32
የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 0 www.tlcfan.org በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

  • Upload
    vothuy

  • View
    392

  • Download
    42

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

0 www.tlcfan.org

በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 2: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

1 www.tlcfan.org

የዳንኤል ሳምንታት የመጀመሪያ እትም

Copyright ©2005 የሁለተኛ እትም REVISED 2015

መብቱ የተጠበቀ ነው፦

All rights Reserved to: Bible Teacher Pastor Leon Emmanuel

FOUNDER OF

THE LION S CALL FOR ALL NATION INTERNATIONAL MINISTRY

Permission is granted to copy and quote freely

from this publication for non-commercial purposes.

Page 3: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

2 www.tlcfan.org

ማውጫ

ርዕሶች ገጽ

1. የዳንኤል ሰባ ሳምንቶች...................................................................................3

2. ኢየሱስና ሰባ ሳምንት...............................................................................................11

3. የዳንኤል ሰባ ሳምንትና አሳቹ ክርስቶስ......................................................................15

4. የዳንኤል ሰባ ሳምንት መጀመሪያና መጨረሻ.............................................................21

5. ኢዮቤልዮና የዳንኤል ሰባ ሳምንቶች..........................................................................25

Copyright © 2005

All rights Reserved to Pastor Leon Emmanuel

Page 4: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

3 www.tlcfan.org

የዳንኤል ሰባ ሳምንቶች

በዚህ በመጨረሻው ዘመን ያለ በብዙዎች ዘንድ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የሰባት

አመት መከራ መነሻውን የደረገው ዳንኤል ስለ ሰባ ሳምንቶች በሚናገረው ትንቢታዊ ቃል ላይ

ነው። ሰዎች በዚህ 70 ሳምቶች ላይ የራሳቸውን የሆነ ብዙ መረዳት ያስቀምጣሉ። ያአንዳዶቹ

ሰዎች መረዳት ደግሞ የሚያሳየው ያልተሟላን እውቀት መያዛቸውን ነው። ይህ 70 ሳምንት

የትንቢት ዘመን እንደ ተፈጸመ የምድር ጥናት ተመራማሪዎች ይናገራሉ። በ1800 ዓ.ም ይህኑን

የመጽሐፍ ቅዱስን ሃሳብ የሚያጸና መረጃ ተገኝቷል ብለው ሃሳባቸውን በመረጃ ይደግፋሉ። ይህን

በመላው አለም ተሰራጭቶ ያለውን የተሳሳተና የተምታታ መረዳት ለማስተካከል የዳንኤል 70 X

7= 490 ዓመት የሚመጣ ገና የሚፈጸም ወይስ የተፈጸመ ትንቢት መሆኑን በዚህ ጽሁፍ በዝርዝር

እንመልከታለን።

ከጥቂት ጊዜ በፊት በዳንኤል ላይ ያለውን 70 ሳምንት ሚስጥር ለመመርመር ራሴን

አተጋሁ። ከቀደሙ መንፈሳዊ አባቶቼ እንደተማርኩት ከመጨረሻው ጀምሬ ወደ ኃላ መቁጠሬንና

መመርመሬን ጀመርኩ። የኢየሱስ ስቅለት ቀን ተብሎ በተቀመጠው ቀን መነሻዬን አድርጌ ወደ

ኃላ 490 ዓመት ቆጠርኩ። ይህም ጅማሬውን ለማግኘት በማሰብ ነው። ብዙ የጥናት ሥራዬ

ምርመራዬ ራሴን ስላደከመኝ በእውነት ላይ የተመሰረቱ ታሪኮችንን መመርመር ጀመርኩ።

መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በእውነት በታሪክ የተፈጸሙትን ሃሳቦች በመመልከት የውስጥ እይታን

በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ መፈለግ ጀመርኩ። ከዚያም በኃላ እምነቴ እውነቱን ሳገኝ ጨመረ።

ይህም ከእግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ያለውን ድምጽ እንደሰማ የታሪክ ጥናቴም ስላገዘኝ ነው።

ይህም የእምነቴን አቅጣጫ አስተካከለው።

በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ትንቢት ለእኛ የተጻፈልን እንደምናውቀው በዳንኤል 9 ላይ

የተነገረው ሕዝቡን በመወከል ዳንኤል ለሕዝቡ ንስሃ ከገባ በኃላ ነው። ይህም ዳንኤል በኤርሚያስ

ትንቢት ላይ የተጻፈውን የእግዚአብሔር ፍርድ በእስራኤል ላይ ለ70 ዓመት እንደሚቆይ

የተነገረውን ትንቢት ዳንኤል ካነበበ በኃላ ነው። ዳን.9፥2 ምንም እንኳን ይህ በኤርሚያስ የተነገረው

የ70 ዓመት ትንቢት ወደ ፍጻሜው እንደሚመጣ እርግጠኛ ቢሆንም ዳንኤል የባቢሎን ግዛት

እንዲያበቃ በጸሎቱ ማብቂያ ላይ እግዚአብሔርን ጠይቋል። ገብርኤልም ለዳንኤል በመገለጥ

እንዲህ አለው።

“ ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥

የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥

ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ

ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።” ዳን.9፥24

Page 5: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

4 www.tlcfan.org

ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ የዘላለምን ጽድቅ ያገባና

ራእይንና ትንቢትን ያትም ቅዱሳንንም ይቀባ ዘንድ የሚወስደው 70 ሱባኤ ነው። ይህ የፍርድ

ወቅት በፍጥረታዊው ባቢሎን ላይ ያተኮረ ቢሆን ኖሮ ዳንኤል በሚጸልይበት ወቅት ዘመኑ ተፈጽሞ

ነበር።

ይሁንና ባርነቱ እግዚአብሔር የሚናገረው ባርነት ግን ገና አላበቃም ነበር።

ምክንያቱም ይህ ባርነት ከባቢሎን በኃላ እንደሚቀጥል እግዚአብሔር ለናቡከደንፆርና ለዳንኤል

በዳንኤል 2 ና 7 ላይ የተናገረው ነው። ይህ ባርነት ከወርቁ ራስ ከሆነው ከባቢሎን አልፎ የሚቀጥል

ነበር። ይህ ባርነት በሜዶንና በፋርስ በግሪክና በሮም የሚቀጥል ነበር። ደግሞም በተከፋፈሉት

መንግስታትም ዘመን የሚቀጥል ነው።

ስለዚህም በባቢሎን ስር መገዛት የመጀመሪያው በባርነት የመገዛት መንገድ ጅማሬ

ነበር እንጂ ፍጻሜው አልነበረም። ይህም የትንቢቱን መንፈስዊ አካል ስንመከት ነው። ይህም

ባርነት ከ70 ሱባኤ በላይ የሚጠይቅ ነው። ይህም ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም

ያስተሰርይ የዘላለምን ጽድቅ ያገባና ራእይንና ትንቢትን ያትም ቅዱሳንንም ይቀባ ዘንድ ነው።

እነዚህ ዘመናት የዓመቱ 70 ሳምንታት/ ሱባኤ በመባል ይታወቃል።

“ሳምንት” በመጽሐፍ ቅዱስ የስባት ቀን ወይም የሰባት ዓመት ዘመን ምሳሌ ነው።

ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሕግ ሁሉ ሰባት ዓመት የምድር ረፍት ወይም ስንበት እንዲሆን

ያዛል። ይህ ደግሞ ስባት ዓመትናን ስባተኛ ቀንን አንድነት ያሳያል። ከፍ ባለው በእግዚአብሔር

ቃል መረዳት መሰረት ሳምንት የሰባት ዓመትም ጥላ ነው። ይህ ደግሞ በአንድ ላይ 70x7= 490

ዓመት ይሆናል ማለት ነው።

“25.ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ

ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት

ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት

ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለ።”

ይህን ትንቢት ለመረዳት ሁለት አይነት የአዋጅ ብይኖችን እንመልከታለን።

የባቢሎን መንግስት በሜዶናዊው ዳሪዮስና በፋርሳዊው ቂሮስ ተሽሯል፣ ተተክቷል ወይም

መንግስቱ ተገልብጧል። የቂሮስ አዋጅ በ534 B.C. ሕዝቡ ከባቢሎን ወጥተው ወደ ድሮ

መኖሪያቸው እንዲመለሱ ፈቅዷል። ይህም ኢየሩሳሌምን ተመልሰው እንዲገነቧት ነው። ዕዝራ.1፥

2 ነገር ግን ሕዝቡ መቅደሱን በዚያን ወቅት እንደገነቡት የሚናገር ምንም መረጃ የለም።

Page 6: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

5 www.tlcfan.org

76 ዓመት በኃላ እርሱ ሰባት ዓመት ከገዛ በኃላ በአርጤክስስ በ458 B.C. ሁለተኛ

አዋጅ ወጣ። ዕዝራ.7፥11 ምንም እንኳን ስለ ኢየሩሳሌም መገንባት ምንም ባይናገርም የ70

ሳምንት ዘመን መቆጠር የጀመረው ያኔ ነበር። ምክንያቱም የፋርስ ንጉስ መሰዋዕትን ሊሰዋ

የሚሰዋውን እንስሳ እንዲገዛለት ዕዝራን ይነግረዋል። ዕዝ. 7፥23

ይህም የሚያሳየው ዕዝራ ስለ ራሱ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ስለ ንጉሱና ስለ መንግስቱም

መስዋዕትን ያቀርብ እንደ ነበር ነው። ይህ መስዋዕት የሚያመለክተው ሃጢያት ይፈጽምና

በደልንም ያስተሰርይ ዘንድ መጀመሩን ነው። ዳን.9፥24 ጀመረ እንጂ በዚያ ብቻ አልተፈጸመም

ወይም አላበቃም።

የኢየሩሳሌም መገንባት የፍቃድ አዋጅ የወጣው መስዋዕቱን ዕዝራ ካቀረበ ከ13

ዓመት በኃላ ነው። አርጤክስስ የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንዲሰራ ነህሚያን ልኮታል ነህምያ ቅጥሩን

በሙሉ ገንብቷል። ነህምያ.2፥1-5 ሰለዚህ ለእኛ ትምህርት የሚሆነን ሁለት ወሳኝ ቀኖች

ልንመለከት ይገባል።

ዕዝራ በ458 B.C. ነህሚያ 445 B.C. ከክርስቶስ ዘመን በፊት ያሉት ሁለት ዘመኖች

ናቸው። እነዚህ ቀኖች የዳንኤል 70 ሳምንት መጀመር መነሻ ቁልፎች ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ

ላይ ተቀምጠው የምናገኛቸው ትንቢቶች በተለያየ አገላለጽና በተለያዮ ነብያቶች ከመጻፋቸው

የተነሳ ሲቀመጥ ዘመኑ ከአንድ በላይ የሆነ መጀመሪያ እንዳለው መመልከት እንችላለን። ሁለቱም

የዘመን መጀመሪያዎች የራሳቸው የሆነ ፍጻሜም አላቸው። በላይ ባሉት ቀኖች መነሻ መሰረት

ፍጻሜው በ33 ዓ.ም ክርስቶስ በተሰቀለበት ጊዜና በ47 ዓ.ም ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ

ለአገልግሎት የተላከበት ወቅት እንደ ሆኑ ከትንቢቱ መረዳት እንችላለን።

እነዚህ የትንቢት መጨረሻ ቀኖች ራሳቸው ደግሞ ለሚቀጥለው የትንቢት መፈጸም

ዘመን መጀመሪያ ቀኖች ናቸው። እነዚህ 40 የኢዮቤልዮ ቀኖች ናቸው። በዝርዝር በኃላ

እንመለከታቸዋልን። የሁለቱ የትንቢት ቀኖች ማብቂያ ተነስተን ደግሞ ሌላውን የትንቢት ዘመን

ፍጻሜ ስንመለከት ደግሞ 1993 ና 2007 ዓ.ም መሆናቸውን እናያለን። ይህ ደግሞ አሁን ላለን

ለእኛ አስፈላጊ የሆነን የጊዚያዊ መልዕክትን ያስተላልፋል የሚል እምነት እና መረዳት ላይ

ያመጣናል። የእግዚአብሔር ትንቢት በየዘመኑ እንዳቀማመጡ የሚፈጸም ነው። እነዚህ የትንቢት

ክበብ ዙር ዘመኖች በመካከላቸው ምንም ክፍተት ሳይኖራቸው እርስ በእርሳቸው ተሳስረው እንደ

ሰንሰለት እርስ በርሳቸው ተያይዘው የሚገለጡ ናቸው። ታሪክ ራሱ ይህን በማጽናት ትንቢቱን

የበለጠ ያጠረክረዋል፣ አስረግጠዋል።

Page 7: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

6 www.tlcfan.org

ወደ ዳንኤል ምዕራፍ ዘጠን እንመለስና ቀሪውን የትንቢት መልዕክት በደንብ አጢነን

እንመልከት። ዳን.9፥25 ላይ 70 ሳምንት/ሱባኤ 7 + 62 +1 ተብሎ ተከፋፍሎ እናገኘዋለን። ከ62

ሳምንት ካለፈ በኃላ መሲሁ እንደሚመጣ ይናገራል። ይህም በ70ኛው ሳምንት ነው። ሰለዚህ 70

የዳንኤል ሳምንት ጀምሮ ያለቀው ከ26 - 33 ኤ.ዲ ባለው ዘመን ውስጥ ነው። ይህም መሲሁ

መጥቶ የአገልግሎት ሥራውን የፈጸመበት ዘመን ነው።

“25፤ ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ

ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት

ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።

26. ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም፤

የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ፤ ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥

እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤ ጥፋትም ተቀጥሮአል።”

መሲሁ ክርስቶስ ኢየሱስ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላገኘ ንጉስ ነው። በአዲስ ኪዳን

