27
ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ - ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ? / ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ? ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳ - “ ሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ( ሳሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ) ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ( ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ) - ሳሳሳሳሳ - ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ - ሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳ ( ሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ) ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ - ሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ - ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ( ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳ ) ሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳ ሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳ . 14:6 ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳሳሳ ሳሳሳሳሳ ሳሳ ሳሳ ?

Science and Rel

Embed Size (px)

DESCRIPTION

science and reli

Citation preview

Page 1: Science and Rel

ሳይንስና ሃይማኖት - እንዴት ይተያያሉ?ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ

ሃይማኖት ምንድን ነው? ሃይማኖት ማለት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ግንኙነት ነው፡፡ ሃይማኖተኛ ሰው ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ያለው ሰው ማለት ነው፡፡ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም የሆነ ግንኙነትና ኅብረት ሊኖረው እንደሚገባ ሲያሳስብ እንዲህ ሲል ጽፏል፡- “የማንም ዓይን ያለ እግዚአብሔር (ከእግዚአብሔር ተለይቶ) ሊያይ አይገባውም፣ እጅም ያለ እርሱ መንቀሳቀስ የለበትም፣ ልብም እግዚአብሔርን የማያስደስተውን ነገር ማሰብ የለበትም፡፡” ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ያለው አንድነት (ግንኙነት፣ ኅብረት) - ሃይማኖት - በቅዱስ መጽሐፍ ከጋብቻ ጋር - የበጉ ሠርግ፣ ወልደ እግዚአብሔር ከምታምን ነፍስ ጋር ከሚያደርገው ረቂቅ ተዋሕዶ ጋር ተነጻጽሮ የተገለጸው ያለ ምክንያት አይደለም፤ ሃይማኖት ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ተዋሕዶአዊ አንድነት ስለሆነ ነው፡፡

ሃይማኖት እግዚአብሔር ራሱን ለሰው ልጅ የገለጠው መገለጥ ነው፡፡ ሃይማኖት የሰው ልጅ ሊቀበለው በሚችለው መጠን እግዚአብሔር ስለ ራሱ ማንነት ለእኛ የገለጠው እውነታ ነው፡፡ እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ፣ ባሕርዩም የማይለወጥ ስለ ሆነ ሃይማኖት (ይህ አምላክ ስለ ራሱ የገለጠው መገለጥ) አንድና የማይለዋወጥ ነው፡፡ 

እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው በውስጡ የፈጠረውን እርሱን እንዲፈልግና ሕሊናው ወደ እርሱ እንዲሳብ አድርጐ ነው የፈጠረው፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ሰው በውስጡ ፈጣሪውን የመፈለግ ዝንባሌ አለው፡፡ እግዚአብሔርን ተመራምሮ የደረሰበትና ያገኘው ሰው ሳይሆን መጀመሪያ ራሱን ለፍጥረቱ የገለጠው እግዚአብሔር ነው፡፡ ሰው በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል የመፈጠሩ አንዱ ምሥጢርም ይኽ ነው፡፤ በውስጣችን ያ የእግዚአብሔር አርአያ ስላለ ያ አርአያ ወደ ዋናው መልክ - ወደ አስገኚው ወደ እግዚአብሔር - ይመራናል፡፡ ሃይማኖት የለንም የሚሉ ሰዎች ሳይቀሩ ዓይነቱና መልኩ ይለያይ እንጂ በሆነ ነገር ማመናቸው አይቀርም፡፡ ዛሬ ክርስትናውን ችላ እያለ በመጣው በምዕራቡ ዓለም ሕዝብ ዘንድ በሚገርም ሁኔታ ሌሎች እምነቶች (መተታ መተቶችንና “ከዋክብት ቆጠራን” ጨምሮ) ቀስ በቀስ ቦታውን እየያዙ መጥተዋል፡፡ “ፍካሬ ከዋክብት” በብዙ ጋዜጦችና መጽሔቶች የክብር ቦታውን ይዞ ይገኛል፡፡ ይኽ የሚያሳየን ሰው በመንገድ ላይ እየተሰናከለ ቢቀርም በውስጡ ግን አምላኩን እንዲፈልግ የሚያደርግ ነገር አብሮት ያለ መሆኑን ግን ያሳየናል፡፡ ቀድሞ በፍልስፍናው ዓለም ብዙ ርቀት የተጓዘውና ጠልቆ ገብቶ የነበረውና ኋላ ወደ ክርስትና ተመልሶ ብዙ ሥራዎችን የሠራው የሰሜን አፍሪቃዋ የሂፖ ጳጳስ የነበረው አውግስጢኖስ “ልባችን አንተን ለማምለክ የተፈጠረ ስለሆነ አንተን እስከሚያገኝ ድረስ ዕረፍት የለውም” ሲል እንደ ተናገረው በሃይማኖት ከእግዚአብሔር ጋር የማይኖር ሰው ዕረፍትና ሰላም የለውም፡፡ የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነውና፡፡ 

ሃይማኖት እግዚአብሔር ራሱን ያሳየበት መንገድ ነው፡፡ ሃይማኖት ወደ እርሱ ታደርሰን ዘንድ እግዚአብሔር የሰጠን መንገድ ናት፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” ያለው ለዚህ ነው፡፡ ዮሐ. 14:6 በነቢዩ በሆሴዕም “ይህን ነገር የሚያስተውል ጠቢብ፥ የሚያውቃትም አስተዋይ ማን ነው? የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነው፥ ጻድቃንም ይሄዱበታል፣ ተላላፊዎች ግን ይወድቁበታል” በማለት ሃይማኖትን “የእግዚአብሔር መንገድ” ሲል ገልጾአታል፡፡ ሆሴ. 14፡9 ይህቺ ሃይማኖትም ራሱ አካላዊ ቃል ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በቃልና በተግባር ያስተማራት፣ በሞቱና በትንሣኤው ያረጋገጣትና በቤተ ክርስቲያን ስትመሰከርና ስትጠበቅ የምትኖረው የክርስትና ሃይማኖት ናት፡፡ ሳይንስስ ምንድን ነው? ሳይንስ scire - ማወቅ ከሚለው የላቲን ግሥ እና scientia - ዕውቀት ከሚለው ስም የተገኘ ቃል ነው፡፡ "ሳይንስ በጥናት ወይም በልምድ የተገኘ ዕውቀት ነው፤ ወይም የተፈጥሮ ሕግጋትንና የአሠራራቸውን አጠቃላይ እውነታዎች የሚመለከትና የሚዳስስ ዕውቀት ነው፣ በተለይም ደግሞ በሳይንሳዊ መንገድ የተገኙና የተፈተሹ እና ቁሳዊውን ዓለም የተመለከቱ እውቀቶች ነው፡፡" ሆኖም ሳይንስ የሚለውን ቃል ሰዎች በተለያየ ሁኔታና ደረጃ ሲጠቀሙበትም ይታያሉ፡፡ ሳይንስ ጠቅለል ባለ መንገድ በሥነ ፍጥረት ያሉና የሚታዩ ክስተቶችን፣ ኩነቶችንና እርስ በርስ ያላቸውን ዝምድናና ሁናቴ በማየት፣ በሙከራና በመሳሰሉት መንገዶች በማጥናት ለማወቅ የሚደረግ ጥረትና በዚሁ መንገድ የሚታወቅ ዕውቀት ነው፡፡ ሳይንስ ዕውቀት የማግኛ መንገድ ነው፡፡ ይህም ተፈጥሯዊ ክስተቶችን ለመረዳትና ለመግለጽ ምልከታን፣ ሙከራንና ጥናትን ይጠቀማል፡፡ እንዲሁም ሳይንስን በዚህ መንገድ የተገኘ የዕውቀት ክምችትን (ዕውቀትን) ለማለትም ይጠቀሙበታል፡፡ ከአሥራ ሰባተኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ጀምሮ በተለይም በምዕራባውያን ዘንድ እያደገና ሥር እየሰደደ የሄደው በሥነ ፍጥረትና በሥነ ሕይወት ዙሪያ የሚደረገው ምርምር ሳይንስ የሚለውን ስያሜ በመያዝ ከሃይማኖት ጋር ባለው ዝምድናና ቁርኝት ዙሪያ የተለያዩ መልኮችን ይዞ ሲገለጥ ቆይቷል፡፡ በሳይንስና በሃይማኖት ግንኙነት ዙሪያ የተለያዩ አመለካቶች አሉ፡፡ እነዚህም በአንድ ጽንፍ "ሁለቱ እርስ በርስ ሊስማሙ የማይችሉ ተቃራኒዎች ናቸው" የሚሉት ሲሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ "አይጣሉም፣ ተስማሚና ተመጋጋቢ ናቸው" የሚሉ ሲሆኑ በእነዚህ ሁለት የዳርቻ አመለካከቶች ወይም አቋሞች መካከል ደግሞ የተለያዩ ዓይነት አመለካከቶች አሉ፡፡ በሃይማኖት ጎራ አለን ከሚሉት ሰዎች መካከል "ሳይንስ የክህደት ምንጭ ነው፣ ከሳይንስ አንዳችም ጥሩ ነገር ወይም እውነት አይገኝም፣ ሳይንስና ሃይማኖት ተቃራኒ ናቸው" የሚሉ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ በሳይንሱ ጎራ ደግሞ "ሃይማኖት የዓለም የችግሯ ሁሉ ምንጭ ነው፣ ስለዚህም ሃይማኖትን ማጥፋት የተሻለች ዓለም ለመፍጠር የመጀመሪያው እርምጃ ነው" የሚሉ አሉ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ በሃይማኖት አለን ከሚሉ ሰዎች ሳይንስ አመጣው የተባለውን ነገር ሁሉ የገባቸውንም ያልገባቸውንም እንደ ብርቅና ድንቅ ሰፍ ብለው የሚቀበሉና ዕፁብ ዕፁብ እያሉ የሚያዳንቁም አይጠፉም፡፡ 

