20

Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd
Page 2: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd
Page 3: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

3

ከቀጣዩ አምስት ዓመት

/2003-2007/ የዕድገትና

የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ

ለግንዛቤ የተወሰዱ

ዋና ዋና ነጥቦች

በመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትበኢንፎርሜሽን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

የተዘጋጀ

መስከረም 2003 ዓ.ም.አዲስ አበባ

Page 4: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

4

መግቢያየኢፌዴሪ መንግሥት ባለፉት አመታት አገሪቷ

ከድህነትና ከኋላ ቀርነት እንድትላቀቅ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በመንደፍ አስተማማኝ የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲ መሠረት ጥሏል፡፡ በተለይም ፈጣንና ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማምጣት የሚያስችል ግብርናና ገጠርን ማዕከል ያደረገ የልማት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ስልት በመቅረጽና ተግባራዊ በማድረግ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል፡፡ ለዚህም ባለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት የአገሪቱ ኢኮኖሚ በየዓመቱ በአማካይ የ11 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡ በአብነት ይጠቀሳል፡፡

በመንግሥት የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና በህዝቡና በልማታዊ ባለሀብች ተሳትፎ የተመዘገበው እድገት ፈጣንና ዘላቂነት ያለው ብቻ ሳይሆን መሠረተ ሰፊና ህዝቡን በየደረጃው ተጠቃሚ ያደረገ ጭምር ነው፡፡ ይህንን ለውጥና እድገት ዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም /IMF/ ፣ የዓለም ባንክ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ /ADB/፣ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም /UNDP/፣ የልማት ድጋፍ ቡድን/DAG/ እንዲሁም ሌሎችም በኢትዮጵያ ገጽታ ላይ በጎ አመለካከት ያላቸው ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ተቋማት፣ መገናኛ ብዙኃን እና አንዳንድ ታዋቂ ምሁራን ያረጋገጡት ጉዳይ ነው፡፡ በሌላ በኩልም አገሪቷ ማህበራዊ ልማትን በማፋጠን እና ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ መንግሥትን ዕውን በማድረግ ረገድ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ድል አስመዝግባለች፡፡

መንግሥት በቀጣይም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኀበራዊ መስኮች ካለፉት ዓመታት በእጅጉ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብና በኢኮኖሚው ውስጥ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል የአምስት ዓመታት /2ዐዐ3-2ዐዐ7/ ሀገር አቀፍ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አዘጋጅቷል፡፡ በዕቅዱ ዙሪያም በክልል እና በከተማ አስተዳደር ደረጃ የሚገኙ የተለያዩ የኀብረተሰብ ክፍሎች መወያየት ከጀመሩ ቀናት ተቆጥረዋል፡፡

በዚህ ዕቅድ መሠረት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የአገሪቱ ኢኮኖሚ በየአመቱ በአማካይ እስከ 15 በመቶ ያድጋል ተብሎ ሲጠበቅ፣ የግብርና ምርቱ በእጥፍ ከፍ እንደሚል ታሳቢ ተደርጓል፡፡ በኢንዱስትሪው ዘርፍም በዓመት እስከ 18 በመቶ እድገት ይጠበቃል፡፡ ከዚህ አንጻር የገቢ ምርቶችን ለሚተኩ ኢንዱስትሪዎች ከመቼውም ጊዜ የላቀ ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲስፋፉ እንደሚደረግ ዕቅዱ ያመለክታል፡፡

በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በመታገዝ የወደፊቷን አፍሪካ የምትወክል ኢትዮጵያን እንገንባ!

Page 5: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

5

ዕቅዱን ለማሳካት ከሚከናወኑ ሌሎች ተግባራት ውስጥ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችም ይገኙበታል፡፡ በዚህ ዘርፍ ከዋና ዋና የመንገድ ሥራዎች በተጨማሪ ለሁሉም የገጠር ቀበሌዎች ደረጃውን በጠበቀና ክረምት ከበጋ የሚያገለግል እና ከዋና መንገድ ጋር የሚያገናኝ አዲስ የገጠር የመንገድ ግንባታ ሥራ ይካሄዳል፡፡ የባቡር ትራስፖርትን በተመለከተም እስከ 2ሺህ 395 ኪሎ ሜትር የሚደርስ የኤሌክትሪክ ባቡር መስመር ይዘረጋል ተብሎ ታቅዷል፡፡

