙ የታሪክ ጉዞዋ በሃይማኖት መሪዎች መነፈሳዊ ብርታት በሊቃውንቶቿ ትምህርት በካህናቶቿ አገልግሎትና በምእመናኗ ጽንዐ ሃይማኖት ህልውናዋን አንድነቷ ተጠብቆ መኖሩን ሁሉም የሚመሰክረው ታሪክ ነው።

ይህን ለዘመናት ተጠብቆ የኖረውን ሃይማኖቷን አንድነቷን ቀኖናዋን በመጣስ ዘረኛውና ጏሰኛው የወያኔ መንግስት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ውስጥ በመግባት ቅዱስ ሲኖዶስን በሁለት መልኩ ከፋፈሎት ይገኛል፣

ሲኖዶስ ማለት የሃይማኖት ፓርላማ ማለት ሲሆን እነሱም ፡ 1 - ትክክለኛው ወይም ስደተኛው ሲኖዶስ

2 - ህገወጡ ወይም የወያኔ ሲኖዶስ በመባል በሁለት መልኩ ይከፍላሉ;;

ይህም የሆነው በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 1984 አ ፡ም የወያኔ መንግስ ስልጣን ከያዘበት ጀምሮ ሲሆን

1=ትክክለኛው ወይም ስደተኛው ሲኖዶስ የሚባለው በደርግ መንግስት ጊዜ የነበሩት በብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬወስ ፓትሪያሪክ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የበላይነት የሚመራው ሲሆን የሚገኘውም በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ከተማ ውስጥ ነው፡

8

2= ህገወጡ ወይም የወያኔ ሲኖዶስ የሚባለው ደግሞ በቀድሞው ፓትሪያሪክ በብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትሪያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዬጵይ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ና የአለምአብያተክርስቲያናት ለሰላም የክብር ፕሬዘዳት በኢትዮዽያ አቆጣጠር ከ፪፻፭ ጀምሮ ደግሞ ከራሳቼው ጎሳና ዘር ያልወጡት በአቡነ ጳውሎስ ምትክ በተተኩት በአቡነ ማትያስ የበላይነት የሚመራው የወያኔ ሲኖዶስ ይባላል፡፡

አቡነ ጳውሎስ ማለት የወያኔ መንግስት ለፖለቲካውና ለቅርስ ዘረፋ እንዲመቼው በደርግ ጊዜ የነበሩትን ፓትሪያሪክ የኔ ጎሳና ዘር አይደሉም በማለት ከደርግ መንግስት ጋር ጥላቻ በማድረግ በፍጥነት ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መንግስታዊ ትዛዝ በማስተላለፈ ከፓትሪያሪክ ላይ ፓትሪያሪክ ያለምንም የሲኖዶስ ምርጫ በህገ ወጥ የወያኔ መንግስት ሹሙአቼዋል፣

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ

የፈጸሟቸው ዐበይት ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፦

ለዘመናት በአንድነቷ የምትታወቀው ቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ፓትርያርኩ ለግል ዝናና ስልጣናቸው ሲሉ በእልህ በሚፈጽሙት ድርጊት ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሁለት ተከፍላለች፡፡ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ በሚገኙ ምዕመናን መካከል ከፍተኛ ልዩነት ተፈጥሯል፡፡ በአባቶች መካልም በጥርጣሬና በጥላቻ ከመተያየት ባሻገር መወጋገዝን አስከትሏል፡፡ ይኸውም ዛሬ ከፈጠረው ችግር ባሻገር ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን ለትውልድ የሚተርፍ ከፍተኛ ፈተና ነው፡፡ ለዚህም አንዱና ዋናው ምክንያት ቅዱስ ፓትርያርኩ ምንም ዓይነት የእርቅና የስምምነት በር እንዳይከፈት በማድረግ ወይም በመዝጋት እርቅ እንዳይመጣ ሰላምም እንዳይወርድ

አፍነው በመያዛቸው ነው፡፡ ለምሳሌም በጥቅምት ወር 2000 ዓ.ም የቀረበውን የእርቅ ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ይጠቀሳል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሥራ አስፈጻሚነትና የአስተዳደር ሥልጣን በተመለከተ በሕገ ክርስቲያን አንቀጽ

30 ቁጥር 1 እስከ 21 እንደሰፈረው፡-

1. የቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደር በየጊዜው የሚወስናቸውን ጉዳዮች ከየቤተ

ክርስቲያናቱና ከልዩ ልዩ መ/ቤቶች የሚቀርቡትን ጥያቄዎች በሕጉ መሠረት መፈፀምና ማስፈፀም፣

9

2. ዋናውን መ/ቤት፣ የኮሚሽኑን፣ የቦርዶችን፣ የድርጅቶችንና የመምሪያዎችን በአጠቃላይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር የሚገኙትን የሥራ ዘርፎችን ሁሉ ማስተዳደርና መምራት፣

3. ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብ በትክክል ገቢ መሆኑንና በሕጋዊ መንገድ ወጪ እየሆነ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት መዋሉን መቆጣጠር፣

4. የመምሪያና የልዩ ልዩ ድርጅቶች ሓላፊዎችን እያጠና እና ፓትርያርኩን እያስፈቀደ መሾም፣ የሥራ ሓላፊዎችን የሥራ ዝውውርና ዕድገት በአስተዳደር ጉባኤ እየተጠና እየተወሰነ እንዲፈፀም ማድረግ፣

5. በየደረጃው ያለውን የሠራተኛ መብትና ግዴታ ማለትም የጡረታ፣ የጤና አጠባበቅ፣ የደረጃ ዕድገት፣ የፈቃድ አሰጣጥ፣ የዲስፕሊን ውሳኔ አፈጻጸም እና የመሳሰሉትን ሁሉ በሕጉ መሠረት መፈጸማቸውን መቆጣጠርና አመራር መስጠት፣

6. በበጀት የተመደበውን ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያኒቱ ንብረት በፊርማው ማንቀሳቀስ፣

7. ማናቸውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ገንዘብ ገቢና ወጪ በሕጋዊ የሂሳብ

አያያዝና ደንብ መሠረት መሠራቱን መታተልና መቆጣጠር. . . ወዘተ እንደሚያካትት ተደርጓል፡፡

ነገር ግን ይህን ድንጋጌ በመጣስና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ዋና ሥራ አስኪያጅ ስልጣን በመጋፋት ቅዱስ ፓትርያርኩ በማን አለብኝነት አመመራቸው የወደዱትን ለመጥቀም ሲሉ አላግባብ ሹመዋል፣ የደረጃ እድገት ሰጥተዋል፣ ቀጥረዋል፣ አዛውረዋል፡፡ በግል የጠሉትንም ከቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ውጪ ሽረዋል፤ ከደረጃ ዝቅ አድርገዋል፣ ደመወዝ አግደዋል፣ ከሥራ አባርረዋል፡፡ በዚህም የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብ ለከፍተኛ ብክነት ዳርገዋል፡፡

የሲኖዶሱን ሥልጣን በተመለከተ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 7 በቁጥር

11 እና 12 ላይ ማለትም፡-

• በውጭ አገር ለአገልግሎት የሚመደቡ እንዲሁም በአገር ውስጥ ትምህርት ተምረው የውጭውን ትምህርት መማር የሚችሉ ካህናትን እየመረጠ እንዲላኩ የማድረግ፣

• ማንኛውም ሰው ቤተ ክርስቲያኒቱን ወክሎ ለሥራም ሆነ ለጉብኝት ወደ

10

ውጭ አገር በሚላክበት ጊዜ ቅዱስ ሲኖዶስ እየፈቀደ መሆኑን ይደነግጋል፡፡

• እንዲሁም የፓትርያርኩን ሥልጣንና ተግባር በሚገልጸው አንቀፅ 15

ቁጥር 12 ላይ ፓትርያርኩ በውጭ ስብሰባ ለመገኘትም ሆነ ጉብኝት ለማድረግ በሚፈልጉበት ጊዜ ስለ ተልእኮው ጉዳይ አስቀድሞ በቅዱስ ሲኖዶስና ቋሚ ሲኖዶስ ማስወሰን እንደሚገባቸው ተደንግጓል፡፡

ነገር ግን ፓትርያርኩ ለቅዱስ ሲኖዶስ ባላቸው ንቀት ምልዓተ ጉባኤውን ሳያስፈቅዱ ክብረ ቤተ ክርስቲያንን በሚያስነቅፍ መልኩ ፕሮቶኮል ያልጠበቁ እንቅስቃሴዎችን አድርገዋል፡፡ ያለምንም ብቁ ምክንያትና ተልዕኮ በየጊዜው በቤተ ክርስቲያኒቱ ብር በተራ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት በተለያዩ ዓለማት አጀብ በማስከተል በመውጣት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብ ለስብከተ ወንጌል ከማዋል ይልቅ መንሸራሸሪያ አድርገውታል፡፡ በዚህም የድሀይቱን ቤተ ክርስቲያን ገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ እንዲባክን አድርገዋል፡፡

የታላላቅ ገዳማት አበምኔቶችና የታላላቅ አድባራት አስተዳዳሪዎች በየሀገረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት እየተመረጡ ሲቀርቡላቸው መዓርግ ስም እየሰጡ መሾም ሲገባቸው ከተሰጣቸው ሥልጣን ገደብ አልፈው ማንንም ሳይጠይቁ በመሾምና በመሻር ፓትርያርኩ ሕግን ተላልፈዋል፡፡ በተጨማሪም የተመደበ በጀት ይኑር አይኑር ሳይጠናና ሳይረጋገጥ “ዓላማዬን ያሳኩልኛል” ያሏቸውን ሰዎች ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት

ጽ/ቤትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በመላክ፣ በግዴታም እንዲቀበሉ በማስገደድ ከሕግ የወጣ ተግባር ፈጽመዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ሀገረ ስብከቱንና አድባራቱን የእዳ ተሸካሚ አድርገዋቸዋል የቤተ ክርስቲያኒቱ የሀገረ ስብከት አወቃቀር መሠረት የሚያደርገው የዞን አስተዳደርን ስለሆነ እንደ መንግሥት አወቃቀር ከክልል መስተዳድሮች ጋር በቀላሉ ተቀራርቦ ለመሥራት የሚያስችል አሠራር የለም፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት የመዋቅር ማስተካከያ ያስፈልጋል፡፡ በተለይም በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች ቤተ ክርስቲያኒቱን በክልል ደረጃ ሊወክል የሚችል አሠራር ተዘርግቶ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከየክልሎቹ መንግሥታት አሠራር ጋር በቀላሉ ተቀራርባ መሥራት የሚያስችላትን አወቃቀር መፍጠር ነበረባት፡፡ ሆኖም ፓትርያርኩ ስልጣኔን ይሸራርፍብኛል ከሚል አቋም ይህን ለመተግበር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ችግሩ እስከ አሁን ዘልቋል ጋጠ ወጥ በሆኑ ዘፈኖቿ በዓለም ዘንድ የምትታወቀውንና እነዚህ ዘፈኖቿን ኢትዮጵያ ውስጥ ለመዝፈን

11

የመጣችውን (ቢዮንሴ የምትባል) ዘፋኝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት የቤተ ክርስቲያንን፣ የአባቶችንና የምዕመናን ክብር በሚነካ መልኩ የፈጸሙት አሳዛኝ ታሪካዊ ስህተት የእርሳቸውን መንፈሳዊ መሪነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡ በእርግጥ ግለሰቧ ቤተ ክርስቲያንን መጎብኘት ከፈለገች እንደማንኛውም ጎብኚ ልትጎበኝ ትችላለች፡፡ ነገር ግን ያ ሁሉ የዐውደ ምሕረት አጀብ አስፈላጊ አልነበረም፡፡ እርሳቸውም ቢሆኑ መነጋገር ካስፈለጋቸው በእንግዳነቷ በቢሮአቸው ጋብዘዋት ማነጋገር ሲችሉ ብጹዓን አባቶችን ሰብስበው ለስምንት ሰዓታት ሙሉ በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ሲጠብቁ መዋላቸው የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር የሚያጎድፍና የምእመናንን አንገት ያስደፋ ተግባር ነው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን ፈቃድና እውቅና ሳያገኙና የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖና ሳይጠብቁ

አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን እንደ ቀበሌ ጽ/ቤት በመቁጠር የራሳቸውን ምስል ማስለጠፋቸውና ለዚህም የስዕል ሰሌዳ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብ ለግለሰቦች መበልጸጊያና ለብክነት መዳረጋቸው ቤተ ክርስቲያኒቱንና ምእመናንን ያሳዘነና በማሳፈር ላይ ያለ ጉዳይ ነው፡፡ ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሚያዝዘው መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ሳይፈቅድና አመራር ሳይሰጥ በራሳቸው የግል ፈቃድ ዝክረ ቤተ ክርስቲያን በማለት በሽልማት ስም ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ ሰዎችን በማሰባሰብ ግልጽ ባልሆነ መንገድ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም በርካታ ገንዘብ የገቢና ወጪ ሕጋዊ አሠራር በሌለው መንገድ ከቤተ ክርስቲያኒቱም ጭምር እንዲሰበሰብ አድርገዋል፡፡ በዚህም ምዕመናን ቤተ ክርስቲያኒቱን በጥርጣሬ እንዲመለከቷት በር ከፍተዋል፡፡ ከራስ ወዳድነታቸው የተነሳ ለራሳቸው ስጋዊ ዝና ሲሉም የቤተ ክርስቲያኒቱን ታሪክ በትውልድ ፊት አጉድፈዋል፡፡

በመከራ ውስጥ አልፎ የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርት ለተማረው ተገቢ ሥራ መደብ ከመስጠት ይልቅ ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደግል ድርጅት በመቁጠር በዘመድ አዝማድ ወይዘሮዎችና አቶዎች ወሳኝ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቦታዎች እንዲይዙ በማድረጋቸው ቤተ ክርስቱያኒቱን ለከፍተኛ ምዝበራና ውርደት አጋልጠዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሥነ ምግባር የሌላቸው ወይዘሮዎችን በማረም ፈንታ ሽፋንና ደጋፊ በመሆን ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ በደል እየፈጸሙ ነው፡፡

በቤተ ክርስቲያኒቱ ገንዘብና ንብረት ላይ በማን አለብኝነት በማዘዝ ዛሬ ቤተ ክርስቲያኒቱ በከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ላይ እንድትገኝ አድርገዋል፡፡

በአምባገነናዊ አስተዳደር ሂደታቸው የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ፈረሰ፣

12

ንብረት ተዘረፈ፣ ገንዘብ ተመዘበረ፣ ቀኖና ተፋለሰ፣ አድልዎ ነገሰ፣ የሰው መብት ተጣሰ፣ ወዘተ በማለት ማስተካከያና እርምት እንዲደረግ የሚጠይቁ ብፁዓን አባቶችን ለማስደንገጥ ከሀገረ ስብከታቸው ያነሳሉ፣ በጠላትነትም ይፈርጃሉ፡፡ በመንግሥት ባለስልጣናት ስምም ያስፈራራሉ፡፡

ከሀገር ውጭ ያለችውን ቤተ ክርስቲያን እንዲያገለግሉ ብቃት ያላቸውን ሰዎች ከመላክ ይልቅ በገንዘብና በዘመድ አዝማድ የሚላከው ይበልጣል፡፡ በዚህ መልኩ የተላኩት ብዙ ሰዎች ለቤተ ክርስቱያኒቱም ዕድገት ሳይሆን ከሃገር መውጣታቸውን ለግል ጥቅማቸው ማስፈጸሚያ በማድረግ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን በማዋረድ ምዕመናንን እያሳቀቁ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመ ነው፡፡

ለቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች በመጡ የተለያዩ የውጭ የትምህርት ዕድሎች ዘመዶቻቸውን በቤተ ክርስቱያኒቱ ስምና ገንዘብ ልከዋል፡፡ የሔዱትም ሰዎች አብዛኞቹ በዚያው ስለሚቀሩ የተያዩ ኤምባሲዎችና

ቆንስላ ጽ/ቤች ለቤተ ክርስቲያኒቱ ያላቸው እምነት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅ እያለ መጥቷል፡፡ ይህም ለቤተ ዘመድ የሚሠሩት ተራ ጥቅማ ጥቅም ቤተ ክርስቲያኒቱን ብዙ የውጭ ሀገር ሰዎች በዝቅተኛ አይን እንዲመለከቷት አድርጓል፡፡

በዘመነ ፕትርክናቸው ከምንጊዜውም በላይ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መዳከሙ ብቻ ሳይሆን መጥፋቱ ግልጽ ነው፡፡ ለዚህም አንዱ ማሳያ ቤተ ክርስቲያኒቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያላት የምዕመናን ቁጥር መቶኛ ድርሻ በተዓምራዊ ፍጥነት እየቀነሰ መምጣቱ ነው፡፡ በአንጻሩም የሌሎች እምነት

ተከታዮች በከፍተኛ ጥፍነት እያደገ መሆኑን የ1999 እና 2000 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የህዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት በግልጽ እያሳየን ነው፡፡

በሙስናና በተለያዩ ከፍተኛ ችግሮች በደል ተገኝቶባቸው ከመንግሥት በግምገማ የሚባረሩ አካላትን ከጥፋታቸው ሳይታረሙ ከነችግራቸው በማቅረብ ቤተ ክርስቱያኒቱን የዘራፊዎች ዋሻ አድርገዋልታል፡፡

ያለምንም ይሉኝታ በቤተሰብና በቤተዘመድ በእውቅና እንዲፈጸም በሚያደርጉት የቅጥር ሂደት ባለሙያዎችና ምሁራን በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ምንም ድርሻ አግኝተው ሙያቸውን ለቤተ ክርስቲያን ማበርከት እንዳይችሉ አድርገዋል፡፡

በየአህጉረ ስብከቶች የሚገኙ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቱያናት እየተዘጉ ካህናትና አገልጋዮቿ በረሀብና በመተዳደሪያ እጦት እየተሰደዱ

13

ባሉበት በአሁኑ ወቅት ፓትርያርኩ ግን ለዚህ አንዳች መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ስለራሳቸው ዝናና ክብር የህዝብ ግንኙነት ሥራ እንዲሠራላቸው

አሜሪካን ሃገር ለሚገኘው የሃገር ፍቅር ሬዲዮ አዘጋጅ 100‚000.00

(መቶ ሺህ ብር) እንዲሰጥ ማድረጋቸው ዕለት ዕለት የሚያስጨንቃቸው የራሳቸው ስምና ዝና መታወቅ እንጅ የቤተ ክርስቲያን ችግር መፍትሔ ማግኘቱ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ጋር ተያይዞ በሀገር ውስጥ በየክልሉ እንዲሁም ከሀገር ውጭ በሚፈጠሩ ችግሮች በስተጀርባ እርሳቸው የተለያየ የጥቅም ግንኙነት ስለሚያደርጉ ለችግሮቹ መፍትሔ ለመስጠት አስቸጋሪ ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡ ለችግሮቹ መፍትሔ ከስጠትም ይልቅ ችግሮቹ በተከሰቱበት ሀገረ ስብከት አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ በመግባት ግጭቶች እንዲባባሱ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

በተለያዩ ጊዜያት የቤተ ክርስቲያኒቱን የኢኮኖሚያዊ ልማት ተሳትፎ ያሳድጋሉ፣ ገዳማትንና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ከመዘጋት ያድናሉ ተብለው የታመባቸው የተለያዩ የልማት ፕሮጀክት ጥናቶች ለምሳሌ የቱሪዝም፣ የግብርናና ወዘተ ተግባራዊ እንዲሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ከተወሰነ በኋላ ሥራ ላይ እንዳይውሉ ሆን ብለው አምባገነናዊ ሥልጣናቸውን በመጠቀም ተዳፍነው እንዲቀሩ አድርገዋል፡፡

ፓትርያርኩ በሚሰጧቸው የልብ ልብ ስለ ፓትርያርኩ እንጂ ስለ ቤተክርስቲያን የማያውቁና የማይጨነቁ ቤተ ዘመዶቻቸው ሊቃነ ጳጳሳትን ሳይቀርና እውነተኞች የቤተ ክርስቲያኒቱን አገልጋዮች እየገላመጡ እና እያሳቀቁ ነጻነት እንዳይሰማቸው ያደርጋሉ፡፡

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንና የኪራይ ቤቶች አስተዳደር የገንዘብ ስርጭት እና አጠቃቀም ላይ የእርሳቸውን የግል ጥቅም በሚያስከብር ስውር መንገድ የሚሠራበት ሁኔታ በመኖሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለከፍተኛ ሙስና እየዳረግዋት ነው፡፡ ለምሳሌ ቢያንስ በወር ውስጥ ለግል ጥቅማቸው ህጋዊ ባልሆነ አሠራር ከቤቶች ኪራይ እስከ

10‚000.00 (አሥር ሺህ) ብር ይወስዳሉ፡፡ ይህም በቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብት ላይ በማን አለብኝነት እንደፈለጋቸው እያዘዙ መሆኑን በግልጽ ያሳያል፡፡

የቤተ ክርስቲያኒቱን ሚዲያዎች በተገቢው መንገድ አደራጅቶ ለምዕመናን የማስተማሪያ እና ቤተ ክርስቲያኒቱን ማስተዋወቂያ መንገድ ከማድረግ ይልቅ ያለምንም ኤዲቶሪያል ፖሊሲና ግልጽ አሠራር ለራሳቸው

14

መጠቀሚያ እንዲሁም ማሳደሚያ አድርገዋቸዋል፡፡ ይህም ሰዎችን ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ የተሳሳተ ስዕል እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡

፨ በ 1997 በነበረው የወያኔ ምርጫ በኃላ በተፈጠረው የምርጫ ማጭበርበር ውጤት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ቤተ ክርስቲያን ለመፀለይ በገቡበት ሰአት እናንተ በምርጫ ሰአት መንግስትን ስትቃወሙ የነበራችው ናችው በማለት ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመደወል ተማሪወቹን ከሚፀልዩበት ቦታ ላይ በፖሊስ በማስደብደብ ቶሎ ለቀው እንዲውጡ አድርገዋል፣

፨ በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ትላልቅ ቤተ ክርስቲያኖች ውስጥ ለቅርስና ንብረት ዘረፋ እንዲመቻቼው የራሳቼውን ዘርና ጎሳ የትግሬኛ ተናጋሪ የሆኑትን ሰዎች በመምረጥ በአለቅነት ይሾማሉ፣

፨ በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ትላልቅ ቤተ ክርስቲያኖች መግቢያ በር ላይ የራሳቼውን ፎቶ በትልቁ አሰርተው በመትከል ህዝቡ ቤተ ክርስቲያን በሚሳለምበት ጊዜ ቤተ ክርስቲያንኑን ትቶ ለእሳቼው ፎቶ እንዲሰግድ በማድረጋቼው ህዝቡ ፎቶው ይነሳልን ብሎ ጥያቄ ቢያቀርብም ተቀባይነት አቶ ይሄው እስካውን ድረስ ባለበት ይገኞል፣

፨ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ መድኃኔ አለም ቤተ ክርስቲያን መግቢያ በር ላይ በህይዎት እያሉ ጥሩ ስራ እንደሰራ ሰው በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ከየ ቤተ ክርስቲያኖች ወጭ በማስደረግ የራሳቼውን ምስል የሚያሳይ ሃውልት ያለማንም የህዝብ ፈቃድና የሲኖዶስ ፈቃድ በራሳቼው መብት ሃውልት አሰርተዋል፣

፨ በተወሰነ አመትም ጳጳሳትን በግድ የኔ ደጋፊ ካልሆናችው በማለት በፌዴራልና በመንግስት ደህንነቶች አስገርፈዋል በጥቂቱ እነ አቡነ ሳሙኤል እነ አቡነ ይሳቅ በምሳሌነት የጠቀሳሉ፣

፨ በውጭ ሃገር በተሰደዱ ጳጳሳት ስም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤተ ክርስቲያ ቃለአዋዲ በሚያዘው ቀኖና ህግ መሰረት ትዛዙን በመሻር አንድ ጳጳስ የሚሾመዉ ሲሞት ብቻ ነበር እሳቼው ግን የማን አለብኝን መብት በመመካት ከሹመት ላይ ሹመት ሰጥተዋል ኣቡነ መልከ ፄዴቅ ኣቡነ ዜና ማርቆስ አቡነ ኤልያስ በሚባሉ ዻዻሳት ስም መሰየማቼው በምሳሌነት ይጠቀሳሉ፣

፨ በአንድ ወቅት በጉራጌ ዞን እስላሞች አላህ ወአክብር እያሉ ቤተ ክርስቲያኗን

15

ሲያቃጥሏት እርሳቼው እንደ ቤተ ክርስቲያን የበላይ ሃላፊነታቼው በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት እርምጃ አልዎሰዱም ምክንያቱም መንገስት በሃይማኖት ጦርነት ህዝቡ ይነሳብኛል ብሎ ስለሚይስብ በሚድያ እንዳይነገር ትዛዝ አስተላልፈዋል፣

፨ በተለያዩ የውጭ አለማት ወላጆቻቼውን ላጡ ህፃናት ና ለተቼገሩ የገጠር ቤተ ክርስቲያናት ገዳሞች አድባራት በእርዳታ የሚላከውን ብር ና በትላልቅ ሃብታም በተባሉ ቤተ ክርስቲያኖች የሚገባውን ገንዘብና ንብረት በመዝረፍ ለግላቼው

ለህይወታቼው መጠበቂያ የሚሆን መሳሪያ የማያስመታ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጭ በማስደረግ መኪና ገዝተዋል፣

ይህ ሲደረግ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ምክንያቱም ከዚህ በፊት በህይዎት ያልፉት አባቶች እንኩአን እንደዚህ አይነት መኪና ሊገዙ ቀርቶ ለእግራቼው ጫማ እንኩአን

አይለብሱም ነበር እነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በምሳሌነት ይጠቀሳሉ በገጠሩ ዙሪይ

16

ሰንቶቹ ናቼው የቆርቆሮ ክዳን አጥተው በእሳር ክዳን የሚገኙት ሰንቶቹ ናቼው መቀደሻ ልብስ የሌላቼው መብራት እጣን ጧፍ ዘይብ የተለያዩ የቤተ ክርስቲያን መገልገያ አጥተው በችግር የሚሰቃዩት እርሳቼው ግን ለራሳቼው ወገኖችና ዘሮች ብቻ ነው የሚጠቅሙት፣

፨ ሆንብለው ከመንግስት ጋር አብረው በመስራት የአማራውን ታሪክ ከጥንት ጀምሮ የነበረውን ለማጥፋት ና መቀሌ አክሱም የተባለችውን የትውልድ ቦታቼውን ለማሳደግ ታሪካዊ የትምህርት ቦታዎችን ከጎንደር ወደ አክሱም ለመውሰድ ሞክረዋል ለዚህም የቅድስት ቤተልሔም የድጋ ምስክር ትምህርት ቤት በምሳሌነት ይጠቀሳል፣

አቡነ ጳውሎስ

፨ የተለያዩ ትላልቅ ሃገራዊ ጉዳዮችን ሲወስኑ እንደስርአቱ የነበረበት በመላ ሲኖዶስ ሁሉም የሃገረ ስብከቱ ሊቀጳጳሳት ባሉበት ማስዎሰን ሲገባቼው እርሳቼው ግን መንግስትንና ስልጣናቼውን መከታ በማድረግ የራሳቼውን ቤተሰቦችና ትግሬዎችን ሰብስበው በመያዝ ውስጥ ለውስጥ ያስወስናሉ.

ቤተሰቦቻቼውንም በየ ቁልፍ ቦታዎች ላይ በማስገባት የታወቁ ነበሩ እነ ንቡረእድ ኤልያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ስራ አስክያጂ፣ዋና ፀሐፊ ያሬድ፣

የሊቃውነት ጉባኤ ጉሃፅባ የተባሉት በጥቂቱ በምሳሌነት ይጠቀሳሉ፣

፨ የነዚህ ፓትሪያሪክ ስርአት ያልተለመደና ከኣንደ ሃይማኖት መሪ አባት የማይጠበቅ ስራ ሲሰሩ ኖረዋል አሁንም በህይዎት ቢያልፉም ስራቼው

በዘሮቻቼው ቀጥሏል..

፩ ትክክለኛው ወይም ስደተኛው ሲኖዶስ የሚባለው በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ የ ሚገኘው ሲሆን

ወያኔዎች ሲገቡ በጊዜው ስልጣኑን የ ያዘው መንገስት ጠቅላይ ሚኒስተር

የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ ከቅዱስ ፓትሪያሪኩ ጋር አብረን አንሰራም

17

በማለታቼው ሁኔታው እስኪረጋጋ ድረስ መንግስትም ማስተዋል እስኪያገኝ ጊዜ

ለመስጠት ነሃሴ 28 ቀን 1983 አ ም ሲኖዶስ ስራውን እያከናወነ እርሳቼው ግን

ፀሎትና ቡራኬ እያደርጉ እንዲቆዩ በከፍተኛ የመንግስት ተፅኖ ተወሰነ፡

መስከረም 28 ቀን 1984 አ ም ቅዱስ ፓትሪያሪኩ አቡነ መርቆሬዎስ ያለአግባብ

መንበረ ፓትሪያሪኩን ለቀው እንዲዎጡ በቁጥር 69፣298፡84 ከመንግስት

ባለስልጣን ትዛዝ ደረሳቼው፡፡ ቅዱስ ፓትሪያሪኩ መስከረም 30 ቀን 1984 አ

ም ክ መንበረ ፓትሪያሪኩ ተገደው በዎታደሮች ተገደው በመውጣት በአዲስ

አበባ ከተማ ለ አንድ አመት ያክል ባልታዎቀ ቦታ ተቀመጡ፡

ቅዱስ ፓትሪያሪኩም ጥር 15 ቀን 1984 አ ም የሽጝሩ መንግስት ፕሬዜዳት

ለነበሩት ለአቶ መለስ ዜናዊ እና ለጠቅላይ ሚንስቴ ለአቶ ታምራት ላይኔ

ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለጠቅላይ ቤተ ክነት ዋና ስራ አስኪያጅ በፃፉት

ደብዳቤ ሃዋሪያዊ ተልኩአቼውን ለማከናወን የሚከለክል አንዳችም

የህመምችግር እንገሌለባቼው ስራቼውንም በሚገባ መስራት እንደሚችሉ

ይህንንም የቅዱስ ሲኖዶ አባላት እንደሚአውቁ በደብዳቤም ቢገልፁ ይህ ሁሉ

ቅዱስ ፓትሪያሪኩ ጥረት ከምንም ሳይቆጠር በማን አለብኝናቀኖና ቤተ

ክርስቲያን ተጥሶ አባ ጳውሎስ ሃምሌ 5 ቀን 1985 አ ም ላይ በፓትሪያሪክነት

ተሰየሙ ፡

አቡነ መርቆሬዎስም የ ቤተ ክርስቲያን ልጆች አጅበዋቼው በሞያሌ በኩል ወደ

ኬንያ ጎረቤት ሃገር ጥቅምት 1 ቀን 1985አ ም ተሰደዱ፡፡ አያይዘውም

በጥቅምት ወር 1985 አ ም በወያኔ መንግስት ምክንያት ሃገር ለቅቄ ተሰድጄ

ብዎጣም ህጋዊ የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት

ፓትሪያሪክ እስከሞት ድረስ እርሳቼው እንደሆኑ ለመላው የኢትዬጵያ ህዝበ

ርስቲያን በራዲዮና በጋዜጣ በይፋ አባታዊ መልክታቼውን አስተላለፉ፡፡ ከዛም

በዋላ አሜሪካ ሃገር በመግባት ቅዱስ ሲኖዶስን በስደት ሃገር አቋቋሙ፡

ከቅድስት ኢትዬጵያ ሃገራቼው የተሰደዱ ሊቀ ጳጳሳት

ስም ዝርዝር

፩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትሪያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ

ኢትዬጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

፪ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሃፊ

18

፫ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ሊቀ ጳጳስ

፬ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ ሊቀ ጳጳስ

፭ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የአውሮፓና የአፍሪካ ተወካይ ሊቀ ጳጳስ ሲሁኑ በአሁኑ

ሰአት በውጩ አለማት በአሜሪካና በአውሮፓ እንዲሁም በአፍሪካ ውስጥ

እነዚህ አባቶች ሰደትን ተቀብለው የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ

ክርስቲያን አማንያን ባሉበት በክፍለ አለማት ዙሪያ ቅዱስ ሲኖዶስን በማቋቋም

የሊቀ ጳጳሳትንና ኤጲስ ቆጶሳትነት የቅስና ዲቁና ስልጣን ና ሹመት በመስጠት ና

በየቦታው በመወከል እየተዘዋወሩ የቅዱስ ወንጌል ስርአት ትምህርት እንዲሁም

በቅዳሴ በፍትሃት በጥምቀት የተለያዩ መፈሳዊ አገልግሎት ኢትዮጵያ ውስጥ

እንደሚሰጠው ባላነሰ መልኩ በየቦታው ቤተ ክርስቲያን በማቋቋም የቤተ

ከርስቲያኗን ህግና ስርአት በመጠበቅ መልኩ መንፋሳዊ አገልግሎት ና ሃዋርያዊ

ተልኩአቼውን እያከናወኑና እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

እግዚአብሄር አምላክ የወያኔን መንግስት በቃህ ብሎ በስደት ያሉትን

አባቶቻችንን በሰላም ለቅድስት ሃገራቼው ያብቃቼው አሜን፡፡

19

ሚ ላዕሌነ፤ ምን ገዶን?

ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ “አሜሃ ይከውን ኃዘን ዘኢይበቊዕ ኃዘን = ያን ጊዜ ኃዘን

ይሆናል ግን የማይጠቅም ኃዘን ነው” እንዳለ የማይጠቅም ኃዘን የሚያዝኑ

ብዙዎች ናቸው። ከነዚያው ዘንድ ቅሉ ይሁዳ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው።

ይሁዳ በፈጸመው እኩይ ግብር ኃዘን በተሰማው ጊዜ የሄደው ወደ ካህናቱ

አለቆችና ወደ ሕዝቡ ሽማግሎች ነበር። በደሉንም መናዘዝ የጀመረው በደልን

ፀነሰው፣ ወልደውና አሳድገው ለመዓርገ ሞተ ነፍስ ላደረሱና ላበቁ ፈሪሳውያን

ነበር። በማቴዎስ 23፥15 “አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፣

በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት

ወዮላችሁ” ተብሎ እንደተጻፈ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ይሁዳን በክፉ ግብራቸው

አጥምቀው የነሱ ፈጻሜ ፈቃድ/ፈቃድ ፈጻሚ ለማድረግ ብዙ ደክመዋል።

ጨርሶ የድኅነት በር እንዳይከፈትለት አድርገው ለገሃነም ዳርገውታል። “ከጥፋት

ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም” እንዳለ ወንጌለ ዮሐንስ። (ዮሐ 16፥12)

20

ወደ እነዚህ ሰዎች ዘንድ ሄዶ ነው ይሁዳ ብሶቱን ለመግለጽ የሞከረው። የብዙ

ጊዜ ሕልማችን ግቡን የመታው በዚህ ሰው ተሳትፎና ትብብር ነው ብለው ጊዜ

ሰጥተው ሊያነጋግሩትና ሊያጽናኑት ፈቃደኞች አልነበሩም። እነሱ ምን

ገዷቸው። ቢገዳቸውማ ንጹሕ እንዲፈስ ደሙ በእኛ በልጆቻችን ላይ ይሁን

ብለው ይምሉ ነበርን? እነሱስ ይሁን ወደው በፈጸሙት ነው። ልጆቻቸው ምን

አደረጉ? ኧረ ወዲያ እነሱ ምን ገዷቸው።

ዛሬም ይህንኑ ታሪክ በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደገሙ ያሉ ሰዎች አሉ። እነዚህ

በአየርም በመሬትም፣ በየብስም በባሕርም፣ በአራቱ ማዕዘን ሁሉ ይዞራሉ።

ዓላማቸውም የሚቻል ከሆነ ቤተ ክርስቲያንን ከመሠረቷ አፈራርሶ መጣልና

ትውልዱ የሚረከበው ሐዋርያዊ ትምህርተ ሃይማኖትና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን

እንዳይኖር ማድረግ ነው። ይህን በማድረጋቸው ምን ይጠቀማሉ ቢሉ? ምን

ገዷቸው የሚል ነው መልሱ። ቤተ ክርስቲያኒቱ ልብስ ጉርስ ሰጥታ፣ ጉባኤ

ዘርግታ፣ መምህር መድባ፣ የአገልግሎት መድረክ ሰጥታ ለቁም ነገር

ካበቃቻቸው በኋላ “ዘይሴሰይ እክልየ አንሥአ ሰኰናሁ ላዕሌየ፤ እህሌን

የተመገበ ሰኰናውን በኔ ላይ አነሣ” እንዳለ ነቢዩ በሌሊት ከቤተ ጉባኤ እየወጡ

ቤተ ክርስቲያን ሞታ የምትቀበርበትን ጉድጓድ ሲቆፍሩ ያድራሉ። በውስጣቸው

ነጣቂ ተኵላዎች ሆነው ሳለ የበግ ለምድ ለብሰው ከእውነተኞቹ አገልጋዮች ጋር

ተሰልፈው ይቆማሉ። እንኳን እግዚአብሔር እኛም አውቀናቸዋል። እስከ መከር

አብረው ይደጉ የሚል አምላካዊ ቃል ስላለ የመከሩን ዘመን እየጠበቅን ነው

እንጂ። ወይ ግሩም! መከሩማ ዕለተ ምጽአት አይደለምን የሚል ቢኖር አዎ

እርግጥ ነው ግን እግዚአብሔር ሰይፈ በቀሉን በመናፍቃን ላይ የሚያነሣበት ጊዜ

ሁሉ መከር ነው ብለን እንመልሳለን። ጉባኤ ኒቂያ፣ ጉባኤ ቁስጥንጥንያ፣ ጉባኤ

ኤፌሶን የመከር ወቅቶች ነበሩና። ከስንዴው ጋር አብረው አድገው የነበሩ

እንክርዳዶች በጥብዓተ ሃይማኖትና በነገረ ሃይማኖት ማጭድ እየታጨዱ በቃለ

ግዘት ታስረው ወደማይጠፋው እሳት ተጥለዋልና።

ፈሪሳውያን ከቤተ መቅደስ እንዲወጣ ያደረጉት በይሁዳ እጅ ላይ የነበረውን

ሠላሳ ብር ነው። (የሰጡት እነሱ መሆናቸው ሳይዘነጋ) የዛሬዎቹ አጽራረ ቤተ

ክርስቲያን ግን እነሱ ከሚሞነጫጭሯቸው ምኑናት/የተናቁና የተዋረዱ

መጣጥፎቻቸው በቀር ምንም አይነት ነገር በቤተ ክርስቲያን እንዲኖር

አይፈልጉም።

እስቲ ከሞነጫጨሯቸው አንዱን እናንሣ። «ፋሲካችን ማነው? ክርስቶስ ወይስ

ማርያም» የሚለውን ጥያቄ በማንሣት በበዓለ ሃምሳ ቅድመ ጸሎተ ኪዳን

21

የሚደርሰውን «ለአዳም ፋሲካሁ፤ የአዳም ፋሲካ» የሚለውን የምስጋና ክፍል

ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድርሰት ነው በማለት ካህናቱ ምሥጢሩን ሳይረዱ፣ ምን

ያህል ስህተት እንደሆነ ሳይገነዘቡ በልማድ በዜማ ስለሚሉት የዚህ ድርሰት

ችግር ሳይታያቸው ያለምንም ቅሬታና መሳቀቅ አፋቸውን ሞልተው ያዜሙታል

እያሉ የድንቁርናቸውን ጣሪያ ያሳዩናል። ምን ገዷቸው። «ልጅ ለናቷ…» አይደል

የተባለው። ካህናቱ የዚህ ኃይለ ቃል ምሥጢር ካልገባቸው እነሱን ከሰማይ

መልአክ ወርዶ አስተምሯቸው ነው? ወይስ እነርሱ ራሳቸው ከሰማይ ወርደው

ይሆን? ይህ ሥርዓት የሚከናወነው በአንድ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ብቻ ቢሆን

ጥያቄያቸው ለውይይት በቀረበ ነበር። ነገር ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

ቤተ ክርስቲያን ባለችበትና ካህናቶቿና ምእመናኖቿ ባሉበት የሚከናወን ልዩ

ሥርዓተ ጸሎት ነው። አስተውሉ! «ካህናቱ» የሚለው ቃል ከላይ እስከታች

ያሉ አገልጋዮችን የሚወክል ቃል ነው። እንዳው በኔ ሞት አላዋቂ ማነው?

መልሱን ለአንባቢ።

ፋሲካ ማለት ምን ማለት ነው?

1· እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ ብሎት ነበር። «ትበልዕዎ በጒጒዓ እስመ

ፋሲካሁ ለእግዚአብሔር = የእግዚአብሔር ፋሲካ ነውና በፍጥነት

ትመገቡታላችሁ» ዘጸ 12፥11፤ የእግዚአብሔር ፋሲካ የተባለው እስራኤል

በቤታቸው የሠዉት በግዓ ፋሲካ ነው።

ዕዝራም «በሙሴ መጽሐፍ እንደተጻፈው በኢየሩሳሌም ባለው በእግዚአብሔር

አገልግሎት ላይ ካህናቱን በየማዕርጋቸው ሌዋውያኑንም በየክፍላቸው አቆሙ

ምርኮኞቹም በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ፋሲካውን አደረጉ

ካህናቱና ሌዋውያኑም አንድ ሆነው ነጽተው ነበር። ሁሉም ንጹሐን ነበሩ

ለምርኮኞቹም ሁሉ፣ ለወንድሞቻቸውም ለካህናቱ፣ ለራሳቸውም ፋሲካውን

አረዱ» ብሏል። ዕዝራ 6፥18-20፤

ስለዚህ በዚህ ክፍለ ንባብ መሠረት ፋሲካ ማለት አንደኛ፦ በዓልን

የሚያመለክት ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ለበዓሉ የሚቀርበውን መሥዋዕት

ያመለክታል።

2· ደስታ ማለት ነው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ «ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐፂባ

በደመ ክርስቶስ = ምድር በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካን ታደርጋለች» ብሎ

ዘምሯልና። የዚህ ክፍለ ንባብ ምንጭ «ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትሐሠይ ምድር =

22

ሰማይ ደስ ይለዋል ምድርም ደስ ይላታል» የሚል ነው። ሥረወ ቃሉም

የሚገኘው በኢሳይያስ 44፥23 ላይ ነው። ስለዚህ ፋሲካ ማለት ደስታ ማለት

ነው።

3· ማዕዶት ወይም መሻገሪያ ማለት ነው። «ፋሲካ ብሂል ማዕዶት ብሂል

በዘቦቱ ዓዶነ እሞት ውስተ ሕይወት = ፋሲካ ማለት ከሞት ወደ ሕይወት

የተሻገርንበት ማዕዶት ማለት ነው» ብሎ እንደዘመረ ቅዱስ ያሬድ።

4· ቀዳማዊ ሕግ ማለት ነው። «ዛቲ ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ = ይህች ፋሲካ የሕግ

መጀመሪያ ናት» እንዲል።

5· የትንሣኤው መታሰቢያ ነው። «ፋሲካ ፋሲካ ፋሲካ ተዝካረ ትንሣኤሁ

ለመድኃኒነ = ፋሲካ የመድኃኒታችን የትንሣኤው መታሰቢያ ናት» እንዲል።

6· ትንሣኤ ማለት ነው። «ትንሣኤ ሰመያ ለበዓለ ፋሲካ = የፋሲካ በዓልን

ትንሣኤ ብሎ ሠየማት» እንዲል። ትንሣኤም ሁለት አይነት ነው። ትንሣኤ

ልቡናና ትንሣኤ ዘጉባኤ። በውኑ መንፈሳዊ እረፍትና ደስታ ለማግኘታችንና

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደእኛ ለመምጣቱ ምክንያት እመቤታችን

ቅድስት ድንግል ማርያም አይደለችምን? ፀረ ማርያም አቋም ያላቸውና ነዳያነ

አእምሮ የሆኑ ይህ አይዋጥላቸውም ይሆናል። ለነገሩ ምን ገዷቸው።

ከላይ ፋሲካ ማለት ቀዳማዊ ሕግ ማለት ነው ማለታችን ይታወሳል።

የመጀመሪያውን ቃለ ብሥራት በመስማት እመቤታችን ዓለሙ በኃዘን

እንዳይጠፋ «ይኩነኒ = ይደረግልኝ» በማለት ቀዳማዊት አይደለችምን። ከሷ

ተወልዶ ዓለሙን ከወደቀበት መርገም እንደሚያድነው ሲነግራት እራሷን

አሳልፋ አልሰጠችምን? ከዚህ በላይ ፋሲካ መሆንና መባል ከወዴት አለ? ልጇን

እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስን ራሱን ለመስቀል አሳልፎ በመስጠቱ ፋሲካችን

ስንለው እሷንም ለእግዚብሔር ፈቃድና ዓላማ ለእኛም የዘለዓለም ሕይወት

ምክንያተ ድኅነት ለመሆን ራሷን አሳልፋ ስለሰጠች የአዳም ፋሲካ እንላታለን።

ሌላው ይህን ክፍለ ጸሎት ለመንቀፍ የተዘጋጁ ሰዎች የራሳቸው የሆነ ችግር

አለባቸው። የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል፦

1፣ ይህ ጸሎት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚጸለው በቃል ነው። በቃል ለማጥናት

ደግሞ ትጋትና ማስታወስ አስፈላጊ ነው። እነዚህ ሰዎች ሙሉ ጊዜያቸውን

23

የሚያውሉት ለከንቱ ወሬና ለከርሣቸው የሚሆን ፍርፋሪ ለመፈለግ ስለሆነ

አይሆንላቸውም። ከሊቃውንቱ ጋር አብረው ቆመው መጽሐፍ ዘርገተው ቢታዩ

ደግሞ ውርደት ይመስላቸዋል። እነዕገሌ ሁሉ በቃላቸው ነው ምነው እናንተስ

ከሚለው ጥያቄ መሸሽ ይፈልጋሉ። ከማን አንሼ አይነት ነገር ይመስላል።

2፣ የአገልግሎት ፍቅርና መንፈስ ጨርሶ የላቸውም። እንቅልፋሞችም ናቸው።

ተርእዮ ይወዳሉ። ሰው በሚበዛበት ጊዜና መድረክ እንጂ መገኘት የሚፈልጉት

በተመስጦ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር በሚቀርብ አገልግሎት መገኘት አይወዱም።

ማን ሊያያቸው። ቀድማችሁ ገብታችሁ አገልግሉ እንዳይባሉ አገልግሎቱን

ማጥላላት ምርጫቸው ሆነ።

3፣ እኩይ ዓላማቸውን ለማሳካት አይመቻቸውም። ለምሳሌ «ተፈሥሒ ማርያም

ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ ዓፅመ ገቦሁ» የሚለውን

ሲጠቅሱ «እስመ ግእዛኖሙ ኮነ ለወልድኪ በትንሣኤሁ = በልጅሽ ትንሣኤ

ነፃነታቸው ተደርጓልና» የሚለውን መጥቀስ አይፈልጉም። በትርጓሜያችን

መጽሐፍ ጭብጡን አይለቅም ለሸፋጭ ለለዋጭ አይመችም የሚል ሐተታ

አለ። ለሸፍጣቸው ስለማይመቻቸው ለማጥፋት የቻሉትን ያህል ይደክማሉ።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ፋሲካ» የተባለው በለበሰው ሥጋ

ነው። ይህም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ «ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር

ዘየአትት ኃጢአተ ዓለም = የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ

እነሆ» በማለት የተናገረውን የሚተረጉም ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት እግዚእነ

ኢየሱስ ክርስቶስን «በግ» እያሉ ሲገልጹት እሱ ራሱ በርሱ ያመኑ ምእመናን

«በጎች» በማለት ይጠራቸዋል። ይህ ማለት የምእመናን «አባግዕ» መባልና

መሆን የክርስቶስን ስፍራ ይይዛል ወይም ይተካል ማለት አይደለም። ለዚህ

ነው ሊቁ «ለአዳም ፋሲካሁ» ካለ በኋላ «እስመ ግእዛኖሙ ኮነ ለወልድኪ

በትንሣኤሁ = በልጅሽ ትንሣኤ ነፃነታቸው ተደርጓልና» በማለት ማስረጃ

ያስቀመጠው።

ቅዱስ ኤፍሬምም በቀዳሚት ውዳሴው «ትትፌሣሕ ገነት እመ በግዕ ነባቢ

ወልደ አብ ዘይነብር ለዓለም = ለዘለዓለም ጸንቶ የሚኖር የአብ ልጅ የተናጋሪው

በግ እናት ገነት/እመቤታችን ደስ ትሰኛለች» ብሏል። እናቱ ስትደሰት የማይደሰት

ልጅ የለምና። «ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ» ብሎ የገባለትን ቃል

የፈጸመለት ከእመቤታችን ሰው በመሆን ነውና። እባብ የሞቱ ምክንያት እንደሆነ

ሁሉ እመቤታችንም የድኅነቱና የፋሲካው ምክንያት ናትና።

24

ሊቃውንት በየድርሳናቸው «ትምክሕተ ኵልነ፣ አንቲ በአማን ምክሐ ዘመድነ፣

ትክምሕተ ዘመድነ በወሊዶተ ዚአከ = የሁላችን መመኪያ፣ አንቲ የባሕርያቺን

መመኪያ ነሽ፣ አንተን በመውለዷ የባሕርያችን መመኪያ ናት» እያሉ የገለጿት

የአዳም ፋሲካ/ደስታ በመሆኗ ነው። እግዚአብሔር ከሰማይ ወደምድር

በተመለከተ ጊዜ እሱን የሚፈልግ ጠቢብ ሰው አለማግኘቱን ቅዱሳት መጻሕፍት

ይመሰክራሉ። መዝ 13፥2፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ለአዳም የገባው ቃል ኪዳን

የሚፈጸምበት ዘመን ሲደርስ መልአኩን ልኮታል። «ወበሳድስ ወርኅ ተፈነወ

ገብርኤል መልአክ እምኀበ እግዚአብሔር = በስድስተኛው ወር መልአኩ ቅዱስ

ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ» እንዳለ ወንጌለ ሉቃስ። ሲያበሥራትም

«ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ = ደስ የተሰኘሽ

ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ» በማለት

ነው። ስለዚህም ድንግል ማርያም የአዳም ፋሲካ/ደስታ ናት።

ቅዱስ መጽሐፍ ሔዋንን «የሕያዋን ሁሉ እናት» (ዘፍ 3፥20) ብሎ ሲጠራት

እመ ሕይወት ድንግል ማርያምን ፋሲካ ብንላት አላዋቂነት ነውን?

ቸር ወሬ ያሰማን፤

አሜን;;

25

ዋልድባ ገዳም

የኢሕአዴግ መንግሥት በዋልድባ እና አካባቢው በግድብ ሥራ፣ በፓርክ

እና በስኳር ፋብሪካ ግንባታ ስም የሚያካሒደውን የገዳሙን ድንበር፣ ትውፊት

እና መንፈሳዊ ይዞታ የመግፋት መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ በመቃወም ላይ ላሉ

ገዳማውያን አበው እና እመው

“በዋልድባ ጉዳይ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድነት እንቆማለን፣ ጳጳሳት ውሳኔያችሁ

ይሰማ፣ የአባቶቻችን ርስት ተጠብቆ ለትውልድ ይተላለፍ፣ የገዳማት

አባቶቻችን መብት ይጠበቅ፣ መንግሥት የመነኮሳቱን ድምጽ ይስማ፣ ዋልድባ

የቅዱሳን እንጂ የኢንቨስተር አይደለችም፣ አባቶቻችን ያስቀመጡልን ገዳማት

ሲፈርሱ ዝም አንልም፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ዝምታችሁ ይብቃ፣ ገዳማትን

የሚያፈርስ መንግሥት አንፈልግም፣ የሥልጣኔ ምንጭ የሆነች ቅድስት ቤተ

ክርስቲያን መብቷ ይከበርላት፣ ገዳማት የጸሎት ቦታ እንጂ የመዝናኛ ቦታዎች

አይደሉም፣ አድባራትንና ገዳማትን ማጥፋት ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነው፣

የአባቶቻችን ተረፈ፡አጽማቸው ይከበር፣ አጽማቸውን ቆፍሮ ማውጣት ይቁም፣

ልማት ገዳማትን በማፍረስ አይመጣም፣ ሃይማኖታችን የማንነታችን መገለጫ

ነው፤ ሃይማኖት ከሌለ ሀገር አይኖርም፣ ገዳማት የሚያፈርስ መንግሥት

ተቀባይነት የለውም፣ ቅዱስ ሲኖደስ የገዳማትን ይዞታ የማስከበር ግዴታ

አለበት፣ ገዳማትን ማጥፋት በታሪክ ያስጠይቃል፣ ገዳማትን የሚያፈርሱ

አይከበሩም፣ ዋልድባን ለማጥፋት የሚሞክሩ ይጠፋሉ፣ ገዳማቶቻችን ታሪካችን

ናቸው፣ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ለሃይማኖታቸው ዝም አይሉም፣ መንግሥት

ሃይማኖታችን ከማጥፋት ይቆጠብ፣ አጥፊዎች ለፍርድ ይቅረቡ”

ቅዱሳን አበው እንደ ጽፍቀተ ሮማን የሰፈሩበት፣ እንደ ምንጭ የሚፈልቁበት

ገዳሙ እመቤታችን ከልጇ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ

ስደት ወቅት በኪደቱ እግር ከረገጧቸው መካናት አንዱ ነው፡፡ በወቅቱ ጌታችን

የወይራ ተክል ተክሎና አለምልሞ አርኣያ ስቅለቱን ገልጾበታል፤ ለቅዱሳኑ “እንደ

ኢየሩሳሌም ትኹንላችሁ፤” ብሎ ቃል ኪዳን በመስጠት እህል እንዳይዘራባት፣

ኀጢአት እንዳይሻገርባት፣ ከድንግል አፈሯ የተቀበረ እንዳይወቀስባት

እንዳይከሰስባት አዝዟል፡፡ በሰሜን ተራራዎች ግርጌ ዙሪያዋን በሰሜን አንሴሞ፣

በምሥራቅ ተከዜ፣ በምዕራብ ዘወረግ እና በደቡብ ዜዋ በተባሉ አራት ወንዞች

በተከበበችውና የኢትዮጵያ ገዳማት ሁሉ መመኪያ በተባለችው ገዳም ከሙዝ

ተክል ከሚዘጋጀው ቋርፍ እና ቅጠላ ቅጠል በቀር እህል አይበላባትም፡፡

26

በዚያ ቅዱሳን አበው፣ መነኮሳት እና መነኮሳይያት ረሀቡንና ጥሙን ታግሠው፣

የአገርን ቅርስና ሀብት ጠብቀው ለኢትዮጵያና ለመላው ዓለም እያለቀሱና

እየጸለዩ፣ ዲማ በተባለው ፍልፍል ዛፍ በኣታቸው እያለፉ ኖረዋል፤ ቦታው

ከፍተኛ የድኅነትና ሃይማኖት ሥፍራ ነውና ዛሬም ለአገር ሰላም፣ ፍቅርና ዕድገት

ያልተቋረጠ ጸሎት እየተካሄደበት የሚገኝበት ቢሆንም ለ፪፲፻ ዓመታት

በነገሥታቱ ሳይቀር ተጠብቆ የኖረውን ክብሩንና ሞጎሱን የሚፈታተን፣ ገዳማዊ

ሕጉንና ሥርዐቱን የሚጋፋ፣ ማኅበረ መነኮሳቱንም ለከባድ ኀዘንና ጭንቀት

የሚዳርግ አደጋ ተጋርጦበታል፡፡

የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ ማኅበር፣ የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ

ምሕረት ገዳም ማኅበር እና የዋልድባ ዳልሽሓ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም

ማኅበር ምልአተ ጉባኤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ መለስ ዜናዊ በጻፉት አምስት

ገጽ ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው÷ በዓዲ አርቃይ ወረዳ በኩል የዋልድባን ገዳም

ውስጡን በፓርክነት ለመከለል በቀለም የተቀለሙ ምልክቶች እየተተደረጉ ነው፡

፡ በወልቃይት ወረዳ ልዩ ስሙ መዘጋ በተባለ የገዳሙ የእርሻ እና አዝመራ ቦታ

ላይ መንግሥት የዛሬማን ወንዝ ገድቦ የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም በሰፊው

እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በገዳሙ ክልል ዘልቆ የሚያልፍ ጥርጊያ መንገድ

ለመሥራት በግሬደር እና ሌሎችም ከባድ የሥራ መሣሪያዎች በሚካሄደው

ቁፋሮ የቅዱሳን አባቶች ዐፅም እየታረሰና እየፈለሰ መሆኑ የገዳሙን መነኮሳትና

መናንያን ከፍተኛ ሐዘንና ጭንቀት ላይ ጥሏቸዋል፡፡

የማኅበረ መነኮሳቱ ደብዳቤ ጨምሮ እንደሚያብራራው የዛሬማ ወንዝ ግድብ

ሲቆም በውኃ ሙላቱ ሳቢያ ከሚጠፉት የገዳሙ ወሳኝ ይዞታዎች መካከል

የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

1 ልዩ ስሙ አባ ነፃ የተባለ የብዙ ቅዱሳን ዐፅም በክብር የፈለሰበትና የረገፈበት፣

ብዙ መነኮሳት እና መናንያን የሚቀመጡበት (የሕርመት፨ተዐቅቦ ቦታ) የጻድቁ

አቡነ ተስፋ ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንና መቃብር እንዲሁም የሙዝ ቋርፍ

በከፍተኛ ደረጃ የሚዘጋጅበት እጅግ ሰፊ የሆነ የአትክልት ሥፍራ፤

2 በመዘጋ የሚገኙት ሞፈር ቤቶች፨በገዳሙ ውስጥ እህል ስለማይበላ የዓመት

ቀለብ የሆነ ቋርፍ የሚዘጋጅበት የአትክልት ስፍራ፨፤

3 በመዘጋ የገዳሙ መነኮሳት እህል የሚቀምሱበት ቤት፤

27

4 ጥንታውያን የሴቶች መነኮሳይያት መኖሪያ ገዳሞችና ታሪካዊ ቦታዎች፤

እነዚህም፡፡

4 1 ማየ ሕርገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከመነኮሳት፣ መነኮሳይያት፣

መናንያን፣ የገዳሙ ተማሪ ቤቶችና መኖሪያ ቤቶቻቸው፤

4።2) ዕጣኖ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የመነኮሳት፣ መነኮሳይያት

አጠቃላይ መናንያን የገዳሙ የቤተ ክህነት ትምህርት መማሪያ ቤቶች

ከመምህሮቻቸውና ተማሪዎቻቸው ጋራ፤

4።3) በተለይም በዋልድባ አብረንታንት ውስጥ ያሉ ባሕታውያን፣ መነኮሳትና

መናንያን የሙዝ ቋርፍ የሚዘጋጅበት ገዳሙ በዋናነት የሚተዳደርበት እጅግ ሰፊ

የአትክልት ቦታ፤

4።4) ደላስ ቆቃህ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን የመነኮሳት፣ መነኮሳይያት፣

መናንያን መኖርያ ቤቶች፣ የገዳሙ ቤተ ክህነት ት፨ቤቶች፣ መምህሮቻቸውና

ተማሪዎቻቸው እስከ መኖርያ ቤቶቻቸው ናቸው፡፡

ከላይ የተዘረዘሩት የገዳሙ ይዞታዎች ከጠፉ ገዳሙ ምንም ዐይነት የገቢ

ምንጭና መተዳደር ፨በደላሳ ቆቃህ እንደ ማሽላ፣ ዳጉሳ በማምረት፨

የማይኖረው በመሆኑ መነኮሳቱ፣ መነኮሳይያቱ፣ መናንያኑ፣ መምህራኑና

ተማሪዎቻቸው ለረሃብ እና ስደት የሚዳረጉ በመሆኑ ማኅበሩ ሙሉ በሙሉ

እንደሚያከትምለት ያስረዳው ደብዳቤው÷ መንግሥት ሐዘናቸውንና

ጩኸታቸውን ሰምቶ የገዳማቸውን ሕግ እና ሥርዐት እንዲያስከብርላቸው

ተማፅነዋል፡፡

ቀደም ሲል በተለይም ከ1997 ዓ።ም ወዲህ ማይ ሰርኪን ከተባለው ቦታ ወርቅ

እናወጣለን በሚሉ ቆፋሪዎችና ዕጣን እንለቅማለን በሚሉ መቀርተኞች

(ቁጥራቸው በዐሥር ሺሕዎች በሚገመት ሰፋሪዎች) ተጥለቅልቀው ሲታወኩና

ሲረበሹ መቆየታቸውን የጠቀሰው የማኅበረ መነኮሳቱ ደብዳቤ አሁን ደግሞ

ፓርክ ለመከለል፣ የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋምና ጥርጊያ መንገድ ለማውጣት

የሚካሄደው እንቅስቃሴ ለገዳሙ ህልውና በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ

እንደሆነበት አትቷል፡፡

በበጋ ወቅት መንሥኤው የማይታወቅ የሰደድ እሳት ከሚያወድመው ደን ባሻገር

28

በወርቅ ጫሪዎቹ እና በዕጣን መቀርተኞቹ ሳቢያ አበው መነኮሳት ጭብጥ ቋርፍ

ይዘው ሱባኤ የሚይዙባቸው፨የሚሰወሩባቸው ዛፎች (ፍልፍል ዲማ)፣

መድኃኒትነት ያላቸው ዕፀዋትና የግሑሳኑ መሳፈርያ የሆኑት የዱር እንስሳት

(አንበሳ፣ አጋዘን፣ ነምር) ከገዳሙ እየጠፉ መሆናቸውም ተመልክቷል፡፡

ከማኅበረ መነኮሳቱ ጋራ ባለፈው ዓመት የመዘጋ እና የወልቃይት ነዋሪዎች ማይ

ገባ ንኡስ ወረዳ ላይ የተቃውሞ ድምፃቸውን በሰልፍ ማሰማታቸውንም ያወሱት

የገዳማቱ ተወካዮች ልማትን የሚቃወሙ ባይሆንም ስለ ዕቅዱ ምንም

የተገለጸላቸው ነገር ባለመኖሩ ቦታው የጸሎት፣ የተጋድሎና የቅድስና መሆኑ

ቀርቶ የዓለማውያን መናኸርያ፣ የነጋድያንና የሕዝብ መስፈርያ፣ የመኪና

መሽከርከርያ እንዲሆን ፈቃደኞች እንዳይደሉ የገዳሙ ማኅበር አባላት

ገልጸዋል፤ በገዳሙ ልዩ ሥራ እንዳይሠራ “እንበለ ፈላሲ ኢይባዕ ነጋሲ” በማለት

ቀደምት አባቶቻቸው ያስተላለፉትን የውግዘት ቃል በማስጠበቅ በቅዱሳኑ ፈለግ

ሕግና ሥርዐት መጓዛቸውን እንደሚቀጥሉም በጥብቅ አስተውቀዋል፡፡

በአምስት ዓመቱ የመንግሥት ልማት እና ትራንፎርሜሽን ዕቅድ መሠረት

በስኳር ምርት ራስን ለመቻል ከሚቋቋሙት ዐሥር ግዙፍ የስኳር ፋብሪካ

ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የ፬።፪ ቢልዮን ብር ዕቅድ የተያዘለት ይኸው

የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ ፋብሪካው በ30፣000 ሄ፨ር ላይ

የሚለማውን የሸንኮራ ተክል የሚጠቀም ሲሆን የውኃ ምንጩም በዛሬማ ወንዝ

ላይ የሚሠራው ርዝመቱ ፸0 ሜትር፣ ከፍታው ፩፫፰ ሜትር የሆነና ፫።፰

ቢልዮን ሜትር ኪቢዩክ ውኃ የመያዝ አቅም ያለው ግድብ ነው፡፡

ውኃው ያርፍበታል በተባለው ማይ ዲማ በተባለው ቦታ የሚገኙት የማር ገጽ

ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የማይ ገባ ቅዱስ ሚካኤል፣ የዕጣኖ ቅድስት ማርያም እና

የደለሳ ቆቃህ አቡነ አረጋዊ አብያተ ክርስቲያን እንደሚነሡ ተነግሯል፡፡

ሥራውን ያካሂዳል የተባለው የፌዴራል ውኃ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ሲሆን

በአሁኑ ወቅት ለ፲፣000 የፕሮጀክቱ ቋሚ እና ጊዜያዊ ሠራተኞች የካምፕ

ግንባታ እየተከናወነ፣ ቦታውንም ምቹ የማድረግ ሥራ እየተሠራ መሆኑ

ተዘግቧል፡፡

በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ፡ ሽሬ እንዳሥላሴ እና በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት

