39
የየየየየየ የየየየየ የየየየየየ የየየየየየየ የየየየየየ የየየየየየ የየየየ የየየ የየየየ የየየየየየ የየየየ

Competence Manual

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: Competence Manual

የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት

የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ አተገባበር ማኑዋል

የቴክኖሎጂ ሽግግር አተገባበር ማንዋል

Page 2: Competence Manual

ማውጫ

መግቢያ 2

የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ - ትርጉምና ጽንሰ ሃሳብ 4

ዋና ዋና የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ፕሮግራም አማራጮች/መንገዶች 5

የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ሂደቶች 7

የቴክኒካልቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ፕሮግራም ዝግጅት 10

የቴክኒካል አቅም ግንባታውን ውጤት መገምገም 11

የክህሎት አቅም ግንባታ አተገባበር ስልት 13

የባለ ድርሻ አካላት ሚና 14

ለቴክኒካልክህሎት አቅም ግንባታ ተግባሪዎች አጠቃላይ ማስታወሻ 16

1

Page 3: Competence Manual

1.መግቢያ

አሁን ያለንበት ዘመን አለማቀፍ የኢኮኖሚ ትስስር የሰፈነበት ሲሆን ኢትዮጵያም የዚሁ ትስስር አካል ናት፡፡ ከዚህ ጋር

ተያይዞ የሚከሰተው አለምአቀፍ የገበያ ውድድር ደግሞ ድንበር ዘለል ከመሆኑ የተነሳ በመጪው ጊዜ የገበያው

ባለቤት የሚሆኑት በሂደቱ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው አምራቾችና አገልገሎት ሰጪ ኢንተርፕራይዞች ብቻ ናቸው፡፡

አንድ ኢንተርፕራይዝ ደግሞ ከተወዳዳሪዎቹ ልቆ እንዲገኝ ከሚያደርጉት ጉዳዮች አንዱ ያለው የሰው ሃይል ክህሎት

ደረጃ ነው፡፡

በቂ ቴክኒካል ክህሎት ፣የስራ ፈጣሪነትባህሪይ፣ ምርጥ ቴክኖሎጂና የጥራትና ምርታማነት አሰራር የታጀበ

አመራረትና አገልግሎት ከለሌ በስተቀር ማንኛወም አይነት ግብአት፣ መሰረተ ልማትና ዘመናዊ አደረጃጀት ቢኖርም

ለትርፋማነትና ለተወዳዳሪነት ሊያበቁ እንደማይችሉ የተለያዩ የጥናት ውጤቶች ያመለክታሉ።

ከዚሁ ግንዛቤ በመነሳት አዲስ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ ተቀርጾ ወደ ስራ እየተገባ

ነው። በዚህ ስትራቴጂ መሰረት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማልማት ከተቀመጡት የድጋፍ ማእቀፎች

ውስጥ አንዱ ለኢንተርፕራይዞቹ ብቃት ያለው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልገሎት መስጠት ነው።

“ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ማለት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ችግር በፍላጎት ላይ ተመስርቶ

የለየና የተሟላ መረጃ ማደራጀትና የመስጠት፣ስልጠናና ምክር፣ የቴክኖሎጂ ልማት፣ግብይት፣ምርጥ ተሞክሮ

”ቅመራና ማሰተላለፍን ሚያካትት ድጋፍ ነው

የማስተላለፍ ስልቶቹም፤

የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ

የስራ ፈጣሪነት አቅም ግንባታ

የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ

የጥራትና ምርታማነት አቅም ግንባታ ናቸው

ይህ መመሪያ በቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ አተገባበር ላይ የሚያተኮር ሲሆን አላማውም ፈጻሚዎች ስለ

ቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ተገቢውን ግንዛቤ ጨብጠው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በገበያ ላይ