በኢነርጂው ዘርፍ ደግሞ በሚቀጥሉት ዓመታት ስምንት ሺህ ሜጋ ዋት የሚያመነጩ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ከታዳሽ ኃይል ምንጮች ለማስፋፋት እንዲቻል በዘርፉ እስከ አሁን የተሰራውን በአራት ዕጥፍ ለማሳደግ ታስቧል፡፡ እንዲሁም በቴሌኮሙኒኬሽን መስክ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል፡፡

በተመሳሳይ አጠቃላይ የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋንን ወደ 98 ነጥብ 5 በመቶ ለማሳደግ ሲታቀድ፣ የቤቶች ቁጥርንም አሁን ካለበት 213ሺህ ወደ 7ዐዐሺህ ለማድረስ ታስቧል፡፡ በማህበራዊ መስክም የትምህርትና የጤና አገልግሎትን ለማስፋፋትና ጥራትን ለማሻሻል ለሚከናወኑ ሥራዎች በእቅዱ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፡፡

በተጨማሪ የአቅም ግንባታና የመልካም አስተዳደር ግቦችን ለማሳካት፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ብቃትና ተጠቃሚነት ለማሳደግ፣ ማህበራዊ ደህንነትን ለማረጋገጥ እና የሥነ ሕዝብ ልማትን ለማጎለበት፣ የባህልና ቱሪዝም መስክን ለማሳደግና ለማስፋፋት እንዲሁም አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚከናወኑ ተግባራትም በዕቅዱ ውስጥ ተካትተዋል፡፡

በአጠቃላይ በቀጣዩ የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የትግበራ ዘመን መጨረሻ ኢንዱስትሪው በኢኮኖሚ ውስጥ የመሪነት ሚናውን ለመረከብ ዝግጅቶች የሚጠናቀቁበት እና የሚሌኒየሙ የልማት ግቦች ሙሉ በሙሉ የሚሳኩበት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም እስከአሁን የተደረሰበትን የኢኮኖሚ እድገት በማስጠበቅ በተቀናጀና በተባበረ አገራዊ የልማት ክንድ ካለፉት ዓመታት በእጅጉ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የዜጎች፣ የልማታዊ ባለሃብቶችና በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላት ጥረትና ድርሻ በእጅጉ ያስፈልጋል፡፡ እነሆ የወቅቱ መልዕክታችንም ለኢኮኖሚ ልማት እቅዳችን ተግባራዊነት እጅ ለእጅ ተያይዘን እንረባረብ! የሚል ይሆናል፡፡

የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱን ተግባራዊ በማድረግ የኢትዮጵያን ህጻሴ አስተማማኝ እናድርግ!

Page 6: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

6

ከቀጣዩ አምስት ዓመት

/2ዐዐ3-2ዐዐ7/ የዕድገትና

የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ

ለግንዛቤ የተወሰዱ

ዋና ዋና ነጥቦችየልማት ዕቅዱ መነሻዎች

የቀጣዩ የአምስት ዓመት /2ዐዐ3-2ዐዐ7/ የልማት ዕቅድ መነሻዎች የአገሪቱ ራዕይ፣ በአለፉት ዓመታት ተፈጻሚ በሆኑ ዕቅዶች የተመዘገቡ ውጤቶችና በአፈጻጸም ሂደት የተገኙ ተሞክሮዎች ናቸው፡፡

የአገሪቱ ራዕይ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2ዐ17 በህዝብ ተሳትፎና በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትና መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት፣ ከድህነት ተላቅቃ መካከለኛ ገቢ ያላት ኢትዮጵያን ዕውን ማድረግ ነው፡፡

የልማት ዕቅዱ መሪ አጀንዳ ባለፉት ዓመታት ተፈጻሚ ከሆኑ የልማት ዕቅዶች የተገኘውን መሠረተ ሰፊ፣ ፈጣን፣ ቀጣይና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ዕድገት አጠናክሮ በመቀጠል ድህነትን በሂደት ማስገወድ ነው፡፡

የልማት ዕቅዱ ዓላማዎችአጠቃላይ ኢኮኖሚው በየዓመቱ ቢያንስ በአማካይ

11 በመቶ ዕድገትን በማስመዝገብ በኢኮኖሚያችን መታየት የጀመሩትን ማነቆዎች በማስወገድና በማቃለል የሚሌኒየም ልማት ግቦችን ማሳካት፣

የዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ግንባታችን በህዝብ ተሳትፎ ይጠናከራል!