ዓዲ አርቃይ ወረዳ ክልል በሚገኙት ሦስቱ የዋልድባ ገዳማት በአጠቃላይ

ከ፴00 ያላነሱ መነኮሳትና መነኮሳይያት የሚገኙ ሲሆኑ የሴቶች ገዳም በሆነው

የዳልሽሓ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ከ፩፶0 ያላነሱ ሴት መነኮሳይያት

29

ይገኙበታል፡፡ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ምክሆን ለገዳማተ ኢትዮጵያ

ማኅበር ዘቤተ ሚናስ ዋነኛው የሕርመት፨ተዐቅቦ ቦታ ሲሆን ወንዶች መነኮሳት

ብቻ ያሉበት፣ እስከ ፶ ዓመት ድረስ በአርምሞ ከሰው ተነጋግረው የማያውቁ

ቅዱሳን በዘመናችን ሳይቀር የሚገኙበት ነው፡፡

ገዳሙን በማደራጀት እና የተባሕትዎን ኑሮ በማጠናከር በ፩፬ኛው መቶ ክፍለ

ዘመን ከነበሩትና ሰባቱ ከዋክብት ከሚባሉት የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደቀ

መዛሙርት አንዱ ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል (ሳሙኤል ፀሐይ ዘዋሊ) ይጠቀሳሉ፤

ገዳሙን ያቀኑትም በዐምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት በ፩፫፩፱ ዓ።ም ነው፡፡

የገዳሙን ኑሮ መልክ የሰጡት ከደብረ ሊባኖስ በሄዱት እንደ አባ ሙሴ

የመሳሰሉት አባቶች ሲሆኑ “በገዳም እንኖራለን፤ እህል አይገባንም” በማለት

ከእርሳቸው ጊዜ ጀምሮ የመነኮሳቱ ምግብ ቋርፍ ፡ ሙዝ በጨው ተቀቅሎ

እንዲሆን ተወስኗል፡፡

የዋልድባ መነኮሳት ከነገሥታት ጉልት አይቀበሉም ነበር፤ ሲሰጥም አጥብቀው

ይቃወሙ ነበር፡፡ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ፨፩፬፪፮ ፡ ፩፬፷ ዓ።ም፨ ዘመነ መንግሥት

የዋልድባ ገዳም በአራቱ ጅረቶች መካከል እንዲሆን ተከልሎ ገዢ እንዳይገባ፣

አራሽ እንዳይሠማራ ተከልክሏል፡፡

30

ድብደባና የመብት ጥሰት ከደረሰባቸው ገዳማውያን መካከል

የሚከተሉት ይጠቀሳሉ

1- አባ ገብረ ስላሴ ዋለልኝን ሐምሌ ፩፫፣ ፪፻፬ ዓ።ም። ከምሽቱ ፩፪ ሰዓት

ከገዳሙ በሚሊሻና በሁለት ፖሊሶች አስወጥተው እንኮይላህም ድረስ

ከወሰዷቸው በኋላ ተከትለው የሄዱ ሌሎች መነኮሳትን ስንቅ ማቀበል

እንደማይችሉ ገልጸው ማይጸብሪ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል፣

በጊዜውም ደብድበዋቸዋል፡፡

2- አባ ወልደጊዮርጊስ ኃይለ ማርያም እና አባ ገ፨ማርያም ገ፨ዮሐንስን ሐምሌ

፪፩ ቀን ፪፻፬ ዓ።ም በገዳሙ ስርዓት መውጣት በማይቻልበት የህርመት ሰዓት

ከሱባኤ አስወጥተው የጦር መሳሪያ አላችሁ በማለት ቤታቸው ከተበረበረ በኋላ

ምንም አለመገኘቱ እየታወቀ ከመነኮሳቱ ለይተው ወደ ማይጸብሪ ወስደዋቸዋል፡

፡ ፖሊስ ጣቢያ ሳይሆን የጸጥታ ፖሊስ ቢሮ እያሳደሩ ሌሊት ሌሊት በሽፍን

መኪና እየወሰዱ የምንኩስና ቆባቸውንና ቀሚሳቸውን በማስወለቅ ሰረንቲያ

በተባለ ወንዝ በሽቦ በተደጋጋሚ ደብድበዋቸዋል፡፡ ዋልድባ መኖር አትችሉም

ብሎ አስተዳዳሪው ከለከላቸው፡፡ አክሱም ጸሎት እያደረግን እንኑር ሲሉ

አስተዳዳሪው ዕአክሱምስ ቢሆን የማን ግዛት ነው፧ዕ በማለት ሙሉ በሙሉ

ከትግራይ ካልወጣችሁ ትገደላላችሁ፣ ገዳያችሁም አይታወቅም ብሏቸዋል፡፡

አሁን የት እንዳሉ አናውቅም፣ ከደረሰባቸው ግፍ አንጻርም ሁሉን ሰው

ስለሚጠራጠሩ በስልክ ለማግኘት ያስቸግራል፡፡

3- መናኝ ክንፈገብርኤል ወልደሳሙኤል ነሐሴ ፪፻፬ ዓ።ም። ከአባ ነፃ አካባቢ

ለገዳም ተልዕኮ ሲንቀሳቀስ ተይዞ ማይገባ አስገብተው ወልቃይት ወረዳ ላይ

ለሳምንት አስረው ከደበደቧቸው በኋላ ማይጸብሪ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ

ለአራት ወራት ፍርድቤት ሳይቀርብ ታስሮ ለበዓለ ልደት ተለቋል፡፡

4- አባ ገ፨ስላሴ ገ፨እግዚአብሔር ነሐሴ ፳ ፪፻፬ ያለምንም ምክንያት ጠቅላይ

ሚኒስትሩንና አቡነ ጳውሎስ በመሞታቸው ደስ ብሎሃል ብለው ከገዳሙ

አስወጥተው ፖሊሶች ወልቃይት ወረዳ ማይገባ አስረውኝ ከ፱ ቀን በኋላ ፍ፨

ቤት በዋስ ተለቀዋል፡፡

5- መናኝ ወልደሩፋኤል ወልደሳሙኤል ከገዳሙ ውስጥ ለተልዕኮ ሲንቀሳቀስ

ነሐሴ ፪፮ ቀን ፪፻፬ ዓ።ም። ላይ ፌዴራል ፖሊሶችና የአካባቢ ሚሊሻዎች

31

አገርህ የት ነው ብለው ከጠየቋቸው በኋላ ደበደቧቸው፣ ደብዳቢው መዝን

የተባለ ታጣቂ ነው፡፡ ከደበደቡት በኋላ ሌሎች ማኅበረ፡መነኮሳት ወዳሉበት

ማይለበጣ አምጥተውት ብዙዎቻችን እየሰማን ዕዱላው ተስማማህ ወይ፧ዕ

እያሉ ተዘባበቱበት፡፡ በድብደባውም እጃቸው ተሰብሯል፡፡ ከዋልድባ ውስጥ

በድብደባው ምክንያት አብረንታንትን ለቀው ዋልድባ ዳልሻ ከተባለው ቦታ

ይገኛሉ፡፡

6- ቤተ፡ሚናስ ውስጥ በመነኮሳት መካከል የጠፈጠረውን አለመግባባት

ለመፍታት የአካባቢው ነዋሪዎች ለማስታረቅ ማህበረ መነኮሳቱን ፈቃድ

ጠይቀው ማህበረ መነኮሳቱም ስለተስማማ ለሽምግልና ፵ የሐገር ሽማግሌ

ተመርጠው በገዳሙ ማኅተም ጥሪ ተደርጎላቸው ነበር፡፡ ለህጋዊነትም

መንግሥት እንዲያውቀው የወረዳውን አስተዳደር ጠይቁ ብሎ ማኅበረ መነኮሳቱ

ስለጠየቁ የማይፀብሪ አስተዳደር መነኮሳቱን የምታስታርቁ ከሆነ እርምጃ

እወስድባቸዋለሁ አላቸው፡፡ ይህን ማስጠንቀቂያ የሰሙት ሽማግሌዎች ሲቀሩ

ከሽማግሌዎቹ መካከል አራቱ ማለትም አቶ አለምሸት ሙሉ፣ አቶ ተክሌ ገ፨

ኪዳን፣ አቶ አምባቸው ጥላሁንና አለቃ መሀቤ ገ፨መስቀል ይህን ስላልሰሙ

ወደ ገዳሙ ለማስታረቅ ስለመጡ ሀሙስ ዕለት ጥር ፪፣ ፪፻፭ ዓ።ም የማይጸብሪ

ወረዳ ጸጥታ ሰራተኛ ነኝ ያለ አቶ ረዘነ የተባለ ሰው አስሮ ይዟቸው ሄዶ ፍ፨

ቤት ሳይቀርቡ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋቸው ለቀዋቸዋል፡፡ ከሽማግሌዎቹ

አንዱን አቶ አለምሸትን የትግራይ ተወላጅ ስላልሆንክ ወደ ሀገርህ ወደ ክልል

ሦስት ለቀህ ሂድ በማለት አዘውታል፡፡

7- ጥር ፪ ፪፻፭ ዓ።ም። አባ ወ፨ገብርኤል ገ፨ስላሴና አባ ገ፨ህይወት ተ፨

ማርያምን ማይለበጣ ገዳሙ ውስጥ እያለን የማይጸብሪ ፖሊሶች በዓታችን

ውስጥ እያለን ከጓደኞቻችን ለይተው ካስወጡን በኋላ ትፈለጋላችሁ ብለው

ከባላገር ቤት ለየብቻ አሳደሩን፡፡ ለሽንት እንኳ እንውጣ ብለን ስንጠይቅ በጥፊ

እየደበደቡ አሳደሩን፡፡ ጠዋትም እንደናንተ ያለ ሽፍታ መነኩሴ አግኝተናል

ብለው ለጸሎት ደንደረቋ ከተባለ ቤ፨ክን ስመለስ አባ ኃ፨ማርያም ገ፨ስላሴን

እና መናኝ ታዲዮስ ገ፨መድህንን ጨምረው ማይጸብሪ ወስደው አሰሩን፡፡

ለአራት ቀን ካቆዩን በኋላ ነጻ ናችሁ ተብለን ተለቀቅን፡፡ በግምት ፲ ኪ።ሜ

ያህል ወደ ገዳሙ መመለስ ከጀመርን በኋላ እንደገና በሽፍን መኪና ተከታትለው

እናንተ ሽፍቶች ቁሙ ብለው መልሰው እያዳፉ እስር ቤት መለሱን፡፡ የወረዳው

አስተዳዳሪ ከእስር ቤት አስጠርቶ ቢሮው ከወሰደን በኋላ ከስራ ባልደረቦቹ ጋር

ሆኖ ዕእናንተ ተመልሳችሁ ወደ ገዳም መግባት አትችሉም፣ የወጡትም

32

አይመለሱም፣ በገዳሙ የቀሩትንም እየመነጠርን እናወጣቸዋለን፤ እንገባለን

ካላችሁ ገዳያችሁን ሳታውቁ ትገደላላችሁ ብሎናል፡፡ የጎጃም፣ የጎንደርና የሸዋ

ሌባ ተሰብስባችሁ ከገዳሙ ልትቀመጡ አትችሉም ብሎናል፡፡ በተደጋጋሚ

ባደረገው ንጝር ከማሰርና ከመደብደብ አልፎ አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ወደ

ዋልድባ ገዳም መግባት አትችሉም፣ ከውስጥ ያሉትንም ጠራርጌ አወጣቸዋለሁ

በማለት፣ ይህን ባታደርጉ ግን ገዳያችሁ ማን እንደሆነ ሳይታወቅ ትገደላላችሁ

ስለተባልን አቅም ያለን መነኮሳት ወጥተናል፡፡

በተጨማሪም ከገዳሙ ለመውጣትም ሆነ ወደ ገዳሙ ለመግባት

በምንንቀሳቀስበት ጊዜም የትግራይ ክልል ነዋሪ መሆናችሁን የሚያሳይ የቀበሌ

መታዎቂያ ካላመጣችሁ እያሉ ያስገድዱናል፡፡ የገዳሙ ማኅተም ያለበት

መታዎቂያ ስናሳይ ተቀባይነት የለውም እየተባልን መንቀሳቀስ እንዳንችል

ተደርገናል፡፡ አሁን ወደ ጎንደር ስንመጣም ያስሩናል ብለን በትክክለኛው

መንገድ መውጣት አልቻልንም፡፡ ስለሆነም ተጨማሪ የሁለት ቀን የእግር

መንገድ በርሃ ለበርሃ ተጉዘን ጎንደር ገባን፡፡ በዋናው መንገድ ለመምጣት

የሞከሩት ታስረዋል፡፡ ማኅበረ፡መነኮሳቱን በዘረኝነት ከበተኑ በኋላ ፫፩ ያህል

መነኮሳት ይህን ማመልከቻ ስናቀርብ ሌሎች ብዙዎች ገዳም ቀይረው ሄደዋል፡፡

እኛን ካስወጡ በኋላ የገዳሙን አስተዳደር ከወረዳ አስተዳደር የተላኩ

ሚሊሻዎችን ይዘው መምህር፣ እቃቤትና ሌሎች ሰራተኞችን በአዲስ

አዋቅረዋል፡፡ ይህም ግልጽ የሆነ ጣልቃገብነት ነው፡፡ የገዳሙንም ስርዓት

ያልጠበቀ ነው፡፡

ይህ ሁሉ የመብት ጥሰት የሚደርስብን ምንም ጥፋት ተገኝቶብን አይደለም፡፡

በእኛ እምነት ይቅርና የብዙ ዘመን ታሪክ ያለው ዋልድባ አብረንታንት ገዳም

ማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ ባለ ገዳም ውስጥ መንፈሳዊ ስርዓቱን

ተከትለን የመኖር መብታችን ሊጠበቅልን ይገባል፡፡ ይሑንና በተደጋጋሚ

ያለአግባብ እየታሰርን፣ እየተደበደብን፣ የመንቀሳቀስ ነፃነታችን ተገድቦ፣ የግድያ

ማስፈራሪያ በመንግሥት ባለስልጣን እየደረሰን በገዳማችን ለመኖር

አልቻልንም፡፡ ዋስትናም አጥተናል፡፡ የሌላ ሀገር ዜጋ የሆንን ይመስል ያለጥፋት

በመንፈሳዊ በዓታችን እንዳንኖር የማናውቀውን ፖለቲካ ተገን ባደረገ ዘረኛ

አስተሳሰብ በገዳማችን የመቀጠል መብታችንና የገማኅበረ፡መነኮሳቱ ህልውና

አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ በገዳሙ መነኮሳት ላይ እየደረሰ ያለው ችግር በእኛ ብቻ

ሊያቆም የሚችል ሳይሆን ውሎ አድሮ መጥፎ ጠባሳ የሚተው ጉዳይ በመሆኑ

የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በሙሉ መፍትሄ እንዲሰጠን

33

እንዲያደርጉልን እንጠይቃለን፡፡

ስለሆነም የሚመለከተው የመንግሥት አካል ወደ ገዳማችን ያለችግር መግባት

እንድንችል ዋስትና እንዲሰጠን፣ መደብደብና ማስፈራራት እንዳይደርስብን፣

በነጻነት የመኖርና የመንቀሳቀስ መብታችንን እንዲያስጠብቅልን፣ መብታችንን

በተደጋጋሚ የጣሱብንን የመንግሥት አካላትም ላይ የእርምት እርምጃ

እንዲወስድልን፣ የወረዳው የጸጥታ አካላትና አስተዳደርም ህገ፡ወጥ በሆነ

መልኩ በገዳሙ አስተዳደር ላይ ሹም ሽር ማስደረግን ጨምሮ የሚፈጽሙትን

ግልጽ የሆነ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙልን እንዲደረግልን በቤተክርስቲያን

አምላክ ስም እንጠይቃለድብደባና የመብት ጥሰት ከደረሰባቸው ገዳማውያን

መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ

8- አባ ገብረ ስላሴ ዋለልኝን ሐምሌ ፩፫፣ ፪፻፬ ዓ።ም። ከምሽቱ ፩፪ ሰዓት

ከገዳሙ በሚሊሻና በሁለት ፖሊሶች አስወጥተው እንኮይላህም ድረስ

ከወሰዷቸው በኋላ ተከትለው የሄዱ ሌሎች መነኮሳትን ስንቅ ማቀበል

እንደማይችሉ ገልጸው ማይጸብሪ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል፣

በጊዜውም ደብድበዋቸዋል፡፡

9- አባ ወልደጊዮርጊስ ኃይለ ማርያም እና አባ ገ፨ማርያም ገ፨ዮሐንስን ሐምሌ

፪፩ ቀን ፪፻፬ ዓ።ም በገዳሙ ስርዓት መውጣት በማይቻልበት የህርመት ሰዓት

ከሱባኤ አስወጥተው የጦር መሳሪያ አላችሁ በማለት ቤታቸው ከተበረበረ በኋላ

ምንም አለመገኘቱ እየታወቀ ከመነኮሳቱ ለይተው ወደ ማይጸብሪ ወስደዋቸዋል፡

፡ ፖሊስ ጣቢያ ሳይሆን የጸጥታ ፖሊስ ቢሮ እያሳደሩ ሌሊት ሌሊት በሽፍን

መኪና እየወሰዱ የምንኩስና ቆባቸውንና ቀሚሳቸውን በማስወለቅ ሰረንቲያ

በተባለ ወንዝ በሽቦ በተደጋጋሚ ደብድበዋቸዋል፡፡ ዋልድባ መኖር አትችሉም

ብሎ አስተዳዳሪው ከለከላቸው፡፡ አክሱም ጸሎት እያደረግን እንኑር ሲሉ

አስተዳዳሪው ዕአክሱምስ ቢሆን የማን ግዛት ነው፧ዕ በማለት ሙሉ በሙሉ

ከትግራይ ካልወጣችሁ ትገደላላችሁ፣ ገዳያችሁም አይታወቅም ብሏቸዋል፡፡

አሁን የት እንዳሉ አናውቅም፣ ከደረሰባቸው ግፍ አንጻርም ሁሉን ሰው

ስለሚጠራጠሩ በስልክ ለማግኘት ያስቸግራል፡፡

10- መናኝ ክንፈገብርኤል ወልደሳሙኤል ነሐሴ ፪፻፬ ዓ።ም። ከአባ ነፃ አካባቢ

ለገዳም ተልዕኮ ሲንቀሳቀስ ተይዞ ማይገባ አስገብተው ወልቃይት ወረዳ ላይ

ለሳምንት አስረው ከደበደቧቸው በኋላ ማይጸብሪ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ

ለአራት ወራት ፍርድቤት ሳይቀርብ ታስሮ ለበዓለ ልደት ተለቋል፡፡

34

11- አባ ገ፨ስላሴ ገ፨እግዚአብሔር ነሐሴ ፳ ፪፻፬ ያለምንም ምክንያት ጠቅላይ

ሚኒስትሩንና አቡነ ጳውሎስ በመሞታቸው ደስ ብሎሃል ብለው ከገዳሙ

አስወጥተው ፖሊሶች ወልቃይት ወረዳ ማይገባ አስረውኝ ከ፱ ቀን በኋላ ፍ፨

ቤት በዋስ ተለቀዋል፡፡

12- መናኝ ወልደሩፋኤል ወልደሳሙኤል ከገዳሙ ውስጥ ለተልዕኮ ሲንቀሳቀስ

ነሐሴ ፪፮ ቀን ፪፻፬ ዓ።ም። ላይ ፌዴራል ፖሊሶችና የአካባቢ ሚሊሻዎች

አገርህ የት ነው ብለው ከጠየቋቸው በኋላ ደበደቧቸው፣ ደብዳቢው መዝን

የተባለ ታጣቂ ነው፡፡ ከደበደቡት በኋላ ሌሎች ማኅበረ፡መነኮሳት ወዳሉበት

ማይለበጣ አምጥተውት ብዙዎቻችን እየሰማን ዕዱላው ተስማማህ ወይ፧ዕ

እያሉ ተዘባበቱበት፡፡ በድብደባውም እጃቸው ተሰብሯል፡፡ ከዋልድባ ውስጥ

በድብደባው ምክንያት አብረንታንትን ለቀው ዋልድባ ዳልሻ ከተባለው ቦታ

ይገኛሉ፡፡

13- ቤተ፡ሚናስ ውስጥ በመነኮሳት መካከል የጠፈጠረውን አለመግባባት

ለመፍታት የአካባቢው ነዋሪዎች ለማስታረቅ ማህበረ መነኮሳቱን ፈቃድ

ጠይቀው ማህበረ መነኮሳቱም ስለተስማማ ለሽምግልና ፵ የሐገር ሽማግሌ

ተመርጠው በገዳሙ ማኅተም ጥሪ ተደርጎላቸው ነበር፡፡ ለህጋዊነትም

መንግሥት እንዲያውቀው የወረዳውን አስተዳደር ጠይቁ ብሎ ማኅበረ መነኮሳቱ

ስለጠየቁ የማይፀብሪ አስተዳደር መነኮሳቱን የምታስታርቁ ከሆነ እርምጃ

እወስድባቸዋለሁ አላቸው፡፡ ይህን ማስጠንቀቂያ የሰሙት ሽማግሌዎች ሲቀሩ

ከሽማግሌዎቹ መካከል አራቱ ማለትም አቶ አለምሸት ሙሉ፣ አቶ ተክሌ ገ፨

ኪዳን፣ አቶ አምባቸው ጥላሁንና አለቃ መሀቤ ገ፨መስቀል ይህን ስላልሰሙ

ወደ ገዳሙ ለማስታረቅ ስለመጡ ሀሙስ ዕለት ጥር ፪፣ ፪፻፭ ዓ።ም የማይጸብሪ

ወረዳ ጸጥታ ሰራተኛ ነኝ ያለ አቶ ረዘነ የተባለ ሰው አስሮ ይዟቸው ሄዶ ፍ፨

ቤት ሳይቀርቡ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋቸው ለቀዋቸዋል፡፡ ከሽማግሌዎቹ

አንዱን አቶ አለምሸትን የትግራይ ተወላጅ ስላልሆንክ ወደ ሀገርህ ወደ ክልል

ሦስት ለቀህ ሂድ በማለት አዘውታል፡፡

14- ጥር ፪ ፪፻፭ ዓ።ም። አባ ወ፨ገብርኤል ገ፨ስላሴና አባ ገ፨ህይወት ተ፨

ማርያምን ማይለበጣ ገዳሙ ውስጥ እያለን የማይጸብሪ ፖሊሶች በዓታችን

ውስጥ እያለን ከጓደኞቻችን ለይተው ካስወጡን በኋላ ትፈለጋላችሁ ብለው

ከባላገር ቤት ለየብቻ አሳደሩን፡፡ ለሽንት እንኳ እንውጣ ብለን ስንጠይቅ በጥፊ

እየደበደቡ አሳደሩን፡፡ ጠዋትም እንደናንተ ያለ ሽፍታ መነኩሴ አግኝተናል

ብለው ለጸሎት ደንደረቋ ከተባለ ቤ፨ክን ስመለስ አባ ኃ፨ማርያም ገ፨ስላሴን

35

እና መናኝ ታዲዮስ ገ፨መድህንን ጨምረው ማይጸብሪ ወስደው አሰሩን፡፡

ለአራት ቀን ካቆዩን በኋላ ነጻ ናችሁ ተብለን ተለቀቅን፡፡ በግምት ፲ ኪ።ሜ

ያህል ወደ ገዳሙ መመለስ ከጀመርን በኋላ እንደገና በሽፍን መኪና ተከታትለው

እናንተ ሽፍቶች ቁሙ ብለው መልሰው እያዳፉ እስር ቤት መለሱን፡፡ የወረዳው

አስተዳዳሪ ከእስር ቤት አስጠርቶ ቢሮው ከወሰደን በኋላ ከስራ ባልደረቦቹ ጋር

ሆኖ ዕእናንተ ተመልሳችሁ ወደ ገዳም መግባት አትችሉም፣ የወጡትም

አይመለሱም፣ በገዳሙ የቀሩትንም እየመነጠርን እናወጣቸዋለን፤ እንገባለን

ካላችሁ ገዳያችሁን ሳታውቁ ትገደላላችሁ ብሎናል፡፡ የጎጃም፣ የጎንደርና የሸዋ

ሌባ ተሰብስባችሁ ከገዳሙ ልትቀመጡ አትችሉም ብሎናል፡፡ በተደጋጋሚ

ባደረገው ንጝር ከማሰርና ከመደብደብ አልፎ አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ወደ

ዋልድባ ገዳም መግባት አትችሉም፣ ከውስጥ ያሉትንም ጠራርጌ አወጣቸዋለሁ

በማለት፣ ይህን ባታደርጉ ግን ገዳያችሁ ማን እንደሆነ ሳይታወቅ ትገደላላችሁ

ስለተባልን አቅም ያለን መነኮሳት ወጥተናል፡፡

በተጨማሪም ከገዳሙ ለመውጣትም ሆነ ወደ ገዳሙ ለመግባት

በምንንቀሳቀስበት ጊዜም የትግራይ ክልል ነዋሪ መሆናችሁን የሚያሳይ የቀበሌ

መታዎቂያ ካላመጣችሁ እያሉ ያስገድዱናል፡፡ የገዳሙ ማኅተም ያለበት

36

መታዎቂያ ስናሳይ ተቀባይነት የለውም እየተባልን መንቀሳቀስ እንዳንችል

ተደርገናል፡፡ አሁን ወደ ጎንደር ስንመጣም ያስሩናል ብለን በትክክለኛው

መንገድ መውጣት አልቻልንም፡፡ ስለሆነም ተጨማሪ የሁለት ቀን የእግር

መንገድ በርሃ ለበርሃ ተጉዘን ጎንደር ገባን፡፡ በዋናው መንገድ ለመምጣት

የሞከሩት ታስረዋል፡፡ ማኅበረ፡መነኮሳቱን በዘረኝነት ከበተኑ በኋላ ፫፩ ያህል

መነኮሳት ይህን ማመልከቻ ስናቀርብ ሌሎች ብዙዎች ገዳም ቀይረው ሄደዋል፡፡

እኛን ካስወጡ በኋላ የገዳሙን አስተዳደር ከወረዳ አስተዳደር የተላኩ

ሚሊሻዎችን ይዘው መምህር፣ እቃቤትና ሌሎች ሰራተኞችን በአዲስ

አዋቅረዋል፡፡ ይህም ግልጽ የሆነ ጣልቃገብነት ነው፡፡ የገዳሙንም ስርዓት

ያልጠበቀ ነው፡፡

ይህ ሁሉ የመብት ጥሰት የሚደርስብን ምንም ጥፋት ተገኝቶብን አይደለም፡፡

በእኛ እምነት ይቅርና የብዙ ዘመን ታሪክ ያለው ዋልድባ አብረንታንት ገዳም

ማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ ባለ ገዳም ውስጥ መንፈሳዊ ስርዓቱን

ተከትለን የመኖር መብታችን ሊጠበቅልን ይገባል፡፡ ይሑንና በተደጋጋሚ

ያለአግባብ እየታሰርን፣ እየተደበደብን፣ የመንቀሳቀስ ነፃነታችን ተገድቦ፣ የግድያ

ማስፈራሪያ በመንግሥት ባለስልጣን እየደረሰን በገዳማችን ለመኖር

አልቻልንም፡፡ ዋስትናም አጥተናል፡፡ የሌላ ሀገር ዜጋ የሆንን ይመስል ያለጥፋት

በመንፈሳዊ በዓታችን እንዳንኖር የማናውቀውን ፖለቲካ ተገን ባደረገ ዘረኛ

አስተሳሰብ በገዳማችን የመቀጠል መብታችንና የገማኅበረ፡መነኮሳቱ ህልውና

አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ በገዳሙ መነኮሳት ላይ እየደረሰ ያለው ችግር በእኛ ብቻ

ሊያቆም የሚችል ሳይሆን ውሎ አድሮ መጥፎ ጠባሳ የሚተው ጉዳይ በመሆኑ

የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በሙሉ መፍትሄ እንዲሰጠን

እንዲያደርጉልን እንጠይቃለን፡፡

ስለሆነም የሚመለከተው የመንግሥት አካል ወደ ገዳማችን ያለችግር መግባት

እንድንችል ዋስትና እንዲሰጠን፣ መደብደብና ማስፈራራት እንዳይደርስብን፣

በነጻነት የመኖርና የመንቀሳቀስ መብታችንን እንዲያስጠብቅልን፣ መብታችንን

በተደጋጋሚ የጣሱብንን የመንግሥት አካላትም ላይ የእርምት እርምጃ

እንዲወስድልን፣ የወረዳው የጸጥታ አካላትና አስተዳደርም ህገ፡ወጥ በሆነ

መልኩ በገዳሙ አስተዳደር ላይ ሹም ሽር ማስደረግን ጨምሮ የሚፈጽሙትን

ግልጽ የሆነ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙልን እንዲደረግልን በቤተክርስቲያን

አምላክ ስም እንጠይቃለን፡፡

በማለት መንግስትን ጠይቀዋል ነገር ግን ምንም ኣይነት ምላሽ ኣላገኙም

37

እግዚኣብሒር ኣምላክ ገዳሙን ይጠብቅ አሜን፣

ትንሣኤ ዘክርስቶስ - የክርስቶስ ትንሳኤ

ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት በመቃብር፤

ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት የሞላው እንዴት ነው?፤

38

እንዴት ተነሣ?

ለምን በአዲስ መቃብር ተቀበረ?

እንዴት በዝግ መቃብር ተነሣ?

መቃብሩን ማን ከፈተው?

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድኅነተ ዓለምን በመስቀል

ላይ ከፈጸመ በኋላ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ወረደ÷ ይኸውም በመቃብር

ፈርሶ በስብሶ መቅረትን ሊያስቀርልን ነው፡፡ በአካለ ነፍስ ደግሞ ወደ ሲኦል

ወረደ÷ ይኸውም በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን ይሰብክላቸው ዘንድ ነው፡፡

መለኮት፥ በተዋሕዶ፥ ከሥጋም ከነፍስም ጋር ነበረ፡፡ ለዚህ ነው፥ መቃብር

ሥጋን ሊያስቀረው ያልቻለው፤ ሲኦልም ነፍስን ማስቀረት አልተቻለውም፡፡

ቅዱስ ዳዊት፡- « ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ

ዘንድ አትተዋትም» ያለው ይኽንን ታላቅ ምሥጢር በትንቢት ቃል ሲናገር ነው፡

፡ መዝ ፲፭÷፲፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም፡- «ክርስቶስ ደግሞ ወደ

እግዚአብሔር (ወደ አብ÷ ወደ ራሱና ወደ መንፈስ ቅዱስ) እንዲያቀርበን፥ እርሱ

ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት (ስለ ሰው ልጆች

ኃጢአት ተላልፎ በመሰጠት) ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ (በፈቃዱ ነፍሱን

ከሥጋው ለየ)÷ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ÷ (ያን ሥጋ ነፍስ እንድተለየችው

መለኰት አልተለየውም)÷ በእርሱም ደግሞ (መለኰት በተዋሐዳት ነፍስ) ሄዶ

በወኅኒ ለነበሩት ነፍሳት ሰበከላቸው፤» ብሏል።

ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት በመቃብር፤

ጌታችን በከርሰ መቃብር የቆየው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ነው፡፡ «ሥጋዬ

ደግሞ በተስፋ ታድራለች፤» የሚለው ቃለ ትንቢት የሚያረጋግጥልን ይኽንኑ

ነው፡፡ መዝ ፲፭፥፱፡፡ ምሥጢራዊ ትርጉሙም «ወደ መቃብር የወረደ ሥጋዬ

በተስፋ ትንሣኤ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በመቃብር አደረ፤» ማለት ነው፡

፡ ተስፋ ትንሣኤውም በተዋሕዶ ከሥጋ ጋር ወደ መቃብር የወረደ መለኰት

ነው፡፡ ነቢዩ ሆሴዕም፡- «ኑ÷ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና÷

(በሞተ ሥጋ ላይ ሞተ ነፍስን ጨምሮ የፈረደብን እርሱ ነው)÷ እርሱም

39

ይፈውሰናል፤ (መርገመ ሥጋን መርገመ ነፍስን አስወግዶ ከሞት ወደ ሕይወት

ያሸጋግረናል)፤ እርሱ መትቶናል÷ እርሱም ይጠግነናል፡፡ ከሁለት ቀን በኋላ

ያድነናል፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል፡፡» በማለት ትንሣኤ ክርስቶስ

በሦስተኛው ቀን መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ሆሴ ፮÷፲፪፡፡ ይልቁንም ጌታችን ራሱ

በመዋዕለ ሥጋዌው፡- ከሽማግሌዎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ

ይቀበልና ይገደል ዘንድ፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው

ለደቀመዛሙርቱ በግልጥ ነግሯቸዋል፡፡ ማቴ ፲፮÷፳፩፡፡ በገሊላም ሲመላለሱ፡-

«ወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው÷

ይገድሉትማል÷ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤» ብሏቸዋል፡፡ ማቴ ፲፯÷፳፡፡

ጻፎችና ፈሪሳውያንም ምልክት በጠየቁት ጊዜ፡- «ክፉና አመንዝራ ትውልድ

ምልክት ይሻል÷ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም፡፡ ዮናስ

በዓሣ አንበሪ ሆድ፥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደነበረ÷ እንዲሁ የሰው ልጅ

(ወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስ) በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት

ይኖራል፡፡» ብሏቸዋል፡፡ ማቴ ፲፪፥፴፰-፵።

ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት የሞላው እንዴት ነው?፤

ጌታ በከርሰ መቃብር የቆየው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ነው፡፡ ይኽንንም

ለመረዳት ዕብራውያን ዕለታትን እንዴት እንደሚቆጥሩ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

እኛ በሀገራችን የሌሊቱን ሰዓት መቁጠር የምንጀምረው ከዋዜማው ከምሽቱ

አንድ ሰዓት ነው÷ የቀኑን ሰዓት መቁጠር የምንጀምረው ደግሞ ከማለዳው አንድ

ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ የሌሊቱ ሰዓት የሚያ ልቀው ከማለዳው አሥራ ሁለት ሰዓት

ሲሆን፥ የቀኑ ደግሞ ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ሲሆን ነው፡፡ የቀኑም

የሌሊቱም ሰ ዓት ተደምሮ ሃያ አራት ሰዓት ይሆናል፡፡ ሁሉም ሰዓት ዕለቱን

ይወክላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው እሑድ ዕለት ከሃያ አራቱ ሰዓ ት በአንዱ

ቢወለድ እሑድ ተወለደ ይባላል÷ ቢሞትም እሑድ ሞተ ይባላል፡፡ ዕለቱ

በሚጀምርበትም ሰዓት ሆነ፥ በሚያልቅ በት ሰዓት፥ ድርጊቱ ቢፈጸም ያ ሰዓት

እንደ አንድ መዓልትና እንደ አንድ ሌሊት ይቆጠራል፡፡ አውሮፓውያን አንድ

ብለው ሰዓት መቁጠር የሚጀምሩት በእኛ አቆጣጠር ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ነው፡

፡ እስከ ሃያ አራት ይቆጥሩና በእኛ አቆጣጠር ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሲሆን

ይጨርሳሉ፡፡ ሃያ አራት ሰዓት ሲሆን ዜሮ ይሉና እንደገና አንድ ብለው መቁጠር

ይጀምራሉ፡፡ በሌላ አነጋገር ከሌሊት እስከ ሌሊት ይቆጥራሉ፡፡ አሜሪካውያን

ደግሞ በእኛ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲሆን አንድ ብለው ይጀምሩና በእኛ ከቀኑ

ስድስት ሰዓት ሲሆን አሥራ ሁለት ብለው ይጨርሳሉ፡፡ ከዚያም በእኛ

40

አቆጣጠር ከቀኑ ሰባት ሰዓት እንደገና አንድ ብለው ይጀምሩና በእኛ ከሌሊቱ

ስድስት ሰዓት ሲሆን አሥራ ሁለት ብለው ይጨርሳሉ፡፡

ዕብራውያን ግን ዕለትን መቁጠር የሚጀምሩት ከዋዜማው ማለትም

በአውሮፓውያን ከአሥራ ሰባት ሰዓት÷ በአሜሪካውያን ከአምስት ሰዓት (P.M.)

÷ በእኛ ደግሞ ከምሽቱ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ

እስከ ቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ድረስ ሃያ አራት ሰዓት ቆጥረው አንድ ቀን ይላሉ፡

፡ ከላይ እንደተገለጠው እያንዳንዱ ሰዓት የዕለቱን መዓልትና ሌሊት ይወክላል፡፡

በዚህ መሠረት ጌታችን ከመስቀል ወርዶ የተቀበረው ዓርብ ቅዳሜ ከመግባቱ

በፊት ነው፡፡ ዓርብ ዕለቱ የሚጀምረው ከዋዜማው ሐሙስ በእኛ አቆጣጠር

ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ስለዚህ ጌታ የተቀበረው በዓርብ ሃያ

አራት ሰዓት ክልል ውስጥ በመሆኑ እንደ አንድ መዓልትና ሌሊት ይቆጠራል፡፡

ሁለተኛው ደግሞ ዓርብ ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ቀን

አሥራ አንድ ሰዓት ያለው ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ቅዳሜ ከቀኑ አሥራ አንድ

ሰዓት ጀምሮ እስከ እሑድ ቀን አሥራ አንድ ሰዓት ያለው ነው፡፡ ከዚህ በኋላ

የሰኞ ምሽት ይገባል፡፡ ጌታ የተነሣው በሦስተኛው ቀን እሑድ መንፈቀ ሌሊት

ነው።

እንዴት ተነሣ?

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሣው

በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ነው፡፡ ይህ ኃይልና ሥልጣን የባሕርይ ገንዘቡ ነው፡፡

ይኽንንም፡- «ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ (ሰውነቴን ከሞት አነሣት ዘንድ)

አኖራለሁና (በፈቃዴ እሞታለሁና)፤ ስለዚህ አብ ይወደኛል፡፡ እኔ በፈቃዴ

አኖራታለሁ እንጂ (ነፍሴን በፈቃዴ ከሥጋዬ ለይቼ በገነት÷ ሥጋዬንም

በመቃብር አኖራቸዋለሁ እንጂ) ከእኔ ማንም አይወስዳትም፡፡ (ያለ እኔ ፈቃድ

የሚፈጸም ምንም ነገር የለም)፡፡ ላኖራት (ነፍሴን በገነት÷ ሥጋዬን በመቃብር

ላኖራቸው) ሥልጣን አለኝ፤ ደግሞም ላነሣት (ነፍሴን ከሥጋዬ አዋሕጄ

ላነሣት) ሥልጣን አለኝ፡፡» በማለት አስቀድሞ ተናግሮታል፡፡ ዮሐ ፲÷፲፯-፲፰፡፡

ነቢዩ ኢሳይያስ፡- «ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ

እንደሚነዳ ጠቦት÷ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈ

ተም፡፡» በማለት መናገሩ ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ እንደሚሞት የሚያጠይቅ

ትንቢት ነበር፡፡ ኢሳ ፶፫፥፯፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም ከዚህ የሚመሳሰል

41

ቃል ተናግሯል፡፡ ፩ኛጴጥ ፪÷፳፴፡፡ በዚህ ዓይነት ነቢያትም ሐዋርያትም

የተናገሩለት ኢየሱስ ክርስቶስ በኃይሉ በሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጐ÷ ሙስና

መቃብርን አጥፍቶ ተነሥቷል፡፡ እርሱ የትንሣኤና የሕይወት ባለቤት ነውና፡፡

ዮሐ ፲፩÷፳፭፡፡

ይህ እንዲህ ከሆነ÷ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ፡- «የሕይወትን ራስ ገደላችሁት፤»

በማለት አይሁድን ከወቀሳቸው በኋላ፡- «እርሱን ግን እግዚአብሔር ከሙታን

አስነሣው፤» ለምን አለ? የሚል ጥያቄ ይነሣ ይሆናል፡፡ ይኽንን ኃይለ ቃል

በመያዝ «አብ አስነሣው እንጂ በራሱ አልተነሣም፤» የሚሉ አሉና፡፡ እነዚህም

ትርጓሜውን ያልተረዱ ምሥጢሩን ያላስተዋሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ሐዋርያው

«እግዚአብሔር አስነሣው፤» ያለው «እግዚአብሔር» የሚለው ስም የሦስቱም

መጠሪያ እንጂ የአብ ብቻ አለመሆኑን ስለሚያውቅ ነው፡፡ ምክንያቱም፦

ወልድም እግዚአብሔር ተብሎ ይጠራል፡፡ ዮሐ ፩÷፩ ፣ የሐዋ ፳÷፳፰፡፡ መንፈስ

ቅዱስም እግዚአብሔር ተብሎ ይጠራል፡፡ ዮሐ ፩÷፪፡፡ ስለዚህ፦ ሥላሴ በፈቃድ

አንድ በመሆናቸው፥ «አንዲት በሆነች በአብ በራሱና በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድና

ሥልጣን ተነሣ፤ አንድም፦ ወደ መቃብር የወረደ ሥጋ፥ መለኰት የተዋሐደው

ስለሆነ ተነሣ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር በመሆኑ ተነሣ፤» ተብሎ

ይተረጐማል፥ ይታመናል፡፡ ትንቢተ ነቢያትም የሚያረጋግጥልን ይኽንኑ ነው፡፡

«እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ÷ የወይን ስካር እንደተወው

እንደ ኃያልም ሰው፤ ጠላቶቹንም በኋላቸው መታ፤» ይላል። መዝ ፸፯፥፷፭።

ለምን በአዲስ መቃብር ተቀበረ?

በእስራኤል ባሕል፥ የአባቶቻቸው አፅም ካረፈበት መቃብር፥ የመቀበር ልማድ

አላቸው፡፡ ዮሴፍ በግብፅ የእስራ ኤልን ልጆች፡- «እግዚአብሔር ሲያስባችሁ

አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ፤» ብሎ ያማላቸው፥ የአባቶቹ

የአብርሃም እና የይስሐቅ የያዕቆብም አፅም ካረፈበት ለመቀበር ፈልጐ ነው፡፡

ዘፍ. ፶÷፳፭፡፡ በቤቴል የነበረውም ሽማግሌ ነቢ ይ፡- «በሞትሁ ጊዜ

የእግዚአብሔር ሰው በተቀበረበት መቃብር ቅበሩኝ፤ አጥንቶቼንም በአጥንቶቹ

አጠገብ አኑሩ፤» ብሏል ፡፡ ፩ኛነገ ፲፫÷፴፩፡፡ ጌታችን የተቀበረው እንደ

እስራኤል ባሕል የቅዱሳን አፅም ካረፈበት ሳይሆን ማንም ካልተቀበረበት

ከአዲስ መቃብር ነው፡፡ ይኸውም ዮሴፍ ለራሱ ያዘጋጀው ነው፡፡ «ዮሴፍም

ሥጋውን ይዞ በንጹሕ በፍታ ከፈነው÷ ከዓለት በወቀረ ው በአዲሱ መቃብርም

42

አኖረው÷ በመቃብሩም ደጃፍ ታላቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ፤» ይላል ማቴ

፳፯÷፶፱፡፡ ይህም የሆነው እርሱ ባወቀ በርሱ ጥበብ ነው፡፡ እንዲህም በማድረጉ

አይሁድ ለትንሣኤው ምክንያት እንዳያበጁለት አድርጓቸዋል፡፡ በብሉይ ኪዳን

እንደተጻፈው፥ ከነቢዩ ከኤልሳዕ መቃብር ተቀብሮ የነበረው ሰው፥ የነቢዩ

አጥንት በነካው ጊዜ፥ በተአምር ተነሥቷል። ፪ኛነገ ፲፫÷፳፡፡ እንግዲህ

ጌታችንም፥ ከአንዱ ቅዱስ መቃብር ተቀብሮ ቢሆን ኖሮ፥ ሞትን ድል አድርጐ

በሚነሣበት ጊዜ «በራሱ አልተነሣም፥ የቅዱሱ አፅም ነው ያስነሣው፤» ባሉት

ነበር፡፡ ይኸንን ምክንያት ለማጥፋት ነው፥ በአዲስ መቃብር የተቀበረው።

እንዴት በዝግ መቃብር ተነሣ?

ጌታችንን ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ገንዘው ከቀበሩት በኋላ፥ የካህናት አለቆችና

ፈሪሳውያን ወደ ጲላጦስ ተመልሰው፡- « ጌታ ሆይ÷ ያ ሰው (ክርስቶስ)፥ ገና

በሕይወቱ ሳለ፥ ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ፥ እንዳለ ትዝ አለን፡፡ እንግዲህ

ደቀመዛሙርቱ መጥተው በሌሊት እንዳይሰርቁት ለሕዝቡም ከሙታን ተነሣ

እንዳይሉ÷ የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለችና መቃብሩ

እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ አሉት፡፡ ጲላጦስም፡- ጠባቆች

አሉአችሁ፥ እንዳወቃችሁ አስጠብቁ፤» አላቸው፡፡ እነርሱም ሄደው ከጠባቆች

ጋር ድንጋዩን አትመው መቃብሩን አስጠበቁ፡፡» ማቴ ፳፯፥ ፷፫÷፷፮፡፡ በታላቅ

ድንጋይ የተገጠመው መቃብር፥ ድንጋዩ እንደታተመ፥ ክርስቶስ ሞትን ድል

አድርጐ ተነሥቷል፡፡ ይኸውም፦ ምንም የማያግደው መለኰት በተዋሕዶ

ከሥጋ ጋር በመቃብር ስለነበረ ነው፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ እንደተናገረው፥

በተዋሕዶ፥ የቃል ገንዘብ ለሥጋ፥ የሥጋም ገንዘብ ለቃል በመሆኑ ነው፡፡

ለምሳሌ፦ አይሁድ ብዙ ጊዜ በድንጋይ ቀጥቅጠው ሊገድሉት ሲፈልጉ፥ እያዩት

ይሰወርባቸው ከእጃቸውም ይወጣ ነበር፡፡ በመካከላቸው አልፎ ሲወጣ

አያዩትም ነበር፡፡ ዮሐ ፰÷፶፱፤ ፲፥፴፱፡፡ ይህም የሆነው፥ እንደ ነፍስና ሥጋ

ተዋሕዶ፥ መለኰት ሥጋን በመዋሐዱ ነው፡፡ ከትንሣኤው በኋላም ከአንዴም

ሁለት ጊዜ ከተዘጋ ቤት በሩ ሳይከፈት የገባው ለዚህ ነው፡፡ ዮሐ ፳÷፲፱፤ ፳፮፡፡

በልደቱም ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና እንደታተመች

የተወለደው ለዚህ ነው፡፡ ኢሳ ፯÷፲፬፡፡ ማቴ ፩÷ ፳-፳፫ ፣ ሉቃ ፪÷፮-፯፡

43

መቃብሩን ማን ከፈተው?

ጌታችን የተነሣው መግነዝ ፍቱልኝ፥ መቃብሩን ክፈቱልኝ ሳይል ከሆነ፥

«መቃብሩን ማን ከፈተው? ለምንስ ተከ ፈተ?» የሚል ጥያቄ ይነሣ ይሆናል፤

በወንጌል እንደተጻፈው፥ የአይሁድ ሰንበት ቅዳሜ ካለፈ በኋላ፥ እሑድ

በማለዳ፥ ፀሐይ ሲወጣ፥ መግደላዊት ማርያም÷ የያዕቆብም እናት ማርያም

ሶሎሜም ሽቱ ሊቀቡት ወደ መቃብሩ መጥተው ነበር፡፡ ትልቁ ጭንቀታቸው

«ድንጋዩን ከመቃብሩ ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል?» የሚል ነበር÷ ድንጋዩ እጅግ

ትልቅ ነበርና፤ አሻቅበውም አይተው ድንጋዩ ተንከባሎ እንደነበር ተመለከቱ፡፡

ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጐናጸፈ ጐልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ

አዩና ደነገጡ፡፡ በጐልማሳ አምሳል የተገለጠላቸው የጌታ መልአክ ነው፡፡ እርሱ

ግን፡- «አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን እንደምትፈልጉ

አውቃለሁ፤ ተንሥቷል በዚህ የለም፡፡» አላቸው፡፡ ማር ፲፮÷፩-፮፡፡ ጌታችን

በዝግ መቃብር ከተነሣ በኋላ ባዶ የነበረውን መቃብር የከፈተው ይህ የጌታ

መልአክ ነው፡፡ የከፈተበትም ምክንያት በእምነት የመጡ እነዚህ ሴቶች ያልተነሣ

መስሏቸው ዘወትር በመመላለስ እንዳይቸገሩ ነው፡፡ አንድም ትንሣኤውን

እንዳይጠራጠሩ ነው፡፡ በቅዱስ ማቴዎስ ወንጌልም «በሰንበትም መጨረሻ

የመጀመሪያው ቀን ሲነጋ፥ መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ማርያም

መቃብሩን ሊያዩ መጡ፡፡ እነሆም የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለወረደ ታላቅ

የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ፡፡ መልኩም

እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ፡፡ ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት

የተነሣ ተናወጡ፡፡ እንደ ሞቱም ሆኑ፡፡ መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው፥

እናንተስ አትፍሩ፤ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንደምትሹ አውቃለሁና፤ እንደ

ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤» የሚል ተጽፏል፡፡ ማቴ ፳፰÷፩-፮፡፡ ደቀ

መዛሙርቱ በእርግጠኝነት ትንሣኤውን ያመኑት መልአኩ ወደ ከፈተው

መቃብር ገብተው መግነዙን ካዩ በኋላ ነው። ዮሐ ፳፥፯።

በኲረ ትንሣኤ፤

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለባሕርይ አባቱ፥ ለአብ

44

ለእናቱ ለድንግል ማርያምም የበኵር ልጅ ነው፡፡ ዕብ ፩÷፮፣ ሉቃ ፪÷፯፡፡ ለበጎ

ነገርም ሁሉ በኵር በመሆኑ የትንሣኤያችንም በኵር እርሱ ነው፡፡ «አሁን ግን

ክርስቶስ ላንቀላፉት በኵራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቷል፡፡ ሞት በሰው (በቀዳማዊ

አዳም) በኵል ስለመጣ፥ ትንሣኤ ሙታን በሰው (በተዋሕዶ ሰው በመሆኑ

ዳግማዊ አዳም በተባለ በክርስቶስ) በኩል ሆኗልና፡፡ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ

እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ

ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኵራት ነው፤» ይላል፡፡ ፩ኛቆሮ ፲፭÷፳-፳፫፡፡

በተጨማሪም፡- «በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥሯልና፥ ከፍጥረት

ሁሉ በፊት በኵር ነው፡፡ (ከፍጥረታት በፊት የነበረ÷ የፍጥረታት አለቃ÷

የፈጠረውን ፍጥረት የሚገዛ ነው)፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሯል ፤ እርሱም

ከሁሉ በፊት ነው፤ (ለዘመኑ ጥንት የሌለው ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር

በአንድነት በህልውና የነበረ ነው)፤ ሁሉም በእርሱ ተጋጥሟል፡፡ እርሱም የአካሉ

ማለት የቤተ ክርሰቲያን ራስ ነው፤ እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ መጀመሪያ

ከሙታንም በኵር ነው፡፡» የሚል አለ፡፡ ቈላ ፩÷፲፮-፲፰፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም፡-

«ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም÷ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት÷

ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ

ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን፤» ብሏል። ራእ ፩፥፭።

በብሉይ ኪዳን እነ ኤልያስ÷ እነ ኤልሳዕ ሙት አስነሥተዋል፡፡ ፩ኛነገ ፲፯፥፳፪ ፣

፪ኛነገ ፬÷፴፪-፴፰፡፡ በአዲስ ኪዳንም ራሱ ባለቤቱ የመኰንኑን ልጅ ÷

የመበለቲቱን ልጅ÷ አልዓዛርንም ከሞት አንሥቷቸዋል፡፡ ማቴ ፱÷፳፭፣ ሉቃ

፯÷፲፭ ፣ ዮሐ ፲፩÷፵፬፡፡ ነፍሱን በመስቀል ላይ በፈቃዱ አሳልፎ በሰጠም ጊዜ

አያሌ ሙታን ከእግረ መስቀሉ ተነሥተዋል፡፡ ማቴ ፳፯÷፶፫፡፡ እነዚህ ሁሉ በኵረ

ትንሣኤ አልተባሉም፡፡ ምክንያቱም፦ አንደኛ፥ በራሳቸው ኃይል የተነሡ

አይደሉም፡፡ ሁለተኛ፥ ለተወሰነ ጊዜ ከኖሩ በኋላ ተመልሰው ሞተው ትንሣኤ

ዘጉባኤን የሚጠብቁ ሆነዋል፡፡ ሦስተኛ፥ ፍጡራን ናቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ

ግን የባሕርይ አምላክ በመሆኑ በራሱ ኃይልና ሥልጣን ተነሥቷል፡፡ ዳግመኛም

አይሞትም፡፡ ይኽንንም፡- «ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደፊት እንዳይሞት፥

ሞትም ወደፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና ÷ መሞትን አንድ ጊዜ ፈጽሞ

ለኃጢአት ሞቷልና፡፡» በማለት ሐዋርያው ገልጦታል፡፡ ሮሜ ፮÷፱፡፡ ጌታችንም፡

- «ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ ሞቼም ነበርሁ እነሆም ከዘላለም

እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፤» ብሏል። ራእ ፩፥፲፰።

ከትንሣኤው በኋላ ለምን ተመገበ?

45

ጌታችን በተዘጋ ቤት ገብቶ ለደቀ መዛሙርቱ በተገለጠ ጊዜ፥ መንፈስ የሚያዩ

መስሏቸው ኅሊናቸው ደንግጦ÷ ልባቸውም ፈርቶ ነበር፡፡ እርሱም፡- «ስለ ምን

ትደነግጣላችሁ? ስለምንስ አሳብ በልባችሁ ይነሣል? እኔ ራሴ እንደሆንሁ

እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት÷ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና፥

እኔን ዳስሳችሁ እዩ፤» ካላቸው በኋላ እጆቹንና እግሮቹን አሳይቷቸዋል።

እነርሱም ከደስታ የተነሣ ገና ስላላመኑ ሲደነቁ ሳሉ፡- «በዚህ አንዳች የሚበላ

አላችሁን?» አላቸው። እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ ከማር ወለላም

ሰጡት፤ ተቀብሎም በፊታቸው በላ፥ ይላል። ሉቃ ፳፬÷፴፮ -፵፫። ለሦስተኛ

ጊዜ በጥብርያዶስ በተገለጠላቸውም ጊዜ አብሯቸው ተመግቧል፡፡ ዮሐ ፳፩÷፱-

፲፬። ይኽንንም ያደረገው ከትንሣኤ በኋላ መብላት መጠጣት ኖሮ አይደለም፡፡

አለማመናቸውን ለመርዳት ነው፡፡ ደቀመዛሙርቱ በተዋሐደው ሥጋ ለመነሣቱ

እርግጠኞች እንዲሆኑ ነው፡፡ ከወንጌሉ እንደምንረዳው ደቀመዛሙርቱ ይበልጥ

እርግጠኞች የሆኑት ስላዩት ሳይሆን፥ ያቀረቡለትን በመብላቱና በመጠጣቱ

ነውና፡፡

ለምን አትንኪኝ አላት?

መግደላዊት ማርያም ገና ሰማይና ምድሩ ሳይላቀቅ፥ በማለዳ፥ ሽቱ ልትቀባው

ከመቃብሩ አጠገብ ተገኝታ ነበር። እንደደረሰችም ድንጋዩ ከመቃብሩ አፍ

ተፈንቅሎ አየች። ይህች ሴት በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ከባለቤቱ

ብትሰማም፥ « እንደተናገረ ተነሥቶ ነው፤» ብላ አላመነችም። ላለማመኗም

ምክንያት የሆነው፥ «እኛ ተኝተን ሳለን ደቀመዛሙርቱ በሌሊት ሰረቁት፤»

የሚለው የጭፍሮች ወሬ ነው። ጭፍሮቹ እውነትን በሐሰት ለውጠው ይኽንን

ያወሩት፥ በገንዘብ ተደልለው ነው፡፡ ማቴ ፳፰÷፲፩-፲፭፡፡ ለዚህ ነው ወደ

ደቀመዛሙርቱ ሄዳ፡- «ጌታን ከመቃብር ወስደውታል፥ ወዴትም እንዳኖሩት

አላውቅም፤» ያለቻቸው፡፡ ዮሐ ፳÷፪፡፡ ከመቃብሩ ራስጌና ግርጌ ሁለት

መላእክት ተገልጠውላት፡- «አንቺ ሴት ስለምን ታለቅሻለሽ?» ባሏት ጊዜም፥

«ጌታዬን ወስደውታል፥ ወዴትም እንዳኖሩት አላውቅም፤» ብላቸዋለች፡፡ ዮሐ

፳÷፲፫፡፡ በመጨረሻም ጌታ ራሱ ተገልጦላት፡- «አንቺ ሴት ስለምን ታለቅሻለሽ?

ማንንስ ትፈልጊያለሽ?» ሲላት አላወቀችውም፡፡ ለዚህ ነው፥ አትክልት ጠባቂ

መስሏት፡- «ጌታ ሆይ፥ አንተ ወስደኸው እንደሆንህ፥ ወዴት እንዳኖርኸው

ንገረኝ፥ እኔም ወስጄ ሽቱ እንድቀባው፤» ያለችው፡፡ ዮሐ. ፳÷፲፭፡፡ በዚህን ጊዜ፥

46

«ማርያም»፥ ብሎ በስሟ ቢጠራት በድምፁ አወቀችውና «ረቡኒ ( መምሕር

ሆይ)» አለችው፡፡ መልኩን አይታ፥ ድምፁን ሰምታ÷ ትንሣኤውን አረጋግጣ፥

«አምላኬ» አላላችውም፡፡ ስለዚህ «ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና፤ አትንኪኝ፥ ነገር

ግን ወደ ወንድሞቼ (ወደ ደቀመዛሙርቴ) ሄደሽ እኔ ወደ አባቴና ወደ

አባታችሁ÷ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ አርጋለሁ ብሏል፥ ብለሽ

ንገሪያቸው፤» አላት፡፡ እንዲህም ማለቱ የእርሱ የእግዚአብሔር ልጅ መባልና

የእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች መባል ፍጹም የተለያየ በመሆኑ ነው፡፡ እርሱ፥

«አባቴ» ቢል የባሕርይ ልጅ በመሆኑ ነው፡፡ እነርሱ ግን የጸጋ ልጆች ናቸው፡፡

እርሱ፥ «አምላኬ» ቢል ስለተዋሐደው ሥጋ ነው፡፡ የተዋሐደው የፈጠረውን

ሥጋ ነውና ፡፡ እነርሱ ግን «አምላካችሁ» ቢባሉ ፍጡራን ስለሆኑ ነው፡፡

በዚህም እርሱ ፈጣሪ እነርሱ ፍጡራን መሆናቸውን አስረግጦ ተናግሯል፡፡

ቶማስን ግን፡- «ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ

አግባው ፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን፤» ብሎታል፡፡ ዮሐ ፳፥፳፯ ፡፡

ምክንያቱም አይቶ፥ ዳስሶ፥ «ጌታዬ አምላኬም» ብሎ የሚያምን ነውና፡፡ አንድም

ሥጋውንና ደሙን ለመዳሰስ÷ ለመፈተት፥ የተጠራ የተመረጠም ካህን ነውና፡፡

ተስፋ ትንሣኤ፤

በብሉይ ኪዳን ዘመን ሁሉም በአዳም ኃጢአት ምክንያት እየተኰነኑ በሞተ

ነፍስ ተይዘው ወደ ሲኦል ይወርዱ ነበር ። ፩ኛ ቆሮ ፲፭ ÷፳፪፡፡ «ነገር ግን

በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ ከአዳም ጀምሮ እስከ

ሙሴ ( እስከ ክርስቶስ) ድረስ ሞት ነገሠ፤» የተባለው ለዚህ ነው፡፡ ሮሜ ፭÷፲፬፡

፡ ከዚህ የተነሣ እነ አብርሃም እንኳ ሳይቀሩ የወረዱት ወደ ሲኦል ነው፡፡ እነ

ኢሳይያስ፡- «ጽድቃችንም ሁሉ እንደመርገም ጨርቅ ነው፤» ያሉት ለዚህ ነው፡፡

ኢሳ ፷፬ ÷፮፡፡ እነ ኤርምያስም፡- «ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም፥ ስንዴን ዘሩ

እሾህንም አጨዱ፡፡» ብለዋል፡፡ ኤር ፲፪÷፲፫። በዚህ ምክንያት የብሉይ ኪዳን፥

ዘመን ዘመነ ፍዳ÷ ዘመነ ኵነ ÷ ዘመነ ጽልመት ተብሏል፡፡ በዚህ ዘመን እነ ቅዱስ

ዳዊት፡- «አንሥእ ኃይለከ÷ ወነዓ አድኅነነ፤ ኃይልህን አንሣ÷ እኛንም ለማዳን ና

፤ (በሥጋ ተገልጸህ÷ ሰው ሁነህ አድነን)፤» እያሉ ወልድን ተማጽነዋል፡፡ መዝ

79÷ 2 ፡፡ «ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ፤ ብርሃንህንና እውነትህን ላክልን፤ (ብርሃን

ወልድን÷ እውነት መንፈስ ቅዱስን ላክልን) ፤ እነርሱ ይምሩን÷ ወደ ቅድስናህ

ተራራና ወደ ማደሪያህ÷ (ወደ ገነት ወደ መንግሥተ ሰማያት) ይውሰዱን »፤

47

እያሉም አብን ተማጽነዋል፡፡ መዝ ፵÷፫፡፡ ይህም የሚያመለክተው በዚያ

በጨለማ ዘመን ሆነው ተስፋቸው የክርስቶስ ትንሣኤ እንደነበረ ነው፡፡ በሞት

አጠገብ ሕይወት÷ በመቃብር አጠገብ ትንሣኤ እንዳለ ተስፋ እንዲያደርጉ

የሚያደርጋቸው የክርስቶስ ትንሣኤ ነውና፡፡ ያንጊዜ ከሲኦል እንደሚወጡ፥

የተዘጋች ገነትም እንደምትከፈትላቸው ያውቃሉና፡፡

የክርስቶስ ትንሣኤ የአዳም ልጆች በጠቅላላ ትንሣኤ ዘጉባኤን በተስፋ

እንዲጠብቁ አድርጓቸዋል፡፡ ይህም ተስፋ ሃይማኖት እንዲይዙ÷ ምግባር

እንዲሠሩ አጽንቷቸዋል፡፡ ምድራዊውን እንዲንቁ፥ ሰማያዊውን እንዲናፍቁ

አድርጓቸዋል፡፡ « ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ

ቃሉ እንጠብቃለን፡፡» ይላል፡፡ ፪ኛ ጴጥ ፫÷፲፫፡፡ ቅዱሳን በሃይማኖት

አይተዋታል፡፡ «አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ÷ ፊተኛው ሰማይና

ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና÷ ባሕርም ወደፊት የለም፡፡ ቅድስቲቱም ከተማ

አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለባልዋ እንደተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከሰማይ

ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ፡፡» ይላል፡፡ ራእ ፳፩÷፫፡፡

እግዚአብሔርም፡- «እነሆ÷ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እፈጥራለሁና፥

የቀደሙትም አይታሰቡም÷ ወደ ልብም አይገቡም፡፡ ነገር ግን በፈጠርሁት ደስ

ይበላችሁ፥ ለዘላለምም ሐሴት አድርጉ፤ እነሆ÷ ኢየሩሳሌምን ለሐሴት÷

ሕዝቧንም ለደስታ እፈጥራለሁና፡፡» ብሏል፡፡ ኢሳ ፷፭፥፲፯።

ሙታን እንዴት ይነሣሉ?

እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሲፈጥረው የሚያንቀላፋና የሚነቃ አድርጐ

ፈጥሮታል፡፡ ማንቀላፋቱ የሞት፥ መንቃቱ ደግሞ የትንሣኤ ምሳሌ ነው፡፡ አቤል

ከሞተ በኋላ በደሙ መናገሩም የትንሣኤ ምሳሌ ነው፡፡ ዘፍ ፬÷፲፡፡ የሄኖክም

ከዓይነ ሞት ተሰውሮ በእግዚአብሔር መወሰድ የትንሣኤ ምሳሌ ነው፡፡ ዘፍ

፭÷፳፬፡፡ ፍጥረታት በጠቅላላም ትንሣኤን የሚሰብኩ ናቸው፡፡ የፀሐይ

መውጣት የመወለድ÷ የፀሐይ መጥለቅ የመሞት÷ ከጠለቀች በኋላም እንደገና

መውጣት የትንሣኤ ምሳሌ ነው፡፡

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙታን እንደሚነሡ

በቃልም በተግባርም አስተምሯል፡፡ በቃል ፡- «በመቃብር ያሉት ሁሉ ድምፁን

የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ መልካምም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ÷ ክፉም

48

ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ፡፡» ሲል አስተምሯል፡፡ ዮሐ

፭÷፳፱፡፡ በተግባርም የአራት ቀን ሬሳ አልዓዛርን አስነሥቷል፡፡ ዮሐ ፲፩÷፵፫፡፡

ቅዱሳን ነቢያት፡- እነ ኢሳይያስ «ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፥ ሬሳዎችም ይነሣሉ፡

፡» ብለዋል። ኢሳ ፳፮÷፲፱፡፡ እነ ዳንኤልም፡- «በምድርም ትቢያ ውስጥ

ካንቀላፉት ብዙዎች (ሁሉም) ይነቃሉ፤ እኵሌቶችም ወደ ዘላለም ሕይወት÷

እኵሌቶችም ወደ እፍረትና ዘላለም ጉስቊልና፡፡» ብለዋል፡፡ ዳን ፲፪÷፪፡፡

በተለይም ለነቢዩ ለሕዝቅኤል፥ እግዚ አብሔር፦ በአፅም የተሞላ ታላቅ ሸለቆ

ካሳየው በኋላ፥ «እነዚህ የደረቁ አጥንቶች ተመልሰው በሕይወት የሚኖሩ ይመስ

ልሃልን?» ሲል ጠይቆታል፡፡ ሕዝቅኤልም፡- «እግዚአብሔር ሆይ÷ አንተ

ታውቃለህ፤» የሚል መልስ ሰጥቶቷል፡፡ በመጨ ረሻም እነዚህ ሁሉ ሕይወት

ዘርተው ሲነሡ አይቷል፡፡ ይኸንንም፡- «እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ÷

ትንፋሽም ገባባቸው፥ ሕያዋንም ሆኑ÷ እጅግም ታላቅ ሠራዊት ሆነው

በእግራቸው ቆሙ፡፡» በማለት ገልጦታል፡፡ ሕዝ ፴፯፥፩-፲፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ሙታን ትንሣኤ በሚገባ ቋንቋ አብራርቶ

በምሳሌ ሲያስተምር «ነገር ግን ሰው፥ ሙታን እንዴት ይነሣሉ? በምንስ ዓይነት

አካል ይመጣሉ? የሚል ይኖር ይሆናል፡፡» ብሎ ከጠየቀ በኋላ፥ «አንተ ሞኝ

አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም፡፡» ብሏል፡፡ ከዚህም አያይዞ

«የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲሁ ነው፡፡ በመበስበስ ይዘራል÷ ባለመበስበስ

ይነሣል፤ በውርደት ይዘራል በክብር ይነሣል፤ በድካም ይዘራል÷ በኃይል

ይነሣል፤ ፍጥረታዊ አካል ይዘራል÷ መንፈሳዊ አካል ይነሣል ፤ ፍጥረታዊ አካል

ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ፡፡ እንዲሁ ደግሞ፡- ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው

ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም (ክርስቶስ) ሕይወትን የሚሰጥ

መንፈስ ሆነ፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ ፍጥረታዊው ቀጥሎም መንፈሳዊው ነው

እንጂ መንፈሳዊው መጀመሪያ አይደለም። የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ

ነው። ሁለተኛው ሰው ( ክርስቶስ ) ከሰማይ ነው፡፡ መሬታዊው እንደሆነ

መሬታውያን የሆኑት ደግሞ እንዲህ ናቸው÷ ሰማያዊው እንደ ሆነ ሰማያውያን

የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው ፡፡ የዚያንም የመሬታዊውን መልክ እንደ ለበስን

የሰማያዊውን መልክ ደግሞ እንለብሳለን፡፡» ብሏል። ፩ኛቆሮ ፲፭÷፴፭-፵፱፡፡

በፊልጵስዩስ መልእክቱም፡- «ክቡር ሥጋውን እንደሚስል የተዋረ ደውን

ሥጋችንን ይለውጣል፡፡» ብሏል፡፡ ፊል ፫÷፳፩። ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም፡-

«እርሱን እንድንመስል እናውቃለን፤» ብሏል፡፡ ፩ኛ ዮሐ ፫÷፪።

የትንሣኤ ጸጋ፤

49

በክርስቶስ ትንሣኤ ያገኘነው ጸጋ ታላቅ ነው። ከጨለማ ወደ ብርሃን

ወጥተናል÷ ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋግረናል ። ሙታን የነበርን ሕያዋን÷

ምድራውያን የነበርን ሰማያውያን÷ ሥጋውያን የነበርን መንፈሳውያን ሆነናል፡፡

«ሞት ሆይ÷ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ÷ ድል መንሣትህ የት አለ?» የምንል

ሆነናል፡፡ ሆሴ ፲፫÷፲፬ ፣ ፩ኛቆሮ ፲÷፶፭፡፡ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ «እኛ አገራችን

በሰማይ ነውና÷ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ

ክርስቶስን እንጠ ባበቃለን፤ እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ

እንደሚችልበት አሠራር ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋች ንን

ይለውጣል፡፡» የምንል ሆነናል፤ ፊል ፫፥ ፳-፳፩፡፡ ናፍቆታችን ሁሉ በትንሣኤ

ያገኘነውን ጸጋ እውን ማድረግ ነው፡፡ «ድንኳን የሚሆነው ምድራዊው

መኖሪያችን ቢፈርስ፥ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘላለም ቤት የሚሆን

ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ እንዳለን እናውቃለንና፡፡ በዚህ ውስጥ በእውነት

እንቃትታለንና÷ ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድን ለብስ

እንናፍቃለንና ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም፡፡» ይላል፡፡ ፪ኛቆሮ ፭፥፩-፪፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም፡- «ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው

ተስፋና ለማይጠፋ÷ እድፈትም ለሌለበት÷ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ

ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ይባረክ» ብሏል፡፡

፩ኛጴጥ ፩÷፫፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም፡- «በሚመጡ ዘመ ናትም በክርስቶስ ኢየሱስ

ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳ የን ዘንድ

ከእርሱ ጋር አስነ ሣን፤ በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊው ስፍራ ከእርሱ ጋር

አስቀመጠን።» ብሏል። ኤፌ፪÷፮-፯።

የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን አሜን፡፡

ሱባኤ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ምንይመስላል?

ሱባዔ፦ በሰው፤ በቦታና በሰአት ስለሚከናወን የሶስቱም ማለትም የሰአት፤

የሰባዊነትና የመካን ድምር ነው። ሱባዔ በኦርቶዶክስ

50

ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥልቅ፤ ረቂቅና ምጡቅ ግንዛቤ አለው። በመንፈሳችንና

በሥጋችን መካከል ያለውን ሚዛን አለመሰበሩንና አለማጋደሉን፤ በፈጣሪያችንና

በራሳችን መካከል፤ በህዝባችንና በራሳችን መካከል ያለንን ግንኙነት

የምንፈትሽበት ነው። በሩቅና በቅርብ ያለውን አካባቢያችንን ማየት የምንችልበት

ተራራ ነው። ውስጣዊ ህሊናችንን የምናይበት ረቂቅ መስታወት ነው። የራቀውን

አቅርቦ የረቀቀውን አጉልቶ የሚያሳየን፤ እመቀ እመቃት፡ አየረ አየራት፡ ያሉትን

ሁሉ ፍጥረታት የምንፈትሽበት ተራዛሚ መነጽር ነው።

ሱባዔ፦ በሰው ብቻ የተወሰነ አይደለም። በደማቸው ሞቃትነትና ቀዝቃዛነት

የሚለያዩ ፍጥረታት በየደረጃቸው ሱባዔ ይገባሉ።

የፍጥረታትን ቅደም ተከተል በመጠበቅ የደመ ሞቃት እንስሳትንና፤ የዘንዶን

ሱባዔ ከዳሰሰን በኌላ፤ የዘመናችን በተለይም የመነኮሳት ሱባኤ ከጥንታዊት

ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሱባዔ ተቀይሮ፤ ከደመ ሞቃት

እንስሳት ምን ያህል እንደራቀና ወደ ዘንዶ ሱባዔ እንደተቀረ በማነጻጸር፤ ይህ

የዘንዶ አይነት ሡባዔ የማይታረም ባለበት የሚቀጥል ከሆነ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ

አባላት ሁሉ ወንዱም ሴቱም በተለይ ትዳር ያፈረሰ በዝሙት በሌብነት

በዘራፊነት የተከሰሰ ሁሉ ቆቡን እያጠለቀ፤ ምንኩስና ቁምስና ወደ ተላበሰ

ቅስናና ሊቀ ጳጳስና እኛም እንግባ ብሎ መነሳቱ መፍትሄው ይመስለኛል።

ሁሉንም አይተን ከምዳሜ ለመድረስ ከደመ ሞቃት እንስሳት ሱባዔ

እጀምራለሁ።

የእንስሳት ሱባዔ

በዚህች ጦማር የምናተኩረው በዘንዶ ሱባዔ ላይ ቢሆንም፤ የሚያድጉ የሚያረጁ

የሚሞቱ ደመ ሞቃት እንስሳትም ሰባኤ አላቸው። ሥጋቸው እንዲበሉ

የተፈቀዱት እንስሳት ቀኑን ሲሰበስቡ የዋሉትን ከሆዳቸው ወደ አፋቸው

መልሰው በማምጣት በማመንዥክ ሱባዔ ይገባሉ። እኛ ሰዎች የምናመነዥከው

አእምሯችን የቋጠረውን ሀሳብ ነው። ከሳረ በላዎች እንስሳት እንለያለን።

የዋጠውን እያራገፈ እንደገና ለመዋጥ ከሚቅነዘነዝ ዘንዶም እንለያለን።

ጥልቀቱንና ይዘቱን በዚህ ጥናት ለተሰማሩ ጠበብቶች ልተወውና፤ ሰባዊ ሱባዔን

በጉሉህ መረዳት እንችል ዘንድ፤ የዘንዶን ሱባዔ በቅድሚያ ለመግለጽ

እሞክራለሁ።

51

የዘንዶ ሱባዔ

ሱባኤ፤ ሰው ጉሉሁንና ረቂቁን የሚታየውንና የማይታየውን ፈተና (challenge)

አሸንፎ የሚወጣበት ስልት ስለሆነ ተጠልፎ ከወደቀበት ከዘንዶ ተለይቶ

አይታሰብም። ስለዚህ ከሰባዊ ሱባኤ በፊት ሰው ተፈትኖ የወደቀበትን ዘንዶን

መመልከቱ ሰባዊ ሱባኤን ስንመለከት በጥልቅ እንድንረዳው ያግዘናል። ዘንዶ

ደመ ቀዝቃዛ ነው። ሰውነቱን እንደ ወቅቱ ይለዋወጣል። ስለ ሰውነቱ ሙቀት፤

ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት እንደ ዘመናውያን ሊቃውንት “በ50 ዲግሪ

ፋራናይት ያወርደዋል” አይበሉ እንጅ፤ ከፍና ዝቅ እንደሚያደርገው ይናገራሉ።

የዋጠው ከሰውነቱ ጋራ እስኪወሀድና፤ የተሸከመው አሮጔ ሰውነቱ ሲከብደው

ለማስወገድ ራሱን ይደብታል። (ሱባዔ ይገባል)። የድበታውን ጊዜ (ሱባዔውን)

ጨርሶ አሮጌ ገላውን ሸልቅቆ ካስወገደና ስባቱንም ካቃጠለ በኋላ፤ ባካካባቢው

አየር ንብረት እየተገፋ ባዲስ ኃይልና ጉልበት የሚውጠውን ፍለጋ በመቅበዝበዝ

ይንቀሳቀሳል። ዘንዶ ያለመደውን አያውቅም። ይልቁንም ያለመደውን

ይውጣል። የሚያመነጨው የሙቀት ሃይል እንደሌሎች እንስሳት ከሚመገበው

አይደለም። ባካባቢው አየር ንብረት ላይ የተመሰረተ ነው። ስለ ዘንዶ ባህርይ

እጅግ በጣም ያስገረመኝ፤ የኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አባቶች “ዘመን ሲከፋ

ሰው እርሱ በርሱ የሚባላ ዘንዶ ይሆናል” ብለው ሲናገሩ የሰማሁትን፤ የተፈጥሮ

ሳይንስ ሊቃውንት “በርዝመትና በስፋት ከሱ እኩል የሆነውን ዘንዶ ሌላው

ዘንዶ ይውጠዋል” ብለው የገለጹትን በተግባር ማየቴ ነው። ማረጋገጥ ከፈለጉ፤

[ይህን እባብ እባን ሲውጥ የሚያሳይ ቪዲዮ ]: በመጫን ይመልከቱ::: ቀጥለን

ሰባዊ ሱባኤን በጥሞና እንመልከት።

ሰባዊ ሱባኤ

ክርስቶስ “ሰው በዳቦ ብቻ አይኖርም” (ማቴ ፬፡፬) ብሎ ስለ ሰባዊነት ባህርይ

ተናግሯል። ይህ ንግግር ከመለኮታዊ እና ከሰባዊ ውህደት የመነጨ ስለሆነ

መለኮት የማያጥፈው ሰው የማይሽረውና የማያሻሽለው በግድ መሆን ያለበት

ኩነት ነው። ስለዚህ ሰው ገደሉን ሳያይ፤ ሳሩን ብቻ እያየ ከደል የሚገባ እንስሳ

ሆኖ፤ ወይም የሚውጠውን በመፈለግ ተቅበዝባዥ ዘንዶ ሆኖ የተፈጠረ

አይደለም። ቅዱስ ጳውሎስ “መብልዕ ለከርሥ። ወከርሥኒ ለመብልዕ።

ወእግዚአብኄር ይስዕሮሙ ለክሌሆሙ” (፩ ቆሮ ፮፡፲፫) ማለትም፦ “ምግብ

ለሆድ ነው። ሆድም ለምግብ ነው። እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ያጠፋቸዋል”::

ይህም ማለት፤ በሆዳምነት ሱስ ከሰባዊነት ባህርይ ወደ ደመ ቀዝቃዛው ዘንዶነት

52

መቀየር ነው። አርአያነታችን የዘንዶ ሳይሆን የመለኮት ነውና፤ እግዚአብሔር

ለራሱ አርአያ ቀናኢ በመሆኑ ይቆጣል። ይቀጣል።3 በዚህ ብኩን ዓለም ውስጥ

ኑሮን ለማሸነፍ መባክንና መቃተታችን ቅዱስ ጰውሎስ እንደተናገረው

የክርስቶስን ነገረ መስቀል (ሱባዔ) ያስረሳናል። (ገላት ፫፡፩)። ስለዚህ

ሊቃውንት አበው “ንትመየጥ፤ ንትባደር፤ ናፍጥን ለንስሐ”( ሃ አ ም ፴፯፡፪. ፲፩.

፲፬) ማለትም፦ ከሆዳምነት ወደ ሱባዔ እንመለስ፤ ለንስሀ አንዘግይ፤ እናፍጥን፤

በሱባዔ ለሚገኝ በረከትና ጸጋ እንወዳደር በማለት አጠንክረው ተናገሩ።

ክርስቶስ “ሸክማችሁ የከበደባችሁ ወደኔ ኑ” ብሎ ከራሱ በቀር ማንም

ሊከፍትልን የማይችለውን የሱባዔ በር ከፍቶልናል። ከዚህም በመነሳት

ሐዋርያት “መዳን በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች

የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለም”(የሐዋ ፬፡፲፪) እያሉ አስተምረዋል።

ሐዋርያትን የተከተሉ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት እነ ባስልዮስም “ዝንቱ ውእቱ

ንጉሠ መላእክት ወሊቃነ መላእክት ወይእኅዝ ኃይላተ ወያነጽህ ኩሎ ወይመልክ

ኩሎ ፍጥረተ”(ም ዕ ፴፫፡፵፮) “ የሊቃነ መለእክት ንጉሥ ሃይልን የሚቆጣጠር

ሁሉን የሚያነጻ ፍትረቱን የሚገዛ ክርስቶስ ነው። አድኖናል አጽድቶናል።

አጽድቆናል። ” እያሉ አስተማሩ። ቅዱስ ጎርጎርዮስም “ኢኮነነ ክርስቶስ እኅወ

በግብር ሐዲስ አላ ለቢሶ ሥጋ ዚአነ በተዋህዶ ዘኢይትነገር” ማለትም፦

በማይመረመር መለኮታዊ ጥበቡ ያዳነን ከሰባዊነታችን በራቀ በሩቅና ረቂቅ

መንገድ ሳይሆን የሚዳሰሰውን ሰባዊነታችን ከመለኮቱ ጋራ በማዋሀድ ነው”

እያለ ተናገረ። (ሃ አ ፴፰፡፭)። ይዚህ ሁሉ ትምህርት መነሻ የተከናወነው

በሱባዔ ቀመር ነው። (ገላ ፬፡፬)። ምንም እንኳ ክርስቲያኖች፤ በጥምቀት

ከክርስቶስ ጋራ ሞተን እንደተቀብረን፤ ከአሮጌው ሰውነትም በመላቀቀ አዲስ

ሰውነት እንደለበስን ብናምንም፤ በዚህ ዓለም ስንኖር በተቀደሰው ጋብቻ

የተመሰረተው ትዳር የሚያስከትለውን ሀላፊነት ለመወጣት በምናደርገው

መባከንና መቃተት፤ ቅዱስ ጰውሎስ ለገላትያ ሰዎች እንደተናገረው በሱባዔ

የተከናወነልንን የክርስቶስን ነገረ መስቀል ያስረሳናል። ይሸፍንብናል። (ገላት ፫፡

፩)። አውቀንም ሆነ ሳናውቅ ሰው ልንጎዳ እንችላለን። እንሳሳታለን። አንሳሳትም

ማለት ደግሞ በዚህ ዓለም አንኖርም ማለት ነው። ሐዋርያው ዮሐንስ “ኃጢአት

የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን። እውነትም በኛ የለም” እንዳለውም፤

የበለጠ መሳሳት ነው። ሱባኤ ኑዛዜ ነውና፤ ሱባዔ ገብተን “በኃጢአት ብንናዘዝ

ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመጻም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ” አምላክ

ከተሳሳትንበት እንድንመለስ የሚረዳን በሱባኤ ነው። “ኃጢአት አላደረግንም

ብንል፤ ሐሰተኛ እናደርገዋለን። ቃሉም በኛ ውስጥ የለም (፩ኛ ዮሐ ፩፡፰᎗፲)”

53

ስለዚህ ሱባኤ አያስፈልገንም ማለት ስህተት ነው። ይህን የተገነዘበ ዮሐንስ

አፈወርቅም “ሶበ ንኤብስ ለእግዚ ኩሎ ዕለተ ንትነሣእ እንከ እንዘ ለንስሀ እንዘ

ሕያዋን ንሕነ በውስተዝ ዓለም(ሃ ፷፭፡፲፮) ብሏል። ማለትም፦ በእለታዊ

ተግባራችን ስንባክን አውቀንም ሳናውቅም በምድር ሰውን፤ በሰማይ አምላክን

እንበድላለን እናሳዝናለን። ስለዚህ በህወት እስካለን ድረስ የንስሀ (የሱባዔ) ጊዜ

ሊኖረን ይገባል። ክርስቶስ ከፍሎልኛል በማለት ሱባዔ አያስፈልገኝም ማለት፤

ከወደቅንበት ተነስተን እንድንገባ ክርስቶስ በምሥጢረ ተዋህዶ የከፈተልንን በር

መካድ ነው። በየእለቱ ለምንፈጽማቸው በደሎች ክርስቶስን ተባባሪና ተካፋይ

ማድረግና ወደ ዘንዶነት ተንሸራት መግባትን ያስከትላል። በእምነት ውስጥ ሳለን

ለሚገጥመን ውድቀት ቅዱስ ጎርጎርዮስ “ወአንስአነ በጽድቀ ትንሣኤሁ እምነ

ሙታን ወአርኀወ ለነ ኆኃተ ንስሐ” (ሃይ ፴፮፡፴፰) እንዳለው የምንወስደው

ድርሻ አለነ። ማለትም፦ በትንሳዔው ቅድስና ከተቀደስን በኋላ ብንወድቅ

እራሳችንን እንድንመረምር የንስሀ በር ከፈተልን። ይህም የተከፈተልን በር፤ ሳር

ከሚበሉ እንስሳትና ከዘንዶ የምንለይበትን የሰባዊነታችንን ሚዛን ለመፈተሽ

የምንገባው ሱባኤ ነው። ራሳችንን ከምንፈትሽባቸው ሱባዔዎቻችን አንዷ

የፍልሰታ ሱባዔ ናት።

ፍልሰታ

ስለ ፍልሰታ ሱባዔ ሳስብ ሊቃውንት አባቶች የሚናገሯቸው ብዙ ትዝታዎች

ይመጡብኛል። በመግቢያ ላይ “ሱባዔ፦ በሰው፤ በቦታና በሰአት ስለሚከናወን

የሶስቱም ማለትም የሰአት፤ የሰባዊነትና የመካን ድምር ነው” እንዳልኩት

ፍልሰታ በኛና በፈጣሪ፤ እንዲሁም በኛና በቀሩት ፍጥረታት መካከል ያለውን

ልዩነት የምናስብበትና የምናሰላስልበት ወቅት ነው። በዚህ ወቅትም የጋስጫው

አባ ጊዮርጊስ ፈጣሪንና ተፈጥሮን ያደነቁበትን ድርሰት ለምናስበውና

ለምናሰላስለው መመሪያያችን አርገን እንጠቀምበታለን። ድርሰቱም የሱባዔን

ሁለንተና የምንዳስስበትን ሰአት ጊዜና ወቅት ስላካተተ ሰአታት ይባላል።

ፍልሰታን አስመልክቶ የተጻፈውን ማንበብ ከፈለጉ ለማንበብ ቀጥሎ ያለውን

ሰንሰለት ይጫኑ:: ፍልሰታ] በፍልሰታ ሱባዔ በአንገታችን ነጠላ እየቋጠሩ ወደ

ቤተ ክርስቲያን ከላኩን እናቶች ጋራ የምናስታውሳቸው ብዙ ቅዱሳን አባቶች

አሉን። አባቶች ስልም፤ ቆሞስ አባ እያሉ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ

የእባብ መንጋ የሚለቁባትን አባ ፋኑዔልን የመሳሰሉትን ማለቴ አይደለም።

በንጽህና በቅድስናና በመልካም ምሳሌ ሆነው፤ ሳር ከሚያመሳኩት እንስሳት፤

እርስ በርስ ለመባላት ከሚያሳምጥ ሆዳምነት (ዘንዶነት) እርቀው፤ ለቅድስና

54

ለዘላቂ ነገር ለህዝብ ለሃይማኖት ባደረጉት ተጋድሎ ትዝታና ቅርስ አውርሰውን

ያለፉትን እንደነ አባ ጊዮርጊስ የመሳሰሉትን ማለቴ ነው (፩ኛ ቆሮ ፬፡ ፲፭)

ክርስቶስ “ሰው በዳቦ ብቻ አይኖርም” ብሎ የሰውን ኑሮ ከሳረ በላዎች

እንስሳትና ከዘንዶ ለይቶ የተናገረውን የተረዱ አባቶች ማለቴ ነው። ቅዱስ

ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች “የሚሻለውን ነገር እፈተነ “ከጌታችን ከኢየሱስ

ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ

ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ በእውቀትና

በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ እጸልያለሁ “( ፊል ፩፡፲፩)።

እንዳለው፦ በፍልሰታ ሱባዔ፤ ከታች አምናው ሱባዔ፤ ባምናው ሱባኤ፤ካምናው

ሱባኤ ደግሞ በዘንድሮው ሱባዔ ምን እንዳሻሻሉ ራሳቸውን የታዘቡበት ነው።

በዘንድሮው ሱባዔ ደግሞ የከርሞውን አሻግረው በመመልከት የተሻለውን

እየመረመሩና እየፈተኑ ለመኖር መፈጠራቸውን እንዳይዘነጉ ፍልሰታን

ተጠቅመዋል። አሁንም በአታቸውን ያለቀቁ የፍልሰታን ሱባዔ በመጠቀም ላይ

ጥቂት4 ሊኖር ይችላሉ። አባቶቻችን፦ “ወፈድፋደሰ ንብል . . . . . እንዘ ንሕነ

ውስተ ዛቲ አሐቲ ልሕኲት ሰመዮ ሥጋ ዚአነ አብያተ ዘጽቡር እስመ ነፍሳቲነ

ሕዱራት ውስቴታ”(ሃ አ ም ፹፩፡፲፩” ማለትም፦ የሰውነት መለኪያችን

ከእንስሳት የምንለይበት ከፈጣሪ ጋራ የምንመስልበት በሥጋችን ያለቸው ረቂቅ

የማሰብ ኃይላችን ናት። እንዳትቆሽሽ እንዳትረክስ እንዳትጎድፍ የምንጠነቀቅላት

በፈራሹ ሥጋችን ያለችው መንፈሳችን ናት።” እያሉ ፍልሰታን

ተጠቅመውባታል። ፈለጋቸውን በመከተል እኛም ያለንበትን ዘመንና

የሚካሄደውን እንድናጤንባት ቅብብሎሹ ያስገድደናል።

ፍልሰታ ፦ እርስ በርስ በመሳመጥ ላይ ካለው ተመናዊ (ዘንዶነት) ራሳችንን

አግልለን“ኦ እግዚኦ አምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘአንሳእከነ እምድር

ወአልአልከነ እመሬት ከመ ታንበረነ ምስለ መላእክቲከ ወመስለ መላእክተ

ሕዝብከ” (ሥ ቅ ገ ፳፪፡፳፭) ማለትም፦ ከአፈር ፈጥረህ ሰው አድርገህ

አቆምከን። ብንወድቅም ከወደቅንበት አንስተህ ከመላእክትና በቅድስና ከማእረገ

መለእክት ከደረሱት ቅዱሳን ጋራ ታከብረናለህ።” እያልን በሩጫና በመቃተት

የምንፈጽመውን በጥሞና በማስተዋልና በተረጋጋ መንፈስ የምንመረምርባት

ናት። ትኩረታችን እንጉርጉሯች የተመሰረቱት፤ የአባ ጊዮርጊስ ስሜት እና

ትኩረት የተመሰረቱባቸው ሰአታት በተባለው መጽሀፍ ነው። በዚህ መጽሀፍ

እየተመራን፤ “እመኒ ወደቁ እትነሳእ ነሲእየ ሰለስተ አስማተ እትመረጎዝ።

ወእመኒ ሆርኩ ውስተ ጽልመት እግዚአብሔር ያበርህ ሊተ” ብወድቅም የስላሴን

ረድኤት ተመርኩዤ እነሳለሁ። ጉዞዩ በጨለማ ውስጥ ከሆነብኝም

55

እግዚአብሔር ያበራልኛል” እያልን ሰአታትን፤ ዕለታትን፤ ወራትንና ዘመናትን

በማሰላሰል፤ የሚውጠውን ብቻ ከሚያስብ ዘንዶ ልዩ የሆነውን ሰባዊነታችንን

እናደንቃለን። “ዘገብሮ ለአዳም በዘዚአሁ አርአያ ወአምሳል” እያልን በኛና

በፈጠሪያችን መካከል ያለውን ረቂቅ አርአያነት እንመረምራለን። “በተነ ጊሜ

ረቂቅ ዘየአቁሮ ለማይ ወያወርዶ እምኑኀ ሰማይ” ማለትም፦ በረቂቅ ተን ውሀን

ታሸክማለህ፤ ወደ ኑኀ ሰማይ ታወጠዋለህ። እንደገና ወደ ምድር ታወርደዋለህ”

እያልን መግቦቱን ከሀሊነቱን እናደንቃለን። የተነ ጊሜ ዑደት በመሬት ያለውን

ጠባየ ፍጥረት መለዋወጡን በልዩ ዜማ እናንጎራጉራለን። በዚሁ መጽሐፍ

እየተቃኘን በኛና በፈጠሪያችን መካከል ያለውን ረቂቅ አርአያነት ማሰባችንን

በመንፈቀ ሌሊት እንጀምና፤ “ገባሬ መላእክት አበ ኩሉ ሠርጎ ዓለም ሣራሪሃ

ለምድር ጥበብ ወአዕምሮ እምአብ ዘሀሎ እምቅድም ውስተ ዓለም ተፈነወ ዝ

ህሉና ዘኢይትነሰት ወዘ ኢይተረጎም መንፈስ ዘኢያስተርኢ” ። ይህም ማለት፦

የጥበብና የአዕምሮ ባለቤት፤ የሁሉ አባት፡ ዓለምን የፈጠርክ፡ ቅድመ ዓለም

የነበርክ፤ በማይመረመርና መግለጽ በማይቻል መንገድ ሰባዊነትን ለማዳን ከአብ

ዘንድ የተላክ” በሚለው በነግሁ ኪዳን የየእለቱን ሱባዔ እንደመድማለን። ይህች

ዓለም ያልነበረችበት ጊዜ ነበር። አሁን አለች። ክርስቶስ የተናገረው የህልውናዋ

ሱባዔ የሚቆምበት ሰአት እስኪደርስ ድረስ ወደፊት ትኖራለች። አሁን እኔ

አለሁባት። እሷም አለችብኝ፤ እኔ በሷ የማልኖርበት፤ እሷ በኔ የማትኖርበት ጊዜ

ደግሞ በቅርቡ ይመጣል። እስኪዚያ ድረስ ምን እያደረኩ እቆያለሁ? ትላንት

በላሁ ተኛሁ ተነሳሁ። ዛሬ እየበላሁ እየተኛሁ እየተነሳሁ ነኝ። ነገ እበላለሁ

እተኛለሁ እነሳለሁ። እየበላሁ እየጠጣሁ እየተኛሁ እየተነሳሁ የማልኖርባት

ያችን ጊዜ እጠብቃለሁ? ታዲያ ፈጣሪ ወደዚህ ዓለም ያመጣኝ እየበላሁ

እየተኛሁ እየተነሳሁ ብቻ ትንሿን ህይወቴን ላሳልፍባት ነው? ይህ ከሆነ

የማስብበትንና ሀሳቤን የምገልጽበት በሀለፊ በኩነትና በመጽያት ላይ

የተመሰረተውን ቋንቋየን ገና አልተገነዘብኩትም ማለት ነው። ይህም ከሰባዊ

ሱባኤ ተንሸራቶ ግራ ቀኝ ማየት ወደ ማይችለው ከዘንዶ ሱባዔ መግባት ነው።

ትልቁ ሱባኤ ምንኩስናና ገዳም ነው!

ከላይ እንዳልኩት ሰው የሆነ ሁሉ “ወባህቱ ፈቃዱ ለእግዚአብሔር አምላከ ጸጋ

ንኩን ማእምራነ ቦቱ በልብ ዘሥጋ ወሶበ ነአምሮ ወነአምን ቦቱ ንከውን ደቂቀ

እግዚአብሔር ወውሉደ ጥበብ ወመካነ ለምግባረ ሠናያት ወመፍቅርያነ ኂሩት

ወጸላእያነ ለእከይ ወቀንያነ ለግብሩ ከመዝ”( ሃይ አ ም ፲፱፡፴፭)”

እንደተባለው፤ ማለትም፦ ማንም ክርስቲያን “በአርያውና በምሳሌው የፈጠረኝ

56

አምላክ ከኔ የሚጠብቀው በሱ ምሳሌነቴ አዋቂ አስተዋይና የጥሞና፤ የጥበብ፤

የምህረት፤ የይቅርታና የፍቅር ምንጭ፤ እንድሆን ነው። በተቃራኒው ዘንዶነትን

ክፋትንና ቂምን የምዋጋ እንድሆን ነው።” ብሎ እያሰበ እያሰላሰለ ተጠንቅቆ

መኖር አለበት። ምንኩስና ግን “ይህችማ ምንላት” ብሎ ክርስቲያን

እንዲያደርገው የታዘዘው ሁሉ አነሰኝ ከዚያ የራቀ፤ የረቀቀና እጅግ የላቀ ስራ

መስራት አለብኝ ብሎ፤ ምሎ፤ ተገዝቶ፤ ሞቶና ተገንዞ የሚገባበት ሱባዔ ነው።

በትዳር ተይዘው ሀላፊነታቸውን ለመወጣት በመባከን ላይ ካሉት ክርስቲያኖች

በአጽንኦ በአት እጅግ የተሻለ ቅዱስ በመሆን ለምሳሌነት መላ ዘመኑን የሚገባው

ሱባዔ ነው። “ወዝንቱ ውእቱ ሕይወቶሙ ለደቂቀ ቤተ ክርስቲያን እንተ

ሐዋርያት ወፈድፋደሰ ለእለ የሀድሩ ውስቴታ ተጋዳልያን መነኮሳት

ወይደልዎሙ ይንግርዎሙ ለደቂቆሙ ይኩኑ ከመዝ። ወለእመሰ ኢይንግርዎሙ

ለደቂቆሙ ይኩኑ ከመዝ፤ ኢይበሉ ንህነ ክርስቲያን ወንድህን”( ፴፬) ማለትም፦

“የሚመነኩሱት ለእውነት እንሞታለን። በዚህች ዓለም ምኞት አንሸነፍም ብለው

ብቻ አይደለም። ምሳሌነታቸውን ለሚመለከቷቸው እንዲያተምሩ ነው። ይህን

ባያስተምሩ በትሩፋት ተጋድሎ የሚገኘውን ን የቅድስና ዋጋ ሊያገኙ ይቅርና፤

ያልመነኮሰው ህዝብ የሚያገኝውን ጸጋና በረከት ያጡ ናቸው” ተብሏል።5

በመግቢዋ ላያ ከቦታው ስንደርስ እንመለከተዋለን ያልኩትን እዚህ ላይ

ላምጣውና፤ ሰለ ሱባኤ ስንነጋገር፤ በትዳር ተወጥሮ በመቃተት ላይ ካለው ህዝበ

ክርስቲያን እጅግ የወረዱ መነኮሳት ቆሞሳትና ሊቃነ ጳጳሳት እንደተፈለፈሉ

ተመልከተናል። ወደ ዕብራውያን በተላከው መልከት “አንድ ጊዜ ብርሃን

በርቶላቸው ሰማያዊውን ስጦታ ተረድተው ከመንፈስ ቅዱስ ተካፋዮች

የሆኑትን፤ መልካሙን የእግዚ ቃልና የሚመጣውን ዓለም ተረድተው ከተረዱ

በኋላ የካዱትን፤ እንደገና ወደ ንስሀ መመለስ አይቻልም። ምክንያቱም

በክፋታቸው የእግዚ ልጅ እንደገና ሰቅለውታል”(ዕብ ፮፡፮)። ተብሎ የተነገረውን

በተግባር በማዋል ላይ ያሉ ጵጵስናውን ምንኩስናውንና ቅስናውን ያፈራረሱ

ብዙ ናቸው። እነሱም ዶ ክተር አረጋዊ በርኄ፤ “የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ

ግንባር በ1979 አመተ ምህረት አስተሳሰብ ለዋጭ የፕሮፓጋንዳ መርሀ ግብር

ለሚመለምላቸው ቀሳውስት ዘረጋ። የማሰልጠኑ ዓላማ ቤተ ክርስቲያኗን

ከህዝብ ለይቶ በመምታት ስፋቷን ማጥበብና በትግሬአዊነት ላይ ብቻ

የተመሰረተ ስሜት በትግራይ ተወላጆች ጭንቅላት መክተት ነው። ቤተ

ክርስቲያኗ ለረዥም ዘመናት በህዝቡ አዕምሮ ላይ ስትተቀርጸው የኖረችውን

ብሄራዊ የኢትዮጵያነትን ስሜት ከትግራይ ህዝብ አዕምሮ ጠራርጎ በጠባቡ

ትግሬአዊነት ስሜት በመተካት የቤተ ክርስቲያኒቱን ይዘት እያጠበቡ ራሷን ቤተ

ክርስቲያኒቱን መምታት ነው።” ብለው በገለጹት የጥፋት ኮርስ እየተመለመሉ

57

የገቡ ናቸው። በስፋት ለመረዳት ከፈለጉ "የነ ፋሌቅ ወጥመድ" በሚል ርእስ

የተጻውን ጦማር ያንብቡ። ] ዶ ክተር አረጋዊ እንደነገሩንና በተግባርም

እንዳየነው፤ ከፓትርያርክነት ጀምሮ እስከ ቁምስና ድረስ እነ አቶ ስብሐት ነጋ

ገብረ ኪዳን ደስታና አቶ መለሰ በዘረጉት “ባአስተሳሰብ ለዋጭ የፕሮፓጋንዳ

መርሀ ግብር” በተዋቀረው አመራር ሰልጥነው የተሰማሩ ካድሬዎች ናቸው።

ይህም አመራር የመነኮሳቱን የቆሞሳቱንና የሊቃነ ጳጳሳቱን ባህርይ የቀየረ ነው።

ጵጵስናው ምንኩስናው ቅስናው የሰውነቱን ሙቀት “በ50 degrees

Fahrenheit እንደሚያበርደው ዘንዶ፤ በኮርሱ የተሰማሩት እንደ አባ ፋኑዔል

ያሉ ጳጳሳት ቆሞሳት መነኮሳት የቤተ ክርስቲያናችንን መንፈሳዊ ልዕልና

አውርደው ጥለውታል። የበላውን ለማጣጣም፤ የሰበሰበውን ገንዘብና ንብረት

ለመቁጥር፤ ለመዝናናት የሚያደርገውን መገለል (ድበታ) ሱባዔ ገባሁ ይላል።

በመዝናናት በሽርሽር በህክምና አሮጌውን ገላውን ሸልቅቆ ካስወገደ በኋላ፤

ቀደም ብሎ የተጠቀመበትን ማስመሰያና ማታልያ መንገድ ይቀይርና ባዲስ

ኃይልና ጉልበት የሚውጠውን ፍለጋ በካካባቢው አየር ንብረት እየተገፋ

ያገኘውን ለመዋጥ በመቅበዝበዝ እየተንቀሳቀሰ ነው። ለዘረፋው ይመቸው ዘንድ

ያልገባቸውን ሴቶች ዕልል የሚያሰኙ ቀራፊዎችን ያሰልፋል። [ስለ ቀርፊዎች

የበለጠ ለማወቅ የሚቀጥለውን ሰንሰለት በመጫን ይመልከቱ። ቀራፊ ]። እልል

በሉ እያለ ግርግርና ጫጫታ ይፈጥራል። የመቅነዝነዝ ኃይሉን ካካባቢው አየር

ንብረት ጋራ እያስማማ እንደ ሚንቀሳቀሰው ዘንዶ የዘመኑ ጵጵስናም

ካካባቢውና ከወቅታዊው ከወያኔ መርሆ ጋራ እያስማማ የሚውጠውን

ይፈልጋል። ያሳደገውንና ያለመደውን ቢጤውንም እንደሚውጥ ዘንዶ ፤ የዘመኑ

ጵጵስናና ምንኩስና እርስ በርሱ ይዋዋጣል። ህዝቡ ወዶና ተታሎ የሚሰጠው

ገንዘብ አላረካው አላጠግበው ሲል፤ ያሳደገውንና ያለመደውን ህዝበ ክርስቲያን

የሚሊዮን ዶላር ካሣ ከፈለኝ ብሎ ባደባባይ ይከሳል። የኢትዮጵያ ሊቃውንት

አባቶች “ዘመን ሲከፋ ሰው እርሱ በርሱ የሚባላ ዘንዶ ይሆናል”ብለው ሲናገሩ

የሰማሁትን፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ሊቃውንት እባብ ተመሳስይ መጠን ያለውን

ሌላውን እባብ ሲውጠው በገሀድ አቀረቡት። ስመለከተው ያሁኑ ሁኔታችንን

አብራርቶ ስላቀረበው እጅግ ዘገነነኝ። ጵጵስና እንደ አባ ፋኑኤል አዲስ ተክል

ምንኩስናና ቁምስና ደግሞ እንደ አቶ ሲሳይ ታደሰ ከሆነ፣ የኢትዮጵያ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን አለቃ ገብረ ሐና እና የዲሲው

መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መስራች መላከ ገነት ውቡ ወደ ተናገሩት

ማዘንበል የሚኖርባቸው ይመስለኛል። ያለቃ ገብረ ሐናን ላስቀድም። ወይዘሮ

ማዘንጊያ የሚባሉት ባለቤታቸው ለራት ሽሮ ሲሰሩ በማማሳያው እንጨት

ቅምሻውን አበዙት። አለቃ ታዘቡና “ማዘንጊያ ራታችን እሱ ከሆነ እኔም

58

መቋሚያ ይዥ ልቅረብ” አሉ። መላከ ገነት ውቡም ተመሳሳይ ነገር ተናግረዋል።

በዲሲ መድኃኔዓልም መስራቾች በነ ኮረኔል አስፋው አንዳርጌ እና በአቡነ

ማትያስ መካከል የጋለ ጸብ ተነሳ። አቡነ ማትያስ መላከ ገነት ውቡን ከነ ኮረኔል

አስፋው ጋራ ደርበው ተገቢ ያልሆነ ቃል ተናገሯቸው። መላከ ገነት ውቡ

“ጵጵስና እንደ አባ ማትያስ ከሆነ፤ እኛም ወደ ዳውን ታውን እየሄድን ቆቡን

እያሰራን፤ ልብሱን እያሰፋን ለብሰን ብቅ እንበል” አሉ። ጵጵስና እንደ አባ

ፋኑዔል፤ ቁምስናና ምንኩስና ደግሞ በዚህ አመት ፍልሰታ አባ ፋኑዔል ለታደሰ

እንደሰጡት ከሆነ፤ በሞራል በዝሙት በስርቆት በሀሰት የተከሰሰ ወንጀለኛ ሁሉ

ቆቡን እያሰፋ ጥቁሩን ልብስ እየለበሰ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ሊኖርበት ነው

ማለት ነው።

የኢትዩጵያ ሙስሊሞች አቭዬት ከየት ወደ የት ነዉ? ከአዲስ አበባና ከወልቂጤ በግፍ በደህንነቶች ታፍነው በኤሊያስ ከድር መዝገብ

ተከሰው በአሁኑ ሳአት በቂሊንጦ ማረሜያ ቤት የሚገኙት ወንድሞቻችና

እህታችን መሬማ ሀያቱ ከቃሊቲ ማረሜያ ቤት የቀረቡ ሲሆን ዛሬ ፍርድ ቤቱ

የተከሳሽ ጠበቆች ያቀረቡትን የክስ መቃወሜያ ውድቅ በማድረግ በእለቱ ችሎት

ተከሳሾቹ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ዳኛው በሰጡት ትእዛዝ

መሰረት አንደኛ ተከሳሽ ኢሌያስ ከድርን ጨምሮ ሁሉም ተከሳሾች አቃቢ ህግ

ያቀረበባቸውን ያሰት ክስ እንደማይቀበሉና ድርጊቱንም አለመፈፀማቸውን

ለፍርድ ቤቱ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።ጥፋተኞች አይደለንም

ማለታቸውን ተከትሎ አቃቢ ያቀረበውን የሀሰት ክስ ለማጠናከር የሀስት

ምስክሮችን ለማሰማት ጥርስ አልባው የፌደራሉ ካንጋሮ እንዲያሰማ ትእዛዝ

ሰጥትዋል። በታሰሩበት ቃሊቲ ማረሜያ ቤት በከፍተኛ በደል እየተንገላቱ

የሚገኙት እህቶቻችን ለፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን በተደጋጋሚ ማቅረባቸው

ይታወሳል በዛሬ እለትም በወንድም ኤሊያስ ከድር መዝገብ የተከሰሰቹ

የወልቂጤዋ ሱመያ እህታችን መሬማ ሀያቱ ለፍርድ ቤቱ በድጋሚ. ከሌሎ

እስረኞች ተለይታ የምትጠየቀው በቀን ለ10 ደቂቃ ብቻ እንደምትጠየቅና

የጠያቂ ገደብ እንደተጣለባት ገልፃ ከካንጋሮ ፍርድ ቤቱ በስልጣን ለሚበልጠው

ማረሜያ ቤት ካንጋሮ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እንዲሰጥላት አቤቱታዋን አቅርባለች

ፍርድ ቤቱም ምንም እንኳን ተሰሚነት እንደማይኖረው ቢያውቅም የማረሜያ

ቤቱ አስተዳደር ቀርቦ ስለ ጉዳዩ እንዲያስረዳ ትእዛዝ ሰጥቶዋል።ችሎቱም

59

የአቃቢ ህግን የሀሰት ክስ ያደምጣል ተብሎ ይጠበቃል.

ህዝበ ሙስሊሙ መፍቴ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በዛሬ እለትም በካንካሮው ፍርድ

ቤት የመከላኬያ ምስክራቸውን አስደምጠው የዋሉ ሲሆን ችሎት 4 የሰላም

አንባሳደሮቹን የመከላኬያ ምስክር አድምጦ ውሎዋል። ይመሰክር የነበረው

ጀግናው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በማረሜያ ቤቱ እንቢተኝነት ቀርቦ

መመስከር ሳይችል ቀርቶዋል።ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ ሌሎች አራት የመከላኬያ

ምስክሮችን አድምጦ የዋለ ሲሆን አራቱም ምስክሮ በተላያዩ ጭብጦች ላይ

አስደናቂ የመከላኬያ ምስክርነታቸው መስጠት ችለዋል።በእለቱ ችሎት ቀዳሚ

ምስክር የነበረው ወንድም መሀመድ ሀይሩ ሲሆን በጭብጥ ምሽቱን. የአወሊያ

ሰደቃና አንድነት ፕሮግራም በመንግስት ታጣቂ ሀይሎች መደናቀፋን ተከትሎ

በተደረገው የአዛን ጥሪ ምላሽ ለመስጠት የወሰዱትን እረምጃ በማስታወስ

በእለቱ ወንድሙ ተይዞ መታሰሩን ገልፆዋል።ከዚህ ክስተት ቦሀላ የአቃቢ ህግ

ምስክር የነበረው ሰኢድ ኢብራሂም የተባለው ግለ ሰብ ኡስታዝ አቡበከር

አህመድ ባዩሽ መስጂ እንደነበረ በሀሰት ሲመሰክር መኖሩን የነገረኝ መሀመድ

ሀይሩ ነው በማለት የሀሰት ምስክርነቱን ሰጥቶዋል ይሁን እንጂ እኔ

እስከነጭራሹም አዲስ አበባ አነበርኩም የነበርኩት አዳማ ነው ሲቀጥል ደሞ

ኡስታዝ አቡበክር አህመድን በስም እንጂ አላውቀውም በማለት የአቃቢ ህግን

ሀሰተኝነትና የመሪዎቻችንን ንፁሀንነት ተገቢ በሆነ ሁኔታ ለፍርድ ቤቱ

አስረድቶዋል

የችሎቱ ሁለተኛ ምስክር የነበረው አቶ ነጅሙዲን መሀመድ ሲሆን በጭብጥ

9ኝ ላይ አቃቢ ህግ የአክራሪነት ትምህርት ከሀገር ውጪ ተምረው መጥተው

አስተሳሰቡን እዚህ በማስተማር ከአረቡ አለም ንቅናቄ በማዋሀድ በኢትዬዺያ

ውስጥ ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት አስበዋል በማለት በኡስታዝ አህመድ

ሙስጠፋና በህግ ሙህሩ ካሚል ሸምሱ ላይ ያቀረበውን የሀሰት ክስ ሀሰት

መሆኑንና እነሱ ያስተማሩት በጊዜው እርስ በእርስ ሲማማሩት የነበረው ሌሎች

ጉዳዬችን በውይይት መልክ በማንሳት እንደነበረ ለፍርድ ቤቱ በግልፅ

አስረድቶዋል።

በግዜው ሁለት ርእስ ጉዳዬችን አንስተው መወያየታቸውንና የወይይቶቹም ርእስ

ከመባነን መንቃት በኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ እንዲሁም ህዳሴ የሚል ደሞ

በህግ ሙሁሩ ካሚል ሸምሱ መሪነትና አወያይነት ወይይት ማድረጋቸውን

60

ለፍርድ ቤቱ ገልፆዋል።ይህም ደሞ ሎርማን ስልጠና ሳይሆ ዩንቨርስቲ

እንተዋወቅ ስለነበረ የእርስ በእርስ መማማሬያ መድረክ እንደነበርም ጨምሮ

ገልፆዋል። በዚህ መማማሬያ ፕሮግራም ላይ እስከነጭራሹ ኢስላማዊ መንግስት

ምስረታን በተመለከተ አንድም ሀሳብ አለመነሳቱንም ጭምር አብራርቶ

አስረድቶዋል

የችሎቱ 3 ምስክር የነበረው ሙህዲን አረቦ በጭብጥ 11 ላይ ሲሆን በአወሊያ

መስጂድ የህዝበ ሙስሊሙ መፍቴ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ያደረጉትን ንግግርና

በተለይም እሱ በዋንኛነት ይመስክርለት የነበረው የታሪክ ሙሁሩ ኡስታዝ

አህመዲን ጀበል እሱ በተገኘበት አንድ ፕሮግራም በማስታውስ ያደረገውን

ሰላማዊ የሆነ ንግግር ለፍርድ ቤቱ ገልፆዋል።በወቅቱ ህዝበ ሙስሊሙ

አንስቶዋቸው ከነበሩት 3 ት ህጋዊና ህገ መንግስታዊ የሀይማኖት ነፃነት

ጥያቄዎች አንድ ምርጫ እንደበረ በመግለፅ ኡስታዝ አህመዲን ጀበልም በጊዜው

የበፊቱን የምርጫ ሂደቶች በማስታወስ አሁን ስለሚኖረው ምርጫና ምርጫውን

ሙስሊሙ መሀበረስብ እንዴት ማከናወን እንዳለበት ንግግር ማደረጉን

አስድቶዋል።በተጨማሪም አሁን የህዝበ ሙስሊሙ መፍቴ አፈላላጊ ተደርጎ

የተመረጠው አካል ምርጫው ላይ በምንም አይነት መልኩ አይሳተፍም ብሎ

መነገሩንም ጭምር ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል ።ጥቅሎ በእለቱ በነበረው

ፕሮግራም ኡስታዝ አህመዲን ጀበልም ሆነ ሌሎች የሰላም አንባሳደሮች ምንም

አይነት ህግን የተፃረረ ህዝብን ለሽብር የሚያነሳሳ ንግግር አለማድረጋቸውን

በዝዝር አስረስቶዋል።

የእለቱ ችሎት የመጫረሻውና 4 ኛው ምስክር የነበረው አቶ ሀምዱ እንድሪስ

በጭብጥ 10 ላይ የመሰከረ ሲሆን በሀምሌ 1 ፒያሳ በሚገኘው በበኒ መስጂስ

ተደርጎ የነበረውን ሰደቃና አንድነት ፕሮግራምና በሰደቃና አንድነት ፕሮግራሙ

ላይ የታሪክ ሙሁሩ ጀግና ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ያደረጋቸውን ንግግሮች

በማብራራት አስደናቂ የመከላኬያ ምስክርነቱን ሰጥተዋል።በእለቱ ፕሮግራሙን

ከረፈደ የተገኘው ምስክር ልክ እሱ በመጣበት ሳአት ንግግር ያደርግ የነበረው

አህመዲን ጀበል ምርጫን በተመለከተና ህዝበ ሙስሊሙ ምርጫውን ማድረግ

ያለበት ህገ መንግስቱ በፈቀደለት ሁኔታና በተቋሙ ውስጥ እንደ ሆነ

በተጨማሪም አካሄዱ ፍፁም ሰላማዊና ህገ መንግስታዊ መሆን እንዳለበት

ፕሮግራሙን ለመታደም ተገኝቶ ለነበረው ሙስሊሙም ሆነ የሌላ እምነት

ተከታዬች ንግግር ማድረጉን አስረድቶዋል።በእለቱ አህመዲን ጀበል አድርጎት

በነበረው ንግግር ምንም አይነት ህግን የሚፃረር እንዳነበረ በመግለፅ አስገራሚ

61

የመካኬያ ምስክርነቱን ሰጥቶዋል። በአጠቃላይ በእለቱ የመሰከሩት የሰላም

አንባሳደሮቹ ምስክሮች በየመሰከሩባቸው ጭብጦች አስደናቂ የመከላኬያ

ምስክርበታቸውን የሰጡ ሲሆን ከህግ ባለሞያዎች ለተነሱላቸው ዋናና መስቀለኛ

ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ሰጥተዋል።

ችሎቱ በዚሁ የተጠናቀቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱ 3ቴ የሰጠው ትእዛዝ አለመከበሩ

ለምን እንደሆነ እንዳልገባውና በቀጣይ ዛሬ የሰጠው ትእዛዝ እማይከበርለት

ከሆነ የራሱን እርምጃ እንደሚወሰድ ጥርስ የሌለው የካንጋሮው ፍርድ ቤት ዳኛ

ለችሎቱ ገልፀዋል።በቀጣይነት ትእዛዝ የሰጡ ሲሆን ጀግናው ጋዜጠኛ ተመስገን

ደሳለኝ ህዳር 17 መጥቶ እንዲመስክርና ችሎት ቀሪ የመከላኬያ ምስክሮችን

ህዳር 10 ማለት እሮብ እንደሚሰማ አስታውቀዋል።ህዝበ ሙስሊሙም

ለወኪሎቹ አጋርነቱን ለመግለፅ በብዝት ተገኝቶዋል የህዝብ ወኪሎቹን ችሎት

የሌላ እምነት ተከታዬችም እየታደሙት ይገኛሉ።ቀጣይ በሚኖረውም ችሎት

ህዝበ ሙስሊሙ በመገኘት አጋርነቱን ያሳያል ተብሎ ይጠበቃል።እንዲያሳይም

ጥሪ ተላልፎዋል።የችሎቱን ሙሉ ዘገባ በምሽት ፕሮግራማችን የምናቀርብ

መሆኑን ከወዲሁ ለመግለፅእኖዳለንበአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ፍትህ ሲዘነበል

የህብረተሰቡ ዘርፈ ብዙ የግል እና የጋራ የህይወት መስኮች በአሉታዊ መልኩ

መቃወሳቸው የተለመደ ነው፡፡ በዚህም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጤናማ

ግንኙነት ሊያሻክር እና ሊያናጋ መቻሉ እሙን ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የፍትህ

መጓደልን ያስከተለው የመብት ጥሰት ግለሰብን ሳይሆን አንድን ቡድን በጥቅሉ

ዒላማ ያደረገ ሲሆን የዚያ ቡድን አባላትን እድሜ፣ ጾታ፣ እውቀት፣ የሃብት

ደረጃ እና የተሰማሩበትን ሙያ ሁሉ ሳይለይ ሁሉንም ተጎጂ ማድረጉ የተለመደ

ነው፡፡ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ መንግስት የከፈተው ገሃዳዊ የመብት ጥሰት

ወንጀል ሁሉንም ሙስሊም የነካ መሆኑም ከህዝብ እይታ የራቀ አይደለም፤

መንግስት በሐይማኖታችን ጣልቃ ሲገባ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በንቀት

የደፈረበት አጉል ጀብዱ ነበርና፡፡

መንግስት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ እና

በተከበሩ የሃይማኖት አባቶቻችን እልህ አስጨራሽ ትግል እውን የሆነውን

የህዝበ ሙስሊሙን ብቸኛ ተቋም መጅሊስ እንደፈለገ ያለፈቃድ ሲሾፍር

የተዳፈረው ሰፊውን ህዝበ ሙስሊም ነው፡፡ በማን አለብኝነት በተቆጣጠረው

ህዝባዊ ተቋም ስም የአህባሽን አንጃ በልዩ መንግስታዊ ግብዣ ከሊባኖስ

አስመጥቶ በህዝብ ላይ ለመጫን ዑለሞቻችንን እና ኢማሞቻችንን

በመንግስታዊው እስልምና ዓለማዊ በሆኑት የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሃይል

62

አፍኖ በግድ ሲያጠምቅ፣ የሰለጠኑ የሃይማኖት አባቶቻችንንምየታዘዙትን ሰበካ

እንዲፈጽሙ ሲያስገድድ፣ ካልሆነ እርምጃ እንደሚወስድሲያውጅ፣

መስጂዶቻችንንም ለዚሁ ዓላማ በሃይል ሲቆጣጠር የናቀው መላውን ህዝበ

ሙስሊም ነው፡፡ ለህዝብ ሰፊ ግልጋሎት ሰጪ የነበረውን የህዝበ ሙስሊሙን

ተቋም አወሊያንም ለዚሁ መሰሪ ዓላማው ሲወርስ እና ከብዙ ግልጋሎት ውጭ

ሲያደርግ ያከናወነው አሳፋሪ የጣልቃ ገብነት እብሪት ሰለባ የሆነው አሁንም

መላው ሙስሊም ምዕመን ነው፡፡

ለእነኚህ ሁሉ ችግሮች ፍትሃዊ ማስተካከያ በመሻት መፍትሄ እንዲያፈላልጉ

ህዝበ ሙስሊሙ የወከላቸውን እንቁ ኮሚቴዎች በግፍ መዳፉ ስር ሲያስገባ እና

ህገወጥ አፈና ሲፈጽም መንግስት ተገቢውን ክብር የነፈገው ለእነሱ ብቻ ሳይሆን

ለወከላቸው ሰፊው አማኝ ሙስሊም ህብረተሰብ ነው፡፡ አባቶቻችን እና

አያቶቻችን በደምእና በአጥንት ለዘመናት ታግለው ያቆሟቸውን መሳጂዶች፣

መድረሳዎች እና ትምህርት ቤቶች፣ ብሎም ሌሎች በርካታ ሐይማኖታዊ

ተቋማት ሲዘጋ፣ ሲያሽግ፣ በሃይል ድጋፍ ተረክቦ ለመጤው መንግስታዊ የአህባሽ

ደቀመዛሙርቶቹ ሲያወርስ የናቀው ማንንም ሳይሆን የሃገሪቱ ግማሽ አካል

የሆነውን ህዝባችንን ነው፡፡ በዚህም መስጂዶች ሰጋጅ አጥተው፣ ትምህርት

ቤቶች ደሞዝ መክፈል ተስኗቸው ሲዳከሙ የተጎዳው ህዝበ ሙስሊሙ እና

እንደ አይን ብሌኑ የሚሳሳላቸው የነገ ሐገር ተረካቢ ወጣቶች እና ታዳጊ ልጆቹ

ናቸው፡፡

መንግስት ምንም የማያውቁ ህጻናት ሙስሊሞችን ሳይቀር መብታቸውን

በቀጥታ ጥሷል፡፡ የሃይማኖት መብታቸው አንድ አካል የሆነውን እና ‹‹የመማር

ሰብዓዊ መብት›› ከሚገለጽባቸው መንገዶች አንዱ የሆነውን የሃይማኖት

እውቀት ፍለጋ በመከልከል መብታቸውን ነፍጓል፡፡ መድረሳዎቻቸው እና

የትምህርት ማዕከሎቻቸው ሲዳከሙ ከትምህርታቸው የተደናቀፉት እና

ወላጆቻቸው በፍትህ እጦት የሚሰቃዩ ልጆች ሁሉ የዚህ መብት ጥሰት ቀጥታ

ተጠቂዎች ናቸው፡፡

በዚህ የህዝብን መብት የመገርሰስ ተግባሩ መንግስት ያላነጣጠረበት፣ ያልነካካው

እና በሂደቱ ተጠቂ ያልሆነ የህዝበ ሙስሊሙ ክፍል የለም፡፡ ዑለሞች፣

ዳዒዎች፣ አርቲስቶች እና ጋዜጠኞች ለእስር እና ለስደትተዳርገዋል፡፡ በማጎሪያ

ቤቶችም በስደት ዓለምም ስቃይን እንዲጋፈጡ ተደርገዋል፡፡ ብዙ የዩኒቨርስቲ

ተማሪዎች ሙስሊም በመሆናቸውብቻ ከትምህርት ገበታቸው እንዲገለሉ

ተደርጓል፡፡ ለእስርም ተዳርገው ለዓመታት ፍትህን ተነፍገዋል፡፡ ሙስሊም ሴት

63

እህቶቻችን እና እናቶቻችን ከድብደባ፣ መፈንከት እና እስራት ጀምሮ ለአስጸያፊ

በደሎች ተጋልጠዋል፡፡ ሃይማኖታዊ መገለጫችን የሆነው ሒጃብ እና የህይወት

መመሪያችን የሆነው ቁርአን እንዲቃጠሉ ተደርጓል፡፡ ብዙ ወጣቶች ለእስር

ስቃይ እና ያልተገባ ስደት ተዳርገዋል፡፡ የመንግስት ሰራተኞች እና በገዥው

ፓርቲ አባልነት እንዲሁም አመራርነት ይሰሩ የነበሩና ኢፍትሃዊነቱን የተቃወሙ

ሙስሊሞችም ብዙ እንግልት አስተናግደዋል፤ እያስተናገዱም ነው፡፡ የመንግስት

ግፍ ለአገዛዙ ታማኝ አገልጋይ የነበሩ ከፍተኛ ባለስልጣናትን እና

ቤተሰቦቻቸውንም አላስተረፈም፡፡ ሙስሊም ነጋዴዎችም ከበፊት ጀምሮ

የሚደርስባቸው ፖለቲካዊ በደል ሳያንስ ተጨማሪ ቁጥጥር እና ምጣኔ ሃብታዊ

ጫና እየተደረገባቸው፣ በተጨማሪም እንደሌላው ህዝበ ሙስሊም የእስርና

ድብደባ ገፈት ቀማሽ እየሆኑ ነው፡፡

ይህ ሁሉ ግን ህዝብን ከሰላማዊ የመብት ማስከበር ትግሉ ስንዝር ወደ ኋላ

አልገፋውም፡፡ ከሚከተለው የሰላማዊነት መርህ አንዳችም እንዲያፈገፍግ እና

እንደመንግስት ወደተራ ሁከት እንዲዞር አልዳረገውም፡፡ ከዓላማውም ፍንክች

አላለም፡፡ ይልቁንም ከቀደምት ጀምሮ በሂደት ሲፈጸሙበት የነበሩ የመብት

ጥሰቶችን ለማስከበር፣ የፍትህን ባንዲራ ለህዝባችን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ

ለማስቻል ‹‹የፍትህ ያለህ!›› ሲል ከርሟል፡፡ አሁንም ለወደፊትምፍትህ ሳይሰፍን

መቆሚያው ከድቷት ያንጋደደችው የፍትህ ሚዛን ምጥነቷ ሳይስተካከል ወደኋላ

እንደማይል እየገለጸ ነው፡፡ ለዚህም ነው ህዝበ ሙስሊሙ ከተነሳንለት የመብት

ማስከበር ራዕያችን ባሻገር ‹‹የተዘነበለውን ፍትህ በትግላችን እናቀናለን!›› ሲል

የሚደመጠው፡፡

በእስከዛሬው ትግላችን እንደተስተዋለው ህዝብ ሙስሊሙ ቃሉን ጠባቂ፣

ለዓላማው ጽኑ ነውና ግቡን በሰላማዊ መንገድ ዳር ያደርሰዋል - ኢንሻአላህ!

መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹ጀግና ማለት በአካል ታግሎ የሚጥል ሳይሆን በቁጣ

ወቅት ራሱን ከስሜታዊ ጥፋት የሚያቅብ ነው›› እንዳሉንሁሉ እኛም እንድንቆጣ

ሲፈልጉ ሳንቆጣ ሰላማዊነታችንን ይዘን እንታገላለን! ‹‹ከትግል በላጩ

በአምባገነን መሪ ፊት እውነት መናገር ነው›› ባሉን መሰረትም መንግስታዊውን

ጭቆና በገሃድ አውግዘን እንታገላለን! እውነትን ተናግረን፣ ለእውነት ዘብ ቆመን፣

በእውነትላይ የተመሰረተ እኩልነት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ እውን እንዲሆን

እንተጋለን፡፡ ህዝብም ለአስተምህሮው በመገዛት ሰላማዊነትን በመዳረሻነት፣

መብት እና ፍትህ ማስከበርን በግብነት አንግቦ በአላህ ፈቃድ እስከድል ደጃፍ

ይጓዛል፤ ፍትህ ሲዘነበል ተመልካች አንሆንምና!

