45
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ዓመታዊ ሪፖርት 2006/ ፳፻፮

የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ

ሳይንስ አካዳሚ

ዓመታዊ ሪፖርት

2006/፳፻፮

Page 2: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው
Page 3: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው
Page 4: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው
Page 5: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የፕሬዝዳንቱና የሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሩ መልዕክት 81. ታሪካዊ ዳራ 9 1.1. . . ተቋማዊ አስተዳደርና አደረጃጀት 10 1.2 የአካዳሚው ስትራቴጂክ ዕቅድ 11 1.3 የአካዳሚው ዋና ዋና ስኬቶች 132. በ2006 ዓ.ም የበጀት ዓመት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ዓ.ም የበጀት ዓመት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ዓ.ም የበጀት ዓመት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት 14 2.1 አካዳሚውን በሚመለከት ያለውን ግንዛቤ ማሳደግና ጠቀሜታውን ማጠናከር 15 2.1.1 አዳዲስ አባላትን መምረጥምረጥም 16 2.1.2 የኢትዮጵያ ወጣት ሳይንስ አካዳሚንሚንሚ መመሥመሥመ ረትሥረትሥ 16 2.2 የአካዳሚውን እንቅስቃሴዎች ማሳደግ ማሳደግ ማሳደግ 17 2.2.1. . . የአካዳሚውን ዋና ጽ/ቤት ማስጐብኘት 71 2.2.2. . . የኢ.ሳ.አ. ተወካዮች የውጭ አገር ጉብኝት 81 2.3 ወሳኝ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባቢያ ጥናቶችን ማካሄድና መድረኮችን ማዘጋጀት 02 2.3.1 የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ፓኔል (መድረክ) ምሥምሥም ረታሥረታሥ 20 2.3.2 የብሔራዊ ምርምር ምክር ቤት የጋራ መግባቢያ ጥናት 22 2.3.3 የኢትዮጵያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የሎጂ የሎ ሰው ሃብት ፍላጐትና አቅርቦት ጥናላጐትና አቅርቦት ጥናላ ት 23 2.3.4 የሳይንስ መሣሪያዎች ፖሊሲና የሲና የሲ ምርምር ሥራ በኢሥራ በኢሥ ትዮጵያ ያለበትን ሁኔታ የሚገመግም ጥናት 32 2.4 ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽንን ማበረታታት 25 2.4.1 ዘጠነኛው የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች ዓመታዊ ጉባኤና ተጓዳኝ ሁነቶች 52 2.4.2 በአፍሪካ የትምባሆ ማጨስ መስፋፋትን በተመለከተ የተደረገውን ጥናት ሪፖርት ይፋ ለማድረግ የተካሄደ አውደ-ጥናት 32 2.4.3 "በናይል ተፋሰስ የሚገኙ ግድቦች አካባቢያዊና ማህበራዊ ተፅዕኖ" ሕዝባዊ ገለፃ 43 2.4.4 በኢትዮጵያ የግብርና ባዮቴክኖሎጂን ጠቀሜታ ሎጂን ጠቀሜታ ሎ ለማሳደግ ስለሚቻልበት የሚመክር ኣውደ ጥናት 43 2.5 ለልሕቀት ዕውቅና መስጠት 43 2.6 የአካዳሚውን ተቋማዊ አቅም ማጎልበትና ቀጣይነቱን ማረጋገጥ 53 2.6.1 የአካዳሚውን ሥራ በአግባቡ ማከናወንሥራ በአግባቡ ማከናወንሥ 35 2.6.2 የኢ.ሳ.አ. ሥራ ዕቅድና በጀትሥራ ዕቅድና በጀትሥ 63 2.6.3 የአካዳሚውን ዋና ጽ/ቤት ህንፃ ማሳደስና ግቢውን ማስዋብ 73 2.6.4 የተሸከርካሪዎች ግዢ 73 2.6.5 የአካዳሚውን ፖሊሲና የአሲና የአሲ ሠራር መሠራር መሠ መሪያ መሪያ መ ሰነዶችን ማዘጋጀትና ማፅደቅ 73 2.6.6 የፕሮጀክት ሀሳቦችን ማዘጋጀትና ለሚመለከተው ማቅረብ 83 2. 6.7 . 6.7 . የአካዳሚውን ሕትመቶች ማሰራጨት 383. የሒሳብ መግለጫ 394. የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ 41አባሪ፡ የወቅቱ የኢሳአ የቦርድ አባላት 44

ማውጫ

Page 6: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው
Page 7: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው
Page 8: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

8

የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው ዓመት ነው፡፡ መንግስት ለአካዳሚው የሥራ እንቅስቃሴዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገበት የመጀመሪያው ዓመትም ነው፡፡ ይህ በመሆኑም በርካታ የአፍሪካ አካዳሚዎች በምሳሌነት የሚመለከቱት ተቋም ለመሆን ችሏል፡፡ አካዳሚው ከመንግስት ያገኘው እውቅናና የገንዘብ ድጋፍ በስትራቴጂያዊ ዕቅዱ መሠረት አያሌ ተግባራቱን በስኬት እንዲያከናውን የሚያስችሉት ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ የዘርፍ መስሪያ ቤቶች አካዳሚው ሊሰጥ የሚችለውን ድጋፍና አገራዊ ኃላፊነቶቹን በተመለከተ የሚኖረው ግንዛቤ እንዲጎለብት ያደርጋል፡፡ በዚህ ረገድ አካዳሚያችን ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘው ድጋፍ ወሳኛ ነበር ለማለት ይቻላል፡፡

ሪፖርቱ በሚሸፍነው ጊዜ ውስጥ አካዳሚው መንግስትን የማማከር ሚናውን እውቅና በሰጠ መልኩ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በቀረበለት ጥያቄ መሠረት የአገሪቱን የሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰው ሃብት ፍላጎትና አቅርቦት ጥናት በማካሄድ ለመጪዎቹ አስር ዓመታት የሚኖረውን ሁኔታ ለመተንበይ የሚያስችለውን ስራ ጀምሯል፡፡ የአካዳሚው ጽ/ቤትና ቦርዱ ለዚህ ጥናት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከፍተኛ ባለሙያዎችን ያቀፈ አጥኚ ቡድን በማዋቀር ሥራውን የጀመረ ሲሆን በበጀት ዓመቱ መገባደጃ ላይ ጥናቱ ከፍተኛ እመርታ አሳይቷል፡፡

ሌላው በበጀት ዓመቱ ለአካዳሚው ወሳኝ ሁነት ሆኖ ያለፈው አካዳሚውን ዘጠነኛውን የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች ዓመታዊ ስብሰባ ከህዳር 2-5/2006 ዓ/ም

በአዲስ አበባ ማስተናገዱ ነበር፡፡እንደ ስብሰባው አቢይ

አካልም ለአፍሪካ ልማት የባዮቴክኖሎጂ ሚና በሚል ርዕስ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአመርቂ ተሳትፎ ተካሂዷል፡፡ በጉባኤው ላይ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተጋበዙ ታዋቂ ምሁራንና ተመራማሪዎች ለተሳታፊዎች ግኝቶቻቸውንና አስተያየቶቻቸውን በማጋራት የባዮቴክኖሎጂ አብዮትን መቀላቀል ለአፍሪካ አወንታዊ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡ ጉባኤው በአፍሪካ ፖሊሲ አውጪዎች ላይ ያተኮረ በ12 የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች የጸደቀ ባለ 12 ነጥብ የጋራ አቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡ ስብሰባውን በተሳካ ሁኔታ ማካሄድ መቻሉም የአካዳሚውን መጎልበት አመላካች እንደሆነ ይታመናል፡፡

አካዳሚው ከመንግስት በአደራ የተረከበውን የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የቀድሞ መኖሪያ ህንፃ ዕድሳት መጀመሩ ሌላው የ2006 በጀት ዓመት አብይ ጉዳይ ነው፡፡ ምንም እንኳን ዕድሳቱ በታቀደው መሰረት ባይጠናቀቅም ከዋናው ህንፃ እድሳት አንጻር ወሳኝ የሚባሉ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ በግቢው ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ሕንጻዎችን በማደስ ለሚገነባው የሳይንስ ማዕከል አገልግሎት እንዲውሉ የማዘጋጀት ሥራም ተጀምሯል፡፡

ይህ ሪፖርት በአብዛኛው በሥራ ቡድኖች ግንባር ቀደምትነት በበጀት ዓመቱ በአካዳሚው የተከናወኑ አንኳር ተግባራትን ጠቅለል ባለ ሁኔታ እንደሚያስቃኝ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ በዚህ አጋጣሚም የአካዳሚው የዘርፍ የሥራ ቡድኖች ላስመዘገቡት ውጤትና ከጽ/ቤቱ ጋር ላደረጉት መልካም የሥራ ትብብር ጽ/ቤቱ አድናቆቱን ይገልጻል፡፡

የፕሬዚዳንቱና የሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሩ

መልዕክት

ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነፕሮፌሰር ደምሴ ሀብቴ

ፕሬዘዳንት ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር

Page 9: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

9

ታሪካዊ ዳራየኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚን የመመሥረት ጥረት ታሪክ ከ 1960ዎቹ የመጀመሪያ ዓመታት ይነሳል። ሆኖም የተጠናከረ ጥረት ማድረግ የተጀመረው በ 2000 ዓ.ም. ሲሆን ይኸውም የሳይንስን ባህልና ሳይንስን መሠረት ያደረገ ዕድገት በአገሪቷ ውስጥ እንዲካሄድ ለማገዝ ፍላጐት ባላቸውና ጉዳዩ ያገባናል ባሉ ጥቂት ሳይንቲስቶች የርስ በርስ ውይይት የተጠነሰሰ ነበር። በቀጣይነት የተደረጉት ውይይቶችና እንቅስቃሴዎች ፍሬ አፍርተው አካዳሚው ሚያዝያ 2 ቀን 2002 ዓ.ም. በይፋ ተመሰረተ። ለአካዳሚው እንቅስቃሴ ሕጋዊ ዕውቅና መስጠት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱም የካቲት 22 ቀን 2005 ዓ.ም. በአዋጅ ቁጥር 783/2005 እንደገና ተቋቋመ።

1

Page 10: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

10

ሁሉንም መደበኛ አባላት የያዘው ጠቅላላ ጉባኤ የአካዳሚው ወሳኝ የበላይ አካል ነው። ስምንት ተመራጭ አባላትንና፣ ሶስት የመንግስት ተወካዮችን (አንድ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተወካይና ሁለት ከመንግስት የምርምር ተቋማት የተወከሉ) የሚያካትተው ቦርድ ደግሞ የአካዳሚውን የአስተዳደርና ማስተባበር ተግባራትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል። ቦርዱ በየሶስት ወሩ መደበኛ ስብሰባዎች ያካሂዳል። አሁን በሥራ ላይ ያለው ቦርድ ሰኔ 13 ቀን 2005 ዓ.ም. አካዳሚው በአዋጅ ቁጥር 783/2005 መሠረት ከተቋቋመ በኋላ የተመረጠ ሲሆን የአባላቱ ዝርዝር በአባሪ 1 ተገልጿል።

የአካዳሚው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ፕሬዚዳንቱን፣ ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንቱን፣ ም/ፕሬዚዳንቱን እና

ዓቃቢ-ነዋይን የሚያካትት ሲሆን፤ የአካዳሚውን ጽ/ቤት የጠቅላላ ጉባኤውንና የቦርዱን ውሣኔዎች አተገባበር በቅርብ ይከታተላል፣ ለጽ/ቤቱ አመራርና ድጋፍ ይሰጣል። የአካዳሚው የዕለት ከዕለት ተግባር አፈፃፀም በኃላፊነት የሚመራው ለቦርዱ አጠቃላይ መመሪያ ተገዢ በሆነው ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ነው። በተጨማሪም ዋና ዳይሬክተሩ ከአካዳሚው ጋር ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ተቋማትና ድርጅቶች ጋር መልካም የሥራ ግንኙነት እንዲመሠረት ያደርጋል። ጽ/ቤቱ የአካዳሚውን የዕለት ከዕለት ተግባራት የማከናወን ኃላፊነት አለበት።

የአካዳሚው መደበኛ አባላት በሙያቸው ባበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ በጠቅላላ ጉባዔው የሚመረጡ በአገር ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡

1.1. ተቋማዊ አስተዳደርና አደረጃጀት

ጠቅላላጉባኤ

የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ

ዋና ፅ/ቤት(የሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር)

