8
በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ንግድን... በ2ኛው ገጽ ዞሯል 78ኛ ዓመት ቁጥር 170 ረቡዕ የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 ብር ግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ በግል ድርጅቶች ውስጥ ለሚሠሩ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና ፕሮግራም ሽፋን በመስጠትና የአቅዱ አባል በማድረግ የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ መብት በማረጋገጥ በዘርፉ የተሠማሩትን ዜጎች የማኅበራዊ ዋስትና ተጠቃሚነት ዕውን በማድረግ የተረጋጋና ምቹ የሥራ አካባቢን ለማስፈን የተቋቋመ ተቋም ነው። የግል ድርጅት ሠራተኞች በማኅበራዊ ዋስትና ሽፋኑ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ሠራተኞቹም ሆኑ አሠሪ ድርጅቶች አስፈላጊ መረጃዎችን ማሟላት ብሎም የግል ድርጅቶች ሠራተኞች አዋጅ የጣለባቸውን ግዴታ መወጣት ይጠበቅባቸዋል። ሠራተኞችን ለማስመዝገብ ዐቅድ አባልነት ምዝገባ ማንኛውም የግል ድርጅት የተቋቋመበትን ሕግ፣ የግል ድርጅቱ ሠራተኛ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀጠር የሞላውን የሕይወት የጡረታ መዋጮ በ30 ቀናት ውስጥ ገቢ መደረግ አለበት ታሪክ፤የተሰጠውን የቅጥር ደብዳቤ፣ የጋብቻና የልደት ሰርተፊኬት፣ አስቀድሞ የጡረታ ወይም ማኅበራዊ ዋስትና ፈንድ መዋጮ የተከፈለ አገልግሎት ፈጸመ ከሆነ ለፈጸመው አገልግሎት እና ሌሎች መረጃዎችን አጠናቅሮ ለኤጀንሲው ውሳኔ ማቅረብ፤ ከሰኔ 17/2003 ዓ.ም በኋላ የተቀጠረ የግል ድርጅቱ ሠራተኛ የግል ድርጅቱ በተቋቋመ ወይም ሠራተኛው በተቀጠረ በ60 ቀናት ውስጥ መመዝገብ አለበት፤ • ማንኛውም የግል ድርጅት ሠራተኛ ሲቀጠር የማኅበራዊ ዋስትና የምዝገባ መለያ ቁጥሩን ለተቀጠረበት መሥሪያ ቤት ወይም የግል ድርጅት የማሳወቅ ግዴታ አለበት። • ቅጽ ጡ 1 በሁለት ኮፒ ይሞላል • የሠራተኛው ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ • በሁለትና ከዚያ በላይ ድርጅቶች ውስጥ የሚሠራ አንድ ሠራተኛ ከሚሰራባቸው አንዱ ድርጅት መርጦ በጡረታ ዐቅድ ይሸፈናል፤ በሌሎች በሚሠራባቸው የግል ድርጅቶች ከሚከፈለው ደመወዝ ላይ የጡረታ መዋጮ አይቀነስም፤ • ማንኛውም የግል ድርጅትም ሆነ ሰራተኛ በራሱና በቤተሰቡ፤ በደመወዙና በማንኛውም የምዝገባ ማስረጃዎች ላይ ለውጥ ሲኖር በ60 ቀናት ማሳወቅ ይኖርበታል። • ከ45 ቀናት በላይ የሆነው ሠራተኛ መዋጮ የሚቀነሰው ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ ነው። የግል ድርጅቶች ወይም የአሠሪው ተግባርና ግዴታ • ማንኛውም የግል ድርጅት ሕጋዊ ፈቃድ ለመስጠት ሥልጣን ካለው አካል የተሰጠውን የዋና ምዝገባ ፈቃድ እንዲሁም የግል ድርጅቱን ማቋቋሚያ ሰነድ ኮፒ በሕጋዊ የግል ድርጅቱ ማኅተብ አስደግፎ በማቅረብ ድርጅቱ በተቋቋመ በ60 ቀናት ውስጥ ማስመዝገብ፤ • ድርጅታቸውንና ሠራተኞቻቸውን ማስረጃዎች በማሟላት መመዝገብና ማስመዝገብ ይገባቸዋል • አሰሪዎች ሠራተኞቻቸውን ሲያስመዘግቡ የሠራተኞቻቸውን የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። • አሠሪዎች ከሠራተኞቻቸው ደመወዝ የቆረጡትንና የድርጅቱንም የጡረታ መዋጮ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ድርሻ በማከል በየወሩ የጡረታ መዋጮውን ለኤጀንሲው ገቢ ማድረግ አለባቸው አንቀጽ 11 ንዑስ • የጡረታ መዋጮ ገቢ በመብለጥ/በማነስ ልዩነት ካለው በ30 ቀናት ውስጥ ለኤጀንሲው ማሳወቅ ይኖርባቸዋል። • ከሠራተኞች ሊቀነስ የሚገባው መዋጮ ሳይቀነስ የቀረ የግል ድርጅት ክፍያውን ራሱ ለመፈጸም ኃላፊ ይሆናል • እያንዳንዱ የግል ድርጅት የሠራተኞችን የጡረታ መዋጮ ከደመወዛቸው ቀንሶ የራሱን መዋጮ ጨምሮ ለጡረታ ፈንድ በየወሩ የማስገባት ግዴታ አለበት፤ • የጡረታ መዋጮ የሠራተኞች የወር ደመወዝ ከተከፈለበት ወር መጨረሻ ቀን አንስቶ በ30 ቀናት ውስጥ ለጡረታ ፈንድ ገቢ መደረግ አለበት • የሥራ ውል ሲደረግ የ45 ቀን የጊዜ ውል ከተደረገና ቀኑ የሰራተኛው የሥራ ውል ከቀጠለ ለሙከራ ከተቀጠረበት ሠራተኛው ለሙከራ ከተቀጠረበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ የጡረታ መዋጮ ይከፈላል • የጡረታ መዋጮ የሚከፈለው ለሠራተኛው በየወሩ ከሚከፈለው መደበኛ የወር ደመወዝ ላይ ነው • አሠሪዎች የሰበሰቡትን የጡረታ መዋጮ ደመወዝ ከተከፈለበት ወር ቀጥሎ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ለፈንዱ ገቢ ካላደረጉ ገቢ ላልተደረገው መዋጮ ደመወዝ ከተከፈለው ወር ካለው ወር የመጀመሪያው ቀን አንስቶ በየወሩ በባንኩ የማስቀመጫ ወለድ መጠን መሠረት ወለድና 5 ከመቶ ቅጣት ጨምሮ የመክፈል ግዴታ አለበት። ስ.ቁ- 011 1 55 03 67/68/76 ነጻ ስልክ ቁጥር 888/1/2/7 ፋክስ 251 11 1 55 03 69 ድረ ገጽ- www.poessa.gov.et ኢ ሜይል [email protected] ማኅበራዊ ድረ ገጽ- www.Facebook. com/poessa ፖ.ሳ.ቁ. 33921 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ... በ2ኛው ገጽ ዞሯል የወረቀት ... በ2ኛው ገጽ ዞሯል ዳንኤል ዘነበ አዲስ አበባ፦ የሰው ልጅ ለአካላዊ ዕድገቱ ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ መጻሕፍት ደግሞ የአዕምሮ ምግብ ናቸው። እነዚህን የአዕምሮ ምግቦች ለአንባቢዎቻቸው ለማድረስ በራቸውን ከፍተው ከሚጠባበቁት መጻሕፍት መደብሮች አንዱ በሆነው በጃፋር ቅርንጫፍ ኢማድ የመጽሀፍ መደብር ተገኝቻለሁ። አምስት በአራት በሆነች አነስተኛ መደብር ውስጥም በርካቶች ለመግዛት፣ ጠይቆ ለመሄድ፣ ጓደኛውንና/ዋን ለማጀብ ገባ ወጣ የሚሉ ይስተዋላሉ። እኔም በመደብሩ ገባ ወጣ የሚሉትን ደንበኞች የወረቀት ዋጋ የንባብ ባህልን አያበረታታም አጎናፍር ገዛኽኝ አዲስ አበባ፡- የትግራይ ክልል የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አዋጅ ህገ መንግስቱን የሚጥስ በመሆኑ እንዲጣራለት አቤቱታ ማስገባቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ። በፌዴሬሽን ምክር ቤት የዴሞክራሲያዊ አንድነት፣ የህገ መንግስት አስተምህሮና የሰብዓዊ መብት ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ጸሀፊ ወይዘሮ ፍረወይኒ ገብረእግዚአብሔር፤ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፣ የኮሚሽኑ መቋቋም ‹‹ህገ መንግስቱን ይጥሳል›› የሚሉ አሉና በዚህ ላይ ሃሳባቸው እንዲሰጡ ሲጠየቁ በሰጡት ምላሽ ፣የትግራይ ክልል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቤቱታ ማስገባቱን አንስተው ዝርዝር ማብራሪያ እንደማይሰጡ ገልጸዋል። የትግራይ ክልል ተቃውሞውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አስገብቷል ወይዘሮ ፍረወይኒ ገብረ እግዚአብሔር፤ ፎቶ፡- በገባቦ ገብሬ ለምለም መንግስቱ አዳማ:- በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታትና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ባለፉት ስድስት ወራት በተሰሩ ስራዎች የህዝብ ሰላም እንዲመለስ መደረጉ ተገለጸ፡፡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ትናንት በአዳማ ከተማ በተጀመረው አምስተኛው የጨፌ ኦሮሚያ አራተኛ አመት የሥራ ዘመን ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በሀገሪቷ የመጣውን ለውጥና የልማት በኦሮሚያ ክልል ሰላምን ለማስፈን ውጤታማ ስራ መሰራቱ ተገለጸ ንግድን ለማሳለጥ ተጨባጭ ርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ ማብራሪያ የማይሰጡበት ምክንያትም የህገ መንግስት አጣሪ ጉባዔ በቀጥታ ምላሽ ሊሰጥበት ወይም አቤቱታውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲያየው ሊልከው ስለሚችልና እርሳቸውም የምክር ቤት አባል ስለሆኑ የአስተሳሰብ ተጽዕኖ ላለማድረግ ለመጠንቀቅ መሆኑን አብራርተዋል። ለአቤቱታውም ሥርዓቱን ጠብቆ ምላሽ እንደሚሰጥም አመላክተዋል። የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ሲጸድቅ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በህገ መንግስቱ የተሰጠውን ስልጣን “ይጥሳል ፣አይጥስም” የሚል ክርክር መካሄዱ፣ የትግራይ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መቃወማቸውና በአብላጫ ድምጽ መጽደቁ ይታወሳል። የትግራይ ክልል ምክር ቤትም አዋጁ ህገ መንግስቱን ስለሚጥስ እንደማይቀበለውና አቤቱታውንም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ለማቅረብ መወሰኑ የሚታወስ ነው። በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ከወይዘሮ ፍሪወይኒ ገብረ እግዚአብሔር ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለ ምልልስ በገጽ 11 እንዲያነቡ ጋብዘንዎታል። በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- በአገሪቱ ሁሉን አቀፍ ልማት ለማምጣት፣ ከብድርና ከተፈጥሮ ጥገኝነት ለመላቀቅ ጥራት ያለው ዕድገት እንዲመጣ እና ንግዱን ለማሳለጥ የሚያስችል ተጨባጭ ርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ። በአገሪቱ ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ የሚገመግመውና አቅጣጫ የሚሰጠው ኮሚቴ ያለፈውን አንድ ወር የንግድ አፈፃፀም ትናንት ገምግሟል። በግምገማው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ የእስካሁኑ የአገሪቱ የንግድ እንቅስቃሴ አወዛጋቢ ነበር። መንግስት የአገር ውስጥ ገቢን ለማሳደግ ቢያቅድም በተግባር ግን አዳዲስ ቢዝነሶች ወደ መስመሩ አልገቡም። ዜጎች የንግድ ሃሳብ ቢኖራቸውም አሳሪ በሆነው ህግ ምክንያት ወደ ተግባር ለመቀየር ይቸገራሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣የአገልግሎት አሰጣጡ ኋላ ቀር ፣ቢሮክራሲውም አሳሪ ነው ብለዋል፡፡ ስለሆነም ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ባለሀብቶች የንግድ ሁኔታውን ምቹ ለማድረግ አዳዲስ ሃሳቦችንና አሰራሮችን በመተግበር ትርፋማ ለመሆን እንደሚሰራ አመልክተዋል። ከዚህም በተጨማሪ፤ የፋይናንስ ፖሊሲ፣ የመንግስት ገቢ፣ የበጀት ጉድለትና በጀትን የማጣጣም ስራም እንደሚከናወን ገልጸው፣ መንግስት የግብር ሥርዓቱን ለማስፋት አሰራሩን በማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታውቀዋል። አገሪቱ የተጫናትን እዳ ለመቀነስም ገቢን ለማሳደግና የመንግስት ወጭ ለመቀነስ ይሰራል ብለዋል። ኮሚቴው የአንድ ወር የንግዱን አፈጻጸም ሲገመግም ፎቶ፡- ዳኜ አበራ

78 ንግድን ለማሳለጥ ተጨባጭ ርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ€¦ · ንግድን... በ2ኛው ገጽ ዞሯል 78ኛ

  • Upload
    others

  • View
    17

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: 78 ንግድን ለማሳለጥ ተጨባጭ ርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ€¦ · ንግድን... በ2ኛው ገጽ ዞሯል 78ኛ

በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር!

ንግድን... በ2ኛው ገጽ ዞሯል

78ኛ ዓመት ቁጥር 170 ረቡዕ የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 ብር

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ በግል ድርጅቶች ውስጥ ለሚሠሩ የግል ድርጅቶች

ሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና ፕሮግራም ሽፋን በመስጠትና የአቅዱ አባል በማድረግ የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ መብት በማረጋገጥ በዘርፉ የተሠማሩትን ዜጎች የማኅበራዊ ዋስትና ተጠቃሚነት ዕውን በማድረግ የተረጋጋና ምቹ የሥራ አካባቢን ለማስፈን የተቋቋመ ተቋም ነው። የግል ድርጅት ሠራተኞች በማኅበራዊ ዋስትና ሽፋኑ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ሠራተኞቹም ሆኑ አሠሪ ድርጅቶች አስፈላጊ መረጃዎችን ማሟላት ብሎም የግል ድርጅቶች ሠራተኞች አዋጅ የጣለባቸውን ግዴታ መወጣት ይጠበቅባቸዋል።

ሠራተኞችን ለማስመዝገብ• ዐቅድ አባልነት ምዝገባ ማንኛውም

የግል ድርጅት የተቋቋመበትን ሕግ፣ የግል ድርጅቱ ሠራተኛ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀጠር የሞላውን የሕይወት

የጡረታ መዋጮ በ30 ቀናት ውስጥ ገቢ መደረግ አለበትታሪክ፤የተሰጠውን የቅጥር ደብዳቤ፣ የጋብቻና የልደት ሰርተፊኬት፣ አስቀድሞ የጡረታ ወይም ማኅበራዊ ዋስትና ፈንድ መዋጮ የተከፈለ አገልግሎት ፈጸመ ከሆነ ለፈጸመው አገልግሎት እና ሌሎች መረጃዎችን አጠናቅሮ ለኤጀንሲው ውሳኔ ማቅረብ፤

• ከሰኔ 17/2003 ዓ.ም በኋላ የተቀጠረ የግል ድርጅቱ ሠራተኛ የግል ድርጅቱ በተቋቋመ ወይም ሠራተኛው በተቀጠረ በ60 ቀናት ውስጥ መመዝገብ አለበት፤

• ማንኛውም የግል ድርጅት ሠራተኛ ሲቀጠር የማኅበራዊ ዋስትና የምዝገባ መለያ ቁጥሩን ለተቀጠረበት መሥሪያ ቤት ወይም የግል ድርጅት የማሳወቅ ግዴታ አለበት።

• ቅጽ ጡ 1 በሁለት ኮፒ ይሞላል• የሠራተኛው ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ• በሁለትና ከዚያ በላይ ድርጅቶች ውስጥ

የሚሠራ አንድ ሠራተኛ ከሚሰራባቸው አንዱ ድርጅት መርጦ በጡረታ ዐቅድ ይሸፈናል፤ በሌሎች በሚሠራባቸው የግል ድርጅቶች ከሚከፈለው ደመወዝ ላይ የጡረታ መዋጮ አይቀነስም፤

• ማንኛውም የግል ድርጅትም ሆነ ሰራተኛ በራሱና በቤተሰቡ፤ በደመወዙና በማንኛውም የምዝገባ ማስረጃዎች ላይ ለውጥ ሲኖር በ60 ቀናት ማሳወቅ ይኖርበታል።

• ከ45 ቀናት በላይ የሆነው ሠራተኛ መዋጮ የሚቀነሰው ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ ነው።

• የግል ድርጅቶች ወይም የአሠሪው ተግባርና ግዴታ

• ማንኛውም የግል ድርጅት ሕጋዊ ፈቃድ ለመስጠት ሥልጣን ካለው አካል የተሰጠውን የዋና ምዝገባ ፈቃድ እንዲሁም የግል ድርጅቱን ማቋቋሚያ ሰነድ ኮፒ በሕጋዊ የግል ድርጅቱ ማኅተብ አስደግፎ በማቅረብ ድርጅቱ በተቋቋመ በ60 ቀናት ውስጥ ማስመዝገብ፤

• ድርጅታቸውንና ሠራተኞቻቸውን ማስረጃዎች በማሟላት መመዝገብና ማስመዝገብ ይገባቸዋል

• አሰሪዎች ሠራተኞቻቸውን ሲያስመዘግቡ የሠራተኞቻቸውን የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

• አሠሪዎች ከሠራተኞቻቸው ደመወዝ የቆረጡትንና የድርጅቱንም የጡረታ መዋጮ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ

ድርሻ በማከል በየወሩ የጡረታ መዋጮውን ለኤጀንሲው ገቢ ማድረግ አለባቸው አንቀጽ 11 ንዑስ

• የጡረታ መዋጮ ገቢ በመብለጥ/በማነስ ልዩነት ካለው በ30 ቀናት ውስጥ ለኤጀንሲው ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።

• ከሠራተኞች ሊቀነስ የሚገባው መዋጮ ሳይቀነስ የቀረ የግል ድርጅት ክፍያውን ራሱ ለመፈጸም ኃላፊ ይሆናል

• እያንዳንዱ የግል ድርጅት የሠራተኞችን የጡረታ መዋጮ ከደመወዛቸው ቀንሶ የራሱን መዋጮ ጨምሮ ለጡረታ ፈንድ በየወሩ የማስገባት ግዴታ አለበት፤

• የጡረታ መዋጮ የሠራተኞች የወር ደመወዝ ከተከፈለበት ወር መጨረሻ ቀን አንስቶ በ30 ቀናት ውስጥ ለጡረታ ፈንድ ገቢ መደረግ አለበት

• የሥራ ውል ሲደረግ የ45 ቀን የጊዜ ውል ከተደረገና ቀኑ የሰራተኛው የሥራ ውል ከቀጠለ ለሙከራ ከተቀጠረበት ሠራተኛው ለሙከራ ከተቀጠረበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ የጡረታ መዋጮ ይከፈላል

• የጡረታ መዋጮ የሚከፈለው ለሠራተኛው በየወሩ ከሚከፈለው መደበኛ የወር ደመወዝ ላይ ነው

• አሠሪዎች የሰበሰቡትን የጡረታ መዋጮ ደመወዝ ከተከፈለበት ወር ቀጥሎ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ለፈንዱ ገቢ ካላደረጉ ገቢ ላልተደረገው መዋጮ ደመወዝ ከተከፈለው ወር ካለው ወር የመጀመሪያው ቀን አንስቶ በየወሩ በባንኩ የማስቀመጫ ወለድ መጠን መሠረት ወለድና 5 ከመቶ ቅጣት ጨምሮ የመክፈል ግዴታ አለበት።

ስ.ቁ- 011 1 55 03 67/68/76ነጻ ስልክ ቁጥር 888/1/2/7 ፋክስ 251 11 1 55 03 69

ድረ ገጽ- www.poessa.gov.et ኢ ሜይል [email protected]ማኅበራዊ ድረ ገጽ- www.Facebook.

com/poessa ፖ.ሳ.ቁ. 33921

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

በኦሮሚያ... በ2ኛው ገጽ ዞሯል የወረቀት ... በ2ኛው ገጽ ዞሯል

ዳንኤል ዘነበ

አዲስ አበባ፦ የሰው ልጅ ለአካላዊ ዕድገቱ ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ መጻሕፍት ደግሞ የአዕምሮ ምግብ ናቸው። እነዚህን የአዕምሮ ምግቦች ለአንባቢዎቻቸው ለማድረስ በራቸውን ከፍተው ከሚጠባበቁት መጻሕፍት መደብሮች አንዱ በሆነው በጃፋር ቅርንጫፍ ኢማድ የመጽሀፍ መደብር ተገኝቻለሁ። አምስት በአራት በሆነች አነስተኛ መደብር ውስጥም በርካቶች ለመግዛት፣ ጠይቆ ለመሄድ፣ ጓደኛውንና/ዋን ለማጀብ ገባ ወጣ የሚሉ ይስተዋላሉ።

እኔም በመደብሩ ገባ ወጣ የሚሉትን ደንበኞች

የወረቀት ዋጋ የንባብ ባህልን አያበረታታም

አጎናፍር ገዛኽኝ

አዲስ አበባ፡- የትግራይ ክልል የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አዋጅ ህገ መንግስቱን የሚጥስ በመሆኑ እንዲጣራለት አቤቱታ ማስገባቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ።

በፌዴሬሽን ምክር ቤት የዴሞክራሲያዊ አንድነት፣ የህገ መንግስት አስተምህሮና የሰብዓዊ መብት ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ጸሀፊ ወይዘሮ ፍረወይኒ ገብረእግዚአብሔር፤ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፣ የኮሚሽኑ መቋቋም ‹‹ህገ መንግስቱን ይጥሳል›› የሚሉ አሉና በዚህ ላይ ሃሳባቸው እንዲሰጡ ሲጠየቁ በሰጡት ምላሽ ፣የትግራይ ክልል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቤቱታ ማስገባቱን አንስተው ዝርዝር ማብራሪያ እንደማይሰጡ ገልጸዋል።

የትግራይ ክልል ተቃውሞውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አስገብቷል

ወይዘሮ ፍረወይኒ ገብረ እግዚአብሔር፤

ፎቶ

፡- በ

ገባቦ

ገብሬ

ለምለም መንግስቱ

አዳማ:- በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታትና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ባለፉት ስድስት ወራት በተሰሩ ስራዎች የህዝብ ሰላም እንዲመለስ መደረጉ ተገለጸ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ትናንት በአዳማ ከተማ በተጀመረው አምስተኛው የጨፌ ኦሮሚያ አራተኛ አመት የሥራ ዘመን ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በሀገሪቷ የመጣውን ለውጥና የልማት

በኦሮሚያ ክልል ሰላምን ለማስፈን ውጤታማ ስራ መሰራቱ ተገለጸ

ንግድን ለማሳለጥ ተጨባጭ ርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ

ማብራሪያ የማይሰጡበት ምክንያትም የህገ መንግስት አጣሪ ጉባዔ በቀጥታ ምላሽ ሊሰጥበት ወይም አቤቱታውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲያየው ሊልከው ስለሚችልና እርሳቸውም የምክር ቤት አባል ስለሆኑ የአስተሳሰብ ተጽዕኖ ላለማድረግ ለመጠንቀቅ መሆኑን አብራርተዋል። ለአቤቱታውም ሥርዓቱን ጠብቆ ምላሽ እንደሚሰጥም አመላክተዋል።

የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ሲጸድቅ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በህገ መንግስቱ የተሰጠውን ስልጣን “ይጥሳል ፣አይጥስም” የሚል ክርክር መካሄዱ፣ የትግራይ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መቃወማቸውና በአብላጫ ድምጽ መጽደቁ ይታወሳል። የትግራይ ክልል ምክር ቤትም አዋጁ ህገ መንግስቱን ስለሚጥስ እንደማይቀበለውና አቤቱታውንም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት

ለማቅረብ መወሰኑ የሚታወስ ነው። በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ከወይዘሮ ፍሪወይኒ

ገብረ እግዚአብሔር ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለ ምልልስ በገጽ 11 እንዲያነቡ ጋብዘንዎታል።

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ አበባ፡- በአገሪቱ ሁሉን አቀፍ ልማት ለማምጣት፣ ከብድርና ከተፈጥሮ ጥገኝነት ለመላቀቅ ጥራት ያለው ዕድገት እንዲመጣ እና ንግዱን ለማሳለጥ የሚያስችል ተጨባጭ ርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።

በአገሪቱ ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ የሚገመግመውና አቅጣጫ የሚሰጠው ኮሚቴ ያለፈውን አንድ ወር የንግድ አፈፃፀም ትናንት ገምግሟል።

በግምገማው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ የእስካሁኑ የአገሪቱ የንግድ እንቅስቃሴ አወዛጋቢ ነበር። መንግስት የአገር ውስጥ ገቢን ለማሳደግ ቢያቅድም በተግባር ግን አዳዲስ ቢዝነሶች ወደ መስመሩ አልገቡም።

ዜጎች የንግድ ሃሳብ ቢኖራቸውም አሳሪ

በሆነው ህግ ምክንያት ወደ ተግባር ለመቀየር ይቸገራሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣የአገልግሎት አሰጣጡ ኋላ ቀር ፣ቢሮክራሲውም አሳሪ ነው ብለዋል፡፡ ስለሆነም ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ባለሀብቶች የንግድ ሁኔታውን ምቹ ለማድረግ አዳዲስ ሃሳቦችንና አሰራሮችን በመተግበር ትርፋማ ለመሆን እንደሚሰራ አመልክተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ፤ የፋይናንስ ፖሊሲ፣ የመንግስት ገቢ፣ የበጀት ጉድለትና በጀትን የማጣጣም ስራም እንደሚከናወን ገልጸው፣ መንግስት የግብር ሥርዓቱን ለማስፋት አሰራሩን በማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታውቀዋል። አገሪቱ የተጫናትን እዳ ለመቀነስም ገቢን ለማሳደግና የመንግስት ወጭ ለመቀነስ ይሰራል ብለዋል።

ኮሚቴው የአንድ ወር የንግዱን አፈጻጸም ሲገመግም

ፎቶ

፡- ዳ

ኜ አ

በራ

Page 2: 78 ንግድን ለማሳለጥ ተጨባጭ ርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ€¦ · ንግድን... በ2ኛው ገጽ ዞሯል 78ኛ

2 የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን

የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻ ፕሮጀክት በሙከራ ተጀመረ

የአዲስ አበባ ወንዞችና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ፕሮጀክት ሸራተን ሆቴል ፊት ለፊት ከሚገኘው ከቀድሞ የፌዴራል ፖሊስ ጋራዥ ግቢ ውስጥ በተደረገ መርሐ ግብር ተጀመረ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) መጀመሩን ሲያበስሩ እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ አዲስ አበባን እንደስሟ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።