64

‹‹ፍትህ ሲዘነበል ተመልካች አንሆንም!››

በአንቀፅ 27 ንኡስ አንቀፅ 4 «ወላጆች እና ህጋዊ ሞግዚቶች በእምነታቸው

መሰረት የሃይማኖቶቻቸውንና የመልካም ስነምግባር ትምህርት በመስጠት

ልጆቻቸውን የማሳደግ መብት አላቸው» ይላል፡፡ ዛሬ ግን ህግ ለማስከበር

ቆመናል የምትሉ ወገኖቻችን ወላጆች ልጆቻቸውን በእስልምና አስተምህሮ

የመቅረፅ መብታቸውን እንደወንጀል ቆጥራችሁ ቤተሰቦቻችንን እና የሃይማኖት

አስተማሪዎቻችንን ስታንገላቱ እና ስታፈናቅሉ፣ ተማሪዎቻቸውንም ያለምንም

የህግ አግባብ ስትበትኑ እየተመለከተን ቆይተናል፡፡ ወላጆች ከ18 አመት በታች

ላሉ ልጆቻቸው የሃይማኖት ትምህርት ማስተማር እንዳይችሉ ለማድረግ

ወደፊት እቅድ እንዳለም ጭምር ጭምጭምታዎች ሲሰሙ ቆይተዋል። እኒህና

መሰል ተግባራት ሰብአዊ መብትን በቀጥታ የሚጋፉ እና ሃገራችን

የፈረመቻቸውን አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ቻርተሮች የሚረጋግጡ

ከመሆናቸውም ባሻገር የህግ የበላይነት ሲሰፍን በህግ ፊት የሚያስጠይቃችሁ፣

እኛም የምንጠይቃችሁ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡

የህገ መንግስቱ አንቀፅ 27 ንዑስ አንቀፅ 5 «የሃይማኖት እና የእምነት መብት

ሊገደብ የሚችለው የህዝብን ደህንነት፣ ሰላም እና ጤና፣ ትምህርት፣ የህዝብ

የሞራል ሁኔታ፣ የሌሎችን ዜጎች ነፃነቶች እና መሰረታዊ መብቶች፣ እንዲሁም

መንግስት ከሃይማኖት ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚወጡ ህጎች ነው» ይላል፡፡

በዚህ አንቀፅ መሰረት ሊመጣ የሚችል ማንኛውም ገደብ የሚደረገው የሃገር

ስጋት ሲሆን ብቻ ሆኖ።ሳለ በተግባር በተለያዩ ተቋማት ሲደረግ የቆየው ገደብ

ግን ሚሊዮኖችን እያስቆጣ ይገኛል፡፡

ዛሬ እኛ ኢትጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ትግላችንን ለ3 አመታት ያህል

በህጋዊ መንገድ አካሂደናል። በህገመንግስቱ ጥላ ስር ሆነንም ለህገመንግስቱ

መከበር ከእናንተ «ህግ አስከባሪ» ተብላችሁ ከተሾማችሁት በላይ ተቆርቋሪ

መሆናችንን ባለፉት አመታት በተግባር ከማሳየት አልፈን በርካታ ወንድምና

እህቶቻችንን ለዚሁ የህገመንግስት መከበር ትግል መስዋዕት አድርገናል።

በትግሉ ሜዳ ብዙ ብናጣም እስከዛሬም ድረስ የወኪሎቻችንን በሰላም የመፅናት

እና ለሰላም የመቆም ቃል ኪዳን ጠብቀን፣ በሃገራችን ሰላምና ፍትህ

የሚሰፍንበትን መንገድ ከእናንተ በላይ አስበንና ተቆርቋሪዎች ሆነን ቆመናል።

ይህ ለእናንተ ትምህርት ሊሆናችሁ ሲገባ ዛሬ እናንተ እኛን ወደጫፍ ለመግፋት

እና ስህተት ለማሰራት፣ ብሎም የሃገርን ደህንነት በምትፈጥሯቸው የእለት

ተእለት ወጥመዶች ለመጥለፍ የምታደርጉት ጥረት ነገ በህግ ፊት፣ ከዚያም

65

ሲያልፍ በታሪክ ተወቃሽ ያደርጋችኋል፡፡

«ህግ አስከባሪዎች» ሆይ! ይህች ደሃ ሃገራችን እናንተን ይህን ኃላፊነት

የሰጠቻችሁ እና ለዚህም ክፍያ የምትከፍላችሁ እኛ ኢትዮጵያውያንን

እንድታገለግሉ እንጂ የዜጎቿን መብት እንድትረግጡ እንዳልሆነ ተገንዘቡ።

የሃገር ደህንነትን ማስከበር ማለት የእኛ የኢትዮጵያውያንን ደህንነት ማስከበር፣

የእኛ የኢትዮጵያውያንን የእምነት ነፃነት ማክበር፣ የእኛ የኢትዮጵያውያንን

በነፃነት ወጥቶ በነፃነት የመግባት መብት ማክበር፣ ያሰብነውን ያሻነውን ማመን፣

ያሻነውን የመተው መብታችንን መቀበል መሆኑን ተገንዝባችሁ ለሃገራችን

ደህንነት እና ለህዝባችን ሰላም ቁሙ። ይህ ለህሊናችሁ የሚሆን ጥሪ ነው።

ዛሬ ለህሊናችሁ የምናደርገው መልካም ጥሪ እና አቤቱታ ነገ የህግ የበላይነት

ሲከበር በፍርድ ቤት ላደረሳችሁብን የህግ ጥሰት የምናቀርበው የክስ ፋይል

ይሆናል፡፡ ህገ መንግስታችን ተጥሶ፣ ደንባችን ተረግጦ፣ በሃገራችን ከፍተኛው

የህግ መሰረት የሆነው ህግ እና ድንጋጌ ተንዶ ይህንን ያለአንዳች ማመንታት

የጨፈለቁ፣ ያዋረዱ እና ያንኳሰሱ ለፍርድ የማይቀርቡባት ኢትዮጵያ

ለሁላችንም የማትበጅ ናትና በሃገራችን የህግ የበላይነት ሰፍኖ ወንጀለኛ ተጠያቂ

የሚሆንበት፣ ተበዳይ የሚካስበት ፍትሃዊ ዘመን እንደሚመጣ ተስፋ እያደረግን

አሁንም ደግመን ደጋግመን ከዚህ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ በአመክሮ

እንጠይቃለን፡፡በአንቀፅ 27 ንኡስ አንቀፅ 4 «ወላጆች እና ህጋዊ ሞግዚቶች

በእምነታቸው መሰረት የሃይማኖቶቻቸውንና የመልካም ስነምግባር ትምህርት

በመስጠት ልጆቻቸውን የማሳደግ መብት አላቸው» ይላል፡፡ ዛሬ ግን ህግ

ለማስከበር ቆመናል የምትሉ ወገኖቻችን ወላጆች ልጆቻቸውን በእስልምና

አስተምህሮ የመቅረፅ መብታቸውን እንደወንጀል ቆጥራችሁ ቤተሰቦቻችንን እና

የሃይማኖት አስተማሪዎቻችንን ስታንገላቱ እና ስታፈናቅሉ፣ ተማሪዎቻቸውንም

ያለምንም የህግ አግባብ ስትበትኑ እየተመለከተን ቆይተናል፡፡ ወላጆች ከ18

አመት በታች ላሉ ልጆቻቸው የሃይማኖት ትምህርት ማስተማር እንዳይችሉ

ለማድረግ ወደፊት እቅድ እንዳለም ጭምር ጭምጭምታዎች ሲሰሙ

ቆይተዋል። እኒህና መሰል ተግባራት ሰብአዊ መብትን በቀጥታ የሚጋፉ እና

ሃገራችን የፈረመቻቸውን አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ቻርተሮች የሚረጋግጡ

ከመሆናቸውም ባሻገር የህግ የበላይነት ሲሰፍን በህግ ፊት የሚያስጠይቃችሁ፣

እኛም የምንጠይቃችሁ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡

66

የህገ መንግስቱ አንቀፅ 27 ንዑስ አንቀፅ 5 «የሃይማኖት እና የእምነት መብት

ሊገደብ የሚችለው የህዝብን ደህንነት፣ ሰላም እና ጤና፣ ትምህርት፣ የህዝብ

የሞራል ሁኔታ፣ የሌሎችን ዜጎች ነፃነቶች እና መሰረታዊ መብቶች፣ እንዲሁም

መንግስት ከሃይማኖት ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚወጡ ህጎች ነው» ይላል፡፡

በዚህ አንቀፅ መሰረት ሊመጣ የሚችል ማንኛውም ገደብ የሚደረገው የሃገር

ስጋት ሲሆን ብቻ ሆኖ።ሳለ በተግባር በተለያዩ ተቋማት ሲደረግ የቆየው ገደብ

ግን ሚሊዮኖችን እያስቆጣ ይገኛል፡፡

ዛሬ እኛ ኢትጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ትግላችንን ለ3 አመታት ያህል

በህጋዊ መንገድ አካሂደናል። በህገመንግስቱ ጥላ ስር ሆነንም ለህገመንግስቱ

መከበር ከእናንተ «ህግ አስከባሪ» ተብላችሁ ከተሾማችሁት በላይ ተቆርቋሪ

መሆናችንን ባለፉት አመታት በተግባር ከማሳየት አልፈን በርካታ ወንድምና

እህቶቻችንን ለዚሁ የህገመንግስት መከበር ትግል መስዋዕት አድርገናል።

በትግሉ ሜዳ ብዙ ብናጣም እስከዛሬም ድረስ የወኪሎቻችንን በሰላም የመፅናት

እና ለሰላም የመቆም ቃል ኪዳን ጠብቀን፣ በሃገራችን ሰላምና ፍትህ

የሚሰፍንበትን መንገድ ከእናንተ በላይ አስበንና ተቆርቋሪዎች ሆነን ቆመናል።

ይህ ለእናንተ ትምህርት ሊሆናችሁ ሲገባ ዛሬ እናንተ እኛን ወደጫፍ ለመግፋት

እና ስህተት ለማሰራት፣ ብሎም የሃገርን ደህንነት በምትፈጥሯቸው የእለት

ተእለት ወጥመዶች ለመጥለፍ የምታደርጉት ጥረት ነገ በህግ ፊት፣ ከዚያም

ሲያልፍ በታሪክ ተወቃሽ ያደርጋችኋል፡፡

«ህግ አስከባሪዎች» ሆይ! ይህች ደሃ ሃገራችን እናንተን ይህን ኃላፊነት

የሰጠቻችሁ እና ለዚህም ክፍያ የምትከፍላችሁ እኛ ኢትዮጵያውያንን

እንድታገለግሉ እንጂ የዜጎቿን መብት እንድትረግጡ እንዳልሆነ ተገንዘቡ።

የሃገር ደህንነትን ማስከበር ማለት የእኛ የኢትዮጵያውያንን ደህንነት ማስከበር፣

የእኛ የኢትዮጵያውያንን የእምነት ነፃነት ማክበር፣ የእኛ የኢትዮጵያውያንን

በነፃነት ወጥቶ በነፃነት የመግባት መብት ማክበር፣ ያሰብነውን ያሻነውን ማመን፣

ያሻነውን የመተው መብታችንን መቀበል መሆኑን ተገንዝባችሁ ለሃገራችን

ደህንነት እና ለህዝባችን ሰላም ቁሙ። ይህ ለህሊናችሁ የሚሆን ጥሪ ነው።

ዛሬ ለህሊናችሁ የምናደርገው መልካም ጥሪ እና አቤቱታ ነገ የህግ የበላይነት

ሲከበር በፍርድ ቤት ላደረሳችሁብን የህግ ጥሰት የምናቀርበው የክስ ፋይል

ይሆናል፡፡ ህገ መንግስታችን ተጥሶ፣ ደንባችን ተረግጦ፣ በሃገራችን ከፍተኛው

የህግ መሰረት የሆነው ህግ እና ድንጋጌ ተንዶ ይህንን ያለአንዳች ማመንታት

የጨፈለቁ፣ ያዋረዱ እና ያንኳሰሱ ለፍርድ የማይቀርቡባት ኢትዮጵያ

67

ለሁላችንም የማትበጅ ናትና በሃገራችን የህግ የበላይነት ሰፍኖ ወንጀለኛ ተጠያቂ

የሚሆንበት፣ ተበዳይ የሚካስበት ፍትሃዊ ዘመን እንደሚመጣ ተስፋ እያደረግን

አሁንም ደግመን ደጋግመን ከዚህ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ በአመክሮ

እንጠይቃለን፡፡ምንም እንኳን መጅሊስ እንደ ተቋም ሃብትነቱ የሰፊው

ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ቢሆንም መንግስት ፍፁም ሃይማኖታዊ ተልዕኮ

ማስፈፀሚያና ለፈጣሪና ለእምነቱ ባለቤቶች ተጠሪ የሆነውን መንፈሳዊ

ተቋማችንን ጠልፎታል፡፡ በመሆኑም መጅሊስና ስግስግ ቀበሌኛ ሹመኞቹ

ተጠሪነታቸው ለመንግስት እንጂ ለሰፊው ህዝበ ሙስሊም አይደለም፡፡ አንድ

መንፈሳዊ ተቋም ባለቤትነቱም ተጠሪነቱም ለህዝብ ሳይሆን ለመንግስት

የሆነባት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የምንኖረው፡፡ በመሆኑም ሌት ተቀን የሚባክኑት

ሹመት የሰጣቸውን መንግስት ዓላማ በማሳካት መንግስትን ለማስደሰት እንጂ

ህዝቡን ለማስደሰት አይደለም፤ ሆኖም አያውቅም፡፡ መንግስትና የመንግስት

ሹመኞች እንደ አባትና ልጅ ናቸው፡፡ መንግስት በሃይማኖት ሳቢያ ህዝብን

ከህዝብ ለማጫረስ ባክኗል፤ ከስሯልም፡፡ የመጅሊሳችን ሹመኞችም ቢሳካልን

ብለው መማሰን መጀመራቸውን በአደባባይ ስናይ ቆይተናል፡፡

ዘመነ ኢህአዴግ መግባቱን ተከትሎ ሃይማኖትን በነፃነት ከመደራጀት እስከ

መተግበር የነበረችው ጭላንጭል ከተዳፈነችበት ከ1980 አጋማሽ ወዲህ

መንፈሳዊ ተቋማችን በደርጉ ሥርዓት የቀረው ‹‹ውርስ-ለመንግስት›› ፖሊሲ

ተግባራዊ የተደረገበት ተቋም ሆኗል፡፡ ይሁንና ሙስሊሙ ህብረተሰብ እጅግ

ተደራራቢ ከነበሩ ሃይማኖታዊ ጭቆናዎች መላቀቅ የጀመረበት ወቅት የነበረ

በመሆኑ የተነሳ ከወቅቱ ሀገራዊ አለመረጋጋት ጋር ተዳምሮ እንዲህ እንደዛሬ

በሳል የሆነ፣ የተቀናጀና አንድነትና መግባባት የሰፈነበት ንቅናቄ በመፍጠር

ተቋሙን ከውርስ ነፃ ማድረግ ሳይቻለው ቀርቷል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የልብ ልብ የተሰማው መንግስት የተቋሙን ስያሜ መቀየር

ሳያስፈልገው ውርሱ ያደረገውን ሹመኞችን ሲሾም ሲሽር ከረመበት፡፡ በጓሮ

ሹመት ተሸከርካሪ ወንበር ላይ ያፈናጠጣቸው ሹመኞች በሙሉ በንግግርም

ይሁን በተግባር የሙስሊሙን ልብ ሳያደሙ፣ ሙስሊሙ ከሌሎች እምነቶች ጋር

ተቻችሎና ተከባብሮ እንዳይኖር እንቅፋት ለመሆን ሳይጥሩና ሳይተገብሩ

ከወንበራቸው ወርደው አያውቁም፡፡ ፖለቲካዊ መሳሪያነታቸውን ለማረጋገጥ

ሲሉ የሚያስተላልፏቸው አወዛጋቢ፣ ቁምነገር አልባና ጠብ የለሽ በዳቦ

መልዕክቶች ሰላማዊ ትግላች ከመጀመሩ አስቀድሞ ህዝብ ወካይ እንዳልሆኑ

በተለያዩ አጋጣሚዎች ከማሳወቅ አልፎም ዛሬ ላይ መንፈሳዊ ተቋማችንን

68

የሚያላግጡበት አመራር ተብዬ ግለሰቦች ይቅርና ተቋማችን በራሱ በእነኚህ

ሰዎች መዳፍ ስር ገብቶ በሙስሊሙ ስም የሚያካሂዳቸው ተግባራት ህዝባዊም

ህጋዊም ዕውቅና እንደሌላቸው ህዝበ-ሙስሊሙ በዒድ አደባባይ የሹመቱን

ተምሳሌታዊ ስርዓተ ቀብር በመፈፀም አውጇል፡፡

ይህንን መንፈሳዊ ተቋም ‹‹መጅሊሳችን›› ብለን የምንጠራው ህግና ስርዓት

አክብረን ሃይማኖታዊ እሴቶቻችንን በእምነቱ መሠረታዊ አስተምህሮት መሰረት

በጋራ የምንፈፅምበት ንብረትነቱ የራሳችን የሆነ ድርጅት በመሆኑ ነው፡፡ ይህ

ሲባል ደግሞ ተቋሙ ፍፁም ነፃ ሆኖ በተለይም አገራዊ ከሆኑ የልማት

አጀንዳዎች ርቆ ብቻውን ይጓዛል ማለት እንዳልሆነ በጣም ግልፅ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ይህን መሰል መንፈሳዊ ተቋም እውን ሆኖ ለማየትና

ተጠቃሚ ለመሆን ከምኞት የተሻገረ ትርጉም ያለው እንቅስቃሴ እያደረግን

እንገኛለን - ይሳካል፡፡ ያኔ ከህጋዊ ተቋማችን ህጋዊ አመራሮች የሚወጣው

መልዕክት የልዩነትና የጠብ መነሻ ሳይሆን የአንድነትና የፍቅር መዳረሻ ይሆናል -

ላለፉት ሶስት ዓመታት ስናካሂደው ከቆየነው ሰላማዊ ትግላችን ዋነኛና ትላልቅ

መገለጫዎች አንዱ ህዝባዊ አንድነት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይኸው ህዝባዊ

አንድነት ደግሞ መገለጫ ከመሆንም አልፎ የትግሉ ትሩፋት ለመሆን በቅቷል፡፡

እጅግ አንጸባራቂ እና በሚዛን የማይለካ አንድነት ተስተውሏል፡፡ የትግሉ አባጣ

ጎርበጣ እና ፈታኝ ጊዜያት የታለፉት በዚሁ የአንድነት ጸጋ ነው፡፡ ለማቋረጥ

አስቸጋሪ በሆነው የመስዋእትነት ባህር ላይ መንሳፈፍ የተቻለውም በዚሁ

የህዝባዊ አንድነት ታንኳ ላይ ነው፡፡ ሃይማኖታችን ላይ ከመንግስት በኩል

ለተሰነዘረው ህገ ወጥና ኢ-ህገ መንግስታዊ ጥቃት መከታ ለመሆን ለሰኮንድ

ያላመነታው ህዝበ ሙስሊም አንድነቱን በሚያንጸባርቅ ግብረ መልሱ

የማያወላዳ መልእክት በደል ለሚያደርሱበት አካላት አስተላልፏል፡፡

ይህ አንድነት ከህዝብ ወረድ ብለን ስናየው በትግል አራማጆች ዘንድም ጠልቆ

የተስተዋለ መሆኑን አንረዳለን፡፡ በተለይም እስካሁን የታየው የትግል አራማጆች

መናበብ እና የህብረተሰቡ ስሜት መዋሃድ ከአላህ ውጭ የማናገኘው ትልቁ

የትግላችን በረከትና ፍሬ ነው፡፡ እርስ በእርስ የሚናበቡና የትግሉን ዓላማ

በሚገባ የሚረዱ አራማጆች የየትኛውም ትግል ሞተር ናቸውና ከዚህ አኳያ

ሙስሊም ታጋዮችም ታሪክ የማይረሳውን ድንቅ ሚና መጫወት ችለዋል፡፡

ይህ በህዝብም ሆነ በትግሉ አራማጆች ደረጃ ገንኖ የተስተዋለው ህዝባዊ

አንድነት እንዲሁ ከመሬት የተገኘ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከጅምሩ ባዳበርነው

የትግላችን ዓላማ እና መርህ ዙሪያ ጥልቅ ግንዛቤ በመወሰዱ ነው፡፡ ሙስሊሙ

69

ህብረተሰብ የትግሉን ዓላማዎችም ሆነ መርሆች ጥርት ባለ መልኩ ተረድቶ

መንቀሳቀሱ በትግሉ ሜዳ የማይዋዥቅ አንድነቱን ይዞ እንዲገኝ አስችሎታል፡፡

ይህ አንድነቱ የትግሉ መራዘም፣ የጥቂት አፈንጋጭ እና ‹‹እኔ አውቅልሃለሁ›› ባይ

አምባገነን አስተሳሰቦች መፈጠር አብሮነቱን እንዳይፈትነው ያደረገው ሲሆን

እንደህዝብ ሁላችንም ለምን እንደምንታገል በልቦናችን አውቀን

በመስዋእትነታችን በተግባር ያረጋገጥነው እውነታ ለመሆንም በቅቷል፤

!ሀገራችን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የህዝቧን ደህንነት በማክበርና

ስብእናቸውን በማስከበር ረገድ ቃል የገባችና ይህንን ህግ እና ደንብ ያለአንዳች

አድሎና ልዩነት ለዜጎቿ የመጠበቅ ኃላፊነትን የተረከበች ሀገር ናት፡፡ በዚህም

መሰረት በአንቀፅ 28 «በስብዕና ስር የሚፈፀሙ ወንጀሎች» በሚል ርዕስ

በአንቀፅ 28 ንዑስ አንቀፅ 1 ኢትዮጵያ ባፀደቀቻቸው ዓለምዓቀፍ ህጎች እና

በሌሎች የኢትዮጵያ ህጎች በሰው ልጅ ላይ የተፈፀሙ ተብለው የተወሰኑትን

ወንጀሎች የፈፀሙ አካላት፣ ማለትም የሰው ዘር ማጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት

ቅጣት እርምጃ መውሰድ፣ በአስገዳጅ ሁኔታ ሰውን የመሰወር ወይም ኢሰብአዊ

የድብደባ ድርጊቶችን የፈፀሙ ሰዎች ላይ ክስ ሲቀርብ በይርጋ አይታገድም፤

በህግ አውጭው ክፍልም ሆነ በማንኛውም የመንግስት አካል ውሳኔ በምህረት

ወይም በይቅርታ አይታለፉም» ይላል፡፡

በዚህ አንቀፅ በግልፅ እንደተደነገገው ሀገራችን ኢትዮጵያ የዜጎቿን ስብዕና

የሚነኩ ማናቸውንም እርምጃ የሚወስዱ፣ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በቤተ

እምነት እና በመኖሪያ፣ እንዲሁም በስራ ቦታ ያሉ ምዕመናንን ህይወት የቀጠፉ

«ህግ አስከባሪ» አካላት ለወንጀላቸው ሳይጠየቁ የሚያልፉበት አግባብ ሊኖር

አይገባም። የህግ የበላይነት ሲሰፍንም በሚሰጥባቸው ፍርድ የሚወሰነው ውሳኔ

በይርጋ ሊሻር እና ሊቀል የማይችል ነው፡፡

ስብዕናን ይነካሉ ተብለው ከተጠቀሱት ወንጀሎች ግድያ አንዱና ከፍተኛው

ቢሆንም በአስገዳጅ ሁኔታ ሰውን የመሰወር ወንጀልም በእጅጉ አስጠያቂ ነው፡፡

ነገር ግን በሃገራችን ይህ ወንጀል በየእለቱና ያለአንዳች ይሉኝታ እየተፈፀመ

መሆኑ፣ እንደቀላል ተወስዶ የዜጎች መብት የሚረገጥበት፣ ዜጎች ታፍነው

ተወስደው ቤተሰቦቻቸው የት እንደሆኑ የማያውቁበት አጋጣሚ በርካታ መሆኑ፣

ዜጎች የታሰሩበትን ቦታ ለቤተሰብ ማሳየት እንደ ውለታ የሚታይና የግለሰቦች

መብት መሆኑ የተዘነጋበት ጊዜ መምጣቱ እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ ዜጎቻችን

ያለጥፋት መታሰራቸው ሳያንስ የት እንዳሉ የሚጠይቁ ቤተሰቦች የሚማፀኑበት፣

የሚቀጡበት እና የሚታሰሩበት ዘርፈ ብዙ በደል የሚፈፀምባት ሃገር መሆኗ

70

እጅግ ያሳዝናል፡፡ በዚህ አንቀፅ መሰረት እኛ ኢትዮጵያውያን በሃገራችን የህግ

የበላይነት የሰፈነ ቀን ህጉን እና መብታችንን የረገጡትን ለፍርድ እንደምናቀርብ

ፈፃሚዎቹም በሚገባ እንደሚረዱት እናምናለን፡፡

በዚህ አንቀፅ እንደተገለፀው ሌላው ኢሰብአዊ የሆነው ድርጊት ድብደባ ነው፡፡

ይህ በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን ለማስጠበቅ በሚወጡ ወገኖቻችን ላይ

በየጊዜው የሚፈፀምና ህግ አስከባሪ በተባሉት ወገኖች እንደተራ ነገር ተደርጎ

እየተወሰደ የሚገኝ ወንጀል በአንቀፅ 28 በከፍተኛ ደረጃ የሚያስቀጣ እና

ቅጣቱም ያለአንዳች ይግባኝ የሚፀና፣ እንዲሁም በማንኛውም አካል ሊቀነስና

ሊሻር የማይችል ነው። በዚህ ድርጊት ላይ የተሰማራችሁ «ፀጥታ

አስከባሪዎች»ም ከዚህ ድርጊት እንድትቆጠቡ ህዝብ በተደጋጋሚ

እያስታወሳችሁ ይገኛል፡፡

በአንቀፅ 28 ንዑስ አንቀፅ 2 ከዚህ በላይ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ

አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ የተጠቀሱትን ወንጀሎች ፈፅመው የሞት ቅጣት

የተፈረደባቸው ሰዎች «ርዕሰ ብሄሩ ቅጣቱን ወደ እድሜ ልክ እስራት ሊያሻሽል

ይችላል» ይላል፡፡ ግና ይህን አይነት ወንጀል በህዝባችን ላይ የሚፈፅሙ ሰዎች

እስከሞት የሚደርስ ፍርድ የሚያስቀጣ ወንጀል መፈፀማቸውን ያለማወቃቸውና

ይህንን ከባድ ወንጀል ሲፈፅሙ ግዳጃቸውን እንደተወጡ አድርገው

ማቅረባቸው እጅግ አሳዛኝ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለዚህ ይህ ህገ ስብዕናን

የሚያጎድል ወንጀል፤ ማለትም፡- የሰው ዘርን የማጥፋት እርምጃ፣ ያለፍርድ

ህይወት የማጥፋት እርምጃ፣ አስገዳጅ ሰውን የማፈንና የመሰወር እርምጃ፣

እየተለመዱ የመጡት ድብደባን የመሰሉ የወንጀል ድርጊቶች፣ ይባስ ብሎም

የስራ ክፍላችሁ ዋና ተግባር አድርጋችሁ የያዛችኋቸው እና በአፀያፊ ሁኔታ

በወገኖቻችን ላይ የምትፈፅሟቸው ወንጀሎች በከፍተኛ ደረጃ በህግ

የሚያስጠይቋችሁ እና በታሪክ ፍርድ ፊትም የሚያቆሟችሁ መሆኑን አውቃችሁ

እንድትጠነቀቁ ህብረተሰቡ አሁንም ያሳስባችኋል፡፡መንግስት በሙስሊሙ

ህብረተሰብ ህልውና ላይ እንደዘመተ በግልጽ ካሳየባቸው እርምጃዎች ውስጥ

አንዱ በቅርቡ የተፈጸመው የሀምሌ 11ዱ ጥቁር ሽብር መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚያች ቀን በሙስሊም እህቶች ላይ መንግስት ያደረሰው አስጸያፊ እና ኢ-

ግብረገባዊ ድርጊት ዒላማ ያደረገው የሙስሊሙን ክብር በማጉደፍ ላይ ነበር፡፡

በወቅቱ መንግስት ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ‹‹አስከብሬዋለሁ›› እያለ

የሚለፍፈውን ‹‹የሴቶች መብት›› እና ‹‹የሃይማኖት ነጻነት›› ባዶነት በተጨባጭ

አረጋግጧል፡፡ የጥቁር ሽብር ድርጊቱ የበርካታ ሙስሊም እህቶችን ክብር

71

ከማጉደፉም ባሻገር ሂጃብን ከምዕመናት ላይ አስወልቆ በማቃጠል መንግስት

ለህዝብ እና ለህገ መንግስት ያለውን የጥላቻ እና ንቀት መጠን በግልጽ

አሳይቷል፡፡ የያዘውን ጸረ-ኢስላም እና ጸረ-ሙስሊም አቋምም በገሃድ

ያስመሰከረበት ታሪካዊ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡ ላለፉት ጥቂት የማይባሉ

ዓመታት የሙስሊሙ ህብረተሰብ የግል እና የቡድን መብቶች በመንግስት

መገርሰሳቸው ሳያንስ በእስልምናችን ክብር እና ህልውና ላይ ያነጣጠረ እጅግ

አስቀያሚ ድፍረት መፈጸሙ በእርግጥም በእጅጉ የሚያቆጭ ነው፡፡

በተጨማሪም መንግስት የህዝበ ሙስሊሙን የትምህርት እድል ተጠቃሚነት

ለመሸርሸር በየዩኒቨርስቲው ያሉ ሙስሊም እህቶችን በሒጃብ፣ ወንዶችን ደግሞ

በሰላት ምክንያት ከትምህርት ማዕቀፍ ለማግለል ስልታዊ እርምጃ መውሰድ

ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በበርካታ የትምህርት ተቋማት ሙስሊም

እህቶቻችን በእስልምና ድንጋጌ ግዴታ የሆነውን ሒጃብ በመልበሳቸው ብቻ

ከፍተኛ አስተዳደራዊ ጫናን ተጋፍጠዋል፤ ፖለቲካዊ አፈና ደርሶባቸዋል፤

በሃይማኖታቸው እና በሴትነታቸው እንዲሸማቀቁ ለማድረግ ተሞክሯል፤

ብሎም ከትምህርት ገበታቸው በማፈናቀል የመማር እና የእምነት መብታቸው

ተጥሷል፡፡

የሙስሊም ሴቶች ሃይማኖታዊ፣ ጾታዊ እና ተምሮ የመስራት መብት በመንግስት

አካላት መነፈጉ በትምህርት ተቋማት ብቻ ሳይገደብ በስራ ቦታዎችም

መንጸባረቅ መጀመሩም ይህን መሰሉ የመብት ጥሰት በተናጠል የሚከናወን እና

ድንገት የሚፈጠር እንግዳ ክስተት እንዳልሆነ ግልጽ ማሳያ ነው፡፡ ለሰላማዊው

የሃይማኖት መብት ማስከበር ሂደታችን አጋር በመሆናቸው በየእምነት

ተቋማቶቻችን በሃይል ሰርገው በገቡ የመንግስት አካላት በየጊዜው ታፍነው

የተወሰዱ ምዕመናት ላይ የሚፈጸመው ሒጃባቸው ላይ ያነጣጠረ ዘለፋ መረን

የለቀቀ እና የችግሩን አድማስ ስፋትም ይበልጥ የሚያመላክት ነው፡፡ በተለይም

ትርጉም አልባ እየሆነ በመጣው የፍርድ ሂደት ፍትህ ተነፍገው፣ ለረጅም ጊዜ

በቃሊቲ ታጉረው እየተንገላቱ ያሉት ፍርድ አልባ እህቶች በሙስሊም

ሴትነታቸው እና በአለባበሳቸው ምክንያት የደረሱባቸው የቃላት ጥቃቶች እና

የስነልቦና ጫናዎች የመንግስት በሙስሊም ሴቶች ክብር ላይ ያነጣጠረ ህገ ወጥ

ተግባር ከልኬት ማለፍ ጠቋሚ ነው፡፡፡

ይሁን እንጅ የሒጃብ ጉዳይ በየትኛውም መልኩ ከየትኛውም የመንግስት አካል

ጋር የማንደራደርበት መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ በጥቁር ሽብሩ ቀጥተኛ ተጠቂ

የነበሩት እህቶች በደረሰባቸው የመብት ጥሰት ቅስማቸው ከመሰበር ይልቅ

72

በድርጊቱ ተሳታፊ የነበሩትን የጥቁር ሽብር ግብረ-አበሮች በህግ ፊት ለማቆም

የጀመሩት እንቅስቃሴ ለዚህ ምስክር መሆን የሚችል ክስተት ነው፡፡ ሙስሊም

ሴቶች ሃይማኖትን ላማከለ ሒጃብ ነክም ይሁን ሌላ ተዛማጅ የጾታ ትንኮሳ

እንደማይንበረከኩ ያሳዩበት ተምሳሌትም ነው፡፡ መንግስት እየወሰደ ያለው

ሒጃብን የማስወለቅ እና በማቃጠል የስነልቦና ሽንፈት የማከናነብ መሰሪ ዓላማ

ፈጽሞ ሊሳካ እንደማይችል ከዚህ የተሻለ እማኝ መጥራት አያሻም፡፡

‹‹በሂጃብ ላይ የተከፈተው ዘመቻ ይበልጥ ወደ ሂጃብ ያቀርበናል!›› በሚለው

የሳምንቱ አጀንዳ ውስጥ ይህንን የመንግስት የጥፋት ተልዕኮ የሚያጋልጡ

በተጨባጭም ህዝባዊ ምላሽ የሚሰጥባቸው ተግባራት የሚኖሩን ይሆናል እጅግ

የሚበዙት ከእስር ቤትና ከፍርድ ሂደቶች ጋር የተያያዙ ነበሩ፡፡ እነዚህ እስር

ቤቶችና ፍርድ ቤቶች በሙስሊም እስረኞችና ባለጉዳዮች ተጨናንቀው

መታየታቸውም የተቋሞቹ እለታዊ ተግባር ሆኗል፡፡ ‹‹የሙስሊም መፍትሄ

አፈላላጊ ኮሚቴዎች የፍርድ ሂደት ቀጥሏል፤ የኮሚቴዎቻችን የዛሬው ምስክር

የማሰማት ሂደት ዳኞች ባለመገኘታቸው ሳይካሄድ ዋለ፤ ወንድም እከሌ ጨለማ

ክፍል ታሰረ፤ እከሌ የተባለው ታሳሪ ምግብ እንዳይገባለት ተከለከለ፤ ፍርድ

ቤት የቀረቡ ሙስሊም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለወር ተቀጠሩ፤ የእከሌ ከተማ

ሙስሊም እስረኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ፤›› ወዘተ አይነት ዜናዎችን መከታተል

ከጀመርን ሰንብተናል፡፡ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የሚገኙ በርካታ ሺህ

ሙስሊሞች እስር እና ፍርድ ቤቶችን ሞልተው ይታያሉ፡፡ በእስር ቤቶችም ሆነ

በፍርድ ቤቶች ከእስረኞቹ በተጨማሪ ችሎት ለመታደምም ሆነ ለመዘየር

በስፍራው የሚገኙ ሙስሊሞችም እጅግ በርካቶች ናቸው፡፡ ‹‹ይህ ሁሉ ለምን

ሆነ?›› ካልን የተሰራ ወንጀል ኖሮ ሳይሆን ለመብት ታጋይ ሆነው

በመገኘታቸው፤ የሀይማኖት ነፃነትም ሆነ ህገ መንግስቱ ባስቸኳይ ይከበር ዘንድ

በመጠየቃቸው ብቻ ሆኖ እናገኘዋለን!

በእነዚህ እስር ቤቶችና ፍርድ ቤቶች የሚታዩት ትእይንቶችም እጅግ አሳፋሪዎች

ናቸው፡፡ ሴቶችና ህፃናት ፆታዊ ሁኔታቸውን አደጋ ላይ በሚጥል አያያዝ ስር

ይገኛሉ፡፡ እስረኞች በአሰቃቂ ሁኔታ ይደበደባሉ፡፡ ፍርድ ቤቶችም ቢሆኑ

የሙስሊም እስረኞችን ጉዳይ ገለልተኛ ሆነው መዳኘት በሚችሉበት ምህዳር

አልተሰየሙም፡፡ ለወትሮው እስር ቤቶችን የምናውቃቸው ወንጀለኞችን

ለመቅጣትና ለማረሚያነት ነበር፡፡ አሁን እየሆነ ያለው ግን የተገላቢጦሽ ነው፡፡

እስር ቤቶች ስለ ሰላም የሚዘምሩ፣ ስለፍትህ የሚጮሁና መብት የሚጠይቁ

ዜጎች ማጎሪያ ካምፕ ሆነዋል፡፡ ለሀገር ልማት አዎንታዊ ሚና ሊጫወቱ የሚችሉ

73

በርካቶች የእስር ቤት ቁልፍ ተከርችሞባቸው ይገኛሉ፡፡ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ

ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ተማሪዎች በእስር ቤት እንዲታጎሩ

ሆነዋል፡፡ ‹‹ለምን?›› ቢባል ስለ ሰላምና ፍትህ በመጮሃቸው፣ የመብት

ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ብቻ ነው፤ ምንም እንኳ መንግስት በ‹‹ሽብርተኝነት››

ስም ቢከሳቸውም! እርግጥ ነው የኢስላምን ታሪክ መለስ ብለን ብንቃኝ ሁሌም

ቢሆን ዑለሞች፣ ለዲን ተቆርቋሪዎች እና ታግለው የሚያታግሉ ሁሉ

መኖሪያቸው እስር ቤት ነበር፡፡ ለተወነጀሉበት የሀሰት ክስ የሚለጠፍላቸውም

ስም ተመሳሳይ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖም ግን አሸናፊዎቹ እነሱ ነበሩ፡፡ ኢስላም

እያበበ እንጂ እየከሰመ አልመጣም፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ የአላህን ፈተና

አልፈዋል፡፡ ከትውልድ ትውልድም ስማቸው ሲዘከር ይኖራል፡፡

አዎን! በሰላማዊ ትግል ታሪክ ዓለም ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት የቻሉ

ሁሉ ለማለት ይቻላል መኖሪያቸው እስር ቤት፣ ስማቸውም አሸባሪ እንደነበር

ታሪክ ምስክር ነው፡፡ ማህተማ ጋንዲና ኔልሰን ማንዴላ አለማችን ካፈራቻቸው

ድንቅ የሰላማዊ ትግል ተምሳሌቶች መካከል ግንባር ቀደሞች ናቸው፡፡ እነኚህ

ሁለት የሰላማዊ ትግል ፈርጦች ታዲያ ‹‹ሽብርተኛ›› የሚለውን ስያሜ ጨምሮ

በባላጋራዎቻቸው ያልተለጠፈላቸው ስም አልነበረም፡፡ ሁለቱም ጀግኖች ረጅም

ለሚባል ጊዜ በእስር ቤት እንዲኖሩ ተፈርዶባቸዋል፡፡ በስተመጨረሻ ግን

74

አሸናፊዎቹ ጠላቶቻቸው ሳይሆኑ እነሱ ነበሩ፡፡ ሰላማዊ ትግል በተነሳ ቁጥር

እነዚህ ሁለት ሰዎች በአለም ህዝብ ዘንድ ስማቸው አብሮ ይነሳል፡፡ ፍሬያቸው

አፍርቶም ትውልድ ይዘክራቸዋል፡፡ ወደራሳችን ተጨባጭ ሁኔታ ብንመለስ

የሀገራችን እስር ቤቶች የዛሬ ታጋዮችን እና የነገ ተስፋዎችን የያዙ ወሳኝ ቦታዎች

ሆነው እናገኛቸዋለን ፡፡ እነዚህ የቁርጥ ቀን ዜጎች በማይገባቸው ቦታ እንዲታጎሩ

ሆነዋል፡፡ የማይመጥናቸው ስምም ተለጥፎላቸዋል፡፡ ቢሆንም ነገ የእነሱ ቀን

እንደምትሆን ምንም ጥርጥር የለውም! ፀሃያቸው የማትጠልቅ የምትመስላቸው

የዛሬዎቹ አምባገነኖችም ድንቅ የሰላም ታጋዮችን ባልሰሩት ወንጀል ለማሸማቀቅ

ይጥሩ ይሆናል፡፡ ሌሊቱ ሲነጋ ግን መሸነፋቸውን ያያሉ፡፡ ትውልድ ሁሉ

በእኩይ ተግባራቸው ሲያፍርባቸውና ሲሳለቅባቸውም ለማየት ይገደዳሉ፡፡

በአንፃሩ ደግሞ በጀግኖች ታሳሪዎች ፅናት እና በእነሱ ፈለግ መጪው ትውልድ

ፍትህ ለሰፈነባት ኢትዮጵያ የሚተጋ ዜጋ መሆኑ አይቀርም፡፡ ያኔ የዛሬ

ታሳሪዎቻችን ገድላቸው ይዘከራል፤ በዳዮችና ሴራቸው ይከስማል፤ ለችግር

በማይበገር ሰላማዊ ትግል የጭካኔ እሳታቸው ይዳፈናል፤

ኢሃዴግ በሙስሊሙ ሃይማኖት ጣልቃ መግባት የኢትዮጵያዉያንን ሰላማዊ ትግል በሐይል መቀልበስ ያልቻለዉ ህወሃት መራሹ መንግስት፤ ትግሉ ወደ ድል ደጃፎች የሚያደርገዉን ጉዞ ለማፋለስ የተለያዩ ሴራዎችን ያሴራል። ከነዚህም የተንኮል መንገዶች ዋነኛዉ በሰላማዊ ትግል ላይ የተሰማራዉን ሙስሊሙን ማህበረስብ ማከፋፈል፣የሰላም አምባሳደር የሆኑትን ኮሚቴዎችን ባደባባይ ባሸባሪነት እየፈረጀ…በምስጢር በጣም ድንቅ የሆኑ የኢትዮጵያ ልጆች መሆናቸዉን በመግለጽ በመንግስት ላይ የሚደረጉ ተቃዉሞዎች ቢረግቡ ሊፈታቸዉ እንደሚችልና ነገሮች ሁሉ ወደነበሩበት እንደሚመለሱ የዉሽት ቃልኪዳን ይገባል። ህወሃት በስም የሚቀርባቸዉ ወይም ከዲያስፖራ አገር በመግባት ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎትያላቸዉንሰዎችበመደለልበአንድነትየሚታገለዉንሙስሊሙማህበረሰብ እንዲሸረሽሩ ስዉር የማታለል ተልእኮም ይሰጣል። አንባገነናዉያን እርቅና ሽምግልናን ከሚገቡበት አጣብቂኝ ለማምለጥ ከሚጠቀሙባቸዉ የማሳሳቻ መሳሪያዎች ዋነኛዎቹ ናቸዉ።ሐይልን ለህዝብ መስጠት የማይፈልግ አንባገነናዊ መንግስት በሽምግልና እና በእደራደራለሁ ማታለያ የአዞ እንባዉን እያፈሰሰ የሰላማዊ ትግል ትሩፋቶችን እንክት አርጎ እንደሚበላ ለማወቅ ብዙ ምርምር ባያሻዉም የአለማችንን ወቅታዊ ሁናቴዎችን ማጤን ብቻ ይበቃዋል። አወቀዉትም ይሁን ሳያዉቁት፣ መልካም ይመጣል ብለዉ በመታለል፣ በሰላማዊ ትግሉ በመዛል (በመዳከም) ነገሮች ወደነበሩበት እንዲመለሱ በመሻት፣ የተጀመሩ ኢንቨስትመቶች እንዲያልቁ ካልያም አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ለመጀመር መዉጫ ቀዳዳን ለሚፈልገዉ ህወሃት መራሹ መንግስት መዉጫን በነጻ ለመቸር (መዉጫን ጀባ ለማለት) የሚንደፋደፉ ወገኖች በየቦታዉ እየተታዩ ነዉ።

75

ትላንት በኢህአዴግ የተንገፈገፉ ዛሬ ከኢህአዴግ ጋር መሞዳመዱን ዲሞክራሲያዊ መብት እንደሆነ በድፍረት መግለጽ የጀመሩም አሉ። ኢትዮጵያዉያንን በጅምላ እያገላታ ያለዉን፣ ሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን አስሮ በምድራዊ ቸነፈር ያሰቃየዉን፣ቁርዓንና ሒጃብን ያቀጠለዉን፣ መስጊዶቻችንን የሚያፈርሰዉን፣መስጊዶቻችንን ወርሶ ካድሬ ሚሾመዉን፣ መጽሄት ጋዜጦቻችንን የዘጋዉን፤…ኡለሞች፣ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች ካገር እንዲሰደዱ ያደረገዉን ፣እምነትን ነጥቆ በአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ለማጥመቅ የሚዳክረዉን፣ በደም የተበከሉ እጆቹን በእምነት ተቋም ዉስጥ በማስገባት የአገርን ሉአላዊነት ለማናጋት ሌት ተቀን የሚሰራዉ ህወሃት መራሹ መንግስት ጋር መሞዳመዱ እንደመብት ከታየ…ከሐይማኖት በላይ የመንግስትን አጀንዳ ለማራመድ የሚቅበዘበዙ ጥቂቶች አንገዋሎ መለየቱና መቃወሙ መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታ የሆነበት ወሳኝ አጋጣሚ ከፊት ለፊታችን ላይ ተጋርዷል። “በረዶ አዘል የህወሃት የጥቃት ዶፍ ከመዉረዱ በፊት የአዞእንባ አልቃሹን ህወሃት እንጠንቀቀዉ!” በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች የሚደረገዉን ሰላማዊ ትግል ሙሉ ለሙሉ ቢደግፉም በጣት የሚቆጠሩ ጥቂቶች ግን ለህወሃት መራሹ መንግስት መዉጫ ቀዳዳን ይፈልጉለታል።

የህወሃት መራሹን የማታለልና የማዘናጋት ሴራ ወደ መሬት ለማዉረድ የሚንቀሳቀሱ እነማን ናቸዉ?

· ከዲያስፖራ ወደ ኢትዮጵያ የሚመላለሱ የይስሙላ የኢንቨስትመንት ቀረቤታ ያለቸዉ

ወይም ኢንቨስት ማረግ የሚፈልጉ ጥቂቶች

· ከባለስልጣናት ጋር ቀረቤታ ያላቸዉ ወይም ባለስልጣን ዘመድ የቤተሰብ አባል

ያላቸዉ።ባሉበት የምቾት አለም ዉስጥ በሰላም መቀጠል የሚፈልጉ

· ከመንግስት ባለስልጣናት ሁሉም ነገር ወደነበረበት ይመለሳል ተብለዉ የዉሸት ቃል

የተገባላቸዉ

· ዲያስፖራ በሚገኙ ኤምባሲዎች በልማት ስም በብሔር ብሔረሰቦች ጉዳይ ወጣ ገባ

የሚሉ

· ከዲያስፖራ ወደ አገር ቤት ባጋጣሚ የሔዱና መሬት ላይ ያለዉን ተቃዉሞ እና

የመንግስት በደል በሚገባ ያላጤኑ

· አገር ቤት ሆነው ያንባገነናዊዉ ስርዓት ተጠቃሚ የሆኑ፤ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች

የሚያደርጉት ሰላማዊ ትግል ያላቸዉን መረጋጋት እና ከስርዓቱ የሚያገኙትን ጥቅም

የነካባቸዉ

· ከአንባገነናዊዉ ስርዓት ጋር ቁርኝት ያላቸዉና ከስርዓቱ የሚጠቀሙ፤ የሙስሊሞች

ቅዋሜ ከገፋ ስርዓቱን ሊንደዉ ይችላል የሚል ፍራቻ ያለቸዉና ስርዓቱን ለማዳን

የሚሯሯጡ

· ከሐማኖት በፊት የብሔር ጉዳይ የሚያስቀድሙና ብሔርተኛዉን መንግስት ማዳን

የሚፈልጉ

· ህወሃት መራሹ መንግስት ከጥፋቱ ተምሮ እራሱን አሻሽሎ ይስተካከላል ብለዉ

የሚያምኑ። ከተስተካከልም በተስተካከለዉ መንግስት ዉስጥ እራሳችንንም ጠቅመን

76

ወገናችንን እንረዳለን ብለዉ በየዋህነት የሚያስቡ

· በማህበረሰቡ ዉስጥ ቦታ የነበራቸዉ ግን ከሰላማዊ ትግሉ ፍጥነት ጋር አበረዉ መጓዝ

ያልቻሉ።በድምጻችን ይሰማ በህቡእ የሚደረገው ስኬታማ ትግል ተሰሚነትን

የነጠቃቸዉ…የተሰሚነትን ቦታ ፈላጊዎች

· አፈንጋጮች፦ ከብዙሗን አመለካከት ዉጪ የራስቸዉን በጣም አናሳ ንኡስ ክፍል

ለመስረት የሚጠሩ። ተምረናል፣አንብበናል በማለት የነርሱ አስተሳሰብ የላቀና የመጠቀ

እነደሆነ በማሳየት፤ ብዙሃኑ የሚያደርገው ትግል የመንጋ(mob) ጥረት ነዉ ብለዉ

የሚያጣጥሉ። ተግባር የለሽን (theory) ትግል በሞላቀቅና በፍልስፍና ለማስረጽ

የሚሞክሩ ናቸዉ።

· አደገኞቹ፦ መንግስትን መቃመም፤ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ክልክል ነዉ የሚል

ዲሞክራሲ ከሌለባቸዉ የአረብ አገራት የመጣ አመለካከትን (Dogma) ለመተግበር

የሚሹ። እነዚህ አካላቶች ከጠላት ጋር ማበርን ተገቢ ነዉ የሚሉበት አጋጣሚ

ስለሚኖር አደገኛነታቸዉን ከግምት ዉስጥ ማስገባቱ ግድ ይላል።

· የሚፈሩ፦ በመላዉ አለም በሙስሊሞች ላይ የሚደረሰዉን ጥቃት በማየት ‘የባሰዉን

አታምጣዉ!’ በሚል እሳቤ ‘እስኪያልፍ ያለፋል!’ እያሉ በጭቆና ዉስጥ መኖር

የሚፈልጉ።

· ግራ የተጋቡ፦ የሙስሊሙን ህገመንግስታዊ መብት መከበር ቢደግፉም፤ ህወሃት

መራሹ መግስት በአወሊያ ያቋቋመዉ የስሙላ ቦርድና መጅሊስን አስመልክቶ ያደረገዉ

የሐስት ምርጫ ለዉጥ ነዉ ብለዉ ማመካኛ(excuse) የሚሰጡ። በድንበር የለሹ

የህወሃት ፕሮፓጋንዳ ግራ የተጋቡ።

· ጀዝባ እና ስራ ፈቶች፦ በሱስ የተጠመዱ፣ የኔ የሚሉት ስራ የለላቸዉ ማንኛዉንም

መግስታዊ ሴራ በርካሽ ክፍያ ከመፈጽም ወደ ሗላ የማይሉ ናቸዉ። እነዚህ ግለሰቦች

ዛሬን በልቶ ማደር እንጂ ነገን አርቀዉ መመልከት የማይችሉም ናቸዉ። በህገወጡ

መጅሊስም ይሁን በመስጊድ ነጠቃ ወቅት የመንግስትን ሴራ ለማስፈጽም ያለ እፍረትና

ፍርሃት ይንቀሳቀሳሉ።

የሌላ እምነት ተከታዮችን መላክ፦

መፍትሔዉ ያለዉ ህወሃት በቂሊንጦ እስር ቤት አስሮ በሚያሰቃያቸዉ የሰላም

አምባሳደሮችና የሚሊዮኖች ወኪሎች ዘንድ መሆኑንን እያወቀ፤ ቀደም ሲል ህወሃት

ከተቃዋሚዎች ጋር በነበረዉ ችግር አመርቂ የፖለቲካ ስራ ያሰራቸዉን ሰዎች ዛሬም

የሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል ለማሰናከል ሲጠቀምባቸዉ ይስተዋላል።ኢትዮጵያዉያን

ሙስሊሞች ካለፉት የፖለቲካ ስተቶች የተማሩ በመሆናቸዉ ህወሃትን ያልተበላበትን

እቁብ እንዲፈልግ እያሳፈሩት ነዉ። ‘ድመትን በር ዘግተህ አትደብድባት’ የሚለዉ

አባባል በራሱ አንባገነናዊ የዞረ ድምር ለናወዘዉ ህወሃት መልስ ሰጪ ነው። የህወሃት

መዉጫ ቀዳዳ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የጠየቀውን ጥያቄ ባግባቡ መመለስና መመለስ

ብቻ ነዉ። ባቋራጭ የሚፈለጉ መዉጫ ቀዳዳዎች ሽንቁር (ክፍተት) ለመፈጠር

77

ከሚደረጉ የጨቋኝ ፈላጭ-ቆራጮች ሴራ ቢሆኑ እንጂ ምንም ሊሆኑ አይችሉም።

በርግጥ ህወሃት መራሹ መንግስት መፍትሔን የሚሻ ከሆነ እራሱ ወደ አዘጋጀዉ

የማጎሪያ እና የማሰቃያ ቀዬ ወደሆነዉ ቂሊንጦ እስር ቤት ዝቅ ቢል መፍትሔን ያገኛል።

ካልያ የድመቲቱ ተረት እዉን መሆኑ አይቀሬ ነዉ። በርግጥ ድመቲቱ መዉጫ ቀዳዳ

ስታጣ ልትቧጥጥ ልትቧጭር ትችላለች፤ በስተመጨረሻ ግን ያካባቢዉ ሰዉ ተሰባስቦ

ያቺን መረን የለቀቀች ድመት በቁጥጥር ስር ያዉላታል። እነሆ የድመቲቱን መቧጨርና

መቧጠጥ የቻለዉ ትዉልድ ትግላችን እስከድል ደጃፎች ድረስ በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

እያለ ወደፊት እየገሰገሰ ነዉ።

ከልብ የሰረጸ ህዝባዊ እንቅስቃሴ አይቀለበስም።ተወልዶ፣ አድጎ፣ ጎርምሶ፣ ወጣትን

የተላበሰዉ ሰላማዊ ንቅናቄ ጎልማሳ ሲሆን ብልሃትና ዘዴን ይቀዳጃል። ብልሃትና ዘዴን

የተቀዳጀዉ ሰላማዊ ንቅናቄ ወሳኝ ለዉጥን ለማምጣት ስልታዊ ዝምታን፣ስልታዊ

ማፈግፈግን እና ስልታዊ ቅኝትን ይጠቀማል። ጉዞዉ ረጅም መሆኑንን የተረዱት

ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች የትግል ሐይልን ለመቀዳጀት ስልታዊ አካሔድን ሲመርጡ

ስጋት የገባዉ ማፍያዉ ህወሃት ኮንደሚኒየም፣ መሬት እሰጣችሗለሁ በማለት የድለላ

ተገባር ወደ ማህበረሰቡ የሚልካቸዉ የፖለቲካ ቤተ-ሙከራ የዋሃን ሰራተኞች

መሰማራታቸዉ እየታየ ነዉ። እፈኝ የማይሞሉ የዋሃን ከህወሃት በላይ እምነታቸዉን

በህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ እና በድምጻችን ይሰማ ላይ ጥለዉ

ቢረጋጉ መልካም ነዉ የሚልም ትችት ይሰነዘራል።

“ዝምታ ወርቅ ነዉ!” በኢንቨስትመንትም ይሁን በኮንዶሚኒየም ስጦታ ወይም በሌላ

ጥቅም የተሸበቡ ሰዎች በዝምታ ልማታዊ ዜጎች መሆን ይችላሉ። ግን ድንበርን አልፈዉ

ሙስሊሙ ማህበረሰብ ደሙን ያፈሰሰበት ትግል ላይ በደም የተጨማለቀዉን የህወሃት

እጅ ለማጠብ ደፋ ቀና የሚሉ ከሆነ…ከጨቋኝ ጋር በማበር ለሚመጣ ተጠያቂነት

እራሳቸዉን ለምን ያጋልጻሉ የሚልም ጥያቄ ይነሳል።

ህዝብ በሰላማዊ ትግል የሚቀዳጀዉ ዉጤት ዘገምተኛ እና ዘለቄታዊ ነዉ። በዚህ እልህ

አስጨራሽ የትግል ሒደት ዉስጥ ግዜ ዋነኛ መሳሪያ ነዉ። የግዜን መዝለግ ለራስ

ጠቀሜታ እንዲዘነበል ለማደርግ አንባገነናዉያን የግዜን ስርቆት ይፈጽማሉ። ቀደም ሲል

ግዜን ለመስረቅ ያደባዉ ህወሃት ህዝብን ያልማከለ የሽምግልና ሴራዉን ፈጽሞ

አይደለም ሽምግልናዉ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ለማሰባሰብ በሰሜን አሜሪካ

የሚገኝ እደዣንጥላ የተዘረጋ ድርጅት መክኗል። አሁንም ዳግም ህወሃት በመደራደር

ስም ያደመነዉ የጥቃት ደመና በረዶ አዘል ዶፉን ሊያዘንበዉ እየጠቋቆረ በመሆኑ

ጥንቃቄ በሚያሻበት ወስኝ ወቅት ላይ እንገኛለን። በጽናት መታገል እንጂ መለሳለስ አንባገነናዉያንን አያረግባቸዉም። ጫናዉ ግፊቱ

ሊቀጥል ይገባል፤ ህወሃት መዳራደር ከፈለገ ከዲያስፖራ በልማትና በኢንቨስትመንት

ስም ወይም በካንዳሚኒየምና መሬት ታገኛላቹ ድለለላ በመለመላቸዉ ግለሰቦች

ሳይሆን፤ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ዘንድ ተመርጠዉ ዛሬ ቂሊንጦ እስር

78

ቤት ከሚገኙ ጀግኖች ጋር ነዉና ልብ ያለዉ ልብ ይበል።

የወያኔ ምርጫ መቃረብ ኢዮጵያን ከነስርዓቷና ባህሏ እልም አርጎ ሳይጠፋ እንደማዝለቅ ከወዲሁ

ይታወቃል። ለሃገሪቱ ውድቀት ተጠያቂው እኛም ኢትዮጵያዊያን መሆናችን

አያጠራጥርም ምክንያቱም ለፍቅርና ለሰላም ለአንድነትና ለሃይማኖት ቦታ

አልሰጠንምና ነው ያለ ሃይማኖትና ያለመልካም ስራ እግዚአብሄር ማስደሰት

አይቻልም ለእግዚአብሄርም ባለመገዛታችን ኢህአዲግ በትውልድ ላይ የጣለው

ጠበሳ ይህ ነው አይባልም ብቻ ቤት ይቁጠረው።

በስደት እየወጣ በየመንገዱና በየበረሃው ጠፍቶ የቀረውን ቤት ይቁጠረው።

በሃረብ አገራት በደላላ እየወጡ በፈላ ውሃ እየተላጡ ከሞቱትም በላይ ካሉትም

በታች ሆነው የቀሩት ቤት ይቁጠረው። በሀገሪቱ ላይ የተዘረጋው የትምህርት

አቀራረፅ ዶሮ ከነጫጩቷ የዋለችበትን ይመስላል በስነ ምግባር እጦት ተላሸቀና

የደሸቀ የትምህርት አሰጣጥ የገደለውን ትውልድ ቤት ይቁጠረው

በቤትክርስቲያን ላይ በአቡነ ጳውሎስ በኩል እየታዘዘ የነርሱን የውጭ ሃገር

ባንክ ማበልፀጊያና በልዩ ልዩ ምክንያት እየወጣ የቤተክርስቲያኒቱ ገንዘብ ከምን

ላይ እንዴት እንደሚውል አሁንም ቤት ይቁጠረው። ትውልድ ሞራለቢስ፣

ወኔቢስ፣ ሳይሞት የሞተ፣ ሳይቀበር የተቀበረ በኢህአዲግ ነውና ዝሙተኛ

ሀሰተኛ ስግብግብ ከዳተኛና ችኩል የታሪክ አተላ የተፈጠረ በዘመነ ኢህአዲግ

ስለሆነ የቀረውን ሁሉ ቤት ይቁጠረው። ሄርዶስ ስልጣኑን ከመውደዱ የተነሳ

ዝሙት እየፈፀመ ይህን ስራውን የተቃወመውን መጥምቀ መለኮት ዮሃንስን

በዳንሰኛዋ ሄሮድያን አስገድሏል። ኢህአዲግ በሃገሪቱ ላይ ያደረሰው ጥፋትና

በደል ከዚህ ቢበልጥ እንጂ አያንስም።

ሀ። የተሰደደው ለ።በጦርነት ያለቀው ሐ።በረሃብ የሚያልቀው መ።በበሽታ

የወደቀው ሠ።እያበደ የቀረው ረ።ሞራሉ ተነክቶ ሳይማር እየተቅበዘበዘ ፉዞ

ሆኖ የቀረው ይህ ነው አይባልም ብቻ ቤት ይቁጠረው ሰ።ጎረቤት ከጎረቤት

ጏደኛ ከጏደኛ እንዳያወራና በሃሳብ እንኯን ተሰብስቦ ችግሩን በጋራ እንዳይፈታ

በዘርና በሃይማኖት ክፍልፍል አድርጎ አገራችንን ለባዳ አሳልፎ መስጠቱንና

የወደፊት አገራዊ ህልም እንዳይኖረን አድርጎ መና ያስቀረውን ቤት ይቁጠረው።

79

ቢሾም ሌባ ውሸታም ዘረኛ ሙሰኛ ዝሙተኛ እንዴት ብሎ ነው ለሃገር ማሰብና

መጨነቅ የሚኖረው ስለዚህ ኢህአዲግ የሰራው ወንጀል ይህ ነው ተብሎ

ስለማይገመት አሁንም ቤት ይቁጠረው ሌላ ምን ይባላል ለምህራቢያን

የሚጋለብ ፈረስ ሆኖ እስከተገኘ ድረስና ለወላጅ ፍቅርና ህብረት እስካጣ ድረስ

በሰወኛ ሊወድቅ አይችልም ነገር ግን እግዚአብሄር እንዲረዳን እባካችሁ

ባመንበት ሁሉ ፀንተን እንቁም ከዝሙት እንጠንቀቅ እላለሁ። እግዚአብሄር

የኢትዮጵይያን የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላቷን ይጣልልን።

ግማሹ ህዝብ ይህን ሁሉ ስቃይ ከማሳለፍ በማምለጥ ስደትን

የመረጥነው ብዩዎቻችን ነን። ነገር ግን ወያኔ የሚባል አውሬ መንግስት የውጭ

አልጋ የቤት ቀጋ እንደሚባለው ስለሆነ እነኝህ በእስር ቤት የሚገኙ ንፁሃኖች

ናቸው ይህን ሁሉ ስቃይ የሚኖሩት ምንም አይነት ጥፋት ሳይኖርባቸው ወያኔ

ጥፋት ኣለባቸው እያለ ቢያስወራም እነርሱ ግን ወያኔ እንደሚያወራው ሳይሆን

በተቃራኒው ናቸው።

ጎረቤት አክብሩ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ የተቸገረን እርዱ፣ በማይጠቅም ነገር

ዜጎቻችሁን አታቃጥሉ በማለት ወደ ጥሩ ስነምግባር ስለሚመሩን ነው ወያኔ

ያሰራቸው። ምክንያቱም እሱ የሚፈልገው እንደርሱ አረመኔ የሆነውን እንጂ

ጥሩ ሰው አይወዱም። እነዚህን ለምን አሰርካቸው ሲባል ሙስሊም መንግስት

ስለሚፈልጉ አለ፣ እነዚህ ህዝቦች ግን ለእስላም መንግስት ይመረጥልን የሚል

ሃሳብ አንድም ቀን አላቀረቡም። ብቻ ለወያኔ እንዲህ እለዋለሁ እንዲሁም

ለባልደረቦቹ፣ ስጋ እንደ ጉንዳን ደምን እየጠጡ ወንጀለኛ ሆነው ንፁሃን ሲቀጥ፣

ቀናቶች ቢረዝሙም የትም አታመልጡ። ተዘርዝሮ አያልቅም የወያኔ ታሪክ

በአጭሩ ይህንን ይመስላል። የሃገሬ ልጆች በእስር ቤት፣ በስደት ላላችሁ፣ አጠር

ያለች ግጥም እንዲህ ልበላችሁ። ቢበዛም ስቃዩ ከሃገር መሰደድ የዝያ፣ በሰሃራ

ስቃዩን ማየቱ በእስር ቤት እስራት፣ በዱላ በረሃብ መሰቃየቱ፣ በሰው ጫማ

መረገጡ፣ በረሃ ላይ መሰቃየቱ፣ በስው ጫማ መረገጡ፣ በረሃ ላይ መሰቃየቱ፣

በሰው ጫማ መረገጡ፣ በረሃ ላይ መሰቃየቱ ቢበዛብንም ይሄ ሁሉ። መታሰሩ

መደብደብ፣ውሃ ጥሙ እርሃብ፣ ሃገር ጥሎ መሰደዱ፣ አብሽር ወገኔ ያልፋል ቀኑ፣

አብሽር ወገኔ ያልፋል ቀኑ። አይ ወገኔ አባረረን አሰቃየን ከሃገር ሁል ጊዜ የለም

ስልጣን ትሞታለህ አንድ ቀን የዛች ጊዜ ጌታህ ፊት ስትቀርብ ምን ትል ይሆንß

ይች ቀን መች ትሆን ያች ቀን። የርሱን ፍጡር ስታሰቃይ ስታስር ላንተ ደግሞ

አለልክ፣ ገሃነም አለልክ እኮ ገሃነም። አንተ ስልጣን ስትመካ፣ እኛ ደግሞ አለልን

እኮ እውነትን አውጪ ትልቁ ጌታ፣ እውነትን አውጪ ትልቁ ጌታ። አይ ወያኔ

80

ወንጀለኛ ሆነህ ንፁሃን ስትቀጣ፣ እንዲህ እለዋለሁ ስጋዬን እየጎዱ ደመን

እየጠጡ ወንጀለግና ሆነው ንፁሃን ሲቀጡ ጊዜው ቢረዝም እንጂ የትም

አያመልጡ።

ሥልጠናው እርግጫ፤ መንገዱ ውንብድና፤ መንፈሱ ፍጥጫ የወያኔ ተፈጥሮ

ይሄው ነው። ሥርዓትና ወያኔ ተያይተውም አያውቁም። ይልቁንም ሥርዓተ –

አልበኝነት የዋኘበትና የናኘበት መሆኑን ከተፈጠረበት ሀገርን የማክስል

ተልዕኮው ቀን ጀምሮ ያሉት ሁኔታዎች አንድ በአንድ ቢፈተሹ ፍሬ ነገሩን

ማግኘት ይቻላል።

2007 electionወዬኔ በተፈጥሮው የአውሬነት ሰብዕና የተለበሰ ነው። አውሬነት

ደግሞ ጸረ ሰው በመሆኑ በሰበነክ ጉዳዮች ላይ የሚወስዳቸው መጠን ያለፈ

የጭካኔ እርምጃዎች እራሳቸው ቆመው ይመሰክሩበታል። እርግጥ ወያኔ

በተለዋዋጭ ባህሪው አጥፊ ፍላጎቱን ለማስፈጸም አስችሎታል። በማጭበርበር

– በማምታታት ደጉን የኢትዮጵያ ህዝብ አጃቢ በማደረግ ለሥልጣን መብቃቱ

ብቻ ሳይሆን፣ የሚገርመው ህዝባዊ የእንቢተኝነት ሞገዳማ ነበልባሉ ዘመን

መራዘሙ ምክንያቱ ቅጥፈቱና እራሱን ገልጦ ለማሳዬት ድፍረት የሚያንሰው

በመሆኑ ነው። ወያኔ በክንብንብ ኖሮ በክንብንብ ያልፋል። አልማጭ!

