16
www.andinet.org 11 ማክሰኞ ነሐሴ 2 ቀን 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ዋጋ 5.00 የኢሕአዴግ ህዳሴና ያቋም መለሳለስ ከልብ ወይንስ የጊዜ መግዣ? ያገር ፍቅር ልክፍት ከናቴ ማህጸን ነው ስፈጠር ከጥንቱ ከህይወት መስመሩ ካገናኝ ከእትብቱ ወይስ ከእናቴ ጡት ካይኖችዋ እይታ ከየት ነው ያገኘኝ ከቶ ከምን ቦታ 8 5 ዜጐችን የፀረ ሙስና ትግሉ አካል እንዲሆኑ ተጠየቀ “ኢህአዴግ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ቦንብ ከመቅረብ ሊቆጠብ ይገባል፡፡” የኢራፓ አመራሮች ርዮት ዓለሙ በህመም ላይ እንደምትገኝ ተገለፀ የነጋዴና መንግሰት ድብብቆሸ ይቁም ዛሬ የምንኖረው አሳፋሪ ቡሉኮ ለብሰን ነው!! የቀድሞ የኢትዮጵያ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐሊክ /ኢህዲሪ/ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያም ባለፈው ሐሙስ ዕለት አውስትራሊያ አገር በሚተላለፈው ኤስ ኤስ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ካሣሁን ሰቦቃ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡ የቃለምልልሱን ዝግጅት ክፍሉ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡ 7 11 11 11 13

11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

  • Upload
    others

  • View
    10

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

�PB ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

11

ማክሰኞ ነሐሴ 2 ቀን 2003 ዓ.ም1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ዋጋ 5.00

የኢሕአዴግ ህዳሴና ያቋም መለሳለስ ከልብ ወይንስ የጊዜ መግዣ?

ያገር ፍቅር ልክፍትከናቴ ማህጸን ነው ስፈጠር ከጥንቱ ከህይወት መስመሩ ካገናኝ ከእትብቱወይስ ከእናቴ ጡት ካይኖችዋ እይታ

ከየት ነው ያገኘኝ ከቶ ከምን ቦታ85

ዜጐችን የፀረ ሙስና ትግሉ አካል እንዲሆኑ ተጠየቀ

“ኢህአዴግ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ቦንብ ከመቅረብ ሊቆጠብ ይገባል፡፡”

የኢራፓ አመራሮች

ርዮት ዓለሙ በህመም ላይ እንደምትገኝ ተገለፀ

የነጋዴና መንግሰት ድብብቆሸ ይቁም

ዛሬ የምንኖረው አሳፋሪ ቡሉኮ ለብሰን ነው!!

የቀድሞ የኢትዮጵያ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐሊክ /ኢህዲሪ/ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያም ባለፈው ሐሙስ ዕለት አውስትራሊያ አገር በሚተላለፈው

ኤስ ኤስ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ካሣሁን ሰቦቃ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡ የቃለምልልሱን ዝግጅት ክፍሉ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

711

1111

13

Page 2: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

ኢ/ር ዘለቀ ረዲ

ርጥብ እንጨት ወ ደ ተ ፈ ለ ገ ው አ ቅ ጣ ጫ በ መ ለ መ ጥ ሊገራና ሊታረቅ ይችላል፡፡ ደረቅ

እንጨት ከሆነ ግን እጣ ፈንታው መሠበር ነው፡፡ እናርቅህ ቢሉት አይታረቅም፡፡ እንደተወላገደ ተሠባብሮ ለማገዶነት በመዋል መንደድ ነው…የደረቅ ሰው ተግባርም ከደረቅ እንጨት የተለየ አይደለም፡፡ እንደ ደረቀ፣ እንደ ገረረ እንደተወላገደ የሰዎችን ምክርና ሐሳብ ሳይቀበል ይሠበራል፡፡

በሀገራችን የነበሩ መሪዎችን ባህሪ ስንመለከት ባብዛኛው አቋማቸው አንድ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ባቋማቸው እንደገረሩ ትንሽ እንኳን ቅልብስ ሳይሉ ተገልጋዩ ሕዝብ ወደ ሚፈልገው አቅጣጫ በመሄድ ፈንታ የሚጓዙት እነሱ ወደሚፈልጉበት አቅጣጫ ነው፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት እነሱ የሚያስቡት ሁሉ ትክክልና ሕዝብን የሚጠቅም እየመሰላቸው ነበር፡፡ ውለው አድረው ትክክል አለመሆኑን ቢገነዘቡ እንኳን የነሱን ሥልጣን የሚያቆይ መስሎ ከታያቸው ስለ ሕዝብ ጥቅም መጓደልና ስለ አገር መሞት ደንታ የላቸውም፡፡ ባቋማቸው እንደ ፀኑ ለሕልፈት ይበቃሉ፡፡

መሪዎቹ ከፊት ለፊታችሁ ገደል አለ ተብለው ቢነገሩ ምልስ በማለት ፈንታ ወይንም ቆም ብለው እውነት መሆን አለመሆኑን ከማስተዋል ይልቅ ዐይኖቻቸውን ጨፍነው ወደ ገደሉ መግባትን ይመርጣሉ፡፡ ሌላው መሪ በገደሉ ገብቶ ተሠባብሮ ሲሞት

ቢያዩት እንኳን እነሱም በዚያው ገደል ገብተው ተሰባብረው እስካልሞቱ ድረስ የኋለኛው ከፊተኛው ቅንጣት ትምህርት አይማሩም፡፡ ይህም የመታረቅና የማረቅ ባህሪ የሌላቸው መሆናቸውን አመላካች ነው፡፡

በዚህ ሁኔታ በርካታ ምሳሌዎችን መመልከት ይቻላል፡፡ በደርግ ጊዜ ደርግ የሚሠራውን እርሱ የሕዝብን ትንፋሽ አዳምጦ፣ ሙያተኞችን አማክሮና ጊዜና ሁኔታዎችን ጠብቆ አልነበረም፡፡ የሚሠራው፤ በራሱ ፈቃድ፣በራሱ ጊዜ፣በራሱ ውሳኔ ነበር፡፡ ይህ በመሆኑ በዘመኑ የሠራቸው እጅግ ጠቃሚ ነፃ የሕዝብ መገልገያ ተቋማት (ሠፈራንና መንደር ምሥረታን ጨምሮ)ከሱ ውድቀት በኋላ ፈራርሰዋል፡፡ የዚህ ምክንያት በጊዜው ሲገነቡ ወይንም ሲመሠረቱ ያለሕዝብ ፈቃድና ተሳትፎ በመሠራታቸው የኋላ ኋላ ሕዝቡ “የኔ አይደሉም፤ የኔ አሻራ የለባቸውም” በሚል እንደ ጠላት ንብረት ሲያፈራርሳቸው ማየት የሚያናድድና የሚያስቆጭ ነገር ነው፡፡

የኀብረት ሱቃቸውን፣ ወፍጮዎችና ባጭሩ የመሠረተ ልማት አውታሮችን ደርግ እንደ ወደቀ እየተሻሙ አፈራረሷቸው፡፡ መንደር ምሥረታን በተመለከተም የገዛቤታቸውን እያፈረሱ ወደ ቀድሞ ባድማቸው ተመለሱ፡፡ ይህንን በማድረጋቸውም ረኩበት እንጂ አልተፀፀቱበትም፡፡ ምክንያቱም ቀደም ሲል እንደተገለፀው ደርግ ያለፈቃዳቸው በእልህ በራሱ ጊዜ ስለሠራቸው ወይንም ሰላቋቋማቸው እነሱም እልህ ይዟቸው ነበርና ጠቃሚዎቹን ሁሉ እንደሚጠቅሙ እያወቁ አፈራረሷቸው፡፡

በደርግ እግር የተተካው ኢሕአዴግም ተከትሎ ያለው የደርግን ፈር ይመሥላል፡፡ እሱም የደረቀ እንጨት እንጂ እንደ ርጥብ እንጨት ልምጥ የሚል አይደለም፡፡ 20 ዓመታት አየነው፡፡ እሱም የሚገነባቸው የመሠረተ ልማት አውታሮች አይጣልበትና ከሱ ውድቀት በኋላ ስለመቀጠላቸው ወይንም ስለ አለመፍረሳቸው ምንም ዓይነት አስተማማኝ የሆነ ዋስትና የለም፡፡ ዋስትናው ሕዝብ “የኔ” ብሎ እንዲቀበላቸው ባለቤት መሆኑ ማረጋገጥ ሲቻል ብቻ ነው፡፡

በመሠረቱ ሕዝብን ባለቤት ለማድረግ በጣም የሚያደክምና ሩቅ የሚያስኬድ አይደለም፡፡ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ ያለ መንግሥት ከሆነ በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣን የራሱ የሕዝብ መሆኑን አውቆና ተገንዝቦ የሂደቱ ሙሉ ተካፋይ ሲሆን ነው፡፡ አንድ ዴሞክራት ነኝ የሚል መንግሥት ሥርዓቱን በሕዝብ ፍላጎት ማስኬድ ካልቻለና በጉልበት ጨፍልቆ እገዛለሁ ካለ ውድቀቱ የከፋ ነው የሚሆነው፡፡ ውድቀቱም አሱ ከነሥርዓቱ ብቻ ሳይሆን በዘመቻ የተገነቡት የመሠረተ ልማት አውታሮች በሙሉ ይወድማሉ፡፡ እንዲህ ከተኮነ ደግሞ እድገት ብሎ ነገር የሚታሰብ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ አሳዛኝ ገጽታም መታየት ያለበት ከዚህ አንፃር ነው፡፡

እንደ አፍሪካ ባሉ ዴሞክራሲ ባልሰፈነባቸው ሀገራት ሥልጣኑን የጨበጡት ወይንም የሚጨብጡት ከሕዝብ ፍላጎት ውጭ በመፈንቅለ መንግሥት ወይንም በትጥቅ ትግል ስለሆነ የሚሠሯቸው ሥራዎች ሁሉ በነሱ መልካም ፈቃድና ለሥልጣናቸው

ማቆያ በሚያመች ሁኔታ በመሆኑ ሕዝብ የኔ ብሎ የሚቀበላቸውና የሚንከባከባቸው ወይንም የሚጠብቃቸው ባለመሆናቸው አድሮ ፈራሾች መሆናቸው አያጠራጥርም፡፡ ባጭሩ የሕዝብ “የኔነት” ስሜት አይኖራቸውም፡፡ ባገራችን የሚታየው ሁኔታም ይኸው ነው፡፡

ባደጉት ሀገራት ግን ሕዝቡ የሲቪክ ማህበራትን ያቋቁማል፤አቋቁሞሞ ይጠብቃል፤ ይንከባከባል፤እነዚህ የሲቪክ ማህበራት ደግሞ ላንድ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ዋንኛዎቹ ምሰሶዎች ናቸው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሌለባቸው ሀገራት የሚቋቋሙ ሲቪክ ማኅበራት ቢኖሩ እንኳን ጠቀሜታቸው የተቋቋሙበትን አላማ ሥተው ገዥውን መደብ በመሣሪያነት ማገልገል እንጂ ከስም ባለፈ ለሕዝብና የማኅበራቱን አባላት መብት የሚያስጠብቁ አይደሉም፡፡ በዚህ ምክንያትም ሕዝብና መንግሥት ውሃና ዘይት በመሆን ሳይዋኃዱ በመጨረሻ ይለያያሉ፡፡

እንዲህ አይነቱን የተዛባ ሂደት አንዳንድ ሀገር ወዳድና ምሁራን ሲተቹ ተቀጽላ ስም ይወጣላቸውና ከገዥው ቡድን በኩል የሚያሸማቅቅና አንገት የሚያስደፋ የውግዘት ናዳ ይወርድባቸዋል፡፡

በሌላ በኩልም የገዥው መንግሠት ካድሬዎች የተዛባና በእውነት ላይ ያልተመሠረተ ሪፖርት ለቁንጮ ባለሥልጣናት ሕዝብ ሥርዓቱንም ሆነ የሥርዓቱን ሂደት እንደወደደና እንደተቀበለው ስለሚያቀርቡ ከፍተኛ ባለሥልጣናትም የህንን ሪፖርት አምነው በመቀበል ሕዝብ የሚፈልገውን ትተው ወይንም ሳያውቁት የካድሬዎቹን ሪፖርት መሠረት በማድረግ የጭፍን ሥራ ስለሚሠሩ መንግሥትና ሕዝብ ሆድና ጀርባ ሆነው ጉዞው የቁልቁሎሽ ነው፡፡ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፡-

እንደሚታወቀው የትምህርት ፖሊሲው ተቀይሮ 10ኛ ክፍል ላላለፉ ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ በማሠልጠን ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የታቀደው እቅድ ተግባራዊ እየሆነ ነው፡፡ እነዚህ ተማሪዎች “coc” ፈተና እንዲወስዱ የተደረገ ሲሆን ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች ሥራ የማግኘት እድላቸው ፈተናውን እንዳለፉት አይሆንም፡፡ ነገር ግን የዚህ የሲኦሲ ፈተናን ክብደቱን ለመግለጽ ሲሉ c በቁቤ ጨ ማለት ሲሆን በኦሮሞኛ ቋንቋ “ጨራ” ብለው ተርጉመውታል፡፡ 0ን ደግሞ “ኦሮሞ” ብለውታል፡፡ የመጨረሻዋን c ደግሞ “ጩፋ” ብለዋታል፡፡ ካንድ ላይ ሲነበብ “ጨራ ኦሮሞ ጩፋ!” ብለው ተርጉመውታል፡፡ ወደ አማርኛ ሲመለስ “የኦሮሞን እድል መዝጋት” የሚል ነው፡፡

እንግዲህ የዚህ ዓይነት ስሜት የተፈጠረበቸው ወጣቶች cocን በራሳቸው አተረጓጎም ተርጐመውታል፡፡ ትርጉማቸውም ከራሳቸው ብሶት የነሱና ከብሔረሰብ ጥቅምና እድል ጋር ያያይዙታል፡፡ ይህ ደግሞ መልካም ነገር አይደለም፡፡ በጥቅሉ ስናየውም ሕዝብ የሚፈልገው ሌላ ገዥዎች የሚሠሩት ለነሱ በሚያመቻቸው መንገድ መሆኑን ነው፡፡

በመሠረቱ ተማሪ ተፈትኖ መውደቅና ማለፍ የነበረና ያለ ነው፡፡ ለምሳሌ የሚኒስትሪ ፈተና

የወደቀ ተማሪ ሚኒስትሪን እድሉን እንደዘጋበት አድርጎ ሲያማርር ተሰምቶ አይታወቅም፡፡ ይህን coc ፈተናንም አምነው እንዲቀበሉትና የኔነት ስሜት እንዲያድርባቸው ይቻል ነበር፡፡ ነገር ግን የሥርዓቱ ባህሪ ሆነና ከጩኸትና ጥድፊያ በስተቀር የዘላቂነት ሥራ ለመሥራት አልተፈለገም፡፡

አሁንም ይህንን አስተያየት የሰጡትን ግለሰብም ሆነ ተማሪዎችን ከመወንጀል ተቆጥቦ መንግሥት ተለሳላሽ በመሆን ነገሮችን በሰከነ መለኩ በመመልከት ለማስተካከል ቢሞክር ያስመሰግነዋል እንጂ አያስወቅሰውም፡፡ ከዚህ አልፎ ግን መንግሥት ነገሮችን በተቃራኒው በመተርጎም እንደሁልጊዜው የውግዘት በትሩን የሚያነሳ ከሆነ የደረቀ እንጨት ከመባል አይድንም፡፡

መንግሥት አንድ በጥሞና አይቶና ተገንዝቦ ሊተገብረው የሚገባው ነገር አለ፡፡ ይኸውም አንድ መንግሥት አንዲትን ሀገር ሲያስተዳድር የነበረው መንግሥት በሌላ ሲተካ ጠንካራ መሠረት ያለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣የሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍሎች ያማከለ ፌደራላዊ አወቃቀር የዜጎችን ሰብአዊ መብት የጠበቀ ፖሊሲ ያስቀመጠ ከሆነ እሱን የተካው አዲሱ መንግሥት እንዳለ በመቀበል ጅምሮች እንዲያልቁ፣ያለቁ እንዲጠበቁና እንክብካቤ እንዲደረግላቸው፣ያረጁ እንዲታደሱ ወይንም በአዲስ እንዲተኩ ካደረገ ታሪካዊ ያደርገዋል፡፡ አገርም ታድጋለች፤ ባገራችን ግን እየሆነ ያለውና ሆኖ ያለፈው የተገላቢጦሹ ነው፡፡ የቀዳማዊ ኃ/ሥላሴን ጅምሮች ደርግ በማምከን በኮሚኒስት ሥርዓት በመተካት ሲያውረገርግ ቆይቶ በመጨረሻ ከሥልጣኑ ሲገፈተር በተራው ኢሕአዴግ የሱን ሥራዎች እስከነ ሥርዓቱ እንዳሉ አፈራርሷቸዋል፡፡ ነገ የኢሕአዴግ ሥራዎች ስላለመፍረሳቸው ማረጋገጫ የለንም፡፡ በዚህ ምክንያት ድህነት መታወቂያችን ቢሆን የሚደንቅ አይሆንም፡፡

ዜጎች መንግሥትን የመተቸት፣የመቃወም፣ የመንቀፍ መብት አላቸው፡፡ ዴሞክራት መንግሥት ከሆነ የዜጎችን ጥቆማ ተቀብሎ ራሱን አርሞና አስተካክሎ ከሁኔታዎች ጋር መጓዝ ይጠበቅበታል፡፡ ደረቀ እንጨት ከሆነ ግን ይሠበርና አገርንም አብሮ ያሠብራል፡፡ በመሠረቱ የሐሳብ ተቀናቃኞችን ቀድሞ ማጥፋት ቀጥሎ የራስን ጥፋት እንደማመቻቸት ይቆጠራል፡፡ የሐሳብ ተቀናቃኞች መኖር ስህተትን ፈጥኖ ለማረም ያግዛል፡፡ አባቶች “መካሪ የሌለው ንጉሥ ያላንድ ዓመት አይነግሥ” የሚሉት ያለምክንያት አይደለም፡፡

ደርግ የገረረና የጎበጠ ሐሳብ በመያዝ ከሕዝብ ፍላጎትና ስሜት በመራቅ በሠራዊት ብዛት በመመካት ከሥልጣን ላይ ለመቆየት ብዙ ጥረት አድርጓል፡፡ ግን አልሆነለትም፡፡ ደርግ የዘነጋው ነገር ቢኖር ሠራዊቱ የሕዝብ ልጅ መሆኑን ነው፡፡ ኢህአዴግ ከደርግ ባለመማር ተመሳሳይ ድርጊት ብቻ ሳይሆን በከፋ መልኩ ቀጥሏል፡፡ የሕዝብ ጩኸትና ብሶት አይሰማውም፡፡ የተቃዋሚዎችን ሐሳብ አይቀበልም፡፡ ነፃ ሚዲያ ማየት አይፈልግም፡፡ ለማንኛውም ኢሕአዴግ ደረቅ እንጨት መሆን የለበትም የማሰቢያ ጊዜው አሁን ነው፡፡

ደረቅ እንጨት ይሠበራል እንጂ አይታረቅም

አሁንም ይህንን አስተያየት የሰጡትን ግለሰብም ሆነ ተማሪዎችን ከመወንጀል ተቆጥቦ መንግሥት ተለሳላሽ በመሆን ነገሮችን በሰከነ መለኩ በመመልከት ለማስተካከል ቢሞክር ያስመሰግነዋል እንጂ አያስወቅሰውም፡፡ ከዚህ አልፎ ግን መንግሥት ነገሮችን በተቃራኒው በመተርጎም እንደሁልጊዜው የውግዘት በትሩን የሚያነሳ ከሆነ የደረቀ እንጨት ከመባል አይድንም

ፊቸር

Page 3: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

“ኢትዮጵያውያን ፓለቲካቸውና ሰለሜ ሰለሜ ዳንሳቸው አንድ ዓይነት ነው፡፡”

B.B.C

ይህ ለጹፌ መነሻ ያደረኩት ጥቅስ በቢ.ቢ.ሲ ጋዜጠኞች በስላቅ የተነገረው “ቅንጅት የኢትዮጵያ ተስፋ” የተባለው ድርጅት የብሔራዊ ምርጫ 97 ዓ.ም ድል ማድረጉ በተበሰረ ማግስት መሪዎቹና ዋና ዋና አባላቱ በመላው ኢትዮጵያ ተጠራርገው ወኀኒ የወረዱ ሰሞን የተነገረ አስቂኝ ምፀት ነበር፡፡

ቅንጅት የድልም የውድቀትም ምልክት ሆኖ ቢያልፍም ወላድ በድባብ ትሒድና የኢትዮጵያ ዴሞክራቶች ለሌላ ታላቅ አገራዊ ንቅናቄ እየተጠራርሩ ያሉበት መባቻ ላይ ደርሰናል፡፡

የቀድሞው የሶቤት ህብረት መንግስትን በድቡሽት ላይ የገነባውና መልሶም ያፈራረሰው “የሶቤየት ፕሮፓጋዳ” ተነቅሎ መጥቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ውሰጥ ከተተከለ እነሆ 20 ዓመት ሞላው፡፡ ዜጐችን ከአገራቸው እንዲሰደዱ ከሚያደርሰው ሥራ አጥነትና የኑሮ ስቃይ ይበልጥ የሚያሳምመው ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መሆኑን ለኢትዮጵያውያን ግልጽ ከሆነ ሁለት አስርተ ዓመታት ዓለፉት፡፡ ከሰባ ዓመታት በላይ በሐሰተኛ “ትልቅነት” ሲያስፈራራ የኖረው የሶቤየቶች ፕሮፓጋንዳ አንዲት

ጥይት ሳትተኮስ በሚስተር ሚካኤል ጐርባቾብ ዲስኩር ብትንትትኑ ወጣ፡፡ በውጤቱም የኮሚኒስት ጐራው ከመቅለጡም በላይ የቀዝቃዛው አለምጦርነት እንዲያበቃ አድርጐታል፡፡

በልማድ “ድርጅታዊ ሥራ” እየተባለ የሚጠራው የፖለቲካ ቧልት ከጉባኤ በፊት ተወስኖ ባለቀ ጉዳይ ላይ ተሰብስቦና አጨብጭቦ በመለያየት እንደ ዛሬው አይብዛ እንጅ በደርግም ዘመን ሲሰራበት የቆየና አገራችንን ያቆረቆዘና ተመፅዋች ምድር ሆና እንድትቀር ያደረገ መቅሰፍት ነው፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ የተተከለው የፖለቲካ ስርዓት ከታላላቅ ብሔራዊ ጥቅሞችና ከመልካም የታሪክ አገጣሚዎችና ውጤቶች የበለጠ በቀጣፊ ፕሮፓጋንዳ ይደሰታል፡፡ ህዝብ በረሃብና በኑሮ ውድነት ሲሰቃይና ስንገላታ በመንግስት ይዞታ ሥር ያሉ መገናኛ ብዙሃን ስለ አባይ ግድብ የአለምን ህዝብ ሁሉ ለፈንጠዚያ እንዲወጣ ሳያሰልሱ ይሰብካሉ፡፡ በጣም የሚገርመው ከሰባት በማያንሱ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችና አስራ ሁለት ያህል የሬዲዮን ጣቢያዎች ተከፍተው በአደንቋሪ ፕሮፓጋንዳ ሕዝቡን ሲያሸማቅቁ ውለው ያድራሉ፡፡

እጅግ የሚያስደንቀው አንድም ሌላ ነፃ ሃሣብ ለአንዲት ቀን ከቶ ለአንዲት ሰዓት እንኳ አስተናግደው የማያውቁ ይልቁንም የኢትዮጵያን ሐቅ አዛብተውና ገልብጠው በማውራት ግብር ከፋዩን ሕዝብ ያሳዝኑታል፡፡ ቅኝቱም

ሆነ ዜማው ከአንድ ኮሬ የሚቀዳ ከቶም ለታሪክ እና ለትውልድ ደንታ በሌላቸው ተራ ፕሮፓጋንዲስቶች በኢትዮጵያ ግብር ከፋይ ሕዝብ ሀብት ይቀልዳሉ፡፡ ይባስ ብለው ከአሜሪካ የሚተላለፈውን የVOA የሬዲዮ ጣቢያ ልሳን ለመዝጋት ይቅበዘበዛሉ፡፡ ብዙ ሚሊዮን ዶላርም በማባከን ላይ መሆናቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው፡፡ ይህ ተጠያቂነት የሌለው መንግስት የአሜሪካ ዴሞክራሲ ሊቀለበስ በማይችልበት ዘመን ላይ የደረሰ መሆኑን መገንዘብ ያቃታቸው የእኛ መሪዎች እዚያው ድረስ ሔደው ስለብሮድ ካስት ተቃራኒ ሕግ ሊያስተምሩ ይዳዳቸዋል፡፡ ከሰባ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚኖሩባት ሀገር የአንድ ቡድን የጠነዛ ፕሮፓጋንዳ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን እየተፈታተኑ ናቸው፡፡ ሚዲያው የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሀብት እንደ መሆኑ የሁሉንም ፓርቲዎች ነፃ ሃሣብ በማንሸራሸር የተወጣጠረውን የሃገራችን የፓለቲካ ግባት ማርገብ በተቻለ ነበር፡፡

የአቶ መለስ ፓርቲና መንግስት የ2002 ዓ.ም ብሔራዊ ምርጫ ውጤት በመዝረፍ ከተቆጣጠረ በኃላና ከምን ጊዜምው በላይ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ሀብት ለሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳ ተግባር በማዋል ህዝቦችን የተጋፈጠውን የኑሮ ውድነትና ረሃብ ማስታገስ አልተቻለውም፡፡ ይለቁንም መንግስት ያለበትን ገበያን የማረጋጋት ሀላፊነት ወደጐን ገፍቶ በሙስና ውስጥ ተዘፍቋል፡፡ መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦችን መደጐም ሲገባውና ሃላፊነቱን መወጣት ሲሳነው ተቃዋሚዎችን ያስጠነቅቃል፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ በኤርትራ ላይ ጦርነት ያውጃል፡፡ ድፍን ሃገርና የአለም ህብረተሰብ የእርሱን ዕቅድ እንዲደግፍ በጥብቅ ይለፍፋል፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል አመንጪ ግድብ ሰርቶ ለሱዳንና ግብፅ የመብራት ሃይል በመሸጥ ያሰበ መንግስት ዳቦ ለተራበ ሕዝብ የሚበላውን ለማቅረብ እንደተዘጋጀ መልካም ሰው ሀገሩን ሁሉ ማንጫጫት ያምረዋል፡፡

በእንዲህ ዓይነት ፕሮፓጋንዳ የተጥለቀለቀው የታቃውሞ ጐራው ፖለቲካ ከዳበሳ ጉዞው ሳይለቀቅ አዲስ የዴሞክራሲ ጎህ እየቀደደ ነው እየተባልን እንሰባከለን፡፡ የተቃውሞ ጐራው ከተተበተበበት የብትንትንነት አደረጃጀትና አባዜ መላቀቅ ያለበትን ለማመልከት ከዚህ የሚከተሉትን ጥቂት መሠረታዊ ነጥቦችን መመልከት ጠቃሚ ይሆናል

• ጎራው በአብዛኛው ከተንጠለጠለበት የግለሰቦች ስብዕና ላይ ወርዶ በመሬት ላይ የቆመ በዴሞክራያሲያዊ መንገድ ማዋቀር

• ከግል አመራር ወደ ተዋህዶ የጋራ ዴሞክራያሲያዊ አመራር ላይ መድረስ

• ለአንጀኛነት ለክፍፍል እና ለቡድንተኝነት ስሜት የሚያጋልጡ ድርጅታዊ ማነቆዎችን በድፍረት ማስወገድ

• ነፃ ሀሳብ፣ የጋራ አመራር፣ ነፃ ውይይት እንዲጎለብት መታገል

• በገዥው ቡድን ድክመቶችላይ በመመስረት ብቻ የተቃውሞ ሃሳብን ከማደራጀት ይልቅ በጥናትና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ እስትራቴጂ ፕላን ማዘጋጀት፡፡ በዚህም የሃገሪቱን የሕዝቡን ፍላጐት ገባ ብሎ መመርመር፡፡

