60

የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና
Page 2: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ተልዕኮ፡ የጤና መድህን ስርአትን ለማስፈፀም ቀልጣፋና ብቃት ያለው አሰራር በመዘርጋት፣ የአባላት መዋጮን በማሰባሰብና በማስተዳደር ሁሉን አቀፍ የሆነ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ሽፋን ያለ ህክምና ወጪ ስጋት ተደራሽነትና ቀጣይነት ባለው መልኩ ለዜጎች መሰጠቱን ማረጋገጥ።

ራዕይ፡ በ 2017 ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ፍትሃዊ እና ቀጣይነት ያለው የጤና መድህን ተጠቃሚ ሆነው ማየት

ዕሴቶች• ቅድሚያ ማህበረሰብ• መደጋገፍ • ግልጽነት• አሳታፊነት• ተጠያቂነት • ታማኝነት

የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ

Page 3: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

አድራሻ

የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ

ስልክ፡0115576723 / 0115576730 ፋክስ፡0115576742

ፖ.ሳ.ቁጥር፡ 21254/1000 ኢ-ሜይል፡[email protected]

ዌብ ሳይት፡ www.ehia.gov.et

ዳማ ትሬድ ህንጻ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ (ወረዳ-8)፣

አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ

ጤና መድህን መጽሔት ልዩ ዕትም ቅጽ 02፣

ቁጥር 02 መስከረም 2009 ዓ.ም

በኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የኮሙኒኬሽንና ሞቢላይዜሽን ዳይሬክቶሬት

እየተዘጋጀ የሚታተም።

ዋና አዘጋጅ•አቶ አሰፋ ይርጋለም

አዘጋጆች•አቶ ጌታቸው ጥሩነህ

•አቶ ዓቢይ ጌታሁን

•አቶ ዘላለም አበበ

•አቶ ሀብታሙ ቦጋለ

•አቶ ብርሃኑ ይመር

•ወ/ት ቤዛ እሸቱ

ኮምፒውተር ፅሑፍ•ወ/ት ኤደን በሪሁን

ግራፊክስ ዲዛይንPSD Adverttisng & Print

+251 (0) 0911 24 92 76

ማውጫ

7-11 ወቅታዊ ዜናዎች

12 ክቡር አቶ ሀይለማሪያም ደሣለኝ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ስለ ጤና መድህን ከተናገሩት በጥቂቱ

16 በእንግዳ አምድ ፡ አቶ ታደለ ይመር የኢትዮጵያ አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት

20 ደምበጫ- የማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን ተምሳሌት!

26 የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህንን - ከሙከራ ወደ ሀገር አቀፍ የማስፋት እንቅስቃሴ

32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ትራንስፎርሜሽን

38 የጋና ጤና መድህን በአፍሪካ ብሎም በዓለም ተምሳሌት የመሆን ጥረት

42 መዝናኛ

44 የኢትዮጵያ የጤና መድህን የጥቅም ማዕቀፍ እስከ ምን ድረስ?

48 የሀገራት የጤና መድህን ተሞክሮከ

52 ከአባላት አንደበት

56 ከፎቶ መህደር

Page 4: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 20094

የዋና አዘጋጁ መልዕክት

ውድ አንባቢያን! የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ አመታዊ መፅሔትን ሁለት ብለናል። በመጀመሪያው ዕትማችን ለሰጣችሁን ምክረ ሀሳብ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። በሁለተኛው እትማችን የኢትዮጵያ

አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትን አቶ ታደለ ይመርን እንግዳችን አድርገን በጤና መድህን ስርዓት ዙሪያ ቆይታ አድርገናል። አቶ ታደለ ማህበራዊ የጤና መድህን ስርዓት ከጥንስሱ ጀምረን አብረን ነበርንበት ይላሉ። ጤና መድህን ለሠራተኛው ብቻ ሳይሆን ለአሰሪውም ጭምር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ይዘረዝራሉ።

መፅሔታችን ከያዘቻቸው አበይት ጉዳዮች አንዱ ለጤና መድህን አባላትና ተጠቃሚዎች የሚያገኟቸውን ጥቅሞች በዝርዝር የቀረበበት አምዳችን ይገኝበታል። በተጨማሪም ከኢትዮጵያ በፊት የጤና መድህን ስርዓትን ተግባራዊ ያደረጉ ሀገራት ለአባሎቻቸው የሚሰጡትን የጥቅም ማዕቀፎችን የዳሰስንበት አምድንም ይዟል መፅሔታችን። ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓት በሀገራችን ተግባራዊ መሆን ከጀመረ አምስት አመታትን አስቆጥሯል። በነዚህ ዓመታት በመስኩ በርካታ ስኬቶች እየተመዘገቡ ነው። በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓት የላቀ ስኬት ካስመዘገቡት ወረዳዎች መካከል አንዷ የሆነችውን የደምበጫ ወረዳ ተምሳሌትነት በተሞክሮ አምዳችን ይዘናል። የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህንን በሀገር ደረጃ ለማስፋፋት የተዘጋጀው ስትራቴጂ ምንነትም በመፅሔታችን ተተንትኖ ቀርቧል።

ከአባላት አንደበት፣ መዝናኛ፣ የፎቶ ገፅ፣ የዜና አምዶችና ልዩ ልዩ መልዕክቶች በመፅሔታችን ውስጥ ተካተው ቀርበዋል። እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ መፅሔታችንን አንብባችሁ የምትሰጡን ምክረ ሃሳብ ለመሻሻል ይረዳናልና አድርሱን::

መልካም ንባብ።

Page 5: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 20095

መንግስት ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የነደፈውን መከላከልን መሰረት ያደረገ የጤና ፖሊሲ ከመላ የአገራችን ህዝቦች ጋር በመሆን ተግባራዊ በማድረግ

በጤናው ዘርፍ የነበሩትን ስር የሰደዱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ደረጃ በደረጃ በመቅረፍ እመርታዊ ስኬቶችን አስመዝግቧል። የህዝባችንን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሳደግ በአገራችን ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ያረጋገጡ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል። መንግስት የጤና ፖሊሲውን ሲቀርጽ ዋነኛ መነሻው የጤና ዘርፉን መሰረታዊ ችግሮች በመቅረፍ የአገራችንን ዜጎች ጤንነት ማስጠበቅ ላይ ያተኮረ ነበር። አብዛኛዎቹ ህዝቡን ለህመምና ሞት ሲዳርጉት የነበሩ የጤና ችግሮች በመከላከል ሊወገዱ የሚችሉ በመሆናቸው መንግስት የተከተለው የጤና ፖሊሲ በሽታን መከላከልን ማእከል አድርጓል። መከላከልን ማእከል ያደረገው የጤና ፖሊሲያችን ለህክምናም አስፈላጊውን ትኩረት የሰጠ ነው።

መንግስት ላለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት በሽታን በመከላከል ላይ ባተኮረ ፕሮግራምና ፖሊሲው አማካኝነት ጤናማና አምራች ዜጋ ማፍራትን ዋነኛ ግቡ አድርጎ መጠነ ሰፊ ስራዎችን በማከናወኑ ዘርፈ ብዙ ስኬቶች ተመዝግበዋል። በሂደቱም ህዝባዊ ንቅናቄን በመፍጠር ለረጅም ጊዜ ሰፍኖ የቆየውን ኋላቀር አመለካከት፣ አሰራርና አደረጃጀት በትክክለኛ ፖሊሲና አደረጃጀት በመቀየር ህብረተሰቡን የመከላከሉ ስራ ባለቤትና ግንባር ቀደም ተዋናይ አድርጓል። ከግለሰብ ጀምሮ በቤተሰብና ማህበረሰብ ብሎም በአገር አቀፍ ደረጃ ስኬታማ ተግባራትን አስመዝገቧል። እነዚህ በጤናው መስክ የተመዘገቡ ውጤቶች ህዝባችንንና አገራችንን ተጠቃሚ ከማድረጋቸው በተጨማሪ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረኮች ከፍ ያደረጉና እውቅና ያሰጡ ናቸው። ኢትዮጵያ በዘርፉ ባገኘቻችው

የክቡር የጤና ጥበቃ ሚንስትሩ መልዕክት

ዶ/ር ከሰተብርሀን አድማሱየኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚንስትር

እውቅናዎችና ሽልማቶች በፖሊሲ አቅጣጫዋ ስኬት ብዙዎች የአገራችንን ሞዴል ለመከተል እንዲነሳሱ አስችላለች።

መንግስታችን ላለፉት 10 ዓመታት የጤና አገልግሎት ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ፍትሀዊነቱን በጠበቀ መልኩ ለማዳረስ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በመመደብ ጤና ተቋማት በየአከባቢው እንዲገነቡ አድርጓል። ይሁንና ህብረተሰቡ የጤና አገልግሎት ፈልጎ ወደ ህክምና ተቋማት ሲሄድ በህክምና ወቅት ከኪስ በሚጠየቀው ክፍያ ማነቆነት የተነሳ የጤና ተቋማትን በሚፈለገው ደረጃ እየተጠቀመባቸው አይደለም።

ስለዚህ የሀገራችንን የጤና ልማት ግቦች ለማሳካትም ይሁን ጤናማ ዜጋ በመፍጠር ሁለንተናዊ ዕድገት ለማስመዝገብ እንዲቻል የጤና ፋይናንስ ስልታችን ህብረተሰባችንን የጤና አገልግሎትን ለመጠቀም በሚገፋፋና በሚያስችል መልኩ መቃኘት አስፈልጓል። የጤና ፖሊሲያችን የጤና ፋይናንስ ሥርዓቱ ምንጮች ከመንግስት፣ ከዓለም ዓቀፍ ምንጮችና ከግል ሊሆን እንደሚችል በግልጽ አስቀምጧል። ቀጣይነት ያለው የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ማቅረብ እንዲቻልም ወደ ፊት የጤና መድህን ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ከዛሬ ሀያ ዓመት በፊት በግልፅ አመላክቷል። መነሻውም በእርዳታ ከመንጠልጠል ይልቅ የውስጥ አቅምን በማሳደግና የህብረተሰቡን ባለቤትነት በማረጋገጥ ዘላቂ የጤና ፋይናንስ ምንጭ ለማበጀት ነው። በመሆኑም በውስጥ አቅም ላይ ተመስርቶ ቀጣይነት ያለውና ያልተቆራረጠ የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለማቅረብ እንዲቻል የጤና መድህን አሰራር ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ አማራጭ የለውም። የጤና መድህን ሥርዓቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊው የህግ ማዕቀፍ ወጥቶ ወደ ተግባር ለመግባት የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጀምሯል። በዋናነት የጤና መድህን ሥርዓትን መተግበር የአንድ ልማታዊ መንግስት መገለጫ እንደመሆኑ መጠን መንግስትና ህዝቡ እጅና ጓንት ሆነው ሊፈጽሙት ይገባል።

የሀገራችንም ሆነ የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ እንደሚያሳየን የጤና መድህን ስርዓትን በተሳካ መልኩ ለመፈፀም የጉዳዩ ባለቤት የሆነው ዜጋ ድርሻ ቁልፍ ቢሆንም በተለይ የፖለቲካ አመራሩ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው። በጋና፣ በሩዋንዳ፣ በደቡብ ኮሪያ እንዲሁም በጀርመን በጤና መድህን ስርዓት የታየው ተቀባይነትና ውጤት የፖለቲካ አመራሩ ድጋፍና ክትትል ስላልተለየው ነበር። በሀገራችን የጤና መድህን ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ የጤና ፋይናንስ ጉድለትን በመሙላት የፈውስ ህክምና አገልግሎትን ለሁሉም ዜጋ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የሚኖረውን ፋይዳ ተገንዝቦ ለስኬታማነቱ መስራት ምሁራንን ጨምሮ ከሁሉም ወገን ይጠበቃል የሚለውን መልዕክቴን ለማስተላለፍ እወዳለሁ። አመሰግናለሁ።

Page 6: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 20096

የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ መልዕክት

ኢትዮጵያ በ2017 ፍትሃዊነት የነገሰባት፣ መካከለኛ ገቢ

ያላት ሀገር ለመሆን ራዕይ ይዛ እየተጋች ትገኛለች፡

፡ የዚህ የአገራችን ራዕይ አካል የዜጎችን የጤና

አገልግሎት ፍትሃዊ ተደራሽነት ለማሻሻል እና በጤና አገልግሎት

ወጪ ምክንያት የሚደርስባቸውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ

ጫና ለመቀነስ የተዘረጋው የጤና መድህን ሥርዓት አንዱ ነው፡

፡ ይህ የጤና መድህን ሥርዓት ለጤና ሥርዓቱ ቀጣይነትና በራስ

አቅም የጤና ወጪን የመሸፈን ሀገራዊ ኩራትን ከማረጋገጥ አልፎ

የጤና ሥርዓቱን ከውጪ ድጋፍና እርዳታ ለማላቀቅ ዓይነተኛ

መሳሪያ ነው፡፡ በሀገራችን የጤና መድህን ሥርዓትን መተግበር

እንደ አማራጭ የሚወሰድ ፕሮግራም ሳይሆን አንድ ልማታዊ

ዴሞክራሲያዊ መንግስት ለህዝቡ ማቅረብ ያለበት ማህበራዊ

ግዴታ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የሥራ አመራር ቦርድ ባለፉት

ሁለት ዓመታት የጤና መድህን ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ

የሚያግዙ የተለያዩ ውሳኔዎችን ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ የጤና መድህን

ስርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ የወጡ አዋጅና ደንቦችን ለማስፈፀም

የሚረዱ የተለያዩ መመሪያዎችን በማውጣትም ድጋፍ ሲያደርግ

ቆይቷል፡፡

በቀጣይም በማህበራዊ የጤና መድህን ስርዓትም ሆነ በማህበረሰብ

አቀፍ የጤና መድህን ስርዓት ትግበራ ላይ ቦርዱ ሲሰጥ የቆየውን

አመራር በቀጣይ ጊዜያትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማረጋገጥ

እወዳለሁ፡፡ የጤና መድህን ሥርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ

የመንግስት አመራር አካላት ቁርጠኝነት፣ የአሰሪዎች፣ የሲቪክ

ማህበራትና የመላ ህዝቡ ተሳትፎ ወሳኝነት አለው፡፡ የጤና

መድህን ስርዓትን ተግባራዊ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ተሞክሮ

እንደሚያሳየን ለጤና መድህን ስርዓት ስኬት የመንግስት፣

የግሉ ዘርፍ፣ የሰራተኞች፣ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማትና

ባለሙያዎች፣ በአጠቃላይም የህብረተሰቡ የጋራ ርብርብ ወሳኝ

ነው፡፡ በየደረጃው የምንገኘው የመንግስት አመራር አካላት የጤና

መድህን ስርዓትን የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽንና የዘላቂ ልማት

ራዕያችን አካል አድርገን በመያዝ ለዜጎች ፍትሀዊ እና ጥራት ያለው

የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት በቀጣይ መስራት ይጠበቅብናል፡፡

የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የሥራ አመራር ቦርድ፣

የኤጀንሲው ማኔጅመንት ኮሚቴ፣ በየደረጃው የሚገኙ የቅርንጫፍ

ጽ/ቤቶች አመራርና ሰራተኞች የጤና መድህን ስርዓትን

በማስፈፀም ረገድ ከፊታችን የሚጠብቁንን ተግባራት ለመፈፀም

ከምንጊዜውም በላቀ ደረጃ የምንረባረብበት ዓመት ይሆናል፡

፡ በተጨማሪም ከማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ሥርዓት

መስፋፋት ጋር ተያይዞ ሁለቱንም የጤና መድህን ሥርዓቶች

በብቃት በመፈፀም የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ኤጀንሲው

ተቋማዊ አደረጃጀቱን በማጠናከር እስከታችኛው መዋቅር ድረስ

ቀርቦ መደገፍ እና ለበለጠ ውጤት መሥራት ይገባል፡፡ መልካም

አዲስ አመት፣ መልካም የስራ ዘመን፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

አብራሃም ተከስተ (ዶ/ር)የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ

Page 7: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 20097

በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ባለው የጤና አገልግሎት ሥርዓት ተጠቃሚዎች ከጤና ጠቅላላ ወጪ አንድ ሦስተኛ የሚሆነውን በአገልግሎት ወቅት በሚከፍሉት ክፍያ እየተሸፈነ ነው። ይህ

የአከፋፈል ሥርዓት ከፍትሀዊነት አንፃር ስናየው የራሱ የሆነ ችግር ያለበት ነው። ይኸውም ግለሰቦች ለጤና አገልግሎት የሚከፍሉት ክፍያ የገቢ መጠናቸውን ያላገናዘበና ሳይታቀድ የሚከፈል መሆኑ ነው። በሌላ በኩል ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በአቅም ማነስ ምክንያት ወደ ህክምና የሚመጡት አብዛኛውን ጊዜ ህይወታቸውን ለማትረፍ ሲሉ ህመማቸው ሲፀናባቸው በመሆኑ ከሚያጋጥማቸው ስቃይና ህመም ባለፈ ለህክምና የሚያስፈልጋቸው ወጪ ከፍተኛ ነው። በሌላም ጎኑም በቀላል ህክምና እና ወጪ መዳን ሲቻል ህመም ሲሰማቸው ህክምና ባለማግኘታቸው ምክንያት ውድ በሆኑ መድሃኒቶችና የህክምና ሂደቶችን ማለፍ የግድ ይላቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ተጠቃሚዎች ለጤና አገልግሎቱ ክፍያ የሚፈጽሙት የጤና አገልግሎቱ በሚሰጥበት ጊዜ በመሆኑ የወጪ ጫና በማሳደር አገልግሎቱን ከመጠቀም የሚያግዳቸው ሲሆን አገልግሎቱን ለመጠቀም ከወሰኑም በተለይ በአነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ የሚተዳደሩት የህብረተሰብ ክፍሎች ያላቸው ጥሪት ተሟጦ ወደ ድህነት አረንቋ የሚገቡበት ሁኔታ ይፈጠራል። በዚህም የተነሳ እስካሁን እየተከተልነው ያለው የጤና ፋይናንስ ሥርዓት ሪፎርም እንደሚያስፈልገው በመንግስት ደረጃ ታምኖበት የጤና መድህን ሥርዓት ተግባራዊ እየተደረገ ነው። የቆየው አሠራር የግለሰቦችንና ቤተሰቦችን የኢኮኖሚ አቅም ከማዳከም አልፎ በሀገር ደረጃ አብዛኛው የምንገለገልባቸው የመድሃኒትና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች ከውጭ በግዥ የሚገቡ በመሆናቸው የሚጠይቀው የውጭ ምንዛሬ ከፍተኛ በመሆኑ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል። በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች በመቅረፍ የጤና አገልግሎት በፍትሀዊነት ለመላ ህብረተሰቡ ለማቅረብ የጤና መድህንን መተግበር ተኪ የሌለው አማራጭ ስልት ነው።

አቶ አታክልቲ አብርሃየኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት ቀደም ሲል በአራቱ ክልሎች የተጀመረው የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን (ማዐጤመ) ከአስራ ሶስት ወረዳዎች የሙከራ ትግበራ አልፎ ወደ ማስፋፋት ትግበራ ተሸጋግሯል። በአሁኑ ሰዓት በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በ226 ወረዳዎች እየተተገበረ ይገኛል። እስከያዝነው 2008 በጀት ዓመት አጋማሽ ድረስ 12,174,907 ዜጎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል። የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን ፕሮግራም እንደ እኛ ሀገር በግብርናና የዕለት ጉልበት ሥራ የሚተዳደር በርካታ ዜጎች ያላቸው የአፍሪካና የኤዥያ ሀገራት ተግብረውት ውጤት ተገኝቶበታል። ማዐጤመ ሲጀመር አልጋ በአልጋ የነበረ ባይሆንም ምልዐተ - ህዝቡና አመራሩ በአደረገው ርብርብ ተስፋ ሰጭ ውጤት ሊመዘገብ ችሏል። በማዐጤመ ፕሮግራም ትግራ ሂደት አሁንም ያልተሻገርናቸው ተግዳሮቶች ያሉ ቢሆንም ከህዝባችን ጋር ሆነን የማንፈታው ችግር እንደማይኖር በመተማመን የማስፋፊያ ትግበራው በፍጥነት እየተካሄደ ነው።

የጤና መድህን ፕሮግራሙን አገልግሎት ማግኘት በጀመሩት አካባቢዎች የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነትና ጥራት ጨምሯል። ስለሆነም ቀደም ሲል በአርሶ አደሩ አካባቢና ጥቂት መለስተኛ ከተሞች ላይ ብቻ ተወስኖ የነበረውን የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን ትግበራ በሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደሮች የከተማ እና አርብቶ አደር ነዋሪ ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ ነው። የማህበራዊ የጤና መድህን ሥርዓትን በመደበኛ ክፍለ - ኢኮኖሚ ተሰማርቶ በሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል ዘንድ ተግባራዊ ለማድረግ መንግስት በአስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ትግበራው በተሟላ ሁኔታ እንዲጓዝ ሰፊ የዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው። በዚህ የዝግጅት ሥራ ረገድ የአሠሪ መስሪያ ቤቶችና ሠራተኞች ድርሻ የጎላ ነው። አሠሪዎች መላ ሠራተኞቻቸውን በጤና መድህን ጽንሰ ሀሳብ ዙሪያ በማወያየት እና አስፈላጊ መረጃዎችን ሞልቶ በመላክ ሊተባበሩ ይገባል። ሠራተኞችም በተመሳሳይ የጤና መድህኑን ጠቀሜታ በውል በመገንዘብ የራሳቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ትክክለኛ መረጃ ለአሠሪ መስሪያ ቤቶቻቸው በመስጠት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው። የጤና መድህን ሥርዓትን መተግበር እንደ መንግስት የአንድ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት መገለጫ ነው። ከዚህ ባለፈ ዜጎች በዜግነታቸው በሀገራቸው የጤና አገልግሎት ሥርዓት ውስጥ ሀብታም ድሀ ሳይባል እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሥርዓት የማረጋገጥ ጉዳይ ነው። እንደ ሀገር ስናየው ደግሞ የህዳሴ ጉዟችንን በድል ለማጀብ ጤናማ ዜጋ ማፍራት ተኪ የሌለው ተግባር በመሆኑ በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት መረባረብ ይኖርብናል። በዚህ የልማት ዕቅድ ውስጥ የጤናውን ዘርፍ ትራንስፎርም ለማድረግ ከተወጠኑ አራት ዋና ዋና ሥራዎች መካከል የጤና መድህን ሥርዓትን በገጠርና በከተማ ነዋሪው ዘንድ መተግበር ቀዳሚው ነው። ስለሆነም ሀገራዊ ራዕያችንን ለማሳካት ይቻል ዘንድ በሀገራችን በአጭር ጊዜ በማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን ሙከራ ትግበራ ያገኘናቸውን ስኬቶች በማህበራዊ የጤና መድህንም ለመድገም የበኩላችንን ኃላፊነት እንወጣ ለማለት እወዳለሁ። አመሰግናለሁ!