ቀባ አድርጎ አብልጭልጮ አንድ ህዝበ ጠቀም ዬሚመሰል ግን ገዳይ ፖሊሲ

ያወጣል። ወገን ላይ ላዩን ብቻ አይቶ የተሻለ – የበለጠ – የሚሆን ነገር ተገኘ

ብሎ በፍቅር ከአዲሱ የሽፍታ ቅብ ፖሊሲ ጋር ደፋ ቀና ሲል፣ ቀስ እያለ

እዬሸረሸረ ወደ አቀደውና ወደ አለመው ላጥ ወደ አለው ገደል ይዞ መሄድ ብቻ

ሳይሆን፤ ተስፋን ከነስብዕና ቅጥቅጥ አድርጎ ይቀጣበታል። “ወንዝ ሲወስድ

እያሳሳቀ” ይበል የለ – እንደዛ ነው ነገሩ።

ወያኔ በሥልጣን መባቻው ነፃ ፕሬስ አንደ ጉድ ፈቀደ። ማህሌት፤ አዕምሮ፤

ሙዳይ፤ ጦቢያ፤ አፍሪካ ቀንድ፤ ኢትዮጲስ፤ ሳታናው ወዘተ … መጽሄቱም

ጋዜጣውም በገፍ መታተም ጀመሩ። ነፃነት የጠማው ብዕር ስለ ነፃነት፤

ስለመናገር መብት፤ ስለ የህግ የበላይነት፤ ስለ ኢትዮጵያዊነት፤ ስለ አብሮነት፤

ስለ ፍቅር የሚገባውን ያህል ቀን ከሌት – ማሰኑ። … ህዝቡም የራበውን

መተንፈሻ ስላገኘ በሽሚያ፤ በቋሚ ደንበኝነት ጸሐፍትን አበረታታ – አደነቀ –

ሃቅንና እውነትን ከበከበ … ግን ቀጠለ ….? እእ ….

“የፕሬስ ነፃነት በኢትዮጵያ” የወያኔ የመቅጫ መንገዱ ማሟሻ ነበር። ነፍሱን

81

ይማረውና በጋዜጠኛ ተፈራ አስማረ ግንባር ቀደምትን ወህኒ ቤቶች በመጽሄትና

በጋዜጣ አዘጋጆች ተጨናነቁ። ፍርድ ቤቶችም ሚዛንን ገልብጠው

የሚሰቅሉበትን ሁኔታ ወያኔ አመቻችቶ አደራጀላቸው። ከዚህ በኋላ ዒላማውን

ጎሰኛው ወያኔ አስተካክሎ እስኪበቃው ድረስ ነጻውን ፕሬስ ወቃው። የመናገር፤

የመጻፍ፤ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ ሆነ የማንበብን የለመለመ ተስፋንም ገንዞ

በድፍረት ቀበረው። ጭላጭሏንም ሶሞኑን ዳፍንት አለበሰው። ደፋሩ ጋዜጠኛ

ተመስገን ደሳለኝ ቀርቶት ነበር እሱንም ለእግር – ብረት፤ ከህዝብ እውነተኛ

ብሶት ተነስታ ጭብጥን – በጭብጥ አዋዳ ለመንፈሳችን ሁነኛ ስንቅ የነበረቸው

የተመስገን ትእግስቱ /ደሳለኝ/ ብእር – የካቴና ስንቅ ሆነች። ይህቺ የእርግጫ

ምርጫ ስትመጣ ጉድጓድ ውስጥ ተቀብሮ የቆዬ ውሻ ያደርገዋል። ደም –

ደምም ይሸተዋል – አረሙ።

ይህን ለምሳሌ አነሳሁ እንጂ ወያኔ አቅዶ የሚወጣቸው ማናቸውም ትልሞች

ሁሉ የተከደነ ወይንም የተሸፈነ የበቀል ተልዕኮ አሽኮኮ አድርገው ነው

የሚወጡት። አንዷ ቃል ወይንም ሐረግ ለምለም ዝግን ትመስላለች። ግን

በመርዝ የተቀመመች የመሞቻ እንክብል ናት። አረሙ ወያኔ የተነሳበት ሆነ

ያለመው ቂምና በቀልን ሥልጣን ይዞ እንዴት ተግባር ላይ ማወል እንደሚችል

ነበር። በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ከእጁ የገባ ማናቸውም ፍጡር የማናቸውም

ዓይነት ሰቆቃ መፈተኛ ነው የሚሆነው። ይህን በግለሰብ ደረጃ አይተን ወደ

ሀገራዊ ጉዳይ ስናመጣው ስንት በደልና መከራ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ

ተሸከመች መገመት ይቻላል።

እኛ ደግሞ ነገረ ሥራችን ግልጥና ቀጥተኛ ስለሆን የምንፈልገውን፤ ያስብነውን፤

ውስጣችን የሚነግረንን፤ ያቀድነውን በነፃው ሚዲያ በሉት በመጸሐፍ

እናወጣለታልን። ይህ እሱ ቆልፎ ላስቀመጠው ሸሩ ድውለቱ ነው። በቀጣዩ

ጊዜያት ወራት ሆነ አመታት በተገባው ተሰናድቶ አዲስ መሰል ግን በቀልን

ያረገዘ ደንብና ህግ ያሰናዳበታል። ወይንም ስስ ነው በተባለው ቦታ እዬሰበረ

የሚያኖር አዲስ ህግ ያረቅበታል …. ውድ የፁሁፌ ታዳሚዎች ታስታውሱ ከሆነ

የሳውዲው የወገን ሰቆቃ ወያኔ የተጋለጠበት፤ ዬኢትዮጵውያን ቁጣ የነደደበት

ወቅት ነበር። ታዲያላችሁ ወያኔ ቀዳዳውን ለብዶ የሸፈነበት መሳሪያው የተከበሩ

ዶር/ ካሳ ከበደ ከኢሳት ጋር በነበራቸው ቆይታ በሰጡት የበሰለ በተመክሮ

የፀደቀ ትንተና ነበር። ዝሎ የነበረው የወያኔ መንፈስ ተነቃቅቶ ጣዖት

አምላኪዎቹ ከበሯቸውን እንዲያንኳኩ ያገዛቸው።

…. ከዛ ግልብ የታይታ ተግባር በኋላ ለወገኖቻችን ምን ተደረገ? ምንም። ሁሉን

82

ነገር ስታዩት የነፈሰበት ጉድ ነው። መጣፍያ ነገር። ለነገሩ ማጣፊያው ለትንፋሽ

ስለሚያጥረው ነው። ወያኔ የእኔ የሚለው ብቃት እኮ የለውም። የኢሠፓ

ካድሬዎች ናቸው ነፍስ የዘሩበት። …. ስለምን ይህን ወንጀል እንደሚፈጽሙ

አይገባኝም። አዎን ወንጀል ነው። የመጀመሪያው በሁለት ቢላዋ መብላት ሲሆን

ሁለተኛ ደግሞ እንዲህ ላለ ርኩም – እርጉም ሥርዓት ጧፍ አብርቶ

ማሽሞንሞናቸው ነው። ልምድና ተመክሯቸውን በገፍ መለገሳቸው … ታሪክን

የማቃጠል ያህል የሀገር በደል ነው። ተደናብሮ እንዲወድቅ ነበር ማደረግ

የነበረባቸው። ያውም እኮ እነሱም ቢሆን እንደ አሮጌ አካፋና ዶማ ከተጠቀመ

በኋላ …. እህል ውሃቸው እልቅ —-

አሁን ይሄ ምርጫ የሚባለው ነገር ወገኖቻችን በገፍ ወደ እስር ቤት

የሚወረወሩበት፤ ሴት ልጆች በግፍ የሚደፈሩበት፤ ደጁ ሜዳው፤ ዱር ገደሉ

በፍርሃትና በስጋት የሚዋጥበት፤ መተንፈሻ ባንቧዎች ሁሉ የሚዘጉበት ህዝብን

በነቂስ የሚያሳድድበት ዘመቻዊ ትልሙ ነው። እንዲሁም ወያኔ ወዳጅና ጠላቱን

የሚለይበትና በጠላቶቹ ወይንም ፊት – ለፊት በወጡት ተቀናቃኞቹ ላይ ቂምን

ቋጥሮ አጋጣሚ እዬፈለገ የሚያድንበት መረቡ ነው። ከዚህም በላይ በተነጠላዊ

ህይወትም ውስጥ በሚያሰማራቸው ሰላዮቹ አማካኝነት የቤት – ለቤት

ውጥረቱን አጠንክሮ ሰላም የለሽ ኑሮ ህዝባችን እንዲኖረው የሚያደርግበት

እጅግ የረቀቀ የበደል ጋሜና ቁንጮው ወይንም በደልን የሚያስጌጥበት ወቅቱ

ነው። የወያኔ ምርጫ እርግጫን አስልቶ – ወገኖቻችን በጥርስ የሚገበቡት

ተለይተው ከላይ እሰከ ታች ዝርዝራቸው ተይዘው በዓይነ ቁራኛ የሚጠበቁበት

የመጠራቅቅ ወቅት ነው። …. በአፈና፣ በማሳደድ፣ መርዝ በመስጠት፣ ከሥራ

በማስለቀቅ፣ ከእድገት በማገድ፣ ከቦታ በማዛወር ማናቸውም አለ የተበለ የቂም

እርምጃውን የሚወስድበት የማጥቂያ፤ አቅዶ የሚፈጽመው አሳቻ * መንገዱ

ነው። ለዛውም ከእርግጫ – ከፍጥጫ – ከአውሬነት ስብእናው ጋር …..

ስለዚህ ይህን አራት አመት እዬቆጠረ በሚያመጣው የማሳደድ ዘመቻ መደገፍ

– መሳተፍ – ማሟሟቅ – ተስፋ ማደረግ - አጀንዳ ማድረግ – መንፈስን

መስጠት – መስዋዕትን መክፈል – መዋለ ንዋይ ማፍሰስ ያስፈልጋዋልን? …..

ሂደቱ “ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማለይ” ሥነ ውበታዊ ፈሊጥ በእውን

ተግባራዊ የሚሆንበት ከመሆኑ በተጨማሪ …. በወገኖቻችን ላይ በስተጀርባ

የሚፈጸው ድርብ ድርብርብ ሰቆቃ ደግሞ ሚዛን ከቶውም ሊወጣለት

አይችልም። ዛቪያው ይሸከረከራል ወገን ይታረስበታል – በግፍ።

ስለዚህ የተገፋ ወገን፣ የከፋው ወገን፣ የተከዘ ወገን፣ የተራበ ወገን –

83

ባይታዋርነት በሀገሩ ላይ ተፈርዶበታል፤ በሌላ በኩልም ሳይፈልግ ወይንም

ሳይመኘው የተሰደደው ወገንም ቢሆን ሃገሩ በዓይኑ እንደ ዞረች – እዬቀረ ነው።

ስለሆነም ወገን ምን ማደርግ አለበት? ነው የጹሁፉ መሰረታዊ አናት።

የአጭበርባሪን – የእርግጫ ምርጫ ለእሱ የሚፈይደው አንዳችም ነገር አንደሌለ

ካለፉት ምርጫዎች በስማ በለው ሳይሆን በህይወት ተኖረበት። አሁን

የምርጫው ውጤት በድርጅታዊ ሥራ ድልድል ተደርጎበታል። ለሁሉም ቦታ

በውስጥ ታዋቂነት ሰው ተመድቦበታል። ለምስል ነው ዬምርጫ እርግጫ

ዳንኪራ የተሰናዳው። ወያኔ የሚመራበት ርዕዮት የሶሻሊዝም አናርኪዝምን

ነው። ስለዚህ ሰፊው ዬኢትዮጵያ ህዝብ የመከራው ገመድ የሚበጥስበትን ዘላቂ

ተከታታይ ተግባር መከወን ይኖርበታል።

መበታታኑ ሆነ ተነጠላዊ ትግል ሀገር ቤት ላይ የሚያወጣ መንገድ አይደለም።

የወልን ችግር በወል ለመወጣት በጋራ መነሳትን ይጠይቃል። ሰራተኛ፤

ጋዜጠኛ፤ ጸሐፊ፤ የእምነት ማህበር ምእመናን፤ ነጋዴ፤ ተማሪ በዬጊዜው

ብሶታቸውን በአንድም በሌላም መንገድ ይገልፃሉ። …. አንድ ነጣላዊ ፍላጎትን

ብቻ አንግበው። ነገር ግን ጠቃሚው ነገር ይህን ተናጠላዊ ፍላጎት ወደ አንድ

ማዕከል አምጥቶ ህዝባዊ አልገዛም ባይነትን በተከታታይ አደባባይ ማዋል ብቻ

ነው መፍትሄ ሊሆን የሚችለው። የአንድ አካል ብቻ ሩጫ – ትንሽ ነጥብ፤

የሁሉም አካል የጋራ ሩጫ ግን ሙሉ ተስፋን በእጅ ያስገባል። ጥላቻው

ሥራዓቱና የሚተዳደርባቸው ህግጋት ብቻ በመሆናቸው ይህን በበሰለ አምሮ

አመዛዝኖ ሥርዓቱን እስከነመመሪያው እንዲወገድ የማደረግ ዘመቻ ነው ለነፃነት

ትግሉ ስንቅም ትጥቅም ሊሆን የሚገባው። ግለሰብ ቢወርድ ግለሰብ ይተካል።

ሄሮድስ መለስ ዜናዊ አለፉ … ግን ሥርዓቱ አለ። … ለዛው ኢትዮጵያዊነትን

እዬነቀለ። የአቶ በረከት ሆነ የአቦይ ህልፈት ወይንም የአቶ ቴወድሮስ አድሃኖም

የአውሮፕላን አደጋ ደርሶባቸው ቢያልፉ እንኳን መፍትሄ አይሆንም።

መፍትሄው ጠላታችን የሆነው የወያኔ ማንፌስቶ ከጥቅም ውጪ የሚያደርግ

ሥርአት መፍጠር ነው። ለዚህ ደግሞ ፍላጎትን ወደ አንድ አቅጣጫ ማምጣት

መሰረታዊ ጉዳይ ነው።

ይህ ደግሞ ይቻላል “ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ጌጡ”

መከራውን – ስቃዩን – ፍዳውን – አታካች ኑሮውን ህዝብ አዳምጦ ለምላሹ

እያንዳንዱ በነፍስ – ወከፍ የሚሳተፍበት “ሰላማዊ አመጽ” በመንፈስ ማህጸን

ሲነግሥ የቅጽበት እንቅስቃሴ ዬእልፍኝ ባለቤትነትን ያውጃል። ዛሬ እንዲህ

ተፈሪ የሆነው የወያኔ የእርግጫ ህግ ህዝባዊ አመጽ ሲፈናዳ ህጉ እራሱ

84

መሸሸጊያ ትንሽ ቁጥቋጦ ብቻ ነው የሚፈልገው። መጓጓት መልካም ቢሆንም

ጉጉትን ማናር ግን የተገባ አይደለም። የጉጉት ህያውነትን በእጅ ያለ ብቃት ብቻ

ነው የሚወስነው። የበቃ ተግባር – የበቃ ጉጉትን ያሳካል። ቤት ውስጥም ሆኖ

እኮ ጸጥ ብሎ ማመጽ ይቻላል።

ምርጫውን ወያኔ የሚካሂደው ሳይወድ የተቀበላቸውን አሻንጉሊቱን ጠ/ሚር

አውርዶ የራሱን ደም የሆኑትን አቶ ቴወድሮስ አዳህኖምን ለማጸደቅ ነው። ያው

ከላይ የጠቃቀስኩላችሁ የቂም ማወራረጃው ሁነቶች እንደተጠበቁ ሆነው።

ስለሆነም የነጻነት ትግሉ የእሱን የጢባጢቦ ግርድፍ ተውኔቱን ለራሱ አሸክሞ፤

ቀጣይ ሥራን መስራት ያስፈልጋዋል። “የእርግጫን ምርጫ” አይደለም ለ2007

ተሳክቶለት በቀጣዩም 2011 ክፍለ ጊዜ ቢያመጣው ከህሊና መሰረዝ ያስፈጋል።

“የእርግጫ ምርጫ” ለእኛ በዕድ ራዕይ ነውና። እስከ እርግጫ ምርጫው መባቻ

ሆነ እስከ ምርጫው ድንፋታ ስክነት ከዚያም ባለፈ ወደ ነፃነታችን ሊያሸጋግረን

የሚችለው ድልድዩ ተጎሳቅሎ ሊቆይ ይችላል። ይህን ግምት ውስጥ ማስገባት

ይገባናል። … ድሉ ዛሬ ወይንም ነገ ላይሆን መቻሉ የነፃነት ትግል ባህሪ ነው።

ትግል ረጅሙን የጨለማ ጉዞ ተጋፍጦ ነው ብርሃን ማግኘት የሚቻለው …

ተፈጥሮው ይሄው ነው። አታካች – አቅምን ፈታሽ ነው – የነፃነት ትግል።

ትንፋሹ ግን ጠንካራና የማይሞት ነው።

አሁን ባለፈው አመት ሰፊ የማደራጀት የተቃውሞ ተግባራት ሀገር ቤት

ተከውነዋል። እነዛ መልካም ናቸው። ያደጉና የሰለጠኑም ነበሩ። አሁን ደግሞ

ትግሉን ከፍ በማደረግ “ወያኔ በቃህን! ከሥልጣን ውረድ” የሚል መንፈስን

መፍጠር – ማደራጀትና መምራት ያስፈልጋል። ምርጫው የእኛ አይደለም።

ወደፊትም ወያኔ እስከ አለ ድረስ የእኛ ሊሆን ከቶውንም አይችልም። የእኛ

ምርጫን የምንጠብቀው እራሳችን አምጠን በምንወልደው ነፃነት ብቻ ነው።

ነፃነቱን በመንፈሱ የጸነሰ የነፃነት አርበኛ የጊዜው መርዘም ወይንም የሂደቱ

አድካሚነት ወይንም የመንገዱ ኩረታማናት ወይንም የተስፋው ሩቅነት ምኑም

አይደለም። እንዲውም ለነፃነት ትግል የጊዜ መስፈርት ግጥሙ አይደለም።

ስለሆነም ለዘላቂ ፍላጎት ዘላቂ ጽናት በእጅጉ ያስፈልጋል። ጽናቱን ወያኔ

በሰላዮቹ አማካኝነት ብል አስብልቶ ተስፋ ቆራጭነት እንዲነግሥ ሊያደርግ

ይችላል። ቀሪዎቹ ጽናት ያላቸው ሃይላቸውን ለወያኔ ግብር ሳያውሉ በሥልጡን

ስልታማ አመራር ትግላቸውን ቆርጠው መቀጠል ይኖርባቸዋል። ወገኖቼ አንድ

ሰው ብዙ ነው። ይህን አንዲት ጠንካራ ሴት እጅግ ዝቅ ካለ ማህበረሰብ

ተፈጥራ ለተነሳችበት ዓላማ አይደለም ሀገሯን አህጉሩን እንዴት እንደ ፈወሰች

85

ጹሑፉን ስጨርስ አስነብባችኋለሁ። እንኳንስ ከአንድ በላይ ሆነን ….። የነፃነት

ትግሉ ቤተስብ ሲሰበሰብ አዳራሹ ሞላ አልሞላ ጭንቀታችን ሊሆን አይገባም።

ከተሰብሳቢዎቹ በአንዱ መንፈስ ውስጥ ያለው ቅዱስ ሃይል አቅሙ ብሩክ

ሊሆን ይችላል። አድህኖት ሊሆን ይችላል። ብርሃን ሊሆን ይችላል። ስናሸንፍ

ደግሞ አጃቢያችን እልፍ ነው የሚሆነው …

ትግላችን የመምረጥ መብት ሀገር ቤት ብቻ ሳይሆን፤ ውጪ ሀገር ለሚኖሩ

ኢትዮጵውያን በዬሚኖሩበት ሀገር ድምጻችን የመስጠት መብታችን አስኪረጋገጥ

ድረስ መድከም ይኖርብናል። ይህ ሊሆን የሚችለው ግን የጎሳ አስተዳደር

ከነማኒፌስቶው ግብዕተ – መሬቱ በህዝብ ህብረ አመጽ ሲደረመስ ብቻ

ይሆናል። እንችላለን! ከቆረጥን! አሁንም እንደ ገና ሃይላችን አቅማችን ገንብተን

ከብረት ቁርጥራጭ በተሰራ ዬመንፈሰ ጥንካሬ ትግላችን ከመራነው ነገን

እናበራለን …. እኛም እንበራለን – በመሬታችን ላይ።

የማከብራችሁ ደሞቼ የሀገሬ ልጆች የነፃነት ትግሉን ፍላጎት እናሳድገው። ወያኔን

ተወዳድሮ በምርጫ ማሸነፍ እንደማይሆን እናውቀዋለን። ከጎሳ ሥርዓት

ተፈጥሮ ስንነሳ የምናገኘው አምክንዮ ይሄው ነውና። ነገር ግን ወያኔን ከሥሩ

ለመንቀል የምንሰራቸው የመንፈስ ሥራዎች በራሳቸው ለድል ያበቁናል። የወያኔ

ሥርዓት እሾኃማ ብቻ ሳይሆን ለትውልዱ መርዛማ ነው። ስለሆነም መወገድ

አለበት። ሰሞኑን ዛሬም ባዬሁት ሪፖርት በትንታጎቹ በነአቶ ሃብታሙ አያሌው

ክስና በውዴ በአብርሽ የክስ ጭብጥን በሚመለከት እንዴት አድርጎ እንደ

በለተው አይታችኋል። ውዴን አብርሽን ወደ ማነው ጠጋ ያደረገው ወደ

ደምሂት አያችሁት ይህን ፍልስፍና … እባካችሁ የኔዎቹ ጊዜ ወስዳችሁ

መርምሩት። … በኛ መንፈስ እንዴት ቢላዋውን አስልቶ ሽንሸና ለመፈጸም እንደ

ተሰናዳ። እንዲህ ነው ሃሳባችነን ህሊናችንን ወላዊ ጥንካሪያችን ስንጥቅጥቅ

የሚያደርገው። ስለዚህ ወያኔ ለኢትዮጵያዊነት ህልውና አጥፊ ዘር ነውና

መወገድ አለበት። ወያኔ አረማሞ ዘር * ነው።

እርገት ይሁን – አንድን ነገር ማብሰል ያለብን ይመስለኛል። ይሄ “ወያኔ

አልቆላታል፤ ባዶ ቀርቷል” በማለት የምናቃልለው ነገር መቆም ያለበት

ይመስለኛል። ጠላትን ማቃለል የተገባ አይደለም። ባቃለልነው ቁጥር ሃይላችን

ይሰንፋል። ጉልበታችን ይዝላል። ለነፃነት ትግሉ ልንሰጥ ያሰብነው ጉልበትም

በተቀናሽ እሳቤ ይሆናል። ወገኖቼ – የኔዎቹ ወያኔ ሥልጣን ላይ ያለ፣ በተሟላ

ሎጅክስቲክ የተደገፈ፤ በውጭ ሃይሎች ሙሉ ድጋፍ የሚደረግለት መሆኑን

መዘንጋት የለብንም። ከዚህም በላይ የጎጥ ድርጅት መሆኑ ደግሞ ሌላው

86

ስብጥር ዕዳ ነው። …. ጎጡ በጋብቻ – በዝምድና – የተሳሰረ ነው። ስለዚህ

ይሄን ጥሶ ለመውጣት የነፃነት ትግሉ የበለጠ ሃይልና ጥንካሬ ይጠይቀዋል።

ጊዜም። የፍላጎታችን መዳረሻ መዝግዬትም ምክንያቱ ይሄው ነው። ስለሆነም

ሳያጋኑ ወይንም ሳያንኳስሱ …. ሚዛኑን በጠበቀ …. ግንዛቤ መጓዙ ጠቃሚ

ይመስለኛል።

የምርጫ ሽር ጉድ በ2007ቷ በሚካሄደው ፓርላሜንታዊ ምርጫ መቅረብና

መወሰን ያለበት አንድ ጥያቄ ይህ ነው፣ የኢትዮጵያ ህዝቦች አሁን እንደ

ኤሮፓውያን አቆጣጠር 2014 ያሉበት የኑሮ ሁኔታ ከቀድሞ 200 ወይም 2005

ከንበሩበት የኑሮ ሁኔታ ይሻላል ወይ´ß ህዝቦች ካለፉት አመታት በተሻለ ሁኔታ

ላይ የማይገኙ ከሆነ እንደ አሮጌ ሸማ ናቸው። በየጊዜው ካልታጠቡና

ካልተለወጡ ይበሰብሳሉ ይገማሉም። በጣም የሚገርም ነገር ነው ምስኪን

ኢትዮጵያውያን አንድ የበሰበሰ የገማ ሸማ ለሌላ 5 ዓመታት በጠቅላላው

ለ25ዓመታት ስትለብስ አያሳዝንም በቅርቡ ያረፉት የአቶ መለስ ዜናዊ ፓርቲ

የሆነው ኢህአዲግ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር 96.6

በመቶ ድምጽ በማምጣት ድልን ተቀዳጀሁ ያለበትን እርባና የለሽ ንግ ግር

በመተቸት የተሰማኝን ሃዘን ገልጨ ነበር። የእራስ በእራስ የእንኩኣን ደስ ያላችሁ

ንግ ግራቸው አቶ መለስ ያንን አስደንጋጭ የምርጫ ውጤት ይህ የኢህአዲግ

87

የጥረት ውጤት በአገራችን ላሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የማያሻማ መልእክት

አስተላልፉኣል በማለት ዲስኩራቸውን አሰምተዋል። በዚያ ንግ ግራቸው

በኢትዮጵያ በግልፅ ተመዝግበው የሚገኙት 79 የፖለቲካ ፓርቲዎች በጥቅሉ

የአንድ ከመቶን ሩብ ቁራጭ እንኩኣን የማይሞላ ድምፅ ማግኘት ያልቻሉትን

የይስሙላ ፓርቲዎች ነው።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን ምርጫውን

ተዘዋውሮ ከተመለከተ በኃላ የምርጫ ውጤት እርባና የለሽነት እና ኢታማኒነት

በማስመልከት በወቅቱ እንዲህ የሚል መልእክት አስተላልፉኣል የምርጫ ሂደቱ

አለም አቀፍ ሂደት መስፈርትን አያሙኣላም በተለይም የምርጫ ሂደቱ ግልጽነት

እና ለሁሉም የተቃዋሚ ፓርቲዎች እኩል የሆነ የፖለቲካ ጨዋታ ምህዳር

የለውም። የቀድሞው የቦት ስዋና ፕሬዝዳንት ከነበሩት ኬቱሚሌ ማሲሬ

የሚመራው 20 አባላትን ያካተተው የአፍሪካ ህብረትየምርጫ ታዛቢዎች ቡድን

ምርጫውን ተዘዋውሮ ከተመለከተ በሁዋላ ሃፍረት ሳያሳዩ አይን አውጥተው

እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፎ ነበር ምርጫው ነፃ እና ፍትሀዊ ነበር።

የታዛቢ ቡድኑ አባላት ገዥው ፓርቲ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን ያስፈራራበትና

እና ያሸማቀቀበት ወይም ደግሞ የመንግስትን ንብረት በህገ ወጥ መልክ ለገዥው

ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ስኬታማነት የተጠቀመ መሆኑን የሚያረጋግጥ

ምንም አይነት ማስረጃ አላገኘንም። የሚል የሸፍጥ የታዛቢነት ተልዕኮውን

አከናውኑኣል። እንደዚሁም ደግሞ የአሜሪካው መንግስት ዋይት ሃውስ እንዲህ

በማለት ዬዞ እንባውን አንብቱኣል፣ ዬለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን

በኢትዮጵያ ስለተካሄደው የ ፳፲ ምርጫ ባቀረበው ዘገባ መሰርት ምርጫው

አለም አቀፍ መስፈርትን የማያሟላ በመሆኑ አሜሪካ ያላትን ስጋት ትገልፃለች

በማለት የይስሙላ ዲስኩሩን ለማሰማት ሞክሩኣል። ሆኖም ኢትዮጵያ ብአሁኑ

ጊዜ የገማ ሸማዋን እንደለበሰች ቁጭ ብላለች።

ዬለፉት ምርጫዎች የሙት መንፈሶች በተካሄደው ምርጫ አቶ መለስ ዜናዊ

፱፮ß፮ በመቶ ድምጽ በማግኘት ድልን ለመቀዳጀት በማሰብ የራሳቸውን መንገድ

በመከተል ፓርቲያቸው እንዲመረጥ በሃይል አስገድደዋል፣ ጉቦ ሰጥተዋል፣

አስፈራርተዋል እንዲሁም መራጩ ህዝብ በፍርሃት ቆፈን ውስጥ ተወሽቆ

የመምረጥ መብቱን በአግባብ እንዳይጠቀም አድርገዋል። ከገጠሩ ህዝብ ድምጽ

ለመሸመት እና በግዳጅ ድምጽ ለማግኘት በሚል ሰይጣናዊ ስልት የውጭ

የሰበዊ መብቶችን እና የኢኮኖሚ እርዳታዎችን ከታለመላቸው ዓላማ ውጭ

በማጠፍ ለእኩይ የምርጫ አላማቸው ማስፈፀሚያ እንዲውሉ አድርገዋል።

88

የወጣቱን ታማኝነት ለመግዛት በማሰብ ለየለቄታው የሚያቆዩ እና ለሃገሪቱ ሆነ

ለወጣቶቹ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን የሚያስገኙ ስራዎችን ሳይሆን ለጊዜው ብቻ

ከርስን ለመሙላት የሚያገለግሉ ተራ ስራዎችን ለማደን ተፍጨርጭሩኣል።

የመንግስት ሃብቶችን እና ንብረቶችን ለእራሳጨው ፓርቲ ድጋፍ ማሰባሰቢያ

ዘመቻ እንዲውሉ አድርገዋል። የእራሳቸውን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለመለየትና

ለማኮላሸት ሰፊ የቁጥጥር ፕሮግራሞች የስለላ እና የመረጃ አቀባይ መረቦችን

የመዘርጋት ስራዎችን አደራጅተዋል።

በቀላል አነጋገር ሲገለፅ የኢህአዲግም የምርጫ ማሸነፍ ዕቅድ አሮጌውን የፍራቻ እና የጥላቻ ስልት በተግባር ላይ ማዋል ነው። ስልጣናቸውን ለመጠበቅ አማራዎችን ማስፈራራት ከችሉና ኦሮሞዎችን በታላቅ ፍርሃት ውስጥ መወሸቅ ከቻሉ ምርጫውን አሸንፈው በስልጣን ላይ ይቆያሉ። ኦሮሞዎች አማሮችን እንዲጠሉ ማድረግ ከቻሉ ምርጫውን አሸንፈው በስልጣን ላይ ይቆያሉ። የኦሮሞዎችን አእምሮ በታሪች ፀፀት ንትርክ ውስጥ በመዝፈቅ በደርዘኖች የሚቆጠሩ ንፁሃን የዩንቨርስቲ ተማሪዎችን እልቂት እንዲረሱ ማድረግ ከቻሉ ምርጫውን አሸንፈው በስልጣን ላይ ይቆያሉ። የክርስቲያኑና የሙስሊሙም ማህበረሰብ በፍርሃት በጥላቻና እያንዳንዳቸው እርስ በእርስ እንዳይተማመኑ ማድረግ ከቻሉ ምርጫውን አሸንፈው በስልጣን ላይ ይቆያሉ። የእነርሱ ሃብታም ደጋፊዎችን ኢህአዲግ የማይኖር ከሆነ በእርግጠኝነት ሃብቶቻቸውን እንደሚያጡ እና ወደ እስር ቤት ዘብጥያ እንደሚጣሉ ወይም ደግሞ ወደ ግዞት እንደሚወርዱ በማስፈራራት ማሳመን ከቻሉ ምርጫውን አሸንፈው በስልጣን ላይ ይቆያሉ። ኢህአዲግ አበዳሪ ድርጅቶቹን እና ለጋሽ ድርጅቶቹን ኢህአዲግ በስልጣን ላይ የማይኖር ከሆነ በኢትዮጵያ ሰማይና ምድር ይገለባበጣል፣ ብሄራዊ ጥቅሞቻቸውም ይቀራሉ በማለት ለማሳመን ለማታለል ከቻሉ ምርጫውን አሸንፈው በስልጣን ላይ ይቆያሉ።

በቅርቡ በሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ኢህአዲግ የሚያሸንፍ ወይም የማያሸንፍ መሆኑን መጠየቅ ፀሃይ ከጠለቀች በሁአላ ጨለማ ምድር ላይ ይስፍናል ወይ እንደማለት ያህል ነው። የምርጫ ዘረፋ ወንጀል የጨዋታ ደራሲነት አቶ መለስ መስርተውታል። የእርሳቸው ቀሪ ሎሌዎች በአሁኑ ጊዜ ሃላፊነቱን ተረክበዋል። የወባ ትንኝ ተመራማሪውና በብርሃን ፍጥነት ወደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት የተሾሙት እንዲሁም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በዚሁ የስልጣን እርከን ይኒቆዩት የቴዎድሮስ አድሃኖም ቀጣይ የጠቅላይ ሚንስትርነት ወንበር በማሞቅ ላይ የሚገኙት የይስሙላ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ እርሳቸውና

89

ባልደረቦቻቸው የሚያከናውኑአቸው ተግባራት በሙሉ በአቶ መለስ ዜናዊ ራዕይ የሚመሩ ጭፍን ናቸው በማለት ሌት ከቀን እንደ በቀቀን ደጋግመው ይናገራሉ። የአቶ መልስ ዕራእይ ምርጫውን ምርጫውን መቶ በመቶ ማሸነፍ ነበር። ያንን ራዕይ ሙሉ ለሙለ በማሸነፍ ለማሳካት የአንድ በመቶ አራት አስረኛ ብቻ ቀርተዋለች።

አቶ ኃይለማሪያም እና ጏዶቻቸው በኣሁኑ ጊዜ ከትልቅ ፈተና ውስጥ ወድቀው ይገኛሉ። የሚካሄደውን ምርጫ ቢያንስ ሃምሳ በመቶ በማሸነፍ የአቶ መለስ ባለዳነታቸው ማረጋገጥ አለባቸው። የምርጫ ማሸነፊያ ነጥብ ወሰናቸው ከወርቃማው ፱፱፣፮ በመቶ ካነሰ በጣም አሳፋሪ ሁኔታ ነው የሚፈጥረው። ቢያንስ መቶ በመቶ በማሸነፍና አቶ መለስ በኩራት ሲታወሱ እንዲኖሩ ለማድረግ አቶ ኃይለማሪያም እና ጏዶቻቸው በ፪፲፻ ለገበሬው ከሰጡት ማዳበሪያ በላይ መለገስ አለባቸው። የገጠር ደሃ ቤተሰቦችን ድምፅ ለመግዛት ለምርታማነት ደህንነት መረብ የከፈለውን ክፍያ ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ ኣለባቸው። እንደዚሁም ወጣቶችን ለማታለልና ታማኝነታቸውን በማረጋገጥ ድምፃቸውን ለማግኘት እንዲቻል የማይክሮ ፋይናንስ ብድር መስጠት አስፈላጊ ነው ከዚህም በተጨማሪ ለከተማ ነዋሪዎች ኮንደሚንየሞችን ለመስጠት ብዙ የባዶ ቃልኪዳን ተስፋዎችን መስጠት አስፈላጊ ይሆንባቸዋል።

በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ኢህአዲግ እራቁት ገላ ካገኘች የወባ ትንኝ ስራ የበለጠ ስራ ጥድፊዛ ኣለባቸው። በጥቃቄ በብልሃትና ቀስ በቀስ በርካታ የጎሳ ቡድኖችን እርስ በእርስ በማጋጨት እና በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ደግሞ ድምጽ ለመግዛት በመርጨት የታኢምዘዕ ዕቅድ ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው። ቀደም ሲል ስኬታማ የሆኑበትን የከፋፍለህ ግዛ ስልት አጠናክረው ይቀጥሉበታል። ለሩብ ምዕተ አመት የጎላ ጥላቻ እሳት ላይ ነዳጅ በመጨመር ላይ ይገኛሉ። ከሳምንት ገደማ በፊት ቢቢሲ በኢትዮዽያ ያለው ገዥ አካል ከመናገሻ ከተማዋ በስተምዕራብ በኩል በ፹ ማይሎች ርቀት ላይ በምትገኘው አምቦ ከተማ ፬፯ የዩንቨርስቲ ተማሪዎችን መግደሉን መዘገቡን ልብ ይሉአል። በክርስትና እና በእስልምና እምነቶች ተከታዮች መካከል የጥላቻ ነዳጅ ለማርከፍከፍ በጣም አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን ይህንን ዕኩይ ምግባር ከመፈፀም አይቦዝኑም። በቆሻሻ እና እርባና የለሽ ማታለሎች የተካኑ ናቸው። የሃገር ውስጥ ገንዘብ አዳዮቻቸው ማለትም ኢኮኖሚውን አንቀው የያዙት የሙስና መጋቢ ወፍራም ዝሆን ደጋፊዎች እገዛ ለማድረግ በማዘጋጀት ወደ እነርሱ ይጎርፋሉ። ከዚህም በላይ ከታኢምዘዕ ጠባቂዎች ጋር አንድ ዓይነት ዕጣፈንታን

90

ይጋራሉ። በተፈጥሮ አበዳሪና ለጋሽ ድርጅቶች እዚህም እዚያም በመርገጥ በመንተባተብ ስለነፃና ፍትሀዊ ምርጫ ለምንም የማይውሉ የይስሙላ ቃላትን ያዥጎደጉዳሉ። እናም የሚሰጡትን የውጪ እርዳታ እና ብድር ከህግ አግባብና ከታቀደለት አላማ ውጭ ለፓርቲ ፖለቲካ ጥቅም ሲያውሉት አይተው እንዳላዩ በመሆን ጆሮ ዳባ ልበስ ይላሉ። ለመሆኑ ተቃዋሚዎችስ ምን እያደረጉ ነው፣ የምን ተቃዋሚ፣ የገዢው አካል ዘዋሪዎች ተቃዋሚዎችን ከመናቅ የዘለለ ምንም ነገር የላቸውም። በተደጋጋሚ እንደምናገረው አቶ መለስና አጫፋሪዎቻቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የእነርሱ የምሁርነት የበታች እንደሆኑ አድርገው ይቆጥራሉ። በአሁኑ ጊዜ የኦባማ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ የሆኑት ሱሳን ራይስ እንዳረጋገጡት አቶ መለስ የሚቃወሙአቸውን ሁሉ የማይረቡና ደደቦች ናቸው ብለው ያምኑ ነበር። አቶ መለስ ለህዝብ ይፋ መግለጫ በሚሰጡበት ጊዜ ከሌሎች የበለጡ መስለው ለመታየት፣ ከለሎች የበለጠ የሚያስቡ በመምሰል ከሌሎች የበለጠ ጥቅም የሚያሳድዱ መሆናቸውን፣ ከሌሎች የበለጠ ተጫዋች ለመምሰል፣ በማታለል ከሌሎች በልጦ ለመታየት መሞከርና ተቀናቃኞቻቸውን ስልታዊ በሆነ መንገድ በማንኛውም ቀን መትተው መጣል የሚችሉ መሆናቸውን ግልፅ አድርገዋል፣ ችለዋልም። የአቶ መልስ ደቀ መዛሙርት በኣሁኑ ጊዜ በጌታቸው ኣስተምህሮና ራዕይ ይመራሉ። እንደርሳቸው ሁሉ እነዚህ ደቀመዛሙሮችም ተቃዋሚ ሃይሎች ለመስራት የተኮላሹ ተነሳሽነት የሌላጨው ለምንም የማይጠቅሙና ለዕነርሱ ስልጣን ምንም አይነት የስጋት ምንጭ ሊሆኑ እንደማይችሉ እምነት አላቸው። የዕነርሱን የስልጣን ተቀናቃኝ ብዙ ክትትል ስነስረአትና ቅጣት እንደሚያስፈልጋቸው ወጣት አጥፊዎች በመቁጠር በአንድ መስመር ላይ ለማሰለፍ ይሞክራሉ። እንደ ልጆች ሁሉ ለአንዳንዶች ከረሜላ ስራ፣ መኪኖች፣ ቤቶችና ሌሎችምለእነርሱ ድጋፍ ሊያሰጡ የሚያስችሉ ባይሆኑም አፍ የሚያሲዙ ወይም ደግሞ ማቋረጫ በሌለው መልኩ ክትትል እና የማሸማቀቅ ስራ ይፈፅምባቸዋል። እውነታው ሲመረምር ግን በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት የኢትዮዽያ ተቃዋሚ ኃይሎች እና በውጭ ያለው የዲያስፖራው ማህበረሰብ በሚያስቸግር ሁኔታ ተከፋፍሉኣል። ጥቂት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በሃገሪቱ ከተደቀነው አደጋ ይልቅ የእነርሱ ስልጣን ያሳሰባቸው ለጋራ መድረክ የሚያገለግል በመተባበር የጋራ የሆነውን ጠላት ተባብሮ ለምጣል ቅን የሆነ ተነሳሽነቱና ፍላጎቱ የላቸውም። የተቃዋሚው ህብረተሰብ ኢህአዲግን ያልተገደበ የገንዘብ ምንጭ ጫና ለመቁኣቋም የሚያስችል የገንዘብ የሃብት እጥረት ይታይባቸዋል። ተቃዋሚ ጋዜጠኞች ይታሰራሉ ማስፈራራትም ይደረግባቸዋል። ወጣት ጦማረኞች እንኩኣ በማዝረባ ሽብርተኝነት ስም ለእስርና ለስቃይ ይዳረጋሉ። የሲቪል ማህበረሰብ የለም፣ በከተማ የተደራጀ ማንኛውም ዓይንት የተቃውሞ ምልክት ለማስወገድ

91

በማስብ ገዥው አካል በልማት ስም ከቀያቸው ያፈናቅላል። ነገሮች ገፍትው ከመጡ የአቶ መለስ ሎሌዎች የአለቃቸውን መሪ ዕቅድ ተግባራዊ ከማድረግ አይመለሱም። አቶ መለስ በአንድ ወቅት ለአንድ የአሜሪካ ዲፕሎማት ሰው እንዲህ ሲሉ ተናግረው ነበር፣ ተቃዋሚዎችን ባለን ኃይል ሁሉ እንደመሻቸዋለን። ህውሃት ወይም ኢህአዲግ ምርጫውን በመግፋት ወይም በመደቆስ ያሸንፋል።

ትልቁ ታዋቂ የሚታወቅ የማይታወቅ ሁሉን ድል አርገን እንቀመጣለን ብለው ነበር።

የዩናይትድ ስቴጽ አሜሪካ የቀድሞው የመክላከያ ፀሃፊ የነበሩት ዶናልድ ሩምፈልድ አንዳንድ ጊዜ የዕንቆቅልሽ የሚያደናብር ንግ ግር ማድረግ ይወዳሉ።

እንዲህም ብለዋል የምናውቃቸው ነገሮች አሉ፣ እኛ እራሳችን ታዋቂ የማይታወቁ እንዳሉ እናውቃለን። ይህም ማለት የምናውቃቸው የማናውቃቸው ጥቂት ነገሮች አሉ። ሆኖም ግን የማናውቃቸው ነገሮች አሉ። አንዳንድ የማናውቃቸው ነገሮች የማናውቃቸው ናቸው።

አቶ መለስ በኢህአዲግ እራሳቸው ብቻቸውን ነበር ኢህአዲግን የመሰረቱት። የኢህአዲግ ውስጥ አእምሮም ጡንቻም ነበሩ። ዋናው ነገር ብቻ አልነበሩም ውና የስልት ነዳፊ፣ ዋና አዛዥም ነበሩ። ሁሉም የአቶ መለስ ሎሌዎች የጭንቅላት አቅም ተደምሮ የርሳቸውን ጭንቅላት አራት አስረኛ አይሆንም። በአሁኑ ጊዜ በኢህአዲግ ውስጥ አቶ መለስን ሊተካ የሚችል አንድም ሰው እንደሌለ የታወቀ የምይታወቅ ነው። የኢትዮዽያ የይስሙላ ጠቅላይ ሚንስቴር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የአቶ መለስን ጫማ ሊሞሉ እንደማይችሉ በአንድ ወቅት ተናገረዋል። ትክክል ናቸው። በኢህአዲግ ውስጥ ማንም አይችልም።

ወዴት ነው ጎተራው ? ሀገር በብረት ሲታጠር — ‘ግንቦት ሃያህ’ ሲከበር፤

አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር — ዘመን በዘመን ሲቀየር፤

የስራ-ፈቶች ስብስብ መንጋ — ‘ፓርላማህ‘ሲከፈት ሲዘጋ..፤

92

ሱፍህን ገጥግጠህ — ከረባትህን ጠፍረህ፣

ወዝህን አሳምረህ — ካሜራ ፊት ቀርበህ፣

ጉሮሮህን..ጠርገህ — ፊትህ የከመርከውን ‘ሃያ ገጽ’ ገልብጠህ፣

ቁጥር እየቆጠርክ፣ አሃዝ እየጠራህ...፣

“ምናምን..ሺ.ቶን፣ ሚሊዮን ስልቻ፣

አምርተን አስገባን በዚህ ዓመት ብቻ...”፣

እያልክ ስትደሰኩር — ትንፋሽህ እስኪያጥር፣

ሰምቼህ ሳበቃ፣ የግርምት ጥያቄ እስኪማ ልሰንዝር፤

በልበ-ሙሉነት “ጠግብን በላን” ያልከው፣

ሕዝቡን ቆጥረህ ይሆን? ወይስ የቤትህን ያንተኑ ግሳት ነው?!

ስርህ ተግተርትሮ፣ ላብ እያሰመጠህ፣

ያቀረብከው ‘ሪፖርት‘ እንዲያ ተውረግርገህ፣

የራስህን በጀት፣ የጓዳህን ወሬ፣

ወይስ የምስኪኗን ኢትዮጵያ ሀገሬ?

እኮ ታዲያ የታል? የተትረፈረፈው፣

የእህል ዘር፣ የእህል ምርት..የት የተከተተው?

እባክህ ንገረን ጎተራው ወዴት ነው?!

እንደልቡ አፍሶ ሕዝብ የሚጠግብበት፣

93

የተትረፈረፈው...የተከማቸበት፣

ንጉስ አብዱላህ አገር ከሳዑዲ አረቢያ?

ከ’ካራቱሪ’ አገር ወይስ ከኢንዲያ?

ወይስ ከ’ሸራተን’ ከ’ሚድሮክ’ መጋዘን?

የት ይሆን ጎተራው? በነካካ አፍህ ጨክነህ ብትነግረን¡

አገር ያለውማ ሕዝቡን እሚያከብር፣

የራሱ አልበቃው ሲል ለመጥገብ ሲቸገር፣

ከሞኝ ደጃፍ ወርዶ፣ ሸጋ ሞፈር ቆርጦ፣

ባላድ፣ በስሙኒ..ጋሻ መሬት ገዝቶ፣

ያገር ደን መንጥሮ — የሰው-ሰው አባሮ፣

መሬት አለስልሶ፣ ውሃ ቦዩን ጠልፎ፣

ቀለቡን ይሰፍራል፤ ምርቱን አትረፍርፎ፤

እሱ ነው እሚያምርበት!

አደባይ ቆሞ ለሕዝብ ቢያቀርብ ‘ሪፖርት’።

እንጂማ አንተማ፣ ክፋት-ምቀኝነት...

መቅኔህ ድረስ ዘልቆ፣ አጥንትህን ቦርቡሮ፣

መላ ሰውነትህ በጥላቻ-በእልህ..በቅንቅን ተወሮ፣

በዚያቹ በምስኪን ባዶ ጎጆው ቀንተህ፣

94

ያያት-ቅድማያቱን ርስት ቀዬ ነጥቀህ፣

በባዶ አንጀቱ በጥይት ቀጥቅጠህ፣

አገርህን ንቀህ፣ ወገንህን ጠልተህ፣

በ’ፌደራል ፖሊስ‘ ለባዕድ ዘብ ቆመህ..፣

ካሜራ ፊት ቀርበህ አረፋ እየደፈቅህ፣ “ጠግበን በላን” ያልከው፣

ምጸት ነው! ምጸት ነው! ለምስኪን ያገር ልጅ ሁለተኛ ሞት ነው!!

ወገኔ ተነስ ! እምቢልታ አሰነፍቶ፤ ነጋሪት ጎሽሞ፤

አዋጅ አስለፍፎ በአደባባ ቆሞ፤

የሚያሰባስብህ፤ የሚያስተባብርህ፤

ሞትን በራሱ ሞት ባርኮ የሚሰጥህ፤

እነደ አጼ ዮሐንስ፤እንደ አቡነ ጴጥሮስ፤

ዛሬ የለም ምኒልክ፤ ወይም ቴዎድሮስ።

እንደ ራስ አበበ፤ እንደ አብዲሳ አጋ፤

እንደራስ ጎበና፤ አሉላ አባነጋ፤

ኃይለምርያም ማሞ፤ ደጃዝማች ገረሱ፤

እነኮስትር በላይ እነ ጥይት ኳሱ፤

አልፈዋል ጀግኖቹ ታሪክ ላገር ሠርተው፤

95

ኢትዮጵያን አገርክን ላንተ አደራ ትተው።

ዛሬ አገርህ ታማ በጣር ተይዛለች፤

“ልጆቼ ድረሱ!” ብላ ትጮሃለች።

ኧረ ጎበዝ ተነስ ስማ የናት ጩኸት!

ባጭር ታጠቅና ፈጥነህ ድረስላት።

“ደረስኩልሽ !” በላት “አይዞች እናቴ”

“ማን አንቺን ይደፍራል ሳለሁ በሕይወቴ”

“ክንዴን ሳልተራስ ሳይሰማ ሞቴ”

“አለሁልሽ!” ብለህ ንገራት ለናትህ፤

አነትም ደስ ይበልህ ኩራ ባንተነትህ።

አዋጅ አትጠብቅ ማንም አይጠራህም፤

ግዳጁ ያንተ ነው ማንም አያዝህም።

አደፍርሰውና ይጥራ ተበውጥብጦ፤

ያበጠው ይፈንዳ ከሚያስጨንቅ አብጦ።

ስንዴው ከእንክርዳዱ፤ ይለይ ምርት ከግርዱ፤

የነ “ማን አለብን እስኪ ይታይ ጉዱ።

እኔ ግን በቅቶኛል ዛሬ ቆርጫለሁ፤

ጠላቴን ባለበት እፋለማዋለሁ።

ምንም አቅም ቢያንሰኝ ቢደክም ጉልበቴ፤

96

ጠላቱን ይወጋል እሾህ ሆኖ አጥንቴ።

እናውቅበታለን ማነጣጠሩን፤

ግንባር መሰንጠቁን፤ ቅልጥም መስበሩን።

እንደ አባቶቻችን ባደዋ፤ በማይጮው፤

ገድለው እንደሞቱት ለሕያው ስማቸው፤

እኛም እንሰዋ ለናት አገራች፤

ለአረንጓዴ፤ ቢጫ፤ ለቀይ ሰንደቃችን።

ወገን አይራብም፤ አይጠማም ውሃ፤

አገሩ ተቀምጦ አይባልም ድሃ።

የመከራ እንቆቆ ስቃይ እየጋቱ፤

ቀን ሲጨልምበት ሲበዛ እንግልቱ፤

ናላውን አዙረው እንዲቆርጥ ተስፋ፤

ከፍቶት ተመርሮ ካገሩ እንዲጠፋ።

በወባ ፤በንዳድ፤ በጊንጥ ተነድፎ፤

በጂኒ፤ በአጋንንት ፤በሽታ ተለክፎ፤

አይቀርም ወገኔ እንደጤዛ እረግፎ።

ይብቃው ለወገኔ ስደት መንከራተት፤

በዱር፤ በገደሉ መሆኑ ያውሬ እራት።

ያሰናባሪ አሣ ፤ያዞና ያርጃኖ፤

97

ቀን ያሞራ ምሳ፤ የጅብ እራት ሆኖ፤

ይብቃው ለወገኔ የሞት ሞት መሞቱ፤

ይኑር በናቱ አገር ታቆ ማንነቱ።

ከንግዲህ ኢትዮጵያ አትበዘበዝም፤

ወያኔና ባንዳ አይነግዱባትም።

አፈር ባፍንጫዬ ሳይንቆረቆር፤

ክንዴን ሳልተራስ ፤ ሳሉል መቃብር፤

ቃል ለምድር ለሰማይ ቃሌን አላጥርፈውም፤

በሕይወቴ እያለሁ ጠላቴ አይደላውም።

ውድ ታጋይ ወገኖቼ ፤ በሃይማኖት ተከታዮች በኩል የሚደርሰው በደል፣ በትውልድ ሐረጋቸው የተነሳ የሚደርስባቸው በደል፣ በተሰማሩበት የንግድ መስክ የተነሳ የሚደርስባቸው በደል፣ በመኖሪያ አካባቢያቸው፣ ለንግድ ተብሎ ከቦታቸው በሚፈናቀሉት ላይ የሚደርሰው በደል፣ በተማሪዎች፣ በአስተማሪዎች፣ በወታደሮች፣ ሁሉም በኢትዮጵያዊነታቸው በደል እየደረሰ ነው። ይህ ሁሉ ኢትዮጵያዊያንን በተለያየ መንገድ ለትግል አነሳስቷል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታገሉ አሉ። ከሀገር ውጪ ባለነው ኢትዮጵያዊያን መካከል የምንታገል አለን። ይህ ለድል የሚበቃው፤ ይህ ሁሉ ኢትዮጵያዊ በሙሉ በአንድነት ተሰባስቦ ሲነሳ ነው። ይሄን ሁሉ ለማስተባበርና ባንድ ለማሰለፍ፤ በአንድነት ተሰባስበን መታገሉ ግዴታችን በምኞት የምንጋልበው ፈረስ፤ ከፈለግነው ቦታ በፍጥነት የሚያደርሰን፤ በምኞት ዓለም ውስጥ ብቻ ነው። እኛ አሁን በአንድነት ያጋጠመን የምኞት ችግር ሳይሆን፤ የሀገራችን ተጨባጭ ሀቅ ነው። ይህ ደግሞ ተጨባጭ መፍትሔ ይጠይቃል። ሀቁን ተረድተን፣ ማድረግ ያለብንን ለይተን፣ ከትናንት ዛሬ፤ ከዛሬ ደግሞ ነገ የተሻለ ግስጋሴ የምናደርግበት ትግል እንዲሆን መጣር አለብን። በተናጠል

98

በግለሰብና በየራሱ ድርጅት ለየብቻ የሚደረገው ትግል፤ ግስጋሴው አመርቂ እንዳልሆነ ተረድተናል። ስለዚህ አንድ የኢትዮጵያዊያን የነፃነት ንቅናቄ መሥርተን፤ ባንድነት መታገል አለብን። ይህ ጥሪ፤ ብዙ የትግል ልምድ ላካበቱትና ለአዲስ ታጋዮች፣ ከፍተኛ ትምህርት ላላቸውና የመማር ዕድሉ ላላጋጠማቸው፣ የላቀ ወታደራዊ ሹመት ላላቸውና ውትድርና ላልቀመሱት፣ ለሁሉም

“ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ እኔም ያገባኛል!” ለሚሉ ግለሰቦችና በድርጅት የተሰባሰቡ ኢትዮጵያዊያን ነው። የሌሎች ቆርጦ አለመነሳት ራሳቸውን እንዲያገሉ ላደረጋቸው፣ በትግሉ መጓተት ተስፋቸው ለመነመነ፣ የኛን ፖለቲካ ጠልተው ዓይኖቻቸውን ለጊዜው ለጨፈኑ ኢትዮጵያዊያንም ጭምር ነው። በርግጥ

መሰባሰብ ቀናና ቀላል ጉዳይ አይደለም። “ማን ጠራው?” እና “መቼና የት

ተጠራ?” የሚሉት ከጥሪው የበለጠ ትክረት ባገኙበት ወቅት፣ ጥሪ ትርጉሙ የጎንዮሽ በተጣለበት ወቅት፤ ተቀባይነት የሚያገኝ ጥሪ ማስተላለፍ ቀላል አይደለም። ሆኖም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሀቅ ከመቼውም በላይ አጣብቂኝ ውስጥ የገባ በመሆኑ፤ የማይቻል የሚባለውን ሁሉ ለማስቻል፤ ጊዜ የምንሻማው ሆኖ፤ ሁሉንም እንድናደርግ ግድ ብሎናል። ይህ የቅንጦት ምርጫችን አይደለም። መሯሯጫ ሰዓት ላይ ነው ያለነው። ስለዚህ፤ የመሰባሰብ ሂደታችንን ከመቼውም ባፈጠነ መንገድ ማራመዱ ግድ ሆኗል። ተግባራዊ ሆነን እስካልተገኘን ድረስ፤ ጊዜ ራሱ መፍትሔ ይዞ የሚመጣበት መንገድ የለውም።

ውድ ታጋይ ኢትዮጵያዊ፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በስደት፤ የሀገራችን ሁኔታ በያለንበት ሁላችንንም የአእምሮ ዕረፍት ነስቶናል። እስከዛሬ በግልዎ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት መስዋዕትነት እየከፈሉ ሲታገሉ ነበር። የሀገራችን የፖለቲካ ሀቅም የትግሉን መቀጠል ያለጥርጥር ግድ ይለዋልና፤ አሁንም ትግልዎ ተገቢ ነው። መታገል ግን፤ ከግብ መድረሻ እንጂ ራሱ ግብ አይደለም ትግሉ የኢትዮጵያዊያን በሙሉ በመሆኑ፤

በታጋዮቹ በሁላችን፤ በግለሰብ ባለነውም ሆነ በድርጅት በተሰባሰቡት መካከል ያለውን፤ የምናልመውን የጋራ ግብ በማውጣት፤ በአንድነት የምንሠራበትን

መንገድ ምርጫ የሌለበት ግዴታ ከፊታችን ላይ ተጋርጧልና፤ አቤት! አለሁ! በማለት በመደጋገፍ ሀገር አድን የሆነ ትግል እንድናደርግ ይህ ጊዜ የሚሠጥ ጉዳይ አይደለም። ግዴታችን ነው። እንዴት ይጀመራል እና ማን ይጀምረው በሚል ጥያቄ መጓተቱ ይቅር አብረን ጀማሪዎች እንሆናለን። ኢትዮጵያዊ ግዴታችንንም እንወጣለን። ለወገንና ለሀገር እንደርሳለን። የታወቀ ነው፤ መሰባሰብ ቀላል ጉዳይ

99

አይደለም። የሚቻልና ቀላል ቢሆን ኖሮማ፤ ካሁን በፊት ይተገበር ነበር። አልተደረገም። አይደረግም ማለት ግን አይደለም። የአሁኑ የማይቻል የተባለ ቀውጢ ሰዓት የሚጠይቀው ደግሞ፤ የማይቻል የተባለውን ማድረግን ነው። ስለዚህ የማይቻል የሚባል መፍትሔ ማቅረብ አለብን። ተቻለም አልተቻለም፤ በአሁኑ ሰዓት በምንም በኩል የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት የሆነውን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ አንኳሰንና አሳንሰን ማየት የለብንም። በምኞትም ይወድቃል ብለን መጠበቅ የለብንም። ያ ከሆነ ደግሞ የበለጠ አደጋ ሊከተል እንደሚችል ለርስዎ እኔ አስገንዛቢ ልሆን አይቃጣኝም። ከዚያ ለመዳን፤ በግልጽ በአንድነት መነሳት አለብን። ይህ ቡድን በምንም መንገድ ወዶ ሥልጣኑን እንደማይለቅ ሁሉ፤ የታጋዩ ክፍል አይሎ ትግሉ ሲጠነክር፤ ያለ የሌለ ጉልበቱን በሕዝቡ ላይ እንደሚያፈሰው መገንዘብአለብን። እናም በትክክል የዚህን ቡድን ጥንካሬና ድክመት ማወቅና ትግሉም በሚያመች መንገድ መመራት አለበት። ይህ ትግል ከግቡ የሚደርሰው፤ በአንድነት ተሰባስበን፣ የአንድነት ራዕይ ኖሮን፤ በአንድ ጠንካራ ድርጅት ሥር፤ በኢትዮጵያዊነታችን ለኢትዮጵያዊነታችን ስንታገል ብቻ ነው። መሰባሰብ አስፈላጊነቱን ተቀብለን፤ ለመሰባሰብ ለሚደረጉ ጥረቶች ግን እጃችንን አጣጥፈን መቀመጥ፤ ታጋይነት አይደለም። መሰባሰቡ ዋና ጉዳያችን ነው ካሉ፣ መሰባሰቡ ለትግሉ መደፊት መቀጠል ወሳኝ ነው ካሉ፣ እስከዛሬ የከፈሉት መስዋዕትነት ዋጋ እንዲኖረው ከፈለጉ፤ የመሰባሰቢያ ጊዜው አሁን ነው። ለትግሉ ያለዎት ጥንካሬ፣ ለስኬቱ ያለዎት ቆራጥነት፣ የታጋይነትዎ ብስለት የሚለካው አሁን ነው። አሁን የትም ማምለጫ የሌለው ትንቅንቅ ውስጥ ነን። በልባችን የያዝነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያቸናፊነት እምነት፤ በሕይወታችን ላይ ሙሉ ቁጥጥሩን ይውሰድ። ቀኑ ሌት፣ ሌቱ ቀን መሆናቸው ትርጉም ይጡ። የሕዝቡን ድል አንግተን፤ ወደፊት መሄድ ብቻ ምርጫ የሌለው ጎዳናችን ይሁን።

የመሰባሰቢያ ዕሴቶቻችን፤

አንደኛ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በገዥዎቹ ከፍተኛ በደል በየጊዜው ደርሶበታል። በዛም አነሰም ሕዝቡ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል፤ በደል ደርሶበታል። አንደኛው ክፍል ከሌለው የበለጠ በደል ደርሶበታል። ይህ የታሪክ ሀቅ ነው። ማንም ሊክደው አይችልም። ሆኖም ግን ይህ በደል የደረስውና በመድረስ ላይ ያለው፤ በገዥዎቹ የግል የሥልጣን ጥማት እንጂ፤ አንደኛው የሀገራችን ክፍል ሌላኛውን የሀገራችን ክፍል ሊወርና ሊያጠቃ በዶለተበት ሂደት አይደለም። ስለዚህ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ የተከታታይ ገዥዎች ተጠቂ መሆኑን መቀበል አለብን። አሁንም ወደፊት ስንመለከት፤ የኢትዮጵያን ገዥዎችና ፍላጎት ደምስሰን፤