• የተለየ ሃሳብ ያላቸውን አባላት ልዩልዩ ስያሜ በመስጠትና ካራክተር (Character) ማግለል ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታውን ክፉኛ ጐድቶታል፡፡

• ለተቃውሞ ጐራው መዳከም አንዱ ምክንያት የፋይናንስ አቅም ደካማ መሆን ስለሆነ በውጭ አገር ሆነ በሀገር ውስጥ ልዩ ልዩ ስልት ከመንደፍ ጀምሮ በዴሞክራሲያዊ ሀገሮች ካሉ ፓርቲዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት በማድረግ አቅምን ማጐልበት፡፡ ስለዚህ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዕራሳቸውን በዚህ መልክ መርምረውና በፅኑ ዴሞክራሲያዊ መሠረት ላይ ብተዋቀሩ በኃላ የቢሮ ስራቸውን አቁመው

በአስቸኳይ ፊታቸውን ወደ ሕዝባቸው ማዞር ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚህ ዕረገድ የመጀመሪያው ተግባራቸው በሕዝቡ ውስጥ ያለውን የኢኮኖሚ የፖለቲካና የማህበራዊ ጉዳይ ፍላጐት አቅም በፈቀደ መጠን እያጠኑ በዚህ አገር የሚታየውን ከፍተኛውን የፖለቲካ ክፍተት ማለትም ነፃ የሲቪክ ማህበራትን በየደረጃው ማደራጀት አጣዳፊ ተግባራቸው ቢሆን ይጠበቃል፡፡

በዚህም መሠረት 1. በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ነፃ የመንግስት ሠራተኞች ማህበራትን ማደራጀት 2. ነፃ የሞያ ማህበራትን 3. ነፃ የሠራተኛ ማህበራትን (laber unian) 4. ነፃ የወጣትና የሴት ማህበራት ወ.ዘ.ተ እነዚህን ሲቪክ ማህበራት በዕርሾ ደረጃ እንኳን ማዋቀር ለምንገነባው የፖለቲካ ስርዓት የማይታለፍ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ምክንያቱም ነገ ለሚቋቋመው ሕዝባዊ መንግስታዊ ስርዓት ዋና መሠረቶች እና ባለቤቶች ናቸውና፡፡

በዚህ ዕረገድ የሲቪክ ማህበራት መቋቋም ለነፃ ሃሣብና ከፍራት ነፃ ሆኖ ለሚኖር ሕብረተሰብ ግንባታ በጣም ተፈላጊ መዋቅሮች ብቻ ሣይሆኑ ለዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ መሠረቶች ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የሲቪል ማህበራት ለዴሞክራሲያዊ ፓርቲዎች ታላቅ ማህበረዊ መሠረቶች ከመሆናቸውም በላይ በነፃ ትግላቸው ያገኟቸው የፖለቲካና የሲቪል መብቶችን እንዲሁም የዴሞክራሲና የሠባዊ መብቶችን ባጠቃላይ የመንከባከብና ከአደጋም የመከላከል ብቸኛ ባለቤቶች ናቸው፡፡

በእንዲህ አይነት ሁኔታ የሚዋቀር የፖለቲካ ስርዓት ማንም ሊቀለብሰውና አምባገነናዊ ክንዱን ሊያሳርፍሰት አይችልም፡፡ ዛሬ እንደሚታየው የኢህአዴግ ሁነኛ ሰዎች አመራር ስር የወደቁ የፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የእምባ ጠባቂ ኮሚሽን የሠባዊ መብት ኮሚሽን ወ.ዘ.ተ የተዋቀሩት ለዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ እየተባለ ከምዕራቡ አለም ብዙ ሚሊዬን ዶላር እየመጣ ሲባክን መኖሩ ይታወቃል፡፡ (Human rights watch) እንዳለው የምዕራቡ አለም ግብር ከፋይ ህዝብ ገንዘብ ለዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ ሳይሆን የኢህአዴግን የፖለቲካ ተቋማት ለማደራጀት የሚውል መሆኑ እጅግ የሚያሳዝን ነው፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የጋራ የውይይት ምክር ቤት በማቋቋም በዴሞክራሲያዊ ግንባታ እየተባለ የሚላከው ከፍተኛ ዕርዳታ ለመንግስት ሳይሆን ለተቃዋሚዎች እንዲሰጥ በፅኑ መታገል ይጠበቃል፡፡

ይህ በኢትዮጵያ የተዋቀረው መንግስታዊ ስርዓት በይስሙላ ዴሞክራሲ ሃያ ዓመታት ሙሉ ከታሪክ ሊማርና ሊገነዘብ ያልቻለ ስርዓት በመሆኑ የቀረበ ሃሣብ ነው፡፡ ስለሆነም በመሃን ፕሮፓጋንዳ ተጥለቅልቆ የዳበሳ ጉዞ ውስጥ የሚዳክረው የተቃውሞ ጐራው ለአዲስ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ በአንድነት የሚቆምበት ጊዜ ነገ ሣይሆን ዛሬ ነው፡፡

ዛሬ በከፍተኛ ፖለቲካ ቁርጠኝነት በጠንካራ ዴሞክራሲያዊ መሠረት ላይ የምንገነባቸው የሲቪክ ማህበራት ነገ ለምንመኘው ሦስቱ የመንግስት ስልጣን አካላት ዋና መሠረቶች ናቸው፡፡ እነሱ በሌሉበት ነፃ ሃሣብና ከፍርሃት ነፃ የሆነ ማህበረሰብ ሊኖር አይችልም፡፡ እነሱ በሌሉበት ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሔድ አይቻልም፡፡ እነሱ በሌሉበት ነፃና ገለልተኛ የምርጫ ታዛቢዎች ሲኖሩ አይችሉም፡፡ እነሱ በሌሉበት ነፃና ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን ሊኖር አይችልም፡፡ እነሱ በሌሉበት ነፃ የዳኝነት ስርዓት ሊከሰት አይችልም፡፡ እነሱን በፅኑ ዴሞክራሲያዊ መሠረት ላይ ማዋቀር ካልቻልን በግማሽ ምዕተ ዓመታት የታገልንለትና የተሰዋንለትን የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትና ነፃ ሕብረተሰብ መገንባት ከቶም አይቻልም፡፡ ሰውን ከነ እምነቱ የመቆጣጠር አባዜ ያለባቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች እጅ ሕዝቡን ፈልቅቆ ማውጣት የሚቻለው ነፃ የሲቪክ ድርጅቶችን በመመስረት ብቻ ነው፡፡ ኢህአዴግ መሠረትሙ የሚላቸው የወጣት የሴት የሠራተኛ ወ.ዘ.ተ ማህበራት የእርሱን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ከነኮተቱ ከመሸለም እና የሥርዓቱ አድማቂ ከመሆን ውጪ ሌላ ተልዕኮ የላቸውም፡፡ በራሳቸውም ነፃ አይደሉምና!

መኃን ፕሮፓ ጋንዳ ….የዳበሳ ጉዞ…ወዴት?ከዳምጠው ዓለማየሁ

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ነፃ የመንግስት ሠራተኞች ማህበራትን

ማደራጀት 2. ነፃ የሞያ ማህበራትን 3. ነፃ የሠራተኛ ማህበራትን (laber

unian) 4. ነፃ የወጣትና የሴት ማህበራት ወ.ዘ.ተ እነዚህን ሲቪክ ማህበራት በዕርሾ ደረጃ እንኳን

ማዋቀር ለምንገነባው የፖለቲካ ስርዓት የማይታለፍ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡

ምክንያቱም ነገ ለሚቋቋመው ሕዝባዊ መንግስታዊ ስርዓት ዋና መሠረቶች እና

ባለቤቶች ናቸውና

ፊቸር

Page 4: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

ከወንድሙ ኢብሣ

ሥልጣንዎን በክብር ቢለቁስ? በቅድሚያ ላንድ መሪ የሚገባውን እጅ

በመንሣት የከበረ ሰላምታዬን አቀርባለሁኝ፡፡ ከዚህ በመቀጠል ለክቡርነትዎ ለመጻፍ የተነሣሣሁበትን በርካታ ጉዳዮች አንድ ባንድ እየነቀስኩ ለማቀረብና ለማስታወስ እሞክራለሁ፡፡

ለክቡርነትዎ ደብዳቤ መጻፍ የጀመርኩት ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡ በዚያን ወቅት የመነሻ ነጥቤም “ውሃ ማቆርና ውጤት ተኮር” በሚሉ ነጥቦች ላይ ነበር፡፡ የምጽፋቸው ጽሑፎች ይድረሱዎ አይደረስዎ የማውቀው ነገር የለም፡፡ የሆነ ሆኖ በወቅቱ እኔ መደበኛ ሥራዬ መምህር ስለነበርኩ ከ200 (ሁለት መቶ) ለማያንሱ ተማሪዎች የክፍል ኃላፊ ስለነበርኩ በውሃ ማቆርና በውጤት ተኮር ዙሪያ ያልተሣካ ቅስቀሳ ማድረጌን አስታውሳለሁ፡፡ በመሆኑም አጀማመራቸው አላምር ስላለኝ አጨራረሳቸውም ማፈሪያ እንዳይሆን በሚል ነበር ለርስዎ የጻፍኩለዎ፡፡ ስጋቴ አልቀረም መክነው ቀሩ፡፡ ዛሬ ተቆፍረው የነበሩ የውሃ ማቆር ጉድጓዶች ከብቶች ውሃ እንጠጣለን ሲሉ እየተደረመሱ ብዙዎቹን ገደሏቸው፡፡ ባንዳንድ አካባቢም ህፃናት እንዋኛለን እያሉ ሰጥመው መቅረታቸው ይነገራል፡፡ ሕዝቡ ተረባረቦ እንዳይደፍናቸው መንግሥት ያስቆፈራቸው ጉድጓዶች ናቸው በሚል ፍራቻ ዛሬም ድረስ አፋቸውን ከፍተው የሚውጧቸውን በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡

ክቡር ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ በ1997 ዓ.ም በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ የተቃዋሚውን ጎራ በመቀላቀል ተወዳድሬ በማሸነፍ በ1998 ዓ.ም ተወካዮች ም/ቤት በመግባት ከክቡርነትዎ ጋር ፊትለፊት ለመገናኘት የታሪክ አጋጣሚ ዕድል ሰጠኝ፡፡ በመሆኑም እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ በምችለው አቅም ሁሉ የወከለኝን ሕዝብ ብሦትና ሰቆቃ ድምፅ ለማሰማት ሞክሬለሁ፡፡ ግን ውሃ ቢወቅጡት እብቦጭ ሆኖ ቀረ፡፡ የተሳካም የተቃናም አንዳችም ነገር የለም፡፡ ትዝ የሚልዎ ከሆነ ሥልጣን እንደ ተቆናጠጡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በቀን ሦስት ጊዜ እንደሚበላ ቃል ገብተው ነበር፡፡ ዛሬ እንኳንስ ሦስት ጊዜ ከናድኛውም ጠፍቶ ቤተሰብ ምሳ ወይንም ራት የሚመገቡት በወረፋ ሆኗል፡፡ ቁርስ የሚታሰብ አይደለም፡፡ ይህ እየሆነ ያለውም በሰዎ ዘመን መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡

ተ/ም/ቤት በ5 ዓመት ቆይታየ ፋይዳ አልነበረውም ማለት ግን አልችልም፡፡ ቢያንስ በአ.አ.ዩ የሕግ ትምህርቴን ተከታትዬ በቢኤ ዲግሪ ተመርቄአለሁ፡፡ ጊዜዬን በዋዛ ፈዛዛ አላሳለፍኩም ተጨማሪ እውቀት ማግኘቴ ቀላል ነገር አይደለም፡፡

ክቡር ጠ/ሚኒስትር የታሪክ ነገር ሲነሳ እንደ ማይጥመዎ ብረዳም መቶ ዓመት ያስቆጠረ ባለመሆኑ ለመጥቀስ ወድጃለሁ፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው፡-

አቶ ነብየ ልዑል የተባሉ የቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ከፍተኛ ባለሥልጣን የነበሩ በ196ዐ ዓ.ም አጭር ሪፖርት ለንጉሡ ካቢኔ አቅርበው ነበር፡፡ እንዲህ ይነበባል፡-

“- - - ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ዘግይተናል፡፡ የሚመጣውን መጠበቅ ብቻ ነው፡፡ የመከላከያ ጊዜው አሁን ሣይሆን ቀድሞ አለፈ፡፡ ይህ ዛሬ የምናየው እንቅስቃሴ ሊመጣ እንደሚችል በሰፊው ሪፖርቴ ላይ መግለጤ ለናንተ የተሰወረ አይደለም፡፡ በሪፖርቴም ላይ ይህንን መሳይ የሕዝብን ብሶትና እንቅስቃሴ ተጠልለው ወታደራዊ አገዛዝን ሊያሰፈኑ የሚችሉ ኃይሎች እንደሚነሱ ገልጨ ነበር፡፡ እነዚህ ኃይሎችም እናንተ እንደምታስቡት ታላላቅ መኮንኖች ወይንም ጀኔራሎች ሳይሆኑ አሥር አለቆችና ተራ ወታደሮች እንደሚሆኑ ገልጫለሁ፡፡ ዛሬ የምንሰማው ግርግርና ትርምስ የንጉሣውያን አገዛዝ የማብቃቱ ዋዜማ ነው፡፡ ከእንግዲህ የሚሆነውንና የሚመጣውን ከመመልከት ውጭ ምርጫ የለንም - - - $ በማለት ከዛሬ 39 ዓመት በፊት በሪፖርታቸው ላይ ማስታወቃቸውን የማናውቅ ጥቂቶች ነን፡፡ ይህንን ቅድመ የጥሪ ደወል ንጉሠ-ነገሥቱና ሹማምንቶቻቸው በወቅቱ ተጠቅመውበት ቢሆን ኖሮ ደርግ ተፈጥሮ የዚችን ሀገር ልጆች መንጥሮ ርቃኗን በማስቀረት ለርስዎ አስከፊ ሥርዓት አጋልጦ ባልሰጣት ነበር፡፡ ግን ትንቢቱ ይፈፀም ዘንድ ግድ ሆነና ደርግም ሀገርን አጥፍቶ ጠፋ፡፡ ይህ ከላይ የተገለፀውን ሀሳብ ሻምበል ኢዮብ አባተ “ጄኔራሎቹ” በተባለው መጽሐፍ ገጽ 12 ላይ ገልጾታል፡፡ አቶ ተስፋዬ መኮንንም “ይድረስ ለባለታሪኩ” በተባለው መጽሐፋቸው ገጽ 163-164 ላይ አስፍረውት ይገኛል፡፡

ይድረስ ለክቡር ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ

በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የተከሰተውን የዋጋ ንረት

ተከትሎ የተቃዋሚ ድርጅቶችና ባለሞያዎች የችግሩን መንስዔና መፍትሔ ቢጠቁሙም መንግሥት ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ሰቆቃ ባለማጤን “ያስመዘገብነው የዕድገት ውጤት ነው” በማለት ሲሳለቅና ትክክለኛ መፍትሔ ለመስጠት ዳተኛ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትታወቅበትን ጠንካራ የፊስካልና ሞኒተሪ ፖሊሲ ዲሲፕሊን ባለማክበር ከዚህ አንፃር የሚሰጠውን የሙያ ምክር መስማት ባለመፈለግና ከተጠያቂነት ለመሸሽ ባለሞያዎችን በተቃዋሚነትና “በኒዎ ሊብራሊዝምነት” ሲከስ ከርሟል፡፡

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በ2004 የበጀት ማብራሪያ ላይ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ መንግሥት ለዋጋ ንረቱ ያደረገውን አስተዋጽኦ በይፋ ተናግረዋል፡፡ ይህም ከሚገባው በላይ በብሔራዊ ባንክ በኩል ገንዘብ ሲረጭ እንደነበር በዝርዝር “ለምክር ቤቱ” አስረድተዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የተነሱት የንግድ ሥርዐቱ ደካማ መሆኑና ሌሎች ጉዳዮች በተባባሪነት እንጅ በዋናነት ሚና እንዳልነበራቸው ጭምር በመግለጽ፡፡ ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሌሎች የመንግሥት ሹማምንት ለችግሩ ዋነኛው መንስዔ ባልሆኑት የንግድ ማህበረሰብ ላይ ሲወስዱት የነበረውን ውግዘትና ወከባ ግን የረሱት ይመስላሉ፡፡

በሀገራችን እየተከሰተ ያለው የዋጋ ንረት ወነኛው መንስዔ የመንግሥት ፖሊሲ ችግርና በዚሁ ምክንያት የተከሰተው የአቅርቦት ችግር ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ መፍትሔው ፖሊሲው ይህንን የአቅርቦት ችግር በሚፈታ መልኩ ማስተካከልና ካልተመጣጠነ የገንዘብ አቅርቦት መታቀብ ነበር፡፡ ነገር ግን መንግሥት ይህንን ከማድረግ ይልቅ በቅርቡ ሕዝቡን ከንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ በሚያጋጭ መልኩ በፍፁም ተገቢ ባልሆነ

ፕሮፖጋንዳ በመታገዝ የዋጋ ጣሪያ በማስቀመጥ በችርቻሮ ላይ የተሰማራውን ዝቅተኛ ነጋዴ ለኪሳራ በመዳረግ የፍጆታ ዕቃዎች ከገበያ ላይ እንዲጠፋ መንስዔ ሆኗል፡፡የችግሩ መባባስ ያስጨነቀው መንግሥት ከወራት በኋላ የተጠበቀው የዋጋ መረጋጋት ሳይሆን መባባስ መሆኑን ተመልክቶ “በጥፍራችንም በጥርሳችንም እናስፈጽመዋለን” ያሉትን የዋጋ ጣሪያ በከፊል አንስተዋል፡፡

የዋጋ ጣሪያ ማንሳት ብቻውን በመንግሥትና በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ መተማመን ይፈጥራል የሚል ዕምነት የለንም፡፡ መተማመን በሌለበት የዋጋ ንረቱን ለማሻሻል የንግዱ ማህበረሰብ/የግሉ ሴክተር/ ሚና ውስን ይሆናል ብለን እናምናለን፡፡ ስለዚህ ችግሩ የራሱ መሆኑን እያወቀ መፍትሔውን ሌላ ቦታ ሲፈልግ የነበረው መንግሥት ይህንን ኃላፊነት በእግረ መንገድ ሳይሆን በይፋ ለሕዝብ በሚገባ ቋንቋ በመግለፅ ይቅርታ መጠየቅ ይኖርበታል፡፡ መንግሥት በሌሎችም ጉዳዮች ተጠያቂነትን በሚያዳብር መልኩ ኃላፊነትን መውሰድ መልመድ ይኖርበታል፡፡ ይህን ጊዜ በግምት ሣይሆን በዕውቀትና በመረጃ የተደገፈ ርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል፡፡ መንግሥት ይህንን ችላ ባለ ቁጥር ከተጠያቂነት መሸሽ ብቻ ሣይሆን አምባገነንነት ባህሪው እየገዘፈበት ይመጣል፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በሀገራችን እየተባባሰ የመጣውን የዋጋ ንረት ለማሻሻል ብቸኛው መፍትሄ አቅርቦትን በዘላቂነት የሚፈታ የፖሊሲ አቅጣጫ መከተል ነው ብሎ ያምናል፡፡ ከዚህ አንፃር ዋናውን ሚና መጫወት ያለበት የግሉ ሴክተር ነው ብለን እናምናለን፡፡ መንግሥት በግሉ ሴክተር ከሚከተለው ፍረጃና ማዋከብ በተቃራኒ ማለት ነው፡፡ የግሉ ሴክተር ለሀገሩ የሚገባውን ሚና ይጫወት ዘንድ ውክቢያ ሣይሆን ምቹ ሁኔታ መፍጠር የመንግሥት ከኃላፊነት የዘለለ ግዴታ ጭምር መሆኑን መረዳት ይገባዋል፡፡

መንግሥት ኃላፊነትን መውሰድ ይልመድ

በቅድሚያ ሰላም ለእናንተ ይሁን እያልን በቅድሚያ ሠላም ለእናንተ ይሁን እያልን ሐምሌ 19/2ዐዐ3 ዓ.ም በደረሰብን የአስተዳደር በደል ደርሳችሁ ችግራችንን ስለተጋራችሁን ከነቤተሰቤ አናመሰግናለን፡፡ በቀጣዩ ጋዜጣ ላይ የሚታረሙትን እንድታስተካክሉ እጠቁማችኋለሁ፡፡

1. አቶ ፀሐይ ዘሙይ 2001 ዓ.ም ቦታውን አንድንሸጥለት እንደጠየቅን፣

2. ሰባት 7 ክፍል ቤትን ለቀን ለአንድ ዓመት 2,675 ብር በወር 220 ብር ሂሣብ አንድንለቅ የጠየቀን ወረዳው ሳይሆን ቂርቆስ ክፍለ ከተማ እንደሆነ እንዲስተካከል በማለት የ475 ዓመት አዛውንት መኖሪያ ቤት አለአግባብ በትዕዛዝ ፈረስ” ለሚለው እርምት እንዲሰጥ ወ/ሮ አምሳለ ዲባባ

ጠይቀውናል፡፡ ለዚህም የዝግጅት ክፍሉ ይቅርታ እየጠየቀ ለተሰጠው አስተያየትም ከልብ እናመሰግናለን፡፡

አያይዘው ወ/ሮ አምሣለ አሁን ባለንበት ሁኔታ ዝናብ በጐርፍ መልክ እቤታችን እየገባ ውሃ እያፈስን እየቀዳን ተራ በተራ እየተጠባበቅን እየኖርን ነው፡፡

የተነቃቀሉ ቦሮችን መስኮቶች በጨርቅ ሸፍነን በሐምሌ ወር ቅዝቃዜ የ75 ዓመት አዛውንት ሴትና

በህመም ላይ የሚገኙ አዛውንት ይዘን መቀመጥ ተገደናል፡፡ይህ በእንዲህ እያለ አሁን ባለሁበት ሁኔታ የማንነት ጥያቄ ተፈጥሮብኛል፡፡ የት ነው ያለሁት? እኔ ማን ነኝ? ዜግነቴስ? በሚል ጥያቄ ጭንቀት ውስጥ ገብቻለሁ፡፡ ምክንያቱም በገዛ ቤታችንና ንብረታችን ሠርተን

እርማት አውጡልኝ

ፍኖተ -ነፃነት ጋዜጣ ሐምሌ 2ዐዐ3 ዓ.ም

ተመሠረተ፡፡ ፍኖተ ነፃነት በአንድነት ለዴሞክራሲና

ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሥር የሚታተም

በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊ፣ በመዝናኛ፣ በኢኮኖሚያዊና

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር የፓርቲው ልሣን

ነው፡፡

ማኔጂንግ ዳይሬክተር፡- ዶ/ር ኃይሉ አረዓያ

ዋና አዘጋጅ፡- አንዳርጌ መሥፍን

አድራሻ፡- የካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የቤ.ቁ አዲስ

አዘጋጆች፡- ብዙአየሁ ወንድሙ

ብስራት ወ/ሚካኤል

አምደኞች፡- ዶ/ር ኃይሉ አረዓያ

ኢ/ር ዘለቀ ረዲ

አንዱዓለም አራጌ

ግርማ ሠይፉ

ዳምጠው አለማየሁ

ተስፋዬ ደጉ

በላይ ፍቃደ

ወንድሙ ኢብሳ

ኮምፒውተር ጽሑፍ፡- የሺ ሃብቴ

ብርትኳን መንገሻ

አከፋፋይ፡-ነብዩ ሞገስ

አሣታሚው፡- አንድነት ለዴሞክሲና ለፍትህ ፓርቲ

.............................(አንድነት)

አድራሻ፡- የካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የቤ.ቁ 1223

አታሚ፡- ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

አራዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 07 የቤ.ቁ 984

የዝግጅት ክፍሉ

ስልክ +251 922 11 17 62

+251 913 05 69 42

+251 118-44 08 40

ፖ.ሳ.ቁ፡ 4222

ኢሜይል፡[email protected]

[email protected]

ፋክስ ቁጥር፡- 251-111226288

ርዕሰ አንቀፅ

ወደ ገፅ 12 ዞሯል ወደ ገፅ 14 ዞሯል

Page 5: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

ፖለቲካ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በሁለት ክንፎች በመክፈል ማየት የሚቻል ይመስለኛል፡፡ ብሔርተኞችና ኅብረ-ብሔራዊ ፓርቲዎች ልንላቸው እንችላለን፡፡ ብሔርተኞቹ ላንድ ብሔር “ነፃነት” የሚታገሉ ሲሆን የነዚህ ፓርቲዎች ዋንኛው ምሳሌ ኢሕአዴግ ነው፡፡ በሌላ በኩል ህብረ-ብሔራዊ የሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች ዋናው ግባቸው ከግለሰብ ነፃነት በመነሣት ለሁሉም ዜጎች መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት ነው፡፡ ለዚህ ምሳሌ የሚሆኑን የቀድሞው ቅንጅትና ያሁኑ አንድነት ናቸው፡፡

አደረጃጀታቸው በመለያየቱ እነዚህ ሁለት ክንፎች ሊቀራረቡ የሚችሉ የማይመስሉ እሳቤዎችን ለየፓርቲዎቻቸው እንደ መሠረታዊ ፍልስፍና ይዘው መጓዝ ችለዋል፡፡ ለምሳሌ በኢትዮትያ የታሪክ ትንታኔና ሂደት፣በኢትዮጵያዊነት ላይና ሊመሠረት ስለሚገባው የዴሞክራሲ ሥርዓት ዓይነት ላይ ግልፅ ልዩነቶች አንፀባርቀዋል፤

በኢትዮጵያ ታሪከ ላይ የነበራቸውን አቋም ወስደን ብናይ ብሔረተኞቹ የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ ዓመት ታሪክ ነው በማለት አጥብቀው ይከራከራሉ፡፡ የጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ “የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑ ነው?” የሚለው ንግግራቸው መነሻው የመቶ ዓመት ታሪክ ትንታኔ መሆኑን መጠራጠር ይቻላል፡፡ ባንፃሩ ሕብረ-ብሔራዊ የሆኑት ድርጅቶች የኢትዮጵያን ታሪክ ቢያንስ ወደ ሦስት ሺህ ዘመን ያደርሱታል፡፡ ለዚህም የመከራከሪያ ነጥቦቻቸው የአክሱም ስረወ-መንግሥትንና ከዚያም ቀደም ብለው የነበሩትን በማስረጃነት በመጥቀስ ነው፡፡ ያገራችንን ታሪክ ወደ መቶ ዓመት የሚያመጡት ብሔርተኞች መነሻቸው አሁን ያለውን ያገራችንን ወሰንና ሕዝቦች በጋራ መኖር የጀመሩበትን ጊዜ በመውሰድ ነው፡፡