ፕሮግራምና ፕሮጀክት

የሥራ ቡድኖች

ግብርና

ምህንድስናና ቴክኖሎጂ

ጤና

ተፈጥሮ ሳይንስ

ማህበራዊ ሳይንስና ሂዩማኒቲስ

አስተዳደርና ፋይናንስ የሕዝብ ግንኙነትቤተ መፅሐፍትና

ቤተ መዘክር

ቋሚ ኮሚቴ

ገቢ አሰባሳቢ

ሕዝብ ግንኙነት

እጩ አባላት አቅራቢ

የህትመት

ሽልማት

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ድርጅታዊ መዋቅር

Page 11: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

11

አካዳሚው መጀመሪያ በተቋቋመ ማግስት የሚመራበትን የመጀመሪያው የአምስት ዓመት (2003 - 2007) ስትራቴጂክ ዕቅድ አዘጋጀ። ስትራቴጂክ ዕቅዱ የአካዳሚውን ርዕይ፣ ተልዕኮ፣ መሠረታዊ መርሆዎችና ዓላማዎችን፤ እንዲሁም ዋና ዋና መርሃ-ግብሮች ያመለክታል፡፡ በዚህም መሰረት የአካዳሚው ርዕይ በኢትዮጵያ የሳይንስ ዕውቀትንና ባህልን ማሳደግና የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል ሲሆን ተልዕኮው ደግሞ የሳይንስ ባህልና ፈጠራን ማስፋፋትና አገር በቀል ዕውቀትን ጨምሮ የሳይንስ እውቀትን ወደላቀ ደረጃ ማሳደግ ነው። አካዳሚው በ2003 - 2007 ስትራቴጂክ ዕቅዱ የሚከተሉትን ዋና ዋና መርሃ - ግብሮች ለይቶ አስቀምጧል። i. የአካዳሚውን ምንነትና ጠቀሜታ በሚመለከት ያለውን ግንዛቤ ማሳደግና ማጠናከር፤ ii. ወሳኝ በሆኑ ብሔራዊ ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ጥናቶችን ማካሄድና የውይይት መድረኮችን ማመቻቸት፤ iii. ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራን ማበረታታት፤ iv. የላቁ የሳይንስ ተግባራትን ላከናወኑ ሰዎች ዕውቅና መስጠት፤ v. የአካዳሚውን ተቋማዊ አቅም መገንባትና ቀጣይነቱን ማረጋገጥ።

የአካዳሚው ስትራቴጂክ ዕቅድ ትግበራ በሚከተሉት አምስት የአካዳሚው የዘርፍ የሥራ ቡድኖች ይታገዛል ፡-

• የግብርና ሳይንስ • የምህንድስናና ቴክኖሎጂ • የጤና ሳይንስ • የተፈጥሮ ሳይንስና • የማህበራዊ ሳይንስና ሂዩማኒቲስ

በእያንዳንዱ ዘርፍ የተቋቋሙት የሥራ ቡድኖች በስትራቴጂክ ዕቅዱ ከሚመለከተው ዘርፍና ከአካዳሚው ዓላማዎች አንፃር የተቀመጡትን ዋና ዋና መርሃ-ግብሮች ወደ ተግባር የመለወጥ ኃላፊነት ያለባቸው ቋሚ ኮሚቴዎች በመሆን ያገለግላሉ። የዘርፍ ቡድኖቹ ተግባራት ከቦርዱ በተሰጠ የጋራ የስራ ዝርዝር የሚመራ ሲሆን ቦርዱ የእያንዳንዱን ቡድን ስራ የሚመራና የሚያስተባብር ሰብሳቢ ይመድባል፡፡

1.2 የአካዳሚው ስትራቴጂክ ዕቅድ

የማህበራዊ ሳይንስና ሂዩማኒቲስ የጤና ሳይንስ

የተፈጥሮ ሳይንስናየምህንድስናና ቴክኖሎጂየግብርና ሳይንስ

Page 12: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

12

አካዳሚው ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ሲመሰረት፤ ሚያዝያ 2 ቀን 2002 ዓ. ም.፤ አፍሪካ አዳራሽ

Page 13: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

13

አካዳሚው ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ከኢትዮጵያ መንግስትና ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው እህት አካዳሚዎች በተደረገለት የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ ራሱን ለማቋቋምና ተልዕኮውን ለመወጣት ጥረት አድርጓል። በተለይም ከዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚና ከዩናይትድ ኪንግደም ሮያል ሶሳይቲ የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች ልማት ድጋፍ መርሐ ግብሮቻቸው በኩል የጎላ ድጋፍ ተደርጐለታል፡፡ በተደረገለት ድጋፍም አካዳሚው ከተቋቋመበት ጀምሮ በነበሩት ሦስት ዓመታት ውስጥ መሰረታዊ የሆኑ ዓላማዎቹን በማሳካት ረገድ አበረታች ውጤቶችን አስመዝግቧል ለማለት ይቻላል። መጠቀስ ከሚገባቸው ስኬቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው። • እንደተቋቋመ መጠነኛ ሠራተኞችን የያዘና የሥራ ቁሳቁሶች የተሟሉለት ጊዜያዊ ጽ/ ቤት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ - አራት ኪሎ ግቢ ውስጥ መመስረቱ፤ • ሰፊ ግቢ ያለውን የብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደ ሥላሴ የቀድሞ መኖሪያ ቤት በቋሚ ጽ/ ቤትነት እንዲገለገልበት ከመንግሥት በባለአደራነት መረከቡ፤ • የመጀመሪያውን የአካዳሚው የሳይንስ ኮንግረስ በተሣካ ሁኔታ ማካሄዱ፤ • በአገር አቀፍ ደረጃ የቅድሚያ ትኩረት በተሠጣቸው ርዕሶች ላይ የተለያዩ አውደ ጥናቶችን፣ ህዝባዊ ገለፃዎችንና ውይይቶችን ማድረጉ፤ • በማስረጃ ላይ የተመሠረተ የፖሊሲ ምክር ለመንግሥትና ለሌሎች ተቋማት የሚሰጥ አካል ስለመሆኑ ግንዛቤ ተወስዶ በአዋጅ ቁጥር 783/2005 ዕውቅና ማግኘቱ፤ • ዘጠነኛውን ዓመታዊ የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ ማስተናገዱ፤

• ከኢትዮጵያ መንግስት ዓመታዊ የበጀት ድጋፍ ለማግኘት መቻሉ።

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ስኬቶች አካዳሚው በተረጋጋ መሠረት ላይ እንዲቆም ከመርዳታቸውም በላይ ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ ጥረቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ረድተውታል፡፡ ይህ የ2006 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርትም አካዳሚው ከሐምሌ 1/2005 - ሰኔ 30/2006 ዓ.ም. ድረስ ባለው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ባከናወናቸው ተግባራትና ባስመዘገባቸው ውጤቶች ላይ በማተኮር የተዘጋጀ ነው።

1.3 የአካዳሚው ዋና ዋና ስኬቶች

አካዳሚው በዓዋጅ ቁጥር 783/2005 መሰረት ሲመሰረት፤ ሰኔ 13/2005 ዓ.ም፡ አፍሪካ አዳራሽ

Page 14: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

14

አካዳሚው የ2006 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ አዘጋጅቶ ለመተግበር ተንቀሳቅሷል፡፡ ዕቅዱም የአካዳሚውን ዋና ዋና መርሃ-ግብሮች ትግበራና የአቅም ግንባታ እንቅስቃሴዎችን ለመምራትና ከመንግስት የበጀት ድጋፍ ለማግኘት ቁልፍ መሣሪያ ሆኖ አገልግሏል። ዕቅዱን ለመተግበር የተከናወኑት አበይት ተግባራትም የሚከተሉት ነበሩ።

በ 2006 ዓ.ም የበጀት ዓመት

2የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

Page 15: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

15

የማህበራዊ ሳይንስናሂዩማኒቲስ

የጤና ሳይንስ

የተፈጥሮ ሳይንስ

የምህንድስናናቴክኖሎጂ

የግብርና ሳይንስ

የሳይንስ ዘርፍ

ሁሉምዘርፎች

አባላት ተባባሪ አባላት

ድምር

4 2 6

5 1 6

9 14 23

2 13 15

27 33 60

7 3 10

2.1.1 አዳዲስ አባላትን መምረጥ

አካዳሚው በ2006 በጀት ዓመት አዳዲስ መደበኛና ተባባሪ አባላትን በመምረጥ የጠቅላላ አባላቱን ቁጥር ከ79 ወደ 137 አሳድጓል። በተቀመጠው መመሪያ መሰረት የምርጫ መስፈርቱን የሚያሟሉ ዕጩዎች የተጠቆሙት በአመዛኙ በአምስቱ የአካዳሚው የዘርፍ የሥራ ቡድኖች በኩል ነበር። ለምርጫው የተጠቆሙት ዕጩዎች በቦርዱ ተገምግመው በድምሩ 27 መደበኛና 33 ተባባሪ አባላት መጋቢት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. በተካሄደው ሁለተኛው ዓመታዊ የጠቅላላ ጉባኤው መደበኛ ስብሰባ ተመርጠዋል። ከአምስቱ የሳይንስ ዘርፎች የተመረጡት አዲስ መደበኛና ተባባሪ አባላት ዝርዝር፣ የትምህርት ደረጃና ዘርፋቸው በአባሪነት የተያዘ ሲሆን ማጠቃለያው ከዚህ በታች የተመለከተው ነው፡፡

የአካዳሚውን አባላት ቁጥር ማሳደግ በዋናነት የአካዳሚውን የሰው ሃይል ብቃት ባላቸው ምሁራን ለማጠናከር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በትምህርት፣ በምርምርና በተቋም አቅም ግንባታ ረገድ ለተበረከቱ የላቁ አስተዋፅዖዎች እውቅና መስጠቱ በተለያዩ የሳይንስ ዘርፍች የተሰማሩ ወጣት ምሁራንን እንደሚያነቃቃና እንደሚያተጋ ይታመናል።

2.1አካዳሚውን በሚመለከት ያለውን ግንዛቤ ማሳደግና ጠቀሜታውን ማጠናከር

Page 16: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

16

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የድህረ-ምረቃ ትምህርት በሚሰጥባቸው ዩኒቨርስቲዎችና በምርምር ተቋማት የወጣቶችን የሳይንስ መድረክ ለመመሥረት ፕሮጀክት ነድፎ ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ ተንቀሳቅሷል። ፕሮጀክቱ በዩናይት ኪንግደም ሮያል ሶሳይቲ ድጋፍ የተካሄደ ሲሆን መድረኮቹን ለመመሥረት እንዲቻል ቀደም ሲል በሰባት ዩኒቨርስቲዎች ከወጣት ምሁራን ጋር የምክክር ስብሰባዎችን አካሂዷል። ውይይት የተካሄደባቸው ዩኒቨርስቲዎችም አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ባህርዳር፣ ጐንደር፣ ጅማ፣ ሀረማያና ሃዋሳ ናቸው። በስብሰባዎቹ የወጣቶችን የሳይንስ መድረክ መቋቋም አስፈላጊነት፣ እንዲሁም እንዴት እንደሚመሠረትና እንደሚሰራ ውይይት ተደርጓል። የአካዳሚው ተወካዮችም ጉዳዩን ከዩኒቨርስቲ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር ተወያይተውበታል፡፡ በሁሉም የምክክር ስብሰባዎች ላይ ወጣት ምሁራኑ የራሳቸው የሆነ ስለ ሳይንስና ምርምር የሚወያዩበትና መረጃዎችንና ልምዶቻቸውን የሚለዋወጡበት መድረክ እንዲኖራቸው ጥልቅ ፍላጐት እንዳላቸው ለመገንዘብ ተችሏል። በተጨማሪም የሚፈጠሩት የወጣት ሳይንስ መድረኮች የወደፊቱ የአገሪቷ ተመራማሪ ምሁራን መፍለቂያና የአካዳሚው ተተኪ አባላት ምንጭ የመሆን ዓቅም ሊኖራቸው እንደሚችል ግንዛቤ ተወስዷል፡፡

ከእያንዳንዱ የምክክር ስብሰባ የተገኘው ዋናው ውጤት በየዩኒቨርስቲዎቹ ሊመሰረት የታሰበውን የወጣቶች ሳይንስ መድረክ የሚያደራጅ መስራች ኮሚቴ ማቋቋም ነበር፡፡ የመስራች ኮሚቴው አባላት በየዩንቨርስቲዎቹ ወጣት ምሁራንና በአካዳሚው መካከል እንደ አገናኝ ድልድይ ሆነው እንደሚያገለግሉ ታሳቢ ተደርጎ የነበረ

ቢሆንም ከሁሉም የመሥራች ኮሚቴዎች ውስጥ በተፈለገው አቅጣጫ በመንቀሳቀስ የወጣቶች የሳይንስ መድረክን ሐምሌ 18 ቀን 2005 ዓ.ም. ለመመስረት የበቃው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መሥራች ኮሚቴ ብቻ ነበር።

አካዳሚው ከዚህ በመነሳት የወጣቶች የሳይንስ መድረኮች ቀጣይነት ሊኖራቸው የሚችለው ሊያሰባስባቸው የሚችል አንድ ጥላ ሲኖር ብቻ እንደሆነ ግንዛቤ ወስዷል።

ይህንን ተግባራዊ ለማድረግም የኢትዮጵያ ወጣቶች ሳይንስ አካዳሚን በአገር-አቀፍ ደረጃ የመመስረቱን ተነሳሽነት ወስዷል። ለዚህ ሥራ ማስፈጸሚያም ከዩናይትድ ኪንግደም ሮያል ሶሳይቲ የአፍሪካ አካዳሚዎች ፕሮግራም ድጋፍ ተገኝቷል።