በ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በጀት በቫርኔሮ ኩባንያ ተግባራዊ የሚሆነው የሙከራ ፕሮጀክት ከእንጦጦ እስከቀበናና አቃቂ ወንዞች ድረስ ለሚዘረጋው ሰፊ ፕሮጀክት በማሳያነት እንደሚያገለግል የምክትል ከንቲባ ታከለ የቴክኒክ አማካሪ ወይዘሮ መስከረም ታምሩ ተናግረዋል። ኮንትራክተሩ ቫርኔሮ ካሁን ቀደም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተሠርቶ የነበረውን የአዋጭነት ጥናት መነሻ እንደሚያደርግና የፕሮጀክት ዲዛይን ሠርቶ በየጊዜው እያስገመገመ እንደሚያከናውን፤ ከሙከራ ትግበራው በኋላ የሌሎች ወንዞች ዳርቻዎች ሥራ ጨረታ እየወጣ ለተቋራጮች እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የካቲት 17 ቀን 2011 ዓ.ም (ሪፖርተር)

የኦሮሚያ ክልል ለ717 ውጤታማ አርሶ አደሮች እውቅናና ሽልማት አበረከተ

የኦሮሚያ ክልል የውጤታማ አርሶ አደሮች እውቅና እና ሽልማት መርሃ ግብር “በሺዎች የሚቆጠሩ የልማት አርበኞችን በማበረታታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የልማት አርበኞችን እናፍራ” በሚል መሪ ሃሳብ በአዳማ ገልመ አባ ገዳ አዳራሽ ለ12ኛ ጊዜ ተካሂዷል።

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በዕለቱ ባስተላለፉት መልእክት፤ አርሶ አደሮቹ በርትቶ ከተሰራ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ለወጣቱ ትውልድ ማስተማሪያ እንደሚሆኑ ገልጸዋል። ሀገርን ማሳደግ ከተፈለገ ግብርናውን ማዘመን እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል። ግብርናውን ለማዘመን በመንግስት በኩል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።

ከተሸለሙት ውስጥ አዳዲስ ውጤታማ አርሶ አደሮች ይገኙበታል የተባለ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ ከ130 ሺህ እስከ 10 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ያስመዘገቡ ሴት ውጤታማ አርሶ አደሮች ይገኙበታል። ከ500 ሺህ እስከ 21 ሚሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ወጣት አርሶ አደሮች እና ከ300 ሺህ ብር እስከ 37 ሚለዮን ብር ያስመዘገቡ 211 አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ተካትተውበታል። እውቅና እና ሽልማቱ ከተበረከተላቸው 717 ውጤታማ አርሶ አደሮች ውስጥም 50ዎቹ ከአርሶ አደርነት ወደ ኢንቨስተርነት የተሸጋገሩ ናቸው ተብሏል።

የካቲት 17፣ 2011 ዓ.ም (ኤፍ.ቢ.ሲ)

አዲስ አበባ በሚቀጥለው ሳምንት ዲጂታል የነዋሪዎች መታወቂያ መስጠት

ትጀምራለችአዲስ አበባ ዲጂታል የነዋሪዎች መታወቂያ

በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ መስጠት እንደምትጀምር የከተማዋ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ አስታውቋል።

በኤጀንሲው የነዋሪዎች አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ አብዱራሂም እንዳሉት፤ አዲሱ የዲጂታል መታወቂያ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አገልግሎቱ የሚጀመር ሲሆን፤ የአዲሱ መታወቂያ አሰጣጥ ጥንካሬና ድክመት ታይቶ በቀጣይ በሁሉም ክፍለ ከተማ ወረዳዎች መስጠት ይጀመራል።

አዲሱ መታወቂያ የብሔር ማንነትና የትውልድ ቦታ የሚገልጽ ይዘት የሌለው ሲሆን÷ በአንጻሩ የደም ዓይነት እንዲጠቀስ መደረጉም ተገልጿል። ነባሩ መታወቂያ በዲጂታል ሙሉ ለሙሉ እስኪቀየር ድረስ የወረቀት መታወቂያ አሰጣጡ እንደማይቋረጥ፣ በመታወቂያ ማጭበርበርን ለመቀነስ ትልቅ ሚና እንደሚኖረውም ተጠቁሟል።

የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም (ኢዜአ)

የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሦስተኛ መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ ከወራት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋባዥነት ከተካሄደው የመጀመሪያው የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት ቀጥሎ ሦስተኛው መድረክ ተካሄደ።

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ ዶክተር ዲማ ነገዎ፣ አቶ ብናልፍ አንዱዓለምና አቶ አብርሃ ደስታ ባቀረቧቸው ጽሑፎች ውይይት የተካሄደ ሲሆ፤ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ “የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና የሀገራዊ ፖለቲካ ተሳትፏቸው በታሪክ ሂደት ውስጥ” በሚል የመነሻ ፅሁፍ አቅርበዋል።“የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና በሀገራዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ምን ይሁን?” በሚል ርዕስ ደግሞ ዶክተር ዲማ ነገዎ የመነሻ ፅሁፍ አቅርበዋል። አቶ ብናልፍ አንዱዓለም በበኩላቸው “የሀገረ መንግስት እና የብሄረ መንግስት ግንባታ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ አቅርበዋል። እንደዚሁም ማህበራዊ ሚዲያና የመናገር ነፃነት ላይ ያተኮረ የመወያያ ርዕስ በአቶ አብረሃ ደስታ ቀርቧል።

የካቲት 16፣ 2011 ዓ.ም (ኤፍ ቢ.ሲ)የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር

ቤቶችን የማፍረስ ዕርምጃ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ከማስተር ፕላን ውጪ

ተገንብተዋል የተባሉ ከ12,000 በላይ ቤቶች እንዲፈርሱ መወሰኑና ቤቶቹም መፍረስ መጀመራቸው ውዝግብ አስነስቷል።

የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ ሐቢባ ሲራጅ ቤቶቹ እንዲፈርሱ የተወሰነው የከተማውን ማስተር ፕላን በመጣስ፣ ለአረንጓዴ ልማት የተተውና የተከለከሉ በወንዞች ዳርቻዎች ላይ የተገነቡ በመሆናቸው እንደሆነ አስረድተዋል። በሕግ ከተፈቀደላቸው ቦታ ውጪ ተጨማሪ ቦታ አጥረው የያዙ ባለሀብቶችም የዚሁ አካል ናቸው ብለዋል።

ከ12,300 በላይ ካርታ የሌላቸው ቤቶች በከተማዋ መኖራቸውንና እየፈረሱ ያሉ ቤቶች በመንግሥት ይዞታ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸዋል። የከተማ አስተዳደሩ ከመመሥረቱ ሦስት ዓመት በፊት ግብር የከፈሉበት ደረሰኝ ማቅረብ አለመቻላቸውን አስረድተዋል። ቤቶቹን የማፍረስ ዘመቻው በማስተር ፕላኑ መሠረት እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

የካቲት14 ቀን 2011 ዓ.ም (ሪፖርተር)

ፍሬህይወት አወቀ

አዲስ አበባ፦ በየአደባባዩ መንገድ ዘግተው የሚነግዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ስርዓት የማስያዝ ስራ እየተሰራ መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ መደበኛ ያልሆነ ንግድ ስርዓት ማስያዝ ዳይሬክቶሬት አስታወቀ።

የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳኛቸው ሉሌ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑና የቀበሌ መታወቂያ ያላቸውን በመለየት በየአደባባዩ በመንገድ ላይ ንግድ የተሰማሩ ዜጎችን ስርዓት የማስያዝ ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ዳይሬክቶሬቱ ደንብና መመሪያ ወጥቶለት ከተቋቋመ አስር ወር ሲሆነው፤ በዚሁ ጊዜ ውስጥ የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ አዘጋጀቶ ወደ ስራ ገብቷል የሚሉት ዳይሬክተሩ፤ በተያዘው የአጭር ጊዜ ዕቅድም በመዲናዋ በአስሩም ክፍለ ከተማ በዘርፉ የተሰማሩ 58 ሺህ ስድስት የመንገድ ላይ ነጋዴዎችን መመዝገቡን ተናግረዋል።

ከነዚህም መካከል በደንብና በመመሪያው

የጎዳና ላይ ንግድን ስርዓት ለማስያዝ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

መታቀፍ የሚችሉ የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑና የቀበሌ መታወቂያ ያላቸውን 32 ሺህ 735 የመንገድ ላይ ነጋዴዎች ተለይተዋል። ከነዚህም ውስጥ

በአስር ወር ውስጥ 16ሺህ 718 የመንገድ ላይ ነጋዴዎችን ወደ ስርዓት በማስገባት በተወሰነላቸው ቦታና ሰዓት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን

ነምበር/ አውጥተውና እንደ ንግድ ፈቃድ የመለያ ባጅ ተሰጥቷቸው እንዲሰሩ ተደርጓል።

የተቀሩትንም እንዲሁ ወደ ንግድ ስርዓቱ የማስገባት ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጣዩና የመጨረሻው ዕቅድ የሚሆነው ነጋዴዎቹን በመደገፍ፤ የገበያ ትስስር በመፍጠር፤ ቁጠባ እንዲቆጥቡና ሀብት እንዲያፈሩ በማድረግ እስከ ሁለት ዓመት ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል። ከሁለት ዓመት በኋላ ግን ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ ንግድ እንደሚሸጋገሩ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በዘርፉ የተሰማሩት ነጋዴዎች በተወሰነላቸው ሰዓትና በተለየላቸው ቦታ ብቻ የሚሰሩ እንጂ በቦታው ላይ በአጣናም ይሁን በድንጋይ የመገንባት መብት የላቸውም። በተሰጣቸው የሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠቅመው ወደ መደበኛ ነጋዴነት መሸጋገር አለባቸው ይህ ካልሆነ ግን መደበኛና ግብር ከፋይ የሆነውን ነጋዴ ማዳከም ይሆናል። ስለሆነም መደበኛው ነጋዴ ሳይጎዳ፤ ለትራፊክ ፍሰቱም እንቅፋት ሳይሆኑ በተወሰነላቸው ጊዜና ቦታ ብቻ ሰርተው ከሁለት ዓመት በኋላ መሸጋገርና ለሌሎች ቦታ መልቀቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ዘላለም ግዛው

አዲስ አበባ፡- አዲስ የተቋቋመው የኢት ዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በእውቀታቸው ለአገራቸው አስተዋጽኦ ማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገለጸ። ኤጀንሲው ስራውን ጀምሯል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ የኤጀንሲውን መቋቋም አስመልክተው ትናንት በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ ኤጀንሲው ዳያስፖራው በእውቀቱ ለአገሩ አስተዋጽኦ ለማድረግ፣መብትና ተሳታፊነታቸውን ለማሳደግ የሚያስችል ነው።

እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ፣ከኤጀንሲው መቋቋም በኋላ ፕሮፌሰሮች፣ ዶክተሮችና ሳይንቲስት ኢትዮጵያውያን ለማገዝ ፍቃደኛ ናቸው። የእነርሱን ሃሳብ ማዳመጥ፣ መቀበልና ማሳተፍ ይገባል።

ሆስፒታሎችና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የባለሙያ ክፍተት አለባቸው ያሉት ዳይሬክተሯ፤ ለእረፍት ወደአገር ቤት ሲመጡ በፈቃደኝነት እንዲያገለግሉ የሚደረግበት ሁኔታ ይመቻቻል ብለዋል። በኢንቨስትመንትና በንግድ ስራ ንቁ ተሳታፊ የሚሆኑበት አሰራር እንደሚዘረጋም አመልክተዋል።

ኤጀንሲው መንግስት ባወጣው መስፈርት

ኤጀንሲው ዳያስፖራው በእውቀቱ ለአገሩ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ የሚያስችል ነው

መሰረት የውጭ ግንኙነትንና የአስተዳደር ስራዎችን የሚሰሩ 53 ባለሙያዎችና ሰራተኞች መቅጠሩን፣ በውጭ አገር በሚገኙ 60 ሚሲዮኖች ውስጥ ቅርንጫፎች እንዳሉትና በጀት ተመድቦለት ራሱን ችሎ መመስረቱንም ጠቁመዋል። አሁን ጽህፈት ቤቱን ካዛንቺስ በሚገኘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ማድረጉን በመጠቆምም፤ በቀጣይ የራሱ ህንጻ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ኤጀንሲው ‹‹እኔ ለኢትዮጵያ ኢትዮጵያም ለኔ›› የሚል መርህ እንዳለው ጠቁመው፤ አገሪቱ ለዳያስፖራው የምትሰጠው ነገር እንዳለ ሁሉ፤ ዳያስፖራውም ለሀገሩ የሚያደርገው አስተዋጽኦ ስላለ ግንኙነቱ የሁለትዮሽ እንደሚሆን ጠቅሰዋል። ዳያስፖራው ሃሳቡን የሚገልጽበት የመረጃ መለዋወጫ መስመር እንደሚዘረጋም አመልክተዋል።

ዳያስፖራው ወደ አገሩ ሲመጣ በኢንቨስትመንት፣ በንግድና በሌሎቹም ዘርፎች የሚያገኘውን ጥቅምና አሰራሩን እንዲያውቅ በየሚሲዮኑ ያሉ ባለሙያዎች መረጃ የሚሰጡበት ስርዓት እንደሚኖርም ዳይሬክተሯ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ከአገሩ ውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ዜጋን ያለምንም ልዮነት ያስተናግዳል ያሉት ዳይሬክተሯ፤ ለአውሮፖ፣ ለአሜሪካ ለምዕራብ አገራት ወይንም በአረብ አገራት ለሚኖሩ ዳያስፖራዎች የተለየ አገልግሎት

የሚቀርብበት ወይንም የተለየ ክብር የሚሰጥበት አሰራር አይኖርም፤ ሁሉም በኢትዮጵያዊነቱ እኩል የሚስተናገድበት ቤቱ ይሆናል ብለዋል።

ለዳያስፖራው ልናስብለት ልንቆረቆርለትና ችግር ሲደርስበትም ለመድረስ ያለበትን የምናውቅበት ስርዓት እንዘረጋለን ያሉት ወይዘሮ ሰላማዊት፤ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መረጃ የሚያዝበት የመረጃ ቋት ለማዘጋጀት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ኤጀንሲው በመቋቋሙ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግና ተጠያቂነት እንዲሰፍን የሚያስችል አሰራር እንደሚዘረጋና የዳያስፖራውን ችግር መቅረፍ እንደሚቻል ያላቸውን ተስፋም ተናግረዋል።

በዳያስፖራው ይነሱ የነበሩትን ቅሬታዎች በጥናት ለመለየትና የዓለም አቀፍ ተሞክሮ ለመቀመር ታስቦ ኤጀንሲው ወደ ትግበራ ሳይገባ መዘግየቱን አስታውሰው፤ የውጭ አገር ተሞክሮ፣ በህግ፣ በአሰራርና በመመሪያ ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመመርመር ሊያሰራ የሚችል መዋቅርና አሰራር ተዘጋጅቶ መጽደቁን ተናግረዋል። የተለዩ ውጤታማ አሰራሮች እንደሚቀጥሉና ክፍተቶች የሚታረሙበት አካሄድ እንደሚከተልም ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ተጠሪነቱ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመሆን እንደ አንድ ፌዴራል መስሪያ ቤት መቋቋሙ ይታወቃል።

እያስተዋልኩ ወደ ውስጥ ዘለቅኩ። አይኖቻቸውን ከመጻሕፍት መደርደሪያ ግራና ቀኝ በሚያማትሩ ደንበኞች መካከል ደንበኞቿን እንደየፍላጎታቸው ከምታስተናግደዋ ወጣት ጋር ለደቂቃዎች ተያየን። ወደ እርሷም ጠጋ በማለት ራሴን አስተዋውቄ የመጣውበትን ዓላማ አስረዳኋት። እርሷም ያለማንገራገር ልታስተናግደኝ ፈቃደኝነቷን በመግለፅ ደንበኞቿን አስተናግዳ እስክትጨርስ እንድታገስ ጠይቃኝ ወደ ስራዋ ተመለሰች።

እኔም በመደብሩ ውስጥ ከነበሩት ገዥዎች አንዱ ከሆነው ወጣት ጋር «ግብይት እንዴት ይሆን?» ስል ጥያቄ በማንሳት ጥበቃዬን በስራ አጅቤ ቀጠልኩ። በእጆቹ የያዘውን የልጆች አጋዥ መጻሕፍትን እያገላበጠ ከተመለከተ በኋላ፤ ጥሩ መሆኑንና የአራተኛና የሁለተኛ ክፍል ተማሪ ለሆኑት ልጆቹ አጋዥ መጻሕፍትን ለመግዛት ወደ መደብሩ ጎራ ማለቱን አወጋኝ።

በግል ስራ የሚተዳደረው አቶ ፍቅሩ ዓሊ፤ የመጻሕፍት ዋጋ በመወደዱ መግዛት ያሰበውን በሙሉ መግዛት እንዳልቻለና ዋጋውም ከጠበቀው በላይ መጨመሩን ገለፀልኝ። ከዋጋው ጋር ተያይዞ ከዓመት ዓመት የመጨመሩ ሁኔታ በመጻሕፍት ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም። የደብተር ዋጋም ቢሆን ከዕለት ዕለት ውድነቱ እየጨመረ እንደመጣ በማንሳት መላ ሊፈለግለት ይገባል፤ ይህ ካልሆነ ግን እየሞተ ያለውን የንባብ ባህል ይበልጥ ይገድለዋል ሲል ሃሳቡን ገልጿል።

ከአቶ ፍቅሩ ጋር የነበረኝን ቆይታ በዚሁ አብቅቼ በመደብሩ የሽያጭ ባለሙያ ከሆነችው ሂንዲያ ሺፋ ጋር ለመወያየት ጊዜው ሆነና ቀጠልኩ። ሂንዲያ፤ በሀገራችን ኢትዮጵያ የወረቀት ዋጋ መጨመሩን ተከትሎ የመጻሕፍት ዋጋም አብሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የንባብ ባህሉን እየጎዳው ነው

ስትል ሃሳቧን ትናገራለች። በመሆኑም ትላለች፤ ደንበኞች በከፍተኛ ሁኔታ

ያማርራሉ። ለዚህ ደግሞ ከወረቀት ጋር ተያይዞ የሚፈጠር እንደሆነ ምክንያት ታስቀምጣለች። በርካታ ደንበኞች ነበሩኝ። በአሁኑ ወቅት እነኚህ ደንበኞቼ ቁጥራቸው ተመናምኗል። ምናልባት የቴክኖሎጂ መስፋፋት፣ የህብረተሰቡ የንባብ ባህል መቀነስ፣ የመጽሐፍ ዋጋ እየናረ መምጣቱ እንደ ምክንያትነት ሊጠቀሱ እንደሚችሉም የግል ሃሳቧን ሰንዝራለች።

ሌላው በመጽሐፍት መደብሩ ያገኘሁት ደንበኛ በኔትዎርክ ማርኬቲንግ ሙያ ውስጥ የተሰማራ መሆኑን የገለጸልኝ ኤፍሬም በላይ ነው። ኤፍሬም፤ የወረቀት ምርት ዋጋ መጨመር የፈጠረውን ችግር መንግስት ለመፍታት አቅሙ እንዳለው ያለውን እምነት ይገልፃል። መንግስት ትልቅ አቅም አለው ብዬ አምናለሁ። መንግስት በምግብ ዘይቶችና በነዳጅ ላይ ድጎማ ሲያደርግና የዋጋቸውንም ሁኔታ በትኩረት ለመቆጣጠር ሲሞክር አስተውለናል።

መንግስት ለነዚህና መሰል መሰረታዊ ፍጆታዎች ብቻ ድጎማ ማድረጉ በቂ አይሆንም። ምክንያቱም ትውልድ የሚቀረጸው በመማርና በማንበብ ጭምር ስለሆነ፤ እውቀትን ለማሸጋገርም መጻሕፍት ያስፈልጉናል። የመማር ማስተማሩንም ሁኔታ ለመከወን ደብተር እና መጽሀፍ መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው። ይህ ደግሞ የሚያመላክተው በወረቀት ላይ የሚደረገው ድጎማ እጅጉን አስፈላጊ ነው በማለት አስተያየቱን ሰንዝሯል።

ኤፍሬም ቀጠል አድርጎ፤ በዚህ ረገድ ሌሎች አገራት ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ዜጎቻቸውን እንደሚያበረታቱ ጎረቤት አገር ኬኒያን ምሳሌ በመጥቀስ በወረቀት ምርቶች ላይ ከፍተኛ ቅናሽ እንደምታደርግ ይናገራል። ከዚህ በተጨማሪም፤ ታክስ ላይ ማሻሻያ በማድረግ

የህትመት ውጤቶች የህብረተሰቡን አቅም ባገናዘበ መልኩ ገበያ ላይ እንዲውሉ ማስቻላቸውን በስራ አጋጣሚ በሄደበት ወቅት መታዘቡን በመግለጽ በሀገራችንም መንግስት ለህትመት ሚዲያው የታክስ እፎይታ ፈጥሮ፤ ቅናሽ እንዲሁም ድጎማ ቢያደርግ የንባብ ባህሉንም ማበረታታት ነው በማለት ሃሳቡን ይቋጫል።

የህትመት ዘርፍ ሰፊ ቢሆንም እየተሰራበት አይደለም የሚሉት የዋንኮ ማተሚያ ቤት ኃላፊ ናቸው። ኃላፊዋ፤ የወረቀት ችግር ትልቅ ማነቆ እንደሆነ በመግለጽ አስተያየታቸውን ሲሰጡ፤ ዋንኮ ማተሚያ ቤት መጻሕፍት፣ መጽሄት፣ ብሮሸርና ሌሎች የህትመት ስራዎችን እንደሚያከናውን በመጠቆም፤ የወረቀት ዋጋ መናር በህትመት ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን ይናገራሉ። በሀገራችን የወረቀት አምራች ድርጅቶች በሚፈለገው መጠን ያለመኖራቸው ብቻ ሳይሆን ጭራሹኑ የሉም ማለት በሚያስችል ደረጃ ላይ መሆናቸውንና ያሉት የወረቀት አምራች ድርጅቶችም ከሁለት እንደማይበልጡ ገልፀዋል።

የድርጅቶቹ በበቂ ሁኔታ አለመኖር ደግሞ የህትመት ደርጅቶችንም ሆነ የህትመት ውጤቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እየጎዳ ይገኛል። የህትመት/ማተሚያ ቤቶቹ የሚፈልጉትን አይነት ወረቀት በሚፈለገው ጊዜና መጠን ለማግኘት ይቸገራሉ። ከዚህ በተጨማሪ የሚገነቡት በከፍተኛ ወጪ በመሆኑ ተጽዕኖው የጎላ ነው። የዋጋ መጨመር ደግሞ ተወደደም ተጠላ በተጠቃሚው ጫንቃ ላይ ማረፉ የግድ መሆኑን አብራርተዋል።

በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የወረቀት የፓኬጂንግና ፕሪንቲንግ ዳይሬክተር አቶ አንዷለም ለገሰ፤ የወረቀት ምርት ዋጋ ከጊዜ ወደጊዜ እያሻቀበ መምጣቱን ይስማማሉ።

በሀገራችን ፍላጎትን ከአቅርቦት ያጣጣሙ በቂ አምራች ፋብሪካዎች አለመኖራቸውንም በምክንያትነት ያነሳሉ። የወረቀት ምርት ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ማሻቀቡ በህትመት ውጤቶች የሕብረተሰቡን ፍላጎት ማሟላት አልተቻለም በማለት የችግሩ ስፋት ከዋጋ በላይ መሆኑን ይናገራሉ።

በአገር ውስጥ ያሉት የወረቀት አምራቾች በዓመት እስከ 90 ሺህ ቶን የማምረት አቅም ቢኖራቸውም፤ የሚገኘው የምርት መጠን ግን ከ60 ሺ ቶን የሚበልጥ አይደለም። አምራች ኢንዱስትሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ያለውን የወረቀት ፓኬጂንግ ፍላጎት ለማሟላት ያልቻሉበት ምክንያት መኖሩን በመግለፅ ችግሩን ለመቅረፍ ተቋሙ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራና መፍትሄ ለመስጠትም እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ኢንዱስትሪዎች በኢንዱስትሪ ዞን ወይም ፓርክ እንዲጠለሉና የመሰረተ ልማት ችግሮች እንዳያጋጥሟቸው በማድረግ፣ ተመጋጋቢ ስርዓት ለመፍጠር አገሪቱ ለኢንቨስትመንት ምቹ መሆኗን በማስተዋወቅ፤ በአገር ውስጥ የሚገኙ ባለሀብቶችን በዘርፉ እንዲሰማሩ በማበረታት፤ ብሎም አገር ውስጥ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው እንዲሰሩ ትኩረት ቢደረግ ችግሮቹ ሊቀረፉ ይችላሉ በማለት ሃሳባቸውን አብራርተዋል።

በመጨረሻም በአገሪቱ የወረቀት ምርት በሰባት ኢንዱስትሪዎችና በ60 ሺ ቶን መገደቡንና ፍላጎትን ለማሟላት ከውጪ በዓመት እስከ 150 ሺ ቶን የወረቀት ምርት እንደሚገባ በመግለጽ ለዚህም ሀገሪቷ 3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደምታደርግ ገልጸዋል። የሀገሪቱ የወረቀት ፍላጎት በዓመት ከ200 ሺ ቶን በላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በ2030 ዓ.ም የፍላጎቱ ደረጃ አድጎ ከሁለት እጥፍ በላይ የወረቀት ፓኬጂንግ ያስፈልጋልም ብለዋል።

ከ1ኛው ገጽ የዞረ

የወረቀት ዋጋ የንባብ...