በ1997 ዓ.ም አጠቃላይ የምርጫ ውጤት እስከታወቀበት ጊዜ ድረስ ከሞላ ጎደል የሁለቱ ክንፎች መለያዎች የተጠቀሱት ነበሩ፡፡ ሕብረ-ብሔራዊዎቹ ይህንን ሐሳብና ስለባንዲራ ወይንም ኢትዮጵያዊነት ያላቸውን ሃሣቦች አደባባይ ይዘው በወጡ ቁጥር ከኢሕአዴግ በኩል የሚሰነዘርባቸው አፀፋ “ነፍጠኞች! ትምክህተኞች!” የሚል ነበር፡፡በ1998 ዓ.ም በኢሕአዴግ የታተመ አንድ መጽሐፍ አለ፡፡ መጽሐፉን የፓርቲው አባላትና መምህራን በሰፊው ተወያይተውበታል፡፡ በወቅቱ የቅንጅት መሪዎችና አባላት ቃሊቲ ነበሩ፡፡ መጽሐፉ ሕብረ-ብሔራዊ የሆኑ የፖለቲካ ድረጅቶችን በተለይም ቅንጅትን በተቸበት ክፍሉ የኢትዮጵያ ሕብረ-ብሔራዊነት የሚያራምዱ ፓርቲዎች “የለበሱት የኢትዮጵያዊነት ካባ ሲገለጥ አማራነት” እንዳለበት ያትታል፡፡

የተገለፀውን ሐሳብ ይዘን ጥቂት ዓመታት ከምርጫው ወደ ኋላ በሐሳብ መጓዝ ብንችል ከኢሕአዴግ ካድሬዎች አፍ ከማይጠፉት ቃላት ውስጥ “ነፍጠኞች፣ትምክህተኞች” ቀዳሚዎቹ ነበሩ፡፡ በፓርቲው እምነት መሠረት ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊያሠፍነው ላቀደው “የዴሞክራሲ ሥርዓት” ዋነኛ ጠላቶች “ነፍጠኞችና ትምክህተኞች” ናቸው፡፡ መገለጫዎቻቸውም አክሱም፣ላሊበላ፣ጎንደር፣አፄ ቴዎድሮስ፣አፄ ምኒልክ. . . እያሉ ይቀጥላሉ፡፡ እዚህ ላይ የአድዋ ድል መቶኛ ዓመት አከባበር ሥነ-ሥርዓት ላይ ባፄ ምኒልክ ስብዕናና በጦርነቱ የነበራቸው ሚና ላይ በሁለቱ ክንፎች መካከል የነበረውን ከፍተኛ ክርክር ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡

የሆነ ሆኖ ሕብረ-ብሔራዊ የሆኑት አራት የፖለቲካ ድርጅቶች ጥምረት ወይንም ቅንጅት ፈጥረው ኢሕአዴግን መገዳደር (መፎካከር) የቻሉት እሱም ጠንካራ ፈተና የገጠመው በ1997 ዓ.ም በሦስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ወቅት ነበር፡፡ የተጣመሩት አራቱ ሕብረ-ብሔራዊ ፓርቲዎች ይዘውት ወደ ሕዝብ የቀረቡት መፈክር በመሠረታዊነት የኢትዮጵያን ብሔረተኛነት ላይ በማተኮር ሲሆን ባንፃሩ ደግሞ ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ደካማ

ጎኑ ይኸ ነበር ሊባል ይቻላል፡፡ ሌላው ቀርቶ ምርጫ 97 ሰሞን ተዘጋጅተው በነበሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክሮች ቅንጅትን ይገልፁት የነበረው “ትምክህተኛና ነፍጠኛ!” እያሉ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከአምስት በላይ ብሔርተኛ ፓርቲዎችን አቅፎ ይዞ የነበረው ኅብረት በግልፅ ቅንጅትን እንዲያ ሲናገር አልተደመጠም፡፡ ይህም የመሪዎቹን የፖለቲካ ብስለትና ብልጠት የሚያመላክት ነበር፡፡

ኢሕአዴግ በደረሰበት ሽንፈት ምክንያት ከምርጫው በኋላ ቀድሞ ይጠቀምባቸው የነበሩትን እሳቤዎች የለወጣቸው ወይንም ባዲስ ስያሜ የተካቸው ይመስላል፡፡ አምኖበት ይሁን አይሁን የማውቀው ነገር የለም፡፡ በግልፅ ስለመለወጡም የተናገረው ነገር የለም፡፡ የሕዝብን ትኩረት ለመሳብ በሚመስል ሁኔታ ግን ሕብረ-ብሔራዊ ድርጅቶች ያራምዱት የነበረውን መርህ በመንጠቅ ማራመድ ይዟል፡፡ “የባንዲራ ቀን” ተብሎ መከበር የተጀመረውም ከ97 ዓ.ም ምርጫ ወዲህ መሆኑ ልብ ሊባል ይገባዋል፡፡

“በነፍጠኞችና በትምክህተኞች” ምትክ አዲስ ተለጣፊ ስም የሰጣቸው “የኒኦ-ሊበራሊዝም ተላላኪዎች” የሚል ነው፡፡ መቸም ይሁን መቸ ኢሕአዴግ ለሚፎካከሩት ሁሉ አዲስ ተለጣፊ ስም መስጠት አይሳነውም፡፡ እናም በ2002 ዓ.ም ምርጫ መድረክን በቅስቀሳና በክርክር ወቅት ይገልፀው የነበረው “የኒኦ-ሊበራሊዝም ተላላኪዎች!” እያለ ነበር፡፡ በፓርቲው አገላለፅ መሠረት ከ“ነፍጠኛነትና ትምክህተኝነት” ወደ “የኒኦ-ሊበራሊዝም ተላላኪነት!” ስማቸው የተቀየረው ተቃዋሚዎች ጠንከር ባለ መንገድ አዲሱ ስማቸውን መቀበል/ አለመቀበላቸውን ሲገልፁ ገጥሞኝ አያውቅም፡፡ በእርግጥ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፍ ላይ

ሃሳቡን ማንሣታቸውን ሳይዘነጋ ማለቴ ነው፡፡ በዚያ ምርጫ ሰሞን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው ስለ ኒኦ-ሊበራሊዝም ፍልስፍና ግሩም ትንታኔ አቀረቡ፡፡ ትንታኔያቸው በፈጠረብኝ ጉጉት አነሳሽነት በተቃዋሚ ፓርቲዎች አቋሞች ላይ የዳሰሳ ጥናት አድርጌአለሁ፡፡ የጥናቴ ውጤትም እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ ውስጥ አንድም ፓርቲ የኒኦ-ሊበራሊዝምን ፍልስፍና የሚያራምድ የለም፡፡ አንድም!

በተለያየ ምክንያት ሳልደርስባችሁ የቀረሁት የፍልስፍናው አራማጅ ፓርቲዎች ካላችሁ “አለን” በሉኝ፡፡ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር እንዴት ተጣጥሞ ሊሄድ እንደሚችል አስረዱኝ፡፡ ሁሉም ሕብረ-ብሔራዊ ፓርቲዎች ግን የሊበራል ዴሞክራሲን ተከታይ መሆናቸውን ተረድቻለሁ፡፡ ኢሕአዴግ እንዲህ ይበላቸው እንጂ አንድነትም ሆነ መድረክ ወይንም ሕብረ-ብሔራዊ የሆኑት ድርጅቶች “መርሃችን፣ወይንም ፖሊሲያችን አሊያም ፕሮግራማችን ኒኦ-ሊበራሊዝም ነው” ሲሉ ሰምቼ ወይም አንብቤ አላውቅም፡፡

ኢሕአዴግ የሕብረ-ብሔራዊ ድርጅቶችን መፈክር ወይንም መርህ መንጠቁ ሌላው ማስረጃ ከመቶ ዓመት የታሪክ አስተሳሰብ ወጥቶ በ2000 ዓ.ም ያከበረው የኢትዮጵያን ሚሊኒየም አንዱ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ኢሕአዴግ ተጣድፎ እንጂ ሚሊኒየሙ መከበር የነበረበት በ2ዐዐ1 ዓ.ም ነበር፡፡ 2000 ዓ.ም ተሳናባቹ ዘመን ነበር፡፡ የሆነ ሆኖ የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ ዓመት ታሪክ ነው ብሎ ሲከራከር የነበረ ፓርቲ በድንገት የ2ዐዐዐ ዓመት በዓል ማክበሩ ያቋም ለውጥ እያደረገ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ በርግጥ አንዳንዶች እንደሚሉት እስራምዕቱን ያከበረው ኢሕአዴግ ያቋም ለውጥ አድርጎ ሣይሆን ሁለት ሺህ ዓመቱ

የኢሕአዴግ ህዳሴና ያቋም መለሳለስ ከልብ ወይንስ የጊዜ መግዣ?

ከተስፋዬ ደጉ

ወደ ገፅ 9 ዞሯል

Page 6: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

በኢትዮጵያ የግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ ከ60 ዓመታት በፊት ጀምሮ ፖሊሲ ተቀርጾለት እንቅስቃሴ ውስጥ የነበረ ቢሆንም አሁንም ድረስ በዳዴ ላይ ይገኛል፡፡ በዘውዳዊው ሥርዓት ጊዜ ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች እንዲሁም ለውጭ ሃገር ኢንቨስተሮች (በተለይም ደቾች፣ ጣሊያኖችና ግሪኮች) በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ረድቷቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡ የኢንዱስትሪው ዘርፍ በወቅቱ በአፍሪካም ደረጃ ሲታይ በአንፃራዊ መልኩ ተሻለ እንደነበር ማስረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ደርግ ይህን መልካም ጅምር ቀለበሰው፡፡ በተለይም ይከተለው በነበረው ርዕዮተ-ዓለም ምክንያት በማቆጥቆጥ ላይ የነበሩትን ፋብሪካዎች በመውረሱና ለግል ባለሃብቱ የኢንቨስትመንት ጣራ በመደንቀሩ፣ የኢንዱስትሪ ልማት በመንግስት እጅ ብቻ የተንጠለጠለ እንዲሆን አደረገው፡፡ በመሆኑም ደርግ የግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ ሊጫወት የሚገባውን ሚና ነፍጎ፣ በርዕዮተ-ዓለም ተተብትቦ የለውጥ በሩን ጠርቅሞ ዘጋው፡፡ ይሁንና ደርግ በመጨረሻዎቹ የጣር አመታት የቅይጥ ኢኮኖሚ መስመር ለመከተልና የኢንቭስትመንት ገደብን ለማንሳት ተንቀሳቅሷል፡፡

በተራው የገዢነት መንበሩን የተቆናጠጠው ኢሕአዲግ በድል አጥብያ በ1983 ዓ.ም. በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተዳከመውን የሶሻሊስታዊ አስተሳሰብ ሸሽጎ በፓርቲው ፕሮግራም ለማምታታት ይረዳው ዘንድ ለግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚና ለመድበለ ፓርቲ አስተሳሰብ እውቅና ሰጥቻለሁ ብሎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ለረጅም ዓመታት ሲመራበት የነበረው የማርክሲስት ሌኒስት (ማሌ) አስተሳሳሰብ በሥልጣነ-መንበሩ ላይ ከተፈናጠጠም በኋላም የአገዛዙ ርዕዮተ-ዓለም እንደሆነ በተግባር ቀጥሏል፡፡

ኢህአዴግ እሰከ አሁንም አዳብሎ የሚከተለው አብዮታዊ ዴሞክራሲ የሚሉት ሶሻሊስታዊ አመለካከት አርሶ አደሩንና የሠራተኛውን ክፍል እንደ ስልጣን መደላድል አርጎ የሚቀበልና፣የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ እንደ ወላዋይና ሊታገሉት የሚገባ ባላንጣ መደብ አድርጎ የሚወስድ ነው፡፡ በዚህም የግሉን ክፍለ-ኢኮኖሚ በጠላትነት በሚፈርጅ አስተሳሰብ እየተነዳ ለመሬት ፖሊሲ ለውጥ፣ለፋይናንሻል ገቢያው መከፈት፣ በቴሌ-ኮምዩንኬሺን ሴክተር መሳተፍን ወ.ዘ.ተ ፍፁም እንዳይቻል እንቅፋት ሆንዋል፡፡ እነዚህ የአገዛዙ ደንቃራ ፖሊሲዎች ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ሊደረግ የሚገባውን ሽግግር የማይቻል አድርጎታል፡፡

ከ1997 ዓ.ም. ወዲህ ደግሞ አገዛዙ እየተከተለ ያለው መንግስታዊ ካፒታሊዚምን (State Capitalism) ነው፡፡ የዚህ አስተሳሰብ ግብ ጥቂት የከተማ አድርባይ ነጋዴውን ክፍል ይዞ የግንባሩን የረጅም ጊዜ የገዥነት ቅዠት ማረጋገጥ ነው፡፡ መንግስታዊ ካፒታሊዚም በባህሪው እጅግ የተለጠጠና ትልቅ መንግሥትንና እዚህ ግባ የሚባል ሚና የሌለውን የግል-ክፍለ ኢኮኖሚ የሚፈጥር ነው፡፡ ለዚህም ነው በኢሕአዴግ የአምስት ዓመት የዕድገትና መሠረታዊ ለውጥ ዕቅድ (Growth and Transformation Plan) 99.6% ይሳካል ተብሎ የሚለፈፈው፡፡

አንድነት እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሰፊ የመዋቅራዊ ችግር ባለበት ሀገር፣መንግሥት በኢኮኖሚው ሚና አይኑረው የሚል ክርክር አያነሳም፡፡ ይሁን እንጂ ለዴሞክራሲ መጎልበት እርሾ ሆኖ ሊያግዝ የሚገባውን የግል ክፍለ-ኢኮኖሚ ትርጉም አልባ ማድረግ በሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ሽግግርንና የልማት ጭላንጭልን ገደል መክተት ነው፡፡ ከአንድ አገዛዝ የእድሜ ዘመን የዘለለ ሃብት ማፍራት ከማይችሉ ጥቂት ነጋዴዎች ይልቅ፣ ለጥሮ ግሮ አዳሪ ነጋዴዎች ቦታ መስጠት የሚያስፈልገውም ለዚህ ነው፡፡

በተሳሳተ የፖለቲካ መስመር እየተመራ ያለው አገዛዙ ኢትዮጵያን በገዛባቸው የሃያ ዓመታት የእውር ድብር ጉዞው የግሉን ዘርፍ በዓለም ገበያ ይቅርና ከውጭ ወደ ሀገር ቤት ከሚገቡ የቻይና ሸቀጦች ጋር የመወዳደር አቅም መፍጠር አልቻለም፡፡ የማኑፋክቸሪንግ መሠረቱንም አሳፋሪ በሆነ ደረጃ ካጠቃላይ

ኢኮኖሚው ከ5 በመቶ ያልዘለለ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ የአገዛዙ ዘይቤ በጥረትና በፈጠራ ከሚገኝ ዕድገት ይልቅ፤ በእኖር ባይነትና በአድርባይነት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

አገዛዙ ለዚህ የተለጠጠ፣ውጤት አልባና የጭቆና መሣሪያ ለሆነው የ“ልማታዊ መንግሥት” አቅጣጫው የግሉን ክፍለ-ኢኮኖሚ እንደ መስዋዕት አቅርቦታል፡፡ አጠቃላይ የመንግሥት ወጪ በ1997 ዓ.ም. ከነበረበት 20 ቢሊየን ብር በ2003 ዓ.ም. ወደ 75 ቢሊየን ብር ከፍ አድርጐታል፡፡ አንድነት መጀመሪያውንም የተስተካከለ የኢኮኖሚ ፖሊሲና የኢኮኖሚ መሠረት ቢኖር የበጀቱን ከፍ ማለት እንደ በጎ ርምጃ በወሰደው ነበር፡፡ ነገር ግን እየተወሰደ ያለው ርምጃ የግብር ይውጣና የኢኮኖሚው አቅም ሊሸከመው ከሚችለው በላይ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ቅጥ ያጣ የመንግስት በጀት የዋጋ ውድነቱን ከማባባሱ በተጨማሪም በግብር ከፋዩ ላይ ከፍተኛ ጫናን ፈጥሯል፡፡ በ1997 የመንግስት ገቢ 14 ቢሊየን ብር የነበረ ሲሆን፣በ2002 ደግሞ 51 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል፡፡ የሚሰበሰበው ታክስ መልሶ የንግዱን ተወዳዳሪነትና ምርታማነትን ከማሻሻል ይልቅ፤ለከፍተኛ ምዝበራ የተጋለጠ እንዲሆን ማድረጉ በገሃድ የሚታወቅ ነው፡፡ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በሚያወጣው ዘገባ መሠረት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሙስና ከሚታይባቸው ሀገሮች አንዷ እንደሆነች ይታወቃል፡፡

አብዛኛው የአገዛዙ ሹመኞች በሙስና መጨማለቃቸውን ታክስ ከፋዩ ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ ባቋራጭ የቪላ፣የፎቅ ቤት፣የዘመናዊ መኪናና የመሬት ባለቤት ያልሆነ የስርዓቱ ሹመኛ አለ ማለት አያስደፍርም፡፡ በቅርቡ የወጣው የተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት (UNDP) ሪፖርት እንደሚያስረዳው ከኢትዮጵያ 140 ቢሊየን ብር በላይ መመዝበሩን በግልፅ አሳይቷል፡፡ ታዲያ ይህ ሲታይ ሙሰኛ “ጥገኛና ኪራይ ሰብሳቢ” የሚለው አባባል ከኢህአዴግ ይልቅ ለማን ይቀርባል;ነጋዴው በቅርቡ በተጣለበት ከፍተኛ ግብር የተነሳ እሮሮ ከፍ አድርጎ እያሰማ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ፈፅሞ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከ40 እና 50 እጥፍ በላይ ግብር ተጨምሮበታል፡፡ አገዛዙ ግን ግብር የጨመርኩት የነጋዴው የእለት ሽያጭ በመጨመሩ ነው የሚል ፌዝ ቢጤ ሃሣብ ሰንዝሯል፡፡ ይህንም የዘፈቀደ አሠራሩን “በጥናት የተደረስበት” እንደሆነ እየገለፀ ነው፡፡ በጥናት ላይ ተመሠረተ የሚባለው የግብር ልኬት በተግባር ሲገለፅ ግን አጠቃላይ ያለው የቁሳቁስ መጠን አምስት ሺ ብር የማይሞላን ንግድ ቤት፤ስምት ሺ ብርና ከዚያ በላይ እንዲከፍል የሚያስገድድ እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡

ኢህአዴግ ነጋዴው ዓመቱን ሙሉ በዋጋ ቁጥጥር፣ ለአባይ መዋጮና በእንደገና ምዝገባ ስም ሲያዋክበው አርፍዶ፤ በዓመቱ መገባደጃ ላይ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የግብር ተመን ጭኖበታል፡፡ ልክ እንደ ደርግ ጊዜ ሁሉ ነጋዴው አወናባጅና አጭበርባሪ የሚል ስም ወጥቶለት ከሕብረተሰቡ ጋር ለማቃቃር ገዢው ፓርቲ በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች ሁሉ ተዘምቶበት እንደነበር የቅርብ ግዜ ትውስታ ነው፡፡ አገዛዙ “በጥናት ደረስኩበት” ብሎ በገለፀው የዋጋ ተመን መሠረት የነጋዴውን የትርፍ መጠን እቀንሳለው ብሎ ተንቀሳቅሶዋል፡፡ ገብያውንም ለብዙ ምስቅልቅል ዳርጎት ነበር፡፡ ታዲያ የነጋዴው ትርፉ መቀነስ ከተቻለ፣ ነጋዴው አስጨናቂ ለሆነ የገቢ ግብር መዳረግ የለበትም፡፡ የንግዱ ማሕበረ-ሰብ ይህን ኢ-ፍትሐዊ የሆነ በግብር ስም የሚደረግ ገፈፋ አቤት ብሎ የሚከላከልበት የፍትሕ አደባባይ ጠፍቷል፡፡ የግብር ቢሮ ሹማምንት በግብር የጎበጠውን ነጋዴ አጥጋቢ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ግማሹን ከፍለህ ተከራከር ማለትን የፍትሕ አልፋና ኦሜጋ አድርገውታል፡፡ በየሚዲያው የሚሠጡት መግለጫም ከዚህ የከፋ ሆኗል፡፡ ነጋዴው በግብሩ ከተማረረ፣ የተወሰነበትን ከፍሎ ንግዱን ዘግቶ መሄድ መብቱ እንደሆነ በማንአለብኝነት እየተናገሩ ነው፡፡ ነገር ግን የንግዱ ማሕበረ-ሰብ መድረሻ የለውም ብለው

ካልሆነ በስተቀር የነጋዴው ሕይወት ሲፋለስ እነርሱም የቆሙበት መሬት እንደሚከዳቸው ረስተውት አይመስለንም፡፡ ኢሕአዴግ ነጋዴው ከየትም ተፍገምግሞ የሚከፍለውን እያንዳንዱን ብር በግልፅነት፣በፍትሐዊነት፣ በተጠያቂነትና ውጤታማ በሆነ መንገድ የመጠቀም ልማድ የለውም፡፡ የሚሰበሰበውም ብር ለከፍተኛ ሙስናና ለተዝረከረከ የመንግሥት ወጪ ሲውል ተደጋግሞ ታይቷል፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ “የልማት ሠራዊት ግንባታ” በሚል ፈሊጥ የግብር ከፋዩን ብር የካድሬ ማሰልጠኛ ሲያደርጉት ተስተውሏል፡፡ ኢ-ህገ-መንግሥታዊ በሆነ ሁኔታ የመንግሥትና የፓርቲ ሥራ እንዳይለይ ተደርጎ እንደተዋሃደ ይታወቃል፡፡ በተመሳሳይ መንገድም የኢሕአዴግና የመንግሥት በጀት ተለይቶ የመያዙም ሁኔታ ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም፡፡

በየወረዳው የስርዓቱ ካድሬዎች የሚረጩት ገንዘብ በተጠያቂነት ስሜት አይወጣም፡፡ በእከከልኝ ልከክልህ ዓይነት የመንግስት አስተዳደር ዘይቤ የሚመራ ሀገር የተሰበሰበውን የግብር ብር ከሠፊው ነጋዴ ነጥቆ፣ ለአድርባይ ባለፀጎች የፕሮጀክት ማሟያ የሚሆን ነው፡፡

አንድነት ዜጎች በአገራቸው ሠርተው ከሚያገኙት ገቢ ግብር መክፈል አለባቸው፤የዜግነትም ግዴታ ነው ብሎ ያምናል፡፡ ይሁን እንጂ መንግሥትም ግዴታ አለበት፡፡ ግብር ክፈሉ ብሎ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን፣የዜጎችን የኢኮኖሚና የፖለቲካ መብት ማክበር ግዴታው ነው፡፡ አገዛዙ ነፃ ምርጫን አይፈቅድም፡፡ በነፃነት የመናገርና የመደራጀት መብትን አያከብርም፡፡ በሕዝብ ሃብት የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን ለአንድ ወገን ጭፍን ድጋፍ እንዲሰጡ ሆነው የተዋቀሩ ናቸው፡፡ ታክስ ክፈሉ ብሎ ደረቱን ነፍቶ የሚጠይቅ መንግሥት ለማንኛውም ዕድል መስፈርቶቹን የፓርቲ አባልነትና ታማኝነት ሊያደርግ አይገባም፡፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 25 መሠረት ዜጎች ሁሉ እኩል ናቸው ተብሎ ቢደነገግም እስካሁን ድረስ መመዘኛው ችሎታና ብቃት ሊሆን አልቻለም የፖለቲካ ታማኝነት እንጂ፡፡ የትምርት ዕድል (በተለይ ድህረ ምረቃ) በገዢው ፓርቲ የሚወሰን ሳይሆን፣በነፃ ውድድር የዜጎች በእኩልነት መግባት የሚችሉበት ሊሆን ይገባል፡፡ ይህ ባልተሟላበት ግብርን በፈቃደኝነት መክፈል የሚታሰብ አይሆንም፡፡ የሕዝብን ፍላጎቶች ለማሟላት ፈቃደኝነት የሌለው መንግሥት ከሕዝብ ፈቃደኝነትን ሊጠብቅ አይችልም፡፡

በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ውስጥ ከሚታየው ሁኔታ አንፃር በኢትዮጵያ የመንግሥት የታክስ ገቢ ድርሻ ከአጠቃላይ ኢኮኖሚው መጠን አንፃር ዝቅተኛ ነው፡፡ እንዲሁም በኢትዮጵያ የታክስ ከፋይ መሠረቱ እጅግ ትንሽ ነው፡፡ በተጨማሪም የታክስ ገቢው በዋነኝነት ከኢንዱስትሪውና ከአገልግሎት ዘርፉ የሚገኝ ነው፡፡ ኢንዱስትሪው በስብጥርም ሆነ በስፋት አነስተኛ ነው፡፡ በመሆኑም ያለውንም ትንሽ የንግድ እንቅስቃሴ ጨርሶ ላለማዳፈን መጠንቀቅ ይገባል፡፡

አንድነት ፓርቲ አሁን ካለው ጊዜ ይልቅ መጪው ግዜ ለግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ እጅግ አስቸጋሪ እንደሚሆን ይገነዘባል፡፡ በ2004 ዓ.ም. መንግስት ከ76 ቢሊዬን ብር በላይ ግብር ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡ በኢህአዴግ የአምስት ዓመት የዕድገትና መሠረታዊ ለውጥ ዕቅድ (Growth and Transformation Plan) መሠረት በ2007 ዓ.ም. መንግሥት ከ127 ቢሊየን ብር በላይ ከታክስ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡ ይህ በግልፅ የሚያሳየው መንግሥት በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ላይ ተንፈራጦ ከፍተኛ የአፈና መዋቅር ለመገንባት ላይ ታች እያለ እንደሆነ ነው፡፡ በተለይ እንደ ኢህአዴግ በሕዝብ ያልተመረጠና ግልፅነት የሌለው መንግሥት መኖሩ ችግሩን አወሳስቦታል፡፡

በመሆኑም የንግዱ ከፍለ ኢኮኖሚ ለራሱ ህልውና ብሎ ተባብሮ መቆም አለበት፡፡ ነጋዴው በነፃነት በሀገሩ መስራት ተስኖት፣ በገዛ አገሩ እንደባላንጣ “መመንጠር ያለበት ጫካ” ተደርጎ እየተወሰደ ነው፡፡ ወደ ግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ መቀላቀል ለእስርና ለእንግልት የሚዳርግ

ተግባር ተደርጎ እየታየ ነው፡፡ ስርዓቱ የሥራ ፈጠራ ክህሎት እንዲዳብር ከማበረታታት ይልቅ፣የነግዱ ማሕበረ-ሰብ በሰቀቀን ወደ ሚኖርበትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ጭራሹንም አስተዋፅኦ ማድረግ ወደ ማይችልበት ደረጃ ጨርሶ እየገፋው ነው፡፡

መንግሥት ከሚከተለው የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለም አንፃር የሚጠበቅ ቢሆንም፤በመንግሥትና በንግዱ ማህበረሰብ መሀል ያለው አለመተማመን ከመሻሻል ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት ነው፡፡ አገዛዙ በግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ ላይ የሚከተለውን የተሳሳተ ፖሊሲ መቀየር ይገባዋል፡፡ ስለሆነም፤

1. ኢህአዴግ ራሱ ነጋዴ ነው፤ ራሱ ሕግ አውጪም፤ሕግ አስፈፃሚም ነው፡፡ ይህም የግሉን ክፍለ-ኢኮኖሚ እንደ ባላንጣ እንዲያውም አስገድዶታል፡፡ ገዥው ፓርቲ ከእንዲህ ዓይነት አካሄድ ተቆጥቦ የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ በወሬ ሳይሆን በተግባር የኢኮኖሚው ሞተርነቱን ተቀብሎ መስራት ይጠበቅበታል፡፡

2. በዘመቻ ዕቅድን ለማሳካት መሯሯጥ ብቻ ሳይሆን፣ በጥሞና የታክስ ከፋዩን ሮሮ የሚሰማ ጆሮ ሊኖረው ይገባል፡፡

3. በንግዱ ክፍለ-ኢኮኖሚ ላይ የተጫነው አስጨናቂ የሆነ ግብር መከለስ ይገባዋል ብሎ አንድነት ያምናል፡፡ ያለችውንም ጠባብ የግብር መሠረት ጨርሶ ከመናድ ይልቅ የተዝረከረከውን የመንግስት አስተዳደር ወጪ በመቀነስ፣ አገዛዙ ራሱን ከሙስና ማፅዳት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