ዕቅዱን ለማሳካትም አካዳሚው በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና የምርምር ተቋማት ውስጥ ከሚገኙ ወጣት ምሁራን ጋር ውይይትና ግንኙነት በማድረግ ላይ ይገኛል። ለሚመሠረተው የወጣቶች ሳይንስ አካዳሚም አስፈላጊውን ድጋፍና የጽ/ቤት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ለምስረታው በአካዳሚው ጽ/ቤትና በአምስቱ የሥራ ዘርፍ ቡድኖች የተዘጋጁ መመዘኛ መስፍርቶች ፀድቀዋል። የመሥራች አባላቱ ምርጫም እስከ ጥር 2007 ዓ.ም. ድረስ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል። ዕድሜያቸው 42 ዓመትና እና ከዚያ በታች የሆኑ፣ የፒኤችዲ ዲግሪ ያላቸውና በምርምር ተግባር የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ወጣት ምሁራን ለኢትዮጵያ ወጣት አካዳሚ መሥራች አባልነት በዕጩነት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

2.1.2 የኢትዮጵያ ወጣት ሳይንስ አካዳሚን መመሥረት

Page 17: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

17

2.2.1. የአካዳሚውን ዋና ጽ/ቤት ማስጐብኘት

በ2006 ዓ.ም. የአካዳሚው የአገር ውስጥና የውጭ አገር አጋሮችና ባለድርሻ ተቋማት በጉለሌ የሚገኘውን ዋና ጽ/ቤት እንዲጐበኙ ተደርጓል። አበይት ከሆኑት የሥራ ጉብኝቶች መካከል በኢንተር አካዳሚ ካውንስል (IAC) የተሰየመው የባለሙያዎች ቡድን በመጋቢት ወር ያደረገው ጉብኝት ይጠቀሳል። ቡድኑ አካዳሚውን ከመጋቢት 22 - 23 ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስ የጐበኘ ሲሆን በዚህ ጊዜም የአሜሪካ ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎችን ልማት ድጋፍ ፕሮግራም ለአካዳሚው የሰጠውን የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ አተገባበር፣ ያስገኘውን ውጤትና ያመጣውን ለውጥ ገምግሟል። ቡድኑ ከአካዳሚው አመራር አባላትና ከአካዳሚው ጋር በቅርብ ከሚሰሩ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ዋነኛ አጋሮች ጋር ውይይት በማድረግ አካዳሚው ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የደረሰበትን ደረጃና ያስመዘገበውን ተጨባጭ ውጤት መርምሯል። ቡድኑ ተመሳሳይ ግምገማ በጋና፣ ካሜሩን፣ ዩጋንዳና ደቡብ አፍሪካ አካሂዷል።

2.2 የአካዳሚውን እንቅስቃሴዎች ማሳደግ

Page 18: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

18

የአካዳሚው ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንት ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ ከህዳር 14-15 ቀን 2006 ዓ.ም. በለንደን በተካሄደው ዓለም-አቀፍ የዕውቀት ልውውጥ ኮንፈረንስ (G-KEN) ተሳትፈዋል። አብዛኞቹ የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች በለንደን የሚገኙ የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አባላት ሲሆኑ፣ ሁለት ከደቡብ አፍሪካ፣ አንድ ከጀርመንና አምስት ከኢትዮጵያ የተጋዙ እንግዶችም ተሳትፈዋል። ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ በተጨማሪም በዩጋንዳ ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ አስተናጋጅነት በካምፓላ በሚዘጋጀው 10ኛው የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች ዓመታዊ ጉባኤ የዝግጅት ስብሰባዎች አካዳሚውን በመወከል ተካፍለዋል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ፕ/ር ሽብሩ ተድላ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገሮች የሳይንስ ካውንስል አውደ-ጥናት ላይ ከህዳር 17-18 ቀን 2006 ዓ.ም. ተሳትፈዋል።

የኢ.ሳ.አ. አመራር አባላት በተለያዩ አገሮች አካዳሚውን በመወከል የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በዚህም ከተለያዩ አካዳሚዎችና ተቋማት ልምድ ለመቅሰምና ከአካዳሚው የሚጠበቀውን ድርሻ ለማበርከት ተችሏል፡፡ ሪፖርቱ በሚሸፍነው ጊዜ ውስጥ የተደረጉት ዋና ዋና ጉብኝቶች የሚከተሉት ነበሩ።

2.2.2. የኢ.ሳ.አ. ተወካዮች የውጭ አገር ጉብኝት

Page 19: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

19

የአካዳሚው ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ፕ/ር ማስረሻ ፈጠነ ከሚያዚያ 27 እስከ ግንቦት 3 ቀን 2006 ድረስ በደቡብ አፍሪካ የሳይንስ አካዳሚ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አድርገዋል፡፡የጉብኝቱ ዋና ዓላማም የደቡብ አፍሪካን የሳይንስ አካዳሚ አደረጃጀት፣ የአባላት ጥንቅር፣ የመግባቢያ ጥናቶችንና ሌሎች ፕርግራሞችን መቃኘትና ጠቃሚ ልምድ መቅሰም ነበር፡፡

በናይሮቢ፣ ኬንያ ከጥር 25-28 ቀን 2006 ዓ.ም. በተደረገው የዓለም-አቀፍ የወጣቶች አካዳሚ ኮንፈረንስ ላይ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በዋና ዳይሬክተሩ ፕ/ር ማስረሻ ፈጠነ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የወጣቶች ሳይንስ መድረክ ሰብሳቢ በአቶ ማንይንገረው ሸንቁጥ ተወክሏል። ቡድኑ የኢትዮጵያን ወጣት ሳይንስ አካዳሚ ለመመስረት የሚያስችል ጠቃሚ ልምድና መረጃ አግኝቷል።

ፕ/ር ፅጌ ገ/ማርያም በባንጋሎር፣ህንድ ከህዳር 12-14 ቀን 2006 ዓ.ም. በተደረገው የዓለም ሳይንስ አካዳሚዎች ስብሰባ ተካፍለዋል። የስብሰባው መሪ ርዕስ "በማደግ ላይ ያሉ አገሮች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተግዳሮትና መልካም-አጋጣሚ" የሚል ነበር። ከስብሰባው ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽንን ለአገር ዕድገት ለማዋል ስለሚቻልበት ትምህርት ተወስዷል።

Page 20: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

20

አካዳሚው ከስትራቴጂክ ዕቅዱና ከመንግስት ተቋማት ከሚቀርብለት ጥያቄ በመነሳት የተለያዩ የጋራ መግባቢያ ጥናቶችን በማካሄድ ላይ ይገኛል። በጥናቶቹ ላይ አግባብነት ያላቸው የአካዳሚው አባል የሆኑ ወይም ያልሆኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች ይሳተፋሉ። የጥናት ግኝቶቹ ተጠናቀው ከመታተማቸው በፊትም በረቂቅ ሪፖርቶቹ ላይ ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት እንዲወያዩባቸው ይደረጋል። የቅድሚያ ትኩረት በተሰጣቸው ብሔራዊ ጉዳዮች ላይ አካዳሚው በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸው የመግባቢያ ጥናቶችና የአቅም ግንባታ ተግባራት የሚከተሉት ነበሩ።

2.3.1 የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ፓናል (መድረክ) ምሥረታ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመሆን በእንግሊዝ፣ በኖርዌይና በዴንማርክ መንግስታት ከሚደገፍ የስትራቴጂክ የአየር ንብረት ተቋማት ግንባታ ማዕቀፍ "የአካባቢ አገልግሎትና የአየር ንብረት ለውጥ ትንተና " ለተሰኘ ፕሮግራም የ18 ወራት የገንዘብ ድጋፍ አግኝቷል። አካዳሚው ፕሮግራሙን የሚተገብረው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአፍሪቃ ቀንድ የአካባቢ መረብና የአየር ንብረት ሳይንስ ማዕከል ጋር በመተባበር ነው። በዋናነትም የኢትዮጵያን የአየር ንብረት ለውጥ ክትትል መድረክ የመመስረቱን ኃላፊነት ወስዷል። መድረኩ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ከአየር ንብረት ጋር በተያያዘ በአገሪቷ የሚታየውን አካባቢያዊ ለውጥ እንዲከታተሉ የሚያስችላቸውን መረጃ እየተነተኑ የሚያቀርቡ የተለያዩ ባለሙያዎችን ያካተተ ሲሆን፤የአየር ንብረት ለውጥን መሠረት ያደረገውን የሀገሪቱን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ስትራቴጂ ትግበራ የሚደግፉ እርምጃዎች

እንዲወሰዱ ለማድረግ እንደሚያግዝ ይታመናል።

ወሳኝ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይየጋራ መግባቢያ ጥናቶችን ማካሄድና

መድረኮችን ማዘጋጀት2.3

የፓናሉ ምስረታ ዓውደ ጥናት

Page 21: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

21

የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ፓናል (EPCC) በራሱ የምርምር ሥራ አይሰራም፤ ከአየር ንብረት ጋር ወይንም ተያያዥ ከሆኑ ክስተቶች ጋር ያሉ የክትትል ሥራዎችንም አያከናውንም። የፓናሉ ባለሙያዎች ግምገማ የሚመሰረተውም በዋናነት ለህትመት በበቁ ሳይንሳዊ ፅሁፎች በተዘገቡ ግኝቶች ላይ ይሆናል። ከተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የሚውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች በፓናሉ በሪፖርት አዘጋጅነት፣ በግብአት ሰጪነትና ገምጋሚነት በፈቃደኝነት እንዲያገለግሉ ይጠበቃል። ውጤቱም በልማት ዘርፍና በሳይንስ ማህበረሰብ መካከል የተቀናጀ አሰራር በመፍጠር ከአየር ንብረት ለውጥ ክትትል ጋር በተያዘ የተጠናቀሩ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ለውሳኔ ሰጪ አካላት የሚያቀርብ የተደራጀ የመረጃ ቋት ይሆናል።

አካዳሚው የፕሮጀክት አስተባባሪና የሚስፈልጉትን ሌሎች ሰራተኞች በመቅጠር የፕሮጀክቱን አስፈፃሚ ጽ/ቤት አቋቁሟል። ጽ/ቤቱም በአካዳሚው ዋና ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፤ የፕሮጀክቱን በይፋ ሥራ መጀመር የሚያበስር አውደ-ጥናት ከየካቲት 20 - 21 ቀን 2006 ዓ.ም አካሂዷል።

የፓናሉ ምስረታ ዓውደ ጥናት ተሳታፊዎች

Page 22: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

22

በአገሪቷ በአጠቃላይ የአየር ንብረት ለውጥን በሚመለከት የሚካሄዱ ምርምሮችን በመቃኘት ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ የገመገመ ጥናት ተደርጎ ከዋና ዋና ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገው ውይይት የተሰጡ ግብረ-ምላሾች የተካተቱበት የግምገማ ሪፖርት ተጠናቅሯል።

2.3.2 የብሔራዊ ምርምር ምክር ቤት የጋራ መግባቢያ ጥናት

በ2004 ዓ.ም. የወጣው ብሔራዊ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ የአገሪቷን የምርምር አቅም ለማጠናከርና ፈጠራንና ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን ለማላመድ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማጐልበት ብሔራዊ የምርምር ም/ቤት እንደሚመሰረት ያመለክታል። በፖሊሲው መሰረት የተቋቋመው ብሔራዊ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ምክር ቤትም ለጉዳዩ በሰጠው የቅድሚያ ትኩረት የምርምር ምክር ቤቱ ተመሥርቷል። ለምክር ቤቱ ማቋቋሚያ ሰነድ ዝግጅት ከአካዳሚው ግብዓት የተሰጠ ሲሆን የም/ቤቱን አደረጃጀትና አሠራር ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ እንዲረዳ አካዳሚው ‘የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርምር ምክር ቤት’ በሚል ርዕስ የመግባቢያ ጥናት በማካሄድ ላይ ይገኛል። ለሥራው ማከናወኛም ከዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች የድጋፍ ፕሮግራም 50‚000 ዶላር፣ ከስዊድን ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (SIDA) ደግሞ 1.6 ሚሊዮን ብር ተገኝቷል።

አካዳሚው ጥናቱን ለማካሄድ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጣ የአካዳሚውን አባላት ያካተተ የከፍተኛ ባለሙያዎች ቡድን መሥርቷል። ቡድኑም የጋራ መግባቢያ ጥናቱ ለምርምር ም/ቤቱ አመሠራረት ያሉትን አማራጮች እና አደረጃጀቱ ምን መምሰል እንዳለበት፤ እንዲሁም የባለድርሻ አካላትን አስተዋጾኦ ለማመልከት የሚያስችሉ ጠቋሚ ሐሳቦችን ለማመንጨት እየሠራ ይገኛል።

ለፓናሉ ሥራ የቴክኒክ ድጋፍ የሚሰጡ የማስተባበሪያ አሃዶች ተለይተው የቴክኒክ ቡድኖቹን ለመደገፍ ስምምነታቸውን ገልፀዋል። የቴክኒክ ቡድኖቹ አባላትም ከእያንዳንዱ ዘርፍ ሂደቱን ለማሳለጥ የተመረጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ናቸው።

ስድሳ ከሚሆኑ መሪ አዘጋጆች፣ አዘጋጆችና ገምጋሚ አርታኢዎች ጋር ስምምነት ተፈርሟል።

የፓናሉ ድረ-ገፅና ፌስ ቡክ ተከፍተው የፕሮጀክቱን እንቅስቃሴዎች ለማስተዋወቅ እያገለገሉ ይገኛል።

ፓናሉን ለመመሥረት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አስፈላጊ የሆኑትን ትብብሮች በሚመለከት ከተለያዩ መ/ቤቶች ጋር ምክክር ተካሂዷል። ከነዚህም መካከል ብሔራዊ ሜትዮሮሎጂ ኤጀንሲ፤ የአካባቢና ደን ሚኒስቴር፤እና የውሃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስቴር ይገኙበታል።