በዚህ ጽሑፍ ለማየት የምንሞክረው በመጀመሪያ የሁለቱን ምንነትና የመሠረተ ነገራቸውን ልዩነት፣ ቀጥሎም በሁለቱም ዘንድ ያሉና የሚያመሳስሏቸውን ነገሮች፣ ሦስተኛ ሁለቱን የሚያጋጯቸውን ምክንያቶች እናያለን፡፡ አራተኛ አካዳሚያዊ ዕውቀት ካላቸው (ተምረዋል ከሚባሉ ወይም ተምረናል ከሚሉ) የቤተ ክርስቲያን ልጆች ምን ይጠበቃል? የሚለውን እናይና በማጠቃለያው እንደመድማለን፡፡

Page 2: Science and Rel

መነ ጽጌ«ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ ሄሮድስ ዘመን ከልጅሽ ጋር ከሀገር ሀገርስትሸሺ ከአንቺ ጋር መሰደዱን አሳስ

ቢ ፤ድንግል ሆይ ከዓይንሸ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ 

ፊት የወረደውንመሪር እንባ አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ረሐቡንና ጥሙን፣ ችግሩንና ሐዘኑን፣ ከእርሱ ጋርየደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ  ››አሳስቢ

ቅዳሴ ማርያም

ጽጌ ማለት አበባ ማለት ሲሆን ዘመነ ጽጌ ማለት የአበባ ዘመን ማለት ነው፡፡በሀገራችንመስከረም 25 ቀን ዘመነ ክረምት አልፎ መስከረም 26 ቀን ዘመነ ጽጌ ይጀምራል፡፡ ዘመኑ አበቦችየሚያብቡበትና ሜዳዎችንና ተራሮችን የሚያስጌጡበት ዘመን ነው፡፡ ፍሬ የተባለ ጌታን ያስገኘችእመቤታችን በአበባ ትመሰላለችና ዘመኑ የጌታንና የእመቤታችንን ነገር በአበባና በፍሬ ለመመሰልየተመቸ ነው፡፡ስለዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመስከረም 26 ቀንጀምሮ እስከ ኅዳር 6 ቀን ድረስ የጌታን እና የእመቤታችን ስደት ታስባለች፡፡በዚህ ዘመን ቅዱስ ያሬድ እና አባ ጽጌ ድንግል ባዘጋጇቸው ድርሰቶች የጌታችን እና የእመቤታችንስደት በማኅሌት ይታሰባል፤ ምስጋና እና ልመና ይቀርባል። ምእመናን ቤተክርስቲያናቸውበሠራችላቸው ሥርዓት መሠረት በፍቅርና በደስታ  ይዘክሩታል ፡፡ከዚህም በተጨማሪ ስደቱንለማሰብና በረከት ለማግኘት በርካታ ክርስቲያኖች  የአዋጅ ጾም

ባይሆንም በፈቃደኝነት ዘመኑንበጾም ያሳልፉታል፡፡የእመቤታችን ስደት የመጀመሪያው የአዲስ ኪዳን ስደት ነው፡፡ ከገነት የተሰደደውንአዳምን 

ወደ ቀደመ ክብሩና መንበሩ ከዚያም ወደ ሚበልጥ ክብር ለመመለስ የተወለደውጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገና ከህፃንንቱ ጀምሮ ስደትን እና መከራን ተቀብሏል፡፡ወንጌላዊው ማቴዎስ እንደጻፈው፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ጊዜሰብአ ሰገል «የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት አለ? በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንስግድለትመጥተናል» እያሉ በኮከብ እየተመሩ በመጡ ጊዜ በይሁዳ፣ በገሊላና በሰማርያ የሮማውያንተወካይ የነበረው ንጉሥ ሄሮድስ የጌታችን ንግሥና ምድራዊ ንግሥና መስሎት መንግስቴንሊቀማኝ ነው ብሎ ደነገጠ፡፡ ፊሪሳውያን «መሲህ ተወልዶ ከሮማውያን አገዛዝ ነጻ ያወጣናል፡፡»ብለው ያምኑ እንደነበር ስለሚያውቅም ይህ የተፈጸመ መስሎት ጭንቀቱ በረታ፡፡ የተወለደውንሕፃንም ለመግደል ተነሳ፡፡        ስለዚህም ሰብአ ሰገልን አስጠርቶ «ሂዱ ሕፃኑን ፈልጉ ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔምእንድሰግድለት ወደ እኔ ተመልሳችሁ ያለበትን ንገሩኝ» በማለት በሽንገላ ተናገራቸው፡፡ጠቢባኑምከሄሮድስ ከተለዩ በኋላ በኮከቡ እየተመሩ ጉዞአቸውን ቀጥለው ጌታችንን ከእናቱ ጋር 

Page 3: Science and Rel

አገኙት ፤ተንበርክከው ሰገዱለት፤ ወርቅ ፣ ዕጣን፣ ከርቤ እጅ መንሻ አቀረቡለት፡፡የእግዚአብሔር መልአክወደ ሄሮድስ እንዳይመለሱ፤ ነገር ግን መንገድ ቀይረው ወደ ሀገራቸው እንዲሄዱ በነገራቸውመሠረት በሌላ መንገድ ወደ መጡበት ተደብቀው ተመለሱ፡፡ሄሮድስም ሰብአ ሰገልእንደተሳለቁበት ባወቀ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ /ጌታን ለማስገደል በማሰብ /በአማካሪዎቹ ግፊት  ጌታበተወለደባት ከተማ በቤተልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን ከአንድ ዓመት ተኩል እስከ ሁለትዓመት የሚሆን ዕድሜ ያላቸውን ሕጻናትን አስገደለ፡፡ /ማቴ. 1.13-18