4. በኢትዮጵያ ከ40 በመቶ በላይ የሆነው የንግድ እንቅስቃሴ ከሕጋዊ ማዕቀፍ ውጪ (informal economy) እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እነዚህ በዚህ መስክ የተሠማሩ ዜጎች ደረጃ በደረጃ ወደ ታክስ ስርዓቱ የሚገቡበት ሁኔታ ላይ ማተኮር ያስፈልጋል፡፡

5. ገዥው ፓርቲ ከሀገር ጥቅም ይልቅ ለስልጣን ማስቀጠያ ይጠቅመኛል በሚል ለአፈና በሚያወጣው ወጪ ሊጠየቅ ይገባዋል፡፡ ዜጎች ለልማት እንዲውል የሚከፍሉት ታክስ ድረ-ገፆችን ለማገድ፣ የቪኦኤና የጀርመንን ድምፅን ለማፈን፣ኢሳት በኢትዮጵያ እንዳይተላለፍ ለማፈን እየዋለ ነው፡፡ የግብር ከፋዩን ገንዘብ የአምባገነንነት ማጠናከሪያ ሊሆን አይገባም፡፡ ይህን መሰሉ አሠራር ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶችን ከመርገጡም በላይ የታክስ ከፋዩን የላብ ውጤት ለአፍራሽና አንዳች ሀገራዊ ፋይዳ ለሌለው የአፈና ተግባር ማዋል ነው ብሎ አንድነት ያምናል፡፡

6. የታክስ አስተዳደሩን ውጣ ውረድ በማቃለል፣የተቀላጠፈ አሰራር መዘርጋት እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡

7. በንግድ ሥራዓቱ ውስጥ ግልፅነት ያስፈልጋል፡፡ ከሕግ ማዕቀፍ ውጭ የተቋቋሙ የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች ቢያንስ ቢያንስ በየዓመቱ ኦዲት እየተደረጉ ውጤቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ መሆን አለበት፡፡

አንድነት ፓርቲ የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት ለማድረግና ተጠያቂነት ያለው መንግሥት ለመመስረት በሚደረገው ትግል የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ የጎላ ሚና ይጫወታል ብሎ ያምናል፡፡ በመሆኑም የንግዱ ማሕበረ-ሰብ ጥቅሞቹና መብቶቹ ተከብረውለት ላገር እድገትና ብልፅግና ሊያበረክተው የሚችለው አስተዋፅኦ ሳይገደብ እንዲንቀሳቀስ አንድነት አበክሮ ይታገላል፡፡

ሐምሌ 29 2003 ዓ.ምአዲስ አበባ

በንግዱ ሕብረተሰብ ላይ የተጣለው የግብር ጫና ፍትሐዊነት የጎደለው የሞኝ በትር ነው!ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY

(UDJ)

Page 7: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

ኢኮኖሚ

ግርማ ሠይፉ ማሩ

በሰሞኑ የመንግሰትና ነጋዴ የግብር ፍጥጫ በከተማችን ዋነኛ ርዕሰ ነው፡፡ ይህንን አሰመልክቶ በኢቲቪ የግብር ሰብሳቢው መ/

ቤት ምክትል ዳይሬክተር ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ /የኢቲቪ ሀርድ ቶክ በሚመሰል መልኩ/፡፡ ለምን ያህል ግብር ከፋይ መሳጭ እንደነበር ባላውቅም ዋና ዋና የሚባሉ ጥያቄዎች ተነሰተው ምላሽ ተሰጥተዋል፡፡ ያሰገረመችኝ መልስ ግን ዘመናዊ መኪና አቁመው የቅሬታ ፎርም ይሞላሉ የምትለዋ ነች፡፡ እነዚህ አሰተያየቶች መሰለኝና ደሳለኝን ያሰፋፋሉ የሚል ፍርሃት አለኝ፡፡ በሰሞኑ ብዙ አሰገራሚ ገጠመኞች የሰማው ሲሆን አንዱ ላጋራቹ፡፡ አንድ ገዥ ወደ ትንሽ መደብር ሄዶ ሣሙና ሰንት ነው ሲለው ሰላሣ ሰምንት ሺ ይለዋል ይንን ሣሙና ነው ያልኩህ ሲለው ይቅርታ ግብር ያልክ መስሎኝ ነው አለው ይባላል፡፡ ቀልድ አይደለም፡፡

ይህንን የግብር ከፋይና አሰከፋይ ፍጥጫ አሰመልክቶ የግሌን ላጋራችሁ ወደድኩ፡፡ ከግብር ከፋይ በተለይ ሁኔታ ዋነኛ ሰለባ የሆነው የግምት ግብር ከፋይ ነው፡፡ ግምት ለምን ሲባል ነጋዴው ገቢና ወጪውን በመዝገብ ሰለማይዝ ነው መልሱ፡፡ ነጋዴው ለምንድነው መዝገብ የማይዘው የሚለው ጥያቄ መፈተሸ ይኖርበታል፡፡

በኔ ዕይታ፤

• በነጋዴው አንፃር አነሰተኛ የቀን ገቢ ግምት በማሰመዝገብ አነሰተኛ ግብር ለመክፈል የሚደረግ ጥረት ሲሆን ይህም በገቢ ሰብሳቢመ/ቤት ሠራተኞች ይፋ ያልሆነ ድጋፍ ይደረግለታል ምክንያቱም የሰራተኞቹ ሰልጣን የሚመነጨው ከመገመት ሰለሆነ (ይህ ግምት ለረጅም ጊዜ ሳይከለሰ በመቅረቱ የግብር አሰገቢ መ/ቤት ሠራተኞችን ሰልጣን ቀንሶት ነበር)፤

• ነጋዴው እንደፈለገው በመግዛትና በመሸጥ፤ እንደፈለገው በማውጣት የገንዘብ ማንቀሳቀስ “ነፃነት” ፍላጎት ሰለአለው የሂሣብ ሠራተኛ እንዲኖረው ያለመፈለግ በሰፋት ይታይበታል፤

• ዋነኛው ምክንያት ግን በአብዛኛው ነጋዴ ዘንድ ያለው መዝገብን የመያዝ ጥቅም ላይ ያለው የግንዛቤ ውሱንነት ነው፡፡

ዋነኛው ጉዳይ ላይ ስናተኩር ግብር ከፋዩና ማህበራቸው ንግድ ምክር ቤት እንዲሁም መንግሰት በየፊናቸው ምን እያደረጉ ነው? ብለን መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡

መንግሰት ዓላማው ግብር መሰብሰብ ብቻ በሚመስል መልኩ ገቢ ላይ አተኩሮ እየሰራ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር በወር አንድ ደረሰኝ የማይቆርጥ ግብር ከፋይ ሁሉ የዕለት ሸያጭ መመዝገቢያ ማሻን እንዲተክል ያሰገድዳል፡፡ የዕለት ሸያጭ መመዝገቢያ ማሽን ግን ለግብር ከፋዩ ከመዝገብ መያዝ ጋር ያለውን ጠቀሜታ ማሰረዳት የሚችል የግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ሠራተኛ ማግኘት ግን ዕልም ነው፡፡ ሁሉም በማሰገደድ ነው፡፡ በቅርቡ ጉዳዬ በፍጥነት አልተሰተናገደም ብዬ ለአቤቱታ የሄድኩበት ሥራ አሰኪያጅ ግዴታህን ተወጣ ነው ያለኝ፡፡ ማሰገደድና ግዴታ ብቻ የሞላበት ሆኖዋል፡፡ ግብር ከፋዩ ይህንን ግዴታውን ከመወጣቱ ጉን ለጎን (ገቢውን በትክክል መሣወቁን ማለት ነው) በወጪ አንፃር ያሉትን መብቶቹን በትክክል እየተጠቀመ አይደለም በመሆኑም ገቢውን ለማግኘት ሲዳክር አንዴ ከግራ አንዴ ከቀኝ ኪሱ ሲከፍላቸው የሚውላቸውን ክፍያዎች የሚታዩበት መንገድ ይጠፋል፡፡ መንግሰት ገቢውን አውቆዋል (በግብር ከፋዩ ወጪ በተተከለ ማሽን፤ ወይም በመከረኛ ግምት) ወጪውን በትክክል ማሳየት የግብር ከፋዩ ጉዳይ ነው በማለት ቸል ተብሎዋል በዚህም መነሻ የተጋነነ ግብር በግብር ከፋዩ ላይ ተጥሎዋል፡፡ መንግሰት ከዚህ ዘለግ አድርጎ ማሰብ ይጠበቅበታል፡፡

ግብር ከፋዩ ከገቢው ላይ እንደፈለገ ወጪን ማውጣት ነፃነት የመሰለውን ያህል ነፃነት እንዳልሆነ መረዳት ያለበት ወቅት አሁን ነው፡፡ ሰለዚህ ግብር

ከፋዩና ማህበሩ ንግድ ምክር ቤት ጠንቅቀው ሊረዱትና ትኩረት ሊሰጡት የሚገባው የግብር ከፋይ ወጪ በሥርዐት ተመዝግቦ መያዝ መሆን ይኖርበታል፡፡ ገቢው መንግሰትን የሚያክል አባት አለውና፡፡ በግሌ ግብር ከፋይነት የሚያኮራ መሆኑን እገነዘባለሁ፤ ግብር ከፈይና አሰከፋይ ግን አይጥና ድመት ድብብቆሸ መቆም አለበት፡፡ ከዚህ አንፃር ግብር ከፋይም አሰከፋይም ማድረግ ያለባቸውን መጠቆም ተገቢ ነው፡፡

መንግሰት የገቢው መሰመር እንጂ ሌላው አያገባኘም በሚል ሰሜት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በመግታት በባለሞያ ተዘጋጅቶ ለሚቀርቡ የገቢና ወጪ መግለጫዎች ማበረታቻ በመሰጠት አብዛኛው ግብር ከፋይ በባለሞያ እንዲጠቀም በማድረግ እና ባለሞያዎች ህግና ደንብ በማስከበር ዋነኛ ተሣታፊ እንዲሆኑ በማድረግ በግብር አሰከፋይ መ/ቤት የሚታየውን እሮሮና እንግልት በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ እንደሚቻል መገመት ይቻላል፡፡

ግብር ከፋዮች ምንም ትንሽ እንቅሰቃሴ ቢሆን ያላቸው ገቢና ወጪያቸውን በማሰረጃ አሰደግፈን በማቅረብ ከግምት አሰራር ከዚህም ጋር ተያይዞ ከሚመጣው መንግሰት እነዲላይደርግኝ ይችላል ከሚል ፍርሃት የሚመነጭ የአሰተሳሰብ ነፃነት ማጣትን ሊያሰቀር ይገባዋል፡፡ ንግድ ምክር ቤት ይህንን ችግር ለመፍታት ተግቶ መሰራት እንዳለበት አምናለሁ፡፡

አሁን ያለንበትን አሳዛኝ የግብር ከፋዮች ሁኔታ ለማሻሻል በመረጃ ላይ የተመሠረተ የግበር ሥርዐት እንዲሰፋፋ በግብር ከፋዮች አካባቢ ያለውን የግንዛቤ ችግር መቅረፍ ትኩረት የሚሻ ነው፡፡ አሁን ባለን ግኑኝነት ይህች ሀገር የጋራችን ከሆነች አሁን የተጣለው ግብርም ለሀገር ነው ካልን፤ ይህ ግብር ለዘንድሮ በተጋነነ ሁኔታ ሳይከፈል ቢቀር/ማሻሸያ ቢደረግለት/ ገንዘቡ የሚቀረው ዜጎች እጅ ነው፡፡ መንግስት ዜጎች ወደ ንግድ ሥርዐቱ እንዲገቡ ማትጋት እንጂ ጠቅልለው ከንግድ እንዲወጡ ማድረግ አይጠበቅበትም፡፡

በመጨረሻ ሁሉም ግብር መክፈል አለበት ሰንል ጥቃቅን ተብለው ያለደረሰኝና የዕለት ሸያጭ መመዝገቢያ ማሸን የሚንቀሳቀሱትን ይጨምራል፡፡ ጥቃቅን መሆን መብታቸው ቢሆንም በንግድ ሥርዐት መግባትና ግብር መክፈል ግን እንደሌሎቻችን ሁሉ ግዴታ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ለገማቾች አንድ መረጃ ልስጥና ላብቃ በኢቲቪ ለፕሮፓጋንዳ የሚቀርቡት የልማት አርበኞች/ሚሊየነሮች በገለፁልን መሰረት ግብር ተጥሎባቸው ይሆን? ከሆነ አሁንም በግብር ከፋይነት ያቅርቡልን፡፡ ይህ ሚሊየነር አርሶ አደሮችንም ይጨምራል፡፡

የነጋዴና መንግሰት ድብብቆሸ ይቁም

መንግሰት የገቢው መሰመር እንጂ ሌላው አያገባኘም በሚል ሰሜት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በመግታት በባለሞያ ተዘጋጅቶ

ለሚቀርቡ የገቢና ወጪ መግለጫዎች ማበረታቻ በመሰጠት አብዛኛው ግብር ከፋይ በባለሞያ

እንዲጠቀም በማድረግ እና ባለሞያዎች ህግና ደንብ በማስከበር ዋነኛ ተሣታፊ እንዲሆኑ

በማድረግ በግብር አሰከፋይ መ/ቤት የሚታየውን እሮሮና እንግልት በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ

እንደሚቻል መገመት ይቻላል፡፡

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የሚመረውና ሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ብፁዕ ሊቀጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ በማረፋቸው ሥርዓተ ቀብር አፈፃፀማቸውን በሚመለከት መግለጫ አወጣ

ቅዱስ ሲኖዶሱ እንዳስታወቀው ከሆነ የብፁዕነታቸው ክቡር ሥጋ የሚያርፍበትን ቦታ ሲመርጥ እንደቆየና ከዚያም በቴክሳስ ክፍለ ሀገር በሚገኘው በሂውስተን ከተማ በተመሰረተው

የቅዱስ ሲኖዶስ ገዳም ክቡር ሥጋቸው በቋሚነት አርፎ ገዳሙም በስማቸው በቋሚነት መሰየሙን አስታውሰው እስከዚያው ግን በጊዜያዊነት በሲያትል እንዲቆይ መታሰቡን አስታውቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ ብፁህ አቡነ ዜና ማርቆስ የመሰረቱትና ለረጅም ጊዜያት ያገለገሉበት በሲያትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን የሚገኘው መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ክቡር አፅማቸው እንዲያርፍ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ባደረጉት ጥረት ቅዱስ ሲኖዶስ የተቀበለውና ያፀደቀው መሆኑን

ገልፆ በዚህም መሠረት የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ቅዳሜ ነሐሴ 21 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም (August 27,2011) ሥለሚፈፀም ምዕመናን በሲያትል መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክርስቲያን የመጨረሻ የክብር አሸኛኘት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በስማቸው የተሰየመው በሂውስተን ከተማ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ገዳምም መታሰቢያነቱ በብፁዕነታቸው ስም ለዘለዓለሙ እንደሚቀጥል ቅዱስ ሲኖዶሱ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በሰሜን አሜሪካ ይኖሩ የነበሩት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ አረፉ

Page 8: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

የአደባባይ ሚስጥሮች

መዝናኛከናቴ ማህጸን ነው ስፈጠር ከጥንቱ ከህይወት መስመሩ ካገናኝ ከእትብቱወይስ ከእናቴ ጡት ካይኖችዋ እይታከየት ነው ያገኘኝ ከቶ ከምን ቦታ ያገር ፍቅር ልክፍት ያገር ፍቅር በሽታ;

ከረገጥኩት መሬት በውስጥ እግሬ ገባወይስ በጥዋት ፀሐይ ተወጋሁ ከጀርባከበላሁት ቆሎ ጠረሾ አምባሻከእንጀራ በሹሮው ጥቅል የእናት ጉርሻከጠጣሁት ወተት ከጠጣሁት ውሃከእረኝነት ውሎ ከዱር ከበረሃ;

በነሐሴ ምሽት በቡሄ ጨለማሆያሆዬ ስንል አሲዮ ቤለማእደጉ ልጆቼ! ብለው ሲያቀብሉንየቡሄ በረከት የዳቦ ሙልሙሉን ከሙልሙሉ ይሆን ከቃናው ከጣዕሙወይስ ከምረቃው ከቃል ከትርጉሙ;

ከቶ ከየት ይሆን ከምኑ ከስንቱሳላውቀው የነካኝ ያገር ፍቅር ልክፍቱ;

ቄስ ትምህርት ቤት ይሆን ከየንታ ቤት ታዛ“ሀ ሁ” ስል “ለ ሉ” ስል ፊደልን ሳባዛ በቀለም በፊደል በነጥብ ተመስሎ በውስጤ የገባ ዓይነኩሌን ከፍሎወይስ ውሎ አድሮ ነው ከፊደል በኋላ የንታን “ሄድኩኝ”ብዬ ስገባ ካስኳላ;

ገባ በጆሮዬ ተመስሎ ዜማ“ኢትዮጵያ ሆይ” ብለው ሲጠሯት ስሰማ“ተጠማጅ አርበኛ ባገር መውደድ ቀንበር”ለሶስቱ ቀለማት በሰልፍ ሲዘመርአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ባንዲራስትወጣና ስትወርድ ስንዘምር በጋራ;

በክፍል ውስጥ ይሆን በዕውቀቱ ገበታሳላውቅ ሳላስበው ልቤ የተመታ;ከመጽሓፉ ይሆን ከታሪክ ፀሐይወይስ ከመምህሩ ከዚያ ዕውቀት አስፋፊባገር ፍቅር ልክፍት ተለክፎ አስለካፊ;

አባ ቄሱ ይሆኑ ሳላውቀው ያጠቁኝበክርስትና ስም በእምነት ያጠመቁኝባገር ፍቅር እሳት ለመንደድ ያበቁኝ; ከቶ ከየት ይሆን ከምኑ ከስንቱድንገት የነካካኝ ያገር ፍቅር ልክፍቱ;

ከምሥራቁ ይሆን ካገሬ ምዕራቡወይስ ከሰሜኑ ወይስ ከደቡቡየትኛው ነፋስ ነው ከየት የከነፈያገር ፍቅር ልክፍት ጥሎብኝ ያለፈ;

ባዕድ አገር ብሄድ ባሕር ተሻግሬዕውቀትን ፍለጋ ርቄ ከሃገሬ“ላገር ፍቅር በሽታው ላገር ፍቅር ልክፍቱ ባገር ነው” እያለ ያለ መድኃኒቱየባዕድ አገሩን ማዕሰርቱን በጣጥሶሲያከንፍ ያመጣኛል መልሶ መላልሶ፡፡

ኑሮ ከፋኝ ብሎ ሲፈልስ ወጣቱኑሮ ከፋኝ ብሎ ሲፈልስ አዛውንቱአገር ከፋኝ ብሎ ሲሰደድ ሙሁሩሰው መኖር ሲያቅተው በትውልድ አገሩ“ልሂድ” “ልውጣ” ሲሆን የሰው ንግግሩ“አንተ እንኳን አትሄድም ባታስበው “ብሎ ያገር ፍቅር ደዌ ይዞኛል ቸክሎ፡፡

እንዲህ ከጠበቀ መተሳሰራችንየእናትና የልጅ የውል ማተባችን

እንዲህ ልጄ ካልሺኝ ውድ እናት አገሬ ውድ እናቴ ክብሬእኔም ልቤ ይርጋ ልጽና በመግባሬበክቡር ከርስምድርሽ ይሁን መቃብሬ፡፡

ያገር ፍቅር ልክፍት

ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ

የማን ኮከብ ትሆን?አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ባንዲራችን፣ብለን እንዳልዘመርን በልጅነታችን፣ኮከብ ሲፈነጠቅ ምን አለ ሕዝባችን?በባንዲራዬ ላይ ከመሀል የገባሽ፣ከዘጠኙ አለማት ወደዚህ የመጣሽ፣የማን ኮከብ ትሆኝ ማንስ ለጠፈሽ፣ከሳተርን ይሆን ወይስ ከጁፒተር ወይስ ከሩቅ ቦታ ከፕሎቶ መጣሽበባንዲራዬ ላይ ከመሀል ቁጭ ያልሽ? ፍፁም አልገባኝም የኮከቧ ነገር፣በተቀፅላነት መሃሏ በክብር ሙሉነሽ አበባየሁ

ትሪሊዮን ምንድነው?“3.4 ትሪሊዮን ለመሰብሰብ አስበናል” አንድ

ግብር ሰብሳቢ “ትሪሊዮን ምንድነው” ነጋዴውሰሞኑን ከገጠሙኝ ገጠመኞች አንዱን

ላካፍላችሁ፡፡ በያዝነው ጥቂት ወራት በተለይም ባለፈው ሰኔና ሐምሌ ወር ውስጥ ነጋዴው በግብና በቫት ክፍያና ተመን አተማመን ላይ ሲተራመስ መከረሙ የአደባባይ ምስጥር ነው፡፡ የማተራመሱ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሎአል፡፡ ዛቻ እና ማስፈራራቱም እንደዚያው ነው፡፡ ይህንኑ የማተራመስ ሥራ ለመታዘብ ወደ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መስተዳድርና ወረዳዎች ስዘዋወር ነበር፡፡

በተይም አንድ ቀበሌ ውስጥ የነበረው እሰጣገባ ቀልቤን ሳበው፡፡ አንዱ ግብር ከፋይ በተተመነለት ተመን በመበሳጨት ከግብር ሰብሳቢው ሠራተኛ ጋር ይሟገታል፡፡ “ምን ሠርቼ ነው ይህን ያህል የምከፍለው? በቀን ስንት ባገኝ ነው? ይህን ያህል የምታስጨንቁኝ? ስንት ብር ፈልጋችሁ ነው?” በማለት ጥያቄ ይደረድራል፡፡ ግብር ሰብሳቢው ተረጋግቶ “ እኛ መሰብሰብ የፈለግነው 3.4 ትሪሊዮን ነው”ይለዋል፡፡ ነጋዴው ንዴቱን ትቶ ድንጋጤ ቢጤ ካሳየ በኋላ ቀና ብሎ እየተመለከተው “ትሪሊዮን ደግሞ ምንድነው?” ሲል ጠይቋል ሠራተኛውም የብር መጠን ነው ሲለው ነጋዴው ጭንቅላቱ እየነቀነቀ ሄዷል፡፡

ሞባይል ያልገዙ ብፁዓን ናቸው!!

በአንድ ወቅት በአንድ መዝናኛ ማዕከል ከጓደኞቼ ጋር መጠጥ ብጤ ይዘን ተቀምጠን ነበር፡፡ መጠጥ ቤት የገባነው በቀን በመሆኑ ተሰብስበን ጫወታ ብንይዝም ብዙ የሚያዝናና አልነበረም፡፡ መጠጥ ቤቱ ውስጥ ከነበሩት ሰዎች አንዱ አንድ መከራከሪያ ነጥብ ያነሳል፡፡ “ሞባይል የሚይዝ ሰው ሁሉ ውሸታም ነው” ይላል፡፡ “የለም ሞባይል የያዘ ሁሉ ውሸታም አይደለም፡፡ ሞባይል በራሱ ውሸት ይዞ አይመጣም ሞባይል የቴክኒዎሎጂ ውጤት ነው፡፡ የሥራ መሣሪያ ነው፡፡” እየተባለ ክርክሩ በስፋት ቀጠለ፡፡ ሐሣቡን ያነሳው ግን ፍንክች ሊል አልቻለም፡፡ “ሁሉም ውሸታም ነው! ውሸታም ነው!” እያለ ደጋገመው፡፡

በተለይ እኔ “ እንዴት ሞባይል የያዘ ሁሉ ውሸታም ይባላል? እኔ ሞባይል አለኝ ውሸታም ተብዬ ልፈረጅ አልችልም” በማለት አምርሬ ተከራከርኩ፡፡ መጀመሪያ ሐሳቡን ያነሳው ግን በምንም ዓይነት ሊሸነፍ አልችለም፡፡ በዚህ ላይ እያለን አለቃዬ በሞባይሌ ላይ ደወሉልኝ፡፡ “ፈልጌህ ነበር የት ነህ? አሁን መምጣት ትችላለህ?” አሉኝ:: ድንጋጤ ተሰማኝ እረፍት ላይ ብሆንም መጠጥ የጀመርኩት በቀን በመሆኑ አሳፈረኝ:: አለቃዬ ቢሮ ብገባ ሊሸታቸው ይችላል መሄድ የለብኝም ብዬ ወሰንኩ፡፡ እዚያው ክርክሩ መሐል ሆኜ መልስ ሰጠኃቸው:: “ከአዲስ አበባ ውጪ ነኝ:: ዛሬ መምጣት አልችልም” አልኳቸው፡፡ “በል ነገ ጥዋት እንድትመጣ” ብለውኝ ተሰነባበትን፡፡ ሁሉም ሳቁብኝ:: በተለይ ሐሳቡን ያነሳው ሰውዬ ከመቀመጫው ተነስቶ ጨፈረ፡፡ “ይኸውላችሁ:: አላልኳችሁም!! ዝም ብላችሁ ትከራከራላችሁ፣ 20 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንዲህ ለምትጋለጠው ትከራከራለህ” ብሎ አሳፈረኝ፡፡ ይህ እያስገረመኝ ስሞኑን በአንድ ቤተክርስቲያን አካባቢ ሣልፍ አንድ ነገር ሰማሁ ቄሱ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ክርስቲያኖች ውሸትን ተጠየፉ” እያሉ ያስተምራሉ፡፡ “ሰዎችን ለውሸት ከሚገፋፉ ነገሮች አንዱ ሞባይል ነው፡፡ እውነት እውነት እላችአለሁ! ሞባይል ያልገዙ ብፁአን ናቸው” ሲሉ የእኔ ውሸት ትዝ አለኝ ብቻዬን ሳኩኝ፡፡

ኪነ-ጥበብ ሙዚቃ፣ ሥዕል፣ ፊልም፣ ድራማ፣ ሥነ-ፅሁፍ፣ ሥነ -ህንፃ ጥበብን በአንድ ላይ የያዘ ትልቅ የሕዝብ ሃብት ነው፡፡

ይህ ጥበብ የአድን ሀገር ሕዝብ ባህል፣ ወግ፣ እሴት፣ አኗኗር፣ አገዛዝ፣ ልቅሶ፣ ሠርግ የመሣሰሉት የህዝብ ፍላጐት ዓላማ እና እንቅስቃሴ የሚያንፀባርቁ የጋራ ሃብቶች ናቸው፡፡

እነዚህ በአግባቡ ካልተጠበቁና ካልተያዙ ከህዝብ ይልቅ የግል ፍላጐት ማንፀባረቂያና ዓላማ ማስፈፀሚያ ወደ መሆን መሸጋገራቸው የማይቀር ነው፡፡ እነኚህ ወደ ግል ፍላጐት ብቻ መዞራቸው ደግሞ የባህል መወራረስን ሳይሆን መበረዝን፣ ታሪክን ከማጠናከር ይልቅ ወደ ማፋለስ ይሄዱና ባለቤት የሆነውን ህዝብ ወይም ሀገር ባይተዋር ያደርገዋል፡፡ እዚህ ላይ ግለሰቦች በቀና አስተሳሰብ ካላሰቡበት እና ካልተጠነቀቁበት አደጋው ለተተኪ ትውልድም ይተርፋል፡፡ ስለዚህ ልናስብብበት ይገባል፡፡ ሁሉንም የኪነ-ጥበብ ውጤቶች በአንድ ጊዜ መቃኘት ባይቻልም ጥቂቶቹን ያሉበትን ሁኔታ ለማየት እንሞክራለን፡፡