የፓናሉ ተግባራት በፕሮጀክቱ በፀደቀው የሥራ ዕቅድ መሠረት የሚካሄዱ ሲሆን የተከናወኑት ዋና ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው።

Page 23: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

23

• በሀገሪቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ አሁን ያለውን የሰው ሃብት ፍላጐትና አቅርቦት ገምግሞ የሚሻሻልበትን ምክረ-ሀሳብ ማመንጨት፤

• በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ሥራ ላይ ከዋለው የ70፡30 የትምህርትና ስልጠና ድልድል ፖሊሲ ጋር በተያያዘ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰው ሃብት ፍላጐትና አቅርቦት ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ምን መሆን እንዳለበት ትንታኔ ማቅረብ፤

• በአገሪቱ የምርትና የአገልግሎት የኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ የሚታዩ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰው ሃብት ፍላጐትና አቅርቦት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሁኔታዎችን መመርመር፤

• ለኢንዱስትሪው ዘርፍ ወደፊት የሚያስፈልገውንና ሊቀርብ የሚችለውን የሰው ሃብት ለማመጣጠን የሚያስችል ስትራቴጂ መንደፍ፤ በዚህም የአገሪቷን የትምህርትና ፖሊሲ ሥልጠና የወደፊት አቅጣጫ ማመላከት።

በተጨማሪም ቡድኑ በመንግስት የተቋቋመውን ብሔራዊ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ም/ቤት ለማገዝ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የምርምር ም/ቤቱን መመስረቻ መመሪያ በማዘጋጀት ተሳትፏል። አግባብነትና ዘላቂነት ያለው የምርምር ም/ቤት አወቃቀርና አሠራር እንዲኖር ለማስቻልም በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ምክረ-ሀሳብ ለማቅረብ ተግቶ እየሰራ ይገኛል።

ቡድኑ ከጥናቱ ጋር በተያያዘ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይ ሀገራዊውን የምርምር ገጽታ ግምገማ አጠናቋል። ይህም በጥናቱ ማጠቃለያ ላይ ለሚቀርበው ምክረ-ሀሳብ መሠረት ሆኖ የሚያገለግል ይሆናል። ቡድኑ አጠቃላይ ስራውን እያገባደደ ሲሆን የጥናቱ የመጨረሻ ሪፖርት ተጠቃሎ በጥቅምት ወር 2007 ዓ.ም. የባለድርሻ አካላትን የሚያወያይ አውደ-ጥናት ለማካሄድ ዕቅድ ተይዟል።

2.3.3 የኢትዮጵያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰው ሃብት ፍላጐትና አቅርቦት ጥናት

በኢትዮጵያ ያለውን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሰው ኃይል ፍላጐትና አቅርቦት ለማጥናት ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በቀረበለት ጥያቄ መሠረት አካዳሚው በ2006 በጀት ዓመት አጋማሽ ላይ እንቅስቃሴ ጀምሯል። የጥናቱ ዋና ዓላማ በምርትና አገልግሎት ሰጪ ዘርፎች ባለው የሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰው ሃብት ፍላጐትና አቅርቦት ውጤት ላይ በመመርኮዝ በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት የሚያስፈልገውን መተንበይ ነው። የጥናቱ ዝርዝር ዓላማዎችም የሚከተሉት ናቸው።

አካዳሚው ለዚህ ጥናት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከአባላቱ መካከልና ውጪ በጉዳዩ ላይ የላቀ ዕውቀትና ልምድ ያላቸውን ከፍተኛ ባለሙያዎች ያሰባሰበ የጥናት ቡድን አቋቁሟል። የጥናቱ ውጤትም ለአገሪቱ የሰው ሃብት ልማት ስትራቴጂና ዕቅድ መጠናከርና መተግበር የጎላ አስተዋፅዖ ሊያደርግ የሚችል ሰነድ እንደሚሆን ይጠበቃል።

አካዳሚው ጥናቱን ለማካሄድ የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር የተፈራረመ ሲሆን ጥናቱ በ2007 በጀት ዓመት አጋማሽ ላይ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል። እስካሁን በተደረገው እንቅስቃሴ የጥናት ቡድኑ የመጀመሪያውን ሪፖርት በሚኒስቴሩ ለተቋቋመውና የተለያዩ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ተወካዮችን በአባልነት ለያዘው የቴክኒክ ኮሚቴ በማቅረብ የጥናቱን አካሄድና የሚጠበቀውን ውጤት አስገምግሟል። ከተለያዩ ምንጮች መረጃዎችን የማሰባሰቡ ሥራም የፍላጐትና አቅርቦት ሁኔታውን ለይተው እንዲቃኙ በተቋቋሙት ሁለት ንዑስ ቡድኖች እየተካሄደ ይገኛል።

2.3.4 የሳይንስ መሣሪያዎች ፖሊሲና የምርምር ሥራ በኢትዮጵያ ያለበትን ሁኔታ የሚገመግም ጥናት

የስዊድኑ ዓለም-አቀፍ የሳይንስ ፋውንዴሽንና የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚ “ውጤታማ የሳይንስ መሣሪያዎች ፖሊሲን በአፍሪካ ማጐልበት” በሚል ርዕስ የጋራ ፕሮጀክት ቀርጸው በመተግበር ላይ ይገኛሉ። የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ ቁልፍ የሚባሉ የምርምር ተቋማት የሚያካሂዷቸውን የምርምር ተግባራት መዳሰስና ከተቋማዊ አወቃቀራቸው ጋር በተያያዘ የሳይንስ መሣሪያዎች ያሉበትን ሁኔታበመገምገም የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ማመላከት ነው። ለአብነትም ሦስት የአፍሪካ አገራት (ኢትዮጵያ፣ ጋናና ኬንያ) ተመርጠው ዝርዝር ጥናት እንዲካሄድ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚም ከብሔራዊ የሥነ-ልክ (ሜትሮሎጂ) ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን ከስዊድን ዓለም አቀፍ የሳይንስ ፋውንዴሽንና ከአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚ በቀረበለት ጥያቄ መሠረት የአገር ውስጥ ጥናት አካሂዷል። በዚህም መሠረት በአገሪቱ ያለው የሳይንስ መሣሪያዎችና የምርምር ሁኔታ በአብዛኛው ፖሊሲ-ነክ ጉዳዮችን በሚያመላክት መልኩ ተጠንቷል። ጥናቱን ለማካሄድና በውጤቱ ላይ የሁለት ቀን የባለድርሻ አካላት ብሔራዊ የምክክር አውደ-ጥናት ለማካሄድ የፋይናንስ ድጋፍ የሰጠው የስዊድኑ ዓለም አቀፍ የሳይንስ ፋውንዴሽን ነበር። ጥናቱ በአገሪቱ የቅድሚያ ትኩረት የተሰጣቸውን የምርምር መስኮች፣ በሥራ ላይ ያሉትን ልዩ ልዩ ፖሊሲዎች፣ የሳይንስ መሣሪያዎችን በሚመለከት በሥራ ላይ ያሉትን መመሪያዎችና ህጐች፣ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች የታዩ የፖሊሲ ተሞክሮዎችን በአገር ደረጃ ቃኝቷል።

Page 24: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

24

ጥናቱ የተካሄደው በዋናነት አግባብነት ያላቸውን ሰነዶች በመፈተሽና ዋና ዋና በሚባሉ ተቋማት ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን ባለሙያዎችና የሥራ ኃላፊዎች ቃለ-መጠይቅ በማድረግ የተሰበሰቡ መረጃዎችን በመተንተን ነበር። በጥናቱ የተካተቱት ተቋማትም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ሃረማያ ዩኒቨርስቲ፣ ጅማ ዩኒቨርስቲ፣ ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ፣ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ፣ መቀሌ ዩኒቨርስቲ፣ ሃዋሳ ዩኒቨርስቲ እና ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትና የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ነበሩ።

ጥናቱ በሳይንስ መሣሪያዎች አመራረጥ፣ አገባብ፣ አጠቃቀም፣ ጥገናና አወጋገድ ሂደት የሚታዩትን ዋና ዋና የሚባሉ ችግሮች ለይቷል። ችግሮቹ መሳሪያዎቹ በግዢ ወይም በስጦታ ከሚገኙበት አንስቶ አገልግሎት ሰጥተው እስከሚወገዱበት ጊዜ ድረስ ባሉት ደረጃዎች በሙሉ እንደሚዘልቁ ለመረዳት ተችሏል፡፡

እንዲሁም ጥናቱ መሣሪያዎቹ ከሚመረጡበት አንስቶ እስከ ሚወገዱበት ድረስ ባለው ሒደት ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ በፖሊሲ አውጪዎችና በየተቋማቱ መሪዎች ሊተገብሩ የሚገባቸውን የመፍትሄ ሀሳቦች ጠቁሟል። ከነዚህም መካከል መሣሪያዎቹ የሚመረጡበት፣ የሚገዙበት፣ ጥቅም ላይ የሚውሉበትና የሚወገዱበት ደረጃውን የጠበቀ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል በተቋምም ሆነ በብሔራዊ ደረጃ የሳይንስ መሣሪያዎችን ማዕከል ማቋቋም በዋና የመፍትሄ ሀሳብነት ተጠቁሟል። የሳይንስ መሣሪያዎች በግዢና በስጦታ በሚገኙበት ወቅት ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን፣ አስተዳደራቸውን፣ አወጋገዳቸውን፣ ጥገናቸውን፣ እንዲሁም የሰነድ አያያዝንና የሰው ኃይል ልማትን ያካተተ ሁሉን-አቀፍ ብሔራዊ የሳይንስ መሣሪያዎች ፖሊሲ ማዕቀፍ መውጣት እንዳለበትም ጥናቱ ይጠቁማል።

የጥናቱ የማጠቃለያ ሪፖርት ለዓለም አቀፍ የሳይንስ ፋውንዴሽን ቀርቦ በፋውንዴሽኑ ድረ-ገፅ ላይ ተጭኗል። ዓለም-አቀፍ የሳይንስ ፋውንዴሽንና የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚም የሦስቱን አገሮች ጥናቶች መሠረት በማድረግ የፖሊሲ አቅጣጫ ጠቋሚ ፅሁፍ በተለይም በሦስቱ አገራት ፖሊሲ አውጪዎችና በአፍሪካ ህብረት ላይ በማተኮር አዘጋጅተዋል።

Page 25: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

25

2.4.1 ዘጠነኛው የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች ዓመታዊ ጉባኤና ተጓዳኝ ሁነቶች

ኢ.ሳ.አ. ዘጠነኛውን የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች ዓመታዊ ጉባኤ እ.አ.አ. ከታህሳስ 9 - 12 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አስተናግዷል። የስብሰባው ዋነኛ ትኩረትም "ባዮቴክኖሎጂ ለአፍሪካ ልማት ያለው ሚና" የሚል ነበር። የጉባኤው ዝግጅት የተጀመረው በ 2005 በጀት ዓመት ብሔራዊ አዘጋጅ ኮሚቴ በመመስረት ሲሆን ዝግጅቱን በበላይነት ለመምራት ከስምንት የአፍሪካ የሳይንስ አካዳሚዎች የተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎችን በአባልነት የያዘ ዓለም-አቀፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ተመስርቷል። በኮሚቴው የተወከሉት ሀገሮችም ካሜሩን፣ ኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪካና ዩጋንዳ ነበሩ።

ዓለም አቀፍ ኮሚቴው የመጀመሪያውን ስብሰባ ከጥቅምት 08 - 09/2005 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በማካሄድ የጉባኤው ጭብጥ ‘ባዮቴክኖሎጂ ለአፍሪካ ልማት’ እንዲሆን ወስኗል። ከኢትዮጵያ፣ ከኬንያ፣ ከዩጋንዳ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከናይጄሪያ፣ ከዴንማርክና ከአሜሪካ ሰባት ታዋቂ ሳይንቲስቶች በጉባኤው እንዲናገሩ በዚሁ ስብሰባ ተመርጠዋል። ሁለተኛው የዓለም አቀፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ደግሞ ከግንቦት 26-30 ቀን 2005 ዓ.ም. በጣልያን ቤላጂዮ በሚገኘው የሮክፌለር የስብሰባ ማዕከል ተደርጎ የጉባኤው ዝርዝር ይዘት ተወስኗል።

ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽንን ማበረታታት

2.4

ከዓለም አቀፍ አዘጋጅ ኮሚቴው ስብሰባዎች አንዱ፤ ቤላጂዮ፣ ጣሊያን፤ ከግንቦት 26 - 30 ቀን 2005 ዓ. ም

ብሔራዊ አዘጋጅ ኮሚቴው በሥራ ላይ

Page 26: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

26

ተ.ቁ ርዕስ አቅራቢ

1

2

3

የቴክኖሎጂ አብዮቶችና አፍሪካ

የባዮቴክኖሎጂ ምንነት፣ ታሪካዊ አመጣጥና ሂደቱ

የባዮቴክኖሎጂ ሚና በግብርናው ዘርፍ

ፕ/ር ማስረሻ ፈጠነ (ከኢ.ሳ.አ.)