ስራዎች ለማደናቀፍ ከፍተኛ ገንዘብ መድበውና መሳሪያ በገፍ ወደ ሀገር ውስጥ አስገብተው ሁከት በማንሳት የህዝብን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ የጥፋት ኃይሎችን የክልሉ መንግስት ለሴራቸው ቦታ ሳይሰጥ በትዕግስትና በብልሃት በመስራቱ የህዝብ ሰላም እንዲመለስ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

የጥፋት ኃይሎቹ በተለይ የኦሮሞ ህዝብ ልማቱን እንዳያሳድግ፤ እርስ በርሱም እንዲጠላለፍ በማድረግ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የጠቆሙት አቶ ለማ፣ የክልሉ መንግስት እኩይ ተግባራቸውን ለማክሸፍ በሰራው ስራ የጥፋት ኃይሎቹ እንዲያፍሩ መደረጉን አመልክተዋል፡፡ በውስጥም በውጭም ሆነው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የጥፋት ኃይሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከአካባቢያቸው መፈናቀላቸውንና የሰው ህይወትና ንብረትም መጥፋቱን ተናግረዋል፡

እንደርሳቸው ገለጻ፤ የግሉን ባለሀብት ተሳትፎ በመጨመር የዜጎች ህይወት እንዲለወጥ፣ ምርታማነታቸው እንዲጨምር የማድረግና ቢሮክራሲውን ማነቆ ለመፍታት ይሰራል። በመንገድና በሃይል አቅርቦት ረገድም የግል አልሚዎች ወደ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማፍሰስ ፍላጎት አሳይተዋል።

የንግዱን ሁኔታ ቀላል ማድረግ ዋና ዋና አልሚዎች ወደ አገሪቱ በመምጣት በግብርና ምርቶች ማቀነባበር፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በማዕድን ልማት እንዲሰማሩ እንደሚደረግ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበበ አበባየሁ በበኩላቸው፤ በአጭር ጊዜ ንግድን ለማቀላጠፍ እንዲቻል ሰማንያ ጉዳዮች ለማስተካከል መለየታቸውን ተናግረዋል። ኮሚቴው ከስምንት የመንግስት ተቋማት ጋር አንድ በአንድ ቁጭ ብሎ መወያየቱን ጠቁመው፣ ውይይቱ ከተካሄደባቸው ተቋማት መካከል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል፣ የግብር ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ አስተዳደርና ሌሎች መሆናቸው አመልክተዋል።

በውይይቱም አስር አመላካች ነጥቦችንም መለየታቸውን የጠቀሱት አቶ አበበ፣ እነዚህም የንግድ ፈቃድ፣ የግንባታ ፈቃድ፣ ንብረትን የማስመዝገብ ሂደት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ የብድር አቅርቦት፣ ግብር መክፈልና አከፋፈል፣ ዓለም አቀፍ ንግድ፣ ኪሣራና ዕዳን ማደራጀት፣ የአነስተኛ ባለ አክስዮኖች ጥበቃ እንዲሁም ውል ማስፈጸም መሆናቸውን አብራርተዋል።

ኮሚሽነሩ እንዳሉት፤ እነዚህ ነጥቦች እስካሁን የአዋጅ፣ የመመሪያና ደንብ ማሻሻያ በማድረግ ንግዱን ለማሳለጥ አመላካች በመሆናቸው ከጠቅላይ አቃቤ ህግ ጋር በመሆን አዋጁ ተረቅቆ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ተልኳል። በቅርቡም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ተግባራዊ ይሆናል። ከዚህም በተጨማሪ ተቋማትን የማዘመን ስራ በቅርቡ ይጠናቀቃል።

ኢትዮጵያን በፖሊሲና በህግ ረገድ በቀላሉ ንግድ ሊሰራባት የምትችል አገር ለማድረግ እየተሰራ መሆኑና በቀጣይ የኢንቨስትመንት ማዕከል እንደምትሆን ተስፋቸውን በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ይህ አሰራር እንዲፋጠን መመሪያ መስጠታቸውን ዋና ኮሚሽነሩ አመላክተዋል።

ንግድን ለማሳለጥ...ከ1ኛው ገጽ የዞረ

፡ በሰውና በሀገር ልማት ዕድገት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱትን የጥፋት ኃይሎች ለፍትህ ለማቅረብና የተፈናቀሉ ዜጎችንም ወደ የአካባቢያቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

በክልሉ በኢኮኖሚና በማህበራዊ አገልግሎቶች ባለፉት ስድስት ወራት በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤቶች መገኘታቸውን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በተለይም አርሶ አደሩ ከተበጣጠሰ የእርሻ ስራ ወጥቶ በኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴ እንዲጠቀም በተደረገው ጥረት በ284 ወረዳዎች አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ማልማት መቻሉንና በዚህም ውጤት መገኘቱን አስረድተዋል፡፡

በ2010/ 2011 የምርት ዘመንም ከ819 በላይ ሄክታር መሬት ታርሶ 9.1 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን አመልክተዋል፡፡ በማዕድን ልማት ዘርፍም 96 ቶን ታንታለም፣

304 ኪሎ ግራም ኤመራድ እና ሌሎች ማዕድናትን ማምረት መቻሉንና ከዘርፉ ሰባት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል፡፡ በውሃ አቅርቦትም የክልሉ የንጹህ የውሃ መጠጥ ሽፋን ከነበረበት 63 ነጥብ ስምንት በመቶ ባለፉት ስድስት ወራት በተሰሩ ስራዎች 64 ነጥብ አምስት በመቶ ማድረስ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

አንዳንድ የጉባኤው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት፣ ፀጥታን ለማስፈንና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ የተሻለ ቢሆንም፤ ከዚህ የበለጠ መከናወን እንዳለበትና በመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ የታዩት መዘግየቶች መስተካከል እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

ጉባኤው በሁለት ቀናት ቆይታው በህብረት ስራ ኤጀንሲ አዋጅ ላይና በሌሎችም አጀንዳዎች ላይ ይወያያል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመት እንደሚሰጥም ይጠበቃል፡፡

በኦሮሚያ ክልል...

የጐዳና ላይ ነጋዴዎችን ከሁለት ዓመታት በኋላ ወደ መደበኛ ንግድ ለማሸጋገር እየተሠራ ነው

ከ1ኛው ገጽ የዞረ

Page 3: 78 ንግድን ለማሳለጥ ተጨባጭ ርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ€¦ · ንግድን... በ2ኛው ገጽ ዞሯል 78ኛ

ይህ ዓምድ በተለያዩ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዜጎች ነፃ አስተያየታቸውን የሚሰጡበት ነው።በዓምዱ ላይ የሚወጡ ጽሑፎች የዝግጅት ክፍሉን አቋም አያመለክቱም።አጀንዳ

ርዕሰአንቀፅ

3የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን

አድራሻ:- አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 001

የፖ.ሣ.ቁ፡ - 30145

አዲስ ዘመንበ1933 ዓመተ ምህረት ተቋቋመ በየዕለቱ እየታተመ የሚወጣ

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም

ኢትዮጵያውያን አንድነታቸው ጎልቶ ከወጣባቸው ጊዜያት ሁሉ ተነጥሎ እንደ ምሳሌ የሚነገረውበ1888 ከጣልያን ወራሪ ጋር የተደረገው የአድዋ ጦርነትና ድል ነው። አዎን ከዚያ ቀደም አርባናሃምሳ በማይሞሉ ዓመታት ውስጥ በየአካባቢው በነበሩ ነገስታት እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ባይነትሳይስማሙ ቀርተው እርስ በርስ ጦር ይማዘዙ ነበር። ይሁን እንጂ፤ ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸውየጋራ አካፋይ ነበራቸው። አገር የሚባል!እናም የተለያዩ ስልቶች ተጠቅሞ ቆይቶ፤ በመጨረሻ ጦርና ሰራዊቱን አዘጋጅቶ ኢትዮጵያን

ለመውረር የመጣውን የኢጣልያ ጦር በአንድ ሆኖ በመዋጋትና የአገርን ሉዓላዊነትና የህዝቦቿንአንድነት በማስከበር ሁሉም በአንድነት ቆሟል።ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን የሀገር ጉዳይ ሲነሳ አንዳችም ልዩነት አይታይባቸውም ነበር።

ለእነርሱ አገር ማለት፤ ኢትዮጵያ ማለት አንድና አንድ ብቻ ነበረች፤ ናትም። በዚህም ምክንያትየወቅቱ መሪ ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ህዝባቸው ጦር ሰብቆና ስንቁን ሰንቆ፤ በሰጡት የቀጠሮ ቀን፤ባሉት ቦታ ከትቶ እንዲጠብቃቸው አዋጅ ሲያስነግሩ የህዝቡ ምላሽ አንድ ዓይነት ነበር። የአገሩናየድንበሩ መደፈር ከዙፋኑ በላይ ነበር የቆረቆረው፤ በወቅቱ የነበረው የመጓጓዣና የመገናኛ አውታርእጅግ አስቸጋሪ ቢሆንም የወራት መንገድ በእግሩ ተጉዞ ክተት ወደተባለበት ወረኢሉ ለመድረስ ግንአንዳችም አላገደውም ነበር።የአገር ፍቅር እንደሰብዓዊ ግንኙነት በቃል ብቻ የሚገለጽ አይደለም። የያኔዎቹ ኢትዮጵያውያንጀግኖችም የሀገር ፍቅራቸውን ደም በማፍሰስ፣ አጥንት በመከስከስና መተከያ የሌለው ክቡርሕይወታቸውን በመስጠት ገልጸዋል።አገራቸው ስትደፈር፤ መሪያቸው ጥሪ ሲያቀርብ “እኔ…”አላሉም “እኛ አለን” ብለው ነበር በአንድ

የተሰለፉት። ምናልባት በዘመን ትሩፋት የቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች እና ዘመናዊ በምንባልበት በአሁኑወቅት ልናደርገው አይደለም ልናስበው በሚያጠራጥረን ሁኔታ እኒያ የዚያን ዘመን አባቶች የአስተሳሰብስልጣኔ አሳይተውናል።የኢጣሊያ ወራሪ ኃይል የሰሜኑን የአገሪቱ ክፍል ወርሮ ወሰኑን ወደ መሀል ለማስፋፋት ባሰበበት

ወቅት የታጠቀው ዘመኑ የደረሰበትንና አቅሙ የፈቀደለትን የጦር መሳሪያ ነበር። በአንጻሩ ኢትዮጵያውያንየታጠቁት እጅግ ኋላቀር መሳሪያ ቢሆንም፤ የሰነቁት የአገር ፍቅር እና የአልደፈርም ወኔ ነበርናከአራቱም አቅጣጫዎች ተምሞ ለአገሩ ዘብ ቆመዋል። ያኔ ኢትዮጵያውያንን እገሌ ከእገሌ ሳይባልበአንድ ያቆማቸውና እስከአፍንጫው ከታጠቀው ወራሪ ኃይል ጋር በግንባር ያፋጠጣቸው የአገር

ፍቅራቸውና የነጻነት ቀናኢነታቸው ነበር። እንጂማ፤ ዛሬ የሚባለው ሁሉ ያኔም ነበር። ዛሬ የሚጠራው ያኔምይጠራ ነበር። መቋጠሪያው ውሉ ግን አንድ እና አንድ ሲሆን እሱም አገር ብቻ ነበር!የአገር ፍቅር ፆታ አይለይም፤ ብሔር አይጠይቅም፤ ዕውቀትና ሙያ አምጡ አይልም። መመራመርና

መፈላሰፍም የግድ አይልም። ይህ ከውስጥ የሚመነጭ አክብሮት የሚገለጽበት የውዴታ ስሜት ነው። እናምአባቶቻችን በቁሳዊ ስልጣኔ ኋላቀር ቢሆኑም በአስተሳሰባቸው የዘመኑና የረቀቁ በመሆናቸው ጦርነት ገጥመውድል አደረጉ። የድላቸው መሰረት ደግሞ በአገር ፍቅር ስሜት በአንድነት መቆማቸው ነው።ይህ አንድነታቸው ያስመዘገበው ድል ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪቃውያንም ዓይን መክፈቻ

የምስራች ነበር/ነው። በርግጥም የአድዋ ድል የኢትዮጵያውያን ብቻ አይደለም። ይልቁንም የመላው ጥቁርህዝብ ድል ነው። ዛሬም 123ኛው የድል መታሰቢያ ቀን ሲዘከር የአባቶቻችን አንድነታቸውና የሀገር መውደድስሜታቸው አብሮ ይታሰባል።የአድዋ ድል የአንድነትና የሀገር ፍቅር ስሜት ውጤት ነው። ይህ ውጤት ደግሞ ሁሉም በቅኝ ግዛት ጥላ ስር

የነበረና ለነጻነት የሚታገል የዓለም ህዝብ የተጋራውና የሚጋራው የብርሃን ቀንዲል ነው። ዛሬ ከአንድ መቶ ሃያዓመታት በላይ ሲዘከር የኖረውን የአድዋ ድል ማሰብ ያለብን ወደልቦናችን ተመልሰን መሆን አለበት። ለመለያያሰበብ እየፈለግን ያጋደምነውን የልዩነት መስመር አሽቀንጥረን በመጣል ዳግም ልንዋደድ፤ መልሰን በአንድልንቆም ይኖርብናል። ያለስምምነት አንድነትና ህብረት፤ ያለአንድነትና ህብረት ደግሞ እድገትና ብልጽግናአይታሰብም።እኛ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ወቅት ከምንም በላይ አንድነትና ህብረት ያስፈልገናል። እንደቤተሰብ፤ ልጅ

ወልዶ ለማሳደግ ከፈለግን፤ እንደዜጋ በየአቅጣጫው ወጥተን ገብተን ለመስራት ከተመኘን ከምንም በላይ አገርበምትባል ትልቅ ጥላ ስር በህብረት ልንሰባሰብ ይገባል።ወጣቶች ሀገርን ከቋንቋ በላይ ሊያውቋትና ሊገነዘቧት፤ ተፋቅረው ሊንከባከቧት የግድ ይላል። ይሄ ደግሞ

የሁሉም ሃላፊነት ነው። ትምህርት ቤቶች በስነምግባርና በስነዜጋ ትምህርት ከምንምና ከመቼውም ጊዜ በላይስለሀገር ሊያስተምሩ ይገባቸዋል። መንግስትና ሁሉም ያገባኛል ባይ ተቋማት አንድነትን፤ በጋራ መቆምንሊሰብኩና ሲያሳውቁ ይገባል።የአድዋ ድል በእኛ በኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን በአፍሪካውያንም ዘንድ የነጻነትና የአልደፈርም ባይነት

ተምሳሌት ነውና በጀመርነው ድህነትን የማጥፋት አገራዊ ዘመቻ በአንድ ቆመን ድሉን ልንደግመው ይገባል።በልዩነታችን ደምቀንና አንድነታችንን በሚያጎሉ አገራዊ ትሩፋቶች ታጅበን ያማረና የሰመረ ነገን ለተተኪዎችእንድናስተላልፍ ቅድሚያ ለአገር፤ ቅድሚያ ለህብረት ማለት ተገቢ ነው እንላለን።

ዛሬም ቅድሚያ ስለአገር ብለን እንቁም!

የዕለቱ ምክትል ዋና አዘጋጅ፡ - ዳንኤል ታምሩ ፈረደ

ስልክ ቁጥር- 011 -126-43-19

ጌትነት ምህረቴ

አጐናፍር ገዛኽኝ

መልካምስራ አፈወርቅ

ዳንኤል ዘነበ

ግርማ መንግስቴ

ፍሬህይወት አወቀ

ዋና አዘጋጅ - ፍቃዱ ሞላኢ ሜይል - [email protected]አድራሻ - የካ ክፍለ ከተማወረዳ - 13የቤት ቁጥር - B402 H11ስልክ ቁጥር - 011 -126-42-40

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅስልክ - 011 -126-42-22

የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ዘርፍየኢሜይል አድራሻ [email protected]

ስልክ - 011 - 156-98-73ፋክስ - 011 - 156-98-62

የማስታወቂያ መቀበያ ክፍልስልክ - 011 - 156-98-65

የማስታወቂያ ሽያጭ ማስተባበሪያስልክ - 011 -1 -26-43-39

ማከፋፈያ ስልክ - 011 - 157-02-70

website www. press.et

email. [email protected]

Facebook Ethiopian Press Agency

የዝግጅት ክፍል ፋክስ- 251-011-1-56-98-62

በይገደብ አባይ

በ ዓለማችን በትልቅነቱ የመጀመሪያውንደረጃ የያዘ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብነው፡ ፡ 22 ሺ 500 ሜጋዋት ሃይል የማመንጨትአቅም አለው፡ ፡ የግድቡ ግንባታ ሲጀመር፤ በአካባቢውስነምህዳር እና በህብረተሰቡ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖያመጣል ከሚለው የ‹‹ተቆርቋሪዎች›› እሮሮ እናተቃውሞ ጀምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችንከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ ያደረገ ፕሮጀክት በሚልዓለም ያወገዘው ግድብ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል፡ ፡

አሁን ላይ ይህ ሁኔታው ተቀይሮ በዓለማችንአሉ ከሚባሉ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦችመካከል በሚሰጠው ከፍተኛ ጥቅም የሚወደስግድብ ለመሆን በቅቷል፡ ፡ ይህ ግድብ ስሪ ጎርጅስበመባል የሚታወቀውና ከ400 በመቶ በላይ ተጨማሪወጪ ወጥቶበት የተጠናቀቀው የቻይና ሃይልማመንጫ ግድብ ነው፡ ፡ በዓለም ላይ በርዝመቱሶስተኛ በሆነው በያንግዚ ወንዝ ላይ የተገነባው ስሪጎርጅ ግድብ ብዙ ፈተናዎችን አልፎ ዛሬ በቻይናየሀይል አቅርቦት ላይ አዎንታዊ ሚና በመጫወትላይ ይገኛል፡ ፡

ስሪ ጎርጅ ግድብን ለማሳያነት የተጠቀምኩትየሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በባህሪያቸውከተያዘላቸው ጊዜና በጀት በላይ ፈጅተውእንደሚጠናቀቁ ለማሳየት ያህል ነው፡ ፡ የህንዱ ሳርዳርሳሮቫር 513 በመቶ፣የማሌዢያው ባኩን 417በመቶ፣ የሩሲያው ሳያኖ-ሹሼንስካያ 353በመቶ፣የካናዳው ላግራንዴ 246በመቶ ተጨማሪ ወጪወጥቶባቸው ከተጠናቀቁት የሀይል ማመንጫፕሮጀክቶች መካከል በዋነኛነት ይጠቀሳሉ፡ ፡የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች መጀመሪያታሳቢ ሲደረጉ እድገትን የሚያፋጥኑና ለልማትአይነተኛ መንገድ መሆናቸው ታምኖባቸው ቢሆንም

በጥንቃቄ ካልተያዙና ካልተመሩ ግን የሀገር ኢኮኖሚላይ ጉዳት ሊያደርሱ እንደሚችሉ የዘርፉ ባለሙያዎችይናገራሉ፡ ፡

የታላቁ ህዳሴ ግድባችንም ያጋጠሙት እንቅፋቶችእና ፈተናዎች በተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ላይ ያጋጠሙበሌሎች የሰለጠኑ ሀገራትም ቢሆን የታዩ ክስተቶችናቸው፡ ፡ ዋናው ነገር ፈተናዎችን ተቋቁሞ ለውጤትእንዲበቃ መደገፍ ከሁላችንም የሚጠበቅ ሃላፊነትመሆኑን መረዳት ጊዜው የሚጠይቀው ጉዳይ መሆኑነው፡ ፡ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ያጋጠሙትችግሮች በግልጽ የታወቁ በመሆናቸው መንግስትላለፉት ወራት መፍትሄዎቹን ሲያመቻችቆይቷል፡ ፡ችግሮቹ በዋናነት በሀይድሮ ኤሌክትሮመካኒካል እና በሃይድሮሊክ ስቲል ስትራክቸር ስራዎችያጋጠሙ የመዘግየት ችግሮች ናቸው፡ ፡

ችግሮቹ በዋናነት በሀይድሮ ኤሌክትሮ መካኒካልስራዎች የሀገራችን ባለሙያዎች የነበራቸው ልምድአናሳ መሆን፣ የማምረት፣ የተከላ እና የፕሮጀክትአስተዳደር ልምድ ውስንነት፣ የፕሮጀክቱን ጥልቀትናውስብስብነት በትክክል በመረዳት አፋጣኝ መፍትሄያለመውሰድ፣ በብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግኮርፖሬሽን የተሰሩ ስራዎች (Bottom outlet,culvert, waterway penstock, gates)ጥራትና ልኬት ፕሮጀክቱ በሚፈልገው ደረጃአለመሆን በዋናነት ያጋጠሙ ችግሮች ናቸው፡ ፡

መንግስት ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየትምክንያት ናቸው ያላቸውን ችግሮች ገምግሞ ሁሉንአቀፍ ማሻሻያ ሲያከናውን ቆይቷል፡ ፡ በተለይምበመስኩ አለም አቀፋዊ ዕውቅና ያላቸውና ፕሮጀክቱንየሚያውቁ የውጭ ኩባንያዎች ወደ ሥራ እንዲገቡበማድረግ፤ የግድቡን ግንባታ በአራት ዓመታትውስጥ ለማጠናቀቅ ርብርቡ ቀጥሏል፡ ፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ስራአስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ ግድቡን ሙሉ በሙሉአጠናቅቆ ከፍሬው ለመቋደስ በሚደረገው ጥረትሁለት ዋና ዋና ተግዳሮቶች የሚያጋጥሙ መሆናቸውንይናገራሉ፡ ፡ ችግሮቹም ፤ በብረታ ብረት ስራዎችላይ የታዩ እንከኖችን የማረም እና ለቀሪዎቹ ስራዎችፋይናንስ ማፈላለግ ናቸው፡ ፡

በብረታ ብረት ስራዎች ላይ የታዩ እንከኖችንየማረም ሃላፊነትን በዘርፉ የተሰማሩት ኩባንያዎችቢሆንም፤ የፋይናንስ ምንጮቹ ግን እኛውመሆናችንን መዘንጋት አይገባም፡ ፡ የፋይናንስ ጉዳይ፤ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ችግር አይሆንም፡ ፡ምክንያቱም ኢትዮጵያውያን፤ ለህዳሴ ግድብየሚሰስቱት ነገር እንደሌለ በቢሊዮን የሚቆጠርብሮችን በመስጠት እና በመለገስ አስመስክረዋልና፡ ፡

የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጓተት ኢትዮጵያውያንንያስከፋውን ያህል ጉዳዩ ያስደሰታቸውም አልጠፉም፡ ፡ጉዳዩ በተለይ አንዳንድ ግብጻውያንን ጮቤአስረግጧል፡ ፡

የግድቡ ግንባታ የሚጠናቀቅበት ጊዜ በአራትዓመት መራዘሙ ያስደሰታቸው አንዳንድ ግብጻውያንበተለይም ታዋቂ ጋዜጠኞች በተለያየ መንገድደስታቸውን ገልጸዋል፤ ‹‹ጸሎታችን ሰመረ›› ያሉምአልጠፉም፡ ፡ታዋቂው የግብጽ ቴሌቪዥን አዘጋጅአምር አዲብ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚጠናቀቅበትጊዜ በአራት ዓመት መራዘሙን ሲሰማ ‹‹ይህ ከአላህየተላከ ገጸበረከት ነው፡ ፡ ›› ነበር ያለው፡ ፡አምር በዚህብቻ አላበቃም ‹‹ኢትዮጵያውያን ወንድሞቼንልነግራቸው እፈልጋለሁ፡ ፡ አትቸኩሉ፣ ታገሱ፤የገነባችሁትን በሙሉ አፍርሱና እንደ አዲስግንባታውን ጀምሩ ባይሆን መሀንዲሶችእንልክላችኋለን››ሲል ተሳልቋል፡ ፡

የዚህ ጋዜጠኛ ንግግር ፤እኛ እንደ ዓይናችንብሌን በምንሳሳለት የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ልማታችንንየማይፈልጉ ሀይሎች ምን ያህል እንቅልፍ አጥተውእንደሚኖሩ የሚያሳይ ነው፡ ፡ በግድቡ ዙሪያ ለደቂቃእንኳን መዘናጋት እንደሌለብን ይልቁንምአንድነታችንን ማጠንከር እንደሚገባ መልዕክትየሚያስተላልፍ ነው፡ ፡ ‹‹የግድቡ ግንባታ ይዘገያል››መባሉን ግብፃውያን እንደ ፈጣሪ ስጦታቆጥረውታል፡ ፡እውነቱን ለመናገር ለዘመናት በአባይውሀ የመጠቀም ተፈጥሯዊ መብታችንን ሳንጠቀምበትቆየን እንጂ አባይስ ከማንም በላይ ስጦታነቱለኢትዮጵያውያን ነበር፡ ፡ አሁንም ግን አልረፈደም፡ ፡እናም ግንባታውን በተያዘለት ጊዜ አጠናቅቀን ጥቅምላይ በማዋል የጠላቶቻችንን አንገት በማስደፋት

ወገንን መካስ ይገባናል፡ ፡የህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየቱ ኢትዮጵያውያንን

ማስከፋቱ ተገቢ ነው፡ ፡ ይህ መከፋት ቁጭትየወለደው ነው ብዬ አምናለሁ፡ ፡ ከድህነት ለመውጣትበምናደርገው ትግል ትልቅ እገዛ ያደርግልናል በሚልበተስፋ ስንጠብቀውና እንደ ዓይናችን ብሌን በስስትስናየው የኖርን ፕሮጀክት በመሆኑ መከፋታችንምክንያታዊ ቢሆንም እንኳ እየቆዘምን ልንኖር ግንአይገባም፡ ፡ ዳግመኛ በእልህና በወኔ ተነሳስተንግድባችንን ለማጠናቀቅ መትጋት አለብን፡ ፡ ከፊታችንሁለት አማራጮች አሉን፡ ፡ ህዳሴ ግድብ ተጓተተ፣ተዘረፈ፣ቆመ…ወዘተ እያሉ እና እየቆዘሙ መኖርአሊያም በቁጭት ተነሳስቶ ግድቡን መደገፍ ብሎምማጠናቀቅ፡ ፡

ግድቡን ገንብቶ ማጠናቀቅ አማራጭየሚቀመጥለት ጉዳይ አይደለም፡ ፡ ግድቡን ማቆምመሸነፍ ነው! ሽንፈትን መቀበል ደግሞየኢትዮጵያውያን ባህል አይደለም፡ ፡ ግድቡንአለማጠናቀቅ በኢትዮጵያ ተፈጥሮ የነበረውንየይቻላል መንፈስ በማኮላሸት ዳግም ወደ ነበርንበትየጭለማ ዘመን ለመመለስ መፍቀድ ማለት ነው፡ ፡ይህ የማይሆን ነገር ነው፡ ፡ ማንም ሰው ከብርሀንጨለማን ሊመርጥ አይችልም፡ ፡ ማንም ሰው እናቱናእህቱ በኤሌክትሪክ እጦት ምክንያት ለዘመናትበጭለማ ውስጥ እንድትዳክር፤ በኩበት ጢስእየተጨናበሰች እንድትኖር አይፈቅድም፡ ፡ኢትዮጵያውያን ከመቼውም ጊዜ በላይ መተባበርአለብን፡ ፡ በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚገኙኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ግድቡንመደገፍ አለባቸው፡ ፡

እርግጥ ነው በሀገር ውስጥ ካለው ኢትዮጵያዊተሳትፎ አንጻር ሲታይ የዳያስፖራው ማህበረሰብድጋፍ ውስን ነው ማለት ይቻላል፡ ፡ በዳያስፖራውናበመንግስት መካከል የነበረው ጤናማ ያልሆነ ግንኙነትየዳያስፖራውን ተሳትፎ እንዲያንስ አድርጎታል፡ ፡በሀገር ውስጥ ያለው ኢትዮጵያዊ ዘር፣ቋንቋ፣ሃይማኖት ሳይለየው ድጋፉን የለገሰ ቢሆንምቁጥሩ 3ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ በሚታሰበውዳያስፖራ ማህበረሰብ ዘንድ የነበረው ድጋፍ ግን

የሚጠበቀውን ያህል ካለመሆኑም በላይበተቃውሞም ጭምር የታጀበ መሆኑ ሲያስተዛዝበንቆይቷል፡ ፡ በአንዳንድ የአሜሪካ ግዛቶች የፖለቲካእስረኞችን የማትፈቱ ከሆነ የህዳሴ ግድብንአንደግፍም በማለት ህዳሴ ግድብን እንደመደራደሪያያቀረቡበት ሁኔታ ሌላው አሳዛኙ ክስተት ነበር፡ ፡ዳያስፖራው በፖለቲካ ልዩነት ብቻ ፖለቲካንከህዳሴ ግድብ ነጣጥሎ ባለማየቱም የህዳሴ ግድብቦንድ ሺያጭ በአሜሪካ እንዲስተጓጎል አድርጓል፡ ፡መንግስት የታላቁ ህዳሴ ግድብን የሚገነባውየተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ብሎምየእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ህይወት የተሻለ ለማድረግመሆኑን መዘንጋት አይገባም፡ ፡ ከዚህ አንጻርዳያስፖራው የቀጣዩን ትውልድ መጻኢ ህይወትለማሻሻል በሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋፅኦየማድረግ ሀገራዊ ግዴታ እንዳለበት ሊረዳ ይገባል፡ ፡

በአሁኑ ወቅት ምቹ ፖለቲካዊ ሁኔታተፈጥሯል፡ ፡ ዳያስፖራው በተለያዩ አህጉራትጠንካራ ኮሙዩኒቲዎች ያሉት በመሆኑ መንግስትበተለይም የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት እነዚህን ኮሙዩኒቲዎችበስፋት በመጠቀም ዳያስፖራው ድጋፍ እንዲያደርግመስራት አለበት፡ ፡

ዳያስፖራው በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በቂመረጃ የሌለውና ከፖለቲካዊ ፋይዳው ይልቅበቀጣይ ለሀገራችን የሚኖረውን ኢኮኖሚያዊጠቀሜታ ያልተረዳ መሆኑን ግምት ውስጥበማስገባት በዳያስፖራው ማህበረሰብ ተደማጭየሆኑ መገናኛ ብዙሃንን ተጠቅሞ ህዳሴ ግድብንየተመለከቱ ግልፅ፣ወቅታዊና እውነተኛ መረጃዎችለዳያስፖራው ማህበረሰብ የሚቀርብበትን ምቹሁኔታ መፍጠር ተገቢ ነው፡ ፡ያለብንን የሀይል ችግር በመቅረፍ ከሌሎች

ህዝቦች ጋር በኢኮኖሚ ለመተሳሰር ያስችለናል ብለንየጀመርነውን የህዳሴ ግድብ ብናጠናቅቀው ብሔራዊኩራታችን እንደሚሆን ሁሉ የሚጠበቅብንን ድጋፍባለማድረጋችን ምክንያት ግድቡ ሳይጠናቀቅ ቢቀርዕድሜ ልካችንን የምንሸማቀቅበት ብሔራዊ ውርደትመሆኑን ለአፍታም እንኳን ልንዘነጋ አይገባም፡ ፡

ግድቡን ማጠናቀቅ ብሔራዊ ኩራት፤

አለማጠናቀቅ ግን ብሔራዊ ውርደት!

