Transcript
Page 1: የቴክኖሎጂ ችካሎች በኬሚስቱ እይታ  ፫ . ጤና እና መድሐኒት

የቴክኖሎጂ ችካሎች በኬሚስቱ እይታ፫. ጤና እናመድሐኒት

ኬሚስትሪ ረጅም ዕድሜ እንድንኖር፣ እንድንደሰት እና ጤነኞች እንድንሆን ለማስቻል በጤና መስክ ውስጥ ለብዙ ሕይወት- አዳኝ ስር- ነቀል ለውጦች አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በአብዛኛው የሰው- ልጅ ታሪክ ውስጥ መድሐኒት እና የጤንነት ክብካቤ ኋላ- ቀር ነበሩ፡፡ ሰዎች ሲታመሙ ወይም ሲቆስሉ ሐኪሞች የሚያደርጉት ሥራ

እነርሱን ከማጽናናት እና ከማጽዳት እምብዛም ያልበለጠ ነበር፡፡ ሐኪሞች በሽታዎችን በመፈወስ፣ ጉዳቶችን በማስተካከል እና እንዲያውም የጤና ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት በመከላከል ረገድ ባለፉት 100

ዓመታት ውስጥ ስር- ነቀል ለውጦች አምጥተዋል፡፡ ትጉህ ኬሚስቶች እና ኬሚካዊ መሐንዲሶች ድንቅ መድሐኒቶችን በመሥራት፣ አዳዲስ የሕክምና መሣሪያዎችን በመፍጠር እና የበሽታ አመራመር ዘዴዎችን በማጥራት ዘመናዊ መድሐኒቶችን ለማስገኘት ረድተዋል፡፡

ሚሊዮናት የሰው- ልጅ ሕይወቶች የተረፉት እና የተሻሻሉት በኬሚስትሪ አማካኝነት በለሙ የጤና እና የሕክምና ግስጋሴዎች ነው፡፡

፫.1 የሕመም እና የብግነት (inflammation) አያያዝሞርፋይንአስፒሪንኮርቲዞን

፫.2 ሣይኮቴራፒዩቲክ ኤጀንቶችክሎርፕሮማዚን

ትሪሳይክሊክ አንቲዲፕሬሳንትስቤንዞዲያዜፒንስ

፫.3 ነቅአ- ዘሮች (hormones) እና የነቅአ- ዘር ተቆጣጣሪዎች(hormone regulators)

ኢንሱሊንቴስቶስቴሮን

ፕሮጄስቲንስ፣ ኤስትሮጂንስ እና በአፍ የሚወሰዱ የወሊድ መከላከያዎች (oral contraceptives)

፫.4 ጋስትሮ- ኢንቴስቲናል ኤጀንቶች የአልሰር ሕክምና እድገት

፫.5 ሕክምናዊ ፍተሻ እና የበሽታ ምርመራ የሕክምና ምስል ማሳያ ቴክኖሎጂዎች የሕክምና አይሶቶፖች የኬሚካል መፈተሸዎች (assays) መልማት

የግል ክትትል (personal monitoring) እድገት

፫.6 ፀረ- አስተላለፊመድሐኒቶች (anti-infective drugs) ሣልቫርሣን እና ፕሮንቶሲል

ፔኒሲሊን ዚዶቩዳይን (AZT)

፫.7 የ ካርዶቫስኩላር አያያዝ የልብ ምትን መቆጣጠር የልብን ሥራ ማቆም ማከም

የደም መቋጠርን መግታት የደም ኮሌስትሮል ደረጃን መቆጣጠር

፫.8 የካንሰር ኬሚካዊ ሕክምና (chemotherapy) የካንሰር ኬሚካዊ ሕክምና እድገት

ሲቶቶክሲክ መድሐኒቶችታሞክሲፌን

፫.9 ድንቅ የጤንነት መንከባከቢያ ቁሶችሰው- ሠራሽ ቅልጥሞች እና ሕክምናዊ መሣሪያዎች

ሕክምናዊ መሣሪያዎችፀረ- ተባያት (disinfectants) እና አንጪዎች

(bleaches)

Page 2: የቴክኖሎጂ ችካሎች በኬሚስቱ እይታ  ፫ . ጤና እና መድሐኒት

፫. የቴክኖሎጂ ችካሎች በጤና እና በሕክምና ውስጥ

እለታተ-ግኝቶች

1899 ሕመምን፣ የመገጣጠሚያ ብግነትን እና እብጠትን ለመዋጋት አስፒሪን ተፈበረከ፡፡

1909 ሣልቫርሣን የተባለው የመጀመሪያው ዋና ኬሚካዊ መድሐኒትተሠራ፡፡

1922 ከስኳር- በሽታ ጋር የተዛመደውን ክፍተኛ የደም ግፊት ለመቀነስ ኢንሱሊን ጥቅም ላይ ዋለ፡፡

1923 የሞርፊን ኬሚካዊ መዋቅር ታወቀ፡፡

1927 ኤስትሮጂን ን በሽንት ውስጥ ለማግኘት የእርግዝና ምርመራተፈጠረ፡፡

1935 ፕሮንቶሲል ገዳዩን የ ስትሬፕቶኮካል ብግነት ፈወሰ፡፡

1942 የ ናይትሮጂን ሰናፍጭ የካንሰር ኬሚካዊ ሕክምናን ዘመንከፈተ፡፡

1943 ፔኒሲሊን ብግነትን ተዋጋ እና የፀረ- ሰውነት (antibiotic) ሕክምናን አበሰረ፡፡

1954 ዲጎክሲን የደም መቋጠርን፣ ትሮምቦቲክ በሽታን ለማከምተረጋገጠ፡፡

1954 ክሎርፕሮማዚን ዘመናዊውን ፀረ-ሣይኮቲክ ሕክምና አስጀመረ፡፡

1960 ኤኖቪድ ተመረተ እና ለአፍአዊ የወሊድ መቆጣጠሪያነት ለገበያ ወጣ፡፡

1963 ቅጠላ- ቅጠላዊ የሕዋስ ክፍፍል ተከላካይ (herbal cytotoxic) መድሐኒቶች ካንሰርን ለመዋጋት ጥቅም ላይ ዋሉ፡፡

1976 የጨጓራ ቄስለቶች (ulcers) ‘ ሲታከሙ ሆድ ቃ ውስጥ የአሲድ ርጭትን ለመግታት ታጋሜት ተሠራ፡፡

1977 ቴሞክሲፌን በካንሰር ኬሚካዊ ሕክምና ውስጥ የነቅአ- ዘር(hormone) ገቺዎችን አስተዋወቀ፡፡

1987 ዚዶቩዳይን (AZT) ለኤች.አይ.ቪ. በሽታ ሕክምና እንዲውል የአሜሪካ ፌዴራል የመድሐኒቶች አስተዳደር ፈቃድ ሰጠ፡፡

ፖል ኤኸሪሽ፣ የሣልቫርሣን ፈልሳፊ

ኢንሱሊን ን ለመጀመሪያ ጊዜ የሠሩት ፍሬዴሪክ

ባንቲንግ እና ቻርልሰ ኤች. ቤስት

ፐሮንቶሲል

አሌክሣንደር ፍሌሚንግ

በመስታወት መስኮት ላይ ሆኖ የተሠራውሥዕል

የፔኒሲሊን እንቅስቃሴ

ኤኒቪድ

የሕዋስ ክፍፍል ተከላካዩ መድሐኒት፣ የታክሶል

ኬሚካዊ መዋቅር

የሆድ‘ ቃ ቁስለት

ሐምራዊውጥብጣብ ለፀረ-ጡት- ካነሰር፣ ቀዩ ጥብጣብ ደግሞ ለፀረ- ኤይድስ ዘመቻ ተምሣሌቶች ናቸው፡፡

አስፒሪን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈበረኩት እንክብሎች

(1900)

የሞርፊን ኬሚካዊ መዋቅር

የእርግዝና ፍተሸ


Recommended