ፕ/ር እንዳሻው በቀለ (ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ)

ዶ/ር በላይነህ አድማሱ (ከኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት)

4

5

6

የጤና ባዮቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን በኢትዮጵያ

ባዮቴክኖሎጂና ደህንነተ-ሕይወት

የባዮቴክኖሎጂ ፖሊሲ አስፈላጊነት

ዶ/ር አብርሃም አሰፋ (ከአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት)

ዶ/ር አዳነ አብርሃም (ከኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት)

ዶ/ር እሌኒ ሺፈራው (ከኢትዮጵያ ብዝሃ-ሕይወት ኢንስቲትዩት)

ሠንጠረዥ 2 - የሕዝባዊ ገለፃንና ውይይቱ አርዕስትና አቅራቢዎቹ

ቅድመ-ጉባኤ ህዝባዊ ገለፃና ውይይት

አካዳሚው ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ባገኘው ድጋፍ እና ከኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ተቋም ጋር በመሰረተው ትብብር ከዋናው የህዳር ወር 2006 ዓ.ም. የባዮቴክኖሎጂ ጉባኤ ቀደም ብሎ የህዝባዊ ገለፃና ውይይት መድረኮችን በተለያዩ የባዮቴክኖሎጂ አርዕስት ላይ አካሂዷል። የሕዝባዊ ውይይትና ገለፃ መድረኮቹ አጠቃላይ ዓላማ ባዮቴክኖሎጂ ለልማት ስላለው ጠቀሜታ መሠረታዊ ዕውቀት ማስጨበጥ ሲሆን፤ አካዳሚው ሳይንሳዊ መረጃዎችን ለተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ለማድረስ የሚስችለውን አቅም በማዳበር ላይ ያተኮረ ነበር።

በዚህም መሠረት ስድስት ተከታታይ ወርሃዊ መድረኮች ተዘጋጅተው ገለፃዎች በከፍተኛ ባለሙያዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል (ሠንጠረዥ 2)፡፡ በአጠቃላይ 887 የሚሆኑ የተለያየ ሙያ ያላቸው ግለሰቦች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴያትር አዳራሽ በተካሄዱት በስድስቱ መድረኮች ተካፍለዋል። ተሳታፊዎቹ የመንግስት ባለሥልጣናት፣ ፖሊሲ አውጭዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን፤ የምርምር ተቋማት፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራንና ተማሪዎች፤ እንዲሁም ከአጠቃላይ የማህበረሰቡ ክፍል የመጡ ነበሩ። ከስድስቱ መድረኮች የመጨረሻዎቹ ሁለቱ የተካሄዱት በ2006 የመጀመሪያው ሩብ የበጀት ዓመት ነበር።

Page 27: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

27

ከገለፃና ውይይት መድረኮቹ በተጨማሪ መስከረም 4 ቀን 2006 ዓ.ም. የፓርላማ አባላትና ሌሎች ፓሊሲ አውጪዎች የተሳተፉበት የአንድ ቀን አውደ-ጥናት ተካሂዷል። በአውደ-ጥናቱ ባዮቴክኖሎጂን በሚመለከቱ የተለያዩ ሕግ-ነክና የፖሊሲ ጉዳዮች፤ እንዲሁም ቴክኖሎጂው ለአገር ልማት የሚያደርገውን አስተዋፅኦ ለማጠናከር በአገር ደረጃ መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች ውይይት ተደርጓል።

በተከታታይ ለስድስት ወራት በተካሄዱት የህዝባዊ ውይይትና ገለፃ መድረኮች የቀረቡትን ጥናታዊ ጽሑፎችና የተደረጉትን ውይይቶች ያካተተ አንድ መፅሐፍ በአማርኛ ቋንቋ ታትሞ ለተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች ተሰራጭቷል። የገለፃና ውይይት መድረኮቹ ዋና ዋና ጭብጦችም በእንግሊዘኛ ቋንቋ ታትመው ለዓለም-አቀፉ የህዳር 2006 የባዮቴክኖሎጂ ጉባኤ ተሰራጭተዋል። የገለፃና የውይይት መድረኮቹን ዝግጅት መጠናቀቅ አስመልክቶ በኢ.ሳ.አ. ዋና ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ በመድረኮቹ ተሳታፊ ለነበሩ እንግዶች የገለፃና የውይይቶቹን ፅሁፎች የያዙ ሲዲዎች ተሰጥተዋል።

የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች ልማት ፕሮግራም

/ASADI/ ቦርድ ስብሰባ

የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች ልማት ፕሮግራም ቦርድ ዓመታዊ ስብሰባ እ.አ.አ ከሕዳር 9 – 10 ቀን 2013 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ተካሂዷል፡፡ ስብሰባው በቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ድጋፍ የሚካሄደውን የአፍሪካ አካዳሚዎች ልማት የድጋፍ ፕሮግራም የ 10 ዓመት አፈፃፀም በመገምገም ላይ ያተኮረ ነበር። የኢ.ሳ.አ. ፕሬዝዳንት ፕ/ር ደምሴ ሀብቴና በወቅቱ ም/ፕሬዝደንት የነበሩት ፕ/ር ማስረሻ ፈጠነ በስብሰባው ላይ ተገኝተው አካዳሚው ከተመሠረተበት ከ2002 ዓ.ም. ጀምሮ ያከናወናቸውን ተግባራትና የተገኙትን ዋና ዋና ውጤቶች በሚመለከት ሪፖርት አቅርበዋል። በዚህም የቦርዱ አባላትና የሌሎች አካዳሚዎች ተወካዮች ኢ.ሳ.አ. በተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ ጠቀሜታውን በሚመለከት ግንዛቤ ለመፍጠርና ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ ያደረገውን ጥረት በሚመለከት ግንዛቤ አግኝተዋል።

Page 28: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

28

‘ባዮቴክኖሎጂ ለአፍሪካ ልማት’ ዓለም-አቀፍ ጉባኤ

‘ባዮቴክኖሎጂ ለአፍሪካ ልማት’ በሚል ጭብጥ የተካሄደው ዓለም-አቀፍ ጉባኤ ህዳር 10 ቀን 2006 ዓ.ም. በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠ/ሚኒስትር በክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የተከፈተ ሲሆን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ የተከናወነው በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አፍሪካ አዳራሽ ውስጥ ነበር። በሥነ-ሥርዓቱ ከ 200 በላይ ተጋባዥ እንግዶችና የጉባኤው ተሳታፊዎች የታደሙ ሲሆን ለጉባኤው ዝግጅት እገዛ ያደረጉት የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች መረብ፣ የዩናይት ስቴትስ ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ፣የዩናይትድ ኪንግደም ሮያል ሶሳይቲና የጀርመን ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ ተወካዮች ንግግር አድርገዋል። ከመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ በፊት ለአገር ውስጥና ለዓለም-አቀፍ የብዙሃን መገናኛ ተወካዮች በአካዳሚው የአመራር አባላት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

እ.አ.አ. ህዳር 11 እና 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ደግሞ ሳይንሳዊ ጉባኤው በሂልተን ሆቴል የተካሄደ ሲሆን 113 የሚሆኑ ዓለም-አቀፍና የአገር ውስጥ ተሳታፊዎች ታድመዋል። ከጉባኤው ተሳታፊዎች 66 ከባህር ማዶ የመጡ ሲሆኑ የአሜሪካ፣ አውሮፓና አፍሪካ ሳይንስ አካዳሚ ተወካዮችና የአምስት አፍሪካ አገራት ፖሊሲ አውጪዎች ተወካዮች ተገኝተዋል።

‘ባዮቴክኖሎጂ ለአፍሪካ ልማት’ ዓለም-አቀፍ ጉባኤ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት፤ አፍሪካ አዳራሽ፤ ሕዳር 1 ቀን 2006ዓ.ም.

Page 29: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

29

ከሳይንሳዊ ጉባዔው አንዱ ክፍል

‘ባዮቴክኖሎጂ ለአፍሪካ ልማት’ ስለሚኖረው ሚና የተደረገ የፓነል ውይይት

Page 30: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

30

ጉባኤው 12 ነጥቦችን የያዘ የጋራ መግለጫ (የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች 9ኛ ጉባኤ መግለጫ) በማውጣት ተጠናቋል። መግለጫው ‘ባዮቴክኖሎጂን ለአፍሪካ ልማት’ ጠቀሜታ በማዋል ላይ ያተኮረ ሲሆን በተለይ የአፍሪካ የፖሊሲ አውጪዎች፣ ምሁራን፣ ህግ አውጪዎች፣ አግባብነት ያላቸው የሚኒስቴር መ/ቤቶች (ለምሳሌ የሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የግብርና፣ የጤናና የአካባቢ ሚኒስቴሮች) መውሰድ የሚገባቸውን እርምጃዎች ይጠቁማል። የጋራ መግለጫው በ12 የሳይንስ አካዳሚዎች የፀደቀ ሲሆን እነርሱም የካሜሩን፣ የኢትዮጵያ፣ የጋና፣ የኬንያ፣ የሞዛምቢክ፣ የናይጄሪያ፣ የሴኔጋል፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የሱዳን፣ የታንዛንያ፣ የዩጋንዳና የዚምባብዌ ሳይንስ አካዳሚዎች ናቸው። መግለጫው በእግሊዘኛና በአማርኛ ቋንቋዎች ታትሞ ተሰራጭቷል።

የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች 9ኛ ዓመታዊ ጉባኤ ለአካዳሚው የመጀመሪያውን ዓለም-አቀፍ ጉባኤ የማዘጋጀት ዕድል የሰጠ ነበር። በጉባኤው የአፍሪካ አካዳሚዎችና ፖሊሲ አውጪዎች በባዮቴክኖሎጂ ዙሪያ አመለካከታቸውንና ሀሳቦቻቸውን እንዲለዋወጡ ከማስቻሉም በላይ ባዮቴክኖሎጂን ለአህጉሪቷ ልማት በማዋል ሂደት የሚኖሩትን መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮቶች አንስተው እንዲወያዩባቸው አድርጓል። የጉባኤው ወጪ በዋነኝነት የተሸፈነው ከዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች ልማት ፕሮግራም በተገኘው የ200 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሲሆን የጀርመን ሳይንስ አካዳሚ (ሊዎፖልዲና) በአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች መረብ በኩል የአባል አካዳሚዎችን ተሳታፊዎች ወጪ ሸፍኗል። በተመሳሳይ መልኩም የዩናይትድ ኪንግደም ሮያል ሶሳይቲ የራሱን የልዑካን ቡድን ወጪ ሸፍኖ በጉባዔው ተሳትፏል።

ከአገር ውስጥ ተባባሪዎች በዋነኝነት ድጋፍ የሰጠው የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ሲሆን፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች ልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር ለስድስት ተከታታይ ወራት የተካሄዱትን የባዮቴክኖሎጂ ህዝባዊ ገለፃና ውይይት መድረኮች ወጪ ሸፍኗል። በተጨማሪም ለገለፃዎቹ የቀረቡትን ጽሑፎችና ውይይቶችን ጥንቅር አካቶ የያዘውን ጽሑፍ የዝግጅትና የህትመት ወጪ ሸፍኗል። የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኤኮኖሚክ ኮሚሽንም አካዳሚው የጉባኤውን መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በአፍሪካ አዳራሽ ከክፍያ ነፃ እንዲያካሂድ ረድተውታል።

በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በአፍሪካ ሳይንስ

አካዳሚዎች የተካሔደ ዓውደ ጥናት

የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች በዓለም-አቀፍ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ ሊኖራቸው የሚችለውን ወሳኝ ሚና በመገንዘብ የኢ.ሳ.አ. ከአሜሪካ ብሔራዊ ሳይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዙ የአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ለመወያያት ከህዳር 4 - 5 ቀን 2006 ዓ.ም. የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች ተወካዮች የተሳተፉበትን አውደ-ጥናት አዘጋጅቷል። የአውደ-ጥናቱ ዋና ዓላማ የአየር ንብረት ለውጥ እየታየ መሆኑንና የሚያስከትላቸውን አሉታዊ ተፅዕኖዎች በግልፅ ለማሳየት የሚጥሩ አካላት እንዲጠናከሩ በማድረግ ላይ ያተኮረ ነበር። በተጨማሪም አውደ-ጥናቱ ሳይንቲስቶች የሚከራከሩበት፣ የሚተባበሩበት፣ የአየር ንብረትና ተጓዳኝ ጥናቶችን ግኝቶች የሚገመግሙበትና የሚያቀናጁበት ነፃ የግንኙነት መድረክ የማመቻቸት ዓላማ ነበረው።

Page 31: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

31

በዓውደ ጥናቱ ላይ ውይይት ሲደረግ

በዓውደ ጥናቱ የተደረጉ የቡድን ውይይቶች

Page 32: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

32

በአሜሪካ ብሔራዊ ሳይንስ አካዳሚ፣ በአፍሪካ የሳይንስ አካዳሚች መረብና በዩናይትድ ኪንግደም ሮያል ሶሳይቲ የተቀናጀ ድጋፍ በተካሄደው በዚህ አውደ-ጥናት ላይ በድምሩ 62 የሚሆኑ የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች ተወካዮች፣ ሳይንቲስቶች እና የአገር ውስጥ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳትፈዋል። ከተሳታፊዎቹ 50% የሚሆኑት ከባህር ማዶ የመጡ ሲሆኑ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ከፍተኛ ባለሙያዎች የሆኑት ፕሮፌሰር ጆናታን ፓትዝ (ከአሜሪካ) እና ዶ/ር ሮዛሊንድ ኮርንፎርዝ (ከእንግሊዝ)፤ አውደ-ጥናቱን መርተዋል። በአውደ-ጥናቱ ላይ ሌሎች የመወያያ ጥናቶችም ቀርበዋል። በተጨማሪም አውደ-ጥናቱ የባለሙያዎች ገለፃዎች እና የቡድንና የጋራ ውይይቶች የተካሄዱበት ነበር።