የሚያጋጥሟቸውን የተለያዩ የክህሎት ክፍተቶች በመለየት ብቃትና ትርጉም ያለው የአቅም ግንባታ ስራ

እንዲያከናውኑ ለማስቻል ነው።

2

Page 4: Competence Manual

2. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ - ትርጉምና ጽንሰ ሃሳብ

ክህሎትን /competence በተመለከተ የተለያዩ መዝገበ ቃላት የተለያዩ ትርጉሞች የሚሰጡት ቢሆንም ለዚህ

መመሪያ አጠቃቀም ክህሎት ማለት አንድን የተወሰነ ስራ በተቀመጠለት መስፈርት ወይም ደረጃ/standard

3

Page 5: Competence Manual

መሰረት ማከናወን ማለት ነው። ይህም ለስራው የሚያስፈልጉትን የእጅ ሙያ እውቀትንና አመለካከትን ያጠቃለለ

ነው።

ወደ ስራ አለም ያልገባው የስራ ሃይል በቴ/ሙ/ ትምህርትና ስልጠና መደበኛ ፕሮግራሞች በትበብር ስልጠና

አማካይነት ሙሉ የሙያ ብቃት (እውቀት፤ክህሎት፤አመለካከት) አግኝቶ ወደ ስራ አለም እንዲቀላቀል ይደረጋል።

በሌላ በኩል በስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አንቀሳቃሾችና ሰራተኞችን

በፍጥነትና በየጊዜው ከሚፈጠሩ የቴክኖሎጂና የገበያ መለዋወጥ ምክንያት የሚያጋጥሟቸውን የቴክኒካል

ክህሎት ክፍተቶች በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አማካይነት በቴ/ሙ/ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በሚከናወን

የክህሎት አቅም ግንባታ ፕሮግራም መሰረት እንዲሟሉ ይደረጋል።

የአንድ ኢንተርፕራይዝ የተወዳዳሪነት አቅም በሰራተኞች ብቃትና የቴክኒክ ክህሎት ደረጃ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

በመሆኑም ሰራተኞችን በየጊዜው ስራው የሚፈልገውን የክህሎት ደረጃ እንዲጨብጡና የስራ አፈፃፀማቸውና

ምርታማነታቸው እንዲጎለብት ማድረግ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ የመቆየትና

ያለመቆየት ጉዳይ ነው፡፡ አዳዲስ ሰራተኞች በሚቀጠሩበት ጊዜ፣ አዳዲስ አሰራሮች ሲዘረጉ ወይንም አዳዲስ

ምርቶችን ለማምረት ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ለሰራተኞች በቂ ስልጠና መስጠት ይገባል፡፡ ድርጅቱ እያደገ

በሄደ መጠን ውጤታማ ለመሆን እንዲችል የሰራተኞችን ክህሎት በአይነትና በደረጃ መለወጥና ማሳደግ ግድ

ነው፡፡

የቴክኒክ ክህሎት ብቃት ኢንተርፕራይዞች በሚያመርቱት ምርትና በሚሰጡት አገልገሎት ተወዳዳሪነት ላይ

ቀጥተኛ አስተዋጽዎ አለው። የቴክኒክ ክህሎት አቅም ያለው ኢንተርፕራይዝ የክሀሎት አቅሙ ደካማ ከሆነው

ኢንተርፕራይዝ የበለጠ በገበያ ላይ ተወዳዳሪና ትርፋማ ነው።

ለምሳሌ ያህል ጥሩ መሰተንግዶ ያለበት ሆቴል ጥሩ መሰተንግዶ ከለሌበት ሆቴል የተሻለ ተወዳዳሪና

በደንበኞችም ተመራጭ ነው። ጥሩ መስተንግዶ ሊሰጡ የሚችሉ ደግሞ በመስተንገዶ ስራ ክህሎት ያለው

ሰራተኞች ናቸው። ከዚህ ምሳሌ መረዳት የምንችለው የመስተንግዶ ክህሎት ክፍተት አንዱ መሆኑን ለይቶ በሱ

ላይ የክህሎት አቅም መገንባትና ያለውን የገበያ ችግር መፍታት እንደሚቻል ነው።

በመሆኑም የቴክኒክ ክህሎት አቅም ግንባታ ማለት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በገበያ ላይ ተወዳዳሪ

እንዳይሆኑ የሚያደርጓቸውን የክህሎት ክፍተቶችን ነቅሶ በመለየት እነዚህን ክፍተቶች ሊያስወግድላቸው

የሚያስችል አቅም መፍጠር ማለት ነው።

የተለየ የቴክኒክ ክህሎት ክፍተት ሳይኖር የክህሎት አቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን ማቀድና ማከናወን እንደ ብክነት