Page 8: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 20098

በጤና መድህን ትግበራ ላይ ዩኒቨርስቲዎችና የምርምር ተቋማት ቁልፍ ሚና እንዲጫወቱ ተጠየቀ

የጤና መድህን ትግበራውን ሂደት የምርምር አጀንዳቸው በማድረግና የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ በኩል ያላቸውን ከፍተኛ አቅም እንዲጠቀሙም ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲም፣ ከጅማ ዩኒቨርስቲ ጋር የተጀመረውን በጎ ጅምር እንደ መነሻ በመውሰድ በቀጣይ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ጋር ለመስራት ማቀዱንም ጨምረው ገልፀዋል።

በጅማ ዩኒቨርስቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ወንዳፍራሽ ሙሉጌታ በበኩላቸው ዩኒቨርስቲው በማህበረሰብ አገልግሎት ያለውን ውጤታማ ልምድ የጤና መድህን ስርዓት ላይ ለመጠቀም ከኤጀንሲው ጋር በመተባበር እንደሚሰራ ገልፀዋል። በተለይ ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ትግበራ በሚካሄድባቸው የጅማ ዞን ወረዳዎችን ዩኒቨርስቲው በቀጣይ እንደሚደግፍ ተናግረዋል።

በአውደ ጥናቱ ላይ ከጤና መድህን ኤጀንሲ፣ ከአጋር ድርጅቶችና ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ከ150 በላይ ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን፣ በጤና መድህን ስርዓት ላይ ያተኮሩ 12 ጥናታዊ ፅሑፎች በተለያዩ ምሁራን ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ከጅማ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በጅማ ከተማ ያዘጋጁት አገር አቀፍ ኮንፈረንስ በጤና አገልግሎት ፍትሀዊ ተደራሽነት ላይ

ያተኮረ ነው።

የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አታክልቲ አብርሃ በሀገራችን የጤና ተቋማትን በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ በማድረግ በኩል ውጤታማ ስራ መሰራቱን ጠቁመው፣ የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቀጣይ ትኩረታችን ሊሆን ይገባል ብለዋል። በሀገራችን ሁለት አይነት የጤና መድህን ማዕቀፎች ተዘጋጅተው ወደ ስራ እየተገባ መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓትን ከ200 በላይ በሚሆኑ የገጠር ወረዳዎች ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል። በቀጣይ አገልግሎቱን ተግባራዊ ወዳልተደረገባቸው ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ዩኒቨርስቲዎችና የምርምር ተቋማት ከየአካባቢያቸው ማህበረሰብ ጋር በቅርበት የሚሰሩ እንደመሆናቸው፣

Page 9: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 20099

የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ የመምህራን ማህበር ጋር በመተባበር ያዘጋጁትና በጤና መድህን ሥርዓት ላይ ያተኮረ ውይይት

በአዳማ ከተማ ተካሂዷል። በምክክር መድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት ኢትዮጵ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ዮሀንስ በንቲ የጤና መድህን በሀገራችን መተግበሩ በተለይ ለመምህራን የላቀ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል። መምህራን በአዕምሮ ልማት ላይ እንደመሥራታቸው መጠን በቅድሚያ እራሳቸው በአካልና በአዕምሮ ጤናማ መሆን የግድ ይላቸዋል ፤ ለዚህ ደግሞ የጤና መድህን ሥርዓት ትልቅ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። አያይዘውም የጤና መድህን ዋስትና የአንድ ሀገር የዘመናዊነት መገለጫ እንደመሆኑ መጠን የመምህራን ጥቅሞችን ባስጠበቀ መልኩ መተግበር እንዳለበት ጠቁመው ለጤና መድህኑ ስኬታማነት ከመንግስት ጋር በጋራ ለመሥራት ቁርጠኛ እንደሆኑ ጭምር ፕሬዘዳንቱ አረጋግጠዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አታክልቲ አብረሃ እንደገለጹት ከሀገሪቱ ዜጎች አንድ ሶስተኛ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል የሚገኘው በተለያዩ ደረጃ ባሉ የትምህርት ተቋማት እንደመሆኑ መጠን ለጤና መድህን ትግበራ ውጤታማነት የመምህራን አስተዋጽኦ ከፍተኛ

ነው። አያይዘውም በአርሶ አደሩ አካባቢ እየተተገበ ያለውን የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን ውጤታማ ለማድረግ መምህራን በየትምህርት ተቋማቱ ለተማሪዎችና ወላጆች ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ የድርሻቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ብለዋል። በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የመምህራን ማህበሩ አመራር ተሳፊዎች እንዳረጋገጡት የግንዛቤ ፈጠራ መድረክ መዘጋጀቱ ለጤና መድህን የነበረንን ጭፍን ጥላቻና የተዛባ አመለካከት ያጠራ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል።

በምክክር መድረኩ ተገኝተን በጤና መድህን አተገባበር ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ስናረጋግጥ ከግማሽ ሚሊዮን የማያንሰውን መላ መምህራን በመወከል ነው ያሉት የመምህራን ማህበሩ አመራሮች እኛ መምህራን ባለን የሥራ ሁኔታና ባህሪ ሰዎችን የማሳመን አቅማችንና ተቀባይነታችንን ተጠቅመን የቤተሰባችንን መረጃ ሞልቶ በማስተላለፍም ይሁን በማስተባበር የድርሻችን እንወጣለን ብለዋል። የግንዛቤ ፈጠራ መድረኮችም በቀጣይ በየደረጃው ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። የጤና መድህን ሥርዓት ላይ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ከኢትዮጵያ የመምህራን ማህበርና የክልል መምህራን ማህበራት የተውጣጡ አመራሮች ተሳትፈውበታል።

የጤና መድህን ሥርዓት ለመምህራን የላቀ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለጸ

Page 10: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200910

የማህበራዊ የጤና መድህንን ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናክረው

መቀጠላቸው ተገለጸ

የማህበራዊ የጤና መድህንን መጀመር የሚያስችል የዝግጅት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ተጠባባቂ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙላት ተገኝ ገለጹ።

መንግስት ለዜጎች ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት በፍትሃዊነት ለማቅረብ ከዘረጋቸው ሥርዓቶች አንዱ መደጋገፍን መሠረት ያደረገው የማህበራዊ የጤና መድህን ሥርዓት አንዱ እንደሆነ አስታውሰው በመላ ሀገሪቱ በመደበኛ ክፍለ ኢኮኖሚ የሚተዳደሩ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ሥራ እየተሠራ ነው።

የጤና መድህኑ አባላት በጤና መድህን ሥርዓት ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ይዘው የራሳቸውንና ቤተሰባቸውን መረጃ እንዲያስመዘግቡ በፌደራልና በክልል ደረጃ ሰፋፊ መድረኮችን በመፍጠር ግንዛቤ መፍጠር መቻሉን አቶ ሙላት ገልጸዋል። ኃላፊው አያይዘውም ለጤና መድህን አባላት የሚሠጠውን የጤና አገልግሎት በተሻለ ሁኔታ ለማስኬድ እንዲቻል በሁሉም ክልሎች በየደረጃው ለሚገኙ የጤና ተቋማት ኃላፊዎችና የጤና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል። በተያያዘም በጤና መድህኑ ትግበራ ወቅት የሚያስፈልጉ ማንኛውም ቅጻ ቅጾችና ፎርማቶች በበቂ መጠን ታትመው ወደ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እንዲሰራጩ ተደርጓል ብለዋል። ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም መንግስት የማህበራዊ የጤና መድህን እንዲጀመር አቅጣጫ ሲያስቀምጥ መጀመር የሚያስችል በኤጀንሲው ደረጃ የሚጠበቁ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን ገልጸዋል። በመጨረሻም ለጤና መድህኑ ስኬት አባላት የራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ትክክለኛ መረጃ ለአሠሪ መስሪያ ቤቶቻቸው በመስጠት ፤ አሰሪዎችም መረጃውን አጠናቅረው ወደ ኤጀንሲው በመላክ ድርሻቸውን እንዲወጡ ኃላፊው አሳስበዋል። ከአምስት ዓመት በፊት በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያና በደ/ብ/ብ/ህዝቦች ክልሎች በሙከራ ደረጃ ተጀምሮ በማስፋፋት ሂደት ላይ በሚገኘው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ከአስራ ሁለት ሚሊዮን

በላይ ህዝብ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ከተለያዩ የሠራተኞች ማህበራት

ፌዴሬሽኖች የተውጣጡ አመራሮች ተሳትፈውበታል። የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አታክልቲ አብርሃ በአዳማ ከተማ የተካሄደውን የውይይት መድረክ ሲከፍቱ እንደተናገሩት፣ የጤና መድህን ስርዓት በተለያዩ ተቋማት ተቀጥሮ የሚሰራውን የህብረተሰብ ክፍል በገንዘብ እጥረት ምክንያት በቂ ህክምና ያለማግኘት ስጋትን ያስወግድለታል። መንግስት የጤና መድህን ስርዓትን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለማዳረስ ጤናን ለሁሉም ዜጎች ተግባራዊ ለማድረግ የጀመረውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ የሰራተኞች ማህበራት አመራሮች የወከሏቸውን ሠራተኞች ግንዛቤ በማስጨበጥ ለፕሮግራሙ ስኬት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በበኩላቸው በጤና መድህን ስርዓት ትግበራ የሠራተኛውን ድምፅ በመወከል የሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽኑ በኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የሥራ አመራር ቦርድ አባልነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የጤና መድህን ስርዓት ለሠራተኛው የሕብረተሰብ ክፍል ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ለስኬታማነቱ ከኤጀንሲው ጎን በመሆን እንሰራለንም ብለዋል። በማህበራዊ የጤና መድህን ስርዓት ላይ አትኩሮ በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ከኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን፣ ከምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን፣ ከባንክና መድን፣ ከአገር አቀፍ እርሻ ፌዴሬሽን፣ ከቱሪዝም ፌዴሬሽን፣ ከኮንስትራክሽን ፌዴሬሽን፣ ከትራንስፖርትና መገናኛ ፌዴሬሽን፣ ከሀይል ማመንጫ ፌዴሬሽን፣ ከጨርቃጨርቅ ፌደሬሽን፣ ከንግድና ቴክኒክ ፌዴሬሽኖች የተውጣጡ የሠራተኛ

ማህበራት አመራሮች ተሳትፈዋል።

ኤጀንሲው ከሠራተኛ ማህበራት አመራሮች ጋር በጤና መድህን ዙሪያ ውይይት አካሄደ አቶ ሙላት ተገኝ

Page 11: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200911

የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓት በመላ ሀገሪቱ ተግባራዊ ይደረጋል።

የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ በ2009 በጀት ዓመት የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓትን በመላ ሀገሪቱ ተግባራዊ ለማድረግ ማቀዱን

አስታወቀ። የኤጀንሲው ተ/ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልጀሊል ረሻድ እንደገለፁት፣ ከሚያዝያ/2003 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ እና በትግራይ ክልሎች በተመረጡ ወረዳዎች የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የሙከራ ትግበራ ሲካሄድ ቆይቷል። በአራቱ ክልሎች የተጀመረውን የሙከራ ትግበራ በ2009 በጀት ዓመት በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ለማስፋፋት እንቅስቃሴ መጀመሩንም አቶ አብዱልጀሊል ተናግረዋል። እስካሁን የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓት ተግባራዊ በተደረገባቸው አራቱ ክልሎች ከ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ አባወራ እና እማወራዎች በአባልነት መታቀፋቸውን ጠቁመው፣ ከ12 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ አባላትና ቤተሰቦቻቸው የጤና ዋስትናቸውን ማረጋገጥ እንደቻሉም አመልክተዋል።

በክልሎቹ በተደረገው የማዐጤመ ትግበራ በአማራ

ክልል የሚገኙት የቦረና እና የደምበጫ ወረዳዎች ነዋሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ የጤና መድህን ስርዓት ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ገልፀው፣ በሌሎች ወረዳዎችም የሙከራ ትግበራው ውጤታማ ነበር ብለዋል። ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓት ተግባራዊ በተደረገባቸው ወረዳዎች የህብረተሰቡ የጤና አገልግሎት አጠቃቀም እየተሻሻለ መምጣቱንና፣ በገንዘብ እጦት ምክንያት ይፈጠር የነበረውን በቂ ህክምና ያለማግኘት ችግርንም መቅረፍ መቻሉን እንዲሁም ከአሁን ቀደም ቤተሰቦች ህመም ባጋጠማቸው ጊዜ ለህክምና የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ንብረታቸውን ይሸጡ የነበረበትን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ማስቀረቱን ተናግረዋል። ኤጀንሲው በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዘመን የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓትን በሀገሪቱ ከሚገኙ ወረዳዎች 80 በመቶ በሚሆኑት ላይ በመተግበር የህብረተሰቡን የጤና ዋስትና ለማረጋገጥ እንደሚሰራ አስታውቀዋል። እንደ አቶ አብዱልጀሊል ገለፃ፣ ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ ሲጠናቀቅ ማህበራዊና ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓትን በአንድነት የያዘ ሀገር አቀፍ የጤና መድህን ስርዓት ተግባራዊ ይደረጋል።

Page 12: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200912

የጤና መድህን ዋናው ዓላማ ታመን ከወደቅን በኋላ

ወደህክምና ማዕከላት መሄድ ሳይሆን ጤንነታችን እየተጠበቀ

የሚቀጥልበት ሁኔታ የሚያመቻች ስርዓት ነው። አብዛኛው ሰው ብዙ ደመወዝ ያለውም ሰው ጭምር

በየጊዜው የጤና ምርመራ እያደረገ አይደለም። የጤና ምርመራ

የማያደርግበት ዋነኛው ምክንያት ደግሞ በየጊዜው መክፈል

ስለማይችል ነው።

““

Page 13: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200913

የጤና መድህን በገጠሩ አካባቢ ህዝቡ በጣም የወደደው ስርዓት ነው። የሙከራ ትግበራ ባካሄድንባቸው የገጠር ወረዳዎች በሙሉ

አርሶ አደሩ ተቀብሎታል። በአፍሪካም ከ30 በላይ ሀገሮች የጤና መድህን ሽፋንን ለዜጎቻቸው እየሰጡ ይገኛሉ። ስለዚህ ሀገራችንም የጤና ፋይናንስን በተመለከተ ተገማች በሆነ ሁኔታ ለመስራት የሚያስችል የጤና መድህን ዋስትና ሊኖራት ይገባል። እኛ በተለምዶ ታመን ሳንወድቅ በፊት ሀኪም ቤት አንሄድም፣ ታመን ከወደቅን በኋላ ወደሀኪም ቤት መሄዱ አንደኛ ከፍተኛ ወጪ ያስወጣናል፣ ሁለተኛ በህይወት የመቀጠል እድላችንም ዝቅተኛ ነው።

የጤና መድህን ዋናው ዓላማ ታመን ከወደቅን በኋላ ወደህክምና ማእከላት መሄድ ሳይሆን ጤንነታችን እየተጠበቀ የሚቀጥልበት ሁኔታ የሚያመቻች ስርዓት ነው። አብዛኛው ሰው ብዙ ደመወዝ ያለውም ሰው ጭምር በየጊዜው የጤና ምርመራ እያደረገ አይደለም። የጤና ምርመራ የማያደርግበት ዋነኛው ምክንያት ደግሞ በየጊዜው መክፈል ስለማይችል ነው። እኔ በአምስት አመት፣ በአራት አመት ጊዜ ውስጥ ስለማልታመም (ሀኪም ቤት ስለማልሄድ) ለምንድነው የምከፍለው የሚሉ ሰዎች አሉ፤ ይሄ ስህተት ነው። በበሽታ ከወደቁ በኋላ ወደ ሀኪም ቤት መሄድ የሚደረገውን ህክምና በአንድ በኩል ውድ ያደርገዋል በሌላ በኩል የተጎዳ ጤንነት ስለሚኖር ለአደጋ የሚያጋልጥ

ነው። ስለዚህ የጤና መድህን ዋስትና ለዜጎች ትልቅ እፎይታ የሚፈጥር ስርዓት ነው። የጤና መድህን ስርዓት ብዙ ሀገሮች ተግብረው ውጤት ያመጡበት ነው። በዚህ ላይ መንግስት ሀላፊነት እየተሸከመ ነው ያለው። አንድ የመንግስት ሠራተኛ ለጤና መድህን ከደመወዙ በሚያዋጣበት ጊዜ መንግስትም እኩል መዋጮ ለሠራተኞቹ የሚከፍልበት ሁኔታ ነው ያለው። ስለዚህ ይሄ ስርዓት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ ከመላው የጤና መድህን ዋስትና ተጠቃሚዎች ይጠበቃል። የጤና መድህን አባል የምንሆን ሰዎች ገቢያቸው አነስተኛ የሆኑ ዜጎቻችንንም እንደግፋለን ሁላችንም በምናጠራቅመው መዋጮ አንዱ የአንዱን ሸክም ለመሸከም የሚያስችል ሀገራዊ የመደጋጋፊያ መንገድ ነው። ስለዚህ በአጠቃላይ በድምር ውጤት በሚታይበት ጊዜ የጤና መድህን ዋስትና በጣም ጠቃሚ የሆነ ፕሮግራም ነው። አንዳንድ የሚነሱ ችግሮችን በውይይት በመቅረፍና መተማመን በመፍጠር ማሻሻያዎች ማድረግ ያለብን ካለም አድርገን ማህበራዊ የጤና መድህን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል።

ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2008 በጀት አመት የመንግስትን የግማሽ በጀት አመት አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽ በአጭሩ የተወሰደ።

“የጤና መድህን ለዜጎች ትልቅ እፎይታን የሚፈጥር ስርዓት ነው። ”

ክቡር አቶ ሀይለማሪያም ደሣለኝየኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

Page 14: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

PSD Graphics 0911249276

Page 15: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና
Page 16: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200916

የጤና መድህን ለሠራተኛው ብቻ ሳይሆን ለአሰሪውም ጭምር ጥቅም እንዳለው ተወያይተናል። በእኛ በኩል አዋጁ ገና በረቂቅ ላይ እያለ ጀምሮ

ለአሰሪዎች በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተናል። አዋጁ ከወጣ

በኋላም በደንቡ ላይ ጭምር በደንብ ተወያይተናል። በውይይቶቹ የተነሱ

ሀሳቦች ተወስደው ማሻሻያዎች ተደርገውባቸዋል። ከዚህ በላይ

በአሰሪዎች በፌዴሬሽናችን አማካኝነት በኢትዮጵያ የጤና መድህ ኤጀንሲ የስራ አመራር ቦርድ አባል ሆነን እየሰራን ነው

ያለነው።

አቶ ታደለ ይመርየኢትዮጵያ አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት

እንግዳችን

Page 17: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200917

የጤና መድህን፡- የጤና መድህን አዋጅ ሲረቀቅ የአሰሪዎች ፌዴሬሽን ተሳትፎ ምን ይመስል ነበር?

አቶ ታደለ ይመር፡- የቀድሞው የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የአሁኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የጤና መድህን ስርዓትን በዚህ አገር መጀመር እንፈልጋለን ኑ እንመካከር ብለው ጠሩን። አዋጁ እኛ ባለንበት ነው ባዶ ወረቀት ይዘን የተጀመረው። አስቀድሞ ተዘጋጅቶ የተጀመረ ነገር የለም። ከባዶ ነገር ከተነሳን በኋላ የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ይምጣ ብለን ባለሙያዎች እንዲያጠኑት ተደረገ። የተለያዩ ሀገራት ተሞክሮና የሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ ገብቶ የአዋጁ ረቂቅ ተዘጋጀ። በረቂቁ ላይ ለወራት የዘለቁ ውይይቶች አድርገናል። በኋላም አሰሪዎችም በሙሉ ተገኝተው በጉዳዩ ላይ እንዲመክሩ ባቀረብነው ሀሳብ መሠረት መድረክ ተፈጥሮ ክቡር ሚኒስትሩ በተገኙበት ተወያይተናል። በአጠቃላይ የጤና መድህን አዋጅ ሲረቀቅ ጀምሮ አብረን እየተሳተፍን ነው የተዘጋጀው።

ጤና መድህን፡- የጤና መድህን ስርዓትን አስፈላጊነትና ለአሰሪዎች ያለውን ጠቀሜታ ቢገልፁልን?

አቶ ታደለ፡- የጤና መድህን ስርዓት ሠራተኛውን ብቻ ሳይሆን አሰሪውንም ነው የሚጠቅመው። የቀጠረው ሠራተኛ ሲታመም መጨነቁ አይቀርም። የጤና መድህን ትልቅ ጭንቀት ነው ከባለሀብቱ ላይ የሚያወርድለት። አንዳንድ ሰዎች እኛ

የጤና ኢንሹራንስ አለን ለምን የጤና መድህን እንገባለን ሲሉ ይደመጣሉ። ምን ያህሎቻችን ነን ለሠራተኛችን ሙሉ የጤና ሽፋን የምንሰጠው? ምናልባት ለሠራተኛ 25 ወይም 50 በመቶ የህክምና ወጪውን እንሸፍን ይሆናል እንጂ ሙሉ ለሙሉ የሚሸፍን ማግኘት አስቸጋሪ ነው። በጤና መድህን ግን አባሉን ጨምሮ የትዳር አጋር፣ 18 ዓመት ያልሞላቸው ልጆች በ3 በመቶ መዋጮ ማሳከም ይቻላል እያለ ነው መንግስት። በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው። አይበለው እንጂ አንድ ከባድ ህመም ቢገጥመን አሁን ባለው የህክምና ዋጋ ለጤና መድህን ከምናዋጣው ብዙ እጥፍ ልንከፍል እንችላለን። ብዙ ጊዜ በየሄድንበት የሚያጋጥመን ነገር አለ። የእከሌ ልጅ ታማ ሆስፒታል ተኝታለች እስኪ ገንዘብ እናዋጣላት፣ እከሌ ታሞ አልጋ ላይ ወድቋል እስኪ የአቅማችንን እናድርግለት እያልን እኮ ነው የምንኖረው። እንደዚህ ነወይ መዝለቅ ያለብን? አይደለም። ለሁላችንም የሚበጀውን ነገር ነው ማሰብ ያለብን። ሁሉም ሰው የጤና አገልግሎት ያለገንዘብ ችግር የሚያገኝበት መንገድ መቀየስ አለብን። በሌላም ሀገር ያለው ልምድ ይሄው የጤና መድህን ስርዓት ነው። ሰው አልጋ ላይ ሲወድቅ ከንፈር መምጠጥ ብቻ ምን ይፈይዳል።

እኛ አሰሪዎች አንድ ሰራተኛችን ታሞ ቤቱ ቢተኛ ሙሉ ደመወዙን እየከፈልን እስከ ስድስት ወራት የመጠበቅ ኃላፊነት አለብን። ነገር ግን አስቀድሞ የጤና እንክብካቤ ከተደረገለት ይሄ ሁሉ ችግር ተቃለለ ማለት ነው። ስለዚህ ለጤና መድህኑ ስኬት እኛም ኃላፊነት አለብን።

ውድ አንባብያን፤ የዛሬው የጤና መድህን መፅሔት እንግዳችን አቶ ታደለ ይመር ይባላሉ። በደሴ ከተማ የተወለዱት አቶ ታደለ ትውልዳቸው ከደሴ ይሁን እንጂ አምቦ፣ ሰላሌ፣ ጉደር፣ አዳማ፣ አሰላ እና አዲስ አበባ በተለያዩ ጊዜያት ያደጉባቸውና የተማሩባቸው ከተሞች ናቸው። የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ፣

በአዳማ እና በአሰላ ከተማ የተከታተሉ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከታትለው በማዕረግ ጭምር ተመርቀዋል። አስተዳደጌ ብዙ ፈተናዎች የበዙበት ነበር በማለት የሚያስታውሱት አቶ ታደለ ይመር፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ፋኩልቲ በቀን ይከታተሉት የነበረውን ትምህርት የህይወትን ፈተና ለመታገል ወደ ማታ ትምህርት እስከመቀየር ደርሰዋል። በህግ ሙያቸው ተመርቀው እየሰሩ እያለ አንድ ወዳጃቸው “በጥብቅና ስራ ብቻ ህይወት አይገፋም፣ ተጨማሪ ነገር መስራት ያስፈልጋል። ” ሲል ምክሩን ይለግሳቸዋል። ምክሩን ተጠቅመውም አንድ አነስተኛ ሆቴል መክፈታቸው የንግዱን አለም ሀ ብለው እንዲቀላቀሉ ምክንያት ሆኗል። በአነስተኛ ሆቴል የተጀመረው ንግድ ዛሬ አልታድ የተሰኘው ስመጥር ኩባንያ ባለቤት እስከ መሆን አድርሷቸዋል። ለራሳቸው ስራ ይፈልጉ የነበሩ ሰው ዛሬ የብዙ ሰዎች ቀጣሪ ሆነዋል። አቶ ታደለ ይመር ያለፉባቸው የህይወት ጉዞዎች በርካታ ናቸው። ዋና ዋናዎቹን ለመጥቀስ ብቻ በንግድ ም/ቤት አመራርነት አገልግለዋል፤ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሲሆኑ የሲቪል ማህበራት ጥምረትንም ይመራሉ። ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የስራ አመራር ቦርድ አባል ናቸው። አቶ ታደለ ይመርን በጤና መድህን ስርዓት ዙሪያ የዚህ ዕትም እንግዳችን አድርገናቸዋል። መልካም ንባብ።

Page 18: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200918

እኔ 100 ዓመት እና ከዚያም በላይ ልኖር እችላለሁ ብዬ ላስብ፤ ነገር ግን 100 ዓመት ሙሉ ግን እንዴት ጤነኛ እሆናለሁ ብዬ ማሰብ እችላለሁ። ባለቤቴስ? ልጆቼስ? ጎረቤቶቼስ? እድሜውን ሙሉ አብሮኝ የሚሰራው ሠራተኛስ? የሱ ቤተሰቦችስ ዕድሜያቸውን ሙሉ ጤነኛ ይሆናሉ? አይሆኑም። አንድ ሰው እኔ አልታመምምና ለምን የጤና መድህን አባል እሆናለሁ የሚለው ተገቢ አይደለም። እኛ በምናዋጣው ገንዘብ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ይታከሙበታል። የጤና መድህን ስርዓትን እንደ ኢንሹራንስ ነው ልናየው የሚገባው። እኔ ለምሳሌ ለተሽከርካሪዬ ኢንሹራንስ እከፍላለሁ፤ በተሽከርካሪዬ ላይ አደጋ ሊደርስ ወይም ላይደርስ ይችላል። ነገር ግን አደጋ አልደረሰምና ገንዘቤን መልሱልኝ ማለት አልችልም። ምክንያቱም አደጋ ላጋጠማቸው ሌሎች ተሽከርካሪዎች ከእኔም ከሌሎችም ከወሰዱት ክፍያ ነው የኢንሹራንስ ሽፋን የሚሰጡት። የጤና መድህን ሽፋንም ተመሳሳይ ነው። አንዱ አንዱን የሚደግፍበት ስርዓት ነው።

ጤና መድህን፡- በጤና መድህን አዋጅና ደንቦች ላይ ከአሰሪዎች ጋር የተደረጉ ውይይቶች ነበሩ? ከነበሩ የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች ምን ነበሩ?