እንዴት በሃይማኖት መሪዎች ሃሰት ምስክርነት እንደተገደለ እንመለከታለን። ማቴ.21፥38 ዳንኤል

ሲናገር የዚህ ስራቸው ፍርድ የሚመጣውም አለቃ ማለት የሮምን መንግስት አስቀድሞ

በመመልክት እግዚአብሔር የሰማውን ይናገራል።

ሮም ከነሰራዊቷ ኢየሩሳሌምን ወራ የኢየሩሳሌምን ከተማና መቅደሱን እንደሚያጠፉ

እግዚአብሔር ቀድሞ ተናገረ። የኢየሩሳሌምና የመቅደሱ በጦርነት መፍረስ አስቀድሞ

በእግዚአብሔር በትንቢት የተተነበየ ቀድሞ በእርሱ የተወሰነ ጉዳይ ነው። እግዚአብሔር

ኢየሩሳሌም እንደምትፈርስ አስቀድሞ ትንቢትን ተናገረ። ይህ ሁሉ ትንቢት በድጋሚ በኢየሱስ

እራሱም ሰለ ሰርግ በተናገረው ምሳሌያዊ ትንቢት ላይ በግልጽ ተቀምጦ እናገኘዋለን፦

“1.ኢየሱስም መለሰ ደግሞም በምሳሌ ነገራቸው እንዲህም አለ።

2 መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች።

3 የታደሙትንም ወደ ሰርጉ ይጠሩ ዘንድ ባሮቹን ላከ ሊመጡም አልወደዱም።

4 ደግሞ ሌሎችን ባሮች ልኮ። የታደሙትን። እነሆ፥ ድግሴን አዘጋጀሁ፥

ኮርማዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፥ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤

ወደ ሰርጉ ኑ በሉአቸው አለ። 5 እነርሱ ግን ቸል ብለው አንዱ ወደ እርሻው፥

ሌላውም ወደ ንግዱ ሄደ፤ 6 የቀሩትም ባሮቹን ይዘው አንገላቱአቸው

ገደሉአቸውም። 7 ንጉሡም ተቈጣ፥

ጭፍሮቹንም ልኮ (ሮምና ሰራዊቱ) እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤

ከተማቸውንም አቃጠለ።” ማቴ.22፥1-7

Page 8: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

7 www.tlcfan.org

ኢየሱስ ይህንን ሲናገር ሰለ መለኮታዊው የእግዚአብሔር እቅድ በዳንኤል ላይ ስለ

ተነገረውም ትንቢት መረዳት ነበረው። ኢየሱስ ትንቢትን የሚመረምር ብሎም በምሳሌ ትንቢቱን

ደግሞ የሚያጠነክር ነው። ደቀመዛሙርቱ እንዳሉት ትጉ በቃልም ብርቱ እንደ ነበር መመልከት

እንችላለን። የሮም ሰራዊትም የእግዚአብሔር ነገስታት ተብለው መቀመጣቸውንም አሰተውሎ

ነበር። ሮማውያን ምድሪቱን ይወሩና ያጠፉ ዘንድ የእግዚአብሔር ሃሳብ የሚያስፈጽሙ በእርሱ

ለዚያን ዘመን የተመረጡ የእግዚአብሔር ጭፍሮች እንደ ነበሩ ኢየሱስ ያውቃል። እግዚአብሔር

እንደላካቸ ለምንም እንደሚልካቸ ጠንቅቆ ያውቃል።

ዳን.9፥26 በኢየሩሳሌም ይህ ጦርነት የተደረገው ከዳንኤል 70 ሳምንት ትንቢት

ከተፈጸመ ከ40 ዓመት በኃላ ነው። 70 ሳምንት ትንቢት ከ26-33 ኤ.ዲ ድረስ የቆየ ነበር። ጦርነቱ

ደግሞ ከ66-73 ኤ.ዲ ድረስ ቆይቷል። ኢየሳሌምና መቅድሷ በ70 ኤ.ዲ ፈጽመው የእግዚአብሔር

ጭፍሮች የሆኑት ሮማውያን ፍርሰዋታል።

ሁሉ የትንቢት ክበብ ዘመን ፈጽመው አንድ በአንድ የተያያዙና በምድር ከተፈጠረው

ታሪክ ጋር በትክክል የሚጋጠሙ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። በመንፈሳዊያን ታሪክ ተመራማሪዎችና

ታላላቅ ቲዮሎጂያንም ጭምር ይህ ታሪክ የታመነ የሆነ የተፈጸመና የተከሰተ ነገር ነው። ይሁንና

ብዙ በጥልቀት የሚመረመሩ ብዙ መልዕክቶችን የያዘ ትንቢት መሆኑን ማወቅ ይገባናል። በዚህ

ትንቢት ውስጥ የተሰወረ ብዙ የተያያዘ ብዙ ሚስጥር ሌላም ለእኛ ዘመን ሁሉ የሚሆን ትንቢት

በእኛ ዘመን የሚፈጸም ትንቢት አለ።

የዳንኤል 70 ሳምንታት ሁለት ጀማሬና ምጻሜ እንደ ነበራቸው ከላይ ተመልክተናል።

እነዚህን ቀኖች በትክክል ማወቅ ይገባናል። እነዚህ ቀኖች 458 ና 445 ናቸው። እነዚህ ዘመኖች

በ7ኛውና 20ኛው የአርጤክስ የግዛት ዓመት ውስጥ የነበሩ ዘመኖች ናቸው። ይህንን ዕዝራ.7፥8ና

ነህ.2፥1 በመመልከት ማለጋገጥ እንችላለን። የበለጠ ደግሞ መረዳት ከፈለግን መጽሐፍ ቅዱስን

ሰለዚያ ዘመን የሚናገሩ እውነተኛ ቃሎችንና የታሪክ መዛግብቶችን ልንመረምር ይገባናል።

ሰንመረምር በ “ሉናር ኤክሊፕስ” ለ30 ዓመት በነገሰው በፋርሳዊው ዳሪዮስ ታሪክ መዝገብ ላይ

ተመዝግቦ እናገኘዋለን። ይህ ንግስናው በታሪክ ሰናጠናው ከ521-486 ቢ.ሲ የቆየ ነበር።

ፒቶልሚ ግብጻዊው የከዋክብት ተመራማሪ በዚያን ዘመን የሆነ “ሉናር ኤክሊፒስ’’ እንደ

ነበር ተናግሯል። ይህም መሆኑ በዳሪዮስ ዘመን በ20ኛውና በ31ኛው ቢ.ሲ ነው ብሎ አስረግጦ

ያስረዳል። በዚህ ዘመን ያሉ የከዋክብት ጥናት ተመራማሪዎች ቴክኖሎጂን በመጠቀም በቀላሉ

የሚያገኙበት ዘመን ላይ መጥተናል እነርሱም “ኤክሊፕስ” የነበረው ኖቬንበር/ሐምሌ.19, 502

B.C. ላይና በጁላይ/ታህሳስ.25/491 B.C. ላይ እንደ ሆነ አስረግጠው ይናግራሉ።

Page 9: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

8 www.tlcfan.org

ዳሪዎስ በዚያ ወቅት በፋርስ ገዢ እንደ ነበር በሁለት ምስክር ያስረግጥልናል። ይህን

ካወቅን በኃላ የአርጤክስ 21 ዓመት ማለት ከ465 እስከ 485 B.C. መሆኑን እንረዳለን። አርጤክስ

ዙፋኑ ወሰደ፦ የመጀመሪያ ዓመቱን ንግስና በፋርስ በ464 B.C. ላይ ነበር። ሰባተኛው አመት

ንግስናው ዘመን በ458 B.C. ና 20ኛው ዓመት ደግሞ 445 B.C. ነበር። ሁሉ ታሪክም ጭምር

በዚህ ቀን ትክክለኛነት ይስማማል።

የታሪክ ተመራማሪዎች ሁሉ እንደ ሚስማሙበት ኢየሱስ የተሰቀለው በ33 A.D

ነው። ኢየሱስ በዳንኤል በ70 ሳምንት ትንቢት ማለቂያው ላይ እንደ ተገደለ በዳንኤል ትንቢት

መሰረት ግልጽ ነው።

“እርሱም (ኢየሱስ) ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም

እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፤

እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።”

ዳን.9፥27

ብዙዎች መሲሁ የተገደለው በ62ኛው ሳምንት ላይ ነው ብለው ያስተምራሉ። ይህ

ደግሞ ከኢየሱስ ስቅለት ቀንና ከታሪክ ጋር ፈጽሞ አይጋጠምም። ደግሞም በቁጥር 27 ላይ

“እርሱም” የሚለውን ቃል ኢየሱንስ ሳይሆን የሚናገረው አሳቹ ክርስቶስን ነው ብለው ያስተምራሉ።

ኢየሱስ መስዋዕት ነበር። መስዋዕት በመሆኑ ደግሞ መስዋዕትን ሁሉ ያስቀረው እርሱ እንጂ አሳቹ

ክርስቶስ አይደለም።

በ70ኛው የዳንኤል ሳምንት መካከል ላይ በዮሐንስ ለመጠመቅ ቀረበ። ዮሐንስም

የዓለምን ሁሉ ሃጢያት የሚያስወገድ የመስዋዕት በግ እንደ ሆነ መሰከረለት። ዮሐ.1፥29 የአዲስ

ኪዳን ካላንደር እንደ ሚያሳየው ኢየሱስ የተጠመቀው 30 ዓመቱ ከሞላ ከጥቂት ቀናት በኃላ ነው።

ይህም ሴፕቴምበር/ በመስከረም/ 29 A.D ላይ ነው።

ሁለት ወሳኝ የሆኑ ክንውኖች አሉ። አንደኛው የኢየሱስ በ70 ሳምንት መካከል

መጠመቁ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በ70 ሳምንት መጨረሻ ክርስቶስ መሰቀሉ ነው። በፊት ኢየሱስ

በ70 ሳምንት መካከለኛ ቀን ተሰቅሏል ብዮ እኔም ጥናቴን ከመጨረሴ በፊት አስብ ነበር። ነገር

ግን ታሪክንና የእግዚአብሔር ቃል ስመረምር ትክክለኛ መረዳት እንዳልሆነ ተገንዝቢያለሁ።

ደግሞም ኢየሱስ ከ490 ዓመት በፊት ማለት ከ 33 ኤ.ዲ በፊት መሞት እንደ ሌለበት በእርግጥ

ተገንዝቤ አምኛለሁ። ምክንያቱም የ490 ዓመት ቁጥር ሚስጥርና ትንቢት ስለሚያበላሽ ፈጽሞ

ቀኑና ቁጥሩ ከምንም የእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይገጥም ነው።

Page 10: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

9 www.tlcfan.org

ጴጥሮስ ኢየሱን ሲጠይቅ ማቴ.18፥21 ከኢየሱስ ትክክለኛውን መልስ አግኝቷል። ኢየሱስ

ይቅርታው የሚሆነው 7 ጊዜ 70 = 490 ዓመት ነው። ይህ አባባሉ ዘመንን ከማጥናቴ በፊት

የምገምተው ውስን የሆነ ነገርና ቁጥር ብቻ ነበር። ነገር ግን ዘመንን ማጥናትና መመርመር

ከጀመርኩበት ዓመት ጀምሮ ሁሉ ቁጥር በውስጡ የሰወረውን ድምፅ ሰጥቶን እንዳምን እምነተ

ጠንካራ አድርጎኛል። ለዚህም መረዳት መሰረት የሆነኝ ሕጉ ነው።

ኢዮቤልዮ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ የዘመን ቁጥር ክበብ የተቀመጠ ታላቅ

መለኮታዊ የእግዚአብሔር ሕግ መሆኑ ያስያል። 49/ 490 ዓመት የምሕረት የጸጋው ክበብ ዘመን

ነው። ሕዝቡ በዓመት አንዴ ምሕረትን ይቀበል ነበር። ይህም ሊቀ ካህኑ የፍየሉን ደም ይዞ ወደ

ቅድስተ ቅዱሳን ከገባ በኃላ ነው። ይህም ከመሰዊያው በታች ለዓመት የተጠራቀመውንም ሃጢያት

ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስተሰረይ ነው።

እግዚአብሔር ትውልድን በዓመት አንድ ጊዜ ይቅር ይላል። ይህ የዓመት ዙር በየዓመቱ

የሚደጋገም የሃጢያት ስርየት እስከ ሚያቆም ለምን ያህል ጊዜ መቀጠል አለበት? መቀጠል

ያለበት እስከ 490 ዓመት ነው። ለዚህ ነው ኢየሱስ ለጴጥሮስ አስረግጦ ቁጥሩን ያስተማረው።

ይህን መርህ ለማስተማር ወዲያውኑ ኢየሱስ ለጴጥሮስ ምሳሌ ነገሮታል። ይህን ምሳሌ ጊዜ ወስደን

ልናጠና ይገባል። ማቴ.18፥23-35 በመጽሐፍ ቅዱስ ሃጢያትም እንደ እዳ እንደሚያየው በብዙ

ጥቅስ ማረጋገጥ እንችላለን። ሰለዚህ ይህ ሰው እዳውን ፈጽሞ የሚሰረይበት ይህ 490 ዓመት

እንደ ሆነ ኢየሱስ በምሳሌው ያሳያል። ይህም ምሳሌው በደንብ በመንፈስ ቅዱስ ከተፈታል ነው።

ኢየሱስ የተሰቀለበት ቀን 490 ዓመት ፍጻሜ ነበር። ይህን ስንል የዚያን ዘመን 490 ክበብ

ማለታችን ነው። ይህ ዘመን የሚደጋገምና ዞሮ የሚመጣ ስለ ሆነ ክበብ ብዮ ጠራዋለው። ይህ

ክብ ስለሚዞር ተመልሶም በሌላ ትውልድ 490 ዓመት ሰለሚመጣ ነው። ኢየሱስ በ 490 በመሰቅሉ

እዳችንን በመስቀል ላይ በመክፈሉ ሁሉ ይቀርታን መቀበል እንዲችል አስችሎታል። የዓለምን

ሕዝቡ ሁሉ እዳ በመስቀል ላይ ከፈለው። የዳንኤል 70 ሳምንት ትንቢት ይህን የ490 ዓመት

የኢየሱስ ክርስቶስን የመስቀል ስራ ሚስጥር ለማሳየት ነው።

ኢየሱስ ብዙዎች እንደሚሉት በ70ው ሳምንት መካከል ከሞተ ይህን 490 ዓመት ሃሳብ

ያፈርሳል። ደግሞም የጥምቀቱ እለት መሰቀል ሊኖርበት ነው። ምክንያትቱ 490 ወደፊት ሲመጣ

ኢየሱስ የተጠመቀበት ቀን ላይ ይውላልና ነው። ይህ ሃሳብ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው። ኢየሱስ