Page 4: 78 ንግድን ለማሳለጥ ተጨባጭ ርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ€¦ · ንግድን... በ2ኛው ገጽ ዞሯል 78ኛ

ዓለም አቀፍየካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን 7

በአዲስ አበባ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር በየአስራ አምስት ቀን ረቡዕ የሚወጣ

ተስፋ ያልተጣለበት የአውሮፓ ኅብረት-አረብ ሊግ ጉባዔአንተነህ ቸሬ

የመጀመሪያው የአውሮፓ ኅብረት እና የአረብ ሊግ የጋራ ጉባዔ (EU-Arab

League Summit) ሰሞኑን በቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ በምትገኘው የግብጿ ሻርም አል-ሼክ ከተማ ተካሂዷል፡፡ የአረቡ ዓለም በእርስ በእርስ ጦርነቶች፤ በባህረ ሰላጤው ፖለቲካዊ ፍጥጫና በሌሎች ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፤ እንዲሁም አውሮፓ ደግሞ በ‹‹ብሪኤግዚት (Brexit)››፤ በስደተኞችና በምጣኔ ሀብት ቀውስ ጉዳዮች ተወጥረው ባሉበት ወቅት ለሁለት ቀናት የተካሄደው የጋራ ጉባዔ፣ የአውሮፓንና የአረቡን ዓለም ትብብር ለማጠናከር ታስቦ የተካሄደ እንደሆነ የአውሮፓ ኅብረት ባወጣው መግለጫ ላይ ተመልክቷል፡፡

ከ40 አገራት የመጡ መሪዎችና ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት በታደሙበት የሻርም አል-ሸኩ ጉባዔ ላይ የመካከለኛው ምስራቅ ሰላምና የስደተኞች ጉዳይ፤ የሶሪያ፤ የየመንና የሊቢያ የእርስ በእርስ ጦርነቶች፤ እንዲሁም የምጣኔ ሀብት ቀውስ ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳዎች እንደነበሩ ተዘግቧል፡፡

የግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ እና የአውሮፓ ካውንስል ፕሬዚዳንት ዶናልድ ተስክ በጋራ በመሩት በዚህ ጉባዔ ላይ ከታደሙት የአውሮፓና የዓረቡ ዓለም አገራት መሪዎች መካከል የጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል፤ የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ፤ የብሪታኒያዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ፤ እንዲሁም የሳዑዲ አረቢያና የኩዌት ነገሥታት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ይሁን እንጂ፤ ‹‹ጉባዔው ተሰብስበን መከርን›› ብሎ ከማውራት የዘለለ ፍሬ የሚያፈራ ሊሆን እንደማይችል የፖለቲካ ተንታኞች እየገለፁ ነው፡፡ መቀመጫውን ዶሃ ባደረገው የአረብ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት ሶርያዊው ማርዋን ካባላን፤ ከጉባዔው ፍሬ ያለው ነገር እንደማይጠብቁ ይናራሉ፡፡ ‹‹እኔ በግሌ ከጉባዔው ትርጉም ያለው ነገር አልጠብቅም፡፡ መሪዎቹ ለውይይት በቀረቡት ሁሉም አጀንዳዎች ላይ መስማማት እጅግ ያዳግታቸዋል›› ይላሉ፡፡

እርሳቸው እንደሚሉት፣ ጉባዔው ፕሬዚዳንት አል-ሲሲ ስልጣናቸውን የሚጋፋቸውን ማንኛውንም ድርጊት ለመቆ ጣጠር ሲሉ የሚወስዷቸው ርምጃዎች አወዛጋቢ

ቢሆኑም፤ ሰውየው በቀጣናው ተፅዕኖ ፈጣሪ መሪ እንደሆኑ ለማሳየት እድል ይፈጥርላቸዋል::

ባለፈው ሳምንት የግብፅ ባለስልጣናት በቀድሞው የአገሪቱ ዓቃቤ ሕግ ሂሻም ባራካት ግድያ የተጠረጠሩ ዘጠኝ የሙስሊም ወንድማማችነት (Muslim Brotherhood) ፓርቲ አባላትን በሞት መቅጣታቸው ይታወሳል፡፡ እ.አ.አ በ2015 ለተፈፀመው የባራካት ግድያ ኃላፊነት የወሰደ አካል ባይኖርም፤ የግብፅ ባለስጣናት ግን ድርጊቱን በሕግ በተወገዘውና የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ ፓርቲ በሆነው በሙስሊም ወንድማማችነት ላይ አመካኝተዋል፡፡

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ደግሞ፤ የግብፅ ፓርላማ አብደል ፋታህ አል-ሲሲ እስከ 2034 (እ.ኤ.አ) በስልጣን ላይ ለመቆየት እድል የሚሰጣቸውንና የአገሪቱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክፉኛ የኮነኑትን ሕግ አፅድቋል፡፡

ማህጁብ ዝዌሪ የተባሉ ዮርዳኖሳዊ የመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካ ተንታኝ፤ ግብፃውያን የአረብ ሊግን የሚፈልጉት በቀጣናው ያላቸውን የበላይት ለማሳየት ብቻ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ተንታኙ እንደሚሉት፤ ግብፅ ያለ አረብ ሊግ በአካባቢው ተፅዕኖ መፍጠር አትችልም፡፡ ሊጉ ግብፃውያን በአረቡ ዓለም መሪና ኃያል ሆነው እንዲታዩ ትልቅ ሚና አለው፡፡

ተንታኞቹ እንደሚገልፁት፤ በጉባዔው ላይ የተሳተፉት የአውሮፓ አገራት መሪዎች ትኩረት መስጠት የሚፈልጉት ከሰሜን አፍሪካና ከሶሪያ ወደ አውሮፓ ስለሚገቡ ስደተኞች ጉዳይና ስለሽብርተኝት ነው፡፡ የአውሮፓ መሪዎች የአረቡን ዓለም ቀጣና የሽብርተኞችና የታጣቂ ቡድኖች መፈልፈያና የስደተኞች መነሻ አድርገው ስለሚቆጥሩት ችግሩን ለመፍታት የአረብ አገራት መሪዎችን ድጋፍና ትብብር ይሻሉ፡፡

ካላባን ‹‹የአውሮፓ አገራት የችግሮቹን ገፈት እየቀመሱ ቢሆንም የችግሮቹ ምንጮች በሆነው አካባቢ ዘላቂ ለውጥ እንዲመጣ ጠንከር ያለ ርምጃ ሲወስዱ አይታዩም፡፡ ይባስ ብለው የአውሮፓ አገራት የአረብ አምባገነኖችን ሲደግፉ ይስተዋላል፤›› ይላሉ፡፡

የአረብ አገራት መሪዎች ባለፈው ወር ቤይሩት ወስጥ በተካሄደው የአረብ ኢኮኖሚ ጉባዔ ላይ ሊባኖስ ውስጥ ስላለው የስደተኞች ቀውስ ሳይነጋገሩ ቀርተዋል፡፡ በሶሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ከተሰደዱ ከስድስት

ሚሊዮን ሶሪያውያን መካከል ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡት ሊባኖስ ውስጥ ተጠልለለው ይገኛሉ፡፡ በጉባዔው የሊባኖስ ፓርላማ አፈ ጉባዔ ናቢህ ቤሪ ለስደተኞች ችግር እልባት ለመስጠትና ሶሪያን መልሶ ለማቋቋም የሶሪያ ተሳትፎና ትብብር ወሳኝ እንደሆነ ተናግረው ነበር፡፡

ሃምዛ አል-መስጠፋ የተባሉ ሶርያዊ የጥናትና ምርምር ባለሙያ በበኩላቸው የሻርም አል-ሼኩ ጉባዔ ልክ ቤይሩት ውስጥ እንደተካሄደው የምጣኔ ሀብት ጉባዔ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል የሚል እምነት የላቸውም፡፡ የአረብ ሊግ ከሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች መካከል ብዙዎቹ ተፈፃሚ እንደማይሆኑ የሚጠቅሱት ሃምዛ አል-መስጠፋ፣ በአውሮፓ ኅብረትና በአረብ ሊግ ጉባዔ የተደረሱ ስምምነቶች ተፈፃሚነት አጠራጣሪ ነው ሲሉ ይናገራሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፤ አሜሪካን በተመለከተ በሚነሱ ጉዳዮች ላይ ከወገንተኝነት የፀዳ አቋም ከመያዝና ወሳኔ ከማሳለፍ ይልቅ ሁለቱም ማኅበራት የአሜሪካን መንገድ መምረጥ ይቀናቸዋል፡፡

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ያላት ፖሊሲ ግልፅ እንዳይሆን አድርጓል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ከፍልስጤም የሰላም ስምምነት እስከ ሶሪያ ወታደራዊ ዘመቻ ያሳዩት አቋም አሜሪካ ለበርካታ ዓመታት በመካከለኛው ምስራቅ ላይ ስታራምደው የቆየችውን ስትራቴጂ የገለባበጠ ሆኗል፡፡

በእርግጥ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ

በሶሪያ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች ከሶሪያ እንደሚወጡ ይፋ ሲያደርጉ ውሳኔው ራሱን ‹‹እስላማዊ መንግሥት (Islamic State)›› እያለ የሚጠራው ቡድን ተመልሶ እንዲያንሰራራ በማድረግ በቀጣናው ተጨማሪ የፀጥታ ስጋትና የስደተኞች ቀውስ እንዲፈጠር ያደርጋል በማለት የአውሮፓ ኅብረትና የአረብ ሊግ የፕሬዚዳንቱን ውሳኔ መቃወማቸው ሁለቱ ማኅበራት የፕሬዚዳንቱን ውሳኔ ለማስቀልበስ አጋጣሚ እንደሚያገኙ አል-ሙስጠፋ ያስረዳሉ፡፡

እስላማዊ መንግሥት በሶሪያ ውስጥ በጠቅላላ ሽንፈት አፋፍ ላይ መገኘቱ የቡድኑ ተዋጊዎች ወደ አውሮፓ ሊሸሹ ይችላሉ የሚል ስጋት ያደረባቸው የአውሮፓ አገራት መሪዎች፤ የአሜሪካ ወታደሮች ከሶሪያ ይወጣሉ የሚለውን ውሳኔ ከመቃወምም አልፈው በፕሬዚዳንት ትራምፕ ላይ ከረር ያለ ትችት እንዲሰነዝሩ ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በአሜሪካ በሚደገፈው የኩርድ ታጣቂ ቡድን የተማረኩትን አንድ ሺህ የአሸባሪው ቡድን አባላት የመልቀቅ እቅድ አላቸው መባሉም ዜጎቻቸው ቡድኑን የተቀላቀሉ የአውሮፓ መሪዎችን ክፉኛ አስደንግጧል፡፡

በጉባዔው የተገኙ የአረብ አገራት መሪዎችም ከአውሮፓውያኑ ጋር ስለሚነጋገሩባቸው ጉዳዮች ስምምነት ላይ ሳይደርሱ ወደጉባዔው እንደገቡ ሲገለፅ ነበር፡፡ ዝዌሪ እንደሚሉት አብዛኞቹ የአረብ አገራት ከአውሮፓ አገራት

ጋር ያሏቸውን ጉዳዮች በጋራ በሚያደርጓቸው የሁለትዮሽ ስምምነቶች በኩል መጨረስ ይፈልጋሉ፡፡ ‹‹ላለፉት 20 ዓመታት የተካሄዱ መሰል ጉባዔዎች አንዳችም ለውጥ አላመጡም:: የአውሮፓ አገራት የአረቡን ዓለም ችግሮች ለመፍታት ልባዊ ቁርጠኛት የላቸውም›› ይላሉ::

ከጉባዔው አጀንዳዎች መካከል አንዱ እንደነበር የተነገረለት የእስራኤል-ፍልስጤም የሰላም ድርድር የአውሮፓንና የአረቡን ዓለም ሰዎች በቀላሉ ያስማማል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ካባላን እንደሚሉት፤ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ናት ብለው እውቅና ከሰጡ ወዲህ ክፉኛ የተበሳጩት አረቦቹና በሰላም ድርድሩ ተስፋ የቆረጡት የሚመስሉት አውሮፓውያኑ በጉዳዩ ላይ ተቀራርቦና ተስማምቶ ለመስራት ይቸገራሉ፡፡

‹‹አል ሻባካ (Al Shabaka)›› የተባለው የፍልስጤም የፖሊሲ ማዕከል ዳይሬክተር ናዲያ ሂጃብ፤ የአውሮፓ ኅብረት ባሳየው ቸልተኝነትና አቅመ ቢስነት ምክንያት የፍልስጤማውያን መብት ጥሰት ጉዳይ ተቀብሮ እንዲቀር ተደርጓል›› በማለት ለአልጀዚራ ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ ለሁለት ቀናት በግብፅ ሻርም አል-ሼክ የመከሩት የአውሮፓና የአረቡ ዓለም አገራት መሪዎች ፍሬ ላለው ነገር እንዳልተሰበሰቡ የፖለቲካ ተንታኞቹ ያስረዳሉ፡፡

በእርግጥስ ጉባዔው እንደተባለው ‹‹የታይታ ብቻ ሆኖ ይቀራል ወይ?›› ለሚለው ጥያቄ ጊዜ እውነተኛውን ምላሽ ይሰጣል፡፡

ውብሸት ሰንደቁ

የአዲስ አበባ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ዜጎችን ህይወት ለመቀየር ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል:: ሆኖም ቢሮው ብቻውን ሊወጣ የማይችለው ማህበረሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ከማህበረሰብ ተሳትፎ አይነቶች የሚጠበቁ በርካታ ሲሆኑ በዋናነት በሚከተሉት አምስት ደረጃዎች ይገለፃሉ፡፡ አንደኛው መረጃ ማግኘት ነው፡፡ የመረጃ ልውውጥ መኖር አንዱ አይነት የማህበረሰብ ተሳትፎ መገለጫ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ለሌሎች አይነት ተሳትፎዎች ውጤታማነት እንደመንደርደሪያ የሚረዳ ነው፡፡ መረጃ በመንግሥትና በህዝብ መካከል ለሚፈጠር አመኔታ መጐልበት ወሳኝ ነው፡፡ ዜጎች ኢ-መደበኛ ካልሆኑ መንገዶች በሚያገኟቸው የተዛቡ መረጃዎች የተነሳ በመንግሥትም ሆነ መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት በሚሠሩ የልማት ሥራዎች የተሳሳተ አመለካከት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በመሆኑም ወቅታዊ፣ግልፅ እና ትክክለኛ መረጃ ማግኘት የአመለካከት ክፍተቱን በመሙላት ህብረተሰቡ በየአካባቢው በሚሠራው የልማት ሥራ ያለውን አመኔታ ያሳድጋል፡፡

ሀሳብ መስጠት ሁለተኛው የማህበረሰብ ተሳትፎ ነው፡፡ በመንግሥትም ሆነ መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት በየአካባቢው የሚሠሩ የልማት ሥራዎች ላይ አስተያየት፣ ሃሳብ፣ ትችት እና አማራጮችን ማቅረብን የሚመለከት ነው፡፡ በዚህ ደረጃ ህብረተሰቡን በአካባቢው በሚሰሩ የልማት ስራዎች በብቃት ለማሳተፍ ተሳታፊዎች በቅድሚያ በቂ መረጃና ስለ ጉዳዩ በቂ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የሚኖራቸው ተሳትፎ ለይምሰል ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡

ማካተት ሦስተኛው የማህበረሰብ ተሳትፎ ማሳደጊያና ማበረታቻ መንገድ ነው፡፡ በዚህ ደረጃ የልማት ሥራዎች በቀጥታ ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን የሚፈፀሙና ፍላጐታቸውን በአግባቡ በመረዳት ጥቅማቸው መጠበቁን ባረጋገጠ ሁኔታ በጋራ የሚሰራበት የተሳትፎ ሁኔታ ነው፡፡ ከዚህ በመቀጠል የሚገኘው አራተኛው በትብብር

”እጅ ለእጅ ተያይዘን ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ዜጎችን ሕይወት እንቀይር!”

መሥራት ነው፡፡ ህብረተሰቡ ዋነኛው የሥራው ባለቤት ሆኖ ከዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ትግበራ ድረስ ባሉ ሂደቶች እንዲሳተፍ በማድረግ እና በተለያየ ሂደት ውሳኔ በሚሰጥበት ጊዜ ከሕዝብ ጋር ግንባር በመፍጠር ድርሻ እንዲኖራቸው ሲደረግ ነው፡፡ አምስተኛው የወሳኝነት ድርሻ ወይም የበቃ ተሳትፎ ነው፡፡ በአካባቢው የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን አስመልክቶ ማናቸውንም ውሳኔ የመስጠት ሙሉ በሙሉ በማህበረሰቡ እጅ እንዲሆን የሚያስችል የተሳትፎ ደረጃ ነው፡፡

እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ጉዳዮች የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደጊያና ማረጋገጫ መንገዶች ሲሆኑ ከጎዳና የሚነሱ ዜጎችን ውጤታማ ለማድረግ አይነተኛ ሚና እንዲኖር ያደርጋል፡፡ በቅርብ ጊዜ ተጀምሮ እየተካሄደ ያለው የጎዳና ተዳዳሪዎችን ከጎዳና የማንሳት ሥራ ብዙዎች ከጎዳና ህይወት እንዲወጡ ለማድረግ የታሰበ ነው:: በዚህ ሂደት የሚካተቱት ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ሰዎች፣ የአካልና የአእምሮ ጉዳተኞች፣ ጧሪና ደጋፊ ያጡ አረጋውያን፣ ያለወላጅ

ወይም ያለአሳዳጊ የቀሩ ህፃናት፣ የወሲብ ንግድ ተዳዳሪዎች፣ በልመና ላይ የተሰማሩ ሰዎች፣ የአልጋ ቁራኛ ሆነው ረዳት የሌላቸው ህመምተኞች እና የሱስ ተገዥዎችና የመሳሰሉት የህብረተሰብ ክፍሎች ይገኙበታል፡፡ እነዚህን ተጋላጭ ዜጎችን ለመደገፍ እና በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስፈልግ ሀብትን በማህበረሰብ አቀፍ አደረጃጀት ለማሰባሰብ እና ለማስተዳደር በማስፈለጉ የማህበራዊ ዋስትና ፈንድ በደንብ ቁጥር 106/2011 ተቋቁሟል፡፡

የማህበራዊ ዋስትና ፈንድ ማለት ከህብረተሰቡ፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከግለሰቦች፣ ከሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ከኃይማኖት ተቋማት፣ ከመንግሥት ልማት ድርጅቶች፣ ከከተማ አስተዳደር እና ከሌሎች ህጋዊ ምንጮች በአይነት፣ በገንዘብ፣ በእውቀት እና በጉልበት የሚገኝ ድጋፍ ነው፡፡ በዚህ መሰረት የትረስት ፈንድ ምንጭ ከከተማው አስተዳደር የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ፤ ከህብረተሰቡ የሚሰበሰብ ድጋፍና ስጦታ፤ ከንግዱ ማህበረሰብና ከተለያዩ ግለሰቦች የሚሰጥ ልዩ ልዩ ድጋፍ፤ ከሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች የሚገኝ

እርዳታና ድጋፍ፤ ከኃይማኖት ተቋማት የሚገኝ ድጋፍና ስጦታ፤ ከመንግሥት ልማት ድርጅቶች የሚሰጥ ድጋፍና ስጦታ፤ ከእድሮች ወይም ኡላማዎች የሚሰጥ ድጋፍና ስጦታ፤ ከሲቪክ ማህበራት የሚደረግ ድጋፍና ስጦታ እና ሌሎች ህጋዊ ምንጮች ይሆናሉ፡፡ የፈንዱ የበላይ ጠባቂ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ፕሬዚዳንት ወይም ፕሬዝዳንቷ የሚሰይሙት ሰው ይሆናል፡፡

የትረስት ፍንዱ ዓላማ ለማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን በዘላቂነት ማቋቋም፤ማህበራዊ ችግር ተጋላጭነትን መከላከል፤ የሥራ ፈጠራ ክህሎት ያላቸው ደሀ ሴቶችና ወጣቶችን መደገፍ እና በጎ ፈቃደኝነት ባህል እንዲሆን ማበረታታት ነው፡፡

ቅዳሜ ጥር 25 ቀን 2011 ዓ.ም ተቋቋሚዎቹን ከአራት ክፍለ ከተሞች ማለትም አዲስ ከተማ፣ አራዳ፣ ቂርቆስ እና ልደታ 3500 ያህል ዜጎች ተነስተው ወደ ሦስት ማእከላት ማለትም ግሎባል ኢንፋንታይል (የካ)፣ ፊንፊኔ ትምህርት ቤት (ቂርቆስ)፣ ሚኪሊላንድ ማዕከል (ኮ/ቀራኒዮ) ገብተዋል፡፡ በማዕከላቱ የምግብ፣ የንፅህና እና አልባሳት፣ የመኝታ እና ተያያዥ አገልግሎት፣ የህክምና፣ የመረጃ ስራ እና ፍላጎት ዳሰሳ በመስፈርቶች መለየት፣ የሳይኮሶሻል ድጋፍ ስልጠና፣ የመዝናኛ ስራ (ስፖርት፣ ቲቪ (እንደየማዕከሉ ሁኔታ) መፃሐፍት፣ የመጫወቻ ግብዓቶች፣ የተለያዩ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ማስተናገድ እና እንደ ሰላም ማስፈን ያሉ አገልግሎቶችና ድጋፎች እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ ከህብረተሰቡ እና ባለሀብቱ የሚጠበቀው የመጀመሪያው እንደ አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ባለቤትነት ሥራውን በቅርብ መከታተል እና ለሚተገበሩ ሥራዎች ፈር ቀዳጅ ተባባሪ መሆን ነው፡፡ ማንኛውም ድጋፍ እና አስተዋፅዖ የእውቀት፣ በገንዘብ፣ በአይነት፣ በጉልበት፣ የቅርብ ክትትል እና ማበረታታት እንዲሁም ልመና እና መንገድ ላይ የሚደረግ እርዳታ አለማበረታት ከህብረተሰቡ ይጠበቃል፡፡ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የባንክ አካውንትና ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቴዎድሮስ አደባባይ ቅርንጫፍ 1000272444726 ለዚሁ ዓላማ የተከፈተ የሂሳብ ቁጥር ነው፡፡ በተጨማሪም በኢትዮ ቴሌኮም 6400 ላይ A ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመርዳት ሥራ ላይ የዋለ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ቁጥር ነው፡፡

’እጅ ለእጅ ተያይዘን ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ዜጎችን ሕይወት እንቀይር!!”