አቶ ታደለ ይመር፡- በአዋጁ ላይ ሶስት አራት ጊዜ ነው የተነጋገርንበት። የጤና መድህን ለሠራተኛው ብቻ ሳይሆን ለአሰሪውም ጭምር ጥቅም እንዳለው ተወያይተናል። በእኛ በኩል አዋጁ ገና በረቂቅ ላይ እያለ ጀምሮ ለአሰሪዎች በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተናል። አዋጁ ከወጣ በኋላም በደንቡ ላይ ጭምር በደንብ ተወያይተናል። በውይይቶቹ የተነሱ ሀሳቦች ተወስደው ማሻሻያዎች ተደርገውባቸዋል። ከዚህ በላይ አሰሪዎች በፌዴሬሽናችን አማካኝነት በኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የስራ አመራር ቦርድ አባል ሆነን እየሰራን ነው ያለነው። ሰራተኞችም በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አማካኝነት በቦርድ አመራርነት እየሰሩ ነው። በጋራ ቁጭ ብለን እየመከርን እየወሰንን ነው ያለነው።

ጤና መድህን፡- በቀጣይ ለማህበራዊ የጤና መድህን ትግበራ ከአሰሪዎች ምን ይጠበቃል ይላሉ?

አቶ ታደለ ይመር፡- ለኢትዮጵያ አሰሪዎችም ሆኑ ባለሀብቶች የማስተላልፈው መልዕክት በአሰሪ ህጋችን ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው አንድ ሰራተኛ ከቀጠረ ሰው ጀምሮ ህጋችን ያንን ሰው አሰሪ ይለዋል። አለም አቀፍ ኮንቬንሽኖችም

(ስምምነቶችም)ቀጥረህ የምታሰራው ሠራተኛ አንድ ሰውም ቢሆን ቀጣሪው ስለሆንክ ለዚህ ሰው ማንኛውንም መብቶቹን ልታከብርለት ይገባል ይላል። አንድ በፋብሪካችን (መ/ቤታችን) ውስጥ የሚሰራ ሰው ደመወዙ አንድ ሺህ ብር ቢሆን በወር ለጤና መድህን የሚያዋጣው 30 ብር ነው። በአመት 360 ብር አዋጥቶ የራሱን፣ የሚስቱን፣ የልጆቹን የጤና ዋስትና ያረጋግጣል። ይሄ ሰውዬ ልጁ፣ ሚስቱ ወይንም እራሱ ቢታመም ስንት ብር እንደሚያወጣ የምናውቀው ጉዳይ ነው። የካርድ፣ የምርመራ፣ የመድሃኒት ተብሎ የሚጠየቀውን መሸፈን አይችልም። ስለዚህ የሠራተኞቻችንን ደህንነት ማረጋገጥ አለብን። ሠራተኛም ቢሆን ጤና መድህን ጥቂት ገንዘብ አዋጥቶ የራሱንና የቤተሰቡን የጤና ዋስትና ማረጋገጥ የሚያስችለው በመሆኑ ረጋ ብሎ ጠቀሜታውን ማጤን ይኖርበታል ባይ ነኝ።

ጤና መድህን፡- አንዳንድ አሰሪዎችና ሠራተኞቻቸው መ/ቤታችን የህክምና ወጪን ስለሚሸፍን የጤና መድህን አባል መሆን አይገባንም ሲሉ ይደመጣሉ። እዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?

አቶ ታደለ ይመር፡- እርግጥ ነው አንዳንድ ተቋማት የሰራተኞቻቸውን የህክምና ወጪ ይጋራሉ። አንዳንዱ 25 በመቶ ሌላው 50 በመቶ ይከፍላሉ። 100% የህክምና ወጪ የሚሸፍኑ በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። እነሱም ቢሆኑ የሰራተኛውን እንጂ የቤተሰቡን የህክምና ወጪ አይሸፍኑም። አሁን መንግስት ተግባራዊ ሊያደርግ ያቀደው የጤና መድህን ስርዓት ግን የሰራተኛውን የትዳር አጋር እንዲሁም 18 ዓመት ያልሞላቸውን ልጆቹን ጭምር ነው ተጠቃሚ የሚያደርገው።

ከዚህ በላይ ማሰብ ያለብን ግን የጤና መድህን ትልቁ ጉዳይ በራስ ወይም በቤተሰብ አባል ላይ የሚደርስን የጤና እክል ከመታደግ ባለፈ በመደጋገፍ መርህ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን ወገኖቻችንን በየወሩ በምናደርገው መዋጮ የምንደግፍበት እድል ይሰጠናል። የሌሎችን ሸክም እናቀልላቸዋለን። ጤና መድህን የተሻለ ገቢ ያለው አነስተኛ ገቢ ያለውን፣ ጤነኛው በአንፃሩ ታማሚውን የሚደግፍበት ስርዓት በመሆኑ ለዚህ ስኬት ሁላችንም መረባረብ ይገባናል። እስካሁን እኮ አንድ ግለሰብ ሲታመም ሜዳ ላይ ነበር የሚወድቀው፣ አሁን ግን ሜዳ ላይ አትወድቅም የሚለው የተደራጀ የህዝብ አጋር እያገኘ ነው።

Page 19: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200919

ሌላው ጉዳይ ከዚህ ቀደም ለሰራተኞቻቸው የህክምና ወጪ ይሸፍኑ የነበሩ ድርጅቶች ሠራተኞቻቸውን ለጤና መድህን ስላስመዘገቡ ብቻ ከዚህ በፊት ሲሰጡት የነበረውን አገልግሎት ያቆማሉ አይልም አዋጁ። በህብረት ስምምነት የተገኙ ጥቅማጥቅሞችን ማስቀጠልን ይፈቅዳል። ከዚህ በፊት ይሰጥ የነበረውን ሁሉ መቀጠል ወይም በጤና መድህኑ የማይሰጡ አገልግሎቶችን ከሠራተኞቹ ጋር በመመካከር ማሟላት ይችላል። የጤና መድህን ስርዓትን ከአገራዊ ጥቅሙ አኳያ ነው በዋናነት ማየት የሚገባን ባይ ነኝ።

ጤና መድህን፡- በመጨረሻ የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ እድሉን እንስጥዎት?

አቶ ታደለ ይመር፡- በህይወት እያለሁ የሀገሬን እድገትና ብልፅግና ማየት እፈልጋለሁ። የወገኔ የጤና መድህንን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ ዋስትናዎቹ ተረጋግጠው ማየት በጣም የሚያጓጓኝ ነገር ነው። እድገት ስልጣኔ ማለት እኮ ይሄ ነው። ለዚህ ስኬት ደግሞ ሰራተኛውም፣ አሰሪውም መንግስትም በአንድነት መረባረብ ይገባናል።

ጤና መድህን፡- አቶ ታደለ ውድ ጊዜዎትን ሰጥተው ለቃለ-ምልልስ ስለተባበሩን እናመሰግናለን።

አቶ ታደለ፡- እኔም አመሰግናለሁ።

የጤና መድህን ትልቁ ጉዳይ በራስ ወይም በቤተሰብ አባል ላይ የሚደርስን የጤና እክል ከመታደግ ባለፈ በመደጋገፍ መርህ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን ወገኖቻችንን

በየወሩ በምናደርገው መዋጮ የምንደግፍበት እድል ይሰጠናል። የሌሎችን ሸክም እናቀልላቸዋለን። ጤና መድህን የተሻለ ገቢ ያለው አነስተኛ ገቢ ያለውን፣ ጤነኛው

በአንፃሩ ታማሚውን የሚደግፍበት ስርዓት በመሆኑ ለዚህ ስኬት

ሁላችንም መረባረብ ይገባናል።

Page 20: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200920

ህጻን ህይወት አበበ ሁሌም እንደምታደርገው ከጎረቤት እኩያ ህጻናት ጋር እየተጫወተች ነበር። በባዶ

እግሯ በቡረቃ ወዲህ፣ ወዲያ ስትል ድንገት ‹‹ ጠቅ! ›› የሚያደርግ ሃይለኛ የህመም ስሜት ተሰማትና ጨዋታዋን ለማቋረጥ ተገደደች። የህመሟ መንስኤ ምን እንደሆነ ለማወቅ ወደ አመማት ቦታ ለማየት ሞከረች። ተረከዟ አካባቢ እየደማ ነበር። በእጇ ተረከዝዋን ነካ፣ነካ አደረገችው። ሃይለኛ የህመም ሥሜት ድጋሚ ተሰማት። ‹‹ እሾክ ወግቶኛል ማለት ነው!!›› አለችና እያነከሰች ወደ ቤቷ ሮጠች።

ወደቤት እንደገባች የተፈጠረውን አንዳች ሳታስቀር በሚጣፍጥ የህጻን አንደበቷ ለእናቷ ወ/ሮ የውብርስት አንለይ ተረከችላት። ወ/ሮ ውብርስትም ህጻናት ሲቦርቁ በእሾህ መወጋታቸው ያለ ነገር በመሆኑ ለሌላ ጊዜ ጫማዋን ሳታደርግ ከቤት እንዳትወጣ አስጠንቅቀው እሾሁን በመርፌ ተጠንቅቀው ያወጡላታል።

ህይወት ልጅ ነችና የጨዋታ ነገር ሆኖባት እናቷን ተደብቃና ጫማዋን አድርጋ በድጋሚ ወደ ጨዋታዋ ለመመለስ ሞከረች። የሚሰማት ህመም ብዙም አላላወሳትም።

ደምበጫ- የማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን ተምሳሌት!

ስኬት

በሀበታሙ ቦጋለ

Page 21: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200921

እናትም የልጃቸውን ከቤት ድጋሚ መውጣት ብዙም ልብ ሳይሉት የቤት ውስጥ ጉድጉዳቸውን ቀጠሉ። በእንዲህ አይነት ሁኔታ ቀኑ አለፈ።

በማግስቱ ጠዋት የቤተሰቡ አባላት ለ ተ ለ መ ደ ው የ ሥ ራ እ ን ቀ ስ ቃ ሴ ለመሰማራት ተፍ ፣ ተፍ ሲሉ ህጻን ህይወት ግን መኝታዋ ውጥ ሆና ህመም የወለደው የስቃይ ድምጽ እያሰማች ታለቅሳለች። አባት ማልደው ወጥተዋል። እናት ምን እንደተፈጠረ ህይወትን ሲጠይቋት ትናንት እሾህ የነቀሉላትንና ያለመጠን ያበጠውን እግሯን አሳየቻቸው። እናት ደነገጡ።

የጤና መድህን ካርዳቸውን ካስቀመጡበት አንስተው አጠገባቸው ወደሚገኝ ‹‹ ዋድ ጤና ጣቢያ›› በፍጥነት ገሰገሱ። ጤና

ጣቢያው እንደደረሱ የመድን ካርዳቸውን በማሳየት ህይወትን ከድንገተኛ ታካሚ ክፍል አስገቧት። ህይወት አስፈላጊ ምርመራ ከተደረገላት በኋላ ለእናትየው‹‹ በወጋት እሾህ ምክንያት የተከሰተው ጉዳት ከአቅማችን በላይ ስለሆነ በአስቸኳይ ህጻንዋን ይዘሽ ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል ውሰጃት!!.... የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አባል ስለሆናችሁ ክፍያውን መድህኑ ስለሚሸፍንላችሁ ጊዜ አታባክኑ!! ›› የሚል ማስጠንቀቅያ ይደርሳቸዋል።

ወ/ሮ ውብርስት ከጤና ጣቢያ የሰሙትን ነገር ሁሉ ለባለቤታቸው ለአቶ አበበ የሹ በመግለጽ በፍጥነት ከደንበጫ ወረዳ በሃምሳ ኪሎ ሜትር ወደምትገኘው ደብረማርቆስ ልጃቸውን ይዘው

ይገሰግሳሉ። ሆስፒታል እንደደረሱ ‹‹ የሪፈር ›› ወረቀታቸውን ሲያሳዩ ለህጻኗ አስቸኳይ ህክምና ለማድረግ የሆስፒታሉ ሰራተኞች ይረባረባሉ። ከተገኘው ምርመራ ውጤት ህይወት ቀዶ ጥገና እንደሚያስፈልጋት ተገለፀላቸው። እንደቀልድ በጫወታ ወቅት እግሯን የወጋው እሾህ ህይወቷን እንዳይቀጥፈው ህጻን ህይወት ለአስራ ሰባት ቀናት በሆስፒታሉ በተደረገላት ከፍተኛ ህክምና ህይወቷ ሊተርፍ ቻለ። ከህመሟ ሙሉ፣ በሙሉ እስክትፈወስ አሁንም እየተመላለሰች የህክምና ክትትል ይደረግላታል።

‹‹ ልጄን እንደቀልድ አጥቻት ነበር›› ይላሉ የህይወት እናት ወ/ሮ ውብርስት አንለይ። ‹‹ በተባረከ ቀን የማህበረሰብ አቀፍ

Page 22: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200922

የጤና መድህን አባል በመሆኔ ዶሮ የማትገዛ ትንሽ ገንዘብ በቅድሚያ አዋጥቼ ይኸው የልጄን ህይወት ለማትረፍ ችያለው።››

የህጻኗ አባት አቶ አበበ የሹ በበኩላቸው በጤና መድህኑ የተደረገላቸውን ድጋፍ ሲገልጹ ‹‹ ለልጄ ህክምና የወጣው ወጪ በገንዘብ ሲገመት ከአሥራ ሁለት ሺህ ብር በላይ ይሆናል። እንግዲህ ይታያችሁ ይህን ድንገት አምጣ ብባል ያለኝ አማራጭ ሁለት ነበር።ገንዘብ የሚያበድረኝን ሰው መፈለግ ወይ የልጄን ህይወት ለማዳን ያለኝን መሸጥ!! …. ይሄ ጤና መድህን በወረዳችን የተጀመረው እንደኔ ያሉትን ሁሉ ለመታደግ ነው። ››

***የደምበጫ ወረዳ በአማራ ክልላዊ መንግስት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን ውስጥ ትገኛለች። 25 የገጠርና 2 የከተማገጠርቀበሌ፣ በአጠቃላይ 27 ቀበሌዎች ያላት ሲሆን 147,710 ህዝብ ይኖርበታል። በዚህችወረዳ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት መስጠት የጀመረው የዛሬ ሁለት ዓመት በ 2006 ዓ.ም ነበር።

በእነኚህ ሁለት ዓመታት እንደ ህጻን ህይወት አበበ በድንገት በሚከሰት ህመመም ሊሞቱ ይችሉ የነበሩ ዜጎችን ህይወት ታድጓል፣ እንደ አቶ አበበና ወ/ሮ ውብርስት ቤተሰብ ዶሮ በማትገዛ አነስተኛ ቅድሚያ መዋጮ በርካታ ቤተሰብ ለህክምና ወጪ ሲል መበደር ወይም ንብረቱን መሸጥ ሳይጠበቅበት የያዘውን የአባልነት ካርድ በማሳየት ብቻ የህክምና አገልግሎት ማግኘት ችሏል።

‹‹ ገና እንደጀመርን አገልግሎቱ አዲስ እንደ መሆኑ መጠን ህብረተሰቡን ማሳመን ከባድ ፈተና ሆኖብን ነበር። ›› ይላሉ ወ/ሮ ያጀብ ሥማቸው በደንበጫ ዙርያ መረዳ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አስተባባሪ። ‹‹ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መስራት የጀመርነው ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ነው። በወረዳዋ የጤና መድህኑ አባል መሆን የሚችሉ20,056 አባወራዎች ይኖራሉ። ከነዚህ ውስጥ አገልግሎት

መስጠት በጀመርንበት ዓመት በ2006 ዓ.ም አባላት ለመሆን የተመዘገቡልን የአባወራዎች ብዛት 7,798 ብቻ ነበሩ። ይህ ማለት አባል መሆን ከሚችለውየወረዳዋ ነዋሪዎች ውስጥ 39 በመቶ ብቻ ነው። ይህ ደግሞ በአመራሩ ዘንድ ጥያቄ ፈጠረ። ችግሩ እኛ ስለ አገልግሎቱ ለህብረተሰቡ በደንብ ማስረዳት አቅቶን ነው ወይስ ህብረተሰቡ አገልግሎቱን አይፈልገውም? በሚለው ነጥብ ላይ የወረዳው ካቢኔ ከፍተኛ ግምገማ አካሄደ።›› በማለትወ/ሮ ያጀብ ሥማቸው የወረዳዋ ስኬት ከየት እንደጀመረ ያስታውሳሉ።

ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የወረዳው መስተዳድር ተሰሚነት ያለቸውን የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች፣ በወረዳዋ የገጠር ቀበሌዎች ሰፊ ሥራ የሚሰሩ ሰራተኞችን፣ የቀበሌ ሚኒሻዎችን ፣ የግብርና ልማት ሰራተኞችንና የጤና ኤክስቴንሽኞችን በማሰባሰብ ሰፊ ውይይት ተካሄደ። በውይይቱ ላይም ‹‹ እውነት ይሄ የምትሉት የጤና መድህን በትክክል የሚተገበር ከሆነ ህዝባችን ከፍተኛ ተጠቃሚ ሥለሚሆን ሁላችንም በቁርጠኝነት ለመስራት ቃል እንገባለን!!›› የሚሉ አስተያየቶች ከየአቅጣጫው ጎረፉ።

የወረዳዋ መስተዳድር ምን ብናደርግ ነው ሥለ አገልግሎቱ ህዝቡን በሚገባ አስረድተን ለአባልነት ማንቀሳቀስ የሚቻለው? በሚለው ነጥብ ላይ ሰፊ ውይይት አካሄደ።የስብሰባው ታዳሚዎችም ‹‹ የጤና መድህን ሳምንት›› የሚል የህዝብ ንቅናቄ ለመፍጠርና አንደኛ ህዝቡ ስለ ማ.አ.ጤ.መ በሚገባ ተረድቶ አባል እንዲሆን ግንዛቤውን ማስፋት፣ ሁለተኛ ሥራው የሚመለከታቸው አካላት ሙሉ አትኩሮታቸውን ሙሉ በሙሉ የጤና መድህኑ ሥራ ላይ እንዲያውሉ፣ ሦስተኛ ለአባልነት የሚያስፈልጉ የምዝገባና የአባልነት መታወቂያ ቁሳቁስ በቅድምያ ተዘጋጅቶ እንዲጠናቀቅ ስምምነት ላይ ተደረሰ።

ከዚያ በየቀበሌው አባል የሆኑትን፣አባል ካልሆኑት የመለየትና ደረሰኞችን የማዘጋጀት የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቆ በወረዳዉ በሚገኙ ቀበሌዎች

Page 23: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200923

ሁሉ ሥለ ጤና መድህኑ ምንነትና ጠቀሜታ ለህብረተሰቡ ለማስረዳት የወረዳውን የካቢኔ አባላት ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉ ‹‹ በጤና መድህኑ ሳምንት›› ሊሰሩ የታቀዱ ተግባራትን እውን ለማድረግ ከጫፍ እስከጫፍ ተንቀሳቀሱ። በተደረገውም የግንዛቤ ማስጨበጫ ለአባልነት የሚጠበቅባቸው ዓመታዊ ክፍያ 144 ብር ብቻ በመሆኑ በቆላ አካባቢ የሚኖሩ የወረዳው ነዋሪዎች በርበሬ አምራቾች ናቸውና ‹‹ የምትሉን እውነት ከሆነ የጠየቃችሁን 4 ኪሎ በርበሬ ዋጋ የማትሆን ናት !!›› ሲሉ ደገኞቹ ደግሞ ‹‹ ይህቺማ የአንድ ዶሮ ዋጋም አትሞላም !!›› በማለት በገቢያቸው አይነትና መጠን የዓመታዊ መዋጮዋቸውን አስልተው አባል ለመሆን ቃል ገቡ።

‹‹ በዚያች ሳምንት ውስጥ 10,606 አባወራዎችን በአዲስ አባልነት መመዝገብ ቻልን። ይሄም በፊት ከነበሩን አባላት ጋር ተደማምሮ የአባላቶቻችን ቁጥር መጠን ከ 99 % በላይ ደረሰ።›› በማለት ስለ በጤና መድህኑ ሳምንቱ የተከናወነውን የህዝብ ንቅናቄወ/ሮ ያጀብ ስማቸው ያስታውሳሉ።

‹‹ የሥኬታችን ሚስጢር ለጋራ ዓላማ አንድ ሆነን መነሳታችን ነው!!›› ይላሉ አቶ ዕድሜዓለም አንተነህ የደንበጫ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ። ‹‹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ህዝቡን ከጥግ እስከ ጥግ ለማንቀሳቀስ ከመነሳታችን በፊት ከማን ምን ይጠበቃል? ሚለውን ለመመለስ ሞክረናል። እንደ ወረዳ መስተዳድር ከወረዳው ምን ይጠበቃል? ... የቀበሌዎችስ ኃላፊነትና ድርሻ ምንድነው? በወረዳችን ሥድስት ጤና ጣቢያዎች አሉ። አገልግሎት ከመስጠት

አንጻር ለመድህኑ ስኬት ከእነሱስ ምን ይጠበቃል?...የህብረተሰቡስ መብትና ግዴታ ምንድነው? የሚሉትን ጥያቄዎች አጥርተን በመንቀሳቀሳችን የተገኘውን ስኬት ከማስገንዘባችን በተጨማሪም ባለፈው አመት የጤና መድህን አባል የነበሩ ሰዎች የአባልነት ዕድሳት 100% ለማከናወን ችለናል። ዛሬ በየትኛውም የወረዳው ክፍል ስለ የ.ማ.አ.ጤ.መ ጠቀሜታ የማያውቅ የለም።››

***መንግስት የጤናውን ዘርፍ ለሁሉም ዜጋ ተደራሽ ለማድረግ በዋነኝነት መደበኛ ባልሆነ ክፍለ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚገኘውን የህብረተሰብ ክፍልን የሚያቅፈው ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓት በአራት ክልሎች

‹‹ የሥኬታችን ሚስጢር ለጋራ

ዓላማ አንድ ሆነን መነሳታችን ነው!!››

አቶ ዕድሜዓለም አንተነህ

Page 24: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200924

ማለትም በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት እና በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በሚገኙ 13 ወረዳዎች በ2003 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ነበርበሙከራ ደረጃ የጀመረው።

የዛሬ አምስት ዓመት የተጀመረው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመገምገም በተሰራ የማስፋፍያ ሥራ በአሁን ወቅት ከ 300 በላይ በሚሆኑ የሀገሪቱ ወረዳዎች በተለያየ ምዕራፍ እየተተገበረ ነው። ይህም በተመሳሳይ ሥርዓቱን ለመተግበር ከሞከሩ ሌሎች አገሮች አንጻር ሲታይ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተመዘገበ ከፍተኛ ስኬት ሊባል የሚችል ነው።

በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አተገባበር ላይ የሚታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ከክልል፣ ክልል፣ ከዞን ዞን፣ ከወረዳ ወረዳ የተለያዩ ቢሆንም በደንበጫ ወረዳ እየተከናወነ ያለው የአመራር ሰጪዎች ትጋትና የጤና አገልግሎት ተቋማት እያሳዩ ያሉት ፈጠራ የታከለበት ጠንካራ ሥራ ለሌሎችም ትልቅ አርዓያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። በቅርቡ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በተደረገ ድጋፋዊ ጉብኝት ( Supportive supervi-sion ) የመድህን ሥርዓቱ በተተገበረባቸው ተመሳሳይ ወረዳዎች ከአባላት ከተሰሙ ቅሬታዎች ውስጥ ‹‹ በአባልነታችን በርካታ ጥቅሞችን ብናገኝም አገልግሎት በምናገኝበት የጤና ተቋማት የመድሀኒት እጥረት ስላለ ከውጭ ግዙ ሥለምንባል ያውጣነው ወጪ ተመላሽም ቢሆን ላላስፈላጊ እንግልት እየተዳረግን ነው።›› የሚል ነበር።

ቀደም ሲል ይህ ችግር በደንበጫ ወረዳም ይከሰት ሥለነበር ችግሩን ለመቅረፍ የደምበጫ ጤና ተቋማት ለመላው ሃገሪቱ ምሳሌ የሚሆን ትስስር ፈጠሩ።በወረዳውማ.አ.ጤ.መሲጀመርአገልግሎትለመስጠትውልይዘው የገቡ 6 ጤናጣቢያዎችና 3 ሆስፒታሎች ናቸው።በአገልግሎት ተቋማት ውስጥ የሚከሰተውን የመድሃኒት እጥረትና የአባላት እንግልት ለማስቀረት በደንበጫ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ 6ቱ ጤና ጣቢያዎች ተናበው የሚሰሩበትን መንገድ ቀየሱ።

አቶ አንተነህ ጀምበሬበደምበጫ ዙርያ የዋድ ወረዳ ጤና ጣቢያ ተወካይ ኃላፊ

የጤና መድህኑ በወረዳችን ከመጀመሩ በፊት ህብረተሰቡ ወደ ጤና ተቋም ለመምጣት መበደር አለበት አልያም

ያለውን ጥሪቱን ለመሸጥ ይገደድ ነበር። በዚህ የተነሳ ሌላ አማራጮችን ሲጠቀም ቆይቶ ሊሞት ጥቂት ሲቀረው ነበር ወደ ጤና ተቋማት በቃሬዛ የሚመጣው። ዛሬ

ከዚህ አልፎ የጤና መድህኑ መጀመሩ የጤና ጉዳይ ያገባኛል የሚልና አገልግሎቱን

የመገምገም ብቃት ያለው ሞጋች ማህበረሰብ ፈጥሮልናል።

Page 25: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200925

‹‹ በወረዳችን አንድም የጤና መድህኑ አባል ከውጪ መድሃኒት መግዛት የለበትም የሚል ጠንካራ አቋም ሥድስቱም ጤና ጣቢያዎች ውስጥ የምንሰራ ባለሙያዎች ያዝን።›› ይላል አቶ ስለሺ ጥላዬ የመድሃኒት ባለሞያና የዋድ ጤና ጣቢያ ተወካይ። ‹‹ የእኛ ዓላማ በጤና ትራንስፎርሜሽኑ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው አገልግሎት ለማግኘት ለሚመጡ ደንበኞቻችን ቅንና ርህሩህ አገልጋይ መሆን ነው። የዋድ ጤና ጣቢያ በሥድስት ቀበሌ ለሚኖሩ 38, 138 ህዝብ አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተቋቋመ ነው። የጤና መድህኑ ከመጀመሩ በፊት በቀን ከ 20 እስከ 30 ሰዎችን ብቻ ነበር የምናስተናግደው። አሁን ካለምንም ማጋነን በቀን 80 እስከ 90 ታካሚ እናስተናግዳለን። ይህ መሆኑ ጤና ጣቢያው ከመድህኑ በሚያገኘው የአገልግሎት ክፍያ የገቢ መጠኑ እጅግ ጨምሯል። ስለሆነም በውስጥ ገቢያችን የሚጎድሉንን የመድሃኒትና የላብራቶሪ ቁሳቁሶችን ያለምንም ችግር እናሟላለን።ድንገተኛ የመድሃኒት እጥረት ቢከሰት እንኳን በፈጠርነው ትስስር የጎደለንን መድሃኒት ወደ አንዱ ደውለን እንዋሳለን፣ ሌሎችም ተመሳሳይ ችግር ሲገጥማቸው ከእኛ ይዋሳሉ። ይህ የጤና መድህን መጀመሩ ለህብረተሰቡ ብቻ ሳይሆን ለአገልግሎት ሰጪዎችም ትልቅ የሙያ እርካታ አስገኝቷል። በፊት ህመምተኛው የሚታዘዝለትን መድሃኒት የመግዛት አቅም አለው ወይስ የለውም በማለት እንጨነቅ ነበር።››

አቶ አንተነህ ጀምበሬ የደምበጫ ዙርያ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን በወረዳቸው መጀመሩ ያመጣውን

ጠቀሜታ በአድናቆት ይገልጻሉ።‹‹ የጤና መድህኑ በወረዳችን ከመጀመሩ በፊት ህብረተሰቡ ወደ ጤና ተቋም ለመምጣት መበደር አለበት አልያም ያለውን ጥሪቱን ለመሸጥ ይገደድ ነበር። በዚህ የተነሳ ሌላ አማራጮችን ሲጠቀም ቆይቶ ሊሞት ጥቂት ሲቀረው ነበር ወደ ጤና ተቋማት በቃሬዛ የሚመጣው። ዛሬ ከዚህ አልፎ የጤና መድህኑ መጀመሩ የጤና ጉዳይ ያገባኛል የሚልና አገልግሎቱን የመገምገም ብቃት ያለው ሞጋች ማህበረሰብ ፈጥሮልናል። ከዚህ በተጨማሪ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የውስጥ ገቢያቸው በሁለትና ሦስት

እጥፍ በመጨመሩ የጎደላቸውን ነገር ለሟሟላትሰፊ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል።

በአጠቃላይ የደምበጫ ወረዳ በሁለት አመት ውስጥ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህንን በተሳካ መልኩ ተግባራዊ ከማድረግ ረገድ ለሌሎችም ክልሎች ሦስት ዋና ዋና ቁምነገሮችን በአርዓያነተአስመዝግበዋል። አንደኛ የአመራር አካሉ ሙሉ ጥሞና ሰጥቶ ለአገልግሎቱ ቁርጠኝነት ማሳየቱን፣ ሁለተኛ የጤና ተቋማቱን ዝግጁነትና መናበብ፣ ሦስተኛ የህብረተሰቡን ግንዛቤና ተሳትፎ መገንዘብ ይቻላል።

‹‹ በዚያች ሳምንት ውስጥ 10,606 አባወራዎችን በአዲስ አባልነት መመዝገብ ቻልን። ይሄም በፊት ከነበሩን አባላት ጋር ተደማምሮ

የአባላቶቻችን ቁጥር መጠን ከ 99 % በላይ ደረሰ።››

ወ/ሮ ያጀብ ስማቸው

Page 26: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200926

ጤና ተቋማት የህብረተሰቡን ባለቤትነት ለመጨመርና ቀልጣፋ የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል በሥራ ቦርድ እንዲመሩ ማድረግ፣

ሕክምና ነክ ያልሆኑ አገልግሎቶችን በሶስተኛ ወገን እንዲሰሩ በውል ማስተላለፍ፣

የጤና አገልግሎት ክፍያ የሕብረተሰብን አቅም ባገናዘበ መልኩ በየጊዜው እንዲከለስ ማድረግ፣

የጤና ባለሙያዎች ከመደበኛ የስራ ስዓት ውጪ በጤና ተቋሙ ውስጥ በተከፈተ የግል ሕክምና ክፍል እንዲሰሩ መፍቀድ ናቸው።

እነዚህ ማሻሻያዎች የመጀመሪያ ደረጃ ማሻሻያ (First Generation) በመባል የሚታወቁ ሲሆን በአብዛኛው ትኩረታቸው በአቅርቦት በኩል የነበረውን ክፍተት ማቃለል ነው።

ስኬት

በማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን የማስፋት ስትራቴጂ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር በተካሄደበት ወቅት

የኢፌዴሪ መንግስት ለጤናው ዘርፍ የሚውለውን የፋይናንስ አሰባሰብና አጠቃቀም ለማሻሻል የሚረዳ የጤና ፋይናንስ ስልት እ.ኤ.አ ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ በመተግበር ላይ ይገኛል።

በዚህ የፋይናንስ ስልት ለጤናው ዘርፍ የሚውለውን አጠቃላይ የሀብት መጠን የሚጨምሩ፣ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት የሚያሻሽሉ፣ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ፣ የጤናው ዘርፍ የመልካም አስተዳደር እና የተጠያቂነት ሁኔታን የሚያሰፍኑ፣ የጤና ባለሙያዎች በመንግሥት ተቋማት ውስጥ እንዲቆዩ የሚያበረታቱ እና ተነሳሽነትን የሚጨምሩ የተለያዩ እርምጃዎች ተቀምጠዋል። እነሱም፡-

የጤና ተቋማት ከአገልግሎት ክፍያ የሚሰበስቡትን ገንዘብ የውስጥ ገቢያቸው አድርገው እንዲጠቀሙበት ማስቻል፣

አቅም የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በመንግስት ድጎማ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ እና ህብረተሰባዊ ፋይዳ ያላቸውን የጤና አገልግሎቶች ለሁሉም ዜጋ ያለክፍያ ማቅረብ፣

የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህንን - ከሙከራ ወደ ሀገር አቀፍ የማስፋት እንቅስቃሴበዘላለም አበበ

Page 27: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200927

በመጀመሪያ ደረጃ ማሻሻያዎች በርካታ አበረታች ውጤቶች የተገኙ ቢሆንም በጤናው ዘርፍ የፋይናንስ ስልት ላይ ባሉ አጠቃላይ ተግዳሮቶች ምክንያት አሁንም የተለያዩ ችግሮች ይንፀባረቃሉ።

የጤናው ዘርፍ ፋይናንስ ካሉበት አጠቃላይ ችግሮች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።

የሀገሪቱ የጤና ፋይናንስ በአብዛኛው በልማት አጋሮች እርዳታ ላይ የተንጠለጠለ መሆኑ፣

መንግስት ከአጠቃላይ ታክስ እና ሌሎች ገቢዎች ውስጥ ለጤናው ዘርፍ የሚያስፈልገውን ያህል በጀት ለመመደብ የአቅም ውስንነት ያለበት መሆኑ፣

የጤና አገልግሎት የክፍያ ስርዓት

ዜጎች እንደ አቅማቸው የሚከፍሉበት ባለመሆኑ ፍትሐዊነትን ያሰፈነ ባለመሆኑ፣

በሕክምና ወቅት ዜጎች ከኪሳቸው የሚያወጡት ወጪ ከፍተኛ በመሆኑ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጫናዎች የሚዳርግ መሆኑ በዋናነት የሚነሱ ችግሮች ናቸው።

በመሆኑም በመጀመሪያው ደረጃ የጤና ፋይናንስ ማሻሻያዎች የተገኙት ውጤቶችን ለማጠናከርና አሁንም የጤናውን ዘርፍ የፋይናንስ ስርዓት እየተገዳደሩ ያሉትን ችግሮች ለማቃለል መንግስት ሁለተኛ ደረጃ ማሻሻያ (Sec-ond Generation) የፋይናንስ ስልት ተብሎ የሚታወቀውን የጤና መድህን

ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል።

በኢፌዴሪ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በ2000 ዓ.ም. የፀደቀው የጤና መድህን ስትራቴጂ መንግስት ሁለት ዓይነት የጤና መድህን ሥርዓት እንደሚተገብር ያስቀምጣል። እነሱም የማህበራዊ የጤና መድህን እና የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓቶች ሲሆኑ ሁሉም ዜጋ በጤና መድህን የሚታቀፍበት አሰራር ተዘርግቷል።

የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን

የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን ተጠቃሚ የሚያደርገው በአብዛኛው በገጠር የሚኖረውን የሕብረተሰብ ክፍል ሲሆን በከተማም ከመደበኛ ክፍለ-ኢኮኖሚ ውጪ የሆኑትን ዜጎች

ከሙከራ ወደ ሀገር አቀፍ የማስፋት እንቅስቃሴ

Page 28: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200928

ማለትም በአነስተኛና በጥቃቅን ስራዎች የተሰማሩትን የህብረተሰብ ክፍሎች ጭምር የሚያካትት የጤና መድህን ሥርዓት ነው።

የሙከራ ትግበራው አጀማመር

በአገራችን የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህንን ተግባራዊ ለማድረግ የተመረጠው አካሄድ በተወሰኑ ወረዳዎች የሙከራ ትግበራ በማድረግና ከትግበራው የሚገኙትን ልምዶች በመቀመር ወደ ማስፋት ስራ መግባት ነው።

በዚሁ መሰረት ማዐጤመ በአራት ክልሎች ማለትም በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ ብ/ብ/ሕዝቦች እና በትግራይ ክልሎች ውስጥ በተመረጡ13 ወረዳዎች ላይ ከ 2003 ዓም ጀምር ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል።

የሙከራ ትግበራው ውጤቶች

የማዐጤመ የሙከራ ትግበራ ለሁለት ዓመታት ከተከናወነ በኋላ በሙከራ ትግበራ ወቅት የተገኙ ውጤቶችና ያጋጠሙ ችግሮችን የሚዳስስ የግምገማ ጥናት በ2006 ዓ.ም. ተከናውኗል። በተደረገው የግምገማ ጥናት ፕሮግራሙ በአመዛኙ ውጤታማ መሆኑንና በአገር አቀፍ ደረጃ ሊሰፋ እንደሚችል ይጠቁማል።

ከማአጤመ የሙከራ ትግበራ የተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች የሚከተሉት ናቸው።

ሰፊ የአባልነት ሽፋን፡

ማአጤመ በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ በተደረገባቸው ወረዳዎች በማአጤመ መታቀፍ ከሚገባቸው አባወራዎች ውስጥ 52.4 በመቶ የሚሆኑ በአባልነት ተመዝግበዋል። ይህም ኘሮግራሙ

በሕብረተሰቡ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት እና የሚመለከታቸው የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት የሰጡትን ትኩረት ያሳያል።

ከፍ ያለ የጤና አጠቃቀም ምጣኔ፡

የማአጤመ የግምገማ ጥናት የማአጤመ አባላት የጤና አጠቃቀም ምጣኔ በዓመት 0.7 እንደደረሰ ያሳያል። ይህም በሐገር አቀፍ ደረጃ በወቅቱ ከነበረው 0.34 ምጣኔ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ እመርታ ሲሆን ማአጤመ የሕብረተሰቡን ዝቅተኛ የጤና አገልግሎት አጠቃቀም ልምድ እንደጨመረ የሚያሳይ ዋነኛ አመላካች ነው።

የጤና አገልግሎት ጥራት መሻሻል፡ የማአጤመ ኘሮግራም በሙከራ ደረጃ በተተገበረባቸው ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የጤና ተቋማት የነበረው የመድኃኒት እና ሌሎች ግብዓቶች አቅርቦት ሁኔታ ከማአጤመ ትግበራ ጋር ተያይዞ እየተሻሻለ መምጣቱን ከጤና ተቋማት የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በተጨማሪም ተጠቃሚዎች በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለውጥ እየታየ መሆኑን እንደመሰከሩ የግምገማ ጥናቱ ያስቀምጣል።

ለጤናው ዘርፍ መዋለ ንዋይ መጨመር፡

በማአጤመ አማካኝነት የሚሰበሰበው ገንዘብ የሚውለው የጤና ተቋማት ለህብረተሰቡ ለሰጡት አገልግሎት ክፍያ የሚውል ሲሆን በሙከራ ወረዳዎች ውስጥ መጠኑ ቀላል የማይባል የገንዘብ መጠን ከሕብረተሰቡ መዋጮ እና ከመንግስት ድጎማ ለማሰባሰብ ተችሏል። ይህም የጤናውን ዘርፍ የፋይናንስ ፍላጎት ከውጭ ተፅዕኖ በማላቀቅ

ቀስ በቀስ በውስጥ አቅም ለመሸፈን የሚደረገውን ጥረት ያግዛል።

የሕብረተሰብ ተሳትፎና ባለቤትነት መጠናከር፡

የማአጤመ ተቋማት ሕብረተሰቡን በስፋት በማሳተፍ መብቱን በተደራጀ ሁኔታ ለመጠየቅ እንዲችል እድሉን በመፍጠር አስተዋጽኦ አበርክተዋል። በተጨማሪም ሕብረተሰቡ በማአጤመ የአስተዳደር መዋቅር ውስጥ ውክልና ያለው በመሆኑ የህብረተሰቡ የባለቤትነት ስሜት እንዲያድግና የማአጤመ ተቋማት አሰራር ከሕብረተሰቡ ፍላጎትጋር የተጣጣመ እንዲሆን አድርጓል።

የአቅም ግንባታ ማጎልበት፡

ከሙከራ ትግበራው ዓላማዎች መካከል አንዱ በአገር አቀፍ፣ በክልል፣ በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ ማአጤመን የመምራትና የመፈጸም አቅም መፍጠር የነበረ ሲሆን በዚህ ረገድ ሰፊ አቅም ለማዳበር ተችሏል።

የሙከራ ትግበራው ተግዳሮቶች

የማአጤመ የሙከራ ትግበራ የተለያዩ ተግዳሮቶች የነበሩበት ሲሆን ከእነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።

• ማአጤመ አዲስ ኘሮግራም እንደ መሆኑ መጠን በአባላት መካከል የግንዛቤ ክፍተት በመኖሩ የአባላት ምዝገባና እድሳት የሚጠበቀውን ያህል ያለመሆኑ፣

• የማአጤመን መረጃዎች በተሟላ መልኩ ለመያዝ እና ሪፖርት ለማድረግ የአቅም፣ የመዋቅር፣ የተነሳሽነት፣ ወዘተ ችግር መኖር፣

• የማአጤመ የምዝገባ እና የገንዘብ

Page 29: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200929

አሰባሰብ ስራ ዓመቱን ሙሉ የሚከናወን የነበረ በመሆኑ አድካሚና ለብክነት የመጋለጥ እድሉ ሰፊ መሆኑ፣

• በአንዳንድ የጤና ተቋማት ለማአጤመ ትግበራ እንቅፋት የመሆን አመለካከት መኖር፣

• በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላት ለማአጤመ ትግበራ በእኩል ደረጃ ትኩረት አለመስጠት ተጠቃሽ ናቸው።

የማአጤመ የማስፋትእንቅስቃሴ

መንግስት በማአጤመ የሙከራ ትግበራ ወቅት የተገኙትን ልምዶች በመቀመር እና ያጋጠሙትን ችግሮች በመለየት ፕሮግራሙን በአገር አቀፍ ደረጃ ለማስፋት የሚያስችል ስትራቴጂ የተቀረጸ ሲሆን በማስፋት ስትራቴጂው ላይ በተቀመጡት አቅጣጫዎች መሰረት ሐገራዊ የማስፋት መመሪያ አውጥቷል።

ሁሉን አቀፍ የጤና ተደራሽነትን /Universal Health Coverage/ ለማረጋገጥ ማአጤመ የራሱ የሆነ ጉልህ ድርሻ ያለው ሲሆን የማአጤመ ማስፋት ስትራቴጂ ይህንን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

የማአጤመ የማስፋት ስትራቴጂ የሚከተሉት ዋና ዋና ዓላማዎች አሉት፡-

• የማአጤመ ተቋማት ደረጃ በደረጃ በሁሉም የአገሪቱ ወረዳዎች እንዲመሰረቱ ማስቻል፣

• የማአጤመ ተቋማት የፋይናንስ ዘለቄታዊነት እንዲጠናከር ማድረግ፣

• የማአጤመ ተቋማት በቂ አቅም አንዲኖራቸው የሚያስችል

የአመራር እና የአሰራር አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ እና ብቃት ያለው የሰው ኃይል እንዲኖር ማድረግ ይገኙበታል።

የማስፋት አካሄድ

የማአጤመ ማስፋት ስትራቴጅ በሙከራ ትግበራው ወቅት የተገኙ ተሞክሮዎችን በመውሰድ ማአጤመ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ተቀራራቢነት ባለው መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን የሚያስችሉ አካሄዶችን ለይቶ አስቀምጧል።

የማስፋት እንቅስቃሴው አድማስ

የማአጤመ የማስፋት እንቅስቃሴ አድማስ ከላይ ወደ ታች በተዋረድ እና ወደጎን የሚደረጉ የማስፋት ስራዎችን ያካትታል።

ከላይ ወደታች በተዋረድ ማስፋት፡ በዚህ ስልት ለማአጤመ ትግበራ የሚያስፈልጉ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች እና የአሰራር ስርዓቶች በሁሉም የመንግሥት እርከኖች ቅርጽ ይዘው እንዲኖሩ ይደረጋል። ይህም ሲባል ለማአጤመ ማስፋት አስፈላጊ የሆኑ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና የአሰራር ማንዋሎች በሚመለከታቸው አካላት ተዘጋጅተው ከጸደቁ በኋላ ከላይ እስከ ታች ባለው የመንግሥት መዋቅር ሳይሸራረፉ ተግባራዊ ማድረግን ያጠቃልላል።

ወደ ጎን ማስፋት፡ በዚህ አካሄድ ማአጤመን በዘጠኙ ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ ማድረግ ሲሆን ይህም የማአጤመ ተቋማትን በአገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና ቀበሌዎች ለመተግበር ያለመ ነው። ይህም በጤናው ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ በተቀመጠው መሰረት

የክልሎችን እና የወረዳ መስተዳድሮችን የዝግጁነት ሁኔታ በመዳሰስና በማብቃት ማአጤመ በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች የሚስፋፋበትን መንገድ ማመቻቸት ማለት ነው።

የማስፋት ምዕራፎች

የማአጤመ የማስፋት ተግባር ተፈጸሚ የሚሆነው ደረጃ በደረጃ ሲሆን ይህም ክልሎች የሚያስፈልጋቸውን የበጀትና የቴክኒክ አቅም ለማቀድ እንዲችሉና በሁሉም ወረዳዎች በተከታታይ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለማስቻል ነው። የማስፋት ስራው በሁለት ምዕራፎች የሚፈጸም ሆኖ የመጀመሪያው በነባር የሙከራ ክልሎች እና ዝግጁ በሆኑ ሌሎች ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ሙከራውን በማጠናከር መተግበር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ማአጤመ ወደ ሌሎች አዳዲስ ክልሎች የሚስፋፋበት ምዕራፍ ነው።

የማአጤመ መሰረታዊ ገፅታዎችን ወጥ ማድረግ

ማአጤመ ካለው ባህሪ አንፃር እንደ ክልሎች ነባራዊ ሁኔታ በተወሰኑ አሰራሮች ላይ ልዩነት የሚጠበቅ ቢሆንም በማስፋት ስራው ወቅት ከሙከራ ትግበራው በተለየ ሁኔታ የተወሰኑ መሰረታዊ ገፅታዎችን ወጥ ለማድረግ ታቅዷል። ይህም በማአጤመ ተቋማት መካከል ክልላዊ እና ሀገራዊ ትስስር እና ትብብር ለመፍጠር ከማስቻሉም በላይ ማአጤመን ለመደገፍ በሚደረጉ ስራዎችና ግምገማዎች ላይ የተሻለ ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ ለመሆን ያስችላል።

በዚህ መሰረት በማአጤመ ማስፋት ስትራቴጂ በአገር አቀፍ ደረጃ ወጥ እንዲሆን የሚጠበቁ መሰረታዊ ገጽታዎች የሚከተሉት ናቸው።

Page 30: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200930

አባልነት፡ በሙከራ ትግበራ ወቅት የማአጤመ አባልነት እንደየክልሎች ውሳኔ በግለሰብ ወይም በቤተሰብ ደረጃ የነበረ ሲሆን ይህ አሰራር አሉታዊ ተፅዕኖ በመፍጠሩ ምክንያት በማስፋት ስትራቴጂው የማአጤመ አባልነት ወጥ በሆነ መልኩ በቤተሰብ ደረጃ ብቻ እንዲሆን አቅጣጫ ተቀምጧል። ይህም በማአጤመ ስርዓት ውስጥ የሚኖረውን መደጋገፍ ትርጉም ባለው መልኩ ያጎለብተዋል ተብሎ ይጠበቃል።