የተሰቀለው እዳችንን የከፈለው በ70 ሳምንት መጨረሻ 490 ዓመት ላይ ነው። ለዚህ ነው ስቅለቱ

በ33 ኤ.ዲ እንጂ 30 ኤ.ዲ አይደለም ብዮ እኔም የማምነው። ታሪክ ራሱ ይህንን እውነት

ይደግፋል። ኢየሱስ ራሱን ለዮሐንስ ባቀረበ ጊዜ ለሕዝቡ የሚሆን መጽዋዕት መሆኑን ያሳየበት

እንጂ የሚሰዋበት ቀን አልነበረም።

Page 11: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

10 www.tlcfan.org

ወደ ምድረ በዳ የሚላከውንም ፍየል ለማመልከት ኢየሱስ እንደ ተጠመቀ ወደ ምድረ

በዳ በመንፈስ ቅዱስ ተወሰደ። ማቴ.3 ሉቃ.3 ማቴ.4፥1 ላይ መመልከት እንችላለን። ይህም

በዘሌዋውያን 16 በሕጉ የተተነበየውን ትንቢት ለመፈጸም ነው።

“7.ሁለቱንም አውራ ፍየሎች ወስዶ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በእግዚአብሔር

ፊት ያቆማቸዋል። 8. አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱን ዕጣ

ለእግዚአብሔር ሌላውንም ዕጣ ለሚለቀቅ 9. አሮንም የእግዚአብሔር ዕጣ የሆነበትን

ፍየል ያቀርባል፥ ስለ ኃጢአትም መሥዋዕት ያደርገዋል፣”

H175 shall castH5414 lotsH1486 uponH5921 the twoH8147 goats;H8163 oneH259

lotH1486 for the LORD,H3068 and the otherH259 lotH1486 for the scapegoat.H5799 "for Azazel."

በዘለዋውያን ላይ የተጻፉትን ሁለት ፍየሎች ለኢየሱስ ክርስቶስ ጥላ ናቸው። ኢየሱስም

በአዲስ ኪዳን ተገልጦ ይህንን ፈጽሞታል። የመጀመሪያው ፍየል የሕዝቡን ሃጢያት ለማስወገድ

የሚሞት ሲሆን። ሁለተኛው ደግሞ የሚለቀቅ ነበር። ኢየሱስ ራሱን ለዮሐንስና ለካህናት ፍየል

አድርጎ አቀረበ ከዛም በመንፈስ ተመርቶ ወደ ምድረ በዳ ተወሰደ። ይህም በዲያቢሎስ ይፈተን

ዘንድ ነው። “scapegoat” የሚለው ቃል ዕብራይስጡ ለአዛኤል ይላል። አዛዝኤል የዲያቢሎስ

የብሉይ ኪዳን ስሙ ነው። ሁለተኛው ፍየል በብሉይ ኪዳን የሚለቀቀው ለዲያቢሎስ ነበር።

ኢየሱስም ይህን ፈጽሟል።

“26.ለመለቀቅ የሚሆነውን ፍየል የወሰደ ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም

በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል፣”

ወደ ምድረ በዳ ኢየሱስን የነዳው ሰው ማነው? ይህ ሰው በአዲስ ኪዳን የመንፈስ

ቅዱስ ጥላ እንደ ነበር በማቴ.4፥1 ላይ ተገልጿል። ይህ ደግሞ ኢየሱስ የሃጢያት መስዋዕት ሆኖ

በአዲስ ኪዳን ተገልጾ ሁሉን በመንፈስ ቅዱስ እገዛ ፈጽሞታል። ምድረ በዳውንም ያቋረጠ በብሉይ

ኪዳን በዘለዋውያን ላይ ብርቱ ሰው የተባለው በአዲስ ኪዳን ደግሞ ብርቱ የሆነው መንፈስ ቅዱስ

ነው። የመለቀቁን ሕግ በኢየሱስ በ70 የዳንኤል ሳምንት መካከል ላይ በዮሐንስ እንደተጠመቀ

ተፈጽሟል።

Page 12: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

11 www.tlcfan.org

ኢየሱስና ሰባ ሳምንት

የዳንኤል ሰባ ሳምንት ከ26-33 A.D የተከናወነው ከኢየሱስ ስቅለት ጋር ፈጽሞ የተያያዘ

ነው። ልክ እንደዚሁ ኢየሱስ በማቴዎስ 18 ላይ ስለ 490ኛው አመት እንዲነቃና እንዲያስተውል

ጴጥሮስን አድርጎታል። ይህም ኢየሱስ በ490ኛው አመት መሰቀል እንዳለበትም ለማሳየት ነው።

ጴጥሮስ የቤተክርስቲያን ጥላ ነው። ዛሬ ቤተክርስቲያ ይህን ሚስጥር ልታውቅ ምዕመኖቿን

ልታስተምር ይገባል።

ኢየሱስ በ33 A.D እንደ ተሰቀለ ማረጋገጥ እንችላለን? አዎ እንችላለን። ይህ በመጽሐፍ

ቅዱስ ተመራራማሪዎችም ሆነ የአቢያተክርስቲያን መሪዎችና ሐዋርያት የተረጋገጠ ነው። ኢየሱስ

በ 30 ዓመቱ ተጠምቆ ለሦስት አመት ተኩል አገልግሎ ተሰቅሏል። ሉቃ.3፥23

ኢየሱስ የተወለደው የመለከት በዓል ላይ ነው። ይህም በ2ኛው B.C ላይ ነው። የኢየሱስ

ልደት በብዙ የታሪክ መጽሐፎች ተዘግቦ አይገኝም። ምክንያቱም ይህ ውልደት በታሪክ ውስጥ

ትልቅ ስፍራ ይሰጠው የነበረው ይህ ነገር ሁሉ እነርሱ እንደ ጠበቁት ቢከናወን ነበር። ነገር ግን

የኢየሱስ አመጣጥም ሆነ አወላለድ እነርሱ እንደ ጠበቁት አልተከናወነምና ብዙ የዘገባ ስፍራ

ውልደቱ አልተሰጠውም ነበርና ነው። በአንዳንድ ታሪክ መጽሐፍ ላይ ግን ከሄሮድስ ሞት ጋር

በተያያዘ መልኩ ታሪክ ላይ ስለ ሄሮድስ ሲተርኩ በዘመኑም ሄሮድስ የሰራውን ሲናገሩ የኢየሱስንም

ልደትና የሕፃናትን ማስጨረስ አዋጅ ጠቅሰውት ይገኛል። ምክንያቱም ሄሮድስ የሞተው ሕጻናቱ

ካስገደለ ከወር በኃላ እንደ ሆነ ታሪክ ይዘግባል። ካህኑ የታሪክ ጸሐፊ ጆሲፈስ ሄሮድስ የሞተው

70 ዓመት ሲሆነው እንደ ሆነ ይናገራል።

Antiquities XVII, vi, 1 says,

"And as he despaired of recovering (for he was about the seventieth year of his age), he grew fierce

and indulged the bitterest anger upon all occasions." in Wars of the Jews, I, xxxiii, 1, where he says,

"for he was almost seventy years of age."

የታሪክ ሰዎች ሄሮድስ ይህን ሥራውን የጀመረው በ25 ዓመቱ በ47 B.C እንደ ሆነ

ይናገራሉ። አባቱ በገሊላ እንዲያገለግል የሾመው በዚህ እድሜው ነበር። ሄሮስ 70 ዓመቱ በሆነ

ጊዜ 2ኛው B.C እንደ ነበር ታሪክ በእርግጠኝነት ይናገራል። ይህ ደግሞ የኢየሱስ የተወለደበትን

ዘመን ያስረዳል። ጆሲፈስ ሄሮድስ ከሞተ ከጥቂት ሳምንታት በኃላ የጨረቃ ግርዶሽ እንደ ነበርና

ከኢየሩሳሌም ይታይ እንደነበር ያናገራል።

Page 13: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

12 www.tlcfan.org

ይህ ደግሞ የበለጠ ሞቱን በሳይንሳዊ ምርምር ትክክለኛ ቀኑን ለመረዳትን እርግጠኝነቱን

ለማወቅ በተጨማሪ ያስችለናል። እነዚህን ግርዶሾች የየዘመኑ የታሪክ ተመራማሪዎች ከትንሽ እስከ

ትልቁ ሰለ ሚዘግቡት ቀኑንና ሰዓቱን የተከናወነውንም ነገር ይዘግባሉ። ይህ ቀን January 9, 1

B.C. ነው።

እውነተኛ ግርዶሽ ከሄሮድስ ሞት ቀን በኃላ ከኢየሱስም መወለድ በኃላ የሆነው ግርዶሽ

ነው። ይህም ከላይ በጠቀስኩት ቀን ላይ የተከናወነ የጨረቃ ግርዶሽ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ

የተወለደው Sept. 29, 2ኛው B.C. ላይ ነው። እንግዲህ የባዕድ አምልኮ የሆነውን የክርስቶስ

ልደት ቀን ለምታከብሩ እርግጡን እወቁት። በተወለደበትም ወቅት ሄሮድስ 70 ዓመቱ ነበር።

በጎቻቸውን በውጭ የሚጠብቁ እረኞች በተወለደ ቀን በምሽት መጥተው በግርግም

ተመልክተውታል። ሉቃ.2፥16 ከሦስት ወር በኃላ ሰባ ስገሎች መጡ በዚህ ወቅት ነው ሄሮድስ ስለ

ኢየሱስ መወለድ በይበልጥ የተረዳው። በዚህ ወቅት ሰባ ስገሎች በቤት እንጂ እንደ እረኞቹ

ማርያም፣ ዮሴፍ ህጻኑን በግርግም አላገኟቸውም። ነገር ግን ሰባ ሰገሎች በቤት አገኟቸው።

አሁንም የምስለው የሰባ ሰገሎች ስዕል የባዕድ አምልኮ ጋር መያያዙን ይህ ያጋልጣል።

ትምሕርታችን ግን እርሱ አይደለም። ማቴ.2፥11 በዚያኑ ምሽት ሰባ ሰገሎችም ሆኑ ዮሴፍ በእልም

ከእግዚአብሔር ምሪትን ተቀበሉ ሰለ ሄሮድስም እቅድ በእግዚአብሔር በህልም ተገለጠላቸው።

ማቴ.2፥12-13 ከዚህም የተነሳ ኢየሱስን ወደ ግብፅ ይዘውት ሸሹ።

ሙሴ በሦስት ወሩ ወደ ግብጽ እንደ ወረደ ኢየሱስም ወደ ግብፅ የወረደው በሦስት

ወሩ ነበር። ይህ ደግሞ ጥላው በትክክል መፈጸሙት የትንቢቱን ቅኝትና ትክክለኛነት ያጎላዋል።

ዘጸ.2፥1 ኢየሱስ ላይ የተፈጸመው ነገር በትንቢት ጥላነት ከሙሴ ጋር ተነጻጽሮ አንድ በአንድ

የሚታይ ነው። ሐዋ.3፥22,23

ሰባ ሰገሎች በ December 2ኛው B.C. ይህን የክሪስመስ በዓል አድራጊዎች ታሪክን

ዘግበው ስጦታ የሚቀያየሩበት ቀን ነው። ይህም በዓል እስከ ዛሬ ድረስ በመላው ዓለም በክርስትና

እምነት ተከታዬች ዘንድ በዲሴንበር 25 ላይ በየዓመቱ የሚደረግ ነው። ይህን ቀኑን እንድንረዳ

እንጂ እኔ ራሴ የክርሲመስን በዓል ተከታይም ሆነ አክባሪ አይደልሁም ሰጦታም አልቀበልም

አልሰጥምም። እኔ የእግዚአብሔር በዓሎች የምጠብቅና የማከብር እንጂ የታሪክ ተመራማሪ ወይም

የነገስታቶችን በዓል ተከታይም ሆነ አክባሪ አይደለሁም። ልሆንም አልፈልግም።

የአንዳንዶች ችግር ሰባ ሰገሎች በምሽት በጎቻቸውን ከሚጠብቁት ጋር መጥተዋል

ብለው ማመን ነው። ሰባ ሰገሎችና እረኞቹ የመጡበት ቀኖች የሦስት ወር ልዮነት አላቸው።

ምክንያቱም ማሪያም ኢየሱስን ወልዳ ወዲያው ወደ ግብጽ ለመውረድ የሚሆን አቅም ባልነበራት

ደግሞም መንጻትዋንና ኢየሱስን የማስገረዝን ሕግ ለመፈጸምም ባልቻለች ነበርና ነው።

Page 14: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

13 www.tlcfan.org

ነገር ግን ማርያም ሰባ ሰገለ ከመምጣታቸው በፊት የመንጻዋን ቀን ጨርሳለች ወደ

መቅደስ ወስዳ ኢሱስን አስገርዛለች። ከሽማግሌው ስምዖንም ትንቢታዊ መልዕክትም ስለ

ሚመጣው ስደትም የመገለጥን መልዕክት ከሽማግሌው ተቀብላለች። ስለዚህ ይህ ብቻ የበጎቹ

እረኛና የሰባሰገል መምጣት በአንድ ቀን እንዳልሆነ እንድንመለከት ያስችለናል። ኢየሱስ 2ኛ B.C

እንደተወለደ ብዙዎች አረጋግጠዋል። ለምሳሌ ቀጥታ የወሰድኩትን ያንብቡ፦

there were, before

the year 500, no less than ten Christian witnesses who agreed on the year in which Christ was born."