የአዲስ አበባ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ

በጉባዔው ከ40 የአውሮፓና የአረብ አገራት የመጡ መሪዎችና ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ተሳትፈዋል

የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የባንክ አካውንትና ቁጥር ኢትዮጵያ

ንግድ ባንክ ቴዎድሮስ አደባባይ ቅርንጫፍ

1000272444726 ለዚሁ ዓላማ የተከፈተ የሂሳብ ቁጥር ነው፡፡

በተጨማሪም በኢትዮ ቴሌኮም 6400 ላይ A ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ዜጎችን

ለመርዳት ሥራ ላይ የዋለ የገንዘብ ማሰባሰቢያ

ቁጥር ነው፡፡

Page 5: 78 ንግድን ለማሳለጥ ተጨባጭ ርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ€¦ · ንግድን... በ2ኛው ገጽ ዞሯል 78ኛ

የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን 9

ኢኮኖሚ

አንተነህቸሬ

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትከሚቋቋሙባቸው ዋነኛ ዓላማዎች አንዱ የጥናትናምርምር ስራዎችን መስራትና የማኅበረሰብአገልግሎት ተግባራትን ማከናወን (Researchand Community Service) ነው፡ ፡ ይህየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባርም በተቋማቱበየጊዜው የሚከናወኑ የጥናትና ምርምር ስራዎችበተግባር ተመንዝረው ለኅብረተሰቡ ተጨባጭለውጥ ማምጣት የሚችል ፋይዳ እንዲኖራቸውያደርጋል፡ ፡

በኢትዮጵያ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣውየከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም የጥናትና ምርምርስራዎችን እያከናወኑና የማህበረሰብ አገልግሎትንእየሰጡ ይገኛሉ፡ ፡ ተቋማቱ ከሚያከናውኗቸውየጥናትና ምርምር እንዲሁም የማኅበረሰብአገልግሎት ተግባራት መካከል ከኢኖቬሽንናቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በትብብርየሚያከናውኗቸው ስራዎች ይጠቀሳሉ፡ ፡ ሚኒስቴሩበጀት መድቦ ከተቋማቱ ጋር በትብብርከሚሰራቸው የጥናትና ምርምር ስራዎች መካከልጥቂቶቹ ወደ ተግባር ተሸጋግረው አገልግሎትእየሰጡ ይገኛሉ፡ ፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በሰሜን ሸዋዞን፣ ኤፍራታና ግድም ወረዳ ይምሎ ቀበሌአስተዳደር ያከናወነው የተቀናጀ የዓሳና የዶሮእርባታ፤ እንዲሁም የማዳበሪያ ዝግጅትናየአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት የዚህማሳያ ነው፡ ፡

ይህ ፕሮጀክት በአነስተኛ መሬት ላይ የዓሳናየዶሮ እርባታ፤ እንዲሁም የማዳበሪያ ዝግጅትናየአትክልትና ፍራፍሬ ልማት የሚከናወንበት፤በቴክኖሎጂ የታገዘ የተቀናጀ የግብርና ስራ ነው፡ ፡የፕሮጀከቱ መሪ ተመራማሪ ዶክተር ገዛኸኝ ደግፌእንደሚሉት፤ ፕሮጀክቱ የዓሳና የዶሮ እርባታንጨምሮ የማዳበሪያ ዝግጅት የሚከናወንበትናበትንሽ መሬት ትልቅ ውጤት የሚያስገኝ ስራበመሆኑ ማኅበረሰባዊ ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው፡ ፡ፕሮጀክቱ በዘልማድ ሲሰራ የቆየው ስራበቴክኖሎጂ በመታገዝ ተመጋጋቢ የሆኑ የግብርና

ስራዎችን በአንድ ላይ አስተሳስሮ በአጭር ጊዜውጤት የሚገኝበት ጥምር ተግባር ነው፡ ፡

በዓሳና በዶሮ እርባታ ሂደት ከሚያጋጥሙችግሮች መካከል አንዱ የዓሳና የዶሮ መኖ ዋጋውውድ መሆን ነው፡ ፡ በዚህ የተቀናጀ የዓሳና የዶሮእርባታ መርሃ ግብር አንዱ ከሌላው ተጠቃሚበመሆኑ ችግሩን ለማቃለል ያግዛል፡ ፡ በዚህፕሮጀክት ከሚከናወኑ ተግባራት አንዱ የማዳበሪያምርት ነው፡ ፡ ዶክተር ገዛኸኝ ስለ ማዳበሪያውሲገልፁም፤ ‹‹ከየአካባቢው የተሰበሰበ ቆሻሻለትሎች ተሰጥቶ ትሎቹ ቆሻሻውን በመብላትወደ ማዳበሪያነት ይቀይሩታል፡ ፡ ይህቨርሚኮምፖስት በመባል የሚታወቀው ማዳበሪያበዓለም ላይ በአልሚነታቸው ከታወቁ የተፈጥሮማዳበሪያዎች መካከል አንዱ ነው፡ ፡ የማዳበሪያውኬሚካዊ ይዘት በቤተ-ሙከራ ሲለካ ከሌሎቹማዳበሪያዎች ሁሉ የተሻለ ነው›› ይላሉ፡ ፡ ከዚህበተጨማሪም፤ ውሃ የመያዝ አቅሙም በጣምከፍተኛ ነው፡ ፡ ማዳበሪያው አንድ ጊዜ መሬትላይ ከተደፋ በኋላ ለረጅም ጊዜ ማዕድናቱንእንደያዘ ይቆያል፡ ፡ ቨርሚኮምፖስትን በመጠቀምየሚተከሉ አትክልት ከሌሎቹ ፈጥነው ያድጋሉ፡ ፡የይምሎ ቀበሌ አርሶ አደሮችም ማዳበሪያውንመጠቀም እየጀመሩ እንደሆነም መሪ ተመራማሪውይናገራሉ፡ ፡

መሐመድ ሸህ አሊ የ‹‹ኅብረት በአንድ የይምሎወጣቶች የዶሮና ዓሳ እርባታ ማኅበር›› አባልናየኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በትብብር ባከናወኑት ፕሮጀክትተጠቃሚ የሆነ ወጣት ነው፡ ፡ ማኅበሩ አምስትአባላት ያሉት ሲሆን፤ ሁለቱ ከስደት (ሳዑዲአረቢያ) የተመለሱ ናቸው፡ ፡

መሐመድ ለሦስት ዓመታት ያህል በስደትእንደቆየና አስተማማኝ የሆነ የኑሮ መሰረትእንዳልነበረው ያስታውሳል፡ ፡ በመስከረም ወር2010 ዓ.ም እርሱና አራት ጓደኞቹ በፕሮጀክቱታቅፈው ስራውን ከጀመሩ ወዲህ ግን ‹‹እንዲህመሆኑን ብናውቅ ለስደት አንዳረግም ነበር››ያስባላቸውን ለውጥ ማየታቸውን ይናገራል፡ ፡

‹‹በትንሽ መሬት ላይ ዶሮና አሳ እናረባለን፤አትክልትና ፍራፍሬ እናለማለን፤ ማዳበሪያምእናመርታለን፡ ፡ የእንቁላል ዶሮዎችን አርብተንበሁለት ዙር ለገበያ ካቀረብነው እንቁላል ካገኘነውገቢ በማኅበራችን የባንክ አካውንት ከ41ሺ ብርበላይ ቆጥበናል፡ ፡ የገበያ ችግር የለብንም። ብድርምከማኅበሩ መውሰድ እንችላለን›› ይላል፡ ፡

ከዚህ በተጨማሪም፤ ሁለት ጊዜያት የአርሶአደር መድረኮችን በማዘጋጀት ቀደም ሲል ዶሮም

ሆነ ዓሳ ለማርባትና ለመጠቀም ብዙም ፍላጎትላልነበረው የአካባቢው ሕዝብ ግንዛቤ በመፍጠርለውጥ እንዳመጡም ያስረዳል፡ ፡ ለምሳሌ ያህልምቀደም ሲል ሁለት ወይም ሦስት ዶሮዎችን ብቻገዝተው የማርባት ልምድ ከነበራቸው አርሶ አደሮችመካከል ዛሬ አንዳንዶቹ እስከ 300 ዶሮዎችገዝተው እያረቡ እንደሆነ በመጥቀስ፤

የይምሎ ቀበሌ የእንስሳት እርባታ ባለሙያውመስፍን ጸጋዬ ወጣቶቹ ስላገኙት ውጤትምስክርነቱን ይሰጣል፡ ፡ ፕሮጀክቱ የተቀናጀናሁሉን አቀፍ የግብርና ስራ የሚከናወንበት በመሆኑወጣቶቹን ተጠቃሚ ማድረግ እንደቻለ የሚናገረውመስፍን፣ ‹‹የማኅበሩ አባላት እያከናወኑት ያለውተግባር ለአካባቢው አርሶ አደሮች መነቃቃትንበመፍጠሩ አሁን አሁን ብዙ ዶሮዎችን እያረቡያሉ አርሶ አደሮች ይገኛሉ፡ ፡ ከዚህ በተጨማሪምአርሶ አደሮቹ ለስራው የሚያስፈልግ ቦታእንድንመርጥላቸውና ሙያዊ የምክር አገልግሎትእንድንሰጣቸው እየጠየቁን ነው›› በማለትፕሮጀክቱ ከማኅበሩ አባላት አልፎ በአካባቢውኅብረተሰብ ዘንድ በጎ ውጤት እያስገኘ ስለመሆኑያብራራል፡ ፡

የማኅበሩ አባላት አሁን ባገኙት ውጤትተወስነው የመቀመጥ ፍላጎት የላቸውም፡ ፡መሐመድ እንደሚለው፤ በቀጣይ ጊዜያትስራቸውን በማስፋት ከዚህ የበለጠ ውጤትለማስመዝገብ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው፡ ፡‹‹ምስጋና ድጋፍ ላደረጉልን አካላት ይሁንናስራችን ከዚህ ለተሻለ ትጋትና ስኬት አነሳስቶናል፡ ፡እኛ በሕይወታችን ላይ ያየነው ለውጥ ለሌላውምእንዲዳረስ የአካባቢው አርሶ አደሮችቨርሚኮምፖስት ተጠቅመው ምርታቸውንእንዲያሻሽሉ ለማሳየት እቅድ አለን›› በማለትማኅበራቸው ከአባላቱ በተጨማሪ የአካባቢውኅብረተሰብም ተጠቃሚ እንዲሆን የሰነቀውንዓላማ ያስረዳል፡ ፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከከፍተኛትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበርከሚያከናውናቸው የጥናትና ምርምር ስራዎችመካከል ወደ ተግባር ተቀይረው ማኅበረሰባዊአገልግሎት እየሰጡ ያሉት ፕሮጀክቶች ቁጥራቸውጥቂት መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃዎች ያሳያሉ፡ ፡

ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፤ሚኒስቴሩ ባለፉት አራት ዓመታት ከ300 ሚሊዮንብር በላይ በጀት በመመደብ ከ60 በላይ ለሚሆኑ

የዩኒቨርሲቲዎችን ምርምሮች ለፍሬ የማብቃት ጅምርየዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ስራዎች ድጋፍማድረጉን ጠቅሰው ተጠናቅቀው ወደተግባርየገቡት ግን ጥቂት እንደሆኑ ይናገራሉ፡ ፡

እንደርሳቸው ገለፃ፣ በሚኒስቴሩ ድጋፍከተከናወኑት ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው የይምሎቀበሌ የተቀናጀ የዓሳና የዶሮ እርባታ፤ እንዲሁምየማዳበሪያ ዝግጅትና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትፕሮጀክት በትንሽ ሀብትና በአጭር ጊዜ ውጤትማምጣት የሚችል ስራ በመሆኑ የኅብረተሰቡንተጠቃሚነት የሚያሳድግ ተግባር ነው፡ ፡ ፕሮጀክቱአርሶ አደሮች በጓራቸው ከዶሮ፣ ከአትክልትናፍራፍሬ ልማት በተጨማሪ ዓሳ በማርባት ተጠቃሚእንዲሆኑ ስለሚያደርግ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥየሚደረገውን ጥረት ያግዛል፡ ፡

ፕሮጀክቱን ወደሌሎች አካባቢዎች ለማስፋትየሚያስችል የአሰራር መመሪያ ስለተዘጋጀ በቀጣይጊዜያት ስራው በሌሎች ክልሎች እንደሚተገበርምጠቁመው፤ የአማራ ክልልም በይምሎ ቀበሌአስተዳደር የተገኘውን መልካም ተሞክሮ በመቀመርየተቀናጀ የዓሳና የዶሮ እርባታ፤ እንዲሁምየማዳበሪያ ዝግጅትና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትፕሮጀክቱን በሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ማስፋትእንዳለበትም ያስገነዝባሉ፡ ፡

በአጠቃላይ በሚኒስቴሩና በዩኒቨርሲቲዎችትብብር የሚከናወኑት የምርምር ሥራዎች የከፍተኛትምህርት ተቋማት ከተቋቋሙባቸው ዓላማዎችመካከል አንዱን የሚያሳኩ በመሆናቸውየኅብረተሰቡን ኑሮ በዘላቂነት እንዲለውጡ ታሳቢተደርገው ሊከናወኑ እንደሚገባም ዶክተር ኢንጂነርጌታሁን ያሳስባሉ፡ ፡

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የምርምርናቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝደንት ዶክተርአልማዝ አፈራ መሰል ፕሮጀክቶች ለወጣቶችየሥራ እድል እንደሚፈጥሩና ፕሮጀክቱምተጨማሪ ተግባራትን ለማከናወን ልምድ የተገኘበትእንደሆነ ይናገራሉ፡ ፡ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲወደ ተግባር የሚቀየሩ ብዙ የምርምር ስራዎችእንዳሉትና ይህን የተቀናጀ የዓሳና የዶሮ እርባታ፤እንዲሁም የማዳበሪያ ዝግጅትና የአትክልትናፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት ወደሌሎች አካባቢዎችለማስፋት በትኩረት መስራት እንደሚገባምያሳስባሉ፡ ፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያከናውኗቸው ጥናቶችና ምርምሮች ወደ ተግባር ተቀይረውበኅብረተሰቡ ኑሮ ላይ ተጨባጭና አወንታዊለውጥ እንዲያመጡ ከተፈለገ በጀት መመደብብቻ ሳይሆን ምርምሮቹን ለሚያከናወኑ አካላትጥብቅ ክትትልና ድጋፍ ሊያደርጉላቸው ይገባል፡ ፡

አዲሶቹን ደረጃዎች (IFRS) ለመተግበር ሪፖርት አቅራቢአካላት ሊያደርጉት የሚገባ ዝግጅት

መንግስት የሀገሪቱን ኢንቨስትመንት፣ የኢኮኖሚ

ዕድገት የሚደግፍና የሕዝብ ጥቅምን የሚያስጠብቅ

በአግባቡ የሚመራ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ሙያ

በሀገሪቱ ውስጥ እንዲፈጠር ጠንካራ ፍላጎት አለው፡ ፡

ከፍተኛ ጥራት ያለውን የዓለም አቀፍ ፋይናንስ

ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎችን ተቀብሎ

በስራ ላይ ማዋል የሀገራችንን ኢኮኖሚ ዕድገት

እምቅ አቅም ለመጠቀምና አጠናክሮ ለማስቀጠል

ወሳኝ ነው፡ ፡ የነዚህን ደረጃዎች መተግበር ዓለም

አቀፍ ኢንቨስተሮች በሀገራችን የፋይናንስ ሪፖርት

አዘገጃጀትና አቀራረብ የጥራት ደረጃ ላይ

የሚኖራቸውን አመኔታ ይጨምራል።

ኢንቨስትመንትን በማበረታታት የኢኮኖሚ እድገቱን

የሚያስቀጥል ከመሆኑ ባሻገር የኢኮኖሚ መረጋጋትን፣

የሀብት አስተዳደርን፣ ግልፅነትንና ተጠያቂነትን

በተቋም እና በመንግስት ደረጃ እንዲጠናከር

በማድረግ በሀገሪቱ የዕድገት አቅም ላይ ጥልቅ የሆነ

ውጤት ያሳድራል፡ ፡

ስለሆነም ቦርዱ የሕዝብ ጥቅምን የሚያስከብር

ሞያውን ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መልኩ

ለመቆጣጠር የሚያስችሉትን የዓለም አቀፍ

ተሞክሮዎች፣ የአሰራር ልምዶችና ቴክኒኮችን

የሚጠቀም ብቃት፣ጥንካሬና ዘላቂነት ያለው

ተቆጣጣሪ አካል እንዲሆን ይጠበቃል፡ ፡ ቦርዱ

ከሚመለከታቸው ሌሎች ተቆጣጣሪ አካላት ጋር

በጋራ በመስራት የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት

ደረጃዎችን በኢትዮጵያ ውስጥ ለመተግበር

የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ መሰረት የሚሆኑ ከህጎች

እና የአሰራር ሥርዓት ለውጦች ጋር የተያያዙ

የዝግጅት ሥራዎችን በሚያከናውኑበት የሽግግር

ጊዜ ውስጥ ደረጃዎቹን በሥራ ላይ የማዋል

የመጨረሻው ግዴታ ባለባቸው ሪፖርት አቅራቢ

አካላት በኩልም አብሮ የሚሄድ ተመጣጣኝ የዝግጅት

ሥራ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡ ፡በዚህ ረገድ በሚመለከታቸው የሪፖርት አቅራቢ

አካላት በኩል ተገቢው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገመሆኑን ለማረጋገጥ ቦርዱ በየዓመቱ የቅኝት

ጥናቶችን በድርጅቶች ላይ ያደርጋል። ከቅኝት ጥናቱየሚገኘውን መረጃ የትግበራ ሥራው በታቀደውመሠረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማስፈጸምአስፈላጊ ነው የሚለውን እርምጃ ለመውሰድለሚነድፈው እቅድና የአፈጻጸም ስትራቴጂበግብዓትነት ይጠቀምበታል፡ ፡

የአዲሶቹን ደረጃዎች (IFRS) ትግበራ በተመለከተበኦዲት ድርጅቶች የሚቀርብ የሂሳብመግለጫዎቻቸውን በዓለም አቀፍ ደረጃዎች መሰረትማዘጋጀት የሚጠበቅባቸው የሪፖርት አቅራቢድርጅቶች ዓለም አቀፍ ደረጃዎች በተጨማሪየፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች ትግበራ ሌላኛው አብይባለድርሻ አካል የሂሳብ መግለጫዎቹን ኦዲትየሚያደርጉ የኦዲት ድርጅቶች ናቸው፡ ፡ በመሆኑምየኦዲት ድርጅቶች ደንበኞቻቸው የሆኑ ሪፖርትአቅራቢ አካላት የዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በመተግበርእያደረጉት ካለው ዝግጅት አንፃር በራሳቸው በኩልስላለው ዝግጅት የሚገልጽ ሪፖርት በማዘጋጀትናበሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርታቸው ውስጥ በማካተትከ2008/09 ጀምሮ ለቦርዱ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡ ፡ቦርዱ የኦዲት ድርጅቶቹ የሚልኩትን የሥራ

እንቅስቃሴ ሪፖርት በመተንተን የኦዲት ድርጅቶች

ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በመተግበር ምን ያህልዝግጅት እንዳደረጉ ይመረምራል፡ ፡ ከዚህም በመነሳትቦርዱ በቂ ዝግጅት ያላደረጉ የኦዲት ድርጅቶችንበዝግጅታቸው ላይ ተጨማሪ ጥረት በማከልበጥልቀት እንዲያዘጋጁት ትእዛዝ ይሰጣል፡ ፡ ቦርዱበቀጣይ እነዚህን የኦዲት ድርጅቶች የኦዲትሪፖርቶቻቸውን ጥራት ለማሳደግ እና ለማስጠበቅየዘረጉት የጥራት ቁጥጥር ሥርዓት አጥጋቢ እናበአግባቡ እየተሰራበት መሆኑን ለማረጋገጥ ምርመራናቁጥጥር ማድረጉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡ ፡የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች

ፍኖተ ካርታ አስተግባሪ ግብረ ሃይል ስለማቋቋም

ፍኖተ ካርታውን ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ለመተግበርከመንግስት እና ከግሉ ዘርፍ የተውጣጣና የተቀናጀየትግበራ ግብረ ኃይል መኖር አስፈላጊ ነው፡ ፡በመሆኑም ቦርዱ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ለመተግበርያዘጋጀውን ፍኖተ ካርታ አስተባብሮ የሚያስተገብርከጉዳዩ ጋር አግባብ ካላቸው የመንግስት ድርጅቶች፣የሪፖርት አቅራቢዎች እና ኦዲት ድርጅቶችየተውጣጣ የፍኖተ ካርታ አስተግባሪ ግብረ ኃይልያቋቁማል፡ ፡ የትግበራ ግብረ ኃይሉ ትኩረት ማሻሻያሊደረግባቸው የሚገቡ የሂሳብ አያያዝና የሪፖርት

አዘገጃጀትና አቀራረብ መዋቅሮች ጋር ተያያዥነትያላቸውን ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን በመለየትማሻሻያዎች እንዲደረግባቸው የውሳኔ ሃሳብ ማቅረብይሆናል፡ ፡የግብረ ኃይሉ ዋና ተግባርም ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን

ከመተግበር ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጉዳዮችን መፍታትናደረጃዎቹን የመቀበሉ ሂደትም የተረጋጋ እንዲሆንድጋፍ ማድረግ ነው፡ ፡ ግብረ ኃይሉ እንደ አስፈላጊነቱበግብር ነክ፣ ከፋይናንስ ተቋማት አሰራር(Prudential Requirements) የኦዲት ግምገማ፣የትምህርት እና ስልጠና ጉዳዮች … ወዘተ ዙሪያየሚሠሩ ልዩ ልዩ የስራ ቡድኖችን ያቋቁማል፡ ፡

ግብረ ኃይሉ በዝግጅት ምዕራፍ ወቅትየሚያከናውናቸው ተግባራት ማሻሻያ ሊደረግባቸውየሚገቡ ህጎችና ደንቦችን መለየትና ማሻሻል ነው።የአንድ አገር የሂሳብ አያያዝ ሥርዓት ከበርካታ የአገሪቱህጎችና ደንቦች ጋር በእጅጉ የተገናኘ ነው። በመሆኑምማንኛውም በሂሳብ አያያዝ ሥርዓቱ ላይ የሚደረግለውጥ ተዛማጅ በሆኑ ህጎች ላይ ጭምር ለውጥማድረግን የሚያካትት ይሆናል፡ ፡ በሀገራችንደረጃዎቹን የመተግበሩን ሂደት የተሳካ እንዲሆንለማድረግ ማሻሻያ ሊደረግባቸው የሚገቡ ተዛማጅህጎችና ደንቦችን የመለየትና የማሻሻል ቁልፍ ተግባርበትግበራ ግብረ ኃይሉ ይሰራል።የአገራችን የግብር ህግ እነዚህን ዓለም አቀፍ

የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎችን በመቀበላችን ምክንያትከሚከሰቱ ለውጦች ጋር የተጣጣመ እንዲሆንማሻሻያዎች ሊደረግበት ይገባል፡ ፡ በግብር ህጉድንጋጌዎች ላይ የሚደረጉት ማሻሻያዎች ከፋይናንስሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች ጋር በጥብቅየተገናኙ መሆን ይኖርባቸዋል፡ ፡ ከዚህ በተጨማሪበዓለም አቀፍ ደረጃዎች በግብር ህጉ ድንጋጌዎችመካከል የሚኖር ልዩነት ሪፖርት አቅራቢ አካላትበሚያዘጋጁት የግብር ማሳወቂያ መግለጫ ላይየሚደረጉት ማስተካከያዎች እንዲበዙ በማድረግአላስፈላጊ የስራ ጫና ይፈጥራል የሚል ስጋትበሪፖርት አቅራቢዎችና በባለሙያዎች ዘንድ ሲነሳይደመጣል፡ ፡

ስለሆነም የግብር ህጉን ድንጋጌዎች ለማሻሻልየሚቻልባቸውን መንገዶች የሚያፈላልግና አዳዲሶቹንደረጃዎች ከመቀበል ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉችግሮችን መፍታት በሪፖርት አቅራቢዎች ላይየሚፈጠረውን አላስፈላጊ የግብር ጫና በመቀነስዓለም አቀፍ ደረጃዎች ተግባራዊ በመደረጋቸውምክንያት በሪፖርት አቅራቢዎች መካከል ያለውግብር የመክፈል ግዴታ ሚዛናዊነቱን እንዳይስትየሚያደርግ የትግበራ ኃይል ቡድን ይቋቋማል፡ ፡ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን መተግበርን ተከትሎ

ከሚከሰቱ ለውጦች ጋር እንዲጣጣሙ ለማድረግእንደየዘርፉ ባህርይ በፋይናንስ ተቋማት ላይ ተፈጻሚእየሆኑ ያሉ አስገዳጅ የሪፖርት አቀራረብ ቁጥጥርሥርዓቶችን መገምገምና መከለስ አስፈላጊ ነው፡ ፡በዚህም መሰረት ቦርዱ በባንክ፣ በኢንሹራንስ፣በፋይናንስ ኢንቨስትመንት እና በማይክሮ ፋይናንስተቋማት አካባቢ ያለውን ሁኔታ የሚያጠናናየሚያጋጥሟቸውን ወቅታዊ ጉዳዮችና ዓለም አቀፍደረጃዎችን ለመቀበል በሚያደርጉት ዝግጅት ሂደትላይ ምክር እና ድጋፍ የሚሰጥ ተዛማጅ ከሆኑተቋማት የተውጣጣ የግብረ ኃይል ቡድኖችያቋቁማል፡ ፡

ተቆጣጣሪ አካላት የሚያወጧቸውን ግዴታዎችከዓለም አቀፍ ደረጃዎች አኳያ ከላቀ ተሞክሮ ጋርበተጣጣመ መልኩ አንድ ተቆጣጣሪ አካላት የሪፖርትአቅራቢ ድርጅቶችን የተወሰኑ የፋይናንስ መረጃዎችንለትክክለኛው ዓላማ ሲባል እንዲያሳውቋቸውየሚጠይቁበት ሁኔታ አለ፡ ፡ ይሁን እንጂ አንዳንዴየዚህ አይነቱ የቁጥጥር ግዴታዎች አግባብነት ካላቸውየሂሳብ አያያዝና ደረጃዎች ከሚደነግጉት አሰራርየሚለይ ሆኖ ይገኛል፡ ፡ የሂሳብ አያያዝና የኦዲትደረጃዎችን መተርጎምን በተመለከተ ግብረ ኃይሉከእነዚህ የቁጥጥር/ ክትትል አካላት ጋር በቅርበትበመስራት በተቆጣጣሪ አካላት ፍላጎቶችና በፋይናንስሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች መካከልተቃርኖ እንደይኖር በማድረግ በአገሪቱ እምነትየሚጣልበት የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብሥርዓት እንዲኖር ያደርጋል፡ ፡

በመሆኑምየኦዲትድርጅቶችደንበኞቻቸውየሆኑ

ሪፖርት አቅራቢ አካላት የዓለምአቀፍደረጃዎችን

በመተግበር እያደረጉት ካለውዝግጅት አንፃር

በራሳቸውበኩል ስላለውዝግጅት የሚገልጽ ሪፖርት

በማዘጋጀትናበሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርታቸውውስጥ

በማካተት ከ2008/09 ጀምሮለቦርዱ ማቅረብ

ይጠበቅባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያፕሬስ ድርጅት ከኢትዮጵያሂሣብ አያያዝእናኦዲት ቦርድጋርበመተባበር

በየሳምንቱ ረቡዕ የሚወጣ

ፕሮጀክቱ የዓሳና

የዶሮእርባታን

ጨምሮየማዳበሪያ

ዝግጅት

የሚከናወንበትና

በትንሽመሬት ትልቅ

ውጤት የሚያስገኝ

ስራ በመሆኑ

ማኅበረሰባዊ

ጠቀሜታውላቅ

ያለ ነው፡፡

Page 6: 78 ንግድን ለማሳለጥ ተጨባጭ ርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ€¦ · ንግድን... በ2ኛው ገጽ ዞሯል 78ኛ

‹‹ችግር ያለበት ልሂቅ ሄዶየሚወሸቀው ብሄሩ ውስጥ ነው››

ፖለቲካ11የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን

ፎቶ-በገባቦገብሬ

አጎናፍር ገዛኸኝ

የፌዴሬሽንምክርቤት በህገመንግስቱበክልሎችመካከል የሚፈጠር የወሰን

አለመግባባት ለመፍታት፤ በህዝቦችየሚቀርቡየማንነትጥያቄዎችንመፍትሄ ለመስጠት፣የሰላምዕጦትን የመፍታት፤ የህገመንግስትአስተምህሮናሌሎችተዛማጅሃላፊነቶችተሰጥተውታል። ይሁን እንጂ፤ የተሰጡትንሃላፊነቶችበተገቢውደረጃየመወጣትችግርእንዳለበት ተደጋግሞይነሳል። በዚህምየተነሳበአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ችግሮችመፈጠራቸውንተንተርሶ በብዙዎችዘንድይወቀሳል። በእነዚህእናበሌሎችተያያዥጉዳዮች ዙሪያ በፌዴሬሽን ምክር ቤትየዴሞክራሲያዊአንድነት፣ የህገመንግስትአስተምህሮናየሰብዓዊመብትግንባታቋሚኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ፍረወይኒገብረእግዚአብሔርን ቃለ መጠይቅአድርገንላቸዋል። እንደሚከተለውምአቅርበነዋል።አዲስ ዘመን፡ - በአገሪቱ ያለውን የሰላም

ችግር ለመፍታት ቋሚ ኮሚቴያችሁ ምን እየሰራነው?ወይዘሮ ፍረወይኒ፡ - ቋሚ ኮሚቴያችን

ከስያሜው ጀምሮ ዴሞክራሲዊ አንድነት፤ የሰላምግንባታ እና የህገ መንግስት አስተምህሮ እንደሚሰራነው የሚያሳየው፤ እነዚህ ስራዎች ተያያዥነትያላቸው ናቸው። ዴሞክራሲያዊ አንድነትንለመፍጠር፤ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና ህገመንግስቱን ለማስተዋወቅ በቋሚ ኮሚቴያችንትልቅ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው።ስራችንን እያከናወንን ያለነውም የህዳር 29ን

በዓል በዋናነት ግንዛቤ ለመፍጠር በመጠቀም ነው።በየዓመቱ በዓሉን በመጠቀም ግንዛቤ የሚፈጥሩናየሚያሳድጉ ስራዎችን እንሰራለን። የተለያዩ ጽሁፎችበምሁራንና በፖለቲካ መሪዎች እየተዘጋጁለህብረተሰቡና ለምክር ቤት ይደርሳሉ። መቶሚሊዮን ህዝብ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ማስተማርስለማይቻል ፤ በፎረሞችና በተለያየ አደረጃጀቶችምበኩል ህገ መንግስቱን ለህብረተሰቡ የማስተዋወቅስራ እናከናውናለን። በእነዚህ አደረጃጃቶችምየአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ወደ ህዝቡ ተደራሽየማድረግ ስራም እየሰራን ነው። ከዚህምበተጨማሪ፤ የህገ መንግስት አስተምህሮ በዴሞክራሲተቋማት በኩል ተደራሽ እንዲሆን እናደርጋለን።እንዲያም ሆኖ ግን፤ ህገ መንግስቱን በህዝብየማስረጽ ክፍተት እንዳለ እያየን ነው።

አዲስ ዘመን፡ - ህገ መንግስቱን በህዝብውስጥ ማስረጽ ካልቻላችሁ ታዲያ ምንናእንዴት ለመስራት አቅዳችኋል?