በአውደ-ጥናቱ ማጠቃለያም በተደረገው ጥልቅ ውይይት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸውን መረጃዎች በመለየት፤ በጋራ ሊሰሩ የሚችሉ ጥናቶችንና የአፍሪካ አካዳሚዎች ፖሊሲ አውጪዎችን ሊደግፉ የሚችሉባቸውን መንገዶች በተመለከተ የቅድሚያ ትኩረት ጉዳዮችን ለመጠቆም ተችሏል።

የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች መረብ /NASAC/ ጠቅላላ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ

የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች መረብ /NASAC/ጠቅላላላ ዓመታዊ ጉባኤ እ.አ.አ. ህዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ተካሂዷል። ስብሰባው የመረቡን ዓመታዊ የሥራ ክንውን በመገምገም በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ውሣኔዎችን አሳልፏል። የቀድሞው የመረቡ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ሮቢን ክሪው (ከደቡብ አፍሪካ ሳይንስ አካዳሚ) የአገልግሎት ዘመናቸውን ስለጨረሱ በምትካቸው ፕ/ር ሙስጠፋ ቦሲሚና (ከሞሮኮ ሳይንስ አካዳሚ) በጠቅላላ ጉባኤው አዲሱ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

2.4.2 በአፍሪካ የትምባሆ ማጨስ መስፋፋትን በተመለከተ የተደረገውን

ጥናት ሪፖርት ይፋ ለማድረግ የተካሄደ አውደ-ጥናት

“በአፍሪካ የትምባሆ ማጨስ መስፋፋትን ለመከላከልና በጤና፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የሚያስከትለውን ጫና ለመቀነስ የሚያስችል ውጤታማ ተግባር እንዲካሄድ የተደረገ ጥሪ” በሚል ርዕስ የወጣውን ሪፖርት በአዲስ አበባ ይፋ ለማድረግ መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. አካዳሚው በኢንተርኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል ያዘጋጀው አውደ-ጥናት ተካሂዷል። ለአውደ-ጥናቱ ዝግጅት ድጋፍ የሰጠውም የአሜሪካ የብሔራዊ ሳይንስ አካዳሚ ነበር።

ሪፖርቱ የተጠናቀረው ከስምንት የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች በተውጣጡ 16 ባለሙያዎች ሲሆን ሁለቱ (ዶ/ር ሰለሞን በኩረ እና ፕ/ር ዳመን ኃ/ማርያም) በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የተወከሉ ነበሩ። የጥናቱን ሀሳብ ያመነጩት የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች መረብ እና የአሜሪካ ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ ነበሩ። የጥናት ኮሚቴው በአፍሪካ የትምባሆ አጠቃቀምና ምርት ምን እንደሚመስል፤ እንዲሁም በጤና፣ በኢኮኖሚና በአካባቢ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ የሚያሳዩ መረጃዎችን በጥልቀት መርምሯል። በተጨማሪም ሪፖርቱ የትምባሆን ተጠቃሚነት መስፋፋት ለመከላከልና ለመቆጣጠር በአፍሪካ ያሉትንና የሚያስፈልጉትን ፖሊሲዎችና ሕጎች እነዲሁም እነዚህን ለመተግበር ያሉትን ሁኔታዎች፣ እንቅፋቶችና መልካም አጋጣሚዎች ይተነትናል።

የጥናቱ ዋና ዋና ግኝቶችና የመፍትሄ ሀሳቦች በጥናቱ ኢ.ሳ.አ.ን ወክለው በተሳተፉ ባለሙያዎች ከ60 በላይ ለሚሆኑ የአውደ-ጥናቱ ተሳታፊዎች ቀርበዋል። ተሳታፊዎቹም ከተለያዩ የሚኒስቴር መ/ቤቶች፣ ከክልል ጤና ቢሮዎች፣ ከዩኒቨርስቲዎች፣ ከምርምር ተቋማት፣ ከመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም አዲስ አበባ ከሚገኙ ዓለም-አቀፍ ድርጅቶች የተወከሉ ነበሩ።

ባለድርሻ አካላቱ ትምባሆ ማጨስ በአጠቃላይ በአፍሪካ አህጉር በተለይ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርሰውን አሉታዊ የጤና፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተፅዕኖ በሚመለከት ውጤታማ ውይይት አድርገዋል። ከባለድርሻ አካላቱ የተውጣጡ አባላትን ያቀፈ ኮሚቴ በኢ.ሳ.አ. ስር ተመስርቶ በትምባሆ ጉዳይ ላይ መንግስትን እንዲያማክርም ምክረ-ሃሳብ ቀርቧል። በተጨማሪም ወጣቶች ከትምባሆ ማጤስ እንዲገቱ በስፋት እንዲሰራና ህዝቡን ስለጉዳቱ የማስተማር ፕሮግራም እንዲነደፍ በአውደ-ጥናቱ ተጠይቋል።

Page 33: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

33

በሪፖርቱ ይፋ ማድረጊያ ዓውደ ጥናት የተደረጉ ውይይቶች

Page 34: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

34

የጥናት ሪፖርቱ ቅጂዎች ለዓውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች በሙሉ የተሰራጩ ሲሆን አካዳሚው ሪፖርቱን ለሕዝቡና ለሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ለማዳረስ በአካባቢ ቋንቋዎች መተርጎምን ጨምሮ ጠንክሮ እንደሚሰራ አረጋግጧል፡፡ የአውደ ጥናቱን ዝግጅት የመሩትና ያስተባበሩት የአካዳሚው የጤና ዘርፍ ቡድንና በጥናቱ አካዳሚውን ወክለው የተሳተፉት ሁለቱ ባለሙያዎች ነበሩ፡፡

2.4.3 “በናይል ተፋሰስ የሚገኙ ግድቦች አካባቢያዊና ማህበራዊ ተፅዕኖ” ሕዝባዊ ገለፃ

ሰኔ 5 ቀን 2006 ዓ.ም.ከላይ በተገለፀው ርዕስ ላይ በእሸቱ ጮሌ አዳራሽ (ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ፣ አ.አ.ዩ.) በአንድ ከፍተኛ ባለሙያ ገለፃ ተሰጥቷል። ገለፃው በኢ.ሳ.አ. የማህበራዊ ሳይንስና ሂዩማኒቲስ ዘርፍ ቡድን የተዘጋጀ ሲሆን ገለፃውን ያደረጉት ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በተመለከተ በተቋቋመው ዓለም-አቀፍ የባለሙያዎች ፓናል የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን መሪና በአገር ውስጥም የብሔራዊ ባለሙያዎች ፓናል ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው ነበሩ። በገለፃው በተፋሰሱ ላይ በተሰሩ ግድቦች የደረሱ ዋና ዋና አካባቢያዊና ማህበራዊ ተፅዕኖዎችና በመሰራት ላይ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አንጻር የተደረጉ ጥናቶችና ዝግጅቶች ተብራርተዋል። የተፋሰሱ አገራት ተወካዮች (ለምሳሌ የግብፅና የሱዳን)፣ እንዲሁም ከዓለም ባንክና ከአፍሪካ ህብረት የተወከሉ ተሳታፊዎች በገለፃውና ውይይቱ የተካፈሉ ሲሆን ተመራማሪዎች፣ ከልዩ ልዩ ተቋማት የመጡ የሥራ ኃላፊዎች እና ተማሪዎችም ተሳታፊዎች ነበሩ።

2.4.4 በኢትዮጵያ የግብርና ባዮቴክኖሎጂን ጠቀሜታ ለማሳደግ ስለሚቻልበት የሚመክር ዓውደ ጥናት

አካዳሚው ”የግብርና ባዮቴክኖሎጂን ጠቀሜታ በኢትዮጵያ ማጠናከር” በሚል ርዕሰ-ጉዳይ ብሔራዊ አውደ-ጥናት ለማካሄድ ለአሜሪካ ኤምባሲ የድጋፍ ጥያቄ አቅርቦ አወንታዊ ምላሽ አግኝቷል። አውደ-ጥናቱን ለማካሄድ የተወሰነው ቀደም ብሎ በአዲስ አበባ ”የባዮቴክኖሎጂ ሚና ለአፍሪካ ልማት” በሚል ዓቢይ ጉዳይ የተካሄደውን ዓለም አቀፍ ጉባኤ ውሣኔ መሠረት በማድረግ ነበር።

አውደ-ጥናቱ ኢትዮጵያ የግብርና ባዮቴክኖሎጂን ለመጠቀም ያላትን ብሔራዊ አቅም እንደሚዳስስና የቴክኖሎጂውን ተጠቃሚነት ለማስፋፋት ሊወሰዱ የሚገባቸውን የአጭርና የረጅም ጊዜ እርምጃዎች ለይቶ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል። የኢ.ሳ.አ. ጽ/ቤትና የአካዳሚው የግብርና ዘርፍ ቡድን የአውደ-ጥናቱን ዝርዝር ዕቅድ አውጥተው በ2007 በጀት ዓመት የመጀመሪያው አጋማሽ ለማካሄድ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ አካዳሚው ከነሐሴ 15-16 ቀን 2005 ዓ.ም. በዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት /USAID/ አስተባባሪነት የተካሄደው የግብርና ባዮቴክኖሎጂ ዓለም-አቀፍ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ አባል እንዲሆን በቀረበለት ጥያቄ መሠረት በመሳተፍ ላይ ይገኛል። ሌሎቹ የአውደ-ጥናቱ ዝግጅት ተባባሪዎችም የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ተቋምና የዩናይትድ ስቴትስ የግብርና ዲፓርትመንት ናቸው።

በአካዳሚው ስትራተጂክ ዕቅድ ላይ ከተካተቱት ዋና ዋና ፕሮግራሞች መካከል ለላቀ ውጤት ዕውቅና መስጠት አንዱ ቢሆንም እስካሁን ምንም አይነት ተግባራዊ እርምጃ አልተወሰደም። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት ለላቀ ውጤት ዕውቅና በመስጠት ሂደት ውስጥ ከመገባቱ በፊት አካዳሚው ራሱ በአግባቡ መታወቅና ጠንካራ መሠረት መያዝ አለበት ከሚል እምነት የተነሳ ነው። በአሁኑ ወቅት ግን አካዳሚው በአዋጅ መቋቋሙንና ከዋነኛ ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት እያጠናከረ መምጣቱን ግምት ውስጥ በማስገባት ዕውቅና የመስጠቱን መርሐ-ግብር ተሸላሚዎችን ለመምረጥ የሚያስችሉ መስፍርት በማውጣት በ2007 በጀት ዓመት ለመጀመር ዕቅድ ተይዟል።

ለልሕቀት ዕውቅና መስጠት

2.5

Page 35: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

35

የሥራ መደብ ብዛት

1

2

3

2

2

2

ብዛት

1

1

1

2

6

2

ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር

የፕሮግራም/ፕሮጀክት አስተባባሪዎች

የፕሮግራም ኦፊሰሮች

ህትመትና ኮሙኒኬሽን

ፋይናንስና አስተዳደር

የቢሮ ፀሐፊዎች

የሥራ መደብ

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂባለሙያ

ንብረት ክፍል

የቢሮ ረዳት

ሹፌሮች

ጥበቃዎች

የጽዳት ሠራተኞች

ሠንጠረዥ 4፣ የኢ.ሳ.አ. ዋና ጽ/ቤት ሠራተኞች

የአካዳሚውን ተቋማዊ አቅም ለማጎልበትና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባሮች ተከናውነዋል፡፡

2.6.1 የአካዳሚውን ሥራ በአግባቡ ማከናወን

አካዳሚው ሥራዎቹን የሚያከናውነው በተቋማዊ አወቃቀሩ ባሉት አካላት አማካኝነት ነው። በዚሁ መሰረት የአካዳሚው የበላይ ውሣኔ ሰጪ አካል የሆነው ጠቅላላ ጉባኤ ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን መጋቢት 18 ቀን 2006 ዓ.ም. በአካዳሚው ዋና ጽ/ቤት አካሂዷል። በስብሰባው ከ76 የጠቅላላ ጉባኤው አባላት ውስጥ 40 የተሳተፉ ሲሆን የአካዳሚው የ2006 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር የሥራ አፈፃፀም ተገምግሟል፤ የ2005 በጀት ዓመት ኦዲት ሪፖርትም ቀርቦ ጸድቋል። ፕ/ር ማስረሻ ፈጠነ የአካዳሚው ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ሆነው በመሠየማቸው ከቦርድ አባልነትና ከም/ፕሬዝዳንትነት ኃላፊነታቸው በመልቀቃቸው ፕ/ር ፅጌ ገ/ማርያም በቦርድ አባልነት የተተኩ ሲሆን፤በቦርዱ አባልነት ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር ብርሃኔ ገብረ ኪዳን ደግሞ በም/ፕሬዝዳንትነት ተመርጠዋል። በተጨማሪም ጉባኤው ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን በቋሚነት በጥቅምት ወር ቅዳሜ ቀን ለማድረግ ወስኗል።