Page 7: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

7

የትምህርትና ጤና አገልግሎት ሽፋንን በመጨመርና ጥራቱን በማረጋገጥ ላይ የተመሠረተ ማህበራዊ ልማት በማካሄድ የሚሌኒየም ልማት ማህበራዊ ግቦችን ማሳካት፣

የተረጋጋ፣ ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ መግሥትን በመፍጠርና በማጠናከር ለቀጣይ የአገር ግንባታ ሥራ ምቹ መደላድል መፍጠር፣

ከላይ የተገለፁትን ዋና ዋና ዓላማዎች በተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ማዕቀፍ ውስጥ በመፈፀም የልማቱን ቀጣይነት ማረጋገጥ፡፡

የልማት ዕቅዱ መሠረታዊ አቅጣጫዎች /Pillar Strategies/ፈጣን፣ ቀጣይና ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ዕድገት

ማስመዘገብ፣የግብርና ዘርፍ ዋና የዕድገት ምንጭ ሆኖ

እንዲቀጥል ማድረግ፣የኢንዱስትሪው ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ ቁልፍ

ሚና እንዲጫወት ማስቻል፣የመሠረተ ልማትን ማስፋፋትና ጥራትን

ማረጋገጥ፣የማህበራዊ ልማትን ማፋጠንና ጥራትን

ማረጋገጥ፣አቅም ግንባታንና መልካም አስተዳደርን ማሳደግ

እናየሴቶችንና የወጣቶችን ብቃትና ተጠቃሚነት

ማሳደግ፡፡

ፈጣን፣ ቀጣይና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብበአለፉት 5 ዓመታት የተመዘገበውን የኢኮኖሚ

ዕድገት በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በዘላቂነት አጠናክሮ መቀጠልና ህዝቡን በየደረጃው ተጠቃሚ ማድረግ፣

ዕድገትን ለማፋጠን በሚያስችሉ የኢኮኖሚ መሠረተ ልማትና የማኀበራዊ ልማት ዘርፎች

የመሠረተ ልማት መስፋፋት የእድገታችን መፋጠን ኃይል ነው!

Page 8: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

8

ላይ ከአሁን በፊት የተሰጠውን ትኩረት አጠናክሮ መቀጠል፣

እንዳለፉት ዓመታት የግብርናውን ምርታማነት በማሳደግና ዘላቂነትን በማረጋገጥ ግብርና በቀጣዩ ዓምስት ዓመት የኢኮኖሚ ዕድገት ዋነኛ ምንጭ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ፣

የወጪ ንግድ መር ኢንዱስትሪ ልማትን መሠረት በማድረግ የኢንዱስትሪው ዘርፍ በኢኮኖሚ ውስጥ ተገቢውን ሚና እንዲጫወት ማድረግ፣

ውድድርን መሠረት በማድረግ ገቢ ንግድን ለሚተኩ ኢንዱስትሪዎች በቂ ትኩረት በመስጠት ኢንዱስትሪ ከሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች በላቀ ፍጥነት እንዲያድግና ለቀጣዩ የልማት ምዕራፍ መሠረት እንዲሆን ማድረግ፣

ፈጣን፣ ፈጣይና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን በማስፈን የሥራ ዕድልን ማስፋፋትና ድህነትን በሂደት ማስወገድ፣

የኢኮኖሚ ዕድገት አማራጮች ፈጣን፣ ዘላቂና ፍትሃዊ ዕድገት ለማረጋገጥ በቀጣዩ አምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የትግበራ ዘመን ሁለት የኢኮኖሚ ዕድገት አማራጮች ታይተዋል፡፡ እነዚህም መሠረታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት አማራጭ (Base case scenario) እና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት አማራጭ (High case scenario) ናቸው፡፡በመሠረታዊው የኢኮኖሚ ዕድገት አማራጭ

ኢኮኖሚው ላለፉት አምስት ዓመታት በየዓመቱ በአማካይ ያስመዘገበውን የ11 በመቶ ዕድገት ቀጣይነት ማረጋገጥ፣

በከፍተኛው የኢኮኖሚ ዕድገት አማራጭ የግብርና ምርትንና አጠቃላይ ኢኮኖሚውን በ2ዐዐ2 ከነበሩበት በ2ዐዐ7 ዕጥፍ ማድረግና ይህንኑ ለማሳካት ኢኮኖሚውን በየዓመቱ በአማካይ በ14.9 በመቶ ማሳደግ፣ የኢንዱስትሪውን ዕድገት በማፋጠን ዘርፉ በኢኮኖሚው ውስጥ የመሪነት ሚናውን ሊረከብ የሚችልባቸውን ሥራዎችን ማጠናቀቅ፣

የልማታችን ስኬት በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታችን ይጠናከራል!