ወይዘሮ ፍረወይኒ፡ - ይህን ችግር ለመፍታትየዴሞክራሲ ተቋማት፣ የትምህርት ዘርፍ እና ሌሎችባለድርሻ ተቋማት የተሳተፉበት የህገ መንግስትአስተምህሮ ስልት ተቀይሷል። ስልቱንም ተግባራዊለማድረግ አስተምህሮቱን የሚመራና የሚያከናውንተቋም እንዲቋቋም ለማድረግ አዋጅ ተዘጋጅቶበሚኒስትሮች ምክር ቤት በኩል ለእንደራሴዎችምክር ቤት እንዲጸድቅ ገብቷል። በመሆኑም ይህችግር በቅርብ ጊዜ ይፈታል የሚል እምነት አለኝ።ይህ ሲሆን ለዴሞክራሲና ለሰላም ግንባታ ትልቅሚና ይኖረዋል።

አዲስ ዘመን፡ - የህገ መንግስት አስተምህሮተቋም ምን ምን ጉዳዮችን ይሰራል?

ወይዘሮ ፍረወይኒ፡ - ተቋሙ በማዕከልደረጃ ትልቅ ሆኖ እንዲቋቋም ነው የተፈለገው፤በውስጡ የተለያዩ የልህቀት ማዕክል ይኖሩታል።የትምህርት ሚኒስቴር አንዱና ዋናው ተዋናይ ነው።ምክንያቱም ሩብ ሚሊዮን የሚሆኑት ዜጎች ያሉትበትምህር ቤት ነው። በስነ ምግባርና ስነዜጋ ትምህርትለእነዚህ ዜጎች ስለህገ መንግስቱ ማስተማርና ማስረጽይገባል። የስነ ዜጋ ትምህርትም ይህን ታሳቢ ባደረገመልኩ እየተሻሻለ ነው። የዴሞክራሲ ተቋማትየሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና እንባ ጠባቂ ተቋምናቸው። ምክር ቤቶች እና የሚዲያ ተቋማት ህገመንግስቱን በማስረጽ ረገድ ሰፊ ስራ ያከናውናሉ።የሲቪክና የሙያ ማህበራት መብታቸውናግዴታቸውን እንዲከበር ይሰራል። የጸጥታናየፍትህ ተቋማትም ህጉን ለማክበርና ለማስከበርትልቅ ስራ ያከናውናሉ። እነዚህንና ሌሎች ተቋማትንአደራጅቶ በመስራት የልህቀት ማዕከል በመሆንሰፊ ተግባር ይሰራል። በአጠቃላይ ህገ መንግስቱንየማወቅና የማሳወቅ ስራ ያከናውናል። ህገመንግስቱን ከማስረጽ ባለፈም በአገሪቱ ሰላምናጸጥታ እንዲሰፍንም ይሰራል።አዲስ ዘመን፡ - አሁን ከሚታየው ችግር

አንፃር በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነትአለ?ወይዘሮ ፍረወይኒ፡ - ዴሞክራሲያዊ አንድነት

በብዙ መንገድ ሊገለጽ ይችላል። ለአንድነታችንችግር የሆነ የብሄር ብሄረሰቦች ጭቆናና ማንነትያለማግኘት ችግር ነበር። ይህ መፍትሄ አግኝቷል።ዛሬ ሁሉም ብሄሮችና ብሄረሰቦች ማንነታቸውናእኩልነታቸው እውቅና አግኝቷል። እስካሁን 76

ብሄር ብሔረሰቦች በፌዴሬሽን ምክር ቤትተመዝግበዋል። እነዚህ ሁሉ ብሄራዊ ማንነታቸውታውቆላቸዋል ማለት ነው። ይህ ማለት ግን፤ሌሎች ጥያቄዎች የሉም ማለት አይደለም። ወደፌዴሬሽን ምክር ቤት ያልመጡ ተሟጥጠውያልተፈቱ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ።ከዚህም በላይ፤ ብሄር ብሄረሰቦች ማንነት

ማግኘት ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን በራሳቸውእንዲያስተዳድሩ፤ ቋንቋቸውንና ባህላቸውንእንዲያሳድጉ ተደርጓል። ማንነታቸውንዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲገልጹናእንዲያስተዋውቁ ዕድል ተፈጥሯል። አንዱ ብሄርየራሱን ከማሳወቅ ጎን ለጎን የሌሎችንምእንዲያውቅና አክብሮ እንዲኖር የሚያስችሉስራዎችን ሰርተናል።ሌላው፤ የዴሞክራሲያዊ አንድነት መገለጫው

ህዝቦች በየደረጃው ውክልና ማግኘታቸው ነው።ምክር ቤቶች የህዝቦች ፍላጎት የሚገለጽባቸውናቸው። በፌዴሬሽን ምክር ቤት እንኳን ብናይሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እኩል ውክልናከማግኘታቸው በተጨማሪ በአንድ ሚሊዮን ህዝብተጨማሪ አንድ ተወካይ አላቸው። በዚህም ምክርቤቱ የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ፍላጎትየሚንጸባረቅበትና ውሳኔ የሚያልፍበት ነው ማለትይቻላል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትምበተመሳሳይ በህጉና በሥርዓቱ መሰረት ይወከላሉ።የክልል ምክር ቤቶችም በተመሳሳይ ሁኔታተደራጅተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ክልሎች ርስበርሳቸው የሚደጋገፉበትና የሚተዋወቁበት ሥርዓትተቀይሷል። በተመሳሳይ ከፌዴሬሽን ምክር ቤትጋር የጋራ የምክክር መድረክ አላቸው። በቅርብጊዜ በመቀሌ አንድ የምክክር መድረክ እናካሂዳለን።ከዚህ በፊት ብዙ ምክክሮች አካሂደናል። በመሆኑምክልሎች ልምዳቸውን የሚለዋወጡበትናችግሮቻቸውንም የሚወያዩበት ሥርዓት አለ።

አዲስ ዘመን፡ - እነዚህ የዘረዘሯቸውተቋማትና ስራዎች በኢትዮጵያ ለምንዴሞክራሲያዊ አንድነትን አላመጡም?

ወይዘሮ ፍረወይኒ፡ - ስራዎቹ ጉድለትየለባቸውም ማለት አይደለም። ጉድለቶችን ለማረምየፌዴራልና የክልል መንግስታት ህጋዊ አሰራርእንዲኖራቸው፤ ግንኙነታቸውም የፖሊሲና የህግማዕቀፍ እንዲኖረው ለማድረግ አዋጅ ተዘጋጅቶወደሚኒስትሮች ምክር ቤት ተልኳል። የሚኒስትሮችምክር ቤት ከተመለከተው በኋላ ለእንደራሴዎችምክር ቤት ቀርቦ ይጸድቃል የሚል እምነት አለኝ።ይህ ዴሞክራሲያዊ አንድነታችንን ቀጣይነት ባለውአግባብ ሊያጎለብትልን የሚችል ነው።የህግ ማዕቀፉ አንዱ ክልል ከሌላው ጋር

ያለውን ችግር ቁጭ ብሎ ሊወያይ የሚያስችልሥርዓት ይዘረጋል። የክልሎች፣ የህግ አውጭዎች፣የህግ አስፈፃሚዎች፣ የህግ ተርጓሚዎች እና የዘርፍተቋማት መድረኮችን በመፍጠር ዴሞክራሲያዊአንድነታችንን ያጠነክራሉ። ችግሮች ሲፈጠሩበእንጭጩ ለመፍታትም ያስችላል። ጥሩተሞክሮዎቻችን እያጎለበትን፤ አንዱ አንዱን ረግጦማለፍ ሳይሆን ርስ በርስ ተደጋግፎ ለመሄድያስችላል። አዋሳኝ ክልሎች፣ ዞኖች፣ ወረዳዎችእና ቀበሌዎች የጋራ ፕሮጀክቶቻችውን በጋራይፈጽማሉ። ተመሳሳይ ተቋማት አብሮ ለመጠቀምየሚያስችል አካሄድ ይፈጥራል። የጋራችግሮቻቸውን በጋራ የሚፈቱበት ሥርዓትይዘረጋል።በአጠቃላይ አሁን ላይ የድርጅቶች ፖለቲካዊ

ግንኙነትና የመንግስታት ግንኙነት በሚፈለገውደረጃ እንዳልሆነ እያየን ነው። መልካም እሴቶችንለማጠናከር ይሰራል። በአንዳንድ አካባቢዎችበተወሰኑ ልሂቃንና ቡድኖች አነሳሽነት ጫናናየሰዎች ማፈናቀል ይታያል። ይህን አስተሳሰብበመግዛትም በተወሰኑ ዜጎች የመቃቃር ሁኔታይታያል። እነዚህን ዴሞክራሲያዊ አንድነታችንንየሚሸረሽሩ አስተሳሰቦችን ለማስታረቅ ፖለቲካከባቢውን ማስተካከል ያስፈልጋል። ይህ ሲስተካከልየህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ትናንት የነበረ ዛሬም ያለወደፊትም የሚቀጥል ስለሆነ አብሮነቱይስተካከላል።አዲስ ዘመን፡ - አሁን በአገሪቱ ያለው

መቃቃር የተፈጠረው በፖለቲካ ልሂቃንናየተወሰኑ ዜጎች ብቻ ነው? የህዝቡ መጠላላትናመጠላለፍስ? መገፋፋቱና መገዳደሉስ?ወይዘሮ ፍረወይኒ፡ - ችግር ያለበት ልሂቅ ሄዶ

የሚወሸቀው ብሄሩ ውስጥ ነው። እንደዚህ አይነትአካሄዶች ናቸው በህዝብ ውስጥ መቃቃርየፈጠሩት፤ በማህበረሰቡ ዘንድ ችግር አለመኖሩንየምታየው በአንድ ብሄረሰብ አባላት ላይ ችግርሲፈጠር የአካባቢው ህብረተሰብ ‹‹በመጀመሪያበእኔ ልጅ ላይ ጉዳት አድርሰህ ነው ከዚያ በኋላእርሱን የምትጎዳው›› ይላል። ይሄ ማለት እሱንከምትጎዳው እኔን ጉዳኝ የሚል ነው። ይህ ጥሩእሴታችን በህዝቡ መካከል ጠንካራ ግንኙነትመኖሩን የሚያመለክት ነው። ይህን ሚዛን አስይዞመሄድ ይገባል። እንደዚህ አይነት ችግር በሁሉምአካባቢ የለም። ህዝብ አብሮ የኖረ፤ የተዋለደ እናብዙ ነገር አብሮ ያሳለፈ ነው።

ችግሩ ያለው በልሂቃን መካከል ነው።የልሂቃኑን ችግር ስንፈታ የተሳሳተ አመለካከትያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ካሉ ችግሩ ይፈታልየሚል እምነት አለኝ። በማህበረሰቡ ውስጥበአንዳንዶች ዘንድ አሁንም በጎ ያልሆነ አመለካከትግን አይኖርም ብለን አንወስድም። ልሂቃኑሲስተካከሉ ግን ማህበረሰቡም ወደ ቀልቡይመለሳል። ምክንያቱም ማህበረሰቡ የተዋለደ፣የተጋመደ፣ የተዛመደ ስለሆነ የማይለያይናየማይበጣጠስ ነው። ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብከምዕራብ እስከ ምስራቅ ጫፍ አብሮ የኖረና ሊለያይየማይችል ነው። ስለዚህ ችግር የሚፈጥሩ ልሂቃንንእያስተካክልን በሄድን ቁጥር ሁሉም ችግሮችእየተፈቱ ይሄዳሉ። ታዲያ፤ የተወሰኑ ጫፍ የወጣአመላካከት ያላቸው ሰዎች አይኖሩም ግንአይባልም። አብዛኛው ማህበረሰብ ግን በአብሮነትየሚያምን ነው። እየተጎዳና ችግር እየደረሰበትምጭምር የእኔ ወንድም የሚል ህዝብ ነው።እኛ መድረኮች ፈጥረን ስናወያይ ማህበረሰቡ

የሚያነሳው ይህንን ነው። በጌዲዮና በጉጂ መካከልያለውን ማህበረሰብና አባገዳዎች ስናወያይ መለያየትእንዳማይችሉና የጋራ የግጭት አፈታት ስልትጭምር እንዳላቸው ነው የሚያወሩት፤ ችግርየፈጠረው ማነው ስትል ሄዶ ሄዶ የሚያርፍውውስን ልሂቃን ላይ ነው። በሁሉም አካባቢዎችተመሳሳይ ችግር ነው የሚያነሱት፤ በተወሰኑ ሊህቃንየተሳሳቱ አይኖሩም ማለት ባይቻልም፤ ማህበረሰቡግን ያለው በአንድነት ነው። እናም ልሂቃኑሲስተካከሉ የተሳሳቱት ይታረማሉ የሚል እምነትአለኝ።አዲስ ዘመን፡ - ለመሆኑ የተሰጣችሁን ሰላም

የማስፈንና የህገ መንግስት አስተምህሮ ሃላፊነትበትክክል ተግባራዊ አድርጋችኋል?ወይዘሮ ፍረወይኒ፡ - በክልሎች፣ ዞኖች፣

ወረዳዎችና ቀበሌዎች ያለው ግንኙነትእንዲስተካከልና የተፈጠሩ ግጭቶች እንዲፈቱሰርተናል፤ እየሰራንም ነው። በአንዳንድ አካባቢዎችበተለያዩ ሁኔታዎች ምክንያት በሚፈለገው መጠንማካሄድ ባንችልም፤ በርካታ ስብሳባዎችንአካሂደናል። ባህላዊ የግጭት አፈታትሥርዓታቸውን ተጠቅመው ግጭቶቻቸ ውን

እንዲፈቱ ለማድረግ ተሰርቷል። ምክር ቤቱምየክልሎችን የባህላዊ የግጭት አፈታት ስልትለመቀመር እየሰራ ነው። ከዚህ በተጨማሪ፤ ግጭትከመፈጠሩ በፊት ለመከላከል የሚስችል ጥናትእያደረግን ነው። ተጋላጭነትም ለመተንተን እየተሰራሲሆን፤ በዚህም ላይ ውይይት አድርገን ለመፍታትከተለያዩ ተቋማት ጋር በመሆን እየሰራን ነው።እነዚህ ዴሞክራሲ አንድነታችንን የሚያጠናክሩአንኳር አንኳር ጉዳዮችን እየሰራን ነው።አዲስ ዘመን፡ - አንዱ ለግጭት መንስዔ

እየሆነ ያለው የፌዴሬሽን ምክር ቤትና ክልሎችከማንነት ጋር ያሉ ጥያቄዎችን በአግባቡያለመመለሳቸው ጉዳይ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘምን እየሰራችሁ ነው?

ወይዘሮ ፍረወይኒ፡ - ይህ ጉዳይ የራሱ ቋሚኮሚቴ አለው። ጥልቅ መረጃ ከዚያ ማግኘትይቻላል። ሌሎች የግጭት መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዮችቢኖሩም የማንነት ጉዳዮች የግጭት መንስዔዎችናቸው የሚለው ትክክል ነው። እነዚህንምለማስተናገድ ምክር ቤቱ በህገ መንግስቱና በአዋጅየተሰጠውን ሃላፊነት እየተወጣ ነው። በህጉ መሰረትየማንነት ጉዳዮች በመጀመሪያ በክልል ምክር ቤቶችበየደረጃው ምላሽ እየተሰጣቸው መምጣትአለባቸው። በክልል ምክር ቤቶች ምላሽ ካልረኩወይም በሁለት ዓመት ውስጥ ምላሽ ካላገኙ ወደፌዴሬሽን ምክር ቤት መምጣት ይችላሉ። በዚህሂደት አልፈው መልስ ያላገኙ የሉም።

አዲስ ዘመን፡ - የሰላም የታጣውናዴሞክራሲዊ አንድነት የጠፋው ፌዴሬሽንምክር ቤት የማንነትን ጥያቄ ባለመመለሱ ነውየሚሉ ሰዎች አሉ። የእርስዎ ምላሽ ምንድነው?

ወይዘሮ ፍረወይኒ፡ - እኛ እንደዚያ አይነትግምገማ የለንም። ይህ የሚመነጨው በአንድ በኩልከግንዛቤ ማነስ ነው። በክልል ምክር ቤት ሳይቀርብበቀጥታ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚቀርብጉዳይ/አቤቱታ አለ። ይህንን ግንዛቤ አስይዘን ወደክልል የምንመልስበት ሁኔታ አለ። አንዳንድ ምክርቤቶች ደግሞ በቶሎ ምላሽ ያልሰጡ አሉ። እነዚህአቤቱታዎች ጊዜውን ጠብቀው ወደ ፌዴሬሽንምክር ቤት አልመጡም። ከክልል ምክር ቤቶች ጋርበተደረገ አንድ የጥናት መድረክ ለረጅም ጊዜ ምላሽያላገኙ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጣቸው ከክልሎችጋር የጋራ መግባባት ተደርሷል። በአጭር ጊዜ ውስጥምላሽ ካልሰጡ ግን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገብቶምላሽ እንደሚሰጥ ተገልጿል። በአጠቃላይ ግንህጋዊ አሰራሩን ጠብቀው የመጡና የፌዴሬሽንምክር ቤት ያልመለሳቸው የማንነነት ጥያቄዎችየሉም።አዲስ ዘመን፡ - ከአስተዳደራዊ ወሰን ጋር

በተያያዘ አገሪቱን ሊበትን የሚችል ችግርእንዳለ ነው የሚታየው፤ ይህን የመፍታትሃላፊነታችሁን በምን ደረጃ እየተወጣችሁ ነው?ወይዘሮ ፍረወይኒ፡ - በሁለት ክልሎች መካከል

አለመግባባት ካለ በመጀመሪያ ሁለቱ ክልሎች ቁጭብለው የሚፈቱበት ሥርዓት አለ። ሁለቱም ክልሎችመፍታት ካልቻሉ፤ ሁለቱም ወይም ከሁለቱ አንዱመፍታት አለመቻላቸውን ጠቅሶ ጥያቄ ሲያቀርቡ/ብነው ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጉዳዩን ለማየትየሚገባው፤ አሁን ባለው ሁኔታ ክልሎች ከአቅማችንበላይ ነው ብለው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያስገቡትጥያቄ የለም። ከዚህም ጋር ተያይዞ በወረዳና በቀበሌደረጃ ያለ፤ በክልል ምክር ቤቶች መታየት የሚገባውወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ይመጣል። ይህምየግንዛቤ ችግር ነው። ሲመጡም ማብራሪያ እየሰጠንመልሰናል። በዚሀ ረገድ ቀደም ሲል የመጣው

የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል ጉዳይ ነው። እሱምበአስፈፃሚው እንዲታይና እንዲፈታ ተሰማምተዋል። ምክር ቤቱም የተደረገውን የመግባባቢያስምምነት አይቶ እውቅና ሰጥቷል። ከዚህ ውጭግን በህጉ መሰረት የመጣ የአስተዳደር ወሰንጥያቄ/አቤቱታ የለም። ከግንዛቤ አንፃር የፌዴሬሽንምክር ቤትን ስልጣንና ሀላፊነት ካለማወቅ ነው።ይህ የእኛ ግንዛቤ ያለማስጨበጥ ችግር ነው።በቀጣይ ይህንን ችግር በማስተማር እንፈታዋለን።አዲስ ዘመን፡ - አንዱ ስራችሁ ግጭቶች

ከመፈጠራቸው በፊት መከላከል ነውና አቤቱታሲደርሳችሁ በህጉ መሰረት ሂደቱን ጠብቆአልመጣም ብላችሁ ዝም ነው የምትሉት?ወይዘሮ ፍረወይኒ፡ - የሰላም ኮንፍረንስ

የምናካሂደው በማህበረሰቡ ውስጥ ያለው ችግርእንዲፈታ ነው። ህብረተሰቡ ውስጥ ዛሬ ያልፈነዱ፤ነገር ግን ነገ ሊፈነዱ የሚችሉ ችግሮች ወጥተውእንዲፈቱ ነው ኮንፍረንስ የምናካሂደው፤ ህዝብከተቀራረበ ራሱ ለችግሩ መፍትሄ ያስቀምጣል።የምናወያየው እነዚህን እምቅ ችግሮች ለመፍታትነው። በዩኒቨርሲቲዎችም ትምህርት እንሰጣለን።ይህን የምናደርገው የዜጎች መብት መጠበቅ አለበትከሚል መነሻ ነው። በሃላፊነታችን ሳንገደብ ከሌሎችተቋማት ጋር ሆነን እየሰራን ነው።

አዲስ ዘመን፡ - ክልሎች ሚናቸውንእየተወጡ አይደለም። ሚናቸውን እንዲወጡየፌዴሬሽን ምክር ቤት ምን ያህል ሃላፊነቱንተወጥቷል?

ወይዘሮ ፍረወይኒ፡ - ይህን ለሚመለከተውቋሚ ኮሚቴ ብታነሳው ጥሩ ነው።

አዲስ ዘመን፡ - የፌዴሬሽን ምክር ቤትበርካታ ስራዎች አሉት። ለዚህ የሚመጥንየሰው ሃይልና በጀታችሁ ምን ያህል ነው?

ወይዘሮ ፍረወይኒ፡ - እንደ ምክር ቤትስንገመግም ትልቁ ማነቋችን የሰው ሃይል ነው።ይህ ከበጀትም ከሌሎች ጉዳዮችም ጋር ይያያዛል።ይህን ለማስተካከል ምክር ቤቱ እየሰራ ነው። በሰውሃይል ለማጠናከርና በተግባር የተፈተኑባለሙያዎችን የሚሰብ ለማድረግ እየሰራን ነው።የግጭት አመላካች ካርታ ለመስራት ታስቦ በበጀትችግር ለረጅም ጊዜ ቆይቷል። የፌዴሬሽን ምክርቤት እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችልአሰራር ቀርጾና ከማስተካከያው ጋር ለህዝብተወካዮች ምክር ቤት በቀጥታ አቅርቦ ለማስጸደቅእየሰራ ነው። የሰው ሃይሉንና የበጀቱን መጠንየእኔ ሃላፊነት ስላልሆነ ጽሕፈት ቤቱ ቢገልጥልህጥሩ ነው።አዲስ ዘመን፡ - አዲስ የተቋቋመው

የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ኮሚሽንየፌዴሬሽን ምክር ቤትን ስልጣን ይጋፋልይባላል። እንደ ፌዴሬሽን ምክር ቤትአቋማችሁ ምንድን ነው?

ወይዘሮ ፍረወይኒ፡ - ይቅርታ፤ በዚህ ጉዳይላይ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አቤቱታ ገብቷል።ወደ ህገ መንግስት አጣሪ ጉባዔ ቀርቧል።ለአቤቱታው ግን ስርዓቱን ጠብቆ ምላሽ ይሰጣል።የህገ መንግስት አጣሪ ጉባዔ በቀጥታ ምላሽ ሊሰጥወይም አቤቱታው ወደኛ ሊመጣም ይችላል።እኔም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል ስለሆንኩየአስተሳሰብ ተጽዕኖ እንዳላደርግ መጠንቀቅእፈልጋለሁ። ስለዚህ እዚህ ሀሳብ ባልሰጥ ጥሩነው።አዲስ ዘመን፡ - ለሰጡኝ ቃለ ምልልስ

አመሰግናለሁ።ወይዘሮ ፍሬወይኒ፡ - እኔም አመሰግናለሁ።

- ወይዘሮ ፍረወይኒ ገብረእግዚአብሔር

ከክልል ምክር

ቤቶችጋርበተደረገ

አንድ የጥናትመድረክ

ለረጅምጊዜ ምላሽ

ያላገኙ ጥያቄዎችምላሽ

እንዲሰጣቸው

ከክልሎችጋርየጋራ

መግባባት ተደርሷል

Page 7: 78 ንግድን ለማሳለጥ ተጨባጭ ርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ€¦ · ንግድን... በ2ኛው ገጽ ዞሯል 78ኛ

የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን 13

ማኅበራዊ/ልዩ ልዩ

ከቤት ወደ ቤት...