100

የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነትና ሉዓላዊነት የትግላችን መሠረታዊ ዕሴት አድርገን መነሳት ነው። ካሁን በኋላ ሕዝቡ ወሳኝነቱና የበላይነቱ ከጥያቄ ውስጥ የማይገባ ቋሚ መብቱ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን። ሁለተኛ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስትሰፋና ስትጠብ ለዘመናት ኖራለች። በዚህ እንኮራለን። ታሪካችን ሙሉ ለሙሉ ትክክለኛ ተግባራትን ብቻ ያስመዘገበ ነው ብሎ የሚከራከር የዋህ ነው። ገዢዎች፤ ከመንደር እስከ በዙፋኑ ላይ የተቀመጡ ሁሉ፤ ሕዝቡን ባጠቃላይ፤ እስር በርሳቸው ደግሞ በተለይ፤ ሲጣሉና ሲዋጉ፣ አልፎ ተርፎም አንዳንዶቹ ለሥልጣን ሲሉ ከባዕድ እያበሩ የሀገራቸውን መሪዎች መዋጋታቸው ሀቅ ነው። ይህ ሁሉ ታዲያ የታሪካችን አካል ነው። ልንሸመጥጥና ልንክደው አንችልም። በገዥዎቹ ፍላጎት ተመርቶ አንደኛው ክፍል ሌላውን አጥቅቷል። በተመሳሳይ መንገድ ደግሞ በተራው ሌላው ብድሩን መልሷል። ይህም ታሪካችን ነው። ይህ ሁሉ ተደምሮ ነው የአሁኗ፣ የሀገራችን፣ የኢትዮጵያ ታሪክ። ከዚህ የምንማረው፤ ማንም ገዥ ሆኖ ሰነበተ ማንም፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ አንድ ሀገር ሆና፤ ደካማም ይሁን ጠንካራ በየወቅቱ አንድ መንግሥት ኖሯት፣ ለረጅም ጊዜ እንደቆየችው ሁሉ፤ አሁንም በአንድነቷና በአንድ ሀገርነቷ መቀጠሏን ማረጋገጥ አለብን። ሶስተኛ፤ በሰዎች መካከል ላለ ማናቸውም ግንኙነት፤ በመካከላቸው የሚያስተሳስራቸው፤ በጋር የሚስማሙበት የመተባበሪያ ሕጋቸው ነው። ይህ ሕግ ነው በመካከላቸው የሚኖረውን አብሮ የመቀጠል ሂደት የሚወስነው። እናም ሕጉ ካልተከበረ፤ በመካከላቸው ያለው አብሮነት ትክክለኛ አይደለም ማለት ነው። ስለዚህ በመተማመን አብሮነታቸው እንዲቀጥል፤ ሕጉን ማስከበሩ ግዴታ ነው። ይህ በሁለት ሰዎች መካከልም ሆነ በአንድ ሀገር ሕዝብ መካከል አንድ ነው። ሕጉን፤ ደንብ፣ ስነ ሥርዓት፣ በማለት እንደያስፈላጊ ቦታው ስም ሊሠጠው ይችላል። ሆኖም ግን መሠረታዊ ይዘቱ፤ በሰዎች መካከል፣ አብሮነታቸውን የሚያስረው፤ በመካከላቸው ያለው ሕግ መሆኑ ነው። ስለዚህ በሕግ መገዛትና የሕጉ መከበር፣ ግዴታ መሆኑን መቀበል አለብን። እናም በሀገራችን የሕግ የበላይነት መስፈን መሳኝ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን። አራተኛ፤ በአንድ ሀገር የሚኖሩ ሰዎች፤ የሀገራቸው ዜጎች በመሆናቸው፤ እያንዳንዳቸው እኩል የሀገሪቱ ባለቤቶች ናቸው። ለዚህም፤ የሀገሪቱ ሕግ ሁሉንም በእኩልነት መመልከት አለበት። ግዴታቸውም ሆነ መብታቸው በዜግነታቸው ላይ የተመሠረተ ነው። የሀገሪቱ ዜጎች በሙሉ፤ እኩል የሆነ መብትና ግዴታ አላቸው። ስለዚህ ከዜግነታቸው የሚመነጨው የግለሰብ ዴሞክራሲያዊ መብታቸው፤ ያላንዳች መሰናክል መከበር አለበት። በአንድ መንገድ ወይንም በሌላ፤ ሁለት ወይንም አስር ሆነው እኛ ስለተደራጀን የበለጠ መብት ይኑረን የሚባልበት ጨዋታ አይደለም። ማንም ግለሰብ፤ የሀገሪቱ ዜግነት እስካለው ድረስ፤ ሙሉ መብቱ የተከበረ ነው። ይህ፤

101

ለሁሉም፤ የትም ቦታ የሚሠራ፤ የኢትዮጵያዊ ዜግነት መብታቸው ነው። እናም የግለሰብ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበራቸውን ማረጋገጥ አለብን። በነዚህ አራት ነጥቦች ዙሪያ፤ ሁላችን ለንቅናቄው እንሰባሰብ። እኒህ መታገያችን ናቸው። እኒህ የኢትዮጵያዊያን መታገያ ዕሴቶቻችን ናቸው። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፤ እኒህም ሊቀየሩ፣ ሊያንሱ፣ ሊበዙ፣ ሊቀየጡ ይችላሉ። ይኼን በአንድነት በምንሰባሰብበት ጊዜ እንወስነዋለን። አሁን ለመጀመር መንደርደሪያችን እናድርገው። ይህን ወራሪ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ልንጥለው

የምንችለው፤ በኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። እሱ ፀረ-ኢትዮጵያዊያን ነው፤ እኛ ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ነን። የምንታገለው ለኢትዮጵያዊነታችን ነው። በዚህ ተደራጅተን መታገል አለብን። የምንደራጀው በየኢትዮጵያዊያን የነፃነት ንቅናቄ ነው። ይህ ትግል ወደፊት ሊሄድ የሚችለው፤ ይህ የምንመሠርተው ደርጅት፣ አደረጃጀቱና የአባላቱ የትግል ፍላጎት ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ድርጅት ጥንካሬና ጥረት ልቆ ሲገኝ ብቻ ነው። ይህ ትግላችን፤ የተለዩ አርቆ አሳቢ መሪዎችን ይጠይቃል።አሁን በየድርጅቶች የመሪነቱን ኃላፊነት የጨበጡት ሁሉ፤ ከድርጅቶቻቸው በላይ ሀገራቸውንና የሕዝቡን ትግል ተሸክመው፤ ለዚህ ትግል ድልና ለዚህ ትግል ድል ብቻ ድርጅቶቻቸውን ተገዥ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ነገና ተነገ ወዲያ የሚመጣውን አስቀድመው በማየት፤ በሥራቸው የተሰባሰቡ ታጋዮችን በትክክለኛው መንገድ ሲያዘጋጇቸውና ሲመሯቸው ነው ትግሉ ወደፊት የሚሄደው። በትግሉ ሂደት፤ እንደሁኔታው መለዋወጥ፤ እነሱም ራሳቸውን እና ደርጅቶቻቸውን፤ ትግሉ በሚጠይቀው መሠረት ማሳደግና ማስተካከል አለባቸው። መሰባሰቡና በአንድነት ሁላችን መታገላችን የዕለቱ ጥያቄ ነው። ለትግሉ የምንሰለፍንበት የኢትዮጵያዊያን የነፃነት ንቅናቄ የሚጠነክረው፤ በኢትዮጵያዊነታችን አምነንና ሀገራችን ባለችበት አሳዛኝ ሁኔታ ተቆርቁረን፤ የሀገራችንን ነፃነትና ለሕዝቡ ነፃነት የሚሆነውን መፍትሔ በተለያዬ መልክ የምንመለከት ሁሉ፤ በአንድነት ተቀምጠን፤ በመካከላችን ባለው ስምምነት፤ የጋራ የሆነ አቋማችንን ለድርጅቱ ምሰሶ ስናደርገው ነው። አንድ አመለካከት ያለው አንድ ድርጅት ብቻውን ሥልጣን ላይ ባሁኑ ሰዓት ከወጣ፤ መልሰን መደንከር ነው። ይኼን የኢትዮጵያዊያን የነፃነት ንቅናቄ የሚመሩት፤ ከግለሰብ ማንነታቸው በላይ፤ ኢትዮጵያዊያንን እና ኢትዮጵያን ያስቀደሙና ብቃታቸውንና ችሎታቸውን ያለምንም ስስት ለትግሉ የሚያውሉ መሆን አለባቸው። የትግሉ ስኬት በነዚህ መሪዎች ችሎታና ጥረት ይወሰናል። ከመጀመሪያው በሥራቸው ተተኪ የሚሆኑትን አዘጋጅተው፤ ቀጣይነትን የሚያስተማምኑ መሆን አለባቸው። የሀገሪቱን ምርጥ ታጋይና አታጋይ መሪዎችን፤ ትግሉን ወደፊት የሚገፉ ወጣት ታጋዮችን ማሰባሰብ አለባቸው። እኒህ ደግሞ፤ አሁን በትግሉ በተሠማሩ

102

ድርጅቶችና በትግሉ ዙሪያ ባሉ ግለሰቦች መካከል ነው የሚገኙት። ሌላ ከሰማይ የሚወርዱ መሪዎች የሉንም። እናም በትግሉ ዙሪያ ያለነው በሙሉ መሰባሰብ አለብን። ባሁኑ ሰዓት ስለያንዳንዱ ሀገራዊ ጉዳዮች ባንድ ላይ መጨነቅ የለብንም። የጉዳዮች ቅደም ተከተል ማድረግ አለብን። መጀመሪያ ሀገራችን እንደመዥገር እየመጠመጠ ያለውን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ማስወገድ ነው። በሂደቱ በሀገር ቤት ያለውና ከሀገር ውጪ ያለው የታጋይ ክፍል በአንድነት የሽግግር መንግሥት ማቋቋምና ህዝቡ ሉዓላዊነቱ፣ ሀገራችን አንድነቷ፣ ሕግ የበላይነቱና የኢትዮጵያዊያን የግለሰብ ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበሩበትን ሁኔታ ማዘጋጀት ነው። ከዚህ በተረፈ፤ የዓለም አቀፍ ስምምነቶች፣ ውሎችና ደንቦች ሊከበሩ የሚገባቸው፤ የኛን ጥቅም የሚያስጠብቁ ሆነው እስከተገኙ ድረስ ብቻ ነው። እኒህ መታሠሪያና መታነቂያ ገመድ ሆነው፤ አንገታችን እንድናስገባ የሚጠብቁ መሆን የለባቸውም። ታሪካችን ብዙ አስተምሮናል። እናም ማንኛውም ስምምነት፣ ውልና ደንብ፤ በዚህ መነፅር ይመረመራል። አሁን ማድረግ ያለብን፤ ትክክለኛውን የትግል መስመር ተከትለን፤ ትክክለኛ የሆነ የኢትዮጵያዊያን የነፃነት ንቅናቄ መመሥረት ነው። ኢትዮጵያዊው ትግል፤ በሰላምም ሆነ በሌላ መንገድ በትክክለኛ እየተመራ አይደለም። ይኼ የሆነው፤ ታጋዮች ጠፍተው ሳይሆን፤ አንድነትን ያሰመረ የመታገያ ማዕከል በቦታው ኖሮ፤ ትግሉን አቀናጅቶ የሚመራ ንቅናቄ ባለመገኘቱ ነው። መሠረታዊ የሆነውን የትግሉን ምንነት በደንብ ተረድተን፤ ለዚሁ ትግል ተመጣጣኝ የሆነ ትብብርና ድርጅት ስለሌለን ነው። ትግሉን በትክክል ለመምራት ደግሞ፤ የአንድነት ትግል መሆኑን መረዳታችን፤ መቅደም ይገባዋል። እናም ይሄን የማራመድ ኃላፊነቱ አለብን። መሰባሰብ

ይገባናል። የኢትዮጵያ ሀዝብ በሕ.ወ.ሓ.ት./ኢሕአዴግ ግፈኛ

ስርዓት እየደረሰበት ያለዉ ግፍ እስራትና ግድያ እየተባባሰ መምጣቱ

የሚያጠያይቅ ስላልሆነ የመብት የነጻነትና የሀገራችን ሉዓላዊነት ትግል ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ መጠናከር አለበት። ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን

በተደጋጋሚ አያሌ ጠላቶች አንበርክከዉ ያስረከቡንን ዉድ አገራችን ኢትዮጵያ

በተባበረ ክንዳችን ፅናታችንና አንድነታችንን መጠበቅና መከላከል አለብን፡ ዜግነታዊ ግዴታችንም ነዉ።

ከዚህ ድንቅ ጀግና ህዝብ ተወልደን ህዝባችን ሲረገጥ ንብረቱ ሲዘረፍ የህግ

የፍትህ ያለህ ሲል ከዛም አልፎ ዳር ድንበራችን ሲደፈር ባይተዋር ሆነን ዝም

ብሎ መመልከት አግባብነት የሌለዉና አሳፋሪ ድርጊት ነዉ። የኢትዮጵያ

ጠላቶች በቛንቛ በጎሳና በሀይማኖት ከፋፍለዉ አርስ በራሳችን ለማጨፋጨፍና

እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ኣይነቱ ኣካሔዳቸዉን እጅ ለእጅ ተያይዞ በህብረት

103

ተፋልሞ ማክሰምና በምትኩ አንድነትንና መከባበርን ያካተተ ኢትዮጵያዊ

ስሜትና ወኔ መስፈን አለበት። ስለዚህም አገር ኣድን አንቅስቃሴ መደረግ

አንዳለበት በፅኑ አናምናለን። የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችም የህዝቡን አጀንዳ

በማስቀደም የእርስ በርስ ያለመግባባቱን ትተዉ ልዩነታቸዉን እያጠበቡ

የመቀራረብና አብሮ የመስራትን እንቅስቃሴ አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ

እናሳስባለን። እንዲሁም በመሳሳት በጥቅምና በጭፍን ዘረኝንት ከአረመኔዉ

ሕ.ወ.ሓ.ት ጎራ ተሰልፋሁ አገርንና ህዝብን የሚጎዳ ህገ ወጥ ድርጊቶች

በመፈጸም ያላችሁ ሁሉ፡ የጊዜ ጉዳይ እንጂ የወያኔ ስርዓት መገርሰሱ አይቀርምና

ሀዝባችን በማካሄድ ላይ ያለዉን የመብትና የአገር ሉዓላዊነት የማስከበር ትግል

ጎን ትሰለፉ ዘንድ አሁንም ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባልን። ጋሻ

ለኢትዮጵያዉያን ይህ የሕ.ወ.ሓ.ት./ኢሕአዴግ አስከፊ አገዛዝ ከስሩ ተነቅሎ

ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚበጅ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እስኪገነባና የኢትዮጵያ

ሉዓላዊነት ፍጹም እስኪከበር ድረስ ለትግሉ የምናበረክተዉ አስተዋፅአኦ

ይቀጥላል።

አይቀሬው የህውሓት ውድቀትና በፍርሃት ድባብ ውስጥ የምትኖረው መቀሌ የሞያ ነፃነት በተገደበባት “ነፃ የፍትሕ” የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት

በሌሉበት! የሕግ የበላይነትና ተጠያቂነት በጠፋበት" በጋብቻና በዝምድና

የተሳሰረ አንድ ፈላጭ ቆራጭ ፓርቲ የሀገሪትዋን ሁለንትናዊ ሰብኣዊ

ማተሪያላዊና አእምራዊ ሀብት ተቆጣጥሮ ራሱ ሕግ አውጪ! ራሱ ሕግ ተርጓሚ!

ራሱ ሕግ ፈፃሚና አስፈፃሚ በሆነበት" ባጠቃላይ ፍርሃት! ዱላ! ድሕነትንና

ረሃብን እንደ የፓለቲካ መሳሪያ አድርጎ በመጠቀም ለያይቶና አደንቁሮ የሚገዛ

አምባ ገነን መንግስት ባለበት ድሃ ሀገር የሚኖር ሕብረተሰብ ምን ያህል ለአፈና!

አድልዎ! ጭቆና እና ዝርፊያ የተጋለጠ እንደሆነ መገመቱ አያዳግትም::

አብዛኞቻችን ከደርግ ውድቀት በሗላ በእርስ በርስ ጦርነት የደቀቀውን ሀገርና

ህዝብ እፎይታ አግኝቶ በይቅርታ መንፈስ ሁላችንም በአንዲት እናት ሀገር ጥላ

104

ስር ታቅፈን! ተቻችለን! ተፋቅረንና ተከባብረን በጋራ የምንገነባት አንዲት

ዲሞክራሲያዊት እናት ሀገር ትኖራለች የሚል ነበር ተስፋችንና ምኞታችን፡፡

የህወሓት/ኢሕአዴግ ስርዓትም ካለፉት መንግስታት ተምሮ በሀገራችን ቢያንስ

የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መሰረት ይጥል ይሆናል የሚል በጎ እምነትና ግምት

ነበረን፡፡ በሂደት የሚታዩ አንዳንድ የልማት እንቅስቃሴዎችም እንደ መልካም

ጅምር በመውሰድ" ነገር ግን በመልካም አስተዳድር! በፓለቲካዊ ምሕዳር!

በምርጫና በሀገራችን ድሕንነት ዙሪያ የሚታዩ መሰረታዊ ችግሮች ዛሬ ነገ

ይታረማሉ በማለት ዜጎች በተደራጀም ሆነ በተናጠል ላለፉት አሰርቱ ዓመታት

ብሶታቸውን ሲያሰሙና አቤት ሲሉ ቆይቷል:: ይሁን እንጂ ሰሚ ጆሮ

አልተገኘም:: ህወሓት/ኢሕአዴግ በትረ ስልጣኑን ከጨበጠና ካደላደለ በሗላ

እሱም በተራው የጥፋት መንገድ በመከተል የህዝቡን የለውጥ ጥማትና

የፍትሕ ተስፋ አጨልሞታል:: ትናንት በደርግ ቀይ ሽብር የተቀጣውና

የደነገጠው ሕብረተሰብ ለውጥ ይመጣል ብሎ ሲጠብቅ ዛሬም በፀረ ሽብር

አዋጅ እንዲገዛ! እንዲሸማቀቅና እንዲሰጋ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ትላንት

ለዴሞክራሲና ለሰው ልጅ ነፃነት ሲባል የተከፈለውን ኩቡር የህይወት

መስዋእትነት ተረስቶ ዛሬ የህወሓት/ኢሕአዴግ የአንድ ድርጅት አባልና ታማኝ

ካልሆንክ በስተቀር የመደራጀት! የመናገር! የመስራት! ባጠቃላይ እንደ አንድ

ዜጋ በህይወት የመኖር ነፃነትህን ተነጥቆ ለፍልሰት! ለእስር! አሊያም ለሞት

ትዳረጋለህ፡፡ የተከበረና አኩሪ ባህል ያለው ጨዋ ህዝብ ዛሬ ወዳጅ" ማሀል

ሰፋሪና ጠላት ብሎው በመፈረጅና በመከፋፈል አንዱ አንዱን የገዛ ወንድሙን

በጎሪጥና በጥርጣሬ ዓይን እንዲተያዩ እየተደረገ ይገኛል፡፡ አንድ ዜጋ የተለየ

ሃሳብ ወይም የሌላ ድርጅት አባል በመሆኑ ብቻ እንደ ነውርና እንደ ወንጀለኛ

ተቆጥሮ በህዝብ ፊት የተለያዩ አስነዋሪ የማስፈራሪያ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ

በተወለባት ምድር ሓፍረት እንዲሰማው" ከሕብረተሰቡ እንዲነጠልና እንዲሰጋ

ከማድረግ ባሻገር ይባስ ብለው ሲሞት እንዳንቀበረው" እሳት እንዳናስጭረው"

የሚል የወረደ ማሕበራዊ ውግዘትና ተፅእኖ እንዲፈፀምባቸዉ እየተደረገ

ይገኛል፡፡ ሌሎችም በዚሁ ፅሑፍ ለመጥቀሱ የሚከብድና የሚዘገንን ድርጊት

በተለይም ለአርባ ዓመታት ያህል በአንድ ሞኖፓላዊ ድርጅት ህወሓት ተይዞ

የሚገኘው የትግራይ ህዝብ ታሪኩንና መለያ ባህሉን በጉልበት በማፈራረስ እና

105

በመበረዝ በምትኩ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ቅይጥና የተዳቀለ የካድሬዎች ግራ

አስተሳሰብ እንዲተካ በማድረግ እርስ በርሱ እያናከሱ በላዩ ላይ ይህ ነው

የማይባል ግፍ እየተፈፀመበት ይገኛል፡፡ ልብ በሉ!! ተወልደን ባደግንበትና

እትብታችንን በተቀበረበት መንደር ዛሬ ይህ ዓይነት የስነ ልቦና ጦርነት

በያንዳንዳችን ቤት ቢደርስብን ምን ይሰማናል? ትላንት ጫካ ገብተው ስለ ነፃነት

ሲዘምሩ! በሰማእታት ስም ሲምሉ! ለህዝብ ሲያስተምሩና በሽዎች የሚቆጠሩ

ለጋ ወጣቶችን ቀብረው ስልጣን ላይ የወጡ የፓለቲካ መሪዎቹ ያ ሁሉ ለህዝብ

የገቡበትን ቃል ረስተው ዛሬ ብዙሃኑን ለልመናና ለስቃይ ዳርገው እነሱ በሙሱና

ሲጨማለቁ! ከሕግ በላይ በመሆን በህዝብ መብት ላይ ሲቀልዱ! በገዛ ወገናቸው

ላይ ሲጨክኑና ሲያሰቃዩ በውል ስናይ እውነት ምን ይሰማናል?

የህወሓት/ኢሕአዴግ ስርዓት የሁሉም ዜጋ ሕገ መንግስታዊ መብትና ደሕንነት

ጠብቆ በእኩል ከማስተዳደር! ከመጠበቅና እንደ መንግስት ከመስራት ይልቅ

ራሱን ታች ወርዶ ከሕብረተሰቡ ወይም ተቃዋሚ ናቸው ከሚላቸው ሰዎች ጋር

የሚናቆርና የሚያውክ ከሆነ ህዝቡ ለማን አቤት ይበል? ዛሬ የምንኖረው

በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰው ልጅ ከአካባቢው የእይታ አድማስ አልፎ ዓለምን

መዳሰስ በጀመረበት" በተለይም ዴሞክራሲ" የሕግ የበላይነት" መልካም

አስተዳደር" ሰብኣዊ መብትና የነፃነት ጥያቄዎች ድንበር አልባ (ዩኒቨርሳል)

የሰብኣዊ ፍጡር እሴቶች በሆኑበት በሰለጠነ ዘመን ሆኖ ሳለ ነገር ግን ህዝባችን

ብሎም ወጣቱ ትውልድ አደንቁረህ ግዛ በሚል የህወሓት/ኢሕአዴግ ያረጀ

ያፈጀ ፈሊጥ ሳይወድ በግድ እንደ ወባ ክትባት የአንድ ፓለቲካዊ ቡድን ጠባብና

ሞኖፓላዊ አስተሳሰብ ተሸብቦ እንዲያድግ የሚገደድበት ምክንያት ምንድን ነው?

የሚሉ ጥያቄዎች ለሰሚ ብቻ ሳይሆን ለተመልካችም ግራ የሚያጋቡ የዘመናችን

የሀገራችን እንቆቁልሽ ናቸው፡ ፍርሓት (ወኔ ሰላቢ በሽታ) ህዝቡን አስደንግጦ!

አስፈራርቶ! አሸብሮና ወኔ ሰልቦ መግዛት በደርግ ጊዜም የነበረ ቢሆንም የዛሬው

ግን የረቀቀና ዓይን ያወጣ ሁኔታ ነው ያለው፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር

የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ለኢትዮ ያ ህዝብ ካወረሱትና ካበረከቱት ትልቁ

ስጦታና ራዕይ “ፍርሃት” ነው፡፡ ፍርሃት በአሁኑ ጊዜ ህወሓት/ኢሕአዴግ

ህዝቡን አንበርክኮና ፀጥ ረጭ አድርጎ በሀይል ለመግዛት የሚጠቀምበት ትልቁ

የፓለቲካ መሳሪያው መሆኑን ፍርሃት በሕብረተሰቡ ውስጥ ገብቶ ምን ያህል

106

አስከፊና አስፈሪ ሁኔታ እንደፈጠረ ከቦታ ወደ ቦታ ስንቀሳቀስ በደረስኩበት ቤት

ሁሉ የማገኛቸው ሰዎች አንዳንዶቹ በስጋትና በጭንቀት ተውጠው እንባ

እየተናነቃቸው ሲነግሩኝ ውስጤ በጣም ይሰማኝ ነበር፡፡ አዎ!! ሁኔታውን

በአካል ተገኝቶ ለተመለከተው ሰው እውነትም ባለቤት ያጣ ያልታደለ ህዝብ!

ያልታደለች ሚስኪንዋ ድሃ ሀገር! የሚያሰኝ ነው፡፡ እኛን የሚያስተዳድሩን እኮ

መንግስት የላካቸው ካድሬዎችና ታማኞች ናቸው፡፡ በሕብረተሰቡ ዘንድ አፍ

ጠባቂዎች እየተባሉ የሚጠሩ የተለያዩ የስለላ መረቦች በየመንደሩ በውስጣችን

እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ለመቆጣጠር እንዲመቻቸውም ከላይ እስከ ታች ሕዝቡን

አንድ ለአምስት አደራጅተውታል፡፡ ቀጥሎም የቤተ ሰብ ሸንጎ የሚባልም አለ፡፡

ከዚህም አልፎ የፌዴራል ፓሊስ! ያካባቢው ፓሊስ! ሚሊሻና የተለያዩ ስውር

ታጣቂዎች ሁሉም በአብዛኛው ጊዜ የሚጠብቁት የህዝቡን ድህንነትና የዜጎች

ህልውና ቅድሚ በመስጠት ሳይሆን የኛን ነፃ እንቅስቃሴ የሚገድቡና አፋችንን

የሚጠብቁ ሀይሎችም ናቸው፡፡ ሌላ ቀርቶ በቤተሰብ መካከልም መተማመን

የለም፡፡ ባል ካፈነገጠ በሚስቱ ወይም በዘመዶቹ ሚስት ካፈነገጠች ደግሞ

በባልዋ ወይም በልጆችዋ እየገቡ ትዳር እንዲፈርስ ወይም እንዲካሰሱ ያደርጋሉ፡

፡ ከተናገርክ ደግሞ አፍ እላፊ እየተባለ ከስራ ትባረራለህ! መሬትህን ወይንም

ንብረትህን ትነጠቃለህ! በህዝብ ስም ከውጭ የሚመጣ እርዳታም እንዳታገኝ

ይደረጋል! ከዚህም አልፎ እንደ ጠላት የተፈረጁ የተቃዋሚ ፓለቲካ ድርጅቶች

ስም እየተለጠፈብህ የትምክህተኞች አቀንቃኝ! አሸባሪ! ከሃዲ! ወዘተ በሚል

ሰበብ ተከሰህ ወደ አቦይ ታአገስ (እስር ቤት) ትገባለህ፡፡ ከዚያ በሗላ ጠያቂ

የለህም፡፡ ወይም ሀገር ለቀህ ትጠፋለህ አሊያም ትሰወራለህ፡፡ ባጠቃላይ ሌላ

ሰው ወይም ሕብረተሰቡ ተቃውሞ ወይም የፍትሕ ጥያቄ እንዳያነሳ ለማድረግ

እኔን አይተህ ተቀጣ የሚል ሌላ ስውር መልእክት በሚያስተላልፍ መልኩ ግፍ

በዚህ ምክንያት የሆድ ቁስል ይዘን እያወቅን እንዳላወቅን አፋችንን ይዘን ዝም

እንላለን፡፡ ለማንስ አቤት እንበል፡፡ ከጎጥ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ አመራር ያለው

የካድሬና የስለላ ሰንሰለት ነው፡፡ እኛ እኮ በሀገሪቱ ሕገ መንግስት አለ ሲባል

በወሬ እንሰማለን እንጂ ሕጉ ፈፅሞ እኛን አይመለከተንም፡፡ ሕግና ስርዓት

ቢኖርማ እንዲህ አይሆንም ነበር፡፡ እኛ እኮ እስካሁን ድረስ የምንተዳደረው

በትጥቅ ትግሉ ጊዜከነበረው የድርጅቱ ሕግና ስርዓት የተለየ አይደለም፡፡ ድሮ

ሲያስተዳድሩን የነበሩት የህወሓት ካድሬዎች ናቸው አሁንም ከላይ እስከ ታች

አፋችሁን ያዙ እያሉ እየኰረኰሙ እየገዙን ያሉት እነሱ ናቸው ሌላ አዲስ ነገር

107

አልመጣም”

የሃሳብ ነፃነትና መደራጀት

የሃሳብ ነፃነትና መደራጀት በሕገ መንግስቱ ሰነድ ቁልጭ ብለው ከተቀመጡት

መሰረታዊ" ሰብኣዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ይሁን

እንጂ እነዚህ መብቶች ከወረቀት አልፈው በመሬት ላይ አይታዩም፡፡ ሕጉ

ለባለሰልጣናት እንጂ ለሰፊው ህዝብ ባዕድ ነው፡፡ ሕጉ የአንድ ድርጅት

የበላይነት ጠባቂና መሳሪያ እንጂ የህዝቡንና የሀገሪትዋን ሉአላዊ ክብር

የሚጠብቅ ሞሶሶ አይደለም፡፡ ሕጉ ሌሎችን በተለይም በጠላትነት

ለሚያዩዋቸው ተቃዋሚ ድርጅቶችን ለመምታት" ለማሳደደድ" ለማሰርና

ለማዳከም የሚጠቀሙበት ትልቁ መሳሪያ እንጂ ለእኩልነትና ለፍቅር የቆመ

አይደለም፡፡ በሌላ አነጋገር የዳኝነት" የፍትሕ" የምርጫና ሌሎች የዴሞክራሲ

ተቋማት የአንድ ድርጅት አገልጋይና መሳሪያ በሆኑበት" ባጠቃላይ በስልጣን ላይ

ያለው መንግስት ኢሕአዴግ የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ዜጎች እንደባላንጣ ፈርጆ

ሰበብ አስባብ እየፈለገ በመምታት ራሱን አውራ ፓርቲ ነኝ ብሎ የሰየመ አምባ

ገነናዊ ስርዓት በነገሰበት ሀገር ስለ የሃሳብ ነፃትነትና መደራጀት ብሎ ማንሳት

አይቻልም፡፡ በተለይም አሁን ከአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በሗላ ብሶበታል፡፡

በተለይም የመለስ ራእይ ወራሽ ነን የሚሉ ቡድኖችና ባለስልጣናት ራሳቸው

በራሳቸው መተማምን አቅቷቸው ሁሉም ነገር በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ስር መሆን

አለበት በሚል ጭፍን አስተሳሰብ ላይ በመመስረት ያለ ምሕረት እየጠረጉ ወደ

ፍፁም ጠቅላይ (ቶታሊቶሪያን) የሆነ ስርዓት ተሸጋግሯል፡፡ ከዚህ በመነሳት ዛሬ

በሀገራችን ሰላማዊና ሕጋዊ የትግል መንገድ ተከትለው ሕጋዊ ፈቃድ አውጥተው

በመንቀሳቀስ ላይ በሚገኙ ተቃዋሚ የፓለቲካ ድርጅቶች ላይ እየደረሰ ያለው

አፈናና ወከባ ይህን ነው ብሎ ለመናገር ይከብዳል፡፡ ባንድ በኩል ፈቃድ እየሰጠ

በሌላ በኩል ደግም ህገ መንግስት የሰጣቸውን መብት እንዳይጠቀሙ

በመከልከልና ብሎም በመገደብ መፈናፈኛ አሳጥቷቸዋል፡፡ ከህዝብ ጋር

እንዳይገናኙ" አባላት እንዳይጠጉዋቸው" ህዝባዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ

እንዳያደርጉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መሰናክል በመፍጠር የተለያዩ ፀረ

ዴሞክራሲና ኢፍትሓዊ የሆኑ እርምጃዎች እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ሕብረተሰቡን

በተለይም አዲሱ ትውልድ ለለውጥ ሊያነሳሱ ይችላሉ ብሎው የሚገምትዋቸው

በአመራር ላይ የተቀመጡ ወጣት ምሁራን ላይ ሆን ብሎው በማነጣጠር በፀረ

108

ሽብር አዋጅ እያመኻኙ ማሰር ስራዬ ብሎው ተያይዞውታል፡፡ ድርጊቱ ደረጃው

ይለያይ ይሆናል እንጂ በሁሉም አካባቢ በሁሉም ተቃዋሚ ድርጅቶች ላይ

የሚፈፀም ቢሆንም በተለይም ዓረና ትግራይ በሚባል በትግራይ ውስጥ በህግ

ተፈቅዶለት በሚንቀሳቀስ ድርጅት ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍ እንደ ምሳሌ

ወስደን ብናይ በመላ ሀገሪቱ ያለው አስከፊ የፓለቲካ ደባብ ትክክለኛ ገፅታ

ማሳያ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡ ድርጅቱ በይፋ በሕግ ከተቋቋመ ጀምሮ አቅሙ

በፈቀደው መጠን ይንቀሳቀሳል፡፡ ድርጅቱ የተፈጠረበት ሁኔታ መለስ ብለን

ስናይ ትግራይ “የተለየ አመለካከት የያዘ ትግርኛ ተናጋሪ ቀርቶ የተለየ መልክ

ያላት ወፍ እንኳን ዘወር አትልበትም በማለት ለአርባ ዓመታት ያህል የህወሓት

ትልቁ መደበቂያ ምሽግና ብቸኛ የጓሮ አትክልት ሆኖ በቆየው ምድር ላይ”

በመሆኑ ለዓመታት ያህል ስር የሰደዱ የተለያዩ የመጨቆኛ መረቦችንና

ሞኖፓላዊ አስተሳሰቦችን ሰብሮ የመርፌ ቀዳዳን የምታህል መንገድ አልፎ

በምትኩ ዴሞክራሲያዊና የሰለጠነ ራእይ ይዞ ወደ ሕብረተሰቡ ለመግባት ምን

ያህል አስቸጋሪና ውስብስብ ትግል የሚጠይቅ መሆኑን ለመገመቱ አያዳግትም፡፡

ወደ ጠንካራ ሀገራዊ ድርጅት መፈጠር እንደ መሳለል ሆኖ ያገለግላል ተብሎ

በሚሊኖች ዘንድ ተስፋ የጣለለት ዓረና በትግራይ አማራጭ ፓርቲ በመፈጠሩ

የሚያስደነግጣቸውና እንደ ትልቅ ስጋት የሚያዩት የህወሓት መሪዎች ብቻ

አይደሉም፡፡ ሌሎችም የኢትዮ ያ መፈራረስና ጥፋት የሚመኙ በተለይም

በትግራይ በትግራይ ምድር ላይ ኢትዮጵያዊነት ማንነትና ሀገራዊ ራዕይ የሰነቁ

ለህዝቦችዋ አንድነትና ክብር የሚሟጎቱ ሀገር በቀል ብሄረተኞች እንዳይበቅሉ

የሚሰጉ እንደ ሻዕቢያና ጀሌዎቻቸው የመሳሰሉት ሀይሎች ይህቺን ባቄላ ካደረች

አትቆረጠምም በማለት ዓረና ትግራይን ከእንጭጩ ለማጥፋትና ለማዳከም

የዘወትር ተግባራቸውና ሕልማችው መሆኑን ህዝቡ ከጥዋቱ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡

ሌላውን ትተን በቅርቡ የብዙሃን መገናኛዎችንና ማህበራዊ ድህረ ገፆችን

እየተጠቀሙ በዓረና አባላትና መሪዎቹ ላይ የተቀናጀ ጥቃት ለመፈፀም ምን

እያሉ እንደሆነ በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡ የሚገርመው አንዳንዶቹ

እንዲያውም ለነገሩ ለይስሙላ ተቃዋሚዎች ነን ይበሉ እንጂ በተግባር ሲታይ

ስውር አጀንዳቸው ከህወሓት/ኢሕአዴግ በላይ ዓረና ትግራይን እንደስጋት

የሚያዩት መሆናቸውን በግልፅ የሚያመላክት ነው፡፡ ሆኖም ሀቁ “እኛም

አውቀናል ጉድጓድ ጭረናል” እንደተባለው ሁሉ ጭቆና ያንገሸገሸው ህዝብ ነፃ

እስካልወጣ ድረስ ይቅርና የወሬ ጋጋታ ሚሊዮን ጦርም ቢሰለፍ ከመታገል

ወደሗላ ሊመልሰው የሚችል ምድራዊ ሀይል እንደማይኖር ሊያውቁት በተገባ

109

ነበር፡፡ከዚህ የተሳሳተ አመለካከትና ግምት በመነሳት በተለይም በመንግስት

በኩል የዓረና ትግራይ ፓርቲ አባላት ለሆኑ ዜጎች የሚደርስባቸው ጫና" ግፍና

አፈና ለመቀበል አይደለም ለማሰብም በጣም ያስቸግራል፡፡ ካድሬዎቹ ራሳቸው

ከሳሽ" ራሳቸው መስካሪ" ራሳቸው ዳኛና አሳሪ እየሆኑ ማሰቃየት" ከህብረተሰቡ

እንዲገለሉ ማድረግ" ከስራ ማባረር" ሀገር ያፈራውን ጥቅማ ጥቅም መከልከል

የተለመደ ስራ ሆኗል፡፡ የትምክህት ሀይሎች አመለካከት አራማጆች" እንዲሁም

በነሱ አጠራር አሸባሪዎችና ታሪካዊ ጠላቶቻችን ናቸው ከሚሉዋቸው ጋር

በማዛመድ ተላላኪዎችና ወኪሎች ናችሁ” በመባል እየተወነጀሉ አብረው

የጥቃቱን ሰለባ እንዲሆኑ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ከዚህ የተነሳም ማሕበራዊ

ቀውስና ጫና እየደረሰባቸው ያበዱ ወይም የት እንደገቡ የማይታወቁ የድርጅቱን

አባላት ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ በዚህ ዓይነት በተመሳሳይ እየተከሰሱና

እየተጠረጠሩ ቤታቸው የፈረሰ ቤተሰብ" የተፋታ ትዳርና ሳይወድ በግድ ከሞቀ

ቤቱና ከቀዩ እየፈለሰ ወደ ስደት የሚጎርፈው ወጣት ቤቱ ይቁጠረው፡፡ ለአብነት

የሚከተሉትን ግለሰቦች የደረሰባቸው ግፍ እንመልከት፡፡

መምህር ሀይሌ አሰመኽኝ የሚባል የህወሓት የቀድሞ ታጋይ የነበረና

በሗላም በባድመ ጦርነት የቀኝ እጁን ተቆርጦ ወደ ቤቱ የተመለሰው ወገን

የአረና ትግራይ አባል በመሆኑ ብቻ በአካባቢው ካድሬዎች በተደረገበት

ክትትልና ወከባ ምክንያት እንዲያብድ ተደርጎ አሁን የት እንዳለ አይታወቅም፡፡

ቤተሰቡም ድርብ ድርብርብ ሃዘን ሆኖባቸው እያለቀሱ ይገኛሉ፡፡ በሸራሮ

ከተማም በተመሳሳይ አካሃን አቶ ፍፁም ያሃንስ በሚባል ወገናችን በደረሰበት

ተፅእኖ አብዶ የከተማው ህዝብ መቀጣጫ ሆኖ ይገኛል፡፡

በዛና ከተማ እና አካባቢዋ በጣም ታዋቂ የነበረው የድሮ የህወሓት ታጋይ ዛሬ

የአረና አባል በመሆኑ ብቻ ካድሬዎቹ ሲከታተሉት ከቆዩ በሗላ እሱን

የሚያጠቁበት የተለያየ ምክንያት በመፈለግ በቤተሰቡ ላይ ጫና በመፍጠርና

በመካከላቸው ጣልቃ በመግባት የገዛ ዘመዶቹና ቤተሰቦቹ ሳይቀሩ እንዲከሱት

እና ተባባሪ እንዲሆኑ በማድረግ በደረሰበት ተፅእኖ ከቤቱና ከቀዩ እንዲባረር

ተደርጎ አሁን አዲስ አበባ ይገኛል፡፡ ይህንን እውነታ በግልፅ የነገረኝ ስሙን

እንዲጠቀስ ያልፈለገው የመንግስት ሰራተኛ የሆነው የራሱ ወንድም ነው፡፡

ሌላ አንድ ወጣትም ተመሳሳይ ፈተና ገጥሞታል፡፡ ልጁ የአረና አባል

110

አይደለም፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን ወጣቱ ከአንድ የአረና ትግራይ አባል በመንገድ

ተገናኝተው ቆሞው ሲያወሩ እንደአጋጣሚ ሆኖ ሌላ አንድ የሚያውቀው ልጅ

ሰላም ብሎት አብሮት ትንሽ መንገድ ይጋዛል፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በሗላ ልጁ

ወደ ስራ ቦታው ሄደና ገና ስራ ከመጀመሩ በፊት ለካስ መረጃ ተላልፎ ቆይቷል

በአስቸካይ አስተዳደር ጋር ይጠራል እና ይገባል፡፡ ሃላፊውም “ከመቼ ጀምረህ

ነው የአረና ትግራይ አባል የሆንከው?” ብሎ ድንገተኛ ጥያቄ ይጠይቀዋል፡፡

“የማናውቅ እንዳይመስልህ እውነቱን አውጣ” ብሎ ያስፈራራዋል፡፡ ልጁም

በድንጋጤ የአረና አባል እንዳልሆነ ቢገልፅለትም ሃላፊው በፍፁም ሊቀበለው

አልቻለም፡፡ እናም ከዛ በሗላ ከባድ ማስጠንቀቅያ ተሰጥቶት ወደ ስራው

ተመልሷል፡፡ የልጁ አባትም አብረውት በዚሁ መስሪያ ቤት ውስጥ በዘበኝነት

ተቀጥረው ይሰራሉ፡፡ አባትየውም በተመሳሳይ ተጠርተው ልጃቸው ዓረና

እንደሆነ እና ስራቸው አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ተነግረዋቸው እሳቸውም

ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶዋቸው ወደ ስራቸው ይመለሳሉ፡፡ ሁለቱም ማታ በቤት

ከተገናኙ በሗላ አባትየው ልጃቸውን ቁጭ አድርገው የዓረና አባል መሆኑን እና

አለመሆኑን ሲጠይቁትና ሲመረምሩት አመሹ፡፡ እሱም እንዳልሆነ ገለፀላቸው፡፡

በመጨረሻ አባትየው “በል ስማ ከዚህ በሗላ የአረና ትግራይ አባል ሁነህ

ካገኘሁህ ግን ሰው ያላደረገውን ባንተ ላይ አደርጋለሁ” አሉት፡፡ ልጁም ገርሞት

“ምን ታደርጋለህ አባዬ” ብሎ ሲጠይቃቸው እገድልሃለሁ አሉት በገዛ ልጃቸው፡

፡ ይህን ቃል የነገረኝ ራሱ ልጁ ከጋደኞቹ ፊት ቁጭ ብለን ስናወራ ነው፡፡ ልጁ

አሁን በአዲስ አበባ ከተማ በደህና ቦታ ተቀጥሮ እየሰራ የሚገኝ የመንግስት

ሰራተኛ ነው፡፡ አሁን ልጁ ለስርዓቱ ያለውን ታማኝነት ለመግለፅና እንዲሁም

ከአባቱ ጋር ተግባብቶ ለመኖር ሲል በማያምንበት ጉዳይ በየቀኑ ህወሓትን ደግፎ

በየፌስቡኩ ሲሳደብ ይውላል፡፡ አብርሃ ደስታ ለረጅም ጊዜ በቅርብ ርቀት

ሲከታተሉት ከቆዩ በሗላ የመንግስት ጣት ተቀስሮባቸው የስርዓቱን የአፈና ሰለባ

ከሆኑት ሰላማዊ ታጋዮች አንዱ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፓለቲካ ሳይንስ መምህር

የሆነው ወጣት አብራሃ ደስታ ነው፡፡ ከመታሰሩ ጥቂት ቀናት በፊት በስልክና

በአካል በመቐለ ከተማ ተገናኝተን አብረን ቁጭ ብለን በሰፊው እንድናወራ እና

ይበልጥ ማንነቱን እንዳውቀው እድል አግኝቼ ነበር፡፡ አብራሃ በፅሁፍ እና

በአካል ስታየው በጣም ይለያያል፡፡ ከምጠን በላይ ትሁት" ሕግና ስነ ስርዓት

አክባሪ ሰው ነው፡፡ ረጋ ብሎ የመናገር እና

የማስረዳት ችሎታው ከፍተኛ ነው፡፡ ተግባቢ ነው፡፡ አድማጭ ነው፡፡ በፍፁም

111

አይጠጣም አያጤስም፡፡ ለስላሳ ይደግማል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ

ዘንድም በስራ ችሎታቸውና በሞያ ብቃታቸው ከሚደነቁትና ከሚከበሩት ሰዎች

አንዱ ነው፡፡ አብርሃ ደስታ ለሰላማዊና ሕጋዊ ዴሞክራሲያዊ ትግል ያለው

ፅናትና እምነት በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባርም በሄደበት ሁሉ በህዝባዊ

ስብሰባም ሆነ በግል ሲወያይ በሰላም ታግሎ እንዴት ለውጥ ሊመጣ

እንደሚችል ሲያስተምር ቆይቷል፡፡ በስብሰባ በህዝብ ፊት ቀርቦየማሳመን

ችሎታውም ከሞያው ብቃት ተዳምሮ ዘመን የፈጠረው ታጋይ እየተባለ

በብዙዎቹ ዘንደ ይነገርለታል፡፡ ብቃቱንና ፅናቱን የቀድሞ የአረና ትግራይ

አመራር የነበረው እና በሀገራዊ ምርጫ ዋዜማ ባልታወቀና በረቀቀ ሁኔታ

በጭካኔ የተገደለው የወጣቱ ታጋይ አረጋዊ ገብረዮሐንስ ወኔ ወራሽ ነው

እየተባለ ይነገርለታል፡፡

አብርሃ ደስታ ህወሓትን በሃሳብ እንደተሸነፈና ከመሳደብ" ከማሸበርና በጉልበት

ከማሰር በስተቀር በህዝብ ፊት በአደባባይ ቆሞ በሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ

በግልፅ ለመወያየት የሞራል መሰረትና ብቃት የሌለው የበሰበሰ ድርጅት መሆኑን

በግልፅ ይናገር ነበር፡፡ይህም ህወሓቶች የተለየ ሃሳብ ይዞ በግልፅ መወያየት

ያልለመዱት የፓለቲካ ባህል ስለሆነ እንደድፍረት በመቁጠር ጥርስ ተነክሶበት

ከቆየ በሗላ እንደተለመደው አብርሃ ደስታን የሚያጠምዱበት ቀንና አጋጣሚ

ሲከታተሉና ሲጠብቁ ከርሟል፡፡ በመጨረሻም ከትግል አጋሮቹ ጋር ቁጭ ብለን

እያወራን እያለ ስለ የስርአቱን ምንነት" ያለው ክፋትና አፈና ከባህሪያቸው ጋር

አያይዞ ብዙ ዝርዝር ነገሮች አወሳልን፡፡ ስለራሱ የግል ጉዳይም በማንሳት ከአንድ

የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲ ጋር የዶክትሬት ፕሮገራም ይከታተል እንደነበረ እና

በማያውቀው ሁኔታ ስለተቋረጠ ወደ ሚመለከተው አካል ሄዶ መማር

እንዳልቻለ ነገረን፡፡ ለምን እንደተቋረጠ ቢጠይቅም ባለስልጣኑ በፌዝ “አንተ

ስለ ትምህርት ታወራለህ፡፡ ያንተ መማር ይቅር አዎ!! በኔ እምነት በማስረጃ ላይ

የተደገፈ ነገር ካለ አንድ ሰው ሕግ ፊት መቅረብ የለበትም የሚል ጭፍን እምነት

የለኝም፡፡ ነገር ግን ዜጎች የተለየ እምነት ስለያዙ ብቻ ለአንድ ድርጅት የፓለቲካ

ጠቀሜታ ተብሎ (politicaly motivated) ወይም በቂም በቀል ተነሳስቶ

በሰላማዊያን ዜጎች ላይ የሚፈፀም የስም ማጥፋትና የክስ ሂደት ድራማ ግን ሕገ

ወጥ ድርጊት ብቻ ሳይሆን በኢትዮያዊነታችን የርህራሄ ባህላችንም አኳያ ሲታይ

ኢሰብኣዊነት" ከሃላፊነትና ከስነ ምግባር ውጭ ስለሆነ አልደግፈውም ብቻ

ሳይሆን መወገዝ ያለበት ነው፡፡ በዚሁ መለኪያ በአብርሃ ደስታ ላይ የተፈፀመ

112

እንግልትና እስር ሲታይ ከነ ብርቱኳን ሜደክሳ እና ሌሎች በቃሊቲና በማእከላዊ

እስር ቤቶች ታጉረው ከሚገኙ የህሊና እስረኞች የሆኑት ወጣት ፓለቲከኞች

ወንድሞቻችን ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ የክሱ ቀደም ተከተልና አካሄድ ስናየው

ሕጋዊ መሰረትና እውነትነት የሌለው መሆኑን የሚያሳየው መጀመሪያ እንደ

እንስሳ በጉልበት መደብደብ" ከዚያ በሗላ ማሰር" ከተደበደቡና ከታሰሩ

በሗላም ከዳኝነት በፊት ከሰብኣዊ አያያዝ ውጭ ለፐሮፓጋንዳ ጠቀሜታ ሲባል

በቪድዮ እየቀረፁ ለፓብሊክ ማጋላጥ፡፡ ከዚያም ቀጥሎ ለይስሙላ ማስረጃ

ፍለጋ መሄድ ሲሆን የመጨረሻ ዕድላቸው ደግሞ በወህኒ ቤት እንዲበሰብሱ

ወይም የይቅር ወረቀት እንዲፈርሙ በማድረግ የትግል ወኔያቸው አኰላሽቶ

መልቀቅ ነው ፡፡ ይህ የዜጎች ሰብኣዊ ክብርና ሕገ መንግስታዊ መብት

የሚዳፈርና የሚፃረር" ከአንድ መንግስት ነኝ ከሚል አካል የማይጠበቅ ሕገ ወጥ

ተግባር ከመሆኑም በላይ ኢትዮ ያ የፈረመችባቸው ዓለም አቀፍ የሰብኣዊ

ፍጡርና የሕግ እስረኞች አያያዝ ሕግጋትም የሚጥስ ነው፡፡ አብርሃ ለምሳሌ

ያህል ጠቀስኩት እንጂ በሌሎች ክፍላተ ሀገር በወጣት ታጋይ ወንድሞቻችን ላይ

እየተወሰደ ያለው እርምጃም አላማው ተመሳሳይ ነው፡፡ በኢትዮ ያ በሀገር ደረጃ

የትግል አንድነት እየተፈጠረ ከሄደና ወጣት ምሁራን ወደ ትግሉ እየተቀላቀሉና

የፓለቲካ አመራሩን እየተኩ ከሄዱ ለህወሓት/ኢሕአዴግ ትልቅ ስጋትና የፓለቲካ

ኪሳራ ነው ከሚል ስሌት የመነጨ የፍርሃት እርምጃ መሆኑን ያዳባባይ ሚስጢር

ነው፡፡ የሚገርመው ግን ህወሓቶችና ኢሕአዴጎች በወገን ላይ አፈናና ግፍ

መፈፀማቸው ብቻ አይደለም፡፡ ነገር ግን አምባ ገነኖች የህዝብ እሮሮና ብሶት

የዶሮን ያህል ግምት ሳይሰጡ በሰራዊት ጉልበት" በጦር መሳሪያ ጋጋታና ክምር

ተማምነው ግለሰቦችንና ታጋዮችን ባሰሩና ጭቆናውን እያከረሩ በሄዱ ቁጥር

የህዝቡን ልብ የበለጠ እንዲሸፍትና ሽዎች ታጋዮች እንዲፈልቁ ያደርጋል እንጂ

ትግሉን ማዳፈን እንደማይቻል ካለፈው ታሪክ ሳይማሩ አሁንም ተመሳሳይ

ድራማ መስራታቸውን ነው፡፡ እንዲህ ከቀጠለ ደግሞ ወደዱም ጠሉም

ዕድሜያቸውንም በዚያው መጠን እያጠረ መሄዱ የማይቀር ተፈጥራዊ ሂደት

መሆኑንም በውል ሳይገነዘቡ መቅረታቸው ነው የሚያሳዝነው፡፡ ከላይ

የተጠቀሱትን የመልካም አስተዳደር እጦት መንሲኤያቸው ሁሉም ከአንድ ወንዝ

የሚቀዱ ናቸው፡፡ ይህ ማለት በሀገሪቱ ውስጥ ካለው ጠባብ የፓለቲካ ምሕዳር

የሚመነጩ ናቸው ማለት ነው፡፡ የህወሓት/ኢሕአዴግ ስርዓት የህዝቡን

መሰረታዊ ችግሮች ሊፈታ የማይችል" ዴሞክራሲያዊ ባህርይ የሌለው"

መሰረቱን የተናደና የተፋለሰ ፓሊሲ የሚከተል በመሆኑ ብቻ የሚመነጩ

113

ችግሮች ናቸው፡፡ መፍትሔውም የግለ ሰዎች መቀያየር ሳይሆን መሰረታዊ

የአስተሳሰብ" የፓሊሲና የስርዓት ለውጥ ያስፈልገዋል ብዬ በፅኑ አምናለሁ፡፡

በኔእምነት ማን ስልጣን ላይ ወጣ አይደለም ችግሬ፡፡ ዋናው ቁም ነገሩ ማን ምን

ዓይነት ለህዝብ የሚጠቅም የፓለሲ ለውጥ ይዞ መጣ ነው መመዘኛዬ፡፡

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ

ባለስልጣናቱ የህዝብ አዛኝ መስለው ለመታየት ሲሉ ቃጤማ አንጥፈው

ለመቀበል ሙከራ ቢያደርጉም የህዝቡን እሮሮና መከራ ግን ለመሸፈን ስላልቻሉ

በሕብረተሰቡ ውስጥ ማለት በመሬት ላይ ያለውን እውነታ ተገንዝባችሁ

በየስብሰባውና በተናጠል ሲቀርቡ የነበሩ ጥያቄዎች የብዙዎቻችን ጥያቄ

መሆናቸውን እገነዘባለሁ፡፡ በተጨማሪም ሰሞኑን በዓይጋ ድህረ ገፅ ላይ አባይ

ወልዱ ሙሱናን በሚመለከት ሁለት ሽሕ ለሚሆኑ ካድሬዎች ሰብስቦ

ያቀረበውን ካንገት በላይ ንግግር አስመልክቶ ህዝቡ የሚሰማውን ሃሳቡ

እንዲሰጥ ተብሎ በህዝባችን ላይ የተጫነው ሸክምና የተጋረጠው ቁስል

በብዙዎቻችን ሆድና አእምሮ ውስጥ የታመቀ ብሶት ገንፍሎ እንደወጣ የሚያሳይ

ሲሆን በሌላ መልኩ ደግሞ የጊዜ ጉዳይ እንጂ በልቡ የሸፈተ ህዝብ እንዳለ

ቁልጭ አድርጎ የሚያመላክት ነው፡፡ አዎ!! የቀረቡት ወርቃማ አስተያየቶች"

ጥያቄዎችና የለውጥ ፍላጎቶች ሁሉ ትልቅ ትርጉም ያላቸው ቢሆኑም ውጤት

የሚኖረው በአግባቡ ተገንዝቦና አጢኖ መልስ ለመስጠት የሚችል የሚሰማ

ጆሮ" ከጊዜው ጋር የሚመጥን አእምሮ" የህዝብንና የሀገርን ጉዳይ የሚያስቀድም

ዴሞክራሲያዊ ተፈጥሮ ሲኖር ብቻ መሆኑን የግድ ይላል፡፡ ይህ ባለቤት ያጣ

ሚስኪን ህዝባችን ከአፈና" ከፍርሃት" ከፍልሰትና ከውርደት ተላቆ የነፃነት አየር

የሚተነፍስበት ስርዓት እንዲፈጠር ሁላችንም የሃሳብ ልዩነታቸንና ሕብረ

ቀለማችንን እንደ ውበትና ፀጋ ተቀብለን በሚያገናኙን ጉዳዮች ዙሪያ ለጋራ

ችግር በጋራ ለመፍታት ተባብረን መቆምና መጮኽ እንዳለብን ጊዜውም ራሱ

እየተናገረ ነው፡፡

114

የወያኔ መንግስት በአማረው ህዝብ ላይ የሚያስከትለው ጭቆና! ወያኔ ሥልጣኑን በባዕድ ድጋፍ ከተቆጣጠረና አገዛዙን ከመሠረተ ወዲህ

ያለፈባቸውን 23 አመታት አቆነጃጅቶ ለመግለፅ መጠነ ሰፊ የሆነ ፕሮፓጋንዳ

ቢጠቀምም ከእለት ዕለት ሀገራችንና ሕዝቧን ወደባሰ አዘቅት እየከታት ለመሆኑ

የሕዝቡ የኑሮ ሁናቴ የሚመሰክረው ነው። በሱ የፖለቲካ መነፅር ለማየት

ካልተፈለገ በስተቀር ኢትዮጵያ ሀገራችን በርካታው ሕዝብ በኑሮው በመማረር

ለስደት የሚዳረግባት፤ ቀሳፊና ተላላፊ በሆኑ ብቻ ሳይሆን በቀላሉ ሊወገዱ

በሚችሉ በሽታዎች እየተጠቃ ሕይወቱን የሚያጣው የዜጎች ቁጥር እየበረከተ

ያለባት፤ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚደፈጠጡባት፤ በሀገሩ

ለባይተዋርነት የሚዳረገው ብዙሃኑ የሆኑባት፤ መልካም አስተዳደር ጠፍቶ

ግብር ከመክፈል ውጭ ዜጎቿ ማግኘት የሚገባችውን የሲቪል አገልግሎት

የሚያጡባት፤ መንገዱ አልጋ በአልጋ እንደማይሆን እሙን እየተባለ የደላቸው

የአገዝዙ አባላት የሚያላግጡባት፤ ከሁሉ በላይ ድግሞ እንደ ሕይወት

እስትንፋስ የሚያስፈልገው ነፃነቱን ባልተጎናፀፈባት ሀገሪቷ በእድገት ጎዳና

እየተጓዘችና ሕዝቡም የእድገቱ ትሩፋት ተጠቃሚ እየተባለ አምባገነንና ጎጠኛ

የአገዛዙ አባላት በጫንቃው ላይ ተቆናጠው ዘላለማዊ የሥልጣን ማራዘሚያ

መሣሪያ ደግነው ምልአተ ሕዝቡ የሚበዘበዝበትና የሚበደልበት ሀገር ናት።

በተለይም በቋንቋና በዘር ልዩነት ላይ የተመሠረተው የፌደራል ሥርዓት

ከመጀመሪያውኑ አንድን ብሔር በጠላትነት ሰይሞ በዘር ማፅዳት ተግባር

ከኢትዮጵያ መልክዓ ምድር ለማጥፍትና የራሴ የግሌ የሚባል የግዛት አካባቢ

ለማቋቋም ባለመ መልኩ የታሰበ ነበርና ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያስከትለው ውጤት

እጅግ አስከፊና አሳዛኝ የሆነ በርካታ ችግሮችንም እየወለደ፤ ጸብና ግጭቶችን

እያበራከተ፤ የዜጎች ሕይወትና የሕዝብ ኃብት በእጅጉ የሚባክንበት ሁኔታ

እየተከሰተ ይገኛል። በምሥራቅ ኢትዮጵያ ደገሃቡርና ጅጅጋ፤ በምሥራቅ ሀረርጌ

ጋራሙለታ፤ በደኖ አንስቶ በባሌና በአርሲ በሚገኙ አካባቢዎች በዘር ላይ

የተመሠረቱ ግጭቶችና የሰው ሕይወትና ንብረት የወደሙበት ሁኔታ በምሳሌነት

ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው። በምዕራብ ኢትዮጵያም ቢሆን በተለያዩ ወቅቶች

በአሶሳ በባምባሲ፣ በሰሪ፣ በጋምቤላ፣ በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ፣ ነቀምት፣

አምቦም በዚሁ አስከፊ ሁናቴ የሚጠቀሱ ናቸው። በአርሲ ክፍለ ሀገር

በአርባጉጉ አውራጃ ውስጥ በሚገኙ ጎሎልቻ፣ ጨሌ፣ጃጁ፣ መርቂ በተሰኙ

ወረዳዎችና አካባቢዎች በርካታ መኖሪያ ቤቶች የወደሙበት፤ ሕይወት

የጠፋበት፤ የሰው ልጅ እንድ ከብት አንገትና ጡቶች የተቆረጡበት አሰቃቂና

አሳዛኝ በደሎች ተካሂደዋል። በሌላ ቦታ ደግሞ ከነነፍሰ ሕይወታቸው ወደገደል

115

ተወርውረው እንዲፈጠፈጡ ተደርገዋል። በሀገራችን ባሁኑ ወቅት በአገዛዙና

አክራሪ ፅንፈኞች አማካኝነት ጠላት ተብሎ በተፈረጀው በአማራ ተወላጅ ላይ

ሽብርና የእልቂት ተግባር ለማካሄድ የመቅሰፍት ዘመቻ እየተጧጧፈ መሆኑን

እንመለከታለን። በሀገር ቤትና በውጭ አገር የሚገኙ እብደት የተጠናወታቸው

ፅንፈኞች አማራው እንዲጨፈጨፍ ጥሪ እንዲያቀርቡ ቅስቀሳ የተደረገላቸው

ሲሆን የዚሁ አቀንቃኝ የሆኑቱ በምዕራቡ ቴሌቪዥንና የሬዲዮ ስርጭቶች

ተገኝተው ለመስማት የሚሰቀጥጥ የጥላቻ ዘመቻቸውን ሲያናፍሱም

ተደምጠዋል። ርግጥም በአማራው ላይ ያንዣበበው የመቅሰፍት አደጋ

እየተስፋፋ ያለ እንደሆነ እንመለከታለን። የአገዛዙን የጀርባ ታሪክ ለተከታተለና

ለሚያወቅ ማንኛውም ዜጋ ያንዣበበውን አደጋ ሊገነዘበው የሚችል ነውና

ክስተቱ የተሳሳተ አስተያየትና ግምት አለመሆኑን የሚረዳው ይሆናል። ወያኔ

ራሱ በ1975 ዓ.ም. ሲያካሂድ የነበረውን ትግል በቁጥር ብዛት ከኦሮሞ ቀጥሎ

ይገኛል ተብሎ በሚገመተው በአማራ በተለይም በሸዋ አማራ ላይ ነው በማለት

ገልፆት እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም። ሟቹ መለስ ዜናዊ በወቅቱ በሰጠው ቃለ

መጠይቅም ያረጋገጠው መሆኑ አይዘነጋም። በጊዜው በጥሞና የሚያዳምጥና

የሚያስተውል ጠፍቶ እንጂ ወያኔ ፀረ አማራነቱን ምንጊዜም ቢሆን የደበቀው

አልነበረም። አሁንማ ብሶባት ያለ ጉዳይ ነው። ወያኔ ሥልጣን ከመቆናጠጡ

በፊት ከሻዕቢያና ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጋር በመተባበር በወለጋ የሚገኘውን

የአሶሳ ከተማ በማጥቃት በመቶዎች በሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የእልቂት

እርምጃ ማካሄዳቸው የሚረሳ አይደለም። ይህንን አሰቃቂና ዘግናኝ የሆነ

ጭፍጨፋ በወቅቱ የእንቅስቃሴው መሪ የነበረው የኤርትራው ኮማንደር

„ኩራት“ በተሞላበት ሁናቴ በአንድ ቃለ መጠይቅ መግለፁም የሚታወስ ነው።

በዚህ ኢሰብዓዊነት በተጠናወተው ድርጊታቸው ከ300 በላይ የሆኑ አማራዎች

ተገድለዋል፡ ተቃጥለዋል፡ ወይንም ታርደዋል። የዚህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ውጤት

በወቅቱ በቪዲዮ ተቀርጾ ለሕዝብ እይታ በቀረበበት ወቅት የብዙዎችን ሕሊና

ማቁሰሉና የማይረሳ ጠባሳ ማሳረፉም የሚዘነጋ አይደለም። ለጭፍጨፋው

ተጠያቂ የሆኑት ሶስቱ ግምባሮች ሁሌም በፀረ አማራና አለፍ ሲልም በፀረ

ኢትዮጵያዊነታቸው የሚታወቁ በዚህም በሕዝብ ዘንድ የተጠሉ ናቸው። እነዚህ

ክፍሎች ለበርካታ አመታት አማራ መሆን ለኢትዮጵያ መቆም ነው በማለት

ስለሚያምኑ ሁሌም የኢትዮጵያ ማንነትን ተቃርነው የቆሙ ናቸው። የአማራ

ሕዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በመሆን እንደ አይን ብሌኑ

የሚሳሳላትን ሀገሩን ኢትዮጵያን ከተለያዩ የባዕዳን ወራሪዎች ተከላክሎና ጠብቆ

የኖረ ከሁሉም በላይ ደግሞ በቅኝ ገዢዎች መዳፍ ሥር እንዳትወድቅ ከፍተኛ

መስዋዕት የከፈለ ሕዝብ መሆኑ በዚህም ለኢትዮጵያዊነት የፀና አቋም ያለው

116

መሆኑ በነዚህ ኃይሎች አይወደድለትም። ለዚህም ነው አማራን ነጋ ጠባ

አድሃሪ፣ ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ፣ የድሮ ሥርዓት ናፋቂ ሌላም አፀያፊ ስሞች

እየለጠፉበትና በጠላትነት እየፈረጁ ለማጥቃት የሚጥሩት። ወያኔ በኢሕአደግ

ሽፋን ሥልጣን ከተቆናጠጠ በኋላ ጸረ አማራ የሆኑ ክፍሎች ሲያልሙት

የነበረውን ጭፍጨፋቸውን በአማራው ላይ ለማካሄድ ሁናቴው

ተመቻቸላቸው። በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ በስደተኝነት ምናልባትም የዚሁኑ