Page 9: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

9

የግብርና ዘርፍ ዋና የዕድገት ምንጭ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ፣

የግብርና ልማት ስትራቴጂ አቅጣጫዎችን በመከተልና በአለፉት ዓመታት በዘርፉ የተገኙ ተሞክሮዎችን መሠረት በማድረግ በአርሶ አደሩ/በአርብቶ አደሩ ደረጃ የተጀመረውን ገበያ ተኮርና የተሻለ ምርት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የማምረት ሂደት አጠናክሮ መቀጠል፣

በግብርናው ዘርፍ የግል ባለሀብቶችን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ማበረታታትና ለሰፋፊ እርሻ አልሚዎች በተሻለ ሁኔታ ድጋፍ ማድረግ፣

ከፍተኛ የመልማት አቅም ላላቸው አካባቢዎች ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ገበያው በሚፈልጋቸውና ሀገሪቱ የተሻለ የገበያ ዋጋ ልታገኝባቸው በምትችልባቸው የምርት አይነቶች ላይ በማተኮር አርሶ አደሮችና የግል ባለሀብቶች እንዲያመርቱ ማበረታታት፣

በዘርፉ የሚደረጉ የልማት ጥረቶችን ለማገዝ የተጀመሩትን የተለያዩ የመንግሥት ኢንቨስትመንትና አገልግሎቶች የማስፋፋት ሥራ አጠናክሮ መቀጠል፣

የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤን አርሶ/አርብቶ አደሩን ባሳተፈ መልኩ በማካሄድ የአፈር ለምነትን መጠበቅ፣ የከርሰ ምድርና ገፀ ምድር ውሃን በማበልፀግ የውሃ አጠቃቀም ማሻሻልና የመስኖ ሥራን ለማስፋፋት ትኩረት መስጠት፡፡

ግብርና በየዓመቱ በፍጥነት እንዲያድግ በማድረግ፡-o የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ፣ በአካባቢና በአገር

ደረጃ ሙሉ በሙሉ ማረጋገጥ፣o የዋጋ ግሽበት ግፊትን በአስተማማኝ መልኩ

የማስወገድ ወሳኝ ድርሻውን እንዲጫወት ማድረግ፣

o የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ ከፍተኛ ድርሻ እንዲያበረክት ማድረግ፣

የዘርፉን የአምስት ዓመት የልማት ዕቅድ ግቦች

በእቅዱ ዘመን መጨረሻ የግብርና ምርትን እና አጠቃላይ ኢኮኖሚውን በእጥፍ እናሳድጋለን!

Page 10: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

10

በማሳካት ሂደት ዘላቂ የግብርና ዕድገት እንዲኖር ሁኔታዎችን የሚያመቻችና መካከለኛ ገቢ ያላት አገር የመፍጠር ራዕይን ለማሳካት ድርሻውን እንዲወጣ ማድረግ፣

የግብርናው ዘርፍ ለኢንዱስትሪ ልማት የበኩሉን ድርሻ እንዲጫወት ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣

የኢንዱስትሪው ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ ቁልፍ ሚና እንዲጫወት ማስቻልበኢንዱስትሪ መስክ ከማንኛውም ዘርፍ የፈጠነና

የተሻለ ልማት በማረጋገጥ፡-o ኢንዱስትሪው ደረጀ በደረጃ በቀጣይ የሀገሪቱ

ልማት መሠረት የሚሆንበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣

o ኢንዱስትሪው የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለማቃለል የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ማድረግ፣

o ኢንዱስትሪው ለግብርና ቀጣይ ልማት የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክት ማድረግ፣

o ኢንዱስትሪው ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥርበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ የላቀ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ ማድረግ፣

ለመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የቴክኖሎጂ እድገትን በማረጋገጥ፡-o የአገራችን ኢኮኖሚ ተወዳዳሪነት እንዲጎለብት

ማድረግ፣o የአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት እንዲስፋፉና

እንዲጠናከሩ ማድረግ፣o ለግብርና ዘርፍ ዕድገት አመቺ ሁኔታ

እንዲፈጠር ማድረግ፣ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት መስፋፋትና

መጠናከር ትኩረት በመስጠት፡-o የሥራ ዕድሎች እንዲፈጠሩ ማድረግ፣o የከተሞችን ዕድገት ማፋጠን፣o ለግብርና ልማት የቅርብ ድጋፍ መስጠት፣በእቅዱ ዘመን መጨረሻ ኢንዱስትሪው በኢኮኖሚው ውስጥ የመሪነት ሚና እንዲጫወት እናደርጋለን!