ከኢትዮጵያየሰብዓዊመብት ኮሚሽን ጋርበመተባበርበየሳምንቱ ረቡዕ የሚቀርብ

ሰብዓዊ መብቶች የሰው ልጆች ሰውበመሆናቸው ብቻ በዘር፣ በፆታ፣ በቋንቋ፣በኃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በሌላ አመለካከት፣በመጡበት ማህበረሰብ፣   በሃብት፣ ወይም በሌላምክንያት ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግየተጎናፀፏቸው መሠረታዊ መብቶች እና ነፃነቶችናቸው፡ ፡   እነዚህን መብቶችና ነፃነቶች መሠረትባደረገ መልኩ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብትሰነድ ፈራሚ ወይም ያፀደቁ አባል ሀገራት የተለያዩግዴታዎችን ይገባሉ፡ ፡ እነዚህ ግዴታዎች ጠቅለልተደርገው በሦስት ይከፈላሉ፡ ፡ እነርሱም ሰብዓዊመብቶችን የማክበር፣ የመጠበቅ፣ የማስከበርእንዲሁም የማሟላት ወይም ተግባራዊ የማድረግግዴታዎች ናቸው፡ ፡

የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈፀማቸውየሚረጋገጠው በምርመራ ነው፡ ፡ የሰብዓዊ መብትምርመራ ማለት ጥቆማን ወይም አቤቱታን መሰረትበማድረግ ወይም በራስ አነሳሽነት ጥሰትስለመፈፀሙ ወይም አለመፈፀሙ ስርዓትን ተከትሎማስረጃዎችን እና ሁኔታዎችን በመተንተን፣በምርመራ የተደረሰባቸውን ግኝቶች እና የተለዩጭብጦችን መሰረት በማድረግ ውሳኔ ላይየሚደረስበት ሂደት ነው፡ ፡ ስለዚህም ምርመራማስረጃዎች ካሉት የሰብዓዊ መብት መስፈርቶችአንፃር በመፈተሽ ጥሰት መፈፀሙ ወይምአለመፈፀሙ የሚረጋገጥበት ስርዓት ነው፡ ፡

የሰብዓዊ መብት እና የወንጀል ምርመራየሚያመሳስሏቸውም የሚያለያዩዋቸውም ነገሮችአሏቸው፡ ፡ በመሰረታዊነት የሁለቱም የምርመራተግባሮች ዓላማ በአንድ በተከሰተ ጉዳይ ላይ ሀቁንወይም እውነቱን ማረጋገጥ ነው፡ ፡ ልዩነታቸውየሰብዓዊ መብት ምርመራ መንግሥት በዓለምአቀፍ ስምምነቶችም ሆነ በሀገሪቱ ህገ መንግሥትሰብዓዊ መብትን ለማክበር እና ለማስከበርየገባቸውን ግዴታዎች ሳይፈፅም እና መሰረታዊመብቶችንና ነፃነቶች ተሸራርፈውብኛል የሚል

በ ሰፊው ግቢ ውስጥ ከተሰባሰቡትሴቶች አብዛኞቹ በተለየ ትኩረት እየተወያዩ ነው።ሁሉም ሃሳብና ጨዋታቸው በአንድ ተቃኝቷል።በዚህ ስፍራ አገናኝቶ የሚያነጋግራቸው ቁም ነገርምን እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቁታል። አጠገባቸውተገኝታ የሃሳብ አካፋይም ተካፋይም የሆነችውየጤና ባለሙያም ለሚጠይቋት ሁሉ ትመልሳለች።እነርሱም ለጥያቄዎችዋ ምላሽ ይሰጣሉ።

የምክክር ስፍራውን አለፍ ሲሉ ሰፋ ባለክፍል በአግባቡ ከተነጠፉ አልጋዎች አጠገብይደርሳሉ። የአልጋዎቹ አቀማመጥ እናቶችበአግባቡ ለመወያየት እንዲያመቻቸው ሆነውየተዘጋጁ ናቸው። በአንዱ ጥግ የተቀመጠውተለቅ ያለ ቴሌሌቪዥን ደግሞ ለመዝናኛና መረጃልውውጥ የሚያግዛቸው ነው። እናቶች በየዕለቱበሚተላለፉ ዝግጅቶች እየተዝናኑ ይማማራሉ።

ከመኝታ ክፍሉ ትይዩ የምግብ ማዘጋጃ ክፍልይገኛል። በዚህ ስፍራ በአግባቡ የተቀመጠውእህል ከአካባቢው አርሶ አደሮች በበጎ ፈቃድየተሰበሰበ ነው። የማብሰያ ዕቃዎቹና ለምግብፍጆታ የተዘጋጀው አቅርቦትም የተሟላ ነው።ይህ መሆኑ እናቶች በውሏቸው እንዳይቸገሩአግዟቸዋል። ያሻቸውን ቀምሰውና ከሻይ ቡናውፉት ብለው መዋል መብታቸው ነው።

ምስራቅ ጎጃም ዞን ሸበል በረንታ ወረዳየሚገኘው የ«ሞዠን» ቀበሌ ጤና ጣቢያ ሁሌምቢሆን ከዚህ ልማድ ርቆ አያውቅም። በርካታእናቶችን አሰባስቦ በአንድ ሲያወያይ ያረፍዳል።እህል ውሃው ተዘጋጅቶ፤ ቡናው ከነቁርሱ ቀርቦቁም ነገር በሚወራበት በዚህ ስፍራ ነፍሰጡርእናቶች ያሻቸውን እያነሱ ይወያያሉ። የሚገኙበትቦታ አንድም ለጤንነታቸው የሚበጅ፤ ሌላምእንደቤትና ጓዳቸው የሚታይ ማረፊያቸው ነው።

እናቶቹ ከያሉበት ተሰባስበው በአንድ ሲውሉስሜታቸው አይራራቅም። ሃሳብና ጨዋታቸውተመሳሳይ ነው። ሁሉም በሆዳቸው ስለያዙትጽንስ በትኩረት ይወያያሉ። አርቀውም ስለነገው

መንግሥት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፀመየሚባለው እንዴት ነው?

በአድሐምዱሪ

ዕቅድ ይነድፋሉ። እያንዳንዳቸው ስለጤንነታቸውሲያስቡ በባለሙያዎች የሚታዘዙላቸውንመድሃኒቶች በጊዜውና በአግባቡ መውሰድአይዘነጉም።

ወይዘሮ ሃይማኖት ደነቀው የ«ስዋ» ተፋሰስቀበሌ ነዋሪ ናት። የ«ኩበት» ከተባለችው ጎጥተነስታ ሞዠን ቀበሌ ለመምጣቷ ምክንያትአላት። ይህን ስታደርግ መምህሩ ባሏ በደስታሸኝቶ ስትመለስም ይቀበላታል። ሃይማኖትየመጀመሪያ ልጇን ነፍሰጡር ናት። ይህን ካወቀችወዲህ የህክምና ክትትል ታደርጋለች። እሷን መሰልእናቶች ሁሌም ቢሆን ወሩን ጠብቀው ብቻእንዲመጡ አይገደዱም። ጤና ባልተሰማቸውናምክር በሚሹ ጊዜም የጤና ባለሙያዎችንማግኘት ይችላሉ።

ሃይማኖት ከዚህ ቀደም በነፍሰጡሮች ላይይከሰት የነበረውን ችግር ታውቀዋለች። የጤናክትትል ካለማድረግ የተነሳ ስለሚከሰተው አደጋናበወሊድ ጊዜም ስለሚያጋጥም የደም መፍሰስዕውቀቱ አላት። ቀደም ሲል በቤታቸውየሚወልዱና ህይወታቸውን የሚያጡ እናቶችቁጥር በርካታ ነበር። አሁን ግን ያ ታሪክእንዳይደገም ሁሉም የራሱን ድርሻ እየተወጣይገኛል።

ወይዘሮዋ እርግዝናው የመጀመሪያዋእንደመሆኑ ከመውለዷ ጥቂት ቀናት አስቀድሞበጤና ጣቢያው አርፋ መቆየት ትፈልጋለች።ለዚህም የጤና ባለሙያዎችና እሷን መሰል እናቶችከጎኗ ሆነው ይንከባከቧታል። እንደአማኝ አስቀድሞወደዚህ መምጣት የከበደውን ያቀልላል። ድንገትምጥ ቢመጣና አስቸኳይ ርዳታ ቢያስፈልግድንጋጤና መዋከብ፣ ድካምና ሩጫ አይኖርም።ለእናቲቱም ሆነ ለልጁ ደህንነት ዋስትና ማግኘትይቻላል።

ሁሌም ማለዳ በነፍሰጡር እናቶችየሚደምቀው ይህ ግቢ መተሳሰብና መተጋገዝመለያው ነው። ቀናቸው ለደረሰ ነፍሰጡሮችየሚሰጠው ትኩረት የሚደረገው እንክብካቤ ለየትይላል። እናቶቹ መውለዳቸው በተሰማ ጊዜም

ገንፎ ተገንፍቶና ቡናው ተፈልቶ የመጀመሪያውደስታ የሚበሰረው በዚህ ስፍራ ነው።

ወይዘሮ አዱኛ ዳምጤ የአንዲት ሴት ልጅእናት ነች። ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት ይህ ግንዛቤስላልነበራት በቤቷ ውስጥ ለመውለድ ተገድዳለች።የዛኔ ያጋጠማትን ስቃይና የደም መፍሰስ መቼምአትረሳውም። በወቅቱ ወደ ጤና ጣቢያ የመሄድልምድ ባለመኖሩ በዚያ ሁኔታ ለማለፍ ግድ ብሏትእንደነበር ትናገራለች።

አሁን ግን አዱኛ ያለፈውን ላለመድገምለክትትል የተገኘችው ቀደም ብላ ነው። ይህንለማድረግ ደግሞ በጤና ጣቢያው አገልግሎትያገኙ እናቶች ተሞክሮ አግዟታል። ወይዘሮዋ«ልጅ በዕድሉ ያድጋል» በሚለው ተለምዷዊብሂል አትስማማም።

«ልጅ ሁሌም ፍላጎቱ ተሟልቶለት ሊያድግይገባዋል» ስትል ታምናለች። እሷም የኑሮ አቅሟዳብሮ የጎጆዋ ሙላት እንዲቀጥል ትፈልጋለች።ትናንት ያለፈችበትን የችግር ህይወት ልጆችዋእንዲደግሙት አትሻም። ትምህርቷን እንድታቋርጥሰበቡም ያለዕድሜዋ የገባችበት ትዳርና ተከትሎየመጣው ልጅ መሆናቸው አልጠፋትም። ይህበመሆኑም ዛሬ ድረስ ይቆጫታል። ሌሎችምክንያቶች ደግሞ ሰባት ዓመታት ያለ ተጨማሪልጅ እንድትቆይ አድርጓታል።

ውሎ አድሮ ግን ይህ አቋሟ ከባለቤቷአላስማማትም። ወዳጅ ዘመዶችዋም ቢሆኑ ሃሳቧንአልደገፉላትም። ይህን ስታውቅ ወይዘሮዋ ቆምብላ አሰበች። ትዳሯን መታደግና ኑሮዋን በአግባቡመምራት ግድ ቢላት፤ የምትወስደውን የወሊድመቆጣጠሪያ ትታ ለማርገዝ ወሰነች።

አሁን አዱኛ ዘጠነኛ ወሯ ገብቷል። በየጊዜውቅድመ ወሊድ ክትትል ለማግኘትም ከጤናጣቢያው ርቃ አታውቅም። ይህ ውሎዋ ደግሞከሌሎች መሰሎቿ ጋር አገናኝቷት ልምድቀስማለች። ሴቶቹ በተገናኙ ቁጥር ስለትዳርናስለጎጇቸው ያወጋሉ። ስለልጆቻቸው፤ ስለነገውህይወታቸውና ስለሚያስቡት ዕቅድ ሁሉይወያያሉ። እግረ መንገዳቸውንም ለገጠሟቸው

ችግሮች መላና መፍትሄ ያበጃሉ።ሌላኛዋ ወይዘሮ እማዋይ ዳምጤም በሞዠን

ጤና ጣቢያ ለመገኘቷ ምክንያቱ ነፍሰጡር መሆኗንማወቋ ነው። እማዋይ ክትትሏን ለማካሄድ በጠዋቱመጀመር እንደሚበጅ ገብቷታል። ውጤቷምየሁለት ወር ነፍሰጡር መሆኗን አመላክቷል።ወይዘሮዋ በከዚህ ቀደሙ እርግዝናዋም የምርመራልምድ እንደነበራት ትናገራለች።

እማዋይ አሁን በጀመረችው የእርግዝና ክትትልይበልጥ ተጠቅማለች። ውስጧን የሚረብሽ ህመምቢጤ ሲሰማት ያለምንም ቀጠሮ የመምጣት ዕድሉንአግኝታለች። ከአርሶ አደሩ ባለቤቷ ጋር ተማክራሁለተኛውን ልጇን ስታረግዝም በሙሉ ፍላጎትናስምምነት ነበር። ለዚህ እውነት ደግሞ የጤናባለሙያዎቹ ድጋፍና ሙያዊ ምክር ይበልጥአግዟታል።

እሷን መሰል ሴቶች ከማርገዛቸው በፊትና በኋላማድረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄ ባለሙያዎቹ ቤትለቤት እየዞሩ ትምህርት ይሰጣሉ። እናቶችምበጤና ጣቢያው በሚያደርጉት ቆይታ ስለህጻናትክትባትና ጤናማ አስተዳደግ በጥልቀት ይወያያሉ።ይህ መሆኑ እማዋይን ለበለጠ እቅድ አዘጋጅቶ፤ስለወደፊቱ በጎነት እንድታልም አስችሏታል። ነገንአርቃ የምታስበው ወይዘሮ ዛሬ ከትናንት የተሻለመሆኑንም አረጋግጣለች።

ሲስተር ሃይማኖት በላይ በሸበል በረንታ ወረዳየሞዠን ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አዋላጅ ባለሙያናት። እሷና መሰሎቿ ዘወትር በሚንቀሳቀሱባቸውአራት ቀበሌዎች ነፍሰጡርን በማወያየት ግንዛቤየማስጨበጥ ሃላፊነት ይወጣሉ። እንደ ሃይማኖትአባባል፤ እነዚህን እናቶች የጤና ጣቢያው ተጠቃሚለማድረግ ጥረታቸውን የሚጀምሩት በየመንደሩከሚያደርጉት የየቀን አሰሳ ነው። ሁሌም ቤትለቤት በሚደረገው ፍለጋ ያገኟቸውን ነፍሰጡሮችወደ ማዕከሉ በማምጣት የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራያከናውናሉ።

እናቶችን በጤና ክትትሉ ተሳታፊ ለማድረግየጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን ጨምሮ የተለያዩሴክተር መስሪያ ቤቶች ተሳትፎ የላቀ ነው።

በከፍተኛ ጥረት መተግበር በጀመረው ሂደትምእናቶችንና ጨቅላ ህጻናትን ከሞትና ከከፋ ጉዳትመታደግ ተችሏል። አሁን በሞዠንና ዙሪያ ገባውቀበሌዎች በቤት ውስጥ መውለድ እንደነውርይቆጠራል። የእርግዝና ወቅት የጤና ክትትልምእንደ ባህል መለመድ ጀምሯል።

አቶ የሺጥላ ጌትነት የሞዠን ጤና ጣቢያ ሃላፊናቸው። በእሳቸው ሃላፊነት የሚመራው ጤናጣቢያ በእናቶችና ህጻናት ጤና ላይ ያስመዘገበውውጤት ከፍተኛ ስለመሆኑ ይናገራሉ።ለተመዘገበው ፍሬያማ ውጤት ምክንያቱ በየጤናኬላው ያለው የዕለት ከዕለት ጥረትና ጠንካራተሳትፎ መሆኑን ይገልጻሉ። ለዚህ ደግሞ የሁሉምሴክተር መስሪያ ቤቶች አስተዋጽኦ ላቅ ያለስፍራ ይሰጠዋል።

በአራቱ ቀበሌዎች በሚደረገው የእናቶችክትትል በተደራጀና በጤና ኤክስቴንሽን በተዋቀረቡድን አስፈላጊውን ሁሉ መከወን የተለመደ ነው።ቅርብ ያልሆኑትንና በረሀ አካባቢ የሚገኙትንእናቶች ተደራሽ ለማድረግም ከመውለዳቸውአስቀድሞ በተዘጋጀላቸው ማረፊያ እንዲቆዩይደረጋል።

እናቶች በማረፊያ ክፍሉ ቆይታቸው ስፍራውንልክ እንደቤታቸው እንዲቆጥሩት ለማድረግምከምግብ አቅርቦት እስከ ማህበራዊ አንድነትየሚኖረው ትስስር የጠበቀ ነው። አራስዋ በስፍራውስትገኝ ለህክምና ብቻ አለመሆኑን የሚያመላክቱእውነታዎች መተግበራቸውም የተለመደ ነው።ይህ መሆኑ ደግሞ ሁሌም የእናቲቱን ጉዞ ከቤትወደ ቤት ያደርገዋል።

በጤና ጣቢያው የወለደች እናት ከሃያ አራትሰአት በፊት ወደቤቷ መመለስ እንደሌለባትበአብዛኛው ማህበረሰብ ዘንድ ይታወቃል። ይህንዓይነቱን ጥረት ለማሳካትም የጤና ባለሙያውተሳትፎ በተለየ ትጋት የተሞላ ነው። ዛሬም ሆነወደፊት የእናቶችንና የህጻናትን ደህንነት ለመጠበቅየሚደረገው ተሳትፎ እንደማይቋረጥ ሃላፊውያረጋግጣሉ። ለዚህም የአካባቢውን ጥንካሬናመተማመን በእማኝነት ይጠቅሳሉ።

አቤቱታ ሲቀርብ የሚጣራበት ሂደት ነው፡ ፡የወንጀል ምርመራ ግን የህግም ሆነ የተፈጥሮሰዎች የሚፈፀሙት የወንጀል ህግ ጥሰትየሚጣራበት ሂደት ነው፡ ፡

በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ምርመራየአቤቱታ አቀራረብ ከወንጀል ክስ አቀራረብሥነ-ስርዓት የተለየ ነው፡ ፡ የሰብዓዊ መብትአቤቱታ የሚያስተናግዱ ተቋማት ለምሳሌየሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ማንም ሰው ያለምንምወጪ፣ በቀላሉ አቤቱታ የሚያቀርብበት ሥርዓትሲኖራቸው የወንጀል ክስ የሚያስተናግዱ ተቋማትለምሳሌ የፖሊስ የክስ አቀባበል ሥርዓት ግንውስብስብ፣ በቅድመ ማስረጃ የተደገፈ እና ወጪየሚጠይቅ ነው፡ ፡

ከዚህ ባሻገር የወንጀል ክርክር ሥነ-ስርዓትከፍተኛ ወጪና ረጅም ጊዜ የሚወስድ እናውስብስብ ሂደት ያለው ነው፡ ፡ በተጨማሪ ፍርድቤቶች በቀረበላቸው ፍሬ ነገር ላይ ብቻ ሲያተኩሩ%ተቀባይነት% ያለው ማስረጃ እንዲቀርብያስገድዳሉ፡ ፡ በዚህም የተነሳ ማስረጃ የማቅረብሂደቱ የባለሙያ እገዛና መደበኛ ፎርማሊቲይጠይቃል፡ ፡ በአንፃሩ የሰብዓዊ መብት አቤቱታበሚቀርብበት ወቅት አቤቱታ አቅራቢውተቀባይነት ያለው ማስረጃ ለሰብዓዊ መብትተቋማት እንዲያቀርብ አይገደድም፡ ፡ ማስረጃማፈላለግ የሰብዓዊ መብት መርማሪዎች ግዴታሲሆን ለአቤት ባይ ግን መብት እንጅ ግዴታአይደለም፡ ፡

በአብዛኛው ጊዜ በሰብዓዊ መብት ተቋማትየሰብዓዊ መብት መርማሪዎች አንድን ተጠርጣሪጥፋተኛ ለማሰኘት የሚያቀርቡት ማስረጃዎችየተጠርጣሪን ጥፋት ከበቂ በላይ (50%+1)ማስረዳት የሚጠበቅባቸው ሲሆን በአንፃሩ አንድየወንጀል መርማሪ የሚያቀርበው ማስረጃየተጠርጣሪን ጥፋት ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይማስረዳት ይጠበቅበታል፡ ፡

የሰብዓዊ መብት ምርመራ ዋና ዓላማየሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈፀም ወይም

አለመፈፀሙን ለመወሰን የሚያስችል ማስረጃዎችንመዝኖ ውሳኔ መስጠት ነው፡ ፡ ውሳኔው የሚሰጠው

ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ያላቸው ማስረጃዎችንከሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች አንፃር በማመሳከርነው፡ ፡ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራየሚከተሉት ዝርዝር ዓላማዎች ይኖሩታል፡ ፡እውነታውን ማውጣት፣ ጥሰት የፈፀመውንሰው/አካል መለየት፣ ዳግም ተመሳሳይ ጥሰትእንዳይከሰት ለመከላከል የሚያስችል የመፍትሄሀሳብ ማቅረብ፤ ክስ እንዲመሰረት ወይምአስተዳደራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ማስቻልእና ተጎጂዎች ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ ማስቻልናቸው፡ ፡ ከዚህም አንፃር የሰብዓዊ መብት ምርመራየሚከተሉት ተግባራትን ማካተት ይጠበቅበታል፡ ፡የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጎጂ የሆኑ ሰዎችንናተያያዥነት ያላቸውን ሰዎች ማንነት መለየት፤ከተጎጂዎች ቃል መቀበል፤ ማስረጃዎችንመሰብሰብ፤ ማደራጀት እና መጠበቅ፤ ምሥክሮችንመለየትና ቃላቸውን መቀበል እና አቤቱታየቀረበበት ጥሰት በማን፣ እንዴት፣ መቼ፣ የትናለምን እንደተፈፀመ መለየት የሚሉት ናቸው፡ ፡

ምርመራ በአንድ ጉዳይ ላይ፣ በአንድ ሰውላይ እና/ወይም በአንድ ተቋማዊ ሥርዓት ላይሊካሄድ ይችላል፡ ፡ የምርመራ ሥራ በቢሮ ውስጥጥናት ወይም በመስክ ወይም ሁለቱንም በመጠቀምሊከናወን ይችላል፡ ፡ ምርመራዎች በመስክየሚደረጉት በቢሮ ለማካሄድ የማይቻል ወይምየማይመች እና በቂ የማይሆን ሲሆን፤ እንዲሁምለምርመራ የተያዘው ጉዳይ ጥሰቱ የተፈፀመበትቦታ በመገኘት ማስረጃ ሊሰበሰብበት የሚገባ መሆኑታምኖበት ሲወሰን ነው፡ ፡ ይህን ተከትሎምየሰብዓዊ መብት ምርመራ በአንድ መርማሪ፣በመርማሪዎች ቡድን፣ በህዝብ ቅሬታ ሰሚ አካላትወይም በምርመራ ኮሚሽን/ቦርድ ሊካሄድይችላል፡ ፡

በሰብዓዊ መብት ምርመራ ጊዜ “መርማሪ”ማለት አግባብነት ባላቸው የሰብዓዊ መብት ህጎችመሰረት በተለያዩ ጊዜያትና አካባቢዎች የሚፈፀሙየሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመመርመርና እውነትንበማውጣት፤ የጥሰት ድርጊት ፈፃሚዎች ጥሰቱን

መፈፀማቸውን ወይም አለመፈፀማቸውንየሚያረጋግጥ በህግ ስልጣን የተሰጠው ሰው ነው፡ ፡

በመሆኑም የሰብዓዊ መብት ጥሰት መርማሪዋነኛ ሥራው ተጠርጣሪውን ከድርጊቱ ሰለባ፤እንዲሁም ተጠርጣሪውን ከድርጊቱ ጋር የሚያገናኝመረጃ መሰብሰብ ነው፡ ፡ በተለይም አንድን ተጠርጣሪጥፋተኛ ለማሰኘት የመርማሪው ማስረጃዎችየተጠርጣሪን ጥፋት ከበቂ በላይ (balance ofprobabilities) ማስረዳት የሚጠበቅበት ከመሆኑአንፃር የማስረጃዎቹን ይዘት ቢያንስ ይህንን ዝቅተኛመስፈርት የሚያሟላ መሆን አለበት፡ ፡ የሚሰጠውውሳኔ መሠረት የሚያደርገው በማስረጃዎች ምዘናበቂነት ላይ በመሆኑ ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራ ይገባል፡ ፡

የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዓይነቶች ማሳያዎችንየሚባሉት ማሰቃየት እና ኢሰብዓዊ አያያዝ፣ ከፍርድውጪ የሚፈፀም ግድያ፣ ከህግ ውጪ መያዝ እናመታሰር፣ በፖሊስ እና በፀጥታ አካል የሚወሰድያልተመጣጠነ የኃይል እርምጃ፣ ኃይልን መሰረትያደረገ ከይዞታ ማፈናቀል፣ አስገድዶ መሰወር፣የግዳጅ የጉልበት ሥራ እና የመሳሰሉት ናቸው፡ ፡ሁሉም የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ህግጋትሰብዓዊ መብቶችን በማክበርና በማስከበር ረገድግዴታ የሚጥሉት በመንግሥታት እንጂ በግለሰቦችላይ አይደለም፡ ፡ በዚህም ምክንያት የመንግሥትወኪሎች ማድረግ ወይም መከወን ያለባቸውንባለማድረግ እንዲሁም መተው ያለባቸውንባለመተው የሚፈፅሙት የሰብዓዊ መብት መተላለፍጥሰት ሲባል በግለሰቦችና በግል ተቋማት አማካኝነትየሚደርስ የሰብዓዊ መብት መተላለፍ ግን ጥቃትተብሎ ይጠራል፡ ፡

መንግሥት የሰብዓዊ መብቶችን የማክበር፣የመጠበቅና የማሟላት ግዴታዎቹን ሳይወጣ ሲቀርየሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈፀመ ይባላል፡ ፡ አንድመንግሥት ሰብዓዊ መብቶችን ጣሰ የሚባለው፣የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ በመንግሥት፣ በመንግሥትወኪሎች ወይም በመንግሥት እውቅና ሲፈፀምእንዲሁም መንግሥት ጥሰት እየተከሰተ ባለበትሁኔታ እርምጃ በማይወስድበት ጊዜ ነው፡ ፡

መንግሥት የሰብዓዊመብቶችን የማክበር፣የመጠበቅናየማሟላትግዴታዎቹን ሳይወጣሲቀርየሰብዓዊመብትጥሰት ተፈፀመይባላል፡፡ አንድመንግሥት ሰብዓዊመብቶችንጣሰ

የሚባለው፣ የሰብዓዊመብትጥሰቱበመንግሥት፣

በመንግሥትወኪሎችወይምበመንግሥትእውቅናሲፈፀም

እንዲሁምመንግሥትጥሰት እየተከሰተ

ባለበት ሁኔታ እርምጃበማይወስድበት ጊዜ

ነው፡፡

አሳሳቢየ ሆነው የእናቶችና ህፃናት ሞትን ለመግታት ጠንካራ የሆነ የግንዛቤ መሰረት ሊኖረው ይገባል። በተለይ በእርግዝና ወቅት እናቶች ጤንነታቸው ተጠብቆ ጤናማ ህፃን