ሙዚቃሙዚቃ ለየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ አዲስ እንዳልሆነ የሚታወቅ

ነው፡፡ ይህም አብሮ ያደገና ጥብቅ ትስስር ያለው እንደ ሆነ ምስክር የሚያሻው ባይሆንም ከዕድገቱ አንፃር ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ነገር ግን ህዝብን ለሥራ በማነሳሳት የሀገርን ገፅታ በመገንባት ባህልን

በማስተዋወቅ እና የገቢ ምንጭ በመፍጠር ረገድ ያለው ጥረት እጅግ በጣም አናሳ ነው፡፡ ምክንያቱም ቋንቋቸውና ባህላቸው የተበረዙ ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች እንኳን በሚደረግላቸው ድጋፍ ወደ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ሰብረው መግባት የቻሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ግን ካሉን የባህልና ቋንቋዎች ብዛት ያለበት ደረጃ የጥበብ ያለህ ያስብላል፡፡

በተለይ ባለፈው በደርግ ሥርዓት ወቅት እንኳ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ሙዚቃ ቡድን በማዋቀር “የህዝብ ለህዝብ” ለተለያዩ የሀገሪቱና የዓለም ክፍል የኢትዮጵያን የሙዚቃ ጥበብ ለማስተዋወቅ ጥሩ ተሞክሮ ቢኖርም አሁን ግን ቦታ የተሰጠው አይመስልም፡፡ በተለይም አሁን ያለው መንግስት የብሔር ብሔረሰብ ቋንቋና ባህል የሚል የፖለቲካ “ነጠላ ዜማ” ከማቀንቀን ያለፈ ሊኪነ-ጥበቡ የተደረገ ድጋፍም ሆነ ማበረታቻ አይታይም፡፡ ሙዚቃው ላይ ስንመጣ ግን እየተበረዘ እንዳለ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡

አሁን እየተሰሩ ያሉ ሙዚቃዎችም ተሰርተው እተደመጡ አንድ ዓመት ሳይሞላቸው ይሰለቻሉ፤ የቀድሞዎቹ ግን

ዛሬም ሳይሰለቹ የመደመጣቸው ምስጢር ምን እንደሆነ የሚመለከተው የመንግስት አካል ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል፡፡ እዚህ ላይ ግን የ”ኢትዮጵያን አይዶል” አዘጋጆች ዳኞችና ተወዳዳሪዎች የሚያደርጉት ጥረት ሊመሰገኑ ይገባል፡፡

ሥዕልየሥዕል ጥበብ እጅግ ቀደምት ከሆኑ ከኢትዮጵያ ሃብቶች አንዱ

ሲሆን የባለሙያዎች ቁጥር እና ሀገራዊ ወግ ዕድገታቸው ግን እጅግ በጣም አዝጋሚ ነው፡፡ አሁን ያሉት የጥበብ ባለሙያዎች ብዙ ቢሆኑም ለህዝብ ዕይታ ያበረከቱት አስተዋፅዖ ግን አናሳ ነው፡፡ ለዚህም ነው በጣት የሚቆጠሩ ጥቂት ባለሙያዎችን የምንጠቅሰው እነኚህ ስመጥር አርቲስቶች በዕድሜ እየገፉ ያሉ ሲሆን ሊሰጠውና ወጣቱን ማበረታታትና ሁኔታዎችን በማመቻቸት ችግራቸውን በመረዳት ለሥዕል ጥበብ ዕደገት የሚነሱ ጥያቄያቸውን ማድመጥና የተግባር መልስ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

ፊልምየተንቀሳቃሽ ምስል (ፊልም) ምንም እንኳ በዳግማዊ ምኒሊክ ዘመን

በ1900 ዓ.ም የተጀመረ ቢሆንም በመንግስት ህጋዊ ዕውቅና ተሰጥቶት በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የተጀመረው ግን በደርግ ዘመን ነበር፡፡ በ1950 ዓ.ም “ሂሩት አባቷ ማነው?” በሚል በሴተኛ አዳሪዎች ዙሪያ የሚያጠነጥን መልዕክት አዘል ፊልም የተሰራ ሲሆን ፊልሙ ተጀምሮ እስኪፈፀምም የግሪኮች እጅ ነበረበት ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ በበኩላቸው በ1970 ዓ.ም አካባቢ ለኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ከፍተኛ አስተዋፅዖ

ኪነ-ጥበብ የህዝብ? ወይንስ…

ለዚህ ደግሞ ተጠያቂው መንግስት ስለሆነ የህትመትና የወረቀት ዋጋን ከመቀነስ በተጨማሪ ልዩ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል፡፡ አለበለዚያ ካለው የህዝብ ቁጥርና ፍላጐት አንፃር የሥነ ፅሑፍ ዕድገት አለ ብሎ ማለት በህዝብ መቀለድ ስለሆነ ቅድሚያ የህዝብን የሥነ-ፅሑፍ ጥበብ ትርታ ፍላጐትን በማድመጥ ለነገ የሚተው ሳይሆን ዛሬውኑ ትኩረት ሊቸረው ይገባል፡፡

ወደ ገፅ 9 ዞሯል

Page 9: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

መጥቶበት እንጂ አምኖበት አይደለም ይላሉ፡፡

ሌላው ፓርቲው ከቀድሞ አቋሙ ወደ ኋላ ያፈገፈገበት ከ2ዐዐ1 ዓ.ም ወዲህ ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ አደባባይ ያወጣው አዲስ ፅንሠ-ሃሣብ “ሕዳሴ” የሚል ነው፡፡ ድልድዮች፣መንገዶች፣ግድቦች ሁሉ “ሕዳሴ” ተብለዋል፡፡ የጠ/ሚንስትሩ በታሪክ መታወስ የሚፈልጉበት ምኞቶች ሁሉ “ደርግን ለመጣል በተደረጉት ትንቅንቶች ባደረጉት አስተዋጽኦና የሕዳሴው ጀማሪ” መሆኑን ነግረውናል፡፡ ለመሆኑ ህዳሴ ምንድን ነው?

የኢሕአዴግ ካድሬዎች ከ2ዐዐ1 ዓ.ም ወዲህ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲገልፁት እንደምንሰማው ከሆነ “የአክሱም፣የላሊበላና የጎንደር የነገሥታትን ግንቦች” መሠረት አድርገው የተነሱ ይመስላሉ፡፡ ከላይ እንደተገለፀው እነዚህ የኢትዮጵያ አምዶች ደግሞ የሕብረ-ብሔራዊ ፖለቲካ ፓርቲዎች የድጋፍ ማሰባሰቢያና የመታገያ ስልቶች ናቸው፡፡ የቀድሞው ቅንጅት ባጭር ጊዜ ውስጥ በተደረገ ቅስቀሳ ሕዝብ ከዳር እስከዳር ተነቅንቶ የመረጠው ይዞት በተነሳው በዚህ መርህ ነበር፡፡ ይህንን ሀቅ ወዲያውኑ ኢሕአዴግ የተገነዘበው ይመስላል፡፡ በመሆኑም ወደ ሕዝብ ለመቅረብ ያነሳው መፈክር “ህዳሴ” የሚል ነው፡፡

የሕዳሴን ፅንሰ ሐሣብ ወይንም ሥረ-ነገር ለመረመረ ብርቱ ግለሰብ ሊያገኝ የሚችለው ታሪክ ይዞት ወደ አውሮፓ ይገባል፡፡ ባጭሩ ለመግለፅ ያህል ምዕራብ አውሮፓ ከ6ኛው እስከ 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመናት ሥልጣኔ ያሽቆለቆለበትና የካቶሊክ ቤተ-

ክርስቲያን የበላይነት የነገሠበት ዘመን ነበር፡፡ በጥንታዊት ግሪክና ሮማውያን ዘመን የነበሩ የሥልጣኔ ምልክቶች በተለያዩ ምክንያቶች በመውደማቸውና በምትካቸው ትቢትና ድንቁርና በመስፈኑ ፍልስፍና፣ጥበብና ዕውቀት ፈላጊያቸው ጠፋ፡፡

ቤተ-ክርስቲያኗ የግለሰቦችን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች በሙሉ የኔ ብላ ያዘች፡፡ እንግዲህ በዚህ ስንፍናና ድንቁርና በሰፈነበት ዘመን ነበር አንዳንድ ፈላስፎችና የጥበብ ሰዎች ብቅ ብቅ ማለት የጀመሩት፡፡ ይህንን የመነሳሳት ዘመንም “ዳግም ልደት” ወይንም “ህዳሴ” በማለት ጠሩት፡፡ ይህን ለማለት ደግሞ ምክንያት ነበራቸው፡፡ የጥንቶቹን የግሪክንና የሮማውያንን የጥበብና የፍልስፍና ውጤቶችን መውረስና እንደገና ለመፍጠር መነሳሳት የሚል በመሆኑ ነበር፡፡ ሚካኤል አንጀሎና ሌኦናርዶ ዳቬንቺ ግንባር ቀደሞች ነበሩ፡፡ እነዚህ ታዋቂ የጥበብ ሰዎች ከቤተክርስቲያኗ ሕግጋትና የበላይነት ተፅዕኖ በማፈንገጥ ዓለማዊ ሥራዎቻቸውን አደባባይ ማውጣት ጀመሩ፡፡ እንግዲህ “ከሺ ዘመን በፊት የነበረው ሥልጣኔ እንደገና ተደገመ፣ታደሰ” እንደማለት ነው፡፡

በቅርቡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያሣየው ዶክመንተሪ ፊልምም “እንደገና” መባሉ “ዳግም ልደትን” ወይንም “ህዳሴን” ለመግለፅ የተሠራ ይመስላል፡፡ “ትላትን ትልቅ ነበርን፤ዛሬ ግን ተቀድመናል” በሚል ቁጭት የተጠነጠነ ይመስላል፡፡ “የራሳችን ፊደላት፣የራሳችን ቋንቋ፣የራሳችን የተከበረ ታሪክ የነበረን ብንሆንም ዛሬ ግን ርሃብተኞች፣ስደተኞች፣ተመፅዋች

ሆነናል” የሚል ነው ማጠቃለያው፡፡የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫ 97 ዓ.ም

ያደረገው ንቁ ተሣትፎና የቀድሞው ቅንጅት አመራርና አባላት፣እንዲሁም ደጋፊዎች የከፈሉት መስዋእትነት መክኖ አልቀረም፡፡ ኢሕአዴግ ወዶም ይሁን ተገዶ ያወግዛቸው የነበሩትን የሕብረ-ብሔራዊ ድርጅቶችን መርሆዎች መቀበሉ በመጠኑም ቢሆን ለመሠንበት እንደበጀው መረዳት ይቻላል፡፡

ኢሕአዴግ አሁን የቀረው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ “ኒኦ-ሊበራሊዝሞች” ማለቱን ትቶ የሊበራሊዝምን ንድፈ ሐሳብ በመቀበል የበለጠ ቀናነቱን ማረጋገጥ ነው፡፡ በርግጥ የግድ አንዲቀበል አይገደድም፡፡ ወይንም ባለመቀበሉ አይወገዝም፡፡ የሌሎችን መብቶችና ራእዮች በመኮነን የሌለና እነሱ መርሃችን ነው ባላሉበት ጉዳይ ላይ ተለጣፊ ስም ሰጥቶ “ኒኦ-ሊበራሊዝም ተላላኪዎች!” በማለት ማውገዝ ግን ተገቢ አይደለም፡፡ ምናልባትም “ነፍጠኞች፣ትምክህተኞች!” እያለ ያወግዛቸው እንደነበረው “ኒኦ-ሊበራሊዝምን” ደግሞ ጥሎ ሌላ ተለጣፊ ስም ያወጣላቸው እንደሆነ ወደ ፊት የምናየው ይሆናል፡፡

“እኔ የምመራበት ፍልስፍና አብዮታዊ ዴሞክራሲ ነው ለዚች ሀገር የሚያዋጣት”ብሎ መከራከር ይችላል፡፡ ማመዛዘኑንና ምርጫውን ግን ለሕዝብ መተው አለበት፡፡ ባንፃሩ የሕብረ-ብሔራዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች የራሳቸውን ፍልስፍና ለሕዝብ በማስተዋወቅ መቀስቀስ መብታቸው ነው፡፡ ሕዝብ የሚጠቅመውንና የሚበጀውን ያውቃልና፡፡ ፍርዱን ግን ለሕዝብ መተው ነው፡፡ ከዚህ መርህ ውጭ ግን ተለጣፊ ስም እየሰጡ

አበርክተዋል እያበረከቱም ይገኛሉ፡፡ነገር ግን አሁን ከቅርብ ጊዜ

ወዲህ የፊልም የቁጥር ደረጃዎች ከፍ ቢሉም በይዘት ጥልቀትና መልዕክት አዘል ጉዳይ ላይ የባህር ማዶ የተሰራ ታሪክ እና ትርጉም ላይ ከመጠንልጠል ኢትዮጵያዊ መልዕክት እና አስተምህሮ ይዞ መቀጠል እንዳለበት ሳንጠቁም አናልፍም፡፡

በሲኒማ ቤቶች ያለው እጥረት እና በክልል ከተሞችም አካባቢ የሚገኙ የፊልም አፍቃሪያንም ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ሲሆን የሚመለከተው የመንግስት አካልም አስፈላጊም ማበረታቻና ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ምክንያቱም ፊልም እንደሌሎቹ የኪነ-ጥበብ ውጤቶች ሁሉ የሀገርን ባህልና ወግ እንዲሁም ገፅታ ግንባታ ላይ ትልቅ ሚና ይጫወታልና፡፡ ለምሣሌ እንደ አሜሪካ ያሉ ሀገራት በ”ሆሊውድ” ኃያልነታቸውን ብቻ ሳይሆን የሚያንፀባርቁበት ትልቅ የገቢ ምንጭም በመሆን ያገለግላል፡፡ ህንድን ብንመለከት ደግሞ ለሀገሪቷ የሥራ ዕድል በመፍጠርና የውጭ ምንዛሪን በማስገባት ትልቁ ኢንዱስትሪ “ቦሊውድ” ነው፡፡ በአህጉራችን አፍሪካ ስንመጣ ደግሞ የናጄሪያው “ኔሊውድ” የተባለው የፊልም ኢንዱስትሪ ከነዳጅ ቀጥሎ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት በመሆን የፊልሙ ኢንዱስትሪ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡

በተነፃፃሪ የፊልም ጥበብ በኢትዮጵያ ከህዝብ ጋር መተዋወቅ ከጀመረ ከመቶ ዓመት በላይ ያስቆጠረ ቢሆንም ዕድገቱ ግን አንገት የሚያስደፋ ነው፡፡ ሲለዚህ ይህን የጥበብ ዘርፍ በማሳደግ በኩል መንግስት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን (መሣሪያዎችን) ከቀረጥ ነፃ በማስገባትና ለባለሙያዎችም አስፈላጊውን ትብብር ከማድረግ በተጨማሪም በትምህርት ተቋማትም እንደ ቴአትር ጥበብ የትምህርት ዘርፍ በመክፈትና

በማሰልጠን ጥበቡን ለማሳደግ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ አለበለዚያ የታሪክ መፋለስ፣ የጭብጥ ይዘት ማጣትና ባህልና ወግን ከመከተል ይልቅ የሌሎች ሀገሮች ጥበብ ላይ ጥገኛ ልንሆን እንችላለንና የሚመለከተው አካል ሊያስብበት ይገባል፡፡

ሥነ-ፅሑፍየሥነ-ፅሑፍ ጥበብ ልክ እንደ

ሙዚቃ፣ ሥዕልና ሥነ-ህንፃ ጥበብ ቀደምት ታሪክ ያለው ሲሆን ዕድገቱ ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በተለይም አሁን እጅግ አሳሳቢና አሰፈሪ ደረጃዎች ላይ ተደርሷል፡፡ ለአንባቢዎች ብዙ የሥነ-ፅሑፍ ውጤቶች ማበርከታቸው ይታወሳል፡፡ ነገር ግን ሀገራችን እንደቀደምት የጥበብ መፍለቂያነቷ ወደ ቀሪው የዓለም ማህበረሰብ ሰብራ መግባት አልቻለችም፡፡ አሁን ደግሞ ደራሲያንን ከማበረታታት ይልቅ አስፈሪ ህጐችን ከማርቀቅ እስከ ህትመት ዋጋ ማናር ያለው ርምጃ ደራሲያንን ብቻ ሳይሆን የተደራሲያን አቅም የሚፈታተንና ቅስም የሚሰብር ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ ተጠያቂው መንግስት ስለሆነ የህትመትና የወረቀት ዋጋን ከመቀነስ በተጨማሪ ልዩ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል፡፡ አለበለዚያ ካለው የህዝብ ቁጥርና ፍላጐት አንፃር የሥነ ፅሑፍ ዕድገት አለ ብሎ ማለት በህዝብ መቀለድ ስለሆነ ቅድሚያ የህዝብን የሥነ-ፅሑፍ ጥበብ ትርታ ፍላጐትን በማድመጥ ለነገ የሚተው ሳይሆን ዛሬውኑ ትኩረት ሊቸረው ይገባል፡፡

ሥነ-ህንፃኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የሥነ-ህንፃ

ጥበብ ያላትና መገለጫዎቿም ሲሆኑ ዛሬ ግን ከመጋዘንነትና የሱቅ አገልግሎት አዳራሽ ከመስጠት ያለፈ ከየት የመጣ

እንደሆነና ምንን እንደሚገልፁ በውል አይታወቁም በየትኛውም ሀገር እንኳ ብዙ የሥነ-ህንፃ ጥበብ ያላቸው ሀገሮች ቀርቶ በቅርብ ነፃነታቸውን የተቀዳጁ ሀገሮች የራሳቸው መገለጫዎች አሏቸው፡፡ ይህም የቀለም ቅባቸው፣ የዲዛይን ጥበባቸው የበርና መስኮት አሰራራቸውና አቅጣጫቸው ማንበብ ለሚችል ሰው መልዕክት አላቸው፡፡

ዛሬ ግን ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ህንፃዎች ምንን እንደሚያመለክቱ እንኳን አሰሪው ባለቤቱ ቀርቶ መሐንዲሶቹ ራሱ አያውቁትም፡፡ ምክንያቱም የሙያ ነፃነታቸው ስለተገፈፈ በማይመለከተው ሰው በመመራት አንዳንዶቹ በሥራቸው እስከማፈርና ስማቸው ሁሉ እንዳይጠቀስ መፈለግ ደረጃ ደርሰዋል፡፡ በተጨማሪም የሚመለከታቸው የከተማ መስተዳደሮች የሚሰጧቸው ተለዋዋጭ ዲዛይንና ማስተካከያ ኃላፊነቱን መውሰድ አለባቸው፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ ህንፃዎች የፀሐይ መውጫ እና መግቢያ ባለመገንዘባቸው የሚሰሯቸው ሙሉ የአሉሙኒየም መስታወት ሽፋን ብዙ ሰዎች የሚያስከትለው የብርሃን ፅብረቃ ለዓይን ህመም ምክንያት እንደሚሆንም ባለሙያዎች ይተቻሉ፡፡ ይህም የዲዛይን ክትትልና ጥራት ማነስ ነው በማለት አስተያየት ሰጭዎች ጠቁመዋል፡፡

በአጠቃላይ ኪነ-ጥበብ እውነት እያደገ ነው ወይንስ እየቀጨጨ የሚለውን የቀድሞው የሀገሪቱን በተለይም ከ1960 1983 ያለውንና ከእኛ በታች የኪነ-ጥበብ ዕድገት የነበራቸው ሀገሮች ዛሬ የደረሱበትና አሁን ያለንበትን ሁኔታ መፈተሸ የከያኒያን ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ብሎም የመንግስት አካላት ድጋፍ አናሳ መሆኑን አምነን በመቀበል ይህም እንዲሻሻል ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል እንላለን፡፡

“ያንቺው ሌባ” የተሰኘ ፊልም ነሐሴ 8 እና 9

ይመረቃልበግሪን ማውንቴን ፊልም ፕሮዳክሽን የተሰራው በደራሲ በላይ ጌታነህ ዳይሬክት የተደረገው “ያንቺው ሌባ” የተሰኝ አስቂኝ የፍቅር ፊልም ነሐሴ 8 እና 9 ቀን 2003 ዓ.ም በተለያዩ የአዲስ አበባና በክልል ከተማ ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል፡፡ የፊልሙ ርዝመት 1፡48 ደቂቃ የሚወስድ ሲሆን 56ዐ,ዐዐዐ ብር ወጪ ተደርጐበታል ፡፡ በፊልሙም ታዋቂና መጣት ተዋንያን ተሳትፈውበታል፡፡ በልዩ የምረቃት ፕሮግራም በሐርመኒ ኢንተርናሽናል ሆቴል ነሐሴ 9፡በ11፡00 ሰዓት እንደሚደረግ ግሪን ማውንቴን ፊልም ፕሬዳክሽን ለዝግጅት ክፍላችን በላከልን ፕሮግራም መረዳት ተችሏል፡፡

ሌዲ ፈርስት” አስቂኝ ፊልም ተመረቀ

በደራሲና ዳሬክተር በላይነህ ጌታነህ የተሠራው “ሌዲስ ፈርስት” የተሰኘው አስቂኝ የፍቅር ፊልም በትላንትውና ዕለት ተመረቀ፡፡ በሰፊና ጥበብ ኢቲ ፊልም ፕሮዳክሽን የተዘጋጀው ይህ በፊልም በትላንትናው ዕለት ሲመረቅ ታዋቂ ተዋንያንና አርቲስቶች የተገኙ ሲሆን በርካታ የፊልም አፍቃሪያን ተገኝተው ተመልክተውታል፡፡ ፊልሙ አስቂኝና አዝናኝ በመሆኑ በርካታ ታደሚዎች በፊልሙ መደሰተቻውን በሥፍራው ለማየት ተችሏል፡፡

ጥበብ ሀበሻ ፊልም አንድ ዓመቱን ሊያከብር ነው“ጥበብ ሀበሻ” አንደኛ ዓመቱን ለማክበር ዝግጅት ላይ መሆኑን ገለፀ ሀሰሻ የሚዲያና ፕሮሞሽን ሰርቪስ ከአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን በጋራ የሚያዘጋጀው “ጥበብ ሀበሻ” የተሰኘ የመዝናኛና መረጃ የሬድዮ ፕሮግራም የተመሰረተበት አንደኛ ዓመት በቅርቡ በሩሲያ ሣይንስና ባህል ማዕከል በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ዝግጅቶች፣ግጥም፣ሙዚቃ፣የትያትር ስራዎች ከታዋቂ ግለሰቦች ጋር የሚደረግ ቆይታ በነሐሴ አጋማሽ ላይ በአሉ ሲከበር በቀጥታ ስርጭት ከF.M 96.3 ጋር በመተባበር ዝግጅቶቹ ለሕብረተ-ሰብ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ እንደሆኑና ዘወትር አርብ ከቀኑ 9፡00-11.00 በኪነ-ጥበብና በሲኒማ ላይ የሚሰራ ፕሮግራም ሲሆን ዘወትር እሁድ ከቀኑ 6፡00-7፡00 በቤተሰብና በፍቅር እንዲሁም ማሕበራዊ ጉዳይ ላይ አስተማሪና አሣታፊ ፕሮግራም እንደሚየዘጋጅ አዘጋጅ ጋዜጠኛ አብርሃም ግዛው ለዝግጅት ክፍላችን ገልጿል፡፡

የኢሕአዴግ ህዳሴና ...

ኪነ-ጥበብ የህዝብ...

ከ ገፅ 5 የዞረ

ከ ገፅ 8 የዞረ

ኪነ ጥበብ

Page 10: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

���0 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

���0 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

ሕግ ዜና

እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ሕገ መንግሥት በተለያዩ መንገዶችና ሁኔታዎች እየተጣሱ እያየን የምናልፍበት ምክንያት ለምንድ ነው የሚለው ነው፡፡ ለኔ የሚመስለኝ ዋናው ምክንያት እነዚህ ግዴታዎችና ሃላፊነቶች እንዳሉብን ያለማወቅ ነው፡፡ለማወቅስ ፍላጐት አለን ወይ? የሚለው ጥያቄም አብሮ ሊነሳ ይችላል፡፡ ወይም አውቀንም ቢሆን ከግድ የለሽነት የተነሳ አይናችንን ጨፍነን እናልፋለን ወይ? የሚል ጥያቄም ሊነሳ ይችላል፡፡

ስለ ሕገ-መንግሥት ማወቅን በተመለከተ ይህን ካልኩ በቅርቡ የኢህአዴግ መንግሥት እየወሰዳቸው ስላሉ ርምጃዎች ከሕገ-መንግሥቱ ድንጋጌዎች ጋር እንደሚጋጩና ሕገ-መንግሥቱን እንደሚጥሱ መገንዘብ አስፈላጊ መሆኑን ለማስታወስ እፈልጋለሁ፡፡ ከዚህ አኳያ የሚነሳው ነጥብ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 29 ላይ ስለተጠቀሰው የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና የመግለጽ መብትን በተመለከተ ነው፡፡ በዚህ በአንቀጽ 29 ውስጥ የሚከተሉት ተድንግገዋል፡፡

29/1 “ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት ለመያዝ ይችላል፡፡

29/2 “ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነፃነት አለው፡፡ ይህ ነፃነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በህትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነፃነቶችን ያካትታል፡፡

እንግዲህ እነዚህ መብቶችና ነፃነቶች በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 10/1 እና 10/2 “ሰብአዊ መብቶችና ነፃነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ የማይጣሱና የማይገፈፉ ናቸው፡፡ የዜጐች እና የሕዝቦች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበራሉ” ተብለው የተጠቀሱትን ጉዳዮች የሚመለከቱ ናቸው፡፡

ፓርቲአችን አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ለዴሞክራሲያዊና ለሰብአዊ መብቶች መከበርና ፍትህ እንዲነግሥ በቆራጥነት የሚታገል ፓርቲ ነው፡፡ ይህን ትግሉንም በሕገ-መንግሥቱ ድንጋጌዎች መሠረት በሰላማዊና በዴሞክራሲያዊ ሲሆን ለሕግ የበላይነትም አበክሮ ይቆማል፡፡ ስለሆነም ሕገ-መንግሥቱን የሚፃረሩ ሕጐች ሲወጡና ተግባራዊ ሲሆኑ እንዲሁም የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎችን የሚፃረሩ አካሄዶች ሲታይ ዝም ብሎ አያልፍም፡፡ አባሎቻችን ደጋፊዎቻችንና አጠቃላይ ዜጐች ሕገ መንግሥቱን እንዲያስከብሩና ራሳቸው ለሕገ-መንግሥቱ ተገዥ እንዲሆኑ ፓርቲአችን ያለምንም ፍራቻ ይቀሰቅሳል፡፡

በመሆኑም አባሎቻችን፣ ደጋፊዎቻችንና ሕዝቡ ይህን የሕገ-መንግሥቱን የማስከበርና ለሕገ-መንግሥቱ ተገዥ እንዲሆኑ ለመቀስቀስ የመጀመሪያ ኃላፊነቱ ሁሉም የሕገ-መንግሥቱ ምን እንደሚል ባግባቡ ማወቅ እንዳለባቸው መጥራትና ማሳሰብ ነው፡፡ ዜጐች ግዴታዎቻቸውን ማወቅና መፈፀም አለባቸው፡፡ መብቶቻቸውን አውቀው ለምብቶቻቸው መከበርም ፀንተው መታገል የሚችሉት ሕገ-መንግሥቱ ያስከበረላቸውን መብቶች ማወቅ ሲችሉ ነው፡፡ ሕገ-መንግሥቱ ምን እንደሚል ዕውቀት ካላቸው ሌሎችንም ማስተማር ይችላሉ፡፡ ሕገ-መንግሥቱ ሲጣስ ሲያዩ ጥያቄ ለማንሳት ብቻ ሳይሆን ስህተት እንዲስተካከል አስፈላጊውንና ተግቢውን ርምጃ ለመውሰድ ይችላሉ፡፡ ይህ ሁሉ እንዲሆን ዜጐች፣ የአንድነት ደጋፊዎችና የአንድነት አባላት ሕገ መንግሥቱ ምን እንደሚል በትክክል እንዲያውቁ ይቀሰቅሳል፡፡ መላልሶ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የሕገ-መንግሥቱን ይዘት አውቆ ተግባራዊ ማድረግ ራሱ ሕገ-መንግሥቱ የጣለብን ኃላፊነትና ግዴታ ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 9 ላይ የሚከተለውን ደንግጐአል፡፡

አንቀጽ 9/1፡- “ሕገ መንግሥቱ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ ነው፡፡ ማንኛውም ሕግ፣ ልማዳዊ አሰራር፣ እንዲሁም የመንግሥት አካል ወይም ባለሥልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ-መንግሥት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም”

አንቀጽ 9/2፡- “ማንኛውም ዜጋ፣ የመንግሥት አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሌሎች ማህበራት እንዲሁም ባለሥልጣኖቻቸው፣ ሕገ-መንግሥቱን የማስከበርና ለሕገ መንግሥቱ ተገዢ የመሆን ኃላፊነት

አለባቸው”የቅርብ ሳምንታት ክስተቶች የሚያሳዩን ግን

የኢህአዴግ መንግሥት እነዚህን መብቶችና ነፃነቶች በገሃድ የሚጥሱ ሆነው ይታዩኛል፡፡ ሦስት ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በቅርቡ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጠኛ ዋና አዘጋጅና የፍትሕ ጋዜጣ አምደኛ ርእዮት አለሙ በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ መሠረት ተይዘው እስካሁን ድረስ በእስር ላይ መገኘታቸው ነው፡፡ እግረ መንገዴን ለመጠየቅ የምፈልገው የእነዚህ ዜጐች አያያዝ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 19 እስከ 21 ድረስ በተደነገገው መሠረት መብታቸውን ባስጠበቀና ባስከበረ መልኩ ነው ወይ? የሚለው ነው፡፡ ወደ ዋናው ነጥቤ ልመለስና የነዚህ ሰዎች መታሰር ምክንያት የሆነው በኢንተርኔት ከአቶ ኤሊያስ ክፍሌ ጋር ግንኙነት ነበራቸው በሚል ነው፡፡ ታዲያ ውጭ አገር ካለ ሰው ጋር መገናኘት እንዴት በሽብርተኝነት ያስከስሳል? በኢንተርኔት ሰዎችን ማግኘት ምኑ ላይ ነው ሽብርተኛ የሚያሰኘው? ኤልያስ ክፍሌስ ማነው? ተግባሩስ ምንድን ነው?