ሊቆጠር ይገባል። ሰራተኛው ከፕሮግራሙ ባገኘው ክህሎት የሚያሰመዘግበው ምርታማነት ለአቅም ግንባታው

4

Page 6: Competence Manual

ከዋለው ሀብትና በክህሎት አቅም ግንባታ ፕሮግራሞች ላይ ለመሳተፍ ከስራ ገበታው በተለየበት ጊዜ ባለማምረቱ

ምክንያት ከሚከሰቱት ወጪዎች/opportunity costs ና ሌሎችም ግብአቶች በላይ መሆን ይኖርበታል ነው።

እንደ ትብብር ስልጠናው ሁሉ በክህሎት አቅም ግንባታ አተገባበር ላይም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከ

ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ጋር በጋራ ማቀድና መስራት ለፕሮግራሞቹ መሳካት ቁልፍ ጉዳይ

ነው።

ይህ መመሪያ የሚያተኩረው በስራ ላይ ያሉ የጥቃቅንና አነስተኛ የኢንዱስትሪ አንቀሳቃሾችንና ሰራተኞችን

ተወዳዳሪነት ለማጎልበት የሚረዱ የቴክኒክ ክህሎቶችን በማስጨበጥ የምርታማነትና ተወዳዳሪነት አቅማቸውን

በማጎልበት ላይ ነው።

መመሪያው ቀደም ሲል የነበረውን የኩባንያ ውስጥ ስልጠና መመሪያ በከፊል የሚተካ ሲሆን የበፊቱን መመሪያ

ካሁን በኋላም ቢሆን ለመካከለኛና ታላላቅ ኢንዱሰትሪዎች የስልጠና አገልገሎት መስጠት በሚያስፈልግበት

ወቅት መጠቀም ይቻላል

3. ዋና ዋና የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ፕሮግራም አማራጮች/መንገዶች

የክህሎት ክፍተት አቅም ግንባታና በተለያዩ ዘዴዎችና ቦታዎች ማከናወን ይቻላል እነሱም፡-

ሀ. የተሻለ የክሀሎት አቅም ባለውና ብቃቱ በተረጋገጠ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሽ

ወይም ስራተኛ አማካይነት በኢንተርፕራይዙ የስራ ቦታ ላይ

ለ. በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሰልጠና መምህር አማካይነት በጥቃቅንና አነስተኛ በኢንተርፕራይዙ የስራ

ቦታ ላይ

ሐ. በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሰልጠና መምህር አማካይነት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና

ተቋማት ውስጥ

መ. የተሻለ የክሀሎት አቅም ባለውና ብቃቱ በተረጋገጠ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሽ

ወይም ስራተኛና በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሰልጠና መምህር በጋራ በሁለቱም ተቋማት ውስጥ

ሰ. በአስመጪዎችና አቅራቢዎች ባለሙያዎች በአዳዲስ የአመራረት ዘዴዎችና በአዳዲስ የመሰሪያ

አጠቃቀም ላይ በአስመጪዎቹ ወይም በኢንተረፕራይዙ የስራ ቦታ ላይ

ከላይ እንደተመለከተው በተለየው የበኢንተርፕራይዙ ቴክኒካል ክህሎት ክፍተት መሰረት አማራጮችን መጠቀም

ይቻላል ። ሆኖም ግን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የአቅም ግንባታ ፕሮግራሙን በማቀድና