ሀገር ዜግነት ተቀብሎ በሚኖረው አሊ ሁሴን መሪነት በአርባጉጉ የተደረገው

ጭፍጨፋ ለዚህ ጉልህ ምሳሌ ነው። እንዲሁም በኖርዌይ ሀገር ነዋሪና በወቅቱ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር መሪ በነበረው ሌንጮ ለታ መሪነት በኢትዮጵያ ምስራቅ

በበደኖ በአማሮች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ተካሂዷል። እርጉዝ ሴቶች በጥይት

ተደብድበዋል፤ ሽማግሌዎችና ወጣቶች ከገደል ተወርውረዋል፡ እልቂት የሚለው

ቃል ሁኔታውን ይገልፃል ቢባል እውነትነት ይኖረዋል። በምሥራቅ ወለጋም

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ምንም አይነት ወንጀል የሌለባቸውን ንጹሃን አማሮችን

በመግደል ተካፋይ ነበር። ፅንፈኛው የኦሮሞ እስላማዊ ቡድንም በአሰቦት ገዳም

የሴትና የወንድ መነኩሴዎችን መጨፍጨፋቸው በጊዜው የስንቶቹን እንባ

ያስፈሰሰ እንደነበር አይዘነጋም። በቅርቡ አገርሽቶበት የተነሳው ፀረ አማራ

ዘመቻ ከመቶ ዓመት በፊት በንጉሥ ምኒልክና ወታደሮቻቸው ኦሮሞዎችን

ገድለዋል የሚሉትን ተንተርሶ እየተናፈሰ የሚገኘው የጥላቻና የበቀል መንፈስ

አማራን ለመወንጀልና በሱ ላይ የዘር ማጥፋት ተግባር ለማካሄጃ ረግረጉን

ለማመቻቸት ሲባል እንደሆነ በግልፅ የሚታይ፤ በተግባርም እየተደገፈ ያለ ነው።

ይኸው የጥላቻና የበቀል ስሜት በይበልጥ ሕይወት እንዲላበስ ደግሞ በአኖሌ

አካባቢ የተገነባው የሰማዕታት መታሰቢያ ሳይሆን የሙታን ቂም ማስነሻ

ኃውልት በአገዛዙ ባለሥልጣናት መመረቁንና እሱን ተስታኮ እየተሰጡ ያሉ

መግለጫዎች የሚያመለክቱት ናቸው። በቅርቡ እንኳን በአምቦ ከተማ

በተማሪዎች በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ፀረ አማራ መፈክር በፅንፈኞች ሲገለፅ

መሰማቱ የዚሁ የጥላቻ ስሜት ውጤት እንጂ ሌላ አይደለም። በሥልጣን ላይ

ያለው አገዛዝ ለዚሁ ይሁንታውን ከመስጠት አልፎ ከተለያዩ የደቡብ

አካባቢዎች በአማራው ላይ የዘር ማፅዳትና ጠራርጎ የማስወጣት ዘመቻን

ሲያናፍስና ሲያራግብም እንደነበር የተደመጠና የተስተዋለ ነው። በአገዛዙ

አቀናባሪነትና ድጋፍ የግድያ ወይንም ደግሞ ለመቶ ዓመታትና ከዚያም በላይ

ተኪና ኃብትና ንብረት አፍርተው እንደማንኛውም ዜጋ ከሌሎች ብሔረሰብ

ተወላጅና እምነት ካላቸው ጋር ተስማምተው ከሚኖሩበት ቀዬ እንዲባረሩ

የሚደረገው ዘመቻ አማራውን ለአደጋና ራሱን እንዳይከላከል ይዳርገዋል። ይህ

ሁናቴ በርካታውን የአማራ ተወላጅና በኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት የሚያምኑ

117

ዜጎቻችን ላይ የከፋ መቅሰፍት ይደርስብናል የሚል የስጋትና የሰቀቀን ስሜት

በልባቸው ውስጥ እያሳደረ ያለ ጉዳይ ነው። ይህንን ፀረ አማራ ዘመቻ የተሳሳተ

ታሪክን ተቀብለው እንደገደል ማሚቶ የሚያናፍሱ አንዳንድ ባዕዳንና የዜና

ተቋማት እየተደገፈ፣ አማራውን እንደ ሕዝብ በፀረ ኦሮሞነት የሚወነጅሉም

ተቀላቅለውታል። የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ሁሌም ከባዕዳን ኃይሎች

ተቃውሞ ያልተለየው ለመሆኑ ደግሞ ያለፈ የጀግንነት ታሪካችን የሚመሰክረው

ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ እርስ በርስ ለማጋጨት ጥረት አድርገው የነበሩት

የእንግሊዙ የናፒየር ጉዞም ሆነ የሙሶሎኒ ቅኝ የማድረግም ሙከራ በአብነት

ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው። በሌላ በኩል በሀገሪቱ በተጨባጭ ያለው ዕውነታ

የአሁኑ አገዛዝ የተለያዩ ብሔረሰቦችን - አማራን፤ ኦሮሞን፣ ሶማሌን፣ ጉራጌን፣

አኙዋክና ሌሎችንም - በመጨቆን ላይ የተመሠረተ መሆኑ ነው። የወያኔ አገዛዝ

በጋምቤላ፣ በኦጋዴን፣ በሲዳማ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ሕዝባዊ ጭፍጨፋ

አካሂዷል። ነገር ግን በአማራው ተወላጅ ላይ የማስፈራራት ስሜትና ዛቻ

በአሁኑ ወቅት እየጨመረ ብቻ ሳይሆን በባዕዳን ሀገር በሚገኙ ከአሜሪካና

ከእንግሊዝ የፖለቲካ ሥርዓት ተጠቃሚ በሆኑ የሁሉም አማራ "ጉሮሮ

እንዲቆረጥ" ጥሪ በሚያቀርቡት ፅንፈኞችም እየተደገፈ ነው። የወያኔ አገዛዝ

በአሁኑ ወቅት እየተውተረተረ ያለ በመሆኑ ይህንን ፀረ አማራ ዘመቻ በ2007

ዓ.ም. ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው „ሕዝባዊ ምርጫ“ ለድጋፍ ማግኛ

መጠቀሚያ ለማድረግ እየጣረ ነውና የተቃጣው አደጋ እውንና የምርም ነው።

ማንም ለኢትዮጵያ ሕዝብና ሀገሪቷ ቀናኢ የሆኑ ሀገር ወዳድ ሁሉ በቸልታ

ሊመለከተው የማይገባው ነው። በመሆኑም የአማራ ሕዝብና ሁል አቀፍ የሆኑ

ኢትዮጵያዊያን ኃይሎች ላይ እያንዣበበ ካለው የጥፋት ሴራ ራሳቸውን

እንዲከላከሉና የዘር ማጥፋት ተግባር፣ ጥላቻና፣ በአማራው ላይ የተቃጣውን

የግድያ ዘመቻ አጥብቀው እንዲቃወሙ ሀገራዊ ጥሪውን ያቀርባል። የሁላችንም

የረጅም ጊዜ ህልም፣ አንድነትዋ የተጠበቀ የበለፀገች ኢትዮጵያን ማየት ነው፡፡

ወደዚያ ለመድረስ ሁሉም ኢትዮጵያውያን አስተዋጽኦአቸውን የሚያበረክቱበት

ለአገሬ እሠራለሁ ብለው በነፃ አየር የሚተነፍሱበት ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ

ምህዳር እንዲፈጠር ካሁኑ ጀምረው እንዲታገሉ ሁኔታን መመቻቸት ይፈልጋሉ፡

፡ ስለዚህም የፖለቲካ ምህዳሩን ማየትና ወዳለምነው ግብ ለመድረስ የሚረዱንን

አቅጣጫዎች መዳሰሱ ጠቃሚ ነው፡፡

118

የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታና የወደፊት የትግል አቅጣጫ ስለአገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ሁላችሁም ታውቃላችሁ፤ ሆኖም የግለሰቦች

አረዳድ ሊለያይ ስለሚችል፣ እኔ የራሴን ግንዛቤ ለመግለጽ እሞክራለሁ፡፡

- የኔን ግንዛቤ ስገልጽ የኔን ሃሳብና አመለካከት ብቻ ተቀበሉ ለማለት ሳይሆን

ዛሬም ይሁን በቀጣይ በሚካሄዱ ውይይቶች የኔም ግንዛቤና አመለካከት

እንደአስተዋጽኦ እንዲወሰድ ምኞቴ መሆኑን ሳልገልጽ አላልፍም፡፡

- ከኔ አመለካከት ጋር የማይስማሙ እንዳሉም እገነዘባለሁ፡፡ በበኩሌ ከኔ ጋር

የማይስማሙትን አከብራለሁ፡፡ ሃሳባቸውንና አመለካከታቸውን ባልጋራምና

ባልስማ ማባቸው እነሱንም ሆነ ሃሳባቸውን፣ አመለካከታቸውንና አቋማቸውን

አዳምጣለሁ አከብራለሁ፡፡ የመረጃ ስህተት ካለ ስህተቴን ለመቀበልና ለማረም

ዝግጁ ነኝ፡፡ የኔን ሃሳብ፣ አመለካከትና አቋም የማይጋሩት ግን እንዲያዳምጡኝና

እንዲያከብሩልኝ አደራ እላለሁ፡፡

- ስላገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ዛሬ ሁሉንምና ዝርዝሮችን ለመተንተን

አይቻልም፡፡ ስለሆነም በኔ እይታ መነካት አለባቸው የምላቸውን አንዳንድ

ጉዳዮች ብቻ አነሳለሁ፡፡ የቤቱ ንቁ ተሳትፎ ውይይታችንን ያዳብራል ብዬ

አምናለሁ፡፡ ስለሆነም በሠፊው እንድትሳተፉ አደራ እላለሁ፡፡ ይህ የኔ

አስተያየት ለውይይታችን መነሻ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

2. የአጋራችን የወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታ

2.1 የሕዝብን ሁኔታ፡-

- ህብረሰባችንን ስናይ ብሶተኛና የማጉረመርም ደረጃ ላይ እንጂ ተናድዶ

ንዴቱን በእንቅ ስቃሴ ለማሳየት ዝግጁ የሆነበት ደረጃ ላይ የደረሰ አይመስልም፡

- ብዙ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ችግሮች አሉበት፡፡ ይህንን ሰቆቃውንና

ብሶቱን ያማርራል፡፡

- በይፋና በአደባባይ አይገልጽም፡፡

- ብሶቱ በማጉረምረም ደረጃ የሚገልጽ ነው እንጂ በአጠቃላይ ወደ

ሕብረተሰባዊ ንዴት አልተለወጠም፡፡

119

- ተናጠል ንዴቶች አልፎ አልፎ ቢገለፁም ሠፊና የአጠቃላይ ሕብረተሰቡ

አልሆኑም፡፡

- እነዚህ ተናጠልና ትናንሽ ንዴቶች ወደ ተደራጀና የተቀናጀ ሕዝባዊ

እምቢተኘነት እና የእምቢተኘነት እንቅስቀሴዎች አልተለወጡም፡፡ በሌሎች

አገሮች በዳቦ ወይም በነዳጅ ዋጋ ላይ ትንሽ ጭማሪ ከታየ የህብረተሰቡ ንዴት

ይገነፍላል፡፡ በኛ ህዝብ ዘንድ ግን ይህ አይታይም፡፡ ምልክት ከታየም ጥቂት፣

ተናጠል፣ ያልተደራጁና ያልተቀናጁ ናቸው፡፡

2.2 ገዢው ፓርቲ Authoritarian ነው አምባገነን ነው

- ኢህአዴግ ለሕዝብ ፍላጎት ደንታ የማይሰጥ ድርጅት ነው ፡፡

- የሕዝብን ፍላጎት አያዳምጥም፡፡

- ሕዝብ እሱን ብቻ መስሎ እንዲያድር የሚፈልግ ነው፡፡

- ከሀገርና ከሕዝብ ይልቅ ፓርቲውን ያስቀድማል፡፡

- በሕገ-መንግሥቱ የተረጋገጡትንና በአንቀጽ 29፣ 3ዐ፣ 31፣ እና 38

የተዘረዘሩትን መብቶች አፍኖአል፡፡

- ተቃዋሚዎችን ለማጥቃት ብሎ ህጎችን በማውጣት፣ ሕግን አስከብራለሁ

እየለ ሰብአዊ መብቶችን ይጥሳል፡፡

- ዴሞክራሲያዊ ተቋማት እንዳይኖሩ አድርጎአል፣ ሦስቱም የመንግሥት

አካላት ለሕዝብ አገልጋዩች ሳይሆኑ የፓርቲው መሣሪያ ሆነዋል፡፡

- ገዢው ፓርቲ ሕገ-መንግሥቱን አያከብርም በሕገ-መንግሥቱ የተከበሩ

መብቶች ተግባራዊ ይሁኑ ሲባል አይፈቅድም፡፡ ሕገ-መንግሥቱ የሚሻሻልበትን

መንገድ ከመክፈት ይልቅ በሚያወጣቸው ሕጎች በእጅ አዙር ያሻሽላል፡፡

በአሠራሩ የሕገ-መንግሥታዊ አስተሳሰብን ዋጋ አሳጥቷል፡፡

2.3 የፓርቲ ሥርዓታችን ዴሞክራሲያዊ አይደለም

- በሕገ-መንግሥት ቢደነገግም ዴሞክራሲያዊ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት

120

ባገራችን የለም፡፡

- እንደሚታወቀው በንጉሱ ዘመን በፓርቲ መደራጀት ክልክል ነበር፡፡

- በደርግ ዘመን በመጀመሪያ ዓመታት ለደርግ ታማኝ የሆኑ ለስሙ ተቃዋሚ

ፓርቲዎች ቢወለዱም በመጨረሻ ግን አገሪቱ በአንድ ፓርቲ ብቸኛ ሥርዓት

(ኢሠፓ)ሥር ወደቀች፡፡

- ኢህአዴግ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ይመሠርታል ተብሎ ቢጠበቅም እሱ

ግን የአውራ ፓርቲን ሥርዓት የሚከተል ሆነ፡፡

- ይህም አውራ ፓርቲነት እንደ አሜሪኮና እንደ ታላቋዋ ብርታንያ

ዴሞክራሲያዊ የሆኑ የሁለት ፓርቲዎች አውራነት ቢሆን ባልገረመን፤ ወይም

እንደ ጃፓንና እንደ እነ እስራኤል ዴሞክራሲያዊና መድብለ ፓርቲ ሥርዓት

በሰፈነበት አውራ ሆኖ ቢወጣ እንቀበል ነበር፡፡ እርሱ ግን በአስገዳጅነት አንድ

አውራ ፓርቲ ሆኖ ሌሎች ግን እንደ ጫጩት እንኳ እንዳይኖሩ አድርጓል፡፡

- እሱን የሚገዳደሩ ጠንካራ ፓርቲዎች እንዳይኖሩ በሙስና አሠራር በ

Patronage እና በልዩ ልዩ ተጽእኖ ለማዳ ያደርጋቸዋል ወይም ከነጭራሸ

እንዲጠፉ ያደርጋል፡፡

2.4 ብልሹ የምርጫ ሥርዓት አለን

- የምርጫ ሥርዓታችን ለአገራችን ውስብስብ ሁኔታ ምቹ አይደለም፡፡ ብዙ

ብሔር ብሔረሰቦች፣ ብዙ ኃይማኖቶችና የተለያዩ ርዕዩተ ዓለመች ባሉበት ሀገር

አሸናፊው ሁሉን የሚወስድበት (First-Past-the Post) ሥርዓት አይመችም ፡፡

- ማህበረሰባዊ ውክልና፣ ተጠያቂነት እና አሳታፊነት (Participatory)

መርህን የተከተለ የተመጣጠነ Proportional ሥርዓት እንዲኖር አይፈለግም፡፡

- ይባስ ብሎ በምርጫዎች መሀከልና በምርጫዎች ወቅት ያለው የፖለቲካ

ሜዳ (ምህዳር) የተስተካከለ አይደለም፡፡ ዴሞክራሲያዊ ፍትሐዊና ነፃነት

የተሞላበት አይደለም፡፡

- በዚህ የምርጫ ሥርዓት ውስጥ ተሸናፊ ፓርቲዎችን የሚመርጥ ብዙ ሚሊዮን

የሕዝብ ክፍል በፖርላማ ደረጃ ድምጽ አልባ ይሆናል ማለት ነው፡፡

121

2.5 የፖለቲካ ልዩነቶች /ችግሮች አፈታታችን ልምድ መፍትሔ

ሰጪ ሳይሆን የሚያባብስ ነው

- ባገራችን የፖለቲካ ችግሮች የሚፈቱት በሠላማዊ መንገድ በውይይትና

በድርድር ሳይሆን፤ በአስተዳደራዊ፣ ወይም በጉልበት ነው፡፡

- ብዙውን ጊዜ በግለሰቦችና በድርጅቶች ዘንድ ህዝብንና ሀገርን ከማስቀደም

ራስን ማስቀደም ይታያል፡፡

- በግለኝነት (የራስን ፍላጎት ማስቀደም) ላይ የተመሠረቱ ልዩነቶችን፣

(የሥልጣን ፍላጎት፣ ለራስ ዝና፣ ገንዘብ/ሀብት ለማግኘት) መፍታት በጣም

አስቸጋሪ ናቸው፡፡

- ያገራችን የፖለቲካ ኃይሎች ልዩነቶችን ለመፍታት፤ የሕዝብ ወሳኝነትን

ለመቀበል አይፈልጉም፡፡ ህዝብ ፡-

- በምርጫ፣ ወይም

- በህዝበ ውሳኔ፡፡ (Referendum) ችግሮችን እንዲፈታ አይፈለግም፡፡

- ብዙውን ጊዜ ውይይቶች/ ድርድሮች የሚፈርሱት ተደራዳሪዎች

ቅድመ ሁኔታዎችን ስለሚያስቀምጡ ነው፡፡

- ለህዝብና ለሀገር ጥቅም ሲባል ሠፊና ሀገራዊ የትብብር መድረክ ለመፍጠር

ፈቃደኝነትና ዝግጁነት ደካማነው፡፡

- በፖለቲካ ፓርቲዎች ዘንድ የተለመደው በአሸናፊነት የማንበርከክ ፍላጎትና

የበላይነት ማስፈን አካሄድ ነው፡፡ እምቢ ከተባለ ደግሞ ለመጥፋትም መንቀሳቅ

አለ፡፡

2.6 የሠላማዊ ትግል ስልቶችን መጠቀም አልተጀረም

- ሠላማዊ ትግል Passive መሆን አይደለም፡፡ ሠላማዊ ትግል በእንቅስቃሴ

የተሞላ ትግል ነው፡፡

122

- ሠላማዊ ትግል፣ ኃይል/ጉልበት አልባ፣ ህጋዊ፣ ህገ-መንግሥታዊና

ዴሞክራሲያዊ ነው፡፡ ሌላን ለመጉዳት /የታለመ አይደለም፡፡

- ሠላማዊ ትግል አንዳንድ ውሳኔዎች፣ አንዳንድ ሕጎችና አንዳንድ ተቋማት

የራስን ወይም የሌላን ሰው መብቶች የማነኩ ከሆነ ለነዚህ ውሳኔዎች፣ ሕጎች፣

ወይም ተቋማት እምቢ ማለትንና ያለመታዘዝን ያካትታል /የሚጠይቅ ነው፡፡

- ሠላማዊ ትግል ዜጎች ባለመታዘዝ፣ ለመከላከያነት የሚጠቀሙበት

የተቃውሞ መሣሪያ ነው እንጂ የነውጥ ወይም የአመጽ መሣሪያ አይደለም፡፡

- የሠላማዊ ትግል ዓይነቶች ብዙ ናቸው፡፡

ለምሳሌ ያህል፡- የአዳራሽ ወይም የአደባባይ ስብሳዎች፣ Sit-ins፣

አድማ/መታቀብ Boycott (ሥራ፣ ትምህርት፣ ግዥ፣ ምርጫ) እና ሰልፍ

የተለመዱ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥም ባገራችን ተግባራዊ እየሆኑ ያሉት

ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

- ሠላማዊ ትግል ሠፊ የመደራጀት፣ የዝግጅት ሥራን ይጠይቃል፡፡

2.7 ውጫዊ ኃይልን የመጠበቅ ልምድና ባህል የተንሰራፋበት

አገር ውስጥ ነን

- ለችግሮች መፍትሔ መለካታዊ ኃይልን መጠበቅ አለ፡፡

- ዜጎች ለራሳቸውና ለሌሎች ዜጎች መብቶች መከበር በራስ ከመታገል ይልቅ

የፖለቲካ ፓርቲዎችን ይጠብቃሉ፡፡

- ከግለሰቦችም ፈውስ የመጠበቅ አዝማሚያም ይታያል፡፡

- የውጭ ኃይሎች (መንግሥታት) ችግሮቻችን ይፈቱልናል ብሎ መጠበቅም

አለ፡፡

- ይህ ሁሉ መንም ውጤት እንዳላስገኘ መላልሰን አይተናል፡፡

3. የወደፊት ትግላችን አቅጣጫ ምን መሆን አለት፣

123

3.1 ህዝብን ለለውጥ እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ፣

- የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በስፋት መሠራት አለባቸው፡፡

- የመረጃ መስጫ ዘዴዎች መጠናከርና መስፋት ይኖርባቸዋል፡፡ (ለምሳሌ

ዘመናዊ/ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን)

- በሕዝብ ውስጥ የማደራጀትና የማቀናጀት ሥራዎች መሠራት አለባቸው፡፡

- እውቀት የሌለው፣ መረጃ የማያገኝ ህዝብ፣ የተደራጀና የተቀናጀ

አደረጃጀቶች የለለው ሕዝብ ለውጥ ሊያመጣ አይችልም፡፡ ከፖለቲካ ድርጅቶች

የሚጠየቀውና የሚጠበቀው የተናደደ ሕብረተሰብን መፍጠር ሳይሆን መረጃ

የሚያገኝ፣ እውቀት ያለው፣ የተደራጀና ድርጅቶቹ የተቀናጁ ሕብረተሰብ

መፍጠር ነው፡፡

- ስለሆነም የወደፊት የትግል አቅጣጫችን የማሳወቅ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ፣

የማደራጀትና፣ ድርጅቶችን የማቀናጀት ሥራን ማዕከል ያደረገ መሆን አለበት፡፡

3.2 ገዢውን ፓርቲ በተመለከተ፡-

- የትኛውም ገዢ መደብ ተገድዶ እንጂ በልመና፣ በመለማመጥ በፈቃደኝነት

ህዝብ የሚፈልገውን ለውጥ አያመጣም፡፡ ገዢው ፓርቲ ለለውጥ የሚገደደው

በሕዝባዊ ኃይል ብቻ ነው፡፡ ገዢውን ፓርቲ ለለውጥ የሚያስገድድው ህዝባዊ

ሠፊ እንቅስቃሴ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም ገዢውን ፓርቲ ለማስገደድ ህዝባዊ

እንቅስቃሴ የሚፈጠርበትን መንገዶች መቀየስና በነሱ ላይ መሥራት የወደፊት

የትግል አቅጣጫችን መሆን አለበት፡፡

3.3 የፓርቲ ሥርዓታችንን የመለወጥ ሥራ አንዱ የትግል አቅጣጫችን መሆን

አለበት

- ይህም የሚሆነው ገዢው ፓርቲ የሚጠቀመውን Patronage (አባታዊነት)

እና የሙስና (Corruption)ስልት የፓርቲዎች አባላት፣ ደጋፊዎችና አጠቃላይ

ህዝቡ እንዲታገሉት ካደረግን ነው፡፡ ይህም አንድ የወደፊት የትግላችን

አቅጣጫ ነው፡፡

- ከዚህ አኳያ አንዳድ ተቃዎሚ ፓርቲዎች ከኢህአዴግ የሚሰጣቸው ድጎማ

124

የጥገኝነትና የጠባቂነት ባህልን የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ ሙሰኝነት

መሆኑን እንዲረዱ በቀጣይነት ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡

3.4 ብልሹ የምርጫ ሥርዓትን መለወጥ የወደፊት የትግል አቅጣጫችን

ማድረግ አለብን፡፡

- ዴሞክራሲ በምርጫዎች ዘመን መሀከልም ሆነ በምርጫ ወቅትም መስፈን

ያለበት ነው፡፡ ስለሆነም የፖለቲካ ምህዳር እንዲስተካከል በቁርጠኝነትና

በቀጣይነት መታገል ይኖርብናል፡፡

- ዴሞክራሲያዊ ሁኔታ ተፈጥሮ ምርጫን በተመለከተ የተመጣጠነ

(Proportional) የምርጫ ሥርዓት እንዲገነባ ለማድግ ሕገ-መንግሥቱ

የሚሻሻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር መታገል አስፈላጊ ነው፡፡

- ከአጭር ጊዜ አኳያ የትግል አቅጣጫችን ለ2ዐዐ5 ምርጫ የተስተካከለ

ምህዳር እንዲፈጠር መታገል ነው፡፡

3.5 ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መንቀሳቀስ

- ላገራችን ችግሮች መፍትሔ ለማፈላለግ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ እርቅ

መጥራት አስፈላጊ ነው፡፡ የፖለቲካ ችግሮችን/ልዩነቶችን ለመፍታት አንድነት

በፕሮግራሙ ያስቀመጠው አቅጣጫ ትክክል ነው፡፡ ስለሆነም ችግሮችን

በሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በውይይትና በድርድር የመፍታትን ባህል

የበለጠ መዳበር የትግላችን አቅጣጫ መሆን አለበት፡፡

ከአጭር ጊዜ አኳያ የመድረክ መፈጠር፣ የ11 ፓርቲዎች በቅርብ ጊዜ የፈጠሩት

መቀራረብ፣ የ2ዐዐ5 ምርጫን በተመለከተ የ33 ፓርቲዎች አብሮ መሥራት

መጀመር

የዚህ አቅጣጫ ጅማሮ ነው፡፡ ስለሆነም የዚህን ዓይነት እንቅስቃሴ ማበረታትና

መደገፍ ይጠበቅብናል፡፡ በቅርብ ጊዜ አንድ ሀገራዊ የምክክር ኮንፍራንስ

እንዲጠራ የሚጠይቅ ሃሳብ እየተጠናከረ መጥቶአል፡፡ ይህን ጥሪ መደገፍና

ማዳበር ይጠበቅብናል፡፡

- ልዩነቶችን በጉልበትና በመሣሪያ ኃይል ለመፍታት መሥራት ይቅር፡፡

125

- ለሥልጣን፣ ለዝናና ለሀብት ብለን መከፋፈልን እናቁም፡፡

- ለውይይቶችና ለድርድሮች ቅድመ ሁኔታ አናስቀምጥ፡፡

- የማንበርከክ/የማስጎብደድ ፍላጎት ባህል ይቅር፡፡

- ፍፁማዊነትን አስወግደን ‹‹የልዩነት መኖር መብት ለዘላለም ይኑር››እንበል፡፡

- ለህዝብ ወሳኝነትና የሥልጣን ባለቤትነት ጠንክረን በቀጣይነት እንታገል፡፡

- የማጎብደድና የተንበርካቢነት ባህልን በጽናት እንታገል፡፡

- ደፋር እንሁን፡፡ መጥፎ የሆነውን ነገር ከማስወገድ አንቆጠብ፡፡ መጥፎውን

እናስወግድ እንጂ አንለማመድ፡፡

3.6 የሠላማዊ ትግል ስልት ባንድ በኩል የፈሪዎች የትግል ስልት ነው ብለው

የሚያጣጥሉ አሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሠላማዊ ትግል (Passivism) ነው

ተብሎም ይወሰዳል፡፡ ነገር ግን የሠላማዊ ትግል ስልት ባግባቡ ጥቅም ላይ

ከዋለ ትልቅ ውጤት የሚያስገኝ ነው፡፡ የሠላማዊ ትግል ስልት ባገራችን ገና

ባግባቡ ጥቅም ላይ አልዋለም፡፡ ስለሆነም የወደፊት የትግል አቅጣጫችን

ለውጥን ለማምጣት የሠላማዊ ትግል ስልትን ባግባቡ መጀመርና ማዳበር መሆን

አለበት፡፡ ሠላማዊ ትግል ባግባቡ መካሄድ አለበት ሲባል ግን ሠፊ ዝግጅት እና

ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ መረሳት የለበትም፡፡

3.7 ውጫዊ ኃይልን ከመጠበቅ ይልቅ በራስ መተማመንና የራስን ችግር

ለመፍታት በራስ መንቀሳቀስ እንዲለመድ ለማድረግ መሥራት ሌላው የወደፊት

በትግላችን ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ በተለይም በሁሉም

የሀገራችን የኃይማኖት ተቋማት ይህን በተመለከተ የአመለካከት ለውጥ

መምጣት ያስፈልጋል፡፡ ቤተሰብ፣ ትምህርት ቤትና የመገናኛ ብዙሃንም ከዚህ

አኳያ የማይናቅ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

የኔን ችግር ፍታልኝ ብሎ ከመፀለይ ችግሮቼን ራሴ ለመፍታት እንድችል ጉልበት

ስጠኝ ብለን አምላክን መለመን ይኖርብናል፡፡

126

ዲሞክራሲ ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ

የዋለበትን ጊዜ ይህ ነው ብሎ ለመናገር የጠለቀ ጥናት ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን

የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ተከትሎ በወጡት ዓለማቀፍ ህጎች እና መርሆች

በመንተራስ በፀደቀው የ1955ቱ ሕገ መንግስት ላይ ዴሞክራሲያዊ መብቶች

በሚል ስያሜ የዜጎች መብቶች ተቀምጠው እናገኛለን፡፡ ያም ቢሆን የንጉሱ

ስርዓት ራሱን ዴሞክራሲያዊ ብሎ ጠርቶ አያውቅም – ደግ አደረገ፤ ፈላጭ

ቆራጭ ነበርና፡፡

የንጉሱ ስርዓት ማብቂያ ላይ ብቅ ብቅ ማለት የጀመሩት ‹የመጀመሪያዎቹ›

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን ዴሞክራሲያዊ ብለው ከመጥራት

ይልቅ ሕብረተሰባዊ፣ አብዮታዊ፣ ወ.ዘ.ተ የሚሉ ቃላትን ተመራጭ ያደርጉ

ነበር፡፡ ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚሆኑን የንጉሱን ስርዓት መገርሰስ ተከትሎ

ብልጭ ብላ በነበረችው ‹የነፃነት ጮራ› በመጠቀም እስከ ቀይ ሽብር ማብቂያ

ድረስ ለምልመው ከነበሩት ፓርቲዎች ውስጥ የዋነኛዎቹን ስያሜ ብንመለከት፤

የመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን)፣ አብዮታዊ ሰደድ፣ የወዛደር

ሊግ (ወዝሊግ)፣ የኢትዮጵያ ጭቁኖች አብዮታዊ ትግል (ኢጭአት) እና

ማርክሳዊ ሌኒናዊ ሪቮሊሽናዊ ድርጅትን (ማሌሪድ)፤ እንዲሁም እነዚህ አምስት

ድርጅቶች በጋራ የመሰረቱትን የኢትዮጵያ ማርክሳዊ ሌኒናዊ ድርጅቶች ህብረት

(ኢማሌዲህ) በአንድ ወገን ስናገኝ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝባዊ

አብዮታዊ ፓርቲን (ኢህአፓ) እናገኛለን፡፡

ከነዚህ ዋነኛ ፓርቲዎች ውስጥ አንዱም ዴሞክራሲን የስም ማሸብረቂያ

ሲያደርጋት አይታይም፤ አልደፈረምም፡፡ ደርግበአፈሙዝ በዙሪያው ያሉትን

ፓርቲዎች አንድ ባንድ ካስወገደ በኋላ የወዛደሩን ፓርቲ የኢትዮጵያ ሰራተኞች

ፓርቲኮሚሽን (ኢሰፓኮ) በኋላ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲን (ኢሰፓ)

መሰረትኩ አለ፤ እስከዚህ ጊዜ ድረስም ዴሞክራሲን ተዳፍሮ ለስም መጠሪያነት

አላዋለም ነበር፡፡ ነገር ግን ወታደራዊው መንግስት በዙሪያው ነፍጥ ያነገቡ

ሀይላት እየገፉ ሲመጡበት እና የምስራቁ ርዕዮተ ዓለም ሲዳከም ተመልክቶ

‹በአዎጅ ሀገር አስተዳድራለሁ› የሚለውን ቀረርቶ በማቆም፤ ለሕዝቡ

‹ዴሞክራሲያዊ ሕገ መንግስት› እነሆ አልኩ ሲል፤ በዛውም የሀገሪቱን ብሄራዊ

መጠሪያ ዴሞክራሲ በተባለችው ምትሃተኛ ቃል አስጊጧት ነበር – ‹የኢትዮጵያ

ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ›፡፡

127

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ግንባር

ከጅምሩ ራሱን ዴሞክራሲያዊ ብሎ በመጥራት የፖለቲካውን ገበያ የተቀላቀለ

ሲሆን፤ እርሱን ከመሰረቱት አራት ፓርቲዎች ውስጥ ከሕዝባዊ ወያነ ሃርነት

ትግራይ (ህወሃት) በቀር ሶስቱ ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)፣

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ)፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች

ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ያችን ‹ወርቃማ ቃል› መለያቸው

አድርገዋታል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም በኢህአዴግ አጋርነት ቀሪዎቹን አምስት

ክልሎች ከሚያስተዳድሩ ፓርቲዎች ውስጥ ከሀረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሀብሊ)

በቀር አፋርን፣ ሶማሌን፣ ጋምቤላን እና ቤንሻንጉል ጉምዝን የሚያስተዳድሩት

አጋር ፓርቲዎች ስያሜያቸውን በምትሃተኛዋ ዴሞክራሲ ያደመቁ ሁነው

እናገኛቸዋልን፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎቻችንም ‹ዴሞክራሲ› ለተባለው ቃል ያላቸው ፍቅር የበዛ

ነው፡፡ ዴሞክራሲን በስያሜነት ያልተጠቀመ የተቃዋሚ ፓርቲ የህዝብን

ይሁንታ አያገኝም የተባለ ያክል፤ የተቃዋሚው ሰፈር በዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣

የዴሞክራሲ ግንባር፣ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ ዴሞክራሲያዊ ህብረት ወ.ዘ.ተ

በሚሉ የዴሞክራሲ ቅጽል የተዋቡ ናቸው፡፡ ይሄን እይታችንን ወደ ሀገሪቱ

መጠሪያነት ስንወስደው ደግሞ፤ የሀገራችን ብሄራዊ መጠሪያ ከዴሞክራሲ ጋር

የተፋቀረ ሆኖ እናገኝዋለን፡፡ ወታደራዊው መንግስት አስራ ሶስት ዓመታትን

ዘግይቶ ባወጣው ሕገ መንግስቱ ንቆ ትቶት የነበረውን ዴሞክራሲ ለስርዓቱ

መጠሪያነት ‹የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ› በማለት

አውሎታል፡፡ ወታደራዊውን መንግስት የተካው ወያኔ በበኩሉ የወታደራዊውን

መንግስት ሕገ መንግስት ቀይሮ ባወጣው አዲስ ሕገ መንግስት ‹የኢትዮጵያ

ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን› እንደመጠሪያነት ተጠቅሞ በአፍሪካ

ራሳቸውን ‹ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ› ብለው ከሚጠሩት ከኮንጎ ዴሞክራሲያዊ

ሪፐብሊክ እና ከአልጀሪያ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጋር በሶስተኝነት ተሰልፏል፡

እንግዲህ የሀገሪቱ መጠሪያ ዴሞክራሲያዊ ከተባለ ሩብ ምዕተ ዓመት

አስቆጥራለች ማለት ነው። እንግዲህ ያንድ ወጣት እድሜ ያስቆጠረው

የዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ብሄራዊ መጠሪያ እውን መሬት ላይ ያለችውን

ኢትዮጵያን ይወክላል ወይ? ትንሹም ትልቁም ‹ዴሞክራሲ› የተሰኝችውን ቃል

እየመዘዘ ስሙ ላይ ሲለጥፍ፤ እውን ራሱን ለዴሞክራሲ ፅንሰ ሀሳብ አስገዝቶ

ነውን? ወይስ እንዲሁ ማታለያ ነች? ነው ጥያቄው፡፡

128

እኛም ሀገር ዴሞክራሲ ዴሞክራሲን በፓርቲ ፕሮግራም አድማቂነት፤

ዴሞክራሲን በሕዝብ ግንኙነት መሪ ቃልነት ይጠቀማሉ ፤ ሕዝቡም

እንደመናፍስቱ ወደነሱ ይቀርባል፤ በዙሪያቸውም ይሰበሰባል፤ ያኔ አይኑን

ያውሩታል በሕዝቡ ስም ይነግዳሉ፡፡ ይህም ማለት ፖለቲከኞቻችን ዴሞክራሲን

እንደ ማር ገምቦ ይገለገሉባታል እንደማለት ነው፡፡ ህዝቡ ማሩን ፍለጋ በማሩ

ዙሪያ ይኮለኮላል፤ ማሩን ግን አያገኝም፡፡

የዘመናዊ ሕገ መንግስታት ፈር ቀዳጅ የሆነው የአሜሪካ ሕገ መንግስት አንድም

ቦታ ዴሞክራሲ ወይም ዴሞክራሲያዊ የሚሉ ቃላትን አይጠቀምም፡፡ በተነፃፃሪ

ባለፉት 25 ዓመታት ያየናት ኢትዮጵያ ከሕገ መንግስታቶቿ እስከ ፓርቲ

ፕሮግራሞች ድረስ ዴሚክራሲን ያልተጠቀመችበት ቦታ ማግኝት ከባድ ነው፡፡

ይህ ሲባል ግን ኢትዮጵያ አብዝታ ዴሞክራሲ ዴሞክራሲ ስላለች አሜሪካ

ደግሞ በሕገ መንግስቷ አንድም ቦታ አላስተናገደችውምና፤ ኢትዮጵያ የተሻለች

ዴሞክራሲ ናት ማለት በፍፁም አይደለም፡፡ ይልቁንም የህዝቡን ፈቃድ

የሚያደርግ እንጅ፤ ዴሞክራሲ፣ ዴሞክራሲ የሚል ሁሉ ዴሞክራሲያዊ

አይደለም፡፡ ለዚህም ላለፉት ከሁለት አስርት አመታት በላይ ሀገራችንን እና

ህዝቧን በጭቆና በአምባገነንነት እየገዛ ያለውን የወያኔ መንግስት ትልቅ ማሳያ

ሆኖ እናገኝዋለን።

በዲሞክራሲ ጥላ በመሽሽግ የውጭውን አለም ይሁንታ ለመጐናጸፍ የሚተጋው

ወያኔ አስተዳድረዋለሁ የሚለውን ህዝብ ጥያቄ ለመመለስ ሲታትር

አይስተዋልም ይልቊን ድምጻችን ይሰማ በማለት ሆ ብሎ የወጣውን ነፃነት

ናፋቂ ትውልድ በያደባባዩ ሲገድል ተመልክተናል ለዚህም በ1997 ምርጫ

ማግስት የደረሰው ህዝባዊ ጭፍጨፋም ሆነ ከዚያ በኋላ የተነሱ ህዝባዊ

ጥያቄዎች ምላሻቸው የጠመንጃ አፈሙዝ እንደነበር የቅርብ ግዜ እውነታዎች

ናቸው።

ወያኔ ብቻውን ለመወዳደር እየተራወጠ ባለበት የ2007 ምርጫ በተለያየ

የመንግስት የሥራ ኃላፊነት ላይ ተቀምጠው ያሉ ካድሬዎችና ደህንነቶች

ሠራተኞችንና ነዋሪዎችን በየቀበሌው እንዲሁም በተለያዩ አዳራሾች እየሰበሰቡ

ኢህአዴግን መምረጥ ግዴታ እንደሆነ ከዛቻና ከማስፈሪያ ጋር መመሪያ እየሠጡ

መሆናቸው ይታወቃል።

129

የገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ደህንነቶች በተለ ያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ነዋ

ሪዎች እንዲሰበሰቡ ካስደረጉ በኋላ ስብሰባው የተጠራበትን አጀንዳ በመተው

“ኢህአዴግን መምረጥ ግዴታ ነው፤ ኢህአዴግን አለመምረጥ ፀረ ህዝብነት ነው፡

፡” በማለት ህዝብን በማሸበር ላይ ይገኛሉ። ወያኔ እና ምርጫ የማይተማመኑ

ሁለት ባልንጀራሞችን ያስታውሰኛል ይህን ያልኩበት ምክንያት *የማይተማመን

ባልንጀራ በየወንዙ ይማማላል* እንደሚባለው ወያኔም ምርጫ ከመድረሱ

አስቀድሞ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችንም ሆነ የነጻነት ታጋይ

ግለሰቦችን/Activist/ ማተራመስ ይጀምራል።

ለዚህም እንደማሳያነት የምንመለከተው ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በዞን9 ጦማርያን

እንዲሁም በተለያዪ የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ንቊ ተሳትፎ የነበራችውን

ግለሰቦች በሀሰት የክስ መዝገብ በማደራጀት ለእስርና ለእንግልት እንዲዳረጕ

በማድረግ የፖለቲካውን ሂደት ለብቻቸው ለመቆናጠጥ ሲታትሩ

እናስተውላለን። ለመሆኑ ወያኔ ስልጣን ላይ የቆየው ህዝባችን መርጦት ነው

እንዴ? የዚህን ምላሽ ለአምባቢው ትቼዋለሁ። በእኔ በኵል ይህንን የአምባገነኑን

መንግስት (ወያኔ) ለማስወገድ በአንድነት እንነሳ እላለሁ።

ድል ለጭቁኑ ህዝብ!!!

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ለማኝ መንግስት አመጣጥና አወዳደቅ

በአሁኑ ጊዜ የረዥም ጊዜ አንባቢዎቼ አንደምያውቁት ሁሉ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ

ያሉኝን ሀሳቦች እና ማሳመኛ የሙገታ ትንታኔዎች ከፍተኛ በሆነ ግልጽነት፣

እርግጠኝነት እና ለየት ባለ አቀራረብ ሁኔታ በእራሴ ቃላት እና ሀረጎች ለመግለፀ

አሞከራለሁ፡፡ በዚህ በአሁኑ ትችቴ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓት በአመጽ እና

በኃይል ከህዝቦች ፍላጎት ውጭ በስልጣን እርካብ ላይ ተፈናጥጦ የሚገኘውን

ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሐት) እየተባለ የሚጠራውን “የለማኝ

መንግስት” ገዥ ቡድን የፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍልስፍና መሰረት የሆነውን

ጽንሰ ሀሳብ በማስተዋወቅ ውስጣዊ ይዘቱን እና ባህሪያቱን ለመመርመር

እሞክራለሁ፡፡

130

በተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ እና የደቡብ ኤስያ አገሮች ብዙ የመከሰቻ

መገለጫዎችን ያካተተ “ልመና” (ወይም ባክሸሽ) የሚባል የተለመደ ባህል አለ፡፡

አንዳንዱ እንደ ኃይማኖታዊ ቀኖና ግዴታ “ምጽዋት በመስጠት” ወይም ደግሞ

ለድሆች ልገሳ በማድረግ “ልመናን” መተግበር ይችላል:: ለተሰጠ አግልግሎት

ይመጥናል ተብሎ ለባለስልጣን በ ”አጅም” (ኪስ ባዶ አንዳይሆን) የሚሰጥም

ክፍያ ተለምዷዊ ድርጊት አለ፡፡ “ልመና” ከዚህም በተጨማሪ የፖለቲካዊ

ሙስናን እና የሞራል ዝቅጠትን ባካተተ መልኩ በከፍተኛ የስልጣን እርካብ ላይ

ያሉት የመንግስት ባለስልጣኖች ሀብትን በከፍተኛ ደረጃ ለማካበት፣ በዝቅተኛ

የስልጣን እርካብ ላይ ያሉት የመንግስት ባለስልጣናት ደግሞ ከእጅ ወደ አፍ

ለሆነው አነስተኛ ወርሀዊ ገቢያቸው የኑሮ መደጎሚያ ይሆናል በሚል ስሌት ልዩ

“ስጦታ” እና “ሽልማት” የሚጠይቁበት የአሰራር ባህል ነው፡፡

“ለማኝ መንግስት” በሚለው ጽንሰ ሀሳብ በዋናነት ዓለም አቀፍ ምጽዋትን

(እርዳታ + ብድር) እና በእርዳታ እና ብድር ስራ ላይ የማጭበርበር ድርጊቶችን

በመፈጸም (ህጋዊ የሆኑ ድርጅቶችን ለህገወጥ ተግባር በማዋል) የተለያዩ

የሙስና ስልቶችን በመጠቀም እራሳቸውን በስልጣን እርካብ ላይ ለማቆየት

የሚፍጨረጨሩትን ገዥ አካሎች እና መንግስታትን ሁኔታ ለመገንዘብ እንዲቻል

በማሰብ ነው፡፡ ቀደም ሲል ለማስገንዘብ እንደሞከርኩት የአፍሪካ ከፍተኛው

የአምባገነንነት ደረጃ “ዝርፊያ” ነው፡፡ ከዚህ ላይ በግልጽ ሊታወቅ የሚገባው

ጉዳይ የለማኝ መንግስት የፖለቲካ ስልጣንን መከታ በማድረግ የመንግስት

ባለስልጣኖች እና ለገዥው ስርዓት ታማኝ አገልጋይ እና ሎሌ የሆኑት የተማሩ

ሰዎች ስልታዊ በሆነ መልክ የህዝብ ህብትን ወደ ግል ኪሳቸው በማስገባት እና

የህዝቡን የግምጃ ቤት ገንዘብ ህገወጥ በሆነ መልኩ ከአገር እንዲወጣ በማድረግ

ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉበትን ዘዴ የአፍሪካ የንቅዘት አስተዳደር በሚል

ቃል ገልጨው ነበር፡፡

የእኔ የአፍሪካ ለማኝ መንግስት ጽንሰ ሀሳብ የፈለቀው አለቃ (ቺፍ) ኦባፌሚ

አወሎዎ በሚባል ታዋቂ ናይጀሪያዊ ብሄራዊ አገር ወዳድ፣ ደራሲ እና

ቃልአቀባይ ከድህረ አፍሪካ ነጻነት በኋላ “የለማኝ መንግስታት መነሳሳት” እና

የእነዚህን ለማኝ መንግስታት እኩይ ምግባራት ቀጣይነት ባለው መልኩ

ለመቆጣጠር እና ለማስወገድ እንዲቻል ተከታታይነት ባለው መልኩ ጥረት

ሲያደርግ እና ምክር ሲሰጥ ከነበረው ስልታዊ አካሄድ ጋር የሚጣጣም እና

አብሮ የሚሄድ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1967 4ኛው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጉባኤ

131

ላይ አለቃ አዎ እንዲህ በማለት ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር፣

በአሁኑ ጊዜ አፍሪካ የለማኝ መንግስታት የውድድር አህጉር ሆናለች፡፡ ቀደም

ሲል ቅኝ ይገዙን ለነበሩት ገዥዎቻችን ምቹ ድልዳል በመሆን እኛ ግን እርስ

በእርሳችን በመመቃቀን እና አንዳችን በአንዳችን ላይ ደባ በመፈጸም ሆን ብለን

የእጅ አዙር ቅኝ ገዥዎችን በየግዛቶቻችን እንዲመጡ እየጋበዝን እንደገና

በአፍሪካ ምድር ላይ እንዲነግሱ እና የኢኮኖሚ እድሎቻችንን አሳልፈን

በመስጠት የእነርሱ ባሪያ በመሆን ላይ እንገኛለን…

…በእርግጥም ያለንን ስልጣን እና የሉዓላዊነት ሽፋን የሚሰጣቸውን ጥሩ

አጋጣሚዎች በመጠቀም እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ መርህ

የሚሰጠውን የህጋዊነት ማዕቀፍ ስልት እና አካሄድ ከግንዛቤ በማስገባት

በገንዘብ ከሚረዱን እርዳታ ሰጭዎች ጋር በመሞዳሞድ ይህንን ድርጊት

ልንቀጥልበት እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ዘለቄታ ያለው ሰይጣን በዚሁ ይቀጥላል…

እናም ለማኙ በቃኝ ብሎ ፊቱን ካላዞረ በስተቀር የልመና ባህሉ ከማንም ጋር

ሳይሆን ከእኛ ጋር ይቆያል፡፡ ብዙ በለመነ ቁጥር የተነሳሽነት ማጣትን፣

ድፍረትን፣ ቁርጠኝነትን እና በእራስ የመተማመን ተግባራትን በማስወገድ

የለማኝነት ባህልን በቋሚ ለማኝነት እረድፍ ላይ ተሰልፎ እንዲገኝ ያደርጋል፡፡

ዴሞክራሲ “በህዝቦች እና ለህዝቦች የተቋቋመ ህዝባዊ አስተዳደር” ነው በማለት

በማያሻማ መልኩ ተገልጿል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ “የለማኝ አገዛዝ” በእርዳታ

ሰጭዎች እና በአበዳሪዎች ለእርዳታ ሰጭዎች እና ለአበዳሪዎች የተቋቋመ

የእርዳታ ሰጭዎች እና የአበዳሪዎች መንግስት ነው፡፡ በሌላ አባባል የለማኝ

መንግስት በምጽዋት ሰጭዎች ለምጽዋት ተቀባዮች የተቋቋመ የምጽዋት

መንግስት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

በኢትዮጵያ በስልጣን እርካብ ላይ ተፈናጥጦ የሚገኘው የህወሐት የለማኝ

መንግስት ከአፍሪካ የለማኝ መንግስታት ውስጥ ጠንካራ ተሳትፎ በማድረግ

ውድድሩን በአንደኝነት ደራጃ ያጠናቀቀ ቁጥር አንድ የለማኝ መንግስት መሆኑ

ከጥያቄ ውስጥ የሚገባ ጉዳይ አይደለም፡፡ በእርግጥም የህወሐት ገዥ አካል

የለማኝ መንግስት በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ የቋሚ ተምሳሌት እና የልዩ ባህሪ

የለማኝ መንግስት ስብስብ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከአፍሪካ አህጉር

ከፍተኛውን የውጭ እርዳታ በመቀበል ላይ የምትገኝ እናወደፊትም የምትቀበል

ሀገር መሆኗየተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በሚገኘው እንደ ኢትዮጵያ

የልማት እርዳታ ቡድን/Development Assistant Group Ethiopia ዘገባ

132

ከሆነ እ.ኤ.አ በ2008 ለልማት እርዳታ ተብሎ በእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች

ለኢትዮጵያ የተሰጠው ገንዘብ 3.819 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን በ2010 ይህ

አህዝ 3.525 ዶላር፣ በ2011 ደግሞ 3.563 ቢሊዮን ዶላር ሆኖ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ

በ2011 እንግሊዝ ኢትዮጵያን በሚቀጥሉት 4 ዓመታት ከአፍሪካ አገሮች ሁሉ

ታላቋ የልማት እርዳታ ተቀባይ አድርጋ መርጣታለች፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ እ.ኤ.አ

በ2005 ለህወሐት የምትሰጠውን የእርዳታ መጠን ከ1.8 ቢሊዮን ገደማ አካባቢ

እ.ኤ.አ በ2008 የእርዳታ መጠኑን በከፍተኛ ደረጃ ከፍ በማድረግ ወደ 3.5

ቢሊዮን አድርሳዋለች፡፡

ዓለም አቀፋዊ ለጋሾች እና አበዳሪ ድርጅቶች ግዙፍ የሆነ መጠን ያለው ገንዘብ

(ለሰብአዊ፣ ለልማት፣ ለወታደራዊ፣ በመንግስታት መካከል በሚደረግ

ለሁለትዮሽ እና በበይነ መንግስታት መካከል በሚደረግ እርዳታ፣ መንግስታዊ

ባልሆኑ ድርጅቶች የሚሰጥ እርዳታ፣ ወዘተ) በድጎማ መልክ እና በቀጥታ ገቢ

በማድረግ እንደ ኢትዮጵያ ላለው ለማኝ አገዛዝ በመስጠት የእራሳቸውን

ስልታዊ እና ጀኦፖለቲካ አጀንዳ ለማስፈጸም ጥረት ደርጋሉ፡፡ የእርዳታ

መረባቸውን በመጠቀም በህዝቦች ጫንቃ ላይ በኃይል ተፈናጥጠው ከዓለም

አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች በእርዳታ እና በብድር በህዝብ ስም የሚሰጣቸውን

ገንዘብ እራሳቸውን ለማበልጸግ የሚያውሉትን ጥቂት የወሮበላ ገዥ ስብስብ

ነቀርሳዎች ለመቆጣጠር ይጠቀሙበታል፡፡ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች ለማኝ

መንግስታትን በመያዝ እንደፈለጉ ለማጦዝ እንዲችሉ ከሚጠቀሙባቸው እኩይ

ምግባሮች ውስጥ ለእነርሱ የታዛዥነት አገልግሎት ለሚሰጡ ለማኝ መንግስታት

ከፍተኛ የሆነ እርዳታ እና ብድር መስጠት ነው፡፡ ለምሳሌ አሁን በህይወት

የሌለው መለስ ዜናዊ ሶማሊያን እ.ኤ.አ በ2006 ከወረረ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ

ለዚህ ገዥ አካል እ.ኤ.አ በ2005 ከነበረበት 1.8 ቢሊዮን ዶላር በከፍተኛ ደረጃ

በማሳደግ በ2008 ወደ 3.5 ቢሊዮን የሚጠጋ ዶላር በእርዳታ መልክ

ሰጥታለች፡፡

አንድ የአደንዛዥ ዕጽ ሱስ የተቆራኘው ሰው የአደንዛዥ ዕጽ የሱስ ወጥመድ

ቁራኛ እንደሚሆን ሁሉ የህወሐት ለማኝ መንግስትም የእርዳታ የሱስ ቁራኛ

ሆኗል፡፡ ያ ገዥ አካል የሚለውን ትዕዛዝ ይከተላል፣ “አገርህ በምን ዓይነት

መንገድ እራሷን እንደምትችል ያለውን ስልት አትጠይቅ ይልቁንም ለአገርህ

በምን ዓይነት መንገድ በመለመን በምንም ዓይነት መንገድ እራሷን እንዳትችል

ለማድረግ ጠይቅ፡፡“ የህወሐት ገዥ አካል አመራሮች እርዳታን እንደ ጥቁር

አባይ ምንም መጨረሻ ሳይኖረው እና ምንም ዓይነት ገደብ ሳያስቀምጥ

133

እንደሚፈስሰው ሁሉ እርዳታንም እንደዚሁ “ነጻ ገንዘብ” አድርገው

ይቆጥሩታል፡፡ ልመናን የሚያካሂዱ ለማኞች ለዘለቄታው ለማኝ እንደሆኑ

ይቀራሉ የሚለውን የአለቃ አዎን ምክር በፍጹም እረስተውታል፡፡ ለህወሐት

አመራሮች ዓለም አቀፋዊ እርዳታዎች እና ብድሮች ልክ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ

እንደሚዘንብ ሁሉ ለእነርሱም እነዚህ እርዳታዎች እና ብድሮች ወቅቱን ጠብቆ

እደሚዘንብ ዝናብ ከምዕራብ አምላክ እንደ መና ከሰማይ እንደሚዘንብ ዝናብ

አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ አንድ ዓመት አነስተኛ የሆነ የእርዳታ ዝናብ ሲኖር

በሌላ ዓመት ደግሞ የተሻለ የእርዳታ ዝናብ ሊኖር ይችላል፡፡ ሆኖም ግን

የምዕራብ አምላኮች በምንም ዓይነት መንገድ ቢሆን የእርዳታ ዝናቡን ለህወሐት

ለማኝ መንግስት ማዝነቡን ሊያቋርጡ አይችሉም፡፡ በተለምዶው አነጋገር

እንደሚባለው አምላክ ጥረት የሚያደርጉትን እና እራሳቸውን የሚረዱትን ሁሉ

ይረዳል የሚለው አምላካዊ ቃል እንዳለ ቢሆንም የምዕራብ እርዳታ አምላኮች

በቁንጮው ላይ ያሉትን የህወሐት አመራሮች እና በየዓመቱ ከሚሰጧቸው

ገንዘብ ውስጥ በግል የሂሳብ አካውንታቸው በማጨቅ ሌላ ተጨማሪ በማሳደድ

ላይ ይገኛሉ፣ አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል ነውና ተረቱ፡፡

በገደብ እና ያለምንም ገደብ ለህወሐት ለማኝ መንግስት ባለፉት ሁለት አስርት

ዓመታት የተሰጠው እርዳታ ውጤቱ አውዳሚ ጉዳይ ነው፡፡ የህወሐት ለማኝ

መንግስት በምንም ዓይነት መልኩ መልካም አስተዳደርን ወይም ደግሞ

መልካም አስተዳደርን ለማምጣት የማስመሰል ስራ እንኳ እንደማይሰራ

በነቢብም ሆነ በተግባር አረጋግጧል፡፡ የህወሐት አመራሮች ምንም ይስሩ

ወይም አይስሩ የእርዳታ ገንዘቡ በኪሳቸው እንደሚገባ ያውቃሉ፡፡ እ.ኤ.አ

በ2005 ሀገራዊ ድህረ ምርጫ ውዝግብን ተከትሎ የህወሐት አገዛዝ የተቃዋሚ

የፖለቲካ አመራሮችን ሁሉንም በሚባል መልኩ፣ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞችን፣

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን፣ እና የሲቪል ማህበረሰብ አመራሮችን ወደ

ማጎሪያ እስር ቤቶች እየወሰደ በሚያስርበት ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ የበለጠ

በመሸለም በ2005 ሰጥታው የነበረውን 1.8 ቢሊዮን ዶላር በከፍተኛ ደረጃ

በማሳደግ እ.ኤ.አ በ2008 ወደ 3.5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ እርዳታ በመስጠት

በመርህ ደረጃ ሌት ቀን የምትለፈልፍለትን ባዶ የሰብአዊ መብት ጥበቃ መፈክር

በተግባር እንዲደፈጠጥ ለአምባገነኖች በመርዳት ሙሉ ተባባሪነቷን

አስመስክራለች፡፡

እንደዚሁም ደግሞ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ተጣብቆ የሚገኘው የህወሐት

ለማኝ መንግስት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ምንም ዓይነት ገደብ ሳይጣልበት

134

ከእርዳታ ሰጭ እና አበዳሪ ድርጅቶች ገንዘብ እንደሚቀበል የሚያወዛግብ ጉዳይ

አይደለም፡፡ ሆኖም ግን አንዳንድ ጊዜ ገደብ በሚጣልበት ጊዜ በምንም ዓይነት

ሁኔታ አስገዳጅ አይሆኑም፡፡ በዚህም ምክንት የህወሐት አጧዦች እና ቁልፍ

አመራሮች አብዛኛውን ጊዜ በእርዳታ እና በብድር የሚመጣውን ገንዘብ

የእነርሱን የዘመድ አዝማድነት ትስስር ለማጠናከር እንዲሁም በስልጣናቸው

ለረዥም ጊዜ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመቆየት ይጠቀሙበታል፡፡ ብልጠት

በተመላበት መልኩ በእርዳታ እና በብድር የተገኘውን ገንዘብ ወደ በጀታቸው

በማዘዋወር በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ለእነርሱ የፖለቲካ ደጋፊዎች የስራ እድል

መፍጠር እና የደህንነት መዋቅሩን በማስፋት የፖሊስ እና የወታደራዊ

አገልግሎቶች ለማጠናከር ይጠቀሙበታል፡፡ እ.ኤ.አ ኦገስት 2011 የምርመራ

ጋዜጠኞች ቢሮ እና ቢቢሲ እንደዘገቡት “የኢትዮጵያ መንግስት በብዙ ሚሊዮን

ፓውንድ የሚቆጠረውን ዓለም አቀፋዊ እርዳታ ከታለመለት ዓላማ ውጭ

የፖለቲካ ተቀናቃኞቹን ለመቅጣት እና ለማሸማቀቅ ተጠቅሞበታል“ በማለት

የሁኔታውን አሳሳቢነት ይፋ አድርገዋል፡፡ የእርዳታ ገንዘብ የመለስ ዜናዊን

መንግስት ለማጠናከር እና የተቃዋሚውን ጎራ ለማዳከም በመሳሪያነት

የተጠቀመበት መሆኑን ቢሮው አሳማኝ በሆነ መልኩ ማስረጃዎችን አቅርቧል፡፡

በፈጠሩት ግዙፍ የፖለቲካ ማሽን (ፖለቲካ ማሺን) በመጠቀም እና

የመራጮችን ድምጽ በመግዛት እና በመስረቅ እ.ኤ.አ በ2010 በተካሄደው አገር

አቀፍ ምርጫ 99.6 በመቶ አመጣሁ በማለት የድል ከበሮውን ደልቋል፡፡

የህወሐት ለማኝ መንግስት በዓለም አቀፉ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች እራሱን

ችሎ መንቀሳቀስ እንዳይችል አበራታች ያልሆኑ ነገሮች ተፈጽመውበታል፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 “የዩኤስ አሜሪካ በአፍሪካ የምታራምደው ፖሊሲ የሞራል

ኪሳራ” በሚል ርዕስ ገዥው አካል ከውጭ በሚገኘው እርዳታ በሴፍቲ ኔት

ፕሮግራም ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ በመሆኑ በመንግስታት በሚሰጡ ግዙፍ

ብድሮች እና የማያቋርጥ የሰብአዊ እርዳታ ለአምባገነኑ ገዥ አካል አሰራር

የሚተው ከሆነ በአግባቡ ያልተመራ የኢኮኖሚ መመሰቃቀል፣ አውዳሚ ሙስና

እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ የሚመጣ ድህነት የሚንሰራፋ ይሆናል፡፡

ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የህወሐት ለማኝ መንግስት በለጋሽ እና በአበዳሪ

ድርጅቶች ዘንድ ተጠያቂነት ያለበት መሆኑን ሳያስመሰክር የልመና ኮሮጆውን

እንደተለመደው በመያዝ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የረኃብ ሰለባ የሆኑ ዜጎችን

ለመመገብ በሚል ልመናውን ቀጥሏል፡፡

በዚህም መሰረት ገዥው አካል በህዝቡ ዘንድ ታማኝነትን ፍጹም በሆነ መልኩ

135

አጥቷል፡፡ እ.ኤ.አ በ2008 በደቡብ ኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ረኃብ አሁን

በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ ተጠያቂ እንዳልሆነ እና በረኃብ ለተጠቃው

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት መጠበቅ ብዙም እንዳላተጨነቀ

የሚያመላክት ነበር፡፡ መለስ በወቅቱ ላሳየው ቸልተኝነት እና የአቅም ማነስ

ችግር ለቀረበበት ክስ በመከላከል እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ያ ጉዳይ በእኛ በኩል

ያልተሳካ ነበር፡፡ በእጃችን ላይ ያለውን አስቸኳይ ሁኔታ በውል

አልተገነዘብነውም ነበር፡፡ በዚህ የተወሰነ አካባቢ የተጎዱ ህጻናት ገጽታዎች

ገዝፈው እስኪወጡ ድረስ የነበረውን ምስቅልቅል ሁኔታ አላወቅንም ነበር፡፡“

የምግብ እህል እጦት ጉዳት የተለመደ እና የማይቀር መሆኑ እየታወቀ እና

በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ እንደሚከሰት እየታወቀ አንድ ሀገርን የሚመራ መሪ

የህጻናቱ አጥንት አንደ ጣረ ሞት እስኪወጣ ድረስ ረኃብ አለመኖሩን እና ዜጎች

በረኃቡ አደጋ መጠቃታቸውን አላወቅንም ነበር ማለት በጣም አስደንጋጭ

ሁኔታን የሚፈጥር እና ኃላፊነትን እንደመዘንጋት የሚቆጠር እና የሚያስገርም

ጉዳይ ነው፡፡ በ2014 የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው ለረኃቡ የለማኙ

የህወሐት አገዛዝ ምላሽ ከዚያ የተለየ አልነበረም፡፡ እንዲህ የሚል ነበር፣

“በእጃችን ላይ በጣም የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ተጎጅዎች

የነበሩ መሆናቸውን ለመገንዝብ ዘግይተን ነበር…“ በስልጣን ላይ ያለው ገዥ

አካል የርኃብ፣ የምግብ እጥረት እና አለመመጣጠን ጥያቄ ዓመት ከዓመት፣

አስርት ዓመት ከአስርት ዓመት ወሳኝነት ባለው መልኩ ማስወገድ ያልቻለው

ለምንድን ነው? ለዚህ ምላሹ በስልጣን ላያ ያለው የህወሐት ለማኝ መንግስት

ከምዕራብ በሚመጣው እርዳታ እና ብድር ንጉሶች እና ንግስቶች በመሆን እጅግ

ከፍተኛ የሆነ ትርፍን የሚያጋብሱበት የመዝረፊያ ስልት ሆኖ ስላገኙት እና

በብዙ ሚሊዮን የሚመጣውን ዶላር በልማት ስራ ላይ ማዋል ለእነርሱ ገንዘብ

መዝረፊያነት የማይስማማ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡ ድህነትን ለዘለቄታው ለማጥፋት

ለእነርሱ ምናቸው አይደለም ሆኖም ግን ድህነትን ታሪክ እናደርጋለን የሚል ባዶ

መፈክር እያሰሙ በህዝብ ላይ ይሳለቃሉ፡፡ ስለሆነም ዓለም አፋዊ እርዳታ

መልካም አስተዳደርን የሚያኮሰስ ብቻ አይደለም ሆኖም ግን እራሱ ድህነት

ነው፡፡

የዓለም ባንክ፣ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ሌሎች የምዕራብ አገሮች ለጋሽ

ድርጅቶች የህወሐትን ለማኝ ገዥ አካል ከውጭ እርዳታ እና ብድር የገንዘብ

ትሩፋት ለማግኘት ከሚሰራበት ሁኔታ ወጥቶ በትክክለኛው መንገድ መስራት

እንዲችል አጽንኦ በመስጠት አስጠንቅቀውታል፡፡ ባለፈው ሳምንት ገዥው አካል

ዓለም አቀፍ የቦንድ ገበያዎችን ለማግኘት እንደሚፈልግ አሳውቆ ነበር፡፡

136

የህወሐት አገዛዝ ለሩብ ከፍለ ዘመናት ያህል ከውጭ እርዳታ እና ብድር

በመቀበል በህዝቦች ስም የሚመጣውን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማጋበሻ

ሲያደርገው ቆይቷል እናም አሁን ደግሞ ሌላ የገንዘብ መለመኛ አማራጭ

መንገዶችን በመፈለግ ላይ ይገኛል፡፡ የህወሐት የገንዘብ ሚኒስቴር እንዲህ

በማለት አውጇል፣ “በዴሴምበር ሁለተኛው አጋማሽ የመጨረሻዎቹ ሁለት

ሳምንታት እና በጃኗሪ የመጀመሪያ ሳምንታት ለዓለም አቀፍ የካፒታል ገበያ

የሚቀርብበት ነው፡፡ መሰረተ ልማትን ለማሻሻል ቦንዶች የእቅዱ አንድ አካል

በመሆን አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡“

ከ23 ዓመታት በኋላ በሚያስደንቅ ሁኔታ የሕወሐት ገዥ አካል የገንዘብ

ገበያ/Capital market ያለ መሆኑን በድንገት ደረሰበት!! በጣም ይደንቃል !!