ሁለተኛው ጉዳይ 21 የኦሮሞ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሽበርተኝነት ተከሰው መታሰራቸው ነው፡፡ እንደተገለፀው ከሆነ እነዚህ ተማሪዎች የዓለም አቀፍ የኦሮሞ ተማሪዎች ማህበር አባል በመሆናቸውና በፌስ ቡክ ርሰበርሳቸውም ሆነ ከሌሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠራቸው ነው ተብሎአል፡፡ ከዚያም አልፎ ይህ የኦሮሞ ተማሪዎች ማህበር በኦነግ የሚታዘዝና የሱን ዓላማ ለማስፈፀም የተደራጀ ነውም ተብሎአል፡፡ በመጀመሪያ የሚነሳው ጥያቄ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 31 ላይ እንደተደነገገው “ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓለማ በማህበር የመደራጀት መብት አለው” የሚለውን መብት ሽብርተኛ ያሰኛል ወይ? ይህ የተማሪዎቹ ማህበር በኦነግ የሚታዘዝ መሆኑ ምን

ማስረጃ አለ? ተማሪዎቹ ድንጋይ እንዳይወረወር፣ በዘርና በጐሳ ዜጐችን መከፋፈል እንዲቀር ብለው ያስቀመጡት ዓላማ የሽብርተኝነትን እንቅስቃሴ ያደርገዋል ወይ የሚል ጥያቄም ያስነሳል፡፡ በአንቀጽ 29 ጋር በተያያዘ ግን በፌስ ቡክ ሃሳብን ከሌሎች ጋር መለዋወጥ ሽብርተኛ ያሰኛል ወይ የሚለው ጥያቄ በአንክሮ መነሳት አለበት፡፡

እነዚህ 21 የዩኒቨርስቲ የኦሮሞ ተማሪዎች የዓለም አቀፍ የኦሮሞ ተማሪዎች ማህበር አባል በመሆናቸው ሽብርተኞች ተብለው ከተወነጀሉ ኢሕአዴግ ራሱ “የሶሻሊስት ኢንተርናሽናል” አባል አይደለም ወይ; በዚህም ከቻይና ኮሚንስት ፓርቲና ከተለያዩ ሶሻሊስት አገራት ጋር ባለው ግንኙነት መሠረት የሚያገኛቸው ጥቅማጥቅሞችና የሞራል ድጋፎች ምን ያህል እንደሆኑ የሚያውቀው ራሱ ነው፡፡

ሦስተኛው ምሳሌ በቅርቡ ኢህአዴግ ለVOA በላከው ባለ 42 ገጽ ጽሑፍ ውስጥ 34 ኢትዮጵያውያን በVOA ፕሮግራሞች እንዳይስተናገዱ መጠየቁ ነው፡፡ ይህም በአንቀጽ 29 ላይ የተከበሩትን መብቶች “ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነፃነት አለው፡፡ ይህ ነፃነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በህትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ የመቀበልና የማሰራጨት ነፃነቶችን ያካትታል” የሚለው የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ መጣሱን ያሳያል፡፡

ከዚህም በመነሳት አባላትና ዜጐች ከላይ የተጠቀሱትን የሕገ-መንግሥት ድንጋጌዎች በትክክል በማወቅ ሁኔታዎችን በመከታተል ሕገ-መንግሥቱን የማስከበርና ለሕገ-መንግሥቱ ተገዢ እንዲሆኑ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡

ሐሳብን በነፃነት መግለጽና ለመብት መሟገት በሽብርተኝነት አያስወነጅልም!

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ

Page 11: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

���0 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

���0 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

ሕግ ዜና

ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ምሁር ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ ቅዳሜ ሐምሌ 30 ቀን 2003 ዓ.ም ከአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ጋር የገዥውን ፓርቲ ልማታዊ መንግስትነት የተቃዋሚዎች ሚና ትኩረት ያደረገ ውይይት በስካይፒ አድርገዋል፡፡

ከዝግጅትቱ አስተባባሪዎች እንደሰማነው ከሆነ ይህን ዝግጅት ያቀናበረው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሲሆን ውይይቱ ከጠኋቱ 3 ሰዓት ላይ ተጀምሯል፡፡ ውይይቱ በስካይፒና በቴሌ ኮንፈረንስ አማካኝነት የተካሄደ ሲሆን ከ200 በላይ ታዳሚዎች በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ፕሮፌሰር መሳይ ያቀረቡት የመወያያ ንግግር አንድ ሰዓት የፈጀ ሲሆን በቀጥታ ለታዳሚዎች በህዝብ ግንኙነት አባላት አማካኝነት በቪዲዮ ቀርቧል፡፡

በገዥው ፓርቲ ላይ የሰላ ትችትና ሂስ በማቅረብ የሚታወቁት ፕሮፌሰር መሳይ በተለይም የገዥው ፓርቲ አካሄድና ባህሪ ያሉትን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ ካነሷቸው የመወያያ ነጥቦች መካከልም ልማታዊ መንግስት

ማለት ተቃዋሚዎችን በማጥፋት ብቸኛ ፈላጭ ቆራጭ ፓርቲ ለመመስረት የሚያስችል የነ አቶ መለስ ስልት ነው ያሉ ሲሆን እንደ አብነትም በ2002 ዓ.ም የተካሄደውን ምርጫ ጠቅሰዋል፡፡

ኢህአዴግ በ2002ዓ.ም የተካሄደውን ምርጫ የፖለቲካ ምህዳሩን በማጥበብና የይስሙላ ምርጫ በማካሄድ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ተወዳድሮ ማሸነፉን የማይቻል አድርጐታል፡፡ ይሄ የልማታዊ መንግስት ነን የሚሉ አምባገነኖች ፀባይ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡

በተለይም በ1997 ዓ.ም የተካሄደውን ምርጫ መለስ ነፃና ዴሞክራሲያዊ እናደርገዋለን ሲል ከልብ ስልጣን ለመልቀቅና ላሸንፈው ፓርቲ ለማስረከብ ተዘጋጅቶ ሳይሆን ተቃዋሚዎች ደካማ ናቸው ከሚል የተሳሳተ አመለካከት በመነሳት ነው፡፡ በተያያዥነትም ለምራባዊያን ዴሞክራሲ ያለ ለማስመሰል የተደረገ ስልት ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ገዥው ፓርቲ አሁንም ነፃና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት የለውም ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ልሂቃንም

ይሄንን ለመፍታት አስተዋፅኦ ማድረግ እንዳለባቸው ነው የገለፁት፡፡ የነ አቶ መለስ የውሸት ምርጫ ያልጣማቸውና እውነተኛ የስልጣን ሽግግር ለማድረግ የኢህአዴግ ባለስልጣናት አልተዘጋጁም ያሉ ቡድኖች ሌላ አማራጭ እንደወሰዱ ገልፀው የኢህአዴግ መንግስት እውነተኛ ዴሞክራሲን እስካልተገበረ ድረስ ህዝቦች መብታቸውን ለማስከበር የተለያዩ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይችላሉ ብለዋል፡፡

ፕሮፌሰር መሳይ አቶ መለስ ዜናዊን እንደ ቀደምቶች የኢትዮጵያን መሪዎች ብቸኛው አዋቂ ብቸኛው መሪ የመሆን ህልም ያላቸውና ከሌሎች ቀድመው ለመታየት የሚፈልጉ ናቸው ያሉ ሲሆን ከዚህ በፊት ጠ/ሚኒስትሩ ከዩኒቨርስቲ መምህራን ጋር ያደረጉትን ውይይት ባማስታወስ ልሂቅነታቸው ለማሳየት የጣሩበት መድረክ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ ሌሎችንም ዝርዝር ጉዳዮች ያነሱ ሲሆን ከተሳታፊዎችም በርካታ ጥያቄዎች ተነስተውላቸው መልስ ሰጥተዋል፡፡

ፕሮሬሰር መሳይ ከበደ ከአንድነት አባላት ደጋፊዎች ጋር ተወያዩ

“ስለ “ፀረ ሙስና ትግሉ ስንናገር ዜጐችን የፀረ-ሙስና ትግሉ አካል ማድረግ የትግሉ ዋነኛ ማጠንጠኛ መሆኑን ማስገንዘብ ያስፈልጋል” ሲሉ ኮሚሽነር አሊ ሱለይማን አስገንዘቡ፡፡ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙ ስና ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ አሊ ሱሌይማን ይህንን ያስታወቁት ሰሞኑን 1ኛው አገር አቀፍ የፀረ-ሙስና ጥምረት ጉባኤ እና 10ኛው የምስረታ በዓል በተከበረበት ዕለት ነው፡፡ ኮሚሽነሩ አያይዘውም “ ስለሆነም በፀረ -ሙስና ትግሉ ኀብረተሰቡን ከጎናችን

የማሰለፉን ጥረት ይበልጥ አጠናክረን የምንቀጥልብት ይሆናል፡፡” በማለት ንግግር አድርገዋል፡፡

አገር አቀፍ የፀረ-ሙስና ጥምረት 1ኛ ጉባኤም በፀረ-ሙስና ትግሉ የኀብረተሰቡን ተሳትፎ በማረጋገጥ መልካም አስተዳደርን የመገንባት እንዲሁም የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን ከዳር የማድረስ አጀንዳ ይዞ የተዘጋጀ በመሆኑ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ነው፡፡” ሲሉ አብራርተዋል፡፡ በሒልተን ሆቴል በተደረገው ስብሰባ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ

ገመዳ ናቸው፡፡ አቶ አባዱላ እናዳሉት “አገር አቀፉ የፀረ-ሙስና ጥምረት ባለፉት ሁለት ዓመታት ያከናወናቸው ተግባራት በመልካም ሁኔታ የሚታዩ ቢሆኑም፣ መላውን ኀብረተሰብ በፀረ-ሙስና ትግሉ ይበልጥ በማሳተፍ፣ ለእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስኬታማነት የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ከምንጊዜውም በላይ መሥራት ይጠበቅበታል፡፡ የተለያዩ አካላት እና አደረጃጀቶች ጥምረቱን እንዲቀላቀሉም ሆነ የጥምረቱ አባላትም ይበልጥ ተጠናክረው የፀረ-ሙስና ትግሉ ማዕከል እንዲሆኑ ጠንክሮ መሥራት አስፈላጊ ነው፡፡” በማለት መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

ዜጐችን የፀረ ሙስና ትግሉ አካል እንዲሆኑ ተጠየቀ

ኢህአዲግ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ቦንብ እየቀበረ ከመሄድ መቆጠብ ይገባዋል ሲሉ

የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ አመራሮች ማሳሰቢያ ሰጡ፡፡ የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ የፓርቲው ዋና ፀሐፊ መ/ር ሰለሞን ግዛው የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ ትግስት ከበደ የፓርቲው የጥናትና ምርምር ኃላፊ መ/ርት መሠረት ዘማሪያን በጋራ በመሆን በኢንተር ኮንትኔታል ሆቴል በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ “ኢህአዴግ ለህዝብ ክብር ሊሰጥ ይገባል፡፡ ህዝብን ማድመጥ አለበት” በማለት ካሳሰቡ በኃላ “የአገራችን

የኢኮኖሚ ፖሊሲ የታመመ ነው፡፡ በአስቸኳይ መፍትሔ ያስፈልገዋል” ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ “በቅንንነት ተወያይቶና ተደማምጦ መፍትሔ መፈለግ ይጠበቅብናል” ብለዋል፡

“ኢራፓ በማንም ሳንባ የሚተነፍስ አይደለም” ያሉት የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ ተሻለ ሠብሮ “በአገራችነ ላይ ያንዣበበውን የድርቅ አደጋ ፓርቲያችን ያለበት የትብብር ፎረም ተወካዮች በቦረና ተገኝተው የተመለከቱት ሲሆን የመጀመሪያ መግለጫም እያወጣን ነን” ሲሉ ገልጸው ዜጐቻችንን ለመታደግ መላው ዜጋና ዓለም አቀፍ ህብረተሰብ እንዲረባረብ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ ዲያስፖራው ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ

የፖለቲካ መስመር ላይ ያዘነብላል፡፡ አልፎ አልፎም በጐሳ የመደራጀት ሁኔታ አለ፡፡ ይህ ደግሞ ያሳስበናል፡፡ ዲያስፖራውን ማደራጀት እንፈልጋለን፡፡ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተቀናጅተውና ተባብረው መታገል ይጠበቅብናል፡፡” በማለት ሰፊ ማብራሪየ ሰጥተዋል፡፡ የፓርቲው አመራሮች አንጽንኦት በመስጠት የተናገሩት “ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ለሚመራው ህዝብ አክብሮት ሊኖረው ይገባል፡፡ የህዝብን ብሶትና ችግር መረዳት ይጠበቅበታል፡፡ የህዝብን ሐሳብና ፍላጐት መጠበቅ አለበት፡፡ ጊዜውን ጠብቆ ለፈነዳ የሚችል ቦንብ እየቀበረ ከመጓዝ ሊቆጠብ ይገባል” በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

“ኢህአዴግ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ቦንብ ከመቅረብ ሊቆጠብ ይገባል፡፡”

የኢራፓ አመራሮች

“በሽብርተኝነት ተጠርጥራ” በፌደራል ወንጀል ምርመራ በእስር ላይ የምትገኘው ጋዜጠኛና መምህርት ርዮት ዓለሙ “በህመም ላይ እንደምትገኝ” ወላጅ አባቷ አቶ ዓለሙ ጐቢቦ ለፍኞተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገለጹ፡፡ አቶ ዓለሙ እንዳሉት ርዮት በህመም ላይ የምትገኝ

ሲሆን መድኃኒት ገዝተን አስብተንላታል፡፡ ሰውነቷ በህመም መጐሳቀሉንና ሐሳቧም በእጅጉ ከመበታተኑም በላይ ከዚህ በፊት ያልነበረባት የመዘንጋት ባህርዬ የተፈጠረባት በመሆኑ ጤንነቷ አሳስቦናል በማለት ገልፀዋል፡፡

ርዮተ ዓለሙ በቋንቋ መምህርነትና በትያትርና ሥነ ጥበብ ሁለት የመጀመሪያ

ዲግሪዎች ያላት ሲሆን በ2004 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኢትዮጵያ ሰተዲ ሁለተኛ ዲግሪዋን /ማስተርስ/ ለመማር ተመዝግባ እንደነበር ከቤተሰቦቿ መረዳት ተችሏል፡፡ ርዮት ዓለሙ እናቷንና እህቷን የምታስተዳድር ሲሆን በመታሰሯ ምክንያት ደሞዟ መቋረጡን ከቤተሰቦቿ መረዳት ተችሏል፡፡

ርዮት ዓለሙ በህመም ላይ እንደምትገኝ ተገለፀ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ ከትላንት በስቲያ ከጥዋቱ 3 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት ድረስ ባከናወነው የማዕከላዊ ም/ቤት ስብሰባ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መስጠቱን ከፓርቲው አመራሮች ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ ”የተደረገው ስብሰባ ሳይሆን ተራ የውንብድና ሥራ” ሲሉ አቶ ያሬድ ግርማ ስብሰባውን አጣጥለውታል፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር እንደገለፁት “ስብሰባው እንዳይከናወን ከፓርቲው በዲስፒሊን የታገዱ አባሎች ረብሻ ለመፍጠር የሞከሩ ሲሆን የፓርቲውን ፕሬዝደንት ኢ/ር ኃይሉ ሻውል መኪና የኋላ ፍሬቻ ሰብረዋል፡፡ ሆኖም ግን ረብሻው በፖሊሶች በቁጥጥር ሥር በመዋሉ ስብሰባውን በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ማከናወን ችለናል” በማለት አስረድተዋል፡፡

በማያያዝም አመራሩ ሲያብራሩ “ም/ቤቱ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ከፓርቲው በዲስፕሊን የታገዱ 11 አመራር አባላትና 3 በማስጠንቀቂያ የነበሩ በጠቅላላ 14 ሰዎች ከፓርቲው እንዲባረሩ ተወስኗል፡፡ በተሰጠውም ድምጽ 8ዐ ለ2 በሆነ የድምፅ ብልጫ ፀድቋል” ብለዋል፡፡ ተቃውሞ ያቀረቡት ሁለቱ የም/ቤቱ አባላት ከየት የተወከሉ ናቸው? በማለት ዝግጅት ክፍላችን ጥያቄ ያቀረበንላቸው አመራሩ ሲመልሱ “የደብረብርሃን አና የአጣዩ ዞን ተጠሪዎች ናቸው” በማለት መልሰዋል፡፡ በመቀጠልም ሲገልጹ “ከዚህ በፊት ከአንድነት ጋር ሊደረግ የታሰበው ድርድር መቋረጡን ተገቢ መሆኑን ም/ቤቱ ተቀብሎ አጽድቆታል ፡፡ ከአንድነት ፓርቲ ጋር ውህደቱ እንዲቋረጥ የተወሰነው አንድነት ከመድረክ ካልወጣ አስቸጋሪ በመሆኑ ነው፡፡ መድረክ ውስጥ ያሉት የብሔር ድርጅቶች ከፓርቲያችን ፕሮግራም ጋር ሊጣጣሙ ስለማይችሉ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ ምን ጊዜም ቢሆን ከአንድነት ጋር ተዋህደን ለመታገል እንፈልጋለን” በማለት ገልፀዋል፡፡ “ማዕከላዊ ም/ቤቱ ባለፈው ጠቅላላ ጉባኤ ተቀዳሚ ም/

ፕሬዝደንት ተደርገው ተመርጠው የነበሩት አቶ ያዕቆብ ልኬ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ባለመወጣታቸው፣በችኩልነት ተደጋጋሚ ስህተት በመፈጸማቸው የፕሬዝደንቱን ሥልጣን በመጋፋታቸው፣ከሥራ አስፈጻሚ አባላት ጋር ተስማምተው መሥራት ባለመቻላቸው፣ከተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንትና ከሥራ አስፈፃማነት እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ አዲስ አመራሮችንም ተሰይመዋል፡፡ በዚሁ መሠረት አቶ፣ወንድምአገኝ ደነቀው ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት፣አቶ አሰፋ ሀ/ወልድ ም/ፕሬዝደንት አቶ ተስፋዬ ታሪኩ በነበሩበት ዋና ፀሐፊ፣ ወ/ት መሶበ ቅጣው ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ ዶ/ር በዛብህ ደምሴ የውጪ ጉዳይ ኃላፊ፣አቶ አዳሙ ተስፋ የአስተዳደርና ፋይናንስ ክፍል ኃላፊ ፣አቶ ጌታቸው ባያፈርስ ትምህርትና ሥልጠና ኃላፊ” ተዳርገው መመደባቸውን አስረድተዋል፡፡ በመጨረሻም አመራሩ ሲገልጹ “ከ1ዐ5 የም/ቤቱ አባላት መካከል 82 አባላት የተገኙ ሲሆን ከ82 ውስጥ 6ቱ በዲስፒሊንና በልዩ ልዩ ምክንያት ከዞን ሰብሳቢነት በተለያየ ምክንያት የተቀየሩ ናቸው፡፡ቀሪዎቹ ነባር የም/ቤቱ አባላት ናቸው፡፡በማለት አብራርተዋል፡፡

በዚሁ ጉዳይ ላይ አስተያየት የሰጡት አቶ ያሬድ ግርማ ስብሰባውን “ተራ የማጭበርበርና የውንብድና ሥራ ነው” ሲሉ ስብሰባውን አጣጥለውታል፡፡ አቶ ያሬድ እንደሚሉት “እኔ ለምሳሌ የማዕከላዊ ም/ቤቱ አባልና የሰሜን ጐንደር መኢአድ ም/ቤት ሰብሳቢ ነኝ፡፡ የስብሰባ ጥሪው አልደረሰኝም፡፡ የም/ቤቱ አባላት ያልሆኑትን አና የእነሱ የግል አሽከር የሆኑትን ብቻ መርጠው በመጥራት በም/ቤቱ ስም ስብሰባ አደረግን ብሎ ማውራት ተራ ውንብድና ነው፡፡ ይህ ፓርቲ ከፍተኛ የሕይወት፣የአካልና የቁስ መስዋዕትነት የተከፈለበት ድርጅት ነው፡፡ ማንም እየተነሳ በማን አለብኝነት የፈለገውን ውሳኔ የሚሰጥበትና አመራሮቹንና አባሎቹን የሚያግድበት የሚያባርርበት መብትም

- አዲስ አመራሮችን ሰየመ

- 14 አመራሮችንና አባሎችን አባረረ

- አቶ ያዕቆብ ልኬን ከሥራ አስፈፃሚና ተ/ም/ፕ አሰናበተ

- የእ/ር ኃይሉ ሻውል መኪና በድንጋይ ተሰበረ፡፡

የመኢአድ ማዕከላዊ ም/ቤት ከአንድነት ፓርቲ ጋር ውህደቱ

እንዲቋረጥ ወሰነበብዙአየሁ ወንድሙ

ወደ ገፅ 13 ዞሯል

Page 12: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

���� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

���� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

ነፃ አስተያየት

እንዳንበላ የተከለከልን ዜጐች ነን፡፡ እኔና ቤተሰቤ ያለ ምንም ተለዋጭ ቤት በከተማውም ይሁን በሌላ ምንም እርስት የለንም፡፡ በአሜሪካን ሀገር የምትኖር እህታችን ከ5 ቤተሠቦቿ ጋር በኢትዮጵያ ሥንዝር መሬት የሌላት፡፡ እዚህ ያለነው ከ8 በላይ የሆንን ከ75 ዓመት አዛውንት እናታችን ጋ የምንኖር የኮንዶሚኒየም

ቤት እንኳን ሳይሰጠን ይዞታችን ላይ መብት እንዳይኖረን እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንድንኖር የተከለከልንበት ምክንያት ግልፅ ሊሆንልን አልቻለም፡፡ በቀሪ ይዞታችን ላይ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንዳንኖርና እንዳናለማ የተከለከልንበት ምክንያት ሊገለፅልን ይገባ ነበር፡፡ መንግሥት ለዜጎች የሰጠው እድል ለምን

ተነፈገን? ቀሪ ይዞታችን ላይ እንዳናለማና መንግሥት በሚጠብቀው አቅጣጫ አስፈላጊውን ግንባታ እንዳናደርግ እድሉን ለምን ተነፈግን? በዚህም ምክንያት ነው እኔ ማን ነኝ? ዜግነቴስ ምንድንነው?የሚል ጥያቄ እንዳነሳ የተገደድኩል፡፡ እኔ ለሃያ ዓመታት በወንጌል አገልግሎትና በሕክምና ሞያዬ ሣገለግል የቆሁ

ሲሆን የወንጌል አገልጋይ መሆን በአካባቢዬ እታወቃለሁ፡፡ እስከ ዛሬ የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል አይደለሁም፡፡ በሃገሬ ላይ መብቴን በመጠየቄ በፖለቲካ ድርጅት አባልነት ፈርጆ ፍትሕን ማዛባት ኢ-ሕገመንግሥታዊ ነው፡፡ መብቴን ለማስከበር እስከ መጨረሻው ድረስ እገፋበታለሁ፡፡

“ዝንጀሮ የጓደኛዋ ጠባሳ እንጂ የራሷ አይታያትም”

ከአቶ ሙሉጌታ በሪሁን ዓሊ

ዓርብ ዓርብ በሳምንት አንድ ቀን የምትወጣው የፍትሕ ጋዜጣ ደንበኛ ነኝ፡፡ አንድም ቀን አምልጣኝ አታውቅም፡፡ በዚህ አጋጣሚ እየተሻሻለች በመምጣቷ አዘጋጆቿን ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ በርቱ ተበራቱ አላለሁ፡፡

ላስተላልፍ ወደ ተነሣሁበት መልእክት ከመግባቴ በፊት አሁንም ትንሽ ስለ ፍትሕ ማለት እፈልጋለሁ፡፡

“ፍትሕ” የሚለው ቃል የኢትዮጵያ ሕዝብ የደም ሥር፣የልብ ራስ ሆኖ ለረጅም ዘመናት ኖሯል፡፡ ዳሩ ግን ፍትሕን ናፋቂ እንጂ ፍትሕን አግኝቶ አያውቅም፡፡ ይልቁንም በፈትሕ ስም አምባገነን መሪዎች በየዘመናቸው እጅግ የሚዘገንኑ ግፎችን ፈፅመውበት አልፈዋል፡፡ የዛሬዎቹም ዘመነኛ መሪዎች በፍትሕ ስም እየፈነጩበት ይገኛሉ፡፡ እንግዲህ የፈትሕ ስያሜ ይንን ለመዘከርና አቅሟ በሚችለው ሁሉ ደግሞ በጊዜው እየተፈፀመ ያለውን ግፍ በማጋለጥ የፍትሕ ገፈፋውን ለማሣየት መሆኑን በተግባር እያስመሰከረች ነው፡፡ የዚህን እውነታ ምሳሌ እየነቀሱ ማሣየት ይቻላል፡፡

የፍትሕ እጦት በየዘርፉ ነውና ሌላውን ሁሉ ትተን መሠረታዊ አገልግሎት ሰጭዎችን (ውሃ፣መብራትና ስልክ) ለሥልጣናት አልፎ አልፎ በቴሌቪዥን መሥኮት ብቅ ይሉና ከመብራቱ መጥፋት የበለጠ የሕዝቡን ሕሊና ያቆስላሉ፡፡