የአካዳሚው ቦርድም በያዘው ዕቅድ መሠረት የሩብ ዓመት ስብሰባዎችን በማካሄድ ለጽ/ቤቱ ልዩ ልዩ መመሪያዎችን ሰጥቷል፤ የሥራ አፈፃፀሙንም ተከታትሏል። ቦርዱ ካከናወናቸው ሥራዎች መካከል የቦርዱን ስብሰባዎች አካሄድ ሥነ-ሥርዓት ደንብ ማውጣቱ እና የአካዳሚውን ፖሊሲዎችና ደንቦች የያዙ ሰባት መመሪያዎችን ጽ/ቤቱ እንዲጠቀምባቸው ማፅደቁ በአበይትነት የሚጠቀሱ ናቸው። የአካዳሚው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴም በወርሃዊ መደበኛ ስብሰባዎቹ የጽ/ቤቱን የሥራ ክንውን በቅርብ በመከታተል እገዛ አድርጓል። አስቸኳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙም አስቸኳይ ስብሰባዎችን አካሂዷል።

የአካዳሚውን ተቋማዊ

አቅም ማጎልበትና

ቀጣይነቱን ማረጋገጥ

2.6

የአካዳሚው የዕለት ከዕለት የሥራ እንቅስቃሴዎች ጽ/ቤቱ ባለው የሰው ኃይል ይካሄዳሉ። በጽ/ቤቱ ጊዚያዊ መዋቅር መሠረት የሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ጽ/ቤት፣ የፕሮግራም ማስተባበሪያ፣ የፋይናንስና አስተዳደር፣ የህትመትና ኮሙኒኬሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ፓናል ፕሮጀክት ተደራጅተው ይገኛሉ። ጽ/ቤቱ በ2006 በጀት ዓመት በአጠቃላይ 25 የቅጥር ሠራተኞ (ሠንጠረዥ 4) የነበሩት ሲሆን ይህ ቁጥር ባለሙያዎችንና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችን በሙሉ ያካትታል።

Page 36: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

36

2.6.2 የኢ.ሳ.አ. ሥራ ዕቅድና በጀት

አካዳሚው ለ2006 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥራ ዕቅድና በጀት አዘጋጅቶ ተግብሯል። ለዕቅዱ ማስፈፀሚያ ዋነኞቹ የፋይናንስ ምንጮችም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነበሩ።

ሠንጠረዥ 5፣ የኢ.ሳ.አ. የ2006 በጀት ዓመት የፋይናንስ ምንጮች

ምንጮች የገንዘብ መጠን(ብር)

943‚120.00

1‚886‚240.00

695‚808.00

518‚841.0010‚000‚000.00

14‚044‚009.00

የሦስተኛው ዓመት የ ASADI ድጋፍ

ለ9ኛው የአፍረካ ሳይንስ አካዳሚ ዓመታዊ ጉባኤ ከ ASADI የተገኘ ድጋፍ

$ ለአየር ንብረት ለውጥ አውደ-ጥናት ከአሜሪካ ሳይንስ አካዳሚ የተሰጠ ድጋፍ

ለልዩ ልዩ ተግባሮች ከRoyal Society የተገኘ ድጋፍ

የኢትዮጵያ መንግሥት የበጀት ድጋፍ

ድምር

በተጨማሪም አካዳሚው ለ2007 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድና ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የዕቅዱ ማስፈፀሚያ በጀት አዘጋጅቷል። ከጠቅላላው የበጀት መጠን 14.8 ሚሊዮን ብር ያህሉ ከመንግስት የሚጠበቅ ሲሆን፤ ዕቅዱም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኩል ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ቀርቧል።

በቀረበው ዕቅድ የተካተቱት ተግባራት በዋነኝነት በአካዳሚው ስትራቴጂክ ዕቅድ የተቀመጡትን አምስት አበይት ፕሮግራሞች ለመፈጸም የተያዙ

ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ተግባራት በ2006 በጀት ዓመት የተጀመሩትን ለማጠናቀቅ በቀጣይነት የሚሠሩ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ በበጀት ዓመቱ የሚጀመሩ ናቸው። ከነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ በአካዳሚው ሥር አዳዲስ ማዕከላትን መገንባት (ለምሳሌ - የሳይንስ ማዕከል፣ የባህልና ፈጠራ ማዕከል እና የአካዳሚው ፕሬስ) እንዲሁም የጋራ መግባቢያ ጥናቶችን ማካሄድና ቅድሚያ ሊሰጣቸው በሚገቡ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት ናቸው።

Page 37: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

37

2.6.3 የአካዳሚውን ዋና ጽ/ቤት ህንፃ ማሳደስና ግቢውን ማስዋብ

በቀደመው ጊዜ በመማሪያ ክፍልነት ሲያገለግሉ የነበሩት ክፍሎች ታድሰው ለአካዳሚው ጽ/ቤትና ለኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ፓናል ፕሮጀክት በቢሮነት እንዲያገለግሉ ተደርጓል። በዚህ መሠረት በስድስት ክፍሎች ላይ የጥገና፣ የማስተካከልና እንደገና የመከፋፈል ሥራ ተሠርቶ ከበጀት ዓመቱ አጋማሽ ጀምሮ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ። በተጨማሪም የዕድሳት ሥራው የስብሰባ አዳራሽ ማዘጋጀትን ያካተተ ነበር። ለቢሮዎቹና ለስብሰባ አዳራሹ ዕድሳት የዋለው የፋይናንስ ድጋፍ የተገኘው ከኢትዮጵያ አየር ንብረት ለውጥ ፓናል ፕሮጀክት ከተመደበው በጀት ነበር።

ታሪካዊውን የብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደ ሥላሴ የመኖሪያ ቤት ህንፃ የማደስ ሥራ በበጀት ዓመቱ ሁለተኛው አጋማሽ የተጀመረ ሲሆን የህንፃ ሥራ ኮንትራክተር በሆነው ተስፋዬ አዴሎ የግል ድርጅት በመከናወን ላይ ይገኛል፤ ክትትሉ ደግሞ በፋሲል አማካሪ ድርጅት ይከናወናል። የግቢውን አስፋልት የመጠገኑን ሥራም በተመሳሳይ ኮንትራክተር ለማሰራት ታስቧል። ፋውንቴን ዓለም-አቀፍ ትሬዲንግ የተባለ ኩባንያ ደግሞ የግቢውን የመሬት ገጽታ የማስተካከልና የማስዋብ ሥራ እያከናወነ ሲሆን በፋሲል አማካሪ ድርጅት

አማካሪነት ክትትል ይደረግበታል።

2.6.4 የተሸከርካሪዎች ግዢ

የአካዳሚውን ሥራ በተሻለ ሁኔታ ለማከናወን እንዲቻል የሦስት ተሸከርካሪዎች ግዢ ተፈጽሞ ጥቅም ላይ ውለዋል። የተሽከርካሪዎቹ ዓይነትም አንድ አነስተኛ ዞትየ ስቴሽን ዋገን፣ አንድ ቶዮታ ፕራዶ ስቴሽን ዋገን እና አንድ ቶዮታ ሚኒ ባስ ናቸው። ተሸከርካሪዎቹን ለመግዛት የዋለው ገንዘብ የተገኘውም የኢትዮጵያ መንግስት ለበጀት ዓመቱ ከሰጠው ዓመታዊ የበጀት ድጋፍ ነበር።

2.6.5 የአካዳሚውን የፖሊሲና የአሠራር መመሪያ ሰነዶችን ማዘጋጀትና ማፅደቅ

የአካዳሚው ቦርድ በጽ/ቤቱ በኩል ተዘጋጅተው የቀረቡትን የፖሊሲና የአሠራር መመሪያ ሰነዶች ገምግሞ አፅድቋል። ሰነዶቹም የሰው ሃብት አስተዳደር፣ የፋይናንስ፣ የፀረ-ሙስና፣ የስነ-ፆታ፣ የኤች አይ ቪ/ኤድስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን አጠቃቀም የሚመለከቱ ናቸው። የፖሊሲና የአሠራር መመሪያ ሰነዶቹ መዘጋጀትና መፅደቅ በአጠቃላይ ለአካዳሚው እንደ አንድ ትልቅ እመርታ የሚታይ ሲሆን በተለይ ለጽ/ቤቱ ደግሞ ተቋማዊ አሰራሩን ለማቀላጠፍ እንደሚረዳው ይታመናል።

Page 38: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

38

በአካዳሚው ዋና ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ የሳይንስ ማዕከል ለማቋቋም በጽ/ቤቱ የተዘጋጀው የመነሻ ሠነድ ከአካዳሚው የተለያዩ የዘርፍ ቡድኖች በተገኙ ግብዓቶች በመዳበር ላይ ይገኛል። ማዕከሉ የማህበረሰቡን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ባህል ለማጎልበት እንዲያግዝ የታሰበ ሲሆን ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የሚመጡ፤ በማንኛውም የዕድሜ ክልልና የትምህርት ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች አስደናቂ የሆኑ የሳይንስ ግኝቶችን አይተው በጋራ የሚደመሙበትና ግንዛቤ የሚጨብጡበት ቦታ እንዲሆን ይታሰባል። በተጨማሪም የመጠየቅና የመመራመር ልምድን የማዳበር፣ የፈጠራ ተሰጥዖን የማበረታታት እና የሳይንስ ዕውቀትን መሻት በአጠቃላይ ማህበረሰቡ ውስጥ እንዲሰርጽ ለማድረግ የሚረዳና በሙከራ የታገዘ የመማር ድባብ የሚፈጠርበት ቦታ እንደሚሆን ይጠበቃል።

በባዮቴክኖሎጂ ዙሪያ በተከታታይ በየወሩ ሲካሄድ በነበረው ህዝባዊ የገለፃና የውይይት መድረክ የቀረቡ ጽሑፎችንና የተደረጉትን ውይይቶች በማጠናቀር በአማርኛ በመፅሐፍ አሳትሞ ለተሳታፊዎችና ለሚመለከታቸው ድርጅቶች አሰራጭቷል።

በጤና ዘርፍ ቡድን አስተባባሪነት የተጠናው የኢትዮጵያን የጤና ምርምር ገፅታ የሚዳስስ ሪፖርትና የፖሊሲ አቅጣጫ አመላካች ሰነድ ታትመው ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሰራጭተዋል።

በኢትዮጵያ የግብርና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሁኔታ ላይ በተካሄደው ሀገር-አቀፍ አውደ-ጥናት የቀረቡ ፅሁፎችና ውይይቶች ተጠናቅረውና በመጽሐፍ መልክ ታትመው ተሰራጭተዋል። የህትመቱን ወጪ የሸፈነው በአዲስ አበባ የሚገኘው የዓለም የግብርና ድርጅት /FAO/ቢሮ ሲሆን የመጽሐፉ ስርጭት በግብርና ሚኒስቴር ዋና ጽ/ቤት በተደረገ ሥነሥርዓት በይፋ ተጀምሯል።

2. 6.7 የአካዳሚውን ሕትመቶች ማሰራጨት

አካዳሚው በዚህ የሪፖርት ዘመን የሚከተሉትን የጥናትና የዓውደ ጥናት ሪፖርቶች አሳትሞ አሰራጭቷል።

በጉራጌ ከፍተኛ ቦታዎች ላይ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ለመሥራት የሚያስችል የፕሮጀክት ሀሳብ በአካዳሚው ጽ/ቤትና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጋራ ተዘጋጅቶ ለኖርዌይ መንግስትና ለዩናይትድ ኪንግደም የልማት ተራድኦ ድርጅት (DFID) ቀርቦ ምላሹ በመጠበቅ ላይ ይገኛል።

በጤና፣ በሥነ-ምግብ እና የተዘነጉ አገር-በቀል ሠብሎችን በማስተዋወቅ ረገድ ጥናት ለማካሄድ የፕሮጀክት ሃሳብ በአካዳሚው ጽ/ቤት እና በጤናና የግብርና የዘርፍ ቡድኖች በጋራ ተዘጋጅቶ ዌልካም ትረስት ለተባለ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ቀርቧል።

i.

ii.

iii.

የአካዳሚው አባል የሆኑና ያልሆኑ ከፍተኛ የውሃ ባለሙያዎችን ያቀፈ ቡድን በአካዳሚው ጽ/ቤት አስተባባሪነት ቀጣይነት ያለው የውሃ ሃብት ልማትን በተመለከተ የፕሮጀክት ሀሳብ በማዘጋጀት ላይ ሲሆን ሰነዱ ሲጠናቀቅ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ይቀርባል።

iv.

2.6.6 የፕሮጀክት ሀሳቦችን ማዘጋጀትና ለሚመለከተው ማቅረብ

አካዳሚው ሊያካሂዳቸው የወጠናቸውን ሥራዎች ከግብ ለማድረስ የሚያስችለውን የገንዘብ፣የቴክኒክና የመሣሪያ ድጋፍ ለማሰባሰብ እንዲረዳው የተለያዩ የፕሮጀክት ሀሳቦችን አዘጋጅቷል። ከተዘጋጁት የፕሮጀክት ሠነዶች መካከልም ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ነበሩ፡–

Page 39: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

39

Financial Statements for the 2006 EFY

The financial statements of the Academy for the 2006 EFY (08 July 2013 to 07 July 2014) was prepared by the Secretariat and audited by TESFAYE MENGESHA & CO.Chartered Certified Ac-countants (London). Accordingly the Balance Sheet and the State-ment of Income & Expenditure as certified by the independent Au-ditors are presented as follows.