5

Page 7: Competence Manual

የማሰልጠኛ ስነ ዘዴዎችና ማቴሪያሎችን ከማዘጋጀት አንስቶ እስከ ፕሮግራሙ ፍጻሜ ግምገማ እስከ ማድረግና

መቀመር ድረስ የሚጫወቱት ሚና በተለይም ከ 1 እስከ 4 ባሉ አማራጮች ላይ ከፍተኛ ነው።

4. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ሂደቶች

4.1. የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ/bench marking

ተወዳዳሪ የሚያያደርጉ ቁልፍ የስራ ሂደቶችን መለየት

ከታች የተመለከተው ምሳሌ በባህላዊ ሽመና ላይ የተለየ ቁልፍ ስራን ያሳያል

6

Page 8: Competence Manual

በተለዩ የስራ ሂደቶች ላይ ያለውን የተወዳደሪነት ክህሎት ደረጃና ከተቀመጠው የሙያ

ደረጃ/ የብቃት አሃድ አንጻር መቀመር

4.2. የቴክኒካል ክህሎት ክፍተት መለየት

የኢንተርፕራይዙን ሰራተኞች ከተቀመጠው የክህሎት ደረጃ ወይም የብቃት አሃድ አንጻር ተወዳዳሪ

መሆን ያላስቻሉ ክፍተቶችን በምዘና መለየት

የሰራተኞችን የቴክኒካል ክህሎት ክፍተት ለመለየት በሚቀጥለው ገጽ የተቀመጠውን የክህሎት

ሰሌዳ መጠቀም ይቻላል

7

Page 9: Competence Manual

የክህሎት ሰሌዳ/competency matrix

የሙያ ደረጃ _________________________

የብቃት አሃድ

______________

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13

8

Page 10: Competence Manual

የሰራተኛው ስም

4.2.1. የክህሎት ሰሌዳው አጠቃቀም

o መጀመሪያ እያንዳንዱ ሰራተኛ ከተሰማራበት ወይም ከተመደበበት ስራ አንጻር በስሙ

ከተቀመጠው የብቃት አሃድ ሳጥን አንጻር ምልክት ማድረግ

o የሰራተኛውን አፈጻጸም ወይም ክህሎት ከተቀመጠው የብቃት አንጻር መገምገም ወይም መመዘን

በአፈጻጸሙ መሰረት የተለያዩ የክህሎት ደረጃዎችን መለየት ይቻላል

ለምሳሌ የብቃቱ ዝርዝር ስራዎች/elements ሙሉ ሙሉ በብቃት ለሚያከናውን ሰራተኛ አረንጓዴ ምልክት

መስጠት

የብቃት አሀዱን ዝርዝር ስራዎች/elements በከፊል በብቃት ለሚያከናውን ሰራተኛ ቢጫ ምልክት መስጠት

የብቃት አሀዱን ዝርዝር ስራዎች/elements ሙሉ ለሙሉ በብቃት ለሚያከናውን ሰራተኛ ቀይ ምልክት መስጠት

5. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ፕሮግራም ዝግጅት

ምሳሌ:- በወሳኝ ስራዎች መሰረት በተለየው የክህሎት ክፍተት መሰረት በሙያ ደረጃና የብቃት አሀድ

አንጻር የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ( ከታች ያለው ስእል)

9

Page 11: Competence Manual

10

Page 12: Competence Manual

5.1. የተለዩ ክፍተቶችን መሙላት የሚያስችል የብቃት አሃድ / elements መምረጥ

5.2. የተመረጠውን የብቃት አሃድ ሊያስጨብጥ የሚችል የስልጠና መርሀ ግብር ማዘጋጀት

መግለጫ :- ከላይ ከምሳሌው ማየት እንደሚቻለው የባህላዊ ሸመናው ዘርፍ በገበያ ላይ ተወዳዳሪ

መሆን ያልቻለበት ምክንያት ብትን የሸሚዝ ጨርቅ ማምረት ባለመቻሉ ምክንያት የብትን ሸሚዝ ጨርቅ

ማምረት ስራ እንደ ክፍተት ተወስዷል።

ይህን ወሳኝ ወሳኝ ስራ ለማከናወን የክህሎት ክፍተት ብቻ ሳይሆን የቴክኖሎጂ ክፍተትም ( ብትን

ሸሚዝ ለማምረት የሚያስፈልገው ሪድ አለመኖሩ) ተለይቷል።

ስለዚህ የክህሎትና የቴክኖሎጂ ክፍተቶች አብዛኛውን ጊዜ ጎን ለጎን የሚሄዱ መሆኑን ግንዛቤ

መውሰድ ተገቢ ይሆናል።

5.3. የስልጠና/ አቅም ግንባታ መርሀግብሩን ለመተግበር የሚያስችል ዝግጅትብቃታቸው በተረጋገጠ

መምህር ወይም ባለሙያ ማድረግ ( በስራ ቦታ ወይም በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት)