የተከዜ ግድብ ሲጠናቀቅ የመብራት አገልግሎት ይሟላል ተብለን ነበር፡፡ ከኛም አልፎ ለሱዳን፣ ለኬንያና ለጂቡቲ

እናከራያለን፡፡ በማለት በተስፋ ሰማይ ምድሩን በመብራት ያንቆጠቁጡታል፡፡ ጠ/ሚንስትሩም የተከዜን የኃይል

ማመንጫ ሲመርቁ በቴሌቪዥን አይተን ነበር፡፡ ግን ምንም፡፡ “ሺ ቢታለብ በገሌ” እንዳለችው ድመት ፕሮፓጋንዳው አንፑል ሊሆን አልቻለም፡፡ ግቤ አንድ ግቤ ሁለትና ግቤ ሦስት ግድቦች እየተባልን ቢለፈፍልንም የጨለማ ሕይወት ከመግፋት አልዳንም፡፡ በሻማ ወራ ወርት ይህን ዘመን እየገፋን እንገኛለን፡፡

ሙስና የኑሮ ውድነትና የማኀበራዊ ሕይወት መዛበትና እየከፋ መምጣት በዚች መጣጥፍ መጥቀሱ እንደመቀለድ ይቆጠራል፡፡ ምንልባትም ራሱን አስችዬ …. በሌላ ጊዜ እመለስበት ይሆናል፡፡

እንግዲህ ስለ ፍትሕ ስያሜና ምንነት ለመንደርደሪያ ይህን ያህል ካልኩኝ ወደ ተነሳሁበት ልመለስ፡፡

ፍትህ ሰኔ 17 ቀን 2003 ዓ.ም በዘገበችው እትሟ “አብዬ ስብሀት” በሚል ርእስ አንድ መልእክት አስተላልፋ ነበር፡፡ በዚህ ጽሑፍ አብዬ ስብሀት የተውገረገሩ መልሶችን በመስጠት እንዲብራሩላቸውና በቂ መልሶች እንዲሰጧቸውም ዋና አዘጋጁን አቶ ተመስገን ደሳለኝን ጠይቀዋል፡፡

ካቀረቧቸው ጥያቄዎች አንዱና ዋናው ጡረታ አለመውጣታቸውን እንደማያውቁና ያልወጡ መሆናቸውን ነው፡፡ እንግዲህ ጡረታ አልወጣሁም ካሉ ከባለቤቱ የበለጠ ምስክር የለምና የሳቸውን አባባል እውነት ነው ብሎ መቀበል የግድ ነው፡፡ በዚህ በኩል የሞራል ካሣ ያስፈልጋቸው እንደሆነም ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ያስቡበት፡፡

በመሠረቱ ያቦይ ስብሀት ጡረታ መውጣት አለመውጣት ትልቅ ጉዳይ ሆኖ ሊያነጋግረን የሚገባ አጀንዳ አልነበረም፡፡ እንደ ሥርዓቱ ሽፍጠኛነትና አሸማቂነት ግን ብዙ ልንል የሚገቡን ነገሮች አሉ፡፡

በወያኔ ሥርዓት በፊት በር በጡረታ አስወጥቶ በኃላ በር ወይንም በመስኮት በማስገባት መሾም አዲስ ነገር አይደለም፡፡ የብአዴን ሊቀመንበርና የሀገሪቷ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ሐዲሱ ለገሠ የመሥራት አቅማቸው እየተዳከሙ በመምጣታቸው ጡረታ መውጣታቸውን በቴሌቪዥን ከራሳቸው አንደበት መሥማታችን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ሦስት ቀናት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው መሾማቸውን ሰማን፡፡ ሌሎች ጡረታ ወጥተዋል የተባሉም ያንባሳደርነት ሹመት እየተቀበሉ መሹለካቸውን በጨረፍታም ቢሆን ሕዝብ ሰምቶታል፡፡ ስለዚህ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ አቦይ ስብሀት ጡረታ አልወጣሁም ቢሉም አይገረመዎ፡፡

ሌላው ያቶ ስብሀት ሐሳብ ስለ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት መዳከም የሰጡት መልስ ነው፡፡

በመሠረቱ የሕውሓት ባለሥልጣናት የማንኛውም እምነት ተከታይ አለመሆናቸውን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለመግለጽ ሞክረዋል፡፡ ለምሳሌ ባንድ ወቅት ክቡር ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ

የየትኛው እምነት ወይንም ሃይማኖት ተከታይ እንደሆኑ ተጠይቀው የሰጡት መልስ የማንኛውም እምነት ተከታ አለመሆናቸውን ገልጸው ወላጆቻቸው ግን አክራሪ የኦርቶዳክስ ሃይማኖት ተከታይ መሆናቸውን ገልጸው ነበር፡፡ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት መዳከም አቦይ ስብሀት በቀጥታም ሆነ በተዘዋሪ መንገድ እንዴት ከደሙ ንፁሕ ነን ሊሉ ይችላሉ; አቦይ ስብሀት ነጋ አቡነ መርቆሪዎስ ምንም ጫና ሳይደረግባቸው ነው አገር ጥለው የኮበለሉት ይሉናል፡፡ አያይዘውም ያቡኑን መኮብለል ካፄ ኃይሌ ሥላሴ መኮብለል ጋር ተመሳሳይ እንደሆነም ነግረውናል፡፡

በመሠረቱ እኔ ያፄ ኃይለ ሥላሴ ተሿሚ ወይንም ተሸላሚ አለመሆኔን በቅድሚያ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ሀቁን ለመናገር ግን ሕሊናየ ያስገይደኛል፡፡ በመሆኑም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በሥልጣን ተቀናቃኞቻቸው በኩል ከሚወቀሱበት በስተቀር እውነቱን መርምሮ ለሚረዳ ዜጋ ኮብላይ አይደሉም፡፡ ሕዝባቸውን የጦር መሣሪያ ተመጣጣኝ ባልሆነ ፋሽሽት ከማስጨርስ የዓለምን ሕዝብ ፍርድ ለማግኘት ሲሉ በጂቡቲ በኩል አድርገው ወደ እንግሊዝ ማቅናታቸውና ከዚያም ወደ ጀኔቭ መሄዳቸው እውነት ነው፡፡ ይህንንም ሲያደርጉ ከመኳንቶቻቸው ጋር መክረው እንደነበር ብዙ ማስረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ግርማዊነታቸው ወደ ጀኔቭ ሄደው ለመንግሥታቱ ማህበር አቤቱታ ማቅረባቸው መኮብላል ከሆነ አቦይ ስብሀትን ጨምሮ የህወሓት አባላት በከፊልም ሆነ በሙሉ ከደርግ ቀይ ሽብር እልቂት አምልጣችሁ ወደ ሱዳን መሠደዳችሁና ወደ በረሃ መግባታችሁ መኮብለል ነበር; የናንተ ሲሆን አርበኝነትና ጀግንነት የሌሎች ሲሆን ፍርሃትና ስደት እንዴት ሊሆን ይችላል; እሳቸውም ካምስት ዓመት የፖለቲካ ትግል በኋላ የእንግሊዝን መንግሥት ወታደሮች ረዳት ይዘው በመምጣት ካርበኞቻችን ጋር በመሆን ፋሽሽቱን ኢጣሊያ ድል አድረገው ወደ ዙፋናቸው ተመልሰዋል፡፡ እናንተም 17 ዓመት ታግላችሁ ደርግን በማሸነፍ ሥልጣን ይዛችኋል፡፡ ሀቁ ይኸ ነው፡፡ ዳሩ ግን “ዝንጀሮ የጓደኛዋ ጠባሳ እንጂ የራሷ አይታያትም” እንዲሉ እናንተም የሌሎችን ስንጥር ፍለጋ እንጂ ያናንተ ፍልጥ የሚያክል ስህተት አይታያችሁም፡፡

አቡነ መርቆርዎስም አገር ጥለው የተሰደዱት የሳቸውን ሕይወት ለማዳን ሣይሆን በወንድማማችነት ተፈቃቅሮና ተከባብሮ የኖረው ሕዝብ በናንተ ዘመን በዘሩ ብቻ ተነጥሎ አማራ እንደ ዱር አውሬ እየታደነ ሲገድል በማየታቸው ይህንኑ ሰቆቃ ለዓለም ሕዝብ ለማሳወቅና ለማጋለጥ ሲሉ ሃይማኖታዊ ግዴታ ሰላለባቸው አገር ጥለው መሰደዳቸው እውነት ነው፡፡ ይህንንም ሀቅ እናንተው “ኦነግ የፈጃቸው” እያላችሁ ታርደው ከተጣሉበት ገደል እያወጣችሁ አፅማቸውን በቴሌቪዥን አላሳያችሁንም; አቶ ስብሀት ይህንን ይክዳሉ; በርግጥ “የኦርቶዶክስ ሃይማኖት መዳከም”

ያሉትን እኔም እጋራዎታለሁ፡፡ መዳከም ብቻ ሣትሆን ዛሬ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ማፈሪያም እየሆነች ነው፡፡ ይህስ በማን ዘመን ነው አቦይ ስብሀት;

የኦርቶዶክስ ሃይማኖት “በወዛችሁ በላባችሁ፣ በድካማችሁ ኑሩ” አለች እንጂ በሙስና በልጽጉ አላለችም፡፡ ዛሬ እንደነ ወ/ሮ እጅጋየሁ ያሉ ቀልጠጤ ወይዘሮ ደቁነው ወይንስ ቀስሰው? ወይንስ ጰጵሰው በቤተክርስቲያን የሚፈነጩባት; አንድ ጳጳስ በሕይወት እያለ ቦሌ መድህኒዓለም ሐውልት ያሠራው ማነው; ይህ የሆነውስ በማን ዘመን ነው; ወይዘሮዋስ የሐውልት ገጸበረከት ለማበርከት ያነሳሳቸው ከብፁዑ አባታችን ምን የከበረ ውለታ ቢውሉላት ነው; ይህስ የከፋ ሙስና አይደለም; እንግዲህ ይኸ ሁሉ ተደምሮ ነው የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የተዳከመችው፡፡ በኮሚኒስት ደርግ ዘመን እንኳን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት እንደ ዛሬው ማፈሪያ አልነበረችም፡፡ ዛሬ ግን ባንድ ብሔረሰብ ልጆች አስተዳደር ታንቃ እየተንፈራገጠች ትገኛለች፡፡ አቶ ስብሀት ልክ እንደሌሎች ቅጥፈቶች ሁሉ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አልተዳከመችም፣ አልሞተችም ሣይሉ ሀቁን በማስቀመጠዎ ሳላመስግነዎ አላልፍም፡፡ ዛሬ አባታችን አባ ጳውሎስ በሚያስተዳድሯት ቤተ ክርስቲያን አድሏዊነት የተነሳ ዲያቆናቱና ቀሳውስቱ በሚደርስባቸው በደል አገር ጥለው ወደ አሜሪካና ጀርመን እንዲሁም ወደ እንግሊዝና ጣሊያን በመሰደድ የከፋ ሕይወት እየገፉ ይገኛሉ፡፡ ይህ በመሆኑም በገጠር ያሉ ቤተ ክርስቲያናት ቀዳሽና አወዳሽ ማጣታቸው ብቻ ሣይሆን ማስቀደሻ ዘቢብ እጣንና ጧፍ አጥተው እየተዘጉ መሆናቸው ይነገራል፡፡ ብፁዕባታችን ግን ምድራዊ ሕይወት ጣፍጣቸው ከላይ እስከታች ነጭ በነጭ አጊጠው በብዙ መቶ ሺ ብሮች በተገዙ ጃፓን ሠራሽ መኪናዎችን እያሽከረከሩ አልተንደላቀቁም ብሎ መከራከር ክህደት ነው የሚሆነው፡፡

በዚህ ላይ የእግዚአብሔር ቃል ሸቀጥ ሆኖ በሲዲና በካሴት እየተቀረፀ በየሜዳው እየተቸበቸበ አስመሳዮች ሲበለጽጉበት ማየት ሃይማኖቱ እየተገዘገዘና እየተዳከመ ለመሆኑ ከበቂ በላይ ማረጋገጫ ነው፡፡ ግን ምን ይደረግ; የእግዚአብሔርን ፍርድ ከመጠበቅ ሌላ የእምነቱ ተከታዮች ሃይማኖትቸውን ያማስጠብቅና የማስከበር አቅም አጥተዋል፡፡ በመጨረሻም የማነሣው ነጥብ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ግርማዊት እቴጌ መነን አስፋውን አስመልክተው የዘገቡት የተዛባ ነው፡፡ ካንድ ፈረንሳይ ጋዜጠኛ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ የሰጡት የሐኪም ወርቅነህ ባለቤት ወይዘሮ ቀፀላ በላቸው እንጂ እቴጌ መነን አይደሉም፡፡ በዚያን ወቅትም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን አላገቡም፡፡ ስለዚህ ተሳስታችሁ ሌሎችን ከማሳሳት መቆጠብ ተገቢ ነው፡፡ በተረፈ በሌላ መጣጥፍ እስከምንገናኝ ላገራችን ህዝቦች መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ፡፡

ኢትዮጵያ ባንድነቷ ፀንታ ትኖራለች፡፡

በመሠረቱ የሕውሓት ባለሥልጣናት የማንኛውም እምነት ተከታይ

አለመሆናቸውን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለመግለጽ ሞክረዋል፡፡ ለምሳሌ ባንድ

ወቅት ክቡር ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ የየትኛው እምነት ወይንም ሃይማኖት ተከታይ እንደሆኑ ተጠይቀው የሰጡት

መልስ የማንኛውም እምነት ተከታ አለመሆናቸውን ገልጸው ወላጆቻቸው ግን አክራሪ የኦርቶዳክስ ሃይማኖት ተከታይ መሆናቸውን ገልጸው ነበር፡፡ በኦርቶዶክስ

ሃይማኖት መዳከም አቦይ ስብሀት በቀጥታም ሆነ በተዘዋሪ መንገድ እንዴት

ከደሙ ንፁሕ ነን ሊሉ ይችላሉ; አቦይ ስብሀት ነጋ አቡነ መርቆሪዎስ ምንም ጫና ሳይደረግባቸው ነው አገር ጥለው የኮበለሉት ይሉናል፡፡ አያይዘውም ያቡኑን መኮብለል

ካፄ ኃይሌ ሥላሴ መኮብለል ጋር ተመሳሳይ እንደሆነም ነግረውናል፡፡

እርማት አውጡልኝ... ከ ገፅ 4 የዞረ

Page 13: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

���� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

���� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

ዜና

የቀድሞ የኢህዲሪ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያም ደቡብ ሱዳን ነፃነቷን ተቀዳጅታ 54 የአፍሪካ ሀገር ኅብረት አባል ሆናለች፡፡ በነፃነት ትግሉ ወቅት በእርስዎ የአመራር ዘመን የኢትዮጵያ አስተዋጽአዎች ምን ነበሩ? በግል እንደወቅቱ መሪነትዎ እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ህዝብ ለትግሉ ስኬት ያደረገው አስተዋጽኦ በታሪክ ምን ሥፍራ ይኖረዋል? ደቡብ ሱዳን በአሁ ወቅት ነፃ አገር በመሆኗ ምን ይሰማዎታል?

ወደ ዋናው ጉዳይ ከመግባቴ በፊት እኔ በአጠቃላይ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ እንደ አንተና አንተን የመሰሉ ኢትዮጵያኖች በተለያዩ ጊዜ በተለያየ አጋጣሚ በተለያየ ርዕስ ላይ ሊያነጋግሩኝ ፈልገዋል፡፡ እንደዚህ ያሉትን ጥያቄዎች ለማስተናገድ ፍላጐት የለኝም፡፡ በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ህዝብ አብዮት ታሪክ የሚመለከት ያዘጋጀሁት መጽሐፍ ከአንድ ወር በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ ወጥቶ ለብዙዎቹ ምናልባት መልስ ይሰጣል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በተከታታይ እስከ ክፍል ሦስት ድረስ ይወጣል፡፡ ከዚህ አኳያ ነው ኢትዮጵያውያን ወንድሞቼን እህቶቼን እኔ የነበርኩበትን ሁኔታ ልመልስ እችላለሁ፡፡ ከዚህ በተረፈ ጋዜጠኞችና አንዳንድ ሰዎችን ላላስተናግድ እችላለሁ፡፡ ለዚህ የበቃንበት ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ በእኔና ከእኔ ጋር በነበሩ ጓዶቼ ከእነሱ ጐን የቆምነው በእውነቱ ከደቡብ ሱዳን ህዝብ ታሪክ ብሶትና አረቦች ከሚያደርሱባቸው ባርነትና ረገጣ አኳያ እጅግ የሚያሳዝን ህይወት የሚገፉ ስለነበሩ ከንፁህ አፍሪካዊ ስሜት ነው፡፡ ከንፁህ ስብአዊ ስሜት ነው፡፡

ያንን ያህል ድጋፍ አገሪቱ ካለችበት ችግር ላይ እያለች የራሷ ጦርነት እያከናወነች ባለችበት ወቅት 80ሺ ጠንካራ ጐሬላ ልናስለጥንላት የቻልነው፡፡ አገሩ ሰፊ ከመሆኑም በላይ መላው የአረብ መንግስታት በእነዚያ ጭቁን ድሀዎች ላይ ይረባረቡባቸው ከነበረው ጭቆና አኳያ ለመመከት ባልተፈለገ ምክንያት ነው፡፡ ሰው ገብረንላቸዋል፡፡ አስልጥነንላቸዋል፡፡ አስታጥቀናቸዋል፡፡ የጦር አመራርና ጠቅላላ የትጥቅና የምክር እስትራቴጂ ረድተናቸዋል፡፡ በአገሩ በሙሉ ተዋጊዎች ብቻ ሳይሆኑ ስደተኛ ህዝብ ከ10-15 ዓመት በላይ ሙሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የተጠለለው፡፡ ስደተኛ እንመግባለን፡፡ ዓለም አቀፍ እርዳታ እየለመንን እናስቀርብላቸዋለን፡፡ ሠራዊቱን እንመግባለን፡፡ ለሠራዊቱ የሚያስፈልገውን ቁሳቁስ እናቀርባለን፡፡ በዚህ ውጤትና በእነሱ ቁርጠኛ ታጋይነት የተነሳ በብዙ ጥረትና ላብና ደም መስዋዕት ዛሬ ነፃ መውጣት ችለዋል፡፡ ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ቢባል ከሁሉ በፊት ያ የተበደለና የተጨቆነ አፍሪካዊ ህዝብ ነፃ መሆኑ ማንኛውንም ሰው የሆነውን ሁሉ ሊያስደስት ይገባል፡፡ እኔም የህዝብን ስሜት ነው የምጋራው፡፡ ሌላ ደግሞ የሰሜኑ ሱዳን መንግስት በአገራችን የሰሜኑን ክፍል ከመነሻው አረቦችን እያስተባበረ ሲያደማን፣ሲያስወጋን ብሎም ዛሬ ኢትዮጵያ የደረሰችበትን ደረጃ ዋናውን አስተዋጽኦ ያደረገ ኢትዮጵያን ያስገነጠለ መንግስት ስለሆነ እኛ 3ሺ 4ሺ ካሬ ሜትር ኤሪያ ከአንድ 3ሚሊዮን የሚደርስ ህዝብ ወገኖቻችን ህዝብ

ተነጥለናል፡፡ እንዲሁም ወደባችንን ባጠቃላይ የዚህ አገር ህዝብ መነጠል የሚያሳዝን ነው፡፡ እና ደግሞ የማይረሳ አጥንት የሚሰብር ቁስል ቢሆንም ቅሉ ከሱዳን ጉዳት ጋር የታየ እንደሆነ ኢትዮጵያን የሚያህል ሀገር ነው፡፡ ዛሬ ሱዳኖች ያጡት ይኸው ለም ዐፈር፣ወርቅ፣ነዳጅ፣ ያካበቱ ሀብት ነው፡፡ ያለ ደቡብ ሲዳን ሱዳን ምን እንደሚመስልና ምን ዓይነት ክፍለ ሃገር እንደሚሆን መገምገም የሚቻል ይመስለኛል፡፡ የቀረው በረሃው ነው፡፡ የቀራው አሸዋው ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፤ደግሞ በምዕራብ ------ ሌላ ትግል ይጠብቃቸዋል፡፡ ምናልባትም ደቡቡን ሊቀላቀሉ ይችላሉ እና ሱዳኖች እየለመናቸው አንድ ወንዝ ኩታ ገጠም ድንበርተኞች ነን፤አንድ ዓይነት ቋንቋና ባህል ያላቸው ህዝቦች በድንበር እንወራለን አገሮች በከፋ መልኩ ብቻ ሳይሆን የተለዋወጧቸው በበጐ ጐኑ የሚነሱ መልካም መልካም ነገሮች አሉ፡፡ ኢትዮጵያኖች በፋሽሽት ወረራ ጊዜ ብዙዎቹ ሱዳን አገር ኖረዋል፡፡ ይህንን እና እንደ ትልቅ ውለታ እንቆጥረዋለን፡፡ እንዲህ ዓይነት ደግ ደጉን ነገር ከማራመድ ይልቅ በአገራችን ጉዳይ ገብታችሁ ይህንን መስራታችሁ አግባብ አይደለንም፡፡ እኛም ከፈለግን በእናንተ ቁስል ደካማ ጐን ገብተን ብዙ ነገር ለማድረግ የሚሳነን አይደለም፡፡ ስለዚህ ይህንን ድርጊታችሁን አቁሙ፡፡ ብለን ከአንዴም ሁለት ጊዜ አገራቸው ድረስ ሄደን ለምነናቸዋል፡፡ ሊቀበሉን አልቻሉም እና ዛሬ የእጃቸውን አግኝተዋል፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ያግንባር ወይም የሱዳን ግንባር የአረቦች የጥፋት መንደርደሪያ እንደመሆኑ መጠን ዛሬ ነፃነቱን ያገኘው አፍሪካዊ የደቡብ ሱዳን ተጠናክሮ የቆመ እንደሆነ በዚያ በኩል ኢትዮጵያ ስጋቷ በጣም የቀለለ ወይም ጨርሶ የተወገደ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በተመሳሳይ በሱማሌ ተደረገው ዛሬ ሱማሌ ለእኛ የምታሰጋ አገር አይደለችም፡፡ ስለዚህ በሱዳንና በሱማሌ በኩል የተደረገው ነገር በአጥቂነት ሳይሆን በእነሱ እብሪተኝነትና እኛን በማጥቃት የወሰዱትን እርምጃ ለመከላከል የተወሰደ እርምጃ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያኖች በሙሉ ሊኮሩ ይገባል፡፡ ከነፃነትና ከአገር ህልውና አኳያ የሚያዝና ግኝት ድል ነው፡፡ በአጠቃላይ ለማጠቃላል የምለው ይህንን ነው፡፡”

“እዚህ አውስትራሊያ ጨምሮ በመላው ዓለም ላይ በስደት ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንና አገር ቤት ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጠቅላላ የሚያስተላልፉት መልዕክት ይኖራል?”

“ኢትዮጵያ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለች ለማንም ግልጽ ነው፡፡ በእርግጥ እንደ ግንዛቤአችንና እንደ ንቃተ ህሊናችን እንደ መረጃ ግንዛቤአችን አመለካከታችን ሊለያይ ይችላል፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ኢትዮጵያን ከዚህ አስከፊ ሥርዓት ለማውጣት መታገል አለበት፡፡ ለዚህ ነገር መተኛት የለበትም፡፡ ይህ ሊሆን ካልቻለ ለዘላለም ለትውልድ አስፋሪና አሳፋሪ ታሪክን ጥሎ ማለፍ ነው፡፡ ዛሬ አሳፋሪ ቡልኮ ለብሰን ነው የምንኖረው ማለት የምችለው ይህንን ነው፡፡”

“የቀድሞው የኢህድሪ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያም ስለትብብርዎ አመሰግናለሁ!”

ዛሬ የምንኖረው አሳፋሪ ቡሉኮ ለብሰን ነው!!