«እነርሱም( ሰብአ ሰገል ) ከሄዱ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ«ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነስ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሸ፤እስክነግርህም በዚያ ተቀመጥ አለው፡፡ » /ማቴ. 2 13  14/እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱንበሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ ልጄን ከግብጽ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብጽሔደ፡፡ ሄሮድስ እስኪሞት ድረስም በዚያ ኖረ፡፡ /ማቴ 2-13-15/ ተብሎ እንደተጻፈ ሁሉ፤ዮሴፍም ተነሣ፤ በዕድሜዋ በጣም ልጅ የነበረችው እመቤታችን ገና የተወለደውን ሕፃን አቅፋየምትቀመጥበት አህያም ተዘጋጀ፡፡ ጉዞአቸውን ጀመሩ፡፡ ከእስራኤል ወደ ግብጽ በእግር ለመሔድየሲናን በረሃ ማለፍ የግድ ነው፡፡ በዚያን ዘመን ከእስራኤል ወደ ግብጽ የሚወስዱ ሦስት የተለያዩመንገዶች ነበሩ፡፡ በሽፍቶች ላለመጠቃት መንገደኞች በቡድን በቡድን ሆነው በእነዚህ መንገዶችይሔዱ ነበር፡፡

እነርሱ ግን ንጉሥ ሔሮድስ ተከታትሎ ሊይዛቸው ስለሚችል በእነዚህ መንገዶች መሔድእንደሌለባቸው ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህም በእግዚአብሔር መልአክ እየተመሩ ባልታወቁ መንገዶችመሔድ ነበረባቸው፡፡ ለበርካታ ቀናትና ሳምንታት ሸለቆዎችን በመውረድና ኮረብታዎችን እየወጡጉዛአቸውን ቀጠሉ፡፡ ሽማግሌው አናጢ ዮሴፍ ከፊት ሁኖ አህያዋን ባልተስተካከለውና ማለቂያየሌለው በሚመስለው የበረሃ መንገድ ላይ ይመራ ነበር። ሰሎሜም ስንቃቸውን ይዛ ከኋላትከተል ነበር፡፡ በጣም አስቸጋሪ እና አስጨናቂ ጉዞ ነበር፡፡ ቀን ቀን የሚያቃጥለውን የፀሐይሐሩር ሌሊት ሌሊት ደግሞ የበረሀውን ውርጭ /ብርድ/ መታገል ነበረባቸው ምግባቸውንምበተአምራት ያገኙ ነበር፡፡

በመጨረሻም በመጽሐፈ ስንክሳር እንደተመዘገበው ግንቦት 24 ቀን ግብጽ ደረሱ፡፡በግብጽም ባሉ የተለያዩ ከተሞች ተዘዋወሩ፣ ጌታም በተለያዩ ቦታዎች በርካታ ተአምራትንአደረገ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ተቀብለው ሲያስተናግዷቸው ሌሎች ደግሞ አሳድደዋቸዋል፤ መከራንምአጽንተውባቸዋል፡፡ በዚሁ ስደታቸው ወቅት ጌታ እና እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያም መጥተውሀገራችንን ባርከዋል።ለሦስት ዓመት ተኩል ያህል በስደት ከቆዩ በኋላ ሄሮድስ ሞተ። ሄሮድስም ከሞተ በኋላ እነሆየጌታ መልአክ በግብጽ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ «የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፤ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ አለው፡፡ እርሱም ተነስቶ ሕጻኑንና እናቱን ይዞወደ እስራኤል ሀገር ገባ» ማቴ 2-19-21/፡፡

ቅዱስ ዮሴፍ ይህንን «.. ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ..» የሚለውን የመልአኩን ቃል የሰማውቁስቋም በምትባል በግብጽ ባለች ቦታ ነው፡፡በኋላ በዚህች ቦታ ላይ ቤተክርስቲያን

በእመቤታችን ስም ተሰርቶ ቅዳሴ ቤቱ ኅዳር 6 ቀን  ተከብሯል። ሃያ ሦስተኛው የእስክንድርያፓትርያርክ ቴዎፍሎስ /384-412 ዓ.ም/ ደግሞ በጌታ 

Page 4: Science and Rel

እና በእመቤታችን ስደት ወቅት የሆነውንነገር እንዲገለጥለት ለብዙ ጊዜ ጸሎት ካደረገ በኋላ ህዳር 6 ቀን እመቤታችን ተገልጣለትበጉዞው ወቅት የሆነውን ነገር ሁሉ ነግራዋለች፡፡ ስለዚህ ኅዳር 6 ቀን በሁሉም ምሥራቃውያንአብያተ ክርስቲያናት የእመቤታችን ከስደት የመመለሷ ነገር የሚታሰብበት  ሁኗል ፡፡ነቢያት ስለጌታ ትንቢት በመናገራቸው፣ እመቤታችን የጌታ እናት በመሆኗ፣ ሐዋርያት ስለጌታበማ

ስተማራቸው ተሰደዋል፡፡የጌታ አገልጋይም እናትም የሆነችው የእመቤታችን ስደት ግን. . .ከሁሉ የሚለይ ነው፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምንስደት ልዩ የሚያደርገው: - 

1.   ሕግን በመተላለፉ ከገነት ተሰዶ የነበረውን አዳምን ለመካስ የተደረገ በመሆኑ 2.   በግብጽ ነግሦ የነበረውን አምልኮት ጣኦት ለማሳደድ የተደረገ ስለሆነ የጌታችንና የእናቱስደት ልዩ ነው፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከናዝሬት ወደ ግብጽ ስትሰደድ የቀን ሐሩርየሌሊት ቁር አግኝቷታል፡፡ እሾህ እየወጋት እንቅፋት እየመታት ተጉዛለች /ተሰዳለች/፤ በስደቷምረሃብና ጥም፣ ችግርና መከራ ደርሶባታል፡፡ በበረሃው ወንበዴዎችን ባየች ጊዜም በስደት ከሄሮድስጭካኔ ከሀገር ያወጣሁትን ልጄን ይገድልብኛል ብላ መሪር እንባ አልቅሳለች፡፡በስደቷ ወቅትበደረሰባት ረሐብና ጥም የተነሣ ወደ መንደር ገብታ ብትለምን በችግር ምክንያት የሰው ፊትማየት ከእሳት የበለጠ ወላፈኑ ስለሚያቃጥል የሰው ፊት ገርፏታል፡፡ የትእማን ቤተሰቦችዘብተውባታል፡፡

«ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም የመጣው ሸክማችንን ሊሸከም ነውናውኃውን ለፍጥረታት የሚሰጥ እርሱ እየጠማው፤ እንስሳትን የሚመግብ እየራበው ምድርንበልምላሜ የሚያለብስ ተራቁቶ ፣የኛን ከገነት መሰደድ የመጣብንን ዕዳ ሊክስልን ከእናቱ ጋርተሰደደ፤ ድንግል ማርያምም የአምላክ እናት ሆና መከራን ቀመሰች፡፡ ጌታን አዝላ በረሐብ አለንጋተገረፈች፡፡        በመጨረሻ ግን ያ ሁሉ የመከራና የስቃይ ስደት ሲያበቃ «አንቺ ሱላማጢስ ሆይተመለሽ» ሲል በመኃልየ ማኀልይ ዘሰሎሞን ተነግሮ የነበረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ከዚያ ሁሉመከራና ስደት በኋላ ልጇን ይዛ ወደ ናዝሬት ተመልሳለች፡፡        የእመቤታችንን ስደት ስናስብ «ሲነቅፏችሁና ሲያሳድዷችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውንሁሉ በውሸት ሲነግሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ፡፡ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁሐሴትም አድርጉ፡፡ ከእናንተም በፊት የነበሩትን ነብያት እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና» /ማቴ 5-11/የሚለውን የስደት ዋጋ ጭምር እያሰብን መሆን ይገባል፡፡ይህንንም የእመቤታችንን ስደት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ድረስ በማኅሌትና በመዝሙር ትዘክራለች፡፡ ካህናቱም በዕለተ ሰንበት ከምሽትጀምረው በማኅሌትና በመዝሙር ምስለ ፍቁር ወልዳን /የልጇ እና የእርሷ/ ሥዕል ይዘውቤተክርስቲያኑን ይዞራሉ፡፡ይህም የእመቤታችንን ስደት ለማጠየቅ ነው፡፡ ሌሎችም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምናጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደረሰባቸውን መከራ ለማስታወስ የፍቃድ ጾምይጾማሉ፡፡እኛ ክርስቲያኖች በቅድስት ቤተክርስቲያን ተገኝተን በመንፈስ የሩቁን አቅርበን የእመቤታችንንስደት በእምነት እያየን በማኅሌተ ጽጌ ድርሰታችን በዜማ «መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ንጹሕ፣ፀአ

Page 5: Science and Rel

ዳ ፣ቀይህና ብሩህ የሚሆን ልጅሽን ታቅፈሽ ርኅሩኅ የሆነ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤልንአስከትለሽ ከሐዘናችንና ከችግራችን ታረጋጊን ዘንድ ፈጥነሽ ድረሽልን» ልንላት ያስፈልጋል፡፡በቅዳሴያችንም «ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ ሄሮድስ ዘመን ከልጅሽ ጋር ከሀገር ሀገር ስትሸሺከአንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ከዓይንሸ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊትየወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ፡፡ ድንግል ሆይ ረሐቡንና ጥሙን፣ ችግሩንና ሐዘኑን፣ ከእርሱ ጋርየደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ እንላለን፡፡

«ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ ሄሮድስ ዘመን ከልጅሽ ጋር ከሀገር ሀገር ስትሸሺ ከአንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ

ድንግል ሆይ ከዓይንሸ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ  አሳስቢ ፤ 

ድንግል ሆይ ረሐቡንና ጥሙን፣ ችግሩንና ሐዘኑን፣ ከእርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ  ››አሳስቢ

ቅዳሴ ማርያም

Page 6: Science and Rel

ዘ መነ ጽጌ

ከገነት የተሰደደውን አዳምን ወደ ቀደመ ክብሩና መንበሩ ከዚያም ወደ ሚበልጥ ክብር ለመመለስ የተወለደው

ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገና ከህፃንንቱ ጀምሮ ስደትን እና መከራን ተቀብሏል፡፡

ጌታ ሲወለድ ሰብአ ሰገል « የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት አለ? በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንስግድለት

መጥተናል» እያሉ በኮከብ እየተመሩ በመጡ ጊዜ በይሁዳ፣ በገሊላና በሰማርያ የሮማውያን ተወካይ የነበረው

ንጉሥ ሄሮድስ የጌታችን ንግሥና ምድራዊ ንግሥና መስሎት መንግስቴን ሊቀማኝ ነው ብሎ ደነገጠ፡፡ ፊሪሳውያን

« መሲህ ተወልዶ ከሮማውያን አገዛዝ ነጻ ያወጣናል፡፡» ብለው ያምኑ እንደነበር ስለሚያውቅም ይህ የተፈጸመ

መስሎትጭንቀቱ በረታ፡፡ የተወለደውን ሕፃንም ለመግደል ተነሳ፡፡

ስለዚህም ሰብአ ሰገልን አስጠርቶ « ሂዱ ሕፃኑን ፈልጉ ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔም እንድሰግድለት ወደ እኔ

ተመልሳችሁ ያለበትን ንገሩኝ» በማለት በሽንገላ ተናገራቸው፡፡

ጠቢባኑም ከሄሮድስ ከተለዩ በኋላ በኮከቡ እየተመሩ ጉዞአቸውን ቀጥለው ጌታችንን ከእናቱ ጋር አገኙት ፤

ተንበርክከው ሰገዱለት፤ ወርቅ ፣ ዕጣን፣ ከርቤ እጅ መንሻ አቀረቡለት፡፡

የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ሄሮድስ እንዳይመለሱ፤ ነገር ግን መንገድ ቀይረው ወደ ሀገራቸው እንዲሄዱ

በነገራቸውመሠረት በሌላ መንገድ ወደ መጡበት ተደብቀው ተመለሱ፡፡

« እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ « ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና

ተነስ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሸ፤ እስክነግርህም በዚያ ተቀመጥ አለው፡፡ » /ማቴ. 2 13  14/

ዮሴፍም ተነሣ፤ በዕድሜዋ በጣም ልጅ የነበረችው እመቤታችን ገና የተወለደውን ሕፃን አቅፋ የምትቀመጥበት

አህያም ተዘጋጀ፡፡ ጉዞአቸውን ጀመሩ፡፡ ከእስራኤል ወደ ግብጽ በእግር ለመሔድ የሲናን በረሃ ማለፍ የግድ ነው፡፡

በዚያን ዘመን ከእስራኤል ወደ ግብጽ የሚወስዱ ሦስት የተለያዩ መንገዶች ነበሩ፡፡ በሽፍቶች ላለመጠቃት

መንገደኞች በቡድን በቡድን ሆነው በእነዚህ መንገዶች ይሔዱ ነበር፡፡

እነርሱ ግን ንጉሥሔሮድስ ተከታትሎ ሊይዛቸው ስለሚችል በእነዚህ መንገዶች መሔድ እንደሌለባቸው ግልጽ

ነው፡፡ ስለዚህም በእግዚአብሔር መልአክ እየተመሩ ባልታወቁ መንገዶች መሔድ ነበረባቸው፡፡ ለበርካታ ቀናትና

ሳምንታት ሸለቆዎችን በመውረድና ኮረብታዎችን እየወጡ ጉዛአቸውን ቀጠሉ፡፡ ሽማግሌው አናጢ ዮሴፍ ከፊት

ሁኖ አህያዋን ባልተስተካከለውና ማለቂያ የሌለው በሚመስለው የበረሃ መንገድ ላይ ይመራ ነበር። ሰሎሜም

ስንቃቸውን ይዛ ከኋላ ትከተል ነበር፡፡ በጣም አስቸጋሪ እና አስጨናቂ ጉዞ ነበር፡፡ ቀን ቀን የሚያቃጥለውን የፀሐይ

ሐሩር ሌሊት ሌሊት ደግሞ የበረሀውን ውርጭ /ብርድ/ መታገል ነበረባቸው ምግባቸውንም በተአምራት ያገኙ

ነበር፡፡

Page 7: Science and Rel

በመጨረሻም በመጽሐፈ ስንክሳር እንደተመዘገበው ግንቦት 24 ቀን ግብጽ ደረሱ፡፡ በግብጽም ባሉ የተለያዩ

ከተሞች ተዘዋወሩ፣ ጌታም በተለያዩ ቦታዎች በርካታ ተአምራትን አደረገ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ተቀብለው