5.4. መርሀ ግብሩን ብቃቱ በተረጋገጠ መምህር ወይም ባለሙያ የቴክኒካል ክህሎት ክፍተት ለታዩባቸው

ሰራተኞች መስጠት

5.5. የቴክኒካል ክህሎት ክፍተቱን መሙላት የሚያስችል አቅም መፈጠሩን በምዘና ማረጋገጥ

5.5.1. ለተለየው የቴክኒካል ክህሎት ክፍተት መሟላት ( በብቃት አሃድ) የምዘና መሳሪያ

መለየት/ማዘጋጀት

5.5.2. የስራ ላይ ምዘና ማካሄድ

5.5.3. አስፈላጊ ከሆነ የምስክር ወረቀት መስጠት

5.6. የክህሎት አቅም ግንባታውን ውጤት መገምገም

የክህሎት አቅም ግንባታ ዋና የማስፈጸሚያ ስልት የስልጠና ፕሮግራሞችን በማዘጋጀትና በመስጠት ነው።

የስልጠናን ፋይዳ ደግሞ ከታለመለት ግብ ስኬታማነት አንጻር መገምገም ያስፈጋል።

የስልጠና ፋይዳ ግምገማን በአራት ዋና ዋና እርከኖች ማከናወን ይቻላል እነሱም:-

5.6.1. ሰልጣኙ ፕሮግራሙ እንደተጀመረ ያለውን ተነሳሽነት/motivation

11

Page 13: Competence Manual

ይህ ግምገማ የተለያዩ መጠይቆችን በቃል ወይም በጽሁፍ በማቅረብ የሚከናወን ሲሆን ይህም

ከመጠይቆቹ በሚገኙ ግብረመልሶች አማካይነት በፕሮግራሙ አሰጣጥ ላይ ቀጣይ ማሻሻዎችን

ለማድረግ ያስችላል

5.6.2. በፕሮግራሙ ማጠናቀቂያ ላይ ሰልጣኝ ሰራተኛው የተላለፈለትን ክሀሎት በሚገባ ለመጨበጡ

የሚደረግ ግመገማሐ.

5.6.3. ሰልጣኝ ሰራተኛው ወደ ስራ ገበታው ከተመለሰ በኋላ የተላለፈለትን ክሀሎት በስራ ላይ

መተገበሩ/application

5.6.4. ሰልጣኝ ሰራተኛው የተላለፈለትን ክህሎት በመተገበሩ ምክንያት በስራው ላይ ያሳየውን ለውጥ

ከምርታማነት አንጻር መገመገም። ይህ ግምገማ ሰልጣኝ ሰራተኛው የክህሎት ክፍተቱ ከመሟላቱ በፊት

የነበረውን የምርታማነት ውጤትን ከክህሎት አቅም ግንባታው በኋላ ካለው ምርታማነት ጋር በማነጻጸር

የሚከናወን ይሆናል።

5.6.5. በማጠቃለያም ስለ ተለየው የክህሎት ክፍተትና ስለ ተወሰደው የአቅም ግንባታ ፕሮግራምና

ፕሮግራሙ በምርታማነት ላይ ያመጣውን ለውጥ በፓኬጅ መልክ ቀምሮ ለሌሎች ተመሳሳይ የቴክኒካለ

ክህሎት ክፍተት ላለባቸው ኢንተርፕራይዞች ማስተላለፍ ያስፈልጋል።

12

Page 14: Competence Manual

6. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ አተገባበር ስልት

ያለንን ሀብት በአግባቡ ስራ ላይ ላይ ለማዋልና የአቅም ውስንነትን ትኩረት ውስጥ በማሰገባት የክህሎት አቅም

ግነባታ ፕሮግራሞቸን በምናካሄድበት ወቅት በአካባቢያችን የትኩረት ኢንዱስትሪዎች መሰረትና በኢንተርፕራይዞች

ውስጥ ባሉ ለተወዳዳሪነት ወሳኝ በሆኑ የስራ ሂደቶች ላይ በሚያጋጥሙ የክህሎት ክፍተቶች ላይ ማተኮር

ይኖርብናል።

በተጨማሪም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የእድገት ደረጃ መሰረት በከፍተኛ የእድገት እርከን ላይ ባሉት