የቀድሞ የኢትዮጵያ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐሊክ /ኢህዲሪ/ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያም ባለፈው ሐሙስ ዕለት አውስትራሊያ አገር በሚተላለፈው ኤስ ኤስ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ካሣሁን ሰቦቃ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡

የቃለምልልሱን ዝግጅት ክፍሉ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

ሥልጣንም የለውም፡፡ ስለዚህ በፓርቲው ውስጥ ያለውን የአምባገነንነትና የብተና ሥራ አጥብቀን አንታገለዋለን፡፡” ብለዋል፡፡ “14 አመራርና አባላት ተባረዋል ከአንድነት ጋር የነበረው ድርድር መቋረጡንም ም/ቤቱ ተቀብሎታል ተብሏል፡፡ “ምን አስተያየት አልዎት” በማለት የጠየቅናቸው አቶ ያሬድ ሲመልሱ “ውሳኔው ህገ-ወጥ ነው፡፡ እንኳን ህጋዊ ያልሆነ ም/ቤት ቀርቶ ህጋዊ እንኳን ቢሆን የታገዱት ሰዎች በተገኙበት ጥፋታቸው ተገልጾ እነሱም ሐሳባቸውን አቅርበው ተደምጠው የሚወሰን እንጂ እነሱ እንዳይገቡ ተደርጐ ሊወሰን አይችልም፡፡ ሂደቱ ከፓርቲው ደንብ ውጪ የተሠራ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም፡፡ ከአንድነት ጋር የነበረው ድርድር መቋረጡ ተገቢ ነው ብሎ ም/ቤቱ ተቀብሎታል መባሉም ሌላው ስህተት ነው፡፡ እንኳን ይህ ህገወጥ ም/ቤት ቀርቶ ህጋዊ ም/ቤቱ እንኳን ቢሆን የጠቅላላ ጉባዔውን ውሳኔና መመሪያ የመሻር መብት የለውም፡፡ ውህደቱ እንዲከናወን ጠቅላላ ጉባዔው ወስኗል፡፡ ከም/ቤቱም

ሆነ ከሥራ አስፈጻሚው የሚጠበቀው ውሳኔውን ማስፈጸም ነው፡፡ ለግል ሥልጣንና ለግል ጥቅም ተብሎ ምክንያት ፈልጐና ቅድመ ሁኔታንና አስቀምጦ የውህደቱን ተግባር ማስተጓጐል ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ ይህ የጠቅላላ ጉባኤውን ውሳኔው ብቻ ሳይሆን የሕዝብን ጥያቄ አለመመለስ የጐደለ ነገር አለ፡፡ በተያያዘ ዜና ሰሞኑን መኢአድ አባላቶቹ እርስ በርስ በቡድን በቡድን ተከፋፍለው ሲበጣበጡና ሲደባደቡ ማየት ተችሏል፡፡ ጽ/ቤቱን በሚቆጣጠሩት በኢ/ር ኃይሉ ሻውል ደጋፊዎችና “በተለያየ ምክንያት ከፓርቲው የታገዱ” የሚባሉትና በአንጂነሩ አመራር እምነት አጣን የሚሉ በርካታ አባላት ከታገዱት አባላት ጋር በመሆን የብጥብጡ ተካፋይ ሆነዋል፡፡ ከታገዱት አባላት/አመራር መካከል አቶ ሚሊዮን ተሾመ አንዱ ናቸው፡፡ አቶ ሚሊዮን እንደሚሉት “እኔ የላዕላይ ም/ቤቱ አባልና የአዲስ አበባ ከተማ መኢአድ ተጠሪ ነኝ አቶ ኃይሉ ሻውል መኢአድን ለማፍረስ በጥፍሩ የቆመ፣ሰው መሆኑ በግልጽ የተንፀባረቀበት ወቅት ቢኖር

ከመቼውም በላይ አሁን ነው፡፡ ከጐዳና እየሰበሰበ በስነ-ምግባር የተባረሩትን፣ በተለያየ ምክንያት የወጡትን እየመለሱ ም/ቤት መሥርቻለሁ በማለት በፓርቲው ውስጥ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉትን አባላትና አመራር በማግለል፤መታሠርን እንደትልቅ ነገር በመቁጠር በአባላት ላይ ሲያላግጥ የቆየ ሌላው የኢህአዴግ መልዕክተኛ ነው፡፡

በተጨማሪም በአጠገቡ የኮለኮላቸው ሰዎች በሙሉ ጋሻ ጃግሬዎች ናቸው፡፡ ኃይሉ ሻውል አባላቱን በመናቅ በወርና በሁለት ወር ለፊርማ ብቻ ብቅ በማለት መኢአድን ለማፍረስ ከሚያሴሩት ውስጥ አንዱ መሆኑን አስረግጨ መናገር እወዳለሁ፡፡” አቶ ሚሊዮን ተሾመ የመኢአድ የላዕላይ ም/ቤት አባልና የአዲስ አበባ ተጠሪ ነኝ በማለት ይገልፃሉ፡፡ ዓርብና ቅዳሜ በተፈጠረው እረብሻ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችና “አሲድ የተረጨበት ሰው አለ፡፡” በማለት ይገልፃሉ፡፡ በእረብሻው ምክንያት የታሰሩ ሰዎች እንዳሉ ታውቋል፡፡

የመኢአድ ማዕከላዊ ... ከ ገፅ 11 የዞረ

Page 14: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

���� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

���� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

ዓለም አቀፍ

የ83 ዓመቱ የ ቀ ድ ሞ ው የ ግ ብ ፅ ፕ ሬ ዘ ዳ ን ት እና ባለ ሥልጣኖቻቸው ለ ፍ ር ድ

ይቅረቡልን ጥያቄ መበራከቱ አሁን ሀገሪቱን ለሚመሩት ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት እረፍትን የሚሰጥ አልነበረም፡፡ ባለፈው የካቲት 2003ዓ.ም ለ18 ቀናት የተቃውሞ የአደባባይ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ የግብፅ ህዝብ ፕሬዘዳንታቸውንና ግብረአበሮቻቸውን ከሥልጣን

ማሰናበታቸው ይታወሳል፡፡ይሁን እንጂ ተቃውሞአቸው

በዚህ ሳያበቃ “ለፍርድ ይቅረቡልን፣ በሰልፍ ወቅት ሰዎችን ገድለውብናል፣ የሀገሪቱንም የገንዘብ ሃብት መዝብረዋል” በሚል አሁንም ህዝቡ ከመጠየቅ አልቦዘነም፡፡ ፕሬዘዳንቱም የግብፅ የባህል ዳርቻ ላይ የምትገኘው ሻርማልሼክ ከተማ ያረፉ ቢሆንም በልብ ድካም ህመም ሆስፒታል በህክምና እየተረዱ በመቆየታቸው የፍርዱ ሂደቱ ሊዘገይ ችሏል፡፡

የህዝብ ጥያቄም በመበራከቱ ረቡዕ ሐምሌ 27/2003 ዓ.ም ልጆቻቸውና ባለሥልጣኖቻቸውን

ጨምሮ የሀገሪቱ የፍርድ ችሎት በፍርግርግ ሽቦ አጥር ውስጥ ሆነው የቀረቡ ሲሆን የቀድሞው ፕሬዘዳንት ግን ከህመማቸው አገግመው ቆመው መራመድ ስላልቻሉ በህመምተኛ መጓጓዣ አል (ስትሬቸር) ሆነው ነበር በችሎቱ ሲታደሙ የቆዩት ይህም በመላው ግብፅ በቴሌቪዥን መስኮት በቀጥታ የተላለፈ ሲሆን የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃንም ሂደቱን ሲያሰራጩ ተስተውሏል፡፡ የአቃቤ ህግና የተለያዩ የዓይን ምስክሮችም ቃል ተደምጠዋል፡፡ የችሎት ስርዓቱም እንዳይተጓጐል በብዙ በሚቆጠሩ ወታደሮች

የተጠናከረ ጥበቃ የተደረገ ሲሆን ፕሬዘዳንቱም በሰላማዊ ሰለፍ ወቅት 85ዐ ሰዎች ለሞቱበትና ፈፀሙት ለተባለው የሙስና የተባሉትን ተግባር ወንጀሎች አልፈፀምኩም ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

ነገር ግን በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ በሀገሪቱ ህግ መሰረት የሞት ፍርድ አሊያም የዕድሜ ልክ እስራት እንደሚጠብቃቸው በግብፅ የሚገኙ የህግ ባለሙያዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ባለንበት ዓመትም እኚህ የ83 ዓመት አዛውንት ተቃዋሚዎቻቸውን በማሰርና

ከሀገር እንዲሰደዱ በማድረግ “ምርጫ” አድርገው አሸንፌአለሁ ብለው ሥልጣናቸውን ቢያራዝሙም አንድ ዓመት ሳይሞላቸው በህዝብ የተቃውሞ ማዕበል ከሥልጣናቸው ሊሰናበቱ ችለዋል፡፡አሁን ባለው ሂደትም የግብፅ ህዝብ ለሁለት የተከፈለ ይመስላል፡፡ ግማሹ እንደ ደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ እርቅ ይውረድ ሲሉ ቀሪዎች ግን “የለም ተፈርዶባቸው ማየት እንሻለን፣ እኛን እንዴት እንዳሰቃዩን ሊያውቁት ይገባል” ሲሉ አስተያየቶቻቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፣ የፍርድ ሂደት ግን ገና ይቀጥላል ተብሏል፡፡

ለፍርድ የቀረቡት የቀድሞው የግብፁ ፕሬዘዳንትሆስኒ ሙባረክ ጉዳይ እያነጋገረ ነው

የአፍሪካ ህብረት የመረጃና መገናኛ ዳይረክቶሬት ሐምሌ 29/2003 ዓ.ም የሶማሊያንና የአፍሪካ ቀንድ ርሃብን በተመለከተ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ የአፍሪካ ህብረት ኮምሽን የባንክ ሒሳብ ከፍቶ ከአፍሪካ መንግስታት፣ ከግል ድርጅቶች እና ከዜጐች ዕርዳታ በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም አካል በሚከተለው የባንክ ሒሳብ ቁጥር ገቢ ማድረግ ይችላል ሲል ህብረቱ ጠይቋል፡፡

African union Horn of Af-rica Drought Relief

Fcy Account N; 02702/953184/00

Commercial Bank of Ethio-pia

AU BranchAddis Ababa EthiopiaSwift code: CBETETAAህብረቱ ነሐሴ 9/2003 ዓ.ም

“የአንድ አፍሪካ ድምፅ ጥሪ ቀን” በሚል የአፍሪካ ቀንድ በተለይም

በሶማሊያ ርሃብን አስመልክቶ በተለያዩ የህብረቱ አባል ሀገራት፣ የአፍሪካ የግል ድርጅቶች፣ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በውጭ የሚኖሩ አፍሪካውያን ሁሉም ግብረሰናይ ድርጅቶችና ግለሰቦች በአይነትም ሆነ በጥሬ ገንዘብ የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማሰባሰብ እና ተጐጂዎችን ለመርዳት እንደሚንቀሳቀስ አስታውቋል፡፡

የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶ/ር ጂያን ፒንግ ይህን

አስመልክቶ ሁሉም አባል ሀገሮች ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉት ድጋፍ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም አባል ሀገራት በተገኙበት ነሐሴ 19/2003 ዓ.ም በአዲስ አበባ በህብረቱ ዋና ጽ/ቤት ሰብሰባ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀድሞ የጋና ፕሬዘዳንት እና የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሶማሊያ ከፍተኛ ተወካይ ሚስተር ጄሪ ራውሊንግስ ከህብረቱ ሊቀመንበር ከሚስተር

አቤንግ ንጉማ ምባሶጐ ጋር ተገናኝተው እንደተወያዩ ጠቅሰዋል፡፡ በዚህም ጥቂት የአህጉሪቱ ከተሞች በመዘዋወር ለድጋፍ እንደሚንቀሳቀሱ ይጠበቃል፡፡

የህብረቱ ተወካይ ቋሚ ኮሚቴዎች መሰብሰባቸውና በመሪዎች ስብሰባ በሊቀመንበሩ የተሰጠውን ውሳኔ እንደሚደግፍ ገልፀው ይህም ለአፍሪካ የሰብዓዊ እርዳታ ምላሽ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አስታውቀዋል፡፡

ከአፍሪካ ህብረት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

ግንቦት 8 ቀን 1981 ዓ.ም በተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መክሸፍ በኋላ ፕ/ት መንግሥቱ ኃ/ማርያም የሀገር ውስጠና የውጭ ሀገር ጋዜጠኞች፡- “መፈንቅለ መንግሥት ይደረጋል ብለው ይገምቱ ነበር;” ብለው ላቀረቡላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፡-

“- - - በእውነቱ ይህ መፈንቅለ መንግሥት በኛ በኩል የተጠበቀና የተገመተ አልነበረም፡፡ ምክንያቱም ጠንካራ ፓርቲ አለን፤ጠንካራ ሕዝባዊ መሠረት አለን፤ጠንካራ መንግሥት አለን፤እያንዳንዱ ዜጋ ከማርቀቁ ጀምሮ ተወያይቶበት፣ተችቶበት፣የራሱንም ሐሣብ

ጨምሮበትና አዳብሮት ሕዝብ ያፀደቀው ሕገ-መንግሥት አለን፡፡ የነቃና የተደራጀ ሕዝብ ብቻ ሣይሆን የታጠቀ ሕዝብም አለን፡፡ - - -$ በማለት ነበር ለጋዜጠኞች መልስ የሰጧቸው፡፡ ትንሽ ለማስታወስ ያህል ብዬ እንጂ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡ ይህ የኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያም ንግግር ለክቡርነትዎ ግርምትን እንደሚፈጥርብዎ አይጠረጠርም፡፡በተለይም “ሕዝብ ከረቂቁ ጀምሮ ተወያይቶበትና ተችቶበት፣የራሱንም ሐሳብ ጨምሮበትና አዳብሮ ያፀደቀው ሕገ-መንግሥት አለን” ያሉት የበለጠ

እንደሚያስገርመዎት ርግጠኛ ነኝ፡፡ የርስዎ ሥርዓትና መንግሥትስ እንዴት ነው; የቀልዱ ሂደት አልቀጠለም; አንዳንዶቹን ባስታውስዎትስ; ገና ከውጥኑ ኤርትራ “በሕዝብ ውሳኔ የራሷን እድል በራሷ ወሰነች” አልተባልንም; ይህን እውነት ነው ካሉኝ የመንግሥቱ ኃ/ማርያም ንግግርም እውነት ነው፡፡ የኢሕአዴግ ሕገ-መንግሥትስ ሕዝብ ከረቂቁ ጀምሮ መክሮበት፣ተወያይቶበት፣ተችቶበትና የራሱን ሐሣብ አዳብሮበት ይሆን የፀደቀው; መልሱን ለሕሊናዎ፡፡ በመሠረቱ በዘመንዎ የተፈፀሙትንና እየተፈፀሙ ያሉትን የክፋትና የጎሰኝነትን ካባ አጥልቀው ወይንም ተከናንበው የሚሠሩ ደባዎችን በዚች ጽሑፍ ዘርዝሮ ለባለቤቱ ላሳውቅ ማለት አይቻልም፡፡ ከዚህ ይልቅ ከኮሎኔል መንግሥቱ ተሞክሮ እየጠቀስኩ በምሳሌ ብነግረዎ ወይንም ባሳየዎ የተሻለ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡

በመጨረሻዋ ሰዓት ኮሎኔሉ ሊወድቁ እየተንገዛገዙ በነበሩበት ወቅት በሸንጎው ስብሰባ ላይ የሸንጎው አባል የሆኑ አንድ የሃይማኖት አባት እንዲህ ብለው ነበር፡-

“ምንድን ነው የምንፈራዎት; የኢትዮጵያን ሕዝብ ቆስቁሰው 17 ዓመት ሙሉመርተው ወደየት ነው የሚሄዱት;ወደ ኤሮፕ ይፈረጥጣሉ የሚል እምነት የለኝም - - -$ በማለት የሃይማኖት አባቱ ሲናገሩ የሸንጎው አባላት ፀጥ ረጭ አሉ፡፡ ጨርሶ የዝንብ ጢዝታ እንኳን አይሰማም፡፡ እንግዲህ ሰው በላው በሚባለው ሥርዓት እንኳን የሸንጎው አባላት እንዲህ በድፍረት የሚናገሩ ነበሩ፡፡ ዛሬ በርስዎ የተወካዮች ም/ቤት የኢሕአዴግ አባላት ርስዎንና ሥርዓትዎን ከማሞካሸት ውጭ በድፍረት ስለ እውነት የሚናገሩ ሕሊና ያላቸውን ፈልጎ ማግኘት አይቻልም፡፡ ለማንኛውም ሌላ ማሣያ ልጨምር፡፡

በዚያው የሸንጎ ስብሰባ ላይ ሌላው

ተናጋሪና የሸንጎው አባል እውቁ ምሁር እውነትን ከመናገር ወደ ኋላ የማይሉት ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ ነበሩ፡፡ ዶክተሩ እንዲህ አሉ፡-

“- - - እኔ ደጋግሜ የምለው ነው ጓድ ፕሬዚዳንት፤ሕዝብና መንግሥት ሆድና ጀርባ ሆነዋል፡፡ ሕዝብ ለመንግሥት ጀርባውን ከሰጠ ከሕዝብ ምንም መጠበቅ አይቻልም፡፡ - - -$ በማለት ኮሎኔሉን የሚያስቆጡና የሚያስደነግጡ ታሪካዊ ንግግሮችን ተናግረው ነበር፡፡ ርግጥ ነው፡፡ርሰዎም ከታሪካዊ ጓደኞችዎ ጋር (ከነአቶ ስየ አብርሃ ጋር) ስትለያዩ “ጃኬታቸውን እያስወለቅን አባረርናቸው” በማለት የድንፋታ ንግግር ሲናገሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ “አሁንስ መንግሥቱ ኃ/ማርያምን አስታወስከኝ” በማለት ሲተቹዎ ርስዎ እልህ እየተናነቀዎ ዋጥ አድርገው ቢችሉትም ወ/ሮ ነገት ዘውዴ ግን ስቅስቅ ብለው አልቅሰዋል፡፡ መንግሥቱ ሲተቹ ግን ኢሠፓ ውስጥ ተንሰቅስቆ ያለቀስ በኢቲቪ አላየንም፤በወሬም አልሰማንም፡፡

ከዚህ ላይ ግን ትልቁ ቁምነገር መንግሥቱ እንዲህ ተብለው ነበር፣እነ ከሌ እንዲህ ብለዋቸው ነበር የሚለው አይደለም፡፡ ዋናው ጉዳይ ክቡር ጠ/ሚንስትር ታሪክ እንዳይደገም ርስዎ ካለፈው ምን ይማራሉ; ምንስ ተምረዋል; ይህ ነው መተኮር ያለበት፡፡ ሕዝብ ዝም ስላለ ሥርዓተዎንና ርስዎን ወዶና አክብሮ እየተገዛልዎ እንዳይመስልዎ፡፡ ዝምታው እዳ ከብዶት፣ጫና በዝቶበት፣አፈናው በዝቶበት ነው፤ችግሩ የሚመጣው እየተንገዛገዘ የተሸከመውን ሸክም አቅቶት የወደቀ አንደሆነ ነው፡፡ የኔ የማሳሰቢያ መልእክትም ከዚህ አንፃር ነው፡፡ የኔ የምስኪን ምክርም ይቀበላሉ ብዬም አይደለም፡፡የድርሻየንና የዜግነቴን ተንፍሸ ይውጣልኝ ብዬ ነው፡፡

ክቡር ጠ/ሚንስትር፤ባፄው ዘመነ መንግሥትም ሆነ በደርግ ጊዜ ሕዝብ ይል የነበረውን ዛሬም በርስዎ

ዘመን እየጮኸ ያለው “የሁላችንም መብት የምታስከብር፣የሁላችንም አገር የምትሆን ኢትዮጵያን እንፍጠር፤ለመፍጠርም አብረን እንገንባ ነው እያለ ያለው፡፡ ለሥልጣን ጥም ሲባል ግን አቅጣጫን እየቀያየሩ የሕዝብን ስሜት መጉዳት ትርፉ ትዝብት እንጂ ከመውደቅ አያድንም፡፡ ለዚህም ነው ባለፉት መሪዎች ጊዜ ይባሉ የነበሩትን አንዳንዶቹን ልጠቅስልዎት የተገደድኩት፡፡

ክቡር ጠ/ሚንስትር፤ርስዎም እንደ ቀደምት የኢትዮጵያ ገዥዎች ወይንም ነገሥታት ገድለውና አምፀው ነው ለሥልጣን የበቁት፡፡ ይህ በመሆኑም አመራርዎ በሴራ የተተበተበና ግልፅነት የገደለው ነው፡፡ የቀድሞዎቹ ገዥዎችስ ሥልጣን አያያዛቸው በመፈንቅለ መንግሥት ቢሆንም ጉዟቸውና አሠራራቸው ቢያንስ ካቅም ማነስ አንፃር ይቀር እንደሆነ እንጂ ለሕዝባቸው ይጨነቁ ነበር፡፡ የርስዎ አመራር ግን ጨርሶ ከሕዝብ ስሜትና ፍላጎት ውጭ ባዶ ፕሮፖጋንዳ ብቻ በማዝነብ የቁልቁልዮሽ መንጎድ ሆኗል፡፡ ያገር ሉዐላዊነትንና ምጣኔ ሀብትን በተመለከተ ባናነሳው ይሻላል፡፡ አንዷን ብቻ ባስረጅነት ጠቅሸ ሀሳቤን ልቋጭ፡፡ የባሕር በራችንን ያጣነው በርስዎ ያገዛዝ ዘመን በመሆኑ ታሪክ ይቅር የማይለው ፍርጃ በመሆኑ የእያንዳንዱን ዜጋ ሕሊና ያቆሰለ ነው፡፡ እንዳደጉት ሀገራት መሪዎች ቢሆን ኖሮ እንኳንስ የባሕር በርን ያህል ነገር ያስረከበ መሪ ተራ ስህተት ሲሠራ ሥልጣኑን ወዲያውኑ በገዛ ፈቃዱ ይለቅ ነበር፡፡ ርስዎ ግን ከሥልጣን ላይ ከተጣበቁ ድፍን 2ዐ ዓመታትን አስቆጠሩ፡፡ ወይ ዘውድ አልጫኑ ወይ የኮሚኒስት መሪ አለሆኑ፤እንዴት ነው ነገርዎ; ከእንግዲህ ቢበቃዎና በክብር ሥልጣንዎን ቢለቁ እስካሁን ለሚወቀሱባቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ሁሉ እንደ ካሣ ይቆጠርለዎታል፡፡ ለማንኛውም ቅንነቱን እግዚአብሔር እንዲያመላክተዎት ከልብ እመኝልዎታለሁ፡፡

በዚያው የሸንጎ ስብሰባ ላይ ሌላው ተናጋሪና የሸንጎው አባል

እውቁ ምሁር እውነትን ከመናገር ወደ ኋላ የማይሉት

ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ ነበሩ

ይድረስ ለክቡር... ከ ገፅ 4 የዞረ

Page 15: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

���� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

���� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org

Although the private sector of the economy in Ethiopia started to function with some degree of policy guidance some 60 years

ago, it is still at the crawling stage. During the era of the monarchy, a somewhat conducive environment was created for domestic and foreign investors such as the Dutch, Italians and Greeks to be engaged significantly in the manufacturing sector. Viewed in the African context, the industrial sector in Ethiopia was comparatively in a better state.

When the Derg came, it slammed the door against the private sector of the industry. It nationalized the factories that were starting to bloom at the time and put a low ceiling on the amount of capital private investors could invest. The development of the industry fell fully in the hands of the government. However, towards the end of its agonizing years, the Derg had moved to do away with the ceiling on investment and to institute a brand of a mixed economy.

In 1991, EPRDF hid its Marxist cloak under and pretended to give recognition to the private sector of the economy as well as to a multi-party system. However, in practice, Marxism-Leninism, which has been its guiding ideology for many years, remains in place to the present, albeit under cover.

The Revolutionary Democracy, which EPRDF follows in tandem with its socialist ideology, compels it to take the peasant farmer and the worker as its power base and to label the middle business class as unreliable and a rival to be fought against. Thus, EPRDF’s attitude towards the private sector of the economy and the community that is associated with it has been fraught with hostility, thus making it impossible to introduce badly needed changes in land policy, to allow the financial market to be open or to allow the private investors to engage in telecommunications business. These policy obstacles have made the transition from agriculture-based to industry-based economy practically impossible.

Beginning in 2005, the government has been following State Capitalism. The objective of this strategy is to mobilize the few opportunist urban businessmen and fulfill the regime’s dream of prolonging its rule. State Capitalism, by its nature, creates an inflated government and ineffective private sector in the economy. That is why a propaganda campaign is waged to make people believe that the Growth and Transformation Plan will be fulfilled.

In a country like Ethiopia, where there is a serious structural deficiency, UDJ does not argue against the government playing a role in the economy. However, it argues that stifling the private sector is stifling the transition to democracy in our country and the hope for development. It further argues that it is better to strengthen the numerous and hardworking merchants than to cling to a few rich.

During its misguided rule of twenty years, the EPRDF regime has not enabled the Ethiopian private sector to compete in the narrow market of cheap Chinese goods dumped in the country, let alone in the wide international market. The contribution of manufacturing to the overall economy of the nation is not more than a pitiful 5 percent. The ruling regime has made the base of growth and development not creativity and hard work but opportunism and cronyism.

The ruling regime has sacrificed the private sector of the economy in order to promote its developmental state capitalism. State expenditure, which was 20 billion birr in 2005, has been raised to 75 billion birr in 2011. Had there been a sound economic base and appropriate economic policies, UDJ would have taken this significant budget growth as a positive trend. However, measures being taken are not only lacking seriousness but also are beyond the capacity of the economy to sustain. The highly inflated budget has not only exacerbated the high cost of living but it has also

created a heavy burden on the taxpayer. In 2005, the state revenue was 14 billion birr.

In2010, 51 billion birr was collected. The tax being collected, instead of encouraging business to be more productive and competitive, is exposing it to open and widespread exploitation. It is known that, according to reports issued by Transparency International, Ethiopia is one of the countries that are plagued by rampant corruption.

The taxpayers know full well that the majority of the regime’s officials are deeply mired in corruption. It is hardly possible to say today that there is no official of the regime who has not become the owner of a villa, a multi-storey building, a modern car, land or a combination of these through shortcuts. A recent report of the UNDP shows clearly that some 140 billion of the taxpayers’ birr has been plundered. Viewed in this context, who stands closer to corruption and to “parasitism and rent collection” than EOPRDF itself?

It is known that the business community is complaining bitterly and loudly against the heavy tax burden imposed on it recently. It has been asked to pay more than 40 to 50 fold of the tax it has been paying previously. The ruling regime says that it has increased the tax because the daily sale of the merchant has gone up. Not only that, it also says that the measure was based on a “conducted study”. This is no more than a cynical joke. The so-called study allows the imposition of a tax of over 8,000 birr on a shop the maximum value of whose asset is not more that 5,000 birr. Instead of working to broaden the tax base, the government seems to be bent on destroying the narrow base that already exists.

The business community is being exposed to outright exploitation in the name of the law with no recourse to justice. The officials in the revenue office do not give the overburdened merchant satisfactory answers. All they tell it is to pay at least half of the imposed tax and complain later. What is more, the statements that the officials make through the media are spreading dismay and hopelessness in the business community. The officials are saying, in a manner that is irresponsible, that if the merchants do not like the tax imposed on them, they can pay what they are asked to pay, close their shops and go home. These officials seem to forget that if the life of the business community is disrupted, theirs would not remain safe.

EPDF lacks the habit of using each birr, that the businessman creates with his sweat, in a manner that is transparent, fair and accountable. It is repeatedly observed that the taxpayer’s money is exposed to corrupt spending. For example, public money is used for training the cadres of the ruling regime. State and party functions are mixed in a manner that is illegal. In fact, it is becoming more and more difficult to discern the difference between the budget of the state and that of the party.

UDJ believes that taxes must be paid. But it also believes that the government has a responsibility. It is not enough for the government to demand taxes from the people. It must, on its part, respect the economic, human and political rights of the people. The ruling regime does not allow free and fair elections. It does not respect the rights of citizens to free expression or association. The public mass media, although funded by the people, blindly support only the ruling regime. Party membership and party loyalty are used as criteria for gaining access to jobs, educational opportunities and other significant benefits. In a situation where there is so much injustice, it is impossible to expect people to pay taxes duly and with a sense of responsibility. A government that is not honest with the people cannot expect honesty from the people.

UDJ fears that the coming days would be worse than those of the present. The government has planned, in 2011-2012, to collect a total revenue of over 76 billion birr. According to its five-year Growth and

Transformation Plan (GTP), EPRDF has set out to collect 127 billion birr in tax revenue in the next five years. It is inevitable that a heavy burden will be imposed particularly on the business community. There will be more repression. Matters will be complicated further as a result of the existence of a regime that is not genuinely elected by the people and is non-transparent and unresponsive to the will of the people.

The Business Community has no alternative but to stand united and protect its existence. It should not be made to feel unable to operate freely in its own country. Nor should it allow itself to be viewed as a second class partner in business, despite the fact that EPRDF views it as a feared rival that should be removed from the scene. The ruling regime must change the misguided policy that it is following regarding the Business Community. Thus, UDJ urges the ruling regime to pay heed to the following:

1. EPRDF is itself a merchant. It is itself a legislator and an executor. This makes it view the business community as a rival and not

as a partner. The ruling party has to free itself from this unhealthy attitude , accept the private sector as the engine of the economy and encourage it in actual practice to play its role in the growth and development of the country.

2. It is dangerous to be in a blind haste to reach campaign goals. The ruling regime must move with caution and give ears to the complaints

of the Business Community.

3. UDJ believes that the burdensome tax imposed on the private Business Bommunity must be reviewed. Rather than destroying the narrow

tax base that is already overburdened, UDJ urges the ruling regime to give more attention to reducing costs by improving the messy and wasteful administration and by cleansing itself from corruption.

4. It is well known that over 40 percent of the economic activities in the country is within the informal sector of the economy. It is necessary

that the people involved in this sector are brought into the tax system step by step.

5. The ruling party has given priority to staying in power by any means than to genuinely promoting the overall interests of the

nation. To this end, for example, it has established a repressive spying system that is costly. It must be held accountable for its extravagant expenditures in this branch. The taxpayer’s money is being used to block websites and to repress mass media such as the VOA, DW and ESAT from being heard and seen in Ethiopia. The taxpayer’s money should not be used for strengthening dictatorship.

6. It is extremely urgent that the red tape in the administration of the revenue collection system be cut and the process made efficient

and responsive to the needs of the people.

7. Transparency is vital in the trading sector as it is in any other sector of the society.. The all-too-pervasive, party-affiliated business

enterprises established outside the legal framework should at least be audited once a year and the result made public.

UDJ believes that the private sector should play a key role in the arduous struggle to empower the Ethiopian people and to establish a government subject to accountability. Therefore, UDJ will strive to contribute its share to the strengthening of the Business Community and to the protection of its rights and interests so that it could play its proper role in the growth and development of the country.

Unity for Democracy and Justice (UDJ)August 5, 2011Addis Ababa

The tax burden imposed on the Business Communityis unwise and unjust!

Tax BurdenPress statement from Unity for Democracy and Justice (UDJ)

Page 16: 11ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/08/Fenote...ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003

PB�� ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም ማክሰኞ ነሐሴ 3 2003 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2 1ኛ ዓመት ቅጽ.1 ቁ.2

www.andinet.org www.andinet.org