መዋጮ፡ የማአጤመ መዋጮ በሙከራ ወቅት ከክልል ክልል ይለያይ የነበረ ሲሆን ከማስፋት ሂደቱ ጀምሮ የመዋጮ መጠኑ ክልላዊ ልዩነት ሳይኖረው ወጥ እንዲሆን አቅጣጫ ተቀምጧል። በዚሁ መሰረት የማአጤመ መዋጮ የሕብረተሰቡን የመክፈል አቅም እና ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ በአባወራ/እማወራ በገጠር ወረዳዎች በዓመት 240 ብር፣ በከተማ ወረዳዎች በዓመት በር 350 እንዲሁም በከተማ አስተዳደሮች እና በከፍተኛ ከተሞች በዓመት ከ500 ብር ያላነሰ እንዲሆን ተደርጓል።

የክፍያ ወቅት፡ በማአጤመ የሙከራ ትግበራ ጊዜ የማአጤመ ክፍያ እንደየክልሎቹ ውሳኔ በየወሩ፣ በየሩብ ዓመቱ እና በየዓመቱ ሲሰበሰብ ቆይቷል። ሆኖም የገንዘብ አሰባሰብ ስራ ሰፊ የቤት ለቤት ቅስቀሳ እና ክትትል የሚፈልግ በመሆኑ ስራው እጅግ አድካሚ ከመሆኑም ባሻገር የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት አዳጋች ነበር። ስለሆነም በማስፋት ስትራቴጂው የማአጤመ የምዝገባ እና የክፍያ መሰብሰብያ ጊዜ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሆኖ ይህም የአካባቢው ሕብረተሰብ ገቢ ሊያገኝ በሚችልበት ወቅት እንዲሆን አድርጓል።

የጥቅም ማዕቀፍ፡ በማአጤመ

የሙከራ ትግበራ ወቅት የማአጤመ የጥቅም ማዕቀፍ በአብዛኛው በአካባቢያቸው በሚገኙ የጤና ተቋማት በሚሰጡ አገልግሎቶች ብቻ ተወስኖ የነበረ ነው። ሆኖም በማስፋት ስትራቴጂው መሰረት በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የማአጤመ አባላት የቅብብሎሽ ስርዓቱን ጠብቀው ከጤና ጣቢያ ጀምሮ እስከ ተርሸሪ ሆስፒታል ደረጃ ድረስ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጎ ተቀምጧል። ይህም አባላት ቀጣይነት ያለው የጤና አገልግሎት ፍትሀዊ በሆነ መልኩ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።

የማአጤመ ተቋማት ምስረታ፡ በሙከራ ትግበራ ወቅት የማአጤመ ተቋማት ተመስርተው አገልግሎት መስጠት የሚጀምሩት አባል መሆን ከሚችሉ የወረዳው አባወራዎች/ እማወራዎች ውስጥ እሰከ 30 በመቶ የሚሆኑት በአባልነት መመዝገብ ሲችሉ ነበር። ይሁንና በሙከራ ትግበራው ከተገኙ ተሞክሮች መካከል አንዱ ማአጤመን በአነስተኛ የአባላት ቁጥር መመስረት በጤና መድህኑ ቀጣይነት ላይ ተፅዕኖ ያለው መሆኑን ነው። ስለሆነም በማስፋት ስትራቴጂው መሰረት አንድ ወረዳ የማአጤመ ተቋም ለመመስረት አባል መሆን ከሚችሉት የወረዳው ነዋሪዎች ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑትን በአባልነት መመዝገብ እንደሚኖርበት የማስፋት ስትራቴጂው ያስቀምጣል።

የማአጤመ የማስፋት ስራ ትኩረቶች

የማአጤመ የማስፋት እንቅስቃሴ ዋና ዋና የትኩረት ስራዎች የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው።

የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ፡ ማአጤመን በመላው አገሪቱ ተግባራዊ እንዲሆን የሚረዱ የሕግ መዕቀፎች ከፌደራል

መንግስት ጀምሮ በሁሉም የመንግስት እርከኖች መዘጋጀት ይኖርባቸዋል። በዚሁ መሰረት የማስፋት ስራው በጤናው ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አቅጣጫ መሰረት እንዲከናወን በፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አማካኝነት የማስፋት መመሪያ የወጣ ሲሆን ክልሎችም እንደ ነባራዊ ሁኔታቸው በማሻሻል ወደ ስራ በመግባት ላይ ናቸው።

የማአጤመ ተቋማዊ መዋቅር መዘርጋት፡ የማአጤመ የማስፋት ስትራቴጂ የማአጤመ መዋቅር በአገራችን ያለውን ፌደራል አወቃቀር መሰረት በማድረግ በፌዴራል፣ በክልል እና በወረዳ ደረጃ እንደሚዘረጋ አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን በየደረጃው ያሉ አካላትን አጠቃላይ ተግባርና ኃላፊነት አስቀምጧል።

ከማአጤመ ተቋማዊ መዋቅር ጋር በተያያዘ የማአጤመን የማስፋት ስራ ውጤታማ ለማድረግ መሟላት ከሚገባቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ አስፈላጊውን የሰው ሃይል በተዘረጋው መዋቅር መሰረት መመደብ ነው። በማአጤመ የማስፋት ስትራቴጂ ላይ እንደተቀመጠው አንድ የማአጤመ የወረዳ የስራ ቡድን መዋቅር ማካተት ያለበት የጤና ባለሙያ፣ የሂሳብ ባለሙያ፣ የመረጃ ባለሙያ እና የመረጃ ረዳት ባለሙያ ሲሆን መዋቅሩም በክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሊጸድቅና በቂ በጀት ሊመደብለት እንደሚገባ ያስቀምጣል።

ጠንካራ የማአጤመ ፋይናንስ ስርዓት መዘርጋት፡

የማአጤመ ሥርዓት የጤናውን ዘርፍ የፋይናንስ ፍላጎት በራስ አቅም ለመሸፈን የሚደረገውን የመንግስት ጥረት እንደሚደግፍ የታመነ ነው።

Page 31: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200931

ስለሆነም ይህንን አገራዊ ግብ ትርጉም ባለው መልኩ ለመደገፍ እንዲቻል የማአጤመ ተቋማት ዘላቂ የሆነ የፋይናንስ አቅም ሊኖራቸው ይገባል። በማስፋት ስትራቴጂው የማአጤመን ፋይናንስ ለማጠናከር ይረዳሉ ተብለው የታመነባቸው ስልቶች ተቀምጠዋል። እነሱም ከከፋይ የማአጤመ አባላት የሚሰበሰበውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በወቅቱ እንዲገባ የሚያስችሉ አሰራሮች ማለትም ለሰብሳቢዎች ማበረታቻ መስጠት፣ የመዋጮ ስብሰባውን ከሌሎች የመንግስት ገቢ አሰባሰብ ስራዎች ጋር ማቀናጀት፣ ከአነስተኛ የገንዘብ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ መስራት፣ የስብሰባ ጊዜውን ከገቢ ማግኛ ጊዜ ጋር ተመሳሳይ እንዲሆን ማድረግ እና የማአጤመ መዋጮ መጠን የህብረተሰቡን ገቢ ባገናዘበ መልኩ በየጊዜው ማሻሻል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። በተጨማሪም የማአጤመ ተቋማት ከመንግስት እና ከሌሎች የልማት አጋሮች የተለያዩ ድጎማዎችን እንዲያገኙ በማድረግ የፋይናንስ አቅማቸውን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የማአጤመ የማስፋት ስትራቴጂ ያስቀምጣል።

በተጨማሪም የማአጤመን የፋይናንስ ስርዓት ለማጠናከር ከሚያስችሉ መንገዶች መካከል አንዱ በወረዳ ደረጃ ተገድቦ የነበረውን የማአጤመ ቋት ወደ ክልል እና ፌደራል ደረጃ ማሳደግ ሲቻል ነው። ስለሆነም እነዚህ የተበጣጠሱ የማአጤመ ቋቶችን በማስተሳሰር የእርስ በርስ መደጋገፉ ይበልጥ እንዲጎለብት በማስፋት ሂደቱ ወቅት የማአጤመ ቋት በሶስት እርከን ማለትም በወረዳ፣ በክልልና በፌደራል ደረጃ እንደሚቋቋም ያስቀምጣል።

የጤና ተቋማት እና የማአጤመ

ተቋማት ቅንጅትን ማጠናከር፡

የጤና ተቋማት በማአጤመ የማስፋት ስራ ውስጥ የማይተካ ሚና እንዳላቸው የታወቀ ነው። ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለማአጤመ አባላት ለማቅረብ የጤና ተቋማት በሰው ኃይል፣ በመድኃኒት አቅርቦት፣ በሕክምና መሣሪያዎችና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶች ተሟልተው መገኘት ያለባቸው ከመሆኑም በላይ የጤና ባለሙያዎች በመልካም ሥነ-ምግባር የታገዘ አገልግሎት እንዲሰጡ ይጠበቃል። ስለሆነም የጤና ተቋማት እና የማአጤመ ተቋማት ግንኙነት በውል የተመሰረተ እና ተጠያቂነት ያለበት መሆን እንዳለበት እንዲሁም ጤና ተቋማትም ጥራት ያለው አገልግሎት ስለመስጠታቸው በሚመለከታቸው አካላት የቁጥጥር ስራ እንደሚሰራ በማስፋት ስትራቴጂው በግልጽ ተቀምጧል።

የተጠናከረ የሕብረተሰብ ተሳትፎን መፍጠር፡

የማአጤመ ትግበራ አዲስ ዓይነት አሰራር ይዞ የመጣ በመሆኑ የሕብረተሰቡን ተሳትፎና የባለቤትነት ስሜት ለማዳበር በቂ የግንዛቤ መፍጠር ሥራ መሰራት እንዳለበት ጭምር በማስፋት ስትራቴጂው ትኩረት ተሰጥቶታል።

ማአጤመ ከ 2003 ዓም ጀምሮ በ13 ወረዳዎች በሙከራ ደራጃ ሲተገበር የቆየ ሲሆን ከሙከራው ስራው በተገኙት አበረታች ውጤቶች በመነሳት በአሁኑ ወቅት ከ320 በላይ ወረዳዎች ማአጤመን እየተገበሩ ወይም ለመተግበር በዝግጀት ምዕራፍ ላይ ናቸው።

መንግስት ፕሮግራሙ ያሉትን በርካታ ጠቀሜታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት የጤናው ዘርፍ

የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አካል ያደረገው ሲሆን እስከ 2012 ዓም ድረስ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት ወረዳዎች እና ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውን ነዋሪ በማአጤመ ለመሸፈን ዕቅድ ተይዟል።

የማአጤመ የማስፋት ስትራቴጂ ይህንን ዕቅድ ለመተግበር ዓይነተኛ መሳሪያ ነው። የማስፋት ስትራቴጅው ከሙከራ ትግበራው የተገኙትን መልካም ተሞክሮዎችና ተግዳሮቶችን በመቀመር የተዘጋጀ ሲሆን ክልሎች ማአጤመን ተግባራዊ ለማድረግ መከተል ስለሚገባቸው አሰራሮች በስትራቴጅው ተመላክቷል። የማአጤመ ማስፋት ስትራቴጂ በጤናው ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ ማአጤመን በተመለከተ የተቀመጡትን ግቦች ለማሳካት የሚያስችል ፍኖተ-ካርታ ያስቀመጠ ሲሆን የተጠናከረ የጤና መድህን ስርዓት ለመፍጠር በየደረጃው ያሉ አካላት ያለባቸውን ተግባርና ኃላፊነት በግልፅ አስቀምጧል።

የማአጤመ የማስፋት ስትራቴጂ አገራችን የጤና መድህን ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ወደ ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን (UHC) የሚደረገውን ጉዞ ለማፋጠን የተቀረጸ ነው። በሂደትም በተበታተነ መልኩ የተቋቋሙት የወረዳ ማአጤመ ተቋማት ወደ ሰፊ የመድህን ተቋም እንዴት መሸጋገር እንዳለባቸው ጠቋሚ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።

Page 32: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200932

በጤንነት የመኖር መብት ህገ መንግስታዊ መብት እንደመሆኑ መጠን ጤናማና አምራች ሀይል መገንባት የአንድ ሀገር መንግስት

ቀዳሚ ኃላፊነት ነው። ጤናማ የሆነ ዜጋ መማርና መመራመር፣ በግብርናውም ይሁን በኢንዱስትሪው ማምረት የሚችል፣ ጤናማ አስተሳሰብ ያለውና ከወንጀል ድርጊት ነጻ ሆኖ ለሀገር ዕድገት ሌት ተቀን የሚተጋ ዜጋ ይሆናል።

በሀገራችን የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ እንዲሁም የአኗኗርና የአመጋገብ ዘይቤውን ለመለወጥ በጤናው ዘርፍ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ነው። እንደሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታም ያለን ሀብት ርካሽ ጉልበትና ሰፊ የመሬት ሀብት እንደመሆኑ መጠን የጤናውን ሴክተር በማዘመን ጤናማ ዜጎችን ማፍራት ሀገራዊ የህዳሴ ጉዟችንን ለማፋጠን ተኪ የለውም። ይህንን ሀገራዊ ፍላጎት ለማሟላት ሁለተኛው የጤናው ሴክተር የዕድገትና ትራንስፎረሜሽን ዕቅድ ተነድፎ በትግበራ ላይ ይገኛል። የዕድገትና

በጌታቸው ጥሩነህ

ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ትራንስፎርሜሽን

ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ግቦችን ለማሳካትም አራት ዋና ዋና የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች ተለይተው ተቀምጠዋል።

• የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊነት፣

• ወረዳ ትራንስፎርሜሽን፣

• የመረጃ አብዮት እና

• ተንከባካቢ፣ አክባሪና ሩህሩህ የጤና ሰው ኃይል መገንባት ናቸው።

የዚህ ጽሁፍ ዓላማ አራቱንም አጀንዳዎች መተንተን ባይሆንም በተለይ ወረዳ ትራንስፎርሜሽን ውስጥ ትኩረት ስለተሠጠው የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን (ማዐጤመ) ጥቂት ለማለት ነው። ስለ ፕሮግራሙ ሁኔታ ከመግባታችን በፊት ጥቂት ስለ ጤና ፋይናንስ ወጪ እና ለውጦች ማንሳት ተገቢ ይሆናል።

አብይ ርዕስ

Page 33: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200933

የህብረተሰቡ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መጥቷል። ቀደም ሲል ከነበረበት 0.33 ወደ 0.77 አድጓል። አምስተኛው ዙር የጤና አካውንት ጥናት (NHA 2010/11) ውጤት ላይ ለመረዳት እንደሚቻለው የነፍስ ወከፍም ሆነ ጥቅል አገራዊ የጤና ወጪ ጨምሯል። የአገሪቱ ጥቅል የጤና ወጪ በ2001 ዓ.ም. ከነበረው 11.1 ቢሊዮን ብር (1.2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር) በ2004 ዓ.ም. ወደ 26.5 ቢሊዮን ብር (1.6 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር) አድጓል። በተመሳሳይ ጊዜ የነፍስ ወከፍ

የጤና ወጪው ከ16.09 የአሜሪካን ዶላር ወደ 20.77 የአሜሪካን ዶላር ከፍ ሊል ችሏል። የነፍስ ወከፍ የጤና ወጪ ጭማሪ መኖሩ መልካም የሚባል ቢሆንም በአገሪቱ በአራተኛው የጤና ሴክተር የልማት መርሀ ግብርም መጨረሻ ላይ ይደረሳል ተብሎ ከተቀመጠው 32 የአሜሪካን ዶላር ግብ እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት የማክሮ-ኢኮኖሚክስ እና የጤና ኮሚሽን ከተቀመጠው 34 የአሜሪካን ዶላር ግብ ጋር ስናነጻጽረው በእጅጉ ያነሰ ሆኖ እናገኘዋለን። ስለሆነም የጤናው ዘርፍ የወጪ መጠን

ከዚህም በላይ መጨመር እንዳለበት መረዳት ያስፈልጋል።

ከዚህ ሌላ ከፋይናንስ ምንጭ አንፃር ሲታይ የአገሪቱ የጤና ዘርፍ የገንዘብ ምንጭ በአብዛኛው ከውጭ ምንጮች የሚገኝ (50 ከመቶ) እና ግለሰቦች በቀጥታ ከኪስ ከሚከፍሉት (34 ከመቶ) ነው። ከኪስ በቀጥታ የሚከፈል ወጪ ከ15 እስከ 20 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት የተለያዩ መረጃዎች ያስረዳሉ። እንዲህ ዓይነቱ ክፍያ በቤተሰብ ገቢ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያሳድር

Page 34: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200934

በመሆኑ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ቤተሰቦች ወደ ድህነት አዘቅት ሊገፋ የሚችል በመሆኑ ተመራጭ አይደለም።

ስለሆነም የጤና አገልግሎት ወጪ ስጋት እንዳይሆን ለመከላከል ቀጣይነት ያለው አማራጭ የፋይናንስ ምንጭ ማፈላለግ ያስፈልጋል። ይህ የፋይናንስ ምንጭ ተጨማሪ ሃብትን ማሰባሰብ የሚያስችል፣ የዜጎችን የጤና ተደራሽነት የሚያሳድግ እና ቤተሰቦችን ከአቅም በላይ ከሆነ ወጪ የሚታደግ መሆን አለበት።

ማዐጤመ ያለበት ሁኔታ

የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን (ማዐጤመ) ቀደም ሲል በአራቱ ክልሎች ማለትም በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልሎች ውስጥ በሉ በአስራ ሶስት ወረዳዎች በሙከራ ደረጃ መጀመሩ ይታወሳል። በአሁኑ ሰዓት በ226 ወረዳዎች እየተተገበረ ይገኛል። እስከያዝነው 2008 በጀት ዓመት ድረስ 12,174,907 ዜጎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል። በዚህ ዘርፍ የተገኘው ውጤት እንደ እኛ ሀገር በግብርናና የዕለት ጉልበት ሥራ የሚተዳደሩ በርካታ ዜጎች ያላቸው የአፍሪካና የኤዥያ ሀገራት አንጻር ስናየው የተሻለ ሆኖ እናገኘዋለን። እነዚህ ሀገራት አሁን እኛ በአራትና አምስት ዓመታት ከደረስንበት ሽፋን ለመድረስ ከአስር ዓመት በላይ ፈጅቶባቸዋል። ማዐጤመ ሲጀመር አልጋ በአልጋ የነበረ ባይሆንም ምልዐተ - ህዝቡና አመራሩ በአደረገው ርብርብ ተስፋ ሰጭ ውጤት ሊመዘገብ ችሏል።

የማዐጤመ ማስፋት ስትራቴጂ

የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን ሙከራ ትግበራ ፕሮግራም ሲገመገም የጤና አገልግሎት የፋይናንስ ተደራሽነትን፣ የጤና አገልግሎት ጥራት መሻሻልን፣ ለጤናው ሴክተር ተጨማሪ ሃብት ማሰባሰብን እና በአመራርና አስተዳደር ደረጃ የህብረተሰብ ተሳትፎን ማሳደግ ችሏል። በተለይ ማዐጤመ በተተገበረባቸው አካባቢዎች እናቶች የአባወራውን መልካም ፈቃድ ሳይጠይቁ እራሳቸው ወይንም ልጆቻቸው ሲታመሙ የአባልነት መታወቂያቸውን ብቻ ይዘው የጤና አገልግሎት ማግኘት መቻላቸው በቤተሰብ ደረጃ የነበረውን ማህበራዊ ቀውስ ከመፍታት አልፎ እናቶችና ህጻናት ጤና ሥራዎች ላይ በጎ አሻራ ማሳረፍ ችሏል። ከዚህ ውጤት በግልፅ መረዳት የሚቻለው ማዐጤመን ማስፋት የአብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል የጤና ዋስትና ማሻሻል መሆኑን እና መንግሥት አስቀድሞ ያቀደውን የጤና መድህንን በመላ አገሪቱ የማዳረስ ዕቅድ የሚደግፍ መሆኑን ነው።

በአገር አቀፍ ደረጃ ማዐጤመን ለማስፋፋት የሚያስችል መደላድል ለመፍጠር የማስፋት ስትራቴጅ ተቀርጿል ። የጤና መድህን ሥርዓቱ በሀገር ደረጃ የሚደራጅበት፣ የሚተገበርበት እና የሚመራበት የሕግ ማዕቀፍም ወጥቷል ። የማስፋት ስራው ክልሎች በየወረዳዎቻቸው ተቋሙን ለማቋቋም የሚያስፈልጋቸውን የፋይናንስ እና የማስፈፀም አቅም እንዲፈጥሩ የሚያስፈልገው ጊዜ ታሳቢ ተደርጎ በተለያዩ ምዕራፎች የሚከናወን ይሆናል። በመጀመሪያ ማዐጤመን በመተግበር ልምድ ባላቸው አራቱ ክልሎች

ትግበራውን በማጠናከር ወደ ሁሉም ወረዳዎቻቸው እንዲዳረስ የሚሰራ ሲሆን ዝግጁ ወደ ሆኑ ሌሎች ክልሎች እና የከተማ አስተደደሮችም እየተስፋፋ ይገኛል። ይህም በቀጣዮቹ ሁለት እና ሦስት ዓመታት ትርጉም ባለው ሁኔታ በሀገር ደረጃ ይተገበራል። በዚህ ጊዜ ውስጥ አርብቶ-አደር ማህበረሰብ ያለባቸውን ክልሎችን ጨምሮ በሁሉም ክልል ወረዳዎች እና የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ሌሎች ወሳኝ የባለድርሻ አካላት ለማስፋፋት የሚስያችል የማስፈጸም አቅም ግንባታ ሥራ በኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ አማካኝነት ይከናወናል።

ስለሆነም የማስፋት እንቅስቃሴው ሙከራውን እየተገበሩ በሚገኙ ማለትም በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደ/ብ/ብ/ህዝቦች እና በትግራይ ክልሎች እና በሌሎች ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ደግሞ ለመጀመር ባላቸው ዝግጁነት መሰረት ወደ ማስፋት እንቅስቃሴው እንዲገቡ ይደረጋል። በማስፋት ሂደቱ በሚካተቱ አዳዲስ ወረዳዎች ማዐጤመ የሚጀመረው በእያንዳንዱ ወረዳ የማዐጤመ አባል መሆን ከሚችለው ውስጥ 50 ከመቶ የሚሆነው በአባልነት ሲመዘገብ ነው። የአሠራር ለውጡ የተደረገበት ምክንያትም ከዚህ በፊት ጥቂት አባላት ይዘው የጀመሩና ከሚሰበስቡት ገንዘብ ይልቅ ወጪያቸው ልቆ ወደኋላ ከተመለሱ ወረዳ ተቋሞች ትምህርት በመውሰድ ነው።

ይህ የማዐጤመ ፕሮግራምን የማስፋት ሂደት መንግስት በ2028 ዓ.ም. ሁሉን ዐቀፍ የጤና ሽፋን በአገሪቱ እንዲዳረስ ያስቀመጠው ግብ ዋነኛ አካል ነው። በዚህ ውስጥ ምልዓተ ህዝቡን በማነቃነቅ ቀጣይነት ያለው ውጤት ለማስመዝገብ የአመራሩ ቁርጠኝነት ወሳኝነት

Page 35: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200935

Health Sector Transformation Plan

The Federal Democratic Republicof Ethiopia Ministry of Health

HSTPHealth Sector Transformation Plan

ይኖረዋል። ስለሆነም በየደረጃው ያለው አመራር ይህንን ግብ ዳር ለማድረስ ግንባር ቀደም ሚናውን መጫዎት ይኖርበታል። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ በ2008 ዓ.ም የወጣው የማዐጤመ ማስፋት ስትራቴጂ ሰነድ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው ማዐጤመ የመንግስት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ ብቻ ሳይሆን በየደረጃው ያሉ አመራሮች የውጤት መመዘኛ መስፈርት ሆኖ እንደሚቀጥል በግልጽ ተመላክቷል። በተጨማሪም ማዐጤመ በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም የጤና አጠባበቅ

ትምህርት ፓኬጅ ውስጥ እንደ አንድ ተግባር እንደሚካተትና በተመሳሳይ የጤና ልማት ሰራዊትን ለማዐጤመ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች መጠቀምም እንደሚገባ ያስቀምጣል።

የማዐጤመ ተቋማትን የፋይናንስ አቅም ለማጠናከር የመዋጮ አሰባሰብ ሂደቱን ቀልጣፋ ማድረግ እና የመዋጮ መጠኑን ቀስ በቀስ በአባላቱ የገቢ እርከን ደረጃ መከፋፈል አስፈላጊ ነው። ተበታትኖ የሚገኘውን የወረዳ የማዐጤመ የገንዘብ ቋት ከፍ ወዳለ የዳበረ ቋት ማለትም

ወደ ክልላዊ እና አገራዊ ደረጃነት በማሳደግ በወረዳ ደረጃ በተመሰረቱት የማዐጤመ ተቋማት መካካል የጎንዮሽ መደጋገፍ እንዲኖር ማድረግ ይገባል። ወደፊት አንድ አሀዳዊ የጤና መድህን ሥርዓት ለመመሥረት የሚደረገውን ጉዞ በማፋጠን ረገድም አስተዋጽኦ ይኖረዋል። የመንግስት ድጎማ ቀጣይነት የሚኖረው ሲሆን በዋናነት ለማዐጤመ መዋጮ መክፈል የማይችሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ይሆናል።

The Federal Democratic Republic Of Ethiopia Ministry Of Health

2015/16-2019/20(2008-2013 EFY)

Page 36: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200936

ወረዳ ትራንስፎርሜሽንና ማዐጤመ እንደ ዋና አጀንዳ?

የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን (ማዐጤመ) ፍኖተ-ካርታ በሁለት ዋና ዋና ብሄራዊ ዕቅዶች የሚመራ ነው። እነዚህም መንግሥት ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን (Universal Health Coverage) እ.ኤ.አ በ2035 ላይ ለመድረስ ያስቀመጠው ራዕይ እና እ.ኤ.አ ከ2015/6 እስከ 2019/20 ድረስ በአገሪቱ የሚገኙ ወረዳዎችን ሙሉ በሙሉ እና ከመደበኛው ክፍለ-ኢኮኖሚ ውጪ ከተሰማራው ጠቅላላው ሕዝብ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆነውን በጤና መድህን እንዲታቀፍ ለማድረግ በጤና ሴክተር ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተጣሉ ግቦች ናቸው። ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን ወደ ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን የሚደረገውን ጉዞ በማፋጠን ሁነኛ ሚና ይጫወታል። በመሆኑም ይህንን ግብ መሠረት በማድረግ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በነደፋቸው አራት የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች ወረዳ ትራንስፎርሜሽን ውስጥ ወሳኙ ጉዳይ የጤና መድህን ሥርዓቱን በገጠር ማስፋፋት ነው።

ሁለተኛው የጤናው ዘርፍ የዕድገትና ትራንስፎሜሽን ዕቅድ ሰፊና የተለጠጠ ዕቅድ ነው። ይህን ሀገራዊ ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ደግሞ ዋናው ፈጻሚ እና መሪ ተዋናኝ ወረዳ በመሆኑ ዕቅዱን ወደ ተግባር የሚለውጠው ወረዳ ነው። ወረዳ ትራንስፎርሜሽን መሠረት ያደረገው ባለው የጤና አወቃቀር ላይ ተመስርቶ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ የጤና ተቋማት ተጠያቂነትን መጨመርና ህብረተሰቡን መሪ ተዋናኝ ማድረግ ነው። የሚጠበቀው ውጤትም ተጠያቂነት

የሰፈነበት የጤና አስተዳደር በመገንባት የህዝቡን የጤና ፍላጎት ማርካት ሲሆን በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ አሰጣጥን በማጎልበት እና መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋፋት ጤና ለሁሉም ግባችንን ማሳካት ነው።

የወረዳ ትራንስፎርሜሽን አተገባበር በዋናነት ሶስት ተያያዥነት ያላቸው ግቦችን ያነገበ ነው። እነሱም በብቃት የሚፈጽም የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት አሀድ መፍጠር፣ ሞዴል ቀበሌዎችን ማስመረቅና ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋንን በማሳካት የወጪ ስጋትን መቀነስ ናቸው። እነዚህን ግቦች ለማሳካት ደግሞ ስድስት ግልጽ ስትራቴጅዎች ተቀርጸዋል። ከእነዚህ

ስትራቴጅዎች አብዛኛዎቹ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የጤና መድህን ሥርዓት ትግበራና ውጤታማነትን የሚያጎለብቱ ሲሆን አንደኛው በዋናነት የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህንን በመተግበር ጤና ለሁሉም የሚለውን ግብ ማሳካት የሚል ነው። ይህን የትራንስፎርሜሽን አጀንዳ ውጤታማ ለማድረግ እራሱን የቻለ የትግበራ ማንዋል በማዘጋጀት ሥራው በፈርጅ በፈርጁ ተግባራዊ ይደረጋል። ዝርዝር ዕቅዱ ላይ እንደተቀመጠው በዕቅድ ዘመኑ ማጠናቀቂያ 80 በመቶ የሚሆነውን የገጠር ወረዳ ህዝብ የጤና መድህን ተጠቃሚ በማድረግ የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ማሳደግ ቁልፍ ጉዳይ ነው። ይህ ግብ ሲሳካ ወደ ፊት እንደ

Page 37: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200937

ሀገር ለምንመሠርተው አንድ የተጠናከረ አሀዳዊ ብሔራዊ የጤና መድህን ምቹ መደላድል ይፈጥራል።

ማጠቃለያ

የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን የማስፋት ስትራቴጂ በአምስት የስትራቴጂ መስተጋብሮች የተዋቀረ ነው። እነዚህ መስተጋብሮች በፕሮግራሙ አማካይነት ወደ ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን በሚደረገው ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ናቸው። እነርሱም የማዐጤመን የህግ ማዕቀፍ እና ተቋማዊ መዋቅር ማጠናከር፣ የፋይናንስ ሥርዓትን ማጠናከር፣ ከጤና አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ያለውን አጋርነት ማጠናከር፣

የኮሙኒኬሽን እና የህብረተሰብ ንቅናቄን ማሳደግ እና የክትትልና የግምገማ ሥርዓቱን ማጠናከር ይሆናል። ስለሆነም እነዚህን ወሳኝ ምሰሶዎች በተሟላ ሁኔታ በመተግበር የማህበሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን ሥርዓቱን ውጤታማ ማድረግ ይገባል።

በአጠቃላይ የማህበሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን ትግበራው ምንም ዓይነት ተግዳሮት አልገጠመውም ባይባልም በህዝቡ የባለቤትነት ተሳትፎና በየደረጃው ባለው አስፈጻሚ አካል ክትትል ተስፋ ሰጪ እየሆነ መጥቷል። ይህንን ውጤት ማስቀጠል የሚቻለው ደግሞ ከነበሩ ድክመቶች ትምህርት

ወስዶ መልካም ውጤቶችን በማስፋት መሥራት ሲቻል ብቻ ነው። ስለሆነም የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን ሥራ የአጋር አካላትን ያላሰለሰ ጥረት የሚጠይቅ በመሆኑ አመራሩ፣ ባለሙያውና ህዝቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተቀናጅቶ መፈጸም ይኖርበታል። በያዝነው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ማጠናቀቂያ በመደበኛና መደበኛ ባልሆነው ክፍለ ኢኮኖሚ የተሰማራውን ዜጋ የጤና መድህን አባል በማድረግ ሁሉም ዜጋ ፍትሀዊና ቀጣይነት ያለው የጤና አገልግሎት የማግኘት ዋስትናውን ማረጋገጥ ይገባል። ዋናው ነገር ጤና!

Page 38: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200938

በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ ማህበራዊ ከለላን ለማረጋገጥ ከሚወሰዱ የማህበራዊ ዋስትና

ርምጃዎች ውስጥ የጤና መድህን ዋነኛውና ቀዳሚው እየሆነ መጥቷል። የመንግስት ስልጣንን ለመያዝ በሚደረግ የምረጡኝ ዘመቻ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአጀንዳነት ይዘዋቸው ከሚቀርቧቸው ጉዳዮች መካከል ‹የጤና መድህን ስርዓትን እናስጀምራለን›፤ የተጀመረም ከሆነ ደግሞ ‹በተሻለ መንገድ የሚመራበትን ስልት እንነድፋለን› የሚለው እንደሆነ ባለፉት አመታት ከተካሄዱ የፖለቲካ ምርጫዎች መረዳት እንችላለን።

ለዚህ አብነት የሚሆነን ደግሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዳግም አገራቸውን

ለአራት አመት እንዲመሩ ያስቻላቸውን በቂ ድምጽ ሊያገኙ የቻሉት በስፋት ‹ኦባማ ኬር› በሚል የሚታወቀውን የጤና መድህን ስርዓት ለማስተግበር ያላቸውን አቋም በመከራከሪያነት ይዘው ብቅ በማለታቸው እንደሆነ ማስታወስ እንችላለን። በተመሳሳይ መልኩ በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ጋና ለፕሬዚዳንትነት ተፎካክረው ድል የጨበጡት ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሀማ የምረጡኝ ዘመቻቸው ውስጥ የጤና መድህን ስርዓትን በተሻለ መንገድ አስፈጽማለው ብለው ለህዝባቸው ቃል በመግባታቸው ነው። ዛሬ ጋና እየተገበረችው ያለው የጤና መድህን ስርዓት በአፍሪካ አህጉር ውስጥ በተምሳሌትነት የሚጠቀስ ሆኗል።

የጋና ጤና መድህን በአፍሪካ ብሎም በዓለም ተምሳሌት የመሆን ጥረት

ተሞክሮ

በአብይ ጌታሁን

Page 39: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200939

የቮልታ ግዛት ነዋሪው ኦሞአኒ ኮብላህ በምርጫ ዘመቻ ወቅት የፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሀማን የምርጫ ምልክት አንግቦ አደባባይ በወጣበት ወቅት ከቢቢሲ ጋዜጠኛ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሹን ሲሰጥ ፕሬዚዳንቱን ለመደገፍ የቻለው ፕሬዚዳንቱ በምርጫው አሸንፈው ወደስልጣን ቢመጡ ለማከናወን ያሰቧቸው ጉዳዮች እንደሆኑ ተናግሯል። ከጉዳዮቹ ውስጥም ‹ለአገሪቱ የጤና መድህን መዳበር መስራት ቅድሚያ የምሰጠው ተግባር ነው› የሚለው አጀንዳቸው ቀዳሚው እንደሆነ ለቢቢሲው ጋዜጠኛ አብራርቷል።

አሁን አሁን የጤና ክብካቤ ፋይናንስ ምንጭ በትክክል ግልጽ ሆኖ ካልተቀመጠ መንግስታትን እየፈተነ የመጣ ጉዳይ ሆኗል። የአለም የጤና ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት ሰዎች ለህክምና

በሚያወጡት ያልታሰበ ወጪ የተነሳ በየአመቱ ቁጥራቸው ከ150 ሚሊዮን የሚልቁት ወደድህነት አዘቅት ይዘፈቃሉ። ስለዚህ ወደስልጣን ለመምጣት ጥረት የሚያደርጉ ኃይሎች ሁሉ ዜጎቻቸው በጤና እክል የተነሳ በሚከሰት ድንገተኛ ወጪ የሚፈጠረውን አደጋ ለመከላከል ቀድመው ስለሚያስቡበት ‹በምረጡኝ› ዘመቻ ወቅት የጤና መድህንን ጉዳይን ዋነኛ የቅስቀሳ መሳሪያቸው አድርገው ይጠቀሙበታል።

ጋና አሁን ላይ የጤና መድህን ስርዓትን መተግበር ከጀመረች አመታትን ያስቆጠረች ብትሆንም የጤና ክብካቤ ፋይናንስን መስመር ለማስያዝ የተለያዩ መንገዶችን ማለፍ ግድ ሆኖባት ነበር። በ1950ዎቹ አገሪቱ ለረጅም አመታት ከቆየ የቅኝ አገዛዝ ቀንበር ነጻ በወጣች ማግስት ክፍያ የማይጠየቅበት ነጻ የሆነ የጤና ክብካቤ አገልግሎት ፖሊሲ ለመከተል ሞክራ ብዙ ርቀት ልትጓዝበት አልቻለችም። በተለይም በ1970ዎቹ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ መግባቱ የነጻ የጤና ክብካቤ ፖሊሲውን ለመቀየር የራሱ የሆነ ጫና ፈጥሯል።

በመሆኑም የነጻ ፖሊሲው አንዳንድ የጤና አገልግሎቶች ላይ ክፍያ መጠየቅ በሚቻልበት መልኩ ተቀርጾ በሌላ ፖሊሲ እንዲተካ ተደረገ። ይህም ቢሆን በታሰበው ልክ ውጤት ሊያመጣ አልቻለም ነበር። በየወቅቱ እየጨመረ ከሚመጣው የጤና ክብካቤ አገልግሎት የዋጋ ተመን ጋር ተያይዞ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚዎች የአገልግሎት ክፍያ የሚጠየቁበት ሌላ ስልት ተነደፈ። ይህ በ1985 ላይ ለአገሪቱ የተዋወቀው ስልት ብዙዎቹን የአገሪቱ ዜጎች ከጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት

ማዕድ እንዲርቁ ያደረገ ነበር። ነገር ግን በ1990ዎቹ ሌላ የጤና ክብካቤ የፋይናንስ ስልት መንደፍና ዜጎችን በስፋት ተጠቃሚ ማድረግ የግድ ስለሆነ መንግስት አለም ዓቀፍ ተሞክሮዎችን በመመልከት ለአገሪቱ አዲስ የሆነ የፋይናንስ ስርዓት ለመዘርጋት ተነሳሳ።

በዚህ ጊዜ በመንግስትና በህዝቡ መካከል የወጪ መጋራትን የሚያስችል ማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን ስርዓትን ‹ሀ› ብሎ በምድረ ጋና ተጀመረ። ስርዓቱ ቢፈጠርም በአጭር ጊዜ ውስጥ አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል በስርዓቱ ውስጥ እንዲታቀፉ ማድረግ ባለመቻሉ አሁንም የሚበዛው የአገሬው ነዋሪ ከጤና ክብካቤ አገልግሎት ማዕድ በሚፈለገው ልክ ተቋዳሽ ሊሆን አልቻለም። በዚሁ ልክ ዜጎች የጤና ክብካቤ አገልግሎት ለማግኘት በሚፈልጉበት ወቅት ከኪሳቸው ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ማውጣቸው ቀጠለ፤ የጤና ክብካቤ አገልግሎት ተጠቃሚነትም እጅግ ዝቅተኛ ነበር። ስለሆነም በአገልግሎት ወቅት ከኪስ የሚወጣ ከፍተኛ ወጪን ለመቀነስና የአገልግሎት ተጠቃሚነትን ማሳደግ እንደሚደቻል ውስን በሆኑት የማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን አባላት አማካኝነት የተስፋ ጭላንጭል በመታየቱ የጤና መድህንን አገራዊ እንዲሆን ለማስቻል በ2003 ላይ ብሔራዊ የጤና መድህን ስርዓት ተፈጠረ።

የጋና ብሔራዊ የጤና መድህን ባለስልጣን ‹በአፍሪካ ብሎም በአለም በተምሳሌትነት የሚጠቀስ ዘላቂ፣ እያደገ የሚሄድና ፍትሀዊ ማህበራዊ የጤና መድህን ስርዓት መዘርጋት› የሚል ራዕይ ሰንቆ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል። ይህንን ለማሳካትም በመንግስት ያለው የፖለቲካ

Page 40: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200940

ቁርጠኝነት፣ አቅሙ የተገነባ የጤና መድህን ሰራተኛ እና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ስርዓቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ናቸው።

ሁሉም የጋና ነዋሪዎች የፋይናንስ ስጋት ከለላ አግኝተው ፍትሀዊ የጤና ክብካቤ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ የሚሰራው የጤና መድህን ስርዓቱ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በደንብ ቀርበው በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ ማድረግ አንዱ ትኩረቱ ነው። ሁሉን አቀፍ የጤና ተደራሽነትን ለማረጋገጥም በዜግነት ጋናውያን የሆኑትም ያልሆኑትም በስርዓቱ የሚታቀፉ ናቸው። የጋና ነዋሪነት ብቻ በቂ ነው።

የጤና መድህኑ የገንዘብ ምንጭ የተለያየ ነው። በእያንዳንዱ ሸቀጥና አገልግሎት ላይ የተጣለ የ2ነጥብ5 በመቶ የብሔራዊ የጤና መድህን ቀረጥ፣ የ2ነጥብ5 በመቶ የማህበራዊ ዋስትና መዋጮ፣ ከተለያዩ ኢንቨስትመንቶች የሚገኝ ብሔራዊ የጤና መድህን ፈንድ፣ እንዲሁም ከጤና መድህን አባላት የሚሰበሰብ መዋጮ የጤና መድህኑን የገንዘብ ቋት የሚሞሉ ምንጮች ናቸው።

ከጤና መድህን አባላት መዋጮ የሚሰበሰብ ቢሆንም አባል ሆነው የማይከፍሉ ወገኖች አሉ። ዕድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ልጆች፣ ነፍሰ-ጡር እናት (የቅድመ ወሊድ፣ የወሊድ እና የድህረ ወሊድ አገልግሎት ለማግኘት)፣ የአዕምሮ ህመም ያለበት ሰው፣ ዝቅተኛ ገቢ ያለው በመሆኑ የደሀ ደሀ ተብሎ በድጎማ የሚኖር፣ የጡረታ ባለመብት፣ ለማህበራዊ ዋስትናና ለብሔራዊ መድህን መዋጮ እየከፈሉ የሚገኙ፣ ዕድሜያቸው ከሰባ አመት በላይ የሆኑ፣ እንዲሁም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በኩል መዋጮ እንዳያዋጡ የተለዩ ክፍሎች ከጤና መድህን አረቦን ክፍያ ነጻ የተደረጉ ናቸው።

የጋና ብሔራዊ የጤና መድህን አባላት ቁጥር፣ የአገልግሎት ተጠቃሚነትና የአገልግሎት ክፍያ ከጊዜ ወደጊዜ እያሻቀበ ይገኛል። በ2005 1ነጥብ3 ሚሊዮን የነበረው የጤና መድህን አባላት ቁጥር ከዘጠኝ አመት በኋላ በ2014 በስምንት ዕጥፍ አድጎ 10ነጥብ5 ሚሊዮን ደርሷል። የጤና ክብካቤ ተጠቃሚነትም እንዲሁ በተመሳሳይ በተመላላሽ እና በተኝቶ ታካሚ ቁጥር ከፍተኛ ማሻቀብ አሳይቷል። የተመላላሽ ታካሚው ቁጥር

በ2005 598 ሺህ በዘጠኝ አመት ልዩነት በ48 ዕጥፍ ጨምሮ 29 ሚሊዮን ሲደርስ የተኝቶ ታካሚው ቁጥርም እንዲሁ ከ29 ሺህ በ55 እጥፍ ጨምሮ 1ነጥብ6 ሚሊዮን ከፍ ብሏል። ከታካሚው ቁጥር ማሻቀብ ጋር መሳ ለመሳ ደግሞ የክፍያ ምጣኔውም በብዙ ዕጥፍ መጨመሩን ማየት ይቻላል። በ2005 7ነጥብ6 ሴዲ (የጋና መገበያያ ገንዘብ) ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ወቅት በ127 ዕጥፍ ጨምሮ 968 ሚሊዮን ሴዲ ደርሷል።

የአገሪቱን ጠቅላላ ህዝብ 40 በመቶ ያህሉን በአባልነት ያቀፈው የጋና ብሔራዊ የጤና መድህን ለአባላቱ የጤና ክብካቤ አገልግሎት እንዲሰጡለት ከ3ሺህ752 የመንግስት፣ ከ207 በዕምነት ተቋማት ስር ለሚተዳደሩ፣ እንዲሁም ከ45 የግል በድምሩ ከ4004 የጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር ውል ገብቷል።

ብሔራዊ የጤና መድህን ተቋሙ የገንዘብ ቋቱ እንዳይጎድል ገቢውን ከጊዜ ወደጊዜ ለማሳደግና ወጪውን ለመቀነስ ጥረት ያደርጋል። ተጨማሪ የገቢ ምንጮችን በማጥናት ስራ ላይ በማዋል እንዲሁም የተቀላጠፈ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት በመፍጠር የወጪ ጫናን ለመቀነስ የሚሰጠው ትኩረት ላቅ ያለ ነው።

የጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት መቆጣጠር (Clinical audits)፣ የአባላት መዋጮን በአግባቡ መሰብሰብ፣ የአገልግሎት ክፍያ ተገቢነትን ለማጣራት የሚያስችል ማዕከል ማቋቋም፣ ኤሌክትሮኒክ የክፍያ ስርዓት መፍጠር፣ የጥቅም ማዕቀፉ ውስጥ የተካተቱን የመድሀኒት መዘርዝሮች ማዘጋጀትና የሚታዘዙ መድሀኒቶች ደረጃ ማውጣት

Page 41: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200941

(Medicines list and prescribing levels)፣ የአገልግሎት ሰጪዎች ክፍያ ስርዓት ክለሳ ብሔራዊ የጤና መድህን ተቋሙ በተለያዩ ጊዜያት ወጪውን ለመቀነስ እንዲያስችለው የወሰዳቸው ርምጃዎች ናቸው።

በተመሳሳይ መልኩ ደግሞ ወጪውን ለመቀነስ ከሚወሰደው ርምጃ ጎን ለጎን የገንዘብ ቋቱን ለማዳበር የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሆኑ ማየት ይቻላል። የጤና መድህን ቀረጥን መጨመር፣ ከመንገድ ፈንድ 5 በመቶ ገቢ ማሰባሰብ፣ ከኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገቢ 20 በመቶ ማሰባሰብ፣ ተጨማሪ የበጀት ድልድል እንዲሰራ ማድረግ፣ ወዘተ ወደ ገንዘብ ቋቱ የሚፈሰውን ገንዘብ መጠን ለማሳደግ ተወሰዱ ርምጃዎች ናቸው።

እንዲህም ሆኖ ግን የአገሪቱ የጤና መድህን ስርዓት ፈታኝ ነገሮችን መጋፈጡ አልቀረም። በራዕዩ ላይ እንደተቀመጠው ዘላቂ የጤና መድህን ስርዓት የመመስረት ሂደቱ ላይ የተለያዩ እንቅፋቶች መጋረጣቸው አልቀረም። አባላት ወደጤና ተቋማት የሚያደርጉት ያልተገባ ምልልስ እና የጤና ባለሙያዎች ለታካሚ የሚያደርጉት ያልተገባ ምርመራና መድሀኒት ማዘዝ አንዱ ችግር ነው። ከዚህ በተጨማሪም

የአገሪቱ ፋይናንስ ሚኒስቴር ለተቋሙ የሚለቀው በጀት መዘግየት ለጤና አገልግሎት ሰጪዎች የሚፈጸመው የአገልግሎት ክፍያ ወቅቱን ጠብቆ እንዳይፈጸም እያደረገ የሚገኝ ነው። ከአባላት መዋጮ ነጻ የሚሆኑትን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በአግባቡና በትክክለኛው መንገድ አለመለየት፣ የተጠናከረ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ስርዓት አለመፈጠር፣ የአበላትና የተጠቃሚዎች መታወቂያ ካርድ አስተዳደር፣ የአባላት ምዝገባ መደጋገም አሁን ድረስ የዘለቁ ችግሮች ናቸው።

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ስለጤና መድህን በስፋት ከማስተማር ጀምሮ የተለያዩ የማስተካከያ ርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ማጠናከር፣ የተቋሙን ሰራተኞች አቅም መገንባት፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ስርዓቱን ማጠናከር፣ የአባላትና የተጠቃሚዎች የመታወቂያ አሰጣጡን ማፋጠን፣ እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ያልተገባ አገልግሎት ለማግኘት የሚደርጉትን ጥረት እንዲከላከሉ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር መዘርጋት የጋና ብሔራዊ የጤና መድህን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራባቸው ያሉ ተግባራት ናቸው።

Page 42: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200942

የኩላሊትን ተግባር የሚያቀላጥፉና ለኩላሊት ጤንነት የሚመከሩ፦

ፈሳሾች፦

የኩላሊት ጤንነትን ከምንጠብቅባቸው መንገዶች አንዱ በቂ ውሃ በየዕለቱ መጠጣት ይጠቀሳል።

ከዚህ በተጨማሪም እንደ አፕል ያሉ ፍራፍሬዎች ጭማቂ መጠጣት የሚመከር ነው።

እንደ ሻይ ያሉ ትኩስ መጠጦችም የሚመከሩ ሲሆን፥ ቀጭን የዝንጅብል ሻይ ቢሆን ደግሞ ተመራጭ ነው።

የሽንትዎ ቀለም ብዙም ያልደፈረሰ ከሆነ በቂ ውሃ በሰውነትዎ እንዳለ አመላካች በመሆኑ ይህን ዘዴ በውሃ አወሳሰድዎ ላይ ሊተገብሩት ይችላሉ።

ከዚህ በተቃራኒው አነቃቂ መጠጦች የሚባሉት እንደ ቡና ፣ ኮካ ኮላ ያሉት መጠጦች አወሳሰድን ግን መቀነስ ያሻል።

ፍራፍሬ እና አትክልቶች፦

ፍራፍሬ እና የአትክልት ምግቦች የኩላሊትን ተግባር በማቀላጠፍ ረገድ አቻ የላቸውም።

በተለይም ከፍራፍሬ እንደ አፕል፣ወይን፣ እንጆሪ ያሉት፥ ከአትክልትም ቲማቲም፣ ሽንኩርት፣ የባሮ ሽንኩርት፣ ድንች፣ ስፒናች፣ ፎሶሊያ የመሳሰሉት ለኩላሊት ጤንነት እጅግ ተመራጭ ናቸው።

ለኩላሊት ጤንነት የሚመከሩ ምግቦች!

መዝናኛ

ውሸታምጓደኛዬ ያልነገረኝን ጉድፍወዳጄ ያልጠቆመኝን እድፍ ከፊቱ ቆሜ ስጠይቅ ቁልጭ አድርጎ እሚያሳየኝመስታወቴ እኮ ነው ምንም አይደብቀኝሲሉ ሰምቻለሁ ተጽፎ አንብቤያለሁ ምነው ታዲያ የኔውስንቶች ሲያሽማጥጡግድፈቴ ታይቷቸው ሲጠቋቆሙቀጫጫ ሸፋፋ … እያሉሲንቁኝ ግራ ገብቶኝፊቱ ቆሜ ህጸጼን እማያሳየኝ ውሸታም ነው መስታወቴ እንኳንስ ህጸጼበሱማየው ፊቴም አይደል የኔ ቤዛ በቀለ

ይህን ያውቁ ኖሯልየሌሊት ወፍ ጆሮዋ ከተደፈነ መብረር አትችልም።

ሲጣሉ እርስ በእርሳቸው የሚሰዳደቡ እንስሳዎች ጎሬላ እና ሰዎች ብቻ ናቸው።

ሻርክ በየሳምንቱ ነባር ጥርሶቹን ሙሉ ለሙሉ በአዳዲስ ጥርሶች ይተካል።

ንግስቲቱ ንብ በጭራሽ ሰዎችን አትነድፍም፤ ሌሎች ንቦችን ግን ትናደፋለች።

እባቦች አይናቸውን ጨፍነውም ማየት ይችላሉ።

ሻርክ ሰውን ለማጥቃት የሚነሳው የሰውየው ገላ በውሃ ከረጠበ ብቻ ነው።

ሎብስተር የተባለው የባህር ውስጥ ፍጥረት አንድ አይኑ ቢጠፋ ሌላ አይን ማብቀል ይችላል።

ምንጭ፡- የዕውቀት ማኅደር ቁጥር 1 መጽሃፍ

Page 43: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200943

አንስተኛ የፖታሲየም መጠን ያላቸው ምግቦች፦

ኩላሊት በዋነኛነት በሰውነታችን የፖታሲየም ማዕድን መጠንን የመቆጣጠር ተግባር ስለሚከውን፥ የምንወስድውን የፖታሲየም መጠን መመጠን ይኖርብናል።

ከዚህ በተጨማሪም በምግቦቻችን የሚገኘው ፖታሲየም መጠን ከፍ ያለ ከሆነ ለስትሮክ እና የልብ ህመም የመጋለጥ ዕድላችንን ከፍ እያደረግን ስለሆነ ልናስብብት ይገባል።

አነስተኛ የፖታሲየም ይዘት ካላቸው ምግቦች መካከል አፕል ፣ አተር ፣ ባቄላ ፣ በቆሎ ፣ ሩዝ ፣ ፓስታ ፣ ኮክ ፣ ቃሪያ ፣ ዝኩኒ የመሳሰሉት ይገኙበታል።

በብረት ይዘታቸው የበለፀጉ ምግቦች፦

በተለይም ተመርምረው ከፍተኛ የሆነ የኩላሊት ጤንነት ችግር አለብዎ ከተባሉ ፤ እርስዎ በሰውነትዎ ከፍተኛ የሆነ የብረት ማዕድን እጥረት አለ ማለት ነው።

ኩላሊት በቀይ የደም ሴል ምርት ላይ ቁልፍ ሚና የሚጫወት ሲሆን፥ ይህንን ተግባርም የኩላሊት ሌሎች ተግባራትን በማይነካ ሁኔታ መከናወን ይኖርበታል።

በመሆኑም በቂ የብረት ማዕድን ይዘት ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር ይመከራል።

ለአብነትም እንደ ጎመን፣ ቆስጣ የመሳሰሉትን ቅጠላማ አትክልቶችን መብላት የሚገባ ሲሆን፥ እንቁላል መመገብም ሰውነታችን በበቂ ሁኔታ ብረትን እንዲያገኝ ያስችለዋል።

ምንጭ፦ http://healthyeating.sfgate.com

አመጋገብዎ ከደም አይነት አንጻር ምን መምሰል አለበት?

“A” ቢመገቧቸው የሚመከሩ፦ አትክልት፣ አሳና የአሳ ተዋጽኦ፣ ፍራፍሬ እና የጥራጥሬ ዘሮች በተለይም አናናስ እና ከጥራጥሬ ደግሞ ባቄላ ይህን የደም አይነት ለታደሉ ሰዎች እጅግ ወሳኝ ምግብ ነው።

መመገብ የሌለባቸው፦ ስጋ እና የስጋ ተዋጽኦ፣ ወተትና የወተት ተዋጽኦ እንዲሁም ከጥራጥሬ ደግሞ ስንዴ አይስማማቸውም።

“B” ለምግብነት የሚመከሩ፦ ከዶሮ ውጭ ስጋ፣ ወተትና የወተት ተዋጽኦ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ከጥራጥሬ ባቄላ፣ እንቁላል፣ ትኩስ ጉበት እና ትኩስ ሻይ ይስማማቸዋል።

መመገብ የሌለባቸው፦ ምስር፣ በቆሎ፣ ሰሊጥ፣ ስንዴ እና ለውዝ ለዚህ አይነት የደም ባለቤቶች አይመከሩም።

“AB” መመገብ ያለባቸው፦ የተዘጋጀና ሙዳ ስጋ፣ አትክልትና አሳ፣ ወተትና የወተት ተዋጽኦ፣ ፍራፍሬ በተለይም እንደ አናናስ ያሉት እና ባቄላን ከጥራጥሬ ይመገቡ።

መመገብ የሌለባቸው፦ ቀይ ጥሬ ስጋ፣ በቆሎ፣ ቦሎቄና የቦሎቄ ዘሮች እንዲሁም የቅባት እህሎችን ከገበታ ቢያስወግዱ ይመረጣል።

“O” መመገብ ያለባቸው፦ በፕሮቲን የበለጸጉ፣ የተዘጋጁ ስጋዎችና አሳ፣ ለውዝ፣ ቀለማቸው ቢጫ እና ቀላ ያሉ የአትክልት ዘሮች እና ፍራፍሬ ቢመገቡ ይመከራል። በተለይም ቀይ ስጋ፣ አሳ፣ ጨዋማ ምግቦች እና ትኩስ ጉበት ተመራጭ ናቸው።

መመገብ የሌለባቸው፥ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ቦሎቄ፣ ምስር እና ጎመን ለዚህ አይነት ሰዎች ለገበታ የማይመረጡ ምግቦች ናቸው።

ምንጭ፦ healthylifeland.com

Page 44: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200944

ማንኛውም የማህበራዊ የጤና መድህን አባልና ቤተሰብ በጥቅም

ማዕቀፉ የተካተቱ የህክምና አገልግሎቶችንና መድሃኒቶችን

የማግኘት መብት አለው።

ለግንዛቤዎ

Page 45: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200945

መንግስት በሀገራችን ሁለት ዓይነት የጤና መድህን ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ እየሠራ ነው። አንደኛው የማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን (ማዐጤመ) የሚባል ሲሆን በኢ-መደበኛ ክፍለ ኢኮኖሚ የተሠማራውን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። በአሁኑ ሰዓት

በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በ226 ወረዳዎች እየተተገበረ ይገኛል። እስከያዝነው 2008 በጀት ዓመት ድረስ 12,174,907 ዜጎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል። ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህንን በሌሎች ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በሙከራ ደረጃ ለመጀመርም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ ነው።

ሁለተኛው ማህበራዊ የጤና መድህን (ማጤመ) የሚባል ሲሆን በመደበኛ ክፍለ ኢኮኖሚ የተሠማሩትን ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ሥርዓት ነው። ማህበራዊ የጤና መድህን በበርካታ የአውሮፓ፣ ኤዥያና አፍሪካ ሀገሮች እየተተገበረ ያለ ሲሆን በእኛ ሀገርም ተግባራዊ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራው እየተጠናቀቀ ይገኛል።

የኢትዮጵያ የጤና መድህን የጥቅም ማዕቀፍ እስከ ምን ድረስ?

የጥቅም ማዕቀፍ (Benefit Package) ማለት ምን ማለት ነው?

የጥቅም ማዕቀፍ ማለት በጤና መድህን ሥርዓት ውስጥ ለአባላትና ቤተሰቦቻቸው በአባልነታቸው ምክንያት የሚያገኙት የጤና አገልግሎት ዓይነት ወይም ዝርዝር

የህክምና፣ የምርመራ እና የመድሀኒት አገልግሎት ነው። የጤና መድህንን የተገበሩ በርካታ ሀገሮች ልምድ እንደሚያሳየው የጤና መድህን አባላት የሚያገኟቸው የጤና አገልግሎት ዓይነቶች ሲቀመጥ አንድም የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ልቅም አድርጎ በመዘርዘር ከዚህ ውጭ ያሉት አገልግሎቶች እንደማይሸፈኑ በመግለጽ ነው።

አንዳንድ ሀገሮች ደግሞ በጤና መድህን የማይሰጡ ተብለው የተለዩ የጤና አገልግሎቶችን በዝርዝር በማስቀመጥ

ማንኛውም ተጠቃሚ ከነዚህ ውጭ ያሉ አገልግሎቶችን በሙሉ ማግኘት እንደሚችል ያስቀምጣሉ። ኢትዮጵያ ያወጣችው የጤና መድህን ሥርዓት በጤና መድህን የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶችን በጥቅል በማስቀመጥ የማይሰጡ አገልግሎቶችን ደግሞ በመዘርዘር ከነዚህ ውጭ ያሉ ሁሉም ዓይነት የጤና አገልግሎቶች ለአባላትና ቤተሰቦቻቸው እንደሚሰጡ ይገልጻል።

በመሆኑም ማንኛውም የማህበራዊ ጤና መድህን አባልና ቤተሰብ በጥቅም ማዕቀፉ የተካተቱ የህክምና አገልግሎቶችንና መድሃኒቶችን የማግኘት መብት አለው። ምንም እንኳ የጥቅም ማዕቀፉ የሚያካትታቸውን የጤና አገልግሎት ዓይነቶች ከብዛታቸው የተነሳ በዚህ አጭር ጽሁፍ መዘርዘር አዳጋች ቢሆንም በየአገልግሎት ዘርፉ የሚሰጡ ዋና ዋና ህክምናዎች ብቻ ከዚህ በታች ለማስቀመጥ መሞክሯል።

በጌታቸው ጥሩነህ

Page 46: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200946

1. የተመላላሽ ህክምና (Outpatient)

የተመላላሽ ህክምና ሲባል ህሙማን በማንኛውም ደረጃ ባለ የጤና ተቋም ተኝተው መታከም ሳያስፈልጋቸው በተመላላሽ ደረጃ የህክምና ባለሙያዎችን እያገኙ የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት ነው።

በዚህ አገልግሎት ሥር ለጤና መድህን አባላትና ቤተሰቦች የሚሠጡ ዋና ዋና የህክምና አገልግሎቶች፡-

• የወሊድ አገልግሎት (Delivery Service)፣

• የህጻናት ህክምና፣

• የውስጥ ደዌ ህክምና፣

• የአእምሮ ህክምና (Mental Health)፣

• የቀዶ ጥገና ህክምና (Surgical Service)፣

• የአጥንት ህክምና (Orthopedics)፣

• ከአንገት በላይ ህክምና (ENT)

• የካንሰር ህክምና (Cancer)፣

• የደም ግፊት ህክምና (Hypertension)፣

• የስኳር ህክምና (Diabetes)፣

• የልብ ህክምና፣

• የዓይን ህክምና (Ophthalmology)፣

• የጥርስ ህክምና (Dental)፣

• የላብራቶሪ ምርመራ፣ (Laboratory)

• የራጅ ምርመራ አገልግሎት (X-Ray)፣

• የፊዝዮቴራፒ ህክምና (Physiotherapy)፣

• የፕሮሲጀር ምርመራ አገልግሎት (Diagnostic Pro-cedures) እና ሌሎች በተመላላሽ የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶችን ማግኘት ይቻላል።

2. የተኝቶ ህክምና (Inpatient)

የተኝቶ ህክምና ሲባል ህሙማን ያጋጠማቸው የህመም ደረጃ በጤና ተቋም ተኝቶ/አልጋ በመያዝ በህክምና ባለሙያዎች የቅርብ ክትትል እየተደረገላቸው የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት ነው። በዚህ አገልግሎት ሥር የሚከተሉት ህክምናዎች ለጤና መድህን አባላትና ቤተሰቦች ይሰጣሉ።

• የፅኑ ህሙማን ክትትል (Intensive Care)፣

• ቀዶ ጥገና ህክምና (Surgery)

• የካንሰር ህክምና (Cancer)፣

• የስኳር ህክምና (Diabetes)፣

• የአጥንት ስብራት ጥገና ህክምና (Fractures)፣

• የዓይን ህክምና (Ophthalmology)፣

• የውስጥ ደዌ ቴራፒ (Internal Medicine Therapy)፣

• የተቅማጥ ህክምና (ለአዋቂዎች) Diarrhea Infections)፣

• የሄፓታይተስ ህክምና (Hepatitis)፣

• የደም ግፊት ህክምና (Hypertension)፣

• የልብ ህክምና (Cardiac Vascular diseases)፣

• የጽንስና ማህጸን ህክምና (Gynecology)፣

• የጨቅላ ህጻናት ህክምና (Neonatal)፣

• የወሊድ አግልግሎት (Maternity)፣

• የአዕምሮ ህክምና (Mental health)፣

• የጥርስ ህክምና (Dental)፣

• የህጻናት ህክምና (Pediatric)፣

• የአንገት በላይ ህክምና (ENT) እና ሌሎች በተኝቶ ህክምና የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶችን ማግኘት ይቻላል።

Page 47: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200947

3. የቀዶ ጥገና ህክምና (Surgery)

የቀዶ ህክምና አገልግሎት ህሙማን በጤና ተቋማት ተኝተው የሚያገኙት የህክምና አገልግሎት ዓይነት ነው። የጤና መድህን አባላትና ቤተሰቦቻቸውም የሚከተሉትን አገልግሎቶች ማግኘት ይችላሉ።

ቀላል ቀዶ ህክምና፣

ከፍተኛ ቀዶ ህክምናና፣

ስፔሻላይዝድ ቀዶ ህክምና ለምሳሌ፡- የልብ፣ የነርቭ፣ የአንጎል ቀዶ ህክምና እና ሌሎች አገልግሎቶችን ያካትታል።

4. የላቦራቶሪ አገልግሎት (Laboratory Investigation & Diagnostic Services)

የላቦራቶሪ አገልግሎት ህሙማን ከሀኪሞች ጋር በሚኖራቸው የህክምና መስተጋብር ለሚያደርጉት አካላዊ ምርመራ (Phys-ical Examination) እና ታካሚው ለሀኪሙ የሚሰጠውን የህመም ስሜትና ሁኔታ መረጃ (Patient History) ለማጠናከር እንዲረዳ ለተጨማሪ ምርመራ የሚታዘዝ የህክምና አገልግሎት ነው። ማንኛውም የጤና መድህን አባልና ተጠቃሚ በርካታ የላቦራቶሪ ምርመራና ዲያግኖስቲክ አገልግሎቶችን ማግኘት

ይችላል። ለአብነትም የኤም.አር.አይ (MRI)፣ የሲቲ - ስካን (CT-Scan)፣ የኢኮካርዲዮግራፊ (Echocardiography)፣ ኢንዶስኮፒ (Endoscopy)፣ የአልትራ ሳውንድ (Ultrasound)፣ የኤክስሬይ (X-Ray)፣ ልዩ ልዩ የኬሚስትሪ ምርመራዎች፣ ወዘተ…. ይገኙበታል።

5. የመድሀኒት አገልግሎት

የጤና መድህን አባልና ተጠቃሚ ወደ ሀገራችን እንዲገቡ የተፈቀዱ ማንኛውም ዓይነት መድሀኒቶችን የማግኘት መብት አለው። የመድሀኒቶቹ ዝርዝር ሰፊ በመሆኑ በዚህ አጭር መግለጫ ማስፈር ባይቻልም ከላይ ለተጠቀሱት የህክምና ዓይነቶች እና ሌሎችም ያልተዘረዘሩ በርካታ የህክምና አገልግሎቶች እንዲውሉ የተመረጡ 538 የመድሃኒት ዓይነቶች በጥቅም ማዕቀፉ እንዲካተቱ ተደርጓል። ስለሆነም ሙሉ መረጃ ማግኘት የሚፈልግ አካል በኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት ወይንም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ቀርቦ ሙሉ ዝርዝሩን መመልከት እንደሚችል ለማስገንዘብ እንወዳለን።

በአጠቃላይ በሀገራችን የሚተገበረው የጤና መድህን ሥርዓት ለአባላትና ቤተሰቦች እንዲሰጡ የሚፈቅዳቸው የጤና አገልግሎት ዓይነቶች ከአንዳንድ ሀገሮች ጋር ሲነጻጸር የተሻለ እንደሆነ ልብ ሊሉ ይገባል።

Page 48: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200948

ይህንንም ለማሳካት መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ያደርጋሉ። መንግስት ፖሊሲውን ወደ ተግባር ለመለወጥ እንዲሁም ጥራቱን የጠበቀና ፍትሀዊ የሆነ የጤና አገልግሎት ለህዝቡ ለማቅረብ እንዲያስችለው ብሔራዊ የጤና መድህን ፈንድ እንዲቋቋም የሚያስችል ህጋዊ መሰረት ከጣለ አመታት አልፈዋል።

የታንዛኒያ ብሔራዊ የጤና መድህን ፈንድ ዋነኛ ዓላማ የጤና አገልግሎት ወጪው የዜጎችን አቅም በማይፈታተን መልኩ አገልግሎት ለማቅረብ አስቀድሞ በሚደረግ አነስተኛ መዋጮ የጤና ፋይናንስ ዓቅም መፍጠር ነው። ብሔራዊ የጤና መድህን ፈንድ የሚያቅፋቸው አባላት የደመወዛቸውን 6% ከአሰሪዎች ጋር እኩል

ሀገራት ለጤና ዘርፍ የሚያስፈልጋቸው ገንዘብ በየአመቱ መንግስታት ከሚመድቡት በጀት እየተቀነሰ የሚመደብ ነው። ነገር ግን የጤና ችግሮች ውስብስብ እየሆኑና የጤና ወጪም እጅግ በማሻቀቡ የተነሳ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማሟላት ሲባል የተለያዩ የገንዘብ ማግኛ

ስልቶች ይቀየሳሉ። እስካሁን ድረስ ከተቀየሱት ስልቶች መካከል የጤና መድህን ስርዓት ውጤታማነቱ ይጠቀሳል።

የጤና መድህን ስርዓትን በየሀገራቸው ተግባራዊ አድርገው ውጤታማ ከሆኑት አገራት መካከል የታንዛኒያ፣ የሩዋንዳንና የደቡብ ኮሪያን ተሞክሮ ልናስቃኛችሁ ወደናል። ሀገራቱ የጤና መድህን ስርዓታቸው ምን እንደሚመስል፣ ለጤና መድህን አባሎቻቸው የሚሰጧቸው የቴና አገልግሎቶችና የአባልነት ሁኔታቸው ምን እንደሚመስል እንመለከታለን።

የሀገራት የጤና መድህን ተሞክሮ

ታንዛኒያ-የጤና መድህን ስርዓት

44 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ታንዛኒያ የጤና መድህን ስርዓትን በመተግበር የአገሪቱን የጤና ሁኔታ ለማሻሻል እየሰራች ትገኛለች። በዚህም ከአምስት አመት በታች የህጻናት ሞት ክስተትን 54/1000 ለማድረስ ችላለች፤ በአጠቃላይ የጤና ሁኔታ መሻሻል በመምጣቱም የዜጎች በህይወት የመኖር ዕድሜ ጣሪያ በአማካኝ 61 ዓመት ደርሷል። ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ የነፍስ ወከፍ የጤና ወጪ ወደ 41 የአሜሪካን ዶላር ከፍ ብሏል።

የሀገሪቱ የጤና እና ማህበራዊ ዋስትና ሚኒስቴር የጤና ፖሊሲ የሚያጠነጥነው በበሽታ በመከላከል፣ በጤና ትምህርትና የፈውስ ህክምና ዙሪያ በመሆኑ በሶስቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት ይሰራል።

በዓቢይ ጌታሁን

Page 49: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200949

በመጋራት በየወሩ እንዲያዋጡ ይደረጋል።

የብሔራዊ የጤና መድህን ፈንድ በአባልነት የሚይዛቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ የማዕከላዊ መንግስት ሰራተኞች፣ የክልልና የታችኛው የመንግስት አስተዳደር እርከን ሰራተኞች፣ ፖሊስ፣ ጡረተኞች፣ በግል ስራ የሚተዳደሩ ግለሰቦች፣ የግል ተቋማት ሰራተኞች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞች ናቸው።

እነዚህ የብሔራዊ የጤና መድህን ፈንድ አባላትና ተጠቃሚዎች ከጤና ተቋማት የተለያዩ የጤና አገልግሎቶችን ያገኛሉ። የሀኪም ምክርና ምርመራ፣ የተመላላሽ ህክምና፣ የተኝቶ ህክምና፣ በህክምና ባለሙያ የሚታዘዙ መድሀኒቶች፣ የላብራቶሪ ምርመራ አገልግሎት፣ የቀዶ ህክምና፣ ፊዚዮቴራፒ፣ የአይን ህክምና፣ እንዲሁም የጥርስ ህክምና በጥቅም ማዕቀፉ ውስጥ የተካተቱ የጤና አገልግሎት ናቸው። ከነዚህ ዝርዝሮች ውጪ የሆኑ የጤና አገልግሎቶች በብሔራዊ የጤና መድህን ፈንድ የማይሸፈኑ ናቸው።

ሩዋንዳ የጤና መድህን ስኬት ማሳያ

በአህጉር አፍሪካ የጤና መድህን ስርዓትን በመተግበር ከቀዳሚ አገሮች ተርታ የምትሰለፈው ሩዋንዳ ሁሉን አቀፍ የጤና ተደራሽነትን በማረጋገጥ በኩል ያመጣችውን ውጤት ማጣጣም ጀምራለች።

ማህበረሰቡን ያሳተፈ የጤና ፋይናንስ ስርዓት ለመዘርጋት ስትነሳሳ የጤና መድህን አባል መሆን በግለሰቦች ፍላጎት ላይ የተመሰረት መሆኑ አጀማመሩ ብዙ መንገራገጮችን እንዲያልፍ አድርጎታል።

የአለም የጤና ድርጅት የአገሪቱ የጤና መድህን ስርዓት ጉዞ ላይ ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ሩዋንዳ የጤና መድህን አባልነትን አስገዳጅ ባደረገችው ማግስት ብዙ እንቅፋቶችን ማስወገድ መቻሏን አረጋግጧል። የጤና መድህን አባልነት አስገዳጅ እንዲሆን በመንግስት ውሳኔ መተላለፉና የመንግስት ድጎማ መጠናከር በአገሪቱ የጤና አገልግሎት አጠቃቀም ላይ መሻሻል አምጥቷል።

Page 50: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በተለያዩ ጊዜያት የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግ ሙከራ አድርጓል። ከህብረተሰቡ ተሳትፎ ባሻገር የወጪ መቀነሻ ስትራቴጂዎችን በመንደፍና በመተግበር፣ እንዲሁም የልማት አጋሮችን ድጋፍ በማጠናከር ረገድ ውጤታማ ስራ ሰርቷል። ይህም በተወሰነ ደረጃ በመንግስት ጫንቃ ላይ ወድቆ የነበረውን ሸክም አቅልሎታል።

በተለይ ሁሉም ሩዋንዳውያን የጤና መድህን እንዲኖራቸው መደረጉ የአገሪቱ የጤና ወጪ ጫና በአንድ ወገን ላይ ብቻ እንዲያርፍ ያደረገው አስተዋፅኦ ከሁሉም በላይ የሚጠቀስ ነው። ስለሆነም የሩዋንዳ መንግስት የጤና መድህን ስርዓትን ለማሻሻል ትኩረት ሊሰጠው ችሏል። የመንግስት አመራሮች ስርዓቱን ለመደገፍ በቁርጠኝነት መስራታቸው፣ የጤና መድህን ስርዓቱ ለማስፈፀም የተቋቋመው መንግስታዊ

ተቋም ሁሉን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማደራጀቱ፣ የሰራተኞች በተለያየ መንገድ አቅማቸውን መገንባት መቻላቸው ለተመዘገበው ውጤት ቀዳሚ ተጠቃሾች ናቸው።

የርዋንዳ ናሽናል ዩኒቨርስቲ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት የቀድሞ ዳይሬክተር ላውረን መሳንጎ እንደሚገልፁት ከሰሀራ በታች ካሉ አገሮች ሁሉ በጤና መድህን ስርዓት የላቀ ውጤት በማምጣት ቀዳሚ ያደረጋት ምስጢር የጤና መድህን አባልነት አስገዳጅ በመሆኑ ነው። በአሁኑ ወቅት የሩዋንዳ የጤና መድህን የአባልነት ምጣኔ 85 በመቶ ደርሷል።

ኮሪያ ሪፐብሊክ

በ12 ዓመት ጊዜ ውስጥ ሁሉን ዓቀፍ የጤና ተደራሽነትን ማረጋገጥ የቻለችው የኮሪያ ሪፐብሊክ የስኬቷ ምንጭ የጤና መድህን ስርዓት መዘርጋቷ እንደሆነ

ትገልጻለች። የአገሪቱ የጤና መድህን ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ከ1963 እስከ 1977 ድረስ ባሉት ጊዜያት ውስጥ እውን የሆነው በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የጤና መድህን አባልነት ውጤታማ ባለመሆኑ የተነሳ የጤና መድህን አባልነት አስገዳጅ እንዲሆን የሚያግዝ የህግ መሰረት ከተጣለ በኋላ በ1977 የተጀመረው የጤና መድህን ስርዓት ሁሉን ዓቀፍ የጤና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ረድቷታል።

ፕሮግራሙ ሲጀምር 500 እና ከዚያ በላይ ሰራተኛ ያላቸው የግል ኩባንያዎች ሰራተኞች ሁሉ ወደጤና መድህን አባልነት እንዲገቡ ከተደረገ በኋላ በሂደት አምስት እና ከዚያ በላይ ሰራተኞች ያሏቸው ተቋማት ወደአባልነት እንዲገቡ የሚያስገድድ እስከመሆን ደርሷል። አባልነት አስገዳጅ እንዲሆን በአዋጅ ሲደነገግ ሁሉም ዜጎች በአንድ ጊዜ

Page 51: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

እንዲገቡ አልተደረገም። ምክንያቱም የአባላት ቁጥር ሲጨምር አብሮ ተያይዞ የሚመጣ ጫና በመኖሩ በሂደት ሁሉም የሚገባበት አሰራር ነው የተዘረጋው።

የኮሪያ ሪፐብሊክ ብሔራዊ የጤና መድህን ፋይናንስ በአብዛኛው የሚመነጨው ከአባላት በሚሰበሰብ መዋጮ ነው። 85 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆነው ፋይናንስ ከአባላት የሚዋጣ ሲሆን 13 ነጥብ 3 በመቶ ከመንግስት ድጎማ እንዲሁም 1 ነጥብ 2 በመቶ ከተለያዩ ምንጮች የሚገኝ ነው።

በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ አንድ የጤና መድህን አባል የገቢውን 6 ነጥብ 07 በመቶ መዋጮ ያደርጋል። አሰሪውም የሰራተኛውን እኩል ድርሻ በተመሳሳይ ያዋጣል። በግል ስራ የሚተዳደሩ የብሔራዊ ጤና መድህኑ አባላት በሚኖራቸው ገቢ፣ ዕድሜና ጾታ የተለያየ ንብረት መሰረት ተሰልቶ ወርሃዊ መዋጮ

እንዲከፍሉ ይደረጋል። ይህ መዋጮ ግዴታ ቢሆንም በአንዳንድ ሁኔታዎች የመዋጮ መጠኑ እስከ 50 በመቶ ድረስ ለአንዳንድ የመድህኑ አባላት ይቀነሳል። በደሴት ወይም ደግሞ ሩቅ በሆኑ የገጠር አካባቢ የሚሰሩ ሰራተኞች እና ቤተሰብ በሀገር ውስጥ ኖሯቸው በውጭ አገር የሚኖሩ አባላት 50 በመቶ የመዋጮ ቅናሽ ይደረግላቸዋል። በሀገር ውስጥ ተጠቃሚ ቤተሰብ የሌላቸው ሆነው በውጭ የሚኖሩ አባላትና በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙ አባላት ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ከመዋጮ ነጻ ናቸው።

በብሔራዊ የጤና መድህኑ የጥቅም ማዕቀፍ ውስጥ የተለያዩ ምርመራዎች፣ መድሀኒቶች እና ቀዶ ህክምና የተካተቱ ሲሆን እንደህመም ዓይነቶቹ ታማሚው ከህክምና ወጪው በአማካኝ 37 በመቶ ያህል እንዲከፍል ይደረጋል።

Page 52: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200952

ከአባላት አንደበት

የጤና መድህን ስርዓት በኢትዮጵያ መተዋወቅ የጀመረበት ጊዜ ገና ጨቅላ የሚባል ቢሆንም የስርዓቱ ተጠቃሚ መሆን የጀመሩ ዜጐች ከጅምሩ ለስርዓቱ ያላቸውን አድናቆት መቸር ጀምረዋል።

በሀገራችን ቀድሞ ተግባራዊ የተደረገው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን (ማዓጤመ) በተጀመረባቸው በትግራይ ፣ በአማራ ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስታት የሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ እተመዘገበ ያለው ውጤት ለዜጐች የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራት የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።

በዋነኛነት መደበኛ ባልሆነ የኢኮኖሚ ዘርፍ የተሠማሩትን የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ የሚያቅፈው የማዓጤመ ስርዓት በ2003 ዓ.ም ከላይ በተጠቀሱት አራቱ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 13 ወረዳዎች ነበር አሀዱ ተብሎ የተጀመረው። አሁን ላይ በአራቱ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 202 ወረዳዎች ተስፋፍቶ እየተሰራበት ይገኛል። በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ደግሞ የወረዳዎቹን ሽፋን በአገር አቀፍ ደረጃ 80 በመቶ ለማድረስ እንደሚሰራ በጤና ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ (HSTP) ላይ ተቀምጧል። የማዐጤመ የሙከራ ትግበራ እና ማስፋፍያ እየተካሄደባቸው ባሉ ክልሎች ስር በሚገኙ የተለያዩ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደሮች ስለማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን የሰጡት አስተያየት የሚከተለው ነው።

ከአባላት አንደበት

በብርሃኑ ኩማ

Page 53: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200953

“ጊዜው ስለሄደ ወሩን በትክክል አላስታውሰው ይሆናል በዕለተ እሁድ አቅራባየ ወደሚገኘው ገብርኤል ቤተክሪስትያን ለፀሎት ሄጄ ቅዳሴ ካለቀ ባኃላ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይተላለፉ ነበር፣ በዕለቱ ከተላለፉት መልዕክቶች ውስጥ አንዱ የጤና መድህን የሚባል ነገር እንደመጣና ይህም አርሶ አደሩ በዓመት ይከፍልና አስከነቤተሰቦቹ ህመም ሲያጋጥማቸው ዓመቱን ሙሉ የሚታከሙበት ስርዓት መሆኑን የቀበሌያችን ሊቀመንበር ሲያስረደ ሰማሁት። አጠገቤ ከነበሩት የአካባቢየ ነዋሪዎች ጋር በጉዳዩ ላይ ስንወያይ በሰበብ አስባቡ ገንዘባችንን ለመውሰድ የተዘረጋ ዘዴ እንደሆነ እንጂ ሰው በመታወቂያ ብቻ እንዴት ይታከማል የሚል ጥያቄ ፈጠረብን።

የቀበሌው ሊቀመንበር ከእኔ ጋር ቅርበት ስላለው ስለጉዳዩ ደጋግሞ ስላስረዳኝ ‹ገንዘቤን ከተበላውም አንተን አምኜ ነው› በማለት የሚያስፈልገውን ክፍያ በመፈፀም በ2003 ዓ.ም የጤና መድህን አባል ሆንኩኝ።እስከ 2006 ዓ.ም የአባልነት ክፍያየን እየፈፀምኩ ምንም ሳልታከም በሰላም ቆየሁ። በ2006 ዓ.ም ግን ድንገት ድካምና የጤና መታወክ ስሜት ተሰማኝና ልሁዲ ጤና ጣቢያ ሄጄ የቻለውን ህክምና አድርጎልኝ በመጨረሻ ወደ ፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል ሪፈር ፃፈልኝ።ፈለገህይወት ሆስፒታልም አስፈላጊውን ምርመራ ካደረገልኝ በኋላ የካንሰር ታማም መሆኔን ገለፀልኝ።

በሆስፒታሉ ለልዩ ልዩ ምርመራዎች፣ ለመድኃኒትና ለአልጋ የሚወጣው ክፍያ ከኪሴ የሚከፈል ቢሆን ኖሮ ምኑን ከምኑ አድርጌ እችለው እንደነበር አሰብኩና የጤና መድህን አባል እንዲሆን የመከረኝን ሰውና ፈጣሪየን በእጅጉ አመሰገንኩ። በሆስፒታሉ ቆይታየ የክፍያ ሂሳብ ደብተር ላይ እንድፈርም ከማድረግ ውጭ አምስት ሳንቲም እንኳን ክፈል አልተባልኩም። ህክምናየን ጨርሼ ከሆስፒታሉ ከወጣሁ በኋላም በቀጠሮየ እየተመላለስኩ የሚታዘዙልኝን መድኃኒቶች እየወሰድኩ በጤናየ ላይ የተወሰነ ለውጥ አለኝ፣ እስከ አሁን ብቻ የጤና መድህን ከ28 ሺ ብር በላይ ወጪ አድርጎ አሳክሞኛል።

ይህን ያህል ወጪ ወጥቶልኝ ስታከም አንድ ጊዜ ብቻ ጋምቢ በተባለ የግል ሆስፒታል ላቦራቶሪ እንዳሰራ ተልኬ 250 ብር ከኪሴ የከፈልኩ ቢሆንም፣ ባቀረብኩት ህጋዊ ደረሰኝ መሰረት ወዲያውኑ ከጤና መድህኑ ተመልሶልኛል።በዓመት ለፍቼ ደክሜ የማመርተው ከቀለቤ ተርፎ አያውቅም። ያለኝ ሀብት ሁሉ ተሰብስቦ ቢሸጥ እንኳን ለህክምናዬ የወጣውን ገንዘብ አያወጣም፤ አዋቂው ፈጣሪ ቢሆንም እንደሰው ሰውኛ ሳስበው አፌን ሞልቼ መናገር የምችለው እስከ አሁን በህይወት አልቆይም ነበር። ‹የቤተሰቤስ እጣ ፋንታ ምን ሊሆን ይችል ነበር?› ብቻ ሳይደግስ አይጣላም ይባል የለ? ፈጣሪ ይመስገን። ጤና መድህኑም ይስፋፋልን።”

“የጤና መድህን ከ28 ሺ ብር በላይ ወጪ አድርጎ አሳክሞኛል”

አቶ ላመስግን እርቄ

በአማራ ክልል ደቡብ አቸፈር ወረዳ የዲላሞ ቀበሌ ነዋሪና የማዐጤመ አባል ባለትዳርና

የስምንት ልጆች አባት

ከአባላት አንደበት

Page 54: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200954

“የጤና መድህን ስርዓት መንግስት ካመጣቸው በርካታ ቅዱስ ተግባራት ቀዳሚው ነው። እኔና ቤተሰቦቼ የጤና እክል ከገጠመን በሚንኖርበት ቆጣ ኩምቦላ ቀበሌ ውስጥ ከሚገኘው የፎንጦ ጤና ጣቢያ አስቀድመን ባደረግነው አነስተኛ አመታዊ መዋጮ አማካኝነት፣ የህክምና አገልግሎት እያገኘን ነው።በአካባቢያችን ማዓጤመ ከመጀመሩ በፊት ህመም በሚገጥመን ጊዜ ለህክምና የሚሆን በቂ ገንዘብ እጃችን ላይ ስለማይኖረን ‹ከዛሬ ነገ ይሻለኛል› በሚል ወደጤና ተቋማት ለመሄድ ስንቸገር ነበር።ህመም ሲበረታብንም ለከፍተኛ ወጪ መዳረግ፣ ብድር ውስጥ መዘፈቅ፣ ሀብት ንብረታችንን ለመሸጥ እንገደድ ነበር።

እኛ ከከፈልነው ዓመታዊ መዋጮ በላይ የህክምና አገልግሎት እያገኘን ነው።የጤና እክል ካልገጠመንም እኛ ባዋጣነው ወዳጅ፣ ዘመዶቻችንና ጎረቤቶቻችን ታክመው ሲፈወሱ ስናይ የጤና መድህን ስርዓት እውነተኛ የመደጋገፊያ መንገድ መሆኑን አይተናል። ”

“ማዐጤመ በወረዳችን በመጀመሩ ባለቤቴና ልጆቼን ጨምሮ ለአባልነት መዋጮ በከፈልኩት አነስተኛ ብር ዓመቱን ሙሉ እንታከማለን። አሁን አንዱ ልጄ ብቻ ታሞብኝ ወደ ጤና ተቋም ብሄድ ለህክምናው የምጠየቀው ገንዘብ ለአመታዊ መዋጮ ከከፈልኩት ብር ይበልጣል።በዓመት አንዴ አርሰን በምናገኘው ምርት አመቱን ሙሉ ባለቤቴ፤ እኔና ልጆቼን ጨምሮ ድንገት ብንታመም ለ10 ሰው ህክምና የሚወጣው ወጪ ያሰጋን ነበር፣ አሁን ያሁሉ ቀርቷል። ባለፈው እኔ ዘመድ ጥየቃ ሄጄ ባለቤቴ ታማ ነበር፣ እንደጋጣሚ እጇ ላይ ገንዘብ አልነበራትም፣ ነገር ግን የማዐጤመ የአባልነት ደብተር ስላላት ከአንድ ሺ ብር በላይ ያስወጣ ህክምና አግኝታ ጠበቀችኝ። ጤና መድህን ባይኖር ኖሮ እኔ ከሄድኩበት ተመልሼ እህል እስክሸጥ፣ እህል ከሌለኝ ብድር እስከማገኝ ህመሙ ይጠናባት ነበር። መንግስታችን ባመጣልን ጤና መድህን በአነስተኛ መዋጮ ህክምና እንድናገኝና ከስጋት እንድንገላገል አድርጎናል” በማለት ሀሳባቸውን አጠቃለዋል።

“የጤና መድህን ስርዓት መንግስት ካመጣቸው ቅዱስ ተግባራት ቀዳሚው ነው”

አርሶ አደር ጡምሳ ቴራሶበደ/ብ/ብ/ ህዝቦች ክልል ከንባታ ዞን

የደምቦያ ወረዳ ነዋሪና የመዕጤመ አባል

አርሶ አደር ኡርጌሳ አራርሳ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የአደአ ወረዳ ነዋሪና የማዕጤመ አባል

“የጤና መድህን በአነስተኛ መዋጮ ህክምና እንድናገኝና ከስጋት እንድንገላገል አድርጎናል”

ከአባላት አንደበት

Page 55: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200955

በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የክልተአውላሎ ወረዳ አይናለም ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት እናት ወይዘሮ ተኽለ ገብረህይወት ልጃቸው ሰላማዊት ‹አድጋ ልትደግፈኝ ነው›

ብለው በሚያስቡበት ጊዜ ጤናዋ መቃወሱ እራስ ምታት ሆነባቸው። መደገፍ ብቻ ሳይሆን ጤናዋን ለመመለስ ሐኪም ቤት በማመላለስ ጥሪታቸውን ማሟጠጣቸው ነገሩን ሁሉ ‹በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ› አደረገባቸው። የልጃቸው ሰላማዊት ጤና መቃወስ ገንዘባቸውንም፣ ጉልበታቸውንም ፈጀው። ከዛሬ ነገ ጤናዋ ይመለሳል ብለው ቢጠብቁም ህመሙ እየጠናባት ሰውነቷ እንደልብ አልታዘዝ፣ አይኗም እንደሚፈልገው ብርሃን አልሰጥ አላት።

ወይዘሮ ተኽለ የልጃቸውን ጤና ለመመለስ አቅማቸው የፈቀደውን ያህል ወደ ጠበልም፣ ወደ ባህል ሐኪምም ተመላልሰዋል። በአቅራቢያቸው በሚገኝ የጤና ተቋም መመላለስም የገንዘብ አቅማቸውን አድቅቆታል። የክልተአውላሎ ወረዳ በ2003 ዓ.ም ያስተዋወቀው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓት (ማዐጤመ) እንዲህ እንደ ወይዘሮ ተኽለ የጤና ወጪ ፈተና ለሆነባቸው ሰዎች መድህን ሆነ። በ2004 ዓ.ም የማዐጤመ አባል የሆኑት ወ/ሮ ተኽለ ለጤና መድህን አባል ከሆኑ ወዲህ በየጊዜው ወደጤና ተቋም ሲሄዱ የሚከፍሉትን ያልተጠበቀ የጤና ወጪ አስቀረላቸው።

የልጃቸው የሰላማዊት ጤና ከታወከበት ጊዜ አንስቶ ለጤና ተቋማት ያወጡት ወጪ ሲያሰሉት እና አሁን የጤና መድህን አባል በመሆናቸው ያገኙትን እፎይታ ሲያነፃፅሩት

ልዩነቱ የምድርና የሰማይ ያህል እንደሆነ ይመሰክራሉ። የጤና መድህን አባል ከሆኑ በኃላ ግን በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የጤና ተቋም ልጃቸው ህክምና አግኝታ ሊሻላት ባለመቻሉ ወደቀጣዩ የጤና ተቋም ሄዳ እንድትታከም በጤና ባለሙያ በመታዘዙ መቐለ ወደሚገኘው የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል በማምራት ሙሉ ህክምና አግኝታ ጤናዋ ሊመለስ ችሏል። የልጃቸው ሰላማዊት የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ቆይታ በአጠቃላይ 10 ሺህ 975 ብር ወጪ ያስወጣ ሲሆን የጤና መድህን አባል በመሆናቸው የተነሳ ሙሉ ወጪያቸው በመድህኑ ተሸፍኖላቸዋል።

የሰላማዊት የጤና እክል ‹የስኳር ህመም› መሆኑ በመታወቁ በአቅራቢያቸው ከሚገኘው የውቅሮ ሆስፒታል በየወሩ መድሃኒት እንድትወስድ በመደረጉ በአሁኑ ሰዓት የልጃቸው ጤና በጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘቱን ያስረዳሉ። ‹‹የጤና መድህን መምጣት እንደኔ ላሉ አርሶ አደር ቤተሰቦች ፍቱን መድሃኒት ነው። አሁን ልጄ የታከመችበትን ገንዘብ ድንገት ክፈይ ብባል ከየት አመጣው ነበር። በሬ ተሸጦም የሚመለስ አይደለም። ጤና መድህን በእውነትም መደጋገፍ መሆኑን እመሰክራለሁ። አሁን እኔ ብቻ ሳልሆን ጎረቤቶቼም የጤና መድህን አለኝታችን መሆኑን ተምረዋል። ›› ይላሉ ወይዘሮ ታኽለ። የጤና መድህን አባል የሚሉት ወ/ሮ ታኽለ ‹ብንታመም ያለስጋት የምንታከምበት፣ ባንታመም ዘመድ ጎረቤት የሚታከምበት ይሆናል› ሲሊ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።

ወ/ሮ ተኽለ ገብረህይወት

‹‹የጤና መድህን መምጣት እንደኔ ላሉ ቤተሰቦች ፍቱን መድሃኒት ነው››

ከአባላት አንደበት

Page 56: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

በጤና መድህን ስርዓት ዙሪያ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ጋር የተደረጉ ውይይቶች

የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ እና የ24ቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊዎች የጋራ የምክክር መድረኮች(አዳማ)

የኢትዮ- ኮሪያ የጤና ዘርፍ የትብብር ፎረም በአዲስ አበባ በተካሄደበት ወቅት

ከፎቶ ማህደር

Page 57: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ሰራተኞች 25ኛውን የግንቦት 20 የብርኢዮቤልዩ በዓል በደማቅ ስነስርዓት አክብረዋል።

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ የገጠርና የከተማ ቀበሌ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል።

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባላት በድሬ ወለታ ጤና ጣቢያ አገልግሎት በመጠባበቅ ላይ (ድሬ ወለታ ቀበሌ፣ ደደር ወረዳ ኦሮሚያ ክልል)

የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አባላት አገልግሎት በማግኘት ላይ እያሉ

Page 58: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200958

በማህበራዊ የጤና መድህን ዙርያ ለትግራይ ክልል፣ የዞን፣ የወረዳ ኣመራሮችና የክልል ሴክተር መስሪያ ቤት ተወካዮች ስልጠና ሲሰጥ‐ (መቐለ ሰማእታት ሐዉልት)

በማህበራዊ የጤና መድህን ስርዓት ዙሪያ ለድሬደዋ ከተማ የመንግስት ሰራተኞች ስልጠና ሲሰጥ

ከፎቶ ማህደር

Page 59: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

ቅጽ 02/ ቁጥር 02 /መስከረም 200959

አቶ ተስፋዬ ኩምሳ የሰበታ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ሥራ አስኪያጅ

ወ/ሮ ህይወት አበበ የሰበታ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የአገልግሎት

ሰጪዎች ጉዳይና የጥራት ማረጋገጫ ክፍል ኃላፊ

አቶ አሰፋ ዲሮየአባላት ምዝገባና መዋጮ

ጉዳይ ክፍል ኃላፊ

አቶ ጥላሁን ከበደየሰበታ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሰው ሀብት

ልማት ክፍል ኃላፊ

የሀዘን መግለጫየኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ አመራሮችና ሠራተኞች ነሐሴ 4 ቀን 2008 ዓ.ም ከሰበታ ወደ ሀዋሳ ከተማ የአመታዊ ግምገማና እቅድ ስብሰባ ለመካፈል በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰባቸው የተሽከርካሪ አደጋ ህይወታቸውን ባጡት አራት የሰበታ ቅርንጫፍ ባልደረቦቻችን ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እንገልፃለን፡፡ የሰበታ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባልደረቦቻችን አቶ ተስፋዬ ኩምሳ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ፣ ወ/ሮ ህይወት አበበ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የአገልግሎት ሰጪዎች ጉዳይና የጥራት ማረጋገጫ ክፍል ኃላፊ፣ አቶ ጥላሁን ከበደ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሰው ሀብት ልማት ክፍል ኃላፊ እና አቶ አሰፋ ዲሮ የአባላት ምዝገባና መዋጮ ጉዳይ ክፍል ኃላፊ የነበሩ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የሰበታ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባልደረቦቻችን በጠንካራ የስራ ዲሲፕሊን፣ በስራ ትጋትና ተነሳሽነታቸው በአርአያነታቸው ተጠቃሽ ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ አመራሮችና ሠራተኞች የደረሰብንን መሪር ሀዘን ተቋቁመን የባልደረቦቻችንን በጎ ጅምር ለማስቀጠል ከምንጊዜውም በላይ ቁርጠኝነታችንን እየገለፅን፣ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መፅናናትን እንመኛለን፡፡

የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ

Page 60: የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ · 2016-11-24 · 32 ማህበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን እና ወረዳ ... በጤናውን ዘርፍ የዕድገትና

PSD Graphics 0911249276