እንዲኖራቸው በህክምና የታገዘ እንክብካቤ ሊፈጠር ግድ ይላል በቅርቡ ወደ ምስራቅ ጐጃም ዞን ሸበል በረንታ ወረዳ ተጉዛ የነበረችው የአዲስ ዘመኗመልካምሥራ አፈወርቅም

በገጠር አካባቢ የሚኖሩ እናቶችንናበጤናአጠባበቅዙሪያየሚደረግላቸውን እንክብካቤ ቃኝታያገኘችውንተሞክሮእንዲህታጋራናለች።

Page 8: 78 ንግድን ለማሳለጥ ተጨባጭ ርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ€¦ · ንግድን... በ2ኛው ገጽ ዞሯል 78ኛ

bVEG 20 9O 201 1 ].(22

በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

zH->�f7

SB-�

ለኤች አይቪ ይበልጥ ተጋላጭነን! እንመርመር ራሳችንን

እንወቅ።

ዳንኤል ዘነበ

«የቀድሞ አትሌቶች ልምድና እውቀት ባክኗል፤እውቅና እያገኙ አይደለም»

ትውልድና እድገትትውልድና እድገቴ በቀድሞ መጠሪያው ምዕራብ

ሸዋ ጅባትና ሜጫ አካባቢ ነው። ዕድሜዬለትምህርት እንደደረሰም ወላጆቼ በአካባቢያችንበሚገኝ አንደኛ ደረጃ ትምህርት አስገቡኝ።ትምህርቴን ከአንድ እስከ አራተኛ ክፍልተከታተልኩኝ። ከአራተኛ ክፍል በኋላ ያለውንደግሞ አዲስ አበባ ነበር የተማርኩት፤ያው የህይወትአጋጣሚ ሆነና ወደ አዲስ አበባ መጣሁ።ትምህርቴንም እዚሁ አዲስ አበባ በሽመልስ ሀብቴትምህርት ቤት መከታተል ጀመርኩ። ከአራተኛእስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል በዚሁ ትምህርት ቤትተምሬያለሁ። የትውልድና እድገቴ ሂደት ይህንይመስላል።

የስፖርት አጀማመርስፖርት ለእኔ ህይወቴ ነው። ገና ልጅ እያለሁ

ጀምሮ ነበር የስፖርት ፍቅር ያደረብኝ፤ በትውልድስፍራዬም ሆነ አዲስ አበባ ከመጣሁ በኋላ በሰፈርውስጥና በትምህርት ቤት በስፖርት እንቅስቃሴአደርግ ነበር። በተለይ ደግሞ በትምህርት ቤት ውስጥበልዩ ሁኔታ ስፖርት አዘወትር ነበር። ሩጫውን፣ጦር ውርወራውን፣ ዝላዩን፣ ቅርጫት ኳሱንእሞክራለሁ። ስፖርት በህይወቴ ውስጥ እስከ እለተሞቴ ተከትሎኝ እንደሚሄድ ጭምር ይሰማኛል።ለስፖርቱ ጥልቅ የሆነ ፍቅር ያለኝ ቢሆንም የህይወቴጉዞ ከትምህርት ቤት ወደወታደር ቤት ነበር ያረፈው፤ዘመናዊ ትምህርቴን እስከ 12ኛ ከተከታተልኩ በኋላየሀገር መከላከያ ሰራዊትን ተቀላቀልኩ። የሀገር ፍቅርስሜቴና ወኔዬ ከልጅነቴ አብሮኝ ያደገ ነውና ሀገሬንበምን ላገልግል ከሚል ጉጉት ነበር ጦሩንየተቀላቀልኩት።“ሁን ያለው ይሆናል” ነውና የልጅነትህልሜን በጦሩ ቤት ዳግም አገኘሁት። የስፖርትእንቅስቃሴ ለማድረግ ተመቸኝ። በጦሩ ቤትበሚደረጉ የውስጥ ውድድሮች ላይም በአትሌቲክስየመሳተፍ አጋጣሚዎች ተፈጠሩ። የልጅነት ህልሜከተቀበረበት ተፈንቅሎ መውጣት ጀመረ። የህይወቴምዕራፍ ወደሌላ አቅጣጫ ተዛወረ።በሀይለስላሴም ሆነ በደርግ ጊዜ በጦሩ ቤት

ስፖርት በከፍተኛ ሁኔታ ይዘወተር ነበር።በየአካባቢው የነበሩት የጦሩ ክፍሎችም በሀገር አቀፍደረጃ በሚዘጋጁ የውድድር አውዶች ውጤታማቡድኖችን ይዘው በመቅረብ ይታወቃሉ። የውጤትታሪክ በያዘው ቤት ውስጥ ዳግም የተወለደው የእኔየስፖርት ህይወት ይሄንኑ መልክ የያዘ ነበር።ለመጥቀስ እንደሞከርኩት በጦሩ ቤት በተደረገ

የውስጥ ውድድር እኔ የመታየት አጋጣሚውአግኝቻለሁ። ያኔ በሀገሪቱ ጠንካራ ተብለው ዛሬምድረስ በታሪክ ከሚወሱት ቡድኖች አንዱ የሆነውንክቡር ዘበኛን ለመቀላቀል በቃሁ። ክቡር ዘበኛ ውስጥከገባሁ በኋላ ችሎታዬን በሚገባ የማውጣት እድልአግኝቻለሁ። በአጭር ጊዜ ውስጥ አይን ውስጥገባሁ። የመጀመሪያው የስኬት በርም ተከፈተ።በ1963 ዓ.ም በሸዋ ሻምፒዮና (ያኔ የሸዋ ጠቅላይግዛት የሚባል አስተዳደር ነበር) ውስጥ መመረጤነበር ይህንን ያበሰረኝ፤ በዚህ ውድድር በ3 ሺህሜትር መሰናክል መድረክ ላይ የነበረኝ ውጤታማነትበሀገር አቀፍም ሆነ ከአገር ውጪ በሚደረጉ የስፖርትውድድሮች በመሮጥ ሜዳሊያዎችን እንድሰበሰብመንገድ ጠርጎልኛል።

የአፍሪካ እና የዓለም አቀፍ መድረክተሳትፎና ውጤት

በሀገራችን ስፖርት እንቅስቃሴ ውስጥ ትልቅታሪክ ባለበት በክቡር ዘበኛ ቤት ውስጥ መቆየቴበአጭር ጊዜ ከሀገር አቀፍ ወደ አህጉር አቀፍውድድር ለመሸጋገር ድልድይ ሆኖኛል። ዓመተምህረቱም 1964 ነበር። በሀገር አቀፍ ውድድርበማሸነፌ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተመረጥኩ።ይሁን እንጂ፤ ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር በሙኒክኦሎምፒክ ለመሳተፍ ከተመረጠው ቡድን ጋርለመጓዝ እየተሰናዳሁ ባለሁበት ወቅት ከአሰልጣኝጋር በተፈጠረ ግጭት ከቡድኑ ውጪ ተደረግሁ።ወደትልቁ የውድድር መድረክ ለመጓዝ የቋመጠውልቤ፤ በዚያም ለመሮጥ የተነሳው እግሬ በትንሽአጋጣሚ “ነበር” ሆኖ ቀረ። ይህ መሆኑ ውስጤንቢረብሸኝም ተስፋ ሳልቆርጥ ልምምድ መስራቴንአላቋረጥኩም። ከአንድ ዓመት በኋላ፤ ማለትምበ1965 ዓ.ም በመላው አፍሪካ አትሌቲክስሻምፒዮና ላይ ለመወዳደር ለብሄራዊ ቡድንተመረጥኩ። ናይጄሪያ ሌጎስ በተካሄደው በዚያሻምፒዮና ላይ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሀገሬንበመድረኩ ወከልኩኝ። በውድድሩ አራተኛበመውጣት ዲፕሎማ ተሸለምኩ። በሩጫውየገባሁበት ሰዓት ፈጣን የሚባል በመሆኑ ለፓንአፍሪካ ለመመረጥ ያስቻለኝ ነበርና ከአንድ ዓመትበኋላ አልጀርስ ላይ ተወዳድሬ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝአጠናቀኩ። በሻምፒዮናው የነበረኝ ተሳትፎና ውጤትደግሞ በአትሌቲክሱ የማደርገውን ጉዞ ቀጣይነትእንዲኖረው ያደረገ ነበር።በአህጉር ደረጃ የነበረኝ የተወዳዳሪነት አድማስ

ከፍ ያለና በተለያዩ የዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ

የመሳተፍ እድሎችም ነበሩኝ። በአሜሪካ አዘጋጅነትበተካሄደውና ከተለያዩ አህጉራት የተውጣጡ ቡድኖችበሚተሳተፉበት ውድድር በ3 ሺህ ሜትር መሰናክልተሳታፊ ሆኛለሁ። በውድድሩ ሶስተኛ በመውጣትለአፍሪካም ሆነ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ሜዳሊያያጠለቅኩበት አጋጣሚ ከብዙዎቹ መካከል የሚጠቀስነው። በአህጉርም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለኝተሳትፎና ውጤት ከዚህ አኳያ ታሪካዊ የሚባልእንደሆነ አስባለሁ። በተወዳዳሪነት ዘመኔ በተለየመልኩ 3ሺህ መሰናክል እውቅና ላትርፍ እንጂ፤በ5 ሺህ ና በ10 ሺህ ሜትር በሀገር ውስጥና ከሀገርውጪ ተወዳድሬያለሁ። በተለያዩ አገራት በመዞርበተወዳደርኩባቸው ጊዜያት ባጠቃላይ 54ሜዳሊያዎች አግኝቻለሁ።

የአሰልጣኝነት ህይወትበክቡር ዘበኛ ቤት ውስጥ የጀመረው የተወዳዳሪነት

ህይወቴ በተለያዩ የታሪክ ገጠመኞች ታጅቦ እዛውተዘጋ። ለስፖርቱ የነበረኝ ጥልቅ ፍቅርና ፍላጎትበዚያው እንድዘልቅ አደረገኝ። እናም የተወዳዳሪነትቆይታዬ ካከተመ በኋላ፤ በዚያው ባሳደገኝ በክቡርዘበኛ ቤት ውስጥ አሰልጣኝ ሆኜ ቀጠልኩ። በሀገራችንየስፖርት ታሪክ ውስጥ ዛሬም ድረስ ስሙ በሚነሳውበጦሩ ቤት ከባልደረቦቼ ጋር በመሆን ታሪክለማስቀጠል ተነሳን። በወቅቱም ማዕከላዊ ኮርንእንዳሰለጥን ተሰጠኝ። በዚያም ውርወራ፣ ዝላይናመሰናክል አሰለጥን ነበር። ከዚያም፤ እድሜዬ ለጡረታሲደርስ በ1987 ዓ.ም ጡረታ ተገለልኩ።የአሰልጣኝነት ቆይታዬ ከተወዳዳሪነት ጊዜ ባልተናነሰስኬታማ እንደነበር አስባለሁ። ለዚህም በአፍሪካሻምፒዮና የወርቅ ጫማ ተሸላሚ የሆነው አትሌትበቀለ ደበሌ የኔ ሰልጣኝ ነበርና እርሱ እንደማሳያይጠቀሳል። አትሌቱ ወታደር ሆኖ የተቀጠረ ቢሆንምለስፖርት የተመለመልኩት እኔ ነበርኩኝ። በቀለንበጊዜው እንዳየሁት በቂ ስልጠናና ክትትልከተደረገለት ውጤታማ እንደሚሆን እምነትአደረብኝ። እርሱም አላሳፈረኝም በአፍሪካ ሻምፒዮናላይ የወርቅ ጫማ ተሸለመ። በአሰልጣኝነት ቆይታዬሌሎች ውጤታማ አትሌቶችን አፍርቻለሁ። ሀገራችንስሟና ታሪኳ ብዙም በማይጠቀሰው የእርምጃ ሩጫተወዳዳሪ የነበረው ሸምሱ ሀሰን የእኔ ሰልጣኝ ነው።

ሸምሱ በተለያዩ አገራት በመሳተፍ ውጤትማስመዝገቡን ታሪክ ምስክር ነው። በአሁኑ ወቅትበአሜሪካን አገር የሚኖረውን አለማየሁ ሮባንከትምህርት ቤት መልምዬ አምጥቼ ውጤታማአድርጌዋለሁ። በዚህም የተነሳ፤ በክቡር ዘበኛተጠንስሶ በተወለደው የስፖርት ህይወቴበአትሌትነትም በአሰልጣኝነትም ስኬታማ ነበርኩብዬ በኩራት መናገር እችላለሁ። ከእኔም ሆነ ከሌሎችቀደምት ስፖርተኞች ስኬት ጀርባ ግን በጦሩ ቤትውስጥ በመንግስትም ይህን በጦሩ መሪዎች ለስፖርትየሚሰጠው ትኩረት የአንበሳውን ድርሻ እንደሚይዝሳልናገር አላልፍም።

ታሪካዊ ድል፤ የጦሩ ጀብድበጦሩ ቤት ለስፖርቱ ትኩረት ተደርጎ የተጠናከረ

ስልጠና ይሰራል ነበር። ያኔ በሀገር አቀፍ ደረጃበሚከናወኑ ውድድሮች ላይ የአትሌቲክስ ዋንጫለአንድ ጊዜም ቢሆን ከክቡር ዘበኛ ወጥቶአያወቅም። በቡድን ስራ ላይ ከፍተኛ ትኩረትተደርጎ ይሰራል። በመሆኑም በአትሌቲክሱ በተለያዩርቀቶች ውጤታማ አትሌቶች በማፍራት ረገድየክቡር ዘበኛን ያክል የነበረ ክለብ የለም ብሎበድፍረት መናገር ይቻላል። ክቡር ዘበኛ በርካታስፖርትኞችን አፍርቷል። ክለቡ ሀገራችንን በዓለምአቀፍ የውድድር አውዶች ላይ ውጤታማእንድትሆን ያደረገ፤ ሰንደቋንም ከፍ ብሎእንዲውለበለብ ያሰቸለም ጭምር ነበር። ሻምበልማሞ ወልዴ፣ ሰለሞን በላይ፣ ካሳ ባልቻ፣ ሀይሉወልደጻዲቅ ፣የማራቶን ጀግናው ደረጄ ነዲ፣ ለማገዳ፣ እነዚህ ሁሉ አትሌቶች ከክቡር ዘበኛ የተገኙየሀገር ባለውለታዎች ናቸው። ለእነዚህ አትሌቶችስኬትና ውጤታማነት ደግሞ አሰልጣኞች የጀርባአጥንት ነበሩ። እንደትውስታም አሰልጣኝናተቆጣጣሪ የነበሩት ተከስተ አባይ አብረው የሚነሱለክለቡ ብቻም ሳይሆን ለሀገር ባለ ውለታ ጭምርናቸው። እናም ክቡር ዘበኛ የሀገሪቱ የስፖርትማህጸን ነበር ማለት ይቻላል። አሁን ባለው የሀገሪቱስፖርት ላይም አሻራው ይታያል።

የአትሌቲክሱ ጋሬጣዎችበአሁኑ ወቅት በስፖርቱ ውስጥ የሚታየውየመለማመጃና የመወዳደሪያ ሜዳ ችግር ከፍተኛ

ተጽእኖ እያሳደረ ይገኛል። በመንግስት በኩል ይህጉዳይ ትኩረት ተደርጎበት ሊሰራ ይገባል። ስፖርቱንበሚፈለገው ደረጃና መልክ ለማከናወን የማዘውተሪያቦታ እንደ ልብ ማግኘት አይቻልም። ለምሳሌ፤የራሴን ተሞክሮ ባነሳ፤ የግል ክለብ አሰለጥን ነበር።ብዙም ሳልገፋበት ማሰልጠኑን በማቆም አቅጣጫዬንቀየርኩኝ። ምክንያቱም የእኔ የማሰልጠን ፍላጎትናየአትሌቶች የመሰልጠን ፍላጎት ብቻ በቂ አይሆንም።ይልቁንም፤ የተሟላ የማሰልጠኛ ቦታ ያስፈልጋል።የስልጠና ሜዳ በሚፈለገው ደረጃና እንደ ልብየሚገኝ ቢሆን ያካበትኩትን እውቀቴንና ልምዴንማጋራት እችል ነበር። ይህ ችግር ከራሴው ተሞክሮመንሳቴ ነው እንጂ በሌሎች ሙያተኞች በተደጋጋሚሲነሳ ይደመጣልና ብሄራዊ ፌዴሬሽኑም ሆነመንግስት ጉዳዩን በሚገባ ሊያጤኑት ይገባል።ኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ሀገር ሆና አትሌቶች በበቂሁኔታ ስልጠና የሚሰሩበት ሜዳ አለመኖሩ ያሳፍራል።አዲስ አበባ ውስጥ አነሰ ቢባል ስምንት የስልጠናሜዳ ሊኖር ይገባ ነበር። እውነታው ግን ይህአይደለም። ሌላው ለሀገራችን አትሌቲክስ የቁልቁለትጉዞ ምክንያት ተደርጎ መወሰድ የሚገባው ልምድናእውቀት ያካበቱ አንጋፋ ስፖርተኞችን መዘንጋትነው።በብሄራዊ ፌዴሬሽኑ አሁን የሚገኙት ወጣት

አሰልጣኞችና አትሌቶች ልምድ ያካበቱ ሙያተኞችንሲጠቀሙ/ሲያማክሩ አይስተዋልም። በኦሎምፒክ፣በአለም ሻምፒዮና ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ሀገርንያስጠሩ ትንታግ አትሌቶች ባለቤት መሆኗይታወቃል። እነዚህን የትናንት ጀግኖች ልምድናእውቀት ከዘመኑ ጋር አዋድዶ መጠቀም ያስፈልጋል።በእርግጥ በአሰልጣኝነቱ ባንመጥን እንኳን፤ ለወጣትአሰልጣኞች ረዳትና አማካሪ በመሆን የቀደመውንልምድ ማካፈል እንችል ነበር። ያለፍንበትንናየሰራንበትን ማሳየቱ ለመጪው ትውልድ ጥሩ ነውብዬ አስባለሁ። በሀገራችን አትሌቲክስ ውስጥ ይህባህል ብዙም የለም። አይስተዋልምም። በሌሎችሀገራት ልምድ ያካበቱ ስፖርተኞችን ከማራቅ ይልቅቀርበው እንዲያግዙ፤ ልምዳቸውን እንዲያካፍሉእንደሚያደርጉ በተለያዩ አጋሚዎች ታዝቤአለሁ።በእኛ ሀገርም ይሄን ልምድ ወስዶ ተግባራዊ ማድረጉጥቅሙ የጋራ ነው። በሀገራችን ነባራዊ ሀቅ የቀደሙአትሌቶች አስታዋሽና እውቅና እያገኙ አይደለም።ይህአይነቱ ውለታበል አካሄድ ስፖርቱን ገድሎታልየሚል እምነት አለኝ።

የሀገር ባለውለታዎች የጊዜ ክፍያ

በሀገራችን የቀድሞ አትሌቶችን ብዙን ጊዜአስታውሶ እውቅና የመስጠቱ ዝንባሌ በእጅጉ ትንሽነው። በዓለም አቀፍ መድረኮች የአትሌቲክስውድድሮች በመሳተፍና በማሸነፍ የሀገራችንን ሰንደቅአላማ በዓለም ህዝብ ፊት እንዲውለበለቡ ያደረጉበርካታ የቀድሞ አትሌቶች አሉ። እነዚህ የቀድሞአትሌቶች አሁንም በህይወት ይገኛሉ። በጉብዝናቸውወራት የሀገራችንን ስም ያስጠሩትን እነዚህንባለውለታዎች ፈልጎ እውቅና መስጠትና ድጋፍማድረግ ትልቅ ቁም ነገር ነው። ይሁን እንጂ፤ ይህአይነቱ ሁኔታ በሀገራችን ብዙም ጠንካራ አይደለም።አስታውሶ እውቅና የመስጠት ባህሉ/ልምዱ እምብዛምነው። ይህ መሆን የለበትም። በእርግጥ በቅርቡብሄራዊ ፌዴሬሽኑ (ምንም እንኳን ቢዘገይም)አስታውሶን ትጥቅና የተወሰነ ገንዘብ ድጋፍአድርጎልናል። ፌዴሬሽኑ ይሄን ሲያደርግ እኔእውነቴን ነው ከእንቅልፌ የባነንኩኝ መስሎኛል።“ለካስ ያውቁናል” ነበር ያልኩት፤ ይህ ዓይነቱ ተግባርሊቀጥል ይገባል።

b9g)[ SG#G b� S ; Kd &VT$ h-4

ኢትዮጵያበተለይ በአትሌቲክስ ስፖርት በትውልድቅብብሎሽየተጓዙጀግኖችባለቤት

ናት። እነዚህጀግኖችበኦሊምፒኮችናበዓለምሻምፒዮናዎችኢትዮጵያንወርቅበወርቅበማድረግ

ችሎታቸውን አስመስክረዋል። በአብሮነት ጉዞ የተገኘውድል የ“ይቻላል”ን ታሪክ በማቀበል ዛሬ ትውልድ

እንዲመሰክርናእንዲማርእያደረገ ይገኛል። ቀደምት አትሌቶችበጉብዝናቸውወራት ለሀገራቸውሮጠው

ያኖሩትን የድል ታሪክ ትውልድሊያወሳውይገባል። ይህን ድል የብርታትናየጽናትምሳሌ አድርጎ የራሱን

ታሪክ ለመስራት እንዲዘጋጅያግዘዋልና፤ ይህን እውነታመነሻናመድረሻበማድረግየአዲስ ዘመን ጋዜጣም

ከቀደምትጀግኖችአንዱ የሆኑትን የቀድሞአትሌት የ፶አለቃኃይለ ሚካኤል ጃርሶን እንግዳ አድርጓል።

የ፶ አለቃ ኃይለሚካኤል በ3 ሺህሜትርመሰናከል፣ በ5 ሺህሜትር፣ በ10 ሺህሜትር በመሮጥ ለሀገራቸው

54 ሜዳሊያዎችያመጡባለውለታናቸው። እኛምበርቱዕ አንደበታቸውየተረኩልንንናከተወዳዳሪነት

እስከ አሰልጣኝነት የተሻገረውን የህይወት ገጻቸውን እንደሚከተለው አቅርበነዋል። መልካምንባብ፤

ዳንኤል ዘነበ

በአምቦ ከተማ 16ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድርእና 12ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል «የባህል ስፖርትተሳትፏችን ለሰላምና ለአንድነታችን» በሚል መሪ ቃልበአምቦ ስታዲየም በስፖርታዊ ጨዋነት ታጅቦ በድምቀትመከበሩ ቀጥሏል። በውድድሩም አማራ፣ኦሮሚያ፣ ደቡብናሐረሪ ክልሎች እንዲሁም አዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማአስተዳደርን በማሳተፍ ትናንት አራተኛ ቀኑን አስቆጥሯል።በትናንት ውሎው በሁለቱም ጾታዎች የሻህ፣ ቡብ፣

ገበጣና የገና ጨዋታ ተከናውነዋል። በዚህ መሰረት በሻህወንዶች ኦሮሚያ ሀረሪን እንዲሁም ድሬ ዳዋ ደቡብን2ለ0 በመርታት ወደቀጣዩ ዙር አልፏል።በተመሳሳይ ዕለት የሴቶች ሻህ ተካሂዷል። አዲስ

አበባና ኦሮሚያ ተገናኝተው አዲስ አበባ ኦሮሚያን 2ለ1ረትቷል። በአማራ ክልል ከሀረሪ ባገናኘው ጨዋታ ደግሞአማራ ሀረሪን 2ለ0 በመርታት ቀጣዩን ዙር በድልተቀላቅሏል። በውድድሩ እየተካሄዱ ከሚገኙት 13

የስፖርት አይነቶች አንዱ የሆነው የቡብ ጨዋታምተከናውኗል። በወንዶች ድሬዳዋ ደቡብን 2ለ0፣ አዲስአበባ ኦሮሚያን 2ለ0 በመርታት ባለድል ሆኗል። ቡብበሴቶች አማራ አዲስ አበባን እንዲሁም ኦሮሚያ ድሬዳዋን 2ለ0 ረትቷል። በገበጣ ባለ 18 ጉድጓድ በሴቶችአዲስ አበባ ደቡብን እንዲሁም ኦሮሚያ ሀረሪን 2ለ0አሸንፏል።በወንዶች ገበጣ ባለ 18 ጉድጓድ ኦሮሚያ ሀረሪን

እንዲሁም አማራ አዲስ አበባን 2ለ0 አሸንፈዋል፡ ፡የውድድሩ ድምቀት በሆነው የገና ጨዋታ በገና የወንዶችውድድር ደቡብ ክልልና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርተጫውተዋል። ከፍተኛ ፉክክር በተስተዋለበት በዚህጨዋታ ደቡብ ከድሬዳዋ አቻ ሲለያዩ አማራ አዲስ አበባን1ለ0 አሸንፏል፡ ፡ሌላው የኮረቤ ውድድር በነጠላ ሴቶች አዲስ አበባ፣

ኦሮሚያ እና ደቡብ ከአንድ እስከሶስት ያለውን ደረጃሲይዙ በወንዶች ነጠላ ውድድር ደቡብ የመጀመሪያውንደረጃ በመያዝ ኦሮሚያና አማራ 2ኛ እና 3ኛ ሆነዋል፡ ፡

በድብልቅ ኮረቤ ውድድር አማራ 1ኛ፣ አዲስ አበባ 2ኛእና ኦሮሚያ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል፡ ፡

የቀስት ውድድር በሁለቱም ጾታዎች የተካሄደ ሲሆንበነጠላ በሴቶችም በወንዶችም የአንደኛነቱ ስፍራ አማራበመያዝ አጠናቅቋል። በተመሳሳይ አዲስ አበባ በሁለቱምጾታዎች ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ወደቀጣዩ ዙር በቀጥታአልፏል።በሌላው የውድድር ሁለትና ሶስት ቀናት ውሎ

የድብልቅ ቀስት ውድድር የሚጠቀስ ሲሆን የድብልቅቀስት የወንዶች ውድድር አማራ 23 ነጥብ፣ አዲስ አበባ16 ነጥብ፣ ኦሮሚያ 11 ነጥብ እና ድሬዳዋ 5 ነጥብአስመዝግበዋል፡ ፡ በድብልቅ ቀስት የሴቶች ውድድርአማራ 10 ነጥብ፣ አዲስ አበባ 9 ነጠብ እንዲሁምደቡብ 4 ነጥብ አስመዝግበዋል።16ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 12ኛው

የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል በስፖርታዊ ጨዋነትበመታጀብ እስከየካቲት 24 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስበ13 የባህል ስፖርት አይነቶች ይካሄዳል።

የወንዶችየገበጣጨዋታውድድር

16ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 12ኛው የባህልስፖርቶች ፌስቲቫል በስፖርታዊ ጨዋነት ታጅቦ ቀጥሏል