የህወሐት ገዥ አካል እንደዚህ ያለ የገንዘብ ማግኛ ዘዴ መኖሩን ከዚህ ቀደም

ፈጽሞ የማያውቀው ስለነበር ህገወጥ በሆነ መልኩ በዩናይትድ ስቴትስ

በቁርጥርጭ ገንዘብ ለኢትዮጵያ ዲያስፖራ የቦንድ ሽያጭ በማቅረብ 5,250

ሜጋዋት የሚሆን አቅም ያለውን ታላቁ የህደሴ (ከንቱ ዉዳሴ) ግድብ እያለ

ሌት ቀን የሚደሰኩርለትን በአባይ ወንዝ ላይ ለመገደብ ጥረት በማድረግ ላይ

ይገኛል፡፡ ከዲያስፖራው ሊገኝ የሚችለው ገንዘብ ለለማኙ ገዥ አካል ክስ

መሙያ ሆና ቀርታለች ። ከዲያስፖራው ገንዘብ የማግኘቱን ጥረት ያላቆሙ

መሆናቸውን የምናውቅ መሆኑን አንዲገነዘቡ የህወሐት ገዥ አካል በአሁኑ ጊዜ

ከህዝብ ጋር ያለውን የመድረክ ላይ ግንኙነት ዘመቻ በማጠናከር ዓለም አቀፍ

የገንዘብ ገበያዎችን ለመድረስ በመኳተን ላይ ይገኛል፡፡ እንደዚሁም ለአስርት

ዓመታት ያህል ህገወጥ በሆነ የገንዘብ ዝውውር ግዙፍ የሆነ ገንዘብ ከኢትዮጵያ

እንዲወጣ አድርጓል፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ/Global

Financial Integrity የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት እንዲህ የሚል ዘገባ

አውጥቶ ነበር፣ “እ.ኤ.አ በ2000 እና በ2009 ዓመታት መካከል ኢትዮጵያ 11.7

ቢሊዮን ዶላር በህገወጥ መልክ ከአገር እንዲወጣ አድርጋለች፡፡“ እስቲ እንግዲህ

አስቡት ወደ 12 ቢሊዮን የሚሆን ገንዘብ በህገወጥ መልክ ከአገር እንዲወጣ

ባይደረግ እና በቀጥታ ለሀገሪቱ የልማት ፕሮግራም የሚውል ቢሆን ኖሮ ምን

ያህል የኢትዮጵያን የልማት ስራ ወደፊት ሊያራምድ ይችል እንደነበር!!!

በኢትዮጵ ያለው የለማኝ መንግስት የሚያስፈልገውን በጀት (በአንድ ዓመት

ውስጥ ሊሰበስብ እና ሊያወጣ ያቀደውን) ለማግኘት ሙሉ በሙሉ በሚባል

መልኩ ጥገኝነቱን ያደረገው ከለጋሽ እና ከአበዳሪ ድርጅቶች ከሚያገኘው

የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡ የዓለም የኢኮኖሚ እና የልማት ትብብር

137

ድርጅት/Organization for Economic Cooperation and Development

የተባለ ዓለም አቀፍ ድርጅት እንዳወጣው ዘገባ ዩናይትድ ስቴትስ፣ እንግሊዝ፣

እና የዓለም ባንክ (ሌሎች የአውሮፓ ወይም ደግሞ በኢንዱስትሪ የበለጸጉ

አገሮችን ሳይጨምር) ከ50-60 በመቶ የሚሆነውን የህወሐትን ለማኝ መንግስት

ሀገራዊ ዓመታዊ በጀት ለበርካታ ዓመታት ባለማቋረጥ ሲሸፍኑ የቆዩ ናቸው፡፡

ዳምቢሳ ሞዮ የሞተ እርዳታ/Dead Aid በሚለው መጽሐፏ በግልጽ

እንዳስቀመጠቸው የህወሐት ገዥ አካል ዋነኛው የገቢ (በጀት) የመገኛ ምንጩ

የውጭ እርዳታ ሲሆን እጅግ በጣም ግዙፍ እና 97 በመቶ የሚሆነውን በጀት

የሚያገኘው ከዚሁ ከውጭ እርዳታ ነው በማለት አጠቃላዋለች፡፡

የበጀት ድጋፍ የሚለው የእርዳታ አሰጣጥ ዘዴ ለልማት እርዳታ በማለት ብዙ

ለጋሽ አገሮች ለድህነት ቅነሳ ስትራቴጂ በሚል ስልት ለበርካታ ታዳጊ አገሮች

በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች እርዳታውን ለመስጠት የመረጡት

የእርዳታ አሰጣጥ ዘዴ ነው፡፡ “የበጀት ድጋፍ” (በጀት ሰፖርት) የሚለው

የእርዳታ አሰጣጥ ዓይነት እ.ኤ.አ በ1989 በዓለም አቀፍ የግንዘብ ድርጅት፣

በዓለም ባንክ፣ እና በአሜሪካ የገንዘብ መምሪያ የዋሽንግተን

ስምምነት/Washington Consensus በሚል የተቋቋመ እና በቀውስ ውስጥ

ያሉ ሀገሮች ኢኮኖሚያቸው እንዲያንሰራራ እና እንዲረጋጋ በሚል እሳቤ

ሀገሮቹን በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ እና የሀገር ውስጥ የስራ ፈጣሪዎች

እንዲነቃቁ እና እንዲነሳሱ ተብሎ የተቀየሰ መጥፎ እና የኒዮሊበራል ጭራቃዊ

አሰራር እና ለእነርሱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንዲስማማ ተብሎ የተዘጋጀ ባዶ ተስፋ

ነው፡፡ (በአንድ መጽሐፍ ውስጥ ባለ አንድ ጽሑፍ ላይ የጸረ ኒዮሊበራል

አራማጅ በሆኑት ጆይ ስቲግልዝ ባቀረቡት ትችት ላይ መለስ እንዲህ ብሎ ነበር፣

“የኒዮሊበራል ፍልስፍና ያለቀለት ጉዳይ ነው፣ የአፍሪካን ተሀድሶ ሊያመጣ

አይችልም፡፡ ስለሆነም የአፍሪካን ተሀድሶ ለማምጣት እና እንደገና የአፍሪካ

መነሳሳት እንዲመጣ ከተፈለገ ሌላ አይነት አካሄድ መምጣት አለበት“)

“በዋሽንግተኑ ስምምነት” መቃብር ላይ ሌባ መንግስታት ከእርዳታ ሰጭ እና

አበዳሪ ድርጅቶች ጥያቄ እና ፍላጎት ከስምምነት እግረ ሙቅ እስራት ነጻ

በማድረግ እራሳቸው ሊጠለሉበት የሚችል የበጀት ድጋፍ የሚል ዛፍ አደገ፡፡

በበጀት ድጋፍ እርዳታ እና አበዳሪ ድርጅቶች የእርዳታ እና የብድር ቅድመ

ሁኔታዎችን መጫን አይችሉም ወይም ደግሞ እርዳታውን ወይም ብድሩን

ከሚቀበለው አገር የተለየ የፖሊሲ አካሄድ እንዲከተል የሚል ማስገደጃ ነገር

የለውም፡፡ ከዚያ ይልቅ ከእርዳታ እና ብድር ተጠቃሚው አገር የልማት ፖሊሲ

138

እና እስትራቴጅ እንዲሁም ድህነት ቅነሳ ፕሮግራሞች ጋር ሊስማሙ የሚችሉ

ስልቶችን መርጠው ይገባሉ፡፡ በቀላሉ ግልጽ ለማድረግ የበጀት ድጋፍ እርዳታ

እና ብድር ተቀባይ አገሮች ያሉትን የሌባ መንግስታት እና በሙስና የበከቱ

መሪዎችን ከህዝብ ተጠያቂነት እና ግልጸኝነት በመከላከል ተንሰራፍቶ

የሚገኘውን ሙስና ለመደበቅ ጥበብ የተሞላበት የአካሄድ ስልት ነው፡፡

እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 2009 አቶ መለስ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የበጀት

ድጋፍ በማድረግ የኢትዮጵያን የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እንዲረዱ

ለዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጥሪ አቀረበ፡፡ የእርሱ ተግባራዊ ሊሆን

የማይችል እና ከሚገባው በላይ የተለጠጠው የእድገት እና የትራንስፎርሜሽን

ዕቅድ በአብዛኛው በበጀት ድጋፍ በውጭ የልማት እርዳታ ላይ የተንጠለጠለ

እ.ኤ.አ በ2015 ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለማሰለፍ

የታቀደ የድንብርብር ዕቅድ ነው (2015 መቸ እንደሆነ ልብ ይሏል!)፡፡ መለስ

በተጨባጭ በተግባር ለማይገለጸው እና በቋፍ ላይ ለተንጠለጠለው ስሜታዊ

ዕቅድ ግዙፍ የሆነ የመሰረተ ልማት ግንባታ እና መጠነ ሰፊ የሆኑ የግብርና

ልማት ምርቶችን በማምረት ኢትዮጵያ የመካከለኛ ገቢ ካለቸው አገሮች ጋር

እኩል ትሰለፋለች የሚል የተወዣበረ አስተሳሰብን ይዞ ነው የድንብርብር ጉዞ

ሲጓዝ የነበረው፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት/United

States Agency for International Development ከ2011- 2015 ባዘጋጀው

አገራዊ የልማት ትብብር ሰነዱ ላይ እንዲህ የሚል ግልጽ መልዕክት አስፍሮ

ይገኛል፣ “ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ወደተረጋጋ ፈጣን

የኢኮኖሚ እድገት በማምራት ጠንካራ መሰረት ያላቸው የማህበራዊ

አገልግሎቶች እና የተመጣጠነ የህዝብ እድገት በማስመዝገብ ወደ አዲስ ምዕራፍ

ሽግግር ታደርጋለች፡፡“ ይላል! ማለት ቀላል ነገር ነውና፡፡ አሁን ላይ ሆነን

የተተነበየለትን የጊዜ ቀመር ስናሰላው 2015 ለመድረስ ሁለት ድፍን ሙሉ

ወራት ብቻ ይቀሩናል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ 2016 ለመድረስ ድፍን አንድ ዓመት

ይቀረናል፡፡ እናም ኢትዮጵያ ከዓለም ከመጨረሻዎቹ ደኃ አገሮች ሁለተኛ

እንደሆነች ጉዞዋን ቀጥላለች!!! የታየ ለውጥ አለ ከተባለ በህዝብ ሀብት

በሚተዳደረው የመገናኛ ብዙሀን ሌት ቀን እንደ መልካም ነገር የሚነዛው ባዶ

የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ብቻ ነው!

139

ልማታዊ መንግስት ከሌባ መንግስት ጋር ሲነጻጸር እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 25/2014 ፕሬዚዳንት ኦባማ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ከዓለም

በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ላይ ካሉ አገሮች አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ

እየሆነ ካለው ሌላ የተሻለ የእድገት ምሳሌ ሊሆን የሚችል በአፍሪካ አይገኝም፡፡“

የፕሬዚዳንቱ ንግግር በየትኛውም ትክክለኛ በሆነ መረጃ ላይ ተመስርቶ የተሰጠ

አይደለም፣ ሆኖም ግን ይህ ድርጊት አሳዛኝ ነው፣ ምክንያቱም አሁን በህይወት

በሌለው በመለስ ዜናዊ ዕኩይ የብልጣብልጥነት ዘዴ ተፈብርኮ የተነዛውን

የቅጥፈት ቁጥር እና ባዶ የምርቃና ትንተና እንዳለ በመውሰድ የታላቋ አገር

የአሜሪካ መሪ ሆነው እንደበቀቀን እንዳለ መድገማቸው አሳፋሪ ነገር ነው፡፡

ባለፉት አስርት ዓመታት መለስ ዜናዊ እና ደቀመዝሙሮቹ በ21ኛው ክፍለ ዘመን

የመጀመሪያዎች አስርት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ልማታዊ መንግስታቸው በተከለው

ጥበብ የተሞላበት አካሄድ በኢትዮጵያ ላይ እስከ አሁን ታይቶ የማይታወቅ

እድገት እንደተመዘገበ በሞኖፖል በተቆጣጠሩት የመገኛ ብዙህን ሌት ቀን

ድንፋታቸውን ያሰሙ ነበር፣ አሁንም በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡ እ.ኤ.አ ማርች

2009 መለስ የውሸት ፈገግታ በተቀላቀለበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ12.8

በመቶ ያድጋል በማለት ትንበያ ሰጥቶ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 የህዝብ ተወካዮች

ምክር ቤት ለተባሉት አጫፋሪዎቹ እንዲህ የሚል ማረጋገጫ ሰጥቶ ነበር፣

“በዚህ ዓመት 10.1 በመቶ የሆነ የኢኮኖሚ እድገት የምናስመዘግብ ሲሆን የዋጋ

ግሽበት ግን ወደ 3.9 በመቶ ይወርዳል፡፡“ እንደዚህ ዓይነቶቹ ከመጠን በላይ

የተጋነኑ የድንፋታ ንግግሮች በተለያዩ በዓለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ ጥንቃቄ

በተሞላበት መልኩ ስለሚታዩ እና ስለሚመዘኑ እርባና የለሽ በመሆን ከቁጥር

የሚገቡ አይሆኑም፡፡ የዓለም የልማት ማዕከል/Center for Global

Development እ.ኤ.አ በ2010 ባወጣው ዘገባ መሰረት እ.ኤ.አ ከ1996 – 2008

ድረስ አማካይ ዓመታዊ የኢኮኖሚ እድገቱ 4.1 በመቶ እንደነበር ጠቁሟል፡፡

እንደዚሁም ደግሞ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የወቅቱን የዓለም ሁኔታ

ከግምት በማስገባት እ.ኤ.አ በ2009 ኢትዮጵያ 6 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት

ልታስመዘግብ እንደምትችል ትንበያ ሰጥቶ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2007 ዘ

ኢኮኖሚስት የተባለው መጽሔት እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር፣

“የኢትዮጵያ መንግስት ከ2003/04 ጀምሮ በየዓመቱ ኢኮኖሚው በሚያስደንቅ

ሁኔታ በ10 በመቶ አድጓል የሚል መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ሆኖም ግን ትክክለኛው

የእድገት መጣኔ ከ5-6 በመቶ አካባቢ ነው፡፡ ይህም የእድገት መጣኔ ከሰሀራ

በታች ካሉ አገሮች አማካይ የኢኮኖሚ እድገት በጣም በትንሹ ከፍ ሊል

ይችላል“ ብሏል፡፡ ይኸው ዘ ኢኮኖሚስት የተባለው መጽሔት ማርች 2012

140

ባወጣው ዘገባ የመለስን የቅጥፈት የኢኮኖሚ እድገት ድንፋታ በማስመልከት

እንዲህ የሚል ማጠቃለያ ሰጥቶ ነበር፣ “የኢትዮጵያ መንግስት ጠቅላይ

ሚኒስትር የሆኑት አቶ መለስ ዜናዊ የተነበዩት ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ

እድገት ተምኔታዊ ይመስላል“

“የመለስ ዜናዊ የውሸት የኢኮኖሚ እድገት” በሚል ርዕስ አዘጋጅቸው በነበረው

ትችቴ ላይ ከጥርጣሬ በላይ በግልጽ ትንታኔ የሰጠሁበት ስለነበረ መለስ

የተቀቀሉ የስታቲስቲክስ ቁጥሮችን እያወጣ በእጅጉ የተሳሳተ መረጃ ይሰጥ

እንደነበር አጠያያቂ ጉዳይ አይደለም፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 ጥቂት የእርሱ

የስታቲስቲክስ ቁጥሮች ስህተት እንደነበረባቸው ለማመን በሚያስመስል መልኩ

የአካሄድ አቅጣጫውን ቀየር አድርጎ እንዲህ ብሎ ነበር፣ ”የኢኮኖሚ እድገቱ

አሀዝ ትክክለኛነት አከራካሪ ሆኗል፡፡ እናም እኛው እርስ በእርሳችን እና ከልማት

አጋሮቻችን ጋር መንግስታችንን ጨምሮ ቀጣይነት ባለው መልኩ ጥቂት በሆኑ

አሀዛዊ መረጃዎች ላይ ውይይት አድርገናል፡፡ ሆኖም ግን ዋናው ጉዳይ ማንም

ሊያስተባብለው የማይችለው ኢኮኖሚያችን ከነበረበት በጣም ዝቅተኛ የእድገት

ደረጃ በመነሳት ባለፉት ስምንት፣ አስር እና ከዚያ በላይ በሆኑ ዓመታት ጊዜ

ውስጥ ከፍተኛ ወደ ሆነ የእድገት ደረጃ ተሸጋግሯል“ ነበር ያለው፡፡ እንዲህ

አይነቱን አካሄድ ቤንጃሚን ዲስራሊ በሚገባ ተመልክተውት ኖሮ እንዲህ ነበር

ያሉት፣ “ቅጥፈቶች አሉ፣ ነጭ ቅጥፈቶች እና አሀዞች/ቁጥሮች ቅጥፈቶች ።

የመለስ በእራሱ አስተሳሰብ እና አካሄድ አይነት የፈጠረው ልማታዊ መንግስት

ሲመረመር በእርግጠኝነት በስስ መጋረጃ የተሸፈነ የኒዮ ሶሻሊስት ርዕዮት

ዓለምን ካባ በማጥለቅ ከኒዮሊበራል ርዕዮት ዓለም በተቃራኒው በመቆም

ድምጹን ከፍ አድርጎ በመጮህ ከወዲያ ወዲህ እያምታታ በመኖር የዘረፋ

ከረጢቱን ለመሙላት የሚናውዝ የሌቦች መንግስት ነው፡፡ በኢራስመስ

ዩኒቨርስቲ ባላጠናቀቀው የሁለተኛ ዲግሪ መመረቂያ የማሟያ ጹሁፍ ላይ መለስ

የኒዮሊበራል ርዕዮት ዓለምን እንዲህ በማለት ኮንኖታል፣ “የኒዮሊበራል

መንግስት እንደ አዳኝ አጥቂ አውሬ ነው፡፡ በጨለማ ውስጥ ሆኖ የሚመለከት

መንግስት ነው“ በማለት ገልጾታል፣ “በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ተሳትፎ እጅግ

የቀነሰ መንግስት“፡፡ መለስ ሙግቱን በመቀጠል የኒዮሊበራል መንግስት

መዋቅራዊ አቅመቢስነት እንዳለበት ተቁሞ ይህ መንግስታዊ ፍልስፍና “የቀለበት

አዙሪቱን እና የድህነት ወጥመድን ሊያሸንፍ እና ሊበጣጥስ አይችልም” ብሏል፡፡

ከአጥቂ/አዳኝ እና በጨለማ ውስጥ ከሚመለከት የኒዮሊበራል መንግስት

በተቃራኒ በኩል ያለውን የእርሱን ልማታዊ መንግስት ደግሞ መለስ እንዲህ

141

የሚል የመሞገቻ ዳህራ አቅርቧል፣ “ልማታዊ መንግስት ልማትን የሚያስበው

በመጀመሪያ ደረጃ እንደ የፖለቲካ ሂደት ሆኖ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሂደት

በቀጣይነት የሚመጡ ናቸው፡፡“ የመለስ ልማታዊ መንግስት የልማት ሂደቱን

ያቅዳል፣ ያደረጃል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣ ይገመግማል፣ ከዚያም አጠቃላይ

ሂደቱን ይቆጣጠራል፡፡ የኪራይ ሰብሳቢነት [የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች

አብዛኛውን ጊዜ ግለሰቦች፣ ወይም ደግሞ ቡድኖች፣ በሌሎች ግብር ከፋዮች

ወይም ደግሞ ተጠቃሚዎች አለያም ሌሎች ግለሰቦች ኪሳራ በየተለየ መልኩ

ኢኮኖሚያዊ ውድድር በማድረግ መንግስት በሌሎች ላይ ግብር እንዲጥል፣

ከእራሱ ማዕከላዊ ግምጃ ቤት ወጭ እያደረገ እንዲሰራ እና የቁጥጥር

ፖሊሲዎችን እያወጣ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን በመቆጣጠር ለእነርሱ

የገንዘብ ወይም ሌሎች ልዩ ጥቅማጥቅሞች የሚያስገኝ የአሰራር ሂደት ነው

በማለት ይገልጹታል] ባህሪን ለማጥፋት የተሟላ አቅም ያለው ብቸኛው

መንግስታዊ ተቋም ልማታዊ መንግስት ነው ይላል መለስ፡፡ በመለስ የኢኮኖሚ

ፍልስፍና መሰረት የግል ዘርፉ በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃዎች ላይ ቋሚ ተመልካች

ነው እናም ምንም ዓይነት የተነሳሽነት ስሜት የማያሳይ አጋር እንኳ ያልሆነ

ኢኮኖሚውን በብቸኝነት ተቆጣጥሮ ለሚያዝዝበት ለልማታዊ መንግስት ታማኝ

ታዛዥ ነው፡፡ መለስ እንዲህ ይላል፣ “ልማታዊ መንግስት ከሌለ አብዛኞቹ

ወይም ደግሞ እነዚህ ሁሉም በመልማት ላይ ያሉ አገሮች በድህነት ወጥመድ

ውሰጥ በመያዝ ወደ ድህነት አራንቋ ውሰጥ በመዘፈቅ የስራ እና የንግድ

እንቅስቃሴውን የሚያራምዱት ስራ ፈጣሪዎች እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው

የህብረተሰብ ክፍል መደቦች ሊፈጠሩ አይችሉም“ ይላል፡፡ የመለስ “የልማታዊ

መንግስት” ፍልስፍና በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ያሉትን የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ

እና የፖለቲካ ችግሮች ለመፍታት ታምራዊ መፍትሄ በመስጠት እድገትን

ማምጣት ይቻላል በሚል የፍልስፍና ዳህራ ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡

“የመለስ ዜናዊ የውሸት ኢኮኖሚክስ” በሚል ርዕስ ባዘጋጀሁት ትችቴ ላይ

የሚከተለውን ማብራሪያ አስፍሬ ነበር፣ “የአቶ መለስ ‘የእድገት እና

የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ’ (የልማታዊ መንግስት መሰረት የሆነው ዋልታ እና

ማገር) ሊኖሩን የሚገቡ ህልቆ መሳፍርት የሌላቸው የፍላጎት ዝርዝሮች ከመሆን

ያለፈ ትርጉም የለውም፡፡ ለኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ራዕይ በመንደፍ

ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የጎለበተባት፣ መልካም አስተዳደር እና ማሕበራዊ ፍትህ

የሰፈነባት አገርን ለመፍጠር ዕቅድ የያዘ ነው፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የተሻሻሉ

ቴክኖሎጂዎችን የሚጠቀም ዘመናዊ እና ምርታማ የሆነ የግብርና ዘርፍ እና

ምርታማ የሆነ የኢንዱስትሪ ዘርፍ በመመስረት እና በአጠቃላይ መልኩ ዘመናዊ

142

ኢኮኖሚ በመገንባት የዜጎችን የነፍስ ወከፍ ገቢ ከፍ በማድረግ መካከለኛ ገቢ

ያላቸው አገሮች ካላቸው ገቢ ጋር እኩል እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ ፈጣን፣

ቀጣይነት እና ሁሉንም ዜጎች እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ የኢኮኖሚ ዕድገት

ለማምጣት እንደ ዋና የማስፈጸሚያ ምሰሶዎች ተደርገው የተያዙት ግብርናን

እንደ ዋነኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ምንጭ ማድረግ፣ ኢንዱስትሪው በኢኮኖሚው

ላይ ገንቢ የሆነ ሚና እንዲጫወት አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን

ማማቻቸት፣ መሰረተ ልማትን እና ማህበራዊ ልማትን ማስፋፋት፣ የማስፈጸም

አቅምን ማጎልበት እና መልካም አስተዳደር በየደረጃው እንዲጎለብት እና ስር

እንዲሰድ ማድረግ፣ ለሴቶች እና ወጣቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት እንዲጠናከሩ

እና ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል“ በማለት ከፍተኛ የሆነ

ድንፋታ ተደርጓል፡፡

ሆኖም ግን እነዚህ ባዶ የምጣኔ ሀብት መፈክሮች፣ በሚያሰለች ሁኔታ

ተደጋግመው የሚነገሩ አባባሎች፣ ባበለስልጣኖች እየተፈበረኩ የሚነገሩ አዳዲስ

ቃላት እና ሀረጎች፣ እንዲሁም ታዋቂነት ያላቸው የዲስኩር ማጣፈጫ አባባሎች

በየጊዜው እየተዥጎደጎዱ የሚባሉ እና የሚነገሩ ቢሆንም የአቶ መለስ የዕድገት

እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እንደሚደሰኮርለት ተጨባጭነት ያለው ውጤት

ከማምጣት እና ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ከማስገኘት ይልቅ ምጣኔ ሀብታዊ

ሀፍረት ተከናንቧል፡፡ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ አሳፋሪ ከሆነ

ልማታዊ መንግስቱም ከዚህ የተለየ ዕጣ ፈንታ የለውም! እ.ኤ.አ በ2009

በበርሊን ከተማ በሚካሄደ በአንደ በከፍተኛ የስልጣን ደረጃ ላይ ባሉ የምዕራብ

ለጋሽ ሀገሮች የፖሊሲ አውጭዎች ስብሰባ ላይ አንድ የጀርመን የዲፕሎማት

ሰው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ችግሮች ዋና መሰረት “የመለስ ደካማ የሆነ የምጣኔ

ሀብት ግንዛቤ መኖር ነው” ብለው ነበር፡፡ (ውይ የሚያሳዝን ነገር ነው!

የጀርመኑ ዲፕሎማት ያልተገነዘቡት እና ያልተረዱት ጉዳይ አለ፣ ይኸውም

መለስ የማስተርስ ዲግሪውን ከኢራስመስ ዩኒቨርስቲ በምጣኔ ሀብት ሊያገኝ

ትንሽ ሲቀረው ነበር የከሸፈው፣ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ1991 ኦፕን ዩኒቨርስቲ

እየተባለ (ኮሮስፖንደንስ ኮርስ) በሚጠራው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ቢዝነስ

አድሚኒስትሬሽን እንዳጠና እና (ከእርሱ ክፍል አንደኛ በመውጣት

እንደተመረቀ) በውል ሳያጤኑት ቀርተው ይመስለኛል፡፡)

መለስ የልማታዊ መንግስትን የአመራር ቀጣይነት (አምባገነንነት) ለማሳመን

በጣም ረዥም ርቀት ተጉዟል፣ ምክንያቱም የፖሊሲ ቀጣይነት አስፈላጊነት ያለ

በመሆኑ ነው ብሏል፡፡ ልማታዊ ፖሊሲ አንድን ደኃ አገር በአንድ በተወሰነ

143

የምርጫ የጊዜ ገደብ ውስጥ በሚደረግ ጥረት ወደበለጸጉት አገሮች ተርታ

ለማሸጋገር ያለው አቅም አስተማማኝ አይደለም፡፡ ቀጣይነት ያለው እና ፈጣን

የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ ከተፈለገ የፖሊሲ ቀጣይነት መኖር አስፈላጊ

ጉዳይ ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ባለበት አገር ላይ የፖሊሲ ቀጣይነት

መኖር ሊወገድ የሚችል ጉዳይ አይደለም፡፡ ልማትን የበለጠ ሊጎዳው

የሚችለው ነገር የፖለቲካ ሰዎች ከአንድ የምርጫ የጊዜ ገደብ በኋላ አዛልቀው

ለማየት አለመቻላቸው ነው፡፡ ስለሆነም ልማታዊ መንግስት ለረዥም ጊዜ

በስልጣን ላይ ለመቆየት እና ስኬታማ የሆኑ የልማት ፕሮግራሞችን ለማካሄድ

እንዲችል ከተፈለገ የዴሞክራሲያዊ ስብዕናን መላበስ አይጠበቅበትም የሚል

መሞገቻ አቅርቧል፡፡ በሌላ አባባል የልማታዊ መንግስት ዋና መገለጫ

ኢዴሞክራሲያዊ መሆን ነው የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

የግል ዘርፉ ሙሉ ለሙለ “ለልማታዊ መንግስቱ” እጅ መስጠት አለበት

ምክንያቱም በመልማት ላይ ባለ አገር ያ መንግስት ብቻ ነው የተረጋጋ፣

ዴሞክራሲያዊ እና ከዚህም ጋር ተያይዞ ልማታዊ ጥሪ የሚያደርገው… ልማታዊ

መንግስት የግል ዘርፉን ተዋናዮች የሚያከናውኗቸው ተግባሮች ልማታዊ ወይም

ደግሞ ክራይ ሰብሳቢ መሆን ባለመሆናቸው ላይ መሰረት በማድረግ ለመሸለም

እና ለመቅጣት ችሎታው እና ፍላጎቱ እንዲኖረው የግድ ይላል፡፡

በማጠቃለያውም መለስ የሚከተሉትን አስደንጋጭ የሆኑ ሆኖም ግን በከፍተኛ

ደረጃ ለእራስ ጥቅም የቆሙ ነገሮችን አስቀምጧል፣

ለልማታዊ መንግስት ምቹ የሆኑ ነገሮች በሌሉበት ጊዜ የተረጋጋ ዴሞክራሲ ብቅ

እንዲል ማሰብ በእርግጠኝነት በጣም ሩቅ ነው፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ ምቹ የሆኑ

ነገሮች ባሉበት እና ለዴሞክራሲ መስፈን ግን ዋስትና በሌለበት ሁኔታ

በእርግጠኝነት የልማታዊ እና የዴሞክራሲያዊ መንግስት የመኖር ዕድል ብቅ

ይላል፡፡ በዚህም መሰረት በመጨረሻ በደኃ ሀገር የተረጋጋ ዴሞክራሲ የመኖር

ዕድሎች ከልማታዊ መንግስት ብቅ ማለት እና ከእርሱ ጋር አብሮ ከሚሄደው

ፈጣን ልማት ጋር በእጅጉ የተዛመዱ እና የተቆራኙ ሆነው ይገኛሉ፡፡

በግልጽ ለማስቀመጥ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት፣ ልማት፣ ዴሞክራሲ፣

መልካም አስተዳደር፣ የሰብአዊ መብት ጥበቃ፣ ወዘተ ለማስመዝገብ

የምትችለው ለልማታዊ መንግስት ርዕዮት ዓለም እራሱን በጽናት ያቆመ እና

በአንድ ሰው አመራር ስር በተዋቀረ በአንድ ዘላለማዊ በሆነ በማይለወጥ

የፖለቲካ ፓርቲ ስትመራ ብቻ እና ብቻ ነው፡፡ ይህ በየትኛውም መደበኛ በሆነ

ሙያው በሚጠይቀው የትምህርት ክፍል ገብቶ ሳይማር እራሱን አዋቂ አድርጎ

144

ከሚያቀርብ እብሪተኛ ሰው የሚመጣ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ልዩ እና ቆንጆ

ህልዮት ነው!

መለስ እራሱን የተዋጣለት የምጣኔ ሀብት ባለሙያ እና ለሁሉም ነገር አለሁ

የሚያስብል ባለብዙ ዘርፍ የዕውቀት ባለቤት እንዲሆን ይመኛል፡፡ በወጣትነት

ዘመኑ ጫካ በነበረበት ጊዜ አሁን ከተጣለው የማርክሳውያን የፖለቲካል

ኢኮኖሚ ህልዮት ጋር በመጣበቅ መለስ (እንዲሁም ደቀመዝሙሮቹ) ስልጣንን

ከተቆናጠጡ በኋላ ስብዕናውን ከፍ አድርጎ በመኮፈስ በኢትዮጵያ የአብዮታዊ

ዴሞክራሲ እና የልማታዊ መንግስት ዋና መሀንዲስ እና ቀማሪ በማድረግ

በየአደባባዩ ዲስኩሮቹን በማቅረብ እራሱን ሰየመ፡፡ ሊታመን በማይችል መልኩ

መለስ ወይም የእርሱ አታላይ እረዳቶቹ የአብዮታዊ ዴሞክራሲን እና የልማታዊ

መንግስትን ህልዮት እንዲቀምሩ እና ወደ ተግባር እንደዲያሸጋግሩ እድሉን

ወስደው ነበር፡፡ ያንን ለመተግበር ከመሞከር ይልቅ ለምጽዋት እጆቻቸውን እና

መዳፎቻቸውን በመዘርጋት በቀጥታ ወደ ሃብታሞቹ በሮች ለምጽዋት

የሚሄዱባቸውን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት፣ የዓለም ባንክ እና የምዕራቡ

ዓለም መንግስታት ኤምባሲዎች ኒዮሊበራል እያሉ የስድብ ናዳቸውን

ማዥጎድደጎድ መረጡ፡፡ “ገንዘብ፣ ጉቦ፣ በጣም አስገራሚ ነገር ነው!!!“

ታላቁ ቅጥፈት በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ልማታዊ መንግስት፣

ታላቁ የታሪክ ፕሮፓጋንዳ ሰው እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ውሸት በዋሸህ ቁጥር እና

ያንን ውሸት እየደጋገምክ ባቀረብከው ጊዜ በእርግጠኝነት ሰዎች እውነት

አድርገው ይወስዱታል፡፡“ ያ ታላቅ ውሸት በዓለም ታላቅ መሪ እየተደጋጋመ

በሚቀርብበት ጊዜ ያ ታላቅ ውሸት ታላቅ እውነታ ሊኖረው የሚያስችል እቅም

ይኖረዋለ፡፡ ሆኖም ግን “ውሸት የፈለገውን ያህል ትልቅ ቢሆንም እውነት ሊሆን

አይችልም፣ ስህተት ትክክል ሊሆን አይችልም እንደዚሁም ሰይጣናዊ ስራ

በታላላቆቹ እና በኃይለኞቹ በተደጋጋሚ የሚፈጸም በመሆኑ ምክንያት ወይም

ደግሞ በአብዛኛው ህዝብ ተቀባይነት በማግኘቱ ብቻ በምንም ዓይነት መለኪያ

ቢሆን ደግነትን ሊጎናጸፍ አይችልም፡፡“

እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 25/2014 ፕሬዚዳንት ኦባማ በኢትዮጵያ ካለው ገዥ

የልዑካን ቡድን ጋር በዋሽንግተን በተገናኙ እና ንግግሮቻቸውን ባደረጉ ጊዜ

145

በሚያሳዝን ሁኔታ ይቅርታ ሊደረግላቸው የማይችሉ መግለጫዎችን ሰጥተዋል፡፡

እንዲህ ብለዋል፣

… በዓለም ላይ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገትን ከሚያስመዘግቡ አገሮች መካከል

አንዷ የሆነችው እና በአፍሪካ አንጸባራቂ የእድገት ስኬቶችን እና እመርታዎችን

እያሳየች ካለቸው ኢትዮጵያ ውጭ ሌላ የተሻለ አገር በምሳሌነት መጥቀስ

አደጋች ይሆናል፡፡

በእውነቱ በአንድ ወቅት ህዝቦቿን ለመመገብ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበረች

ሀገር በአሁኑ ጊዜ ግን መጠነ ሰፊ የሆነ እድገትን ስታስመዝግብ ተመልክተናል፡፡

በአህጉሩ በግብርና ምርት የመሪነቱን ቦታ መያዝ ብቻ ሳይሆን እንዲያውም

በቅርብ ጊዜ ውስጥ የግብርና ምርት ውጤቶችን ብቻ ሳይሆን ኃይልንም ወደ

ውጭ አገር እንደምትልክ ይታመናል፣ ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ

እየተካሄደ ያለው እድገት ለዚህ እውን መሆን ዋና መሰረት ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት በቀላሉ በማረጋገጥ ሊደረስበት

የሚችልን እውነታ በተሳሳተ መረጃ ላይ መሰረት በማድረግ ለጉዳዩ ትኩረት

ሳይሰጡ ጉዳዩን ለህዝብ ይፋ ማድረጋቸው አሳፋሪ ነገር ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ

መግለጫውን ከመስጠታቸው ሶስት ወራት በፊት የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም

አቀፍ የልማት ኤጀንሲ/United States Agency for International

Development እ.ኤ.አ ኦገስት 15/2014 ያቀረበው ዘገባ የፕሬዚዳንቱን መግለጫ

ሙሉ በሙሉ ይቃረናል፡፡

ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ነው ቢባልም ኢትዮጵያ በዓለም ላይ

ካሉ ደኃ አገሮች መካከል አንዷ ሆና ቀጥላለች፡፡ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ

የምግብ እጥረት እና አስከፊ የሆነ የምግብ ዋስትና እጦት በተለይም በገጠሩ

ህዝብ እና አነስተኛ ይዞታ ባላቸው አርሶ አደሮች ላይ የበረታ ሆኖ ይታያል፡፡

በኢትዮጵያ ከሚገኙ እድሜያቸው ከ5 ዓመታት በታች ካሉ ልጆች መካከል

በግምት 44 በመቶ የሚሆኑት ከፍተኛ ለሆነ አስከፊ የተመጣጠነ የምግብ

እጥረት አለባቸው ወይም ደግሞ ከእድሚያቸው ጋር ሊመጣጠን በማይችል

መልኩ የቀጨጩ ናቸው፡፡ ይህ የተመጣጠነ ምግብ ያለማግኘት ችግር ሊመለስ

የማይችል የክህሎት እና የአካል ብቃት ማነስን ያስከትላል፡፡ እንደ የዓለም

የምግብ ፕሮግራም ዘገባ ከሆነ የረዥም ጊዜ አስከፊ የሆነ የተመጣጠነ የምግብ

እጥረት የሚያስከትለው ውጤት የኢትዮጵያን መንግስት በግምት በየዓመቱ

146

የአጠቃላይ ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ምርትን 16.5 በመቶ ያህል ወጭ እንዲያወጣ

ያስገድደዋል፡፡

የህወሐት አገዛዝ እንደሚለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በየዓመቱ በ10 በመቶ

እያደገ የመጣ ከሆነ ሆኖም ግን በተመጣጠነ የምግብ እጥረት ምክንያት

በየዓመቱ በግምት 16.5 በመቶ ያህል ዋጋ ያለውን ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ምርት

የሚያሳጣ ከሆነ ሀገሪቱ በኢኮኖሚ አደገች ማለት ይቻላልን? ይህ ሁኔታ አላይስ

“በሚያሳይ መስታወት” በሌዊስ ካሮል ከተማ ከንግስቲቱ ጋር ያደረገችውን

ንግግር እንዳስታውስ አደረገኝ፡፡ ንግግሩ እንዲህ የሚል ነበር፣ “መሞከር ምንም

ጥቅም የለውም፣ ማንም የማይሆኑ ነገሮችን ማመን ስለማይቻል“ አለች አላይስ

ንዴት በተቀላቀለበት ሁኔታ፡፡ ንግስቲቱ አላይስን እንዲህ በማለት አረመቻት፣

“ብዙም ልምድ የለሽም ለማለት እችላለሁ፡፡ እኔ በአንች የእደሜ ጣሪያ ላይ

በነበርኩበት ጊዜ ሁልጊዜ በቀን ለግማሽ ሰዓት አደርገው ነበር፡፡ ለምን መሰለሽ፣

አንዳንድ ጊዜ ከቁርስ በፊት ስድስት ያህል የማይሆኑ የማይታመኑ ነገሮችን

አስብ ስለነበር ነው“ አለቻት፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ስለህወሐት ለማኝ ገዥ አካል

ከቁርስ በፊት ቢያንስ ስድስት የማይሆኑ የማይታመኑ ነገሮችን ማሰብ ግድ

ይሆንብናል፡፡

እስከ አሁን ድረስ ለበርካታ ዓመታት መለስ እና ደቀመዝሙሮቹ ስለ

ፕሮዳክቲቭ ሴፍቲ ኔት ፕሮግራም/Productive Safety Net Program

(በውጭ እርዳታ የበጀት ድጋፍ አገኛከሁ በሚል ስሌት) የምርት እህል እጥረትን

በማስወገድ እና የቤተሰብን እና የህብረተሰቡን ቋሚ ሀብት በመንከባከብ

የምግብ እርዳታ ጥገኛ መሆንን ማቆም ይቻላል የሚል ቅስቀሳ ያደርጉ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ኦክቶበር በ2011 መለስ ለፓርቲው ታማኞች እንዲህ ብሏቸው ነበር፣

“የተትረፈረፈ ምርት ሊያስገኝ የሚያስችል የዕቀድ ዘዴ አዘጋጅተናል፣ እናም

እ.ኤ.አ በ2015 ምንም ዓይነት የምግብ እርዳታ ሳያስፈልገን እራሳችንን መመገብ

እንችላለን፡፡ የእርሱ የተተረፈረፈ ምርት የማምረት ዕቅድ ሊሳካ ይችል የነበረው

ለም እና ዋና የምርት ማስገኛ የነበረውን በሚሊዮኖች ሄክታር የሚቆጠር ለም

መሬት በረዥም ጊዜ ኪራይ እና በርካሽ ዋጋ ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች

እየተባሉ ለሚጠሩ እና ምርቱን እያመረቱ ወደ ውጭ እያወጡ በመሸጥ ትርፍ

ከማግበስበስ ውጭ ሌላ ዓላማ ለሌላቸው የውጭ ዜጎች (መሬት ተቀራማቾች)

በሊዝ መሸጥ ነበር፡፡“ የተባበሩት መንግስታት ቅርንጫፍ የሆነው እና ረኃብን

ማስወገድ እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ዓላማው አድርጎ የሚንቀሳቀሰው

147

እንደ ትልቁ የሰብአዊ መብት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዘገባ ከሆነ

እ.ኤ.አ በ2014 ለረሀብ ሰለባ የተጋለጡ 2.7 ሚሊዮን ለሚሆኑ

ኢትዮጵያውያን/ት የምግብ እህል እርዳታ ያቀረበ ሲሆን ለ6.5 ሚሊዮን

ለሚሆኑ ለምግብ እህል እጥረት እና ልዩ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አደጋ

ተጋላጭ ለሆኑ የትምህርት ቤት ልጆች፣ አርሶ አደሮች፣ ከኤች አይቪ ጋር

የሚኖሩ ሰዎች፣ እናቶች፣ ህጻናት፣ ተረጂ ስደተኞች እና ሌሎችን ለመርዳት

እቅድ ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 የሰብአዊ እርዳታ

ፍላጎት 3.76 ሚሊዮን ለሚሆን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ፣ በ2011

ደግሞ ቁጥሩ በመጨመር ለ4.5 ሚሊዮን ህዝብ፣ በ2010 ደግሞ ለ5 ሚሊዮን

እና በ2009 ቁጥሩ በመጨመር 6 ሚሊዮን ሲሆን በ2008 በከፍተኛ ደረጃ ከፍ

በማለት ለ34 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን/ት (የአገሪቱን 40 በመቶ የሚሆነው)

ለከፋ ርኃብ ተጋልጦ ነበር፡፡

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ የምግብ እርዳታ የሚተዳደረው እና የሚመራው

በዋናነት በሶስት የውጭ ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች (ምግብ

ለተራቡ/Food for Hungry፣ የህጻናት አድን ድርጅት/Save the Children

የካቶሊክ እርዳታ አገልግሎቶች/Catholic Relief Services በአንድ የሀገር

ውስጥ ባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ማለትም ማህበረ ረድኤት

ትግራይ/Relief Society of Tigray አማካይነት ነው፡፡ ማህበረ ረድኤት

ትግራይ/ማረት እራሱን የህወሐት የሰብአዊ እርዳታ ክንፍ አድርጎ ይቆጥራል፡፡

ቀደም ሲል እንደገለጽኩት “የበጎ አድራጎት እና ማህበራት አዋጅ” እየተባለ

የሚጠራው አዋጅ ከወጣ በኋላ እ.ኤ.አ በ2010 የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት

ጊዜ ውስጥ ብቻ በኢትዮጵያ በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩት የሲቪል ማህበረሰብ

ድርጅቶች ቁጥር ቀደም ሲል ከነበረበት ከ4,600 ወደ 1,400 ዝቅ ብሎ ነበር፡፡

አብቸኛዎቹ በሀገር ውስጥ እንዲንቀሳቀሱ የተፈቀደላቸው የሲቪል ማህበረሰብ

ድርጅቶች የህወሐት ቅርንጫፎች ወይም ደግሞ በግል ወይም በድርጅት

ከህወሐት ጋር አጋርነት የመሰረቱ እና ከድርጅቱ ጋር ዝምድና ያላቸው ብቻ

ነበሩ፡፡ ህወሐት የውጭ እርዳታን የእራሱ ቅርንጫፍ በሆነው በህወሐት/ማረት

አማካይነት ያስተዳድራል፡፡ በቀላል አነጋገር የህወሐት ገዥ አካል ለልማት

እርዳታ በሚል ለምኖ የሚያገኘውን የልማት እርዳታ ከዓላማው ውጭ እና

በእራሱ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅቱ አማካይነት በህገወጥ መንገድ የገዥውን

መደብ አመራሮች እና አባላት ያበለጽጋል፡፡ ከዚህ አንጻር ሲገመገም ይህ

ድርጊት የለማኝ መንግስት መገለጫ ባህሪ ነው፡፡

148

የለማኝ መንግስት አወዳደቅ በኢትዮጵያ፡ ኃብታም ለማኞች በመለመን ድህነትን

ሊያጠፉ እና የኢኮኖሚ ልማትን ሊያመጡይችላሉን?

ከዚህ ቀደም ሲል አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ የአፍሪካ ለማኞች

አለቃ ነው የሚል ጽሁፍ ጽፌ ነበር፡፡ ይህንን መግለጫ ከተንኮል ወይም ደግሞ

ለሰውየው ክብር ካለመስጠት አልነበረም የተናገርሁት፣ ሆኖም ግን

በተጫባጭመረጃላይበመመስረት እንጅ፡፡ እ.ኤ.አ ኤፕሪል 2012 መለስ ቻይና

ደይሊ ለተባለው ጋዜጣ እንዲህ የሚል ቃል ሰጥቶ ነበር፣

“እውነታውእናዋናውነገርይህንንየአፍሪካውያንን/ትንየመሰብሰቢያአዳራሽእንዲገነ

ባቻይናውያንን/ትንየጠየቁአፍሪካውያን/ትናቸው፡፡ ይህንን የመሰብሰቢያ አዳራሽ

ለመገንባት የጠየቁት ቻይናውያን/ት አይደሉም፣ እኛ ነን የጠየቅነው፡፡

እንዲገነቡልን ጠየቅናቸው እናም ተስማሙ፣ ከዚያም አጠናቅቀው አስረከቡን፣

ይህንን የምንተችበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለንም፡፡“ ቻይናውያን/ት

ህንጻውን ለመገንባት 200 ሚሊዮን ዶላር ወጭ በማድረግ የግንባታ ስራውን

አጠናቅቀው የአፍሪካ ህብረት የስብሰባ አዳራሽን አስረክበዋል፡፡

በቀላል አነጋገር አፍሪካውያን/ት እራሳቸው የእራሳቸው አሻራ ያረፈበትን ህንጻ

በአፍሪካውያን የህንጻ ግንባታ ገንዘብ መስራት ይችሉ ነበር፡፡ ሆኖም ግን

በሚለመን ወይም ደግሞ ከሰው ኪስ ከሚወጣ ገንዘብ መስራት እየተቻለ ለምን

ተብሎ ከእራስ ኪስ ይውጣ? በቁስል ላይ እንጨት እንዲሉ በብር የተሰራው

የወለሉ ንጣፍ እና በዋናነት የአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ዋና ዳህራ

የሆነው ንጣፍ በሚያስደነግጥ ሁኔታ የተገለበጠ ግዙፍ የለማኝ ቦርጭን

ይመስላል፡፡ ለዚያም ነው “የአፍሪካ ለማኞች የመሰብሰቢያአዳራሽ” በሚል ርዕስ

በንዴት ተነሳስች ትችቴን ለመጻፍ የተገደድኩት፡፡ የመለስ ልማታዊ መንግስት

እና የደቀመዝሙሮቹ ትርፍ እና ኪሳራ ስሌት መሰረት ያደረገው በአንድ ዓይነት

አመክንዮ በተንጠለጠለ ምርኩዝ ነው፡ በእራስ መንገድ በመለመን የኢኮኖሚ

ልማት እና እድገት ማምጣት እየቻልክ ኢኮኖሚውን በእራስህ ጥረት እና ጥሪት

ለማሳደግ ለምን ትደክማለህ?

የሞተ እርዳታ/Dead Aid በሚል ርዕሰ በተጻፈው መጻሐፏ ዳምቢሳ ሞዮ

በእርዳታ እና በብድር ስም ከምዕራቡ እና ከሌሎች በኢንዱስትሪ ከበለጸጉት

አገሮች ወደ አፍሪካ የሚላከው እና የሚመጣው በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር

ደህነትን ለመቀነስ እና እድገትን ለማምጣት እገዛ አድርጓል፡፡ በእርዳታ እና

በብድር በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር የሚገኝ ቢሆንም እንኳ በአፍሪካ

የድህነት የክስተት እና ጥልቀት ደረጃ እየጨመረ የመጣ ሲሆን የኢኮኖሚ

149

እድገት ግን እየቀነሰ መጥቷል፡፡ የአፍሪካ አገሮች (ገዥዎች) የአገር ውስጥ

ኢኮኖሚዎችን ሊያበላሽ እና ለሙስና መስፋፋት ዋና የመፈልፈያ ምንጭ

ሚሆነው እርዳታ ላይ በሱስ ተጠምደው በቁራኛ ተይዘዋል፡፡ ሞዮ ማንም አገር

ቢሆን የውጭ እርዳታን በመቀበል ያደገ የለም የሚል ድምዳሜ ሰጥታለች፡፡

እንዲህ በማለትም ትሞግታለች፣ “እርዳታ በአፍሪካ አህጉር ምንም ዓይነት የስራ

ዕድል ፈጥሮ አያውቅም፡፡“ እርዳታ በአፍሪካ የፈጠረው ነገር ቢኖር ዜጎችን ሰነፍ

ማድረግ እና የአፍሪካ መሪዎች ከስልጣናቸው የማይነቃነቁ ችካሎች መሆን እና

እንዲያውም የበለጠ ሰነፎች እና የማይነቃነቁ መንግስታት ይሆናሉ ብላለች፡፡

ሞዮ ሙገታዋን በመቀጠል አፍሪካውያን/ት እርዳታ እና ምጽዋት አይፈልጉም፣

ይልቁንም ኢኮኖሚው እንዲያድግ እና ድህነት እንዲቀነስ ንግድ፣ የውጭ

ኢንቨስትመንቶች፣ የካፒታል ገበያዎች፣ ሬሚታንሶች፣ ማይክሮ ፋይናንስ

ይፈልጋሉ፡፡ በገፍ በሚመጣ እና ማቋረጫ በሌለው መልኩ የሚገኝ የውጭ

እርዳታን ሳይቀበሉ በእራሳቸው ጥረት ብቻ የተሳካ ልማትን ያመጡ አገሮች

በማለት ደቡብ አፍሪካን፣ ቦትስዋናን፣ ቻይናን፣ ብራዚልን እና ህንድን

በምሳሌነት ጠቅሳለች፡፡ ለሞዮ አፍሪካውያን/ት ስራ መፈለግ እና ስራ ፈጣሪ

መሆን ይፈልጋሉ፣ እናም ተስፋዋን በፍጥነት በሚያድጉ አፍሪካውይን/ት

ወጣቶች ላይ አድርጋለች፡፡

ሞዮ ሁሉንም እርዳታ አልተቃወመችም፡፡ የተፈጥሮ እና ሌሎች አደጋዎችን

ከማስታረቅ አንጻር በመገምገም ለሰብአዊ እርዳታ ተቃውሞ የላትም፡፡

መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚሰጡ እርዳታዎች በዋናነት በጣም አስቸጋሪ

ለሆኑ መዋቅራዊ ችግሮች ስለሆኑ የታሰሩ እርዳታዎች ናቸው የሚል ሀሳብ

አላት፡፡ የእርሷ ተቃውሞ ያነጣጠረው ከምዕራብ መንግስታት እና ከበርካታ

በይነ መንግስታት ከሚመጣ እና በአፍሪካ መንግስታት እና ገዥዎች በሚባክነው

በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ላይ ነው፡፡ የምዕራብ እርዳታ እና ብድሮች

ሙስናን ያቀጣጥላሉ፣ የአፍሪካ መንግስታት ትምህርትን እና ጤናን ለማዳረስ

እንዲሁም የህብረተሱብን ደህንነት በመጠበቅ እረገድ እና ሌሎችን ከውጭ

መጥተው የእነርሱን ስራ እዲሰሩላቸው በመፍቀድ እረገድ ኃላፊነቶቻቸውን

በአግባቡ እንዳይወጡ ያደርጋሉ፣ አፍሪካውያን/ት ካለውጭ እርዳታ ወይም

ከውጭ እርዳታ ጋር የተያያዙ ድጋፎች ሳይደረጉ በእራሳቸው ጥረት ማደግ

እንዳለባቸው የማይካድ ሀቅ ነው፡፡

የውጭ እርዳታን እና የውጭ እርዳታ መር የአፍሪካ ልማትን ውሸትነት እና

ታሪክ ለማስተባበል ሞዮ ከፍተኛ ክፍያ የሚያስገኙ ስራዎች በሆኑላቸው እና

150

የውጭ እርዳታ ለአፍሪካ ልማት እንደ ተሸከርካሪ ፔንዱለም እንደሚያፋጥን

እምነት ባላቸው በዓለም አቀፍ የድህነት ወትዋቾች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ትችት

ቀርቦባታል፡፡ የዓለም ቢሊኒየር የሆኑት ቢል ጌት የሞዮን መጽሐፍ

ሰይጣናዊነትን የሚያራምድ በማለት ፈርጀውታል፡፡ ሞዮ እንዲህ በማለት ምላሽ

ሰጥታለች፣ “የእኔ መጽሐፍ ሰይጣናዊነትን ይቀሰቅሳል ማለት ወይም ደግሞ

በእኔ የሙስና እሴት ስርዓት ላይ ከፍተኛ የሆነ ትችት ማቅረብ ሁለቱም

አግባብነት የሌላቸው እና ክብርን የሚቀንሱ ናቸው“ ብላለች፡፡ የፈገውን ያህል

መረጃ ቢቀርብ የደማውን ልብ ሊያሽር እና ሊያሳምን የሚችል ነገር ሊኖር

እንደማይችል ግንዛቤ ወስዳለች፡፡ የነብይነት ባህሪን ተላብሶ የውጭ እርዳታ

ድህነትን ለመቀነስ መፍትሄ ነው የሚለውን ይልቁንስ የውጭ እርዳታ ድህነትን

ለመቀነስ መፍትሄ አይደለም የሚለው ግንዛቤ ሊይዝ እንደሚገባ የማሳመኛ

ነጥቦቿን አቅርባለች፡፡

እ.ኤ.አ በ2004 ዩኤስ ኤአይዲ የምግብ ቀውስ አዙሪትን መስበር፡ በኢትዮጵያ

ረሀብን መከላከል በሚል ርዕስ ሲዲሲኢስ/CDCS እንዲታተም አድርጓል፡፡ ያ

ዘገባ እንዲህ የሚል መግለጫን አካቷል፣

ኢትዮጵያ፣ ጎረቤቶቿ እና የልማት አጋሮቿ የአሁኑን እና የወደፊቱን የኢትዮጵያ

ትውልድ የጤንነት እና የኢኮኖሚ ሁኔታ በመጉዳት ወሳኝ ሚና የሚጫወቱትን

ረኃብ፣ ድህነት እና በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የምግብ እጥረት ቀውስ መስበር

ተስኗቸዋል፡፡ ይህንን ፈተና ስኬታማ በሆነ መልኩ ለማለፍ የኢትዮጵያን

አመራር፣ ጽናት፣ እና ለለውጥ ዝግጁ መሆንን ይጠይቃል፡፡ በኢትዮጵያ

ስኬታማነት ላይ መረጃ ማቅረብ አሳማኝ እና ግልጽ ነው፡፡ ሀገሪቱ ከአጠቃላይ

የአፍሪካ አገራት በተለይም ደግሞ ከምስራቅ አፍሪካ አገሮች በተነጻጻነት ስትታይ

ላለፉት በርካታ ዓመታት ስኬታማ ያልሆነ አፈጻጸም ስታስመዘግብ ቆይታለች፡፡

…የኢኮኖሚው ደካማ አፈጻጻም በድርቁ ምክንያት አይደለም ሆኖም ግን ይህ

የመነጨው ቀጣይነት ላለው ጊዜ በቆየው በአገሪቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ችግር

ምክንያት ነው፡፡ ይህም መገለጫው በመንግስት እና በግል ዘርፉ ዝቅተኛ የሆነ

የኢኮኖሚ እድገት እና ኢንቨስትመነት እድገት መጣኔ መኖር፣ ዝቅተኛ

የማስፈጸም አቅም እና ዝቅተኛ የሆነ የግብርና እና ግብርና ያልሆነ እድገት፡፡

በተራው ደግሞ ደካማ የኢኮኖሚ አፈጻጻም ወደ ከፋ የማህበራዊ የቀውስ ደረጃ

ይመራል፣ ይህም በበኩሉ በቋፍ ያለ መንገስትን ፈጥሯል… እ.ኤ.አ በ2014

የህወሐት ለማኝ መንግስት እና የልማት አጋሮቹ እየባሰ የመጣውን ረሀብ፣

ድህነት፣ እና በየጊዜው የሚከሰተውን የምግብ ቀውስ አዙሪት ቀለበት መስበር

151

አልቻሉም፡፡ ያ ሊካድ የማይችል ሀቅ ነው!!!

ለማኝ መንግስት ለደኃ ሀገር? የፈረንሳይ ፈላስፋ እና የዲፕሎማት ሰው የነበሩት

ጆሴፍ ማይስትር እንዲህ ብለው ነበር፣ “እያንዳንዱ አገር ሊያገኝ የሚገባውን

መንግስት ያገኛል፡፡“ ያ ማለት ደኃ ኢትዮጵያውያን/ት ለማኝ መንግስት ሊያገኙ

ይገባቸዋል ማለት ነውን?

ብዙውን ጊዜ በማይስትር መርሆዎች እገረማለሁ፡፡ በትክክለኛው መንገድ

ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎች ባሉበት አገር ድምጽ ሰጭዎች ማንን መምረጥ

እንዳለባቸው ኃላፊነቱ እና ጥንቃቄው የወደቀው በእነርሱ ላይ ነው፡፡ ያ ሳይሆን

ቀርቶ አቅም የሌለውን እና በሙስና የበከተውን ባለስልጣን ቢመርጡ የደካማ

ምርጫቸውን ውጤት ተመራጩን ከተቀመጠበት የሰልጣን ወንበር ላይ እራሱን

በስልጣን ቦታው ላይ ለበርካታ አስርት ዓመታት ሰይሞ ያስቀመጠ እና

ስልጣኑን እና ኃይሉን በመጠቀም እና ምርጫን ሰርቆ ገዥ አካል ቢሆን ምን

ሊደረግ ይችላል? እነዚህ ዜጎች እራሱን በላያቸው ላይ ኮፍሶ ስለተቀመጠ

ይገባቸዋል ሊባሉ ይችላሉን?

እ.ኤ.አ ሜይ 2015 ኢትዮጵያውያን/ት የማይገባቸውን ገዥ አካል ያገኛሉ፣ እናም

እንደገና እነሱ የሚፈልጉትን ዓይነት መንግስት ለማግኘት በሚያደርጉት ጥረት

ይሳናቸዋል፣ ፍጹም በሆነ መልክ ይሳናቸዋል፡፡ በሕወሐት እራሱ እና በህወሐት

እራሱ መካከል ያለ ምርጫ ይቀርብላቸዋል፡፡ በመጨረሻም ቢያንስ 99.6

በመቶ ልዩነት በማግኘት ሌባውን ህወሐት ገዥ አካል ያገኛሉ፡፡

እ.ኤ.አ ጁላይ 2012 “ኢትዮጵያ በቦንድ እርዳታ ላይ” በሚል ርዕስ ተችት

አቅርቤ ነበር፡፡ በዚያ ትችት ላይ ባርነት በአንድ ኃይል መያዝ ወይም ደግሞ

በአንድ በውጭ ኃይል ስር ወይም ቁጥጥር ስር መዋል ማለት ነው፡፡ ህዝቦች

ከፍላጎታቸው ውጭ በግዴታ በባርነት ስር እንዲሆኑ በሚገደዱበት ጊዜ

በባርነት ትስስር ውስጥ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ በእዳ በተያዙ ጊዜ ደግሞ በእዳ

ባርነት የተያዙ ይሆናሉ፡፡ በእርዳታ ሰበብ በተያዙ ጊዜ በእርዳታ ባርነት ቁጥጥር

ስር ይውላሉ ማለት ነው፡፡ አፍሪካውያን/ት እ.ኤ.አ በ196ዎቹ ነጻ

ከመውጣታቸው በፊት አፍሪካውያን/ት በቅኝ ግዛት የባርነት ቀንበር ስር ነበር፡፡

የዓለም አቀፍ እርዳታ የሱስ ቁራኛ የአፍሪካን የቅኝ ግዛት ባርነት ወደ የእጅ

አዙር የቅኝ ግዛት ባርነት አሸጋገረው፡፡ ኢትዮጵያውያን/ት በ21ኛው ክፍል ዘመን

152

ሁለተኛው አስርት ዓመታት ውስጥ በእርዳታ የባርነት የአሸዋ ማጥ ውስጥ

በመስመጥ እና በጣም በመስመጥ በባርነት ተይዘው ይቀራሉ ብሎ መከራከር

በእውነቱ አመክኖያዊ ሊሆን ይችላልን? ምናልባት ሸክስፒር ስለኢትዮጵያ

ድሆች ስሜትን የሚያነሳሳ ሀሳብ ይኖረዋል፡፡ ዓለም የአንተ ጓደኛ አይደለችም፣

እንዲሁም የዓለም ህግ፣ ዓለም አንተን ለማበልጸግ ትዕግስት አይኖረውም፣

ስለሆነም ደኃ አትሁን፣ ከሆንክም ስበረው… “ለማኝ ከለማኝነቱ ማምለጥ

ካልቻለ እና ከልመና ባህሉ ሊመለስ በማይችል መልኩ ፊቱን ካላዞረ ለዘላለሙ

ለማኝ ሆኖ ይቀራል፡፡ ብዙ በለመነ ቁጥር ተነሳሽነት፣ ድፍረት፣ ወደፊት የማለት

እና በእራስ የመተማመን የለማኝነት ባህሪያትን ያጎለብታል፡፡”

ተፈፀመ ::

‘’ወ ስባት ለእግዚአብሔር አሜን’’

153

154