Page 11: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

11

o አዳዲስ ባለሀብቶች እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣

ዘርፉ እንዳለፈው ጊዜ ሁሉ በኤክስፖርት ኢንዱስትሪ የሚመራና ለውጭ ምንዛሪ ማነቆ መቀረፍ፣ ለፈጣን የቴክኖሎጂ ሽግግር ድርሻውን የሚወጣ እንዲሆን ማድረግ፣

ገቢ ምርቶችን የሚተኩ ኢንዱስትሪዎችም የውጭ ምንዛሪ እጥረታችንን በማቃለል ረገድ ከፍተኛ ድርሻ ስላላቸውና ለቀልጣፋ የኢንዱስትሪ ዕድገት መሠረት የሚሆኑ በመሆናቸው ከመቼውም ጊዜ የላቀ ትኩረት በመስጠት እንዲስፋፉ ማድረግ፣

የመሠረተ ልማት ማስፋፋትና ጥራትን ማረጋገጥበመሠረተ-ልማት መስፋፋት መስክ ያጋጠሙ

ዋነኛ ችግሮችን በመቅረፍ በዘርፉ የሚከናወነውን ኢንቨስትመንት በከፍተኛ መጠን መጨመር፣

የአገር ውስጥ ቁጠባን ማሻሻልና ለመሠረተ ልማት መስፋፋት ሥራ የሚያስፈልጉ ከውጭ የሚገቡ ቁሳቁሶችና አገልግሎቶች በተቻለ መጠን በአገር ውስጥ የሚመረቱበትን ወይም የሚቀርቡበትን ሁኔታ መፍጠር እና በውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ላይ የሚፈጥረውን ጫና በከፍተኛ መጠን መቀነስ፣

የኢኮኖሚ ዕድገቱ እንዲፋጠን የሚፈለጉ የትራንስፖርትና መገናኛ፣ የኃይል አቅርቦትን በጥራትና በተወዳዳሪ ዋጋ ማቅረብ፣

ለመንገድ፣ ለባቡር፣ ለኢነርጂ፣ ለቴኮሙኒኬሽን፣ ለመስኖ፣ ለመጠጥ ውሃና ለሳኒቴሽን መሠረተ ልማቶች ከፍተኛ ትኩረት መስጠት፣

መንገድን በተመለከተ በሁሉም ክልሎች አዳዲስ የገጠር የመንገድ ግንባታዎች በማካሄድ ሁሉም የገጠር ቀበሌዎችን ደረጃቸውን በጠበቁና ክረምት ከበጋ በሚያገለግሉ መንገዶች ከዋና መንገድ ጋር ማገናኘት፣

ባቡርን በተመለከተ በሦስት ኮሪደሮችና በአራት መስመሮች ሀገራዊ የባቡር ኔትወርክ /አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያን ህዳሴ በፅኑ ዴሞክራሲያዊ መሠረት ላይ እንገነባለን!

Page 12: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

12

ድሬዳዋ፣ ደወሌ/፣ /አዋሽ፣ ወልዲያ፣ መቀሌ/፣ /ወልዲያ፣ ሰመራ፣ ጋላፊ/፣ /አዲስ አበባ፣ ኢጃጂ፣ ጅማ፣ በደሌ/፣ ሞጆ፣ ኮንሶ፣ ወይጦ/ ግንባታዎችን በመጀመር አብዛኛዎቹን ማጠናቀቅ፣

የሀገሪቱን የኢነርጂ ፍላጎት ለማሟላት ታዳሽ የኃይል ምንጮች በማስፋፋት ንፁህና አየርን የማይበክል ከውሃና ከነፋስ የኢነርጂ አማራጮችን የመጠቀም አቅጣጫ መከተል፣

ቴሌኮሙኒኬሽንን በተመለከተ ወቅቱ ያፈራቸው የመገናኛ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለመሆን እንዲቻል የተጀመረውን የኔትወርክ ዝርጋታ ሰፊ ሥራ ማጠናቀቅ፤ ጥራቱ የተጠበቀ፣ ዘመናዊ፣ የተጣመሩ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን የያዘ አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ በመላ ሀገሪቱ በአፋጣኝ እንዲዳረስ ማድረግ፣

የአገሪቱ የውሀ ሀብትን ለተለያዩ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ዕድገት እንቅስቃሴዎች ዘላቂና ፍትሀዊ በሆነ መንገድ መጠቀምና ማልማት፣ አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ ሽፋንን ማሳደግ፣ የመስኖ ግንባታዎችን ማስፋፋት፣