BALANCE SHEET

ASSETS EMPLOYED

REPRESENTED BYFUND BALANCES

FIXED ASSETS 4,142,732

139

9,400,419

88,897 (28,319)

2,680,074

1499,400,280

9,311,522 2,651,75513,454,254 2,917,657

13,454,254 2,917,657

2,679,925

265,902CURRENT ASSETS

Accounts receivableCash on hand & at bank

CURRENT LIABILITIES

NET CURRENT ASSETS

Accounts Payable

AT 7 JULY 2014 (30 SENE 2006)

2013/(2005)

Birr Birr Birr

3

Page 40: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

40

STATEMENT OF INCOME & EXPENDITURE

INCOME

EXPENDITURES

EXCESS OF INCOME FOR YEARFUND BALANCES B/FFUND BALANCES C/F

Grants/Donations 19,560,634

2,021,54764,584149,479

398,046922,4061,125,532976,182183,925199,82754,950

1,553,5301,050,287

142,3368,73311,735

60,00016,222

105,42822,683

0

996,7790

193,920308,279

95,543698,782297,258107,22033,65554,433

355,37073,56958,1939,362

10,966

09,617

33,9165,530

13,000

9,1004,263,931

9,50034,295

(9,067,432) (3,355,392)10,536,597 918,039

2,917,657 1,999,61813,454,254 2,917,657

0MembershipOther income

Salaries & wagesPensionAdvertising, publication& subscription Consultancy feeRepair & maintenanceTravel & per diemPrinting & stationeryCar rent & and local taxiTelephone & communicationDigital electronics documentationMeetings & accommodationDepreciationFuel & lubricantsInsuranceUtilitiesEstablishmentsHonorariumEquipment rentalOffice suppliesMiscellaneous

FOR THE YEAR ENDED 7 JULY 2014(30 SENE 2006)

2013/(2005)

Birr Birr Birr

Page 41: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

41

ፕሮግራም የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸም የግምገማ አስተያየትተ.ቁ.

1 የአካዳሚውን ገፅታና ጠቀሜታ

በሚመለከት ያለውን ግንዛቤ ማሳደግና ማጠናከር

ወቅታዊና አነጋጋሪ በሆኑ አገራዊ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ጉዳዮች ዙሪያ

የጋራ መግባባት ለመፍጠር የሚያስችሉ የውይይት

መድረኮችን ማመቻቸት

የአካዳሚውን ተግባራትና የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በሚመለከት የተጠናከረ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ መሥራት

አካዳሚውንና ሥራዎቹን ለማሰተዋወቅ በቂ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አልተሰራም፡፡

በጥናትና በዓውደ ጥናት ሕትመቶች ረገድ አበረታች ቢሆንም የአካዳሚው Newslet-ter እና Journal ሕትመት አልተጀመረም፡፡

በባዮቴክኖሎጂ ላይ በአማርኛ የተሰጡ ገለጻዎች ተጠናቅረው በመጽሐፍ መልክ ታትመዋል፤ የጤና ዘርፍ የምርምር ገጽታ ታትሟል፤ የግብርና ዘርፍን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሁኔታ የገመገመው እና የኢትዮጵያ አየር ንብረት ለውጥ የመጀመሪያው ዓውደ ጥናት ሪፖርት እንዲሁም የመነሻ ጥናት ሪፖርቶች ታትመዋል፡፡

ከተለያዩ ሁነቶች ጋር በተያያዘ አካዳሚውን የማስተዋወቅ ሥራ ተሰርቷል።

የአካዳሚውን ሕትመቶች /Newsletter and Journal/ ማሳተም፤

ተጨማሪ የአካዳሚ አባላትን መመልመል

ዘጠነኛውን የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚዎች ስብሰባና ከዚህ ጋር በተያያዘ ባዮቴክኖሎጂ ለአፍሪካ ልማት ያለውን አስተዋጽኦ በሚመለከት የሚመክረውን ዓለም አቀፍ ዓውደ ጥናት በሕዳር ወር 2006 ማካሄድ

የቅድሚያ ትኩረት የሚሰጣቸውን አገራዊ ጉዳዮች በመለየት መግባባት ሊደረስባቸው የሚችሉ ጥናቶችን /Consensus Studies/ ማካሄድ

27 መደበኛና 33 ተባባሪ አባላት ተመርጠዋል፡፡

ዓውደ ጥናቱና ሌሎች ተዛማጅ ስብሰባዎች በተሳካ ሁኔታ ተካሂደዋል፡፡

የሳይንስ መሣሪያዎች ፖሊሲ ጥናት ተደርጎ ዓውደ ጥናት ተካሂዷል፤

በአፍሪካ የትምባሆ ቁጥጥር ጥናት ተሳትፎ ተደርጓል፤ ሪፖርቱ በዓውደ ጥናት ይፋ ሆኗል፡፡

የሴት አባላት ቁጥር አነስተኛ ስለሆነ ከፍ ለማድረግ ጥረት እንዲደረግ ተወስኗል፡፡

ባዮቴክኖሎጂን ለልማት ለማዋልና የአየር ንብረት ለውጥን በሚመለከት ከተደረጉ አህጉር አቀፍ ውይይቶች ጠቃሚ ሐሳቦችና ልምዶች ተገኝተዋል፡፡

የተከናወኑት በቂ ባለመሆናቸው በጠቅላላ ጉባዔው ልዩ ልዩ የቅድሚያ ትኩረት ሀሳቦች ቀርበው በቀጣዩ በጀት ዓመት ዕቅድ ተካትተዋል፡፡

2

የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ4

Page 42: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

42

ፕሮግራም የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸም የግምገማ አስተያየትተ.ቁ.

የሳይንስ፤ ቴክኖሎጂ እና

ኢኖቬሽን ሥራዎችን

ማበረታታት

ለላቁ ግኝቶችና ሥራዎች ዕውቅና መስጠት

-

በስራ ዘርፍ ቡድኖች በኩል ጠንከር ያሉ እንቅስቃሴዎች ቢደረጉ ከዚህ የበለጠ መስራት ይቻል ነበር፡፡

የብሔራዊ የምርምር ም/ቤት ካውንስል የመግባቢያ ጥናት ማካሄድ

የኢትዮጵያን የአየር ንብረት ለውጥ ፓናል መመሥረት

በልዩ ልዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የባለሙያ ገለፃዎችን ማዘጋጀት

ለአገሪቱ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ አፈፃፀም የሚረዱ ጠቋሚ ሀሳቦችን አጥንቶ ማቅረብ

ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ መሠረት የሃገሪቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰው ሃብት ፍላጎትና አቅርቦት ጥናት ተጀምሯል።

የሌሎች ሀገሮችን ልምዶች ለመቅሰም ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ከታሰበው በላይ ጊዜ በመውሰዱ ጥናቱ በታቀደው መሰረት ተጠናቆ ለዓውደ ጥናት ሊቀርብ አልቻለም፡፡

ከባለድርሻ አካላትና ከባለሙያዎች ጋር ጠንካራ ትብብር ተመስርቶ የመጀመሪያው የዳሰሳ ጥናት በመደረግ ላይ ነው፡፡

ለምርምር፣ ጥናትና ኢኖቬሽን ሥራዎች የተደረገ ድጋፍም ሆነ ማበረታቻ አልነበረም፡፡

3

4

በባዮቴክኖሎጂ ላይ ገለጻና የፖሊሲ አውጪዎች ዓውደ ጥናት ተካሂዷል፤

የጥናት ቡድን ተቋቁሞ በካውንስሉ ማቋቋሚያ ረቂቅ ላይ ግብዓት ተሰጥቷል፤

የሌሎች አገሮችን ልምዶችና አገራዊውን ሁኔታ በመቃኘት የካውንስሉ አደረጃጀትና አሰራር ምን መምሰል እንዳለበት ጥናቱ በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡

በኢንዱስትሪ እና በዩኒቨርስቲ ግንኙነት ላይ ያተኮረ የባለሞያ ገለጻ ተሰጥቷል፤

በግብርና ባዮቴክኖሎጂ ላይ ብሔራዊ ዓውደ ጥናት ለማካሄድ ዝግጅት ተደርጓል፡፡

- የታቀደም ሆነ የተከናወነ ተግባር አልነበረም፡፡

ፕሮጀክቱ አስፈላጊው የሰው ሀይልና የቢሮ ፋሲሊቲ ተሟልቶለት ሥራውን በይፋ ጀምሯል፡፡

Page 43: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

ዓመ

ታዊ

ሪፖ

ርት

43

5 የአካዳሚውን ተቋማዊ አቅም

መገንባትና ዘላቂነቱን ማረጋገጥየአካዳሚውን አሠራር ማጠናከር

በአካዳሚው ጽ/ቤት ግቢ የሚገኘውን ዋና ሕንፃ (የብላቴን ጌታ ህሩይ ወ/ሥላሴ መኖሪያ የነበረ)፣ የግቢውን አጥርና መንገዶች ማሳደስ

ከሌሎች አካዳሚዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር

መማሪያ የነበሩ ክፍሎች ታድሰው ለቢሮነት ውለዋል፤ የዋናው ሕንጻ ሙሉ ዕድሳት እና ግቢውን የማስተካከልና የማስዋብ ስራ ተጀምሯል፡፡

ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ተቋማት ጋር ግንኙነቶች ተደርገዋል፤ ከሀገር ውጭ በተዘጋጁ መድረኮች የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ተችሏል፡፡

በተለይ በአፍሪካ የሳይንስ አካዳሚዎች መረብ (NASAC) ማዕቀፍ ሥር የተጠናከረ ተሳትፎ ተደርጓል፡፡

የአካዳሚው ቋሚ አደረጃጀትና መዋቅር ተዘጋጅቶ አልጸደቀም፡፡

ሥራው በአግባቡ ተጀምሯል፡፡

አካዳሚው ስራውን በስርዓት ለመምራት የሚያስችሉት ልዩ ልዩ የስራ መመሪያዎች ጸድቀዋል፤ጽ/ቤቱ የሚያስፈልጉትን ሰራተኞች በተወሰነ ደረጃ በቋሚነት አሟልቷል፡፡

በአካዳሚው ጽ/ቤት ግቢ ወደፊት ለሚሰሩ ፋሲሊቲዎች የፊዚቢሊቲ ጥናት ማጠናቀቅና ሀብት ማፈላለግ

ለአካዳሚው ጽ/ቤት ቢሮዎችንና መገልገያ መሳሪያዎችንና ዕቃዎችን ማሟላት

ጥናቱ በመደረግ ላይ ነው፡፡ ለአካዳሚው የዓቅም ግንባታና የፕሮግራም ስራዎች ማስፈፀሚያ አስተማማኝ ገቢ ለማግኘት በሚቻልበት ላይ እየተመከረ ነው፡፡

በሥራ መገልገያ መሳሪያዎችና ዕቃዎች መሟላት ለሥራ አመቺ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

ክፍሎች ታድሰው ጥቅም ላይ ውለዋል፤ አዳራሽ ተዘጋጅቷል፤ አስፈላጊ ዕቃዎችና መሳሪዎች ተሟልተዋል፡፡

ለሥራ የሚያገለግሉ 3 አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ተገዝተዋል፡፡

ፕሮግራም የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸም የግምገማ አስተያየትተ.ቁ.

Page 44: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

44

አባሪ፡የወቅቱ የኢ.ሳ.አ

የቦርድ አባላት

ሥም ኃላፊነት የመጡበት ድርጅት

1 ፕሮፌሰር ደምሴ ሀብቴ ፕሬዝዳንት በግል

ኤሜረተስ ፕሮፌሰር

አአዩ

አአዩ

አአዩ

አአዩ

አአዩ

ጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤትበሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩየፖሊሲ ምርምር አማካሪ

ሚኒስትር ዴኤታ

ዋና ዳይሬክተር

ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ኢንስቲትዩት

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

በግል

ተቀዳሚ ዋና ፕሬዝዳንት

ምክትል ፕሬዝዳንት

ዓቃቢ-ነዋይ

አባል

አባል

አባል

አባል

አባል

አባል

አባል

አባል (ያለ ድምፅ) እና ጸሐፊ

ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ

ዶ/ር ብርሃኔ ገብረ ኪዳን

ፕሮፌሰር ያለምፀሐይ መኮንን

ፕሮፌሰር አለማየሁ ተፈራ

ፕሮፌሰር ባዬ ይማም

ፕሮፌሰር ሰብስቤ ደምሰው

ፕሮፌሰር ፅጌ ገብረ ማሪያም

ክቡር ዶ/ር ካሱ ይላላ

ክቡር አቶ ማሐሙዳ አህመድ ጋኣስ

ዶ/ር አምኃ ከበደ

ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ

ተ.ቁ.

2

3

4

5

6

7

8

9

10

11

12

Page 45: የኢትዮጵያ ሳይንስ - eas-et.org · cifዷ 8. የ2006 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያው

አድራሻ፡የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ አካባቢ ታሪካዊው የብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደ ሥላሴ የመኖሪያ ቤት ህንፃ

ስልክ፡ (+251) 112595745/50ኢሜል፡ [email protected]ድረ-ገጽ፡ www.eas-et.org ፖ.ሳ.ቁ. 32228 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