These witnesses include Tertullian, Irenaeus, and Eusebius, "the father of Church History." If Jesus

was born in September of 2 B.C., then in what year did He turn 30? Many people would do the

math and say, "28 A.D." (because 28 + 2 = 30). However, it is not quite that simple. When our

present calendar (using B.C. and A.D.) was invented in 526 A.D., they were still not using the

number ZERO. Thus, mathematicians had to move from -1 to +1 without benefit of the zero. And

chronologists had to figure from 1 B.C. to 1 A.D. directly, instead of counting -1, 0, +1, +2, etc. That

means Jesus turned 30 in September of 29 A.D., and He was 33-1/2 in April of 33 when He was

crucified at Passover.

ሌላው የኢየሱስን ልደት ቀን የምንረዳበት ከሮም ታሪክ በመነሳት ነው። መጥምቁ

ዮሐንስ አገልግሎቱን የጀመረው፦ ሉቃ.3፥1-2

“1 ጢባርዮስ ቄሣርም በነገሠ በአሥራ አምስተኛይቱ ዓመት፥ ጴንጤናዊው

ጲላጦስም በይሁዳ ሲገዛ፥ ሄሮድስም በገሊላ የአራተኛው ክፍል ገዥ፥

ወንድሙ ፊልጶስም በኢጡርያስ በጥራኮኒዶስም አገር የአራተኛው ክፍል ገዥ፥

ሊሳኒዮስም በሳቢላኒስ የአራተኛው ክፍል ገዥ ሆነው ሳሉ፥2 ሐናና ቀያፋም ሊቃነ ካህናት

ሳሉ፥ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ ልጅ ወደ ዮሐንስ በምድረ በዳ መጣ፣”

የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው ዮሐንስ የኢየሱስ የስድስት ወር ታላቁ መሆኑን

ነው። እንደ ካህን ቤተሰብ እንደ መሆኑ መጠን አግልግሎቱ የግድ የሚጀምረው እንደ ኢየሱስ

በ30 ዓመቱ ነው። ዮሐንስ አገልግሎቱን የጀመረው በ29ኛው የፋሲካ በዓል ዙሪያ ነው። ኢየሱስ

በዮሐንስ ሊጠመቅ የመጣው በመስከረም 29 (September of 29 A.D) ላይ ነው።

ጢባሪዮስ መግዛት የጀመረው አባቱ አጉስቶስ ቄሳር በነሃሴ 19,14 ኤ.ዲ (August

19, 14 A.D) ከሞተ በኃላ ነው። ይህ በሮም ታሪክ ከሚጠቀሱት ዋንኛ ቀኖች መካከል አንዱ

ነው። እጉስቶስ ቄሣር የሞተበት በ56ኛው አመቱ ነው። ይህም የፓለቲካ ሥራውን ከጀመረ በኃላ

መሆኑ ነው።

Page 15: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

14 www.tlcfan.org

(Aug. 19, 43 B.C.) የጢብሪዎስ ቀን ከ August of 28 A.D. to August of 29 A.D. ድረስ የረዘመ ሲሆን በመሃሉም 29ኛውን ዮሐንስ አገልግሎት የጀመረበትን ቀን የያዘ ነው። ስለዚህ

ይህ መሰረት በማድረግ ኢየሱስ በመለከት በዓል ወቅት በ29 A.D ሰላሣ ዓመቱ እንደ ነበር መረዳት

እንችላለን።

ኢየሱስ በዚያን ቀን የዘለዋውያን 16 ሕግ ትንቢት ይፈጽም ዘንድ ወደ ዮሐንስ ይጠመቅ

ዘንድ መጣ። ከዛም መንፈስ ይፈተን ዘንድ ለ40 ቀን ወደ ምድረ በዳ መንፈስ ነድቶ ወሰደው።

ከዛም ከተመለሰ በኃላ የእግዚአብሔርን መንግስት በመስበክ የመጀመሪያ አገልግሎቱን ጀመረ።

መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ አገልግሎቱን ከጀመረ ከጥቂት ወራት በኃላ ታስሮ በ30 A.D ፋሲካ

በዓል ላይ ተገደለ። ይህ ክንውን የሆነበትን ቀን ተነስተን 70ኛው ፋሲካ ስንመለከት 70 A.D

የሮም ሰራዊት መጥቶ ኢየሩሳሌምን ያጠፋበት ቀን ነው። አንድ ጊዜ የዘመናትን ሚስጥር ስንረዳና

መንፈሱን ስንይዘው ሁሉ ቀኖች በትክክል ይገጣጠማሉ። ይህ ደግሞ እምነታችንንና ትክክለኛ

መንገድ ላይ እንዳለን እንድናይ ይረዳናል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንቢቶች እንዴትና መቼ

እንደሚፈጸሙ ለመረዳት በቀላሉ እንድንችል የዘመናትን ሚስጥር ማወቅ ያስችለናል።

እንግዲህ የዳንኤል 70 ዓመት በApril of 33 A.D ተጠናቋል ማለት ነው። ይህም ዕዝራ

ወደ ኢየሱሳሌም የጀመረውን ተልዕኮ በጀመረ በ12ኛው ቀን ከአምተኛው ወር በኃላ በ490ኛው

ዓመት ነው። ዕዝ.8፥31 እንግዲህ ኢየሱስ የተሰቀለው በ490ኛው ዓመት የፋሲካው በግ

በሚታረድበት በመጀመሪያው ወር በ14ኛው ቀን ላይ ነው። ኢየሱስ የተሰቀለበት ቀን ለሁሉ ነገር

አስፈላጊ የሆነ ወሳኝ ዋንኛ ቀን ነው። ምክንያቱም የ40ኛው ኢዮቤልዮ መጀመሪያ ቀን ኢየሱስ

የተሰቀለበት ቀን መነሻው ስለ ሆነ ነው። ይህም ከኢየሱስ ስቅለት ቀን ተነስተን ስንቆጥር ይህ

40ኛው ኢዮቤልዮ የተፈጸመው ከ1,960 ዓመት በኃላ በእኛ ዘመን አቆጣጠር በ1993 ዓ.ም ላይ

ነው። ይህ የሌላው ኢዮቤልዮ ፍጻሜ ነው። ይህም ዘመን የመንፈሳዊ ታሪክ የከፍታ የሪቫይቫል

ዘመን ነው። ይህንንም በዘመናችን ተፈጽሞ አይተናል።

Page 16: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

15 www.tlcfan.org

የዳንኤል ሰባ ሳምንትና አሳቹ ክርስቶስ

የዳንኤል 70 ሳምንት በኢየሱስ ስቅለት ቀን እለት ተጠናቋል ብለናል። መከራ ሁሌ

ያለ ነገር ነው። መከራ በወራት ወይም በሰባት ዓመታት ብቻ የሚወሰን ነገር አይደለም። ይሁንና

ብዙዎች የመከራ ጊዜ ብለው 7 ዓመታትን ለይተው ሲናገሩ እንስማለን። ይህ የሰባት ዓመት

መከራ ከምንግዜውም የበለጠ መከራ እንደሆነና ይህ መከራ በዳንኤል 70 ሳምንት የተተነበየ ነው

ብለው ያምናሉ። ነገር ግን ልናውቅ የሚገባው የዳንኤል 70 ሳምንት ሰባት የተወሰኑ የመከራ

ወራቶች ወይም አመቶች እንዳሉ ፈጽሞ አይናገርም አየተነብይም።

ይህ ትምህርት የሚያምኑ በዚህ አያቆሙም እነዚህን ዓመታት የአሳቹ ክርስቶስ እንደ

ሆኑ ከዚህ መረዳታቸው ጋር አያይዘው ያስተምራሉ። ዘመኑን ብድግ አድርገው ለአሳቹ ክርስቶስ

ይሰጡታል። ሦስት አመት ተኩል በሰላም ሦስት አመት ተኩል ደግሞ በክፋት እንደሚገዛ

ያስተምራሉ። ይህ ደግሞ ከዳንኤል 70 ሳምንት ትንቢት ጋር ፈጽሞ በምንም የማይገናኝ ነው።

የሚደንቀው ግን ከአንድ ዛፍ ሁለት አይነት ነገር ሊወጣ ይችላል። የሚል የኢየሱስን ትምህርት

የሚቃረን ትምህርት እያስተማሩ እንዳሉ እንኳን ፈጽሞ አይረዱም። ስይጣንም ሆነ አሳች ክርስቶስ

ሰላም ሊያደርግ መቼም አይችልም። ስለዚህ ይህ ቃል ፈጽሞ ለአሳቹ ክርስቶስ ሊጠቀስ

እንደማይገባ ልናውቅ ይገባል። ሰይጣን መቼም ቢሆን መልካም ሊሆን አይችልም!!!

ብዙዎች በአለፉት ዘመናት ስለ አሳቹ ክርስቶስ ብዙ ተናግረዋል። ብዙ የቤተክርሲያን

አገልጋዮች ነን ባዮች መጨረሻቸው ውሸት ሆኖ የተገኘን ትንቢት እንደ እውነት ትንቢት

በምዕመናን መካከል በየመድረኩ ሲናገሩ ቆይተዋል። አሁን ድረስም በድፍረት በማወቅም ሆነ

እውቅት ከመጉደል የተነሳ የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው። አላዋቂዎችን ዝም እናሰኝ ዘንድ ይህ

የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው። ተብሎም ተጽፏል፦ (ጢሞ.) ይህን ለማድረግ እንትጋ።

አንዳዶች የሰዎችን የሥም ቁጥር በመደመርና በመቀነስ ከታሪካዊ ፍጥረታዊ ሁኔታ ጋር

በማነፃጸር አሳች ክርስቶስ ይህ ነው ያ ነው ብለው ሰውን ስይመው አልፈዋል። አሳቹ ክርስቶስ

ከተባሉ መካከል ሳዳም ሁሴን፣ የሮማው ጳጳስ፣ የራሻው መሪ ጎርቫቾቨ፣ ሞሶሎኒ፣ ሂትለር . . .

ናቸው። የሚያስቀው ደግሞ የራሻው መሪ የግንባሩ ለይ በመወለድ የሚመጣ ሽታ ብለን

የምንጠራው በግንባሩ ስለ ነበር የአውሬ ምልክት እንደ ሆነ የሚናገሩ መንፈሳዊ የሚባሉ ሰዎች

የጻፉትን መጽሐፍ እስካሁን በገበያ ላይ እናገኛለን። አንድን ነገር ግን አምኖ መከተል የግል ውሳኔ

ነው። እኔ በግሌ ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ ምንም ላላምን ቆርጫለው። ታሪክ ባጠና እንኳን

የእግዚአብሔር ቃል ለማጠንከር እንጂ ተቃራኒ የሆነ ነገር ላለማመን ውስኜ የእግዚአብሔርን ቃል

ብቻ እከተላለሁ።

Page 17: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

16 www.tlcfan.org

እነዚህ ሁሉ ቃሉ እንደሚገልጻቸው የባቢሎን መሪዎች እንደ ሆኑ አውቃለሁ። የምድር

ነገስታት እንደ ሆኑ አምናለሁ። ነገር ግን አሳች ክርስቶስ እንደ ሆኑ የሚያረጋግጥ ምንም ነገር

የለኝም። ምንም እንኳ ክፉ መሪዎች ቢሆኑም አንዳቸውም አሳች ክርስቶስ እንደሆኑ እርግጠኛ

ሆነን መናገር አንችልም። አሁን በቅርብ የምንሰማው ደግሞ ኦባማ እንደሆነ ነው። ይህ ተረት

ተረት ማቆምያ የለውም። እኛ ልንርቀው እንጂ ልናጠፋው አልተጠራንም ልንሰራው የተገባን

ብዙ ሌላ ስራ አለን። ነገር ግን አላዋቂዎችን ባገኘነው አጋጣሚ እውነትን በፍቅር በመግለጥ ጸጥ

ልናስደርጋቸው ይገባል።

አሳቹ ክርስቶስና በራዕይ ላይ ያለው አውሬ ፈጽመው የተለያዮ እንድ ላይ ሊጣመሩ

የማይችሉ የተለያየ ነገር የሚናገሩ ቃሎችና ትንቢታዊ ስዕሎች ናቸው። ይህን አንድ አድርጎ

መመልከት ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ ከእግዚአብሔር ትክክለኛ የትንቢት መልዕክት ቤተክርሲያን