በከተሞች ፈጣንና ፍትሃዊ ልማትን ለማረጋገጥ ለኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ዕድገት ያላቸውን ሚና መሠረት በማድረግ መሠረተ ልማት እንዲስፋፋ ማድረግ፣ በከተሞች የሚገነቡ የመሠረተ ልማቶች ሰፊ የሥራ ዕድልና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በሚፈጥር መልኩ ተፈጻሚ እንዲሆን ማድረግ፣

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የሰው ኃይልን በብዛት የሚጠቀም፣ ልማታዊ፣ ገበያ መር፣ ጤናማ ውድድር የሰፈነበትና የግሉ ዘርፍ ከፍተኛ ሚና የሚጫወትበት፣ የሴቶችንና ወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በየደረጃው የሚያረጋግጥና የኮንስትራክሽን ዲዛይኖችም የአካል ጉዳተኞችን ያገናዘቡ እንዲሆኑ ማድረግ፣

ሳኒቴሽን በተመለከተ ለሥራና ለመኖሪያ ተስማሚ የሆነ ንፁህ የከተማ አካባቢ እንዲኖር ማድረግ፣

ሩቅ በማይባል ጊዜ ድህነትን ታሪክ እናደርጋለን!

Page 13: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

13

የማህበራዊ ልማትን ማፋጠን እና ጥራትን ማረጋገጥየትምህርትና ሥልጠና አገልግሎት ማስፋፋትና ጥራትን ማሻሻል በተመለከተየተጀመረውን አበረታች ውጤት ማስቀጠል፣

የሕፃናትን በተለይም የሴቶችን የትምህርት ተሳትፎ የሚገድቡ ችግሮችን ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ፣

ለኢኮኖሚ ዕድገቱና ልማቱ በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ ብቁ ዜጋ ማፍራት ቁልፍ በመሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ማስፋፋትን አጠናክሮ መቀጠል፣

o በዚህ ረገድ የሥልጠና ፕሮግራሙን በሳይንስና ምህንድስና መስክ ላይ ያተኮረ እንዲሆንና ጥራቱም ከሌሎች አገሮች መሰል ተቋሞች ጋር በብቃት የሚወዳደር እንዲሆን ማድረግ፣

o የየዩኒቨርስቲዎችን አስተዳደርና አመራር ሥርዓትን በማሻሻል፣ ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎችንና መምህራንን በብዛት በማሰልጠን ጥራቱ የተጠበቀ የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓት እንዲገነባ ማድረግ፣

o የተጀመረው የሙያና የቴክኒክ ማሰልጠኛ ተቋማት ፕሮግራም የመንግሥት አቅም ግንባታ ፕሮግራም አንዱ አካል ሲሆን ፕሮግራሙን የጥቃቅንና አነስተኛ የሥራ ዕድል በመፍጠር የሥራ አጥነትን ለመቀነስ ጥረት ከሚያደርጉ ተቋማት ጋር በመቀናጀት መተግበር፣

በዘርፉ የተቀመጡ የሚሌኒየም የልማት ግቦች በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ ይሳካሉ፣

የጤና አገልግሎት ማስፋፋትና ጥራት ማሻሻልን በተመለከተበመሠረታዊ የጤና አጠባበቅና የመቆጣጠር

አገልግሎት ዙሪያ የሕብረተሰቡን የተደራጀ ተሳትፎ ማዕከል በማድረግ ጥራቱን እና አገልግሎቱን ማሻሻል፣

የትምህርትና የጤና አገልግሎትን በማስፋፋትና ጥራትን በመጠበቅ ምርታማነትን እናሳድጋለን!

Page 14: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

14

የህክምና ተቋማት በሰው ኃይልና በቁሳቁስ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት መጠናከራቸውን ማረጋገጥ፣

በጤናው ዘርፍ የተሰማራውን የሰው ኃይል ክህሎት፣ ስብጥርና አስተዳደር ማሻሻል፣ በተለይም የህክምና ባለሙያዎች ፍልሰትን ለመቀነስ ጥረት በማድረግ ፍልሰቱንም ለማካካስ የህክምና ባለሙያዎችን የማሰልጠን ሥራ በከፍተኛ መጠን እንዲያድግ ማድረግ፣

የግሉ ዘርፍ በጤናው መስክ የሚኖረውን ሚና ይበልጥ ለማጠናከርና ለማስፋት የሚሰጡት የህክምና አገልግሎቶች ጥራታቸውን የጠበቁ ሁሉንም ወገኖች የሚያረኩ እንዲሆኑ የሌሎች አገሮችን ልምድ በመውሰድ ተገቢ የክትትልና የቁጥጥር ሥርዓት እንዲኖር ማድረግ፣