ሲያስተናግዷቸው ሌሎች ደግሞ አሳደዋቸዋል፤ መከራንም አጽንተውባቸዋል፡፡ በዚሁ ስድታቸው ወቅት ጌታ እና

እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያምመጥው ሀገራችንን ባርከዋል።

ለሦስት ዓመት ተኩል ያህል በስደት ከቆዩ በኋላ ሄሮድስ ሞተ። ሄሮድስም ከሞተ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ

በግብጽ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ « የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል

ሀገር ሂድ አለው፡፡ እርሱም ተነስቶ ሕጻኑንና እናቱን ይዞ ወደ እስራኤል ሀገር ገባ» ማቴ 2-19-21/

ቅዱስ ዮሴፍ ይህንን «.. ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ..» የሚለውን የመልአኩን ቃል የሰማው ቁስቋም በምትባል

በግብጽ ባለች ቦታ ነው፡፡

በኋላ በዚህች ቦታ ላይ የእመቤታችን ቤተክርስቲያን ተሰርቶ ቅዳሴ ቤቱ ኅዳር 6 ቀን  ከብሯል። ሃያ ሦስተኛው

የእስክንድርያ ፓትርያርክ ቴዎፈሎስ /384-412 ዓ.ም/ ደግሞ በጌታ እና በእመቤታችን ስደት ወቅት የሆነውን

ነገር እንዲገለጥለት ለብዙ ጊዜ ጸሎት ካደረገ በኋላ ህዳር 6 ቀን እመቤታችን ተገልጣለት በጉዞው ወቅት

የሆነውን ነገር ሁሉ ነግራዋለች፡፡ ስለዚህ ኅዳር 6 ቀን በሁሉም ምሥራቃውያን አብያተ ክርስቲያናት የእመቤታችን

ከስደት የመመለሷ ነገር የሚታሰብበት ሁኗል፡፡

በሀገራችን መስከረም 25 ቀን ዘመነ ክረምት አልፎ መስከረም 26 ቀን ዘመነ ጽጌ ይጀምራል፡፡ ጽጌ ማለት አበባ

ማለት ሲሆን ዘመነ ጽጌ ማለት የአበባ ዘመን ማለት ነው፡፡ ዘመኑ አበቦች የሚያብቡበትና ሜዳዎችንና ተራሮችን

የሚያስጌጡበት ዘመን ነው፡፡ ፍሬ የተባለ ጌታን ያስገኘች እመቤታችን በአበባ ትመሰላለችና ዘመኑ የጌታንና

የእመቤታችንን ነገር በአበባና በፍሬ ለመመሰል የተመቸ ነው፡፡

ስለዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመስከረም 26 ቀን ጀምሮ እስከ ኅዳር 6 ቀን ድረስ

የጌታን እና የእመቤታችን ስደት ታስባለች፡፡

በዚህ ዘመን ቅዱስ ያሬድ እና አባ ጽጌ ድንግል ባዘጋጇቸው ድርሰቶች የጌታችን እና የእመቤታችን ስደት በማኅሌት

ይታሰባል፤ ምስጋና እና ልመና ይቀርባል። እነዚህን ለየሳምንቱ በሚዘጋጁት ትምህርቶች እናቀርባቸዋለን፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ስደቱን ለማሰብና በረከት ለማገኘት በርካታ ክርስቲያኖች ዘመኑን በጾም ያሳልፉታል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በማቴዎስ ወንጌል ትርጓሜው /Homilies on the Gospel of Saint

Mathew/ ይህንን ስደት አስመልክቶ ያስተማረውን ትምህርት ከዚህ ቀጥለን አቅርበናል፡፡

ሰብአ ሰገልም ከሄዱ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ በህልም ለዮሴፍ ተገልጾ፡- ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው

ይፈልገዋልና ተነሳና ሕፃኑን ከእናቱ ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ እስክነግርህም ድረስ በዚህ ተቀመጥ አለው እርሱም 

Page 8: Science and Rel

ተነስቶ  ሕፃኑና እናቱን ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ ልጄን  ከግብፅ ጠራሁት የተባለው ይፈጸም ዘንድ ወደ ግብፅ

ሄደ። ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።

ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደተሳለቁበት ባወቀ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ / ጌታን ለማስገደል በማሰብ / ጌታ

በተወለደባት ከተማ በቤተልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን ሕጻናትን አስገደለ፡፡ /ማቴ. 1.13-18/

እዚህ ላይ ሕፃኑን በተመለከተና ሰብአ ሰገልን በተመለከተ ልንጠይቃቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፡፡ ለምን ሰብአ

ሰገልም፣ ሕፃኑም /ጌታም/ በዚያው አልቆዩም? ለምን እነርሱ እንደ ተሳዳጅ /fugitive/ በድብቅ ወደ ፋርስ፣

እርሱም ከእናቱ ጋር ወደ ግብፅ ሄዱ?

ከዚህ ሌላ ምን መደረግ ነበረበት? ጌታ በሄሮድስ እጅ መውደቅና ከዚያ አለመገደል ነበረበት? እንዲህ

ቢያደርግም ኖሮ ሥጋን መዋሃዱ ግልጽ አይሆንም ነበር፡፡ የክርስቶስ የማዳን ሥራም አይታመንም ነበር፡፡

ሥጋን መዋሃዱን የሚያሳዩ ይህን የመሳሰሉ በርካታ ነገሮች ተደርገው፣ ሥጋን ለበሰ /ተዋሃደ/ መባሉ ተረት

/ውሸት/ ነው የሚሉ ካሉ ሁሉን ነገር እንደ አምላክነቱ ብቻ ቢያደርገውማ ከእነዚህ የሚበልጡ ብዙዎች በተሳሳቱ

ነበር፡፡

ሰብአ ሰገልንም በፍጥነት የላካቸው አንደኛ ለፋርስ ሰዎች መምሀራን እንዲሆኑ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ጌታን

ለማስገደል ላሰበው ሄሮድስ እየሞከረ ያለው የማይቻል ነገርን መሆኑን አስረድቶ የሄሮድስን እብደት ለማቆምና

ንዴቱን አስታግሶ ከከንቱ ድካሙ እንዲያርፍ ለማድረግ ነበር፡፡

ምክንያቱም አምላካችን ጠላቶቹን በግልጽ እና በኃይል ማስገዛት ብቻ ሳይሆን በቀላል እና ትንሽ በሚመስሉ

ነገሮች ማሳመንም፣ ያውቅበታል፡፡

ለምሳሌ ግብጻውያንን በግልጽ /በኃይል/ ንብረታቸውን ለእስራኤል እንዲያስረክቡ ማድረግ ሲችል እርሱ ግን

በጥበብ ያለ ጦርነት ይህንን እንዲያደርጉ አድርጎአቸል፡፡ ይህም አድራጎቱ ከሌሎቹ ተአምራት ባልተናነሰ ሁኔታ

በጠላቶቹ ዘንድ የሚፈራ አድርጎታል፡፡

ለምሳሌ ፍልስጤማውያን ታቦተ ጽዮንን ማርከው በመውሰዳቸው በተቀጠቀጡ ጊዜ የሀገራቸውን ጠቢባን

ከእግዚአብሔር ጋር ለመዋጋት እንዳይሞክሩ በነገሯቸው ጊዜ ከሌሎች ተአምራት ጋር ይህንን እግዚአብሔር

በሥውር የሠራውንምሥራ አንስተውታል፡፡ በግልጽ ከተደረጉት የተለየ አድርገው አላዩትም፡፡ 1 ኛ ሳሙ. 6-6

በዚህ ጊዜም የተደረገው ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ደም የጠማውን ነፍሰ ገዳይ ሊያስደንቅ የሚችል ነገር ነበር፡፡