ዞር እንድትል ተደርጋለች። ይህም ለእግዚአብሔር ትንቢት እውር አድርጓታል።

አውሬዎች በዳንኤል ትንቢት ስዕል መሰረት የስው ልጅ ትውልዶችን በእነርሱ ላይ

በእግዚአብሔር የተሾሙትና የሚሾሙት መንግስታትን የሚያሳዮ ናቸው። ዳን7,8 ለምሳሌ

የባቢሎን መንግስት ግዛትና ገዢው ናብከደነፆር በአንበሳ ተመስሏል። ሌሎቹም ነገስታት በሌላ

በሌላ መልክ ዳንኤል ምዕራፍ ሰባትን በማንበብ መረዳት እንችላለን። ለምሳሌ፦

1) ባቢሎን - አንበሳ 2) ፈርስና ሚዶን - ድብ 3) ግሪክ - አነር(የነብር ዝርያ) 4) ሮም - ስም

የሌለው የብረት ጥርስ ያለው አውሬ ተመስለው በቃሉ ውስጥ እናገኛለን።

መጽሐፍ ቅዱሳዊ የአውሬ ምስል ትርጉም ይህን ይመስላል። ባሕሪያቸው ሲገለጥ

እያንዳዱ አውሬ ለማደግና ለመበልጸግ ሲል ሌላውን አውሬ ወይም ሕዝብ ይበላል ይጨርሳል።

መልዕክቱ በአጭሩ ይህ ነው። መንግስት መንግስትን ያፈርሳል ይህም አንዱን አውሬ ገድሎ

በሞተው ሆዱን ሊሞላና የሞተውን ስፍራ ሊወስድ ነው። ይህም በወታደራዊ መልኩ ስንመለከትው

ደግሞ የሚፈልጉበት ቦታ ለመድረስ መግደል ያለባቸውን ይገድላሉ ማፈረስ ያለባቸውን

ያፈርሳሉ። ሁሉ የባቢሎን ወይም የምድር መሪዎች ያላቸው የአውሬ ልብ ነው። የባቢሎን ንጉስ

ናቡከደነፆርም ይህ ልብ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተሰጥቶት ነበር። ዳን.4፥16

አሳቹ ክርስቶስ የሚገልጠው ዮሐንስ የተጠቀመው ቃል ብቻ ነው። ይሁንና ይህ ቃል

በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ አንድ ጊዜ እንኳን ፈጽሞ አልተጠቀመውም። ዮሐንስ ይህን ቃል 4 ጊዜ

ብቻ ተጠቅሞታል። ይህም በ1ኛና 2ኛ ዮሐንስ ላይ ነው። ይህን ቃል በማጥናት አሳቹ ክርስቶስ

ምን ማለት እንደ ሆነ ሳንፈላሰፍ በግልጽ እንረዳለን። 1ዮሐ.2፥18 ወደፊት ብንኖር ጌታ እንደረዳኝ

ስለ አሳቹ ክርስቶስ በዝርዝር እጽፋለሁ።

Page 18: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

17 www.tlcfan.org

“18 ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ

እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤

ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን፣”

ይህን አይነት የተሳሳተ ትምህርት የሚያስተምሩ በዮሐንስም ዘመን ነበሩ። ስለዚህም

ነው ሰምታችኃል እኔ ግን እውነቱ እነግራችኃለ። እያለ እውነትን ለልጆቹ የሚያስተምራቸው።

የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው የመጨረሻው ቀን የጀመረው ከመስቀሉ ጀምሮ ነው።

ምክንያቱም እስራኤል ከግብፅ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ እውነተኛው ፋሲካ ኢየሱስ የተሰቀለበት

ቀን ለነገሮች ሁሉ መጨረሻና ደግሞም ዋንኛ መጀመሪያ ቀን ስለ ሆነ ነው። በዮሐንስ እይታ

መሰረት የበዓለ አምሳ ዘመን የመጨረሻው ሰዓት ነበር። በእኛ በአሁን ባልንበት ወቅትም ይህ

የመጨረሻ ሰዓት ዳስ በዓል ዝግጅት ዘመን ነው። ስለዚህም ብዙ አሳች ክርስቶሶች ተነስተው

ብናይ የሚያስደንቅ አይደለም ዘመኑ ነውና ነው።

ችግሩ ግን አንዳንድ አማኞች ይህን አሳች ክርስቶስ ከዳንኤል ሰባ ሳምንት ጋር በማያያዝ

አሳቹን ክርስቶስ ነጠላ ወይም አንድ ግለሰብ የሚገዛ ገዢ በማድረግ መሳላቸው ነው። ይህ ከቃሉ

ፈጽሞ የራቀ ነው። ይህን የመሰለ ስዕል በቅዱሳኑ ፊት በመሳሉ የተነሱትን ብዙዎች የክርስቶስ

ተቃዎሚዎች አሳች ክርስቶስ በዙሪያቸው አሁን እየሰሩ ያሉትን ነገር መመልከት እንዳንችል

ምዕመናንን አሳውሯቸዋል። ምክንያቱም ብዙዎች የዳንኤል 70 ሳምንት መፈጸሙን ሰለማያውቁና

ነገር ግን ገና እንደሚፈጸም ስለ ሚጠብቁ ነው። የእግዚአብሔር ቃል የሚናገረው እርግጠኛው

ትንቢት ግን የዳንኤል 70ሳምንታት ኢየሱስ በተሰቀለ ጊዜ ተፈጽሟል። ይህም ትንቢት

የተፈጸመመበት ዘመን በ33 A.D ነው። ዮሐንስ አሳቹን ክርስቶስ በደንብ አድርጎ ሰው በሚረዳው

መልኩ ይገልጣቸዋል በግልጽ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ አስቀምጧቸዋል። 1ዮሐ. 2፥22,23

“22 ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው?

አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።23 ወልድን የሚክድ ሁሉ

አብ እንኳ የለውም፤በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው፣”

ዮሐንስ በዚህ ጥቅስ ላይ እየተናገረ ያለው ኢየሱስ ቀደም ብሎ ያስተማረውን ትምህርት

መሰረት በማድረግ ነው። ዮሐ.8፥19

“19 እንግዲህ። አባትህ ወዴት ነው? አሉት። ኢየሱስ መልሶ። እኔንም ወይም

አባቴንም አታውቁም፤ እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር አላቸው።

20 ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር በግምጃ ቤት አጠገብ ይህን ነገር ተናገረ፤

ጊዜው ገና አልደረሰምና ማንም አልያዘውም።”

Page 19: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

18 www.tlcfan.org

አይሁዶች ኢየሱን ተቃውመውት ነበር ምክንያቱም አብንም አያውቁትም ነበርና

ነው። ይህ ቃል በዮሐ.16፥3ና በ17፥3 ላይ ሊረጋገጥ የሚችል ነው። እነዚህ ኢየሱስን የተቃወሙ

መሪዎች ጻፎች፣ፈሪሳዊያንና ሰዱቃዊያን በዚያን ዘመን የነበሩ አሳች ክርስቶሶች ናቸው። ዮሐንስ

ትምህርቱን በመቀጠል በ1ዮሐ.1-3 ኢየሱስ በሥጋ እንዳልተገለጠ የሚያምን እርሱ የአሳቹ

ክርስቶስ መንፈስ ነው ብሎ ማረጋገጫን ይሰጣል። በ2.ዮሐ.7 ላይ “ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም

ገብተዋልና እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው። ይህ አሳቹና

የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው።” ብሎ እርግጡን ያስቀምጣል።

ይህ ዮሐንስ ያስቀመጠው ስለ አሳቹ ክርስቶስ በግልጽ የሚናገር አሻሚ ያልሆን

ትክክለኛ ትርጉምና ማብራሪያ ነው። ከዚህ የወጣ ማብራሪ መፈለግ ስህተት ነው። የእርሱ ተቀዋሚ

መታወቂያው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሆነና በሥጋ እንደ መጣ የማያምን ሁሉ የክርስቶስ ተቃዋሚ

ነው። ይህ የዮሐንስ ስለ አሳቹ ክርስቶስ የሰጠው ዝርዝር በዘመኑ አይሁዶችን አስቆጥቶ እንደ

ነበር ታሪክ ይዘግባል። ይህ እውነት ለዚህ ዘመን ፈሪሳዊዎችና የሃይማኖት መሪውዎች አሁንም

እንዲሁ ነው።

የክርስቶስ ተቃዋሚዎች የሆኑ እንዲገለጡ ስለማይፈልጉ ነው። የእግዚአብሔር ያልሆነ

ትንቢት ሕዝቡን ተስፋ እያስደረጉ ቅዱሳን በዙሪያቸው እየሆነ ያለውን መመልከት እንዳይችሉ

አይናቸውን ያሳውሯቸዋል። እንግዲህ እርግጡ ይህ ነው። አሳች ክርስቶስ አንድ ግለሰብ

አይደለም። አሳች ክርስቶሶች አሁንም በዚህ ዘመን ያሉ ብዙ ናቸው። ነገር ግን እነዚህን

ሃይማኖተኞች እርስ በእርስ አያይዞ ያለው የሃይማኖት ስርዓት ራሱ የአሳች ክርስቶስ መንፈስ

ነው። አሳቹ ክርስቶስ ደግሜ እላለሁ አድ አካል ይዞ ሊመራ ወደፊት የሚወለድ ሰው አይደለም።

ሊሆን ፈጽሞ አይችልም።

በዚያን ዘመን ይህን አሳች ክርስቶስ ሰው ብናደርገው ሊሆን እንኳ የሚችለው የሃይማኖት

መሪ የተበለውን ሊቀ ካህኑን እንጂ ጨካኝ ገዢ ወይም የሰይጣን ልጅ....ወዘተ አይደለም። አሳች

ክርስቶስ መጀመሪያውኑ በሃይማኖት ጥላ አሳውሮ ራሱን ሸፋፍኖ በፊትም አሁንም ያለ በጊዜው

የሚገለጥ እንጂ የሚወለድም ወደ ፊት የሚመጣ አይደለም። መንፈሱ አሁንም በተለያዮ ሰዎች

ላይ ይሰራል።

እዚህ ነጥብ ላይ ከመጣን አሳቹ ክርስቶስ የሚለው የግሪኩን ቃል ፈተን ደግሞ

እንመልከተው። ግሪኩ እንደሚያስቀምጠው አማርኛችንም ሆነ እንግሊዘኛው አያስቀምጠውም።

ተቃዋሚ የሚለውን ቃል ግሪኩ የሚለው “ፋንታ” የሌላውን ስፍራ ተክቶ መውስድ ብሎ ነው።

ይህን ቃል በማቴ.2፥2 ላይ “ በአባቱ በሄሮድስ ፋንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሰ...” በሚለው

ቃል ላይ ተጠቅሶ እናገኘዋለን።

Page 20: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

19 www.tlcfan.org

ይህ ቃል አሳቹን ክርስቶስ የሚለውን እንደተረጎምን ብንተረጉመው ኖሮ አርኬላዎስ

የሄሮዶስ ተቃዋሚ ልንለው ይገባን ነበር። ነገር ግን ይህ ስፍራ ላይ ግርኩ በትክክል ወደ

እንግሊዘኛም ወደ አማርኛም ተተርጉሟል። አሳቹ ክርስቶስ የሚለውም ቃል እንዲ ሊተረጎም

ይገባው ነበር። ትክክለኛው ትርጉሙ ሊሆን የሚገባው በኢየሱስ ፈንታ የሚለው ቃል ነበር እንጂ

ከኢየሱስ ጋር ጡጫ ሚገጥም አይደለም። ይህም ፋንታ ወይም ምትክ የሚለው ቃል በግሪኩም

ሆነ በአማርኛው በሚገርም ሁኔታ ሁለት ትርጉም ያለው ነው። ልዮነቱ አማርኛው ቃሉን

በማጥበቅና ማላላት የሚገኝ ትርጉም ሲሆን የግሪኩ ግን አንዱ ቃል አንድ ድምፅና ሁለት ትርጉም

አለው። ለዚህ ነው ኢየሱስ ጻፎችና ፈሪሳዊያንን በክርስቶስ ፋንታ ወይም አሳች ክርስቶሶች

እንደሚሆኑ ሰለሚያውቅ እንዲ ብሎ ምሳሌያዊ ትንቢትን ተናገረባቸው መሰለባቸው።

“እርስ በእርሳቸው ወራሹ ይህ ነው ኑ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ ተባባሉ፣

ይዘውም ከወይኑ አታክልት አወጡ ገደሉትም።” ማቴ.21፥38

ይህ ሁሉ ነገር ኢየሱስ እንደ ተነበየው አንድ በአንድ በእነረሱ ተፈጸመ። የወይን

አትክልት ከሆኑት ከአማኞች ከሐዋርያት መካከል አውጥተው ኢየሱስን በውጭ ገደሉት። የገደሉት

ማን እንደ ሆነ ሰላላወቁት እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባል። ማን እንደ ሆነ ጠንቀው ያውቃሉ።

ሥራውም ማንነቱን ሰለገለጠላቸው ገደሉት አውቀው መካዳቸው አሳች ክርስቶስ አደረጋቸው።

የእርሱን ስፍራ በጉልበት ነጣቂዎች አደረጋቸው። ግዛቱ ይወስዱ ዘንድ ርስቱን ይካፈሉ ዘንድ

እያወቁ ገፉት ተቃወሙት ገደሉት። የኢየሱስ ምሳሌ ባሕሪያቸውንና ሥራቸውን የልብ ሃሳባቸውን

ሁሉን እያወቁ ማድረጋቸውን ገለጠ።

እንግዲህ በዚያ ዘመን የነበሩ ሊቀ ካህኖች በዚያ ዘመን ለነበረው ለአሳቹ ክርስቶስ አሰራር

“system” አካል ነበሩ። እነርሱም የኢየሱስን ዙፋን ለጊዜው ገልብጠው በምትክነት ገዝተውበታል።

ይህ በሉይ ኪዳን የሆነ በአዲስ ኪዳን ደግሞ በእነርሱ የተደገመ ነው። አቢሴሎም የዳዊትን ዙፋን

ለጊዜው ገልብጧል። ለጊዜውም ነግሷል። ይህንንም ያደረገው በአኪጦፌል እርዳታ ነበር።

ካህናቶቹ ደግሞ በአስቆርቱ ይሁዳ እርዳታ ነበር። አኪጦፌልም ሆነ ይሁዳ አሟሟታቸው አንድ

ነበር። የካህናቶቹና የአቢሲሎምም መጨረሻም አንድ ነው። አኪጦፌል የዳዊት ጓደኛ እንደ ነበር

ሁሉ አስቆርቱ ይሁዳ እንዲሁ ነበር። ማቴ.26፥50

ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ይለዋል።- “የአመጽ ልጅ”

"Day of the Lord," as a time when "the apostasy [apostasia, "the casting away"]

comes first and the man of lawlessness is revealed [unveiled; exposed], the son of perdition."