የመድሃኒቶችና ሌሎች የህክምና ቁሳቁሶችን ማምረቻ ተቋማት በአገሪቱ እንዲስፋፋ አስፈላጊው ማበረታቻና ማትጊያ መስጠት፣

በዘርፉ የተቀመጡ የሚሌኒየም የልማት ግቦች በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ይሳካሉ፡፡

አቅም ግንባታንና መልካም አስተዳደርን ማሳደግየኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማፋጠን በሁሉም ደረጃዎች መልካም አስተዳደርንና የማስፈፀም አቅም ማሳደግን በተመለከተ፡-

የሲቪል ሰርቪሱን የተቀናጀ አቅም በማሳደግና በማጎልበት የመንግሥት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በብቃት እንዲፈፀሙ ማስቻል፣ በሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም የትግበራ ሂደት እስካሁን የተገኙ ውጤቶችንና ተሞክሮዎችን በመቀመር በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲስፋፉ ማድረግ፣

የፍትህ አስተዳደር ሥርዓቱ የፍትህ አገልግሎት ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ የጀመራቸውን ለውጦች አጠናክሮ እንዲቀጥል ድጋፍ መስጠት፣

አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ እንፈጥራለን!

Page 15: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

15

ግልፅነትን ለማስፈንና ሙስናን ከምንጩ ለማድረቅ ስፋትና ጥልቀት ያላቸው የመልካም አስተዳደር ሥራዎች መስራት፣

የህዝብን ተሳትፎ ለማረጋገጥና የዴሞክራሲ ተቋማትንና ባህልን ለማዳበር ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ መስራት፣

የህብረተሰቡ ሕገ-መንግሥታዊ ግንዛቤና ንቃተ ህግ እንዲጎለብት የተቀናጀ ሥራዎችን መሥርት እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ባህልና ልምድ እንዲዳብር ማድረግ፣

ሕብረተሰቡ ስለ መልካም ሥነ ምግባርና ስለ ሙስና ጐጂነት እንዲማር፣ እንዲያውቅና ጠንካራ የፀረ ሙስና ግንዛቤ እንዲኖረው ማድረግ፣

አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር ትኩረት ሰጥቶ መስራት፣

የባለ ብዙ ዘርፍ ጉዳዮችየሴቶችንና የወጣቶችን ብቃትና ተጠቃሚነት ማሳደግ፣

o የልማት ዕቅዱ ዓላማ ሊሳካ የሚችለው ባለ ብዙ ፈርጅ የሆነው የሴቶችና የወጣቶች ችግር ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ ሲቀረፍና መፍትሄ ሲያገኝ ነው፡፡

o ስለሆነም መንግሥት የሴቶችንና የወጣቶችን ሁለንተናዊ አቅም ማሳደግና መጠቀም እንዲያስችል የሴቶች ጉዳይና የወጣቶች ፖሊሲዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን አቅጣጫ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

o በመሆኑም በልማት ዕቅዱ ዘመን የሴቶችንና የወጣቶችን ፓኬጅ አጠናክሮና አቀናጅቶ ተግባራዊ በማድረግ የሴቶች እና ወጣቶች የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ዕድሎች እንዲሰፉና እንዲጠናከሩ ይደረጋል፡፡

አገራዊ የልማት እቅዱ በሴቶችና በወጣቶች ልማታዊ ተሳትፎ ውጤታማ ይሆናል!

Page 16: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

16

ማህበራዊ ደህንነትo የሀገሪቱን ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት በማፋጠን

ሂደት ማህበራዊ ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚመለከታቸውን አካላት ያሳተፈ የማህበራዊ ደህንነት አገልግሎቶች ማስፋፋት፣ የማህበራዊ ደህንነት ችግሮችን መለየትና እርምጃዎችን መውሰድ፣ የአካልና አዕምሮ ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን አሳታፊና ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎች ማከናወን፣

የሥነ ህዝብ ልማትo የሥነ ህዝብ ዋና ዋና ባህሪያትን ከኢኮኖሚ

አቅም ጋር ለማጣጣም የሚያስችሉ ጠንካራ መሠረቶች መፍጠር፣

ባህልና ቱሪዝም

o የባህል ኢንዱስትሪን በማሳደግና በማስፋፋት ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ድርሻ እንዲኖረው ማድረግ፣ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ተወዳዳሪ ሆኖ በተለይ በአፍሪካ ተመራጭ መዳረሻ እንዲሆንና የሕዝብ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ የአገሪቱን መልካም ገጽታ መገንባት፣

የአካባቢና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮችo በኢኮኖሚ ዕድገትና ማህበራዊ ልማት ላይ

ተፅዕኖ የማያስከትል የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በሥራ ላይ ያሉ የአካባቢ ህጎችንና ነባር የአካባቢ እንክብካቤ ሥርዓቶችን የመተግበር እና በተለይም አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚካሄደውን አገራዊ ጥረት ለማሳካት የሚያስችል አቅም መገንባት፡፡

በተቀናጀና በተባበረ ልማታዊ ክንድ የሚሊኒየሙን የልማት ግቦች እናሳካለን!

Page 17: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

17

ማጠቃለያየአምስት ዓመቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን

ዕቅድ በመሠረታዊ እና በከፍተኛ የዕድገት አማራጮች የተዘጋጀ ነው፡፡ ከፍተኛው የዕድገት አማራጭ የግብርና ምርትን እና አጠቃላይ ኢኮኖሚውን በ2ዐዐ2 ከነበሩበት በ2ዐዐ7 ዕጥፍ የሚያደርግ ነው፡፡ ይህ የዕድገት ግብ ሁሉም የአገሪቱ ዜጎች በየደረጃው ድርሻቸውን ከተወጡ እንደሚሳካ አያጠራጥርም፡፡ ስለሆነም፡-o ይህንን የዕድገት ግብ ለማሳካት ከፍተኛ

ኢንቨስትመንት ይጠይቃል፣o ዕድገቱ የሚጠይቀውን ከፍተኛ ኢንቨስትመንት

ዕውን ለማድረግ ከፍተኛ የአገር ውስጥ ቁጠባ ያስፈልጋል፣

o መንግሥት የህብረተሰቡን የታክስ ግንዛቤ በማስፋት የታክስ ገቢን ትርጉም ባለው ሁኔታ ማሳደግ፣ ከኢንቨስመንት ጋር ያልተያያዙ ወጭዎችን በቁጠባና በማብቃቃት በመጠቀም ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት፣

o የግሉ ዘርፍ፣ ግለሰቦች፣ ቤተሰቦች፣ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ወዘተ… የቁጠባ ባህላቸውን እንዲያሳድጉና እንዲያዳብሩ በማበረታታት የአገር ውስጥ ቁጠባን ማሳደግ፣

o የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚ ተዋናዮችም የቆጠቡትን መዋዕለ ንዋይ በልማት ሥራ ላይ እንዲያውሉ /በኢንቨስትመንት ሥራ ላይ እንዲያውሉ/ ማበረታታትና ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣

በአምስት ዓመቱ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በመመራት በዕቅዱ ዘመን መጨረሻ ኢንዱስትሪው በኢኮኖሚው ውስጥ የመሪነት ሚናውን ለመረከብ ዝግጅቶች የሚጠናቀቁበት ይሆናል፡፡

በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ግዙፍ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ይካሄዳሉ፡፡ የሚገነቡት መሠረተ ልማቶች ለኢኮኖሚው ፈጣን ዕድገትና ማህበራዊ

ኢኮኖሚያችንን በእጥፍ በማሳደግ የአገራችንን በጎ ገፅታ እንገነባለን!

Page 18: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd

ልማት ዘላቂነት አስተማማኝ መሠረት ከመሆናቸው በተጨማሪ ገቢን በማመንጨትና የውጭ ምንዛሬን በማዳን ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ፡፡

በአምስት ዓመቱ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የትግበራ ዘመን መጨረሻ አገራችን በተቀናጀና በተባበረ ልማታዊ ክንድ የሚሌኒየሙን የልማት ግቦች ሙሉ በሙሉ ታሳካለች፡፡

የልማት ዕቅዱ በትግበራ ላይ በሚውልባቸው የሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የተጀመሩ የአቅም ግንባታ ሥራዎች በተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆን መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ግልጽነትንና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጡ ሥራዎች ከምንጊዜውም በላቀ ሁኔታ በትኩረት ይሠራሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የፍትህ ሥርዓቱ የበለጠ ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆንና ዴሞክራታይዜሽን ስፋትና ጥልቀት በአለው ሁኔታ እንዲሰርጽ ይደረጋል፡፡

የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት አገራችንን በ2ዐ17 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ተርታ ለማሰለፍና በተቀናጀና በተባበረ የጋራ ጥረት ድህነትን ታሪክ ለማድረግ የተጀመረውን ህዳሴ ያሳካል፡፡

ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ለማሰለፍ እንተጋለን!

16

Page 19: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd
Page 20: Five Years Plan and Transformation.amharic Indd