ሄሮድስ ሊያስብ የሚገባው እንዲህ ነበር፡፡ ሰብአ ሰገል እንደካዱት፣ እንደተናቀና መሳቂያ መሳለቂያ እንደሆነ ባወቀ

ጊዜመደንገጥ ትንፋሹ መቆም ነበረበት፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ካላሻሉት /ካላስተካከሉት/ ግን እርሱን ከጥፋቱ

ለመመለስ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረገ እግዚአብሔር በእርሱ ጥፋት ሊጠየቅ አይችልም፡፡ ሄሮድስ ከዚህ በኋላ

Page 9: Science and Rel

የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ያደረገው የእብደቱ ብዛት እነዚህ ሁሉ እውነተኛ ግልጽ ነገሮች እንዲያሳምኑት ስላላደረገ

ነው፡፡ ስለዚህ ከጥፋቱ መመለስ አልቻለም፡፡ በክፋቱ ስለ ቀጠለበትም ስለ ሞኝነቱ የከፋ ቅጣት ተቀብሏል፡፡

ሕፃኑ ለምን ወደ ግብጽ ሄደ? የመጀመሪያውን ምክንያት ወንጌላዊው ራሱ በግልጽ ይነግረናል፤ « ልጄን ከግብጽ

ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብጽ ሄደ» /ማቴ. 1-15/

ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ድርጊት ለዓለምመልካም ተስፋ ተሰብኳል፡፡ በዚያን ጊዜ በዓለም ካለው ቦታ ሁሉ

በከፋ ሁኔታ ባቢሎን /ፋርስ/ እና ግብጽ በእምነተ ቢስነት / በአምላክ አልባነት/ ነበልባል ተቃጥለው ነበር፡፡

እርሱም ከመጀመሪያው ሁለቱንም እንደሚያስተካክል ምልክት ሰጥቶ ሰዎችን ማዳኑ /ስጦታዎቹ/ ለዓለሙ በሙሉ

እንደሆኑ አውቀው በተስፋ እንዲጠብቁ አደረጋቸው፡፡ ለዚህም ወደ አንዱ / ባቢሎን፣ ፋርስ/ ሰብአ ሰገልን ላከ፣

ሌላውን /ግብጽን/ ራሱ ከእናቱ ጋር ጎበኘ፡፡

ከዚህም ሌላ በዚህ የምንማረው ሌላ ትምህርት አለ፤ ከፍ ያለ ጽናት ሊኖረን እንደሚገባ፡፡ ይህ ምን ዓይነት ነው?

ክፉ ሃሳብ /ተንኮል/ እና ክፉ ድርጊት ገና በመጠቅለያ ካለበት ጊዜ ጀምሮ በእርሱ ላይ እንደሆነ ተመልከቱ፡፡

በልደቱ ጊዜ መጀመሪያ ክፉ ነፍሰ ገዳይ፣ ተነሳበት ከዚያም ስደት እና ሀገርን ትቶ መሄድ ተከተለ፡፡ ያለ ምንም

ጥፋትና በደል ከቤቷ እንኳን ርቃ ተጉዛ የማታውቀው እናቱ ወደ አረመኔዎች /barbarians/ ሃገር ተሰደደች፡፡

አስጨናቂና አስቸጋሪ የሆነ ረጅም ጉዞ እንድታደርግ ታዘዘች፡፡ ይህንን የሰማ ሰውመንፈሳዊ አገልግሎት ሲፈጽም

አስጨናቂ ችግሮችና ህመሞች ቢደርሱበትና ህመሞች ቢያጋጥሙትመሸበር የለበትም፡፡

« የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ስለፈጸምኩመሸለምመከበርና ታዋቂ መሆን ሲገባኝ ለምን ይህ ሆነ?» ማለትም

የለበትም፤ ነገር ግን ሁላችንም ይህንን እንደ ምሳሌ ወስደን ሁሉን ነገር በደስታ መቀበል አለብን፡፡ መንፈሳዊ

ነገሮች ባሉበት ሁሉ ተቃዋሚ እንደማይጠፋ እና የመንፈሳዊ ነገሮች ሂደትም ይህመሆኑንምመረዳት አለብን፡፡

ቢያንስ ይህ ነገር የሆነው በሕፃኑና በእናቱ ብቻ ላይ ሳይሆን በሰብአ ሰገልም ላይ መሆኑን እናስተውል፡፡ እነርሱም

እንደ ተሳዳጅ /fugitive/ ሆነው በምስጢር እንዲሸሹ ሆነዋል፡፡

ሌላም አስደናቂ ነገር ተመልከቱ፡፡ የእግዚአብሔር ሐገር፣ የተስፋ ምድር የተባለችው ፍልስጤም በጌታ ላይ

የተንኮል መረብ /ሤራ/ ስትዘረጋ የኀጢአትና የጣኦት አምልኮ ሀገር የሆነችው ግብጽ ደግሞ ተቀብላ አዳነችው፡፡

ጌታችን በእግረ ሥጋ በተመላለሰባቸው ዘመናት ያደረጋቸው አብዛኞቹ  ነገሮች ወደፊት ሊመጡ ላላቸው ነገሮች

ትንቢት ናቸው፡፡

ዮሴፍ ጌታንና እናቱን ይዞ ወደ ግብጽ እንዲሄድ በመልአክ ታዘዘ፡፡ ግብጽ በሥፋት ጣኦት የሚመለክባት ሀገር

ነበረች፡፡ ይህም በኋላ ክርስትና በአምልኮት ባዕድ ወደ ነበሩ ህዝቦች /አሕዛብ/ ዘንድ ለመውሰዷ ትንቢት

/ምልክት/ ነው፡፡ እመቤታችን ጌታን ይዛ ወደማታውቀው ሀገር ስትሰደድ ቤተልሄም /ይሁዳ/ ሄሮድስ ባስገደላቸው

ሕፃናት በሰማዕታት ደም ተጥለቅልቃለች፤ የሄሮድስጭፍጨፋና ሕፃናቱን መግደሉ ወደፊት ክርስቲያኖች

Page 10: Science and Rel

በአይሁድ እጅ ለሚቀበሉት ሰማዕትነት ምሳሌ ነው፡፡

መልአኩ ተገልጦ የተነጋገረው ከእመቤታችን ጋር ሳይሆን ከዮሴፍ ጋር ነበር፡፡ ምን አለው? « ተነሳ ሕፃኑንና እናቱን

ይዘህ..» የእመቤታችን በግብረ መንፈስ ቅዱስ መጽነስ ሲነግረው ያለው « እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ

አትፍራ» ነበር፡፡ አሁን ግን እጮኛህን አላለውም « የሕፃኑን እናት» አለው እንጂ፡፡ ምክንያቱም እመቤታችን

ጌታችንን ከወለደች እና በጌታ ልደት ጊዜ የሆኑትን ነገሮች / ኮከቡን፣ ሰብአ ሰገልን/ ካየ በኋላ ሁሉን ነገር ተረድቶ

ተረጋግጦ ነበር፡፡ በቂ ነገር ዓይቶ፣ ባየው ነገር ተረጋግቶ ነበር፡፡ ስለዚህ መልአኩ አሁን በግልጽ ይናገራል

«ልጅህን» ወይም «እጮኛህን» አላለም፡፡ « ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሂድ አለው» እንጂ፡፡ የስደቱንም