Page 21: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

20 www.tlcfan.org

ይህ ጥቅስ በብዙዎች ዘንድ የተሳሳተ ትርጉም ይሰጠዋል። ከሐዋርያው ትክክለኛ ሃሳብ ስንነሳ

የሚያወራው ስለ ባሪያይቱ ኢየሩሳሌም “አጋር” ልጇ አይሁድ “እስማኤልን” ነው። ይህ ገላ.4፥25-31 ላይ

በግልጽ ተቀምጧል። ይህ በዚያን ዘመን ለነበሩም መሪዎች ጻፎችና ፈሪሳዊያን እና ለአስቆርቱ ይሁዳ

“የአመጽ ልጅ” "son of perdition" ዙፋኑን ለጊዜው ለመገልበጥ ለረዳቸው ለእርሱ ምሳሌ ነው። ዮሐ.17፥

12 ይህ የአመጽ ልጅ አሳቹ ክርስቶስ ወይም አንድ ቀን የሚወለድ አድርገው የሚጠብቁት ሰው አይደለም።

የእግዚአብሔር ቃን አጋር ከነ ልጇ እስማኤል ይዛ ስትወጣ ያያል። ይህም በዘመኑ ያለችውን

ዘመናዊዋን አጋርን እንድተጸና የእግዚአብሔር መንግስ ዋና ከተማ ልታደርጋት የምትጥረውን የዘመኗን

ቤተክርሲያን ያሳያል። ነገር ግን ኢየሩሳሌም መልሳ አትገነባም። ይህም በእግዚአብሔር በኢሳያስና

በኤርሚያስ በኩል የተነበየው ትንቢት ፍጻሜ ነው። ኢሳ.29,34, ኤር.19

ሌላ የአሳቹ ክርስቶስ መገለጫ አለ። ማንኛውም ሰው ጅርጅት የክርስቶስን ስልጣን የሚቃወም

እርሱ ከአሳቹ ክርስቶስ ወገን የሚመደብ ነው። ነገር ግን ዮሐንስም ቢሆን ጳውሎስ የተጨነቁትና ሕዝቡን

ያነቁና ያስተምሩ የነበሩት በኢየሩሳሌም ስለ ነበረው አሳቹ ክርስቶስ ነው።

Page 22: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

21 www.tlcfan.org

የዳንኤል ሰባ ሳምንት መጀመሪያና መጨረሻ

የዳንኤል ሰባ ሳምንታት መጀመሪያና መጨረሻ ዘመንና ቀን አላቸው። ይህ ሳምንት

ወይም ዘመን የጀመረው በ 458ኛው B.C. ላይ የፋርስ ንጉስ አርጤክስስ ዕዝራን ወደ ኢየሩሳሌ

ሲሰደው ነው። ይህም ዘመን ንጉሱ በመግዛት ሰባተኛ አመቱ ላይ ሳለ ነበር። የዳንኤል ሰባ ሳምንት

ደግሞ የተፈጸመው በ33ኛው A.D. ላይ ነው።

ከላይ እንዳየነው ሁለተኛው መጀመሪያ ደግሞ 445ኛው B.C. ሲሆን ይህም ንጉሱ

በ20ኛው የግዛት ዘመኑ ነህሚያን የኢየሩሳሊምን ቅጥር እንዲቀጥር ሲልከው ነው። ይህ ደግሞ

በ46ኛው A.D. ላይ ተፈጽሟል። ይህም ሐዋርያው ጳውሎስ ከበርናባስ ጋር የተላከበት ዘመን ነው።

ከላይ ባጠናነው ክፍሎች የፋርስ ካላንደርንና ታሪክን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር

በማነጻጸር የሰባውን ሳምንት መጀመሪያ ዘመኖች እውነተኛ የሆኑት የቶቹ እንደ ሆኑ አሳይቻለሁ።

ይህንንም የጨረቃን ግርዶሽ በመልከትም ነበር። የጳውሎስ ተልኮ በ46ኛው A.D. እንደ ነበር

ማረጋገጥ እንችልለን። ምክንያቱም አዲስ ኪዳን ይህን ያሳየናልና ነው።

የሐዋርያ ጳውሎስ የመጀመሪያ ሥሙ ሳዖል ነው። የእስጢፋኖስን ሲወገር መወገሩን

የደገፈ ሰው ነው። ሐዋ.8፥1 ቅዱሳንን ሁሉ በየስፍራው ሲያሳድድ ቆይቷል። ይህም እርሱና

የእርሱ እምነት ተከታዮች የክርስቲያኖች መንገድ ስህተት ነው ብለው ስለ ሚያምኑ ነበር። ጳውሎስ

የራሱም ምስክርነት ለገላትያ ሰዎች ይሰጣል።፦ ገላ.1፥13,14

“12 ኢየሱስ ክርስቶስ ገልጦልኛል እንጂ እኔ ከሰው አልተቀበልሁትም

አልተማርሁትምም። 13 በአይሁድ ሥርዓት በፊት እንዴት እንደ ኖርሁ ሰምታችኋልና፤

የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ያለ ልክ አሳድድና አጠፋ ነበር፥

14 ለአባቶችም ወግ ከመጠን ይልቅ እየቀናሁ በወገኔ ዘንድ በዘመኔ

ካሉት ብዙዎችን በአይሁድ ሥርዓት እበልጥ ነበር።”

በ 1.ተሰ.2፥14 በሕይወቱ ከነበረው ልምዱ በመነሳት እንዲህ እያለ ምስክርነቱንና

እውነቱን ይናገራል፦

“14 እናንተ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በይሁዳ የሚኖሩትን በክርስቶስ ኢየሱስ

ያሉትን የእግዚአብሔርን ማኅበሮች የምትመስሉ ሆናችኋልና፤ እነርሱ

ከአይሁድ መከራ እንደ ተቀበሉ፥ እናንተ ደግሞ ያንን መከራ ከአገራችሁ

ሰዎች ተቀብላችኋልና። 15 እነዚያም ጌታን ኢየሱስን ደግሞ ገደሉ ነቢያትንም

እኛንም አሳደዱ፥ እግዚአብሔርንም ደስ አያሰኙም፥ ሰዎችንም ሁሉ ይቃወማሉ፥”

Page 23: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

22 www.tlcfan.org

ጳውሎስ በደማስቆ መንገድ ላይ ፈጽሞ ተለወጠ። ሐዋ.9 ይህ ክርስቲያንን የማሰር

ተልኮውን ለመፈጽም በጉዞ ላይ ሳለ የሆነ ነው። የሚያንጸባርቅ ብርሃን በዙሪያው አበራ። ኢየሱስ

ሲናገረው ሰማ። ለጊዜውም እውር ሆነ። ከዛም በሌሎች ሰዎች እየተመራ ወደ ደማስቆ ገባ።

በዚያም በይሁዳ ቤት ተቀመጠ። 9፥11 እዚህ ላይ ነበር ሳዖል ለቤተክርሲያ እውርነት ጥላ ምሳሌ

ሆኖ የነበረው። ይህች እውር የሆነች ቤተክርሲያን የምትኖረው በይሁዳ ቤት ውስጥ ነበር። ይህም

የይሁዳ የክርስቶስ ሻጭ ምሳሌ ነው። “ለአሁን ዘመን የተሰወረ ትንቢት” የሚለውን በሐዋርያት

ስራ ላይ ያተተኮረውን መጽሃፌን ያንብቡ።

ከዛም እግዚአብሔር ሐናንያን ለሳዖል እንዲጸልይለት ላከው። የሳዖል እውርነት

በሦስተኛው ቀን ተፈወሰ። ሐዋ.9፥9 ይህ ትንቢት እንደ ሆነ አምናለሁ። ይህም ቤተክርሲያን

ለ3ሺ ዓመት እንዴት እውር እንደምትሆን የተተነበየ ጥላዊ ትንቢት ነው። ይህም አንዱን ቀን

እንደ አንድ ሺ ስናደርግ ነው። ይህም ጴጥሮስ በተሰጠው ቁልፍ በከፈተው መረዳት ቁልፍ ስንገባ

ነው። 2.ጴጥ.3፦8

ሳዖል ክርስቲያን እንደ ሆነ ወሬው ሲወጣ ከደማስቆ መውጣት የግድ ሆነበት። አሳዳጅ

የነበረው አሁን ራሱ ተሰዳጅ ሆነ። ከደማስቆም አምልጦ ወደ አረባ ሄደ። ገላ.1፥17 በዚያም

ለሦስት ዓመት ቆየ ቁ.18 በአረባም በምትገኘው በኮሬብ እንደ ነበር ይነገራል። ገላ.4፥25 ይህ

ስፍራ ሲና ነው። ምክንያቱም ትክክለኛው ሲና ያለችው በአረብ በምድያም ምድር ነውና ነው።

ዘጸ.2፥14,15

“25 ይህችም አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ ሲና ናት፤

አሁንም ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና።

26 ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት የምትኖር ናት እርስዋም እናታችን ናት፣”

“4፤ ያም። በእኛ ላይ አንተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደረገህ?

ወይስ ግብፃዊውን እንደ ገደልኸው ልትገድለኝ ትሻለህን? አለው።

ሙሴም። በእውነት ይህ ነገር ታውቆአል ብሎ ፈራ። 15፤ ፈርዖንም ይህን

ነገር በሰማ ጊዜ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ። ሙሴ ግን ከፈርዖን ፊት ኰበለለ፥

በምድያምም ምድር ተቀመጠ፤ በውኃም ጕድጓድ አጠገብ ዐረፈ።”

ስለዚህ ሳዖል የእግዚአብሔርን ሕግና ቃል ሲያጠና እንደቆየ እርግጥ ነው። አሁን ጃቤል

አል ላዋዝ በመባል የምትታወቀው የቀድሞዋ ኮሬብ ሲና ነች። Jabal al-Lawz. (ይህን በእርግጠኝነት

ማረጋገጥ ከፈለጉ የዚህን ሰው መጽሐፍ ያንብቡ፦ (Howard Blum's book, The Gold of Exodus, the

Discovery of the True Mount Sinai.)

Page 24: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

23 www.tlcfan.org

ሳዖል ስለ ሁለቱ ኪዳንና ስለ ጸጋና ሕግ ራዕይንና መረዳትን የተቀበለው እዚያ ሆኖ

ሳለ ነው። ይህን ከማንም ሰው አልተማረውም ሌሎች ሐዋርያት እንኳን ይህን ሚስጥር

አላስተማሩትም ይህን እርሱ ከክርስቶስ እንደተቀበለው የመሰክራል። ገላ.1፥16,17

ሦስት ዓመት በጌታ እግር ሥር ከተማረ በኃላ በመጀመሪያ ወደ ደማስቆ ከዛም ተደብቆ

ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። በኢየሩሳሌምም ለመጀመሪያ ጊዜ የጌታ ሐዋርያትን አገኘ። ገላ.1፥18

ከጴጥሮስ ጋር ለ15 ቀን ያህል ቆየ። ከዛመ ከኢየሩሳሌም ከወጣም በኃላ ወደ ጠርሴስ ሄደ። ብዙ

ዓመትም በጠርሴስ ቆየ። በቆይታውም ወቅት በድንኳን በመስፋት ራሱንና ሌሎችን ያስተዳድር

ነበር።

ከዚያም በኃላ መነቃቃት ሆነ ይህም መነቃቃት ከአንጾቂያ የራቀ አልነበረም።

የኢየሩሳሌም ቤተክርሲያን ምስክርነት እንዲሰበስብና የአገልግሎት እገዛ እንዲያደርግ በርናባስን

ላኩት። በርናባስም ሳዖልን ሊያመጣ ወደ ጠርሴስ ወረደ። ምክንያቱም የሳዖል ምስክርነት

በአንጾቅያ ላሉ አይሁዶች መቀየር የደረገው አስተዋጽኦ ታላቅ ነበር። ሳዖል ዓመቱን በሙሉ

በአንጾቂያ ቆየ። ሐዋ.11፥26 ይህም በአጋቦስ የሳዖልን ህይወት የሚለውጠው የጌታ ቃል

ከመምጣቱ በፊት ነበር። ሐዋ.11፥27,28

“27 በዚያም ወራት ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤

28 ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነሥቶ

በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ፤

ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ። 29 ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው

እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች

እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ፤ 30 እንዲህም ደግሞ አደረጉ፥

በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት፣”

ከዛም በአንጾቅያ የሚገኙ ክርስቲያኖች አስቀድመው ለኢየሩሳሌም መዋጮን ላኩ።

ይህም ረሃቡ እንደሚመጣ ከጌታ አስቀድመው ስለ ተረዱ ነው። ይህ መዋጮ ወደ ኢየሩሳሌም

የተወሰደው በሳዖል፣ በበርናባስና ቲቶ ነበር። ይህ የጉዞ ቀን በገላትያ 2፥1 ቀኑ ተቀምጧል።

“1 ከዚያ ወዲያ ከአሥራ አራት ዓመት በኋላ ከበርናባስ ጋር

ቲቶን ደግሞ ይዤ ወደ ኢየሩሳሌም ሁለተኛ ወጣሁ።”

"Then fourteen years after ["within fourteen years"--Wilson's The Emphatic Diaglott]

I went up again to Jerusalem with Barnabas, and took Titus with me also."