ላይ ትኩረት በማድረግ የአቅም ግንባታውን ማካሄድ ስልታዊ ጠቄሜታ እንዳለው ይታመናል።

የክህሎት አቅም ግንባታን ቅድሚያ አሰጣጥ ከኢንተርፕራይዞች ፍላጎትና ካለው የክህሎት ደረጃና ከስራ ሂደቱ

ወሳኝነትና አስፈላጊነት አንጻር ለመገምገም ይቻል ዘንድ:-

እያንዳንዱን ስራ ከአስቸጋሪነት/difficulty ከአስፈላጊነት/importance ከድገግሞሽ/frequency (DIF)

አንጻር መተንተንና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን መወሰን ያስፈልጋል። ይህም ውስን ሀብትን በማያስፈልጉ የስልጠና

ፕሮግሮሞች ላይ እንዳናባክንና በተወሰኑ ችግሮች ላይ ብቻ በማተኮር ውጤታማ እንድንሆን ይረዳናል።

ከዚህ በታች በሳጥኖች ውስጥ የተመለከተው በስራው የአስፈላጊነት ደረጃና ባለው የክህሎት ደረጃ መሰረት

እንዴት ቅድሚያ መስጠት እንደሚኖርብን ያሳየናል

7. የባለ ድርሻ አካላት ሚና

የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ስራ የአንድ አካል የስራ ድርሻ አይደለም። ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ባለድርሻዎች

በሰራው ላይ የተለያዩ ድርሻዎችን በማበርከት መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል።

13

በጣም አስፈላጊ ስራና የተወሰነ

ክህሎት = ከፍተኛ ቅድሚያ

የሚሰጠው

በጣም አስፈላጊ ስራ እና በቂ

ክህሎት = ዝቅተኛ ቅድሚያ

የሚሰጠው

አስፈላጊነቱ ዝቅተኛ የሆነ ስራና

የተወሰነ ክህሎት= ዝቅተኛ

ቅድሚያ የሚሰጠው

አስፈላጊነቱ ዝቅተኛ የሆነ ስራ እና

በቂ ክህሎት = ቅድሚያ

የማይሰጠው

የስራውአስፈላጊነት

የክህሎት ደረጃ

Page 15: Competence Manual

ሀ. የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ

በዘርፉ ተወዳዳሪ ሊያደርጉት ያልቻሉና ከቴክኒካል ክህሎት ክፍተት ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን

ችግሮችና ወሳኝ ስራዎችን በአካባቢው ካለ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም ጋር

በመመካከር መወሰን

በኢንተርፐራይዙ ውስጥ የሰራተኛውን ቴክኒካል ክህሎት ክፍተት ለመለየት የሚረዳ የክህሎት

ሴሌዳ በሚታይ ቦታ ላይ መለጠፍና ክፍተቶቹን ከሰራተኛው አፈጻጻም አንጻር በየጊዜው

ከየቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም ጋር በመሆን መሙላት

በቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታው ላይ እንዲሳተፉ ሰራተኞችን ማበረታታት፣ መመደብና ጊዜ

መስጠት

ለቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን እንደአስፈላጊነቱ ማሟላት

ለ. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም

ለኢንተርፐራይዞች ምርታማነት እንቅፋት የሚሆኑ ከ ቴክኒካል ክህሎት ጋር ተዛማጀነት ያላቸውን

ጉዳዮችን መለየትና መተንተን፣

አለምአቀፍ ምርጥ ተመክሮዎችን በመዳሰስ ተግባራዊ ማድረግ፣

ተለይተው የታወቁትን ችግሮች/ክፍተቶች ለመቅረፍ የስልጠና ፕሮግራም በማዘጋጀት

ለኢንተርፕራይዞች ሰራተኞች ስልጠና መስጠት፣

ከኢንተርፕራይዞች ለአሰልጣኝነት ብቁ ለሆኑ ሰራተኞች የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት የስራ

ባልደረቦቻቸውን እንዲያሰለጥኑ ማድረግ፣

የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ የተቋሙ አንድ የስራ ድርሻ አድርጎ በመውሰድ በአመታዊ የስራ

እቅድ ውስጥ ማካተትና አስፈላጊውን በጀት መመደብ

በዘርፉ ተወዳዳሪ ሊያደርጉት ያልቻሉና ከቴክኒካል ክህሎት ክፍተት ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን

ችግሮችና ወሳኝ ስራዎችን የሚለዩ መምህራንን መመደብና የስራ ዝርዝር ማዘጋጀት

መምህራን ይህንኑን ስራ እንደመደበኛ ስራቸው አድርገው እንዲያከናውኑ ማበረታታትና መደገፍ

ከአንተርፕራይዙ ጋር በመሆን የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን ማከናወን

ሐ. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም መምህር

14

Page 16: Competence Manual

የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታውን ከመደበኛ የማሰልጠን ስራ እኩል ጎን ለጎን ለማከናወን

ዝግጁ መሆን ለፕሮግራሙም ዝርዝር እቅድ ማዘጋጀት

የኢንተርፕራይዞችን የክህሎት ከፍተት መለየትና በዚያው መሰረት የአቅም ግንባታ ስራዎችን በጋራ

በመቅረጽና በመስጠት ሙሉ ተሳትፎ ማድረግ

የአቅም ግንባታ ስራዎችን ወይም የስልጠና ፕሮግራሞችን በየእርከኖቹ ግምገማ ማካሄድና

የተገኙትን ውጠቶች መቀመርና ሪፖርት ማድረግ

መ. የኢንተርፕራይዙ ሰራተኞች

በኢንተርፕራይዙ ወሳኝ ስራ አንጻር ያለበትን የቴክኒካል ክህሎት ክፍተት ለማሳወቅ ግልጽና ዝግጁ መሆን

በሚሰጠው የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ፕሮግራሞች ላይ በንቃት መሳተፍ

ከቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታው ፕሮግራም የተላለፈለትን ክህሎት በቀጥታ በስራው ላይ ማዋልና

ለውጥ ማሰመዝገብ

8. ለቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ተግባሪዎች አጠቃላይ ስልት

1. በተሰማሩበት ሙያ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ተሞክሮ ዘወትር የመቀመር ልምድ ማዳበር

2. የጎደለውን ነገር በመለየት፤ መሻሻል ያስፈልገዋል ተብሎ ለምታስበው ክህሎት ዘወትር ማሰብና ምርምር

ማድረግ

3. በሙያው ላይ የተሻለ ክህሎት ያላቸውን ሰራተኞች መረጃ ቋት መያዝ መቻል

15

Page 17: Competence Manual

4. የ ቴክኒካል ክህሎት ክፍተት መለያ ዘዴዎችን ማሻሻል፣ ማዳበርና ተግባር ላይ ማዋል

5. የ ቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታው በትኩረት ኢንዱስትሪዎች ላይና ወሳኝ በሆኑ ሰራዎች ላይ ብቻ

አንዲያተኩሩ ማድረግ

6. ሊለካ የሚችል፣ውጤታማ፣ተጨባጭ፣እና ጊዜ የተቆረጠለት የ ቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ወይም

የስልጠና ፕሮግራሞች መንደፍ

7. ኢኮኖሚያዊ የሆነ አግባብነት ያለውና ከስራው ጋር ቀጥተኛ አስተዋጽዎ የሚያደርጉ ፕሮግራሞችን

መቅረጽና መተግበር

8. በክትትልና ድጋፍ ወቅት የሚገኙ ግብረመልሶችን በአግባቡ መተንተንን መቀመር

9. በኢንተርፕራይዞች የሚታዩ ችግሮች የ ቴክኒካል ክህሎት ክፍቶት ብቻ ባለ መሆናቸው ከ ቴክኒካል ክህሎት

ጋር ቁርኝት ያላቸውን የስራ ፈጣሪነት፣የቴክኖሎጂና የጥራትና ምርታማነት ክፍተቶችን ዘወትር አብሮ ማየት

16