ምክንያት አብሮ ይነግረዋል፤ « ሄርድስ የሕፃኑን ነፍስ ይፈልጋልና፡፡»

ዮሴፍ ይህንን ሲሰማ ቅር አልተሰኘም፤ « ይህን ነገር ለመረዳት ይከብዳል፤ ሕዝቦቹን ያድናቸዋል አላለከኝም

ነበር? አሁን ደግሞ ራሱን እንኳን ማዳን አይችልምን? እኛም ከቤታችን ወጥተን ርቀን ለብዙ ጊዜ መሰደድ አለብን

አሁን ያለት ነገሮች ከተሰጠው ተስፋ /ቃል/ ጋር ተቃራኒ ናቸው፡፡» አላለም ጻድቅ እና እውነተኛ አማኝ ነበርና፡፡

ምንም እንኳን መልአኩመመለሻውን ግልጽ ሳያደርግ እስከምነግርህ ድረስ በዚያው ተቀመጥ ቢለውም

ስለሚመለሱበት ጊዜ አልተጨነቀም፤ አልጠየቀምም፡፡ ዮሴፍ ፍርሃትም እንኳን አላሳየም፡፡ ሁሉንም ነገር በደሰታ

ተቀበለ እንጂ፡፡

ሰውን ወዳጅ የሆነው እግዚአብሔር መከራንና ደስታን በሰዎች ሕይወት ላይ ያመጣል፡፡ በችግር ወይም በደስታ

ብቻ አያኖርም፡፡ ነገር ግን ሁለቱንም ችግርን /ሀዘንን/ እና ደስታን /ሃሴትን/ እያፈራረቀ ያመጣል፡፡ አሁንም ያደረገው

ይህንኑ ነገር ነው፡፡ ዮሴፍ ድንግልን ጸንሳ ባያት ጊዜ ተጨነቀ፤ ተረበሸ፤ ታወከ፡፡ በዚህ መሃል ግን መልአኩ

ተገልጦ ፍርሃቱን አስወገደለት፡፡ ሕፃኑን ተወልዶ ባየ ጊዜም ከፍ ያለ ደስታ ተደሰተ፡፡ ደስታው ብዙም ሳይቆይ አደጋ

መጣ፤ በሰብአ ሰገል መምጣት ከተማው ተረበሸ ንጉሡም ከእብደቱና ከክፋቱ የተነሳ የተወለደውን ሕፃን ሊገድል

ተነሳ፡፡ ይህጭንቀት ደግሞ በደስታ ተተካ ኮከቡና የሰብአ ሰገል ለጌታ መስገድ እጅግ አስደሳች ነበሩ፡፡ ከዚህ

ደስታ በኋላምጭንቀትና ፍርሃት መጣ፡፡ መልአኩ « ንጉሥ ሄሮድስ የሕፃኑን ነፍስ ይፈልጋል፡፡» ብሎ ነገረው፡፡

በዚህ ጊዜ ጌታችን በሕዝብ ፊት ተዓምራት ለማድረግ ጊዜው ገና ነውና መሰደድ አስፈለገው፡፡ ምክንያቱም ገና

በልጅነቱ ተአምራትን በአደባባይ / በሕዝብ ፊት/ ቢያደረግ፣ ሥጋን እንደተወሃደ አይታመንም ነበር፡፡

በአንድ ጊዜ ሁሉን ማድረግ ሲችል ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅጸን ያደረው፣ እንደ ሕፃናት ጡትን እየጠባ፣

በጥቂት በጥቂቱ ያደገው፣ ሥራውን እስኪጀምርም ሠላውን ዘመን በዝምታ / በስውር ተዓምራት/ ያሳለፈው፡-

የተዋህዶን ነገር እንረዳ ዘንድ ነው፡፡

አይሁድ ትንቢቱን በተመለከተ ጥያቄ ቢያነሱ እና ልጄን ከግብጽ ጠራሁት የተባለው ስለ እኛ ነው ቢሉን ይህ

የትንቢት አካሄድ /መንገድ/ ነው እንላቸዋለን፡፡ ብዙ ጊዜ ስለተወሰኑ ሰዎች የተናገረው የሚፈጸመው በሌሎች

ነው፡፡ ያዕቆብ ሊሞት ሲል ልጆችን ሰብስቦ በኋለኛው ዘመን ምን እንደሚደርስባቸው ሲነገራቸው እንዲህ ብሎ

Page 11: Science and Rel

ነበር፡-

ስምኦንና ሌዊ ወንድማማች ናቸው፤

ሰይፎቻቸው የአመጽመሣሪያ ናቸው፡፡

ከምክራቸው ነፍሴ አትግባ፡፡

ከጉባኤያቸውም ጋር ክብሬ አትተባበር

በቁጣቸው ሰውን ገድለዋልና

በገዛ ፈቃዳቸው በሬን አስነክሰዋልና፡፡

በያዕቆብ እከፍላቸዋለሁ፡፡ በእስራኤልም እበትናቸዋለሁ፡፡ ዘፍ. 49-7

ይህ ግን በእነርሱ አልተደረገም በልጆቻቸው እንጂ፡፡ በዘፍ. 9-25 ላይ ተጽፎ እንደሚገኘውም ኖህ እንዲህ ብሎ

ነበር፡- « ከነአን ርጉም ይሁን ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን» ይህ የተፈጸመው በከንአን ሳይሆን በእርሱ

ዘሮች ነው፡፡

ይህመቼ እና እንዴት እንደሆነ በመጽሐፈ ኢያሱ እና በመጽሐፈ ዜና መዋዕል፤ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ እንዲህም ሆነ

በዮርዳኖስ ማዶ በተራራማው በቆላውም በታላቁ ባሕር ዳርና ሊባኖስ ፊት ለፊት የነበሩ ነገሥታት ሁሉ ኬጢያዊ፣

አሞራዊም፣ ከነአናዊም፣ ኢያቡሳዊም፣ ይህን በሰሙ ጊዜ ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ ወጡ፡፡

በዚያም ቀን ኢያሱ ለማኅበሩ በመረጠውሥፍራ እስከ ዛሬ ድረስ፣ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንጨት ቆራጮች

ውኃም ቀጂዎች አደረጋቸው፡፡ /ኢያ. 9-1-27/

1 ኛ ዜና.8-7 ሰሎሞንም ኬጤያውያንንም፣ አምራውያንንም፣ ፌርዜያውያንንም ኢያቡሳውያንንም የቀሩትን

ከእስራኤል ወገን ያልሆኑትን ሕዝብ ሁሉ... ገባሮች አድርጎ መለመላቸው፡፡

ይስሐቅ « ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፡፡ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ» ፡፡ ብሎ ያዕቆብን የመረቀው ምርቃት

የተፈፀመው በእርሱ ሳይሆን በልጆቹ ነው፡፡ ዘፍ. 27-19

ስለዚህ እርሱ ባይወለድ ኖሮ፣ ትንቢቱ ፍጻሜውን አያገኝም ነበር፡፡ ወንጌላዊውም ያለውን አስተውሉ፡- « ይፈፀም

ዘንድ፡፡» ይህም እርሱ ባይመጣ አይፈፀምም ነበር ማለት ነው፡፡

Page 12: Science and Rel

በዚህኛውም ጊዜ የተደረገው /የሆነው/ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነገር ነው፡፡ መጀመሪያ ለእስራኤል የተነገረው

ነገር በኋላ በጌታ ተፈጽሟል፡፡ ደግሞስ የእግዚአብሔር እውነተኛ ልጅ ሊባል የሚችለው የትኛው ነው? ጥጃን

ያመለከና ለቤልሆር ልጆቹን የሰዋ? ወይስ በባሕሪው ልጅ የሆነና የወለደው አባቱ « የምወደው ልጄ» ብሎ

የሚያመሰግነው?