Page 25: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

24 www.tlcfan.org

ከዚያም በኃላ ገንዘቡን አድርሰው ወደ አንጾቂያ ድጋሚ ሲመለሱ ሳዖልና በርናባስ

ለጌታ ሥራ ተልኮ ተለዮ። ሐዋ.13፥2 ለሳዖል ተልኮን ያመጣው እንዲሁ ደግሞ ሥሙን ከሳዖል

ወደ ጳውሎስ ጌታ የለወጠለት በዚሁ ቀን ነው። ቁ.9 ከዚያን በኃላ ሳዖል ተብሎ መጠራት አቆመ

በሐዋርያት ሥራም ከዚያ በኃላ ሥሙን ሳዖል ብሎ ሲጠራው አንመለከትም።

የጳውሎስ ተልኮ የሆነው በክላውዲዮስ ዘመን የሆነው ረሃብ ከመሆኑ ከጥቂት ጊዜ በፊት

ነው። ክላውዲዮስ የሮማ ገዢ በግዛትይ የነበረው በነዚህ ዘመኖች መካከል ነው። 41- ይህ

ረሃብ በጆሲፈስ መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል።

ከመጽሐፉ በቀጥታ የተወሰደውን ቃል ከታች ያንብቡ፦

"Now her coming was of great advantage to the people of Jerusalem; for whereas a famine did

oppress them at that time, and many people died for want of what was necessary to procure food

withal, queen Helena sent some of her servants to Alexandria, with money to buy a great quantity

of corn, and others of them to Cyprus, to bring a cargo of dried figs. . . And when her son Izates

[the king] was informed of the famine, he sent great sums of money to the principal men in

Jerusalem."

የጆሲፈስ በመጽሐፍ ተርጓሚ ከዚህ ቃል በታች የግርጌ ሃሳቡን እንዲህ ብሎ

ያስቀምጣል። ይህም ይህ ረሃብ በአጋቦስ የተረገረው ትንቢት እንደ ሆነ እውቅናን ይሰጣል።

"Dr. Hudson's note here: 'This,' says he, 'is that famine foretold by Agabus, Acts xi. 28, which

happened when Claudius was consul the fourth time, A.D. 47'. . . ."

ጳውሎስ በተለወጠ በ14ኛ ዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተላከ። ይህም በ33 – 47 ዘመን ላይ

ነው። ይህም ሊመጣ ላለው ረሃብ ቅዱሳን ክርስቲያኖች ዝግጅት እንዲያደርጉ ለማሳሰብና እርዳታን

ለመስጠት ነው። ምክንያቱም ረሃቡ ቶሎ የሚሆን ነበርና ነው። ረሃቡም በ46 A.D. አጋቦስ

እንደተናገረው ሆኗል። ከዚያም የእርዳታ ገንዘብ አድርሶ እንደ መጣ ተላከ ሥሙ ጳውሎስ ሆነ፦

ተቀየረ።

ይህ ነህምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንዲሰራ ከተላከበት ቀን አንስቶ ጳውሎስ የተላከበት

ቀን በትክክል 490ኛው ዓመት ላይ ነው። ይህም በ46-47ኛው A.D ነው። ጳውሎስ የኢየሩሳሌምን

ቅጥር እንዲሰራ ተላከ። ዘመኑ በሚገርም ሁኔታ በትክክል የተጋጠመ የተፈጸመ ነው። ይህ በራሱ

ትንቢታዊ መልዕክትን ለእኛ ይዟል። አርባ ኢዮቤልዮ ፍፃሜ እኛ አሁን ባለንበት ዘመን በ2006-

2007. (40 x 49 = 1,960 ዓመታት) እንዲሆን ያደርገዋል።

Page 26: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

25 www.tlcfan.org

2006 ዓ.ም የ 2,520ኛው በሐጌና ዕዝራ የተገነባው የሁለተኛው ቤተመቅደስ በዓል ቀን

ነበር። የሐጌ ትንቢት እንግዲህ በ2006 ፍጻሜን አግኝቷል። እንዲሁ ደግሞ 2006 የ13ኛ አመት

የኢያሪኮ ሰልፍና መዞር ፍጻሜ ነበር።"Jericho march" ይህም በባቢሎን ዙሪያ በNovember 1993,

40ኛው ኢዮቤልዮ ጀምሯል። የበዓለ አምሣ ኢዮቤልዮ በ 33ኛው A.D በሐዋ.2 ላይ ጀምሯል።

በኢያሪኮ ዙሪያ የተደረገ የ13 ጊዜ የዙር ሰልፍ ተፈጽሟል። ይህን ትንቢታዊ ጥላ መፈጸሙን

ቀድመው በነበሩት ዓመታት ተመልክተናል። እንግዲግ ትንቢታዊ የዘመን ዙረት ሂደት ፍጻሜ

ላይ እንደ መጣን አውቀን ልንነቃ ይገባል።

Page 27: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

26 www.tlcfan.org

ኢዮቤልዮና የዳንኤል ሰባ ሳምንት

የዳንኤል 70 ሳምንታት በአጠቃላይ 10 ኢዮቤልዮች ናቸው። አንድ ኢዮቤልዮ ዘመን

49 ዓመታት ናቸው። ይህም በራሱ በኢዮቤልዮ የመጨረሻው አመት 50 ይሆናሉ። አንድ

ኢዮቤልዮ 49 ዓመታት ይሁን እንጂ ሙሉ ኢዮቤልዮ 50ኛው ዓመት ነው። ነገር ግን 50ኛው

ዓመት ደግሞ ራሱ ለሚመጣው ኢዮቤልዮ አንደኛ የኢዮቤልዮ ዓመት ነው። ይህም ማለት

ለሚመጣው ሳምንት መጀመሪያ ቀን ነው ማለት ነው።

ስለዚህ አስር ኢዮቤልዮ 500 ዓመታት ናቸው። ነገር ግን የኢዮቤልዮ ዓመት በ491ኛው

ዓመት መጀመሪያ ላይ ይጀምራል። በዚያም ሃይማኖታዊ ባዕላቶቹ ይጀምራሉ። ወሮቹ የዓመቱ

ሰንበት በመባል ይቆጠራሉ። ይህም በመስከረም በሰባተኛው ወር የሚጀምር ነው። ይህም የመከር

መሰብሰቢያ የመጨረሻ ወቅት ነው።

ስለዚህ የዳንኤል 70 ሳምንት በኢዮቤልዮ መሰረት ሊታዮ ይገባቸዋ። ኢየሱስ ሲሞት

የኢዮቤልዮ ሰዓት ነበር። ምክንያቱም የእርሱ ሞት እዳን ሁሉ ከፍሎ ሁሉን ነጻ አውጥቷልና ይ

የኢዮቤልዮ ሕግም ፍጻሜ ነው።

ይህ እዳ የዓለም ሁሉ ሃጢያት ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ እዳችንን ከፍሎ ነጻ

አወጣን። ስለዚህ ኢየሱስ የእኛ ኢዮቤልዮ ነው። የሞተው በ490ኛ የኢዮቤልዮ ዘመን ላይ ነው።

ነገር ግን ይህ የታሪክ ሁሉ መጨረሻ አይደለም። ምክንያቱም የመንግስቱ ዙፋን በሃይማኖት

መሪዎች ተገልብጧል ወይም ተወስዷልና ነው። ማቴ.21፥38 ንጉሱ በውሸት ተከሶ ተሰቅሏል።

በመጠቀም ጥቅሱን ይመልከቱት ዳን.9፥26 እንዲህ ያስቀምጠዋል።

ከትውልድ መሃል የተወገደው መሲሁ ኢየሱስ ከቅድስቲቱም ከተማ ተወግዷል። ምክንያቱም ይህ

ነው፦

"And after the sixty and two weeks, cut off is the Messiah,

and the city and the holy place are not his

“26፤ ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥

በእርሱም ዘንድ ምንም የለም፤ የሚመጣውም አለቃ

ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ፤

ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥

እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤

ጥፋትም ተቀጥሮአል።”

Page 28: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

27 www.tlcfan.org

በሌላ አነጋገር የኢየሩሳሌም መፍረስ ከመሲሁ መሞት ጋር ተያይዟል። የዘመኑ ካህናት

በውሽት ከሰሱት ይህም ለሞት ቅጣት የሚያበቃ ክስ ነበር። መለኮታዊውም ፍርድ ቤት ደግሞ

ፍርድን ስለ እርሱ በዚያን ወቅት አስተላልፎ ነበር። ይህም የከተማዋ መፍረስ የሕዝቡም መበታተን

ነው። ዘዳ.19፥16,19 ይህም የእግዚአብሔር ሕግ ምላሽ ነበር፦

“15፤ ስለ በደል ሁሉ፥ ክፉ በማድረግም ስለ ሠራት ኃጢአት ሁሉ በማንም ላይ

አንድ ምስክር አይቁም፤ በሁለት ምስክሮች ወይም በሦስት ምስክሮች አፍ ነገር

ሁሉ ይጸናል። 16፤ በዓመፃ ይከስሰው ዘንድ በሰው ላይ ሐሰተኛ ምስክር ቢቆም፥

17፤ ሁለቱ ጠበኞች በእግዚአብሔር ፊት በካህናቱና በዚያ ዘመን በሚፈርዱ ፈራጆች

ፊት ይቆማሉ፤ 18፤ ፈራጆቹም አጥብቀው ይመረምራሉ፤ ያም ምስክር ሐሰተኛ ምስክር

ሆኖ በወንድሙ ላይ በሐሰት ተናግሮ ቢገኝ፥ 19፤ በወንድሙ ላይ

ያደርገው ዘንድ ያሰበውን በእርሱ ላይ ትመልሱበታላችሁ፤ እንዲሁም

ከአንተ መካከል ክፋቱን ታስወግዳለህ፣”

ቤተክርሲያ ባለፉት ዘመናት ኢየሩሳሌምን የመሲ ገዳይ የኢየሱስ ጠላት በማለት

የተለያዮ ሰሞች በመስጠት ስታወግዛት ቆይታለች። ይገባ የነበረው ግን እግዚአብሔር ምሕረትን

እንዲያደርግላት መለመን ነበር። ይህም የእግዚአብሔር ፍርድ ቅጣት እንዲቆምላት ለመማለድ

ነው። ይህን የሌለ ሥም ቤተክርሲያን ለእነርሱ በመስጠቷ ለንስሃ ልታበቃቸው አልቻለችም።

በተራዋ ደግሞ ቤተክርሲያን በአንደበት እሳት እነርሱን ገረፈች፣ አሰቃየች፣ አሳደደች። ይህ ሁሉ

በእግዚአብሔር አይን ትክክል ያልነበረ ነው። ይህ አይነቱ የቤተክርሲያን እርምጃ ጥላቻን፣

አመጽን፣ አይማኖታዊነትን ጎልቶ እንዲወጣ አድርጎታል።

ይሁንና በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እግዚአብሔር አይናቸውን እንዳሳወረው የሚናገር

ቃል እናገኛለን። ይህ ደግሞ በአጠቃላይ ዕውርነት በላያቸው ላይ እንደ መጣ ቃሉ ይናገራል

ማለት ነው። አሁንም ቢሆን በዕውርነታቸ ልንሰድባቸው አይገባም። እንደሚገባ በፍቅር ከእነርሱ

ጋር ልንኖር ይገባል። ይህ ማለት ሃጢያተኛ እያሉ በአመጽ እያሉ ጻድቃን እንላቸዋለን ማለት

አይደለም። በኢየሱስ ላይ የመሰከሩት የሃሰት ምስክር ይቅር እንላቸዋለን ማለት አይደለም። ነገር

ግን ይህ ሁሉ በእግዚአብሔር የዘላለም እቅድ ውስጥ እንዳለ በማመን ከሰው ሁሉ ጋር አባታችንን

በቃሉ እንዳዘዘን በሰላም ለመኖር እንተጋለን ማለት ነው። ይህም ምሕረትን እንዳባታችን በመከተል

ነው።

እግዚአብሔር ከሞተ አንበሳ ማር የሚያወጣ አምላክ ነውና ሁሉ መማር የእርሱ ሥራ

ነው። ነገር ግን ወደ ንስሃ እንዲ መጡ በወንጌል አሁንም ቢሆን ልናገለግላቸው ይገባል። ይህን

ስንል ኢየሱስን እንጨምርላቸዋለን ማለትም አይደለም።

Page 29: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

28 www.tlcfan.org

ከአሉበት ሃይማኖት ተላቀው ወደ ክርስቶስ ተከታይነት በወንጌል እውነት እናመጣቸዋለን

ማለት ነው። ይህም ወንጌሉን ከሚተረጉመውና ከሚያስረዳው ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር በእርሱ

ፍቃድ ስር ሆነን ነው። ምክንያቱም ይህ አይነቱ የንስሃ ስራ የመንፈስ ቅዱስ ስራ ነው። ማንንም

አንድን ሰው ንስሃ ማስገባት አይችልም። ለዚህም ነው ከላይ እንዳየነው የዳንኤል 70 ሳምንት

ሁለት መጀመሪያና ሁለት መጨረሻ ቀን እዲኖረው የተገባው። የመጀመሪያው 70 ሳምንት የዘመን

ዙረት የዓለም ሁሉ ሃጢያት የተከፈለበት ቀን ሲፈጸም። ሁለተኛው ደግሞ ጳውሎስ የተላከበት

ቀን ተፈጸመ። ጳውሎስም በበዓለ አምሣ ዘመን ላሉ በልዮ መንፈስ ለተሞሉ ለድል ነሺዎች ምሳሌ

ነው።

የጳውሎስ መለወጥ የሆነው ነህሚያ ኢየሩሳሌምን ቅጥር ሊሰራ ከተላከበት ቀን አንስቶ

በ490ኛው ዓመት ላይ ነው። ነህሚያ ማለት የያሕዌ አጽኛኝ ማለት ነው። "the Comforter of Yah."

ነህሚያ የመንፈስ ቅዱስ ጥላ ነበር። መንፈስ ቅዱስም የአዲቱን ኢየሩሳሌም ቅጥር የሚሰራ እርሱ

ነው። ከ490 ዓመት በኃላ ጳውሎስ በመንፈስ ተሞልቶ ወንጌልን እንዲሰብክ ወደ ትውልድ ሁሉ

እስከ ምድር ዳርቻ ተላከ።

የጳውሎሳዊ ተልኮ ትንቢታዊ ክንዋኔው በ 46ኛው A.D ጀምሮ በ 2006 ላይ በ40ኛው

ኢዮቤልዮ የዘመን ዙረት “cycle” ፍጻሜን አግኝቷል። በዚህ ከ2006 ጀምሮ ባሉት ዘመኖች ውስጥ

የዳስ በዓልን ልዮ የሆነን ነገር በድል ነሺዎች መካከል እናያለን። ይህም በጳውሎስ የታየው ጥላ

በእነርሱ ላይ ከሚመጣው መንፈስ የተነሳ ሥማቸው ይለወጣል። እውነተኛ የትንቢቱ አካል ሆነው

ይገለጣሉ። ከዚህ በ2006 ዓመት ጀመሮ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ በተለያዮ ቦታዎች እናያለን።

ይህም በነህምያ ጥላ አድርጎ እግዚአብሔር እንዳስቀመጠው ጥላዊ ትንቢት መሰረት ነው።

ይህ 2006 የ 50ኛው ኢዮቤልዮ መፈጸሚያ ነው። ይህም ከነህምያ 445 B.C. ጀምሮ

ነው። ይህም ቀን በብሉይ ዘመን ስናየው እግዚአብሔር አዳምን ከፈጠረበት ቀን ጀምሮ ከንዓን

እንዲወርሱ ያዘዛቸው ቀን ያ 50ኛው ኢዮቤልዮ ነበር። እንግዲህ ይህ ዘመን የዛን አካል ከመንፈሱ

የተነሳ የምንለብስበት ዘመን ነው። ይሁንና ከዚህ 2006 ይጀምር እንጂ በየተትኛው ዓመት

እንደሚሆን እርግጠኛ ቃል የለንም። ነገር ግን ከዚህ ዓመት በኃላ ባሉት ዓመታቶች በአንዱ ይህ

ፍጻሜን ያገናል።

አዳም ሃጢያትን ሲያደርግ እርስቱን አጥቷል። በዚህም ምክንያት እዳውን እንዲከፍል

ለምድር በባሪያነት ተሽጧል። እግዚአብሔር አብርሃምን ሊጠራ 40ኛን ኢዮቤልዮ ጠበቀ። ከዚያም

በኃላ የአዳምን ልጆች ሕዝቡን ወደ እርስታቸው ለመመለስ 10 ኢዮቤልዮን ጠበቀ። ይህም

የአዳምን ልጆች የእስራኤልን ልጆች ወደ እርስታቸው ለመመለስ ነው።

Page 30: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

29 www.tlcfan.org

ከዚያም 12 ሰላዮች ምድሪቱን ሰልለው መልዕክት አመጡ። 10 ካመጡት ክፉ

መልዕክት የተነሳ ወደ ርስታቸው በዚያን ዘመን ሳይገቡ ቀሩ። ይህ የእግዚአብሔርም ፈቃድ ነበር።

ምክንያቱም ርስቱ ገና መሲሁ ሳይሞት ትክክለኛ ረፍት ሊመጣ አይችልምና ነቅው። ያኔ ቢገቡ

ኖሮ እውነተኛውን እረፍት ለማወቅ ግራ እንጋባ ነበርና ነው። ነገር ግን ሊያስተምረንና

ለእውነተኛው እረፍት ሊያዘጋጀን በእነርሱ እንዲ ሆነባቸው። ይህም ለትምሕርታችን ሆነ።

በብሉይ በአሮጌው ኪዳን ርስቱን መውረስ ፈጽሞ አልተቻለም። እውነተኛው አዳም

ያጣው እርስት የሚገኘው በአዲሱ ኪዳን ነው። እናም አሁን እንደገና ያኔ ሕዝበ እስራኤል በ50ኛ

ኢዮቤልዮ ቀን ደርሰው እንደ ቆሙ እኛም በ2006 50ኛው ኢዮቤልዮ ላይ ቆመናል። ይህም

ማለት በ50ኛው ኢዮቤልዮ ውስጥ 491, 492, 493......እያለ እስከ 500 ያለውን ዓመታቶች

የሚያጠቃልል ነው። ስለዚህ (2006-2007) ያለው ዓመት ታላቁ ኢዮቤልዮ ዓመት የሚጀምርበት

ዓመት ነው።

ምን ማለትህ ነው? ትሉኝ ይሆናል። መልሴ እግዚአብሔር ያውቃል ነው። ከዚህ

ዘመናት በኃላ ዓለምን የሚያነቃንቁ ብዙ ነገሮች በውጭም በውስጥም (ቤተክርስቲያን) እንደሚሆኑ

ታላቅ እምነት አለኝ። ይህ ዘመን ግን እንዴት እንደሚፈጸም ይህን መጽሐፍ ሳዘጋጅ የጠራ

የትንቢት መረዳት ስለሌለኝ ነው። እግዚአብሔር ያውቃል ያልኩት።

ይህን ዘመን በመጽሐፍ ቅዱስ ያለውን ጥላዊ ምሳሌዎችና ትንቢቶች በማጥናት

የደረስኩበት ነው። በደረሳችሁበት መመላለስ ወይም ቃሉን በማጥናት ወደ እዚህ መረዳት

ልትመጡ ለሁሉ ሰው ክፍት ነው። ይህ ታውቁ ዘንድ ግን እወዳለሁ፦ የዳንኤል 70 ሳምንታት

የ50ኛው ኢዮቤልዮ የመጀመሪያዎቹ 10 ኢዮቤልዮዎች ናቸው። እነዚህም 10 ኢዮቤልዮዎች

በሁለት መጀመሪያና መጨረሻ ተመስለው በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ተጽፈው እናገኛቸዋለን።

የእነዚህ አስር ኢዮቤልዮ መጨረሻ ዓመቶች (33 እና 46 A.D) ናቸው።

የቀረው 50-10 = 40 ኢዮቤልዮ ነው። ይህ 40ኛው ኢዮቤልዮ ደግሞ ሲፈጸም ወደ 50ኛው

ኢዮቤልዮ እንገባለን። ይህ 40ኛው ኢዮቤልዮ በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ አጥኚና ተመራናሪዎች

የቤተክርሲያን ዘመን "The Church Age," ብለው የሚጠሩት ነው። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ

የበዓለ አምሣ ዘመን "The Pentecostal Age." እንደ ሆነ በተለያየ መልክ ይገልጸዋል። ይህም

ቤተክርሲያን ከሙሴ በታች ጉዞዋን በብሉይ ጀምራ የነበረችበት ነው፣ ሐዋ.7፥38 ይህችም በምድረ

በዳ የነበረችው ጉባኤ ለቤተክርሲያን ጥላ ነች። የበዓለ አምሣ ዘመን ቤተክርሲያን ጥላ የሆነች

ቤተክርሲያን ጉባኤ ማህበር ነበረች። ይህች ቤተክርሲያን የፋሲካን ዘመን አጠናቃ

ነበር።

Page 31: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

30 www.tlcfan.org

ይህም አሁን እንዳለችው ቤተክርሲያን ማለት ነው። ፋሲካ ዘመን የተጠናቀቀው

በመስቀሉ ላይ ነበር። ከዛም ቀጥሎ ቤተክርሲያን ከሐዋ.2 ጀምሮ በበዓለ አምሣ ዘመን ውስጥ

ነበረች። ከዛም ይህ ዘመን ሲፈጸም ቤተክርሲያን ወይም ድል ነሺዎች ወደ ዳስ በዓል ዘመን

ይሸጋገራሉ። ይህም የበዓለ አምሣ ዘመን ከተፈጸመበት ቀን አንስቶ ነው።

የበዓለ አምሣ ዘመን ደግሞ ከዘመንና ኢዮቤልዮ ጥናት መመነሳት በ May 30, 1993

ከ40ኛው ኢዮቤልዮ በኃላ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ዘመን አቆጣጠር ተፈጽሟል።

አሁን ያለነው በዳስ በዓል ዘመን ጅማሬ ዝግጅት ዓመቶች ላይ ነው። በምድረ በዳ የነበረችው

ቤተክርሲያን 40 ዓመት እንደ ቆየች የአዲስ ኪዳንዋም ቤተክርሲያን 40 ኢዮቤልዮዋን በዚህ ቀን

አጠናቃ ጨርሳለች። ይህን ሁሉ ቀን የምናጠናው ዘመኑ እንደቀረበ አውቀን እንድንነቃ ነው።

እንደ ዘመኑ መመላለስ እንድንችል ነው። ይህ ተፈጽሞ ሳለ አሁን ደግሞ በዚህ በ2006 ዓመት

የሁለተኛው ዘመን ትንቢት ጥላ ፍፃሜ ላይ መጥተናል።

ይህን ስል ልብ ልታደርጉ ወዳለሁ በዚያን ቀን ኢየሱስ ይመለሳል እያልኩ አይደለም።

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ሊያዘጋጅ በአንዳዶች ላይ ይመጣል። ምክንያቱም በዚህ ዘመን

የሚፈጸመው የነህምያ ትንቢት ነው። ነህሚያ ደግሞ ከላይ እንዳየነው የመንፈስ ቅዱስ ጥላ እንጂ

የኢየሱስ አይደለም። ስለዚህ አስቀድሞ ከክርስቶስ መምጣት በፊት የሚሰጠን የሚያዘጋጀን ልዮ

መንፈስ ቅዱስ ነው። ይህ በኢያሱና በካሌብ ላይ እንደ ነበረው ማለት ነው። ይህ ጠቃላላው ጉባሔ

የተቀብለውን መንፈስ ቅዱስ ሙላት አይነት አይደለም ከዛ በክብርም በአሰራርም የተለየ ነው።

ነገር ግን ያው መልንፈስ ቅዱስ ነው። ጳውሎስና ነህሚያ ለዚህ ዘመን ጥላዎች ናቸው። በዚህ

ዘመን ያሉ ድል ነሺዎች ደግሞ ራሳቸው ሦስተኛ ምስክር ናቸው።

የዚህ መጽሐፍ ዋና አላማ ስለ ዳንኤል 70 ሳምታት መሰረታዊ የሆነ መረዳት ለመስጠት

ነው። ብዙ ሃሳቦች በመሃል ብናነሳም የዳንኤል ሰባ ሳምንታትን እውነት እንደተረዳን አምናለሁ።

ይህም በዘመኑ ለሚሆነው ነገር እንግዳ ሳንሆን ተካፋዮች እንድንሆን ለማድረግ ነው። ደግሞም

ትቢትንና ዘመንን መመርመር በቅዱሳን ልብ ውስጥ እንዲጫር ለማድረግ ነው። ይህ በአባታችን

ዳንኤል የነበረ እሳት ነው። ዘመንን ከኤርሚያስ መጽሐፍ መርምሮ ተረዳ። ዘመኑን ማወቅና

መዘጋጀት ከጉዞ ያልወደቀ የጌዲዮን ሰራዊት አይነት ይሆናል። ይህም በመሳፍንት 7 ላይ ታሪኩ

ታገኛላቹ። ሰዎች ከፍርሃት የተነሳ ውድቅ ሆኑ 7፥3 ሌላው ደግሞ የቃሉን ውሃ ባለመለየት ወደቁ

7፥5 አጥርቶ ባለማየት ወደቁ።

ፍርሃት በእምነት ድል ይነሳል። እምነት የእግዚአብሔር ቃል በመስማት የሚመጣ

ነው። የመለየት እጥረት ደግሞ ቃሉን እንደሚገባ በጥንቃቄ ከመሰረቱ

አንስቶ በመረዳት ያሳጣል። ይህ ደግሞ ለድል ነሺነት አያበቃም።

Page 32: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - T.L.C.F.A.N 70 weeks.pdfየዳንኤል 70 ሳምንታት 2015 4 ከሕዝቡ ላይ ሃጢያትን ይፈጽምና በደልንም ያስተሰርይ

የዳንኤል 70 ሳምንታት 2015

31 www.tlcfan.org

ኢየሱስ በእውነትና በመንፈስ እንድናመልከው ይፈልጋል። ሁለቱም አስፈጊ ናቸው።

አንዳንድ ሰዎች በአንዱ ብቻ ያተኮሩ የጠነከሩ ናቸው። እንደዛ መሆን ግን ተገቢ አይደለም።

ለእግዚአብሔር እውነትም ጊዜ በመስጠት መመርመር ይገባል። ሥራውን በሚገባ በዚህ በዘመን

መጨረሻ ለመስራት ሁለቱም ያስፈልጉናል። እንንቃ እንበርታ ቃሉን በትክክል ለመረዳት ቃሉን

በትጋትና በተማሪ መንፈስ እንመርምር። ማራናታ!!!

…………………………………………….ተፈጸመ……………………………………………….