ከዚህም ሌላ / ግብጽ መሄዳቸው/ እመቤታችን ከፍ ያለ ክብር ያላት እንደሆነች እንዲታወቅ ተደርጓል፡፡ ህዝቡ

የሚመኩበትን ከእግዚአብሔር ያገኙትን ስጦታ እርሷም ለራሷ አግኝታለችና፡፡ ማለትም፣ እነርሱ ከግብጽ

በመውጣታቸው / ከስደት በመመለሳቸው/ ይመኩና ይኮሩ ነበር፡፡ ይህንኑ የሚመኩበትን ነገር ለእመቤታችንም

ስጣት፡፡

ያዕቆብና ህዝበ እስራኤል ወደ ግብጽ በመሄዳቸውና ከዚያም በመመለሳቸው የእርሱን ግብጽ ሄዶ መመለስ ምሳሌ

እየፈጸሙ ነበር፡፡ እነርሱ ግብጽ የሄዱት በረሃብ /በድርቅ/ የመጣመሞትን ለማምለጥ ነበር፡፡ እርሱ ደግሞ

በተንኮል መሞትን ለማምለጥ ነው፡፡

እነሱ / ህዝበ እስራኤል/ ግብጽ መሄዳቸው ከረሃቡ /ከድርቁ/ ተርፈዋል፡፡ እርሱ ግን እዚያ በመሄዱ በኪዳተ እግሩ

/ በእግሩ በመርገጥ/ ምድሪቱን ቀድሷታል፡፡

በዚህ ራሱን ዝቅ በማድረጉ መሀልም ግን የአምላክነቱ ማሳያዎች /ምልክቶች/ ተገልጸዋል፡፡ ሰብአ ሰገልና እርሱን

ለማምለክ በኮከብ እየተመሩ መጡ፤ አውግስጦስ ቄሳርም የሕዝብ ቆጠራ አዋጅ በማወጅ ልደቱ ቤተልሔም

እንዲሆን አገለገለ፤ በግብጽም በርካታ ተዓምራት ተደርገዋል፡፡

አሁን ወደ ግብጽ ብንሄድ በረሃው ከማንኛውም የአትክልት ስፍራ የተሻለ ሥፍራ ያማረ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በአስር

ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመላእክት አምሳል ያመሰግኑበታል የሰማእታት ብሔር፣ የደናግል በአት፣ የሰይጣን

አገዛዝ ድል የተመታበትና የክርስቶስ መንግስት ደምቆ የሚያበራበት ቦታ ነው፡፡

በትምህርተ ሃይማኖታቸው /doctrine/ ካላቸው ትክክለኛነት በተጨማሪ፣ በህይወታቸውም ያላቸውን

ቁርጠኝነት ያሳያሉ፡፡ ያላቸውን ሁሉ ትተው ራሳቸውን ከዓለም ካገለሉና ለዓለሙ በሙሉ ከተሰቀሉ በኋላ በድጋሚ

የተቸገሩትን ይረዱ ዘንድ የጉልበት ሥራ ይሠራሉ፡፡

ስለሚጾሙና ብዙ ጊዜ በተመስጦ ስለሚያሳልፉ፤ ቀናቱን /ጊዜን/ ሥራ በመፍታት /ቦዝነው/ ማሳለፍ ተገቢ ነው

ብለው አያስቡም፡፡ ስለዚህም ቀኑን በጸሎት ሌሊቱንም በዝማሬና በትጋት ያሳልፉታል፡፡ ከዚህም የሐዋርያውን አሰር

ይከተላሉ፡፡

« ከማንም ብር ወይም ወርቅ አላስፈለገኝም እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ

እናንተ ታውቃላችሁ፡፡ እንዲህ እየደከማችሁ ድውያንን ልትረዱና፣ « እርሱ ራሱ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብጽዕ

ነው» የሚለው የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ አሳየኋችሁ፤» ሐዋ. 10-34 ይህንን የሐዋርያውን

Page 13: Science and Rel

ቃል ሲሰሙ በበረሃ ያሉት የግብጽ መነኮሳት እንዲህ ይላሉ፡- « እርሱ /ሐዋርያው/ በእግዚአብሔር ቃል

እንዲመግባቸው ብዙዎች እየጠበቁት የእጅ ሥራ ይሠራ ከነበረ፣ መኖሪያችንን በገዳም፣ በዱር፣ በበረሃ ያደረግን፣

የከተማ ጾር /ፈተና/ የቀረልን እኛማ ከጸሎታችንና ከተመስጦአችን የተረፈንን ጊዜ ለተመሳሳይ ሥራ ልናውለው

ምን ያህል ይገባናል)!»

እኛም ራሳችንን እንመርምር ሀብታምም ድሃም የሆንን እነዚህ መነኮሳት ከሰውነት / እጅና፣ እግር/ በስተቀር ምንም

የሌላቸው ሲሆኑ የተቸገሩትን ለመርዳት እንዲህ ከወጡና ከወረዱ የተረፈንን እንኳን ለእነዚህ ሰዎች / ችግረኞች፣

ድውያን/ የማንሰጥ እኛ ለዚህ አድራጎታችን ምን ምክንያት፣ ምን ማስተባበያ ማቅረብ እንችላለን፡፡

ታላቁን አባት ቅዱስ እንጦንስን እናስታውስ፡፡ ይህ ሰው የተወለደው ፈርኦን በተወለደበት ሀገር ነው፡፡ ነገር ግን

በዚህ ምክንያት እነርሱን አልመሰለም፡፡ የነበረው ሰማያዊ ራእይ ስለጠበቀው እግዚአብሔር በሚወደውመልኩ

ህይወቱን አሳልፏል፡፡ ከጽድቁ የተነሳ ከእርሱ በኋላ የሚመጡመነኮሳት ምን ዓይነት እንደሚሆኑ እግዚአብሔር

አሳይቶታል፡፡

ጻድቁ እንጦንስን ታሪክ ማንበብና ማድነቅ ብቻ ሳይሆን በሕይወት መተርጎምም ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለመንፈሳዊ

ሕይወታችን አለመበርታት ቦታን፣ አለመማርን፣ የአባቶችን መርገም... ምክንያት አናድርግ፡፡

ነገሮችን በማስተዋል ስንመለከት እነዚህ ሁሉ ነገሮች ለእኛ መሰናክል መሆን አይችሉም፡፡ አብርሃም ጣኦት

አምላኪ አባት ነበረው /ኢያ. 24-2/ ነገር ግን የአባቱን ክፋት አልወረሰም፣ የሕዝቅኤልም አባት አካዝ ኀጢአተኛ

ሰው ነበር፡፡ ሕዝቅያስ ግን የእግዚአብሔር ወዳጅ ነበር፡፡

ዮሴፍም በግብጽ ሆኖ ራሱን በትምህርት አስጊጧል፡፡ ሦስቱ ሕፃናትም በባቢሎን ቤተመንግስት ሆነው ታላቅ ራስን

መግዛት አሳይተውናል፡፡ ሙሴም በግብጽ ነበር፣ ቅዱስ ጳውሎስም በዓለም ነበር፤ ነገር ግን እነዚህን ሁሉ ያሉበት

ቦታና ሁኔታ ከጽድቅ ጉዞአቸው አላደናቀፋቸውም፡፡

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን